Pages

Dec 29, 2012

እስክንድር ነጋን የሸለመው ድርጅት በሽብርተኝነት ይከሰሳልን ?


ታዋቂው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር
ነጋ ባለፈው ሳምንት ፔን ኢንተርናሽናል ከተባለ ዓለም
አቀፍ ድርጅት ተሸላሚ ሆኗል፡፡ የመረጃ አውታሮች
እንደዘገቡት ከሆነ “እስክንድር እስከ ዛሬ ድረስ
በሚዲያ ላይ ባደረገው አስተዋጽኦ የ2012 ዓለም
አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል፡፡” ተብሏል፡፡
ይህ ደግሞ እጅግ የሚያናድድ ጉዳይ ነው፡፡ ልማታዊ
መንግሥታችን ሽብርተኛ በሎ ያሰረውን ግለሰብ ሁሉም
ሽብርተኛ ብሎ እንዲያምንና እንዲቀበል ስንት ወጪ
ወጥቶበት ዶክመንተሪ ፊልም የተሠራበትን ሰው
ማበረታታት ድፍረት ነው፡፡ በፀረ-ሽብር አዋጁ መሠረት
ሽብርተኛን ማበረታታት በሽብርተኝነት ያስከስሳል
ያስቀጣል፡፡ የኢህአዴግን መልካም ገጽታ የሚያጐድፍ
ነው፡፡ ለመሆኑ ኢህአዴግ መልካም ገጽታ አለው?
ብላችሁ እንድትጠይቁኝ አልፈቀድኩላችሁም!!
በመሆኑም በየደረጃው የተመደባችሁ የኢህአዴግ
ባለሟሎች በነካ እጃችሁ ሞያችሁን ተጠቅማችሁ ፔን
ኢንተርናሽናል ድርጅትን በሽብርተኝነት ክሰሱልን!!?

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate