Pages

Feb 28, 2013

ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!

ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ

“አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉ” አስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ
ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ
ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸው “አቧራው
ጨሰ” የሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ። “ህጻን እናሳድጋለን” እያሉ በዘረጉት ሰንሰለት
የህጻናትን ደም የሚጠጡ “አንቱ” የተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምር …
በሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው
የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል
የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ እነዚህ ጎሣዎች
እጅግ አሰቃቂ የሆነ የአፈናና የጭከና ድርጊት ሲፈጽሙ በወጉ ታጥቀውና ዘመናዊ ተሽከርካሪ በመያዝ ነው። የሚታፈነውን ሰው
ከተቆጣጠሩ በኋላ አዋራ ይነሳል። የሚከንፉበት ተሽከርካሪ አሸዋውን ተርትሮት ሲወረወር የሚነሳው ጭስ ሲበተን እነሱ የሉም።
ቀሪው ተግባር “ሚስትህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ዘመድሽን ለሚያርዱ የሰውነት ክፍል ሌቦች አሳልፈን ሳንሰጥ ዶላር ክፈል
ወይም ክፈይ” የሚለው ድርድር ነው። ይህ ድራማ መሰል ንግድ ሲከናወን ተገደው ይሁን የንግዱ ተባባሪ በመሆን በውል
በማይታወቅ ሁኔታ የድርድሩ አስተርጓሚ ሆነው የሚሰሩት ኤርትራዊያን እንደሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያኖችም አሉበት
ይባላል። ማንም ይስራው ማን ድርጊቱ አሰቃቂ መሆኑ ብዙዎችን አስለቅሷል። አስጨንቋል።
በደላሎች እስራኤል ለመግባት ጉዞ ከጀመሩት ወገኖች መካከል ስንቶቹ በሲና በረሃ ሟምተው እንደቀሩ መረጃ የለም። ከሱዳን ምድር
ወጥተው ግብጽ በመሻገር ሲና በረሃ እንደ ከብት ተበልተው የሚጣሉት ወገኖች ስቃይ ለሰሚው ግራ ነው። ወገኖቻችን ላይ
የሚደርሰው አሰቃቂ መከራ ከቀን ቀን እየተባባሰ ነው። አሰቃቂ ዜናዎች መስማት ለየእለቱ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ጉዳይ
እስኪመስል ተለመዷል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ “እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል” የሚለው የሁሉም ወገን “ዳር ቋሚዎች” ጥያቄ ነው።
“ለጆሮ የሚሰለች ነው፣ እርዳታ መስጠት ታከተን፣ የሚል መልስ የሚሰጡ አጋጥመውኛል። ድርጊቱ ተደጋግሞ ለጆሮ የሚያሰለች
ደረጃ እስኪደርስ እነዚህ ወገኖች የት ነበሩ? ቢያንስ ሌሎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስ ምን ሰሩ? በውጪ አገር ያለን ወገኖች
የሚረዳውንና የማይረዳውን መለየት የተሳነን ይመስለኛል” በማለት በሚኔሶታ የሚኖሩት ወ/ሮ ሰብለ አስተያየታቸውንና
ተማጽኗቸውን ያሰማሉ።
የካቲት 3፤2005 (2/10/2013) የቪኦኤ አማርኛ ክፍለ ጊዜ ያሰማው እረፍት የሚነሳ ዜና እስካሁን አልተቋጨም። ሱዳን ሸገራብ
በሚባለው ሰፊ የስደተኞች ጣቢያ ከባለቤታቸውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩ ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ጥር 22 ቀን 2005 ዓም ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ከቤታቸው ይወጣሉ። በካምፕ ውስጥ ከሚገኘው ቤታቸው ወጥተው በግምት ሰላሳ ሜትር ሳይርቁ
ታፈኑ።
ባለቤታቸው አቶ መልካሙ ባዬ ለቪኦኤ እንደተናገሩት አፋኞቹ ራሻይዳዎች ናቸው። ራሻይዳ የቆዳቸው ቀለም ጠየም ያለ የሱዳን፣

የኤርትራና የግብጽ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ ቀደም ሲል ከሶስት እስከ አራት ሺህ ዶላር እየተቀበሉ በደላላ አማካይነት ስደተኞችን
በሲና በረሃ ወደ ግብጽ ያሻግሩ ነበር። እስራኤል በሲና በረሃ ወደ ድንበሯን ዘልቀው የሚገቡበትን የስውር መንገድ ስትዘጋው
ራሻይዳዎቹ የገቢ ምንጫቸው ተዘጋ። ገንዘብ የለመዱት ወንበዴዎች የንግዱ ስልት ቀየሩና ሰው ማፈን ጀመሩ። አፈናውንም
ከሚያካሂዱባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ ድንበር አቋርጠው የሚጓዙትን አድፍጠው በመያዝ፣ ስደተኞችን ከስደተኛ ካምፕ አፍኖ
በመውሰድ፣ ከሌሎች አፋኞች ስደተኞችን በአነስተኛ ገንዘብ በመግዛት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት ሜሮን እስጢፋኖስ
ይናገራሉ፡፡
ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ ይህንን ዜና ሲሰሙ ደነገጡ። ዜናውን ካሰራጨው የቪኦኤ ዝግጅት ክፍል አድራሻ በመጠየቅ አቶ መልካሙን
አገኟቸው። አቶ መልካሙ በቃለምላልሳቸው ወቅት እንደተናገሩት ሁሉ ለወ/ሮ ሰብለ የደረሰባቸውን ሁሉ አጫወቱ። ወ/ሮ ሰብለ
“የሰማሁት ሁሉ እረፍት ነሳኝ። የማውቃቸውን ሰዎች ማስቸገር ጀመርኩ። ጊዚያዊ የባንክ ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ ማሰባሰብ
ጀመርኩ። ህይወት ለማትረፍ እየጣርኩ ነው” ሲሉ ጥሪ ያካተተ አስተያየት ሰነዘሩ።
ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ አሁን ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው። አፋኞቹ 35 ሺህ ዶላር ካልቀረበላቸው የሰውነት አካል ክፍል ለሚዘርፉት
አራጆች ያስረክቧቸዋል። እዚያ ከደረሱ ድርድር የለም። የሰውነት ክፍላቸው የበለጠ ዋጋ ስለሚያወጣ ሌሎች ወገኖች ላይ
እንደተፈጸመው እርሳቸውም ላይ ይከናወናል።
የ12 እና የ 1 ዓመት ከስምንት ወር ልጅ ያላቸው ወ/ሮ ትዕግስት ባለቤታቸውን በስልክ እንዲያነጋግሩ ይደረጋሉ። ባለቤታቸውም
ይሰቃያሉ። እግራቸውና እግራቸው መካከል ብረት ተደርጎባቸዋል። ይደበደባሉ። ይህ ሁሉ የሚደረገው ባለቤታቸው የተጠየቁትን
ገንዘብ ባስቸኳይ እንዲከፍሉላቸው ለማስጨነቅ ነው። ባለቤታቸው እንደተናገሩት “ምንም አማራጭ የለኝም። የተጠየቀውን ገንዘብ
ማግኘት አልችልም። ልጆቼ ወደፊት ሲጠይቁኝ ለምኜ አቃተኝ ለማለት እየለመንኩ ነው። ባለቤቴ ግን ምንም ማድረግ
እንደማልችል ታውቃለች፤ … ” ብለዋል።
የ 12 ዓመቷ ልጃቸው ሱፊ “እኛንም እንዳይወስዱን ስለምንፈራ ከቤት አንወጣም” በማለት ልብ የሚነካ መልስ ከቪኦኤ ለቀረበላት
ጥያቄ መልስ ሰጥታለች፡፡ “እናቴን አፈኗት” ያለችው ህጻን የበርካታዎችን ልብ እረፍት ነስታለች። ወ/ሮ ሰብለ “እንደዚህ አይነት
አሳዛኝ ሲቃ ተሞላበት ጉዳይ እየሰማን በውጪ ያለን ወገኖች እንዴት 30 ሺህ ዶላር ማዋጣት አቃተን” ሲሉ ይጠይቃሉ። ወ/ሮ
ትዕግስት ጸሃይ ቢተርፉ ለሌሎች በማስተማር ተመሳሳይ ችግር በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እንዳይደርስ የማድረግ ስራ ይሰራል የሚል
እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
በሰብአዊ ተግባርም ሆነ በየትኛውም ዓይነት ማህበር ተመሳሳይ ስራ ተሳትፎ እንደሌላቸው ያስታወቁት ወ/ሮ ገነት፣ ይህን ጉዳይ
የሳቸውን ልብና አእምሮ ዕረፍት ነስቶት ለዚህ ተግባር ራሳቸውን እንደሰጡ ሁሉ፣ ሌሎችም ይህንን ልብ ሰባሪ አደጋ ሌሎች
ወገኖችም ሰምተው ተባባሪ እንዲሆኑ በሚል ለጎልጉል አስተያየት መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ለመንግስት ስለማሳወቃቸው ተጠይቀው በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጸሐፊ ስልካቸውን በማፈላለግ ካገኙ በኋላ ማነጋገራቸውን
ይገልጻሉ። በምላሹም “ይልቁኑ አፋኞቹ ስልካችሁን እንዳያውቁ ተጠንቀቁ። እየደወሉ ይጨቀጭቋችሁዋል” የሚል የማስፈራሪያ
ማስጠንቀቂያ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።
ቴዲ አፍሮ በፑንት ላንድ ሞት የተፈረደበትን የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ቀድሞ በመድረስ ህይወቱን እንደታደገው አቶ
መልካሙ አስታውሰው በተመሳሳይ የባለቤታቸውን ህይወት ሊታደግ የሚችል ወገን ሊኖር እንደሚችል ተቁመው ለማንኛውም
“መፍትሔው እግዚአብሔር ዘንድ ነው” የሚል መልዕክት በቪኦኤ በኩል አስተላልፈዋል።
ወ/ሮ ሰብለ በበኩላቸው “ፈቃደኛነቱ ካለ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን” በማለት የጀመሩት የነብስ ማዳን ስራ በቅርብ
ወዳጆቻቸው መደገፉን አስታውቀዋል። አያይዘውም ሩጫው ከጊዜ ጋር መሆኑንን አመልክተዋል።
ገንዘቡ ከተገኘ ለአፋኞቹ እንዴት ይደርሳል? ወ/ሮ ትዕግስትስ እንዴት ነጻ ይሆናሉ? በሚል ወ/ሮ ሰብለ የሰሙት ነገር እንዳለ
ለተጠየቁት፣ ሰዎቹ እስራኤል አገር ወኪል አንዳላቸውና፣ ገንዘቡ ለወኪሎቻቸው ሲገባ ግብጽ ወስደው እንደሚለቋቸው፣ ይህንን
ለማከናወን የሚችሉ ሴት አቶ መልካሙ ማዘጋጀታቸውን እንደነገሯቸው የሴትየዋን ስም በመጥቀስ ተናግረዋል።
“በድብደባና በስቃይ ደክሜያለሁ። አሁን ገንዘቡ ተከፍሎ ቢለቁኝም በረሃውን አቋርጬ ግብጽ የምደርስበት አቅም የለኝም።
እሞታለሁ። አትክሰሩ። እኔ አልተርፍም። የምትችሉ ከሆነ ህይወቴን ይወስዳት ዘንድ ለፈጣሪ ጸልዩ” ይህ ሲና በረሃ ታፍኖ የቆየ
ኤርትራዊ ወጣት ለወንድሞቹ የተናገረው የመጨረሻ ንግግር ነበር። ወንድሞቹ እስራኤል አገር በስደት ሃዘን ተቀመጡ። ከዚያ በኋላ
ስልካቸውን ቀየሩ። ወንድማቸውን በስልክ ድምጽ ነፍሱ ሳይወጣ ሞቱን ተቀበሉ” ሲሉ የሰሙትን ወ/ሮ ሰብለ አጫውተውናል።

በሌላም በኩል በተመሳሳይ ታፍና የነበረች አንድ ወጣት የሚከፈለው ተከፍሎ በቅርቡ ከግብጽ አዲስ አበባ እንደገባች
አመልክተዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሙት የሲና በረሃ አሰቃቂ ስቃይ ሳቢያ የወ/ሮ ትዕግስት ገብሬን ህይወት ለማትረፍ ራሳቸውን ከፊትለፊት
ያቆሙት ወ/ሮ ሰብለ ሊያነጋግራቸው ለሚፈልግ ሁሉ የኢሜል አድራሻቸውን አስታውቀዋል። yegetasew@yahoo.com
ዝግጅት ክፍሉ፦ በተመሳሳይ፣ በተለያዩ ስፍራዎች የሚፈጸሙትን የወገኖቻችንን ስቃይ አስመልክቶ ላልሰሙ ትምህርት ይሆን
ዘንድ ጽሁፍ ለምትልኩልና ወገኖች ሁሉ ቅድሚያ እንደምንሰጥ ለመግለጽ እንወዳለን። በተለይም በሱዳን የስደተኞች ካምፕ ከ30-
40 ዓመት የኖሩ ስደተኛ ወገኖች ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያዊን ተሳትፎ ምን እንደሚመስል ብትጠቁሙን ጉዳዩን
እንደምናጣራው ከወዲሁ እንገልጻለን።
ወ/ሮ ሰብለና ለተመሳሳይ አላማ የተነሱት እህቶች የሚከተለውን ደብዳቤ ለእምነት ባልደረቦቻቸውና ለቤተክርስቲያን ያቀረቡትን
የተማጽኖና እንቅስቃሴያቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
የካቲት ፲፫/፳፻፬
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈሥ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ የሚያንሱ ከነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳን ስላደረጋችሁ ለእኔ አደረጋችሁ” ማቴ ፳፭ ፥
፴፱
ጉዳዩ፦ በስደት ላይ እያሉ በአጋቾች ለታገቱ እናት ማስፈቻ የሚሆን ገንዘብ ስለማሰባሰብ
የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ በማለት መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያስቀደምን ወደ ጉዳዩ እንገባለን።
ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ በሱዳን አገር ሸገርአብ የስደተኞች ጣቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊት ስደተኛ ሲሆኑ በ01/22/13 ጠዋት ወደ
ቤተክርስቲያን ሲሄዱ በራሻይዳዎች ታግተው በህይወት ለመውጣት ገንዘብ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል።
ባለቤታችው አቶ መልካሙ ባዬ በዛው በሸገርአብ የስደተኞች ጣቢያ ከአንድ ዓመት ከሰባት ወር ህፃን እና ከአስራ ሁለት ዓመት
ታዳጊ ሴት ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩ ሲሆኑ የተጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ምንም አይነት አቅም ስለሌላቸው በ02/10/13/
በተላለፈው የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል የመስታወት ዝግጅት ላይ ወገን ይደርስላቸው ዘንድ ተማጽነዋል ።
/ሙሉ ቃለ-መጠይቁን በዚህአድራሻ ማግኘት ይቻላል?

እኛም ሥማችን ከደብዳቤው መጨረሻ የተዘረዘረው ግለሰቦች ይህንን የተማጽኖ ድምጻቸውን ሰምተን ክርስቲያናዊ እና ወገናዊ
ግዴታችንን ለመወጣት ከአሜሪካ ድምጽ/VOA / ጠይቀን በተሰጠን የስልክ ቁጥር በመደወል አቶ መልካሙን /የታጋቿ ባለቤት /
አነጋግረን በምን ልንረዳቸው እንደምንችል እና አሁን ባለቤታቸው ያሉበትን ሁኔታ በዝርዝር አስረድተውናል።
በእኛ በኩል እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት፦
1. በለንደን የሚገኘውን የAmensity International Sudan Team ስልክ በመደወል በእርግጥም ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ከላይ
በተጠቀሰው ቀን በአጋቾች እንደተወሰዱ በሱዳን ያለው UNHCR እንዳሳወቃቸው ሰምተን ጉዳዩ እውነተኛ እንደሆነ አጣርተናል።
2. በሱዳን ካርቱም ላለው የኢትዮጵያ ኤንባሲ በአንባሳደሩ ጸሐፊ በኩል ጉዳዩ የሚመለከተው ቆንስላ ክፍል ክትትል እንዲያደርግ
አሳውቀናል።
3. የምናውቃቸውን ሰዎች ቃለ ምልልሱን ሰምተው የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥረት እያደረግን ነው።
4. ተጨማሪ የአየር ሰዓት አግኝተው እርዳታ ይጠይቁ ዘንድ በሸገር ሬድዮ የ‘ታድያስ አዲስ’ አዘጋጅ ከሆነው ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር

ተነጋግረን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ 02/16/13 ሌላ ቃለ-መጠይቅ እንዲደረግላቸው አድርገናል
5. በአሁኑ ሰዓትም በዚሁ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የተለያዩ የራድዮ ጣቢያዎች ይህንን አሳዛኝ ነገር ወደ ህዝብ ጆሮ እንዲያደርሱ
እየጠየቅን ነው።
6. በተጠላፊዋ ስም የFacebook ገጽ ከፍተን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች በPaypal እርዳታ የሚሰጡበትን መንገድ እያመቻቸን ነው
7. Tewahedo.org. የተባለው የቤተክርስቲያን ድህረ-ገጽ ይህንን አሰቃቂ ነገር በፊት ገፁ እንዲለጥፍ አስፈላጊ መረጃ ልከናል።
8. ለዚሁ አገልግሎት ብቻ የሚውል የባንክ አካውንት ከፍተናል
በአሁኑ ሰዓት ገንዘቡ በፍጥነት መከፈል ካለመቻሉ የተነሳ በወ/ሮ ትዕግስት ላይ በኤሌክትሪክ እና በእሳት መቃጠል፤ ድብደባ፤
ተዘቅዝቆ መታሰር፤ እንዲሁም የሞቱ ሰዎችን አጥንት እያሳዩ የሥነ-ልቦና ጥቃት ማድረስ እና ሌሎችም ኢ- ሰብአዊ ድርጊቶች
እየተፈጸሙባቸው መሆኑን ባለቤታቸውን በስልክ ባገኟቸው ቁጥር ከሚነግሯቸው ነገር ለመረዳት ችለናል።
ይህንንም ደብዳቤ ለመላክ የተገደድነውም በእኛ አቅም የተጠየቀውን 25,000.00 USD ሰብስበን የእኝህን እናት ህይወት
ለማትረፍ የማንችል መሆኑን በማመናችን እና ይህ ገንዘብ ካልተከፈለ ግን አጋቾቹ “ከፍለን ነው የገዛናት ቢያንስ ያንን ለመመለስ
ኩላሊቷን አውጥተን እንሸጣለን ” በማለት በግልጽ በመናገራቸው ይህ አደገኛ ነገር ከመከሰቱ በፊት ህዝበ ክርስቲያኑ የሚችለውን
አድርጎ እኝህን እናት ለልጆቻቸው እንዲያተርፍላቸው በእግዚአብሔር ሥም በመጠየቅ ነው።
በአሁኑ ሰዓት መዋጮ መጠየቅ እንዴት ከባድ እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው። ጉዳዩ የህይወትና የሞት መሆኑ አስገድዶን እና
ለወገን ደራሽ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ወገናችንን ተስፋ አድርገን ይህንን ለህዝበ ክርስቲያኑ እንድታስተላልፉልን የተሰደዱት ሁሉ
መከታ በሆነችው በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ሥም በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን። ከሁሉ በላይ ማህበረ ካህናቱም እና
ምዕመኑ እኚህ እናት በህይወት ይወጡ ዘንድ ወለተማርያም እያሉ በፀሎት እንዲያሳስቡላቸው እንጠይቃለን።
ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር
እሴተ ህይወት/ኢየሩሳሌም ጸጋዬ/ እህተ ማርያም (አዜብ ሮባ) ሰብለ ወንጌል /ሰብለ ደምሴ/
To wire money:
Seble Demissie Asefa
Swift code for international money wiring :WFBIUS6FFX
Routing number : 121000248
Online or in person transfer in the USA routing number : 019000019.
Account number is 7728584504.
Bank name: Wells Fargo
ስልክ ፡ (612) 636 1266 ስልክ ፡ (651) 366 2310 ስልክ፡ (612) 232 8720
የግርጌ ማስታወሻ፦
የባለቤታቸው አቶ መልካሙ ስልክ ቁጥር 011 249 116 112 170 ሲሆን አስፈላጊውን ጥያቄ ሁሉ ለመመለስ በማናቸውም ሰዐት
ዝግጁ እንደሆኑ ለመግለፅ እወዳለን።

Feb 27, 2013

በእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ላይ ብርበራና ዘረፋ በፈጸሙ ፖሊሶች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መ.ኢ.አ.ድ ጠየቀ

ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አስደንጋጭ በሆነ አሸባሪ ተግባር የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ብርበራና ዝርፊያ በመፈጸሙ ፖሊሶችና ድርጊቱን ባስፈጸሙ የፖሊስ አዛዦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መ.ኢ.አ.ድ/ ጠየቀ፡፡ መ.ኢ.አ.ድ ይህንን የጠየቀው የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው ባለ ሦስት ገጽ መግለጫው ነው፡፡

መግለጫው እንደዘረዘረው ‹‹አገራችን ኢትዮጵያ ከ 1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ በኋላ በተቀረጸው ህገ መንግስት አንቀጽ 11 መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ቢልም ለህ.ወ.ሃ.ት መንግስት ግን በተደጋጋሚ በክርስትናና በእስልምና ሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት የሃይማኖት መሪዎች የህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት የፖለቲካ አስፈጻሚ እንዲሆኑ በኃይል ጭምር ሲተገብር ቆይቷል፡፡›› በማለት ይዘረዝራል፡፡ መግለጫው ባለ አራት ነጥብ አማራጭ ነገሮች በማለትም ዘርዝሯል፡፡ መግለጫው በመጨረሻም ‹‹የእስልምና መንግስት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል የሚለውን ውንጀላ በገለልተኛ አካል ይጣራ፡፡›› ሲልም ጥሪውን አቅርቧል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይመልከቱ፡፡



ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አስደንጋጭ በሆነ አሸባሪ ተግባር የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ብርበራና ዝርፊያ በመፈጸሙ ፖሊሶችና ድርጊቱን ባስፈጸሙ የፖሊስ አዛዦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መ.ኢ.አ.ድ/ ጠየቀ፡፡ መ.ኢ.አ.ድ ይህንን የጠየቀው የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው ባለ ሦስት ገጽ መግለጫው ነው፡፡

መግለጫው እንደዘረዘረው ‹‹አገራችን ኢትዮጵያ ከ 1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ በኋላ በተቀረጸው ህገ መንግስት አንቀጽ 11 መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ቢልም ለህ.ወ.ሃ.ት መንግስት ግን በተደጋጋሚ በክርስትናና በእስልምና ሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት የሃይማኖት መሪዎች የህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት የፖለቲካ አስፈጻሚ እንዲሆኑ በኃይል ጭምር ሲተገብር ቆይቷል፡፡›› በማለት ይዘረዝራል፡፡ መግለጫው ባለ አራት ነጥብ አማራጭ ነገሮች በማለትም ዘርዝሯል፡፡ መግለጫው በመጨረሻም ‹‹የእስልምና መንግስት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል የሚለውን ውንጀላ በገለልተኛ አካል ይጣራ፡፡›› ሲልም ጥሪውን አቅርቧል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይመልከቱ፡፡
መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሚዛን ተፈሪ ሙስሊሞች እየታሰሩ ነው


ሚዛን ተፈሪ ሙስሊሞች እየታሰሩ ነው በደቡብ ክልላዊ መንግስት ቤንች ማጂ ዞን ሚዛን ተፈሪ ከተማ ሰሞኑን ሙስሊሞች እየታሰሩ መሆኑን የዜና ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡
የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንዳስታውቁት የካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም ስምንት
ሙስሊሞች የታሰሩ ሲሆን እስካሁንም እስሩ እንደቀጠለ ነው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም ለዝግጅት ክፍላችን እንዳረጋገጡት በርካታ ሙስሊሞች እየታሰሩ ሲሆን የተሰጠውም ምክ
ንያት አክራሪዎች ናቸው የሚል ነው፡፡ ወደ አካባቢው ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ደውለን ያናገርናቸው ስማቸውን ለመናገር ያልፈለጉ አንድ የስራ ኃላፊ በሰጡን መልስ ‹‹ሦስት ተጠርጣሪዎችን አስረናል፡፡ ምርመራው እየተጣራ ነው፡፡ ተጣርቶ ባላለቀ ጉዳይ ላይ አስተያየት ለመስጠት እንቸገራለን፡፡›› ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!

በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)

ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን  የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ  ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡
ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን  በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና  የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ  የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ  በፍቅር አብረን ኑረናል፤  የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡
እንዴት እንደ  ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ  ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Feb 26, 2013

ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት

ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)

tplf rotten apple
25.02.2013
የዘረኛው የህውሃት ስርዓት በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ ሃገር መገነጣጠሉንና ቤሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠቱንመመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሚታይ እውነታ ነው፡፡
ከምስረታው ጀምሮ ይዞት የተነሳው የኢትዮጲያን ሉዋላዊነት የማፍረስና የመበተን አላማውን መተግበር የጀመረው የሻቢያ አሽከር በመሆን ለሃገር አንድነትና ክብር ዘብ የቆመውን የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት በመውጋት ሃገራችን ያለ ባህር በር እንድትቀርና በኢትዮጲያዊነት የታነፀውን ዘመናዊ የወታደር ሃይል በትኖ በምትኩ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚታይበት፣ ቤሄራዊ ስሜት የሌለው፣ በአለቆቹ ከመታዘዝ ውጪ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት ያልዘለቀው ጀሌዎቻቸውን በህዝብ ላይ አንግሰው ያሻቸውን ሲገሉ፣ የሻቸውን ሲያስሩ እንሆ አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡
በመሰረቱ ይህ እኩይ ስርዓት(ቡድን) በኢትዮጲያዊነት ላይ ካለው የመረረ ጥላቻ የተነሳ አብረው የመሰረቱትን ግን በኢትዮጲያዊነት ላይ ፅኑ አቋም የነበራቸውን ባልንጀሮቻቸውን ሳይቀር እያስወገዱና እያባረሩ በምግባር የሚመቻቸውን በተለይ በህዝብና በሃገር ላይ የጠለቀ ጥላቻ ያላቸውን አስከትለው የጥፋት ዘመናቸውን ቀጥለውበታል፡፡
በተለይ የመንግስት ስልጣን ከያዙ በሗላ ከስልጣን በተጨማሪ በገቢ እራሳቸውን ለማጠናከር ከኢትዮጲያ ህዝብ በዘረፉት ሃብትና ንብረት በትግራይ ህዝብ ስም ባቋቋሙት ኢፈርት ሃገሪቱን ጫፍ እስከ ጫፍ በመቆጣጠር የንግዱን መስክ በበላይነት በመያዝ ገቢና ወጪው የማይታወቅ ትልቅ የሃብት ምንጭ በመፍጠር የአገሪቱን የትኛውም የንግድ እንቅስቃሴ በበላይነት ይዘው ነግሰውበታል፡፡
በተለያየ መስክ ከሚፈፀመው የሰብዓዊ መብት እረገጣ በተጨማሪ የሃገርን ቤሄራዊ ጥቅም አሳልፈው በመስጠት ወይም ገንዘብ የሚይስገኝላቸውን ሁሉ በመዝረፍና በማሸሽ፣ ምስኪኑ ህዝብ በዜግነቱ ሊያገኝ የሚገባውን ብቻ ሳይሆን በስሙ ተለምኖ የመጣውን ሁሉ በመንጠቅ ብዙሃን በርሃብ በሚሰቃይበት ሃገር ለአራት ለአምስት ትውልድ የሚበቃ ሃብት አሽሽተዋል፡፡
ከምርጫ 1997 ዓ.ም በፊት በተወሰነ መጠን እራሳቸው ላወጡት ህገ-መንግስት ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ቢያስቸግራቸውም ህጋዊ መስሎ ለመታየት የሚሞክሩበት ሁኔታዎች ይስተዋሉ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ፍርድ ቤት መመላለስ የእለት ከእለት ስራቸው ቢሆንም ከአሁን በተሻለ የህትመት ውጤቶች በቁጥርም በይዘትም የተሻሉ ነበሩ፡፡ በሌላም በኩል ይህው እኩይ ስርዓት ህግን ከመሻሩ በፊት የፓርላማ ጀሌዎቹንን ሰብስቦ ሊሽር ባስበው ህግ ላይ ሌላ ህግ ሲያወጣ ታይቷል ለምሳሌ የቀድሞ የህውሃት አባል የነበሩት አቶ ስዬ አብረሃ በተከሰሱበት ወንጀል ህጉ የሚፈቅድላቸውን የዋስትና መብት ለመከልከል ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት አዲስ ዋስትና የማያሰጥ የፀረ-ሙስና ህግ ማፅደቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ህውሃት በአመለካከትም ይሁን በግል ጥላቻ የራሱን ሰወች ሲበላ ከቻለ አንዱን በአንዱ ላይ አስነስቶ በማጫረስ አልያም በአደባባይ በደላቸውን እንዲናዘዙ በማስገደድ ከተጠያቂነት እራሱን ሲከላከል መቆየቱ አንድም እራሱን ላለማጋለጥ አልያም በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚፈፅማቸው በደሌች ሰርዞም ደልዞም ህግዊ ለመምሰል የጥር ነበር፡፡
ከምርጫ 1997ዓ.ም በሗላ ያለው በፊት ከነበረው ጋር ማነፃፀር ይከብዳል እጅግ ብዙ እርቀት ወደ ሗላ የመመለስ ያህል ነው ምክንያቱም በዛን ወቅት በተፈጠረው በጣም ጠባብ አጋጣሚ ህዝቡ ለስርዓቱ ይለውን ጥላቻና ለውጥ ፈላጊነቱን እንዲሁም እነሱ በተግባር የማያውቁትን ዴሞክራሲ ህዝቡ ሲዘምርላቸው፣ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከነሱ እንደሚሻል ሲያሳያቸው፣ ይበጁኛል የሃገሬንና የእኔን ህልውና ይጠብቁልኛል፣ ብሩህ የነፃነት ጊዜ ያመጡልኛል ይሆኑኛል ብሎ የሚላቸውን እንደራሴዎቹን ሲመርጥ ለአፍታ ይስተዋልባቸው የነበረው ሰዋዊ ባህሪየቸው ጠፍቶ ጫካ ተወልዶ ጫካ ያደገው አውሬነታቸው ሲመለስ የሚችሉትን ገለው ገሚሱን ወደ ማጎሪያቸው አግዘው ጭልጭል ትል የነበረች ተስፋችንን አደበዘዟት፡፡
ከዚህ በሗላ ያለችው ኢትዮጲያ የግል የህትመት ውጤቶች ሙሉ በሙሉ በማፈን በሃገራችው በሞያቸው ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ጋዜጠኞችን በማሰርና በማሳደድ፣ ለሃገራችን ክብርና ለህዝቧ ነፃነት የሚሟገቱ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት ወይም በሃገራቸው በነፃነት የመኖር መብት አጥተው የሚሰደዱባት አልያም የነሱ የሆነው በሌሎች ተቀምተው የመከራ ቀንበር ከብዶ በግዞት የሚኖርባት ስትሆን ለኢምንት ባለ ጊዜዎች ግን የምድር ገነት ሆና ያሻቸውን የሚሆኑባት የግል እርስት አድርገዋታል፡፡
ይህ ከላይ ያነሳሁትና ተነግሮ የማያልቀው በህዝብ በሃገር ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ በወያኔ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን የኛም ግፍና በደልን የመሸከም አቅም ወይም እንደ ሰው መብታችንን የማስጠበቅ፣ ህልውናችንን ያለማስደፈር ወይም በውርደት መኖር በቃኝ ብለን ሃላፊነታችንን ሳንወጣ እንዲሁ ከድርጅት ድርጅት ስንላተም፣ ከፓርቲ ፓርቲ ስንከለስ በተዘዋዋሪ የወያኔ መሳሪያ ሆነን በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የሚደርሰውን በደልና እንግልት ዘመን እናሻግራለን፡፡
ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ገዢዎቻችን ከተፈጥሮ ባህሪያቸው አንፃር የፈለጉትን ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብ ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ ህዝብ እንደ ህዝብ በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብሎ ለለውጥ እንዲነሳ በህብረት ከመስራት ይልቅ የነሱን መበታተንና መሰነጣጠቅ አውርተን በድክመታቸው ሳንጠቀም መልሰው ተደራጅተው መብትና ክብራችንን ሲገፉንና ሲፃረሩን እናያለን፡፡ ሃገርና ህዝብን ከዚህ እኩይ ስርዓት መታደግን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ትተን በሰሞነኛ የወያኔ የጭካኔ ገድል ላይ ቡና እየጠጣን ስናነሳና ስንጥል ከወሬ የዘለለ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ሳንገባና የታደሉት ለሃገራቸውና ለህዝባቸው የሚከፍሉትን መስዋህትነት የሚሰሩትን ታላቅ ስራ ስናፈርስና ስንክብ የዜግነት ግዴታችንን በአግባቡ ሳንወጣ ለገዢዎቻችን መሳሪያ ሆነን በዛ ደሃ ህዝብና ሃገራችን ላይ ቁማር እንጫወታለን፡፡
ነፃነት በወሬና በዲስኩር አይመጣም የመስዋህቱ አይነት የለያይ እንጂ አነሰም በዛም የነፃነት ትግል ወይ ሃብትን ወይም የህይወት መስዋህትነት ይፈልጋል፡፡ ዶክተር መርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር እንዳለው “ለውጥ በመንኮራኩር ተጭኖ የሚቀርብ ነገር አይደለም ሊገኝ አይችልም፣ በማያቋርጥ ትግል እንጂ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን ለነፃነታችን መጣር አለብን ወገብህ ለመጥ ካላለ ጠላትህ ሊጋልብህ አይችልም. . . . . ከልምድ እንዳየነው ጨቋኝ ገዢ ነፃነትን በፈቃደኝነት አይሰጥም በተጨቋኞች መገደድ እንጂ” ይህ ነው እውነቱ ይህንን ሁሉ በህዝብና በሃገር ላይ የሚደርሰውን ለከት ያጣ ጭቆና የምናይና የምንሰማ በተለይ በሰለጠነው አለም የምንኖር ወገኖች እኛ በሰው ሃገር የምናገኘውን ነፃነት ወገናችን በገዛ ሃገሩ ሲያጣ፣ ይህ ነው የማይባል ችግር ሲወርድበት ከወሬ ያለፈ በተግባር የተፈተን ስራ መስራት ስለምን ተሳነን፣ ስለምን የህይወት መሰዋትነት ለሚከፈልበት የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማገዝ ሰነፍን፣ስለምን ከወያኔ ለምናገኝው ቁራሽ መሬት ብለን የወገኖቻችንን የመከራ ጊዜ እናራዝማለን፣ ቁጥር ስፍር የሌለው ህዝብ በውጪው አለም እየኖረ ስለምን የህዝባችን የመረጃ ምንጭ የሆነው ኢሳት መስራት ያለበትን ያህል እንዲሰራና ህዝባችን እየተራበ መጥገቡን፣ እየከሰረ ማትረፉን፣ እየተቸገረ መበልፀጉን ከሚነግረው የወያኔ ዲስኩር አውጥተን አማራጭና እውነተኛ መረጃ የሚያገኝበትን፣ ወያኔ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው እያደረገ ያለውን ዘርን ከዘር ሃይማኖት ከሃይማኖት የማጋጨትና የመሳሰሉትን የወያኔን ሴራ ህዝቡ እንዲያቅና በአንድነት ለመብቱና ለነፃነቱ እንዲነሳ ኢሳትን በመረዳት የዜግነት ግዴታችንን አንወጣም?
በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የሗሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው አስተሳሰብና የሃይል አገዛዝ ተሸብቦ ያልደረሰበት ጫፍ፣ ያላስነባው ህዝብ፣ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፣ ያላፈረሰው አንድነት፣ያላዋረደው የህዝብ ስብእና፣ ያልገባበት የእምነት ተቋም፣ ያልበተነው የሞያ ማህበራት ከከተማ ነዋሪ እስከ ገበሬው አልፎም እስከ አርብቶ አደሩ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም፡፡
በአሁኑ ወቅት አዛዥና ታዛዥ የሌለበት የወያኔ ስርዓት ዘመኑ እያከተመ መሆኑን ከሚሰራቸው ስራዎች መገንዘብ አይከብድም ህግ ማሰከበር ያለበት መንግስት ላወጣው ህግ መገዛት የማይችልበት ደረጃ ከደረሰ ህልውናው አደጋ ውስጥ ለመሆኑ ማሳያ ነው ለዚህም መብቱን በወያኔ የተነጠቀው ህዝብ የህገ-መንግስቱን አንቀፅ እያሳየ የህግ ያለህ ሲል መደመጡ፡ በግምት የሚመራን ስርዓት የመጨረሻው ጠርዝ ላይ መቆሙን አመላካች ነው፡፡
ስለሆነም ኢትዮጲያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማረግ ለነፃነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ከወሬ በዘለለ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!
ሞት ለወያኔ!!!

ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል

#Ethiopia #StopCensorship

From  Zone 9  blog
FreddomofSpeech.phpለምዕራባዊያኑ የመጨረሻ  ወር በሆነው ዲሴምበር ወር መጀመርያ በሀገረ አሜሪካ ኢትዮጵያዊውን ጦማሪ እና እስክንድርነጋን ለማሰብ የተዘጋጀ መድረክ ነበር፡፡ በመድረኩ ላይ ስለ እስክንድር ነጋ የተናገሩት ተዋናይ ሊዬቭ ሽሬ የይበር እና ጸሐፊ ካርል በርንስቴይን ነበሩ፡፡ በርንስቴይን  ከ40 ዓመታት በፊት የዋሽንግተን ፖስት ዘጋቢ ሆኖ በሚሠራት ወቅት ከባልደረባው ቦብ ዉድወርድ ጋር በመሆ ን በአሜሪካ መንግስት ታሪክ ትልቅ የተባለውን እና የዋተርገቱ ቅሌት በመባል ሚታወቀውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ያሳተፈ የሙስና ቅሌት አጋልጠዋል፡፡ በነዚህ ሁለት ዘጋቢዎች ታሪካዊ ማጋለጥ ምክንያት በወቅቱ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ሆኗል፡፡
የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሳሌ ተደርጋ የምተጠቀሰው አሜሪካ በወቅቱ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ አቅም የሚያንሳት ሀገር አልነበረችም፡፡ የፖለቲካ ባህሏም (በጥቅሉ) ተጠያቂነትን የሚያበረታታ እና ሙስናን የመሰሉ ተግባራትን አፀያፊ አድርጎ የሚቆጥር ነበር/ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህም ሥርዓት መሐከል ግን እንክርዳድ አይጠፋውም፡፡ እናም መደበኛው የተጠያቂነት ሥርዓት ያልደረሰበትን ማማ አራተኛው የመንግሥት ክንፍ  (fourth organ of government) በመባል የሚታወቀው ሚዲያ አጋለጠው፡፡
ነጻ የሆኑ መገናኛ ብዙኃን መኖር እና ዜጎች ሐሳባቸውን መግለጽ እና መወያየት መቻላቸው የመንግሥትን እና የባለሥልጣናቱን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሕዝብን ከአደጋ ለመጠበቅ ቁልፍ መሣሪያዎች ናቸው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ ሀገራት እያንዳንዱ የመንግሥት መዋለ ነዋይ ለሚፈለግለት ዓላማ መዋል አጥብቆ የሚፈለግ ነገር ነው፡፡ እውነታው ግን ይሄ አይደለም፡፡ በደሃ ሀገራት ስልጣን የሚይዙት ሰዎች/የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን አንድም የራሳቸውን ግለሰባዊ ችግር ከሀገሪቱ ችግር በማስቀደም ወይንም በስግብግብነት አልፎ አልፎም ደግሞ ከብቃት ማነስ ሀገራቸው እጅግ አድርጋ የምትፈልገውን መዋለ ነዋይ ያባክናሉ፡፡ ይባስ ብሎም አብዛኞቹ ደሃ ሀገራት የሚመሩት ሁሉንም ነገር መቆጣጠር በሚፈልጉ እና ለምንም አይነት ነጻነት እና መብት ደንታ በማይሰጣቸው መሪዎች  (totalitarian) ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የሀገር ሃብት ሲመዘበር እና አለአግባብ ጥቅም ላይ ሲውል ለምን ብሎ የሚጠይቅ አካል አይኖርም፡፡ ካለምፍዳው እጅግ ብዙ ይሆናል፡፡
የሕዝብ ውክልና የሌላቸው/የሚጎላቸው የድሃ ሀገራት መሪዎች ስልጣን ላይ በሕይወት እስካሉ ድረስ ለመቆየት ሀገራቸው ላለባት ምጣኔ-ሃብታዊ እና ሌሎችም ችግሮች እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ አብዛኛዎቹ መሪዎች ሕዝብ በከፈለው ግብር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙኃንን የራሳቸውን ተረክ ለመፍጠር ይጠቀሙበታል፡፡ እነሱ ከሌሉ ሀገሪቷ የምትገባበትን ‹ሲኦል›  ይሰብኩበታል፡፡ ይህ ብቻ አይበቃቸውም፡፡ ምንም ዓይነት የተለየ ተረክ ለሕዝብ እንዲደርስ አይፈቅዱም፡፡ የሐሳብ አሀዳዊነትን በሕዝብ ላይ ለመጫን ይመቻቸው ዘንድ የበይነ-መረብ ማጥለል፣ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ጋዜጦች፣  መጽሔቶች ይዘጋሉ፤ ጋዜጠኞችን ያዋክባሉ፣  ያስራሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ሀገርን የሚጠቅም ነው ብለው የሚያወጧቸው ምጣኔ-ሀብታዊ (ሌሎችም) ፖሊሲዎችን የተለየ ምልከታ ሰጥቶ ጥቅሞቹን እና ጉድለቶቹን ተንትኖ እና ከሕዝብ ፍላጎት ጋር ያላቸውን መጣጣም አመዛዝኖ ለሕዝብ የሚያቀርብ አማራጭ እንዳይኖር ያደርጋሉ፡፡ እናም ፖሊሲዎች መታረም ከሚችሉት ህፀፆቻቸው ጋር በሰሠሯቸው ሰዎች ተደጋግመው ከተወደሱ በኋላ ወደሥራ ይገባሉ፡፡
እነዚህ መሪዎች አንድ መሠረታዊ የሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮን ዘንግተዋል፡፡ ማንኛውም ጤነኛ ሰው የሚቀበለውን መረጃ እንደተሰጠው አይውጠውም፡፡ ሁልግዜም ባይሆን ባመዛኙ፣  የሰው ልጆች የሚሰጣቸውን መረጃ ማመዛዘን ይፈልጋሉ –  በተለይም ድጋፍ መስጠት/አቋም ሊይዙበት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሲሆን፡፡ አማራጭ ትንተና ያጡ ዜጎ ችአንድ አንዳንዶቹ (ጥቂቶቹ) የራሳቸውን ትንተና በመስጠት አቋም ሲወስዱ አብዛኞቹ ለድጋፍም ሆነ ለተቃውሞ የሚበቃ አቋም ለመውሰድ በቂ ትንተና ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡በመጨረሻም ፖሊሲውን ተፈፃሚ ለማድረግ የሕዝብ ተሳትፎ/ድጋፍ አጥሮናል ብለው የሚያማርሩ የመንግሥት ድምፆችን መስማት እንጀምራለን፡፡
ምጣኔ ሃብት እና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት
እ.አ.አ 1989 ድሬዝ እና ሴን የተባሉ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪዎች ባያደረጉት ጥናት ነጻ መገናኛ ብዙኃን ባለበት ሀገር አንድም ግዜ ረሀብ ተከስቶ እንደማያውቅ ጠቁመዋል፡፡ ይህንንም ሲደግፉ ነጻ የሆነ የመረጃ ፍሰት ባለባቸው ሀገራት መንግሥታትን (ዴሞክራሲያዊ ባይሆኑም እንኳን) ከሕዝብ የሚመጣ ጫና ውስጥ ስለሚከታቸው እና ይህንንም ለማስወገድ ሲሉ ቀድመው የሕዝብን ጥያቄ የሚመልስ እርምጃ ስለሚወስዱ እንደሆነ ይተነትናሉ፡፡ ኢሻም፣ ካፍ ማን እና ፕሪቼት የተባሉ ምሁራን እ.አ.አ  1997 ባደረጉት ጥናት መሠረት ደግሞ ግለሰባዊ ነጻነቶች  (ሐሳብን የመግለፅን ጨምሮ) ማክበር በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ምጣኔ-ሃብታዊ ውጤት  (Project’s Rate of return) እስከ 20 በመቶ ያክል ድረስ ይጨምረዋል፡፡ እንደነዚሁ አጥኚዎች ትንተና መሠረት ግለሰባዊ መብቶችን  (ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ/የመሰብሰብ ነፃነት፣ ሐሳብን በነፃነት የመያዝ እና የመግለጽ፣ ሕዝባዊ ጉዳዮች ላይ በነፃነት የመሳተፍ እና ነፃ ማኅበር ማቋቋም) አለማክበር በእኩል መጠን ከሚከሰት የዓመታዊ ምርት መቀነስ፣ የበጀት እጥረት ወይንም የወጪ እና ገቢ ንግድ ላይ ከሚያጋጥም ንዝረት ባልተናነሰ ሁኔታ በመንግስት የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ውጤታነት ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡
እንደ በመንግስት የሚተዳደሩ ፕሮጀክቶች ባይሆንም በግል ባለሀብቶች እና ተቋማት የሚካሄዱ ንግዶች ሐሳብን በነጻነት መግለጽ በሚቻልበት ሀገር ለገበያ የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች እና አገልግሎቶች የኅብረተሰቡን ደኅንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል እንዳይሆኑ ከፍ አድርገው ይጠነቀቃሉ፡፡ በግድየለሽነት ወይንም በአጭር ጊዜ ለመክበር በሚያደርጉት ሙከራ የህብረተሰቡን ደህንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል ዕቃ ወይንም አገልግሎት ቢያቀርቡ ነፃ መገናኛ ብዙሃን ሁኔታውን በማጋለጥ ህብረተሰቡን ከጉዳት ይጠብቃሉ፡፡
የሳንሱርዋጋ
የሐሳብ ብዝኃነትን በመቆጣጠር ሕዝብ እነሱ የሚሉትን ብቻ እየሰማ እንዲነዳ የሚፈልጉ መንግሥታት ሐሳብን ለማፈን ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ሐሳብ ለማፈን ከከሚጠቀሙባቸው መንገዶች በይነ መረብን ማጥለል እና ጦማሮች እዳይከፈቱ ማገድ፣ በይነመረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ መሰለል እና በሳተላይት የሚተላለፉ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች ሞገዶችን መከልከል ይጠቀሳል፡፡
የአውስትራሊያ መንግስት  በ2009 ዓ.ም ሊተገብረው ያሰበው የበይነ መረብ ማጥለልን በተመለከተ ዴቪድ በርድ የተባለ ጦማሪ እንደጻፈው በበይነ መረብ የሚተላለፉ መረጃዎችን ለማጥለል ጥቅም ላይ የሚውሉት ቴክኖሎጂዎች የበይነ መረብ አገልግሎት ፍጥነትን ከ2 በመቶ እስከ 70 በመቶ ይቀንሳሉ፡፡ የማጥለል ሥራውን  ‹በውጤታማነት የሚያከናውኑት› ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ፍጥነቱን በደንብ የሚቀንሱት ናቸው፡፡
ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ደግሞ ኒውዮርክ ታይምስ አንድዜና ለኢትዮጵያዊያን ይዞልን ወጥቶ ነበር፡፡ ፊንፊሸር የተባለ በይነ መረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ ስለላ ለማድረግ የሚያስችል የረቀቀ ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀሙ ከታወቁት  10 ሀገራት አንዷ ሀገራችን መሆኗን፡፡ እንደዘገባው ቴክኖሎጂውን ለመግዛት ከ350ሺህ  በላይ የአሜሪካን ዶላር ወጪ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ቁጥር አንድ ጠላቷ ድህነት ለሆነ ሀገር ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ ዜጎች ላይ ለመሰለል ይህን ያህል ወጪ ማውጣት እውነትም አሀዳዊ ተረክ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደሚኬድ ማሳያ ነው፡፡
በሳተላይት የሚተላለፉትን ሬዲዮ እና የቴልቪዥን ስርጭትን ለመደገፍ ምን ያህል የተወሳሰበ ቴክኖሎጂ እንደሚያስፈልግ እና እሱም ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጣ መገመትም ቀላል ነው፡፡
ምንም እንኳን አከራካሪ ቢሆንም ዜጎች በነጻነት ሲያስቡ እና ሐሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ሲችሉ አዳዲስ እና ውጤታማ የንግድ ሐሳቦች ማፍለቅ ቀላል ይሆንላቸዋል፡፡ ይህም ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መንፈግ ከሚያስከፍሉት ቀጥተኛ ያልሆኑት ዋጋዎች ውስጥ ሊካተት ይችላል፡፡

Feb 24, 2013

ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ

ድምፃችን ይሰማ

በእርግጥ ግለሰቡ የባለስልጣን ግብር አላቸው?
ባሳለፍነው ሳምንት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ዲኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ኢትዮ ቻናል ከተባለው ጋዜጣ ጋር አንድ ቃለመጠይቅ አድርገው ነበር፡፡ ጋዜጣው የመንግስት ፕሮፓጋንዳ መንዣ መሳሪያ ከሆኑ ‹‹የግል›› ጋዜጣዎች ውስጥ አንዱ እንደመሆኑ ምን አይነት ይዘት ያለው ነገር እንደሚያወጣ ለብዙዎች ድብቅ አይደለም፡፡ ያወጣውም ብዙዎች ከሱ የሚጠብቁትን ፕሮፓጋንዳ አይነት ጽሁፍ ነበር፡፡ ኢቲቪ የፍርድ ቤት ትእዛዝን ጥሶ ባስተላለፈው አሳፋሪ ‹‹ዶኩመንታሪ›› ፊልም የተነሳ የደረሰበትን ውግዘት እና የፕሮፓጋንዳውን መክሸፍ ሊያስተባብሉ ነበር አቶ ሽመልስ ከማል በኢትዮ ቻናሉ ቃለ መጠይቅ ብቅ ያሉት፡፡ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ
ቃለ መጠይቁ ከአንድ ትልቅ የመንግስት ባለስልጣን እንደመምጣቱ ጨዋነትን የተላበሰና ደረጃውን የጠበቀ መሆን በተገባው ነበር፡፡ ያ ግን አልሆነም፡፡ አስገራሚ በሚባል ደረጃ ከቃላት አጠቃቀሙ ጀምሮ በሁለመናው ዝቅ ያለ እና የወረደ ነበር፡፡ ቃላቶቹ ተራና ‹‹የመንደር›› ከመሆናቸውም ሌላ ግለሰቡ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የሻቸውን የሚናገሩ እንደሆኑ ያሳብቁ ነበር፡፡ አንድ የመንግስት ባለስልጣን የሚናገራቸውን ነገሮች የኋላ ውጤት ያለምንም ማገናዘብ እንዳመጣለት መናገሩ አገራችን ውስጥ በመንግስት እና በግለሰብ መካከል ያለው ለውጥ ከነጭራሹ እየጠፋ መምጣቱን እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡
ግለሰቡ በረዥሙ ቃለ መጠይቃቸው በርካታ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡ ሁሉንም እዚህ እያነሳን ልንነጋገርባቸው ባንችልም የተወሰኑትን ብቻ ጠቀስ ጠቀስ እያደረግን ምልከታችንን እንሰጥባቸዋለን፡፡
አቶ ሽመልስ በቃለ መጠይቃቸው እጅግ አብዝተው ያነሱት ስለ ‹‹ሽብርተኝነት›› ነው፡፡ የተለያዩ ፖለቲከኞች ስለሽብርተኞች እና አልቃይዳን ስለመሳሰሉ ድርጅቶች የተናገሯቸውን አንዳንድ ጥቅሶች እየጠቀሱ፣ ስለፈንጂ ጉዳት እያነሱ ከኛው ሰላማዊ እንቅስቃሴ መሪዎች ጋር ለማገናኘት ይሞክራሉ፡፡ ሁለቱ የሰማይና ምድርን ያህል የሚራራቁ ነገሮች እንዴት እንደተገጣጠሙላቸው ግልጽ አይደለም፡፡ ‹‹… ይሄ ሴራ ተግባራዊ ሆኖ ቢሆን ኖሮ በበርካታ ንፁኃን ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ኑሮ ላይ፣ በህይወታቸው፣ በንብረታቸው ላይ በግምት ሊሰፈር የማይችል እጅግ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል እሙን ነው፡፡ ስለዚህ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ከፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ጋር ባደረገው ክትትል ይሄንን ሴራ ገና በእንጭጩ ለማምከን ችሏል›› ሲሉም የማይመስል ነገር ይናገራሉ፡፡ አመት ያለፈው እንቅስቃሴያችን ሰላማዊ ብቻ መሆኑ አይደለም ለአገራችን ይቅርና ለዓለምም ተረጋግጧል፡፡ መንግስት በየጁሙአው ‹‹ድንጋይ ይወረወራል›› በሚል ተስፋ እንዲሰባበሩ አንዋር መስጊድ በተቃውሞ ሰአት የሚያስቆማቸው አንበሳ አውቶቡሶች እንኳን አንድም ቀን የመሰበር እጣ አላጋጠማቸውም፡፡ አቶ ሽመልስ ግን በኢቴቪ የተላለፈውን መረጃ አልባ ዶኩመንተሪ ‹‹ባናሳየው ኖሮ አገሪቷ ትፈርስ ነበር›› ለማለት ይዳዳቸዋል፡፡ ይህንኑ ‹‹ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል›› የሚለውን ንግግር ከመደጋገም ባለፈ አንዳችም ማስረጃ ያላቀረበውን ፊልማቸውን እየጠቆሙም ሌላ አስገራሚ ነገር ይነግሩናል፡-
‹‹እነዚህ ሰዎች ከኃይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን መነሻቸውም፣ ማምሻቸውም፣ ግባቸው ፖለቲካዊ መሆኑን እነሱ የሚፈልጉትን የአንድ እምነት ህግጋት እና ይሄንን ህግጋት የሚያስፈፅም አምባገነናዊ ኃይማኖታዊ መንግስት የመገንባት ዓላማ ያላቸው መሆኑን የሚያጋልጡ በርካታ ሰነዶች እየወጡ ነው፡፡ የዚህ ሰነድም አንደኛው የዶክመንተሪው ዓላማም ይሄ ነበር›› ይሉናል፡፡ ፊልሙ ላይ ሕዝቡ እንደተመለከተው ከኮሚቴዎቻችንም ሆነ ከሰላማዊ እንቅስቃሴያችን ጋር የተያያዘ በርካታ የሰነድ ማስረጃ ይቅርና አንድ እንኳ ሰነድ ሊቀርብ አልቻለም፡፡ ይህንን ፊልሙን ያየ ሁሉ አይቶታል፡፡ በተመልካቹ ዘንድ ዜሮ ተቀባይነት ያገኘውም በዚሁ እንደሆነ የዘነጉት ይመስላሉ – አቶ ሽመልስ፡፡
ወረድ ብለው ደግሞ ግለሰቡ ሌላ አስገራሚ ነገር ጠቅሰዋል፡፡ ኮሚቴዎቻችንን አስመልክቶ የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥተዋል፡- ‹‹…እነዚሁ የምናውቃቸው ዛሬ የሙስሊም መሪዎች ነን ምንትሴ ነን እያሉ የወጡ አክራሪዎች ናቸው – እነሱ ናቸው ይሄንን ስብከት የሚያሰራጩት – ይሄን መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም አበጥሮ ያውቀዋል፡፡ በዚህ የሚታለል የለም – ዓላማው ይሄ እንዳልሆነ ይታወቃል›› ብለዋል፡፡
ቃለ መጠይቁን የሞሉትን ‹‹ምንትስ…. ቀጣፊ›› … ወዘተ አይነት ቃላቶች አቶ ሽመልስ ለተቀመጡበት ወንበር እንኳ የማይመጥኑ አሳፋሪ መሆናቸውን ለጊዜው ትተነው ሀሳቡ ግን እጅግ ከእውነታ የራቀ መሆኑን ማስግዘብ ያሻል፡፡ ‹‹መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም አበጥሮ ያውቀዋል›› ማለታቸው በተለይ ትልቅ ሹፈታቸው ነው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙማ ከማን ጋር እንደሆነ በበቂ ሁኔታ አሳይቷል፡፡ ‹‹መሪዎቻችን ይፈቱ!›› የሚል ድምጹን በኢድና በአረፋ ሚሊዮኖች ሆኖ፣ በሌሎችም በርካታ የጁምአ ስግደቶች በተደጋጋሚ አረጋግጧል፡፡ ግለሰቡ ‹‹አክራሪዎች›› ሲሉ ያንጓጠጧቸውን ኮሚቴዎች ህዝበ ሙስሊሙ ‹‹ብርቅዬ የሰላም አምባሳደሮቻችን›› እያለ ነው የሚጠራቸው፡፡ በጥር ወር 2005 ብቻ በአገር አቀፍ ደረጃ 35 ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተደርገዋል፡፡ ሕዝቡ ወደ አደባባይ የወጣው ለምን እንደሆነም መንግስትና ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፉ ማህበረሰብም ጭምር ያውቀዋል፡፡ መንግስት አመቱን ሙሉ በዚህ ጉዳይ ተወጥሮ የቆየውኮ ጉዳዩ የህዝብ እንጂ ‹‹የጥቂት አክራሪዎች›› ስላልሆነ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ አቶ ሽመልስ ሳያውቁት ቀርተው አይደለም – የፖለቲካ ስራ ሆኖባቸው እንጂ፡፡
ሌላ ንግግራቸውን እንመልከት፡- ‹‹የሽብርተኝነት ዋና ዓላማ ህብረተሰቡን ተከታታይ የሆነ የፍርሀትና የሥነ ልቦናዊ ሰቀቀን ውስጥ መክተት ነው፡፡ የፖሊስ ሥራ ደግሞ ከወንጀል ሥራ እና ፍርሀት፣ ከወንጀል ሥጋት ነፃ ማውጣት ነው›› ይሉናል፡፡ ይህን በመርህ ደረጃ መቀበል ለማንም አይቸግርም፡፡ ለሽብርተኝነት ጥሩ ገለጻ ነው የሰጡት አቶ ሽመልስ፡፡ እስቲ ራስዎ ባወጡት መስፈርት እያሸበረ ያለው ማን እንደሆነ እንመልከት፡፡
ሰሞኑን በውድቅት ሌሊት የታጠቁና ፊታቸውን በጭምብል የሸፈኑ ፖሊሶች በየሰፈሩ የሙስሊሞችን ቤት ያለምንም የፍርድ ቤት ማዘዣ ዘልለው እየገቡ፣ እየደበደቡና ያገኙትን ውድ ንብረት (ወርቅና ብር) በግድ እየዘረፉ፣ ከዚያም አልፈው በቤቱ የሚገኘውን ቅዱስ ቁርአንና አረብኛ የሀዲስ መጽሀፍት ‹‹ይተረጎማሉ›› በሚል እየወሰዱ ነው የሚገኙት፤ ልክ እንደ ደርግ ዘመን! ሙስሊሙ በየቤቱ ስጋት ውስጥ ነው ያለው፤ ሽብር ውስጥ!!! እያሸበረው ያለው ደግሞ እርስዎ ‹‹ሥራው ህዝቡን ከወንጀል ሥራ እና ፍርሀት፣ ከወንጀል ሥጋት ነፃ ማውጣት ነው›› ሲሉ ያንቆጳጰሱት ‹‹ፖሊስ›› ነው፡፡ በየጁምአው የሰላማዊውን ሙስሊም ድምጽ ለማፈን ጠመንጃውን ወልውሎ ቆመጡን እየወዘወዘ የሚወጣው የእርስዎና የባልረቦችዎ ታዛዥ የፖሊስ ሀይል ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ተገለባብጧል… እርስዎ ደግሞ የሚነግሩን ሌላ እኛ የማናውቃት ኢትዮጵያ ያለች እንዲመስል አድርጎናል…. መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ የማይገባባት…. ፖሊስ ህዝቡን ከስጋት የሚጠብቅባት…!!!
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
አላሁ አክበር!

Feb 23, 2013

Ethiopian Minister Junedin seeks Asylum in Kenya


EthioChannel’s cover story on Junedin
EthioChannel, pro regime “private” Saturday Newspaper has today reported that
top ruling party official and “the Minister of Civil Service” has sought asylum in
neighboring Kenya. A political scientist with a close knowledge of the former
Minister that De Birhan talked to said that Junedin’s family couldn’t confirm the
Report and that he was not contactable.
Junedin Sado’s wife, Habiba Mohammed, is one of 29 people facing terrorism
charges related to protests by Muslims. Junedin last year published a letter in the
same newspaper defending his wife and criticizing the federal prosecutor’s charges.
In the letter, Mr. Junedin said that he had approached the Saudi Arabian Embassy
in his personal capacity to raise money to build a mosque to fulfil the wishes
expressed in the will of his late mother. The money recovered from his wife, Mr.
Junedin said, was meant for the mosque and not to fund terrorist activities.
Habiba was charged in October 2012 with funneling money from the Embassy of
Saudi Arabia to Islamist terror groups, at a hearing at the Ethiopian Federal High

Court.
Jundein was president of the Oromia Region from 28 October 2001 until 6 October
2005. He subsequently was appointed Transport and Communication Minister,
which is the office he was holding when Prime Minister Meles Zenawi moved him to
the Science and Technology Ministry October 2008. Following the 2010 general
election, Junedin was appointed Minister of Civil Service until November 2012
Prime Minister Hailemariam replaced him with another Minister in his Ministerial
reshuffle. The Oromo People’s Democratic Organisation (OPDO), a constituent of
the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front, the ruling coalition had also
expelled him from the Organisation. It was reported that after “self criticism he was
readmitted and secured his posts”. He previously served as the president of the
OPDO. Although the Ethiopian Parliament had the plan of “removing Junedin’s
immunity” it in its agenda, it was not implemented to that effect. Junedin has also
been the Board Chairman of Addis Abeba University (AAU).
Junedin was one of the “most powerful” ruling Party officials who represented the
regime in various international and local duties. He was also one of the few Ministers
that represented the ruling Party in the Ethiopian General election debates. A close
confident and loyal of the late Prime Minister Meles Zenawi, Junedin was one of the
ardent critics of Ethiopian opposition and Muslim critics/protesters, sources who
knows the Minister closely at the Oromia regional Council recount.
The paper also stated that it was not established how Junedin left for Kenya, so far.
Some sources close to De Birhan had informed us that Junedin had absconded to
Kenya with eight senior members of OPDO and colleagues. There are no details on
the whereabouts of his three underage children

Ethiopia: TPLF cadre exposed in Norway

Feb 22, 2013

ሰመጉ የተላለፈው ዘጋቢ ፊልም የተከሰሱ ሰዎችን ሕገመንግስታዊ መብት የጣሰ ነው ባወጣው መግለጫ አስታወቀ

የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰመጉ በዚሁ መግለጫው በፌዴራል ፖሊስና በብሄራዊ ደህንነት እና ጸጥታ ባለስልጣን ተዘጋጅቶ በኢቲቪ እንዲቀርብ የተደረገው ፊልም ተጠርጣሪዎቹ በሕገመንግስቱ መሰረት በተከሰሱበት ወንጀል ከፍርድ በፊት እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር መብታቸውን የጣሰ መሆኑን ጠቁሞ ይህ በመሆኑም ከአሁን በኋላ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤት የመከላከያ ምስክሮችን የማቅረብ አቅማቸው አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቅሶአል፡፡
የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ ደህንነት እና ጸጥታ ባለስልጣን እንደ ህገመንግስት ተቋምነታቸው በአሁኑ ሰአት በፍትህ ሚኒስቴር የፌደራል ማእከል አቃቢ ህግ በነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ በከፈተው የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ በምርምራ ያገኙትን ማስረጃ እንደሚያቀርቡ ቢጠበቅም፣ ተቛማቱ በህገመንግስቱ አንቀጽ 20 የተደነገገውን ዜጎች ፈርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር መብታቸውን በመጣስ ፣ ተከሳሾች ወንጀል ስለመፈጸማቸው አውጅዋል ሲል አስታውሷል።
ዘጋቢ ፊልሙ ፍርድ ቤቶች በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት የሚያዛባ ይሆናል ያለው ሰመጉ፣ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በመንግስት በኩል የተወሰደውን ድርጊት ከማውገዝ ባተጨማሪ ዘጋቢ ፊልሙን ያዘጋጁት እና እንዲሰራጭ ያደረገው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሚመለከተው የመንግስት አካልም ድርጊቱን በማውገዝ አስፈላጊውን ማስተካከያ  እንዲያደርግ ጠይቋል።

በአጋሮ በርካታ ሙስሊሞች መደብደባቸው ታወቀ

የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የጁመአን ስግደት ተከትሎ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ ቢሞክሩም የፌደራል ፖሊስ አባላት የሀይል እርምጃ ወስደዋል።
በርካቶች መታሰራቸውን፣ መደብደባቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል::
ከፍተኛ ተቃውሞ ከታየባቸው ከተሞች መካከል ሻሸመኔ አንዱ ሲሆን፣ በርካቶች በ04 መስጊድ ተገኝተው ድምጻችን ይሰማ መሪዎቻችን ይፈቱ ማለታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
ተመሳሳይ ተቃውሞዎች በበደሌ፣ መቱና ድሬዳዋ መካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሙስሊሙን ተቃውሞ ለማስቆም የተለያዩ ሙከራዎችን ቢያደርግም ተቃውሞው ከአዲስ አበባ ውጭ አድማሱን እየተስፋፋ ከመሄድ በስተቀር የመቀነስ ሁኔታ አይታይበትም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሜሪካ የሞኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ነገ ፌብሩዋሪ 23 በዋይት ሀውስ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ያደርጋሉ።
ድምፃችን ይሰማ ዋሺንግተን ዲሲ እንዳስታወቀው፤ ሰልፉ የተዘጋጀው የ ኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሞች ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማውገዝና ረዥም ጊዜ ላስቆጠረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ትግል አጋርነትን ለመግለጽ ነው።
የ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላነሱት የመብት ጥያቄ መንግስት ቀና ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ካለመሆኑም በላይ ህግን በሚፃረር ሁኔታ በመብት ጠያቂዎቹ ላይ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን የጠቆመው ድምፃችን ይሰማ፤ ከዚያም አልፎ በሙስሊሙ መሪዎች ላይ የእስር፣የግርፋትና የማንገላታት ድርጊት መፈፀሙን አመልክቷል።
ጥቂት የማይባሉ ሙስሊሞችም በደህንነት ሀይሎች ታፍነው ተወስደው እስካሁን ያሉበት ስፍራ አለመታወቁንም ኮሚቴው በመግለጫው ጠቅሷል።
እንዲሁም ከ 1000 በላይ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በእምነታቸው ሳቢያ ከትምህርታቸው መታገዳቸውን ኮሚቴው ኢሳትን በዋቢነት በመጥቀስ በመግለጫው አስፍሯል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናልም፤እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከሐምሌ 12 ጀምሮ 17 ዋነኛ የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል መሪዎችን ጨምሮ በርካታዎች እንደታሰሩ፣እንደተገረፉ እና እንደተሰቃዩ ሪፖርት ማውጣቱን ድምፃችን ይሰማ አስታውሷል።
ከፊል መንግስታዊ የሆኑ ተቋማትን ጨምሮ ዓለማቀፍና አገር አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የ ኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሞች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና በደል በተከታታይ ማውገዛቸውን ኮሚቴው አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና በእስር ላይ የሚገኙት መሪዎቻቸው በፖለቲካ ተጽጽኖ ስር ከወደቀ ፍርድ ቤት ፍትህን ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎ ፈጽሞ እንደማይጠበቅ ዓለማቀፉ ማህበረሰብና ለጋሽ ሀገራት ሊያውቁት እንደሚገባም ድምፃችን ይሰማ ዲሲ ጠቁሟል።
በመሆኑም የ ኢትዮጵያ መንግስት በራሱ ህዝቦች ላይ እየፈጸመ ያለው የመብት ጥሰትና ወንጀል እጅግ ሳይዘገይ በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት ያገኝ ዘንድ ኮሚቴው ጠይቋል።
የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድሞቻችንም በመንግስት የተለያዩ አፋኝ ፖሊሲዎችና አሠራሮች ተጠቂ መሆናቸውን እንደሚገነዘቡ ጠቀሰው የድምፃችን ይሰማ ዲሲ መግለጫ፤በመሆኑም ክርስቲያን ወንድሞቻቸው ነገ በዋይት ሀውስ ፊት ለፊት ሙስሊሞች በሚያካሂዱት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አብረው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል

የካቲትን የምንዘክረው ከሀገር በቀል ወራሪው ህወሃት ጋር በመፋለም ነው!!

ቀደምቶቻችንን የምናስታውስበት፣ ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ እና አንድነቷን ለማስጠበቅ ያደረጉትን  ተጋድሎ ከምንዘክርበት እለት አንዱ የካቲት 12 ነው። በዚህ ግዜ ይህንን ታሪክ ገልብጦ ለማበላሸትና ለመጻፍ የሚጥረውን፣ የአሁኑን የግራዚያኒ ትንሽ ወንድም ሀገር በቀል ዘረኛ መንግስት  የሆነውን ህወሃት/ኢህአዴግን ሀይማኖት፣ ዘርና ጾታ ሳይለየን የምንታገልበት ሁነኛ ወቅት ላይ እንገኛለን።
የቀድሞዋ የአፍሪካ ሀገራት የነጻነት ተምሳሌት የሆነችው እማማ ኢትዮጵያ፤ ዛሬ ሀገር በቀል በሆኑ የዘረኛ መዥገሮች ስብስብ ተጣብቃ የአበው መሰዋእትነት ከንቱ ይሆን ዘንድ ወያኔዎች እየሰሩ ነው። ጥንታዊ ታሪክን በመፋቅ፣ ባልተደረገና ባልተፈጸመ ታሪክ ለመተካት ወያኔ/ኢህአዴግ እያንዳንዱን የአበውን የታሪክ ማህደር በማጥፋት፣ እንደ አቡነ ጴጥሮስ የመሳሰሉ የጀግኖችን ሀውልት አሻራ በማፍራረስ ርካሽ የሆነ ግዚያዊ የፖለቲካ  ጥቅም ማስገኛ ስራ ላይ በመሰማራት ሀገራችንን ወደኋለዮሽ እድገት እየጎተቷት ይገኛሉ።
ሁለቱን ገዳዮች የሚያገናኛቸው፤ የግራዚያኒ ወታደር አበው ለነጻነታቸው ለአንድነታቸው ሲያደርጉት የነበረውን ተጋድሎ ለማስቆም፤ የህዝቡን የትግል ሞራል ለመግደል የአዲስ አበባን ነዋሪ ቁጥሩ 30ሺ የሚሆን ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ ፋሽስትነቱን ለማሳየት ያደረገው ያልተሳካ ሙከራ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያውያን ለነጻነታቸው የሚያደርጉትን ትግል ይህ አልገታቸውም። በተመሳሳይ ደግሞ ዘመን አመጣሹ የየካቲት አስራ አንዱ ወያኔም፤ እንደፋሽስቱ ሁሉ በንጹሃን ህዝባችን ላይ በጎንደር ስላሴ፣ በምርጫ 97፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ፣ በኦሮምያ፣ በአዋሳ፣ በሀረር አሁን ደግሞ በሙስሊሙ ወገናችን ያደረሰው ጭፍጨፋ፣ እስርና ግድያ ከግራዚያኒ ጋር ያመሳስለዋል። ልዩነታቸው ይሄኛው ሀገር በቀል ወራሪ መሆኑ ነው። ምን አልባትም ወያኔ ልደቴ ብሎ የሚጨፍርበት የካቲት 11 ለሱ የድል ቀን ሲሆን፤ ለእኛ ደግሞ አባቶቻችን የምናስታውስበት የመከራ ቀን ነው።
በየካቲት12 የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ፣ ለአንድነቱ፣ ለሀገሪቱ ከብር የፋሽስቱን ወራሪ ሃይል በመመከት፤ ልጅ አዋቂ ሳይለይ ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን በማስጨነቅ እየሞቱም አልበገርነታቸውን ያስመሰከሩበት ልዩ ቀን ነው። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት ሀገር እንድትሆንም በማድረግ፤ ወርሃ የካቲት ታሪካዊ ወርና በድል አጥቢያነት በሀገራችን እንዲሁም በአሁጉራችን አፍሪካ ዘለአለም እንዲታወስና እንዲዘከር አድርገው  አበው አልፈዋል። ይህን የማስጠበቅ ታሪካዊ የሞራል ግዴታ የማን ነው?
አበው የፋሽስቱን የግራዚያኒ ወራሪ ጦር ድባቅ በመምታት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ አድነው አስረክበውናል። በዚህ ታሪካዊ ገድል በሆነው በወርሃ የካቲት የተሰዉት ጀግኖች፣ የኢትዮጵያ ልጆች አጥንትና ደም መሰዋእትነት ከቶ ከታሪክ ማህደር የማይጠፋ ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። ይህ ትውልድ ይህን የማስጠበቅ የታሪክ ባለተራ ነው እንላለን።
ግንቦት 7፣ የአባቶቻችንን ጀግንነትና ወደር የሌለውን የሀገር ፍቅር፣ የሀገር ክብር፣ የቁርጠኝነት መንፈስና የአደረጉት መሰዋእትነት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ይታገላል። በቁርጥ ቀን ልጆች በቁርጥ ቀን ሰዓትም ለመድረስ፤ እስከመጨረሻው በመታገል ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣትና ይህን ድል ለማስመለስ፤ አስመልሶ ለትውልድ ለማስረከብ፣ ለማስጠበቅ እያንዳንዷን ደቂቃ ሊጠቀምባት ቆርቶ ተነስቷል።እርሰዎስ?
የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡- የኢትዮጵያ ጀግኖች እነ አጼ ሚኒሊክ፣ የበላይ ዘለቀ፣ እነ አብዲሳጋ፣ እነ ዘራይደረስ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አፄ ዮሃንስ፣ እንደ ቋራው ካሳ እና ሌሎችም በበቀሉበት፣ በተፈጠሩበት በጥቁር አፈር ምድር፤ ፀረ-ኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዘረኛ ሃይሎች መፈጠራቸው አሳዛኝ ታሪክ መሆኑን እኛም እንመሰክራልን። ይሁን እንጅ፣ ቅሉ ይህንን በሁለት ትውልድ መካከል የተፈጠረውን የሰማይና የምድር ልዩነት ቁጭ ብለን በማየት ከንፈራችንን እየመጠጥን የምንቀመጥበት ሰአት ላይ አይደለንም። ጥሪ ከወዲያ ማዶ እየተበራከተ ነው። የድረሱልን ጥሪ!
ስለዚህም መላው የሀገራችን ህዝብ ወያኔን ለማስገደድ አሊያም ለማስወገድ አቅሙ በፈቀደ ሁሉ በገንዘብ፣ በእውቀት በጊዜና ጉልበቱ በመርዳት ታግለን የካቲትን የመሰዋእትነት መንፈስ እያስታወስን፣ ግንቦት 7ን የህዝብ ድምጽ ለማስከበር ይህ ትውልድ ሞራላዊ ግዴታ አለበት እና እንነሳ! እንሂድ።
በአንጻሩ በወያኔ መንደር በአጋጣሚም ሆነ በጥቅም ምክንያት ያላችሁ፡- እንደ ጠዋት ጤዛ ብን ብለው ከሚጠፉ አምባገነኖች ጋር በመለጠፍ ህዝባችንና ሀገራችንን መበድልና ማሰቃየት ለታሪክ ተጠያቂነት ይደርጋል። በወንጀል ተባባሪነት ስለሚያስጠይቅ ከወዲሁ መንገድን በማስተካከል እምቢ ለህወሃት፣ በቃኝ ባርነት፤ በሚል የህዝብ አጋርነትና ድጋፍ ወደ አለው የነጻነት ትግል በመቀላቀል ከማይሻር፣ ከማይጠፋ የታሪክ ማህደር ውስጥ ራስዎትን ያስገቡ ዘንድ የካቲት ጥሩ አጋጣሚ ነው።
በተለይም ኢትዮጵያውያን አርበኞች በጠላት ላይ የወሰዱት የማያዳግም እርምጃ ለመድገም እና ኢትዮጵያን ከሀገር ውስጥ ጠላት ከሆነው ህወሃት ለመታደግ፤ ነፃነታችንን አሳልፎ ላለመስጠት፣ ብርቱ ክንዳቸውን በአኩሪ መሰዋእትነት ለማሳረፍ እና ሕያው ምስክር ለመሆን ከተነሱት ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ጋር ሆነን በጋራ በተባበረ ሃይል የምንታገልበት ጊዜ ዛሬ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

The Muslim Brothers Poem on ESAT Fundraising Program with Tamagne Beyene...

መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫልበአለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ችግሮችን መፈልፈያ መሣሪያ ሆናለች፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት ይዘናቸው (ምናልባትም አቅፈናቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ስንንከባለል የቆዩ ችግሮች ሞልተውናል፤ እያሰብን እነዚያን የቆዩ ችግሮቻችንን በመፍታት ፋንታ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈልን የተቆላለፉና የተወሳሰቡ፣ ውላቸው የጠፋ ችግሮችን ፈጥረናል፤ እየፈጠርንም ነው፤ አሁን በመፈጠር ላይ ያለው አዲስ ችግር እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚል ነው፤ እስቲ እንመልከተው፡፡
በሩቁ እንጀምር፤ እስላማዊ መንግሥታት ያቋቋሙ አገሮች አሉ፤ አንዳቸውም ሰላም የላቸውም፤ እስላማዊ ቡድኖች በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአረብ አገሮች በተጀመረው የፖሊቲካ እድገት ለውጥ በቱኒስያና በግብጽ እስላማዊ ቡድኖች አሸንፈው ሥልጣን ይዘዋል፤ በዚህም ምክንያት በቱኒስያና በግብጽ የለውጥ ጥያቄ አገርሽቶ አንደገና ሰዎች እየሞቱ ነው፤ በነዚህና በሌሎችም አገሮች የሚገኙት ወጣቶች የሚፈልጉት የሰው ልጆች ሁሉ መብቶች የሚከበሩባቸውና በሙሉ የግለሰብ ነጻነት የተረጋገጡባቸው አገሮች እንዲኖራቸውና በእኩልነት ኩሩ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ነው፤ የአንድ አገር ዜጎች የተለያየ ዘር፣ የተለያየ የቆዳ ቀለም፣ የተለያየ ቁመትና ውፍረት፣ የተለያየ ጾታና ዕድሜ፣ የተለያየ ቋንቋ፣ የተለያየ ሃይማኖት፣ የተለያየ የፖሊቲካ አመለካከት፣ የተለያየ ትምህርት፣ የተለያየ ሙያና የተለያየ ገቢ ሊኖራቸው ይችላል፤ የጋራ ማንነታቸው ዜግነት ነው፤ እኩልነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ አንድነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ እኩልነታቸውንና አንድነታቸውን የሚያረጋግጥላቸውና ሚዛኑን የሚጠብቅላቸው ከበላይ ሆኖ ሁሉንም የሚገዛው ሕግ ነው፡፡
በቡድን ወይም በጅምላ የሚያስቡ ሰዎች የሕግን ባሕርይ አያውቁትም፤ ‹‹ክርስቲያኖች እስላሞችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ ወይም እስላሞች ክርስቲያኖችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ በሚል አሉባልታ ላይ ክስ ተመሥርቶ ሕጋዊ ፍርድ መጠበቅ አይቻልም፤ በየትም ሆነ በማንኛውም ጊዜ ጽንፈኛ እምነትና አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ፤ እነዚህ ግለሰቦች ሕልማቸውንም ሆነ ቅዠታቸውን በስውርም ሆነ በአደባባይ ይገልጻሉ፤ ለምሳሌ በአሜሪካ ጥቁሮችንና ይሁዲዎችን ከአገሩ ጠራርገን እናወጣና ንጹሕ የነጮች አገር እንፈጥራለን የሚሉ ግለሰቦች አሉ፤ ይህ እምነት ለአሜሪካ ማኅበረሰብ መርዝ ነው፤ አሜሪካ የነጻነት አገር ነው፤ የነጭ ዘረኞቹ መርዛቸውን ለመንዛት መብት አላቸው፤ የዘረኞቹን መብት ለማፈን የሚወሰድ የጡንቻ እርምጃ ሁሉ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ይሽራል፤ ከዚያም በላይ የአሜሪካ መንግሥት በሚከተለው ዘዴ ከነጭ ዘረኞቹ የተሻለ አይሆንም ነበር፤ ስለዚህም ነጭ ዘረኞችን ለመቋቋም የሚወሰደው አርምጃ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ሳይሽርና ነጭ ዘረኞቹም እምነታቸውን የመግለጽ መብታቸው ሳይደፈጠጥ መሆን አለበት፤ የነጻነት ትርጉሙ ይህ ብቻ ነው፡፡
በሥልጣን ወንበር ላይ ስለተቀመጡ ብቻ አንድ ዓይነት የፖሊቲካ እምነት ብቻ ይዞ ሌላውን መደፍጠጥ፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የኦርቶዶከስ ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የእስልምና ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን ልማድና የአሠራር ባህል እየሆነ ሲሄድ ሁሉንም ነገር አንድ ዓይነት ብቻ ለማድረግ የሚታየው ጥረት የኢትዮጵያን ጉራማይሌ ባሕርይ የሚቃረን በመሆኑ ስር አይኖረውም፤ ይህ ሁሉም ሰው ሊያስብበት የሚገባው አንዱ ነገር ነው፤ ሁለተኛው አንድ ወይም ጥቂት ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እናቋቁማለን ቢሉ አገር የሚሸበርበት ምንም ምክንያት የለም፤ ኢትዮጵያን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አገር ለማድረግ የሚመኙም አሉ፤ ኢትዮጵያን ሃይማኖት-አልባ የጉግማንጉግ አገር ለማድረግ የሚፈልጉ አሉ፤ ኢትዮጵያ በአንድ አጋጣሚ ወንበሩ ላይ የወጣ ጉልበተኛ የሚያትምባትን እምነትም ሆነ ሃይማኖት የማትቀበል አገር መሆንዋ ተደጋግሞ የታየ ነው፤ ኢትዮጵያን የይሁዲ አገር ለማድረግ ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የክርስቲያን አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የእስላም አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ሁሉም አልሆነም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ሆና ዘልቃለች፤ ይህንን በማክሸፍ ለማንም ምንም ጥቅም አይገኝም፤ በአንጻሩ ደግሞ የሥልጣን ወንበሩ ላይ የወጡ ጉልበተኞች ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀውን የነጻነት ጮራ እያዳፈኑ የነጻነትን፣ የእኩልነትንና የሕግ የበላይነትን ዓላማ ለማክሸፍ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፡፡
የነጻነትና የሕጋዊነት መክሸፍ የሰላም ጠንቅ ነው፤ የሰላም መክሸፍ የልማት ጠንቅ ነው፤ የልማት መክሸፍ ደሀነት ነው፤ ደሀነት የሞት አፋፍ ነው፤ ይህንን ለመገንዘብ የሚያዳግተው ሃያ አንድ ዓመት የሞላው ሰው አለ? ኢትዮጵያን ለመምራት የሚደናበሩት ሰዎች ሁሉ ሃያ አንድ ዓመት አልፎአቸዋል፤ ነገር ግን ከላይ የተገለጸው የመክሸፍ ጉዞ ጭራሽ አይታያቸውም፤የሚታየውም ሲነግራቸው የተበለጡ ስለሚመስላቸው አይሰሙትም፤ ስለዚህም የሚታየውን ሳያዩ፣ የሚሰማውን ሳይሰሙ ጊዜ የሚበላውን ጉልበታቸውን ብቻ ተማምነው በጭፍን እንምራችሁ የሚሉትን ተከትለን ለእኛ በሚታየንና ለእነሱ በተሰወረባቸው ገደል ውስጥ ለምን አብረን እንግባ? አብረን ገደል በመግባት አንድነታችንን የምንጠብቅ የሚመስላቸው ሰዎች በሁለት በኩል ይሳሳታሉ፤ አንደኛ ከአገዛዙ መሪዎች ዘንድ የሎሌ ተከታይነትን እንጂ የአኩልነት አንድነትን አያገኙም፤ እኩልነት በሌለበት አንድነት አይፈጠርም፤ ሁለተኛ ወደገደል የሚጨምር አንድነትን መምረጥ ሕይወትን ትቶ ሞትን መምረጥ ነው፡፡
በሃያ አንድ ዓመት ውስጥ መክተፍ-መከታተፍ ሙያ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችና ድርጅቶች ሠለጠኑበት፤ መክተፍ-መከታተፍ አብሮ የመኖር ጸር ነው፤ አብሮ የመኖር ጸር የሚሆነው በፍቅር ፋንታ ጥላቻን፣ በሰላም ፋንታ ጠብን፣ በመረዳዳት ፋንታ መጋጨትን፣ በልማት ፋንታ ጦርነትን በመንዛት ነው፤ አንዳንድ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በግልጽም ሆነ በስውር እንደጠላት መቁጠርና በእነሱ ላይ ቂምን እንዲቋጥሩ ማድረጉ የማንንም የፖሊቲካ ቡድን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ይጎዳል እንጂ አይረዳም፡፡
አሁን ደግሞ በአንድ በኩል በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ በየገዳማቱና ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃትና በሊቀ ጳጳሳት ምርጫው ላይ አገዛዙ እያሳየ ያለው ጣልቃ-ገብነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን እያስቀየመና እያስኮረፈ ነው፤ በሌላ በኩል በእስልምና ሃይማኖት ላይም የሚታየውን ጣልቃ-ገብነት ተከታዮቹ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በርትተው በመቋቋማቸው እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ለጆሮ እየቀፈፈና በጣም አሳፋሪ እየሆነ ነው፡፡
ይህ በሃይማኖቶች ላይ የተጀመረው ዘመቻ ውጤት ይኖረዋል፤ ውጤቱ በአገዛዙ የውስጥም ሆነ የውጭ አመራሩ ላይ ከባድ ተጽእኖ ይኖረዋል፤ የሃይማኖቶቹ ጉዳይ እንደጎሣዎች መከታተፍ በኑሮ ላይ ብቻ ጫናውን የሚያሳርፍና በምድር የሚንከላወስ አይደለም፤ ወደሰማይ ያርጋል፤ የሰማይ ሠራዊትን ይጠራል፤ ያንን ኃይል እንኳን የኢትዮጵያ የጦር ኃይልና የአሜሪካውም አይችለውም፤ ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ ልብ ያለው ያስተውላል፤ ዶላር ነፍስን አይገዛም፤ ክብርን አይገዛም፤ ወዳጅንም አይገዛም፡፡
ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም፤ የካቲት 2005

ሰበር ዜና – አስመራጭ ኮሚቴው ለዕጩነት የለያቸው አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!

ሐራ ዘተዋሕዶ

  • ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አልተካተቱም
  • ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው አጠራጣሪ ኾኗል
  • የፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱ ከዕጩዎች ማንነት ጋራ በአግባቡ ይረጋገጥ
  • ‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ››› /ሰሞንኛ አባባል/
የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩ ፓትርያሪክነት አጣርቶ የለያቸውን አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ማቅረቡ ተሰማ፡፡ ከየካቲት ዘጠኝ ቀን ጀምሮ የዕጩዎች ልየታ ሲያካሂድ የቆየው አስመራጭ ኮሚቴው÷ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ስም ዝርዝር፡-
1)  ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ
2)  ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – የወላይታ ዳውሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3)  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4)  ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
5)  ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡
የአስመራጭ ኮሚቴው አጣርቶ ሊያቀርባቸው ከሚችላቸውና የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አባቶች አራቱ በኮሚቴው የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ኮሚቴው በሚያቀርባቸው ዕጩዎች ውስጥ ያልተጠበቁ አባቶች ሊታዩ እንደሚችሉም አስቀድሞ የተገመተ ነበር፡፡
ነገር ግን በብዙ ሺሕ የካህናትና ምእመናን ድምፅ የተጠቆሙትና በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ አንቀጽ 5 የተዘረዘረውን የዕጩ ፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱን ያሟላሉ ተብለው የታሰቡት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል (ከ9000 ያህል ጠቅላላ ጠቋሚዎች 7200 አግኝተዋ)
እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከዕጩዎቹ ሳይካተቱ መቅረታቸው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካላትን መስገረሙ አልቀረም፡፡ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ቀድሞም ከዕጩዎች ዝርዝር እንዳይጨመሩ በአንዳንድ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትና በተለይም ‹‹መንግሥት የሚፈልጋቸውን ብፁዕ አቡነ ማትያስን እናስመርጣለን›› በማለት በመራጮች ላይ ሽብርና ስጋት ሲፈጥሩ በሰነበቱት÷ የእነ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፣ መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም፣ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ፣ መ/ር አባ ገብረ መድኅን ኀይለ ጊዮርጊስ እና መ/ር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተ ቡድን ከፍተኛ ጫና ሲፈጠር መሰንበቱ ተዘግቧል፡፡
ኮሚቴው ዕጩዎቹን የለየበትን ሂደት ወደፊት በዝርዝር ለማወቅ የሚጠበቅ ቢኾንም ስለ ተግባርና ሓላፊነቱን አስመልክቶ÷ በአንቀጽ 6/ሐ – ጥቆማ ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከካህናትና ምእመናን እየተቀበለ እንደሚሠራ፤ በአንቀጽ 6/ሰ – የዕጩዎችን ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ ለ15 ቀናት ይፋ በማድረግ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን እንደሚቀበል፤ በአንቀጽ 6/ሸ – በተቀበላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች መሠረት ዕጩዎቹን ከቅ/ሲኖዶስ ጋራ መርምሮና አጣርቶ የሚቀበለውን ከተቀበለ፣ የማይቀበለውንም ከጣለ በኋላ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ዕጩዎች ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ እንደሚያሳውቅ በግልጽ የተደነገገ በመኾኑ ቀጣይ አካሄዱ ከእኒህ በተጨባጭ መሸራረፍ ከጀመሩ አናቅጽ አኳያ የሚመዘን ይኾናል፡፡
ሐራዊ ምንጮች ከወዲሁ ስለኹኔታው ለመረዳት ባደረጉት ጥረት ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው ጥርጣሬ ያላቸው ሲኾን ከዚህም በመነሣት ውሳኔውን በፊርማቸው ስለማረጋገጣቸውም አበክረው ይጠይቃሉ፡፡
‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ›› የሚለው ሰሞንኛ አባባል ቋጠሮው ሊፈታ እነኾ ቀኑ ቀርቧል፡፡

Feb 20, 2013

በሚኒሶታ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ

“የኢቲቪ ጀሃዳዊ ሀረካት የፈጠራ ድራማ የመብት
ትግላችንን አይገታም” ሲሉ በሚኒሶታ የሚገኙ
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ባወጡት ባለ5 ነጥብ
የአቋም መግለጫ ላይ አስታወቁ።
ሙሉ መግለጫው የሚከተለው ነው። ( መግለጫውን
)pdf ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በቅርቡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጀሀዳዊ ሀረካት በሚል
ስያሜ ተራ የፈጠራ ተራኪ ፊልም ለህዝብ መተላለፉ
ይታወቃል። በማናቸውም መመዘኛ ቅንጣት እውነታን
ያላዘለ አግባብነት የሌለው ውንጀላ የሞላበት ለመሆኑ
ለመረዳት አያዳግትም፤ የፊልሙ አዘጋጆች ምን ያህል
የወረደ የሞራል ዝቅጠት ደረጃ ላይ እንደ ደረሰ
የሚያመላክት ነው።
በዚህ ዓይነት የፈጠራ ተውኔት የሙስሊሙ የመብታችን ይከበር ጥያቄ ለማዳፈን ከንቱነት ነው። ሙስሊሙ
ሕብረተሰባችን ትግሉን በስፉት ከጀመረበት ከ፩ አመት በላይ ፍጹም ሰላማዊ ጥያቄውን እያቀረበ ያለበት ስልት
የሰለጠነና ሕግና ስርአትን የተከተለ ለመሆኑ የማያሻማ እውነታ ነው። በተገላቢጦሽ የመንግስትን ስልጣን የያዘው አካል
ግን ሙስሊሙን ማሸበር፣ ማሰርና መግደል የእለት ተግባር አድርጎታል። በእስር ላይ በሚገኙ በመፍትሔ አፈላላጊ
ኮሚቴ አባላትም ላይ እየደረሰ ያለው የአካል ጉዳትና የአእምሮ ሰቆቃ እጅግ ከፍተኛ ነው።
ይባስ ተብሎም ቅጥ ያጣው የመንግስት ድርጊት የሚያሳየን በፍርድ ቤት ለህዝብ እንዳይታይ እገዳ የተጣለበትን
የኢቲቪ የፈጠራ ፊልም በግለሰብ ቀጭን ትእዛዝ ተሽሮ መቅረቡ ታውቋል። ይሕም ገዢው መንግስት ራሱን ከሕግ
በላይ ማድረጉ እና ራሱ ህግን እንደፈለገው የሚያዘው መሆኑን ነው።
ሪሳላ ኢንተርናሽናል ከዚህ በታች የሚገለጸው አቋም ላይ መድረሱን ለሁሉም አበክርን እንገልፃለን።
፩ኛ. በእስርና በእንግልት

፫ኛ. በግፍ በእስርና በእንግልት የሚገኙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና በየእስር ቤቱ የተሰሩ ሙስሊሞች በሙሉ
ያላ ምንምቅድመ ሁኔታ በነፃ እንዲላቀቁ እንጠይቀለን።
፬ኛ. በሃገሪቱ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎችን አፍኖ ማሰር ከትምህርት ገበታቸው
ያለአግባብ ማገድና ማሸማቀቅ በአስቸኳይ እንዲገታ እንጠይቃለን።
፭ኛ. በሙስሊሙ ህብረተሰባችን የቀረበው ግልፅና መሰረታዊ የመብት ጥያቄ አሁንም ምላሽ የሚሹ በመሆኑ ለዚሁ
ሰላማዊ ትግል ሙሉ ድጋፋችን እንገልፃለን ።
ኢስላም የሰላም ሃይማኖት ነዉ!!
እምነትን በነፃነት መተግበር ሰባዊ መብት ነዉ!
አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! አላሁ አክበር!

Feb 19, 2013

በጂሃድ ሃረካት ፊልም ላይ ከ33ቱ ፔቲሺን ፈራሚዎች የተሰጠ መግለጫ

ንብረትነቱ የሕዝብ ቢሆንም አገልግሎቱ የኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሆነው ኢቲቪ በሰሞኑ የፍርድ ቤት ዕግድ ወደጎን በመግፋት ከተለያዩ ፊልሞች በመቀነጫጨብ ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› በማለት ጉዳያቸው በፍርድቤት እየታየ ባለው በእሥር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ያነጣጠረ ፊልም በተደጋጋሚ አሰራጭቶ ተከታትለናል፡፡ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ጭንቀት የፈጠረበት ዝዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በትናንትናው እለት ሞባይል ኔትወርክ አቋርጦ እንደነበር ታወቀ


ላለፈው አንድ አመት በጽናት የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ የሚገኙት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የፈጠሩበት ጭንቀት ያደናበረው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ  ከጁምአ ጸሎት ስርዓት ጋር ረብሻና ከፍተኛ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት ትናንት ማለዳ በአዲስ አበባ የሞይባል አገልግሎት ከአምስት ሰዓታት በላይ እንዲቁአረጥ አድርጎ እንደነበር ዘጋቢያችን በላከልን ሪፖርት ገለጸ፡፡
እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ከጊዜ ወደጊዜ በጽናት ድምጻቸውን የሚያሰሙት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በመደበኛ የጁምአ ፕሮግራማቸው እርስ በእርስ በመጠራራት እና አጫጭር የስልክ መልዕክቶችን በመለዋወጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊያደርጉብኝ  ይችላሉ በሚል ፍርሃት ሐሙስ ለዓርብ አጥቢያ በግምት ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የተወሰኑ የሞባይል ሰልክ ቁጥሮችን ከግንኙነት ውጪ የማድረግና ኔትወርክ የማቋረጥ እርምጃንም ወስዱአል፡፡
የህዝብ መንገላታት ደንታ የማይሰጠው የወያኔ አገዛዝ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ያነጣጠረ ርምጃው በበርካታ ግለሰቦችና የቢዝነስ ተቋማት ላይም ተመሳሳይ ተጽእኖ በማሳደሩ የእርስ በርስ ግንኙነት ማድረግ ሳይችሉ ለማርፈድ መገደዳቸውን ዘጋቢያችን አያይዞ ገልጹአል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ሁሉም የሞይባል አገልግሎት ያልተቋረጠበት ዋንኛ ምክንያት ምን እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ባገኘው መረጃ የተወሰኑ የደንበኛ ጭነት ያለባቸው መስመሮች ግንኙነት ከተቋረጠ ያልተቋረጠባቸው ስልኮች ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም ማለታቸውን ገልጹአል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ቁጥሮች አለመቋረጣቸው ቴሌ ለሚነሳበት ቅሬታ የኔትወርክ መጨናነቅ ነው በሚል ጉዳዩን ለማስተባበል ስለሚረዳው ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑን እነኝሁ ምንጮች መጥቀሳቸውንና የዚህ ዓይነቱ አሰራር ሲፈጸም የመጀመሪያው አለመሆኑን ማመልከታቸውን ኢሳት ገልጹአል፡፡
በስፋት እንደሚታወቀው ካሁን ቀደምም  መለስ ዜናዊና ሌሎች የአገር መሪዎች በከተማ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ ሲገቡና ሲወጡ መንገዶችን ከመዝጋት ባሻገር ሸብርተኝነትን አስቀድሞ ለመከላከል በሚል የተወሰኑ የሞይባል ግንኙነቶች ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሲቋረጡ መቆየታቸውን ሲዘገብ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በአፋኙ የወያኔ ስርአት በሞኖፖል የተያዘው የቴሌኮም ዘርፍ ለግሉ ዘርፍ ክፍት እንዲሆን ከማይፈለግባቸው ምክንያቶች አንዱ አገዛዙ ባሻው ጊዜ ስልኮችን የማቋረጥ፣የመጥለፍና የመሳሰሉ ህገወጥ ድርጊቶችን ለመፈጸም እንዲረዳው በማሰብ መሆኑን ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ደህንነት መ/ቤት “ጀሃዳዊ ሃራካት” በሚል ርዕስ በሕግ ጥላ ስር የሚገኙ ሙስሊም እስረኛችን በማስገደድ የተጠናቀረ ፊልም ጥር 28 ቀን ምሽት በኢቴቪ ካሰራጨ በኋላ እንደገና ከዳር እስከዳር የተቀጣጠለውን የሙስሊሞች ተቃውሞ ለማዳፈን ዜጎች በነፍስ ወከፍ ኮንትራት ገብተው እያገኙ ያሉትን የሰልክ አገልግሎት ከፈቃዳቸው ውጪ በማቋረጥና በማስተጓጎል ሥራ ውስጥ መጠመዱ አገዛዙ አሁን ያለበትን ገደብየለሽነት ፍርሃት በግልጽ የሚያመላክት ነው፡፡

መሪ አልባዉ የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በስንዴ ግዢ ጉዳይ ሲጨቃጨቅ መክረሙ ተሰማ


ከዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ መሪ የሌለበት የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተብየው መፈራራትና መከባበር የሚባል ነገር ርቆት አባላቱ “ፕሮፓጋንዳ ይሻለናል” ወይስ “ሀቁን ተጋፍጠን መፍትሔ እንፈልግ” በሚሉ ሁለት ቡድኖች ተከፍሎ በየቀኑ ሲጨቃጨቅ እንደሚዉል ለካቢኔዉ ቅርበት ያለቸዉ የታመኑ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩልን ዜና ገለጹ። የስንዴው ፖለቲካ በሚል አርዕስት ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰዉ ዜና መሰረት የወያኔ አገዛዝ አገሪቱ ዉስጥ በኤኮኖሚዉና በማህበራዊ ዘርፎች እየደረሰ ያለዉን ቀዉስ መቆጣጠር አቅቶት አሁን ስራዬ ተብሎ የተያያዘዉ የእህል ውድነት በህዝቡ ላይ በተለይ ወያኔ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ብሎ በሚፈራዉ በከተማዉ ህዝብ ላይ ያስከተለውን ቀውስ በአስቸኳይ “ለማረጋጋት” ምን ያህል ስንዴ ከውጭ እንግዛ በሚል ጭቅጭቅ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮቹ አክልዉ በላኩልን ዜና ገልጸዋል ።

በዚህ ሳምንት ከወያኔ ጓዳ በደረሰን ዜና መሰረት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር በሚል በያዝነዉ ወር 850 ሺህ ኩንታል ስንዴ አገር ውስጥ ገብቷል። የዚህ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ወጥቶበት የተገዛዉ ስንዴ ጉዳይ ቀድሞዉንም በቋፍ የነበረዉን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጭራሽ ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ ዉስጥ እንዲዘፈቅ አደርጎታል። በአንድ በኩል ግዢዉ የሚፈጥረዉ የዉጭ ምንዛሬ ጉድለት የባሰዉኑ የዋጋ ግሽበቱን ያባብሰዋል የሚሉ የካቢኔዉ አባላት ሲኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ “ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ከ1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ስንዴ ከውጭ አምጥተን አከፋፍለናል ሆኖም ምንም አይነት ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣት አልቻልንም ብለዉ የሚከራከሩ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ቁጥራቸዉ ትንሽ ቢሆንም ከእነዚህ ሁለት ቡድኖች ለየት ያለ አስተሳሰብ ያለቸዉና የአገሪቱ ችግር የገባቸዉ አንዳንድ የካቢኔዉ አባላት ደግሞ ችግራችን ስንዴ መግዘት ወይም ማምረት ሳይሆን የገዛነዉን ወይም ያመረትነዉን ስንዴ ለተጠቃሚዉ ህዝብ በሚገባ ማከፋፈል አለመቻላችን ነዉ የሚሉም አልታጡም። ለምሳሌ የወያኔ አገዛዝ እራሱ በሰጣቸዉ መግለጫዎች “በ1.5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ይመረታል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከ3 ሚሊየን ቶን በላይ ስንዴ ኢትዮጵያን ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በስንዴ ምርት ቀዳሚ ያደርጋታል፤ ችግሩ ግን ይህ ብዛት ያለዉ ስንዴም ሆነ ከዉጭ አገር ተገዝቶ የሚመጣዉ ስንዴ ዬት እንደሚገባ አይታወቀም።

ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን በተገኘዉ መረጃ መሰረት ገበያ ለማረጋጋት በሚል ሰበብ ስንዴ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገዛ አየር በአየር ወደ ሌላ አገር እየተዛወረ በመሸጥ ላይ ሲሆን ግዢውን የሚፈቅዱት፣የሚያስፈጽሙት፤ የሚያጓጉዙትና ብሎም ወደ ደቡብ ሱዳንና አረብ አገሮች እያወጡ የሚሸጡት፣ በዘርና በስጋ ዝምድና የተሳሰሩ የህወሀት ሰዎች መሆናቸው በገልጽ ይታወቃል።

መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረባቸዉ ግዜ ማንም ሰዉ ደፍሮ የማያነሳቸዉ ይንንና ይህንን የመሳሰሉ ጉዳዮች ዛሬ የመወያያ አርዕስቶች እየሆኑ በመምጣታቸዉ ስልጣን ከእጃችን ሊወጣ ይችላል በሚል ፍራቻ ብዙ የወያኔ ባለስልጣኖች አገሪቱን ባዶዋን እያስቀሯት መሆኑን ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ፤ በተለይ ከአገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት የሚኮበልለዉ የዉጭ ምንዛሬ ብዛት ያሰጋቸዉ አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ አዳራ ያሉን የገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የህወሀት አባላት ዝርፍያ በዚህ ከቀጠለ በቅርብ ግዜ ዉስጥ የኢትዮጵያ የዉጭ ምንዛ ካዝና ባዶ ይሆናል ብለዋል።

ታስሮ የነበረው ኤርሚያስ አመልጋ ተፈታ

(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት መራሹ የኢትዮጵያ አስተዳደር በሃገሪቱ ውስጥ የሕወሓት ነጋዴዎች ካልሆኑ በስትቀር ሌሎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው በሃገራቸው ነግደው እንዳይበሉ ከፍተኛ ምቀኝነት እንዳለበት በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም። ከዚህ ቀደም በንግድ ብልጠት የሕወሃት የንግድ ድርጅቶችን እርቃናቸውን በኪሳራ አስቀርተው የነበሩት የስታር ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤቶች የሕወሓትን ክፍፍል ተከትሎ በተፈጠረ ድንጋጤ በሙስና ሰበብ ታስረው ከንግዱ ዓለም እንዲወጡ መደረጉ አይዘነጋም።
- የኮካ ኮላ ከፍተኛ ባለ አክሲዮን አቶ ንጉሴም ከአቶ ታምራት ክስ ጋር ተያይዘው በኪሳራ ከሕወሃት ድርጅቶች ተፎካካሪነት ወጥተዋል።
- የሃግቤስ ኢንተርናሽናል ባለቤት ሚ/ር ህራየር ቤንሰን (አርመናዊ ናቸው) እርሳቸውም በሙስና ሰበብ ከአቶ ስዬ አብርሃና ወንድሞቻቸው ጋር እንዲታሰሩ በመደረግ ከሕወሓት ንግዶች ጋር እንዳይፎካከሩ ተደርገው ግማሽ ደርዘን ዓመታትን እስር ቤት እንዲያሳልፉ ተደርገዋል።
- የመስቀል ፍላወር ባለቤት አቶ እስክንድርም በሕወሓት ተመትተዋል
- እነ አቶ ክቡር ገና በተፎካካሪነት ላይ አይደሉም
- በአቢሲኒያ ባንክ ላይ የደረሰውን ከአንባቢዎቻችን እንተወዋለን
- እንደ አቶ ብርሃነ መዋ ያሉ ነጋዴዎች ንግዳቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ተደርገዋል
- ጣይቱ ሆቴልን የገዙትና የዘሞኒተር የ እንግሊዘኛ ጋዜጣ አዘጋጅ አቶ ፍጹም ዘ-አብ አስገዶም እህታቸው የአቶ ስዬ አብርሃን ወንድም አቶ አስፋ አብርሃን ስላገቡ ብቻ ሕወሃት ለሁለት ሲሰነጠቅ “አቶ አሰፋ በአምቻ ጋብቻ ተይዘው ጣይቱ ሆቴልን በቅናሽ ለአቶ ፍጹም እንዲሸጥ አድርገዋል” በሚል ተከሰው ከገበያ እንዲወጡ ተደርጓል
ምን ይሄ ብቻ? ሌላም ሌላም
አዲሱ የወያኔ ሰለባ ደግሞ ኤርሚያስ አመልጋ ናቸው።
ከዚህ ቀደም ቡሬ የተሰኘውን ውሃ በጎጃም ክልል ውስጥ ፋብሪካ ከፍተው ሲያቀርቡ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ “በደረቅ ቼክ ማጭበርበር ወንጀል” ታስረው ተፈትተዋል። መለስ ሞተዋል የሚል ዜና በኢሳት በተነገረበት ወቅት “አልሞቱም አዲስ አበባ ገብተዋል” እያለ በማስተባበል ሥራ ላይ የከረመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ኤሚያስ ታሰሩ ብሎ በሰበር ዜና ቢዘግብም ሪፖርተር ደግሞ ታስረው ተፈቱ ብሏል። የሪፖርተር ዜና እንደወረደ ይኸው፦
የዘመን ባንክና የአክሰስ ሪል ስቴት መሥራች የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከደረቅ ቼክ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው አንድ ቀን በቁጥጥር ሥር ውለው ባለፈው ዓርብ ተለቀቁ፡፡
አክሰስ ካፒታል ግን በአቶ ኤርሚያስ ላይ የተጀመረው ምርመራ መቋረጡን አስታውቋል፡፡
አቶ ኤርሚያስ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ካዛንቺስ (ስድስተኛ) ማዘዣ ጣቢያ አንድ ቀን ካደሩ በኋላ ተለቀዋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ችግሩ የተፈጠረው ባለመግባባት መሆኑን ገልጸው፣ አሁን ግን ምርመራው ተቋርጦ ወደ ሥራ መመለሳቸውን አስታውቀዋል፡፡
አቶ ኤርሚያስ የተጠረጠሩበት ምክንያት የአክሰስ ሪል ስቴት ኩባንያ አንድ ደንበኛ ኩባንያው እሠራለሁ ያለውን ቤት ሠርቶ በወቅቱ አላስረከበኝም በማለት ገንዘባቸው እንዲመለስ ሲጠይቁ፣ አቶ ኤርሚያስ የ350 ሺሕ ብር ቼክ ይፈርሙላቸዋል፡፡
እኝህ ደንበኛ ዘመን ባንክ ሄደው በቼክ የተጻፈላቸውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ ክስ በመሄዳቸው ነው አቶ ኤርሚያስ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተብሏል፡፡
ምንጮች እንደሚገልጹት ግን፣ አካውንቱ ውስጥ ገንዘብ ነበር፡፡ ነገር ግን ሌላ የሪል ስቴቱ ደንበኛ አካውንቱን በፍርድ ቤት በማሳገዳቸው ገንዘቡን ማንቀሳቀስ አልተቻለም፡፡ አክሰስ ካሉት አካውንቶች ውስጥ በአንደኛው ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ እንደነበር ሪፖርተር መረዳት ችሏል፡፡ ይህም መረጃ ለመርማሪዎቹ ቀርቦ የይከፈለኝ ጥያቄ ላነሱት ግለሰብ ገንዘቡ ተከፍሏቸዋል፡፡ ግለሰቡም ወዲያው ክሱን በማንሳታቸው ምርመራው ተቋርጦ አቶ ኤርሚያስ ተለቀዋል፡፡
አክሰስ ሪል ስቴት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአካውንቱ ውስጥ በቂ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጧል፡፡ የተፈጠረው ክስተትም በቢዝነስ እንቅስቃሴ ውስጥ በየጊዜው የሚያጋጥም መሆኑን የገለጸው አክሰስ፣ መርማሪዎቹ ይህንኑ ተረድተው ምርመራውን ማቋረጣቸውን አስታውቋል፡፡
በዘመን ባንክ በአካውንቱ ውስጥ ገንዘብ መኖሩን ተረጋግጦ፣ ችግሩ ሊፈጠር የቻለው በአካውንቱ ውስጥ ገንዘብ ባለመኖሩ ሳይሆን በፍርድ ቤት ውሳኔ በመታገዱ መሆኑን የሚገልጹ አሉ፡፡
ችግሩ የተፈጠረውም በዘመን ባንክ ስህተት መሆኑን የሚገልጹት ምንጮች፣ ባንኩ በጉዳዩ ሳይጠየቅ እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡ የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሚያስ እሸቱን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ብንሞክርም፣ ‹‹በባንኩ ፖሊሲ መሠረት በደንበኞች ጉዳይ ላይ አስተያየት አንሰጥም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ወደተለመደው የሥራ ገበታቸው መመለሳቸውን ያስታወቀው አክሰስ ሪል ስቴት፣ በቀጣይ ሳምንታት ሥራውን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃዎችን ለደንበኞቹ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡
አቶ ኤርሚያስ በኢትዮጵያ ቢዝነስ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ሰዎች ተርታ የሚመደቡ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ባንኮች ውስጥ በመሥራት የሚታወቁት አቶ ኤርሚያስ ኃይላንድ በመባል የሚታወቀውን ውኃ፣ ዘመን ባንክን፣ አክሰስ ሪል ስቴትና ሌሎች ተዛማጅ ቢዝነሶችን በመመሥረት ይታወቃሉ፡፡

አበበ ገላው ተጫማሪ የግድያ ዛቻ ደረሰው


(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተጨማሪ የግድያ ሙከራ ዛቻ እንደደረሰው በጎግል ቮይስ በኩል በድምጽ ማስረጃ አቀረበ። “አበበ ደምህን እንጠጣዋለን ፤ከኛ የትም አታመልጥም”ሲል አስፈራሪው ሰው ይሰማል። ይህን ተከትሎ አበበ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “የህወሃቶች ዛቻ እና የዘረኝነት ፉከራ ቀጥሏል። እስከ አሁን ያልተገለጠላቸው ሃቅ እንኳን ዛቻ ሞት ከትግላችንም ሆነ ከቁርጠኛ ጉዞአችን ፈጽሞ አይገታንም። ነጻነት ወይንም ሞት
ብሎ የተነሳን ህዝብ ማንም አንባገነን አያስቆመውም። እኔ ብሞትም በዛ በታላቅ አደባባይ ላይ የተናገርኩት እውነት ግን
ፈጽሞ አይሞትም፣ ምክንያቱም በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የታመቀ ሃቅ ነውና። ሃቅ ሲታፈን ፈንድቶ
መውጣቱ ያለ እና ወደፊትም የሚኖር ነው።”
ማስፈራሪያውን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ

Feb 17, 2013

በሙኒክ የተሳካ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሄደ

ኢሳት ዜና:-እውቁ የሰብአዊ መብቶች ተማጓች አርቲስት ታማኝ በየነ እና ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው በተገኙበት የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢ ዝግጅት ከተጠበቀው ሰው በላይ በመምጣቱ ቦታ መጥበቡን አዘጋጆች ለኢሳት ገልጸዋል።
የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆነው አቶ አበበ መለሰ እንደተናገረው በጀርመን የኢትዮጵያውያን ዝግጅት ታሪክ ይህን ያክል ህዝብ ሲሳተፍ ማየቱ የመጀመሪያው ነው።
ነገ እሁድ ፌብሩዋሪ 17 ደግሞ አርቲስት ታማኝ በየነ በኢሳት መቀመጫ አምስተርዳም ከተማ ተገኝቶ በሆላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያል። በዚህ ዝግጅት የሀይማኖት አባቶች እና  የሰብአዊ መብት ተማጓቾች ንግግር ያደርጋሉ።
የኢሳት የሆላንድ የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረሀይል በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ ላይ  እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ከዚህ ቀደም በኖርዌይ፣ በስዊድንና በስዊዘርላንድ ደማቅ እና ውጤታማ የድጋፍ ማሳባሰብ ዝግጅት ተካሂዷል።
ተመሳሳይ ዝግጅቶች በለንደን፣ በብራሰልንስና በፍራንከፍርት እንደሚካሄዱ የአውሮፓ የኢሳት ግብረሀይል አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ምርጫ ከ99 በመቶ በላይ በእጩነት የተመዘገቡት ኢህአዴግ ናቸው

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ወኪል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች= በመዘዋወር ያጠናቀረው ዘገባ እንደሚያመለክተው በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባ የወረዳና የአካባቢ ምርጫ፣ ተወዳዳሪ ሆነው በእጩነት የቀረቡት 99 በመቶ የሚሆኑት የኢህአዴግ አባላት ናቸው።
አብዛኞቹ ተመራጮች የመንግስት ሰራተኞችና በጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ተመድበው የሚሰሩ ናቸው። በእጩዎች ስም ዝርዝር ላይ እንደሚታየው ከ40 በመቶ በላይ ተመራጮች ከ3ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል የሚሸፍን የትምህርት ደረጃ አላቸው። 40 በመቶ የሚሆኑት ተወዳዳሪዎች ደግሞ ከ10ኛ ክፍል እስከ ዲፕሎማ የሚደርስ የትምህርት ደረጃ አላቸው። ከ20 በመቶ በላይ ተወዳዳሪዎች  የመጀመሪያ ደግሪ እንዳላቸው ለማወቅ ተችሎአል።
ከ99 በመቶ በላይ በሆኑት  ጣቢያዎች በእጩነት የቀረቡት ኢህአዴጎች ሲሆኑ፣ የተቃዋሚ አባላትን ፈልጎ ማግኘት በእጅጉ አስቸጋሪ ነው።
33 የተቃዋሚ ድርጅቶች በምርጫው ላለመወዳደር የያዙት ጠንካራ አቋም ገዢው ፓርቲ የዘንድሮውን የአካባቢና አዲስ አበባ ምርጫ ብቻውን እንዲሮጥ አስገድዶታል።
በ1997 ዓም ምርጫ ቅንጅት በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ካሸነፈ በሁዋላና ገዢው ፓርቲ ውጤቱን በጉልበት ከቀማ በሁዋላ፣ በአዲስ አበባም ሆነ በመላ አገሪቱ በቂ ፉክክር የታየበት ምርጫ አልተካሄደም።
የገዢው ፓርቲ አባላት እስካሁን ድረስ ምርጫ ካርድ ላልወሰዱት ሰዎች ካርድ እያደሉ እንደሚገኙ በተለያዩ

Total Pageviews

Translate