Nov 27, 2012
የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ እና አገራዊ ፋይዳው፤ አጭር ቁዘማ (ስደተኛው መስፍን ነጋሽ፤ ከአገረ ስዊድን) ላለፉት ሰባት ወራት በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ምህዳር (public sphere) ሳይበርዱ ከሰነበቱት ርእሰ ጉዳዮች አንዱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ እና መንግሥት ለጥያቄው የሰጠው ትርጉምና ምላሽ ይገኝበታል። ነገሩ ሰሞኑን ተካሮ ሰንብቷል። የመነጋገሪያ አጀንዳነቱም እንዲሁ በጣም ጨምሯል። በዚህ ንግግር ውስጥ በስሕተትም በእቅድም እየተምታቱ የሚቀርቡ ጉዳዮች መኖራቸውን ብዙዎች ያስተውሉታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ሆኖም ጉዳዮቹን ነቅሶ ማውጣቱ ለውይይት ብቻ ሳይሆን አቋምን ለመፈተሽም ይረዳል በሚል እምነት ነገሩን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ። ነገሩ ብዙ ጉዳዮችን የሚያሰናስል እንደመሆኑ ቁዘማዬም (reflection) ጥቂት ረዝሞ ልታገኙት ትችላላችሁ። ትእግስታችሁን እማጸናለሁ። በዚህ ጽሑፍ የኢትዮጵያውን ሙስሊሞች ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄዎች በሁለት ምክንያቶች በሌላውም ኢትዮጵያዊ መደገፍ አለባቸው እላለሁ። ሕጋዊ ጥያቄዎቹ ”ከአክራሪነት/ሽብርተኝነት” ጋራ ተደባልቀውና ተምታተው እየቀረቡ ችላ መባልም ሆነ መረገጥ አይገባቸውም ስል እከራከራለሁ። I am at Awelia because injustice is there!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment