Pages

Aug 2, 2013

DW ዘጋቢ አቶ የሃንስ ገ/ማርያም ከአዲስ አበባ ህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን በፖሊስ ላይ ድንጋይ መወርወሩን መሰከረ !

DW ዘጋቢ አቶ የሃንስ ገ/ማርያም ከአዲስ አበባ ህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን በፖሊስ ላይ ድንጋይ መወርወሩን መሰከረ !
ዛሬ የረመዳን ወር የጁመአ ጸሎት የመጭረሻ እለት ሊሆን እንደሚችል በሚነግርለት ቀን በመላው ሃገራችን ሊደረግ ታቅዶ የነበረው ድምጻችን ይሰማ መረሃ ግብር አሸባሪው የኢ.ህ.አ.ዴ፣ግ መንግስት በህዝብ ላይ ሊፈጥር የሚችለውን የሽብር ጥቃት ከወዲሁ ለማክሸፍ ፕሮግራሙ መሰረዙ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ግራ የገባው እና ከአሸባሪ አለቆቹ የተሳሳተ መመሪያ የደረሰው ፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ መሳጂዶችን ከቦ ውሎል።

በተለይ አዲስ አበባ በተለምዶ ፍሉሃ እየተባለ በሚጠራው መስጂድ ጸሎታቸውን ሊያደርሱ በመጡ ንጹሃን ወገኖቻችን ላይ ፖሊስ የተለመደውን ትንኳሳ ለማድረግ ቢሞክርም በህዝበ ሙስሊሙ የመጨረሻ የረመዳን ወር ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚነግረለት ሃይማኖታዊ የፀሎት ስረአቱ እንዳይስተጓጎልበት ጥረት ቢያደርግም መንግስት ቀደም ብሎ ህዝበ ሙስሊሙ መሃል ባሰማራቸው ቅጥረኛ አሸባሪዎች ከጁመአ ሰላት በፊት በአካባቢው በተፈጠረ ግርግር ፖሊሶች አያሌ ሙስሊሞችን በቋመጥ፡ቀጥቅጠዋል ።

ለሃይማኖቱ ቀናኢ የሆነው ህዝበ ሙስሊም የፖሊስን ዱላ ችሎ ሃይማኖታዊ ስረአቱን በአግባቡ በማድረስ ወደ የመጣበት በሰላም ለመመለስ ጥረት ቢያደርግም ሰላምዊን ህዝብ በሁከት ለማተራመስ ተዘጋጅቶ አደባባይ የወጣው የፌደራል ፖሊስ በሌላ አቅጣጭ ወደ የመጣበት በሰላም እየተመለስ የሚገኘውን ህዝበ ሙስሊም ማፈስ መጀመሩን ተከትሎ ከሰላት ስግደት በሃላ ፖሊስ በምዕመናኑ ላይ በወስደው እርምጃ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሙስሊም ወገኖቻችን ያለምንም ጥፋት ለእስር ዳርጝዋል። ይህ ጸሃይ የሞቀ እውነታ ባለበት ሁኔታ DW አቶ የሃንስ ግ/ ማርያም ከአዲስ አበባ ያስተላልፈው ዘግባ ሚዛናዊነትን የጎደለው መሆኑንን ቦታው ላይ የነብሩ ታዛቢዎች ይገልጻሉ ። በወቅቱ እንደ ኢቲቪ ሰራተኞች በፌደራል ፖሊሶች ጥበቃ ይደረግለት የነበረው አቶ የሃንስ ገ/ማርያም በአካባው የነብሩ ሙስሊሞች ለኢንተርቪው ፈቃደኛ እንዳልሆኑለት ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።

አቶ የሃንስ ገ/ማርያም በጋዜጠኝነት የትምህርት ደርጃው ባይታማም አልፎ አልፎ ከኢትዮጵያ የሚያስተላልፋቸው መረጃዎቹ ሚዛናዊነት የሌላቸው እና ለግዢው ፓርቲ ያደላ መሆኑ ይታወቃል። አቶ የሃንስ ገብረማርያም ቀደም ብሎ በትግራይ ሙስሊም ወገኖቻችን የመቃብር ቦታ በመንግስት ያለአግባብ መታረስ ( መፍረስን) ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ ያሰማውን ተቃውሞ ሚዛናዊ በጎደለው መልኩ ከመቀሌ መዘገቡ አይዘነጋም።

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate