Pages

Dec 29, 2012

የውስጥ አፓርታይድ


በዮሴፍ ሽፈራው (ከጀርመን)

ወያኔ /ኢህአዴግ ለ 21 ዓመታት ሀገራችን ኢትዮጵያን በዘር፣ በቋንቋ ፣በቀለም እንዲሁ በመልካ ምድር ከፋፍሎ
ሀገሪቷን ለ40 አና 50 ዓመታት ለመግዛት በነደፋቸው ዕቅዶች መሰረት ንግዱን፤መከላከያውን፣የሀይማኖት
ተቋማትን፣ ምርጫ ቦርዱን፣መገናኛ ብዙሀኑን ፣የፍትህ ተቋማትን ፣የደህንነት ሀይሉን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር
አውሎታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአንድ ሀገር ውሰጥ የአንድ ብሄር ተወላጆች ብቻ የሚማሩበት የትምህርት ተቋም
በማቋቋም የአለማችን ብቸኛ አንባገንነ፣ ዘረኛ የውስጥ አፓርታይድ አራማጅ መንግስት ስለመሆኑ በቂ ምስክር ነው፡፡
በመቀሌ ከተማ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ወይም በሌ.ጀነራል ሳዕረ መኮነን ከሚመራው ስሜን እዝ ፊት ለፊት
ትንሽ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባው መቀሌ ኢንስቲቲዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ(MIT) በሚገባ
የተደራጀ ነው፡፡ የትምህርት ስርዓቱም የአሜሪካንን የትምህርት ስርዓት ተከትሎ የተቀረጸ ሲሆን በሁሉም
የምህንድስና( Engineering )የትምህርት ዘርፎች የክልሉን ተማሪዎች ብቻ ይቀበላል፡፡ በቤተ-መጽሀፍት ፣
በቤተ- ሙከራ እና በኢ.ላይበራሪ(E-library) በሚገባ የተደራጀው ይህ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ትምህርት
ሚኒስቴር ከሚስተዳድራቸው አገልግጎት በመስጠት ላይ ካሉት እና በግንባታ ላይ ካሉት በድምሩ 31 ዩኒቨርሲቲዎች
እውቅና ውጭ ሲሆን የኢንስቲቲውቱን ዲን ጨምሮ አብዛኞቹ የኢንስቲቲዩቱ መምህራኖች የውጪ ዜጎች ናቸው፡፡
የኢንሰቲቲዩቱን ቅበላ በተመለከተ ወያኔ/ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ከወሎ አላማጣን፣ከጎንደር ሁመራን ቆርሶ
ወደክልሉ ግዛት ያስገባቸውን ከተሞች ጨምሮ በሽሬ፣በአክሱም፣በአድዋ፣በአዲግራት፣በመቀሌና በማይጨው ከተሞች
ለከፍተኛ ትምህርት የደረሱ ተማሪዎችን የተዘጋጀውን የክልሉ መግቢ ፈተና ወስደው ወደ ተቋሙ እንዲገቡ
ይደረጋል፡፡ከዚህ ጎን ለጎን ተማሪዎቹ ሀገር አቀፉን (ብሄራዊ) ፈተናውን የመውሰድ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡
ተቋሙ በስሩ የሚተዳደር ቀዳሚኖ የሚባል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲኖረው በክልሉ ጥሩ
ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች መልምሎ ይቀበላል፡፡እነዚህ ተማሪዎች ወደ ኢንስቲቲዩቱ የመግባት እድላቸው ከፍተኛ
ነው፡፡ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በህይወት በነበሩበት ጊዜ አልፎ አልፎ በምርቃት ስነ-ስርዕቱ ላይ በመገኝት ለመራቂዎቹ
በትግረኛ ንግግር ያደርጉላቸው ነበር፡፡የምርቃት ስነ-ስርዕቱም ድምጽ-ወያኔን ጨምሮ በየትኛውም የሀገሪቱ መገናኛ
ብዙሀን እንዲዘገብ አይደረግም፡፡ ተማራቂዎቹ መንግስት ከመደበኛ ስራቸው ጎን ለጎን የደህንነቱን ስራ ይሰሩልኛል
ወደሚላቸው የመንግስት ተቋማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ኢትዮ ቴሌኮም፣በኢትዮጵያ መብራት ሀይል፣ጉምሩክ
፣መከላከያ፣የመረጃ ደህንነት ቢሮ(INSA) በመንገዶች ባለስልጣን እንዲሁም በሌሎች ማንኛውም ተቋማት ያለምንም
ውድድርና የቅጥር ማሰታወቂያ በቀጥታ ተመርቀው እንደወጡ ተመደበው ዳጎስ ያለ ጥቅም እንዲገኙ ሲደረግ ቀሪዎቹ
ደግሞ በውጪ ሀገር በሚገኙ ታላለቅ ዩኒቨርስቲዎች ለተጨማሪ ከፍተኛ ትምህርት ይላካሉ፡፡ ከኢፈርት እህት
ድርጅቶች ጋር በቅርበት የሚሰራው ይህ ኢንሰቲቲዩት በቅርቡ ማስፋፊያ እየተደረገላቸው ካሉት ሞሰቦ ሲሚንቶ፣ሱር
ክንሰተራክሽን እንዲሁም ሌሎች እህት ኩባንያዎች የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ላይ የተመራቂዎች ሚና የጎላ ነው፡፡
የወያኔን ስርዓት የሚያራምዱትን ና የሚደግፉትን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሌላውን ኢትዮጵያዊ በተሳሳተ
የትምህርት ፖሊሲ ትውልዱን እያመከኑ የአንድን ብሄር የበላይነት ላማስቀጠል የሚደረግ ሩጫ አሁንም ተጠናክሮ
እንደቀጠለ ነው፡፡ኢትዮጵያ ሁሉንም ዜጎቹዋን በእኩልነት የምታስተናግድ አንድነቷን የጠበቀች እውነተኛ ዲሞክራሲ
የሰፈነባት ፣ፍትህ፣እኩልነት፣ነጻነት ዜጎቿ የሚያገኙበት እድትሆን ሁላችንም የየበኩላችንን አስተዋጽኦ እናድርግ፡፡
የዜጎችን እኩልት በጋራ እናረጋግጥ!!!

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate