Pages

Jan 6, 2013

አቶ መለስ ዜናዊ የ2012 ታላቅ ኢትዮጵያዊ ይሁኑን?

በያሬድ
አይቼህ
በ2012 በኢትዮጵያውያን ትዝታ ውስጥ በጉልህ የሚታወሰው የአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ነው። አቶ መለስ በጠናታመዋል የሚለው ዜና ተንጠባጥቦ መሰማት ከጀመረበት ከጁላይ 15 ጀምሮ በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳር ውስጥ
ከፍተኛ መናወጥ ተጀመረ። ነዉጡ አላቆመም። አሁንም ቀጥሏል።
የኢትዮጵያ ፓለቲካ የተዋቀረው በተቋም እና ስርዓት ላይ ሳይሆን በግለሰብ እና በባዕዳን ርዕዮተ-አለም ዙሪያ ነው።
ይህ ሁኔታ በኢኮኖሚያቸው ባልዳበሩ አገሮች ሁሉ የሚታይ ክስተት ነው። ስለሆነም የአቶ መለስ በጠና መታመም
የገዢውን ፓርቲ ጭንብሉን ገፍፎ እርቃኑን አስቀረው።
ኢህአዴግ ከተመሰረተ ጀምሮ ሲመሩት የነበሩት አቶ መለስ ናቸው። የአቶ መለስ መታመም ብቻ ሳይሆን ሞተዋል
የሚለው ዜና በፍጥነት መናፈስ ሲጀምር የኢህአዴግ ደጋፊዎችና አባላት ምን ያህል በአቶ መለስ ላይ ጥገኞች
መሆናቸው ቀስ በቀስ ተጋለጠ።
በመጨረሻም ህልፈተ ህይወታቸው በኢቲቪ ሲዘገብ ፡ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ፥ ጡት እንደተከለከለ ህጻን ፥
ተራወጡ። ተንቀጠቀጡ። ሚሆኑትን አጡ።
በአቶ መለስ አምባገነናዊ አገዛዝ ለ21 ዓመታት ሲገዛ የኖረው ህብረተሰባችንም ሆድ ባሰው ፡ መለሰ ሞቱበት! ያለቀሰው
አለቀሰ ፡ የተከዘው ተከዘ። ግን ለምን ያ ሆነ? ሱስ ነዋ! ሱስ! የመለስ ሱስ። በግድ ለ21 ዓመታት ላዩ ላይ ቁጢጥ
ብለው ፡ ከሳቸው ሌላ ሚያየው ፡ ሚያደምጠው ፡ አማራጭ ሳይሆነረው የኖረው ህብረተሰባችን የአቶ መለስ ሱስ
ተጠናዉቶት ነበር።
በሌላ መልኩ ፡ የመንግስት መደናበር አሳፋሪ ነበር። አንዴ “ሽርሽር ላይ ናቸው” ሲሉን። ከዛ “ለአዲስ አመት

ይመጣሉ” ሲሉን … ኸረ ምኑ ቅጡ።
ይህ ሁሉ ግን የአቶ መለስ ጣጣ ነው። አቶ መለስ የፈጠሩት መንግስት ምን ያህል ውስጡ ገለባ እንደሆነ ፡ አመኔታም
ሆነ ታማኒነት የሌለው ፡ የወመኔዎች ስብስብ እንደሆነ ቀስ በቀስ ራሱን አጋለጠ። ደጋፊዎቹንም አከሰራቸው ፡
አሳፈራቸው ፡ አሸማቀቃቸው።
“ለካስ መንግስት ውሸታም ነው!” አሉ ደጋፊዎች። “ለካስ ተቃዋሚዎች ሚሉት እውነት ነው!” ብለው ናላቸው ዞረ።
ኡ!ኡ! አሉ። በሃዘን ላይ ሃዘን። መለስም መንግስትም በድን ሆነው ተገኙ።
ኢሳት እውነተኛ ሆኖ ተገኘ ፡ ኢሳት ተደማጭነቱ ተስፋፋ ፡ የበላይነቱን ተጎናጸፈ ፡ ታማኒነት አገኘ። ለዚህ ሁሉ አቶ
መለስ ምስጋና ይገባቸዋል። መንግስታቸውን አዋርደው ፡ ደጋፊዎቻቸውን አክስረው ፡ ኢሳትን ሸልመው አረፉ።
አቶ መለስ በሞታቸው ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ሲያስታምሙት የኖሩትን ‘ነቀዝና ሌባ’ መንግስታቸውን ድባቅ
መቱልን። ከሞቱም በኋላ መንግስታቸው ‘ታላቁ መሪያችን’ እያለ ውርደቱን አጧጡፎታል።
ታዲያ ከአቶ መለስ ሌላ የ2012 ታላቅ ኢትዮጵያዊ መሆን ሚገባው አለን? ያለ አይመስለኝም።

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate