Pages

Apr 12, 2013

8ተኛ ዓመታችንን ሊያከብሩልን ነው እንዴ

yared elias nome telemark
ምርጫ ማለት ጦርነት ማለት አይደለም ወይም ግርግር አይደለም ምርጫ ማለት ዜጎች በመብታቸው ተጠቅመው የሚፈልጉትን ተጠሪ የሚመርጡበት ማለት ነው መጪውን ሚያዚያ 6 እና 13 የሚደረገውን የአዲስ አበባ እና ድሬደዋ የሚደረገውን ምርጫ አስመልክቶ ሰሞኑን ይህንን የተናገሩት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የፖሊስ ኮሚሽነሩ ለ2 ቀን ለመላው ፖሊስ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ነበር  ምነው እነዚህ ሰዎች ዝም አይሉንም ያለተቃዋሚ ብቻቸውን ሆነው እንኳን ዝም ብለው አይቀመጡም ለምንስ ህዝቡን ይነካኩታል ነው ወይስ በመጪው ግንቦት ወር ላይ በሚደረገው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ችግር እንዳይፈጠር በሚል ሰበብ ባሳለፍነው ሳምንት ሌላ  ከ400 በላይ አድማ በታኝ አጋዚ አሰልጥነው አስመርቀዋል ምንአልባትም አውንም ስለምርጫ ብለው 8ተኛ አመታችንን ሊያከብሩልን ነው እንዴ አቶ ወርቅነህ እንዴት አስበውት እንደሆነ ባላውቅም  ምርጫ ማለት ግርግር አደለም ጦርነት አይደለም እያሉ የተናገሩት ሼም ነው ደግሞስ ምርጫ ብለው በሰላም እርፍ ብለው የተቀመጡትን የሽብሬን እናት ወይም የአድራን እናት እና የነዛ የ200 መቶ ሰው ንጹሃን ዜጎች ባአደባባይ ባንክ ሊዘርፉ ተብለው በግፍ የተጨፈጨፉት ዜጎች ከእነሱህ በተጨማሪ ደግሞ ቆስለው አካለ ጎዶሎ ለሆኑት  ቤተሰብ ግን ምርጫ የሚባለው ምን እንደሆነ መንገር አያስፈልጋቸውም ምርጫ ማለት ለነሱ መራራ ነው ሃዘንም ጭምር ልጆቻቸውን ያስታውሳሉ ስለዚህ ምርጫ የሚባለው ነገር ለኢትዮጵያ ህዝብ ጦርነት ነው ግርግር ነው መርዶ ነው ለቅሶ ነው ሃዘን ነው ለወያኔ ግን ዲሞክራሲ ነው ሰላም ነው ግን አያፍሩም  እረ ተዎን እባካችሁ

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate