በኢትዮጵያ በደን የተሸፈነ መሬት ከ 40 በመቶ ወደ 2፡4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ
ኢሳት ዜና:- በቢዝነስ ዜናዎች ላይ እያተኮረ አዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ሀገሪቱ 37፡6ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ከመቶ ደኖን አታለች::
በሀገሪቱ ያለው እንጨትን በማገዶነት የመጠቀም ፍጆታ በአመት 50 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያመለከተው ይህ ዘገባ የደን መጨፍጨፍ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ ጠቅሶታል::
ይህም ሀገሪቱ ከምትጠቀመው አጠቃላይ ሀይል 80 ከመቶውን ከእንጨትና ከእንጨት ውጤቶች መሆኑ በዘገባው ተመልክቶል::
በኢትዮጵያ በደን የተሸፈኑ መሬቶች ተጨፍጭፈው በርካሽ ዋጋ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሸጡ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል:፡
No comments:
Post a Comment