ህወሃት ጭካኔውን እንደ ጀግንነት፤ ድንቁርናውን እንደ እውቀት ቆጥሮት እኔ ብቻ ጀግና! እኔ ብቻ አዋቂ! ብሎ በትዕቢት አብጦ በማን አለበኝነት ታብዮ የኖረ ዘረኛ ቡድን ነው። የዚህ ቡድን ትዕቢት ልክና ወሰን የለውም። የትዕቢታቸው መገለጫም ብዙ ነው።”እኛ ከሌለን ኢትዮጵያን እንበትናታለን” ብለው የሚዘባትሉትን ማስታወስ ብቻ በቂ ነው። ይሄ የጨካኞች መገለጫ እንጂ የጀግና ጠባይ አይደለም። ጀግና አገር ይገነባል እንጂ አገር አይበትንም። ጀግና ለአገሩ አንድነትና ለህዝቡ ክብር ይዋደቃል እንጂ እኔ ከሌለው አገሪቷን አፈርሳታለው ብሎ አይዘባትልም። ህወሃቶች ከትእቢታቻው ላይ በወንድማማቾች መካከል ጥላቻን የመዝራት የረከሰ ስብዕናቸው ታክሎበት በሰውና በፈጣሪ ፊት የተጠሉ እንዲሆኑ ሁነዋል።መጽሃፍ ቅዱስም “እግዚአብሄር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ፤በወንድማማቾች መካከል ጥላቻ የሚዘራውንም ነፍሱ አጥብቃ ትፀየፈዋለች” ይላል። ህወሃቶች የሚገለጹት በዚህ መልኩ ነው።ከዚህ ሌላ መልክ የላቸውም።
በእነዚህ በሰውና በፈጣሪ ፊት በተናቁና በተጠሉ ቡድኖች አማካኝነት በኢትዮጵያችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም። አዎን በደል አይረሳም። በህወቶች የተፈፀመው በደል የማንረሳው የታሪካችን ህያው አካል ነው።ህወሃቶች በአገራችን ላይ የፈፀሙትን በደል ያላካተተ የኢትዮጵያ ታሪክ ጎዶሎ ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ መጥፎ ገጽታዋ መገለጫ ነው።
የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ! አገራችን እንዲህ ያለ መከራ ውስጥ የገባችው በህወሃቶች ክፋት ብቻ አይደለም፤ የእነርሱን ክፋት እያዩ ዝም በሚሉ ቅን ዜጎችም ጭምር ነው። ከሃያ ዓመት በላይ ፈረጀ ብዙ የሆኑ ግፎችን ተሸክመን ዝም በማለታችን “አህያ” ተብለን ተሰደብን እንጂ ያተርፍነው በጎ ነገር የለም። ዝም ማለት የህወሃቶችን እድሜ አራዝሞ ብዙሃኑ ጥቂቶችን ተሸክመው፤ ጥቂቶቹም ብዙሃኑን ተጭነው የሚኖሩባት አገር እንድትሆን ከማገዝ በቀር ለነፃነታችን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የለም። እኛ ከአያት ቅደም አያቶቻችን የወረሰነውን በነፃነት የመኖር ልማድን ለዘረኞች አሳልፈን ሰጥተን ዝም የምንል አልባሌ ሰዎች ልንሆን አይገባም። የህወሃቶችን ግፍና በደል ተሸክመን እንኖር ዘንድ እኛ እርግማን ያለብንም ዜጎች አይደለንም።
ህወሃት ማለት በአገራችን ላይ የተተከለ መርገምት ማለት ነው።የመርገምትነቱም መገለጫ በዜጎች መካከል መለያየትንና አለመተማመንን ማስፈኑ፤ በሃይማኖቶች መካከልም እየገባ ግጭት ፈጥሮ የንጹሃን ደም በከንቱ እንዲፈስ ማድረጉ፤ንጹሃን ዜጎችን በሃሰት ከሶ ምናምንቴ ግለሰቦችን ምስክር አቁሞ የእድሜ ልክ እስራትና የሞት ፍርድ ፈርዶ ዜጎችን ማሰቃየቱ ጥቂቶቹ የመርገምትነቱ መገለጫዎች ናቸው። እርግጥ ነው ይህን እርግማን ተሸክመው ለመኖር የማይጎረብጣቸው እና የሂሊና ጥያቄ የሌለባቸው ደካማ ግለሰቦች ይኖራሉ። እነዚህ ትርፍራፊ ለቃቀመው ሆዳቸውን ከሞሉ፤ ጭላጭ አግኝተው ከተጎነጩ ሁሉም ሰላም ነው የሚሉ ሰው የመሆን ነገራቸውን ረስተው፤ ራሳቸውን አራት እግር ካላቸው አሳሞችና ፈረሶች ጋር ማመሳሰልን የመረጡ ናቸው። ይህ ምርጫ ግን ትክክል አይደለም። ይህም በራሱ ሌላ መርገምት ነው። ትግል የሚያስፈልገውም እንደነዚህ ዓይነቶቹ ራሳቸውን ከሰው ተራ ያወረዱትን ሰው ወደመሆን ደረጃ ከፍ ብለው እንደ ሰው እንዲያስቡ ለማደረግም ጭምር ነው።
እንግዲህ ለራሱ ክብር የሚሰጥ ዜጋ ይህን መርገምት ተሸክሞ ለመኖር እሺ አይልም። እንዲያውም መርገምቱን ከሥሩ ነቅሎ ወዲያ ለመጣል በሚደረገው ትግል ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊም መሪም ይሆናል። ይህን መርገምት መዋጋት ግዜው የሚጠይቀው የቅን ዜጎች የሞራል ግዴታ ነው። በሌላ በኩል ህወሃትን እንደ መንግስት አይቶ ትዕዛዙን ለመቀበል እሺ ማለት ዘረኝነትንና ግፍን በጣም ጥሩ አድርጎ ማጠናከር ነው። ህወሃትን ለመሰለ ዘረኛ እና ዘራፊ ቡድን መታዘዝ ማለት የዘረኝነቱና የጥፋቱ ተባባሪ መሆን ማለት ነው። ማንኛውም መልካም ሰው ዘረኝነትንና ግፍን በሙሉ እስትንፋሱ የመቃወም የሞራል ግዴታ አለበት። ህወሃትን ሰው ብቻ ሳይሆን ፈጣሪም ተፀይፎታል።ፈጣሪ የተፀየፈውን አለመፀየፍ ከጥሩ ሰው ተርታ የሚያስቆም አይደለም።
በህወሃቶች አማካኝነት የብዙ ንጹሃን ዜጎች ደም በከንቱ ፈሷል። በእነዚህ ዘረኞች አማካኝነት አማሮች ናችሁ ተብለው ከኖሩበት ተነቅለው ወደ አገራችሁ ሂዱ ተብለው ሜዳ ላይ የተበተኑ ዜጎች ብዙ ናቸው። በኢትዮጵያችን ውስጥ ከታች እስከ ላይ እርከን ያሉ የመንግስት ስልጣኖች በሙሉ መሃይማን በሆኑ ህወሃቶች ተይዟል። በህወሃቶች አማካኝነት በጋምቤላ እና በኦጋዴን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል፤በእነዚህ ቡድኖች አማካኝነት ከድሆች ጉሮሮ ተነጥቆ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ በውጭ አገር ባንኮች ውስጥ ተደብቋል። እንግዲህ እንዲህ ዓይነቶቹን የዘመኑ መርገምቶችን በሙሉ እስትንፋስ ለመቃወም አለመነሳት አሳፋሪ ነው።
በእነዚህ ዘረኞች አማካኝነት ሲፈፅሙ የኖሩ በደሎችን መቃወም የወቅቱ ትክክለኛ ተግባር ነው። ከሰሞኑ የግንቦት ሰባት ኃይል የሚባል ቡድን ካሁን ወዲያ ልቅሶው ያብቃ፤ የሚሰደዱ በአገራቸው ረግተው በሰላም ይኑሩ፤ ወጣቱ ተምሮ ድንጋይ ፈላጭ አይሁን፤ ዜጎች በብሄራቸው ብቻ ተለይተው ከኖሩበት ቀየ ተነቅለው ሜዳ ላይ አይጣሉ፤ በልማት ስም ዜጎች መድረሻ አይጡ ብለው ጋሻና ጦራቸውን አንስተዋል። የግንቦት ሰባት ንቅናቄም አገራችን ላይ የተተከለውን ህወሃት የተባለ መርገምት ነቅሎ ለመጣል በሚደረገው ትግል ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል። ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያችን ውስጥ ታሪካዊ እለት ነች። ኢትዮጵያዊያን በድምፃቸው መንግስታቸውን መምረጥ የሚችሉ መሆናቸውን ያሳዩበት እና የነፃነት ጎህ የፈንጠቀበት ዕለት ግንቦት ሰባት ነበረች። በሌላ በኩልም ግንቦት ሰባት ቃየላዊያን የብዙ አቤሎችን ደም ሊያፈሱ የተማማሉበት ዕለትም ነች። በዚህች ዕለት በተሴረው ሴራ የፈሰሰው ደም፤የወረደው እንባ፤ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው ግፍ ትግላችንን ለመሰብሰብ በቂ ምክንያት ነው። ከዚያም ከዚህም ተጠራርቶ በዚህች እለት ዙሪያ ተሰባስቦ ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ ማካሄድ ግዜው የሚጠይቀው የትግል ስልት በመሆኑ ከሰሞኑ የግንቦት ሰባት ህዛባዊ ኃይል ያስተላለፍውን ጥሪ ንቅናቄያችን አድንቆ ተቀብሎታል።
ህወሃቶች ከሃያ ዓመት በላይ አገሪቷን ሰባብረዋል፤ዜጎችን አዋርደዋል። ይሄን ሁሉ ዘመን ከዛሬ ነገ ይሻላሉ፤ ከዛሬ ነገ እንደ ሰው ልጅ ማሰብ ይጀምራሉ፤ ከዛሬ ነገ ከስህተታቸው ተምረው ይመለሳሉ በሚል እሳቤ ታግሰናል። እነርሱ ግን ትዕግስታችንን እንደ ፍርሃት፤ አርቆ አስተዋይነታችንንም እንደ ሞኝነት ቆጥረው የጭካኔ እጃቸውን ከጫንቃችን ላይ ለማንሳት እምቢ ብለው ቆይተዋል። ይሄ ግን ማብቃት አለበት።ማብቃት አለበት ስንል ደግሞ በማንኛውም መንገድ እየሄድን፤ እየወደቅንና እየተነሳን አስቸጋሪውን ጉዞ በአጭር ግዜ ጨርሰን ነፃነታችንን ለማወጅ የሚከፈለውን መሥዋእትነት ለመክፈል ዝግጁዎች መሆናችንን እያሳወቅን ነው።
የተከበራችሁ ወገኖቻችን! ኢትዮጵያችን የምትዋረደው ህወሃቶች በሚፈፅሙት ግፍ ብቻ አይደለም፤ የሚፈፀመውን ግፍ እያዩ ዝም በሚሉ ቅን ዜጎችም ጭምር ነው። ህወሃት የሰው ልጅ ይቅርና ፈጣሪ የተፀየፈው ቡድን ነው። ፈጣሪ የተፀየፈውን ትፀየፉት ዘንድ ግዜው ደርሷል፤ ዝምታው ይብቃ፤ፍርሃቱም ይሰበር። ዛሬውኑ ትግሉን ተቀላቀሉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
No comments:
Post a Comment