Dec 13, 2012
ከሰሞኑ መነጋገሪያ የሆነው ርዕስ በተለይም በየ ሶሻል መድረኩ “ቴዲ አፍሮ በይቅርታህ ተቀበለኝ የሚል የፕሮቴስታንት መዝሙር ለቀቀ” የሚል ነው። እርግጥ ነው ዘማሪው ድምጹ የቴዲን መምሰሉ ብዙዎቹን አደናግሯል። መዝሙሩ በዩቱዩብ እና በሌሎች መንገዶች ከ3 ቀናት በፊት ተለቆ ቴዲ ፕሮቴስታንት ሆነ፤ ሙዚቃም አቆመ በሚባልበት ወቅት እርሱ በካናዳ የሙዚቃ ኮንሰርት አድርጓል። እውን ይህን መዝሙር የዘመረው ቴዲ ነው ወይ? በሚል በርካታ የዘ- ሐበሻ አንባቢዎች በጠየቁን መሰረት ድምጻዊውን ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም። ማናጀሩን ዘካሪያስ ጌታቸውን ግን በስልክ “ሃሎ’ ብለነው ነበር ጉዳዩን ለማጣራት። አቶ ዘካሪያስ ጋር ስንደውል “አሁን ከካናዳ ገብተን ደክሞን ተኝንተናልና ከሁለት ሰዓታት በኋላ ደውልልን” አሉን። በደንብ እንቅልፋቸውን እስከሚጨርሱ ድረስ ጥብቀን ደውለን ስልካችውን ሊያንሱ አልቻሉም። እስካሁንም ቴዲ ይህንን መዝሙር ይዝመረው አይዝመረው ያስተባበለው ነገር የለም። የኛም ሙከራ አልተሳካም። በቴዲ ዌብሳይት፣ በዋናው የፌስቡክ ገጹ ላይም ለማስተባበል አልተሞከረም። በሌሎች መንገዶች ለማጣራት እንደሞከርነው ግን ቴዲ ይህንን መዝሙር እንዳልዘመረው ነ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment