Pages

Jul 31, 2013

ESAT Daliy News Amsterdam July 30 2013 Ethiopia

የሳውዲዋ ልዕልት የመብት ገፈፋ ክስና የኢትዮጵያዊቷ ጉብል አበሳ . . . ነቢዩ ሲራክ (የማለዳ ወግ. . . )


የሳውዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት የ42 አመት እመቤት በምድረ አሜሪካ በቤት ሰራተኛቸው መብት ገፈፋ ተከሰው ለፍርድ ቀርበዋል። ልዕልቷ ኬንያዊዋን የቤት ሰራተኛቸውን በአነስተኛ ክፍያ ከ16 ላላነሱ ሰአታት በመክፈል እና የኬንያዊቷን ሰራተኛ ፖስፖርት ለባለቤቷ ባለመስጠታቸው ተከሰው በምድረ አሜሪካ ለወህኒ ከተዳረጉበት በ5 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ቢፈቱም ዛሬም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ሰምተናን። ይህንን ዜና ሳነብ ያን ሰሞን ” ጋዜጠኛ ነህ አሉ እርዳኝ? ” ብላ ከወደ ደማም በተንቀሳቃሽ ስልኬ እየደወለች የምታነባዋ ኢትዮጵያዊት እህት ፍዳ አስታወስኩ !
princessዛሬ ረፋዱ ላይ ያነጋገርኳት ይህች እህት የሚደርስባት ግፍ ሳያንስ የተሰደደች የምትገፋበትን የወር ደመወዟን ላለፉት በርካታ ወራት እንዳልተሰጣት ገልጻልኛለች ። ዛሬ በጣሙን ከፍቷት እያለቀሰች ከገባችበት ስቃይ እታደጋት ዘንድ ተማጽናኛለች! አቅሙ ኖሮኝ ምንም ልረዳት ባልችልም አበሳዋን ግን እነግራችኋለሁ! ይህች ግፉዕ ደራሽ ያጣችው እህት በኮንትራት ከኢትዮጽያ ከመጣች አመት የደፈነችው በያዝነው ወር መሆኑን ገልጻልኛለች። ከመጣች ቀን አንስቶ ለ16 ላላነሱ ሰአታት እንድትሰራ ስትገደድ ግልምጫ እርግጫና ስድቡን ችላ እንዳሳለፈች እያሳልፈችው ቢሆንም የማትቋቋመው ፈተና ገጥሟታል! የጋብቻ ቃል ኪዳን አስራ ሰርታ ራሷን ለመለወጥ የመጣችው እህት በአሰሪዎቿ ቤተሰቦች ጥቃት ተማራለች! ሚስት በቅናት ተነሳስታ ቁም ስቅሏን የምታሳያት ሳይበቃ የአሰሪዎቿ ሁለት ጎረምሳ ልጆች በየተራ ” እንድፈርሽ !” ብለው የሚያደርሱባትን ትንኮሳ መቋቋም አለመቻሏን እንባ እያዘራች ምርር ብላ እያለቀሰች አጫውታኛለች !
ይህች እህት ወደ ፍትህ አካል የሚያቀርባት ፣ ከገባችበት የመከራ ህይዎት የሚገላግላት የመብት አስከባሪ አካላት አጥታለች ። ኤጀንሲዋን አነጋግራ ” በርረሽ ወጥተሽ እጅሺን ለፖሊስ ስጭ!” ከማለት ያለፈ መፍትሔ አልሰጧትም። አጣብቂኝ የገባችው እህት መፍትሔ ታገኝ ዘንድ የሪያድ ኢንባሲ ሃላፊዎችን ተንቀሳቃሽ ስልክ ሳይቀር ሰጥች ለማረጋጋት የሞከርኩት ቢሳካም ወደ ሃላፊዎች ስልክ ደውላ ከችግሯ ይታደጓት ዘንድ ብትማጸናቸውም ተስፋ ከመስጠት አልፈው የሰሩት ስራ አለመኖሩን እንባ እያዘራች ስታጫውተኝ አሁን አሁን የኢንባሲው ሃላፊዎች ስልክ ስትደውል እንኳ ሊመልሱላት እንዳልቻሉ አጫውታኛለች ። እኔ እስከ ዛሬ ረፋዱ ድረስ ሃላፊዎችን ደውየ ለማነጋገር ያደረግኩት ሙከራ ስልካቸውን ስለማያነሱ ጥረቴ አልተሳካም !
ይህን ግፍ የሳውዲ ህግና መንግስትም አይደግፈውም! ይህ መሰሉን ግፍ በሰራተኛ ላይ መፈጸም ከባድ ቀጣት ቢኖረውም ህግ ፊት የሚያቀርባት ቀርቶ ከገባችበት መቀመቅ የሚያወጣት የሃገሯ ተወካዮችን አጥታ ኑሮን በመከራ እየገፋች መሆኑን ባደረግነው ውይይት ተረድቻለሁ! የሚያሳዝነው ይህች እህት ከዚህ ሁሉ ጭንቀት በኋላ ምን ልትሆን እንደምትችል አላውቅም! ግፉ ከቀጠለ በሚፈጠር ግጭት ምን ሊፈጠርባት እንደሚችል መገመት ይከብዳል! ጎረምሶቹ በጉልበት እንድረፈርሽ ሲሏትም ሆን ሚስት በቅናት ተነሳስታ በምታደርገው የመልስ ጥቃት እንድትጠነቀቅ አበክሬ ከመምከር ባለፈ ምንም ማለት አልቻልኩም! የሳውዲዋ ንግስት ፈጸመችው በተባለው እኛ የአረብ ሃገር ነዋሪዎች መብት ረገጣውን ለምደነው “እዚህ ግባ የማይባል !” የምንለው ጥፋት በነጻዋ አሜሪካ መድር መብት ነክተዋልና ቁም ስቅላቸውን እያዩ ነው ፣ የእኛዋ እህት ደግሞ የግፍ ግፍ እየተፈጠረባት የሃገሯ መንግስ ተወካዮች እንኳ ድረሱልኝ ተብለው ተጠርተው ሊደርሱላት ባለመቻላቸው በሳውዲ ምድር አበሳዋን እያየች ትገኛለች ! የነገን ግን እንጃ. . .
ለሁሉም እኔ ያየሁ የሰማሁትን ተናግሬያለሁ ! ጀሮ ያለው ይስማ . . .!
ቸር ያሰማን 

Jul 30, 2013

አስከፊው ስርዓት ከውስጥም ከውጭም ተወጥሯል።

አበራ ሽፈራዉ /ከጀርመን/

የኢትዬጵያን ሕዝብ ሰብአዊና ቁሳዊ መብቶች በነፆነት ትግል ሰበብ ሕወሐት ለአለፉት 39 ዓመታት ሲረግጥ ቆይቷል።በመግቢያዬ ላይ ሀሳቤን በዚህ መልክ እንዳጠቃልል ያደረገኝ ደግሞ ባለፉት 39 ዓመታት የተከናወኑትን መለስ ብዬ ሳያቸው ከሰመሗቸው፣ካየሗቸውና ካነበብኳቸዉ እንደተረዳሁት በእርግጥም ኢትዬጵያውያን በነዚህ ዓመታት በሕወሐት የለየለትና መሰሪ ተግባር የተነሳ ሲገደሉ፣ሲታሰሩ፣ሰብዓዊ መብታችን ሲረገጥና፤በነፆነት ሥም ብዙዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሕወሐት ጥቅም አስፈፃሚነት ሲሞቱ አልያም የጥቅሙ ተቀናቃኞች በሙሉ ሕይወታቸዉን ሲያጡ ቆይተዋል፤አለፍም ካለ ደግሞ ያፈሩትን ንብረትና ሀብትም ለማጣት ተገደዋል፣ተዘርፈዋል፣
ተነጥቀዋል ፤እምቢ ካሉም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከዚህ አለም በጥይት ተገድለው በሞት ተለይተዋል ።
ከደርግ መንግስት ዉድቀት በኋላም ለ22 ዓመታት የታየው ተጨባጭ ሁኔታ በርግጥም እነዚህ ሕወሐቶች የኢትዬጵያ
ቀንደኛ ጠላቶች መሆናቸውን አለምንም እፍረትና ይሉኝታ ሲያቅዱና ሲተገብሩ ቆይተዋል፤አሁንም ቀጥለዋል፤ተዉ
ያለም የሚጠብቀው እስር፣ግርፋት፣መሰደድና ሞት መሆኑ ለሁሉም ኢትዬጵያውያን ብቻ ሳይሆን ዓለም እያወቀው ያለ
ጒዳይ ሆኗል።
የውጭ ሀገራት የዲኘሎማሲና የውጭ ግንኙነቱም በተወሰኑ የጥቅም ግንኙነት ላይ ብቻ ባተኮረና የኢትዬጵያን ሕዝብ
ጥቅም ወደጐን በተወ መልኩ የተከናወነ ሆኖ ቆይቷል፤በውጭ ሀገራት የዲኘሎማሲ ማህበረሰብ የሠብአዊና የፍትሕ
ጥያቄ ሲቀርብ ግን እርሱ የእኔ ጒዳይ ነው ተዉት እያለ የሰው ልጆችን ከሰብዓዊነት ውጭ በመጨቆን በዚህ ዘመን
የማይጠበቅ የጭቆናና የብዝበዛ ስርዓት በመሆን ቀጥሏል፤በየትኛውም የዓለም ሀገራት የማይፈፀም ግፍ ዛሬ በኢትዬጵያ
ይፈፀማል።
የኢትዬጵያ ሕዝብ የሚያታግለው ስለአጣ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት ያካበተው ርህሩሕነት፣ቸርነት፣ቻይነት፣ይቅር
ባይነት፣በመቻቻል አብሮ በጋራ መኖርንና መስማማትን ይዞ የኖረ ሕዝብ በመሆኑ ዛሬ ሕወሐት/ኢሕሐዴግ እነዚህን
ጠቃሚ የማህበራዊ አኗኗር እሴቶች ለመጣል እየሞከረ ይገኛል፤ይሁንና በሕዝቡ ላይ ከልክ ያለፈ ግፍ በመፈፀሙና
እነዚህን ለአገሪቷም ሆነ ለመሪዎቿ የሚጠቅሙ የማህበራዊ አኗኗር እሴቶችን ከሕዝቡ ላይ ለመሸርሸር በመሞከሩ ዛሬ
ሕወሐት/ኢሕሐዴግን ለመጋፈጥ ብዙዎች ወደ ትግሉ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
ሕወሐት/ኢሕሐዴግ ከለየለት ጥፋቱ ለመመለስ ባለመፈለጉና የሕዝብን ትግስት እንደፈሪ በመቁጠሩ ዛሬ ውጥረቱ
በራሱ በሕወሐት/ኢሕሐዴግ ላይ ነግሷል፤ ወደደም ጠላም ተወጥሯል፤ሕዝቡ በድፍረት በሠላማዊ ሠልፍ ብቻ
ለሕወሐት/ኢሕሐዴግ ጥላቻዉን እየገለፀ ይገኛል፤ይህም በሕወሐት/ኢሕሐዴግ ሠፈር ትልቅ ድንጋጤን በመፍጠሩ
የዉጥረቱን መጠን ለመቀነስ የሚደረጒ ልዩልዩ ስብሰባዎችም ቢሆኑ ሌላ ተጨማሪ ድንጋጤን በገዢዎቻችን ሠፈር
እየፈጠሩ ይገኛሉ።
ሕወሐት/ኢሕሐዴግ የዲሞክራሲና የፍትህ ፅንሰ ሐሳቦች በፍፁም የማይገባዉና በ60ዎቹ የሶሻሊስት አስተሳሰቦች
ተተብትቦ ፤በሰብአዊ ፍጥረት ላይ ባለዉ ንቀት የተነሳና ይኸዉ አሮጌ አስተሳሰቡ ዓለም ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር
አብረዉ ሊጓዙ የሚችሉ ወጣቶችን ለመሰብሰብ ባለመቻሉ፣የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ባለመፈለጉና በዚሁ አሮጌ
አስተሳሰቦችና በጥላቻ ፖለቲካ በተመረዙ ሰዎች እየተመራ በመሆኑ ዛሬ ውጥረቱ በራሱ በድርጅቱ ዉስጥ እየሰፋ
መምጣቱን ከራሱ ከድርጅቱ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
ዛሬ ኢትዬጵያ ግልፅ ባልሆነ መልኩ በተደራጁ ማፍያዎች እንደምትመራ ኢትዬጵያን ብቻ ሳይሆኑ የአለም መሪዎች
ጭምር እያወቁ የመጡ ይመስላል።
በቅርቡ እንኳን በዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ በጁን 20,2013 በኮንግረስ ማን የተከበሩ ስሚዝ ሰብሳቢነት
በኢትዩጵያ ባለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ከመለስ በኋላ የምስክርነት ቃል መስማት በተከናወነበት ወቅት
የተሰነዘሩት አስተየቶችና ለኢትዬጵያ መሪዎች ማነቆ የሚሆኑ ሕጐችን ለማውጣት ቃል መግባታቸዉን ስንመለከት
አሜሪካ ከዚህ ስብሰባ በስተጀርባ በኢትዩጵያ ጉዳይ ላይ ያላትን ዕቅድ ለመተግበር መነሳቷን አልያም የሕወሐት/
ኢሕሐዴግ መሪዎች አካሄድ እንዳላስደሰታቸው ያመለክታል።
ባለፈው ሰሞን የኢትዩጵያ የልማት ድጋፍ ስጪ አገሮች አምባሳደሮች የሰማያዊ ፖርቲ አመራርን ለማነጋገርና አንዳንድ
መረጃ ለመለዋወጥ ማቀዳቸውና መተግበራቸው ከሕወሐት/ኢሕሐዴግ የይስሙላ ዴሞክራሲ ጋር ቅራኔ አንዳላቸውና
በሕዝብ እንቅስቃሴም ዙሪያ የተለየ እይታ ይዘው መቅረባቸውን ፤እንዲሁም ለዘለቄታ ግንኙነታቸውና ጥቅሞቻቸው
ሕዝብ ከጠላው ጋር መስራታቸው በታሪክ ሊያስጠይቃቸው እንደሚችል የገባቸውና ፤እነሱም ለውጥ ፈላጊ
መሆናቸውን ማየት ይቻላል።
አውሮፓ ሕብረት የፖርላማ ተወካዬች በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ለመነጋገር በኢትዩጵያ ያደረጉትን ጉብኝት
ብንመለከት ደግሞ «ኑና እዪ» የተባሉ ይመስል ሕዝቡ ላይ ያለዉን ችግር እራሳቸው በቅርበት ያዩትና እራሳቸውን
ጭምር ያሳዘናቸው መሆኑና ፤የኢትዩጵያ ችግር እምን ደረጃ እንደደረሰ ለመረዳት ችለዋል። እነዚህ የአውሮፓ ህብረት
የፖርላማ አባላት ኢትዩጵያ በምን አይነት ሰዎች እንደምትመራ ለመረዳት እንደቻሉና የተለየ አግራሞት
እንደፈጠረባቸዉ በቀላሉ መረዳት ይቻላል ፤ ከዚህም የተነሳ ይመስላል የህብረቱ አባላት የታሰሩ ጋዜጠኞችና የተቀዋሚ
ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ከስር እነዲለቀቁ ፣ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እንዲከበር ፣የእምነትና የሀይማኖት ተቋማት
መብትና ነፆነት እንዲከበር መግለጫ እስከማዉጣት የተገደዱት።
ይህ ብቻ አይደለም በሃገራችን በሁለቱ ትልልቅ የሐይማኖት ተቋማት አካባቢ ያለዉ « የፍትህ ያለህ » ጥያቄዎች
በኢትዩጵያ መሪዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ባይነት ችግሩ እየተባባሰ ለመፍታት ወደሚቸግር አቅጣጫ እየመጡ መሆኑ የየዕለት
ዜናዎች ሆነዋል።
ሌላው የሕወሐት/ኢሕሐዴግ ባለስልጣናት በመላው ዓለም ከኢትዩጵያን ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር
በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የሚገጥማቸዉ ተቃዉሞ በሌሎች አገሮች ህዝቦች የሌለ በመሆኑ ህወሃቶች ምን ያህል
በአገራቸዉ ዜጎች ዘንድ የተኮንኑ ለመሆናቸዉና አመኔታ የማይጥልባቸው መሆኑ እየታወቀ መምጣቱና በኢትዩጵያ
አስክፊዉ ስርአት መሪዎች አካባቢ ትልቅ ድንገጤን እየፈጠረ መምጣቱ የቅርብ ጊዜያት እዉነታዎች ናቸዉ።
በቅርብ ደግሞ በሶስቱ ዋናዋና በአገር ውስጥ የስላማዊ ትግል አራማጅ ፓርቲዎች ማለትም በሰማያዊ
ፓርቲ፣በአንድነትና በመድረክ ላይ እየደረሰ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ በህዝቡ ተቀባይነት ባይኖርዉም
እንደለመደዉ ለጥቃት መዘጋጀቱንና በነዚህም ፓርቲዎች አባላተ ላይ እየደረሰ ያለዉ እስራትና ማዋከብ በሕወሐት/
ኢሕሐዴግ ፓርቲ ላይ ትልቅ ውጥረትና ድንጋጤ መፍጠሩን ያመለክታል።
ሌላው በተለያዩ ጊዜያት ሕወሐት/ኢሕሐዴግ ለኤርትራ መንግስት የሚያቀርባችዉ በስጦታ የታጀቡ የንታረቅ
ልምምጦች ድንገት ሊነሳ የሚችል ጦርነት በስልጠናቸው ላይ የሚፈጥረዉ ችግር ትልቅ ፍርሃት እንደፈጠረባችውና
ለስልጠናቸዉ ሲሉ የትኛውንም ነገር ለመስጠት መዘጋጀታቸዉን ያሳያል።
እነዚህ በገዢዉ ፓርቲ አካባቢ ያሉት ዉጥረቶች በስለላ መዋቅር ብዛት ፣ በስር ቤቶች ብዛት ፣ በወታደራዊ ትጥቅና
ስልጠና ብዛት መፍትሄ የማያገኙባቸዉ ዋናዋና ምክንያቶች ህዝቡ ክልክ ያለፈ ጭቆና ዉስጥ መዉደቁ ፣ግልጽ ዘር
መድሎ መኖሩ፣ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሙስና መዘፈቃቸዉና የገዢዉ ፓርቲ ንግድ ተቋማት የንግድ
ብዝበዛና ሌሎችም ህዝቡን ስላስመረረዉ ትግሉ የማይቆም ትግል መሆኑን ሁሉም ኢትዮዽያዊ እየተረዳ ያለው ሀቅ
መሆኑም ጭምር ነው።
በአለፉት ዓመታት በዝርፊያ ፣በዘር ማጥፋት ተግባር ፣ ህዝቡን በማሰርና በመግደል፣በዘረኝነት መድሎ፣ በከፍተኛ
ሙስና ተግባርና በሌሎችም ሀገርንና ህዝብን ሊጎዱ በሚችሉ ተግባራት ላይ መሰማራቱ ሊቀጥል እንደማይችል ሁሉም
የተረዳዉ ሀቅ ሆኗል ።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች የስቪክ ማህበራትና ሌሎች የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ አሁን ኢትዩጵያ ካለችበት ሁኔታ
አንፃር ኢትዩጵያን ከለየለት ጭቆና ለማላቀቅ በሚደርገዉ ትግል ይበልጥ መስባስብ ፣መመካከርና የመፍትሄ
አቅጣጫን አስቀምጦ መንቀሳቀስ ጊዜዉ የሚጠይቀዉ ጉዳይ በመሆኑና የሕወሐት/ኢሕሐዴግ ውጥረት በህዝቡና
በሃገሪቷ ላይ ሌላ ተጨማሪ ችግር እንዳይፈጥር አስቀድሞ መከላከል ጠቃሚ ነው እላለሁ።

“ጴጥሮስ ያቺን” ቃል!




abunepetros1ፋሺስቶች ያገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት እንዳይመስላችሁ፡፡ ሸፍታ ማለት ያለ አገሩ መጥቶ የሰውን አገር የሚወር ይህ በመካከላችሁ መጥቶ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእርሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን፡፡”                                                                           አቡነ ጴጥሮስ፡፡
ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን ጀግናው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ በግፍ የተገደሉበት ቀን ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት ለሰማዕትነት ያበቃቸው ዋናው ምክንያት በወቅቱ ለተጠየቁት ቀላል ለሚመስል ጥያቄ “ቃሌን አልክድም” ብለው በመቆማቸው ነበር፡፡
ፋሺስት ኢጣሊያ አገራችንን ወርሮ ሕዝቡን ባስጨነቀ ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ ከአርበኛው ጋር በመቆም የጣሊያንን ሠራዊት በድፍረት ሲቃወሙና አርበኛውንም ሲደግፉ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ከጊዜያት በኋላ በፋሺስቶች ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ጣሊያኖች ራሳቸው በሰየሟቸው ዳኞች ፊት አቡኑን ለፍርድ በማቅረብ ከላይ ሲታይ በጣም ቀላል የሚመስል ጥያቄ ያቀርቡላቸዋል፡፡ የጥያቄው ዓላማ አቡኑን የጣሊያን ተገዢ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን በወቅቱ የነበረውን ሕዝባዊ ዓመጽ ለማብረድ ቢቻልም ደግሞ የብዙሃኑን ድጋፍ ለማግኘት የታሰበበት ነበር፡፡
ስለዚህም የግራዚያኒ ዳኞች አቡነ ጴጥሮስን ለፍርድ ባቀረቧቸው ጊዜ የጠየቋቸው “ሊቀጳጳሱ አቡነ ቄርሎስ እንዲሁም ሌሎች የጣሊያንን የበላይነት ተቀብለዋል፤ እርስዎም እንዲሁ ተቀብለው ሌሎችም እንዲቀበሉ ቢያደርጉ ይሻላል፤ ብቻዎን ማመጽ ምንም አይሰራልዎትም፤ ይህንን ቢያደርጉ ምን ይመስልዎታል …” የሚል እንድምታ ነበረው፡፡ … አቡኑም “ከመሞት መሰንበት” በማለት የቀረበላቸውን ምክር አዘል አስተያየት መቀበል አላቃታቸውም፡፡ ሆኖም ለእምነታቸውና ለሕዝባቸው የገቡትን ቃል ከሚክዱ ሞትን እንደሚመርጡ በድፍረት ለዳኞቹ መለሱላቸው፤ እንዲህም አሉ፤
“አቡነ ቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው፤ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ … ስለ አገሬና ስለ ቤተክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ … እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ፡፡ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ” የሚል ነበር፡፡ (ጳውሎስ ኞኞ “የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት” አ.አ. 1980፤ ገጽ 157)
ረቡዕ ሐምሌ 22 ቀን 1928ዓም (July 29, 1936) አቡነ ጴጥሮስ ከፊት ለፊታቸው የተደገነውን የጣሊያንን መትረየስ ሳይፈሩ ከመገደላቸው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የሚከተለውን በመናገር የመጨረሻ ቃላቸውን ሰጡ፡፡
“ፋሺስቶች ያገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት እንዳይመስላችሁ፡፡ ሽፍታ ማለት ያለ አገሩ መጥቶ የሰውን አገር የሚወር ይህ በመካከላችሁ መጥቶ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእርሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን፡፡” (ዝ.ከ.፤ ገጽ 157)
አቡነ ጴጥሮስ ይህንን ከተናገሩ በኋላ የፋሺስት የጦር መኮንኖችና ጄኔራሎች በተሰበሰቡበት አደባባይ የተሰማው የማያቋርጥ የጥይት እሩምታ ነበር፡፡ በእጃቸው ከያዙት መስቀል በቀር “መሣሪያ” በእጃቸው ያልነበራቸው የሃይማኖት አባት የተናገሩት ቃልና ያደረጉት ቆራጥ ውሳኔ የግራዚያኒን ጦር ወኔ ሰለበው፡፡ ለአቡኑ አንድ ጥይት አልበቃ ብሏቸው የመትረየስ እሩምታ ተኩስ በመልቀቅ በግፍ ረሸኗቸው፡፡
abune_petros removed
የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሲንሳ (ፎቶ Fortune)
ፍርሃት ለአንድ ሰው መትረየስ ያስተኩሳል፤ ለአይጥ ታንክ ያሰልፋል፤ “ለቄጠማ ሰይፍ ያስመዝዛል”፤ የመናገርና የመጻፍ መብቴ ይከበር ለሚል የጸረ አሸባሪ ሕግ ያስወጣል፤ ሰላማዊውን ሰው “አሸባሪ” ያስብላል፡፡ ፍርሃት ያስደነግጣል፤ ያስፈራል፤ ያንቀጠቅጣል፤ ያሸብራል፡፡ ፈሪ የደፋሩ ድፍረት ያስደንቀዋል፤ ድፍረቱን ይመኛል፤ ከዚያ ለመውጣት ግን ራሱ ፍርሃት አንቆ ይይዘዋል፤ ፍርሃት ራሱ ፈሪውን ያስፈራዋል፤ “አልገዛም፤ ቃሌን አልለውጥም” የሚለው የደፋሩ ውሳኔና ቆራጥነት እጅግ ስለሚያሸብረው ራሱ ተሸብሮ ሽብር ይነዛል፤ ያስራል፤ ያሰቃያል፤ ይገድላል፡፡ አልበቃ ሲለው ሃውልት ያስፈርሳል፡፡ ግን አይረካም፤ ምክንያቱም ፍርሃት ሳይሆን ነጻነት ነው ርካታን የሚሰጠው፡፡ ስለዚህ እንደፈራ ኖሮ እንደፈራ ይሞታል፤ ቃሉን የሚጠብቀው ግን በነጻነት ኖሮ በነጻነት ይሞታል፤ ሞቶም ግን በቃሉ ምክንያት ይታወሳል፡፡ የጴጥሮስ ቃል መቼም አይሞትም!!
(ይህ ጽሁፍ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ርዕስ አቶ መክብብ ማሞ ከጻፉት ጦማር ላይ በሰጡን ፈቃድ ለወቅቱ በሚመች መልኩ የቀረበ ነው፤ ለጸሐፊው ምስጋናችን ይድረሳቸው፤ ፎቶ wikimapia)

Jul 29, 2013

የዘመኑ መንፈስ (በእውቀቱ ስዩም)

በእውቀቱ ስዩም

ባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት ይባላል፡፡የብሄርተኝነት ምእመን ከሆንክ የነፍስ አባት ይኖርሀል፣በጭፍን የምትቀበለው ቀኖና ይኖርሀል፣ነገ የምትገባባት የተስፋ ምድር ይኖርሀል፣ከሁሉ በላይ ደግሞ ብርቱ ችግርህን የምትደፈድፍበት የመስዋእት በግ ይኖርሀል፡፡
ሃይማኖቶች ምእመናንን ብቻ ሳይሆን መናፍቃንንም ያፈራሉ፡፡ብሄርተኞች በስሜት የሚነድደውን ምእመን ብቻ ሳይሆን የኔ ቢጤውን መነፍቅም እንደሚያፈሩ አንርሳ፡፡በነገራችን ላይ ሃይማኖትን መካድ ማለት ሃይማኖት የሚያነሳቸውን አብይ ጥያቄዎች መካድ ማለት አይደለም፡፡እንዲሁም፣ ብሄርተኝነትን መካድ ማለት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ህልውና መካድ ማለት አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ፣መናፍቅ መሆን ማለት፣ የብሄርተኛ ነቢያት ሰለ ጭቆና ስለ ነጻነት ብሎም ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀርቡትን አጉል እምነት መጠራጠር ማለት ነው፡፡
ከኢትዮጵያዊነት እንጀምር፡፡
ከዘመናችን የብሔርተኝነት ነቢያት አንዱ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ ከእንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ ስለኢትዮጵያዊነት የሚከተለውን ይላል፡፡
‹‹…ኢትዮጵያን የመሠረታት የሶሰትዮሽ ጦርነት ግብግብ ነው፡፡በአማራው፣በኦሮሞው፣በትግሬው ግብግብ ውስጥ ወደ መጨረሻ ላይ በአመራር ስር የበላይነቱን የያዘው አማራው ነበር፡፡በዚህ የተነሳ አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭት እና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች፡፡…የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት የምንለው የአማራ ባህላዊ ማንነት ነው››
ጃዋር የኢትዮጵያን መሠረት የሦስት ብሄረሰቦች የስልጣን ግብግብ አድርጎ ወስኖታል፡፡ በመጀመርያ፣ ሌሎች ብሄረሰቦች በግብግቡ ተሳትፎ እንዳልነበራቸው አድርጎ ማቅረቡ አንድ
Bewketu Seyoum is a young Ethiopian writer
በእውቀቱ ሥዩም
ጉድለት ነው፡፡ ግን ዋናው ቁምነገር ይሄ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የግጭት ውጤት ብቻ እንደሆነች አድርጎ ማቅረቡ ነው ትልቁ ስሕተት፡፡ ሲጀምር፣ የግብግብ ታሪክ መሠረት ይንዳል እንጂ መሠረት አይገነባም፡፡ እንደኔ ግምት፣የኢትዮጵያ መሠረት የሆነው ብሄረሰቦች ለጋራ ሕልውና ሲሉ የሚያደርጉት የመደጋገፍ ታሪክ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ፣ ታሪክ ከላሾች፣የብሄሮችን የ‹‹ግብግብ››ታሪክ ሞቅ አድርገው፣አኳሽተው ሲጽፉ፣የብሄሮች መደጋገፍ ታሪክን ግን ቸል ይሉታል፡፡ አለያም እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት፣ በጥቂት መስመሮች ብቻ ጨረፍ አድርገው ያልፉታል፡፡ለነገሩ፣ከፋፋይነትን ብቸኛ ያስተዳደር ፈሊጥ አድርጎ የሚቆጥር ሰው በታሪክ ገጾች ውስጥ መመልከት የሚፈልገው ክፍፍልን ብቻ ነው፡፡ታሪክ ግን ብዙ በጎ የትብብር ገጠመኞችን መዝግቧል፡፡ለምሳሌ ጀግናው አጼ ዮሐንስ አራተኛ በበዛሬይቱ ኤርትራ የግብጽን ወራሪ ጦር ድል የነሡት የትግራይ ጀግኖችን ብቻ አሠልፈው አልነበረም፡፡ በዚህ ጦርነት ከግብጽ ጎን ሆኖ፣የተዋጋው አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ዊልያም ዴይ እንደመሠከረው ወልቃይቶች፣ጥልጣል የተባሉ የአፋር ንኡስ ክፍሎች፣የወረኢሉ ኦሮሞዎች ለንጉሰነገስቱ ድጋፍ ለማድረግ ተሸቀዳድመዋል፡፡በራስ ወሌ የሚመሩ የአማራ ወታደሮች ተሳትፈዋል፡፡የጎንደር ቀሳውስት ለጦርነቱ ድጋፍ ለማድረግ አድዋ ገብተዋል፡፡ የጎጃሙ ራስ አዳል የደርሼልሀለሁ አለኝታቸውን አሳይተዋል፡፡ የሸዋው ንጉስ ምኒልክ ሳይቀር በመቶ የሚቆጠሩ በቅሎዎችንና ማበረታቻ ልከዋል፡፡ ዝርዝሩን ማንበብ ለሚፈልግ Muslim Egypt Christian Abyssinia የተባለውን የዚህ ደራሲ ማስታወሻ ገጽ 291-292 ያንብብ፡፡ መጽሐፉን በኢንተርኔት ቤተ-መጻህፍት ውስጥ በብላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡
ከተለያየ መአዘን የመጡ እኒህ ኢትዮጵያውን ከዘመቻው የሚያገኙት ድልን ብቻ አልነበረም፡፡ በዘመቻ ወቅት ባህል ይዋዋሳሉ፣ቃላት ይወራረሳሉ፣ ስንቅ ያዋጣሉ፣ ልምድ ይለዋወጣሉ፡፡ በሂደት ተቃራኒ ከሚመስሉ ልማዶች የነጠረ ኢትዮጵያዊ ባህል እንደ አረቄ ይወጣል፡፡ ይህን በመዋጮ የተገኘ ባህል ‹‹የአማራ ባህል ››ብሎ ማጥበብ የጸና ድጋፍ ያለው አይመስለኝም፡፡
ጃዋር‹‹አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭትና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች›› በማለት ሳይወሰን ‹‹የኢትዮጵያ አገራዊ መለያ ማንነት የምንለው አማራ ብሄራዊ ማንነት ነው›› ሲል ይጨምራል፡፡ ጎበዝ ኧረ በህግ አምላክ!!! የኢትዮጵያ ባህልኮ ካንድ አለት የተጠረበ ሕንጻ አይደለም፡፡ ከብዙ የመዋጮ ጡቦች የተገነባ ነው፡፡ ጃዋር እያንዳንዱን ጡብ ቀርቦ ቢመረምረው እዚህ የደረሰበት እርግጠኝነት ውስጥ የሚደርስ አይመስለኝም፡፡
እስቲ ከደቃቅ ምሳሌ እንጀምር፡፡ ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ስራ ሲሠራ አስቀድሞ የሚመጣው የቡና ስነ-ስራታችን ነው፡፡ አንዲት ጠይም ፣ባለሹርባ ሴት፣ያበሻ ቀሚስ ለብሳ ቡና ስትቀዳ የሚያሳይ ምስል በየቦታው ማየት የተለመደ ነው፡፡ይህ ችክ ያለ ምስል በስነ-ስእል ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ቢዮንሴና ጆን ኬሪ አገራችንን በጎበኙበት ሰአት የቡና ስነስርአት ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ይህ ማለት የውጭ እንግዳ የቡና ስርአታችንን እንደ ኢትዮጵየዊ መለዮ እንዲመዘግብልን ፈልገናል ማለት ነው፡፡ ለዋለልኝ መኮንን እና ለጃዋር መሀመድ ይህ የአማራ ባህል መሆን አለበት፡፡ በመጀመሪያ እይታ ይመስላል፡፡ ጉዱ ዝርዝሩ ላይ ነው፡፡ የሴትዮዋ ሹርባ ከሐማሴን ወይም ከተንቤን ሴቶች ልማድ ጋር ስምም ነው፡፡ ያበሻ ቀሚሱን የሽሮሜዳ ጋሞ የሸመነው ሊሆን ይችላል፡፡ ጀበናው የጂማ ሙስሊም ኦሮሞዎች ያስተዋወቁት ነው፡፡ አቦል ቶና በረካ አረብኛ ወይም የተወላገደ አረብኛ የተገኙ ቃላት ናቸው፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ትንሳኤ በአል በሉባንጃ የሚታጀብ ቡና የማያፈላ ክርስትያን ኢትዮጵያዊ ማግኘት ይከብዳል፡፡ ከጥቂት መቶ አመታት በፊት ግን ቡና የእስላም ልማድ ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ የቡና ትርኢት የሙስሊም አበው በኢትዮጵያ ባህል ላይ የጨመሩት በጎ መዋጮ እድርገን ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ኢትዮጵያ ጊዜ በተባለው አናጢ ከብዙ ጡቦች የተገነባች ናት የምንለው ለዚህ ነው፡፡
ጃዋር አማራው የራሱን ባህል በኦሮሞው ላይ እንደጫነ ሲያምን ተገላቢጦሹ ያለው አይታየውም፡፡ ኦሮሞ በረጅም ዘመን፣በሠፊ ምድር፣ ሰፍሮ የመኖሩን ያክል በጎረቤቶቹና በወደረኞቹ ላይ የባህል ተጽእኖ አላሳደረም ማለት ብርቱ ባህል የለውም ከማለት አይለይም፡፡ ባገራችን ዋና ዋናዎቹ የባህል ቀራጺዎች ጦርነትና ሐይማኖት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ፣ጀግኖችን እና ነገስታትን አባ በዝብዝ አባ ታጠቅ፣ አባ ዳኘው አባ ነጋ ወዘተ እያሉ መሰየም ገናና ኢትዮጵያዊ ባህል መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ብዙዎቻችን የማናውቀው ይህንን ባህል ያስተዋወቁት ለግማሽ ምእተአመት ያክል ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት የየጁ ኦሮሞዎች መሆናቸውን ነው፡፡ ብላቴን ጌታ ማህተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል ቼ በለው በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን እንዲህ በማለት ያረጋግጣሉ-
‹‹ነገስታቱ በ‹‹አባ›› ወይም የእገሌ ባለቤት በሚል ቅጽል ስም መጥራት የጀመሩት የኦሮሞዎችን ወይም የወረሸሆችን ልምድ በመከተል ነው ከ1838 ዓም ወዲህ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡ ወትሮ ግን በተለይም 1474-1713 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ ቅብዓ መንግሥቱ በሚደረግላቸው ሰአት ይወጣላችው የነበረው የግርማ ስም ወይም ስመ መንግስት ‹‹ሰገድ›› የሚል ኃይለቃል በመጨመር እንደነበር ቀጥሎ ያለው ያረጋግጣል፡፡ ወናገድ ሰገድ፣ አጽናፍ ሰገድ፣ አድማስ ሰገድ፣ መለክ ሰገድ፣አድያም ሰገድ ሉል ሰገድ››በማለት ይዘረዝራሉ፡፡
ከጥቅሱ ሦስት ፍሬ ነገሮችን መረዳት ይቻላል፡፡
1- ይህ ባህል ባንድ የዘመን ምዕራፍ ላይ ከኦሮሞ ብሄረሰብ የመነጨ የኢትዮጵያ ባህል ነው፡፡
2- ባህሉ ብርቱ ተጽእኖ ከመፍጠሩ የተነሳ አማራና ትግራይ ነገስታት ለረጅም ዘመን ይጠቀሙበት የነበረውን የስያሜ ዘይቤ ሽሯል፡፡
3- አማራው ታሪክ ጸሀፊ ለባህሉ አስተዋዋቂዎች የባለቤትነት እውቅና ሰጥተዋል፡፡
በሃይማኖት ረገድም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚገጥመን፡፡ ለምሳሌ አቴቴ የሚለውን ቃል ደስታ ተክለወልድ ሲተረጉሙ ‹‹ዛር፣በሴት ስም የምትጠራ፣ ውቃቤ ፣ አማሮች ከኦሮሞዎች የወረሷት ጨሌ የሚያጠልቁላት አቴቴ ጊንቢ ሐራ አቴቴ ዱላ እያሉ እንቀት የሚቀቅሉላት አምልኮ ባእድ፣ትርጓሜ ጠባቂ ማለት ነው››ይላሉ፡፡
‹‹አምልኮ ባእድ ››የሚለውን አሉታዊ ሐረግ፣የክርስትያን አድልኦ ያለበት ፍርድ አድርገን እንለፈው፡፡ ዋናው ፍሬ ነገር፣ የአሮሞው ባህል በአማራው ባህል ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን ማወቃችን ነው፡፡ ይህም አንዱ ብሄረሰብ ሁልጊዜ ጫኝ ፣ ሌላው ብሄረሰብ ሁልጊዜ ተሸካሚ እንደነበረ አድርገው ሊነግሩን የሚፈልጉትን ሰዎች ያስተባብላል፡፡ በሁለቱ ግዙፍ ብሄረሰቦች መካከል የነበረው ግኑኝነት የእኩዮች ልውውጥ ነው፡፡ የባህሎች ውርርስ ነው ማለት እንችላለን፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና፣ የማንኩሳ ዘመዶቼ የሚያስደነግጥ ነገር ሲገጥማቸው ‹‹አቲቲን ወሰድከው›› ይላሉ፡፡ ቀልቤን ገፈፍከው ለማለት ነው፡፡ የኦሮሞ ባህላዊ ተጽእኖ በወለጋ ድንበር ላይ ቆሟል ያለው ማነው?
ስለጉዲፈቻ ባህል ብዙ ሰዉ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ በጦርነት ወቅት ምርኮኞችን ባርያ ማድረግ ወይም መግደል በብዙ ማህበረሰቦች የተለመደ ነው፡፡ በኦሮሞ አበዋዊ ባህል ውስጥ ግን ምርኮኞች በልጅነት ይታቀፋሉ፡፡ ከሌላ ብሄረሰብ ቢመጡም የኦሮሞ ብሄረሰብ የሚያገኘውን መብት ሳይነፈጋቸው ያድጋሉ፡፡ ይህንን ልማድ በአማራው ማህበረሰብ ውስጥም እናገኘዋለን፡፡ ለምሳሌ በጎጃሙ ንጎስ ተክለይማኖትና በወለጋ መሳፍንት መሀል በተደረገው ጦርነት የተማረከው ብላቴና ነገሮ ዋቅጅራን እንደልጅ አሳድገውታል፡፡ ክርስትና አስነስተው ተክለኢየሱስ አሰኝተውታል፡፡ ራሱ በጻፈው ማስታወሻ ‹‹በጠጅና በስጋ አደግሁ›› በማለት የመሳፍንት ልጆች ያገኙት የነበረውን ምቾት ሳይነፈገው ማደጉን ይመሰክራል፡፡ ነገሮ ፣ ከማእረግ ወደ ማእረግ እየወጣ የንጉሱ ጸሐፌ ትዝዛዝ እስከመሆን ደርሷል፡፡ ተመሳሳይ መልኩ በሸዋ ምርኮኛው ቆሴ ዲነግዴ በቤተመንግስት እየተቀማጠለ አድጎ ሐብተጊዎርጊስ በሚል ስመ ክርስትና የኢትዮጵያ የጦር ምኒስትር እስከመሆን ደርሷል፡፡ ሰዎችን በልዩ ቋንቋቸው ምክንያት ባይተዋር ማድረግ ኢትዮጵያዊ ባህል አልነበረም፡፡
እኩዋን ባህላችን አማርኛችን እንኳ የጉራማይሌነታችን ምስክር ነው፡፡ አሁን ኦሮምኛ ያልተነካካ አማርኛ ማግኘት ይቻላል?፡፡ እሰቲ ለናሙና ያክል ‹‹ተወርዋሪ ኮከብ›› ከተባለው የዮሐንስ አድማሱ ምርጥ የአማርኛ ግጥም ውስጥ ጥቂት መስመሮች ልቆንጥር፡፡
1) ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ
ተወርዋሪ ኮከብ በምናውቀው ሰማይ ነበረ በይፋ
2) ሜዳና ተራራ በመሐል ሸለቆ
ጨፌውና መስኩ በኒህ ተደብቆ
3) ሐቀኛ ጠፍቶበት በዋለበት መልቲ
ጌጥ ነው ድንቁርና የገዳዮች ሎቲ
4) ብልጭ ብሎ ጠፋ
ተወርዋሪ ኮከብ የሐሳብ አንጋፋ
በመረጥኳቸው መስመሮች ውስጥ የሚገኙት ‹‹ይፋ፣ ጨፌ፣ መልቲ፣ ሎቲ፣ አንጋፋ፣›› የተባሉት ቃላት ኦሮሚኛ ናቸው፡፡ ካንድ የአማርኛ ግጥም ይህን ያህል ኦሮሚኛ ከተገኘ በሙሉ መዝገበ ቃላት ውስጥ ምን ያህል ሊገኝ እንደሚችል አስቡት፡፡ ይህን ያክል ነው የተዋሀድነው፡፡
የኢትዮጵያ ባህል የተውጣጣ ባህል እንጂ ጃዋር እንደሚለው የአማራ ባህል ብቻ አለመሆኑን በመጠኑም ቢሆን ያሳየሁ ይመስለኛል፡፡ ጃዋርን እዚህ ላይ ላሰናብትና ለማጠናቀቂያ የምትሆን አንዲት አንቀጽ ልጨምር፡፡
ባህልን ማክበር ጥሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በስሜት ሚነድደው የብሄርብሄረሰብ ፖለቲካችን፣ ዜጎች ለባህል ያላቸውን ፍቅር ወደ ጭፍን አምልኮአዊ ፍቅር እያዘቀጠው ነው፡፡
ባባቶቻችንና በእኛ መካከል የባህል ፋይዳ ልዩነት ያለ ይመስለኛል፡፡ አባቶች ባህላቸውን ያገኙት በኑሮ ጣጣ አስገዳጅነት ነው፡፡ ለምሳሌ የኔ አያት ቁምጣ ሱሪ የሚታጠቀው ከሌሎች ብሄረሰቦች ለየት ብሎ ለመታየት አይመሰለኝም፡፡ በቂ አቡጀዲ ስላላገኘ ነው፡፡ ወይም ለስራ እንዲያመቸው ባጭር መታጠቁ ይሆናል፡፡ እኔ ግን የብሄረሰቦች ቀን ሲከበር ቁምጣ ለብሼ ራሴን በማስጎብኘት እንድኮራ ይጠበቅብኛል፡፡ ጉድ እኮ ነው!!! ጋቢ በጥንት ጊዜ የሙቀት ምንጭ ነበር፡፡ ዘንድሮ የኩራት ምንጭ ሊሆን ይቃጣዋል፡፡
የዛሬዎቹ ባህል አምላኪዎች ባህል ሲያስቡ ለውጥን ይረሳሉ፡፡ ባንድ ወቅት የሚያኮራው ያንድ ብሄረሰብ ባህል በሌላው ወቅት ይናቃል፡፡ ባንድ ወቅት የሚያስሸልመው በሌላ ጊዜ ያስቀጣል፡፡ ከጥቂት መቶ አመት በፊት ዝሆን መግደል በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ከበሬታ የሚያጎናጽፍ ተግባር ነበር፡፡ ዝሆን የገደለ ልዩ አምባር ክንዱ ላይ ያጠልቃል፡፡ እስኪ ዛሬ ያባቶቼን ባህል ለማክበር ነው ብለህ ፓርክ ውስጥ አርፎ የተኛውን ዝሆን ግደል፡፡ በአምባር ምትክ ካቴና ይጠልቅልሀል፡፡
የብሄር ብሄረሰቦች አልባሳት የተባለውን የተደጋገመ ግን ያልታሰበበት ቃል ከዚህ አንጻር ቃኙት፡፡ ሲጀምር ፣ዛፍ እንኳ ቅርፊቱን በሚቀያይርበት ዓለም፣ብሄር ብሄረሰቦች በየጊዜው አልባሳታቸውን አይቀያይሩም ወይ?፡፡ የብሄረሰቡ አልባስ ሲባል በየትኛው ዘመን የሚለበሰው ነው? የእንዳለጌታ ከበደ እናት ሲነግሩን፣ ዛሬ በጉራጌ ዘፈን ላይ በቲቪ የምናየው የሴቶች ሻማ ቀሚስ በደርግ ዘመን የተጀመረ ነው፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው ሸማ ነው፡፡ ከሸማው በፊት ደግሞ የቆዳ ቀሚስ ይለበስ ነበር፡፡
ሌላው፣ አንድ ማህበረሰብ አልባሳት በየማእረጉ ልዩ ልዩ ልብሶች ይኖሩታል፡፡ ወታደሩ ያባ ገዳውን ልብስ የሚለብስ አይመስለኝም፡፡ ባሮች ከጌቶች ልብስ ጋር የሚመሳሰል ልብስ እንዲለብሱ አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ በፊውዳል ማህበረሰብ ከላይ አስከታች መልበስ መከናነብ የጨዋነት ምልክት ነው፡፡ ይህንን በሸዋና በትግራይ ብቻ ሳይሆን በቅድመ ምኒልክ ከፋ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ባንጻሩ፣ባሮች በከፊል ተራቁተው መታየት አለባቸው፡፡ ባጠቃላይ በኢትዮጵያ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አለባበስ በበሄረሰብ ላይ ሳይሆን በመደብ ላይ የተመሰረተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህ የብሄር አልባሳት የሚባለው እንደ ማንኛውም ሾላ በድፍን ሐሳብ በጥርጣሬ መታየት አለበት፡፡
ትውልዱ የባህል ፈጣሪ መሆን ሲገባው፣የባህል ሙዚየም ሆኖ ተተክሏል፡፡አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ባንድ ወቅት እንዳለው ‹‹ካባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ፣ እንዳልተፈጠረ ይቆጠራል››
ማሳረጊያ
ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ያቆያት የነገስታቱ ጉልበት ብቻ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ኢትዮጵያ የተሸመነችበትን ውስብስብ ክር ማየት ያልታደሉ ናቸው፡፡ዛሬ ኢትዮጵያን በታትነን ክልላችንን እናድናለን ብለው ባደባባይ ሳያፍሩ የሚናገሩ ሰዎችን የምናይበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡በርግጥ ኢትዮጵያ ማእበል ከበረታባት እንደ ታይታኒክ ትሰጥም ይሆናል፡፡ግን መርከቢቱ ስትሰጥም የመርከቢቱ ሳሎን ብቻውን አይንሳፈፍም፡፡የመርከቢቱ ጓዳ ብቻውን አይተርፍም፡፡ኢትዮጵያ ስትከስም ብሄሮች ተነጥለው ይለመልማሉ ማለት ተፈጥሮ አመሏን እንደ ግትቻ የትም ጥላለች ማለት ነው፡፡

Jul 27, 2013

House of Commons Dr Wondimu Mekonnen

Dr. Wondimu says Semhal Meles deposits $5 billion


የመለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ ሰመሃል መለስ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ 5 ቢሊዮን ዶላር በ2011 ኣስገብታለች። ይህን ያሉት እንግሊዝ አገር እሚገኙት ምሁር እና የመንግስት ተቃዋሚ የሆኑት ዶክተር ወንድሙ መኮንን ናቸው። ዶክተር ወንድሙ የቼኩን ኮፒ አያይዘው ለእንግሊዝ ፓርላማ ሃውስ ኦፍ ኮመንስ አቅርበዋል። ሙሉውን እዚህ ያገኛሉ
Semehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi
Semehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi, “has deposited $5 billion in one of the banks in New York”, said Dr. Wondimu Mekonnen, an academic and opposition figure, during a recent presentation at the House of Commons in the U.K.
Celebrity Net Worth site said Meles Zenawi got a net worth of $3 billion.
Semehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi
Wondimu also showed and distributed to the members of the House who attended his presentation, what he called a “copy of the cheque of the money” she lodged.
Celebrity Net Worth site said Meles Zenawi got a net worth of $3 billion. What a shame! That is wrong guys. Absolutely wrong. I have got a copy of a cheque signed by Semhal Meles Zenawi, the daughter of Meles Zenawi himself, depositing in one of the New York banks $5 billion. I have got and I will give you the copy. Don’t ask me how it came into our possession but that is a fact.
Wondimu further said ”I think, Celebrity Net Worth, got it entirely all wrong. If that was the case, how come, a check in the name of his elder daughter Semhal Meles Zenawi, for US5 billion was deposited into a bank in New York? We will leave the investigation to Department of Fraud and Money Laundering Investigation of the United States”.
In the 10 minute presentation, also posted on Youtube, Wondimu extensively discussed the prevalent corruption in Ethiopia and how the ruling Front is in the core of the corruption scandal titling it “legally corrupt”.

Concluding his speech, Wondimu said
Ethiopians are determined to get rid of these human rights abusers. All we ask the United Kingdom and United States is not stand on our way, by financing and sustaining it to exist. A regime that terrorises its people cannot be an ally against terrorism. I know that, the Ethiopian Regime is playing the Chinese card. This is black-mailing. Just abandon it. Trust us. It will collapse. If you, particularly the British Government, take the right action now, you will remain with friends and trustworthy allies forever – the people of Ethiopia.

Jul 26, 2013

ESAT DC Daily News July 25 2013 ከ40 በላይ የቁጫ ወረዳ ሽማግሌዎች ጉዳያቸውን ለፌደራል መንግስቱ አቀረቡ

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሀምሌ ወር መግቢያ በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩትን  ከ60 በላይ የከተማዋ ታዋቂ ሰዎችን ለማስፈታት እና  ላቀረቡትም ጥያቄ መልስ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ በትናንትናው እለት 40 አገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ጥያቄአቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል።

ምክር ቤቱም ጥያቄውን የማየት ስልጣን ያለው የክልሉ  መንግስት በመሆኑ አጥጋቢ መልስ ሳይሰጣቸው እንደቀረ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ከአገር ሽማግሌዎች መካከል አንዱ ለኢሳት ተናግረዋል
የክልሉ የጸጥታ ዘርፍ ክፍል ሃለፊ የታሰሩት በነጻ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው እንዲታይ ትእዛዝ ቢያስተላልፍም፣ እስረኞቹ ግን አሁንም ፍትህ አጥተው በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ከታሰሩት መካከል ከ70 አመት በላይ እድሜ አላቸው የከተማው ታላላቅ ሰዎች ይገኙበታል።
ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩትን ማሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በቅርቡ በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመዉ ሰቆቃ ሊቆጨን፤ ሊያንገበግበንና ሊያስተባብረን ይገባል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለምአቀፋዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ ዘጠኝ፤ አንቀጽ አስርና አንቀጽ አስራ አንድ የማንኛዉም አገር ዜጋ ያለ አግባብ መታሰር እንደሌለበት፤ በወንጀል ተጠርጥሮ የሚታሰር የማንም አገር ዜጋ በአስቸኳይ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለበትና የፍርድ ቤቱ ሂደት አስከተፈጸመ ድርስ ደግሞ የተጠርጣሪዉ ዜጋ ንጽህና የተረጋገጠ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል። በዚሁ የተመድ አለምአቀፋዊ ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ድንጋጌ ሰነድ ላይ ተመስርቶ የተጻፈዉ የ1994ቱ የኢትዮጵያ ህገመንግሰት አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ ሁለት ደግሞ ማንም ዜጋ ያለ አግባብ መታሰር እንደሌለበት፤ ማንም ዜጋ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዉጭ መታሰር እንደሌለበትና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታሰረ ዜጋም ቢሆን በአስቸኳይ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለበት በግልጽ ይደነግጋል። ኢትዮጵያ ደግሞ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ያረቀቀችና ያጸደቀች አገር ብቻ ሳትሆን ከሃምሳ አንዱ የተመድ መስራች አገሮች ዉስጥ አንዷ ናት።
የ17 አመት የጫካ ዉስጥ ትግል ያካሄደዉና በ1983 ዓም አዲስ አበባ ገብቶ ላለፉት ሃያ ሁለት አመታት የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ጨብጦ የያዘዉ ህወሃት ኢትዮጵያ በፊርማዋ ያፀደቀችዉን የተመድን አለምአቀፋዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌም ሆነ እሱ እራሱ አርቅቆ የጻፈዉን የኢትዮጵያ ህገመንግስት ማክበር ቀርቶ የሰነዶቹ ምንነት በዉል የጋባዉ ድርጅት አይደለም። ህወሀት የተወለደዉና ጥርሱን ነቅሎ ያደገዉ ጫካ ዉስጥ ሲሆን ዛሬም ከ22 አመታት የከተማ ዉስጥ ቆይታዉ በኋላ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር የሚያስተዳድረዉ በዚያዉ ተወልዶ ባደገበትና በተካነዉ የጫካ ዉስጥ ህግ ነዉ። ህወሀትን ይዞት ካደገዉ ባህሉና ከዋና መገለጫ በህሪይዉ ተላቀቅ ማለት ዉኃ መዉቀጥ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም የጥቁር ህዝብ የነጻነት ምልክት የሆነዉን የኢትዮጵያን ህዝብ በጫካ ዉስጥ ህግ መዳኘትና ማስተዳደር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጹም ሊቀበለዉ፤ አለም አቀፉ ህብረተሰብ ደግሞ አፉን ዘግቶ ሊመለከተዉ የማይገባ በህዝብና በአገር ላይ የሚፈጸም ከባድ ወንጀል ነዉ።
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የተቃወመዉን ማሰር፤ ሀሳቡን በንግግር ወይም በጽሁፍ የገለጸዉን ማሰቃየትና የዘረኝነት ፖሊሲዉንና ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማዉን ያወገዘን ዜጋ ሁሉ አስሮ ሰቆቃ መፈጸም ወይም ከአገር እንዲሰደድ ማድረግ ከመደበኛ አገር የመምራት ፖሊሲዎቹ ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ። በወያኔዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወንጀል ተብለዉ ዜጎችን ከሞት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት ድረስ የሚያስቀጡት የፈጠራ ክሶች አፍሪካን ጨምሮ በብዙዎቹ የአለማችን አገሮች ዉስጥ የማይገሰሱ የዜጎች መብቶች ናቸዉ። የሚገርመዉ ወረቀት ላይ የሰፈረዉ የወያኔ ህገመንግስትም ይህንኑ ይደነግጋል፤ ሆኖም ኢትዮጵያ ዉስጥ ሁለት አይነት ዜጎች ያሉ ይመስል በአንድ በኩል ህገመንግስቱ የሚቆምላቸዉ ዜጎች አሉ በሌላ በኩል ደግሞ ህገመንግስቱ የሚቆምባቸዉ ዜጎች አሉ። ዜጎችን በግልሰብ ደረጃ በባህሪያቸዉና በችሎታቸዉ ሳይሆን በቡድን ለይቶ በዘር ማንነታቸዉ የሚመለከተዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ስልጣኔን ይቀናቀኑኛል ብሎ ካሰባቸዉ ከሁለቱ ግዙፍ የአገራችን ብሄረሰቦች ማለትም ከአማራዉና ከኦሮሞዉ ብሔረሰቦች ጋር ለብዙ ግዜ ጥርስ ተናክሶ ቆይቷል። ባለፉት ሁለት አመታት አማራዉን በአማራነቱ ብቻ እያሳደደ መድረሻ ያሳጣዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ በቅርቡ በግፍ ታስረዉ በቁጥጥሩ ስር በሚገኙ 69 የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ይህ ነዉ ተብሎ በሰዉ አንደበት ሲነገር አጅግ በጣም የሚዘገንን ወንጀል ፈጽሞባቸዋል።
መለስ ዜናዊ ከመሞቱ ከአንድ አመት በፊት ከፍርድ ቤት ፈቃድ ዉጭ በግፍ ሰብስቦ ያሰራቸዉና ፍርድ ቤት ሳይቀርቡና ለምን እንደታሰሩ እንኳን ሳያዉቁ ለሁለት አመታት እስር ቤት ዉስጥ የከረሙት 69 የኦሮሞ ተወላጆች ባለፈዉ ሳምንት እስር ቤት ዉስጥ እንዳሉ እጅግ በጣም የሚዘገንን ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል። ባለፈዉ ሀምሌ 6 ቀን ፍርድ ቤት ለመቅረብ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ቀጠሯቸዉ በአራት ወር የተራዘመባቸዉ ስልሳ ዘጠኙ የኦሮሞ ተወላጆች የቀጠሮዉን መራዘም በመቃወም አቤቱታቸዉን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ለማቅረብ ሲሞክሩ የማረሚያ ቤቱ አስተዳዳሪዎች እንዴት እንዲህ ይታሰባል በሚል በቂም በቀል በመነሳት እስረኞቹን በቡድን በቡድን በመከፋፈልና እጅና እግራቸዉን በማሰር ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸዉን ከሆስፒታል ምንጮች የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል። በዕለቱ ድብደባ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ከደረሰባቸዉ እስረኞች ዉስጥ ስምንቱ በድብደባ ብዛት እራሳቸዉን በመሳታቸዉ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ስልሳ ዘጠኙ አስረኞች በሶስት ቡድን ተከፍለዉ ድብደባዉ የተፈጸመባቸዉን ክፍሎች በአይናቸዉ ከተመለከቱ ሰዎች በተገኘዉ መረጃ መሰረት እስረኞቹ የተደበደቡባቸዉ ክፍሎች በደም በመጨቅየታቸዉ አርብ ቀኑን ሙሉ በውሀ ሲታጠቡ አንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ወያኔ ቀድሞዉኑም ቢሆን ያለ አግባብ ባሰራቸዉ ንጹህ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የፈጸመዉ ወንጀል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በየቀኑ የሚፈጽመዉ በደልና ወንጀል አካል በመሆኑ ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የህንን ዘግናኝ ወንጀል በራሱ ላይ እንደተፈጸመ አገራዊ ወንጀል በመቁጠር ከወያኔና ከዘረኛ ስርዐቱ ለመገላገል የሚያደርገዉን ትግል በያለበት እንዲያፋፍም ወገናዊ ጥሪዉን ያስተላልፋል። ኦሮሞዉ ሲጠቃ አማራዉ ካልደረሰለት አማራዉ ሲረገጥ ሶማሌዉ ፤ አፋሩ፤ ሲዳማዉና ወላይታዉ ወዘተ ካልደረሱለት ከፋፋዩ የወያኔ ስርዐት እያንዳንዳችንን ተራ በተራ ማሰቃየቱንና መርገጡን መቀጠሉ የማይቀር ነዉ። ስለዚህ ከወያኔ ጋር በምናደርገዉ የሞት የሽረት ትግል የኛ ኃይል አንድነት የወያኔ ኃይል ደግሞ መነጣጠላችን መሆኑን አዉቀን ይህንን ዘረኛ ስርዐት በቃ ብለን ከጀርባችን ላይ አሽቀንጥረን ለመጣል በህብረት እንነሳ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

በሙስና የተጠረጠሩት የደብረ ጽጌ ቅ/ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ

ሐራ ተዋሕዶ ብሎግ እንደዘገበው፦
በተጭበረበረ ውል ደብሩን ከ3 ሚልዮን ብር በላይ በማሳጣትና ሰነድ በማሸሽ ይጠየቃሉ
ከጥቂት የሙዳይ ምጽዋት ገቢ ምርመራ ብቻ ከ2 ሚልዮን ብር በላይ ጉድለት ተገኝቷል
የአብዛኛዎቹ የደብሩ ሕንጻ ሱቆች የኪራይ ውል በትክክለኛ ሰነድ የተፈጸመ አይደለም
ለማተሚያ ቤት አገልግሎት በተከራየው ክፍል በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የማይታወቅ ሞዴላሞዴል
እንደሚታተምበት ተጠቁሟል
የፕሮቴስታንት ቤተ ጸሎት እንደሚያዘወትሩ የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተዋል
በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ
ዲያቆን ምሩፅ ትኵዕ በተጭበረበረ ሰነድ ከተፈጸመ የኪራይ ውልእና ለሒሳብ
ምርመራ የሚፈለጉ የሙዳይ ምጽዋት የገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎችን
ከማሸሽ የሙስና ወንጀል ጋራ በተያያዘ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው
ተገለጸ፡፡
ዋና ጸሐፊው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ሐምሌ ፲፪
ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ረፋድ ላይ በደብሩ ጽ/ቤት ባሉበት ሲኾን ከዋና ጸሐፊው ጋራ
በተጭበረበረው የኪራይ ሰነድና ውል ለደብሩ የሚገባውን ክፍያ ሳይፈጽሙ
የግል ጥቅማቸውን አካብተዋል የተባሉ ሌሎች ሁለት የሕንጻው የንግድ ቤቶች
ተከራዮችም በተመሳሳይ ቀን መያዛቸው ተመልክቷል፡፡
በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ቀን ጀምሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ
የሚገኙት ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅ እና ሁለቱ ተጠርጣሪዎች፣ ሐምሌ ፲፮ ቀን
፳፻፭ ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ
ምድብ ችሎት መቅረባቸው ተገልጧል፡፡
ዋና ጸሐፊውና የጥቅም ተባባሪዎቻቸው ፈጽመውታል የተባለውን ማጭበርበርና
ምዝበራ የሚያረጋግጡ የሰነድ ማስረጃዎችና የሰው ምስክሮች እንዳሉት ለችሎቱ የገለጸው ፖሊስ፣ በዋና ጸሐፊው ላይ
ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብና የሰው ምስክሮችን ለማዘጋጀት የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችባቸው ክሥ እንደሌለና ከሣሻቸው እንደማይታወቅ በመጥቀስ የፖሊስን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ
በጠበቃቸው በኩል የተቃወሙት ዲያቆን ምሩፅ÷ የሰባት ቤተሰብ አስተዳዳሪ መኾናቸውን፣ የሚጠየቁትን ማስረጃ
ቤተሰቦቻቸው እያቀረቡ መኾኑን፣ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሲውሉ ቢሯቸውን ለመዝጋት እንዳልተፈቀደላቸው እና
ሐምሌ ፳፪ ቀን በደብሩ የቅዱስ ዑራኤል ክብረ በዓል በመኾኑ ሥራዎች እንዳይስተጓጎሉ በመጥቀስ የዋስትና
መብታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸውን በውጭ መከታተል እንዲችሉ እንዲፈቀድላቸው አመልክተዋል፡፡ ዮሐንስ አይዳኝ
እና ዓለም ፍሥሓ የተባሉት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው፣ እነርሱ ውል የያዙበት ሰነድ ከሌሎች ተከራዮች
የተለየ እንዳልኾነ በመጥቀስ የዋስ መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል፡፡
የደብሩን ሕንጻ አራት የንግድ ሱቆች በተጭበረበረ ሰነድ በተፈጸመ የኪራይ ውል በመያዝ ሕገ ወጥ ጥቅም ሲያካብቱ
ቆይተዋል ከተባሉት ሁለት ተጠርጣሪዎች ተፈላጊውን ማስረጃ መሰብሰቡን የገለጸው ፖሊስ÷ ተጠርጣሪዎቹ
ለምርመራ ሥራው ጠቃሚ ማስረጃዎችን በመስጠት አደርገውታል ባለው መተባበር በዋስ ተለቀው በውጭ ኾነው
ጉዳያቸውን መከታተላቸውን እንደማይቃወም፣ ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅ ግን የደብሩ ጽ/ቤት ሓላፊ በመኾናቸው
በተለይ ከሒሳብ ምርመራ እንዳሸሿቸው የሚገመቱት የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎችእስኪገኙ ድረስ
‹‹ማስረጃ ያጠፋሉ፤ ምስክር ያባብላሉ›› በሚል የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል፡፡
ዮሐንስ አይዳኝና ዓለም ፍሥሓ የተባሉት ተከራዮች በብር 50 ሺሕ ዋስ እንዲለቀቁ ያዘዘው ፍ/ቤቱ፣ የዲያቆን ምሩፅን
የዋስትና ማመልከቻ ውድቅ በማድረግና የፖሊስን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጥያቄ በመቀበል ተጠርጣሪው
ለሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም እንዲቀርቡ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡
በቀደመው ዘገባችን እንዳስታውቅነው÷ ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እና ከመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/
ቤት የተውጣጡ ልኡካንበደብሩ የፋይናንስ እንቅስቃሴና አሠራር ላይ ምርመራ እያካሄዱ ባሉበት ኹኔታ የደብሩ
ዋና ጸሐፊ ዲያቆን ምሩፅ ትኵዕ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ከሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለፖሊስ በቀረበ ጥያቄ እንደኾነ
ሲዘገብ፣ ይህም ዲያቆን ምሩፅ በጋብቻ ሰበብ ከአገር ለመውጣት እየተሰናዱ ለመኾናቸው ከመሰማቱ ጋራ ሳይያዝ
እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡
የደብረ ጽጌ ቅዱስ
ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን
ሁለገብ ሕንጸ
ሐራዊ ምንጮች ጉዳዩን
በቅርበት የሚከታተሉ
የደብሩ አካላት ለአብነት
ካቀረቧቸው ማስረጃዎች
እንደተረዱት፣ ዲያቆን
ምሩፅ ከሁለቱ
ተጠርጣሪ ተከራዮች
ጋራ የተጭበረበረ
የኪራይ ውል የፈጸሙት
ነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፫
ዓ.ም እና መስከረም ፲፭
ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ነበር፡፡
በቤት ቁጥር 43
የተለየው የደብሩ ሁለገብ ሕንጻ ክፍል ለአኒሜሽንና ግራፊክስ ቴክኖሎጂ ማሠልጠኛ፣ በቤት ቁጥር 27 እና ቨረንዳ
ቁጥር 4 የተለዩት የሕንጻው ክፍሎች ደግሞ ለዓለም ጠቅላላ ፋይበር ግላስ ሓላ/የተ/የግ/ማ ተከራይተዋል፡፡
ለአራት ዓመት የሚቆየው የኪራይ ውል የተፈጸመበት ሰነድ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በኪራይ ውል አሰጣጥ/ውል
ማራዘሚያ ከሚጠቀምበት ሕጋዊ ሰነድ የተለየና የውል መለያ ቁጥር የሌለው ነው፡፡ በሰነዱ ላይ የሚታየው ክብ
ማኅተም የደብሩ ቢኾንም ቲተሩና ፊርማው ግን ውሉ ከመፈጸሙ በፊት ከአስተዳዳሪነት ሓላፊነታቸው
የተነሡትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የደብሩ አለቃ ነው፡፡
ኹኔታው የበለጠ ሊከፋ÷ እኒህ ሁለት ተከራዮች የደብሩ ሰበካ ጉባኤ የአካባቢውን የኪራይ ዋጋ ባማከለ አኳኋን
በአዲስ መልክ ባስጠናው የኪራይ ተመንና አዲስ የውል ሰነድ መሠረት ውል እንዲያድሱ፣ በዚህ አግባብ የማይዋዋሉ
ከኾነ ደግሞ ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ አጠናቅቀው የንግድ ቤቱን ለደብሩ እንዲያስረክቡ በወቅቱ አስተዳዳሪ በቆሞስ
ፀባቴ መሓሪ ሀብቴ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሷቸው የነበረ መኾኑ ነው፡፡
‹‹ማስጠንቀቂያ በክቡር ቆሞስ ፀባቴ መሓሪ ሀብቴ ውል ደግሞ በአባ ተስፋ ማርያም መከናወኑ ግልጽ ጥፋት መኖሩን
ያሳያል፤›› ይላል የኪራይ ውሎቹን አፈጻጸም ስሕተት ያጠናው የሰበካ ጉባኤው መንፈሳዊ አስተዳደር ያቋቋመው
ኮሚቴ ያቀረበው ሪፖርት፡፡
ከተከራዮች ጋራ የጥቅም ተካፋይ በመኾን የተፈጸሙት የኪራይ ውሎች በሐሰተኛ ሰነድ መስጠታቸው
የተረጋገጠባቸው ዋና ጸሐፊውና የቀድሞው የደብሩ ዋና ተቆጣጣሪ በሰበካ ጉባኤው ፊት ጥፋተኝነታቸውን አምነው
ይቅርታ መጠየቃቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ቤት ብትኾንም፡- የደብሩን ንብረትና
የኪራይ ውሎች እየተከታተሉ ጥቅሙን ማስጠበቅ የሚገባቸው ዋናው ተቆጣጣሪ የተጭበረበረው ውል አዘጋጅና
ምስክር በመኾን በፈጸሙት ጥፋት የአንድ ወር ደመወዛቸውን እንዲቀጡ፣ ሀ/ስብከቱም በዋና ጸሐፊው እና ዋና
ተቆጣጣሪው ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድ፣ ተከራዮቹም በ30 ቀን ገደብ ውላቸው ተቋርጦና የሚፈለግባቸውን
ውዝፍ ዕዳ ከፍለው ሱቆቹን እንዲያስረክቡት ጥር ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም የደብሩ የሕግ ባለሞያ ባለበት በድጋሚ ተወስኖ
እንደነበር ሪፖርቱ ያትታል፡፡
ይኹንና ዋናው ተቆጣጣሪ የተወሰነባቸው ቅጣት ሳይፈጸም ከነበደላቸው ወደ ሌላ ደብር በተመሳሳይ ሓላፊነት
መዛወራቸውን፣ ተከራዮቹም አለመልቀቃቸውን ሪፖርቱ ገልጾ በዚህም ደብሩ በአዲስ መልክ ባስጠናው የኪራይ ተመን
መሠረት ቢያንስ ከሚያዝያ ፳፻፬ ዓ.ም ጀምሮ ማግኘት የሚገባውን ከብር 2,637,603.30 /ብር ሁለት
ሚልዮን ስድስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺሕ ስድስት መቶ ሦስት ከሠላሳ ሳንቲም/ ማጣቱን አስታውቋል፡፡
የቀድሞው የምሥራቅ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በፋይናንስ አሠራርና በሕንጻው ኪራይ ዙሪያ ተፈጸመ
የተባለውን ምዝበራ አጣርተው የሚያቀርቡ ልኡካንን ከአንድም ሁለት ጊዜ ልኮ የነበረ ቢኾንም ለማጣራቱ ሥራ
ግንባር ቀደም ተባባሪ መኾን የነበረባቸው ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅ የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ለማጣራቱ
ሥራ ተባባሪ አልኾኑም፡፡ ዋና ጸሐፊው ለተመደቡት አጣሪዎች እንዲያቀርቡ ከተፈለጉት ማስረጃዎች መካከል፣
ከሐምሌ ፳፻፫ ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኘው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የያዛቸው የ22 ወራት 44 የሙዳይ
ምጽዋት ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎች/ቬርቫሎች/ ይገኙበታል፡፡
ዲያቆን ምሩፅ በሚያቀርቡት ‹‹ሕጋዊ እና በቂ ያልኾነ›› ምክንያት መጥፋታቸው በተገለጹት በእኒህ 44 የገንዘብ
ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎች መሠረት፣ ደብሩ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በመባዕ፣ ስእለት፣ በወርቅና በውጭ ምንዛሪ
የተሰበሰበውን ሳይጨምር ከብር 12 ሚልዮን ብር ያላነሰ የሙዳይ ምጽዋት ገቢ ሊኖረው ይገባ ነበር፡፡
ለሐራዊ ምንጮች የደረሱት መረጃዎች ግን ደብሩ በአሁኑ ወቅት በባንክ ያለው ተቀማጭከብር 5 ሚልዮን
የበለጠ እንዳልኾነ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ከዚሁ ብር 5 ሚልዮን ውስጥም 3.5 ሚልዮን ብሩ ካለፈው የሰበካ ጉባኤ
አስተዳደር የዞረ ነው፡፡ ይህም በወቅቱ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ወደ ደብሩ ካዝና የገባው የሙዳይ ምጽዋት ገቢ ከ1.5
ሚልዮን ያለፈ እንዳልኾነ ያስረዳል፡፡
የሙዳይ ምጽዋቱ ገቢ ከሕንጻው ኪራይ እና ሌሎች የደብሩ የገቢ ምንጮች ጋራ ተደማምሮ በአጥቢያው ቋት መኖር
ከነበረበት ሒሳብ ጋራ ሲነጻጸር በተጨባጭ ያለው መጠን በማነሱ የተደናገጡ የሰበካ ጉባኤ አባላት ተቆርቋሪ
ምእመናንን በማስተባበር ለሀ/ስብከቱ አቤቱታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ አቤቱታቸው በብዙ ጥረት ሠምሮ ከሀ/
ስብከቱ እና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ተውጣጥቶ ወደ ደብሩ የተላከው መርማሪ ልኡክ የማጣራቱን ሥራ እየሠራ
ይገኛል፤ ‹‹ያለቃለ ጉባኤ አንመረመርም›› በሚል ለተጠያቂነት ያስቸገሩት ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅም በሀ/ስብከቱ
ሊቀ ጳጳስ ጥያቄ በሕግ ጥላ ሥር ውለዋል፡፡
ከሁለት ሳምንት በፊት የሒሳብ ምርመራ ሥራቸውን የጀመሩት የሀ/ስብከቱ ልኡካን እስከ አሁን ባደረጉት ማጣራት
ከሚፈለጉት 42 የገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎች 14ቱን አግኝተዋል፤ ከዚህም ተቀባይነት ያገኙት ስድስት ቃለ ጉባኤዎች
ብቻ ሲኾኑ ሌሎቹ የተጭበረበሩና በማስመሰል የተዘጋጁ መኾናቸው ታውቋል፤ መርማሪ ልኡኩ በስድስቱ ቃለ
ጉባኤዎች ላይ ብቻ ተመሥርቶ ባደረገው ማጣራት ከብር 2.7 ሚልዮን በላይ የገቢ ልዩነት/ጉድለት እንደተመዘገበ
መገለጹ የሰበካ ጉባኤውን አባላት አቤቱታ የሚያጠናክር እንደኾነ ተመልክቷል፡፡ የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ከተቆጠረና
አጠቃላይ ገቢው ከታወቀ በኋላ ወደ ሞዴል ፷፬ እንዲሰፍር ተደርጎ በገንዘብ ያዡ አማካይነት በሞዴል ፮ ተጠይቆ
ወደ ባንክ ገቢ እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡
ሞዴላሞዴሎች በድብቅ ይታተሙበታል የሚባለው ማተሚያ ቤት
የደብሩ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ የተጭበረበረውን የኪራይ ውል እንዲያጣራ ያቋቋመው ኮሚቴ ከዘረዘራቸው የውል
አሰጣጥ ችግሮች መካከል÷የውል ጊዜያቸው አልቆ በአዲሱ ውል ያልገቡ፣ ፈጽሞ ውል የሌላቸውና ኪራይ
የማይከፍሉ፣ በውላቸው የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠላቸውና ያልታደሰላቸው፣ ውል ኖሯቸው ክፍያ የማይፈጽሙ /
ውዝፍ ያለባቸው/ እንዳሉ መጠቀሳቸው በመርማሪ ልኡኩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የዋስትና
መብታቸው ለማስጠበቅ ለፍ/ቤቱ ሲናገሩ እንደተደመጡት፣ ከ40 ያላነሱት የሁለገብ ሕንጻው ክፍሎች የኪራይ ውል
ሰነዶች እነርሱ ውል ከያዙበት ሰነድ ጋራ ተመሳሳይ ስለመኾኑ የተናገሩት ቃል ቸል ሊባል አይገባም፡፡
ከሁለቱ ተጠርጣሪ ተከራዮች አንዱ ለማተሚያ ቤት አገልግሎት በተከራዩት ክፍል፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቤተ
ክርስቲያንን ንብረትና ገንዘብ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠርባቸው ሞዴላሞዴሎች በድብቅ እንደሚታተሙባቸው በስፋት
እየተወራ ነው፡፡ የምስጢር ኅትመት የኾኑት እኒህ ሞዴላሞዴሎች ግን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የትንሣኤ ማሳተሚያ
ድርጅት ቁጥጥር በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ብቻ መታተም ያለባቸው ናቸው፡፡ እንደ አንዳንድ ምንጮች ጥቆማ
ከኾነ ይህ ክፍል ‹‹ሞዴል ፴ እንደማያውቀው››ና ጨርሶ ኪራይ እንደማይከፈልበት መነገሩ ያሳስባል፡፡ የሀ/ስብከቱ
ልኡክ የሒሳብ ምርመራ ሥራ ይህን ጉዳይ በሚገባ እንደሚዳስስ ይጠበቃል፡፡
በአጠቃላይ በገቢ
አቅሙና ደረጃው ከሀ/
ስብከቱ ዐበይት አድባራት በቀዳሚነት በሚጠቀሰው በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የፋይናንስ እንቅስቃሴ ላይ የአዲስ አበባ ሀ/ ስብከት የወሰደው ርምጃ  በሀ/ስብከቱና በሌሎች አድባራት ለተንሰራፉት ሙሰኞች/መዝባሪዎች መልእክት
የሚያስተላልፍና እንደ አገባቡም የሕግ ተጠያቂነቱ መቀጠል ያለበት ነው፡፡ በሌላ በኩል ከሚያዝያ
፳፻፫ ዓ.ም ጀምሮ የደብሩ ዋና ጸሐፊ በመኾን ተዛውረው የመጡት ዲያቆን ምሩፅ በአዋሬ አካባቢ የሚገኝና ‹‹ብርሃነ
ኢትዮጵያ›› ተብሎ የሚጠራ የፕሮቴስታንት ቤተ ጸሎት እንደሚያዘወትሩ ለሐራዊ ምንጮች ተያይዞ ከደረሰው
የቪሲዲ ማስረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በቪሲዲው ‹ዲያቆን› ምሩፅ በቤተ ጸሎቱ ከተሰበሰቡት ሰዎች ጋራ ቆመው
‹ሲዘምሩ› ይታያል – ከቤተ ክርስቲያን እየጎረሱ ወደ መናፍቃን መዋጥ፡፡ የዲያቆን ምሩፅን በለምድ የተሸፈነ
ፕሮቴስታንታዊነት የሚያጋልጠው ቪሲዲ የሚሰጠን ፍንጭ አዘውትረን እንደምንለው በቤተ ክህነታችን ውስጥ
ሙስናና ኑፋቄ ያላቸውን ትስስር ነው፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በወባ ከሚሞተው ይልቅ በፖለቲካ ጦስ እና ችግር የሚጎዳው በቁጥር ይልቃል›› ተመስገን ደሳለኝ – [ጋዜጠኛ]

ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት? በተሰኘውና በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ታትሞ በገበያ ላይ በዋለው መፅሀፍ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሰጠው ቃለ – ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ለግንዛቤ
በሚል ለአንባቢዎቹ እንደወረደ አቅርቦታል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
‹‹ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ሳይሆን የፀረ-ኢሕአዴግ ፖለቲካ አቀንቃኝ ነው›› ሲሉ ጋዜጠኛነቱ ላይ ጥያቄ
የሚያቀርቡ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል ከብዙ ፓርቲዎች በተሻለ ገዢው ፓርቲን በብዕሩ የታገለ፣ ጋዜጣ አንባቢው
ኅብረተሰብ ከፖለቲካዊ ፍርሃት እንዲላቀቅ በጽናት የጣረ፣ የቁርጥ ቀን ጋዜጠኛ መሆኑን ምስክርነት የሚሰጡለትም
አሉ። አራት ዓመት ገበያ ላይ በቆየችው ፍትሕ ጋዜጣ፣ ታይተው በጠፉት አዲስ ታይምስ መጽሔትና ልዕልና ጋዜጣ
ላይ ባሰፈራቸው መጣጥፎቹ የመነጋገሪያ ርዕስ የነበረው ተመስገን ለእሱ በተሰጡ ቀጣይዎቹ ገጾች ላይ ከእዚህ መጽሐፍ
አዘጋጆች የቀረቡለትን ሞጋች ጥያቄዎች በመመለስ የ‹‹ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?›› አካል ሆኗል።
በልጅነትህ ምን መሆን ትፈልጋለህ ስትባል ምላሽህ ምን ነበር?
ያደግኩት ፊት በር አካባቢ ነው። ይህ ሰፈር ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ በርካታ የደሀ ሰፈሮች አንደኛው ነው።
ያደግነውም ሆነ የምንጫወተው በቡድን ነበር። ልጅ ሆኜ ሁሌም ማታ ማታ አባቴ ጋዜጣ ገዝቶ ስለሚመጣ ቡና
እየተፈላ ጋዜጣ እንዳነብላቸው ያበረታታኝ ነበር። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል እያለሁ ለቤተሰቡ ጋዜጣ ማንበብ
የዘወትር የማታ ተግባሬ ነበር። ታላቅ ወንድሜ ቢኖርም አባቴ የሚያስነብበኝ እኔን ነበር። ትምህርት ቤትም ክፍል
ውስጥ አነብ ነበር።
አባትህ ማንበብ አይችሉም?
ይችላል። እስከ ዘጠነኛ ክፍል ተምሯል። በኃይለ ሥላሴ ጊዜ እስከ ዘጠነኛ ክፍል መማር ከአሁን ጋር ሲነፃፀር ያው
እንደምታውቁት ነው። [ሳቅ]
ጋዜጣ ማንበቤ፣ ጋዜጠኛ እንድሆን አድርጎኛል እያልክ ነው?
አነብ ነበር እንጂ ጋዜጠኛ እሆናለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። አድጌ መሆን እፈልግ የነበረው መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ
ገብቼ እስከ ጄኔራል ማዕረግ መድረስ ነበር።
የሆንከው የማትፈልገውን ነው ማለት ነው?
ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ጋዜጠኛ በመሆኔ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ። ሁለትም፣ ሦስትም ሰዎች ቢሆኑ እኔ በምሠራው ሥራ
ደስተኛ በመሆናቸው ደስ ይለኛል። በልጅነታቸው የተመኙትን ሲያድጉ የሚሆኑ ጥቂቶች ናቸው። የምንኖረው ደግሞ
የተመኘነውን ሳይሆን የተጻፈልንን ነው። እናንተም ቢሆን ጋዜጠኛ እንሆናለን ብላችሁ ተመኝታችሁ እንደማታውቁ
እገምታለሁ። [ጠያቂዎቹ የፈለጉትን እንደሆኑ ተናግረዋል።]
በልጅነትህ ቶሎ ደምህ የሚሞቅ፣ ከኪስህ ጩቤ የማይጠፋ የፍልውሃ እና የአራት ኪሎ የታወቅክ ተደባዳቢ መሆንህን
ሰምተናል። ትክክል ነን?
[በጣም ሳቀ] አ… ማለት… እእእ… እንትን ነው… ወሬው ትንሽ ግነት አለው ብዬ አስባለሁ። እንደ ማንኛውም ልጅ
ሰፈር ውስጥ ስትውል ‹‹ሰፈሬን አላስደፍርም›› ከሚል እሳቤ ፀብ አይጠፋም። በእኛ ጊዜ ደግሞ የቡድን ፀብ ፋሽን
ነበር። ጩቤ ይዤ የምዞር ተደባዳቢ ግን አልነበርኩም።
ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በሰጠሀቸው ቃለ-ምልልሶች ላይ እንደተናገርከው ወደ ጋዜጠኝነቱ ያመጣህ የሙያው ፍላጎት
ሳይሆን ከ1997 ዓ.ም. በኋላ መንግሥትን የሚሞግቱ ጠንካራ ጋዜጦች አለመኖር አስቆጭቶህ እንደሆነ ገልጸሀል።
አመጣጥህ መንግሥትን ለመቃወም ወይም ተቺ ፖለቲካዊ ሀሳቦችን ለማንሸራሸር ብቻ አይመስልም?
አይመስልም ሳይሆን ነውም፤ ይህ ግምት ሳይሆን እውነታ ነው። ቅድም እንዳልኩት ጋዜጠኛ የሆንኩት ተጽፎልኝ
አይደለም። የጋዜጠኝነት ስሜቱም እንደነበረኝ እርግጠኛ አይደለሁም። ያመጣኝ ጎርፉ ነው። እንደ ማንኛውም ሰው
አገሬን እወዳለሁ። በማንኛውም ቀዳዳ፣ በምችለው መልኩ ለአገሬ የሆነ ነገር ማበርከትን አስብ ነበር። 1997 ዓ.ም.
የተፈጠረው ማዕበል፣ ያመጣበት ጎርፍ ያደናገጠው ኢሕአዴግ በርካታ ጋዜጦችን ከጥቅም ውጪ አደረጋቸው። ከዚያ
በኋላ የተፈጠሩት ጥቂት ጋዜጦች ደጋግሜ እንደምለው አቅሙ ቢኖራቸውም ከኢሕአዴግ ባሕሪ አኳያ ‹‹ዶማን ዶማ፣
አካፋን አካፋ›› ከማለት ይልቅ ቅኔ ለበስ ያደርጉት ነበር። ስለዚህም ይህን የፍርሃት ቆፈን ለመግፈፍ መሞከር አለብኝ
በሚል እንጂ ጋዜጠኛ ለመሆን ስወድቅ ስነሣ ቆይቼ አልመጣሁም። የ97 ጎርፍ ባይመጣ ኖሮ እሆን የነበረው ጋዜጠኛ
ሳይሆን ኦዲተር ነበር፤ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ የውጪ ኦዲተር ነበርኩ።
ፍትሕ ምን ዓይነት ጋዜጣ ነበረች?
የፖለቲካ ጋዜጣ!
አንድ ጋዜጣ፣ ጋዜጣ ለመባል ሊያሟላቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የዓምድ ስብጥር ነው።
በሙሉ ወይም በከፊል ፍትሕ ይህን ይዛ ነበር ብለህ ታስባለህ?
አይ …. እንደሱ ብዬ ላስብ አልችልም። ምክንያቱም የአገራችን ሚዲያ ገና እያደገ ስለሆነ እኛም አንድ ጋዜጣ ሊያሟላ
ያስፈልገዋል ወደሚባለው ደረጃ ለመድረስ ሌት ተቀን እየሠራን ባለንበት ሁኔታ ነው ጋዜጣዋ እንድትቆም የተደረገው
እንጂ እጅግ በጣም ብዙ እንደሚቀረን እናውቃለን።
በአገራችን ያሉ ጋዜጦች አቋማቸው፣ የገጽ ብዛታቸውና የዓምድ መጠናቸው ቢለያይም የሚይዟቸው ነገሮች አሉ።
ለምሣሌ ጤና የአገሪቷ ትልቅ ችግር ነው። በዚያ ዙሪያ የሚደረጉ ወንጀሎች፣ ሙስናዎች፣ በግል ሕክምና ተቋም
የሚካሄዱ ሕጋዊ የሚመስሉ ዘረፋዎች… ብቻ ብዙ ናቸው። የምትሠሩት ለሕዝብ እስከሆነ ድረስ በቀጥታ ከመንግሥት
ጋር የተገናኘው ፖለቲካ ላይ ከማተኮር ባለፈ ሌሎች ችግሮችን ወደ ማጋለጥ ለምን አታተኩሩም?
ኢትዮጵያ ውስጥ በወባ በሽታ ከሚሞተው ይልቅ በፖለቲካ ጦስና ችግር የሚጎዳው በቁጥር ይልቃል። ለዚህ ነው
ከወባው ይልቅ ለፖለቲካው ቅድሚያ የሰጠነው።
[ሳቅ] ፍትሕ ጋዜጣ፣ አዲስ ታይምስ መጽሔት እና ልዕልና ጋዜጣ ላይ ከ12 ሰዎች በላይ የግል ሃሳባቸውን
ይገልጹበታል፤ ከድርጅታችሁ ሠራተኞች ብዛት ይልቅ የዓምደኞቻችሁ ቁጥር ይልቃል። ይሄ ደግሞ የጋዜጣውን
ኤዲቶርያል ሐሳብ ለማንሸራሸር ዕድል አይፈጥርም። ሁሉም አገሪቷ ላይ ያሉ ችግሮችን አስቦ መጥቶ ይተነፍሳል እንጂ
‹‹ሳምንታዊ አጀንዳችን እነዚህ ናቸው›› ተብለው የመሠራት ዕድላቸው አናሳ ነው።
ይሄ የሚታየው ከጋዜጣው አሠራር አኳያ ነው። ኤዲቶሪያላችን የሚያስቀምጠው ነገር አለ። ሃይማኖትን የተመለከቱ
በጣም ስስ የሆኑ ነገሮች አሉ። ከዚያ በተረፈ ጋዜጣው ሙሉ በሙሉ ሐሳብን በነፃነት መግለጽ ላይ የተመሠረተ መሆን
አለበት ስላልን ከርዕስ አንቀጻችን ውጪ ሁላችንም የተለያየ ሐሳብ የምናንፀባርቀው ከዚያ ተነሥተን ነው። ከላይ
እንደገለጽኩት ፍትሕ የተመሠረተችው የጋዜጠኝነት ሙያ ባንገበገባቸው ወይም ባቃጠላቸው ሰዎች ሳይሆን ጭራሽ
ጋዜጠኛ እንሆናለን ብለው ባላሰቡት ነው።
የሆነ ሆኖ ትልልቅ አገራዊ አጀንዳዎች ሲኖሩን ኤዲቶሪያል ቡድናችን ተነጋግሮ በጋራ የሚሠራበት አጋጣሚ አለ። አዲስ
ታይምስ ላይ በ‹‹አባይ ግድብ›› ዙሪያ የሠራነውን መጥቀስ ይቻላል። ልዕልና ላይ ወቅታዊውን የሚዲያ ሁኔታ
በተመለከተ ሠርተናል። ፍትሕ ላይም ደጋግመን ኤዲቶሪያላችን ወስኖ የሠራናቸው አጀንዳዎች አሉ። ስለዚህም ከሞላ
ጎደል የጋዜጣዋን ኤዲቶሪያል ሐሳብ ማንሸራሸር ችለናል ብለን መናገር እንችላለን። አንዱን ሃይማኖት ከሌላው
ሃይማኖት አናጣላም፤ በብሔርም እንደዚሁ ነው። ከእነዚያ ውጪ የሚከለክለን/የማይከለክለን ኤዲቶርያል አቋም
አለን ብለን የምንራቀቅበት ሁኔታ የለም። የጋዜጣው ዋነኛ የማዕዘን ድንጋይ ፍርሃትን መግፈፍ ስለሆነ አሁን
የምንከተለው ስልት ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ።
ይህ ምን ያህል ተሳክቶልናል ብለህ ታስባለህ?
ይሄንንም የምናገረው በግምት ነው እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ የተደረገ ወይም ያካሄድነው ጥናት የለም። ነገር ግን የተሻለ
ነገር አምጥተናል ብዬ አስባለሁ። ሌላ ሰው መጥቶ ‹‹ይሄን … ይሄን ፍትሕ የፈጠረችው አይደለምን?›› እስከሚል
ድረስ ማለት ነው። የመምህራን ተቃውሞ፣ የፀረ- መጅሊስ እንቅስቃሴ የመሳሰሉት ‹‹ስትነጠቅ እምቢ በል›› የሚለው
ፍትሕ የፈጠረችው ለውጥ እና መነቃቃት ነው ብዬ አስባለሁ። በሁለቱም በኩል ፍትሕን እንደሞዴል አንሥተው
በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጽፈው አይተናል።
ስትፅፍ ሐሳብን ገልጸህ መገላገልህን ነው ወይስ የሚያስከትለውን ውጤት (Consequence) ታሰላዋለህ?
ጋዜጠኝነት አርበኝነት አይደለም፤ ጦር ይዘህ ጠላትን ስታይ የምትወረውረውርበት/የምትሰካበት ተግባር አይደለም።
ጋዜጠኛ ከሆንክ የምታነሣቸው ትችቶች እውነትን መሠረት ያደረጉ እና ሕዝብ ሊያውቃቸው ይገባል የምትላቸውን
ነው። መፍትሄ ማግኘት አለባቸው ያልናቸውን ጉዳዮች እናነሣለን። ገዢው ፓርቲ እየሄደበት ያለውን ስሕተት
መጠቆም እና የተሻለ መንገዶችን ማሳየት ላይ አተኩራለሁ። ኢሕአዴግ ብልጥ አምባገነን ነው። የእኛ ጋዜጣ (ፍትሕ)
ታተኩር የነበረው የኢሕአዴግን የብልጠት ሴራዎችን ለሕዝብ በማሳየት እና በማጋለጥ ላይ ነው። የእኔም ጽሑፎች
የሚቃኙት በዚሁ መልኩ ነው።
‹‹ተቃዋሚ›› ከሚባሉት ከአንዳንድ ፓርቲዎች በተሻለ መንግሥትን በጽሑፎችህ ለመገዳደር ትሞክራለህ።
መጣጥፎችህም የጋዜጠኛ ሳይሆን የአርበኛ ወይም የተቃውሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ዓይነት ናቸው።
እንደምታውቁት አደባባያችን ጭር ብሏል። ጠንካራ ተቃዋሚ የለም፤ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት በዘለለ በሰላማዊ
ትግል ውስጥ ያሉ አማራጭ የትግል ስልቶችን አንዱንም አይጠቀሙም። ተቃዋሚዎች ትልቅ ነገር አደረጉ ከተባለ
መግለጫ ማውጣት ነው። መሪያቸው ሲታሰር፣ አቧራ የሚያስነሣና ለትችት የሚዳርግ ፖሊሲ ሲወጣ የእነሱ ሥራ
መግለጫ ማውጣት ነው እንጂ በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ አማራጮችን አይጠቀሙም። ወደ እኛ ስትመጣ
አንድ ጋዜጠኛ ሊያደርጋቸው የሚገቡ አማራጮችን ሁሉ በመጠቀማችን ከፓርቲዎቹ የተሻለ ግምት አስይዞልን
‹‹አርበኛ›› ሊያስብለን ይችላል። ይህን የሚያመጣው የአርበኝነት ሚና መጫወት የነበረባቸው ፓርቲዎች ጭርታን
በመፍጠራቸው እና አንተ የድርሻህን በመወጣትህ ነው። እኔ ግን ከጋዜጠኝነት የዘለለ ሚና አለኝ ብዬ አላስብም።
ፍትሕ ላይ አስፍረኸው የነበረውን ‹‹የፈራ ይመለስ›› የሚለውን ጽሑፍህን ለአብነት ማንሣት ይቻላል። [ጠያቂው
ጋዜጣውን ገልጦ እያሳየው] በሰላማዊ መንገድ ቢሆንም ‹‹መብትህን ለማስከበር ውጣ፣ ተንቀሳቀስ›› የሚል ጥቅል
ሐሳብ አለው። ይሄ የአንድ ጋዜጠኛ ተግባር ሊሆን ይገባዋል?
ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆነ አገር የሌለው ብቻ ነው። አገር የሌለው ደግሞ ማን አለ? ማንም የለም። ጋዜጠኛ ብሆንም
የራሴ የሆነ የፖለቲካ አቋም አለኝ። ጽሑፎቼ ላይ አቋሞቼ ሊንፀባረቁ ይችላሉ። ሥርዓቱ ላይ ያሉ ክፍተቶችን
ለመተቸት ያልከውን ጽሑፍ ጽፌዋለሁ። አምስት ዓመት ያህል የጻፍኩት ግን ‹‹የፈራ ይመለስ›› ብቻ ብዬ አይደለም።
የአንድነት ፓርቲ ልሳን ከነበረችው እና ስትንፋስዋ ከተገታው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ፣ የፖለቲካ አቀንቃኝ (Political
Activist) ስለ መሆንህ ጥያቄ ቀርቦልህ ‹‹አዝማሚያው ሊኖር ይችላል›› ብለህ ነበር። ታዲያ ይህ ከጋዜጠኝነት
መርሕ ጋር በእጅጉ አይጋጭም?
‹‹የፖለቲካ አቀንቃኝ ነህ?›› ያለው ጠያቂው እንጂ እኔ አይደለሁም።
አንተም ግን ‹‹አክቲቪስት ነኝ ባልልም እስከ ዛሬ ፍትሕ ታደርግ የነበረው ከዚህ የዘለለ አይደለም›› ስትል ምላሽ
ሰጥተሀል።
‹‹ጽሑፎቼ ያንን ስያሜ ለማሰጠት አጋድለው ሊሆን ይችላል›› ነው ያልኩት። አንባቢ ከጽሑፍህ ተነሥቶ አርበኛ
ሊልህ፣ ፅንፈኛ ሊልህ፣ የተቃውሞ ፖለቲካ አቀንቃኝና ሌላም ሊልህ ይችላል። እነዚህ ሁሉ ምድቦች ግን እኔ ውስጥ
የሉም። ራሴን የምቆጥረው በአገሩ ላይ የተሻለ ነገር እንዲፈጠር የሚጥር አንድ ጋዜጠኛ አድርጌ ነው።
ስለ ስደተኛ ጋዜጠኞች ያለህ አቋም ምንድን ነው?
ኧኧኧ… [ሳቅ… የቁጥብነት ስሜት እየታየበት] ማንም ሰው ‹‹ለምን የእኔን ፅዋ አልጠጣም?›› ብለህ ልትወቅሰው
አይገባም። የራሱ መከራ የመቀበል አቅም የት ድረስ እንደሆነ ያውቀዋል። እዚያ ደረጃ ሲደርስ ማንም ሰው ይሰደዳል።
ለእኔ ግን መሰደድ የሚወገዝ ተግባር ነው።
ጋዜጠኛ መፍራት/መሸሽ የለበትም እያልክ ነው?
የመፍራት ጉዳይ ብቻ ሆኖ ሳይሆን ችግሩ እኮ ያለ ነገር ነው። እናንተ ጋዜጣ ለመጀመር ፈቃድ ጠይቃችሁ የነበረው
የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ‹‹ልከሰስ ነው›› ብሎ በሸሸበት፣ አዲስ ነገሮች የተሰደዱበት ሁኔታን
እያወቃችሁ ነው። እና ታዲያ ‹‹ይህ ጸበል ለእኛ አይደርሰንም›› ብላችሁ ታስባላችሁ? ታዲያ ልከሰስ ነው፣ ልታሰር
ነውን ምን አመጣው?
ስለዚህ ለተሰደዱ ጋዜጦች ምንም ክሬዲት አትሰጥም ማለት ነው?
[እየሳቀ] ያው ገልጬዋለሁ ‹‹የተሰደዱ ጋዜጠኞች ለፍተዋል፣ ሠርተዋል›› ብዬ ላስተካክለው? [ሳቅ] የእውነት
ሠርተዋል፤ ለፍተዋል። ሲሰደዱ መከራን የመቀበል አቅማችን እዚህ ድረስ ነው ብለው ነው። ባይሰደዱም ያሉት ነገር
(እስር) ሊተገበርባቸው ይችል ነበር። የእኔ ቅሬታ ኢሕአዴግ የለየለት አፋኝ በመሆኑ የጋዜጣ ፈቃድ ሲወስዱ ይህ
እንደሚሆን ስለሚያውቁት ከመሰደድ ይልቅ ፊት ለፊት መጋፈጡ የተሻለ ነው የሚል ነው። የምንፈልገውን ውጤት
የምናመጣው መስዋዕትነት በመክፈል ነው። ጋዜጠኛ የሐሳብ ተዋጊ ነው፤ ምሽጉ ደግሞ ሚዲያው ነው። ስለዚህ
መስዋዕትነቱን እየከፈለ ምሽጉን መልቀቅ አይገባውም። ከአገር የተሰደዱ ጋዜጠኞችን ግን በምንም መልኩ ጥፋተኛ
ልናደርጋቸው አይገባም። የሸሹ ሰዎች ጥፋተኛ ናቸው አለማለቴ እንዲታወቅልኝ ግን እፈልጋለሁ።
አገር ውስጥ ሆነው የሰላ ትችት ለሚሰነዝሩት ክብር ሰጥቶ በተቃራኒው የተሰደዱትን ክሬዲት ማሳነስ ልክ ይሆናል?
አገር ውስጥ ካሉት ከተሻለ በውጪ ወጥተውም አበርክቷቸው ያልተቋረጠ (እየሠሩ ያሉ ጋዜጠኞች) አሉ ብዬ
ስለማስብ ነው። እንዳሉት የሚታሰሩ ከሆነስ ወጥተው የሚችሉትን ማበርከታቸው ተገቢ አይሆንም?
ግልፅ እንዲሆን የምሻው ስደተኛ ጋዜጠኞች ፈሪዎች፣ የማይሸሹ ጋዜጠኞች ደግሞ ደፋሮች ናቸው አላልኩም። ድፍረት
እና ፍርሃትን ከዚህ ውስጥ እናውጣው! ነገር ግን የቁርጠኝነት ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። መከራ የመቀበል ደረጃ
ልዩነት እና የስልት ጉዳይም ነው። እኛ (ፍትሖች) ‹‹እዚሁ ቆስለን፣ እዚሁ ደምተን እንሠራለን›› ስንል፣ ሌሎች
ጋዜጠኞች ደግሞ ‹‹ከመታሰር ከአገር ውጪ ሆኖ አስተዋፅኦ ማድረግ የተሻለ ነው›› ይላሉ። ይሄ የምርጫ ጉዳይ ነው።
በእኔ እምነት ግን ከአገር ውጪ ሆኖ መሥራት የተሻለ አይደለም፤ እዚህ ሆኖ የመጣውን በጸጋ መቀበሉ የለውጡን ቀን
ያቀርበዋል። በተረፈ ትክክሉ ለየራሳችን የሚተው ነው።
የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን አስመልክቶ ‹‹ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ ነገር ይኖራል ጠብቁ›› ብለህ
ፌስቡክ ላይ ገልጸህ ነበር። በሁለተኛው ቀን ማረፋቸው ተነገረ። የኢሕአዴግ የውስጥ ምንጮች አሉህ?
ምንም የማያከራክረው ፍትሕ በአገሪቷ ትልቅ ጋዜጣ ነበረች፤ ዋና መስፈርቱ የኅትመት ቁጥር በመሆኑ። የብዙ ሰዎችን
ትኩረት ስለሚስብ መረጃዎች ወደ እኛ ይመጣሉ። ሥርዓቱ አገርን እየጎዳ እንደሆነ የሚገነዘቡ የሥርዓቱ ወሳኝ
የሆኑም/ያልሆኑም ሰዎች አገርን ከማዳን አኳያ፣ እኛን በማመን አንዳንድ መረጃዎችን ያቀብሉናል።
ጽሑፎችህ ጥልቀት እንደሌላቸው እና ሰዉ ‹‹የእኔ›› ብሎ እንዲያነብ ሰሞነኛ ብሶታዊ ስሜትን ማንፀባረቅ ላይ
እንደምታተኩር የሚተቹህ አሉ።
ሁሉም ጽሑፎቼ ላይ ባይሆንም ይሄ ዓይነት ነገር አለ ብዬ አስባለሁ። ፍርሃትን በመግፈፍ ሕዝብን ወደ አደባባይ
መሰብሰብን ስለማልም፤ [አደባባይ ስል አብዮት አደባባይ አይደለም] ሕገ- ወጥነትን እምቢ እንዲል የማንቃት ባሕሪ
ዋና ዓላማዬ ስለሆነ ሕዝባዊ እና ስሜታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩራለሁ። በአገራችን ላይ የጠፋው ነገር የርዕዮተ ዓለም ዳሰሳ
እና ትንተናዎች ሳይሆን [ይሄን በቂ ምሁራን ብለውታል] ፍርሃትን ማሸነፍ ነው። ለዚህ ደግሞ መፍትሄው አብዮታዊ
ዲሞክራሲን ከሊበራል ዴሞክራሲ ጋር እያነፃፀርክ መተንተን አይደለም። የጠቀስካቸውን ጉዳዮች መዳሰስ ነው። ከዚህ
አኳያ እንዳልከው ጥልቅ ትንታኔ ላይኖረኝ ይችላል። ‹‹የፈራ ይመለስ›› ለማለት ጥልቅ ትንታኔ አያስፈልግህም።
አምስት ዓመት የተጻፉት ጽሑፎች ሁሉ ጥልቀት የሌላቸው ናቸው ብዬ ግን አላስብም።
ከሐሳብ ሙግት ይልቅ ግለሰቦችን ‹‹መጭረፍ›› ላይ ታተኩራለህ። መለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ፣ ፕ/ር አንድሪያስ
እሸቴ፣ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ፋሲል ናሆምና ሌሎችም ላይ ግላዊ መሠረት ያለው ትችት
አቅርበሀል። ችግሮች ያሉት ግለሰቦቹ ጋ ነው ወይስ ተቋማዊ አሠራሩጋ?
ገበያ ላይ ከዋሉ 197 የፍትሕ ኅትመቶች ውስጥ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጽሑፍ ላይ እኔ አለሁ። [በነገራችን ላይ
የፍትሕ የመጀመሪያዎቹ ሕትመቶች ላይ ተመስገን በስሙም ሆነ በብዕር ስም የጋዜጣዋን ከግማሽ በላይ ገጾች ይሸፍን
ነበር።] ከዚያ ውስጥ ግለሰብ ላይ ያተኮርኩት በጣም ጥቂት ጽሑፎች ላይ ነው። ግለሰቦች ላይ የጻፍኩት እኮ አምስት
ጊዜ ብቻ ነው።
ልልህ የፈለግኩት ለውይይት የሚጋብዙ ሓሳቦች (Arguments) ላይ ከማተኮር ይልቅ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር
መለስን ጨምሮ በርካቶች ግላዊ ኹነት ላይ ትንተራሳለህ ነው። [የተቋምም ሆነ የሲስተም ፈጣሪ ሰው መሆኑ እንዳለ
ሆኖ ማለት ነው።]
በርዕዮተ ዓለሞች ላይ፣ በፍትሕ ሥርዓቱና በመሳሰሉት ላይ ለሁለት ዓመት ያህል ሀተታዎች (Features)
ጽፌያለሁ። ስለዚህ ፍትሕ ከመግነኗም በፊት ያለውን ማሰብ/ማየት ያስፈልጋል።
‹‹እስኪ በስብሀት ሙድ እንያዝባቸው፣ ንዋይ ገብረ አምላክ በረሃ እንዳልገቡ አውቃለሁ ምናልባት ውቤ በረሃ ካልገቡ
በስተቀር…›› መሰል ከሞራል እና መገናኛ ብዙኃን ከሚቀርብ ጽሑፍ አንፃር (በተለይ ኮስታራ ጽሑፍ ላይ) ተገቢ
ያልሆኑ ቃላትን ትጠቀማለህና ይህ ሐሳብህን ወደ ስድብ ደረጃ አያወርደውም?
ኧ… ኧ… ኦኬ! ቃላቶቹን የተጠቀምኩት ትንሽ ዘና ለማድረግ ያህል ነው። ለምሳሌ ንዋይ ገብረ አምላክ የኢሕአዴግ
ታጋይ አይደሉም፣ የደርግ ባለሥልጣን ነበሩ። ያንን ይበልጥ ለመግለጽ ‹‹ንዋይ ገብረ አምላክ በረሃ አልገባም፤
ምናልባት ውቤ በረሃ ካልሆነ›› ብያለሁ። ስድብ ነው ብዬ አላስብም ነበር። በዚያ መልኩ ተተርጉሞ ከሆነ በጣም
አዝናለሁ። ምናልባት ቃላቶቹ ወደ ስድብ ወርደው ከሆነ በእጅጉ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ለመሳደብ አልነበረም፤
ከባሕሪም አኳያ የመሳደብ ነገር የለብኝም።
አፍሮጋዳ የሚል መጽሐፍ አንብበሀል? ‹‹ዘመኑ የሚወደው ጥልቀትን አለዝበህ ስሜቱን እንድትነግረው ነው። ቴዲ
አፍሮ እና ይስማዕከ ወርቁ (ዴርቶጋዳ) የተወደዱት ለዚህ ነው›› ይላል፤ ታሪክ ሠሪው ከግልቡ እኩል አይታወቅም
የሚል ይዘት አለው ጽሑፉ። ይሄንን በአንተ ላይ እንዴት ታየዋለህ?
የ‹‹ጥልቀት›› እና የ‹‹ግልብ›› መስፈርቱ ምንድን ነው? የሚለው አንድ ነገር አለ። በእኔ እምነት የቴዲ አፍሮም ሆነ
የዴርቶጋዳ ሥራዎች ግልብ አይደሉም። እነዚህን ‹‹ግልብ›› እንበላቸውና የንዋይ ደበበን ወይም የሰለሞን ተካልኝን
ሥራዎች ‹‹ጥልቀት›› አላቸው እንበል? [የአግራሞት ሳቅ] ጥያቄውን ለመመለስ ግን ምናልባት አገር እና ሕዝብን
የመናቅ ነገር ይመስለኛል። ቴዲ አፍሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድማጮች አሉት እነዚህን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች
አብረህ መተቸት ነው። እነዚህ ኢትዮጵያኖች የወደዱትን ሥራ አናንቀን የተሻለው የትኛው ነው?
ሕዝብ የወደደው ነገር ሁሉ ትክክል ነው ማለት ይቻላል?
እንደ ሕዝብ ስሕተት አለው ብዬ አላስብም። አንድ መጽሐፍ ጥልቅም ይሁን ግልብ ሆኖ ይውጣ፣ ገበያ ላይ ተፅዕኖ
የሚፈጥረው ጋዜጦች ላይ ከሚወጣው ማስታወቂያ ይልቅ ሕዝብ የሚያወራው ነው። የአንተን መጽሐፍ በጣም አሪፍ
ነው እያለ የሚያወራው ከሆነ በቃ አከተመ፤ በጥሩ ሁኔታ ይሸጣል። ‹‹ኡ… የአቤል መጽሐፍ የሞተ ነው›› ብሎ
ሕዝብ የሚያወራ ከሆነ ታቅፈኸው ትቀራለህ። ዴርቶጋዳ በእኔ እምነት ጥሩ መጽሐፍ ነው። ያንን ሁሉ ሰው ማሳማን
የቻለ ሥራ ግልብ ነው? ይሄ ሁሉ ሰው ግልብ እና ጥልቀት መለየት አይችልም? የሚሉ ነገሮች አብሮ ሊታዩ ይገባል
ባይ ነኝ።
ሁሌም መንግሥትን የሚያጠለሹ ጽሑፎችን ብቻ በመጻፍ ትተቻለህ። ይህ ሥርዓት ምንም አልሠራም ብለህ
ታስባለህ?
ሩቅ ሳትሄድ ለምሳሌ አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ፣ ፍትሕ ጥቂት ጊዜ ቢኖሩም የዚህ ሥርዓት ውጤት ናቸው፤
እንደ ድመት ራሱ ወልዶ በላቸው እንጂ። ምንም የምትክደው ነገር አይደለም። በደርግ ጊዜ ‹‹ሠርቶ አደር፣ አዲስ
ዘመን፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ›› እያልክ ትሄዳለህ እንጂ የግል ሚዲያ ሽታውም አልነበረም። በዚህ 22 ዓመታት ጊዜ
ውስጥ የሚመስሉ ነገሮች ብዙ አሉ። ለምሳሌ እናንተ የአውራምባ ታይምስ ባልደረቦች ነበራችሁ። ምንም ይሁን ምን
አውራምባ ታይምስ የተዘጋው በኢሕአዴግ ጫና ነው። ስለዚህ ስለ ፕሬስ ነፃነት የሚኖራችሁ ግንዛቤ እዚያ ላይ
መሠረት ያደረገ ነው። አውራምባ ታይምስ አራት ዓመት ያህል ለመሥራትዋም ቢሆን ምንም ሳያከራክር ክሬዲቱን
መውሰድ ያለበት ኢሕአዴግ ነው። ‹‹ነፃ ፕሬስ›› ብሎ፣ አዋጅ አቋቁሞ፣ ፈቃድ የሰጠው ኢሕአዴግ ነው። ፍትሕ
ተዘግታለች ነገር ግን እስከ ነበረችበት ጊዜ ድረስ ፈቃድ የሰጣት ኢሕአዴግ ነው። እነዚህ እነዚህ በጎ ጎኖች በትልልቅ
ጥፋቶች፣ ውድመቶችና ኪሳራዎች ስለሚጋረዱ ያንን ማየት የማትችልባቸው ሁኔታዎች አሉ።
ፍትሕ ከተዘጋችና አዲስ ታይምስ መጽሔት ላይ ተሻግራችሁ ሥራ ከመጀመራችሁ በፊት 300 ሺህ ብር ወጪ
እንዳወጣህ ፌስቡክ ላይ ጽፈህ አንብበናል። የማስታወቂያ ገቢ አልነበረህምና ጋዜጣ ሸጦ ይሄንን ሁሉ ወጪ መሸፈን
ይቻላል?
ጋዜጣ እየሸጥክ እያለህ ድርጅትን ልታሻሽል ትችላለህ። አቁመህ ግን ይሄን ያህል ትርፍ ወጪ መሸፈን አትችልም።
እንደምታውቁት ባለፈው ዓመት (2004 ዓ.ም.) ግንቦት ወር ላይ ከወጣው መጽሐፌ (የመለስ አምልኮ) ብዙ ብር
አግኝቼበታለሁ። ንገረኝ ካልከኝ መጠኑን ልነግርህ እችላለሁ።
ይቻላል!
እስካሁን ባለው ሁኔታ ከስድስት መቶ ሺህ (600,000) ብር በላይ አግኝቼበታለሁ። ጋዜጣው ቢዘጋም የደጎመኝ ይሄ
ብር ነው። ‹‹300 ሺህ አወጣሁ›› ያልኩት ፍትሕ ማተሚያ ቤት ስትያዝብን 84 ሺህ ብር ከፍለን ነበር።
በተጨማሪም ጋዜጣውን ለማዘጋጀት የከፈልናቸው ወጪዎች ነበሩ። በአዲስ ታይምስ እስክንመለስ ድረስ ማንም
ሠራተኛ ስላልተባረረ ደመወዝ እንከፍል ነበር። 300 ሺህ ብር የደረሱት እነዚህ ወጪዎች ተደማምረው ነው።
መቆየት የቻልነውም በመጽሐፉ ገቢ ነው።
ፍትሕ እንደቆመች በተሻለ ፍጥነት በአዲስ ታይምስ መጽሔት ተመለሳችሁ፣ ለስምንት እትም የሄደችው አዲስ ታይምስ
ስትቆምም አራት እትም በሄደችው ልዕልና›› ለሦስተኛ ጊዜ መጥታችሁ ነበር። በዋነኝት ኦርኬስትራውን የምትመራው
አንተ ነህና ይህ ትጋትህ ለፕሬስ ነፃነት ነው ወይስ ለገንዘብ ነፃነት? [የንግድ ሱቁ የተዘጋበት ሰው ገቢው እንዳይቆም
በፍጥነት ሱቅ አፈላልጎ እንደሚይዘው ሁሉ የእናንተም ወደ ሌላ ፕሬስ የምትጓዙት በፍጥነት ስለሆነ ጥርጣሬ
በመፍጠሩ ነው።]
ትልቁ ስሕተትህ የሚጀምረው [ጠያቂው አቤልን ቆጣ ብሎ እያየ] በኢትዮጵያ የጋዜጣ ንግድ ለገንዘብ ነፃነት ያበቃል
ብለህ መገመትህ ነው። ሐሳቡ የአንተ ካልሆነም ‹‹ሐሳባችሁ ስሕተት ነው›› በልልኝ። በኢትዮጵያ ፕሬስ ውስጥ
ያለህን ይዘህ ገብተህ፣ ባዶ እጅህን ትወጣለህ እንጂ እውነት አትራፊ የምትሆንበት ነው?
ፍትሕ አትራፊ አልነበረችም?
ፍትሕ አትራፊ ነበረች። ለአራት ዓመት ያህል ርምጃዋን ጠብቃ መጓዝ በመቻልዋ በሂደት አትራፊ መሆን ችላለች። ነገር
ግን አዲስ ታይምስን ስምንት ጊዜ ስናሳትም እና ልዕልናን በከፍተኛ (በተጋነነ) ወጪ ንግድ ፈቃድዋን ከግለሰብ ላይ
ስንገዛው ቁማር እንደሆነ እናውቃለን። ከኢሕአዴግ አፋኝ ባሕሪ አንፃር አንድ እትምም ሳንሄድ ሊዘጋት እንደሚችል
እናውቃለን። በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት በኋላ ሥርዓቱ ሆደ ባሻ በመሆኑ ያገኘውን ነገር ሁሉ መርገጥ እና
ማፈን ጀምሯል። ይህ ባለበት ሁኔታ ብዙ ወጪ አውጥቶ፣ በኪሳራ ምክንያት የቆመን ጋዜጣ ከግለሰብ ላይ በተጋነነ
ገንዘብ መግዛቱ ለገንዘብ ያለህን ሐሳብ በፍጹም አያሳይም። ልናተርፍ ይቅርና ያወጣነውን ገንዘብ እንኳን ለማስመለስ
ዋስትና የለንም። የሚገርመው ደግሞ የቃለ-ምልልሱን ተከታይ ክፍል በምታደርጉበት በዚህ ወቅት ልዕልና መቆሟን
የምነግራችሁ የመጀመሪያ ሰዎች ሆናችኋል። ስለዚህ፣ ያወጣነውን ወጪ እንኳን ማስመለስ አልቻልንም ማለት ነው።
እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ‹‹ለገንዘብ ነፃነት ነው የምትሠሩት›› መባል የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ አለማወቅ ይመስለኛል።
ያለንን እያወጣን መቆመራችን፣ ለፕሬስ ነፃነት እንታገላለን ከሚል እሳቤ የመነጨ መሆኑን ያለጥርጥር እናገራለሁ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ራሳቸውን ሳያከብሩ ሌላውን ማክበር፣ ለራሳቸው አድናቆት ሳይኖራቸው
ሌላውን ማድነቅና ጥቂት ግለሰቦች ላይ መንጠልጠል ይፈልጋሉ። መናገር እየቻሉ ‹‹ተመስገን በዚህ ጉዳይ ጻፍበት፣
ተችበት፣ ንገርልኝ›› ሲሉ በጎንዮሽ መልዕክት ማስተላለፍን ይመርጣሉ። ትቀበለዋለህ?
እንዳልኳችሁ እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች እና ሁኔታ አገራችን ላይ በመኖሩ ነው እኔ ጋዜጠኛ የሆንኩት እንጂ ፍላጎቱ
ኖሮኝ ከየትኛውም የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ተመርቄ አይደለም። እንደዚህ ዓይነት ድባብና ፍርሃት ስላለ የግድ
የተወሰንን ሰዎች ሰንደቅ ማንሳት አለብን፤ ሰዎቹ ቢሉም ትክክል ናቸው። የምንሠራው ለእነሱ፣ ለሌላው ሕዝባችንና
ለአገራችን ነው። በዚህ ላይ ደግሞ ለአንድ አገር መስዋዕት ሊሆኑ የሚገቡት ጥቂት ሰዎች ናቸው እንጂ 80 ሚሊዮን
ሕዝብ መስዋዕት ከሆነ ታዲያ ማን ነው በመስዋዕትነት በተገኘ ድል ላይ የሚረማመደው? የአረብ ዓለም አብዮት
በተነሣ ጊዜ ሆን ብለው የመንግሥት የፀጥታ ሠራተኞች ‹‹ይሄ ሕዝብ አንተ ሞተህለት እንዲያልፍለት ነው
የሚፈልገው›› የሚል አፍራሽ ቅስቀሳ ጀምረው ነበር። አገራችን የተሻለች ልትሆን የምትችለው፣ የተወሰንን ሰዎች
መከራውን ከተቀብለን ነው። ፈረንጆቹ ‹‹ነጻ ምሳ የለም›› እንደሚሉት ሕዝቡ በሙሉ መከራና ችግር የሚቀበል እና
የሚቸነከር ከሆነ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራው ያመዝናል። ስለዚህ በጥቂቶች ላይ ቢንጠለጠሉም ተገቢ ነው።
ዱላውን የሚቀበል በሌለበት፣ ለእውነት መታገል እና መስዋዕትነት መክፈል ኪሳራ አይሆንም?
ፍትሕን የመሠረትኩትና እኔ ጋዜጠኛ የሆንኩበት ምክንያት የዚህ ዓይነት ዱላ የሚቀበሉ ዜጎችን ለማፍራት ነው።
እቅዴ ፍርሃትን አሸንፈው እና ከቀንድ አውጣ ዛጎላቸው ውስጥ ወጥተው ዱላ ሊቀበሉ የሚችሉ የፍትሕ ቤተሰቦችን
ማፍራት ነው።
ዱላ ተቀባይ ከሌለስ?
ማፍራት አለብን። እስኪፈራ ድረስ አቅም እስካለ እንሠራለን። እኛ ብናልፍ በርካታ ሰዎች ይቀጥሉታል። ቢያንስ በዚህ
አራት ዓመታት ውስጥ ሁለትና ሦስት ማፍራት እንችላለን ብዬ አስባለሁ። በሂደት እንዲህ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት
እየተባለ ይቀጥላል።
‹‹ዱላ ተቀባዮችን በሂደት እናመጣለን›› ብለሀልና አሁን ዱላ ተቀባዮች ከሌሉ፣ ብዙዎች በፍርሃት ቆፈን ውስጥ
ከባተቱ፣ አንተ ወይም ጥቂቶች ጠንካራ እና ሞጋች ሐሳቦችን መሰንዘራችሁ እናንተን እያገነነ ወደ ጀብደኝነት ደረጃ ከፍ
ያደርጋችኋል እንጂ ተከታዮችን ለማግኘት ያስችላችኋል?
‹‹ተመስገን አርአያዬ ነው›› የሚሉ ሰዎች አሉ። እንዲህ ካሉ እኔ አናጢ፣ ግምበኛ ወይም አስተማሪ አይደለሁም።
አርአያነቴ በጋዜጠኝነት ሥራዬ ነው። ስለዚህ ይህንን አርአያ ይከተላሉ ማለት ነው።
የሠራህባቸው የኅትመት ውጤቶች ከተቋማዊ አሠራር ይልቅ በአንተ ትከሻ ላይ መንጠልጠል ይታይባቸዋል። ጥናት
ባንሠራም፣ ባለን መረጃ መሠረት ከጋዜጣችሁም ጥቅል ፍሬ ነገር ይልቅ አንተ ርዕስ ነህ። በሆነ አጋጣሚ ለአንድ ወይም
ለሁለት ሳምንታት ተመስገን ባይጽፍ የጋዜጣችሁ ሽያጭ አደጋ ውስጥ የሚወድቅ አይመስልህም? [የፍትሕ/አዲስ
ታይምስ/ልዕልና አንባቢያን ማዳመጥ የሚፈልጉት ያንተን ትኩሳት ነው ብዬ ነው።]
ይሄ ሁኔታ ተቋማዊ ሁኔታን ካለመገንባት የሚመጣ ሳይሆን ጋዜጣው ለረዥም ዓመት እንደ አሁኑ ‹‹በድል ጎዳና››
መራመድ ሳይጀምርና በቂ የሠራተኛ ኃይል ሳይኖረው፣ ለረዥም ዓመት በችግርና በብድር [አራጣ እስከ መበደር ደርሼ]
ጋዜጣውን ይዤ የተጓዝኩት እኔ ስለሆንኩ ነው። በ2004 ዓ.ም. ሙሉ ዓመት ግን ጋዜጣው ተቋማዊ ሰውነት ይዞ
እየተጓዘ ነበር። በእኔ እምነት ፍትሕ የተለያዩ ሐሳቦችን ታነሣለች፣ ታስተናግዳለች። አቅም ኖሮንም መክፈል ችለናል።
ይሄ ጋዜጣዋ በድል ጎዳና መጓዝ ከጀመረች በኋላ የመጡ ለውጦች ናቸው። ይሄ ጥያቄ የተነሣው 2004 ዓ.ም. ሳይገባ
በፊት ቢሆን ትክክል ነበር። ከስሜ ውጪ በብዕር ስም ስድስትና ሰባት ጽሑፍ በሳምንት የምጽፍበት ጊዜ ነበር።
‹‹ፍትሕ በድል ጎዳና…›› ካልከው ጋር ልንተራስና፣ በተደጋጋሚ ጊዜ በኅትመት መጠን ቀዳሚ መሆንን እንደ ብቃት
ጥግ ማሳያ ትመለከተዋለህ። ፍትሕ ታብሎይድ ስለሆነች እና ስሜት ቀስቃሽ (Sensational) ጉዳዮችን
ስለምታንፀባርቅ (ስለምታነሣ) እንጂ የጋዜጣዋን በደረጃ ቀዳሚነት እና ጥልቀት፣ ተነባቢነቷን ፈጽሞ አይገልጽም ብልህ
ተሳስቻለሁ?
አዎን! ሙሉ በሙሉ ተሳስተሃል። ምክንያቱም ምንም የማያከራክረው ነገር 2004 ዓ.ም. ሙሉ ፍትሕ በኅትመት
መጠን ቀዳሚ ነበረች። በታብሎይድ ስታይል ብትሄድ፤ አንድ ሳምንት ስሜት ቀስቃሽ ርዕሰ ጉዳይ ስታገኝ ሊሳካልህ፣
ሳታገኝ ደግሞ ላይሳካልህ ነው። ከሳምንት ሳምንት በቋሚነት አንባቢ አፍርተህ መጓዝ ማለት ግን የተሻለ አማራጭ
ይዘህ መጥተሃል ማለት ነው። ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች በጣም ውስን እና ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የሚያያዙ ናቸው።
ለምሳሌ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት ስሜት ቀስቃሽ አጀንዳ ሊሆን ይችላል። ጥሩ አድርገህ ልትሠራበት
ትችላለህ። ሁልጊዜ ግን እሳቸው አይሞቱም። ዓመቱን ሙሉ በቀዳሚነት መጓዛችን የሚያሳየው ቋሚና ታማኝ አንባቢ
ማግኘታችንን ነው። ታማኝ አንባቢ ማግኘት ደግሞ ቀዳሚ መሆን ማለት ነው።
በአገራችን ነፃ ፕሬስ ስሙ ነው እንጂ በአሁን ወቅት አለ ብለህ ታምናለህ?
የለም ብዬ አምናለሁ።
ማሳያህ ምንድን ነው?
ጋዜጠኛው በራሱ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቱ ምን ያህል ተከብሯል? እስክንድር ነጋ፣ መስፍን ነጋሽ፣ ዳዊት
ከበደ፤ አቤል፣ ኤልያስ፣ ውብሸት ወይም አቤ ቶኪቻውን ምን ያህል ነፃ አድርገዋቸዋል? በሚል ነው የሚለካው እንጂ
‹‹ኢሕአዴግ አምባገነን ነው›› ብቻ ብሎ በመጻፍ የጋዜጣህ ነፃነት ወይም ነፃ ጋዜጠኝነት አይለካም። ከዚህ አኳያ
አሁን ወዳሉት የኅትመት ውጤቶች ስትመጣ ‹‹ነፃ ጋዜጣ አለ›› ለማለት ይከብደኛል። [የቃለ ምልልሱን የመጀመሪያ
ክፍል ያደረግነው ፍትሕ ጋዜጣ ከቆመች በኋላ በነሐሴ 2004 ዓ.ም. እንደነበር ልብ ይሏል።] ‹‹ከዚህ በኋላ በዚህ
ርዕስ ላይ እንዳትሠራ›› የሚሉ የጋዜጣ ባለቤቶች ናቸው ያሉት። ዋና አዘጋጆቹም የባልደረቦቻቸውን ሸክም (መስቀል)
መሸከም የማይችሉ ናቸው። በአገሪቱ የፕሬስ ሕግ መሠረት የሚጠየቀው ዋና አዘጋጁ ነው። ፍትሕ ላይ ሁሉም
በሚጽፉት ጽሑፍ አንዳች ነገር እንደማይደርስባቸው ያውቁታል። ስለዚህ እነዚያ ጋዜጠኞች እንዳሻቸው በነፃ ሜዳ ላይ
ይቦርቁበታል ማለት ነው። ማንኛውም ዋና አዘጋጅ ለባልደረቦቹ ያንን ያህል ኃላፊነት መውሰድ አለበት። በዋነኛነት
‹‹ነፃ ጋዜጣ የለም›› የምልህ አፈናው የሚጀምረው ከውስጥ፤ ከባለቤቱና ከዋና አዘጋጁ በመሆኑ ነው። ጋዜጦቹን
በደንብ ተከታተሏቸው፤ የሚጮሁበትና የማይጮሁባቸው ጉዳዮች አሉ። የሚሠሩት ‹‹ይሄ ኢሕአዴግን ያስቆጣዋል/
አያስቆጣውም›› እያሉ በማማረጥ ነው።
ነፃ ሚዲያ አለ ብለህ አታምንም ነገር ግን የኅትመት ውጤቶችህ/ቻችሁ ሲዘጉ እነዚህኑ የፕሬስ አካላት ሁኔታውን ይፋ
እንዲያደርጉ እና አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ትጠይቃለህ። አይጣረስም?
ግልፅ እንዲሆን የምፈልገው ነገር… የሕወሃትን አጀንዳ የሚያራምዱ መገናኛ ብዙኃን እንዳሉ አምናለሁ። ሌሎቹ ግን
ራሳቸው ላይ ቅድመ ቁጥጥር እያደረጉ ራሳቸውን በራሳቸው አዳክመዋል። አንድ ሚዲያ ራሱን ከገደበ፣ ኤዲቶሪያል
ነፃነቱ ላይ ከተደራደረ፣ ‹‹ይዘጉብኛል›› ብሎ ራሱን ከቆጠበ ደካማ ነው። በርግጥ ይህ የሆነው በሥርዓቱ ጫና
ፈጣሪነት ነው። ይህ ማለት ግን ሕወሃት ጠፍጥፎ ሠርቷቸዋል ማለቴ አይደለም። ስሕተታችንን ነግረኸናል በሚል ቅር
ተሰኝተው፣ ከእናንተ ጎን አንቆምም የሚሉ ካሉ የአቶ መለስን አባባል ልዋስና [አቶ መለስ የሚነሡለት በጎ ነገር
ባይኖርም፣ ተረቶቹ ይነሣሉ] ‹‹በሊማሊሞ ማቋረጥ ትችላላችሁ›› እላቸዋለሁ።
እኛ አገር ባለው ሁኔታ አሳታሚዎች ወይም ጋዜጠኞች የጋራ ችግር ሲመጣ፣ የማተሚያ ቤት ዋጋ ሲወደድና መሰል
ችግሮች ሲፈጠሩ ለይምሰል ማኅበር ይቋቋማል፣ ‹‹ኅብረት›› ለመፍጠር ይጥራሉ እንጂ በጥቅሉ አጋርነት
(Solidarity) አለ ለማለት ይቻላል?
እንዳልኳችሁ ምን ያህል ጋዜጦች ነፃ ናቸው? ከ2003 ዓ.ም. በኋላ ገበያ ላይ እስከነበርንብት ጊዜ ድረስ ከአውራምባ
ታይምስ ውጪ ነፃና በራሱ ቆሟል ብዬ የማምነው ሌላ ጋዜጣ አልነበረም። ይሄ የአደባባይ ሃቅ ነው። ሌሎቹ
የየራሳቸው ፍላጎት ያላቸው ናቸው። ራሳቸውን ነፃ ካላወጡ ሰዎች ጋር አብሬ፤ ነፃ ማኅበር መስርቼ እንቀሳቀሳለሁ፣
የፕሬስ ካውንስል መስርቼ እንቀሳቀሳለሁ ብትል አያስኬድም። የፕሬስ ካውንስል በየትኛውም አገር የሚታየው ከሥነ-
ምግባር አኳያ ነው። አፍሪካ ውስጥ ትልቅ የፕሬስ ካውንስል ያለበት የመጀመሪያ አገር ዛምቢያ ትመስለኛለች። እዚያ
ፕሬዝዳቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፍተኛ ባለስልጣናት በአንድ ጋዜጣ የወጣ ዘገባ በደለን፣ ጎዳን፣ ስማችንን አጠፋው
ብለው ሲያስቡ ወደ ፍ/ቤት አይሄዱም። ፕሬስ ካውንስሉ ጋ ሄደው መርምሮ የሥነ-ምግባር ጉድለት ካለበት ቅጣት
ይወስናል። ‹‹ለሦስት ወር አትዘግብ›› ሊል ይችላል። ፕሬስ ካውንስል ይሄንን የሚያደርግ ትልቅ ኃላፊነት የተሸከመ
ድርጅት ነው። ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ካውንስል አደራጅ ሊቀ-መንበር ሚሚ ስብሐቱ ትባላለች።
የምናወራው ስለ ስነ-ምግባር ነው፤ ከግለሰቧ ጋር ምንም ችግር የለብኝም። አንዳንዴ ትራንስፖርት ውስጥ ድምጿን
በሬድዮ ከመስማት ውጪ ስለእሷ ብዙም መረጃ የለኝም። በአካልም ተገናኝተን አናውቅም። ነገር ግን ከአሜሪካ ሬድዮ
ጣቢያ በሥነ-ምግባር ጉድለት የተባረረች፣ በ1998 ዓ.ም. ጋዜጠኞች ሲታሰሩ ‹‹እነዚህ ጋዜጠኞች ሞት ሊፈረድባቸው
ይገባል›› ብላ ስትከራከር የነበረች፣ ጋዜጠኞች በተሰደዱ ቁጥር ‹‹ከሥረው ነው፣ አሸባሪዎች ናቸው›› የምትል፣
ፍትሕ ሲዘጋም ‹‹መንግስት ዘገየ›› ያለች ሴትዮ ሌላውን ጋዜጠኛ እንዴት አድርጋ እንደ ምታስተምር እግዚአብሔር
ነው የሚ ያውቀው።
እንደዚህ አይነት ካውንስልን ስለማታምነው እና ነፃነት እንደሌለው ስለምታውቅ አብረኸው ልትሠራ አትችልም።
በሙሉ መልዕክተኞች ናቸው። በአብዛኛው የመንግሥት አስፈጻሚዎች ናቸው። እነሱ ነፃ መሆን ቢፈልጉም ኢሕአዴግ
በባህሪው ምንም ነገር ነፃ እንዲሆን አይፈልግም። እነዚህ ሠዎች ደግሞ የሥርዓቱ ቀንደኛ አገልጋዮች እና ዋና ተጠሪዎች
ናቸው። ስለዚህ ከእነዚህ ጋር ልትሠራ አትችልም። ይሄ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ አጋርነት እንዳይኖር ያደረገው።
ከመንግሥት ትዕግስት አልባነት አንፃር ብዙዎች ጋዜጣ ለመጀመር ፈቃድ ማግኘት ባልቻሉበት አገር እናንተ ሦስት
‹‹መለያ›› ቀያይራችሁ [አዲስ ታይምስ እና ልዕልና ላይ የቆያችሁት ለአጭር ጊዜም ቢሆን] ስትጫወቱ መታየቱ
ጥርጣሬ የጫረባቸው ወገኖች አሉ። ‹‹የኢሕአዴግ አንድ ክንፍ “ነጻ ሚዲያ አለ” ለማስባል ከጀርባቸው ሆኖ
ያግዛቸዋል›› የሚሉ ድምጾችም ይሰማሉና ምን ትላለህ?
እንዲህ እያሉ የሚያራግቡት ሕሊናቸው በጥቅም የታወሩ ሠዎች ናቸው። ምክንያቱም እኛ በ‹‹አዲስ ታይምስ››ም ሆነ
በ‹‹ልዕልና›› ስንመለስ በሥርዓቱ (በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን) ፈቃድ አይደለም። ሁለቱንም ከባለቤቶቹ
ጋር ተደራድረን ገዝተን ወደ እኛ ከዞረ በኋላ የአንድ ዓመት ፈቃድ ስለነበራቸው በሕጉ መሠረት ለብሮድካስት
ባለስልጣን ያደረግነው ‹‹ዋና አዘጋጅ እና ሥራ አስኪያጅ መቀየራችንን ማስታወቅ እንጂ ማስፈቀድ አይደለም።
በማስታወቅ እና በማስፈቀድ መሀከል ሰፊ ድልድይ አለ።
ስታሳውቁ እናንተ መሆናችሁን ሲረዱ እንዳትንቀሳቀሱ እንዴት አላደረጓችሁም?
ያው ዘጉት እኮ። ከታኅሳስ 30 በኋላ የሥራው ፈቃድ ስለሚቃጠል የአዲስ ታይምስን ፈቃድ ልናድስ ስንል ‹‹ሥም
ያዞራችሁት በሕገ-ወጥ መንገድ ስለሆነ አናድስም›› ብለው ዘጉት። ልዕልናንም የጀመርነው አዲስ ፈቃድ አውጥተን
አይደለም በውልና ማስረጃ ማድረግ የሚገባንን ከጨረስን በኋላ ጋዜጣው ነገ ሊወጣ እንደዛሬ ባለቀ ሰዓት ዋና አዘጋጅ
መቀየራችንን በደብዳቤ አሳወቅን። ሦስት ዕትም ከሄድን በኋላ ብሮድካስት ላይ ያሉ የሥርዓቱ ሎሌዎች ‹‹በሕገ ወጥ
መንገድ ነው ጋዜጣውን ወደ እናንተ ያዞራችሁት›› ብለው ደብዳቤ ጻፉልን። በጣም የሚገርመው ግን ከልዕልና
ባለቤት ጋር ስምምነት ነው እንጂ የፈጸምነው ገና ሥም ወደ እኛ አልዞረም ነበር። አራተኛውን ዕትም ካወጣን በኋላ
በንግድ ሚኒስቴር በኩል ‹‹የንግድ ፈቃዳችሁ ተሰርዟል›› የሚል ደብዳቤ ላኩልን።
እውነታው ይህ ስለሆነ የሚወራውን በማስተባበል ራሴን አላደክምም። እንዲህ ብለው የሚጽፉትም እውነታውን
ያውቁታል። በሦስቱም የኅትመት ውጤቶች ላይ እኛ የምናነሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች የእውነት ሥርዓቱ የሚፈልጋቸው
ወይም ለማስተንፈሻነት የሚጠቀምባቸው ናቸው? አንባቢ ስለሚፈርድ ይህን በማስተባበል ጉልበቴን አላደክምም።
በነገራችን ላይ… ልዕልና ላይ ባሰፈርካቸው መጣጥፎች ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን አንቱታን ትተህ
ሁለተኛ መደብ ነጠላ ስም በመጠቀም ‹‹አንተ›› እያልክ ትገልፃቸው ነበር። ይህ ተገቢ ነው?
ተሳስቼ ሳይሆን ሆን ብዬ ያደረግኩት ነው። ፍትሕ ላይ እያለን ሥርዓቱ በተወሰነ መልኩ ሕግ እንደሚያከብር
የማስመሰል አካሄድ ስለነበረው ለዚያች እውቅና ሰጥቼ ‹‹አንቱ›› እላቸው ነበር። አሁን የተፈጠረው ግን ጭልጥ ያለ
አፈና እና ጉልበተኛነት ስለሆነ እነዚህን ሰዎች አንቱ ማለቱ አግባብ አይደለም ብዬ ስለማስብ ነው። የምታከብረው እኮ
የሚከበርን ሠው ነው። አፋኝ፣ ሕገ ወጥና ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ ጭፍን አምባገነን ስለሆኑ ‹‹አንተ››
ከማለት ባለፈ በአፋጣኝ ከሥልጣናቸው እንዲለቁም እፈልጋለሁ። ‹‹ከሥልጣንህ ውረድ›› እንጂ ‹‹ከሥልጣንዎ
ይውረዱ›› አትልም። ጋዳፊ፣ ሙባረክ ‹‹ውረድ›› ነው የተባሉት።
ጋዜጠኛ ከሥልጣን ሲወርዱ ይዘግባል እንጂ ‹‹ከሥልጣን ውረድ›› ማለት ይገባዋል?
ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ የጋዜጠኝነትን መርህ አክብረህ የምትሠራበት ስላልሆነ ነው። ጋዜጠኝነት መታየት ያለበት
ከአውዱ አኳያ ነው ብዬ አስባለሁ።
ባለፈው ነሐሴ 2004 ዓ.ም. በጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ላይ አንተ፣ አቶ አማረ አረጋዊ [የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ
ባለድርሻ እና ሥራ አስኪያጅ] እና ዶ/ር መሠረት ቸኮል [በዊስኮንሲን ሪቨር ፎልስ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ፕሮፌሰር
የነበሩና በሕዳር/2005 ዓ.ም. በጉበት ካንሰር ሕይወታቸው ያለፈ] ለቃለ ምልልስ ቀርባችሁ ነበር። አቶ አማረ
‹‹ሚዲያ ካውንስሉ የፕሬስ ነፃነትን እየታገለ ነው መጓዝ ያለበት›› ሲሉ አንተ እና ዶ/ር መሠረት ደግሞ ‹‹መጀመሪያ
የፕሬስ ነፃነቱ መቅደም አለበት›› ስትሉ ነበር።
ጋዜጠኞች ናችሁና ብዙ መረጃ አላችሁ። ለረዥም ጊዜያት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ ‹‹አገሪቱ ላይ የቀሩት
ሁለት ነፃ ጋዜጦች ናቸው›› ይሉ ነበር። አውራምባ ታይምስ ከተዘጋች በኋላ ደግሞ አንድ ጋዜጣ ብቻ መቅረቱን
ተናግረዋል። አሁን ደግሞ ‹‹የቀረችው አንድ ጋዜጣ ተዘጋች›› ብለዋል፤ ፍትሕን። ስለዚህ መጀመሪያ የሚያስፈልገው
ሚዲያው ነው። ካውንስሉ የሚያስፈልገው ሚዲያ ሲኖር ነው፤ ሚዲያ ከሌለ ደግሞ ካውንስሉ ምንም አይሠራም።
ሚዲያ የሚኖረው ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሲረጋገጥ በመሆኑ፣ መጀመሪያ መታገል ያለብን ሚዲያ እንዲኖር
ነው። እናንተ የጋዜጣ ፍቃድ ተከልክላችኋል። ታዲያ እንዴት ስለ ካውንስል ይወራል? ማውራት ያለብን [ቆጣ ብሎ]
ፍቃድ ስለ መከልከል/አለመከልከል ነው። ፍቃድ ተከልክለህ ካውንስሉ ምን ያደርግልሀል? ካውንስሉ የሚያያዘው
ከሥራ ጋር ነው፤ ስትሠራ፣ ስታጠፋ ካውንስሉ ያስፈልጋል። ‹‹የዐይንህ ቀለም አላማረኝም›› ተብለህ ፍቃድ
በምትከለከልበት አገር ላይ እንዴት ስለ ካውንስል እናወራለን? ካውንስሉ አያስፈልግም ሳይሆን በሁለተኛ ደረጃ
የሚመጣ ነው። መጀመሪያ ሚዲያው በእግሩ መቆም አለበት። የእነ አማረ አረጋዊና የእነ ሚሚ ስብሐቱ የሚዲያ
ካውንስል ዕቅድ ዝም ብሎ ተራ ቅዠት ነው። ዝም ብለው ድርጅት አቋቋምን ብለው መንፏለል ካልሆነ በስተቀር
ግብዝነት ነው። እኔ አማረ አረጋዊን ከሚሚ ስብሐቱ ጋር አንድ ላይ ደርቤ አላየውም። አማረ የራሱ ፍላጎት
ቢኖረውም፣ የራሱ ኤዲቶሪያል ነፃነት ያለው ጋዜጠኛ አለው። ሚሚን ግን እንደ ጋዜጠኛ ልወስዳት አልችልም፤
ጋዜጠኛ አይደለችምም። ‹‹ጋዜጠኛ አይደለሽም፤ አትችይም›› ተብላ የተባረረች ነች፤ እየሠራች ያለውንም የምታዩት
ነገር ነው። ‹‹ካውንስል መሠረትን›› ብለው በየመድረኩ ለታይታ ለመቅረብ ካልሆነ በስተቀር የትም ሊደርስ
እንደማይችል ከእኔ የበለጠ እነሱ ያውቁታል።
በአንድ ወቅት ላይ ከአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ጋር ፖርላማ ስብሰባ ላይ ተገናኝተን ስናወራ ‹‹ተመስገንን አስረን
አናጀግነውም›› ብለውኝ የነበረ ቢሆንም ለስድስት ቀንም ቢሆን መታሰርህ አልቀረም። ታስረህ ‹‹መጀገን››፣ መሸለም
እንደምትፈልግ፣ ለመታሠር ጉጉ እንደሆንክ የሚደመጡ አስተያየቶች አሉ። ምን መልስ አለህ?
ይሄ እንደ ሰውየው የማሰብ መጠን ይወሰናል። ሲ.ፒ.ጄ. ከሸለማቸው ሰዎች ውስጥ [ከዳዊት ውጪ ያሉት]
አብዛኛዎቹ ታስረው የማያውቁ ናቸው፣ እስር ቤት ሆነው የተሸለሙ በጣም ጥቂቶች ናቸው። በሲ.ፒ.ጄ ለመሸለም
ትልቁ መስፈርቱ በአምባገነን መንግሥት ውስጥ ሳትሸሽ፣ በድፍረት መሥራት ብቻ ነው እንጂ ‹‹መታሰር›› የሚል
ቅድመ ሁኔታ የለውም። ምናልባት መታሰርን እንደ ሁለተኛ መስፈርት ሊወስዱት ይችላሉ። አቶ ሽመልስ ከማል አንተ
[ኤልያስ] በጥያቄህ ላይ እንዳነሳኸው ሁሉ እኔንም ቢሯቸው ጠርተው ‹‹የዳዊት ሽልማት አማልሎህ ከሆነ በጣም
ተሳሰተሃል›› ብለውኛል። ንግግራቸው እና ከንግግራቸው ጀርባ ያለው እውነታ የሚያሳየው ‹‹አሳሪ፣ ጨፍላቂ፣
ደምሳሽ ነን›› የሚል ነው እንጂ አንድ ጋዜጠኛን ጠርተህ ‹‹ለመታሰር ፈልገሃል›› የምትልበት ምንም ምክንያት
የለም። ጋዜጠኛ ካጠፋ መታሰር አለበት። ወንጀል የሠራ ሰው መመከር ሳይሆን መታሰር ነው ያለበት። የአቶ ሽመልስ
ንግግር የሚገልጸው እሳቸው የሚያገለግሉት ሥርዓት ምን ያህል ጨቋኝ፣ አፋኝና የነፃውን ፕሬስ ምኅዳር አጥባቢ
መሆኑን ነው።
… ታስሬ ጀግና መሆን የምፈልገው መቼ ስፈታ ነው? ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ውሰደው! 18 ዓመት ተፈርዶበታል።
ከእነዚህ ዓመታት በኋላ 60 ዓመት ሲሆነው [አሁን አርባ ሁለት ዓመቱ ነው] ወጥቶ የሚያገኘውን የጀግንነት ክብር
ፈልጎ ይታሰራል? ‹‹የማገኘው ክብር አለ›› ብለህ መታሰር፣ ሕይወትህን ልትበላበት የምትችለው ቁማር ነው። አሁን
34 ዓመቴ ነው። 15 ዓመት ቢፈረድብኝ ከእስር ቤት የምወጣው በ50 ዓመቴ ነው። በዚያ 15 ዓመታት ውስጥ
የማጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። የማገኘው ክብር ምንድን ነው? ሁሉንም ነገር ከዜሮና ከአዲስ ነው የምትጀምረው። አቶ
ሽመልስ የሚያንፀባርቁት ነፍሳቸውን ይማረውና የሟች ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ጉልበታም ሐሳብ ነው። ይሄ
የአምባገነኖች ባሕሪ ነው።
(ዘ-ሐበሻ ድረገጽን በየቀኑ በማንበብ ራስዎን በመረጃ ከሰው እኩል ያድርጉ)
በቃሊቲ የስድስት ቀን አክራሞትህ እነማንን አገኘህ? ምንስ ተማርክ?
የታሰርኩት የቀድሞ መንግሥት ባለሥልጣናት ታስረው በነበረበት ‹‹ዞን አራት›› ነው። ዋና ዋናዎቹ ተፈትተዋል፣
ጥቂት ሚኒስትሮች ነበሩ። ለምሳሌ የኢኮኖሚ እና የጡረታ ዋስትና ሚኒስትር የነበሩት ኮሚሽነር ገሠሠ ወልደኪዳን
ነበሩ። ሻለቃ መላኩ ተፈራ [የጎንደር አስተዳዳሪ] እነ ሻምበል በጋሻው አታላይ [የወሎ አስተዳዳሪ] ነበሩ። በርካታ
እስረኞች አሉ። ዶ/ር ተስፋዬ ብሩ፣ የአዋሽ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ለይኩን ነበሩ፤ ብዙ ብትቆይ ከእነሱ ብዙ
ትማራለህ።
የቀድሞ የቤንሻንጉል ጉምዝ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹምን አግኝቻቸዋለሁ። ከእሳቸው የምትማረው
ነገር አለ ብዬ አላስብም፤ ሙስናን ካልተማርክ በስተቀር። [ሳቁ መጣበት] ከብዙዎቹ ጋር አውርተናል፤ ግን ለጊዜው
ባልገልጻቸው ጥሩ ነው። የእስር ዘመንና ሰቆቃቸውን ማበርታት ይሆናል። ብዙዎቹ ከእኔ ጋር የሚያወሩት ስለ ዕድርና
ዕቁብ አይደለም። አስቀድመው የፖለቲካ ጋዜጣ አዘጋጅ መሆኔን ስላወቁ፣ ያወጋነው ፖለቲካዊ ወሬ ስለሆነ፣ ይሄንን
መናገር አስቸጋሪ ነው።
‹‹ለምን እንዳሰሩኝ፣ ለምን እንደፈቱኝ›› አላውቅም ብለህ ከወጣህ በኋላ ጽፈሀል። ዞን 4 ተስማምቶህ ነበር እንዴ?
[ከሳቀ በኋላ] አይደለም። በጥፊ አጩዬህ ይቅርታ መጠየቅ የለብኝም። ሲጀመር መማታት የለብኝም። ዝም ብለህ
ማንንም ሰው እየጠራህ፣ ከቤቱ እየወሰድክ፣ እስር ቤት እየከተትክ፣ የምትፈታበት ሁኔታ መቆም አለበት። መብቴ
ሊከበር ይገባል። የተለቀቅኩት ስድስት ቀን ያለአግባብ ታስረሀል ተብዬ አይደል? ለዚህ ካሳ ማግኘት ነበረብኝ፤
መንግሥትም በይፋ ይቅርታ ሊጠይቀኝ ይገባ ነበር።
ዳግመኛ ወደ እስር ቤት የምትመለስ አይመስልህም? [ይህ ጥያቄ የቀረበለት በድጋሚ በዚህ ጉዳይ ከመከሰሱ በፊት
ነበር።]
በዚህ ጉዳይ ተመልሼ እገባለሁ ብዬ አላስብም።
በድህረ መለስ ኢትዮጵያ ምን ገጽታ የሚኖራት ይመስልሀል? ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት ማን እና ምንድን ነው ብለህስ
ታስባለህ?
ከፋፍለን እንየው፣ መጀመሪያ ከእውነታው እንነሣ። ስገምት ‹‹ድህረ-መለስ›› አስቸጋሪ ሁኔታ ይኖረዋል ብዬ
አስባለሁ። አራቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሥልጣን ሲይዙ ባልተመጣጠነ ጉልበት ነው። ሕወሃት አስኳል ነው። ወሳኝ
ወሳኝ ነገሮችን ይዟል። የመሪነት ባሕሪ አለው። ልክ በደርግ ጊዜ ስትመጣ መፈክሩ ሁሉ ‹‹በጓድ መንግሥቱ
ኃይለማርያም ማዕከላዊነቱ ኢሠፓን እንመሠርታለን…›› ነበር የሚሉት። ኢሕአዴግም ሲመሠረት በሕወሃት
ማዕከላዊነት ነው። ከ1993 ከሕወሃት መሰንጠቅ በኋላ ግለሰብ (አቶ መለስ) ማዕከላዊ ሆነዋል። ይሄ ሁኔታ ጉዳቱን
በግልጽ ያመጣዋል። በተለይ ደግሞ አማራንና ኦሮሞን የሚወክሉ ሁለት ድርጅቶች አሉ። ኦሕዴድ እና ብአዴን
ወክለውት ወደ ግንባር የመጡት የሕዝብ ቁጥር አለ። ከፍተኛ ሥልጣን ይዞ የነበረው ሕወሃት ይዞ የመጣው የሕዝብ
ቁጥር አለው። ምናልባት አሁን የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ‹‹በቁመታችን ልክ ግንባሩ (ኢሕአዴግ) ውስጥ ቦታ
ልናገኝ ይገባል።›› የሚል ጥያቄ ያነሣሉ ብዬ አስባለሁ። አሁን የሥልጣን ትግል (Power Struggle)
ይፈጠራልም፤ ተፈጥሯልም። በተለይ ደግሞ በትግሉ ላይ ተቀራራቢ ዕድሜ ያስቆጠሩ ፓርቲዎች አሉ፤ ሕወሃትና
ብአዴን። ኦሕዴድ ከ1981፣ ደኢሕዴን ከ1983 ወዲህ ስለሆኑ፣ በዚሁ ልክ ነው ግንባሩ ውስጥም የእኔነት ስሜትና
የበላይነት ቁመት የሚኖራቸው። አሁን ያለው የድህረ መለስ ክፍፍል በብአዴንና በሕወሃት መካከል ከፍተኛ ትንቅንቅ
ፈጥሯል። ይሄ ትንቅንቅ የቱ ጋር ሄዶ ሄዶ ያቆማል ሌላ ጉዳይ ነው። ወይ ደግሞ ትንቅንቁ ወደ አደባባይ በወጣ ጊዜ
የሥርዓቱ መጨረሻ ይሆናል። ጉልበት መለካካቱ አይቀርም።
በምኞት ደረጃ የምትለኝ ከሆነ፣ መንግሥት ብሔራዊ ዕርቅ መፍጠር አለበት። ለደርግ ባለሥልጣናት የተሰጠው
ምሕረት ጥሩ ነው። ኢሕአዴግ ብዙውን ጊዜ ፈልጎ፣ የተወሰነ ጊዜ ደግሞ በስሕተት በርካታ ዜጎችን አሰቀይሟል፣
አስኮርፏል፣ በድሏል፣ ለስደት ዳርጓል። እነዚያን ለማምጣት ዕርቁ ያስፈልጋል። ከፖለቲካ ፓርቲዎች [ኦነግ እና ግንቦት
7ን ጨምሮ] ጋር ምሕረት ነግሦ፣ ‹‹አሸባሪ›› ለሚሉት ምሕረት አውርደው፣ የምርጫ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ሁሉም
ፓርቲዎች ፓርላማውን አፍርሠው፣ በእኩል ምኅዳር፣ በእኩል የሚዲያ አጠቃቀም የሚወዳደሩበትን ዕድል መንግሥት
ፈጥሮ፣ ምርጫ እንዲደረግ ቢያደርግ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ።
ስለ አንገት ልብስዋ እናውራ። ፍትሕ ላይ ፎቶህን ለጥፈህ መጻፍ ከጀመርክበት ጊዜ ጀምሮ አንገትህ ላይ የምትታየው
የአንገት ልብስ (Scarf ) በተለያየ አጋጣሚ ስናገኝህም ወልቃ ተመልክተን አናውቅም። አንተ ብቻ ሳትሆን
ባልደረቦችህና የፍትሕ ቤተሰቦችም የአንገት ልብስ አይለያቸውም። የአንገት ልብስዋ መልዕክት ምንድን ነው?
ሻርፑ ራሱን የቻለ መልዕክት አለው።
ልትነግረን ትችላለህ?
ጊዜው ገና በመሆኑ አሁን ልናገረው አልችልም።
‹‹የአንገት ልብስ አብዮት›› የማስነሳት ዓላማ አላችሁ?
በአገራችን ላይ ማንም የማይፈቅድልን፣ ማንም የማይነሳን የፈለግነውን ሕጋዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ሙሉ መብት
አለን። ይሄ ጥያቄ ከላይኛው ጋር ስለሚያያዝ ለጥቂት ወራት ቢቆይ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን፣ የአንገት
ልብሱ ለብርድ ወይም ለጌጥ የሚደረግ አለመሆኑን መናገር እችላለሁ።
ከዚህ በኋላ በሌላ የፕሬስ ውጤት ትመለሳለህ?
CNNን እንደ ሞዴል ወስደን ከሰዎች ጋር በሽርክና ግዙፍ የሆነ የኦን ላይን ሚዲያ (ድረ-ገጽ) ለመመሥረት ብዙ
መንገዶችን ተጉዘናል። አራት የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ቢሮዎች ይኖሩናል። የምንመለሰው በዚህ መንገድ ነው።
ከመሰናበታችን በፊት በኪስህ ስንት ብር እንደያዝክ ልታሳየን ትችላለህ?
አደጋ ይደርስብኛል፣ አንድ ነገር ያጋጥመኛል ብዬ ስለማስብ ከአምስት ሺህ ብር በታች አልይዝም። ብሩን ላሳያችሁ
እችላለሁ፤ ግን አንድ ነገር ላይ መግባባት አለብን። [ሳቅ] ‹‹አበድረን›› የሚል ነገር አልፈልግም። [ስድስት ሺህ አራት
መቶ (6,400) ብር የታሰረ፣ ሦስት ሺህ (3,000) ብር ያልታሰረ መያዙን ፊታችን ቆጥሮ አረጋግጠናል] የሥርዓቱ
ባሕሪ በፈጠረው የተለያዩ ምክንያቶች ከቤቴ ስወጣ ቀና ነገር ይገጥመኛል ብዬ አስቤ አላውቅም። በተወሰነ መልኩ
ገንዘብ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ።
ጨርሰናል። ስለ አብሮ ቆይታችን ከልብ እናመሰግናለን። መልካሙን ሁሉ እንመኝልሀለን።
እኔም አመሰግናለሁ። በእውነቱ ብዙ ጊዜ መናገር የማልፈልጋቸውን ነገሮች እንድናገር ስትገፋፉኝ ስታስገድዱኝ ነበር፤
አስገድዳችሁኛልም። ‹‹Hard Talk›› እንደማለት ነው። ቢሆንም እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ
ጨለማ በነገሠባቸ

ORIGINAL RAW FOOTAGE] Spain Train CRASH Near Santiago De Compostela Ac...

Jul 25, 2013

ሰበር ዜና: ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

Millions of voices for freedom - UDJበደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው ኩታበር ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ያካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ህዝቡ ሰላማዊ እንዲወጣ ኢህአዴግ እያስገደደ መሆኑን ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

የኩታበር ወረዳ ነዋሪ ሰልፍ እንዲወጣ የተደረገው ነገ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠዋት መሆኑም ታውቋል፡፡ በተለይ ሰፊ የማስፈረሳሪያና የቅስቀሳ ስራ እየተካሄደ ያለው በወረዳው ቀበሌ 05፣06 እና 07 መሆኑንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ካድሬዎች ገበሬውን በግድ ከአቅሙ በላይ የዘር ማዳበሪያ ውሰዱ እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከማስከፈላቸው በተጨማሪ ለአልማ(ለአማራ ልማት ማኀበር)፣ለአባይ፣ ለመሬት ግብር እየተባሉ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው እና ነዋሪዎቹ አቅማቸው እንደማይፈቅድ ሲናገሩ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ በመሆኑ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከአካባቢው እየተሰደዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ ማዳበሪያና ዘር አንወስድም ያሉ ገበሬዎችንም መሬታችሁ ይነጠቃል በሚል የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደምሴን ጨምሮ የወረዳው ሹማምንት እያስገደዱ እንደሆነ ነዋሪዎቹ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
ስለጉዳዩ የዝግጅቱ ክፍሉ የወረዳውን አስተዳደር አቶ ደምሴን እና የወረዳውን ግብርና ጽህፈት ቤትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማናገር ጥረት ቢደረግም አልተሳካም፡፡
ምንጭ፣ ፍኖተ ነጻነት

Jul 24, 2013

“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ” ሃይሌ! ወደ ፓርላማ?




haile gebreselasseየዛሬ 10 ወር የሻለቃ ሃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ፖለቲካ የመምጣት ሁኔታን አስመልክቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሃተታ አቅርቦ ነበር፡፡ (እዚህ ላይ ይመልከቱት) ሰሞኑን አትሌቱ ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጎቱንና “በምርጫ” ለመወዳደር መፈለጉ ብዙ እየተባለበት ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን ላለው ሁኔታ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ሃተታ በድጋሚ አትመነዋል፡፡

“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው።
ሃይሌ ይህንን የተናገረው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ ም ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ጋር በመንግስት ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) አስተያየት በሰጠበት ወቅት ነበር። የቀድሞውን ስርዓትና ትውልድ “ድንጋይ ዳቦ በነበረበት፣ ፍራፍሬ ከጫካ ያለምንም ድካም ከሚሰበሰብበት” ዘመን ጋር ያወዳደረው ሃይሌ፣ “የአሁኑ ትውልድ” በማለት ያሞካሸውን ስርዓት ከተፈጥሮ ጋር ጦርነት በማካሄድ ለውጥ ማስመዝገበ መቻላቸውን አስምሮበታል።
“የባለ ራዕዩ መሪ” አቶ መለስ ገድል ለመዘከር በተዘጋጀ ቅንብር ላይ  በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጥ የታየው ሃይሌ “አሁን የት ነው ያለነው?” በማለት ጠይቆ “አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ለማግኘት ነው የምንጋፋው? አውሮፓ ሄደን እዛው ለመቅረት ነው…” በማለት ስደትን መርጠው ከአገራቸው የሚወጡትን ሸርድዶ አልፏል። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ለስደት የሚዳርግ ጉዳይ የለም ወደ ማለት አዝምሞ ተናግሯል። ሃይሌ ይህን ይበል እንጂ በተቃራኒው እስረኞች እንዲፈቱና የፖለቲካ እርቅ እንዲሰፍን እሰራለሁ ከሚሉት ፕሮፌሰር ይስሃቅ ጋር በሽምግልና እያገለገለ መሆኑ በአገሪቱ ውስጥ የሚታው እስርና እንግልት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቅሱ አስተያየት ሰጪዎች የሃይሌን አስተያየት “ለንብረት ዋስትና የሚከፈል የንግግር ቫት” በማለት አጣጥለውታል።
ከኤርትራ ጋር ከተደረገው በቀር በኢትዮጵያ ይህ ነው የሚባል ጦርነት እንዳልተካሔደ ኢህአዴግን የሰላም አባት አስመስሎ ሃይሌ አመልክቷል። በዚሁም ምክንያት ቀደም ሲል ለጦርነት ይውል የነበረው የአገሪቱ በጀት ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ዞሯል ብሏል። የኢህአዴግ ተወካይ መስሎ አስተያየት የሰጠው ሃይሌ “ይህ አሁን የታየው ለውጥ በአስርና አስራ አንድ ዓመት ውስጥ የታየ ነው። አሁን ባለው አካሄድ ከአስር ዓመት በኋላ እንደርሳለን?” ሲል የራሱን ትንቢት አስቀምጧል።
ተቆራርጦ በሚቀርበው አስተያየት እነ ፕሮፌሰር እንድሪያስን በማጀብ ሃይሌ  በመዝገበ ቃላት ላይ ኢትዮጵያን “ረሃብ” በማለት የሚተረጉማት ቃል እንደሚቀየር በልበ ሙሉነት ተናግሯል። “ከሃያ ዓመት በኋላ” አለ ሃይሌ “በመዝገበ ቃላት ላይ የኢትዮጵያ ውርስ ትርጉም ሃብታም በሚል ይቀየራል” ብሏል።
“ድሮ ትረዱን ነበር፤ እናመሰግናለን። አሁን ደግሞ እንረዳችሀዋለን እንላቸዋለን” ሲል አውሮፓና አሜሪካን የመሳሰሉ ታላላቅ አገሮች የኢትዮጵያን እጅ እንደሚናፍቁ ሃይሌ ከምኞት ባለፈ ስሜት ውስጥ ሆኖ ተናግሯል። አገሪቱን ለሃያ አንድ ዓመታት ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ ባልገለጹበት ሁኔታ ሃይሌ ከአስር እስከ ሃያ ዓመት ኢትዮጵያ ሃብታም አገር እንደምትሆን መናገሩ ከምን የመነጨ እንደሆነ ሊገባቸው እንዳልቻለ ብዙዎች እየገለጹ ነው።
“ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል” ሲል ኢህአዴግን የመከረው ሃይሌ የበታች ባለስልጣናት መንግስትን እንዳያሰድቡ መክሯል። “መንግስት ይህንን አድርጉ ላይል ይችላል” የሚለው ሃይሌ የበታች ባለስልጣኖች የሚፈጽሙት ሙስና “መንግስትን ያስወቅሰዋል” በሚል ተቆርቋሪነቱን በይፋ አስታውቋል። ዋናዎቹን የሙስና ተዋናዮች ነጻ በማውጣት የታች ባለስልጣኖችን “እያንገዋለለ” አሳጥቷቸዋል።
“… ለህሊናቸው ሲሉ እንደ መንግስት በማሰብ መስራት አለባቸው” ሲል ትዕዛዝ አዘል ምክርና ማሳሰቢያ ለበታች ባለስልጣናት ያስተላለፈው ሃይሌ የአስተያየቱ መነሻ ከኢህአዴግ ጋር የፈጠረው ዝምድና ውጤት እንደሆነ እየተነገረ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ “ሃይሌ ሃብቱ እየበዛ ሲሄድና የተበደረው ገንዘብ ሲጨምር ኢህአዴግን ወክሎ መናገር ጀመረ” ብለዋል።
አትሌቶችን ሰብስቦ የአቶ መለሰን ሃዘን ሳግ በያዘው ድምጽ እያለቀሰ የገለጸው ሃይሌ ነፍሳቸውን ይማረውና በአቶ መለስ አይወደድም ነበር። በህይወት እያሉም በተደጋጋሚ ያናንቁት ነበር። ሃይሌን እንደሚያደንቁት ተጠይቀው አርቲስት ቻቺን በማሞገስ ጭራሹኑ እንደማያወቁት ዘለውት አልፈውት ነበር። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት ለሃይሌ ቁብ እንደሌላቸው የሚያውቀው ሃይሌ ከአንድ ማስታወቂያ ሰራተኛ ልቆ በፕሮፓጋንዳ ተግባር ላይ መሰማራቱ በቅርብ ጓደኞቹና በአድናቂዎቹ ዘንድ መነጋገሪያ አድርጎታል።
በአዳማው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ በመገኘት ውድ ሽልማቱን ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በማበርከት የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ የታየው ሃይሌ፤ በዚያው ጉባኤ ላይ አቶ መለስንና ኢህአዴግን ማሞገሱ በወቅቱ በርካታ አስተያየት እንዲሰነዘርበት ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም። የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ ያነጋገራቸው እንዳሉት ሃይሌ ወደ ፖለቲካው መንደር በፍጥነት እየተንደረደረ መሆኑን በማስረዳት የሚያውቁትንም ተናግረዋል።
ጣና ሃይቅ ዳርቻ ከልማት ባንክ በአርባ ሚሊዮን ብር የገዛውን ሆቴል ከሁለት ወር በኋላ ሼኽ መሃመድ አላሙዲ በትዕዛዝ እንደነጠቁት በታላቅ ቅሬታ ለህዝብ አስታውቆ የነበረው ሃይሌ የባህር ዳርን ቤተ መንግስት የመጠቅለል ታላቅ ፍላጎት እንዳለው ነው የቅርብ ወዳጁ ለመረጃ አቀባያችንየተናገሩት።
በኦሜድላ ስፖርት ክለብ ውስጥ ሰራተኛ የነበሩትና ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሃይሌ ቅርብ ሰው “ሃይሌ ቤተመንግስትን ይወዳል። ኢትዮጵያንም የመምራት ህልም አለው” በማለት ጭራሽ ተሰምቶ በማያውቀው ጉዳይ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
የአማራ ክልል መንግስት ለሲድኒ ኦሊምፒክ ጀግኖች ግብዣ ባደረገበት ወቅት የባህር ዳር ቤተ መንግስት ጎብኝተው እንደነበር አስተያየት ሰጪው ያስታውሳሉ። ሃይሌ የጃንሆይን መኝታ ክፍል ከተመለከተ በኋላ አሰበ። ከአፍታ በኋላ አልጋቸው ላይ ተቀመጠ። አልጋውን ወደ ላይ ወደታች ካወዛወዘው በኋላ “… ይህንን ቤተ መንግስት…” በማለት እንደሚኖርበት መዛቱን አስታውሰው ተናግረዋል።
ሃይሌ ዝም ብሎ እንደማይናገር ያወሱት እኚሁ በቅርብ የሚያውቁት ሰው ሃይሌ ይህንኑ ህልሙን ተግባራዊ ለማድረግ ዘመቻ የጀመረ እንደሚመስላቸው አስታውቀዋል። በቀጣዩ 2005 ምርጫ ሃይሌ እንደሚሳተፍ በርግጠኛነት ተናግረዋል። ሃይሌ ሁለት ጊዜ በግል ፓርላማ ለመግባት እንደሚወዳደር ካስታወቀ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ራሱን ከምርጫ ዘመቻ ማግለሉን መግለጹ ይታዋሳል።
ሃይሌ ፖለቲከኛ የመሆን የኖረ ህልም እንዳለው ያወሱት ባልደረባው ከተናገሩት በተቃራኒ ሃይሌ የፈለገውን መሆንና ማድረግ የግል ውሳኔው እንደሆነ የሚከራከሩለት አልጠፉም። ሃይሌ ሃብት አለው፣ ከፍተኛ ዝና ገንብቷል። ኢትዮጵያዊያን የማይረዱት እውቅናና ክብር በውጪው ዓለም እንዳለው የሚገልጹት ተከራካሪዎች “አንድ ሰው በተናገረ ቁጥር ለንግግሩ ቀንድና ጭራ መቀጠል ነውር ነው። ሰዎች የመሰላቸውን እንዳይናገሩም የሚገድብ ክፉ ልምድ ነው” ባይ ናቸው። “አያይዘውም ሃይሌ የኢህአዴግ አባል ቢሆን እንኳ አስገራሚ አይሆንም” በማለት ጠርዝ ደርሰው ይሟገታሉ።
በርካታ አትሌቶች የኦህዴድ አባላት እንደሆኑ የሚጠቁሙት እነዚህ የሃይሌ ተከራካሪዎች “ሃይሌ ኢህአዴግን ቢቀላቀል መነጋገሪያ የሚሆነው ጉዳይ ብአዴን ወይስ ኦህዴድ ይሆናል የሚለው ነው” ብለዋል። አርሲ የተወለደው ሃይሌ በሩጫ ከተሳካለት በኋላ በተለያዩ ጉዳዮችና መጠነኛ ግንባታ ወደ ባህር ዳር መጠጋጋቱ በትውልድ አካባቢው ተወላጆች ቅሬታ እንዳስነሳበት በተለያዩ ጊዚያቶች መዘገቡ የሚታወስ ነው።

የፓርላማው ውይይት መታፈኑን በይፋ ያጋለጠው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ከሥራ ተባረረ

(በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊነት” በሚል ጥቅምት 23 ቀን
2005 ዓ.ም ያደረገውን ውይይት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኩል ተቆራርጦና ተዛብቶ እንዲተላለፍ
ተደርጓል በሚል አንድ ዜና መዘገቡ ይታወሳል።
ይህን ዜና በሰንደቅ ጋዜጣ የህዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን
ተወቀሰ” በሚል ርዕስ ከቀረበ በኋላ፤ በዚህ ዘገባ ላይ ተመድቦ የሠራው የቀድሞ የኢቲቪ ባልደረባ ጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻ ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ለዝግጅት ክፍላችን ምላሹን ሰጥቷል።

ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ
(ፎቶ ከሰንደቅ ጋዜጣ)
እነዚህ ዘገባዎች ከተስተናገዱ በኋላ፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ለሰንደቅ ጋዜጣ መረጃ እንደሰጠና ሚስጢር እንዳወጣ
ተቆጥሮ የዲስፒሊን ክስ ቀርቦበታል። ኢ.ሬ.ቲ.ድ በዲስፒሊን ክሱ ላይ አራት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በምስክርነት
ዘርዝሮ አቅርቧል። የድርጅቱ የዲስፒሊን ኮሚቴ በከሳሽ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና በጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻ መካከል የክስ ዝርዝር እና የመልስ መልስ ደብዳቤዎች ሲያዳምጥ ከሰነበተ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም
በቁጥር ቴ02.1/131-304/02/8/ በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ከግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ
ከሥራ የሚያሰናብተውን ቅጣት አሳልፏል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለቤትነት በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ
ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደው ስብሰባ በመልካም
አስተዳደር፣ በተጠያቂነት፣ በሙስና ችግሮችና በመሳሰሉት ላይ ልዩ
ትኩረት በመስጠት የተካሄደ ሲሆን በዚህ ውይይት ላይ የኢፌዲሪ
ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣
በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ
ፀሐዬ፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ የእምባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ወ/ሮ
ፎዚያ አሚን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን
ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ምክትል
ከንቲባ አቶ አበባው ስጦታው እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች
ተገኝተው ነበር።
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጠራውና የአስፈፃሚ አካላትና
የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናን በተመለከተ የተደረገው ውይይት፣
በዕለቱ በሥፍራው ባልነበረ ጋዜጠኛ ተገቢ ባልሆነ መልኩ
ተቆራርጦና ተዛብቶ ለሕዝብ መቅረቡ ትክክል እንዳልነበረ በይፋ
በመግለፁ ምክንያት ከሥራ የተሰናበተው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻን ስለሁኔታው ፋኑኤል ክንፉ አነጋግሮታል።
ሰንደቅ፡- የዚህ ዜና መነሻ አንተን አድርገው ለመውሰድ ያስቻላቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህን ምላሽ መስጠት የሚችሉት እነሱ ናቸው። በሰጡኝ የክስ ዝርዝር ላይ ግን ሌላ ምክንያት ነው
ያስቀመጡት። ወይም ደግሞ ላነሳኸው ጥያቄ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችለው የዚህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ብቻ ነው።
ሰንደቅ፡- እንዴት?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” ለሚለው ዜና መነሻ
ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በእኔ በኩል ያልኩትም አንዳች ነገር የለም። እንደማንም አንባቢ ይህ ዜና በሰንደቅ
ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ነው የተመለከትኩት። ስለዚህም መረጃ ከእኔ አግኝታችሁ ከሆነ አግኝተናል፤ ካላገኛችሁ አላገኘንም
ለሚለው ምላሽ መስጠት የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ይመስለኛል።
ሰንደቅ፡- በርግጥ የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ለዚህ ዜና መነሻ መረጃውን ያገኘው ከሌላ ሶስተኛ ወገን መሆኑን
ማረጋገጥ እንችላለን። ሆኖም ግን ይህ ዜና በወጣ በሳምንቱ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም. እርሶ ለሰንደቅ ጋዜጣ
ማስተባበያ መስጠትዎ የሚታወስ ነው። በወቅቱ ከዜናው ጋር በተያያዘ ለምን ማስተባበል ፈለጉ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት ያዘጋጀውን ፕሮግራም የቀረጽኩት እኔ በመሆኔ ነበር። በሰንደቅ ጋዜጣም የተሰራው ዜና “የባለስልጣናት ድምጽ
ታፈነ” የሚል በመሆኑም ጭምር ነው። ከዚህ አንፃር እንደአንድ ጋዜጠኛ ውይይቱን አፈነ ተብሎ መወንጀል በጣም
አደገኛ ነው። እንዲሁም ማንስ አፈነው? እንዴት ታፈነ? ለሚሉት ጥያቄዎችም ምላሽ የሚፈልጉ መሆናቸው ግልፅ
የሆነ ነገር ነው። በተለይ በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ኃላፊነት ታሳቢ
ስታደርግ በእኔ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ድንጋጤ መገመት ከባድ አይደለም። የእነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት
አንደበትን ለማፈን በእኔ በተራ ረዳት አዘጋጅ ቀርቶ በሌላው የተቋሙ ከፍተኛ አመራር የሚሞከር ተግባር ተደርጎ
የሚወስድ አካል ያለ አይመስለኝም።
ይህ ችግር ከተፈጠረ በኋላም ከስራ ባልደረቦቼ ጋር ተወያይቻለሁ። እንዲሁም አንድ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር
ለማግኘት ጥረት ባደርግም አልተሳካልኝም። የሆኖ ሆኖ ከባልደረቦቼ ጋር ከመከርኩ በኋላ ፕሮግራሙ ታፍኗል ብሎ
ለዘገበው ጋዜጣ ማስተባበያ በመስጠት እራሴን ከጉዳዩ ነፃ ማድረግ እንዳለብኝ ተማምነናል። የመንግስት ከፍተኛ
ባለስልጣናቱም እኔ አለማድረጌን ሊገነዘቡ የሚችሉት ፕሮግራሙ ታፍኗል የሚለውን ዜና ባሰራጫው ሚዲያ መሆኑ
አሻሚ አይደለም። ስለዚህም በዚህ ጉዳይ ላይ ንፁህ መሆኔን ለማረጋገጥ ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በጉዳዩ ላይ
ያለኝን መረጃ ለመስጠት ተገድጃለሁ።
ሰንደቅ፡-እርሶ እንደዚህ ቢሉም፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ታህሳስ 01 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ
ደብዳቤ የዲስፕሊን ኮሚቴው “አቶ አዲሱ መሸሻ በየነ በፕሮግራሙ ኢ.ሬ.ቴ.ድ የባለስልጣኖች ድምጽ አፍኗል።
ፕሮግራሙ ቆራርጧል የሚል የተሳሳተና ከኃላፊነት የራቀ እና በሀሰት የተሞላ መግለጫ ለሰንደቅ ጋዜጣ” ሰጥቷል ሲል
ይከሳል። በዚህ ላይ የእርሷ አስተያየት ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት የኢ.ሬ.ቴ.ድ “የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ”
ያለው ሰንደቅ ጋዜጣ እንጂ እኔ አዲሱ አይደለሁም። በወቅቱም በሰጠሁት ማስተባበያ ተቋሙን በተመለከተ ያልኩት
አንዳች ነገር የለም። የማፈን ነገር ተፈጽሟል ከተባለም ግለሰቡ እንጂ ተቋሙ ሊሆን አይገባም በማለት ነበር ተቋሙን
የተከላከልኩት። በሌሎችም ተቋማት ግለሰቦች ከተቋሙ ዓላማ በመውጣት የሚፈጽሙት ስህተት በእኛም ተቋም
በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጽሟል። ይህ ማለት ግን ግለሰቦች ከተቋም በላይ ናቸው ማለት አይደለም። ስለዚህም ግለሰቦች
በሰሩት ጥፋት በግል መጠየቅ አለባቸው እንጂ በተቋም ደረጃ ስህተቱ ሊታይ አይገባም። ስለዚህም አንድ ሰው በራሱ
መነሻ በፈጸመው ተግባር የተቋም አድርጎ መውሰድ ከሕግም ከሞራልም አንፃር የሚያስኬድ አይመስለኝም።
ሰንደቅ፡- የተከሰስክበት የደብዳቤ ይዘት ሚስጥር በማውጣት የሚል ነው። የሰጠኸው ማስተባበያ ከሚስጥር መጠበቅ
ጋር እንዴት ትገልፀዋለህ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ሚስጥር ማባከን ከመጥፎ ፍላጎት (intention) የሚመነጭ ነው። ሚስጥር
የሚባክነው ተቋምን ወይም ግለሰብን ለማጥቃት ከመፈለግ የሚመጣ ክፉ መንፈስ ነው። ከዚህ አንፃር ስትወስደው፣
እኔ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የሰራሁትን ፕሮግራም የሚመለከት ዜና በመሰራቱ ብቻ ማስተባበያ ሰጠው እንጂ ምን
አጠፈሁ። ከእኔ ጋር ተያያዥነት ያለው ዜና ባይወጣ እኔም ባልተናገርኩ፤ እነሱም ክስ ያሉት ክስ ባልመሰረቱብኝ ነበር።
ስለዚህም የጋዜጠኝነት ሙያዬን (integrity) በሚያጠፉ “አፋኝ” ተብሎ በተሰየመ ሁኔታ ስሜ ጠፍቶ፣ ስሜን
ለመመለስ መከላከሌ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ከሚስጥር ማባከን ከመጠበቅ ጋር ምን ያገናኘዋል?
ሁለተኛው፣ “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የተካሄደው ውይይት ዋናው ዓላማው፣ ውይይቱ ለሕዝብ እንዲቀርብ ነበር። ተደራሽነቱም ለሕዝቡ ነው። ለሕዝቡም
ግልፅ መረጃ ለማቅረብ የተዘጋጀ ውይይት ነበር። ከሁሉ በላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው የስብሰባ ይዘት፣
የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ በዚህች ሀገር ውስጥ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ ለሕዝብ ማሳየት ነበር። ሕዝቡም አደጋውን
በመረዳት ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግንዛቤ ለማስጨበት ያለመ ስብሰባ ነበር። ይህ ታዲያ
ምን ሚስጥር አለው? ሚስጥር ከሆነ መጀመሪያውኑ ሚዲያውን አይጋብዙም ነበር። በወቅቱም ፕሮግራሙ ሲቀረጽም
ሚስጥር ነው ያለ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አልነበረም።
ሌላው በዚህ ተቋም ውስጥ በቆየሁበት የስራ ዘርፎች ሚስጥር ተብለው የሚቀረፁ ስራዎችን ጠንቅቄ አውቃለሁ።
በሚስጥር ደረጃ የተቀረፁ ስራዎችንም ሰርቼ አውቃለሁ። በዚህ ደረጃ የሰራኋቸውን ስራዎች እንኳን ለሶስተኛ ወገን፣
በተቋሙ ውስጥ ማወቅ ከሚገባቸው ሰዎች ውጪ ዉይይት አድርጌም አላውቅም። አለቆቼም ይህን ጠንቅቀው
ያውቁታል።
ሰንደቅ፡- የዲሲፕሊን ኮሚቴው እንደሚለው ከሆነ “በስሜት ያደረኩት ነው” ሲሉ አቶ አዲሱ በኢዲቶሪያል ስብሰባ
ላይ ገልጸዋል ይላል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በነገራችን ላይ የነበረው ኢዲቶሪያል ስብሰባ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ብዙ ርቆ የሄደ ነው። ግልፅ
የፖሊስ ምርመራ ነበር የተደረገብኝ። አስራ አራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባሉበት የተደረገ ስብሰባ ሲሆን አውጣ፣
አታውጣ የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ። እኔ ለማስፈራራት፣ ለማሸማቀቅ የተደረገ ኢዲቶሪያል ስብሰባ ነበር። የቀረበብኝ
ውንጀላ እስከሀገር ክህደት የሚደርስ መሆኑ ነበር የተነገረኝ። የፖለቲካ ይዘት ፈጥረውለት እኔ አንገት ለማስደፋት
በአደባባይ ውጣና ማስተባበያ ስጥ ብለውኛል። የሚገርመው እኔ ነኝ ፕሮግራሙን የቆረጥኩት ያለው አመራር በዚህ
ስብሰባ ውስጥ አንዱ ወቃሽ ሆኖ የተገኘበት ነበር።
ሰንደቅ፡-በዚህ ስብሳባ ደረሰብኝ የሚሉት ጉዳት አለ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- አለ እንጂ። ከዚህ በፊት የኢዲቶሪያል ስብሳባ የምናደርገው አየር ላይ የዋሉ ፕሮግራሞችን ጠንካራና
ደካማ ጎናቸውን ለመገምገም ነው። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የተደረገው ኢዲቶሪያል ግን መንፈሱን የተለየ ነው። የአንድ
ተቋም ኃላፊዎች ተሰብስበው የፖሊስን ስራ በመተካት ያን ሁሉ ወከባ ማስፈራራት ሲፈጥሩ መመልከት በጣም አሳዛኝ
ተግባር ነው። በእኔ ውስጥ የፈጠረው ስሜት ለረጅም ጊዜ ውስጤን ጎድቶታል። በተለይ የኢ.ሬ.ቴ.ድ ተጠሪነቱ ለህዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ይታወቃል። የምክር ቤቱን ውይይት መቁረጡን በግልፅ መናገሩን ሳይፈራ፣ ለምን እኔን
ውይይቱ ተቆርጧል ብልሃል ብሎ ከስራ ሊያሰናብተኝ እንደፈለገ አልገባኝም።
ሰንደቅ፡-በታህሳስ 01 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው ወጪ በሆነው ደብዳቤ ላይ “ፕሮግራሙን ያዘጋጁት
ባልደረባችን አቶ አዲሱ መሸሻ” የሚል ሲሆን፣ በጥር 20 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው የወጣው ደብዳቤ
በበኩሉ “ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ” ናቸው ይላል። ከዲሲፕሊን ኮሚቴው በዚህ
መልኩ ደብዳቤዎቹ ሊዘጋጁ ቻሉ? ፕሮግራሙን የሰራው ማነው ሊባል ይችላል?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ዲሲፕሊን ኮሚቴው ያወጣው ደብዳቤ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው። ለክሱ እንዲረዳቸው አንድ
ደብዳቤ በእኔ አዘጋጁ። ለመከላከል እንዲረዳቸው ደግሞ ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ
ናቸው የሚል ደብዳቤ አዘጋጅ። ይህ በራሱ የሚነግርህ ነገር አለ። በማኛውም ዋጋ እኔ መክሰስ እና ከስራ ማፈናቀል
ለዲሲፕሊን ኮሚቴው የተሰጠው ተልዕኮ ነው። አቶ ሳሙኤል በወቅቱ ትምህርት ላይ ነበሩ። እንዴትም እንደመጡ
አላውቅም።
እውነቱ ግን ጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅዳሜ ፕሮግራሙን ሰርቼ ሙሉ ዝግጅቱ እሁድ ጥቅምት 25 ቀን
2005 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ዜና በኋላ የሚቀርብ መሆኑ ነው። በዚህ ዕለት የሚተላለፍ መሆኑን የሚገልፅ
ከውይይቱ የተወሰዱ አጫጭር ንግግሮች የሚያሳይ ማስታወቂውን /ስፖት/ የሰራሁትም እኔው እራሴ ነኝ።
ሰንደቅ፡- አሁን በዚህ መልስ በእርሶ ላይ የተወሰደው እርምጃ በሌላው ሰራተኛ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን
ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህ ጥያቄ ከነሳህልኝ በውይይቱ ላይ አንድ የተሰነዘረ ነጥብ ልንገርህ። በዚህ ውይይት ከተሳተፉት
ተሳታፊዎች መካከል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዓሊ ሱሌማን አንዱ ናቸው። እሳቸው
ከገጠማቸው አስቸጋሪ የፀረ-ሙስና ትግል ሲገልፁ፤ “የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚታገሉ እና የሙስና
ተግባራትን የጠቆሙና ያጋለጡ ሰዎች በአለቆቻቸው የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እየተወሰዱባቸው ቤሰቦቻቸው
ተበትነዋል። በዚህም የተነሳ እነዚህ ግለሰቦች ምነው ይህን ባልተናገርኩ እያሉ አንገታቸውን ደፍተው ተሸማቀው
እየሄዱ ነው። እነዚህ ሃይሎች ገነው ወጥተው ለፀረ-ሙስና ትግል የተሰለፉ ኃይሎች ግን አንገታቸውን ደፍተው
ይገኛሉ” ነበር ያሉት።
ሰንደቅ፡- አሁን እርሶ ላይ የደረሰውን ነገር ከዚህ ከአቶ አሊ ሱሌይማን አባባል ጋር እንዴት ያስታርቁታል?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የኮሚሽነሩን አስተያየት በእኔ ላይ መፈጸሙን ስመለከት በጣም አስገርሞኛል። ምክንያቱም
በውይይቱ ላይ ተገኝቼ የቀረጽኩት ውይይቱን ለሕዝብ ለማቅረብ እንጂ፣ በዚህ የውይይት ፕሮግራም መቆራርጥ መነሻ
እና በመልካም አስተዳደር ዕጦት ሰለባ ለመሆን አልነበረም። የሆነው ግን በእውነት አስገራሚ ነው። ከስራ
ተፈናቅያለሁ። ልጆቼን ለጊዜው ለወላጆቼ ሰጥቻለሁ። ባለቤቴን ከፍዬ ነው፤ የማስተምረው። የፓርላማውን ውይይት
በፈለጉት መንገድ የቆረጡት ግን ደረታቸውን ነፍተው ለእኔ የስንብት ደብዳቤ ፅፈው ሰጥተውኛል። ኮሚሽነሩም ያሉት
ከላይ የዘረዘርኳቸውን ሂደቶች ነበር። ለእሳቸው አስተያየት ከእኔ በላይ ማረጋገጫ ማን ሊያቀርብ ይችላል?
እዚህ ላይ ማወቅ ያለብህ በጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ይህን እድል አግኝቼ ለመናገር ቻልኩ እንጂ ስንቶቹ የሆዳቸውን
ይዘው የቢሮክራቶች ሰለባ ሆነው ቁጭ ማለታቸውን መዘንጋት የለብንም።
ሰንደቅ፡- ተጠሪነታችሁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። አሁን ደርሶብኛል የምትለውን የመልካም አስተዳደር
ችግር በአካል ሄደህ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል፣ የቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
ያመለከትከው ነገር የለም?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ የወሰድኩት እርምጃ እራሴን ማረጋጋት ነበር። በዚህ ጉዳይ አንተ ሶስተኛ ወገን ስለሆንክ
እንጂ የተፈጠረው ሁኔታ እጅግ ድፍረት የተሞላበት ነው። መዋሸት የማልፈልገው ከስራ ተሰናብተሃል የሚለውን
ውሳኔ ስሰማ ደንግጫለሁ።
ሰንደቅ፡- ለምን?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠራው ስብሳባ ታማኝ ባለመሆኑ ይቅርታ መጠየቅ
የነበረበት ኢ.ቴ.ሬ.ድ ነው። ይህን የምለው የእኛ ተቋም አስፈፃሚ መስሪያቤት በመሆኑ ተጠሪ ለሆነበት ተቋም በሰራው
ስህተት ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል የሚል እምነት ስለነበረኝ ነው። የሆነው ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት
በአግባቡ አልተስተናገደም የሚል መከራከሪያ ባነሳሁት ግለሰብ ላይ፣ የስራ ስንብት ደብዳቤ ሲሰጥ ምን ሊሰማህ
ይችላል። እንደዚህ ዓይነት ድፍረት የተሞላበት እርምጃ እንዴት ይወስዳሉ ብለህ ትገምታለህ። ስለዚህም ግራና ቀኙን
ለመመልከትና የተፈጠረብኝን ጫና ለመርሳት ወደ ሆነ ቦታ ዞር ማለትን ነበር የመረጥኩት።
ሰንደቅ፡- ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ምን ትጠብቃለህ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ከእኔ ስራ መፈናቀል በላይ አጀንዳ ያለው
ይመስለኛል። ምክንያቱም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ተቋም፣ በምን ምክንያት ውይይቱን ሊቆርጠው
ይችላል? ውይይቱ መቆረጡንም ምክር ቤቱ ያውቃል። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ምክር ቤቱ ውይይቱ እየተቆራረጠ
መቅረቡን እንደሚያውቅ እየታወቀ፣ ለምን የሃሰት መረጃ እንዳቀረብኩ ተቆጥሮ ከስራ ገበታዬ እስናበታለሁ?
የፓርላማው ውይይት በትክክል አለመዘገቡን በመቃወም ምላሽ መስጠቴ ዋጋው ከስራ መሰናበት ከሆነ፣ ከእኔ የስራ
ዋስትና በላይ ፓርላማው ሊመለከተው የሚገባ ጉዳይ ነው። ይህን መሰል ብልሹ የመልካም አስተዳደር ከተለመደ
ተቋሙም ወዴት እየሄደ እንደሆነ ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል።¾
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 411 ሀምሌ 17/2005)

Total Pageviews

Translate