(ዘ-ሐበሻ) ለአፍሪካ ዋንጫ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚሄደውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ቡድን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ እየተሯሯጠ የሚገኘውን የደቡብ አፍሪካ
የኢትዮጵያ ኢምባሲን ሴራ ለማክሸፍ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሰፊው
እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የደቡብ አፍሪካ የዘ-ሐበሻ ወኪል ገለጸ። እንደ ወኪላችን ገለጻ
የኢትዮጵያ ኢምባሴ የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ የያዘ ቲቨርትና የወያኔን ኮከብ
ያለበትን ባንዲራ ለመሸጥ ከፍተኛ እንስቃሴ እያደረገ ቢሆንም፤ ሕዝቡ የአንባገነኑን አቶ
መለስ ዜናዊን ፎቶ ያለበትን ቲቨርት እንዳይለብስና የወያኔን ባንዲራ እንዳይዝ በማሰብ
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ እና የቤተ ኢትዮጵያውያን ማህበር በጋራ
ቲሸርቶችን እና ምንም ዓይነት ኮከብ የሌለበትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ
አሳትመው በነጻ እየበተኑ መሆኑ ታውቋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት “በዘርና በሃይማኖት መከፋፈሉ በቃን፤ አንድ ኢትዮጵያዊ
ነን በሚል” ደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች ለሚሄደው ድጋፍ ለመስጠት
ከፍተኛ ርብርቦሽ እያደረጉ ሲሆን ከወዲሁም ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር የምታደርገው
ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ትኬት ተሽጦ ማለቁን ወኪላችን ከደቡብ አፍሪካ
ዘግቧል። ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጨዋታውን ለመመልከት ትኬት
ገዝተዋል ተብሏል; እንደወኪላችን ዘገባ በደቡብ አፍሪካ ከ200 ሺህ በላይ የሚመቱ
ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኢምባሲ የመንግስት አመራሮችን
በተለይም ሃይለማርያም ደሳለኝን ጋብዞ ህዝባዊ ስብሰባ ቢጠራም ሕዝቡ ቦይኮት
በማድረግ የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካ ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ከዛም በኋላ ታማኝ
በየነን ጋብዘው ስታዲየም ሙሉ ሕዝብ በመገኘት አንድነታቸውንና ሃገር
ወዳድነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለስፖርታዊ ጨዋታዎች የሚሄደውን
ብሔራዊ ቡድናችንን ከስፖርታዊው ትኩረቱ ውጭ አቶ መለስ ዜናዊ ሌጋሲ ላይ እንዲያደርግ ከፍተኛ ሥራ እየሰራ መሆኑን የጠቁመው የዘሐበሻው ወኪል የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ደጋፊዎችን
ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊዎች ወደ አንድነት በመምጣት የመንግስትን ሴራ ለማክሸፍ እየተሯሯጡ ይገኛሉ። በተለይም በእምነት ውስጥ ጣልቃ እየገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤ/ክ እና ሙስሊሞችን እያስጨነቀ የሚገኘውን የኢትዮጵያ መንግስት ስታዲየሙ ውስጥም ሆነ ከስታዲየሙ ውጭ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ “መንግስት እጁን ከሃይማኖቶች ላይ
እንዲያነሳ” ለመጠየቅ ሥራ እየተሰራ ይገኛል ያለው ዘጋቢያችን በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የወያኔን ባለኮከብ ባንዲራ ይዞ እንዳይገኝ ጥሪ መተላለፉን በአንጻሩ ሃገር ወዳድ
ኢትዮጵያውያን በተለይ በጆሐንስበርግ ከተማ በነፃ እየበተኑት ያለውን ባንዲራ ይዘው ለብሄራዊ ቡድናችን ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ እየተላለፈ ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጆሐንስበርግ ሲገባ ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
netsanet ke-fetari yeteseten kibur sitota new
ReplyDeletemanim linetiqenim ayigebam