ዘመነ ወያኔ ወይም ዘመነ ኢሀዲግ ???
ለምንድን ነው ወጣቱ ዝም ብሎ የተቀመጠዉ ምንስ እስኪሆን ይሆን ትዕግስቱ አጀንዳ ???????
አንዱ ምን አለ
አትፍረድ!! እኔን ለምሳሌ ውሰድ 1984 ነው የተወለድኩት በዘመነ ኢሀዲግ ካለ ኢሀዲግ ምን አውቄ እኔማ 1997 ያሃ ሁሉ ህዝብ ሲታሰር ሲገረፍ ከሃገር ሲሰደድ ሁሉ በቃ ሲያልቅ ምንም አልተሰማኝም እንደውም ህዝቡን ጥፋተኛ ነበር ያደረግኩት ምክንያቱም ምርጫ አሸነፉ አይደል እንዴ እና ምን አድርጉ ይሏቸዋል ብዬ ነበር እንደገናም ደግሞ በኔ እድሜ ነው ባቡር ያየሁት በኔ ዘመን ነው መንገድ ያየሁት አዎ በኔ ዘመን ነው ፎቅ ያየሁት በኔ ዘመን ነው ኮንዶሚንየም ያየሁት እና ለምን ኢሀዲግን ልጥላ ብዬ አስብ ነበር ይዅው አውን ደረስኩ ተማርኩ ተመረቅኩ ለወግ መአረግ በቃሁ ይዅው ችግሩን የትውልድ ዘመኔንም አየው ለካስ ስው በራሱ ካልደረሰበት አያውቅም ለካስ ሰው ወዶ አደለም ሊቢያ ጣልያን ብሎ በረሃ ላይ ኩላሊት ልቡን እየተነጠቀ የሚሞተው ለካስ ወዶ አደለም ባህር ላይ የሃሳ እራት ሆኖ የሚቀረው ለካስ እህት ዓለም በዓረብ ዓገር የዓገር ውርጅብኝ የሚወርድባት የማንም ዓረብ መጫወቻ የሆነችው ከፎቅ ላይ ራሷን የምትከሰክሰው ለዓመታት ያለምንም ክፍያ ጉልበቷን የምትበዘብዘው እናማ ታውቃለህ ለካስ ኣብሮ መብላት ከሌለ መተማመን ከሌለ ዘረኝነት አገሪቱን ከወረረ በሃገሬ ላይ ካልኖርክ ካልተናገርክ ካልበላክ ካልጠጣክ እንደ፯ተኛ ዜጋ ተቆጥረክ ከኖርክ ዲሞክራሲ የሃገር ዕድገት መንገድ ፎቅ ባቡር 11 % እድገት EBC ላይ ወይም ከበደ ካሣ ብሎግ (LOL) ላይ ብቻ (ፌመስ አደረግኩት አይደል ከቤ ደስ ይበልክ ሎል ሎል) ከሆነ ምኑ ላይ ነው ታድያ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሬ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው በኢሀዲግ ዘመን መወለዴ የሚያኮራኝስ ለምንድን ነው ከነማን ጋር እንደቆመን ራስን እንድንመረምር የሚገፋፋ ስለሆነ በሉ ከግፉ ጨምሩበት እላለሁ። መገፋት አመጽን፣ አመጽ መሰባሰብንና የሀሳብ አንድነትን ይፈጥራልና፦
ለካስ በዘመነ ወያኔ መወለድም እርግማን ነበር ተረግመን ነበር ማለት ነው
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች ሞት ለወያኔ
YAYAZUF
Feb 18, 2015
Jul 8, 2014
ETV Report Andargachew Tsege Detained in Ethiopia
አዎ አንዳርጋቸውን ያንኑ መከረኛ የሽብር ዶክመንተሪ ሊያሰሩት በረሃ ለበረሃ ሲያንከራትቱት ፎቶና ቪዲዮ ሲያነሱት ሚስጢር አውጣ እያሉ ሲደበድቡት ከርመው አድክመውታል። ዶክመንተሪውም ለዚያው ለድፍኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቴሌቪዥን ይቀርብለት ይሆናል።
የተከበሩ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው በኢቲቪ ታዩ! ከዚያም እነዚህን አረፍተ ነገሮች ሲቃ እየተናነቀው ተናገረና።
እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ!
እውነቴን ነው የምልሕ ለእኔ እንደ ምርቃት ነው የተቀበልኩት
እኔ አሁን ምንም የሚያቻኩለኝ ነገር የለም... ጥሩ እረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ
በጣም በጣም ደክሞኛል... በቅቶኛል
እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው
ምንም አይነት ጥላቻ በውስጤ የለም
ምንም አይነት ብስጭት የለኝም
ምንም አይነት መጥፎ ስሜት አይሰማኝም
በቃ... የመጨረሻ እርጋታና እረፍት ውስጥ ነው ያለሁት
የተከበሩ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው በኢቲቪ ታዩ! ከዚያም እነዚህን አረፍተ ነገሮች ሲቃ እየተናነቀው ተናገረና።
እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ!
እውነቴን ነው የምልሕ ለእኔ እንደ ምርቃት ነው የተቀበልኩት
እኔ አሁን ምንም የሚያቻኩለኝ ነገር የለም... ጥሩ እረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ
በጣም በጣም ደክሞኛል... በቅቶኛል
እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው
ምንም አይነት ጥላቻ በውስጤ የለም
ምንም አይነት ብስጭት የለኝም
ምንም አይነት መጥፎ ስሜት አይሰማኝም
በቃ... የመጨረሻ እርጋታና እረፍት ውስጥ ነው ያለሁት
Jun 14, 2014
ቴዲ አፍሮና ውዝግብ ያልተለየው ዝና
በአዲስ አበባ ታትሞ ከተሰራጨው ቁምነገር መጽሔት የተወሰደ
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ወደ ሙዚቃው ዓለም ተቀላቅሎ ወደ ዝና ማማ መውጣት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ መነጋገሪያ ከመሆን ያመለጠ አርቲስት አይደለም፡፡ በ1993 ዓ.ም ማብቂያ ላይ ባወጣው የመጀመሪያ ‹አቦጊዳ› አልበሙ የሙዚቃ አድማጩን ጆሮ ለመቆጣጠር የቻለው ቴዲ አፍሮ በወቅቱ በአለቤ ሾው ፕሮግራም ላይ በእንግድነት ቀርቦ ‹25 ዓመቴ ቢሆንም ፍቅረኛ ገና አልያዝኩም › ባለ ማግስት የከተማው ወጣት ሴቶች አይን ማረፊያ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚሁ ይፋ ካልወጣ የሴቶች አደን ጋር ተያይዞ የመጀመሪያውን ውዝግብ አስተናገደ፡፡ ‹በሴት ልጅ ጡት ላይ ፊርማ ፈርሟል› በሚል ተሰራጨው ወሬ ከከተማ ወሬነት አልፎ የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ገበያ መጥሪያና ማሻሻጪያ ሆኖ ነበር፡፡‹የተባለውን ነገር አላደረኩም፤ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ኩሩዎች ናቸው፡፡ ይህንን ነገር እንዳደርግ አይጠይቁኝም ፤ እኔም አላደረኩትም› ብሎ በወቅቱ ለታተመችው ቅፅ 1 ቁጥር 1 ቁም ነገር መፅሔት ላይ ቢናገርም አድናቂዎቹን ከማሳመን በቀር የወሬ ማጣፈጫነቱን አላስቀረውም ነበር፡፡ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያ ውዝግቡን በዚሁ መልኩ ለመቋመጨት ጥረት ቢያደርግም ከዚሁ አልበሙ በፊት በሰራው የመጀመሪያ ካሴቱ ሳቢያ ለሌላ ውዝግብ የተዳረገው ብዙም ሳይቆይ ነው፡፡ የመጀመሪያ ካሴቱን ሳያወጣ ለዓመታት አስቀምጦት የነበረው ቮይስ ሙዚቃ ቤት የአቦጊዳ አልበሙ የአድማጭን ጆሮ መቆጣጠር ተመልክቶ አዲሱን አልበም ለገበያ ያቀረበው ወዲያውኑ ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያም ‹የአቦጊዳን አልበም ሽያጭ ብቻ ሳይሆን አሁን ያለበሁበት ደረጃ ፈፅሞ የማይመጥን› ያለውን ከዓመታት በፊት የተሰራውን ካሴት ‹ሳያስፈቅደኝ መልቀቅ የለበትም› በሚል ሌላ ውዝግብ ተፈጥሯል፡፡ ተፈጠረው ውዝግብ መሀል ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ገብቶ በሽምግልና ጉዳዩን እንዲፈታ እስኪያደርግ ድረስ በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ መነጋገሪያ ነበር፡፡
ቴዲ በሙዚቃ ስራው ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ህይወቱና በሚያደርጋቸው ቃለ ምልልሶቹ ዝናውን ከፍ እያለ ቢመጣም ምርጫ 97 ተከትሎ ገበያ ላይ በዋለሁ ሶስተኛ ‹ጃ ያስተሰርያል› አልበሙ ሳቢያ ውዝግቡ ከግለሰብ ወደ መንግስት ዞሮ ነበር፡፡ ይፋዊ በሆነ መንገድ መንግስት ተቃውሞውን ባይገልፅም ዘፈኑ በማንኛውም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ላይ እንዳይተላለፍ ከመከልከል ጀምሮ ለጉዳዩ ሌላ ፓለቲካዊ መልክ በመስጠት የውዝግቡን ጡዘት እንዳከረረው እናስታውሳለን፡፡ ከምርጫው ጋር የተያያዘው ውጥረት ቀስ እያለ ቢረግብም ከመንግስት ጋር ያለው ውዝግበ ከአንድ ዘፈን ወደ ሶስት አድጎ ከ‹ካብ ዳህላክና› እና ‹ሼ መንደፈርን› ጨምሮ ታይቷል፡፡ መንግስት በወቅቱ ከነበረው ፖለቲካዊ ራስ ምታት ተረጋግቶ ሚሊኒየሙን ለመቀበል ሽር ጉድ በሚልበት ወቅት ቴዲ አሁንም የህዝቡን የልብ ትርታ ያዳመጠ ‹አበባ አየሽ ሆይ› የተሰኘውን ተወዳጅ ባህላዊ ዜማ ለእርቅ አውሎት ብቅ አለ፡፡ ከፓለቲካ እስረኞች መፈታት ጋር ተያይዞ የእርቅ መንፈሱ በሁሉም ሙዚቃ አድማጭ ጆሮ ማንቃጨል ቢጀምርም መንግስት ግን ዘፈኑን ዘወትር በየሚዲያው ላይ ሲለቀቅ ሁኔታውን በዝምታ ከመመልከት ውጪ ‹ሆ በል ከበሮ ሆ በል አንተ ማሲንቆ ስታይ ሰው ታርቆ› በሚለው ስንኝ ከህዝቡ ጋር እስክስታ ለመውረድ ሳይችል ቀርቷል፡፡የቴዲ አፍሮ የእርቅ መንፈስ ሚሊኒየሙን ብቻ ሳይሆን ባህር ማዶ ተሻግሮ ለመዝፈንና ለማስጨፈር ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ከሚሊኒየሙ ጋር ታኮ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ቢዮንሴ ኖውልስ በቴዲ አፍሮ ‹አበባ አየሽ ሆይ› ዜማ ወገቧን ይዛ ስትጨርፍር ታይታለች፡፡
ቴዲ በዘፈኑ የሀገሩን ልጆች አልፎ የውጪ ሰዎችን ማማለል ቢችልም ከመንግስት ጋር የገባው ውዝግብ ከዚህ ቀደም ከግለሰቦች ጋር እንዳለው አይነት ተራ የሚባል አልነበረምና ወደ እስር ቤት የሚገባበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ በብዙዎቹ አድናቂዎቹ ዘንድ አሁንም ድረስ እንደሚታመነው ‹ቴዲ አፍሮ በመኪና ሰው ገጭቶ አምልጧ› የሚለውን የአቃቤ ህግ ክስ ለመቀበል ዳግም መወለድ የሚያስፈልጋቸው ይመስላል፡፡ ‹ደጉ ይበልጣል› የተባለውን የ18 ዓመት የጎዳና ተዳዳሪ ገጭቶ ስለመግደሉና ስለማምለጡ በወቅቱ መነጋገሪያ የነበረው ክስ ከብዙ የፍርድ ቤት ቀጠሮና ምልልስ በኋለ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ሲቋጭ ‹ቴዲ እንደ በፊቱ ተወዳጅ ሥራዎቹን ይሰጠን ይሆን ›የሚል ጥርጣሬ መኖሩ አልቀረም፡፡ የፈጠራ ስራ ችግር የሌለበት ቴዲ ከእስር ቤት በወጣ በሶስተኛው ወር ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንሰርት በማዘጋጀት ገቢውን በልመና ሥራ ላይ ለተሰማሩ ወገኖች ማቋቋሚያ አደረገ፡፡ በዚህ ኮንሰርት ላይም ያገኘውን ከአንድ ሚሊየንም ብር በላይ ገንዘብም ለኤልሻዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር አስረከበ፡፡
ከሚያወጣቸው አልበሞች ጋር ተያይዞ ውዝግብ የማያጣው ቴዲ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋርም ውዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ከዘፈኖች መመሳሰል ጋር በተያያዘ በሰይፉ ፕሮግራም ላይ በቀረበ ዘገባ ሳቢያ ጉዳዩ በስምምነት እስኪፈታ ድረስ ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ ቴዲ የሌሎቹን ያህል አይሁን እንጂ ከረዥም ጊዜ ማናጀሩ አዲስ ገሠሠ ጋርም ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የተለያዩ ሲሆን በተደጋጋሚ ተሰርቀው በወጡ ነጠላ ዜማዎቹ ሳቢያም የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ የቴዲ አራተኛ ካሴትም ውዝግብ መፍጠሩ አልቀረም፡፡ ‹ጥቁር ሰው› በሚል ርዕስ ያወጣው አልበም ከፍተኛ የሙዚቃ ችሎታውን ያሳየበትና አዳዲስ የአዘፋፈን ስልቶችን ያካተተበት ሥራው ቢሆንም ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ፓለቲካዎ አቋም ጋር ተያይዞ ተቃውሞ የገጠመው ወዲያውኑ ነበር፡፡ ጉዳዩ ከታሪክ አንፃር መታየት ያለበትና የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር በሚል የተሰራ ሙዚቃ እንደሆነ የተለያዩ ሰዎች የየራሳቸውን አስተያየት በማከል በየመገናኛ ብዙሃኑ ላይ ለመከራከር መሞክሩም ፓለቲካዊ መልክ የተሰጠውን ውዝግብ ለማብረድ ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ከዚህ ውዝግብ ቀጣይ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለው ‹ወደ ፍቅር ጉዞ› የሚል ስያሜ የተሰጠው የሙዚቃ ኮንሰርትም በበደሌ ቢራ ስፖንሰር አድራጊነት ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ክልሎች በመጓዝ ለማሳየት ፕሮግራም ቢዘረጋም ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ጋር ተያይዞ ‹ሰጠ› በተባለ ቃለ ምልልስ ሳቢያ በደሌ ቢራ ኮንሰርቱን ሰርዞታል፡፡ በደሌ ኮንሰርቱን ለመሰረዝ ምክንያት የሆነው ቴዲ ሰጠ በተባለው ቃለ ምልልስ ሳቢያ የተቆጡ ወገኖች ‹በደሌ ቢራን እንዳይጠጡ!› የሚል የቅስቀሳ ዘመቻ በመጀመራቸው እንደሆነና ከንግድ ስራ አንፃር ኮንሰርቱን መሰረዝ አዋጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡ ቴዲ የተባለውን ቃለ ምልልስ እንዳልሰጠ፤ ይልቁንም በመፅሔቱ የተፈጠረ ተራ ስህተት እንደሆነ ገልጾ ለመከራከር ቢሞክርም ሰሚ
ያገኘ አይመስልም፡፡ ጉዳዩ ስር እየሰደደ የመምጣቱ አንዱ ማሳያ ተደርጎ የሚወደሰደውም የዘመቻው ቀስቃሾች የቴዲን ኮንሰርት በማሰረዝ ብቻ ሳይገቱ ሌላም የመልስ ምት መሰጠት እንዳለበት የሚያሳስቡ ቅስቀሳዎች ተጠናክረው በመሰጠታቸው የጥቁር ሰው ተነፃፃሪ ተቃራኒ ነጠላ ዘፈን በአንድ አርቲስት
ተሰርቶ ተለቋል፡፡
ይህ የውዝግብ አዙሪት ባልተቋጨበት ሁኔታ ኮካ ኮላ ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ በየሀገሩ ከሚያሰራቸው አርቲስቶች መሀከል አንዱ አድርጎ ቴዲን እንደመረጠው ተሰማ፡፡ቴዲም ከሶስት ወራት በላይ በአዲስ አበባና በኬኒያ እየተመላለሰ የሙዚቃ ስራውን ሰርቶ ቢያጠናቅቅም ተመሳሳይ ችግር መከሰቱ ተነግሯል፡፡ በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ብራዚል እየተካሄደ የሚገኘውን የዘንድሮውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ምክንያት በማድረግ እንደተለመደው ግዙፍ የቢዝነስ ተቋም የሆነው ኮካ ኮላ በተለያዩ ድምጻውያን ሙዚቃዎችን አዘጋጅቶ ራሱን እያስተዋወቀ ነው፡፡ ሙዚቃዎቹ የተሰሩት በብዙ ዓይነት ቋንቋዎችና ከተለያዩ ሀገራት በተውጣጡ ድምጻውያን ሲሆን የተቀረጹት በኮካኮላ ስቱዲዮ /Coke Studio/ ነው፡፡ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ሀገራት የተመረጡ ድምጻዊያን የሠሩት የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አፊሲያላዊ የኮካ ኮላ ሙዚቃ ‹‹The world Is our›› /አለም የኛ ናት/ የሚል ርዕስ አለው፡፡ ይሄንን ሙዚቃ በድምፅ ለመስራት ከተመረጡት በርካታ ዘፋኞች መካከል ኢትዮጵያዊው ቴዲ አፍሮ ይገኝበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 መገባደጃ አካባቢ ቴዲ ለሙዚቃ ኮንሠርት ወደ ኳታር ባቀናበት ወቅት ከኮካ ኮላ ካምፓኒ ስልክ ተደውሎ በዓለም ዋንጫው ሙዚቃ ላይ እንዲሳተፍ ተጠየቀ፡፡ በዚህ መሠረት ከሌሎች አፍሪካውያን ድምጻውያን ጋር በጋራ ካቀነቀነው ዘፈን በተጨማሪ በአማርኛ ቋንቋ የተሰራና በግሉ የተሳተፈበት ሙዚቃ በኮካ ኮላ ስቱዲዮ መቀረጹ ተነገረ፡፡ ሙዚቃውም በ2014 የመጀመሪያ ወራት ላይ ለህዝብ እንደሚቀርብ ተገልጾ ነበር፡፡ ይሁንና በተባለበት ጊዜ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አልተለቀቀም፡፡
በሌሎች ሀገራት ድምጻውያን የተሰሩ ዘፈኖች ግን በይፋ ተለቀው እየተደመጡ ይገኛሉ፡፡ በአማርኛ ቋንቋ የተሰራው የቴዲ ዘፈን ግን መዘግየቱ ሳያንስ በቅርቡ ደግሞ ሙዚቃው ከነአካቴው ከስቱዲዮ እንደማይወጣ ተሰማ፡፡ ይህን ተከትሎ ቴዲ አፍሮ በድረገጹ ላይ ወጣ በተባለ ጽሁፍ ድርጊቱን ኮነነ፡፡ የኮካ ኮላ ካምፓኒ ድርጊት ‹‹ሀገራችን ያዋረደ›› ጭምር መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚከታተለው ገለጸ፡፡ የኮካ ኮላ ዘመቻ በአብዛኛው የዓለም ክፍል የሚታወቀው ኮካ ኮላ በዓለም ላይ 200 ከሚበልጡ ሀገሮች ውስጥ ፋብሪካውን ተክሎ በቀን ከ1.7 ቢሊዮን በላይ የሚሆን ጠርሙስ ኮካ ይሸጣል፡፡ መመረት የተጀመረበትን 128 ኛ ዓመት በማክበር ላይ ያለው ኮካ ኮላ ካለፈው ጥር አንስቶ እስከ መጋቢት ባለው ሶስት ወራት ብቻ 1.5 ቢሊዮን ዶላር አትርፏል፡፡ ኮካ ኮላ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ ተቃውሞዎች ገጥመውት የሚያውቁ ሲሆን ሁሉንም በማይበገረው የገንዘብ ሀይሉ አሸናፊነቱን አረጋግጦ ነው የተወጣው፡፡ ከአረብ እስራኤሎች ጦርነት በኋላ በአረቡ ዓለም በታየው የፀረ እስራኤል ዘመቻ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የአብዛኛዎቹ አረብ ሀገራት ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ለፍልስጤሞች ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ጥረዋል፡፡ አረቦቹ ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ብቻ ሳይወሰኑ ፊታቸውን ወደ ፔፕሲ አዙረዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ይህ ዘመቻ የኮካ ኮላን ገበያ የሚፈታተንና ከገበያ የሚያስወጣ ስላልነበረ በማስታወቂያው ላይ ባፈሰሰው ከፍተኛ በጀት የዓለማችን ቀዳሚ ለስላሳ መጠጥነቱን አስከብሮ ለመቆየት ችሏል፡፡ እ.እ.አ በ1950ዎቹ አጋማሽ ላይም የህንድ ገበሬዎች ኮካ ኮላ ለማሳችን የሚያስፈልገንን ውሃ ተሸማብን በማለት ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ተቃውሟቸውን ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ በዓመት 11 ቢሊዮን ዶላር ለማስታወቂያ ብቻ የሚያወጣው ኮካ ኮላ ንፁህ የመጠጥ ውሃን በማውጣትና ዙሪያ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች የሚመድበውን ማህበራዊ በጀት ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር በማሳደግ ራሱን ከህንድ አርሶ አደሮች ዘመቻ ተከላክሏል፡፡
የኮካ ኮላ የአቀማመም ምስጢር ድብቅነቱን ተከትሎ ሱስ አስያዥ ቅመም እንዳለውና ለጤናም አደገኛ ስለመሆኑ የተወራበት ጊዜ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶም ሰዎችን ሱስ የሚያሲይዝ የኮኬይን ቅመም እንዳለው ሲነገር ኮካ ኮላ ግን ይህ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡ያም ሆኖ ኮካ ኮላ አሁንም
ድረስ በብዙ ሀገሮች ውስጥ ተወዳጅ መጠጥ ቢሆንም እንደ ሰሜን ኮሪያ በርማና ኩባ አይነት ሀገሮች ኮካ ኮላ ፋብሪካ በሀገሮቻቸው እንዲቋቋም ያልፈቀዱ ሀገራት ናቸው፡፡እ.ኤ.አ በግንቦት 8 ቀን 1886 በአትላንታ ጆርጂያ ለራስ ምታት መድሃኒት ይሆናል ብሎ መድሃኒት ቀማሚው ጆን ኤስ ቴምበር ከካካዋ ፍሬ በሶዳ ውሃ በጥብጦ ያዘጋጀው ኮካ ኮላ የተባለው መጠጥ ይኸው ዛሬ በመላው ዓለም ይጠጣል፡፡ በወቅቱ ድካምንና ራስ ምታትን እንዲሁም ድብርትንና የወንዶችን የወሲብ ፍላጎት ያነሳሳል በሚል የተቀመመው ኮካ ኮላ በአዲስ መልኩ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ምስጢራዊነቱን ጠብቆ መመረት ከጀመረ እነሆ ዘንድሮ 120 ዓመታት ሆኖታል፡፡
ዘመቻ ‹‹ኮካ አትጠጡ››የድምጻዊው አድናቂዎችና በሁኔታው ስሜታችን ተነክቷል ያሉ ሰዎች በማህበራዊ ድረገፆች አማካኝነት በኮካ ኮላ ካምፓኒ ላይ መቀየማቸውን የሚያሳዩ ምስሎችንና ጽሁፎችን ለጠፉ፡፡ የካምፓኒውን ምርቶች ባለመጠጣት ተቃውሞአቸውን ለማሰማት ዛቱ፡፡ በተግባር ጉዳዩ ለመፈጸሙ
ማረጋገጫ ባናገኝም በቴዲና በኮካ ኮላ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ አበሳጭቷቸው ከኮካ ምርቶች የታቀቡ ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ግን አያዳግትም፡፡ በተለይ በማህበራዊ ገፆች ላይ በተደጋጋሚ ሲጻፍ የነበረውን ‹‹ፀረ-ኮካ›› ዘመቻ የቅስቀሳ መልዕክቶች ስንመለት የተባለው ድርጊት መጨረሻው የት ነው እንድንል ይገፋናል፡፡ የሙዚቃው አለመለቀቅ ‹‹ሀገራችን ከመናቅ›› የመጣ ነው ከሚል ሀሳብ ጋር አያይዞ ድምፃዊው ቅሬታውን መግለጹ ተቃውሞውን እንዲደምቅ አድርጎታል፡፡ በቴዲ አፍሮ የግል ድረገጽ ላይ ወጣ የተባለው መግለጫ እንዲህ ይላል፡፡‹‹ስለ ዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ
የተሰጠ መግለጫ ባለፉት ወራቶች ቴዎድሮስ ካሳሁን ወይም ‹‹ቴዲ አፍሮ›› ከኮካ ኮላ እና በስፋት ሲወራ ከከረመው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ያለንን አቋም እንድንገልፅ ሚርፍልን ጥያቄዎች ምክኒያት ከፍተኛ ጫና ሲደረግብን ቆይተናል፡፡ በበኩላችን በተገባው የውል ስምምነት ላይ ግንኙነቱን ሚጥራዊነት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባ እና ማክበር የነበረብን ቢሆንም ቅሉ የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ግንኙነት ወሬ እንዴት አፈትልኮ ወጥቶ ህዝብ እንዲያውቀወው እንደቻለ ቢያስገርመንም አሁን ለመገንዘብ እንደቻልነው የቴዲ ከኮካ ጋር ያለው ግንኙነት ኢትዮፒካል ንክ
በተሰኘ የሀገር ውስጥ የኤፍ.ኤም ሬዲዮ የመዝኛ ፕሮግራም አዘጋጆች አማካኝነት ያወጀው እና በሚያስገርም ሁኔታ ለኮካ የቲቪ ሥራም አድናቆቱን በመስጠት ያረጋገጠው የኮካ ኮላ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ምስክር ሙሉጌታ መሆኑን መረዳት ችለናል፡፡
ያለጥርጥር በኮካ ኮላ ስም ቴዲ አፍሮ ለኮካ የቴሌቪዥን ስራ በማገናኘት እና በዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ተነሳሽነቱን የወሰደው የብራንዱ ሥራ አስኪያጅ ነበር፡፡ እኛም ጥያቄን ውድ አገራችንን በመላው የዓም ዋንጫ ተመልካቾች ዘንድ አዎንታዊ ገፅታ የትኩረት እይታ ስር የሚያውላት በመሆኑ እና በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው ታላቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት ከንዋኔ ግዙፍ ቁጥር ያለው የዓለም ህዝብ ዘንድ የአገራችንን እና የህዝባችንን መልካም ገፆች ለማሳየት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ከተሟጠጠ በኋላ ነበር፡፡በመጨረሻም ምንም እንኳን በጉዳዩ ጭብጥ ዙሪያ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ስለተያዘው አቋም የተወሰነ መግባባት ላይ መድረስ ቴሌኮንፈረንስ የሚመለከታቸው ወገኖች እንደሚገኙበት ቃል ተገብቶበት የተዘጋጀ ቢሆንም ውይይቱ ሙያዊ በሆነ መልኩ ያልተዘጋጀ፣ ግልፅነት የጎደለው፣ አለመግባባት እንዳይከሰት ለማድረግ የጋራ መፍትሔ ለመሻት ሳይሆን ቅንነት በጎደለው መልኩ የኛን ሐሳብ ለመረዳት ነበር፡፡ ቴሌኮንፈረንሱ ሆነ ተብሎ ህጋዊ ወኪል የሆነውን ሥራ አስኪያጃችንን በጭብጦቹ ላይ ለመወያየት እንዳይሳተፍ በማግለል መካሄዱ በራሱ ሂደቱ በቅን ልቦና ላይ ያለተመሰረተ መሆኑ ግልፅ ማስረጃ ነው፡፡ በመሆኑም የአርቲስቱ አድናቂ ለሆኑት ኢትዮጵያዊያን እና የውጪ አገር ዜጎች በሙሉ ከኮካ ኮላ ጋር የነበረንን ግንኙነት ያቋረጥን መሆናችንን ለመግለፅ መገደዳችን እያዘንን ስንገልፅ የዓለም ዋንጫ እስከሚከፈትበት ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የወሰደውን እርምጃ በድጋሚ እንዲያጤነው ያደርግ ዘንድ በተደጋጋሚ ጥሪያችንን ስናቀርብ ብሔራዊ ጠርዝ ባለው እና በውድ አገራችን፤ በህዝባችን እና አድናቂዎቻችን ላይ ጭምር የተቃጣውን የፈሪ እና ሀገር ወዳድነት የጎደለው አሳፋሪ የክህደት እና ክብር የሚያጎድፈውን ተግባር ግን ይቅር ላለማለት ወስነናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አስከመጨረሻው ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የተጠናቀቀውን ሥራ እንዲያሰራጨው እና እንዲለቀው ግፊት ማድረጋችንን እንደምንቀጥልበት ለአድናቂዎቻችን እያረጋገጥን ከዚህ ጎን ለጎንም ከሁኔታዎች ጋር አግባብነት ያላቸው ሰላማዊ እርምጃዎችን በመውሰድ የሁለቱንም ወገኖች ገፅታን እና ጥቅምን የሚጎዳ ማናቸውም ውዝግብ በማስቀረት በአድናቂዎቻችን የተጣሉብንን አደራ መተማመን እና እምነት ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡›› ቢቀር ምን ይቀርበታል? ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ከኮካ ኮላ የቀረበለትን ጥያቄ በደስታ ተቀብሎ የዓለም
ዋንጫውን የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በሚገኘው የኮካ ኮላ ስቱዲዮ ተቀርጿል፡፡ ታድያስ መጽሔት ከአሜሪካ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ሙዚቃው እንደማይለቀቅ ከተነገረ በኋላም ኮካ ለድምጻዊው ተገቢውን የካሳ ክፍያ ለመፈጸም መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ የተቀረፀው ሙዚቃ ንብረትነቱ የኔ ብቻ ነው የሚለው ግዙፉ የለስላሳ መጠጥ ካምፓኒ ለጊዜው ዘፈኑ ባይለቀቅም ለድምፃዊው ግን ተገቢውን ነገር እናደርጋለን የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ከተመለከትነው ቴዲ ሙዚቃው ባለመለቀቁ ምንም አይቀርበትም ማለት እንችላለን፡፡ ነገር ግን ድምጻዊው ከሚያገኘው ገንዘብ ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም ፊት የምትታወቅበትን ዕድል አጥታለች፡፡ ቴዲም ቢሆን የደከመበት ሙዚቃ ከስቱዲዮ አለመውጣቱ ምቾት ይነሳዋል፡፡ ለምን ብሎ መጠየቁም ተገቢ መሆኑን የብዙዎቹ አድናቂዎች ሀሳብ ነው፡፡
‹‹ሾላ በድፍን››
ኮካ በዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ራሱን ለማስተዋወቅ የሚረዱ ሙዚቃዎች ሲያዘጋጅ የዘንድሮው ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ደቡብ አፍሪካ ላይ ለተከናወነው የዓለም ዋንጫ ‹‹waving Flag›› በሚል ርዕስ ሶማሊያዊው ድምጻዊ ኬናንን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ድምፃውያን አሰርቷል፡፡
በወቅቱ ይህ ሙዚቃ ተወዳጅ እንደነበር ይታወሳል፡፡የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር አጋር የሆነው ኮካ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ማጀቢያ የሚሆን ሙዚቃ በራሱ ስቱዲዮ መቅረጽ የጀመረው ባለፈው ዓመት ነበር፡፡ ሳምባ በሚባለው የብራዚሎች ባህላዊ የሙዚቃ ስልት የተሰራው ‹‹The World Is Our›› የተሰኘው ሙዚቃ በተለያዩ ሀገራት ሙዚቀኞችና በተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል፡፡ የዚህ ሙዚቃ ዋና አቀንቃኝ በትውልድ ብራዚላዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊ የሆነው ዴቪድ ኮሬይ ሲሆን ካለፈው መስከረም ጀምሮ ከ90 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ተዘዋውሮ ሙዚቃውን መድረክ ላይ ተጫውቷል፡፡
በዲቪድ ኮሬይ በዋናነት የተሰራው ይህ የኮካ ኮላ ሙዚቃ በሌሎች ሀገራት ድምጻውያን በተለያዩ ቋንቋዎች ተቀርጾ ለጆሮ በቅቷል፡፡ ከስቱዲዮ ያልወጣው የቴዲ አፍሮ ብቻ ነው፡፡ ለምን? እስካሁን መልስ የለውም፡፡ የኮካ ኮላ ሰዎች ከአትላንታ ሰጡት በተባለው መግለጫና ቴዲ አፍሮ በድረ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ ሙዚቃው ስላለመለቀቁ እንጅ በምን ምክንያት እንደሆን አይጠቅሱም፡፡ ነገሩ ‹‹ሾላ በድፍን›› ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከሁሉም ነገር በፊት ሙዚቃው ያልተለቀቀው በምን ምክንያት ነው? ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
‹ኮካ ሀገሪቷን ደፍሯል?›
ቴዲ አፍሮ በርካታ አድናቂዎች ካሏቸው አትዮጵያዊያን የሙዚቃ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ለኮካ ኮላ ሙዚቃ ሊሠራ ነው ተብሎ ሲነገር እንደ አንድ በሀገር ኩራት ተቆጥሮ በመገናኛ ብዙሀን ሲዘወርለት ነበር፡፡ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ተጠግቶ ከነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ጋር ተነጻጽሮ ሲቀርብ ነበር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያን በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የሚወክለው›› የሚል መንደርደሪያ ከስሙ በፊት መጠቀስ ጀምሮ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ሙዚቃው አለመለቀቁ በዚያ ሁሉ ሙቀት ላይ በረዶ እንደመጨመር ነው፡፡ ለዚያምነው በማህበራዊ ድረገፆች ‹‹ኮካ ኮላ አትጠጡ›› የሚሉ ኢትዮጵያዊያን በብዛት ብቅ ማለታቸው፡፡ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያን ወክሎ ከተጋዘበና ሙዚቃው በስቱዲዮ ከተቀረጸ በኋላ እዚያው ታፍኖ መቅረቱ ‹‹ክብረ ነክ›› መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡ ‹‹ሀገር ተደፍራለች›› የሚሉ ሀሳቦች በስፋት እየተነሱ ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ መንግስት እጁንእንዲያስገባ የጠየቁም ነበሩ፡፡ ጉዳዩ ግን የሁለት አካላት ስምምነት የሚጠይቅ ነው፡፡ ሀገራዊ አጀንዳ ለመሆን ግን አይበቃም፡፡ ተራ የቢዝነስ ስምምነትና ከዚያ ጋር ተያይዞ የተከሰተ የውል መፍረስ ነው የሚሉም ወገኖች አሉ፡፡
ኮካ ኮላ እንደአንድ የንግድ ተቋም ከድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ጋር የስራ ስምምነት አድርጓል፡፡ በስምምነቱ መሠረት ተፈጻሚ ያልሆኑ ነገሮች ካሉ ቴዲ አፍሮ ህጋዊ ጥያቄ ማንሳት ይችላል፡፡ ይሄን ለማድረግም ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡ እንዴት ተሠራ?ኮካ ኮላ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ሙዚቃ መሪ ድምጻዊ አድርጎ የመረጠው ዴቪድ ኮሬይን ነው፡፡ ይህ ድምጻዊ ከተለያዩ ሀገራት ድምፃዊያን ጋር የየሀገራቱን ቋንቋ በመጠቀም በጋራ ሙዚቃውን ሰርቷል፡፡ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ድምጻውያን ጋር በዚያው ቁጥር ልክ አንዱን ሙዚቃ ደጋግሞ ተጫውቷል፡፡ ይሄን ዕድል ካገኙ ድምፃዊያን መካከል ቴዲ አፍሮ አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቅጅ የሆነውን ሙዚቃ ዴቪድ ኮሬይና ቴዲ በጋራ ቀርፀዋል፡፡ ኮካ ኮላ በተለያዩ ሀገራት የሙዚቃ ስቱዲዮዎች አሉት፡፡ የቴዲ አፍሮና የሌሎች አፍሪካውያን ድምጻዊያን ሙዚቃ የተቀረፀው ናይሮቢ በሚኘው የኮካ ኮላ ስቱዲዮ ሲሆን ጉዳዩን የሚከታተለውና የሚያስፈጽመው ደግሞ ማንዳላ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡ ጣቢያው ግን ሙዚቃውን ‹የውሀ ሽታ› አደረገው፡፡መጨረሻው ምን ይሆን?
ለዚህ ጥያቴ ምላሽ መስጠት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ሙዚቃው ከስቱዲዮ እንዳይወጣ የተደረገበትን ምክንያት አለማወቃችን ከግምት ያለፈ እንዳንናገር ያስገድደናል፡፡ኮካ ኮላ ትልቅ የንግድ ስም ነው፡፡ በሀገራችን በብዛት ከሚዘወተሩ የለስላሳ መጠጦች መካከል አንዱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ድምጻዊ ቴዲ
አፍሮ ደግሞ ብዙ አድናቂዎች ካሏቸው የሙዚቃ ሰዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን ኮካ ኮላ በገበያው ላይ የሚደርስበትን ተጽዕኖ በመፍራት ችግሩን እልባት ይሰጠዋል ብለን መገመት እንችል ይሆናል፡፡በማህበራዊ ድረገፆች ‹‹ፀረ ኮካ›› ዘመቻ የጀመሩ የቴዲ አድናቂዎች የካምፓኒውን ስም ሊጎዱ የሚችሉ ሀተታዎችንም ደጋግመው እያስነበቡ ነው፡፡ ኮካ ለጤና ጠንቅ የሆነ ንጥረ ነገሮች እንዳሉት በመግለጽና የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ያልተለቀቀው ካምፓኒው ለኢትዮጵያ ካለው ንቀት የተነሳ መሆኑን በመዘርዘር አድማ እየቀሰቀሱ ነው፡፡
ይህን ስንመለከት ካምፓኒው በኢትዮጵያ ያለውን ተቀባይነት ላለማጣትና ስሙን ለመጠበቅ ሲል ‹የታፈነውን ሙዚቃ› ሊለቀው ይችላል፡፡
Mar 11, 2014
Mar 1, 2014
የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ
በአንድ ወቅትአንድ ዘጋቢ የኢትዮጵያን ባንዲራ በሚመለከት ተዘዋውሮ ካናገራቸው የመዲናይቱ ነዋሪዎች አንዱ፥ “እኛ አገራችንን የምንወደው ወያኔዎች ስለነገሩን አይደለም። እሱማ ባንዲራችንን ባጥላሉበት ዘመንም አገራችንን እንወድ ነበር፤ አሁንም እንወዳለን፤ ወደፊትም እንወዳለን። ይህ በደማችን ውስጥ ያለና መቼም ቢሆን ከልባችን ሊወገድ የማይችል ነገር ነው፤” ብለው እንደነበር አስታውሳለው ።
ወያኔ ወደ ሥልጣን የመጣው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያጋየ ነበር። በመጣም በነጋታው ሕገ-መንግሥቴ የሚለውን መጨቆኛ መሣሪያ ለማጽደቁ ኑ ብሎ በጠራቸው የሱ ብጤ ዘረኞች ስብሰባ ላይ ሰንደቅ ዓላማችን፣ ሲዋረድ፣ ሲብጠረጠር እንደነበር ለታሪክ ዩ-ትዩብ በተባለው የዘመኑ የድምጽና የተንቀሳቃሽ ስዕል ማሳያ የድረ ገጽ ማሳያ ላይ ለሕብረተሰቡ ለዕይታ በቅቶ ይገኛል።
ሰንደቅ ዓላማችን እንዳገራችን እራሷ ባለታሪክ ናት። ሰንደቅ ዓላማችን፣ እነሱ እንዳሏት “ጨርቅ” ብቻ ሳትሆን ስንት ደም የፈሰሰባት ወድቃ የተነሳች ልዩ የታሪካችን መዘክርና የማንነታችን ማብሰሪያ ሰንደቅ ናት።
ይችን ያክል ሰለባንዲራችን ካልኩ እስቲ ማለት ወደፈለገኩት ነገር ልሂድ ፦ ለብዙ ግዜ መልስ ያላገኘውለት ጥያቄ ነው ይህ በዚህ ምስል ላይ
የሚታየው. Ebbelsgata1,.0183Oslo.Norway ያለ የወያኔ ትኬት ኦፊስ ነው ።
ባንዲራውንም ጨምሮ ማለት ነው ። የማን ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወይስ የወያኔአየር መንገድ ባጋጣሚ በዚህ በኩል ባለፍኩ
ቁጥር ያው የሚታየኝ ነገር ቢኖር የእነዚህ ጨካኝ የሰው አውሬ ሆዳሞች ኢትዮጵያን እየመዘበረና እየገዛ ያለ ሌባ ቀማኛና ሰዶማዊ አገዛዝ ወይንም ደግሞ ዘረኝነት ኧረ ስንቱ ነገር ተነገሮ የማያልቅ መጥፎ ትዝታዎች ብቻ
፦ እስቲ መለስ ብለን እናስብ የወያኔ መንግስት ባሳለፍነው23 ዓመት ውስጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን አይነት ጢባጢቤ
እየተጫወተበት እንደሆነ መቼም በየቀኑ እያደረገ ባለው ወይም እያየንባለውነገር መቼም ሳንበሳጭ የቀረን ኢትዮጵያዊ ምድሩ
ይቁጠረን ግን እስከመቼ ድረስ እስከመቼስ ነው በማናምንበት እና በምንጠላው ነገር ላይ መወሰን የማንችለው
-ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ የግድ የዚህ የወያኔ ትኬት ኦፊስ ብቻ ነው ያለው ?
-ወያኔን መቃወም ካለብንስ በማንኛውምና በምንችለው መንገድ መሆኑን ረስተነዋል ማለት ነው ?
-ወይስ የሃገር ኢኮኖሚ ምና ምን ኧባካችሁ እንዳትሉኝ ወያኔዎች ጢባጢቤ የተጫወቱብን ይበቃናል ለነገሩ እድገትእኮ 11% lol በመቶ ????
በትንሹ ማድረግ ያልቻልነውን እንዴት በትልቁ ማድረግ እንችላለን?
እስከ መቼ ድረስ ነው እነዚህ ሰዎችስ በእንደዚህሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ባንዲራዋ ላይ በእንዲህ አይነት መልኩ የሚቀልዱት እስቲ ተመልከቱት ከዚህ በታች ያለውን ፎቶ የማን ነው የቄሳርን ለቄሳር የሕግዚኃብሔርን ለሕግዚኃብሔር አይደል
እንግዲያውንስ የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ
በትንሹ ማድረግ ያልቻልነውን እንዴት በትልቁ ማድረግ እንችላለን?
እስከ መቼ ድረስ ነው እነዚህ ሰዎችስ በእንደዚህሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ባንዲራዋ ላይ በእንዲህ አይነት መልኩ የሚቀልዱት እስቲ ተመልከቱት ከዚህ በታች ያለውን ፎቶ የማን ነው የቄሳርን ለቄሳር የሕግዚኃብሔርን ለሕግዚኃብሔር አይደል
እንግዲያውንስ የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ
Jan 23, 2014
Ethiopian stand on gay adoption !!
In a recent article in Times of Malta about gay couples adopting children, I discovered anew how pharisaical people’s ignorance and hypocrisy can be. One sentence reads: “Countries like Ethiopia had been closing doors on adoptions for Maltese because of fears that prospective single parents could be gay.”
Ethiopians, renowned for their inability to govern themselves and for living in the second poorest country in the world despite being one of the richest in mineral resources like gold, potash, copper, platinum and natural gas, are closing doors on adoptions by Maltese parents because these might be homosexual.
A country ravaged by illiteracy, corruption, child prostitution and political instability still has the damnable effrontery to pontificate on the sexual orientation of a few good souls willing to take starving Ethiopian foundlings into their care.
If this doesn’t win an award as one of the most banal acts of immorality ever to find its way into State policy, nothing will.
It is staggering that African nations only too willing to accept handouts and ‘aid’ from developed countries that endorse homosexuality will recoil in horror at one of their own being cared for by a gay couple.
Those African politicians who are so morally bankrupt that they will boast of being on the take and even hold ‘bribery auctions’ do not have the right to stand in the way of individuals whose only failings are being gay and wanting to give a few children a better life.
በሰብአዊ መብት አያያዝ አደጋ ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ገፅታ አሁን ደግሞ ተባብሷል ይለናል Human Right Watch በ2014
በሰብአዊ መብት አያያዝ አደጋ ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ገፅታ አሁን ደግሞ ተባብሷል ይለናል Human Right Watch በ2014 የዓለም የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ፡-ኢትዮጵያ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ። መንግስት በሃይማኖታዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ መግባቱን የተቃወሙ ሙስሊሞች ዓመቱን ሙሉ በጸጥታ ሃይሎች የዘፈቀደ እስር፣ እገታ፣ ድብደባ እና ሌሎች ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. የታሰሩት 29ኙ የተቃውሞው መሪዎች የፍርድ ሂደት ከጥር ወር 2013 ጀምሮ ለህዝብ፣ ለመገናኛ ብዙሃን፣ እና ለቤተሰብ አባላት ዝግ ተደርጓል፡፡ እጅግ አወዛጋቢና መሠረታዊ ግድፈት ያለባቸውን ድንጋጌዎች በያዘው የሃገሪቱ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ መሰረት ጥፋተኛ የተባሉ የተቃዋሚ መሪዎች እንዲሁም አራት ጋዜጠኞች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
ከሃገር ውስጥ በሚገኝ ገቢ እና ከውጭ በሚመጣ እርዳታ በሚደገፉ ስፋት ያላቸው የልማት ፕሮግራሞች አፈጻጸም ምክንያት የአንዳንድ ማህበረሰብ ተወላጅ ነዋሪዎች ያለበቂ ምክክር ወይም ምንም አይነት ካሳ ሳይከፈላቸው ከመኖርያቸው እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው አንስተው ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር ሃይል፣ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይፈጸማሉ፤ ለምሳሌ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የሚገኙ ተወላጅ ነዋሪዎች ለዘመናት የኖሩበት መሬት መንግስት ለሚያካሂደው የስኳር መስኖ ልማት ይፈለጋል በሚል መፈናቀላቸው እንደቀጠለ ነው። በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር የሚይዙት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞ አድርገዋል፡፡ የተቃውሞው መነሻ ምክንያት መንግስት በእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ውስጥ እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የአወሊያ መስጊድ ላይ ይፈጽማል የተባለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ነው፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹን ለመግታት መንግስት ሃይል ተጠቅሟል፤ የዘፈቀደ እስር እና ድብደባ በተቃዋሚዎቹ ላይ ፈጽሟል፤ እነዚህ ሕገ ወጥ ተግባራት በሀምሌ 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው በጥቅምት 2012ዓ.ም በጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት ክስ በተመሰረተባቸው 29 ታዋቂ የተቃውሞ እንቅስቃሴው መሪዎች ላይም ተፈጽመዋል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደቱን መገናኛ ብዙሃንን፣ ዲፕሎማቶችን እና የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ህዝብ እንዳይከታተለው ከጥር ወር ጀምሮ ዝግ አድርጎታል፡፡ አንዳንዶቹ ተከሳሾች በእስር ላይ እያሉ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል። እንዲሁም እንዳንዶቹ ተከሳሾች ለሁለት ወራት ያህል የሕግ አማካሪ ወይም ጠበቃ ያላገኙበት ሁኔታና ከቤተዘመድ ጋር ለመገናኘት የነበረውን ችግር ጨምሮ የፍርድ ሂደቱ በሕግ በተቀመጡ ስርዓቶች አግባብ መካሄዱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ በርካታ ግድፈቶች ተፈጽመዋል።
በተከሳሾቹ ላይ በመንግስት ቴሌቪዥን ውንጀላ እና ክስ ያለበት መረጃ በማስተላለፍ መንግስት ተከሳሾቹ ከፍርድ ውሳኔ በፊት ነጻ ሆነው የመገመት መብታቸውን የሚጋፋ ድርጊት ፈጽሟል። መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) ጃሃዳዊ ሃረካት የሚል ርዕስ ያለው ፕሮግራም በጥር ውስጥ የተላለፈ ሲሆን ፊልሙ ከተከሳሾቹ ውስጥ አምስቱ የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት በቁጥጥር ስር እያሉ የተቀረጸ ክፍል አካቷል። ፕሮግራሙ የተቃውሞው መሪዎችን እንደ አሸባሪዎች በመቁጠር የሙስሊሞቹን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከአክራሪ የእስልምና ሃይሎች ጋር አነጻጽሯል፡፡ እስሩ እንዳለ ቢሆንም በ2013ም ተቃውሞው ቀጥሏል፡፡ በነሃሴ ወር መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የረመዳን ወር መጨረሻ የሆነው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሚከበርበት ዕለት የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ የአይን እማኞች በአዲስ አበባ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ተሰማርተው እንደነበረ የገለጹ ሲሆን ታማኝ ምንጮች ደግሞ ሰልፈኞቹን ለመበተን ፖሊስ ከተገቢው በላይ ሃይል እንደተጠቀመ እና ለጊዜውም ቢሆንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳትፎ አዲስ መጭ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ ወር ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፤ ሰልፉ በስምንት ዓመት ጊዜ ውስጥ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው፡፡ የጸጥታ ሃይሎች የሰማያዊ ፓርቲን ጽህፈት ቤት ጥሰው በመግባት በርካታ ሰዎችን በማሰራቸውና የፓርቲውን ንብረቶች በመውረሳቸው ምክንያት ፓርቲው በነሀሴ ወር ሊያካሂድ አቅዶ የነበረው ሰልፍ ተሰርዟል። ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ብሎ ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ለመንግስት አቅርቦ የነበረው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ነበር። የዘፈቀደ እስር እና ጎጂ አያያዝ የዘፈቀደ እስር እና በእስር ቤቶች የሚደረግ ጎጂ አያያዝ ከፍተኛ ችግር መሆኑን ቀጥሏል፡፡ ተማሪዎች፣ የተቃዋሚ ጎራ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች እና ሌሎችም የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት መብታቸውን መግለጽ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው በዘፈቀደ ይታሰራሉ፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በፖለቲካ ምክንያት የሚያዙ ሰዎች ላይ በተለይም እነዚህ ሰዎች ከክስ ወይም ከፍርድ ሂደት በፊት በሚታሰሩበት እና ማዕከላዊ በመባል በሚታወቀው አዲስ አበባ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማዕከል ጎጂ አያያዝ ይፈጸማል፡፡ በሃይል በማስገደድ ከእስረኞች መረጃ፣ የእምነት ቃል እና ሃሳብ ለማውጣጣት እስከ ማሰቃየት የሚደርስ ጥቃት እና ሌሎች ጎጂ አያያዞች የሚፈጸሙባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። የተያዙ ሰዎች በተለይ ክስ ከመመስረቱ በፊት ብዙ ጊዜ የህግ አማካሪ እንዳያገኙ ይደረጋል፡፡ ያልተገባ አያያዝ የተፈጸመባቸው እስረኞች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከፍርድ ቤቶች የሚያገኙት መፍትሄ እጅጉን ውሱን ነው፤ አንዲሁም እስር ቤቶች እና ሌሎች የማቆያ ቦታዎች በገለልተኛ መርማሪዎች በመደበኛነት እንዲጎበኙ አይፈቀድም፡፡ ከመንግስት ጋር ቀረቤታ ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የተወሰኑ እስረኞችን እና እስር ቤቶችን የጎበኘ ቢሆንም በማንኛውም ገለልተኛ የሰብዓዊ መብቶች ወይም ሌላ ድርጅት መደበኛነት ያለው የክትትልና የምርምራ ስራ አይሰራም። በሃምሌ ወር ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረው የአውሮፓ ፓርላማ የልዑካን ቡድን አባላት አስቀድሞ ፈቃድ ተሰጥቶአቸው የነበረ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚገኘውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዳይጎበኙ በባለስልጣናት ተከልክለዋል።
ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት በ2009 ዓ.ም የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ ከወጡ በኋላ በኢትዮጵያ ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት በከፍተኛ ደረጃ ተገድቧል፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጁ በዓለም ላይ ካሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ከወጡ በጣም አፋኝ ህጎች አንዱ ነው፡፡ በሰብዓዊ መብቶች፣ መልካም አስተዳደር፣ ግጭት አፈታት፣ እና የሴቶች፣ የህጻናት እና አካል ጉዳተኛ ሰዎች መብቶች ዙሪያ አድቮኬሲ የሚሰሩ ድርጅቶች ከጠቅላላ ገቢያቸው 10 በመቶ በላይ እርዳታ ከውጭ ምንጮች መቀበል እንደማይችሉ ይደነግጋል፡፡ በዚህ ሕግ ሳቢያ እጅግ መልካም ስም የነበራቸው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ይሰሩ የነበረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ የቀነሱ ሲሆን ሌሎቹም ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ስራዎችን መስራት ጭራሹኑ አቁመዋል። በርካታ ታዋቂ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች በተፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት ሃገሪቱን ለቀው ተሰደዋል፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በከፍተኛ የመንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፤ እንዲሁም በርካታ ጋዜጠኞች ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ ያካሂዳሉ፡፡ መንግስትን በፅኑ የሚተቹ ድረ ገጾች እና ጦማሮች በመደበኛነት ይዘጋሉ እንዲሁም የውጭ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች በተደጋጋሚ ይታፈናሉ። ለነጻ የሃገር ውስጥ ጋዜጦች የሚሰሩ ጋዜጠኞች የሚደርስባቸው ተከታታይ ጥቃት እና ማስፈራራያ እንደቀጠለ ነው።
የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ የፖለቲካ ተፎካካሪዎችን ለማጥቃት፣ ነጻ ሃሳብን ለማፈን፣ እንዲሁም ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በሐምሌ ወር 2012ዓ.ም የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በማሴር እና አሸባሪ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ በሚል በተከሰሰው ጋዜጠኛ እና ብሎገር እስክንድር ነጋ ፈንታ ላይ የተሰጠውን የ 18 ዓመት የእስር ቅጣት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በግንቦት ወር 2013 እንዲጸና ወስኗል። እስክንድር ‘የፔን’ የመጻፍ ነጻነት ሽልማትን በ2012 ተሸልሟል፡፡ የፍትህ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የሆነችው ርዕዮት ዓለሙ ገቤቦ በጻፈችው ጽሁፍ ምክንያት በጸረ ሽብር ህጉ በተጠቀሱ ሶስት ክሶች ተከሳ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶባታል፡፡ በመጀመርያ ተፈርዶባት የነበረው 14 ዓመት በይግባኝ ወደ 5 ዓመት የተቀነሰላት ቢሆንም የቀረው የአምስት ዓመት ፍርድ ላይ ያቀረበችው ይግባኝ በጥር ወር ውድቅ ተደርጎባታል፡፡ ርዕዮት ከፍተኛ ዝና ያለውን የ2013 የዩኔስኮ ጉሌርሞ ካኖ የዓለም ፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸልማለች፡፡ የሙስሊሙ ህብረተሰብ የሚያካሂዳቸውን የተቃውሞ ሰልፎችን ሲዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞች ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል እንዲሁም በዘፈቀደ ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከህትመት ውጭ የሆነው የሙስሊሞች ጉዳይ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ሰለሞን ከበደ በጥር ወር የታሰረ ሲሆን የጸረ-ሽብር ህጉን አዋጅ በመጣስ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ የጋዜጣው የቀድሞ ዋና አዘጋጅ ዩሱፍ ጌታቸው በ2012 በተመሳሳይ ህግ ተከሷል፡፡ ሌሎች በርካታ ጋዜጠኞች በ2013 ከኢትዮጵያ ተሰደዋል፤ ይህም ሃገሪቱን በስደት ላይ ባሉ ጋዜጠኞች ብዛት ከዓለም ሶስተኛ ሃገር አድርጓታል፡፡
ከልማት ፕሮግራሞች ትግበራ ጋር በተያያዘ የሚፈጸም በሃይል ማፈናቀል የኢትዮጵያ መንግስት ከሚያካሂደው የሰፈራ መርሃ ግብር ጋር በተያያዘ አንደሚፈፀሙ የሚገለጸውን በደሎች መንግስትም ሆነ የለጋሽ ማህበረሰብ አባላት በበቂ ሁኔታ መመርመር አልቻሉም፡፡ የመሰረታዊ አገልግሎቶችን አቅርቦት ለማሟላት በሚል ምክንያት በዚህ መርሃ-ግብር 1.5 ሚሊዮን የገጠር አካባቢ ነዋሪዎች ከመኖርያ አካባቢያቸው ተነስተው በሌሎች ቦታዎች እንዲሰፍሩ ተደርጓል፡፡ ይሁንና መርሃ ግብሩ ተግባራዊ በተደረገበት በመጀመሪያው ዓመት በጋምቤላ ክልል አንዳንድ ቦታዎች የተካሄደው ሰፈራ በሃይል የተደረገ ሲሆን ድብደባ እና የዘፈቀደ እስር የተፈጸሙባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ። ከዚህም ሌላ የማስፈሩ ስራ የተካሄደው ከተነሺዎቹ ጋር በቂ ምክክር ሳይደረግ እና በቂ የካሳ ክፍያ ሳይፈጸም ነው። የዓለም ባንክን የአሰራር ተጠያቂነት የሚከታተለውና ከባንኩ ነፃ የሆነው የቁጥጥር ቡድን በስደት ላይ የሚገኙ የአኙዋክ ብሔረሰብ አባላት ባንኩ ጋምቤላ ውስጥ የራሱን የአሰራር ሁኔታዎች ጥሷል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ በማለት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ቦርድ በሐምሌ 2013 ተቀብሎታል። ይህ ሪፖርት በሚዘጋጅበት ወቅት ምርመራው በመካሄድ ላይ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የሚኖሩ 200 ሺህ ተወላጅ ነዋሪዎችን ከመሬታቸው ላይ በማስለቀቅ በ245 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የስኳር ልማት ስራ ማከናወኗን ቀጥላለች። እነዚህ በጥምር ግብርና እና ከብት እርባታ የሚተዳደሩ ተወላጅ ነዋሪዎች ለዘመናት ከኖሩበት መሬት ተፈናቅለው በሰፈራ መርሃ ግብር አማካኝነት በቋሚ መንደሮች እንዲሰፍሩ ተደርጓል።
ዋና ዋና ዓለምአቀፍ አካላት ኢትዮጵያ ከውጭ ለጋሾች እና ከአብዛኞቹ የቀጠናው ጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት አላት፡፡ ይህ ጠንካራ ግንኙነት የተመሰረተው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በምታደርገው አስተዋጽኦ፣ ከምዕራብ ሃገራት ጋር በጸጥታ ጉዳይ ላይ ባላት ትብብር እና የተወሰኑ የሚሊኒየም የልማት ግቦችን በማሳከት ረገድ ባስመዘገበችው እድገት ምክንያት ነው፡፡ ሃገሪቷ ያላት ይህ ጠንካራ ግንኙነት የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ላይ ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በዝምታ እንዲያልፍ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በ2013ም ኢትዮጵያ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያላትን የአደራረዳሪነት ሚና የቀጠለች ሲሆን ወታደሮቿም በአወዛጋቢው አቢዬ ግዛት የሰፈነውን አስተማማኝ ያልሆነ ጸጥታ በማስጠበቅ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደሶማልያ ዘልቀው መግባታቸውን የቀጠሉ ቢሆንም ወታደሮቹ በዚያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል አካል አይደሉም። ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ድጋፍ ከለጋሾች ማግኘቷን የቀጠለች ሲሆን በ2013 ያገኘችው ድጋፍ 4 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል፡፡ የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች አንደመሆናቸው መጠን ለጋሽ ሃገራት እጅግ አስከፊ ሆነውን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ አስመልክቶ ግን ዝምታን መርጠዋል። ከልማት መርሃ ግብሮች አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል የተባሉ በደሎችን አስመልከቶ የሚቀርቡ ክሶችን ለመመርመር የሚወስዱት እርምጃም እጅግ ውሱን ነው።
ግብጻዊያን ኢትዮጵያ በምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያት ከናይል ወንዝ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ወደ ግድቡ ይቀየሳል የሚል ስጋት ስለገባቸው በ2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ እና የግብጽ ግንኙነት የበለጠ ሻክሯል። 85 በመቶ የሚገመተው የናይል ወንዝ ውሃ ምንጭ ኢትዮጵያ ስትሆን ግብጽ ደግሞ ለሚያስፈልጋት ማንኛውም የውሃ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ በናይል ወንዝ ላይ ጥገኛ ነች፡፡ ግድቡ 6 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ከአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ይሆናል፡፡ የግድቡ ግንባታ የተጀመረው በ2012 ሲሆን በ2018 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከምዕራባዊያን ለጋሽ ሀገራት በተጨማሪ ቻይና፣ ህንድ እና ብራዚል የተለያዩ ከፍተኛ መጠን ላላቸው የልማት ስራዎች የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል። ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የውጭ የግል ኢንቨስትመንት እየጨመረ የሚገኝ ሲሆን በ2013 የግብርና ንግድ፣ ሃይድሮኤሌክትሪክ፣ ማዕድን ማውጣት እና ነዳጅ ፍለጋ ኢንቨስትመንት ስራዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ ነው።የግብርና ንግድ ኢንቨስትመንት በዋናነት ከህንድ፣ ከመካካለኛው ምስራቅ እና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚመጡ ሲሆን የመሬት ዋጋው ዝቅተኛ መሆን እና ለጉልበት የሚከፈለው ዋጋ አነስተኛነት ባለሃብቶቹን የሚስብ ሆኗል። እንደ ሌሎቹ በርካታ ትልልቅ የኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች ሁሉ እነዚህ መርሃ ግብሮች ሲተገበሩ ሰዎችን ከመሬታቸው በሃይል የማፈናቀል ተግባር ሊፈጸም ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ።
Jan 21, 2014
የአንድነት ፓርቲ አባል ከጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ጀምሮ በእስር እየተንገላቱ ነው
አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ በሲዳማ ጭሬ የአንድነት ፓርቲ አባል ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ወደ ክልሉ ሲመለሱ አርሲ ሚጣ ነሴቦ ወረዳ ወርቃ ከተማ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም እንደተያዙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከታሰሩበት ወረዳ ያንተ ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ ስለሆነ እዚህ አይታይም በማለት ጥር 9 ቀን ወደ ሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ተወስደው ታሰሩ፡፡ ፖሊስ ጣቢያውም እንድትለቀቅ ከፈለግክ
1ኛ እስከዛሬ የታሰርኩበትን አልጠይቅም
2ኛ ከዚህ በኋላ ወደ ፖለቲካ አልገባም
3ኛ በተፈለኩኝ ሰዓት እቀርባለሁ ብለህ ፈርምና ውጣ የሚል ቅድመ ሁኔታ ቢያቀርብላቸውም አቶ አለማየሁ ግን በሰላማዊ መንገድ የሚታገልና በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አባል ነኝ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም፣ በፍጹም አልፈርምም ብለዋል፡፡ በ 5 ክስ ከሰንሃል 4ቱን ውድቅ አድርገናል በአንዱ ግን እንከስሃለን በሚል ለማስፈራራት ቢሞክሩም አቶ አለማየሁ በአቋማቸው ጸንተዋል፡፡ የሻሸመኔ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተጫን ለምን እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ አቶ አለማየሁ በአሁኑ ሰዓት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ጣቢያ በአደራ ታሰረው የሚገኙ እስረኛ ናቸው፡፡
ሰበር ዜና ! ዛሬም ኢትዮጵያውያን በጅዳ መካ በከፍተኛ ስቃይና እንግልት ላይ ናቸው (በፎቶ የተደገፈ አዲስ መረጃ ከሳዑዲ)
ነብዩ ሲራክ (ከሳዑዲ አረቢያ)
ካሳለፍነው ወር ጀምሮ በመንግስት ጥሪ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች ባቀረቡት ቅሬታ ” ወደ ሃገር እንዳንገባ ተደርገን እየተጉላላን ነው! ” ብለውኛል። በቀን በሚሰጠው ደረቅ ብስኩትና ጥራቱ ባልተጠበቀ ሩዝ መጉዳታቸውን የገለጹልኝ ሲሆን መፍትሔ የሚሰጠን የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ተወካዮች አጥተው ቀን በጸሃይ ፣ ማታ በብርድና በቁር እንግልት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ወደ ሃገር እንግባ ብለው በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡት መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች እዚህ በጅዳ ሽሜሲ ብቻ ሳይሆን በሪያድ እስር ቤቶች እንዳሉ እንግልት እየደረሰብን ያሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸውልኛል።
ሁከት በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ-
ከጅዳ መካው የሽሜሲ መጠለያ ተነስተው ወደ ሃገር ለመሳፈር በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አየር መንገድ ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱ ቁጥራቸው 1500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን “የያዛችሁት እቃ ከሚፈቀደው ኪሎ በላይ ነው !” በሚል የተፈጠረው አለመግባባት ማክሰኞ ከቀትር በኋላ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ እንደነበር እና ከሰአታት በኋላ መረጋጋቱን ተደጋጋሚ መረጃ ደርሶኛል። የማክሰኞው ሁከት መነሻ የተመላሾችን የተከማቸ እቃ ለማየት ወደ ቦታው የደረሱትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊ በቦታው መድረሳቸውን ተከትሎ ሲሆን በእንግልቱ የተበሳጩት ዜጎች ሁከት መቀስቀሳቸው ከአይን እማኞች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለመረዳት ችያለሁ። የአይን እማኞች አክለውም ዜጎች ከሃላፊው ጋር ሊጋጩ ሲሉ በጸጥታ አስከባሪዎች ብርታት መትረፋቸውን ከቦታው በሰአቱ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። ግርግሩ ለሰአት ያህል የቀጠለ ቢሆንም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም። ሁኔታውን ለማረጋጋት በቦታው የተገኙ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች ማረጋጋት ከፈጠሩ እና ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ የአየር መንገዱን ሃላፊ ለጥያቄ ወስደዋቸው እንደነበርና ሃላፊውን ለማስለቀቅ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና ጅዳ የመጡት የሪያዱ አንባሳደር ወደ ቦታው በመንቀሳቀስ ከሰአታት በኋላ ሃላፊውን ይዘው ምሽት ላይ መመለሳቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶኛል።
የሃላፊውን ለጥያቄ መቅረብ ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው አንድ ውስጥ አዋቂ ሲናገሩ ” በአውሮፕላን አቅርቦት እጥረት እና እቃችን ሳንይዝ ወይም በአደራ ተቀብሎ ወደ ሃገር የሚያስተላልፍልን እስካላገኘን ወደ ሃገር አንገባም ያሉትን ዜጎች ጉዳይ እንዲመለከቱ በቆንስላው ጥያቄ ወደ አየር ማረፊያው ያቀኑት የአየር መንገዱ ሃላፊ ስለ ዜጎች መጉላላት መረጃ እንዳልነበራቸውና በቦታው ሲደርሱ ከሁከቱ ጋር ተያይዞ ግራ ተጋብተው ታይተዋል።” በማለት ሲያስረዱ በቆንሰሉና በአየር መንገዱ ሃላፊዎች መካከል የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገላልጠው አጫውተውኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት ከ40 ኪሎ በላይ እቃ መውሰድ አትችሉም የተባሉ ዜጎች እቃ ሃጅ ተርሚናል በሚባለው የአየር መንገዱ ማረፊያ ቦታ በብዛት ተዝረክርኮ እነወደሚገኝና የብዙዎች እቃ አድራሻ እንደሌለው የአይን እማኞች ገልጸውልኛል። “አድራሻ ያለውን እቃም በሚመለከት የጅዳ ቆንስል ሰብስበን እንልከዋለን የሚል ቃል ከመስጠት ባለፈ ምንም አይነት ተጨባጭ እርምጃ እንዳልወሰዱም” በማለት እማኞች ገልጸውልኛል።
ከአስር ቀናት ያላነሰ እንግልታቸውን በማስረዳት የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማላቸው እንባቸውን እያዘሩና በብስጭት ያስረዱኝ ወገኖች በበኩላቸው ” የአውሮፕላኑን ወጭ የሳውዲ መንግስት ከቻለ የኢትዮጵያ መንግስት እቃችን ይዘን እንድንገባ ለምን አላመቻቸልንም? ሌላው ቢቀር መንግስት በሻንጣው መጫንና ለሳምታት ብስኩት እየተሰጠንና በውሃና ምግብ ግዠ የያዝነውን ገንዘብ ስናጠፋና ስንሰቃይ በዚህ ካልረዳን ወገኖቸ ማለቱ አልገባንም ! ዜጎች አይደልንም? ” ሲሉ በማጠየቅ በተጎዳ ሰሜት ገልጸውልኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወንድም እንደገለጹልኝ ዜጎችን ማጓጓዙ እንደ በፊቱ በፍጥነት ባይከወንም አልፎ አልፎ መቶና ከመቶ በላይ ዜጎች በተገኘ የበረራ ክፍት ቦታ እየተላኩ መሆኑን በማስረዳት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የመጣውን ይህንን ችግር የቆንስሉ ሰራተኞች በተደጋጋሚ ለቆንስል ሃላፊዎች ማሰማታቸውን በመግለጽ መፍትሔ ግን እስካሁን አለመሰጠቱን አክለው ገልጸውልኛል።
የካርጎ መዘጋት መዘዝና የነዋሪዎች ሮሮ-
የአየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት ለወራት መሰናከል ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በእቃ አቅራቢ የካርጎ ኤጀንቶች በደል ደረሰብን የሚሉ ዜጎች ቅሬታ እያሰሙ ነው ። ይህ ችግርም በነዋሪዎችና በካርጎ ኤጀንሲ ሰራተኞች መካከል ውዝግብ ማስከተሉ አልቀረም። የአየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ ከስድስት ወራት በላይ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከተዘጋ በኋላ ሰሞኑን ስራ መጀመሩ እየተሰማ ነው ። ያም ሆኖ በጅዳ ዙሪያ ያሉ የካርጎ ኤጀንሲዎች ” ወደ ኢትዮጵያ የካርጎ ግልጋሎት በተለያዩ አቅጣጫዎች እንሰጣለን ! ” በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ለእቃው ማስጫኛ እየተቀበሉ እቃውን ቢረከቡም ከስድስት እሰከ አስር ወራት ለሚቆይ ጊዜ እቃውን በመጋዘ ቃላቸውን ጠብቀው እንዳላደረሱላቸው የመጫኛ ማስረጃቸውን እያሳዩ ቅሬታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ዎች ናቸው ። የሳውዲ ውጡ ህግ ከተነገረ ጀምሮና ከዚያም ወዲህ በተሰጠው የሰባት ወር የምህረት ጊዜ ጠቃሚ የሚሏቸውን ጥሪት እቃቸውን ለካርጎ ቢያስረክቡም አንድም በካርጎው መዘጋት በተጓዳኝ በካርጎ ኤጀንሲዎች ለአንድ ኪሎ እስከ 10 ሪያል በመክፈል እቃቸውን ቢያስገቡም እቃቸውን ደህንነት በማያውቁበት ደረጃ በንብረታቸው ላይ ብክነት እንዳስከተለባቸው እያዘኑ ሮሯቸውን አጫውረተውኛል።
በጀዛን የዜጎች እንቢታ እና የህግ ታሳሪዎች ሮሮ -
በጀዛን ” ወደ ሃገር እንግባ !” የሚሉ ነዋሪዎችን ጥሪ ተከትሎ የመጓጓዣ ሰነድ ለመስራት የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ተወካይ ዲፕሎማት ወደ ቦታው ያቀኑ ቢሆንም “ድረሱልን !” ሲሉ የነበሩ ዜጎች የውሃ ሽታ መሆናቸውን የኮሚቴውን በፊስ ቡክ መኖሩን የሚያሳውቀን የወገን ለወገን የህዝብ ግንኙነት ፊስ ቡክ ጠቁሞናል። በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞችም በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ዛሬም አላቆመም። “ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል! ” እያሉ ነው! በጀዛን ዙሪያ ባሳለፍነው ሳምንት መረጃ ያቀበለን የወገን ለወገን ደራሽ የህዝብ ግንኙነቱ ገጽ ባስተላለፈው መረጃ ወደ ሃገር ቤት ለመሄድ ሰላላሳዩት ዜጎች ትኩረት በመስጠት የዜጎችን ወደ ሃላፊዎች ለመቅረብ እና ለመሸኘት ፍላጎት አለማሳየታቸውን ሲገልጽም ” እነሆ ግዜው ደረሰና የሁለቱም ሃገር መንግስታት ሁኔታዎችን አስተካክለው በሰማት (አሻራ) የሚሰጡበት ቦታ ተበጅቶላቸው ከቆንስላ ፅ/ቤት ተወካይ በቆንስል አህመድ የሚመራ ቡድን ለዜጎቻችን እዚያው እንዲሰራላቸው በማሰብ ወደ ጂዛን ተጓዙ። አሁንም እዚያው ናቸው። ነገር ግን ነገሮች እንደታሰቡ እየሄዱ አይደለም። ታስቦላቸው የተሄደላቸው ወገኖች እየወጡ አይደለም የሚል አሳሳቢ ዜና ሰማን።አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ማቆያ የሚገቡት ሰዎች በቀን መቶም እንደማይደርሱ ተገለፀልን። ከጂዳ ለዚህ ጉዳይ የተንቀሳቀሰው ልኡካን አሁንም ለማገልገል ይጠብቃል፡ ምንም የሚታይ ነገር ግን የለም። በጂዛን አጎራባች ወደ ሆኑ ከተሞችም ከአካባቢው ማህበረሰብ አምስት አምስት ሰዎች ለቅስቀሳ ተልከዋል። ቢሆንም ወገናችን ዜጎቻችን የሚወጡ አይነት አይደለም። በጣም ሚገርም ነው። ” ይላል። የህግ ታሳሪዎች በበኩላቸው የቆንስል ሃላፊዎችን አነጋግረዋቸው “ለእናንተ ጉዳይ አልመጣንም! ” እንዳሏቸው ገልጸውልኛል። የህዝብ ግንኙነቱ ዜጎች ወደ ኋላ ስላፈገፈጉበት ጉዳይም ሆነ በደል ደረሰብን ስለሚሉ ህጋዊ ታራሚዎች የሰጠው መረጃ የለም ። በወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴ ለአንድ ወር በስራ አስፈጻሚነት የሰራሁ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ለቆንስል ሃላፊዎች ያቀረብኩት የዜጎች አቤቱታ እንዲታረም በተደጋጋሚ አሳስቤ የነዋሪውን አቤቱታ በጀርመን ራዲዮ በማቅረቤ በተወሰደ የ ” በዲሲፕሊን! ” እርምጃ ከኮሚቴው አባልነት በተጽዕኖ መነሳቴ ይታወሳል!
የውጭ ጉዳይ ልዑካን በጅዳ -
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡድን ከሶስት ቀናት በፊት ጅዳ ገብተዋል። ልዑካኑ በእስካሁኑ ቆይታቸው የኢህአዴግ የድርጅት አባላትንና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎችን በዝግ ያነጋገሩ ሲሆን የውይይታቸው ትኩረት በመጡበት የዜጎችን ወደ ሃገር መግባት ጉዳይ የማፋጠን ስራ ይሁን በሌላ ተዛማጅ ጉዳይ የሚታወቅ ነገር የለም። የልዑካን ቡድኑ አባላት በእስካሁን ቆይታቸው አደጋውን ለመከላከል በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች የተቋቋመውን የወገን ለወገን ደራሽ ጊዜያዊ ኮሚቴ እስካሁን ያላነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። የልዑካኑ ቡድንን ኮሚቴውን አለማነጋገሩ ቅያሞት የገባቸው አንዳንድ አባላት በበኩላቸው የዜጎች እንግልት በቅንጅት ጉድለት እየተበራከተ በሄደበት በዚህ አጋጣሚ ኮሚቴው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ላልቻለበት ሁኔታ የቆንስሉ እና የአመራሩ ድክመት እንደሆነ በማስረዳት እያደር ለይስሙላ የተቋቋመ እንጅ ወገንን ለመርዳት ከመካዝን ያለውን ውሃ ለማደል እንኳ አቅም አጥቷል በሚል ከማህበረሰቡ ወቀሳ እየቀረበበት መሆኑን በግልጽ አጫውተውኛል።
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑክ በጅዳ ቆንስል የመንግስታችን ተወካዮች ለተጠቀሱትና በከባቢው ላሉ ችግሮች አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰዱ አደጋውን መታደግ ከማንችልበት ደረጃ እንዳይደረስ የብዙ ነዋሪዎች ስጋት ሆኗል። የሳውዲ መንግስትን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስል በማስታወቂያ ብቻ የተደገፈ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ” ሰነድ የሌላችሁ ዜጎቸወ ከሳውዲ ውጡ !” በሚል ማስተላለፋቸው አይዘነጋም። ያም ሆኖ ነዋሪው በርካታ ያልተሟሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማቅረብ ለመውጣቱ ጥሪ “አሻፈረኝ!” ያሉትን በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሮሮ እና ጥያቄ ለመስማትና አፋጣኝ የመፍየትሔ እርምጃ ለመውሰድም የመንግስት ሃላፊዎች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት መፍትሔ ያመላክቱ ዘንድ ደግሜ ደጋግሜ እመክራለሁ !
ዛሬም የመረጃ ክፍተቱ ይዘጋ ፣ የምንናገረው ተጨባጭ መረጃ መሆኑን አጣርታችሁ መፍትሔ አፈላልጉ ስል ደጋግሜ” ጀሮ ያለው ይስማ!” እላለሁ !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
Subscribe to:
Posts (Atom)