Pages

Feb 19, 2013

ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ጭንቀት የፈጠረበት ዝዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በትናንትናው እለት ሞባይል ኔትወርክ አቋርጦ እንደነበር ታወቀ


ላለፈው አንድ አመት በጽናት የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ የሚገኙት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የፈጠሩበት ጭንቀት ያደናበረው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ  ከጁምአ ጸሎት ስርዓት ጋር ረብሻና ከፍተኛ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት ትናንት ማለዳ በአዲስ አበባ የሞይባል አገልግሎት ከአምስት ሰዓታት በላይ እንዲቁአረጥ አድርጎ እንደነበር ዘጋቢያችን በላከልን ሪፖርት ገለጸ፡፡
እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ከጊዜ ወደጊዜ በጽናት ድምጻቸውን የሚያሰሙት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በመደበኛ የጁምአ ፕሮግራማቸው እርስ በእርስ በመጠራራት እና አጫጭር የስልክ መልዕክቶችን በመለዋወጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊያደርጉብኝ  ይችላሉ በሚል ፍርሃት ሐሙስ ለዓርብ አጥቢያ በግምት ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የተወሰኑ የሞባይል ሰልክ ቁጥሮችን ከግንኙነት ውጪ የማድረግና ኔትወርክ የማቋረጥ እርምጃንም ወስዱአል፡፡
የህዝብ መንገላታት ደንታ የማይሰጠው የወያኔ አገዛዝ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ያነጣጠረ ርምጃው በበርካታ ግለሰቦችና የቢዝነስ ተቋማት ላይም ተመሳሳይ ተጽእኖ በማሳደሩ የእርስ በርስ ግንኙነት ማድረግ ሳይችሉ ለማርፈድ መገደዳቸውን ዘጋቢያችን አያይዞ ገልጹአል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ሁሉም የሞይባል አገልግሎት ያልተቋረጠበት ዋንኛ ምክንያት ምን እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ባገኘው መረጃ የተወሰኑ የደንበኛ ጭነት ያለባቸው መስመሮች ግንኙነት ከተቋረጠ ያልተቋረጠባቸው ስልኮች ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም ማለታቸውን ገልጹአል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ቁጥሮች አለመቋረጣቸው ቴሌ ለሚነሳበት ቅሬታ የኔትወርክ መጨናነቅ ነው በሚል ጉዳዩን ለማስተባበል ስለሚረዳው ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑን እነኝሁ ምንጮች መጥቀሳቸውንና የዚህ ዓይነቱ አሰራር ሲፈጸም የመጀመሪያው አለመሆኑን ማመልከታቸውን ኢሳት ገልጹአል፡፡
በስፋት እንደሚታወቀው ካሁን ቀደምም  መለስ ዜናዊና ሌሎች የአገር መሪዎች በከተማ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ ሲገቡና ሲወጡ መንገዶችን ከመዝጋት ባሻገር ሸብርተኝነትን አስቀድሞ ለመከላከል በሚል የተወሰኑ የሞይባል ግንኙነቶች ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሲቋረጡ መቆየታቸውን ሲዘገብ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በአፋኙ የወያኔ ስርአት በሞኖፖል የተያዘው የቴሌኮም ዘርፍ ለግሉ ዘርፍ ክፍት እንዲሆን ከማይፈለግባቸው ምክንያቶች አንዱ አገዛዙ ባሻው ጊዜ ስልኮችን የማቋረጥ፣የመጥለፍና የመሳሰሉ ህገወጥ ድርጊቶችን ለመፈጸም እንዲረዳው በማሰብ መሆኑን ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ደህንነት መ/ቤት “ጀሃዳዊ ሃራካት” በሚል ርዕስ በሕግ ጥላ ስር የሚገኙ ሙስሊም እስረኛችን በማስገደድ የተጠናቀረ ፊልም ጥር 28 ቀን ምሽት በኢቴቪ ካሰራጨ በኋላ እንደገና ከዳር እስከዳር የተቀጣጠለውን የሙስሊሞች ተቃውሞ ለማዳፈን ዜጎች በነፍስ ወከፍ ኮንትራት ገብተው እያገኙ ያሉትን የሰልክ አገልግሎት ከፈቃዳቸው ውጪ በማቋረጥና በማስተጓጎል ሥራ ውስጥ መጠመዱ አገዛዙ አሁን ያለበትን ገደብየለሽነት ፍርሃት በግልጽ የሚያመላክት ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate