“አፍሪኮም ወደ አገርህ ተመለስ”
አፍሪኮም ከጀርመን ውጣ - ዛሬውኑ! አፍሪኮም ከአፍሪካ ውጣ- ቶሎ ብለህ!
የአፍሪካ አንድነትን 50ኛ ዐመት የመመስረቻ በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ የወጣ መግለጫ!
“እኛ እዚህ በአዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ የተሰበሰብነው የአፍሪካ መሪዎችና መንግስታት፣ ማንኛውም አገርና ህዝብ የራሱን ዕድል ወሳኝ መሆኑን እናምናለን፤ በዚህም ምክንያት ነፃነት፣ እኩልነት፣ ትክክለኛ ፍርድና ክብር የአፍሪካ ህዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችና የሚገባውም መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ በመሆኑም የተፈጥሮ ሀብታችን የመጠበቅና፣ ህዝቦቻችንም የተፈጥሮ ሀብታቸውን የመጠቀምና፣ ለሚገባቸው የህብረተሰብና የኢኮኖሚ ዕድገት የማዋል መብታቸው እንደሆነ እናምናለን፤ ለዚህም እንታገላለን።”
እ.አ.አ. በግንቦት 25 1963 ዓ.ም በሞዲቦ ኪዬታና ሲልቫኖስ ኦሊምፒዮ የረቀቀውና፣ በጊዜው ነፃነታቸውን የተቀዳጁት 33 የእፍሪካ መንግስታት ያፀደቁት ስምምነት መልዕክቱና ዋናው መሰረተ-ሃሳቡ ምንድነው? አንድ ነገር ማለት የሚቻለው በተለይም በቻርተሩ ላይ የሰፈረው ቁም ነገር ተግባራዊ አልሆነም፤ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ አንድነት ሊረጋገጥ አልቻለም። ከ50 ዐመት በኋላ የአፍሪካ አንድነት የአፍሪካን አንድነት ድርጅትን ቢተካውም አሁንም ቢሆን ሁሉም የአፍሪካ አገሮች ተፈጥሮ የለገሳቸውን የተትረፈረፈ የጥሬ ሀብት ለመጠቅምና መብታቸውን ለማረጋገጥ በመታገል ላይ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ላይ በተስፋፋው የስራ ክፍፍል አህጉሪቱ በመበደልና ቁራኛ በመሆን ሙሉ መብቷን እንዳታረጋግጥ የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ከፍተኛ እንቅፋት ሆነዋል። እንዲያውም አልፎ ተርፎ በቅርቡ በፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስተር የወጣው መግላጫ እንደሚያረጋግጠው ፓን አፍርካኒዝም የሚለው አስተሳሰብ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሯል በማለት ካለማፈር ይናገራል።
ዛሬ ከሃምሳ ዓመት በኋላ የአፍሪካ አንድነት የተቋቋመበትን በዓል ስናከብር፣ እኛ በጀርመንም ሆነ በአፍሪካ፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የምንገኝና የዓለምአቀፋዊነት ሃሳብ ይዘን የምንታገልና የሚያገናኘን፣ እንደገና የቅኝ አገዛዝን መድህር እንድናገላብጥ ተገደናል። እንደሚታወቀው በ19ኛውና እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የቅኝ አገዛዝ በአፍሪካ ውስጥ ተስፋፍቶና ተንሰራፍቶ እንደነበር ግልጽ ነው። በ1885 በበርሊን ኮንፈረንስ ላይ በተለይም ኮንጎን ዋና የቅኝ ገዢዎች የነፃ ንግድ መድረክ ለማድረግ ስምምነት ሲደረስና ከዚያ በመነሳት ጠቅላላውን አፍሪካ ለመቆጣጠር ጣልቃ መግባት እንደሚያስፈልግ ሲታመን የቅኝ ገዢዎች ወንጀለኛነታቸውን በገሃድ አረጋግጠዋል።
በ2013 ዓ.ም ደግሞ አፍሪኮም አፍሪካን ለመቆጣጠርና ሀብቷን ለመዝረፍ በጀርመን ከተማ ሽቱትጋርት ሲቋቋም የቱን ያህል ትልቅ ወንጀልና፣ አህጉሪቱን በዘለዓለም ውዝግብ ውስጥ ለመክተት እንደታቀደ ማሰብ ይቻላል። በተለም አሁን ባለው ዓለም አቀፋዊ የኃይል አሰላለፍና የጂኦ ፖለቲካ እሽቅድምድሞሽ የአህጉሪቱ ነፃነትና ህዝቦቿም ዕወነተኛ መብታቸውን ለማረጋገጥ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደወደቁ ከአሁኑ መናገር ይቻላል። በተለይም በተደጋጋሚ ጦርነትን በቀሰቀሰና በዚህም አማካይነት ብዙ ጉዳት በደረሰበት በጀርመን አገር ይህ ዐይነቱ የዘረፋ ጦር ሰፈር መቋቋሙ ብዙዎችን ከአፍሪካ ህዝብ ጋር የቆሙትንና የሚተባበሩትን አስቆጥቷቸዋል።
የአፍሪካ የአህጉሩ ኮማንዶ (AFRICOM) በመባል የሚታወቀው የተመሰረተው በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ ሲሆን፣ ዋናው ዓላማውም የምዕራቡን ዓለም የወራሪነት ፖለቲካ ለማረጋገጥና የአፍሪካን ሀብት ለመቆጣጠርና ለመዝረፍ ነው። ለዚህ ሸፋን የሆነው አሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሟን ማስጠበቅ የሚል ሲሆን፣ የአፍሪካ መንግስታትን “የመከላከል ኃይል” በማሳደግ ከውጭ የሚመጣውን አደጋ ለመከላከልና ወደ ውስጥ ደግሞ “ሚዛናዊ ዕድገት” ለማምጣት በሚል ሽፋን ነው።
በአሜሪካ መንግስት ቁጥጥር ስር ያለው አፍሪኮም ወይም የአህጉሪቱ ጦር እ.አ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በሽቱትጋርት የተቋቋመና እዚያው የሚገኝ ነው። የቀድሞው የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር (2005-2009) የነበሩትና የሶሻል ዲሞክራት አባሉ ቫልተር ሽታይንማየርና የቀድሞው የባደን ቩትንበርጉ የክፍለ-ሀገር አስተዳዳሪ (2005-2010) ሁኔታውንና ጉዳዩን ጠጋ ብለው ሳይመረምሩ ይህ የወራሪ ጦር ሰፈር እንዲቋቋም በፊርማቸው ፤ ተስማምተዋልም። በተጨማሪም በሽቱትጋርት ከተማ በአፍሪካ ውስጥ የጦር ልምምድ ለማድረግ የተዘጋጀ የአሜሪካ የባህር ጦር በተጨማሪ ይገኛል።
በጀርመን ህገ-መንግስት በአንቀጽ 26 መሰረት ማንኛውም በጀርመን ምድር አንድን አገር ለመውረር የሚደረግ የጦርነት ዝግጅትን አጥብቆ ይከለክላል። በተለይም በዚህ አንቀጽ መሰረት በዓለም ህዝቦች መሀከል ሊኖር የሚገባውን ሰላማዊና ተከባብሮ መኖርን የሚያደፈርስ ጦርነት ከጀርመን ምድር መቋቋምና መነሳትም እንደሌለበት ቁልጭ አድርጎ አስፍሯል። በተጨማሪም በህገ-መንግስቱ በአንቀጽ 25 መሰረት ማንኛውም የዓለምን ሰላምና በህዝቦች መሀከል የሚኖረውን ተከባብሮ መኖር የሚያደፈርስ ሁሉ የጀርመንንም ህግ የሚጥስ ነው ብሎ ያረጋግጣል። እ.አ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ጀርመን የዓለም አቀፍ ህዝብን የሚመለከት የመቀጫ ህግ የያዘች ሲሆን፣ በዚህም መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በህዝቦች ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ግፍና ግድያ፣ እንዲሁም ፀረ-ህዝብ ድርጊት የምትቃወምና ይህም ከራሷ ህግ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ተቀብላለች። የመቀጫው ህግ እንደሚያረጋግጠው ማንኛውንም ፀረ-ህዝብ ድርጊትና ግድያ በየትኛውም ዓለም የሚካሄደውን የሚመለከትና በጀርመን አገር ብቻ ያልተገደበ መሆኑን ያስታውቃል። አንድን የውጭ ጦር በጀርመን ምድር ለማቋቋም እ.አ በጥቅምት 23፣ በ1954 ዓ.ም ስምምነት የተደረሰበት ከ2+4 ውል ነው። ውሉ ግን ሌላን አገር ለመውረሪያ የሚያገለግል አይደለም።
አፍሪኮም(AFRICOM) በተቻለው መጠን ዋናውን መቀመጫውን በአንድ የአፍሪካ አገር ማድረግ ይፈልጋል። አፍሪኮሞን ወደ አፍሪካ ለማዘዋወር ሙከራ ቢደረግም አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ሲቃወሙት፣ ጥቂት የአፍሪካ አገሮች እያሰቡበት ነው። ሊታለሉም እንደሚችሉ ፍንጮች ያመለክታሉ። በተለይም አሁን ባለው የማታለልና የማሳመን ስትራቴጂ፣ በተጨማሪም የአፍሪካ አገሮችን ልትወረሩና ልትከበቡም ትችላላችሁ በሚል ግፊትና ስሜትን መሰባያ ዘዴ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ሊያምኑና በራቸውንም ክፍት ሊያደርጉና መስፈሪያም ቦታ ሊሰጡ ይችላሉ። እንደሚታወቀው እንደዚህ ዐይነቱ ወራሪ ጦር የሰሜን አትላንቲክ ጦር አባል አገሮችን፣ በተለይም አሜሪካንና አንዳንድ ጠንካራ አገሮችን ሲጠቅም፣ ፈረንሳይም የዚሁ ስምምነት ተጋሪናን አንዳንድ የአፍሪካ ዘራፊ መንግስታትም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ግልጽ ነው። የአፍሪኮም ዋናው መቋቋም ዓላማው የአፍሪካን የጥሬ ሀብት ለመቆጣጠርና ለመዝረፍ ሲሆን፣ በተጨማሪም ብሪክ (BRIC) መንግስታት የሚባሉትን እንደ ራሺያ፣ ህንድ፣ ብራዚልና ቻይናን የመሳሰሉትን ለመግታትና ከነሱ ጋር ለመፋለም የተዘጋጀ ነው። ከዚህም በተጨማሪም በአፍሪካ ውስጥ ራስን ለመቻል የሚደረገውንም ትግልና ጥረት በእንጭቹ ለመቅጨትና ለመዋጋት የሚያመች ነው።
ማንኛውም የሰሜን አትላንቲክ የጦር ስምምነት አገሮች እንደዚህ ዐይነቱ የራሴን ጥቅም ማስጠብቂያ የሚል ድርጅትና በአፍሪካ ላይ የተቃጣ የጦር ኃይል በፍጹም አያስፈልገውም። መብቱም አይደለም። ያም ሆኖ አንዳንዶች የሰሜን አትላንቲክ የጦር ስምምነት አገሮች ከአንዳንድ የአፍሪካ መንግስታት ጋር የሁለት አገሮች ስምምነት በማድረግና እንደልባቸው በመፈንጠዝ በአህጉሪቱ ውስጥ የፈለጉትን ነገር ያደርጋሉ። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ መንግስታት የጦር ኃይሎች ከሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት ጋር በመስራትና በመተባበር የአፍሪካን ነፃነት እያዳከሙ ነው። በተጨማሪም የግል ጦሮች በመቋቋም በአፍሪካ ውስጥ እንደልባቸው በመንቀሳቀስ ስራቸውን እየሰሩ ነው። ይህ ሁሉ እያለ አፍሪኮም ለምን አስፈለገ? በተጨማሪም ሽበረተኝነትን ለመዋጋት በሚል እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱና አፍሪካን እያመሱ ነው። ከዚህ ባሻገር የሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት ከሁለት ዐመት በፊት በሰሜን አፍሪካ የቀሰቀሰውን አብዮትና የህዝቦች የነፃነት ጥማት በእንጭጩ እንዲወድም የማይሰሩት ተንኮል ይህ ነው አይባልም። ይህንንም ለማድረግ በሩቅ ምስራቅና በአካባቢው ያሉትን ፀረ-ዕድገትና ፀረ-ተራማጅ የሆኑ ኃይሎችን በሙሉ እንደሚረዱና እንደሚያስታጥቁ የታወቀ ነው።
የአፍሪካን ህዝቦች ነፃነት የማወደሙና የአፍሪካን ህዝብ ጩኸት ጭጭ የማድረጉ ሁኔታ ስር ሰዷል። ከሰላሳ ዐመት ጀምሮ በአህጉሪቱ የሚካሄደው የመዋቅር መስተካከያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚባለውና በቴክኖክራቶች የሚመራውና ተግባራዊ የሆነው የአፍሪካን ህዝብ ክፉኛ ማዳከሙ ብቻ ሳይሆን፣ ለፖለቲካ ነፃነት የሚያደርገውንም ትግል ደብሳውን አጥፎበታል። አብዛኛውም ህዝብ ለፖለቲካ ያለው ግንዛቤ ጠፍቷል ማለት ይቻላል። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ መንግስታት መሰረታዊ በሆኑ ጥያቄዎች ላይ ሁሉ በመሀከላቸው ምንም ስምምነት የላቸውም። በተለይም በጦር በኩል የተዳከሙና በኮንጎ፣ በአይቮሪ ኮስት፣ በሊብያና በማሊ ላይ የሚደረገውን የውጭ ኃይሎች ወረራና ጣልቃ ገብነት ዝም ብለው እንዲያዩ ተገደዋል። በተጨማሪም እንደ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ናይጀሪያ፣ ቱኔዚያ፣ የማዕከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክና አልጄሪያ ግፊት እየተደረገባቸውና ወደጦርነትም እየተገፉ እንደሆኑ ሁኔታው ያረጋግጣል። ከዚህም በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ለሰሜን አትላንቲክ ጦር መውረሪያ መሳሪያ በመሆን ብዙ አገሮች እንዲወረሩ ሁኔታውን አመቻችቷል፤ እያመቻቸውም ነው። ምናልባትም የአፍሪካ አገሮች በተባበሩት መንግስታት ስር በሚደራጀው ጦርና በኔቶ ውስጥ መሳተፍ እንደሚተባበሩ የሚያሳይ ቢመስልም፣ ይህ ሁኔታ ግን ከዕውነቱ የራቀ ነው። የአፍሪካ መንግስታት ጦሮች በዚህ ዐይነቱ መሳተፍ የግዴታ የኢምፔሪያሊስት አገሮች መሳሪያ እንደሚያደርጋቸው የተረጋገጠ ነው። በሚያዚያ ወር 2013 ዓ.ም 36 የአፍሪካ አገሮች የመጭውን ዘመን አመራር ለማስለጠን በሚል ከእነዚህ አገሮች የተውጣጡ የመኮንን ወጣቶች ወደ ዋሺንግተን ተልከዋል። ይህም ኮርስ በአፍሪካ የማዕከለኛው ስትራቴጅክ ጥናት(African Center for Strategic Studies)(ACSS) የተዘጋጀ ነው። እነዚህ ወጣት መኮንኖች ሰልጥነው ከተመለሱ በኋላ ቲያትራዊ የመተጋገዝ ተግባራዊ የልምምድ ዕቅድ(Theater Security Cooperation Programs) በሚባለው የአፍሪኮም አንደኛው አካል ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል። የአፍሪካ ተጨማሪ ተግባራዊ የልምምድና የደጋፊ ተቋም(African Contingency Operations Training and Assistance) እንደዚህ ዐይነቱን የአፍሪካን ምርጥ መኮንኖች የማስለጠኑን ተግባር ያሟላል። በዚህም መሰረት እነዚህ ኃይሎች በተባበሩት መንግስታት የጦር ስልት ውስጥ ይካተታሉ።
በአለፉት አስር ዐመታት ብዙ የአፍሪካ መንግስታት ወታደሮች በእንደዚህ ዐይነቱ የወረራ ስትራቴጂ ውስጥ በመካተት ተለማምደዋል። በሰሜንና በምዕራብ አፍሪካ በስመ ሽብርተኝነት ፍሊንትሎክ እየተባለ የሚጠራውና የሚካሄደው የጦር ልምምድ፣ ከሩቅ ሆኖ ሁኔታዎችን ለማጣራት የሚካሄደና የአፍሪካ ኢንዴቨር እየተባለ የሚጠራው የጦር ልምምድ፣ ከትላስ ፈጥኖ ደራሽ የሚባለውን በህንድ ውቅያኖስ አካባቢና በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ የሚካሄደውና በዚህ አካባቢ የሚተላለፈውን የንግድ መርከብ ለመቆጣጠር በሚል ሰበብ ብዙ የአፍሪካ ወታደሮች በልምምዱ ውስጥ ተካተዋል።
ከዚህ ስንነሳ የአፍሪካ የሰላምና የደህንነት ሁኔታ በከፍተኛ አደጋ ላይ ይገኛል። የአፍሪካ መንግስታትና ህዝቦች ያሉበት የተዳከመ ሁኔታ በዚህ ዐይነቱ የማጭበርበር ዘዴ ወደ አለመረጋጋትና ብጥብጥ እንዲያመራ እየተደረገ ነው። በዚያውም አህጉሪቱን ለመውረርና እንደገና ቅኝ ግዛት ለማድረግ ያመቻል። በተለያዩ አገሮች የአሽባሪዎች የህቡዕ ቦታዎች በመቋቋምና በሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት በመደገፍ እንደመግቢያ ቀዳዳነት አመቺ ሁኔታ ፈጥረዋል። ይኸኛው በመጠኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ብዙ የማይታወቅ ምስጢር ወደፊት በጉልህ የሚወጣበት ቀን ይመጣል። የኢምፔሪያሊስት አገሮች በየቦታው የሚደፈርሰውን ግጭት ልንቆጣጠር እንችላለን በማለት ጣልቃ በመግባት ለሰላም ዕጦት ዐይነተኛ ምክንያት ሆነዋል። የጠቡም መነሾና የሰላም መደፍረስ ምንጮች የእነሱ የማያቋርጥ የመስፋፋትና የመስገብገብ ፖለቲካ ነው። በየቦታው የተስፋፋው ድህነት፣ እስካሁን ድረስ በዕድገት ስም የተካሄደው የኢኮኖሚ ፖሊሲና ውጤተ-አልባ መሆን፣ የተደራጀ ወንጀለኝነት፣ እነዚህ ሁሉ ከኢምፔሪያሊስት አገሮች የተሳሳተ ፖሊሲና ህዝቦችን ከማስገደድ ጋር የተያያዙ ናቸው። እንደዚህ ዐይነቱ ድህነት የግዴታ ለሰላም ዕጦትና ለአሸባሪዎች መፈልፈያ ምንጭ ሊሆን ይችላል። በተለይ በብዙ የአፍሪካ አገሮች የጥሬ ሀብትን የሚያወጡት የምዕራብ አገሮች ኩባንያዎች ተባባሪ በመሆን ሁኔታውን በማባባስ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ኩባንያዎች አሸባሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ከእነሱ ጋር እየተጋፉ የሀብት ዘረፋ ያካሄዳሉ። ስለሆነም ይህ ዐይነቱ የተወሳሰበና ለብዙዎቹ ግልጽ ያልሆነ ጉዳይ ለሰላም ዕጦትና በተለይም ደግሞ ጣልቃ ለመግባት ተስማሚ ሁኔታን ፈጥሯል። ብዙዎች የአፍሪካ መንግስታት ይህንን ዐይነቱን ተንኮልና ዘረፋ ባለመረዳት ተባባሪ በመሆን ሁኔታው እንዲባባስ እያደረጉ ናቸው። በነፃ ንግድና በሊበራሊዝም ስም የሚካሄደው ዐይን ያወጣ ዘረፋ የአፍሪካ መንግስታትን ዐናቸውን ሰውሮታል። በቀጥታ በሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት ስትራቴጂ ቁጥጥር ስር እንዲወድቁ ተደርገዋል።
ይህ ዐይነቱ የአፍሪካን ጦር በአፍሪኮም ስትራቴጂና በሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት ውስጥ ማካተቱና፣ የአፍሪኮምንም ማዕከል ወደ አፍሪካ ለማዛወር መሞከር የአፍሪካን ነፃነትና የአፍሪካን ህዝቦች መተባበርና ለጋራ ዕድገት መነሳት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያጨናግፍ ነው። አፍሪኮምና ኔቶ ከመተሳሰራቸው የተነሳ መጀመሪያውንና መጨረሻውን ለማወቅ ያዳግታል። ለምሳሌ በግንቦት ወር የኔቶ ዋና ጸሀፊ የሆኑት ሚስተር ራስሙሰን ዋሽንግተን ላይ ምርጡ መሪ በመባል ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። ስለሆነም ኔቶና አፍሪኮም በአፍሪካ ውስጥ ስር ለመሰደድና ሀብቷን ለመዝረፍ ሲሉ አንድ ላይ ተሳስረዋል። አንዱን ከሌላው የማይለይበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
የአፍሪካ አንድነት ከተቋቋመ ከ50 ዐመታት ጀምሮ ብዙ እንቅፋቶች ገጥመውታል። በተለይም ነፃነታቸውን ተቀዳጀትዋል በሚባሉት የአፍሪካ አገሮች ላይ በስንት ትግል የተቀዳጁትን ድል ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዳያደርጉ ቁጥጥር ተደርጎባቸዋል። ከ60ኛው ዓ.ም ጀምሮ ተራማጅ በነበሩ የአፍሪካ ፕሬዚደንቶች ላይ የተካሄደው የመንግስት ግልበጣና፣ ከስልጣናቸውም እንዲባረሩ ማድረግ ወይም ማስገደል፣ ከአፓርታይድ ለመላቀቅ ይደረግ የነበረውን ትግል ለማክሸፍ መሞከር፣ የአሜሪካ ጦር በሶማሌ ላይ ያደረገው ወረራና፣ በሱዳን ላይም የፈጸመው ተንኮል፣ ከአልካይዳ ጋር የሚያደረገው የውስጥ ለውስጥ ንግግር፣ የመስከረም 11 የአሸባሪዎች ድርጊት ከመፈጸሙ በፊት በጂሃዲስቶች የተፈጸመው ድርጊትና ከዚህ ጋር ተያይዞ አሸባሪዎችን መምታት አለብን ተብሎ የረቀቀው ፖሊሲ ሁሉ፣ እነዚህ ሁሉ በአፍሪካ ህዝብ ነፃነትና፣ በአፍሪካ አንድነት የስራ አፈጻጸም ላይ የራሳቸውን አሉታዊ አሻራ ጥለዋል። እ.አ በ2002 ዓ.ም የፓን ሳህል አገሮች የፀረ-አሸባሪ ስምምነት፣ ከሶስት ዐመታት በኋላ ደግሞ የትራንስ ሳሀራ የፀረ-አሸባሪዎች ስምምነት፣ እንዲሁም ሌሎች አምስት አገሮችን በማካተት የየመንግስታቱን አትኩሮ በዚህ ዐይነቱ ለዕድገት በማያመች ተግባር ላይ እንዲሰማሩ አስገድዷቸዋል።
በኋላ ደግሞ የምስራቅ አፍሪካው የፀረ-ሽብር ዝግጀት ወደ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገሮች በመስፋፋት ስድስት የሚጠጉ አገሮችን አካትቷል። በዚሁ ዐመት እ.አ በ2005 ዓ.ም የአፍሪካ አገሮች ያደረጉትን ጥሪ ኒቶ በመቀበል በዳፉር ውስጥ ጣልቃ መግባት ተቻለ። ከዚህ አልፎ በብርጌድ ደረጃ የሚቋቋም ጦር ከሁለት ዐመት በኋላ እንዲቋቋም የመጀመሪያው ዝግጅት ሲጀመር፣ ስራው በ2015 በመጠናቀቅ የሰላም ጥበቃ በሚለው ስም አፍሪካ ሙሉ በሙሉ ነፃቷን እንድታጣ ትደረጋለች ማለት ነው።
በኋላ ደግሞ የምስራቅ አፍሪካው የፀረ-ሽብር ዝግጀት ወደ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገሮች በመስፋፋት ስድስት የሚጠጉ አገሮችን አካትቷል። በዚሁ ዐመት እ.አ በ2005 ዓ.ም የአፍሪካ አገሮች ያደረጉትን ጥሪ ኒቶ በመቀበል በዳፉር ውስጥ ጣልቃ መግባት ተቻለ። ከዚህ አልፎ በብርጌድ ደረጃ የሚቋቋም ጦር ከሁለት ዐመት በኋላ እንዲቋቋም የመጀመሪያው ዝግጅት ሲጀመር፣ ስራው በ2015 በመጠናቀቅ የሰላም ጥበቃ በሚለው ስም አፍሪካ ሙሉ በሙሉ ነፃቷን እንድታጣ ትደረጋለች ማለት ነው።
ይህ ማለት ምን ማለት ነው? የራሳችንን ዕድል በራሳችን የመወሰኑ ጉዳይ እንዳለ ይነጠቃል። የአፍሪካ ህዝቦች ከእንግዲህ ወዲያ የነፃነታቸውን፣ የመብታቸውንና የዕድገታቸውን ዕድል ወሳኝ አይሆኑም ማለት ነው። ኔቶና አፍሪኮም በአንድ የአፍሪካ አገር ውስጥ ጣልቃ ለመግባት በሚፈልጉበት ጊዜ ከነሱ በላይ የተቀመጡትን የሲኒየር ሊይዞን ከመጠየቅ በስተቀር ማንንም መጠየቅ አያስፈልጋቸውም። ይህ ዐይነቱ የሚሊተሪ ሊይዞን የአፍሪካን አንድነት የሚቆጣጠርና የሚከታተል ስልሆነ እንደ አፍሪካ አንድነት ተወካይ ሆኖ የሚሰራ ነው ማለት ይቻላል ። የአፍሪካ መንግስታት ምንም ዐይነት የቁጥጥር መብት የላቸውም ማለት ነው። እኛ የፓን አፍሪካንን አርማ አንግበን የምንታገል ይህንን ወረራ ዝም ብሎ መመልከት ሳይሆን አደገኛነቱን ለዓለም ሰላም ወዳድ ህዝብ በማስታወቅና፣ ለአፍሪካ ህዝብና ለምሁሩም ግልጽ በማድረግ ይህንን ህልምና ዕቅድ እንዲከሸፍ ማድረገ ታሪካዊ ግዴታቸን ነው። አፍሪካን ሚሊታራይዝ ማድረጉ ወደ ጥፋት እንጂ ወደ ሰላም እንደማያመጣን መረዳትና ማስታወቅ ይኖርብናል። አለመረጋጋትን፣ ፀብ መጫርንና ማቀጣጠልንና የባሰውኑ ወደ ከፍተኛ የርስበርስ ዕልቂት ከማምራት በስተቀር ለአፍሪካ አህጉርና ለህዝቦቿ የሚበጅ መንገድ አይደለም። ዘለዓለሙኑ የአፍሪካ ህዝብ በትርምስ ዓለም ውስጥ እንዲኖርና ታሪካዊና የሰለጠነ ስራ እንዳይሰራ የሚያደርግ እጅግ አደገኛ ዕቅድ ነው። ስለሆነም የአፍሪካ ህዝብ ብሄራዊ ነፃነቱ እንዲገፈፍ የሚያደርግ ነው። የአፍሪካ ዕውነተኛ ነፃነት የሚጠበቀው በአህጉሪቱ የተቋቋሙት የውጭ ኃይሎች የጦር ካምፖች ሲፈራርሱና ከእነሱ ጋር የተቆላለፉ የሚሊታሪ ኢንስቲቱሽኖች ሲወድሙ ብቻ ነው። ማንኛውም የአፍሪካ መንግስታት የሚሊታሪና የስለላ ድርጅቶች ከውጭ ኃይሎች ትስስርና ምክር፣ እንዲሁም ስልጠና የፀዱ መሆን አለባቸው። ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ የኢምፔሪያሊስቶች የብጥበጣ ዕቅድና የዘረፋ ስልት መበጠስና መውደም አለበት። ዕምነታችን መሆን ያለበት ዕውነተኛ፣ ከውጭ ኃይሎች ተፅዕኖና የስትራቴጂ ተልዕኮ የተላቀቀ የመላው አፍሪካ የወታደር ተቋም ሲቋቋም ብቻ ነው። ለዚህ ተግቶ መስራት ያስፈልጋል።
የኛው የፓን አፍሪካኒዝም ህልምና ምኞት ጠቅላላው የአፍሪካ ህዝብ ወደ አንድነት እንዲመጣ የሚያደርግና ወደ ጋራ ብልጽግና የሚያመራ መሆን አለበት። የኛ መሰረታዊ ዓላማ የውጭ ኃይሎችን ፍላጎት የሚጻረርና በፍጹም በሰላምንና ዕድገትን ፈላጊነት ላይ የተመሰረተ ነው። የኛው የአፍሪካ ጦር ወራሪ ሳይሆን የአፍሪካን ብሄራዊ ነፃነት የሚያስጠብቅ ነው። ሀብቷንና የህዝቦቿን መብት የሚጠባበቅና የሚከላከል ነው። ስለዚህም በኔቶና በአፍሪኮም የተቋቋመው የወረራ ስምምነት ተፈጥሮአዊውን የሰው ልጅ መብት የሚቃወምና የአፍሪካ ህዝቦች ብቻ ሳይሆኑ የዓለምም ህዝብ በስምምነትና በወንድማማችነት እንዳይኖር የሚያደርግ ነው።
የራሳችንን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ በራስችን አዕምሮ መመራት ያስፈልገናል። ስለዚህም ኔቶና አፍሪኮም ሳይሆኑ የኛን ስራ የሚሰሩልን ራሳችን ለመስራት ከምንግዜውም ታጥቀን መነሳት አለብን። ይህ ብቻ ነው ዕውነተኛውን መንገድ የሚያሳየንና የአፍሪካን አንድነት በማጠናከር ወደ ሰላምና ወደ ተፈለገው ብልጽግና የሚያመራን።
አንድ ላይ በመሆን የአፍሪካን ወጣት በፖለቲካ ረገድ ለማንቃትና ነገሮችን እንዲረዳ ታግተን መስራት አለብን። አፍሪኮም ወደ ቤትህ ተመለስ!! አፍሪካ የአፍሪካውያኖች ብቻ ነው!! ውጭ ሆነ አገር ቤት ውስጥ ያለው ሁሉ መተባበር አለበት። የውጭ አገር ጦር ስፈር መቆም የለበትም፤ አሜሪካ ከጀርመንም ሆነ ከአፍሪካ መውጣት አለበት።
አሸባሪዎችን ማስታጠቁ አሁኑኑ መቆም አለበት። ከጂቡቲ፣ ከትሪፖሊ፣ ከሊብረቪሌ፣ ከሳዖ ቶሜና ከጃሜና መውጣት አለበት።
የዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የአፍሪካን የተፈጥሮ ሀብት መዝረፋቸውን ማቆም አለባቸው። የእርሻ መሬታቸውን መንጠቁ መቆም አለበት። የአፍሪካን የጥሬ ሀብት የሚሸጥና ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ስምምነት የሚያደርግ ማንኛውም የአፍርካ መንግስት በስልጣን ላይ መቆየት የለበትም።
የዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የአፍሪካን የተፈጥሮ ሀብት መዝረፋቸውን ማቆም አለባቸው። የእርሻ መሬታቸውን መንጠቁ መቆም አለበት። የአፍሪካን የጥሬ ሀብት የሚሸጥና ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ስምምነት የሚያደርግ ማንኛውም የአፍርካ መንግስት በስልጣን ላይ መቆየት የለበትም።
ዲሞክራሲና ህዝባዊ ተሳትፎ ብለን በመነሳት የአፍሪካን አንድነት ድርጊት መቆጣጠርና እንዲሻሻል ማድረግ አለብን።
አፍሪካ እንደገና ነፃ መውጣት አለባት!! ስለዚህም ሴትም ሆነ ወንድ፣ ሸማግሌም ሆነ ወጣት፣ ሁሉም በአንድነት በመነሳት አፍሪካን ከውጭ ወረራና ካማተለል ዘረፋ ማዳን አለብን!!
አፍሪካ እንደገና ነፃ መውጣት አለባት!! ስለዚህም ሴትም ሆነ ወንድ፣ ሸማግሌም ሆነ ወጣት፣ ሁሉም በአንድነት በመነሳት አፍሪካን ከውጭ ወረራና ካማተለል ዘረፋ ማዳን አለብን!!
ስለሆነም ይህንን መግለጫ ከዚህ በታች ስማቸው የሰፈረው ድርጅቶች በሙሉ ይተባበራሉ።
የሶስተኛ ዓለም ፎረም (Samir Amin; Bernard Founou)
ፋውንዴሽን ፍራንዝ ፋኖን (Mireille Fanon-Mendes-France)
ሃንኪሊሶ አፍሪካ (Koulsy Lamko)
አፍሪክ እቬኒር ኢንተርናሽናል
የፓን አፍሪካኒስም የስራ ጠረጴዛ ሚዩኒክ (Dipama Hamado)
ሪቫይቫል ፓን እፍሪካኒዝም ፎረም (Gnaka Lagoke)
የቱኔዚያ የውጭ ግኑኝነት ኢንስቲቱት(Ahmad Manai)
የድሮው የደቡብ ማዕከል ዳይሬክተር(Yash Tandon)
የዲያስፖራ ሙዚካ የሁሩ ራዲዮ
የፓን አፍርካ ኔት ወርክ ትብብር- Ajamu Nangwaya, University oft Toronto
ኤሚራ ውድስ-IPS
የአፍሪካ ፎረም ትብብር
አገራዊ የአፍሪካ የምርምርና የዕድገት ትብብር(ARCADE)
የአፍሪካ የባህል ፕሮጀክት በህግ የተመዘገበ
Dr. Horace Campbell-Syracuse Univeristy
Dr. Saer Maty Ba
Dr. Sanou Mbaye
Dr. Boniface Mabanza(Kirchliche Arbeitsstelle Südliches Afrika KASA)
Dr. Werner Ruf(AG Friedensforschung)
Berliner Postkolonial e.V.(Mnyaka Suru mboro und Christian Kopp)
Dipl.Afrikanistin(Ginga Eichler)
Dr. Lutz Holzinger(Journalist an writer in Vienna)
Ababacar Fall, Dakar Senegal
Dr. Henning Melber, Theo Dag Hammarskjöld Foundation, Uppala/Sweden
የሰው መብትና ደሞክራቲ ኮሚቴ- Wolf-Dieter Narr
Jonanes Louis (Univerite Populaire Kwame Nkrumah)
Werner Kersting, Vorsitzender
የሶስተኛ ዓለም ፎረም (Samir Amin; Bernard Founou)
ፋውንዴሽን ፍራንዝ ፋኖን (Mireille Fanon-Mendes-France)
ሃንኪሊሶ አፍሪካ (Koulsy Lamko)
አፍሪክ እቬኒር ኢንተርናሽናል
የፓን አፍሪካኒስም የስራ ጠረጴዛ ሚዩኒክ (Dipama Hamado)
ሪቫይቫል ፓን እፍሪካኒዝም ፎረም (Gnaka Lagoke)
የቱኔዚያ የውጭ ግኑኝነት ኢንስቲቱት(Ahmad Manai)
የድሮው የደቡብ ማዕከል ዳይሬክተር(Yash Tandon)
የዲያስፖራ ሙዚካ የሁሩ ራዲዮ
የፓን አፍርካ ኔት ወርክ ትብብር- Ajamu Nangwaya, University oft Toronto
ኤሚራ ውድስ-IPS
የአፍሪካ ፎረም ትብብር
አገራዊ የአፍሪካ የምርምርና የዕድገት ትብብር(ARCADE)
የአፍሪካ የባህል ፕሮጀክት በህግ የተመዘገበ
Dr. Horace Campbell-Syracuse Univeristy
Dr. Saer Maty Ba
Dr. Sanou Mbaye
Dr. Boniface Mabanza(Kirchliche Arbeitsstelle Südliches Afrika KASA)
Dr. Werner Ruf(AG Friedensforschung)
Berliner Postkolonial e.V.(Mnyaka Suru mboro und Christian Kopp)
Dipl.Afrikanistin(Ginga Eichler)
Dr. Lutz Holzinger(Journalist an writer in Vienna)
Ababacar Fall, Dakar Senegal
Dr. Henning Melber, Theo Dag Hammarskjöld Foundation, Uppala/Sweden
የሰው መብትና ደሞክራቲ ኮሚቴ- Wolf-Dieter Narr
Jonanes Louis (Univerite Populaire Kwame Nkrumah)
Werner Kersting, Vorsitzender
ማሳሰቢያ፣
ይህ ጥሪ ካናዳ ውስጥ በሚኖሩና በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር በሆኑት በሚስተር አዚዝ ሳልሞን ፋል የሚመራ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የተዘጋጀ ጽሁፍ ነው። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሚስተር አዚዝ በምኖርበት ከተማ እኔና የአፍሪካ ሀውስ በመተባበር የአፍሪካ አንድነትን ጉዞ፣ ውጤትና ችግር እንዲሁም የወደፊቱ ሁኔታ ላይ በሴሚናራችን ላይ ተገኝተው ከተሳተፉና፣ እሳቸውም በአፍሪካ ላይ የተጣለውን አደጋ በሰፊውና በሚያመረቃ መንገድ ካቀረቡ በኋላ፣ የሃሳብ ልውውጥ ካደረግን በኋላ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ስለሚሄዱ ይህንን ጽሁፋቸውን እንድተረጉም ስለጠየቁኝ በዚህ መልክ አቅርቤዋለሁ። አቶ አዚዝ ጽሁፉን ይዘው በመሄድ ኢትዮጵያ ውስጥም ለሚመለከቷቸው ባለስልጣናት እንደሚሰጡ አውስተውኛል። ይህም ማለት ይህ ጽሁፍ በሳቸው ፈቃድ የተተረጎመ ነው ማለት ነው። ይህንን ዕድል ስለሰጡኝ በጣም አመሰግናለሁ።
ተርጓሚ፤ ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)
No comments:
Post a Comment