Dec 26, 2012
እውነትን ሸሽተን የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ልናመጣ አንችልም
ዘመነ ካሣ ከጀርመን
ለሁለት አሥር ዓመታት ቤ ተ ክርስቲያንን ለሁለትና ብሎም ለሦስት እንድትከፈል አንድነታ ተናግቶ ካሕናትና
ምዕመናን ተለያይተው አሁን ለደረስንበት ጊዜ የቆየው በሕገ ቤተ ክርስቲያን የተሾሙት ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ
አቡነ መርቆሬዎስ ከጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ወንበራቸው ያለአገባብ በሕመም ምክንያት አሳበው በዘረኛውና
በጎጠኛው ወያኔ መንግሥት አማከይነት እንዲለቁ የተደረገ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው አውነት ነው::
ይሁን እንጂ ይህነ ግዙፍ እውነት በመካድ አዲስ አበባ ያሉት የሲኖዶሰ አባላት በሕመም ምክንያት መሥራት አልችልም
ብለው ነው የለቀቁት በማለት መሠረተ ቢስ የሆነ የሀሰት ቃል ሲናገሩ መሰማት ከመነኮሳት አባቶች ያውም ለእውነትና
ለቤተክርስቲያን ቆመናል ከሚሉ ሰዎች ሲሰማ እጅግ የሚዘገንን ነው ማን ነው ታዲያ እውነት ሊናገር የሚችል ??
አባሕዝቅኤል ተብለው የሚጠሩት ጳጳስ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ዓለም የሚያውቀው እውነት በመካድ ሀሰት
ሲናገሩ ትንሽ እንኳን የማይከብዳቸው ሰው ናቸው
ሰሞኑን በፕሬዝዳንት ግርማ የተጻፈውና ወዲያው የተሻረው ደብዳቤ መልካም የሚያሰኝ ነገር እንዳለ አመላክቶ ነበር፡፡
ሆኖም ዋናው ችግር በማን በኩል እንዳለ የፕሬዝዳንቱን ደብዳቤ ተከትሎ የተወሰዱ እርምጃዎች ትልቅ ማሳያ
ሆነዋል፡፡ ቤተክህነቱ በፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ ስላልተደሰተ መንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ እንደገባ በመቁጠር
ፕሬዝዳንቱን መውቀሱና ፕሬዝዳንቱም የጸፉትን ደብዳቤ ለማጠፍ እንደተገደዱ መረዳት ተችሏል፡፡ ቤተክህነቱ
የፕሬዝዳንት ግርማን ደብዳቤ ተቃውሞ ሲነሳ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገቡ በሚል ቢሆንም በዋናነት ግን አቡነ
መርቆሬዎስን ላለመቀበል ትልቅ ሽፋን የነበረውና «እኛ ይመለሱ ብንልም መንግስት አይደግፋቸውም» የሚለው ሰበብ
በፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤ በጥቂቱም ቢሆን መሸርሸሩ ደስ ስላላሰኛቸውና ከዚህ ውጪ የሚያቀርቡት ምክንያት ብዙ
የሚያራምዳቸው ሆኖ ባለመገኘቱ እንደሆነ ተገምቷል፡፡
አቡነ ጳውሎስ
በሕይወት
እያሉ በውጭ
ካለው
ሲኖዶስ ጋር
ለሚካሄደው
የእርቁ ሂደት
ትልቅ
እንቅፋት
እንደሆኑ
ተደርጎ
አብረዋቸው
ባሉትና ያኔ
ሲቃወሟቸው
በነበሩትና ዛሬ
የሚሉትላለመታረቅ ወስነው እርቁ
ጳጳሳት ጭምር ብዙ ሲባል እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ከእርሳቸው ዕረፍት በኋላ ነገሮች ይለወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም
እንዲያውም ብሰው ነው የተገኙት፡፡ ቀድሞስ አቡነ ጳውሎስ ናቸው እንቢ ያሉት እንበል፤ አሁን ግን አቡነ መርቆሬዎስ
ወደመንበራቸው ሊመለሱ አይገባም የሚሉት ጳጳሳት አላማቸው ምንድነው? የሚለው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በተለይም
«5ኛ ብለን ወደ4ኛ አንመለስም፤ 6ኛ ነው የምንለው» የሚለው ምላሽ ለአቡነ ጳውሎስ ክብር ከመጨነቅ የሚመነጭ
እንዳልሆነ ታውቋል፡፡ ይህን መግለጫ የሰጡት አቡነ ህዝቅኤልን ጨምሮ ሲኖዶሱን እያናወጡ ያሉት ጥቂት አስቸጋሪ
ጳጳሳት አቡነ ጳውሎስ የሾሟቸውና የአቡነ ጳውሎስ ተቃዋሚ ሆነው የዘለቁ ናቸው፡፡ ታዲያ ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ
ለምን እንዲህ አሉ? ይህን አቋምስ ለምን ያዙ ቢባል አንዱ ምክንያት ቀጣዩ ፓትርያርክ ለመሆን እየተሻኮቱ ስለሆነና
የአቡነ መርቆሬዎስ ወደመንበራቸው መመለስ ነገሮችን ሊቀይርባቸው ስለሚችል ነው። እነዚህ ጳጳሳት የግል
ጥቅማቸው እንጂ የቤተክርስቲያን አንድነት እንደማያሳስባቸው ግልጽ እያደረጉ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ለ 20ዓመታት በ ሁለት ሲኖዶስ ስተመራ የቆየችው እኮ የቀድሞው ፓትርያርክ በህይወት እያሉ
ለምን ሌላ ፓትርያርክ ተሾመ በሚል የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ነበር። እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ አንደኛው ከዚህ
ዓለም በሞት ተለዩ። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድነት ለመመለስ ግልጽና ትክክል የሆነው እርምጃ በይህወት ያሉትን
ፓትርያርክ ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን መሪ ማድረግ ነው። ይሄ ለምን ድርድር እንደሚያስፈልገውና ከባድ እንደሆነ
ለህዝብ ግልጽ አይደለም።
የዚህች ቤተ ክርስቲያን አንድ መሆን ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ድርሻ ነበረው ይሁንና የቀኖና ቤተክርስቲያንን
መጣስ ወደ ጎን በመተው ላለመታረቅ ሰንካላ ምክንያት በመደርደር የቤተ ክርስቲያን መከራ እንዲራዘም የሚሮጡ
ትንሽ ናቸው ማለት አይቻልም ከአንዳድ የሥልጣን ጥመኞች ጳጳሳት በግለሰብና በማሕበር የተደራጁ ቡድኖች
በስውርና በግልጽ የሚሸርቡት ተንኮል እጅግ አስገራሚነው የማሕበረ ቅዱሳን አባላት ነን የሚሉት እነ ዲያቆን ዳንኤል
ክብረት የሚሰጡት አስተያየት ስድስተኛ ፐትርያርክ ለማስመረጥ ሕግ በማርቀቅ የሚሮጡት አነ ቄስ ሰሙ ምትኩ
በፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴነት ላይ ታች ከሚሉት እነ አአቶ ባያብል ሙላቴ የሚሸርቡት ተንኮል እጅግ አሳፋሪ
ነው ታዲያ ቀደም ሲል በፓትርያርክ ምርጫና ቅስቀሳ ተጠምዶ የነበረው ደጀሰላም አሁን ላይ ስለ እርቅ መስበኩ ረፈደ
ባይባልም ስለ ቀኖና ቤተክርስቲያን መጣስ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዴት ሊፈርስ እነደቻለ እውነቱን ከመጻፍ
ይልቅ ” አቡነ መርቆሬዎስ የት ነው ያሉት ” በማለት የፍለጋ ማስታወቂያ ሲሠራና የምርጫ ደንብ ሲያረቅ እንደሰነበተ
ሊካድ የማይችል እውነት ነው
ስለዚህ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች መፈትሔው አጭርና ግልጽ ነው ችግሩ የቀኖና ቤተ
ክርስቲያን መጣስ እስከሆነ ድረስ መፍትሔው በሕይወት ያሉትን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ማድረግ
ነው ሐቁንም መከተል ሕገ ቤተ ክርስተያንንንም ማክበር ነው
እውነትን በማድበስበስ መግለጫ በመደርደር አንድነት ሊመጣ አይችልም
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment