Pages

May 31, 2013

የተቃውሞ ሠልፉ ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው! ሠማያዊ ፓርቲ

 ሠማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የተቃውሞ ሠልፍ ዝግጅቱን በታቀደው መሠረት በአመርቂ ሁኔታ እያካሄደ ነው፡፡ በዛሬው ዕለት 5ሺህ የድምጽ መልዕክቶች እና 10 ሺህ የጽሁፍ መልዕክቶች በእጅ ስልክ(በሞባይል) የተላለፈ ሲሆን፣30 ሺህ በራሪ ወረቀቶች እና 2 ሺህ ፖስተሮች ተሰራጭቷል፡፡ ሰው ለሰው የሚደረገው ቅስቀሳ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፤በሚቀጥሉት ቀናትም ቅስቀሳው በልዩ ልዩ ዘዴዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የእሁድ ሰው ይበለን!

የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ

የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓም ተጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከተካሄደ በኋላ ህዝባዊ ትግሉን ወደፊት የሚያራምዱ ዉሳኔዎችን ካሳለፈ በኋለ ባለፈዉ ሰኞ ምሽት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ይህ የንቅናቄዉ አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ንቅናቄዉ ባለፉት ሁለት አመታት የተጓዘባቸዉን መንገዶች፤ ያቀዳቸዉን ስራዎችና የዕቅዱን አፈጻጸም በጥልቀትና በስፋት በመዳሰስ መጪዉ የትግል ወቅት የሚጠይቀዉን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተመልክቶ ዘረኛዉን የወያኔ አገዘዝ በማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የዲሞክራሲ ጥማት ሊያረኩ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸዉን አበይት ዉሳኔዎች አሳልፏል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የንቅናቄዉን የአለፉት አምስት አመታት ጉዞና በዚህ በአራተኛዉ ጉበኤ ላይ የስልጣን ዘመናቸዉን የጨረሱት የንቅናቄዉ ምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ዕቅድና የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ በጉባኤዉ ላይ አዲስ ለተመረጡ የአመራር አባላት ንቅናቄዉ የታሰበበትን ግብ እንዳይመታ አንቀዉ የያዙትን እንቅፋቶች እንዲያስወግድና እንዲሁም የንቅነቁዉ ጥንካሬ በታየባቸዉ መስኮች አቅሙን አጣናክሮ በይበልጥ በመስራት የኢትዮጵያ ህዝብ ከንቅናቄዉ የሚጠብቀዉን የታሪክ አደራ እንዲወጣ አሳስቧል። በጉባኤዉ ወቅት አባላት ያደረጉት አመራሩን የመንቀፍ፤አቅጣጫ የማሳየት፤ ሀሳብ የማመንጨትና በአጠቃላይ በእያንዳንዱ የጉባአዉ ስብሰባ ላይ ባሳዩት ንቁ ተሳትፎ ንቅናቄዉ በህዝባዊ አመጽና እምቢተኝነት ዘርፎች ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍም እያደገ መምጣቱን አሳይተዋል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲሁም የስነ ስርአትና የግልግል ኮሚቴ ሪፖርቶችን አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ ሪፖርቶቹን አጽድቋል። ከዚህ በተጨማሪ የንቅናቄዉን እስትራቴጂና ይህንኑ እስትራቴጂ ተሸክሞ በተግባር የሚተረጉመዉን መዋቅር በአጽንኦት ከፈተሸ በኋላ በስትራቴጂዉ ላይ መጠነኛ ለዉጥ በማድረግ የእስትራቴጂዉንና የመዋቅር ለዉጡን ተቀብሎ አጽድቋል። ይህ የንቅናቁዉ አራተኛ ጉባዜ ንቅናቄዉን ላለፉት ሁለት አመታት የመሩትንና ያገለገሉትን የምክር ቤት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ የስነ ስርአትና ግልግልና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግኖ በማሰናበት በምትካቸዉ ንቅናቄዉን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚያገለግሉ የምክር ቤት አባላት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የስነ ስርአትና ግልግል ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበትን ሁኔታ በዝርዝር ከቃኘ በኋላ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ዉጊያ የተያያዘዉ አገር ዉስጥና በዉጭ አገሮችም ስለሆነ ወያኔን በእነዚህ ሁለት የትግል መስኮች እንደአመጣጡ ከገጠምነዉ የሚሸነፍ ድርጅት መሆኑን ሙሉ በሙሉ በመቀበል አባላቱ ባሉበት ቦታ ሁሉ የሚሰሩት ስራ ወያኔን በማስወገድ ላይ እንዲያተኩር አሳስቧል። ከአለም ዙሪያ ከተለያዩ አገሮች የመጡ የግንቦት ሰባት አባላትን ያሰባሰበዉ አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ የትግል ቃል ኪዳን የታደሰበት፤የመስዋዕትነት ዝግጅት የታየበትና አባላት የትግልና የስራ ልምድ የተላዋወጡበት ከምን ግዜዉም ባላይ የተሳካና የተዋጣለት ጉባኤ ነበር። በመጨረሻ ጉባኤዉ የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ለአባላቱና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ የትግል ጥሪ በማስተላለፍ ደማቅ በሆነ ስነሰርአት ተፍጽሟል።
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ

May 30, 2013

ኢህአዴግ ደብሮታል!!!!!!Abe Tokichaw

575707_555196677856268_1202584028_nባለፈው ጊዜ ግንቦት 17 ሰማያዊ ፓርቲ በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አቅርቦ መነግስት እንደተለመደው ዝም ብሎ ደብዳቤ አንቀበልም በማለት አላየንም አልሰማንም ብሎ የአራዳ ሰፈር ልጆች (ባላየ ባልሰማ ሙድ) እንደሚሉት አይነት ሊያልፈው ነበር፡፡ ነገር ግን ሰማያዊዎቹ ፈቃድ አንጠይቅም ካሳወቅናችሁ ይበቃችኋል ሰልፉን ባልነው ሰዓት እና ቦታ ከማድረግ አንቦዝንም እና አስቡበት ብለው ለበላይ አቤት አሉ፡፡ ያኔም የበላዩ የኦቦ ኩማ ደመቅሳ ቢሮ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ አጉል ግርግር ከሚፈጠር መደራደር ይሻላል ብሎ ዘየደ፡፡ ተደራደረ ለግንቦት 25ም ሰልፉ እውቅና ተሰጠው፡፡ እኛም የሰማያዊን አስጨናቂነት፤ የከንቲባውንም ተጨናቂነት አደነቅን፡፡
ሳስበው ሳስበው ኢህአዴግ የዛን ጊዜ አጣብቂኝ ውስጥ ሆኖ ለሰልፉ እውቅና ከሰጠ በኋላ ደብሮታል፡፡ እንደውም ቀፈፈኝ ብሎ እውቅናውን ቢያነሳ ራሱ ደስ የሚለው ይመስለኛል፡፡ በተለያየ ማህበራዊ ድረ ገጾች ሰልፉ እንዲደነቃቀፍ ስልታዊ እንቅስቃሴ የሚያደረጉ ምልምሎችን እየተመለከትን ነው፡፡ እነዚህ ምልምሎች አንድ ጊዜ “የሰልፉ ቀን ተቀይሯል” ሲሉ ሌላ ጊዜ ደግሞ “ቦታው ተለውጧል” እያሉ የተለያዩ የሚያምታቱ መረጃዎችን እያቀበሉን ነው፡፡ እነዚህ መረጃዎች ከሚያበጁት የሚያፈርሱት ይበልጣልና መረጃ ሳሆኑ “መራጃ” ናቸው ብያቸዋለሁ፡፡ (በቅንፍም የግንበኛ ልጅ መሆን ጥቅሟ ይቺ ናትኮ በእውኑ፤ “መራጃ” ማለት ምን እንደሆነ ከእኛ ውጪ የሚያውቁ ጥቂቶች አይደሉምን… “መራጃ” ድንጋ ለመፈረካከስ የሚያገለግል አንዳች ብረት ነው)
ለማንኛውም አስከ አሁን ድረስ እንደሰማነው ሰላማዊ ሰልፉ በዕለቱ እና በሰዓቱ ይከናወናል፡፡ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በሰልፉ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ኢህአዴግ ደብሮታል፡፡ ኢህአዴግ ቀፎታል፡፡ ኢህአዴግ ሙዱ “ተከንቷል”!

May 29, 2013

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

የዛሬ 7 ዓመት  1997 ዓ .ም ወያኔ ምርጫ ማጭበርበሩ ሣያንሰው በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ የጅምላ ፍጅት ያደረገበት  ነበር :: በኢትዮጵያ ላይ የትግሬ -ወያኔ -ናዚያዊ የዘር -መድልዎ አገዛዝ ከተመሠረተበት ከግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ .ም በኋላም ሆነ ሥልጣን ከመያዙ በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የጅምላ ፍጅትከማድረግ ቦዝኖ አያውቅም  :: ዕለት _ጭፍጨፋው የተደረገበት ሥፍራ _የሞቱ ወገኖች ብዛት _የአካል ጉዳት /መፈናቀል የደረሠባቸው 
ታኅሣሥ 1984 __አርባ ጉጉ (አርሲ )    _____ 46
 ሐምሌ ቀን 1984___አረካ (ወላይታ )_____31_____29 ምንጭ :- EHRCO, THE HUMAN RIGHTS SITUATION IN ETHIOPIA, FOURTH REPORT, January 21, 1993
 መጋቢት 16 1984__ወተር (ሐረርጌ )_______ ከ 29 - 92 ምንጭ :- Human Rights Watch World Report 1993 - Ethiopia 
ሚያዝያ 1984______በደኖ (ሐረርጌ )_____ 150 ምንጭ :- Human Rights Watch World Report 1993 - Ethiopia 
ጳጉሜን 2 1986 ዓ .ም ._አደባባይ እየሱስ (ጎንደር ከተማ )_18 ___17 ምንጭ :- EHRCO, THE HUMAN RIGHTS SITUATION IN ETHIOPIA, SIXTH REPORT, January 4, 1994.
 ሚያዝያ 10 ቀን 1993_አዲስ አበባ _51 ____250 አባይ ሚዲያ : Remembering April 2001′ s Massacre of Ethiopian Students 
መጋቢት 1994 ዓ .ም ቴፒ (ከፋ -ሸካ ዞን )_24+128___4,738 ምንጭ :- IRIN, ETHIOPIA: EU calls for public inquiry into Tepi, Awasa killings 
ግንቦት16ቀን1994..___አዋሣ (ሲዳሞ )__40__400 ምንጭ :- HRW, June 10, 2002. Ethiopia: Police Firing on Unarmed ProtestersHRW, June 10, 2002. Ethiopia: Police Firing on Unarmed Protesters 
ታኅሣሥ3-5ቀን1996.._ጋምቤላከተማ(ጋምቤላ)_424_50,000 Anuak Justice Council 
ግንቦት 29- ሰኔ ቀን 1997 ዓ .ም . ___አዲስ አበባ ጥቅምት 22-25 ቀን 1998 ዓ .ም . _______አዲስ አበባ ምንጭ :-Ethiopia - Amnesty International Report 2007
 ሰኔ 1998_ዲላ (ሲዳሞ )_100 __በሺዎች የሚቆጠሩ ምንጭ :- IRIN, 14June 2006, ETHIOPIA: Ethnic conflict claims 100 lives in the south 

ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ ጨመረ፤ ሕጉ ይሻሻላል ተባለ


                                                     አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ
ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ ጨመረበጋዜጣው ሪፖርተርየፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ተጠርጣሪግለሰቦች በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ ከያዘ በኋላ ለኮሚሽኑ የሚደርሰው የሙስና ጥቆማ ቁጥር መጨመሩ ታወቀ።ኮሚሽኑ በድረገፁ ይፋ እንዳደረገው በተለይ ከግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በኋላ ባሉት አስር ቀናት ብቻ ከዚህ ቀደም ከነበረውጋር ሲነፃፀር የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ በልጦ መመዝገቡን ገልጿል።ኀብረተሰቡ ሙስና አስከፊ ድርጊት መሆኑን ተገንዝቦ ለማጋለጥና ሙስናን ለመዋጋት እያሳየ ላለው ጥረት ኮሚሽኑ ምሥጋናአቅርቧል። ሆኖም ምን ያህል ጥቆማ እንደቀረበለት በቁጥር ከመግለፅ ተቆጥቧል።የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በ2005 በጀት ዓመት አስር ወራት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን ጨምሮ3001 ጥቆማዎችና አቤቱታዎችን መቀበሉን ከነዚህ ውስጥ በኮሚሽኑ የሥልጣን ክልል ሥር የሚወድቁት 1ሺ 335 ወይም 44በመቶ ያህሉ ሲሆን የተቀሩት 56 በመቶ ከሥልጣኑ ክልል ውጪ መሆናቸውን ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን ከሳምንት በፊትለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መግለፃቸው ይታወሳል።nበሌላ ዜና                                                                የፀረ-ሙስና ሕግ ሊሻሻል ነው                                    · የአክሲዮን ማኅበራት፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የልማት ማኅበራት                                                        በአዲሱ የሙስና ሕግ ይካተታሉበዘሪሁን ሙሉጌታየፌዴራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሕግ በወንጀል ሕጉ የተደነገጉ የሙስናወንጀሎች እንደገና የሚደነግግ አዋጅ በማዘጋጀት አሁን እያስቀጣበት ያለውን ሕጋዊ ወሰንበማስፋት አዋጁን ሊያሻሽል ነው።አዲስ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ ሕግ በዋናነት የግል ዘርፍ አካላትን በሙስና ወንጀል ተጠያቂየሚያደርግ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በመቶ ሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ሀብትእያንቀሳቀሱ ያሉ፣ የሕዝብ ሀብት የሚያስተዳድሩ የግል ዘርፍ አካላት ላይ ረቂቅ ሕጉአተኩሯል። እነዚህ አካላት በማንኛውም አግባብ ከአባላቶቻቸው ወይም ከሕዝብ የተሰበሰበወይም ለሕዝባዊ አገልግሎት እንዲውል የተሰበሰበ ገንዘብ፤ ንብረት ወይም ሌላ ሀብትንየሚያስተዳድሩ ወይም የሚያንቀሳቅሱ አክሲዮን ማኅበራት በማኑፋክቸሪንግ፣ በእርሻ፣በንግድ፣ በኮንስትራክሽን፣ በትራንስፖርት፣ በፋይናንስ እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማትመካከል በአክሲዮን የተቋቋሙ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሐዋላ ተቋማት የሙያና የብዙሃን ማኅበራት ፌዴሬሽኖችናኮንፌዴሬሽኖች፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖች፣ ኢንዶውመንቶችና የልማት ማኅበራት (ለምሳሌ አልማ፣ ኦልማ፣ ወዘተን)ያካትታል።ሕጉን እንደገና ለማሻሻል ያስፈለገው ሙስናን የሚፀየፍ ኅብረተሰብ እንዲፈጠር የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር፣ በዓለም አቀፍደረጃም፤ በግል ዘርፍ የሚፈፀም ጉቦኝነትና ምዝበራ በሙስና ወንጀል የሚያስቀጣ በመሆኑ ሲሆን፤ አዲሱ ረቂቅ ሕግምከሲንጋፖር፣ ከስዊዲንና ከደቡብ አፍሪካ ተመሳሳይ ሕጎች በመቀመር መዘጋጀቱም ታውቋል።በአዲሱ ሕግ መሠረት ለሕዝብ ተብሎ የተሰበሰበ ሀብት የሚያንቀሳቅሱ እና የሚያስተዳድሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የፖለቲካድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ ማድረጉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን በሕጉያልተካተቱ ሲሆን፤ ሌሎች የሕዝብን ገንዘብና ሀብት የሚያስተዳድሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት፣ እድር እና ተመሳሳይ ባህላዊወይም ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ማኅበራት አባላቱ እርስ በርስ የሚተማመኑና ለሙስና የመጋለጥ ዕድላቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣በሙስናውም ቀጥተኛ ተጠቂ የሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥቂቶች በመሆናቸውና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብት አነስተኛነት የተነሳበሙስና ተጠያቂ በማድረግ ከሚድነው ሀብት ይልቅ ተጠያቂ ለማድረግ የሚባክነው ሀብት ከፍተኛ በመሆኑ ከሕጉ ውጪተደርገዋል።በአዲሱ የሙስና ወንጀል ረቂቅ ሕግ በግለሰብ ባለሀብት ወይም ባለሀብቶች የተቋቋመ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በሙስናወንጀል አይጠየቅም።¾በሌላ የሙስና ዜናበእነ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገብ ስር የተዘረዘሩት 12 ተጠርጣሪዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው- በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ያሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ዛሬ ይታያል- አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር ድብደባ ተፈፅሞብኛል አሉበአሸናፊ ደምሴየፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረውበሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ተጨማሪ ጊዜበተጠየቀባቸው በእነ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገብ ስር የሚገኙ አስራሁለትተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀኑ ጊዜ ቀጠሮ ሲፀናባቸው፤ የገቢዎችና ጉምሩክባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ በሦስት የተለያዩመዝገቦች የተዘረዘሩትን 22 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለመመርመር ደግሞ ዛሬንጨምሮ ሐሙስና አርብ ተለዋጭ ቀጠሮዎችን ሰጥቷል።ችሎቱ በዕለቱ ሲሰየም ኮሚሽኑ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ለመስማትእንደሆነ ፍርድ ቤቱ አስታውሶ፤ ለፌዴራሉ ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንየምርመራ ቡድን ተወካዮች ሀሳባቸውን እንዲያስረዱ ዕድል በመስጠት ጀምሯል።በችሎቱ የተገኙት የመርማሪ ቡድኑ ተወካይም ቡድኑ ያሳካቸውንና ያላሳካቸውንየምርመራ ውጤቶች በሁለት ከፍለው ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል። በዚህም በዘጠኝተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት በመድረስ የኤሌክትሮኒስ መሳሪያዎችን፣ የተደበቁሰነዶችንና በህገወጥ መንገድ የተገኙ ገንዘቦችን (መኒ ላውንደሪ) መሰብሰቡንጭምር ገልጿል። አክሎም የ28 ተጠርጣሪዎች ክስ መቋረጡን የሚያስረዱሰነዶችን፣ ስምንት በቫት ማጭበርበር ተጀምረው የተቋረጡ ክሶችን፣ ኦዲትያልተደረጉ ሰነዶችን እና የ15 ምስክሮችን ቃል ስለመቀበሉ ካጠናቀቃቸውውጤቶች አንኳሮቹ ናቸው ሲል አስረድቷል።በአንፃሩ ደግሞ የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን አላጠናቀኳቸውምና ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጥያቄ ያቀረበባቸውጉዳዮች መካከል፤ ተጨማሪ የሙስና ወንጀሎች የታገዱባቸው ሰነዶች፣ የታገዱ ንብረቶችን ማጣራት፣ ከአራጣ ብድር ጋርየተያያዙ ጉዳዮችን ማጥራት፣ የምርመራ ስራው ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ቦታዎች የሚካሄድም ጭምር መሆኑን እና በምርመራቡድኑ አማካኝነት የተገኙ ሰነዶችን መርምሮ ከክስ መዝገቡ ጋር እንዲያያዙ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ተጨማሪ 14 ቀናትን ፍርድቤቱ እንዲፈቅድ ጠይቀዋል።ሰኞ ከሰዓት በኋላ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት በቀዳሚነት ጉዳያቸው በችሎቱ መሰማት የጀመረውበሁለተኛ የክስ መዝገብ ስር የተዘረዘሩት 12 ተጠርጣሪዎች ሲሆን፤ በዚህም ስር የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋናዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ጨምሮ ሌሎችም ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ወንጀሉ ተሳታፊ ሆነዋል የተባሉቤተሰቦች በችሎት ቀርበው በጠበቆቻቸው በኩል ጉዳያቸውን አስረድተዋል።አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው በኩል ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄና አቤቱታ መሠረት፣ መርማሪ ቡድኑ በቂማስረጃዎችን ሰብስቤያለሁ ያለ መሆኑን በመጥቀስ፤ አንዳንድ ተጠርጣሪዎችም አሁን ድረስ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክስአለማወቃቸውን እና በጤናና በቤተሰብ ጉዳይ ላይ ተንተርሶ የዋስትና መብታቸው እንዲከብር ጥያቄ አቅርበዋል።የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ በጠበቃቸው አማካኝነት የምርመራቡድኑ አገኘሁት ያለው መረጃ በቂ ሆኖ ሳለ ሁለት ህፃናት ልጆቼ በችግር ላይ ስለሚገኙ የዋስ መብቴ ተጠብቆ ከእስር ልለቀቅይገባል የሚል ሀሳብ አቅርበዋል።አቶ ገብረዋህድ አክለውም፤ ሁለት ህፃናት ልጆቼ የሚንከባከባቸው በሌለበት መልኩ እንዲኖሩ ተገደዋል። ባለቤቴም ሆነች እህቷየተመሠረተባቸው ክስ ሰነድ መደበቅ ቢሆንም ተደብቋል የተባለው ሰነድ ግን ቀድሞም በኮሚሽኑ እጅ የገባ መሆኑን በማስታወስ፤ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች በዚህ ክስ ስር መጠቃለላቸው አግባብአይደለም ብለዋል። ይህም በመሆኑ ፍ/ቤቱ ሁለቱን የቤተሰብ አባላት በዋስ መብታቸው ተጠቅሞ እንዲያሰናብታቸውጠይቀዋል።በሌላም በኩል በተለይም በሁለተኛው የክስ መዝገብ ስር 5ኛ ተከሳሽ ሆነው የቀረቡት የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድበደባ እንደተፈፀመባቸውና ለሁለት ጊዜያት ያክል ራሳቸውን ስተው እንደነበርበማስታወስ፤ “በእስር ቆይታዬ አገሬ ምን እንደምትመስል አውቄያለሁ” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር የልብ፣ የደምና የስኳር ህመምተኛ መሆናቸውን ጭምር በማስረዳት የዋስትና መብት ጠይቀዋል። በዚሁ መዝገብ 3ኛተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት አቶ ጥሩነህ ባልቻ በበኩላቸው ሕገመንግስቱንና ሰብዓዊ መብትን በሚቃረን መልኩ በዱላ የታገዘምርመራ ተፈፅሞብኛል ሲሉ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል።በመዝገቡ ስር ሁለተኛ ተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣና ዋና ኦዲተር አቶ በላቸው በየነ፤ በጠበቃቸውአማካኝነት በቂ ማስረጃና ኤግዚቢት ይዘናል፤ ሠነድ ሰብስበናል ካሉ በኋላ የደንበኛዬን የዋስትና መብት በመገደብ ተጨማሪ የ14ቀናት ቀጠሮ ሊጠይቅ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል። ለ27 ዓመታት በመንግስት መስሪያ ቤት ማገልገላቸውን ያስረዱትተጠርጣሪው፤ እኔ የምተዳደረው በወርሐዊ ደመወዜ ነው ሲሉ በእርሳቸው መታሰር ምክንያት ቤተሰባቸው ችግር እንደገጠመውበመጥቀስ ፍርድ ቤቱን የዋስትና መብት ይከበርልኝ ሲሉ ጠይቀዋል።በድምሩም በችሎቱ ለመርማሪ ቡድኑ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ፍርድ ቤቱ አፅንኦት የሰጡባቸው ሦስት አበይት ጉዳዮችሲኖሩ፤ ይኸውም ቡድኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜን ሲጠይቅ ምንን እንደሚጠይቅ ቢታወቅም ማንን እንደሚጠይቅ በግልፅአለመቀመጡን፣ የሚሰሙት ምስክሮች በማን ላይ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ስለመሆናቸውና የትኛው ተከሳሽ በየትኛው ክስ ስርተጠያቂ እንደሆነ በግልፅ አለመስፈሩ ተጠቁሟል።የምርመራ ቡድኑ ተወካዮች በበኩላቸው ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ፤ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የተጠየቀው ወንጀሉ እጅግውስብስብና ሰንሰለታማ መሆኑን በመጥቀስ፤ ተጠርጣሪዎቹ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ከመሆናቸው አንፃር ከእስር በዋስ ቢለቀቁማስረጃዎችን ከማጥፋትም በላይ ምስክሮችን ሊያሸማቅቁ አሊያም ሊያግባቡ የሚችሉ ናቸው ሲል አስረድቷል።በምርመራ ሂደት ውስጥ ተፈፅሟል ለተባለው ሕገ-መንግስቱን የጣሰ የሰብዓዊ መብት ችግር አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ፣ ጉዳዩለፍርድ ቤት ሲደርስ ተጠርጣሪዎቹ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ችግሮች ካሉ እናርማለንየሚል ምላሽ ሰጥተዋል።የህክምናና የቤተሰብ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡም፤ ታማሚዎች ካሉ ማረሚያ ቤቱ የራሱ የሆነክሊኒክ መኖሩን በመጥቀስ ከክሊኒኩ በላይ ለሆኑ ህመሞች በሪፈራል ደረጃና ከዚያም በላይ ለማሳከም የሚያስችል አቅም መኖሩንጠቅሰዋል። ቤተሰብን በተመለከተ በተለይም 1ኛ ተጠርጣሪ በሰጡት አስተያየት ላይ ተመርኩዘው ሲያስረዱ ከቤተሰቡ የተገኘውሰነድ እንዳለ ሆኖ መርማሪ ቡድኑ የሚፈልጋቸው ሌሎች ሰነዶችም ስለመኖራቸው በመግለፅ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ መብት ከእስርቢለቀቁ አስቸጋሪ ይሆንብናል ብለዋል።በጥቅሉም ለተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት መስጠትን በሚመለከት በወንጀለኛ ሕጉ ላይ፤ የተፈፀመው ወንጀል በሀገር ሀብት ላይከሆነና ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል መሆኑ ከግምት ከገባ ዋስትና እንደማይሰጥ ይደነግጋል ሲሉ ለፍርድ ቤቱአስረድተዋል።የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱም፤ ተከሳሾቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል ከባድና ውስብስብ መሆኑን በመጠቆም የዋስትናመብታቸውን ውድቅ አድርጐ ለመርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ የ14 ቀናትን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። አያይዞም በሰጠው ትዕዛዝ፤የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት በሚመለከት ጥንቃቄ መደረግ እንደሚገባው አሳስቦ የምርመራ ሂደቱም ግልፅ ይሁን ሲል ትዕዛዝበመስጠት ለሰኔ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በተያያዘ ዜና በሙስና ወንጀል የተጠርጣሪዎቹን ቁጥር ወደ 54፤ የክስ መዝገቡን ደግሞ ወደ ሰባት ያደረሰው የእነመልካሙእንድርያስ ጉዳይ በመርማሪ ቡድኑ የተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ በመጠየቁ ለግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። በዚህመዝገብ የተዘረዘሩት ግለሰቦች መልካሙ እንድርያስ የናዝሬት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ሰራተኛ፣ ወ/ሮ አልማዝ ከበደ የባሕር ትራንዚትስራ አስኪያጅ፣ አቶ ዳዊት መኮንን ደላላ እና አቶ ዳዊት አብተው ሠራተኛ ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች የተጠረጠሩት ከትራንዚትድርጅቶች ጋር በመመሳጠር እቃዎች የጉምሩክን ስርዓት ባልጠበቀ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግና ያልተገባሀብትን ማካበት በሚሉ ወንጀሎች ነው።¾ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ የረቡዕ ሚርይ 29 ዕትም አዲስ አበባ

ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚጠራው ሰልፍ ላይ 100ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

በመስከረም አያሌው


የፊታችን ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በሚካሄደው እና ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው
ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለዝግጅት ክፍላችን
እንደገለፁት፤ ፓርቲው ባለፈው ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/
ቤት ፊት ለፊት ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያራዝም መንግስት
በጠየቀው መሰረት የፊታችን እሁድ ያካሂዳል። መንግስት በፀጥታ እና ሰላም ማስከበር
ሂደት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥመው ሰልፉን ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር መጠየቅ
ይችላል የሚል ህግ በመኖሩ ሰልፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲደረግ መወሰኑን
ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ሰላማዊ ሰልፉን በአፍሪካ ህብረት በዓል ወቅት ማካሄድ የተፈለገው ኢትዮጵያ በአሉን
ስለምታዘጋጅ እና መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው ስራ በመሆኑ የኢትዮጵያ
ህዝብና ሚዲያው እንዲሁም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለሚሰሙት ጥያቄው ከፍ
ብሎ ይሰማል ከሚል አስተሳሰብ መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ የሰላማዊ ሰልፉ ቀን
መራዘም ምንም የተለየ ነገር እንደማይፈጥር ገልፀዋል። “የችግሩ ባለቤትም ሆነ
መፍትሔ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። የሚጨቁነንም መንግስት እዚህ ነው ያለው” ያሉት
ፕሬዝዳንቱ፣ ሰልፉ በታሰበለት ቀን ቢካሄድ ጥሩ እንደነበር ገልፀው ቀኑ መቀየሩም ያን
ያህል ለውጥ እንደሌለው ተናግረዋል።
የሰላማዊ ሰልፉ በመራዘሙ በፊት ይሳተፋል ተብሎ ከታሰበው በላይ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ሰላማዊ ሰልፉን በህጉ
መሰረት ማስፈቀዱ እና ህዝቡም ጊዜ ወስዶ እንዲወያይበት በመደረጉ ከ100ሺ በላይ ሰዎች በሰልፉ ላይ ይገኛሉ ተብሎ
ይጠበቃል። በሰልፉ የሚነሱት አራት ጥያቄዎች በመሆናቸው ህዝቡ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና የተነሱ ጥያቄዎችን
የተመለከተ ብቻ እንዲሆንም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ፣
የእስልምናን እምነት ነፃነት በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ፣ የተፈናቀሉ ሰዎች
ወደሚኖሩበት አካባቢ በሰላም ተመልሰው ካሳ እና ድጎማ ተደርጎላቸው ህይወታቸውን እንዲቀጥሉ እንዲሁም የመልካም
አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ እና በስራ አጥነት እና በሙስና ላይ መንግስት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልግ የሚሉ ጥያቄዎችን
አንግበው ሰላማዊ ሰልፉን እንደሚያካሂዱም ተገልጿል።
ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፉ መነሻውን ግንፍሌ አካባቢ ከሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት በማድረግ በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ
እና ቸርቸል ጎዳና አልፎ እስከ ድላችን አደባባይ ወይም ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ የሚደረግ ሲሆን፤ በእለቱም አጠቃላይ
የሀገሪቱን ሁኔታ የሚገልፁ ንግግሮች እና መፈክሮች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።¾
(ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የረቡዕ ሜይ 29 ዕትም)

EPRDF, no identity and no vision

FOR  IMMEDIATE  RELEASE
EPRDF, no identity and no vision
                                                                                                                March 28 2013
For the past twenty one years, the Tigray People Liberation Front (TPLF) that has no mandate to rule Ethiopia has actually ruled Ethiopia with iron fist dashing on the  Trojan horse,  the  EPRDF ( Ethiopian People Revolutionary Democratic Front).  The EPRDF, a political front; composed of a hodgepodge of ethnically assembled organizations, is a hollow group of ethnic demagogues created by its late leader to materialize his lifelong dream of dividing Ethiopia along ethnic lines. Ironically, the EPRDF that blatantly boasts to have averted the disintegration of Ethiopia, firmly stood up to the dreams of its creator and augmented the fragmentation of Ethiopia, the very country it calls home.
On Saturday March 23, 2013, the EPRDF started its 9th and possibly what could be its last congress with an embarrassing; and to the vast majority of Ethiopians with a pointless theme of – “The Thoughts of Meles”.  In fact, if there is one good cause served by the 9th EPRDF congress, it should be that, the Trojan horse EPRDF proved to the Ethiopian people that it is a party in existence with a borrowed identity that rules over a nation of ninety million people with a dead vision of a deceased man. The EPRDF is a party that lives in the past, failed to cease the moment and has no vision for the future.
The four-day congress that ended on Tuesday came to an end with exactly the same hollowness that it started. To the surprise of its own members and diehard supporters, the four -day congress looked like much of a eulogy of a man (dead for seven months) than an occasion to map a vision for Ethiopia’s future.  Despite all indications of the nation’s chronic problems of ethnic conflict, poverty, human rights abuse, deteriorating living conditions, and alarming outflow of skilled manpower, the EPRDF vowed to extend its grip on power and carry on the same old failed policies of the past. All in all, the handmade toy, the EPRDF, shamelessly told the Ethiopian people that it has no vision of its own and nothing new on its plate.
Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy not only invalidates the resolution of the 9th congress of the EPRDF, but it also extends its call to the Ethiopian people inside and outside Ethiopia to come together and fight in unison to stop the implementation of a policy that has a hard to reverse  detrimental effect on our nation. Ginbot 7 reiterates its perennial message to the Ethiopian people and to the international community at large that there are much better alternatives to the tested and failed policies of the EPRDF that benefit the interest of the Ethiopian people, the Horn of Africa and all other parties’ involved. The international community, donor nations and most importantly, the EU, United Kingdom and the United States must come to their senses and acknowledge that freedom; justice and democracy are God given human values that the people of Ethiopia thirst for just like the British and the American people.

May 28, 2013

የእንክርዳድ ውርስ ክፍል ፩ /The Inheritance of Chaffs/

Part-I/
በረከት ስምኦን “የሁለት ምርጫዎች ወግ“ የተሰኘ መፅሐፉን በሸራተን አዲስ ሲያስመርቅ ´´አሮጌዋ ኢትዮጵያ እየፈራረሰች በአዲሷ ኢትዮጵያ እየተተካች…………´´ እያለ ተናግሮ ነበር።በእርግጥ በሌላ በኩል ´´ሀገር ማለት ብሄር ብሄረሰቦች እንጂ ወንዝና ተራራው አይደለም፥የግዛት አንድነት ጉዳይ የነፍጠኝነት ጉዳይ ነው´´ እያሉ የወያኔ ርዕሳን ሲናገሩ መስማቱንም ለምደነዋል።
እስኪ በቅርቡ በተዘጋው የወያኔ የ21 ዓመት የመጀመሪያ ምዕራፍ ´´ገነባናት´´ ያሏትን ኢትዮጵያ እና ለትውልድ ያስተላለፉትን ውርስ እንመልከት።
ሀ. ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውርሶች
1.    መሀይምነት /Illiteracy/
በኢትዮጵያ የወታደራዊው አስተዳደር ሲወድቅ ከመሀይምነት የተላቀቀው የህብረተሰብ ክፍል 60% ሲሆን ይህም ከነበረው ሃምሳ ሁለት ሚሊየን አጠቃላይ ህዝብ ውስጥ 31.2 ሚሊየን ይደርስ ነበር።ከ21 ዓመት የወያኔ አገዛዝ በኋላ ከመሃይምነት የተላቀቀው የህብረተሰብ ክፍል የቁልቁለት ጉዞውን ቀጥሎ 30% ብቻ ሲሆን ይህም ከ80ሚሊየን አጠቃላይ ህዝብ ውስጥ መፃፍና ማንበብ የሚችለው 24 ሚሊየን ሲሆን ከዛሬ 21ዓመት በፊት ከነበረው በ7.2 ሚሊየን ያንሳል።በተጨማሪም 35.2 ሚሊየን አዳዲስ መሃይሞች ሲፈጠሩ በሀገሪቱም ያለው አጠቃላይ የመሃይም ቁጥር 56 ሚሊየን ደርሷል።
መሀይምነት በራሱ የጨለማ ኑሮ ከመሆኑ ባሻገር መሀይም ማህበረሰብ ለኢኮኖሚው ከሚያደርገው አስተዋፆ ይልቅ በሀገር ዕድገት ላይ ሸክም እና ጎታች መሆኑ በተለይ አሁን ካለው የአለማቀፍ ሁኔታ አንፃር የመሀይምነት ጠባሳ በሀገራችን ላይ የሚያስከትለውን ጫና በዚህ አጭር ፅሁፍ መዘርዘር የማይታሰብ ሲሆን አጠቃላይ ሂደቱ ግን በሻዕቢያ ተፀንሶ በወያኔ እየተተገበረ ያለው ‘‘የመቶ አመት የቤት ስራ‘‘ ውጤት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
ለመሆኑ ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎችንና በርካታ ትምህርትቤቶችን የገነባው የወያኔ መንግስት ‘‘ቆመንልሃል“ የሚለውን ህዝብ እንዴት ከመሃይምነት የቁልቁለት ጉዞ ሊታደገው አልቻለም?
1.1  የተገነቡት ተቋማት አላማ ፖለቲካዊ አጀንዳ መያዛቸውእንደሚታወቀው የወያኔ መንግስት በየክልሉ ብሎም በዞን ከተሞች ‘‘ዩኒቨርሲቲ“ እያለ በርካታ ተቋማትን የከፈተ ሲሆን በተጨማሪም በየወረዳውና በየቀበሌው ‘‘ትምህርት ቤት“ መክፈቱ ይታወሳል።ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ ከላይ ሲታይ /From surface value/ በጎ የልማት ጅማሬ ቢመስልም ወደውስጥ ዘልቀን ስናየው ግን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚያስችል ሁኔታ ፖለቲካዊ አጀንዳ የያዘና በአካባቢው ላይ የወያኔን ተቀባይነት ለማስገኘት የሚደረግ ሩጫ ነው።ለምሳሌ ወያኔ በምርጫ -97 በጉራጌ ዞን መሸነፉን ተከትሎ ‘‘ጉራጌው ከነፍጠኛው ጋር ወግኗል“ በሚል በዞኑ ከፍተኛ ቅስቀሳ የተደረገ ሲሆን እንደ አርቲስት መሐሙድ አህመድ አይነት ስመጥር የአካባቢው ተወላጆች በተገኙበት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ለጉራጌ ህዝብ መብት ´´መከበር´´ ያደረገው አስተዋጽኦ በሰፊው ከተነገረ በኋላ መለስ ዜናዊ በወልቂጤ ከተማ በመገኘት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን የመሰረት ድንጋይ አኑሯል።ይህም በዋናነት የጉራጌ ህዝብ በወያኔ ላይ ያለውን ቅሬታ ለማለዘብ ተብሎ የተደረገ የፖለቲካ ስራ ነበር።የእነዚህና መሰል ተቋማት የመጀመሪያ አላማ ፖለቲካዊ ተቀባይነትን ለማግኘት ብቻ የተመሰረቱ በመሆኑ የወያኔ መንግስት ህዝቡን በጅምላ ለትምህርት ማንቀሳቀስ /Mass Mobilization/ ተስኖታል።
በቂ የትምህርት ተቋማት ባልተሟላበት የወታደራዊው መንግስት ዘመን ሰዎች ዛፍ ስር ሳይቀር እንዲማሩ ህዝብን ማንቀሳቀስ በመቻሉ ቢያንስ 60% የሀገሪቱ ህዝብ ከመሀይምነት መላቀቅ ሲችል በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ግን የተሻለ ቁጥር ያላቸው ትምህርትቤቶችና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተገነቡበት ሁኔታ የመሀይምነት አኃዙ ወደላይ ማሻቀቡ በእርግጥ ከወንዝና ተራራ በላይ ህዝቦችን የመውደድ ኢህአዴጋዊ ፍቅር ውጤት ይሆን?´´በኖራ የተለሰነ መቃብር ´´ እንዲል መጽሐፍ።ወትሮስ መቃብር የቱን ያህል ቢያስውቡት አጽም እንጂ ህያው አይኖርበት።
1.2 ትምህርትን ለማስፋፋት በሚል ሽፋን ቀጣይነት ያለው እርዳታ ለማግኘት በኢትዮጵያ ታሪክ እንደወያኔ መንግስት ከለጋሽ ሀገራት የውጭ እርዳታ ያገኘ መንግስት የለም።ይህም ሊሆን ከቻለባቸው ምክንያቶች አንዱ ወያኔ በኢትዮጵያ ትምህርትን አስፋፋለው የሚለው ፕሮፖጋንዳ ሲሆን ለጋሽ ሀገራትንም ለማማለል በየአካባቢው የሚገነቡ ተማሪ አልባ ትምህርት ቤቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።ለጋሽ ሀገራትም ስለተገነቡት ትምህርት ቤቶች እንጂ በውስጡ ስለሚማሩት ተማሪዎች አሀዝ ትኩረት ስለማይሰጡ በትምህርት ማዳረስ ሽፋን ስም ወያኔ ለሚያካሂደው ንግድ አመቺ ሁኔታን ሲፈጥር በኢትዮጵያ ውስጥም መሀይምነት እጅግ እንዲስፋፋ አድርጓል።
2. የከፋድህነትእና-ፍትሀዊየሀብትክፍፍል /Abject Poverty and Unfair Wealth Distribution/
ወጣቱ ደራሲና ጋዜጠኛ መሐመድ ሰልማን ´´ፒያሳ መሐሙድ ጋ ጠብቂኝ´´ በተሰኘው መጽሐፉ ሁለት ኢትዮጵያዎች እንዳሉ ይነግረናል።የኢቲቪዋ ኢትዮጵያና በገሃዱ አለም የምናውቃት ኢትዮጵያ።
ሚሊየነር ገበሬዎች እንደአሸን የፈሉባት፣የኢኮኖሚ ዕድገቷ የምዕራቡን አለም እጅግ በማሳሰቡ ኒዎ ሊበራሎች ዕድገታችሁን ካላቆማችሁ እያሉ ባለስልጣኖቿን የሚወተውቱባት፣አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የውጭ ሀገር ዲፕሎማት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ከሷ ብዙ ሊማሩ እንደሚገባቸው የመሰከሩላትን የኢቲቪዋን ኢትዮጵያ ለወያኔና ሆድ አደር ጋዜጠኞቹ እንተወውና በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የድህነት መጠንና አይነተኛ መገለጫዎቹ እንዲሁም ስላለው ኢ-ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንመልከት።
2.1 እጅግ የከፋ ድህነት /Abject Poverty/:- በኢትዮጵያ ያለውን የድህነት መጠን በቁጥር ከመግለፅ ይልቅ ዋና ዋና መገለጫዎቹን ማየቱ የበለጠ ግንዛቤ ይፈጥርልናል።ይህም ማለት ትርፍራፊ ምግቦች እንደ ምግብ መሸጣቸውን እና አብዛኛው ህዝብ ከቻለ በቀን ሁለቴ አልያም በቀን አንድ ጊዜ መብላቱን እንደዋና የድህነት መገለጫ ሳናነሳ ማለት ነው።
2.1.ሀ. የጅምላ ስደት/Mass Migration/  በኢትዮጵያ ቅድመ ወያኔ ታሪክ የኢትዮጵያ ወጣት በብዛት የተሰደደበት ወቅት ቢኖር የቀይ ሽብር ዘመን ሲሆን ይህም በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ አፈና እንጂ እጅግ ስር በሰደደ ድህነት ምክንያት አልነበረም።ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የኢትዮጵያ ወጣት በጅምላ እየተሰደደ ሲሆን በሀገር ቤት ያለውም ቀዳሚ ምርጫው ስደት እንደሆነ በቅርብ የወጣውን የአለማቀፉ የቀውስ አጥኚ ቡድንን /International Crisis Group/ ጥናት ማየት ብቻ በቂ ነው።
አብዛኛው ስደተኛም የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስደተኛ ሲሆን ከዕድሜ አንፃር በሁሉም የዕድሜ ክልል፣ከፆታ አንፃር ሁለቱም ፆታዎች፣ከትምህርት ደረጃ አንፃር የተማሩትም ያልተማሩትም የተካተቱ ሲሆን ህይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል እያወቁ እንኳን ስደትን መምረጣቸው ዜጎቻችን በሀገራቸው መሰረታዊውን ነገር እንኳን ማግኘት እንዳልቻሉ ከማሳየቱም ባሻገር የድህነቱም መጠን ምን ያህል ስር እንደሰደደ ያሳየናል።
ሀገራችን ተማሪዎቿን እስከ ከፍተኛ ተቋማት ለማድረስ ዋጋ ያልከፈለችበት ያህል ዛሬ በህሊና ብስለት፣በዕውቀትና በዕድሜ አፍላ የሆኑ ወጣቶቻችንን በየስደተኛ ጣቢያው ተጥለው ስናይ ድህነት ከጊዜ ወደ ጊዜ የግዛት አድማሱን እያሰፋ ከገዢዎቻችን እና በዙሪያቸው ካሉት ሰዎች ውጪ ያለውን ሰፊውን የህብረተሰብ ክፍል እጅ ተወርች ጠርንፎ እንደያዘው ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።
2.1.ለ. ከድህነት ጋር ግንኙነት ያላቸው በሽታዎች ሥርጭት /Poverty Related Diseases/  ከድህነት ጋር ቀጥታ ግንኙነት ካላቸው በሽታዎች በዋናነት ኤች አይ ቪ ኤድስ፣የሳምባ ነቀርሳ፣ወባ፣የልጅነት ልምሻ የመሳሰሉት ሲሆኑ ያለምንም ማጋነን ከላይ በተዘረዘሩት የበሽታ አይነቶች የተጠቁ እና እየተጠቁ ያሉ በርካታ ዜጎች ከሚገኙባቸው ሀገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን በተለይ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት እዚህ ደረጃ የደረሰው በወያኔ ዘመን ነው።ለዚህም እንደማስረጃ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ በአንድ ወቅት ሲናገሩ ደርግ ወድቆ ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ በየሆቴሎች እንግዳ መቀበያ ላይ /Reception/ ኮንዶም ይቀመጥ የነበረ ሲሆን ወያኔ አዲስ አበባ ከገባ ከጥቂት ወራት በኋላ ግን ይህ ልምድ የተቋረጠ ሲሆን ቢያንስ ከ1983-1988 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በወያኔ መንግስት በኩል ግንዛቤን በህብረተሰቡ ውስጥ ለመፍጠር የተሰራ ነገር ባለመኖሩ በርካታ ህዝብ በዚህ በሽታ ሊጠቃ ችሏል።በሌላ በኩል ኤች አይ ቪ ኤድስም ሆኑ ሌሎች በሽታዎች ለወያኔ የውጭ እርዳታ መለመኛ መንገድ መሆናቸውን ልብ ልንለው የሚገባ ጉዳይ ነው።
2.1.ሐ. የጎዳና ተዳዳሪነት /Street Life and Loitering/መጠኑ ይለያይ እንጂ የጎዳና ተዳዳሪነት በአብዛኛው አለም የተለመደ ሲሆን ለምሳሌ በጀርመን፣በኢንግላንድና በስካንዲኔቪያን ሀገሮች ሁሉም ዜጋ የመኖሪያ ቤት የሚሰጠው ሲሆን በነዚህ ሀገራት የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ይህን ህይወት በፈቃዳቸው ፈልገው የሚያደርጉት ነው።
ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ ስንመለስ ግን በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ድህነት ገፍቶ ወደ ጎዳና የጣላቸው ሰዎች ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ምሁራን፣ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ምሩቃን፣በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በተለያየ ሙያ ያገለግሉ የነበሩ ዜጎች ሲገኙበት ለዚህም እንደመንስኤ የሚነሳው ዜጎቻችን የወያኔ አባል ካልሆኑ አልያም ፖለቲካዊ አቋማቸው ወያኔን የሚጋፋ ከሆነ በሰፊው የድህነት ባህር ውስጥ እንዲደፈቁና ለጎዳና ህይወት እንዲዳረጉ ይገደዳሉ።
ከዚህም ባሻገር በገጠር አካባቢ መሬት የፖለቲካ መሳሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ ገበሬው በማዳበሪያ ዕዳ ኑሮው ስለሚናጋ በርካታ ህዝብ ወደከተማ እንዲፈልስ በዚያም በጎዳና ላይ ኑሮውን እንዲገፋ ይደረጋል።
2.2 ኢ-ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል /Unfair Wealth Distribution/:-ሀገራችን ኢትዮጵያ ከዕዝ ኢኮኖሚ ተላቃ ገበያ መር ኢኮኖሚ እየተከተለች ነው ከተባለ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ቢሆንም በማህበረሰቡ ውስጥ እየታየ ያለው የሃብት ክፍፍል ግን ፍጹም ገበያ መር ኢኮኖሚ ከሚያስከትለው ተጽዕኖ ተመጣጣኝ ካለመሆኑ ባሻገር በሃገሪቱ ውስጥም እየታየ ነው የሚባለው “ዕድገት“ የጥቂት ቡድኖች ዕድገት ሆኖ እናገኘዋለን።
በመሆኑም በሃገሪቱ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ለመጣው ድህነትና ኢ-ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ዐይነተኛ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙትን ጉዳዮች እንመልከት።
2.2.ሀ. የፖለቲካ ተቋማት አወቃቀር /The Nature of Political Institutions/በግልፅ እንደሚታየው የወያኔ መንግስት የሃገሪቷን የፖለቲካ ተቋማት ያዋቀረበት መንገድ ሁሉን አሳታፊ /All-inclusive/ ያልሆነ ይልቁንም ጥቂት የአንድ አካባቢ ተወላጅ ኅሩያን /Elites/ በዋናነት የሚያሽከረክሩት መዝባሪ ተፈጥሮ /Extractive Nature/ ያለው ሆኖ እናገኘዋለን።ይህ አይነቱ የፖለቲካ ተቋማት አደረጃጀት በባህሪው እውነተኛ መድብለ ፓርቲ /Bona fide Pluralism/ እንዳይፈጠር በግልጽም ይሁን በህቡዕ /Overtly or Covertly/ ስለሚከላከል ተጠያቂነት የሌለበት ገደብ አልባ ሥልጣን /Unconstrained Power/ በጥቂት ኅሩያን እጅ በህግ ላልተገደበ ጊዜ እንዲቆይ ያደርገዋል።ይህም መዝባሪ የፖለቲካ ተቋም ለሀገር እና ለህዝብ ዘለቄታዊ ጥቅም ከመስራት ይልቅ የጥቂት ቡድኖችን ሥልጣን ለማጠናከሪያነት የሚረዱ አቻ መዝባሪ የኢኮኖሚ ተቋማትን /Extractive Economic Institutions/ በመገንባት ላይ ይወሰናል።ከዚህም ባሻገር የስርዐቱ ዋነኛ አጀንዳ የፖለቲካ ሥልጣኑን ማስጠበቅ በመሆኑ የሀገሪቱን አብዛኛ መዋዕለ ነዋይ ህዝብን ለማፈን የተጋነነ የፖሊስ ኃይልን እና የደህንነት ተቋማትን በመገንባት፣በካድሬ ምልመላ እና ስልጠና እንዲሁም በድርጅታዊ ተግባራት ላይ ስለሚያውለው በስርዐቱ ዙሪያ ካሉ ጥቂቶች ውጪ ያለው ሰፊው የህብረተሰብ ክፍል ለገዥዎቹ የሀብት ምንጭ ከመሆን በዘለለ የሃገሪቱ የሀብት ተካፋይ ሊሆን አይችልም።በተጨማሪም በዚህ ዓይነት የፖለቲካ ስርዐት ውስጥ በሙስና ላይ የሚኖረው ተጠያቂነት ለዘብተኛ በመሆኑ ከግለሰብ ጀምሮ እስከተደራጀ የሙስና ወንጀል መመልከት የተለመደ ተግባር ይሆናል።ለዚህም ነው በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ እና የጦር ሹመኞች የሀገሪቱን ሀብት በመዝረፍ እና በማሸሽ ተግባር የተጠመዱት።
2.2.ለ. የኢኮኖሚ ተቋማት አወቃቀር /The Nature of Economic  Institutions/በኢትዮጵያ ያለው የኢኮኖሚ ተቋማት አወቃቀር በዋናነት በሥልጣን ላይ ላለው ቡድን ተጨማሪ ኃይልን በሚፈጥር መልኩ መዝባሪ ባህርይ /Extractive Nature/ ያለው ሲሆን የሀገሪቱ የተፈጥሮ ሃብትም ከሞላ ጎደል በዚህ ቡድንና በሥልጣኑ ዙሪያ ባሉ የጥቅም ተሳሳሪዎች /Cronies/ እጅ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜም ከፍተኛ ብዥታ እየፈጠረ ያለው የእዚህ አናሳ ቡድንና በሥልጣኑ ዙሪያ ያሉ ጥቅመኞችን የሀብት ዕድገት የመላው ህብረተሰብ እና የሀገሪቱ ዕድገት አስመስሎ የማቅረቡ ጉዳይ ነው።
በመሰረቱ መዝባሪ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተቋማት እርስ በእርሳቸው ተመጋጋቢ ሲሆኑ እንዲህ አይነቱ የፖለቲካ ተቋም ሥልጣንን ያለገደብ በጥቂቶች እጅ በማድረግ አቻ የሆኑ የኢኮኖሚ ተቋማትን ለመፍጠር፣የኢኮኖሚ ተቋማቱን በተለየ ሁኔታ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ህጎችንና አዋጆችን ለማፅደቅ፣በገበያው ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር፣ነጻ ፉክክር እንዳይኖር እንቅፋቶችን ለመፍጠር /To erect entry barriers/ ሲረዳ በምላሹ እነዚህ መዝባሪ የኢኮኖሚ ተቋማት የሀገሪቱን ሀብት ከአብዛኛው ህዝብ በመዝረፍ በሥልጣን ላይ ያለውን ቡድን በሀብት እና ኃይል ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርጉታል።
ለዚህም አይነተኛ ማሳያ የሚሆነን የህወሃት ቡድን የፖለቲካ ሥልጣኑን ያለገደብ ሲቆጣጠር “ኤፈርት“ የሚባል መዝባሪ ግዙፍ የንግድ ኢምፓየር የገነባ ሲሆን ከኤፈርት የተረፈውን ክፍተት የፖለቲካ እና የጦር ባለስልጣናት እንዲሁም በሥርዓቱ ዙሪያ የሰፈሩት ጥቅመኞች በግላቸው እና በዘመዶቻቸው ስም ባስመዘገቧቸው የንግድ ተቋማት ስልጣንን ተገን ያደረገ ካፒታሊዝም /Crony Capitalism/ መመስረት ችለዋል።በመሆኑም የወያኔ መንግስት በየጊዜው የሚያወጣቸው ባለሁለት አሃዝ “ዕድገት“ በእርግጥም የኢትዮጵያ ዕድገት ሳይሆን የእነዚህ ጥቂት ቡድኖች ግዙፍ የንግድ ተቋማት እድገት ሆኖ እናገኘዋለን።
 3. ሙስና /Corruption/
´´ምርኮ ፈጠነ፥ብዝበዛ ቸኮለ´´
በአንድ ወቅት በኢትዮጵያን ሪቪው /ethiopianreview.com/ ድረ-ገጽ ላይ ´´አስራአንደኛው ትዕዛዝ´´ /The Eleventh Commandment/ የተሰኘ ጽሑፍ ጽፌ ነበር።በእርግጥ አስራአንደኛው ትዕዛዝ ማለት ´´በፖለቲካችን እስካልመጣህ፥የምንልህንም እስካደረግህ ድረስ ብትሰርቅም፣ብትዘርፍም ምንም አይደል´´ የምትለዋ የወያኔ ያልተፃፈች ህግ ናት።
ለዚህም ነው አንድ የወያኔ ባለስልጣን ለገጣፎ አካባቢ በስሙና በቤተሰቦቹ ስም 60 /ስልሣ/ የመሬት ይዞታዎችን የያዘ፣ለዚህም ነው በሲፒኤ ስኬል መሠረት ደሞዛቸው ከ5000.00 /አምስት ሺህ/ ብር የማይበልጥ ጄነራሎች ከ10,000.00 /አስር ሺህ/ ዶላር በላይ የሚከራዩ ቤቶችን የገነቡት፣ለዚህ ነው የሚንስትሮቻችን ሚስቶች ከቻይና አዲስ አበባ እንዲሁም ከዱባይ አዲስ አበባ የሚመላለሱ ሲራራ ነጋዴ የሆኑት፣ለዚህም ነው የቀድሞዋ ቀዳማዊ እመቤት አዜብ መስፍን በአንድ ቀን የአልባሳትና ጌጣጌጥ ግብይት 1.2 ሚሊየን ዩሮ ወይም በአማካይ 26.4 ሚሊየን ብር ማውጣታቸውን ከስፔን ጋዜጦች ያነበብነው።
እንዲሁ ለማሳያ ያህል ጠቀስኩት እንጂ ከግልገል ካድሬዎች ጀምሮ እስከሚንስትሮቻችን እና የጦር ሹመኞች ድረስ የመግባቢያ ቋንቋቸው ሁሉ ´´በዋሌትህ አስብ፥በእጅህ ተናገር´´ ከሆነ ዘመናት አልፈዋል።ዛሬ ከጥንት ጀምሮ በሙስና ከሚታወቁት ናይጄሪያን ከመሳሰሉ ሀገራት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀን በሙሰኛ ሀገራት የደረጃ ሠንጠረዥ የመጀመሪያው ረድፍ ላይ እንገኛለን።
በሌላ በኩል በ1993 ዓ.ም. የተቋቋመው ´´ፀረ-ሙስና ኮሚሽን´´ በመባል የሚታወቀው መስሪያ ቤት ልክ እንደ ፍርድ ቤቶች ሁሉ የህዝብ አመኔታ የሌለው ተቋም ሲሆን ቀዳሚ አላማውም አስራአንደኛውን ትዕዛዝ የሚተላለፉ የወያኔ ባለስልጣናትን ለመቅጣት እንጂ በርግጥም እንደስያሜው ሙስናን ለመዋጋት የቆመ አይደለም።
» » » »(ክፍል ፪ ይቀጥላል)« « «
» » » »(Part II to be continued)« « «

