እባካችሁ የሜንጫ ማንነት ይፋቅልኝ የፖለቲካል ተንታኝ ምናምን ቴዲ ኣፍሮ በደሌ ጥቁር ሰው የኢትዮዽያ ቇንቇ አማርኝ ብቻ አይደለም በኢትዮዽያ ሙስሊምና በኦሮሞ ህዝብ ትግል መካከል አብረዉ መሄድይችላሉ...........................................
እንዴ ምን እየተካሄደ ነው ??
ሼም በአገረ ኢትዮዽያ ቀረ እንዴ በሜንጫ ነዉ የምንለዉ ያለውን ዝም ባልን እንደገና ዛሬም
በመጀመሪያ የሜንጫ ማንነት እራሱ ይፋቅ ማን ነው ማንን ነው የሚወክለው ????
ህወሃት ልዩነቶቻችንን አብዝቶና አርብቶ ክብራችንን አዋርዶ ረግጦ ሊገዛን ዘመኑን ሙሉ ሠርቷል። ለብዙ ግዜም አንዱን ህዝብ የአንዱ ጠላት አድርጎ ሲሰብክ ኑሯል። ይህንንም እውነት ለማስመሰል በበደኖ ፤በአርባ ጉጉ፤ በሃረርጌና በሌሎች ሥፍራዎች የብዙ ንጹሃን ዜጎችን ደም አፍስሶ ለርካሽ ፖለቲካ ፍጆታ አውሎታል። በደኖ ላይ አፈር ገፍቶ ይኖር የነበረ አማራ የተባለ ዘር የተጨፈጨፈው በህወሃት ፊታውራሪነት ነው። በአርባ ጉጉ ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ሰቆቃ አዛዥና አስፈጻሚው በመለስ ዜናዊ የሚመራው ህወሃት መሆኑን የምንዘነጋው ጉዳይ አይደለም። ልዩነታችን ውበታችን ሊሆን ሲገባው መጠቂያችን ሁኖ ጎድቶናል። በመለያየታችን ምክንያት ብዙሃኑ ለነጻነታቸው የሚያደርጉት ትግል ተዳከመ እንጂ አልጎለበተም። ጥቂቶች ብዙሃኑን ለመጨቆን አቅም አገኙ እንጂ አደብ አልገዙም። ተራርቀን በመቆማችን መለስ ዜናዊና ቡድኑ በክፍተቱ ተጠቀሙ እንጂ ነጻነት የተነፈገው ብዙሃኑ ያገኘው አንዳች በጎ ነገር የለም።
የመለስ ዜናዊና ቡድኑ ብርቱ ፍላጎት ኢትዮጵያዊያኖች የታሪክ እሰረኛ ሆነን ልዩነታችንን ማጥበብ ተስኖን ተከፋፍለን ተዳክመንና ተስፋ ቆርጠን እንድንኖር ነው።ይህን መፍቀድ ደግሞ ውረደት ነው።
በአገራችን ታሪክ ውስጥ በማወቅም ባለማወቅም ብዙ በጎ ያልሆኑ ነግሮች መፈጸማቸው እውነት ነው።ብዙሃኑ በጥቂቶች ተረግጠውና ተጨቁነው መከራቸው በዝቶ ዘመኑን ማሳለፋቸውም የሚካድ አይደለም።ጥንት ስህተት ተፈጽሟል። በዚህ ልዩነት የለንም። ብዙዎቻችን እንስማማለን።ልዩነታችን የሚሰፋው ያን ክፉ ስህተት መልሰን እንደግመዋለን በሚሉና ከስህተቱ ተምረን አንዲት ጠናካራ አገርን እንመስርት በሚባልበት ግዜ ነው።
ህወሃትን የመሰለ ዘረኛና ዘራፊ ቡድን በራሳችን ላይ ተጭኖ እርሱን በአንድነት ሆነን ከመታገል ፈንታ “እንዲያና እንዲህ” ሁነን ነበር እያሉ ማላዘን ጥቅም የለውም። ጥቅም አለው ከተባለም የሚጠቅመው ህወሃትን እንጂ ነጻነቱን ተነፍጎ የኖረውን ህዝብ አይደለም። ነጻነትን ለመቀዳጀት የፈለገ እርሱ የጠላት ጆሮ እየሰማ አይኑም እያየ እጅ ለእጅ ተያይዞ ጠላትን ለመፋለም መዘጋጀት አለበት። አዎን አማራጫችን አንድ ሆነን ህያው የሆነውን ጠላታችንን መታገል ነው። አንድ ሆነን አንታገለም ማለት ጠላት ህዝባችንን እስከ ልጅ ልጆቻችን እንደጨቆነ ይዝለቅ ከማለት ውጪ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም።
በአጠቃላይ አነጋገር ሜንጫ ( jawar mohammed) ዘረኛ፤ ውሸታምና ዘራፊ የሆነ ግለሰብ ነው ከህወሃት ከቀደሙት ወያኔ ዘረኛ ወንበዴ የሚሻልበት በጎ ነገር ሳይኖረው ይሻላል ብሎ መደገፍ አሳፋሪ ነው
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment