Pages

Jan 6, 2013

በአፈናና ግድያ የህዝቡን የነጻነትና የመብት ጥያቄ ትግል ማቆም አይቻልም! ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ


ኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግር ም/ቤት በዛሬው እለት ሙስሊም ወገኖቻችን ባካሄዱት ድምፃችን ይሰማ ተቃዉሞ የተጀመረበትን 1ኛ አመት ለማክበር ባከናወኑት እጅግ ታላቅ ሀገር አቀፍEthiopian National Transitional Council የተቃዎሞ ሰላማዊ ስልፍ ላይ እጅግ በሚያሳዝንና በሚሰቀጥጥ ሁኔታ አንድ እድሜዉ ከአስር አመት በታች የሆነ የሀረር ከተማ ህጻን በጨካኞቹና ጨፍጫፊዎቹ ፌደራል ፖሊሶች ተገድሏል። ምክር ቤቱም የህፃን ልጅ ግድያዉ እጅግ ሰብአዊነት የጎደለዉና የስርአቱን አረመኔነት ደግሞ የሚያረጋግጥ ተግባር መሆኑን በመግለጽ ግድያዉን በምሬት አጥብቆ ያወግዛል። የሽግግር ም/ቤቱም ጉዳዮ ባስቸኳይ ተጣርቶ ግድያዉን የፈፀሙት በህግ ፊት በሃላፊነት እንዲጠየቁ አጥብቆ ይጠይቃል። ግድያዉንም ሁሉም የሀገራችንና የአለማቀፉ ማህበረሰብ እንዲያወግዘዉና በሃገር ዉስጥ ያሉ የፖለቲካና ሲቪክ ድርጅቶችም ግድያዉ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ግፊት እንዲያደርጉና ወንጀለኞቹ ለህግ የሚቀርቡበት ሁኔታ ላይ ተባብረዉ እንዲሰሩ ጥሪዉን ያቀርባል። በዛሬዉ እለት ሰማእት የሆነዉ ህፃን በሁላችንም ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህ፤ ለህዝቦች ነፃነትና፤ እኩልነት በምንታገለዉ ወገኖች ዘንድ ዘላለም በሰማእትነት ሲዘከር ይኖራል። የህፃኑም ሰማእትነት ሁላችንም ለትግሉ ያለንን ቅርጠኝነትና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክርና የድሉንም ሂደት እንደሚያፋጥን ጨቋኞቻችን እንዲረዱ በድጋሚ እያረጋገጥን ለሰማእቱ ልጃችን ቤተሰቦች አምላክ ጽናቱን እንዲሰጥ እንለምናለን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
ሽግግር ም/ቤቱ ስራ አመራር

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate