Pages

Jun 23, 2013

ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሌባ ተባባሪነት ለመደባቸው

ከጥቂት ሳምንታት በፊት(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ በከፍተኛ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ተከሰሱ። ሊቀትጉሃን አስታጥቄ በተመሰረተባቸው ክስ ጠበቆቻቸው ዋስትና ቢጠይቁባቸውም ፍርድ ቤቱ ግን ዋስትና ለመፍቀድ ወይም ላለመፍቀድ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ቢባልም ዘ-ሐበሻ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልደረሳትም።
l። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ
“ፕሬዚዳንት ግርማ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ክስ እንዲቋረጥ ጥሪ ማቅረባቸውን” ያትታል። ዜናውን
ለተመለከተ ከዘራፊው የወያኔ ስርዓት ጋር በመተባበር “አበባ የመትከልና አበባ የመቁረጥ ስልጣን” ብቻ ተሰጥቷቸው
ቁጭ ያሉት ፕሬዚዳንቱ እኚህን በርከት ያሉ አርበኞች አባቶችን ያስለቀሱትን ሊቀትጉሃንን ክሳቸው ተቋርጦ ይፈቱ
ሲሉ በድፍረት መጠየቃቸው የሌባ ተባባሪነቱ ለመደባቸው፤ ወይም ከሌባ ጋር መተባበር ሱስ ሆነባቸው እንዴ?
ያስብላል። የሪፖርተር ዜና እንደሚከተለው ነው። አንብቡትና ትዝብታችሁን ጣሉበት።
በከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው
የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት፣ ዋና ጸሐፊና
የአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ፣ የተከሰሱበት ክስ
እንዲቋረጥላቸው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ለፍትሕ
ሚኒስቴር የጻፉት ደብዳቤ ውድቅ መደረጉን ምንጮች ለሪፖርተር
አረጋገጡ፡፡
የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ
ለፕሬዚዳንት ግርማ በጻፉላቸው የመማፀኛ ደብዳቤ አማካይነት፣ ክሳቸው እንዲቋረጥላቸው ወይም በይቅርታ እንዲታለፉ
ፕሬዚዳንቱ ደብዳቤውን የጻፉት በፍትሕ ሚኒስቴር የሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ለአቶ ብርሃኑ ፀጋዬ መሆኑን
ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡
በከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት ክስ የቀረበባቸው
የኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ፣ ዋና ጸሐፊው ፲ አለቃ ሰጥአርጌ አያሌውና የአስተዳደርና
ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ አቶ በቀለ ሻረው መሆናቸው ይታወሳል፡፡
ፕሬዚዳንት ግርማ ተጠርጣሪዎቹ በአገራቸው የጀግንነት ታሪክ ከፍተኛ ቦታ እንዳላቸው፣ ለአገር ልማትም በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ
እገዛ እያደረጉ መሆናቸውንና ዕድሜያቸውም የገፋ መሆኑን በመግለጽ፣ መንግሥት ይቅርታ አድርጐላቸው ክሳቸው እንዲቋረጥ
በደብዳቤ መጠየቃቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በቁጥር መ/818/2005 የጻፉትን ደብዳቤ የተመለከቱት የፍትሕ ሚኒስቴር
ባለሥልጣናት ጥያቄው ተገቢ አለመሆኑን፣ ግለሰቦቹም የተጠረጠሩበትን የወንጀል ድርጊት ፍርድ ቤት ቀርበው በሚደረግ የግራ
ቀኝ ክርክርና የሕግ ሒደት ብቻ የሚታይ መሆኑን በመግለጽ፣ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረጉት ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
እነ ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ የተጠረጠሩበት ወንጀል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት አቶ አርከበ ዕቁባይ፣
አቅመ ደካማ ለሆኑ አባት አርበኞች የፈቀዱላቸውን 25 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለግል ጥቅም አውለዋል፣ ከሚያከራዩዋቸው
ሕንፃዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ የአከራይ ተከራይ ግብር አለመክፈል፣ ያላግባብ ወጪ ማድረግና በመሳሰሉት ተጠርጥረው
መከሰሳቸውን፣ ዋና ጸሐፊውና የአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊው እያንዳንዳቸው በ25 ሺሕ ብር ዋስ መለቀቃቸውንና
ፕሬዚዳንቱ ባለመቅረባቸው ታስረው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ (ሪፖርተር)

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate