Pages

Oct 24, 2013

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አንድን ጳጳስ ከስልጣን አነሳ


ነገ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎ ባደረገው ምክክር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከስልጣን አነሳ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት የሆኑት አባቶች  ያለ ወትሮው የኢህአዴግ መንግስት ሹማምንት በየአካባቢው በቤተክርስቲያኗ ላይ እየፈፀመ ያለውን ጥፋት በይፋ መናገርና መቃወም የጀመሩ ሲሆን፤በተለይ በዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ውሎው የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ላይ ያሉ በርካታ ችግሮችን አንስተው መወያየታቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ጋራ በተያያዘ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው በአዲሱ ፓትርያርክ ዘመን የተሾሙት መጋቢ ሀዲስ ይልማ ከድተው አሜሪካ መግባታቸው እና በከተማው አድባራትና ገዳማት ላይ የሚታየውን ስር የሰደደው ዘረኝነትና ሙስና ለማስወገድ ኃላፊነት የተሰጣቸው የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አዲስ አበባንም ደርበው እንዲሰሩ ቢሰጣቸውም ችግሮቹ ምንም ሊቀረፉ ባለመቻላቸው ከአዲስ አበባው ስልጣን እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ መደበኛ ዓመታዊ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate