Pages

Feb 13, 2013

የኢሕአዴግ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለአ.አ. አስተዳደር ለመወዳደር መታጨታቸው አነጋጋሪ ሆኗል


በሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር
ገዢው ፓርቲን በመወከል በተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተመርጠው ሲያገለግሉ የነበሩ ከፍተኛ መንግስት
ባለስልጣናት ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አስተዳደር ለመወዳደር እጩ ሆነው መቅረባቸው በተለያዩ ሕብረተስብ ክፍሎች
ውስጥ የተደበላለቀ ስሜት ፈጥሯል።
በተለይ ገዢው ፓርቲ ካለው የአባላት ብዛት አንፃር እና ከተማረ ሕብረተሰብ ክፍልም ከያዘው አንፃር ከከፍተኛ
የመንግስት ስልጣን አውርዶ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት እንዲወዳደሩ መደረጉ ገዢው ፓርቲን የመተካካት
ፖሊሲ ፍሬያማነትን ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል። ፓርቲውም በተወሰኑ ሰዎች ትከሻ ላይ ያረፈ እንዳልሆነ እየታወቀ ለምን
ይህን መሰል አማራጭ ገዢው ፓርቲ መውሰድ እንደፈለገ ለመገመት እንኳን አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ መፈጠሩን አንድ
ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ገልፀዋል።
አዲስ አበባን በአዲስ መልክ ለማጠናከር በሚል መነሻ የተሰጠ ሹመት መሆኑ ቢነገርም፤ በአዲስ አበባ አስተዳደር
ውስጥ ያለው ዋነኛ ችግር የአመለካከት እንጂ የከፍተኛ እና የዝቅተኛ አመራር ችግር አለመሆኑ ነው የሚነገረው።
በአዲስ አበባ አስተዳደር ውስጥ ከማሕፀን ኪራይ ሰብሳቢ እስከ መሬት ኪራይ ሰብሳቢነት የተንሰራፋው ሙስና ለያዥ
ለገናዥ አስቸጋሪ መሆኑ ይታወቃል። አሁን አስተዳደሩን ለማጠንከር በራሳቸው ፈቃድ የተወካዮች ምክር ቤትን
የተሰናበቱት ከፍተኛ ባለስልጣናት በሚያስተዳድሩት የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ምን ያህል ኪራይ ሰብሳቢነትን
ተዋግተዋል? ራሳቸውስ ከኪራይ ሰብሳቢነት ምን ያህል የፀዱ ናቸው? በሕዝቡና በድርጅቱ ካድሬዎች በግልፅ
ተተችተዋል ወይ? ለሚለው ግልፅ የመንግስት ምላሽ ያስፈልጋል ብለዋል ምሁሩ።
በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡና ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሌላ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር በበኩላቸው፤ ገዢው ፓርቲ
የሰለጠነ የፖለቲካ ዱላ እያሳረፈባቸው ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። ይህም ሲባል፤ በአንድ ጊዜ ከሚወሰድ እርምጃ ደረጃ
በደረጃ የመጨረስ የፖለቲካ ጨዋታ ሳይሆን አይቀርም ነው የተባለው።
በሌላ ወገን ያለው አስተያየት የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሚኒስትር መስሪያ ቤት የበለጠ አስቸጋሪ በመሆኑ ችግሩ
የሚፈታው መዋቅራዊ ለውጥ በአስተዳደሩ ላይ ሲደረግ እንጂ አዲስ ተሿሚዎች በማምጣት አይደለም የሚል ነው።
ስለዚህም መንግስት ለምን እነዚህን ከፍተኛ አመራሮች ማምጣት እንደፈለገ በግልፅ ምክንያቱን ሊያስቀምጥ እንዲገባ
ምሁሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።¾

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate