(ከአዘጋጁ፡ ውድ የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አንባቢዎች በቤተክርስቲያን ሰላም እና አንድነት እንዲመጣ የተለያዩ ዘገባዎችን
ስናቀርብ ቆይተናል። በርከት ያሉ አንባቢዎቻችን በምናቀርባቸው ዘገባዎች ያላቸውን ማበረታቻ ስለለገሱን
እናመሰግናለን) ከሁለት ሰዓት በፊት በሰበር ዜናችን አቶ አባይ ጸሐዬ በስደት ያለውን ሲኖዶስ በአሸባሪነት
መንግስታቸው እንደሚከስ መናገራቸውንና የቅዱስ ሲኖዶሱም አስቸኳይ ስብሰባ ለሰላምና ለአንድነቱ መፍትሄ
የማይሰጥ ውሳኔ በማሳለፍ የዛሬውን ውሎ ማጠናቀቁን መዘገባችን ይታወሳል። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አሁንም በዚህ
ዙሪያ ጠለቅ ያለ መረጃ እንዲኖራቸው በማሰብ ወደ ሃገር ቤት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎችን ወደ ምንጮቻችን
ስናደርግ ቆይተናል። ምንጮቻችን ያደረሱን አዲስ መረጃ ቢኖር “የሰላምና የአንድነት ፍጻሜው እልባት ካገኘ በኋላ
ውጭ ሃገር ከሚገኙት አባቶች ጋር በጋራ የፓትርያርክ ምርጫውን እናድርግ በሚለው አቋማቸው የጸኑት የቅዱስ
ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል (ፎቶ) አባይ ጸሐዬና ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም የተገኙበትን ስብሰባ
ረግጠው መውጣታቸው ነው። የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ እዝቅኤል ስብሰባውን ረግጠው ለምን እንደወጡና
የልዩነት አቋማቸውን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንደሚናገሩ ዝተዋል የተባለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት
በከፍተኛ የደህንነቶች ክትትል ሥር እንደሆኑ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።)
ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን አሁንም ተከታትላ አዳዲስ መረጃዎችን ለአንባቢዎቿ ታቀርባለች።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment