Dec 20, 2012
Breaking News (ሰበር ዜና): ኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ ፓትርያርክ ለመምረጥ አስመራጭ ጳጳትን መረጠ
ከማህበረ ቅዱሳንም አስመራጭ ተወክሏል
ሐበሻ) በዳላስ የተደረገው የሁለቱ ሲኖዶሶች ድርድር የተጠናቀቀው በቀጣይ ጥር 16 ቀን 2005 ዓ.ም ቀጣዩ
እርቅ እስከሚደረግ ድረስ እርቀ ሰላሙን የሚያሰናክሉ ነገሮችን ከማድረግ እንዲቆጠቡ የሚል ድርድር ደርሰው ነበር –
ከሁለቱም ወገኖች ያሉት አባቶች። ሆኖም ግን አሁን በሰበር ዜና ለዘ-ሐበሻ በደረሰው ዜና ኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ
ስምምነቱን በመጣስ ፓትርያርክ ለመምረጥ አስመራጭ ጳጳሳትን መምረጡን ታማኝ ምንጮቻችን ገለጹ።
ቤተክህነት አካባቢ ያሉት የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮቻችን ገለጻ 4 ጳጳሳትና ሌሎች አራት ሰዎች ለፓትርያርክ
አስመራጭ ኮሚቴነት ተመርጠዋል።
ለፓትርያርክ አስመራጭነት ኮሚቴ የተመረጡት ጳጳሳት፦
1ኛ. አቡነ ጢሞጢዎስ
2ኛ. አቡነ ቄርሎስ
3ኛ. አቡነ እስጢፋኖስ
4ኛ. አቡነ ቀሌምንጦስ ሲሆኑ
ሌሎቹ 4ቱ ደግሞ፦
1ኛ. ሊቀትጉሃን ሃይለጊዮርጊስ ዳኜ
2ኛ. ሊቀማህምራን ፋንታሁን ሙጬ
3ኛ. አቶ ባያብል ሙላቴ ከማህበረ ቅዱሳን
4ኛ. አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬ ከኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት ናቸው።
የዘ-ሐበሻ ታማኝ የቤተክህነት ምንጮች ጨምረውም ስምንት ጳጳስት ቤተመንግስት ድረስ እየተጠሩ እንደሚሄዱና
የፓትርያርክ ምርጫ በአስቸኳይ እንዲፈጸም እንዲጎተጉቱና እንዲያስፈጽሙ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ ስምንቱ ጳጳስት
ውስጥ፦
1ኛ.አቡነ ጎርጎዮስ
2ኛ. አቡነ ሳሙኤል
3ኛ. አቡነ ቄሌንጦስ
4ኛ. አቡነ ሳዊሮስ እንደሚገኙበት ታውቋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን።
በርከት ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድነት እንዲመጡ ሲጸልዩ የከረመ
ቢሆንም ኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ በመንግስት ጫና መንግስት የሚፈልገውን ፓትርያርክ ለመምረጥ መዘጋጀታቸው
የአንድነት ተስፋውን እንዳጨለመባቸው ከሚሰጡት አስተያየት መረዳት ይቻላል።
ዘ-ሐበሻን ለፈጣን መረጃ ሁሌም ያንብቡ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment