Pages

Nov 26, 2012

የማን ይሆን ድሉ”

“የማን ይሆን ድሉ”???
1. አለማመንን ባርነትን 
ለጠላት በቅኝ መገዛትን
አልሻም ብሎ ባንዳነትን
የጠላት ዝናር ሽልማትን
ቢሞትላት ለእምነቱ ቢሰዋላት ለሀገሩ
ሐውልት ቆመለት ለክብሩ፡፡
ዓለም ቢያወሳ ጀግንነቱን
ቢዘምር አርበኝነቱን
ቢዘክር ሰማዕትነቱን 
በስልጣኔ ፈረስ ተፈናጦ 
በባቡር መንገድ ተቆናጦ
ሰማዕትነቱን ሊያስረሳ
መታሰቢያውን ሊያስነሳ 
አልሆንለት ቢለው ወንበሩ 
ተወዳጀና ከባቡሩ
ቅርስ ማጥፋትን ወደደ 
ታሪክን “ሊክብ” እየናደ፡፡

2. ጀግናው ምሏል ባዛኝቱ
   ጊዮርጊስን ይዟል ለብርታቱ
  ዝመት ተዋጋ ከኔ ጋራ
እንዳታሳፍረኝ አደራ 
ታቦትህ ወጥቷል ከመቅደስህ
በል አብረህ “ዝመት ስለስምህ” 
ብሎ ተመመ ወደ አድዋ 
ጠላትን ሊበትን እንዳሸዋ
በጠላት ሳቀ ኩሩ አርበኛ 
በጀግንነቱ ኮራን አኛ፡፡ 
ስለዚህ ነው በአደባባይ መቆሙ 
ጀግንነቱን ሁሉም እንዲሰሙ 
ነፃነትን በውስጣቸው እንዲያትሙ፡፡
3. ታሪክና ስልጣኔ 
ሊፋለሙ በወኔ
ይኸው ቆመው በዚህ አሉ
ታሪክ ደግሞ የሚያሳየን የማን ይሆን ድሉ???

1. አለማመንን ባርነትን 
ለጠላት በቅኝ መገዛትን
አልሻም ብሎ ባንዳነትን
የጠላት ዝናር ሽልማትን
ቢሞትላት ለእምነቱ ቢሰዋላት ለሀገሩ
ሐውልት ቆመለት ለክብሩ፡፡
ዓለም ቢያወሳ ጀግንነቱን
ቢዘምር አርበኝነቱን
ቢዘክር ሰማዕትነቱን
በስልጣኔ ፈረስ ተፈናጦ
በባቡር መንገድ ተቆናጦ
ሰማዕትነቱን ሊያስረሳ
መታሰቢያውን ሊያስነሳ
አልሆንለት ቢለው ወንበሩ
ተወዳጀና ከባቡሩ
ቅርስ ማጥፋትን ወደደ
ታሪክን “ሊክብ” እየናደ፡፡

2. ጀግናው ምሏል ባዛኝቱ
ጊዮርጊስን ይዟል ለብርታቱ
ዝመት ተዋጋ ከኔ ጋራ
እንዳታሳፍረኝ አደራ
ታቦትህ ወጥቷል ከመቅደስህ
በል አብረህ “ዝመት ስለስምህ”
ብሎ ተመመ ወደ አድዋ
ጠላትን ሊበትን እንዳሸዋ
በጠላት ሳቀ ኩሩ አርበኛ
በጀግንነቱ ኮራን አኛ፡፡
ስለዚህ ነው በአደባባይ መቆሙ
ጀግንነቱን ሁሉም እንዲሰሙ
ነፃነትን በውስጣቸው እንዲያትሙ፡፡
3. ታሪክና ስልጣኔ
ሊፋለሙ በወኔ
ይኸው ቆመው በዚህ አሉ
ታሪክ ደግሞ የሚያሳየን የማን ይሆን ድሉ???

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate