በመንግስት በተጠራ ሰልፍ የሀርቡ ህዝብ ሳይገኝ ቀረ
ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ የሀርቡ አካባቢ ሙስሊም ነዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የቀረበላቸውን የሰልፍ ጥሪ ባለመቀበል አንወጣም ማለታቸው ተገለጸ።
ባለስልጣናቱ ተማሪዎቹን ከትምህርት ቤት በማስወጣት ሰልፍ እንዲያደርጉ ማድረጋቸውም ተዘግቧል።
በገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የቀረበው የሰልፍ ጥሪ ያልተገኘ ነዋሪ 50 ብር እንደሚቀጣ ቢገለጽም ህዝቡ ለማስጠንቀቂያው ቦታ ባለመስጠት በሰልፉ ሳይገኝ ቀርቷል።
ከሬዲዮ ቢላል ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው የፌደራል ፖሊሶችና ያካባቢው ባለስልጣናት በየቤቱ እየዞሩ ለሰልፍ ውጡ በማለት ሲያስገድዱ የነበረ ቢኋንም አብዛኛው ሙስሊም አሻፈረኝ ሲል እምቢ ብሎል።
የሰልፉ አላማ በግልጽ አልተገለጸም ያለው የሬዲዮ ቢላል ዘገባ ሙስሊም ያልሆኒ የአካባቢው ባለስልጣናት ከትምህርት ቤት ይዘዋቸው ለሄዱት ህጻናት ሰልፈኞች አሸባሪነትን እንቃወማለን ፣ አካባቢያችን ሀርቡ ሰላም ናት የሚል መፈክሮችን እያሰሙ እንዲቀበሏቸው ሲሞክሩ እንደነበር ገልጾል።
በቀጥታ ከትምህርት ቤት ወደ ሰልፍ እንዲወጡ የተደረጉት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት.ቤት ተማሪዎች አብዛኞቹ በገዢው ፓርቲ አባላት ሰዎች የሚነገረውን መፈክር ተቀብለው እንዳላስተጋቡም ከዘገባው መረዳት ተችሎል።
በሰልፉ ላይ የአካባቢው መኪኖች ሰልፉን እንዲያጅቡ ታዘው እንደነበር ያመለከተው ዘገባ አናደርገውም ብለው ሳይገኙ መቅረታቸውን ገልጾል።
No comments:
Post a Comment