Pages

Oct 29, 2013

12 women detained across Kingdom for driving


8988939987347357-(1)_0.jpg

Police detained 12 women in various parts of the Kingdom for violating traffic regulations and instructions that prevent women from driving in Saudi Arabia, a local daily reported.
Col. Salman Al-Jemiei, director of the Makkah Traffic Department, confirmed that security patrols arrested three Saudi women on Sunday, all of them in their 40s, for driving cars in different neighborhoods in Makkah.
All the women were accompanied by younger brothers who are not over the age of 15, he said.
The women were immediately detained and referred to authorities as per instructions issued to the Bureau of Investigation and Prosecution.
Security authorities in Jeddah also arrested two women on Sunday in Al-Samer district. Another woman was also arrested on the Jeddah-Makkah Expressway.
According to sources, one of the women arrested was a 50-year-old divorcee. She was arrested while driving her vehicle and was accompanied by her son in Al-Samer neighborhood. The other woman was also a 50-year-old divorced Saudi woman who holds a passport of another country. She was arrested while driving her vehicle, in which she was accompanied by her driver.
The source added that all of them were referred the Al-Samer police station.
Lt. Nawaf Al-Bouq, media spokesman for Jeddah police, said the Ministry of Interior has implemented measures that will control security and take preventative action against security threats.

Oct 27, 2013

መታየት ያለበት ነገር ወይ የኢትዮዽያ መጨረሻ እንዲህ ይሁን"ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር" በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ

"ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ" በሚል፦ መምህር ደረጄ ዘወይንዬ፤ በግብረ ሶዶማዊያኖች፥ ላይ ባደረገው ጥናታዊ ዳሰሳ፣ ከድምጸ ተዋህዶ የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ጋር ባደረገው የቃለ መጠይቅ ቆይታ፥ እንዴት ወደ ግብረ ሶዶማዊነት ሕይወት እንደገቡ፣ በግብረ ሶዶማዊነት ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ ሥራዎቻቸውና እንቅስቃሴዎችቸውን፤ በተመለከተ ሰፋ ያለ፥ በተበራራና ግልፅ በሆኑ ቃላቶች፣ ከግብረ ሶዶማዊያን ሕይወትና ተመክሮ በመነሳት፣ ስለ ግብረ ሰዶማውሪያን እንቅስቃሴ የሚያመለክትና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ፣ ወደዚህ ሕይወት ለገቡት የመውጪያውና የማምለጫው በር፣ ወደዚህ ሕይወት ለመግባት ዳር ዳር ላሉ ደግሞ የደውል ምልክት ነውና። ታዲያ በግብረ ሶዶማዊያን ዙርያ የቀረበው በተጨባጭ ሁናቴ በመረጃና በማሰረጃ ስለሆነ ግንዛቤ እንዳስጨበጠን የታመነ ሃቅ ነው!


"ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር" የሚለውን በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ አዘጋጅና አቅራቢነት በቪዲዮ ወምስል ካቀረበልን ከግብረ ሶዶማዊያን መካክል አንዱና ዋነኛ የሆነው አብይ (ኤሊያና) ስለራሱና ስለ ጓደኞቹ ስል ግብረ ሶዶማዊያን ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ በእውነተኛ ታሪካቸው በተፃፈው መፅሐፍ አማካይነት ስለ ግብረ ሶዶማዊነት ሲናገር እንዲህ ነው የሚለው፦

* "ግብረ ሰዶማዊነት፥ እንደ ማግኔት ነው! አንድ ጊዜ ስቦ ካጣበቀ በኋላ የማይለቅ" ነው ብሎ ይገልፀዋል። (መፅሐፍ፦ የሰዶም ነፍሳት፥ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ)

* በዚህ ቪሲዲም ሆነ መፅሐፍ ላይ አብይ (ኤሊያና) እራሱን ትውልድ ይዳን ግብረ ሶዶማዊነት በኛ ይበቃ በማለት እራሱን አሳልፎ የገለጠ ታላቅ ሠው ነው።

* አብይ (ኤሊያና) ይሁን ሌሎችም በግብረ ሶዶማዊነት ያገኙት አንዳች ጥቅም እንደሌለ ነው የሚስረዱት።

* በግብረ ሶዶማዊነት ያገኘውና ያተረፍ ትርፍ ቢኖር፥ የሥነ-ልቦና ቀውስ፣ የህሊና ወቀሳ፣ በራስ የመተማመን ስሜት ማጣት፣ የፊንጢጣ፣ የኤች ይ ቪ ፖዘቲቭ፣ ለተለያዩ በሽታ መጋለጥ፣ ወደ ተቃራኒ ፆታ መቅረብ አለመቻል፤ እነዚህን ሌሎችንም የመሳሰሉትን ቀውሶችን ለራሳቸው ገንዘብ እንዳደረጉ እንደሆነ ነው የሚገልፁት።

* ትውልድ እስከዳነ ድረስ ሞትም ቢሆን ለእኔ ጥቅሜ ነው!!! (ለሠዎች እራሱን በመግለጡን ምክንያት ለሚመጣበት ማንኛውንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ሲያጠይቅ)


(ከላይ ከዕርሱ፥ እንዳነበባችሁት፣ እንዳያችሁትና እንዳዳመጣችሁ፤ እርስዎ በሃገራች ይህ መኖሩን ያውቁ ነበር? አሁንስ ምን ይላሉ? ስለ ሰዶመ ነፍሳት ምን ተሰማዎት? ምንስ ይላሉ? ከልጆዎ ጋር ስለዚህ አስከፊነት እንዴትስ ሊነጋገሩ አስቧልን? ከወዳጅ፣ ከዘመድ-አዝማድስ ጋር ሊያወሩበት ተዘጋጅተዋልን? ከባልዎ ወይንም ከሚስትዎ፣ አልያም ከፍቅር ጓደኛዎስ ጋር በግልፅ ልትነጋገሩበት ወስናችዋልን? ተወያዩበትና ወስኑ!!!)

