Pages

Jul 14, 2013

አንድነት ፓርቲ በጎንደርና በደሴ የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሯል


አንድነት ፓርቲ በጎንደርና በደሴ የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሯል፡፡ በግምት 2ሺ በላይ የሚሆኑ የደሴነዋሪዎች
ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ተነስተዋል የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት


ለመገኘት ወደ ከተማይቱ ለመምጣት ትራንስፖርት ያስፈልጋቸው የነበሩ ዜጎች በከተማው አስተዳደር ስውር ትዕዛዝ መሰረት
ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የትራንስፖርት መኪኖቹ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ መታዘዛቸውን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለሰልፉ
አዘጋጆች በመደወል እየገለጹ ነው፡፡ሁኔታው ያሳዘናቸው ሰዎች በቻሉት መንገድ ሁሉ ወደ ሰልፉ በመምጣት ድምጻቸውን
እንደሚያሰሙና መሰናክሉን እንደሚያልፉት አስታውቀዋል፡፡ We never give up
———————
Dawit Solomon Yemesgen
የነገው አበባ ለምን ለፌደራል ፖሊስ ይሰጣል?
—————————————–
አበባ የሰው ልጆች በአንድ ድምጽ ፍቅራችንን ወክልልን በማለት የመረጡት ይመስል የፍቅርን አደራ ተሸክሟል፡፡ከሶስተኛው
አለም እስከ አንደኛው የሚገኙ የአዳም ልጆች ‹‹አበባን››የፍቅር ስጦታ በማድረግ ለሚወዱት ይቸሩታል፡፡የሚወዱት
ሲሞትባቸውም ፍቅራቸውን ለሟቹ ለመግለጽ አስከሬኑ ላይ አበባ ያኖሩለታል፡፡
ወደ ደሴና ጎንደር እንምጣ፣ ነገ ከሌላው ጊዜ በተለየ አበቦች ለፌደራልና ለክልል ፖሊሶች በሰላማዊ ሰልፈኞች ይበረከታሉ፡፡እኛ
ኢትዮጵያዊያን የጦርነት ታሪክ የከበበን በመሆኑ ለወታደር ያለን ፍቅር የተለየ ነው፡፡ዛሬ ድረስ ወታደራዊ ዮኒፎርም የለበሰ ሰው
ሲመለከቱ ልባቸው ወከክ የሚልባቸው ቆነጃጅት ቁጥር የትየለሌ ነው፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ግን እንዲህ በስስት የምንመለከተው ወቴ በውስጥ ጉዳይ በአብዛኛው የገዢዎች መገልገያ ሆኖ በእናቱ ልጅ
ላይ ቃታ ሲስብ አይኑን አያሽም፡፡ አዛዦቹ ያሉትን ካልተገበረ ምን እንደሚጠብቀው ስለሚያውቅ ድንጋይ ለወረወረ ሁሉ
አጠፋውን በጥይት ከማድረግ አያመነታም፡፡ለዚህ አንገት ደፊ ታሪካችን ብዙ ማጣቀሻዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡
የነገው ሰልፍ አበባ የሚበረከትበት ዋነኛ አላማ ፍቅርን ለመስበክ ነው፡፡በወታደሩ፣በፖሊሱ፣በደህንነቱና በመንግስት ታማኝ ላይ
የምንመዘው ሰበዝ ቢኖርም ነገ ግን ፍቅርን እንሰጣለን፡፡ምላሹ ምንም ይሁን ምን የአበባው መልዕክት ፍቅር ነው፡፡ የአበባ ቀን
እንበለው ይሆን?
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!
አንድነት ኃይል ነው!! አንድነት ፍቅር ነው!! ፍቅር ያሸንፋል!!

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate