Pages

Jul 13, 2013

የማለዳ ወግ. . .ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ ፣ መብት አስከባሪ አላቸው ለማለት ግን አልደፍርም (አልጀዚራ)

ነቢዩ ሲራክ*”በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! “አልጀዚራ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለስደት ስለሚዳረጉ ዜጎች ዙሪያ ያሰራጨው መረጃ ቀልቤን ቢስብው በማለዳ ወጌልተነፍስ ብዕሬን አነሳሁ ። የአልጀዚራ ቴሌቪዥን Escaping Ethiopia’s unemployment “በኢትዮጵያ ስራአጥንትን ለመሸሸ ” ያለው ዘገባ ስለ ስደቱ ከስደተኞች አንደበት፣ ለቀጣዩ ስደት እየተዘጋጁ ስላሉት ፣ ሰለ ህገ ወጥአሸጋጋሪዎችና ስደቱን ለመገደብ መንግስት እየወሰደ ስላለው ጥረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንእማኝ አድርጎ በዘገባው አሳይቶናል አልጀዚራ ያቀረበወን ዜና እዚህ ላይ ይጫኑና ይመልከቱበዚሁ ዘገባ ላይ በቀረበው መረጃ ስደትን ለማስቆምና የአዘዋዋሪዎችን ወሽመጥ ለመቁረጥ የተጠና ስራ ላቀረቡ ወጣቶችስደትን ለመገደብ በመንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ 27 ዶላር ያበድራል ተብሎ ሰምቻለሁ። የተባለው በእኛሃገር ይሆን ? ስልም ጠየቅኩ ! ” ጀሮ ለራሱ ባዳ ነው “ብየ አላየሁ አልሰማሁም ብየ ልለፈው! አሁን ሰምቻለሁናይሰጣልም ብየ ለቀበለው ። ግናስ ለብድር አሰጣጥ መስፈርቱ ምንድን ነው? ይህ ግን አልገባኝም ! መስፈርቱ ወሳኝሆኖም ይህንንም አድልኦ ሰዎች በፖለቲካ አምለካከት በሃይማኖትና በዘር ሳይለዩ እኩል ታይተው ድጋፉ ይደረጋልበሚል ልቀበለው ። የተባለው ሁሉ እውነት ቢሆን እንኳ የተጠናን ስራ አውርቦ ጠቀም ያለ ብድር የማግኘት እድሉተምሮ ስራ ላጣው አለያም ለነቃው እና ለተደራጀው የከተማ ወጣት እንጅ ለቀረው መፍትሄ አይደለም ።ይህ መፍትሄ በዘገባው ቀርበው ላየናቸውበማንኛውምወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራለመሰደድ ለተዘጋጁት እና ከህጋ የሃገራት ሁለትዮሽስምምነት ውጭ ለሰደዱት ከገጠሩ ክፍል የሚጋዙትቁጥራቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱትእህቶች የሚፈይደው ነገር የለም ።በአረብ ሃገርበኮንትራት ስም የሚሰደዱ እህቶችን እንዳይሰደዱለማገድ አሸጋጋሪ ደላላዎችን ከመቆጣጠሩ ጎን ለጎንዜጎችን ከድህንት የሚዎጡበትን መንገድ መንደፍ ፣የዜጎችን ነጻነት ማክበር አና ሁሉንም ዜጎች እኩልበማየት መሰረተ ልማቶቸን በማስፋፋት የስራ እድልመክፈት ዋናው መፍትሔ ሊሆን ይገባል።“ኢኮኖሚያችን አደገ ተመነደገ” እየተባለ አቅማችንይህ ማድረግ ካልቻለ ብቸኛው መፍትሄው ” አትሰደዱ” ብሎ መልፈፉና እና “ለሚሰሩት እድሉ ” አለ ብሎ መደስኮሩከመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም ! ስደት ክፉ ነገር ነው ፣ እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑትእያላቸው ካላቸው ለመጨመር ከሚሹ ስግንግቦች ውጭ ብዙው ስደተኛ ለመሰደዱ የስራ ማጣት ፣ የድህነትና የኑሮውድነት በቂ ምክንያት እናዳለው በስደቱ አለም ስኖር ካገኘኋቸው ስደተኛ ወገኖቸ የተረዳሁት ሃቅ ነው ።የኑሮ ውድነት ሳያንገሸግሽ ፣ ሳያጨናንቀው ስደትን የሚፈልግ የለም ፣ በሃገሩ ተምሮና ሰርቶ እሱንና ቤተሰቡን መደገፍእየቻለ ስደትን የሚመርጥ የለም ! የመንግስት ሃላፊዎች ለገጽታ ግንባታ የሚለቋቸውን መረጃዎች ገታ አድርገውበስደተኛው ችግር ላይ ቢያንስ ትክክለኛ መረጃ ቢሰጡን መልካም ነበር ። ከሁሉም በላይ ወደ አረብ ሃገራትበኮንተራት ስራ ስም የሚላኩ ዜጎችን ጉዳይ ቆም ብለው ሊመረምሩት ይገባል። ሰው ” በሃገሬ ተቸገርኩ ፣ ተምሬ ስራአጣሁ !” እያለ ስደቱን ማቆም ይከብዳል። ያም ሆኖ በህገ ወጥ ደላላ ተታልለው በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደዱትንለማስቆም መንግስት በስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ስም እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥ የበከተ ድልላ በሰውር የሚሰራውንስራ ሰንሰለቱን ከቁንጮው ሊበጣጥሰው ይገባል ። ስደትን ማሰወቆም ካልቻልን አማራጩ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሃገርእና ሊሰሩት ስለሚችሉት ስራ ትክክለኛ መረጃ እና ቅድም ዝግጅቶችን በትክክል አሟልቶ ማቅረብ አማራጭ ሊታይይገባል። ከዚህ ሁሉ አስቀድሞ ግን ዜጎችን በሃገራት መካከል በሚደረግ የሰራተኛ ውል መሰረት በህጋዊ ኮንትራት ስራዜጎችን መላክ እና ከተላኩም በኋላ በመብት ማስከበሩ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት በፖለቲካታማኝነት ሳይሆን ዲፕሎማሲው ጥብብ የተካኑትን ከሃላፊዎች በበቂ ሁኔታ በአረብ ሃገራት ሊመድብ ይገባል! ያለንትየስልጣኔ ዘመን ነውና መረጃን በመደባበቅ እውነትን ማጥፋት አይቻልም።ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ማቀበል ያዋርዳል እንጂ አያስከብርም ፣ ከሃቅ የራቀ መረጃ ገጽታን ያጨለማል እንጅ ፈካአድርጎ ቀይሮ አያሳይም ! በአልጀዚራ ዘገባ እንደተነገሩት አንዳንድ መረጃዎች አጋጣሚውን ገጽታ መገንቢያ አድርገንእውነቱን የምንሸፋፍን ከሆነ ትልቅ ስህተት ተሳስተናል ! እውነትን በውሸት ለመድፈን ስንቆፍር ነገም እንደ ትናነቱከመከራ መውጣት አይቻለንም ! ዛሬም ጉዟችን ቅጥፈት ከሆነ በምናየው የወገን ሮሮ ፣ የሰቆቃ ድግግሞሽ ስናለቅስእንደኖርን ስናለቅስ እንኖራለን ! አባቶች “በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! ” እኛው ራሳችን በሽታችንስንነግራቸሁ ስሙን ፣ መድሃኒቱንም ፈልጉልን ! የማለዳ ወጌን አበቃሁ !በሽታችን ተረድቶ መድሃኒት ጀባ የሚልየህዝብ አገልጋይ ይስጠን!ነቢዩ ሲራክ

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate