አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ አረብ አገራት በቤት ሰራተኝነት ለሚሄዱ ዜጎች ስልጠና ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት ቢደረግም ሰልጣኞችን ማግኘት አልቻልንም አሉ የተለያዩ የቴክኒክና ሞያ ትምህርት ተቋማት።
ተቋማቱ ለስልጠናው ግብዓት የሆኑ መሳሪያዎችንና አሰልጣኞችን በበቂ ሁኔታ አዘጋጅተው ቢጠብቁም ሰልጣኞች ማጣታቸውንም ነው የሚናገሩት።
ወደ መካከለኛው ምስራቅ በቤት ሰራተኛነት ለመቀጠር የሚያመሩ ዜጎች ከሚደርስባቸው አደጋ እና እንገልት ለመታደግ የስልጠና ስርዓተ-ትምህርት ቀረፃ ተደርጎ ወደስራ መገባቱ ይታወሳል።
ሆኖም ቅሬታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት እነዚህ ተቋማት ለስልጠናው ግብዓት የሆኑ መሳሪያዎችንና አሰልጣኞችን በበቂ ሁኔታ አዘጋጅተው ሰልጣኞች ማጣታቸው ግራ አጋብቷቸዋል።
የከተማዋ ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ በበኩሉ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚሄዱ ሰልጣኞችን መልምሎ ወደ ተቋማቱ መላክ ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነው ይላል።
ኤጀንሲው እንደሚለው ቅድሚያ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት ለመሄድ የተዘጋጁ ዜጎችን መልምሎ እንዲያቀርብ ሃላፊነት የተሰጠው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ፤ በሁለት ተቋማት እንዲሰለጥኑ የላካቸው ሰልጣኞች ሁሉም ማለት ይቻላል ወደ አረብ አገር የመሄድ ሃሳብ የሌላቸውና ከ90 በመቶ በላይ ወንዶች መሆናቸው ዕቅዱ ግቡን የሳተ እንዲሆን አድርጎታል ።
ከዚህም ሌላ ለሰልጣኞች የተዘጋጀው የስልጠና ስርዓት ትምህርት ፤ከቤት አያያዝ እንስሳት ክብካቤና ምግብ ዝግጅት ጋር የተያያዘ ሆኖ ሳለ ፤የመጡት ሰልጣኞች በጥበቃና በአትክልተኛነት ሞያ ለመሰልጠን ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ ከዝግጅቴ ጋር በፍፁም የማይሄድ ነው ሲልም ኤጀንሲው ቅሬታውን ያሰማል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ ፥በእርግጥም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማትና ኤጀንሲው ያነሱት ቅሬታ ትክክል ነው ይላል ፥ ነገር ግን ይህ ችግር የተፈጠረው በቢሮው ቸልተኛነት አይደለም ይላል ።
በዋናነት ቢሮው በተለይም ከአዲስ አበባ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመሄድ የተነሳሱ ዜጎችን የመከታተል ሃላፊነት አለበት የሚሉት በቢሮው የስራ ስምሪትና የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ ካሳ ስዩም ናቸው ።
ነገር ግን ስልጠናውን መስጠት የሚያስችል ስርዓተ ትምህርት ከተዘጋጀ በኋላ ወደ ምልመላው ከመግባታችን በፊት በከተማዋ የሚገኙ የስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር ውይይት ተደርጎ ኤጀንሲዎቹ ወደ እነዚህ አገራት ሰራተኞችን ለመላክ በነሱ ስር የመዘገቧቸውን ዜጎች ለስልጠና እንዲልኩ ጥሪ ቀርቦላቸው፤አንዳቸውም በነሱ በኩል ለቤት ሰራተኝነት የሚሄዱ ዜጎችን አላኩም ፡፡
በዚህም የተነሳ እንደአማራጭ በየክፍለ ከተማው በተለጠፈ ማስታወቂያ መሰረት ለስልጠና የመጡትን ዜጎች ወደ ስልጠና ጣቢያዎቹ ለመላክ ተገደናል ነው ያሉት ሃላፊው።
በዚህ የምዝገባ ሂደት 693 ሰልጣኞች ተመዝግበዋል ከነዚህ ወስጥም ከ90 በመቶ የሚልቁት ወንዶች ናቸው ፤ይህም ሁኔታ በቀጣይ ኤጀንሲው አካሄዱን ቆም ብሎ እንዲመለከት እንዳደረገውም አቶ ካሳ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ተናግረዋል ፡፡

በመሰረት ገዛሀኝ
No comments:
Post a Comment