Pages

Aug 12, 2013

መንግስት አላዋጣ ሲለው ጥሎት የነበረውን ካርታ ዳግም መዘዘው

 
መንግስት አላዋጣ ሲለው ጥሎት የነበረውን ካርታ ዳግም መዘዘው
እውን ይህ ካርታ ይሳካለት ይሆን?

የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መብታችን ይከበር በማለት አሃዱ ብለው ከተነሳንበት ጊዜ አንስቶ በመንግስት አካላቶች በተደጋጋሚ በሚዲያቸው፣በጋዛጣ እንዲሁም በሚያዘጋጁት መፅሄቶች ላይ ሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ እየተንቀሳቀሱ ነው በማለት ትግላችንን ለማሸማቀቅ እና ለዘመናት ተቻችለን እና ተከባብረን ከሌላ እምነት ተከታዬች ጋር የመኖር ባህላችንን አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ብዙ ሲዳክር ቆይቷል፡፡
ሆኖም ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነው በማለት የክርስቲያን ወገኖቻችንን ድጋፍ ለማግኘት ቢጣጣርም
እውነታውን ግን እየዋለ እና እያደረ ለሁሉም እየተገለጠ በመምጣቱ መንግስት አስቦት የነበረው ኢስላማዊ መንግስት የምትለዋ ካርታ አላዋጣ ብላ ብሎም ኪሳራ ውስጥ ከተተችው፡፡
ሟች ጠ/ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ በመሰናበቻ የፓርላማ ንግግራቸው በኢትዬጲያ ውስጥ የሙስሊሞች ቁጥር ይበልጣል፡፡ መንግስት ያንሳል ማለቱ ስህተት ነወ፡፡ ከሃገሪቱ ካለው ህዝበ ብዛት የሙስሊሙ ቁጥር
ስለሚበልጥ ኢስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን በማለት ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው እነዛ ጥቂት ሰለፊዬች በማለት የኢትዬጲያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ በሃሰት መዳመጣቸው የሚታወስ ነው፡፡
የሆኖ ሆኖ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የእምነት ወኪሎቻችንን እኛው እንምረጥ ነው ያልነው አይደለም ሸሪአዊ መንግስት ለመመስረት ማሰብ ይቅርና የሸሪአ ፍርድ ቤታችን እንኳን ይስተካከል ብለን አልጠየቅን በማለት በመላው ሃገሪቱ አንድ አቋም መያዙን ያስተዋለው መንግስት ስቦት የነበረው ካርታ ለጊዜው አላወጣኝም በማለት መልሶ ለመክተት ተገዶ ነበር፡፡ ኮሚቴዎቻችንም ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነበር በማለት ክስ ያቀረበባቸውን በማንሳት ጨዋታውን አክራሪነትን ለማንገስ የሚደረግ ሩጫ በሚል ቀይረውት ነበር፡፡
ህዝበ ሙስሊሙም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመብቱ መከበር ያለውን ቁርጠኝነት እየጨመረ መምጣቱን የተመለከተው መንግስት የውስጥ ሰዎችን ልኮ ትግሉን ለማቀዛቀዝ ሞከረ፡፡አሁንም ዳግም አልሳካ አለው፡፡በሙስሊሙ እና በመንግስት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በዚሁ ሁኔታ መቀጠሉ አብዛሃኛው ማህበረሰብ ችግሩ ምኑ ጋር እንዳለ ለመረዳት አስቻለው፡፡የመንግስት የቅርብ ወዳጅ የሆኑት እነ አሜሪካም እንኳን ሳይቀሩ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች አሸባሪዎች እንዲሁም ፅንፈኞች አይደሉም ሲሉ በአንደበታቸው ተደመጡ፡፤
በምስራቅ አፍሪካ የሽብር ስጋት ቀጠና መሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ቢታወቅም በኢትዬጲያ በኩል ግን ከውስጥ አንዳችም ፅንፈኝነት ምልክት አለመታየቱን አለም አቀፍ ድርጅቶች መሰከሩ፡፡
መንግስት በቻለው አቅም አላማውን ለማሳካት የቀደዳቸው በሮች በሙሉ ለመንግስት ሽንፈትን እንጂ ድልን ሊያስገኙለት አልቻለም፡፤በተደጋጋሚ ሙስሊሙን እርስ በእርስ ለመከፋፈል ሱፊ ሰለፊ ብሎ ቁማር ተጫወተ፡፡ አልተሳካም ዞር በል ተባለ፡፡ ቀጠለ ፅንፈኛ አክራሪዎች መጡላችሁ ብሎ ሰበከ፡፡የሚሰማው ጠፋ፡፡ ድራማ ሰርቶ አቀረበ፡፡ሁሉም ህዝብ በተውኔቱ ደካማነት ሳቀበት ብሎም አላገጠበት፡፤አተርፋለው ብሎ ያላሰበው ኪሳራ ውስጥ ከተተው፡፡
በመንግስት በኩል ተሰልፈው የነበሩት አካላትም ጥያቄ አለን በማለት ገሸስ ማለትን አስቀደሙ፡፡ ይህ አልወጥልህ ያለው መንግስት የመጨረሻ የሚለውን ካርድ ለመሳብ ተገደደ፡፡
በደሴ ከተማ ዋና አጋሩን ሼህ ኑሩን አስከወዲያኛው አሰናበታቸው፡፡ሰውየውን በሂወት እያሉ ከጌታቸው ከአላህ ጋርም ከህዝብ ጋርም አጣልቶ ተጠቀመባቸው፡፤ ግብአተ መሬታቸውንም ካፋጠነ ቡሃላም ከፍተኛ ጥቅም ለማጋበስ ሩጫውን ቀጠለ፡፡፡፤
ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን ማህበረሰብ ለመለያየት እና ለማጋጨት ሼህ ኑሩ ጥሩ አጋጣሚ ፈጠሩ፡፤አክራሪዎች ገደሏቸው፡፡ እኔ መንግስት ፅንፈኞች አሉ ስላችሁ አልሰማ አላችሁኝ በማለት ተቋርጦ የነበረውን አስትንፋሱን ለመመለስ መፍጨርጨር ጀመረ፡፡ሼህ ኑሩን ወደ ቀጣዩ አለም አሰናብቷቸው መንግስት ግን የራሱን ቀጣይ የትግል ሜዳ አመቻቸባቸው፡፤
ከሼህ ኑሩ ሞት ቡሃላም ሌላ አንድ ተጨማሪ ካርታ ተመዘዘ፡፡ ባንዲራ(ሰንደቅ አላማ!!!!!!!). ይህን ሰንደቅ አላማ አዋረዱት አለ፡፡ በመቶሺዎች የሚቖጠሩ ሙስሊሞች በተገኙበት ቦታ አንድ ወጣት ልጅ ከአንዋር መስጂድ ጣሪያ ላይ ያገኛትን በዝናብ እና በፀሃይ የተበጣተሰች ባንዲራ ከወደቀችበት በማንሳት አውለበለባት፡፡ይህ ድርጊቱ በኢቲቪ ካሜራ ስር ገባች፡፤በሚዲያም አቀረቧት፡፡
በእርግጥ የባንዲራው ካርታ ቀደም ተብሎ የታሰበባት ጉዳይ ናት፡፡ ከዚህ ቀደም ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የኢትዬጲያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዳይታይ ሲደብቁ ተስተውለዋል በማለት መወንጀሉ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ ሁላ ሩጫ ቡሃላ በኑር መስጂድ በተካሄደው አስገራሚ ተቃውሞ ልቡ የደነገጠው መንግስት ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ባንዲራ አቃጠሉ በማለት ድራማ ሰርቶ በሚዲያ አቀረበ፡፡የክርስትና እምነት ተከታዬችን ለመኮርኮር እና በሙስሊሞች ላይ ለማነሳሳት ከፍተኛ ስራ ሰራ፡፡በሁሉም ሚዲያዎቹ ይህን ድራማ በሙስሊሞች ስም ሰርቶ ካራገበ ቡሃላ በፊት መዞት ወደነበረው ካርታ ተንደርድሮ ተመለሰ፡፡
የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት ኢስላማዊ መንግትስት ለመመስረት ነው ሲሉ በድጋሚ አወጁ፡፡በኢድ አደባባይ ያን ሁላ ሺህ ህዝብ ደብድበው ጥቂት ሰለፊዬች ኢስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን በማለት ባስነሱት ግርግር እና ሁከት ችግሩ እንደተፈጠረ በመግለፅ ለሚሊዬኖች ሙስሊሞች ንቀታቸውን አሳዩ፡፡
በግብፅ የጠፈጠረውን የፖለቲካ ትኩሳት በመመርኮዝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ከግብፅ እርዳታ እንደሚያገኙ እና ኢስላማዊ መንግስትም ለመመስረት እየሰሩ እንደሚገኙ መስበኩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
በኢድ ሰላት በመላው ሃገሪቱ የተካሄደውን ተቃውሞ ለመግታት ሙሉ ሃይሉን ተጠቅሞ ለማቀዘቀዝ ቢሞክርም ሳይሳካለት የቀረው መንግስት የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊትም ለመሸፋፈን እና ትቶት የነበረውን ካርታ ዳግም በመምዘዝ በሚዲያ በመቅረብ ክርስቲያኖች ሆይ ንቁ ሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱባችሁ እየታገሉ ነው የሚል እንድምታ ያለው መልዕከት ከጠ/ሚኒሰተሩን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዚህ ሁለት ቀናቶች ውስጥ መግለጫቸውን ለሚዲያ ሰተዋል፡፡
ውድ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ሆይ መንግስት እንደ አዲስ የመዘዛት ካርድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ኪሳራን እንጂ ትርፍን እንደማያጋብስለት እሙን ነው፡፡ አዲስ በተጀመረው ፕሮፖጋንዳ ላይ ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር መንግስት ለመፍጠር የፈለገውን እኛን የማጋጨት ስራ ለማክሸፍ ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል፡፡ ከዚህ ቀደም ባዳበርነው ልምድ በመነሳት ይህን ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ለማክሰም ይከብደናል ብዬ አልገምትም፡፡በመሆኑም ሁላችንም በኩላችንን ለክርስቲያን ወገኖቻችን የትግላችንነ እውነታ እና የመንግስትን ቅጥፈት በማጋለጡ ስራ ላይ ለመሳተፍ ቆርጠን መነሳት እንደለብን መልዕክቴን በማቅረብ ሃሳቤን እዚህ ላይ እቋጫውው፡፡

አላህ እውነታውን የምናሳውቅ እና ከሁሉም እምነት ተከታዬች ጋር ኢስላም ባስተማረን መልኩ ተከባብረን የምንኖርባት ሀጋር ያድርግልን፡፡
አቡ ዳውድ ኦስማን ኦስማን
To get more information like this page
https://www.facebook.com/abudawdosman

https://www.facebook.com/abudawdosman

 

 

 

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate