የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል በሚል ስያሜ መመስረቱን ድርጂቱ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ያሳወቀ ሲሆን ይህን መግለጫ ተከትሎም በርካታ የዜና አውታሮች ሲዘግቡት መቆያታቸው ይታወሳል። ከዚሁ ዘገባ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት በትናንትናው እለት ስርጪቱ ከግንቦት 7 ሃይል ቃል አቀባይ ታጋይ ዜና ጉታ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ ቃል አቀባዩ እንደገለጹት የዝባዊ ሃይሉ ራእይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ጠንካራ ኢትዮጵያን እውን ሆና ማየት ነው ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት የንቅናቄው ስም ግንቦት ሰባት የተባለበት ዋነኛ ምክንያት በ1997 ምርጫ ወቅት ግንቦት ሰባት ቀን የኢትዮጵያዊያን ድምጽ ባደባባይ በጉልበት የተነጠቀበት በመሆኑ፣ ቀኑ በኢትዮጵያዊያን ልዩ ቦታ የሚሰጠውና እለቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ዘረኛውን የወያኔ አገኣዛዝ ፍጹም እንደማይፈልግ የገለጸበት እንዲሁም ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ዝግጁነቱን ያረጋገጠበት ቀን በመሆኑ ነው ብለዋል።
የግንቦት ሰባት ሃይልን አሁን መመስረት ለምን አስፈለገ በሚል የኢሳት ጋዜጠኛ ለታጋይ ዜና ጉታ ላቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል።
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ታጋይ ዜና ጉታ ወያኔን በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በምድር ላይ እየተንቀአሳቀሱ ካሉ ሃይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆኑንና፣ ከነኝሁ ሃይሎች ጋር በጋራ ለመስራት አስፈላጊዉን ቅድመ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን እንዲሁም የዚህ ሃይል የትግል ሜዳ መሃል አገርን ጨምሮ ወያኔ ባለበት ሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ነው በማለት፣ በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ አብራርተዋል። ቃል አቀባዩ ለኢሳት እንደገለጡት የግንቦት 7 ሃይል ከትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወይም ደሚት፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህና እኩልነት ግንባር፣ ከጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከተባሉት ድርጅቶች ጋር በጥምረት ለመስራት አስፈላጊው ዝግጅት አጠናቋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መመስረት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባቱና፣ የዘረኛነት አባዜ መርዙን በመርጨት ስራ ላይ መጠመዱ ትግራይ ኦን ላይን በመባል በሚታወቀው ድረ ገጽ ላይ ባወጣው ጽሁፍ ገልጹአል። የዚህን የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል መመስረት ተከትሎ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ዲሴምበር 22 ቀን በዚሁ ድረ ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ እንደሚያመለክተው የግንቦት 7 ሃይል በተለይም በትግራይ ህዝብ ላይ ለመዝመት የተነሳ ሃይል ነው ያለ ሲሆን፣ የትግራይ ህዝብ እሰከ አፍንጫው ድረስ በጦር መሳሪያ የታጠቀ፣ የተደራጀና፣ ወታደራዊ ስልጠናም የወሰደ በመሆኑ ይህን የግንቦት ሰባት ሃይል እሰከ ደም ጠብታው ድረስ ይፋለመዋል፣ ካለ በሁአላ የትግራይ ተወላጆች ይህን ሃይል እንዲፋለሙ ጥሪ አቅርቡአል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በትግራይ ህዝብ ስም መነገድ የጀመረው ገና ወደ ስልጣን ወምበር ከመምጣቱ ቀደም ብሎ እንደነበር በስፋት የሚታወቅ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ የስልጣን ወምበርን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ወዲህ የትግራይን ህዝብ ከሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ የመነጣጠልና እርስ በርስም ጥላቻ እንዲፈጠር በማድረግ ስራ ተጠምዶ እንደቆየ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ አይዘነጋም።
ይህ የመከፋፈል አባዜ የተጠናወተው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ አሁንም፣ ይህን ርካሽ ስልቱን በመጠቀምና የትግራይ ተወላጆችን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ነጥሎ በማውጣት እስካፍንጫቸው የታጠቁና በወታደራዊ ስልጠናም ብቃት ያላቸው በመሆኑ እስከደም ጠብታ ይፋለማሉ በማለት መርዘኛ ፕሮፓጋንዳውን መንዛቱን ቀጥሉአል።
No comments:
Post a Comment