ኢትዮጵያ ፍ/ቤቶት ከአሸባሪ ቡድን ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው ነበር ባላቸው 10 ሰዎች ላይ ከ3 አመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስየእስር ቅጣት ወሰነ
ኢሳት ዜና:-የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የእስር ቅጣት ከወሰነባቸው ውስጥኬኒያዊው ሀሰን ጃርሶ እንደሚገኙበት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ባህሩ ዳርቻ በኬኒያው ጃርሶ ላይ የ17 ዓመት የ እስርፍርድ ወስነውበታል::
በዚህ ከአሸባሪነት ተግባር ጋር በተያያዘ ክስ በቅድሚያ የተካተቱት 11 ሰዎችእንደነበሩ ሲታወቅ አንደኛው በነጻ ተሰናብቷል ስድስቱ ደግሞ በሌሉበትተወስኖባቸዋል::
የኢትዮጵያ የስለላ ድርጅት በዚህ ወር መጀመሪያ አልሸባብ ከተባለውየሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 15 ሰዎች መያዙንማስታወቁን ይህ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::
በምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየጎላ በመምጣበት ጊዜ ነውይህ የፍ/ቤት ውሳኔ የተላለፈው ያለው ዘገባ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን በ2011 ወደሱማሊያ ዳግም መዝመቶንም አስታውሷል::
No comments:
Post a Comment