(በዳዊት ፋንታ)
(By: Dawit Fanta)

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” – ከአቤ ቶኪቻው


                                                                አቶ በረከት

“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ጉንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አለ ታጋዩ…“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ አሁን ደግሞ ለራሱ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ቆጣጥሮታልም፤ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አልኩ እኔ…“ኢህአዴግ ደርግን ደመሰሰ እና ሌላ ቀዳበት” አለ ልጅ ያሬድ! ”ኢህአዴግ ደርግን ደምስሶ በደርግ ዜማ ሌላ ቀዳበት” አልኩ እኔ ዛሬ ግንቦት ሃያ ነው፡፡ አነዛ ፀጉራቸውን አሳድገው አዲሳባ የገቡ ሰዎች ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደር ያሳድጉልናል… ብሎ ተስፋ የጣለባቸው ሁሉ በቴስታ ብለው ከጣሉት እነሆ ሃያ ሁለት አመት እንደዋዛ ሆናቸው፡፡መልካም አስተዳደሯንም ለራሳቸው እያደሯት፤ ዴሞክራሲዋንም ራሳቸው እየኮመኮሟት ህብረተሰቡን እንቁልጭልጭ አሉት፡፡ዛሬ የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር የአባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ ወንዙ ተቀይሶ ምን ላይ ሊሆን ነው… እንዴትነው ነገሩ በሳፋ ነው እንዴ ግድቡ የሚሰራው… ብዬ ልጠይቅ ወይስ አልጠይቅ…!አስታውሳለሁ፤ “አባይ ይገደብ በቃ” ብለው ጠቅላዩ የወሰኑት ከሁለት አመት በፊት “በቃ” በሚል ሀይለ ቃል …ኢህአዴግይበቃዋል ግንቦት ሃያን ዘንድሮ ለመጨረሻ ጊዜ እናከብራለን ከዛም ለድጋፍ ሰልፍ ወጥተን በዛው እንቀራለን፡፡ ኢህአዴግእስካልወረደ ድረስም እቤታችን አንገባም…. የሚል እንቅስቃሴ በፌስ ቡክ በኩል ተጀምሮ የነበረ ጊዜ ነው፡፡በዚህ በ”በቃ” ጦስ እነ ርዮት አለሙ እነ ውብሸት ታዬ እነ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር እነ ሂሩት ክፍሌ ወድያው ለእስርሲዳረጉ ቀስ በቀስ ደግሞ ሌሎችም ለቃሊቲ እና ለቂሊጦ ተዳርገዋል፡፡ (በተለይ የነዚህ ወዳጆቼን ፍርድ ሂደት ስከታተል ነበር እናአጋነንክ ቢሉኝም ባይሉኝም የአቃቤ ህግ ማስረጃ “በቃ የሚለውን የፌስ ቡክ እና የአደባባይ እንቅስቃሴ ትኩር ብላችሁአይታችኋል” የሚል ነበር)እንቅስቃሴው በፌስ ቡክ ተጀምሮ በየአደባባዩም “በቃ” የሚል ሃይለቃል በመፃፍ ተሟሙቆ የቀጠለ ነበር፡፡ በርካቶችም ግንቦትሃያ መስቀል አደባባይ የሚፈጠረውን ተዓምር እያሰቡ አንድም ደስታ አንድም ፍርሃት ሲፈራረቅባቸው አንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ይሄኔ አቶ መለስ ፈርሸው ዘየዱ፤ (ሁል ጊዜ ቁጭ ብለው አሰቡ… እያልንኮ ፍራሽ የሌላቸው አስመሰልናቸው… “ፈርቸው” ማለትፍራሽ ዘርግተው እጅግ በተመስጦ ማሰብ ማለት ነው…) አስበው አስበውም፤ “ለምን አባይን አንገድበውም…” አሉ እርሳቸውብለው እምቢ… እንዴት… ለምን… በምን… አይባልምና እሺ እሺ ተብሎ ተጀመረ፡፡ የዛን ጊዜውን ግንቦት ሃያም መንግስታችንለአባይ ግድብ ድጋፍ ሰልፍ ውጡልኝ፡፡ አለ… በዛውም የህዝቡ የተቃውሞ ሃሳብ ተገደበ፡፡የአቶ መለስን ብልጠት በመኮረጅ ፈተናዎች ይታለፋሉ ብለው የሚያምኑት አቶ በረከት ደግሞ ዛሬ እነሆ በግንቦት ሃያው አባይወንዝን የማስቀየስ ስራ እነደሚሰራ በቴሌቪዥናቸው ብቅ ብለው ነገሩን፡፡ጥሩ ኮርጀዋል…! አኮራረጃቸው ስም ሁሉ ሳይቀር እንደሚቀዳ አይነት ኮራጅ ነው፡፡ህዝቡ ይህንን ዜና ሲሰማ ምን አላቸው… የሚለውን ቤት ለቤት ሄደን መጠየቅ ብንችል ጥሩ ነበር፡፡ መጠየቅ ባንችል ግንመጠርጠር እንችላለን እና አንዲህ እንጠረጥራለን፤“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” ሳይላቸው አይቀርም፡፡

ወያኔ እና እኛ ሙስና ስንል

በቅርቡ በሀገር ውስጥ ገቢና በጉሙሩክ አገልግሎት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ጥቂት ባለስልጣኖችና ተባባሪ የተባሉ ግለሰብ ነጋዴዎች፣ በሙስና ተወንጅለው ወህኒ መውረዳቸውን ተከትሎ ወያኔ ፀረ-ሙስና ድርጅት ለመምሰል ከተግባሩ የበለጠ የከበሮ ድምጽ እያሰማን ይገኛል። አንዳንድ የዋህም ይህን ከበሮ በመስማት ሙስናን ለማጥፋት ዘመቻ የተጀመረ መስሏቸው ተስፋ ሲያደርጉ ይታያል።
በመሰረቱ ሙስና በወያኔ ስርአት ውስጥ የስርአቱ መቆሚያ ምሰሶ ከሆነ ውሎ አድሯል። በሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት እየተመናመኑ በሄዱበት ፍጥነት ነው ሙስና እየደራ የሄደው። ከላይ እስከታች በተዘረጋው የወያኔ ስርአት ውስጥ ከቁንጮ ባለስልጣናት እስከታችኛው አገልጋይ ድረስ በሙስና ያልተዘፈቀ የስርአቱ አገልጋይ መፈለግ ከዝንጀሮ ቆንጆ የመምረጥ ያህል ከባድ ሆኗል።
የወያኔ ትላልቅ ሙሰኞች ለምልክት ትንንሽ ሙሰኞችን አልፎ አልፎ በማሰር ፀረ ሙሰኛ መስለው ሊያሞኙን ቢሞክሩ ዛሬ የመጀመሪያቸው አይደለም። ወያኔ ሙስናን ክስ የሚጠቀምበት አንድም በውስጡ ካፈነገጡ ሃይሎች ጋር የፖለቲካ ልዩነትን ለማወራረጃ ወይም ለውጭ ለጋሾች ሙስናን የሚጠላ መስሎ ለመታየት ሲፈልግ ብቻ መሆኑን ከልምድ እና ከተግባሩ ህዝቡ ያውቀዋል።
የወያኔ መንግስት ሀገሪቱን ወደ ድህነት ማቅ ቁልቁል እያስገባና ሀገሪቱ በእዳ እያስያዘ፣ በአንጻሩ ግን የስርአቱ ቁንጮ ባለስልጣናት በሙስና ተዘፍቀው፣ በልፅገውና ከብረው፤ ራሳቸውን ከሙስና ነጻ ሆኖ ለመታየት ሲያሻቸው ግልገሎቹን በማሰር እና በራሳቸው ሚዲያ አስረሽ ምችው ይጨፍራሉ።
በእኛ እይታ ወያኔ ራሱ ቆሞ የሚሄድ ሙስና ነው። ወያኔና ሙስናን፣ ሙስናንና ወያኔን መለያየት አስቸጋሪም ነው። የወያኔ አባልና ደጋፊ የሚሰበሰበው፣ የሚመለመለው በመንግስት ሀብትና ንበረት ሰዎችን በማባበል ነው። ይህም ሙስና ነው።
ወያኔ ለየእለቱ የፖለቲካ ድርጅታዊ ስራውና በምርጫ ጊዜ በገፍ ካለ አቤት ባይ የሚጠቀመው የመንግስት ገንዝብ፣ ተሽከርካሪ፣ ነዳጅ፣ ቢሮ፣ የሚከፈለው የመንግስት ውሎ አበል፣ የሚገለገልበት የህዝብ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ጋዜጣ ወዘተ የሙሰኝነት ስርአታዊነቱ መገለጫ ነው። የመንግስት ስራ እድልን ከተማሩ ዜጎች ሳይቀር እየነጠቀ በዘርና በወያኔ አባልነት መለኪያ ለተመለመሉ አባሎች የሚሰጠው ስጦታ ዘግናኝ ሙስና ነው።
ኤፈርት የተባለው የወያኔ ኩባንያ ከህዝብና ከመንግስት በተዘረፈ ሀብት መመስረቱን እንደማያውቅ ትተን ትላንት ከባንክ ካለተከራካሪ እየተበደረ የሚነግድብን ንግድ፣ ሲከስር ብድሩና ወለዱን መክፈል ሲያቅተው ወያኔ ሙስና ብለን ይህን እንድንጠራው አይፈልግም።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ ተገዶ ወይም ተወግዶ በሀገራችን በህግና ህግ ብቻ የሚሰራ መንግስት መመስረትን እንደ ግብ የምንቆጥረው ለዚህ ነው። ግንቦት 7 በሀገራችን ሙስና ላይ የአመረረ ትግል ማድረግና ሙሰኞችን ማጥፋት የሚቻለው ወያኔን ያስወገድን እለት ብቻ ነው። ስለዚህም የሀገራችን ህዝብ ሆይ ይህን ተረድተህ ትግሉን በአስቸኳይ ትቀላቀል ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

May 27, 2013

Meles Zenawi Net Worth


Net Worth: 3 milliarder dollarStats

  • Source of Wealthpolitikk
  • Meles Zenawi Age58years gammel
  • Meles Zenawi Birth PlaceAdwa, Etiopia
  • Meles Zenawi Sivil statusGift (Azeb Mesfin)
Meles Zenawi nettoformue: Meles Zenawi Asres var tidligere statsminister i Etiopia som ledet landet fra 1995 til sin død i 2012. Han var også president i Etiopia 1991-1995. Han var en av de siste literate og fremtidsrettede ledere i Afrika. Zenawi hadde en MBA fra Storbritannia, og en mastergrad i økonomi fra Nederland. Hans formue er i dag på 3 milliarder dollar.
Han sluttet seg til Tigrayan Folkets Liberation Front (TPLF) som medlem i 1975. Til slutt ble han valgt som leder for TPLF og EPRDF. Ledet av ham og andre ledere, var TPLF i stand til å overta makten i landet i 1991 som borgerkrigen tok slutt. Ved å bli statsminister, introduserte han en multi-party politisk system og tillot private pressen i landet. Han gikk med på å samarbeide med USA mot grupper og organisasjoner som Al Qaida opererer ut av landet.

Han ble tildelt Rwanda 'National Liberation Medal og også "World Peace Prize" for sitt bidrag til global fred. Zenawi også fikk "Yara"-prisen for å gjennomføre en grønn revolusjon i landet.Noen andre priser han hadde fått inkluderte Afrika Politisk Leadership Award i 2008, og Good Governance award.
Han giftet seg med Azev Mesfin, som er i dag medlem av den etiopiske parlamentet. Meles Zenawi døde i en alder av 57 år den 20. august 2012. Han døde av en infeksjon etter å ha en operasjon på grunn av en hjernesvulst.

የኢህአዴግና የሻዕቢያ ድርድር ተበጠሰ

ኳታር በተናጠል የጀመረችው ኢትዮጵያንና ኤርትራን የማሸማገል ሂደት መበጠሱ ተሰምቷል። ከሽምግልናው ዙሪያ የግብጽ ሚና ስለመኖሩ አመላካች ጉዳዮች አሉ እየተባለ ነው። በድርድሩ ኢህአዴግ በዋናነት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው የትግራይ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደሚት/ ጉዳይ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
አቶ መለስ የኢትዮጵያን ወደብ እንደተራ ጉዳይ አሳልፈው በመስጠት ኤርትራን እንደ አገር እውቅና በሰጡበት ወቅት ድጋፍ ለማሰማት ቀዳሚ የነረችው ኳታር ከበረሃው ትግል ጀምሮ የሻዕቢያ ወዳጅ አገር እንደሆነች ይታወቃል።
haile and esayasከዚሁ የከረመ ወዳጅነት በመነሳት ኳታር በ2008 ከኢህአዴግ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን የጸብ ግድግዳ አፍርሳ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው በዋናነት ሁለቱን አገሮች መልሶ ለማስታረቅ በተያዘ እቅድ ስለመሆኑ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ። በተለይም አሁን ያለው የኤርትራ አስተዳደር እጣ ፈንታ አብዝቶ ያስጨነቃት ኳታር በኤርትራ ወደብ ሊዝ በማድረግ፣ ኢንቨስትመንት ላይ በመሳተፍና ልዩ ድጎማ በማድረግ ቀዳሚውን ስፍራ ስለምትይዝ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ላይ ታች ማለቷ እንደማይደንቅ ስምምነት አለ።
ጎልጉል ምንጭ የሆኑ ዲፕሎማት እንዳሉት ኳታር አሁን እርቁን የፈለገችው በኤርትራ መረጋጋት እንዲፈጠርና የኤርትራ ኢኮኖሚ አንዲያገግም ለማድረግ በሚል ነው። በሌላ በኩል ህወሃት የዘወትር ስጋቱ የሆነውን ሻዕቢያን ለማስወገድ ሌት ከቀን እንደሚሰራና ይህም በድርጅት ደረጃ አቋም የተያዘበት ጉዳይ በመሆኑ የኤርትራ መንግስት መሰረታዊ የአቋም ለውጥ ሳያደርግ ከኢህአዴግ ጋር የድርድር ስምምነት ላይ መድረስ አስቸጋሪ እንደሚሆን ሁሉም ወገኖች የሚረዱት ጉዳይ ነው።
ከውስጥም ከውጪም ፖለቲከኞች ትኩረት ሰጥተው እየተከታተሉት ያለው የሁለቱ አገሮች  የሰላም ድርድር ዲፕሎማቱ እንዳሉት ሁለት አብይ ጉዳዮች አሉበት። ሁለቱ አብይ ጉዳዮች ደግሞ ሊነጣጠሉ አይችሉም። በኤርትራ እለት እለት እየሰለለ የሄደው የአገሪቱ ኢኮኖሚና የኑሮ ውድነቱ የኢሳያስን አስተዳደር አናግቶታል። በተጨማሪ ሆን ተብሎ ይሁን በሌላ ምክንያት ከሃያላኑ አገራት ጋር የገጠሙት የረዥም ጊዜ ፍትጊያ የኢሣያስን ትከሻ አዝሎታል። ከዚህም በላይ እድሜ ለመለስ የፍቅር ጊዜያቸው ሲሻግት “አሸባሪ” አድርገዋቸው።
ከዓለምና ከአህጉር መድረኮች ሙሉ በሙሉ ተገልሎ የከረመው የኢሳያስ አስተዳደር በተለያዩ ደረጃዎች የደረሰበትን እግድና ቅጣት ለመቋቋም የዲፕሎማሲ ዘመቻ የጀመረው ከውጪ ያለውን ችግር ተከትሎ በአገር ውስጥ የገጠመውን ፈተና ለመቋቋም እንደሆነ ተንታኞች ያስታውሳሉ። በውስጥ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አጣብቂኝ ውስጥ ያለው ሻዕቢያ ወንበሩ እየወላለቀ ስለሆነ ከቀድሞው ወዳጁ ህወሓት ጋር ለመወዳጀት ይፈልጋል።
ኤርትራ ኢኮኖሚዋ እንዲነቃቃ ኢትዮጵያን የንግድ ሸሪኳ ማድረግ የመጀመሪያው ስራ ነው።  ያለ ስራ “ሙት” ሆኖ የተቀመጠውን የአሰብን ወደብ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ባነሰ ዋጋ እንድትጠቀምበት ማድረግና ወደቡ ላይ ህይወት መዝራት ዛሬ ላይ ግድ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ጅቡቲ ላይ የራስዋን ወደብ ለመገንባት የጀመረችው እንቅስቃሴና ለጅቡቲ የወደብ ኪራይ የምትገፈግፈው እጅግ ከፍተኛ ወጪ ግማሹ እንኳን ኤርትራ ቋት ውስጥ ቢገባ አሁን የተፈጠረውን የኑሮ ግለት ጋብ እንደሚያደርገው በርካቶች ይስማሙበታል።
በዚሁ መነሻ የኢሳያስ መንግሰት ከገባበት የመኖርና አለመኖር ስጋት ለመገላገል እቅድ ተነድፎለት የተጀመረውን ድርድር ኢህአዴግ የህልውና ጥያቄ በመጠየቁ ሳቢያ ብዙም ሳይራመድ በእንጭጩ ተኮላሽቷል። ኢህአዴግ በድርድሩ መሰረታዊ ሃሳብም ሆነ በሌሎች ዝርዝር የኢኮኖሚ ነጥቦች የተፈለገው ርቀት ድረስ ለመጓዝ ፈቃደኝነቱን ለመግለጽ ጊዜ አልወሰደም ነበር። የለበጣም ቢመስልም አቶ ሃይለማርያም አስመራ ድረስ ለመሄድ ዝግጁ መሆኑንን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
የሆነ ሆኖ ኢሳያስ አሁን ባላቸው የፖለቲካ አቋም ከሳቸው ጋር መነገድ የዛለውን ክንዳቸውን ማፈርጠም በመሆኑ ኢህአዴግ እንዳልተዋጠለት የሚጠቁሙት ዲፕሎማቱ “ፖለቲካዊ ይዘቱ ኢኮኖሚያዊ ሽርክናውን ዋጋ ቢስ አድርጎታል” በማለት ስለማይነጣጠሉት ሁለት ተያያዥ ጉዳዮች አስረድተዋል።
ኳታር ሶማሊያ ላይ በነበራት አቋምና የገንዘብ ተሳትፎ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራት የዲፕሎማሲ መስመር ከመቋረጡም በላይ “ለሶማሊያ ጉዳይ አባቱ ነኝ” ይሉ በነበሩት አቶ መለስ ክፉኛ ተዘልዝላ ነበር። ያ ሁሉ አልፎ ዛሬ በኢንቨስትመንት ስም እርቅ አውርዳ የገባቸው ኳታር በጀመረችው ድርድር ኢህአዴግ ያነሳው መሰረታዊ የህልውና ጥያቄ አላላውስ ብሏታል።
ተቀማጭነታቸው ሎንደን የሆነ የጎልጉል ምንጭ እንዳሉት የኢህአዴግ ለመደራደሪያ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው አጀንዳ ኤርትራ ውስጥ የሚንቀሳቀሰውን የትግራይ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደሚት/ ታጣቂ ሃይሎች ተላልፈው እንዲሰጡት ወይም ወደ ትግራይ ድንበር እንዲገፉለት ነው።
ቀደም ሲል የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ህወሃት አካል የነበሩት እነዚህ ክፍሎች “ኤርትራ ውስጥ ታግተው የተቀመጡ”  ሃይሎች ስለመሆናቸውና ከ30 እስከ 40 ሺህ የሚደርስ ወታደር እንዳላቸው ለህወሃት ቅርበት ባላቸው የተለያዩ መገናኛዎች መዘገቡ ይታወሳል። በገለልተኛነታቸው የሚታወቁ መገኛዎችም ቢሆኑ የደሚት ሃይል ከአርበኞች፣ ከቤንሻንጉል፣ ከጋምቤላ፣ ከአማራ፣ ወዘተ ብረት አንጋቢዎች ጋር በጥምረት ለመሥራት መዘጋጀቱንና ይህም ሁኔታ ለህወሃት ስጋት እንደሚሆን አመልከተው ነበር።
ከኢህአዴግ የሚወጡ የምርመራ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ህወሃት ደሚትን እየፈራ ነው። ደሚት “በኤርትራ የታገተ ሃይል ነው” በማለት የድርጅቱን ሃይል ለማጣጣል ቢሞከርም፣ የደሚት ሃይል እንደሚባለው አለመሆኑንን የሚያረጋግጡ መረጃዎች አቶ መለስ በህይወት እያሉ ቀርቦላቸዋል። ከዚያ በኋላ ነበር ደሚት ጥንካሬው እንዳይጎለብት ህወሃቶች መስራት የጀመሩት።
በወቅቱ ከኢህአዴግ ጓዳ ያፈተለኩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያ አሰብን ለመጠቀም የሚያስችላት ድርድር ተጀምሮ ነበር። በስዊድን የሚኖሩ የጎልጉል ምንጭ የሆኑ የኤርትራ ተወላጅ ከዓመት ከስድስት ወር በፊት የአሰብ ወደብ እንዲታደስና ስራ እንዲጀምር ተወስኖ እንደነበርና ስራው ሲጀመር ስራ አቁመው የነበሩ ሰራተኞችና አገልግሎት አቋርጠው የነበሩ ድርጅቶች ስራቸውን እንዲጀምሩ መመሪያ ተሰጥቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። ስራው አሁን በምን ደረጃ እንደሚገኝ ለጊዜው መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
በተለያየ ወቅት አቶ መለስን ከቀድሞው ወዳጃቸው አቶ ኢሳያስ ጋር መልሶ ለማሻረክ ግብጽን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች እንደተሳተፉ የሚገልጹ አሉ። የግብጽን የሸምጋይነት ሚና ጥርጥር ውስጥ በማስገባት አስተያየት የሚሰጡት ዲፕሎማት አሁን ኳታር ከጀመረችው ድርድር ጋርም ግብጽን ያያይዛሉ። ከኳታር ካዝና በሚወጣ ገንዘብ ሻዕቢያ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች እንዲያደራጅ አጥብቃ የምትሰራውና የምትደጉመው ግብጽ አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያና ኤርትራ አስተማማኝ ሰላም አውርደው በሰላም በጉርብትና እንዲኖሩ አትመኝም።
ኳታር ግን በቀድሞው አቋም መቀጠሉ አግባብ እንዳልሆነና በ2008 ከኢትዮጵያ ላይ እጇን እንድታነሳ ተጠይቃ ባለመቀበሏ የተሰበረው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማቃናት መስራት የጀመረችው ከሊቢያው መሪ ጋዳፊ ሞት በኋላ እንደሆነ የሚገልጹ ክፍሎች ኳታር አሁን በጀመረችው “የትልቅ አገር ነኝ” ስሜትና በአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካ ላይ ያላት ሚና መጎልበት ኢትዮጵያን መወዳጀት ብቸኛው አማራጯ እንደሆነ ይናገራሉ።
ሻዕቢያ እየከሰመ ሲሄድ ኢህአዴግ በሌላ በኩል በአፍሪካም ሆነ በዓለም ደረጃ ማደጉ ለንግድና ለፖለቲካ ዝናዋ ኢህአዴግን መወዳጀት አማራጭ የሌለው ጉዳይ የሆነባት ኳታር ሩጫዋ በጊዜ የተኮላሸው ከኢህአዴግ ወገን በተነሳ “የማይታሰብ” በተባለ ጥያቄ ነው። የደሚት የጦር ሃይል ተላልፎ እንዲሰጠው ወይም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲገፋለት የተየቀው ኢህአዴግ ይህ እስካልሆነ ድረስ ከሻዕቢያ ጋር አንድ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ለመነጋገር አለመቻሉ ለኳታር ሽምግልና የመጀመሪያውና ሊመለስ ያልቻለ ፈተና ሆኗል።
ከድሮ ጀምሮ አድብታ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች በመርዳት የምትታወቀው ግብጽ ኢህአዴግ በፈለገው መልኩ ድርድሩ ሊካሄድ እንደማይችል አቋም ይዛ እየሰራች እንደሆነ፣ ለዚህም ሲባል ከአንዳንድ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ለመነጋገርና በሻዕቢያ አማካይነት ድጋፍ ለመስጠት ፍላጎት ማሳየቷን የጎልጉል ምንጭ የሆኑት ዲፕሎማት አስረድተዋል። ዲፕሎማቱ በደፈናው ከመናገር ውጪ ግብጽን ያነጋገረቻቸውን የተቃዋሚ ሃይሎች አልዘረዘሩም።
ኳታር የምጽዋን ወደብ በሊዝ ከመያዟ በተጨማሪ ለአሰብ ወደብ የነዳጅ ማጣሪያ ማደሻና ለወደቡ ስራ ማስቀጠያ ድጋፍ ማድረጓ አይዘነጋም። ያለ ስራ ተቀምጦ የነበረው ወደብ ለስራ እንዲዘጋጅ የታሰበው ለማን ተብሎና ማን እንዲጠቀምበት ታስቦ ነው ሚለው ጉዳይ ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚጠይቅ አብይ ጉዳይ ከሆነ ዓመት ከስድስት ወር አስቆጥሯል። ኢህአዴግ የሚደጉመው የኤርትራ የሽግግር መንግስት አዲስ አበባ መቋቃሙም የሚታወስ ነው።

Total Pageviews

Translate