Oct 25, 2013

ወያኔ ወደ ሙኒክ መጥቷልና ወገን ተዘጋጅ!!!!!!!!!October 24, 2013


Ethiopia 1997
የወያኔን የዘረፋ ጉዞ ተባብረን እንግታ!!
የወያኔ ቁንጮ የነበረው መለስ ዜናዊ ከሚስቱ ጋር በመሆን ከዘረፉት በላይ ለመዝረፍ በነደፉት የአባይ ግድብ እቅድ ሳቢያ በውጭ ሃገር ካለው ወገናችን ጉልበት በዝባዥ የሆነውን የፈረንጅ ሃገር ስራ ተጋትሮ ያገኛትን ለመመንተፍ የመለስ ውሾች የሆኑት ካድሬ ተብዬዎች ላይ ታች ሲንጠራወዙ ሁለት ዓመት ሆናቸው። ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም እነዚህን ተላላኪ አሽከሮች በየደረሱበት እያሳደዱ ስብሰባ ብለው የጠሩትን ሲያከሽፉ፣ እግሬ አውጭኝ ሲያስሸመጥጡ፣ የእነርሱን ባንዲራ እያነሱ እውነተኛ የኢትዮጵያ ባንዲራ ሲሰቅሉ፣ ወያኔዎቹ የተከራዩትን አራሽ ተቆጣጥረው የራሳቸውን ስብሰባ ሲያካሄዱ፣ ወዘተ ወዘተ ብዙ ገድል አይተናል። ካድሬዎቹ ውሾች ግን ወትሮም የሰውነት ክብር የላቸውምና በደረሰባቸው ተደጋጋሚ ውርደት ተሸማቀው አርፈው አልተቀመጡም።
እየተሽሎኮለኩና እያደቡ ከዳያስፖራው የውጭ ምንዛሪ ለመንጠቅ ዛሬም የሞት ሞታቸውን ያገኙትን ሁሉ ከመቧጠጥ አላረፉም። በዚህም መሰረት በመጪው ኖቬምበር 02/2013 በጀርመን ሙኒክ በአባይ ቦንድ ስም ዩሮ ለመሰብሰብ እየተጠራሩ መሆኑ ተደርሶበታል። በመሆኑም በሃገሩ ጉዳይ የሚንገበገብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከቅርብም ከሩቅም ወደ ሙኒክ እንዲከትና የወያኔን ዘረፋ በተለመደው መልኩ እንዲያከሽፍ የተቃውሞ አስተባባሪ ግብረ-ኃይሉ ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።
በእለቱ በሚደረገው ተቃውሞ የተለመደው የወያኔን የዘረፋ ተግባር ከመግታት በተጨማሪ ትናንት የወያኔ መንግስት በደል እንደፈጸመባቸው አመልክተው የስደት ተገን ያገኙና ዛሬ ከወያኔ ጎን ተሰልፈው ለወገኖቻችን ስቃይና ሞት ተባባሪ የሆኑ ለጥቅምና ለሆዳቸው ያደሩ ባንዳዎችን ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረጽ ስደት ላመለከቱበት ሃገር መንግስት የማጋለጥ ስራ በሰፊው ይሰራል። ሁላችንም በ02/11/2013 ጀርመን ሙኒክ ተገናኝተን የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ።
ወያኔን ለምን እንደምንቃወም እናውቃለን።


*     በስርዓቱ ደባ እየፈራረሰች ስላለችው ሃገራችን
*     በየጊዜው ስለሚጨፈጨፉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን
*     መሬታቸውና እየተነጠቁ ስለሚፈናቀሉ ወገኖቻችን
*     በየእስር ቤቶቹ ስቃይና መከራን እየተቀበሉ ስላሉ ወንድም እህቶቻችን
*     የካድሬ መፈንጫ ስለሆኑት የሃይማኖት ተቋሞቻችን
*     ታሪክ አልባ ስለተደረገው ሃገራዊ ማንነታችን
*     ስለምንናፍቀውና በወያኔ ስለተዘረፈው የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት
*     ስለተረገጠው፣ ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነታችን ወዘተ ወያኔንና በስሙ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ያለማቅማማት እንድንቃወም ያስገድደናል።


ለወያኔ ያደሩ ሆድ አደር ባንዳዎችም ወያኔ ለሚያፈሰው እያንዳንዱ የደም ጠብታ አስተዋጽኦዋቸው መቼም የማይረሳ ስለሆነ ለተጠያቂነታቸውም ጠንክረን እንሰራለን!!
በሙኒክ ለተዘጋጀው የወያኔ ዘረፋ ሁኔታዎችን እያመቻቹ ያሉትን በቅርብ ቀን ፎቶዎቻቸውንና ስማቸውን ለኢትዮጵያውያን ይፋ እናደርጋ

Oct 24, 2013

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አንድን ጳጳስ ከስልጣን አነሳ


ነገ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎ ባደረገው ምክክር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከስልጣን አነሳ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት የሆኑት አባቶች  ያለ ወትሮው የኢህአዴግ መንግስት ሹማምንት በየአካባቢው በቤተክርስቲያኗ ላይ እየፈፀመ ያለውን ጥፋት በይፋ መናገርና መቃወም የጀመሩ ሲሆን፤በተለይ በዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ውሎው የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ላይ ያሉ በርካታ ችግሮችን አንስተው መወያየታቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ጋራ በተያያዘ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው በአዲሱ ፓትርያርክ ዘመን የተሾሙት መጋቢ ሀዲስ ይልማ ከድተው አሜሪካ መግባታቸው እና በከተማው አድባራትና ገዳማት ላይ የሚታየውን ስር የሰደደው ዘረኝነትና ሙስና ለማስወገድ ኃላፊነት የተሰጣቸው የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አዲስ አበባንም ደርበው እንዲሰሩ ቢሰጣቸውም ችግሮቹ ምንም ሊቀረፉ ባለመቻላቸው ከአዲስ አበባው ስልጣን እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ መደበኛ ዓመታዊ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሕዝባዊ እምቢተኝነት በውጭ አገር፤ እንዴት? በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚና ምን ሊሆን ይገባል?

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለገብ ትግል ወያኔ ማስወገድ ይገባል ብሎ የሚያምና ለዚህም የሚታገል ድርጅት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል ሰላማዊም ሰላማዊ ያልሆኑም የትግል ስልቶችን መጠቀም ማለት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚደረጉ ትግሎች ማለት ነው።

ከዚህ አንፃር በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚና ምን ሊሆን ይገባል?

በግንቦት 7 እምነት በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ ሰጭነት ሳይወሰኑ የትግሉ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች መሆን ይኖርባቸዋል። በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔ ጥቅሞችና ተቋማት ላይ በማመጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል።

በዚህ ረገድ የተጀመሩ አበረታች ጥረቶች አሉ፤ ለምሳሌ:
1.ወያኔ ሙስሊሞችን ከክርስቲያኖች ለማጣላት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “እንቢ አንጣላልህም” ያሉት መሆኑ የሚያኮራ ነው። ወያኔ ከጠበቀው በተቃራኒ የሁለቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ መታየቱ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ነው። አብሮነታችንን ማጎልበትና ይህንን በአደባባይ፣ በአዳራሾች፣ በቴሌቪዥን መስኮቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳየት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ውጭ የተጀመረው አገር ቤት መዳረሱ የማይቀር ነው። ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርብናል።
2.ወያኔ በአባይ ግድብ ስም በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በርከት ያለ ገንዘብ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን “ከአባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ” “ከአባይ በፊት ሙስና ይገደብ” እያሉ ወዋጮዎቹን እንቢ ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የታየው ጽናት በጣም አበረታች ነው። የወያኔ ሹማምንት በአባይ ጉዳይ እንኳንስ ገንዘብ ስብሰባም ሊሰበሰቡ አልቻሉም። ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
3.ኢትዮጵያዊያን በስፖርትና በኪነጥበባት መስኮች የሚያደርጓቸው መሰባሰቦች ለትግሉ ትልቅ እገዛ ይሰጣሉ። የኢትዮጵያ ስፓርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) ከወያኔና ከወያኔ ሸሪክ ቱጃር ጋር ያደረገው ትንንቅ የሚያኮራ ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን አገር፣ ነፃነት፣ ክብር ይበልጥብኛል ብለው የቀረቡላቸውን አጓጊ ማባበያዎችን “እንቢ” ብለዋል። ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
4.ባለፈው ዓመት ጋዜጠኛ አበበ ገላው በመለስ ዜናዊ ላይ፤ ዘንድሮ ደግሞ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድና አቶ መስፍን የዘረኛው ወያኔ ግንባር ቀደም አስተባባሪ በሆነው ስብሀት ነጋ ላይ ያሰሙት ተቃውሞ በጣም የሚደገፍና በውጭ አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ባህል ሊሆን ይገባዋል።
5.በስዊድን የሚገኙ የሕግ ባለሙያዎች የጀመሩት እና በኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተሳትፎ እየተካሄደ ያለው የወያኔ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ የማቅረብ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

እነዚህ መልካም ሥራዎች ምሳሌቶች ሲሆኑ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ በላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። አንዳንዱን ለአብነት ያህል ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
1.በአገራችን ውስጥ መሠረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ ከፈለግን ወያኔን ማስደንገጥ፣ ማሸበር፣ ካስፈለገም ማስወገድ የሚችል የአመጽ ኃይል መኖሩ ወሳኝ ነው። እንዲህ ዓይነት የወገን ኃይል ከጀርባው መኖሩ ሲሰማው ነው ሕዝብ ለእንቢተኝነት የሚነሳሳው። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ኃይል ቢቻል መቀላቀል፤ ካልተቻለም በአባላት ምልመላ፣ በፋይናንስ፣ በሎጂስቲክስና ዲፕሎማሲ መደገፍ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ከሁሉ የላቀ የእምቢተኝነት መገለጫ ነው።
2.ትግሉ እየመረረ መሆኑ በመረዳት በርቀት ሆነን ከመብሰክሰክ በትግል ላይ ያሉትን ድርጅቶች መቀላቀል ሌላው አሁኑኑ ልናደርገው የሚገባ ነገር ነው። ድርጅቶች “አይረቡም” ብለን ስላጣጣልናቸው አይጠናከሩም። ድርጅቶችን ማጠናከርና ማዘመን ያለብን እኛው ነው። መሪዎችን ማውጣት ያለብን እኛው ነው። እስካሁን ድርጅቶችን ያልተቀላቀልን ካለን መቀላቀልና ትግሉን ማጧጧፍ ይኖርብናል።
3.በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወያኔን “እንቢ” እንበል። “እንቢ” የማለትን አጋጣሚ ማሳለፍ የለብን። “እንቢ” ማለት የምንችልባቸው አጋጣሚዎች ብዙዎች ናቸው። ለምሳሌ: -

ሀ) ወያኔ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን አዲስ የገንዘብ ማለቢያ ለማድረግ አቅዶ ተነስቷል። ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ቤቶችን በ2 ዓመት ጨርሼ አስረክባለሁ በሚል ማባበያ በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ለመሰብሰብ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይኸንን ነገር አጠንክረን “እንቢ” ማለት ይኖርብናል። “ለኛ ቤት ከመሰጠቱ በፊት፤ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መወደቂያ ያግኙ” ማለት ካልቻልን በራሳችን ማፈር አለብን። የአውሮፓና የአሜሪካ መንግሥታትን አምባገነኖችን በገንዘብ አትደግፉ እያልን እኛ ራሳችን ወያኔን በገንዘብ የምንደግፈው ከሆነማ ከነሱ ብሰን መገኘታችንን እንወቀው።

ለ) ወያኔ በስደተኛ ስም በመካከላችን የሰገሰጋቸውን ካድሬዎችን የማጋለጥ ዘመቻ ማፋፋም አለብን። የወያኔ ደጋፊዎችን በኤርትራ ስደተኞች ስም እንደሚገቡ መረጃዎች አሉ። በደል ደርሶብናል ብለው መንግሥታትን አሳምነው የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ አጠቃን ካሉት አገዛዝ ጋር የሚሠሩ መሆናቸው የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን አጠናቅረን ለየሀገሩ መንግሥታ ማቅረብ እንደ አቢይ ሥራ መያዝ ይኖርብናል።

ሐ) የወያኔ ባለሥልጣናት የሚገዟቸውን ቤቶች፤ የሚያስተዷድሯቸውን ቢዝነሶች እያደንን ማጋለጥ ይኖርብናል።

መ) የወያኔዎች ሹማምንት በአሜሪካና አውሮፓ በነፃነት ሊዘዋወሩ አይገባም። በሄዱት ሁሉ ተቃውሞና ውርደት ሊከተላቸው ይገባል።

ሠ) የወያኔ ቢዝነሶች ላይ ማዕቀብ ማድረግን (ቦይ ኮት) መልመድ አለብን። ጥረቶቻችንን በፈጠራ ከደገፍን ወደ አገር ቤት የምንልከው ገንዘብ የወያኔ የውጭ ምንዛሬ ረሀብ ማስታገሻ የማይሆንበት መንገድ መሻት አለብን።

ረ) ለወያኔ ባለሥልጣኖች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማዋረድ መጀመር አለብን። ስምንተኛ ክፍል እንኳን በወጉ ላልጨረሱ ሰዎች የማስትሬት ዲግሪ እንደሰጡ ማሳወቅ የኛ ኃላፊነት መሆን አለበት።

በግንቦት 7 እምነት ትግሉ በሁሉም ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያዊያን በያለሉበት ቦታ በተደራጀና በተቀናጀ መልክ ወያኔን ፊት ለፊት ከተጋፈጥን የድላችን ቀን እናቀርባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

ጎበዝ ምንድን ነው ነገሩ? – ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለ7 ሰዓታት በመብራት እጦት ሥራ አቁሞ ነበር

 

black_lion_hospital
የኃይለማርያም ደሳለኝ መንግሥት እንዴት ይጠየቃል?
ከመሐመድ አሊ መሀመድ
የገዥው ፓርቲ ልሳን እንደሆነ የሚታወቀው ፋና FM ሬዲዮ በቀትር የዜና እወጃው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከትናንት 10 ሠዓት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ የሆስፒታሉ ታክሚዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አረዳን፡፡ ሬዲዮው የሆስፒታሉ ዲዝል ጄኔሬተርም አገልግሎት እንደማይሰጥ አክሎ በመግለፅ የችግሩን አሳሳቢነት ብቻ ሳይሆን ያለንበትን ሁኔታም ፍንትው አድርጎ አሳየን፡፡ ያለንበትን ሁኔታ በሌላም መንገዶች ስለምናውቀው አሁን አሳሳቢው ጉዳይ በሆስፒታሉ ውስጥ በቀዶ ጥገና ህይወታቸው መትረፍ የሚችል፣ በሰው ሠራሽ መንገድ የሚተነፍሱ ሰዎችና በማሞቂያ ክፍል ውስጥ ያሉ ህፃናት ህይወት ጉዳይ ነው፡፡ በመብራት መቋረጥ ምክንያት ለሚጠፋው ውድ የሰው ህይወት ተጠያቂው ማነው? የሆስፒታሉ አስተዳደር? የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክና መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን? ወይስ ይህ መስሪያ ቤት በሥሩ ያለ ክላስተር ክላስተር አስተባባሪ ሚኒስቴር? መነው ተጠያቂው? በአጠቃላይ የኃይለማርያም ደሳለኝ መንግሥት ተጠያቂ የሚሆን አይመስላችሁም? ግን እንዴት?
- የራድዮ ፋና ዜና እንደወረደ ይኸው፦
የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በኤሌትሪክ መቋረጥ ለ7 ሰዓታት ስራ አቁሞ ነበር
በባሃሩ ይድነቃቸው
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 13፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ለሰባት ሰዓታት መብራት ባለመኖሩ ሆስፒታሉ ተገቢ አገልግሎት መስጠት አቋርጦ ነበር።
የኤሌክትሪክ ሀይሉ በመቋረጡ የቀዶ ጥገናና ጽኑ ህሙማን ታካሚዎች፣ ጠቅላላ ቀዶ ጥገና እና ድንገተኛ ቀዶ ጥገና ህክምና የሚሰጥባቸው ክፍሎች እንዲሁም ያለ ጊዜያቸው የተወለዱና ሙቀት የሚፈልጉ ህጻናት ሙቀት የሚያገኙባቸው ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመው ነበር።
ዛሬ ማለዳ ላይ ዘጋቢያችን በሆስፒታሉ ባደረገው ቅኝት ወቅት የኤሌትሪክ ሃይል በመቋረጡ የተነሳ ሃኪሞቹ ለታካሚዎቹ ኦክስጂን በእጃቸው እየጨመቁ ሲሰጡ አስተውሏል።
የህክምና ባለሙያዎቹ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ በእጃቸው ለነዚህ ከሞት አፋፍ ለደረሱና በተፈጥሮ መተንፈስ ላልቻሉ ህሙማን ዓየር በእጃቸው ሲሰጡ ቆይተዋል።
ያነጋገርናቸው ተረኛ የህክምና ባለሙያዎች እንደገለፁልን ለቀዶ ጥገና ዛሬ ተቀጥረው የነበሩና ያለ ምግብ የቆዩ ህሙማን አገልግሎቱን ማግኘት ስለማይችሉ ለሌላ ጊዜ ቀጠሯቸው እንዲዛወር ተደርጓል።
ይህም ሆስፒታሉ ላይ የስራ መደራረብ ፈጥሮበታል ነው ያሉን ።
ሆስፒታሉ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀበለው ከሁለት ምንጮች ነው።
ነገር ግን የሀይል ማስተላለፊያው ላይ በደረሰ ችግር ምክንያት ኃይል እንዳጣ ተገልጿል።
በማንኛውም ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በሆነ ምክንያት ሊቋረጥ እንደሚችል ቢታወቅም፥ የሆስፒታሉ መጠባበቂያ ጄኔሬተር በማርጀቱ የተነሳ እንደ ሌለ የሚቆጠር ነው ይላሉ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ማህሌት ይገረሙ ።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አሁን ሆስፒታሉ ያለውን ጄኔሬተር ለማደሰ በሂደት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል።
ዶክተር ማህሌት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሶስተኛ የኃይል ምንጭ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ዛሬ ምናልባትም ለ7 ሰዓታት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል ሌላ ጊዜ ለብዙ ሰዓታት ቢቋረጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም።
ይህ እንዳይሆን ግን ሆስፒታሉ ያሉትን አነስተኛ ጄኔሬተሮች ወሳኝ ለሆኑት ክፍሎች የመትከል እቅድ እንዳለውና ከዚህ ባለፈም አዲስ ጄኔሬተር ለመግዛት በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገልፆልናል ።

Oct 22, 2013

ሁሉም ይናገር ሁሉም ይደመጥ!!

ከአንተነህ መርዕድ እምሩ


በድሮ አጠራሩ ሻንቅላ በአሁኑ የጉሙዝ ብሄረሰብ የተማርሁት ትልቅ ነገር አለ። "በትልቆች ጉዳይ ምን ጥልቅ አደረገህ" እየተባልሁ በሚያሸማቅቅ ባህል አድጌ በጉሙዝ ህብረተሰብ ህፃናት ታላላቆቹ ጋር ያለምንም ተፅዕኖ ሲወያዩ መመልከት አስደንግጦኝ ነበር። በጨዋታ መሃል "ግሰም እንግሻ ባኒያ" (እኔንም በተራዬ አድምጡኝ) ካለ አንድ ሰው ልጅንም ቢሆን ፀጥ ብሎ ማዳመጥና ማስጨረስ የተለመደ ክቡር ባህላቸው ነው።

የኔ ሃሳብ ብቻ ይደመጥ፣ አንተን እዚህ ምን አገባህ የሚለው ኢዴሞክራሲያዊ ባህሪ የአምባገነን ገዥዎቻችን ብቻ ሳይሆን የብዙዎቻችን እየሆነ የመጣ ይመስለኛል። አምባገነኖችስ ፀጥ ረጭ አድርጎ ለመግዛት ስለሚያመቻቸው፣ ህብረተሰቡ እውነትን በተረዳ ቁጥር የነሱም አገዛዝ እንዲያከትም ስለሚያደርግ ነው። ለዴሞክራሲ እታገላለሁ የሚለው ወገን የሌሎች ሃሳብ እንዳይደመጥ ጥረት ሲያደርግ ስናይ ግን ዓላማው ከገዥዎቻችን ጨርሶ ያልተለየ መሆኑን ከማረጋገጥ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
 
በቶሮንቶና ባካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 13 ቀን 2013 ዓ ም ለሶስተኛ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ በመሰባሰብ ኢሳትን የሚያጠናክር የገንዘብና ልዩ ልዩ ድጋፍ አድርገዋል። ወያኔ ከአገር አልፎ ውጭም የፈጠረውን ጊዜያዊ ፍርሃት ሰብሮ፣ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የሚደረገውን ትግል ሁሉ ከወያኔ ባልተናነሰ በማደናቀፉ እርኩስ ተግባር የተካኑ የጨለማ ውስጥ ወገኖችም የፈጠሩትን አሉባልታ ከምንም ሳይቆጥር የመጣው ኢትዮጵያዊ ለአገሩ ነፃነት ማንኛውንም መስዋዕት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያረጋገጠበት ነበር።

ቀኑ የጨለመባቸው የወያኔ ደጋፊዎች የተለመደ የማደናቀፍ አንቅስቃሴ ቢያደርጉም ማንነታቸውና አላማቸው ለሁሉም ግልጽ ስለነበር የተሳካላቸው አልሆነም። ከነሱ በባሰ በኋላ በር የተንቀሳቀሱት ግን የህዝብ ወገን መስለው የቆሙ የጨለማ ላይ ፍጡራን ናቸው። የጨለማ ላይ ፍጡራን ያልሁበት ምክንያት አለኝ። እነዚህ ወገኖች እንደሌላው ኢትዮጵያዊ የዴሞክራሲ ታጋይ ወይንም በተፃራሪው እንደቆመው ወያኔ የራሳቸው ህልውና የላቸውም። በጨለማ ውስጥ ብስባሽ እየተመገበ እንደሚያድግ ሸጋታ (በሳይንሱ ፈንገስ) ብርሃን ሳያያቸው ከጨለማ ውስጥ ሆነው ሌሎችን በማደናቀፍና በመጣል የተካኑና የወፈሩ ናቸው።

አደባባይ ወጥተው እውንትን የመጋፈጥ ችሎታው የላቸውም። እነሱ ያልባረኩት፣ እነሱ ያልመሩት እንቅስቃሴ ሁሉ ከንቱ መሆኑን ውስጥ ለውስጥ ከመናገር ውጭ ተጨባጭ ነገር አቅርበው ወይም መርተው ዳር ያደረሱት ነገር የለም። የሰሞኑ እንቅስቃሴያቸው ኢሳትን የተለያየ ስም ለመስጠት ከመዳዳት በተጨማሪ የዕለቱ እንግዳ በሆኑ ሰዎች ስብዕና ዙርያ እየተሽከረከሩ ጥላሸት መቀባት፣ ካልሆነም ወያኔ የፈጠረውን ፍርሃት አጉልቶ በማቅረቡ ተሰማርተው ነበር። ነገር ግን ህዝቡ የብዙ ጊዜ ተመክሮው

ማንነታቸውን አጥርቶ ስላሳየው አልሰማቸውም።ከወትሮው በተለየ ሁኔታም ግልብጥ ብሎ በመምጣት አሳፈራቸው።

ሌላው በጎውና እንግዳው ነገር ኢትዮጵያዊው ዘወትር የሚታማበትን የመዘግየት ባህል ሰብሮ ታዳሚው በሰዓቱ አዳራሹን መሙላቱ ነው። ፕሮግራሙን በስነስርዓትና በብስለት መከታተሉም ከእለቱ እንግዶችና ከፕሮግራሙ ቁምነገር ቀስሞ ለመሄድ ያለውን ጉጉት አመልክቷል። ከቶሮንቶ በተጨማሪ ከኦተዋ፣ ከኪችነር፣ ከዋተርሉ፣ከሚስሳዋጋ፣ ከብራምፕተን እንዲሁም ከአሜሪካ በፋሎ ድረስ የመጡት ኢትዮጵያውያን ሙሉውን ፕሮግራም እስከለሊቱ 2 ኤም ተከታትለዋል።

ኢሳት በየቀኑ የሚያቀርባቸው ዘገባዎች በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም ዙርያ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲረዳ በማድረግ ብዥታን በመግፈፉ የህዝቡ ጥንካሬና የኢትዮጵያ ጠላቶች ማንነት ከምን ጊዜውም በላይ ጥርት ብሎ ወጥቷል። በህዝቡ ገንዘብና ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው ኢሳት የሚገመገመው በየቀኑ አየር ላይ በሚያውላቸው እውነቶች ሲሆን በስራ ላይ ስህተቶች ቢፈጠሩ እንኳ በደጋፊው ህዝብ ምክርና ተግሳጽ ሊያርማቸው ይችላል። ሶስት ዓመት ብዙ አይደለም። የህዝቡ ጠላቶችም ደካማ አይደሉም። ያንን ሁሉ ተቋቁሞ በሶስት ዓመት ውስጥ ያደረገው አስተዋጾ ሲመዘን ግን ለህዝቡ ከሚሰጠው ተስፋ በተጨማሪ ጠላቶቹን እያራደ መሆኑን እያየን ነው።

የዕለቱ የክብር እንግዳ ከሆኑት አንዱ አበበ ገላው ነው። ይህንን ወጣት ጋዜጠኛና አክቲቢስት ለማየት ሆነ ካንደበቱ ለመስማት የሚጓጉ ኢትዮጵያውያን ብዙ ናቸው። አበበ የፖለቲካ ሰው አይደለም። አገሪቱ በዚህ ብትመራ ይሻላታል የሚል ፕሮግራምና ዓላማ ይዘው ከሚንቀስቀሱ የፖለቲካ ሰዎች እሱን የሚለየው እውነቱን ህዝቡ እንዲያውቅ የሚታገል ጋዜጠኛና ፍትህና ርትዕ እንዲኖር የሚታገሉትን ሁሉ

በግንባር ቀደምነት ለመደገፍ የሚንቀሳቀስ አክቲቢስት መሆኑ ነው። የሁሉም ድምፅ ያለምንም ገደብና ተፅዕኖ እንዲሰማ መስዋዕት ለመክፈል የተዘጋጀ ወጣት ነው።

አበበ ከተሰማራበት ሙያው በተጨማሪ ባጋጠመው ተገቢ ቦታና ተገቢ ሰዓት ላይ ተገኝቶ ከሰላሳ ዓመታት በላይ ራሱን በሃሰት ክቦ ማንም አይደፍረኝም ያለውን የመለስን ስብዕና ሰላሳ ሰከንድ በማይሞላ እውነት የሰባበረ ጀግና በመሆኑ ለብዙ ኢትዮጵያውያን አኩሪ ገድል ፈጽሟል። ኢሳትና አበበ ያደረጉት ትልቅ ነገር፤ ታፍኖ የተቀመጠን እውነት ማስተጋባት ነው። የአበበ ሰላሳ ሰከንድ ጩኸትና የኢሳት የሶስት ዓመት እውነት ላይ የተመረኮዘ ዘገባ በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ ቀይረውታል። የአምባገነኖችን ስብዕና ብቻ ሳይሆን እነሱ የፈጠሩትን ፍርሃትም ሰብሯል። ስለሆነም በኢሳት ሆነ በአበበ ላይ የሚያነጣጥሩ ወገኖች ካሉ ህዝቡን በጨለማ ለመግዛት የሚፈልጉ ብቻ ናቸው።

ሁለተኛው የክብር እንግዳ ብርሃኑ ነጋ ነው። ብርሃኑ ነጋን ወያኔ ቢያብጠለጥለው ወይም ሊያጠፋው ቢሞክር አይደንቀኝም። ወያኔ ልቡ ላይ ተወግቶ እንደተያዘ ከጩኸቱ የማይረዳ የለም። በዚያ ዙርያ ግልጽ ስለሆነ ብዙ ማለት ያለብኝ አይመስለኝም።

የገቢ ማሰባሰቡን እንቅስቃሴ ስንጀምር የተለመዱ መሰናክሎች መኖራቸውን አውቀን የተዘጋጀን ቢሆንም በክብር እንግድነት የዶክተር ብርሃኑ ነጋ ስም መታከል ከወያኔ ባሻገር በሌሎች ዘንድ አቧራ ማስጨሱን ስናይ ገረመን። እነዚህ ወገኖች አደባባይ አያውጡት እንጂ የምር ጠላታቸው ወያኔ ሳይሆን ብርሃኑ ነጋና ሌሎች ቅን ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ስራቸው ይመሰክር ጀምሯል። ምክንያቱም

ጉልበታቸውና ጥረታቸው ሲባክን የሚታየው ወያኔን ለመታገል ሳይሆን ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ጠልፎ በመጣል ላይ ነው።

ብርሃኑ ነጋ የሚከተለውን የፖለቲካ አቋም መቶ በመቶ የምቀበለው ባይሆንም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ በጎ ተጽዕኖ በማሳደር ህይወታቸውን ሁሉ ለትግል አሳልፈው ከሰጡት ጥቂት ኢትዮጵያውያን አንዱ በመሆኑ እኮራበታለሁ። ብዙ ከሱ የምንማረው አለና። ገና በወጣትነት በከተማና በገጠር ትግል የጀመረው ብርሃኑ በመጀመርያ ስደቱ ወቅት ስላለፈ ገድል እያወራ ጊዜውን በከንቱ አላሳለፈም። የተሳካለት የአካዳሚ ሰው ሆኖ ወጣ እንጂ። እውቀቱንም እንዳንዳንዶች በዩኒቨርስቲዎች ምኩራብ ገድቦ አልተቀመጠም። አገሩም ተመልሶ ከማስተማር ባሻገር የኢትዮጵያ ኤኮኖሚስቶች ማህበር መስርቶ ኢትዮጵያ ልትከተለው የሚያስፈልጋትን የዕድገት ጎዳና የሚጠቁሙ በርካታ ጠቃሚ የምርምር ውጤቶችን ከባልደረቦቹ ጋር አበርክቷል።

እንደሌሎቹ በደርግ ጊዜ በደረሰው ውድቀት የተፈጠረው የፍርሃት ቆፈን ሳይይዘው እንደገና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ለማስፈን ትግሉን ተቀላቅሎ በቅንጅት የተጫወተውን ሚና እዚህ መዘርዘር ያለብኝ አይመስለኝም። በወያኔ እብሪት ለሁለት ዓመትታት በታሰረበት ወቅትም ቁስሉን እየላሰ እንደሚያስታምም ውሻ በተዘጋበት ክፍል ውስጥ ሆኖ በውድቀቱ እያዘነ ኩርምት ብሎ አላሳለፈም። ከስድት መቶ በላይ ገጽ ያለው "የነፃነት ጎህ ሲቀድ" የሚል መጽሃፍ አበረከተን። በዚህ መጽሃፍ ቅንጅትን፣ ወያኔን፣ ከርቸሌን፣ የኢትዩጵያን ህዝብ እንዲሁም የሚጠብቀንን ፈተናና የወደፊት ተስፋችንን ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል።

በሁለተኛ ስደቱም ቢሆን የ1997 ምርጫ በተከተለው ውድቀት ተሸማቆ አልተቀመጠም። በሙያውም፣ በፖለቲካ ትግሉም የበለጠ ገብቶበታል። አሁን ደግሞ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለባት "ዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ" በሚል የመወያያ ሃሳብ ያካተተ መጽሃፍ እንካችሁ ብሎናል። አቋሙንና ሃሳቡን ባደባባይ ለመናገር የማይፈራ ጀግና በመሆኑ የተሻለ ሃሳብ አለን የሚሉ ወገኖች የተሳሳተ መሆኑን ባደባባይ ወጥቶ ማቅረብ እንጂ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ጭቃ መወርወር የነዚያን ሰዎች ማንነትና ከንቱ አቋም ከማሳወቅ ውጭ የሚፈይደው የለም።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያውያንን ሊያነጋግር ወደቶሮንቶ ብቅ ብሎ ነበር። እንደሌላው ወገኔ እኔም የሚለውን ላዳምጥና ላየውም ወደ አዳራሹ ስደርስ፣ ካዳራሹ ማዶ ጥቂት ሰዎችን መፈክር አስይዞ ብርሃኑ ነጋን የሚያወግዝ ሰው አየሁ። በሁኔታው ባዝንም ከሌሎች ከተደበቁት የዚያ ሰው ድፍረት የተሻለ ሆኖ አገኘሁት። የሚመረጠው ግን ባዳራሹ ተገኝቶ ብርሃኑን በጥያቄ ማፋጠጥና ከሱ የተሻለም ሃሳብ ካለው ለአድማጩ ማቅረብን ነበር። ያ አልሆነም። እነዚህን ዓይነት ሰዎች ክፋት እንጂ የተሻለ ሃሳብ በውስጣቸው ያለ አይመስልም።

ብርሃኑ ካወቅሁት ጀምሮ ራሱን ላደባባይ ያቀረበ ስው ነው። የሚያስበውንና የሚያደርገውን በግልጽ የሚናገር ሰው። ስህተት ካለው ፊት ለፊት ቀርቦ ሃሳቡን በሃሳብ መፋለም እንጂ ከኋላ ሆኖ የፈሪ አሉባልታ፣ የመጠጥ ቤት ቀረርቶ፣ ከፓልቶክ ጀርባ ማንቧረቅ አይጠቅምም። ዴሞክራሲ ባለበት ሃገር ሃያ ሰው ሰብስበው ሃሳባቸውን ማጋራት የተሳናቸው ሰዎች ሌላው ኢትዮጵያዊ የተለያዩ ሃሳቦችን ሊሰማ ሲፈልግ አትሂዱ ማለት ከወያኔ የባሰ የህዝብ ጠላት ያደርጋቸዋል። አንድ ለዴሞክራሲ ቆሜያለሁ የሚል ሰው አይደለም ወገኑ፣ ጠላቱም ሃሳቡን በነጻነት እንዲገልጽ ሊታገልለት ይገባል። ኢሳቶች ስብሃት ነጋን፣ በረከት ስሞንን የመሳሰሉ አፋኝ የወያኔ ባለስልጣናት እንኳ ስልክ እየደወሉ እንዲናገሩ የሚያፋጥጧቸው

እውነት ነው የሚሉትን የራሳቸውን ሃሳብ ከሌላው ጋር በንጽጽር እንዲያቀቡ ነው። እውነቱ ስለሚያጋልጣቸው ብዙ ጊዜ ፈቃደኛ አይሆኑም እንጂ። በግላቸው በያዙት መድረክ የራሳቸውን ሃሳብ ብቻ ህዝቡ እንዲያዳምጣቸው ከማስገደድ የዘለለ ድፍረት የላቸውም። ለራሱ የመናገር ነጻነት ተጎናጽፎ የሌሎችን ነፃነት ለመገደብ ከተንቀሳቀሰ ያ ሰው በውስጡ፣ በሰብዕናው አምባገነንነት አለበት። የበላይነቱን ማረጋገጥ የሚፈልገው በሃሳብና በውቀት የበላይ ሆኖ ሳይሆን የራሱን እምነት በብቸኝነት የሚያስተናግድበት መድረክና አዳማጭ ወገን በመፈለግ ነው።ገና ስልጣን ሳይይዙ የሌሎች ሃሳብ እንዳይደመጥ የተከላከሉ ወገኖች ነገ የስልጣን ባለቤት ሲሆኑ(አያድርገውና) ከወያኔ በባሰ ላለማፈናቸው እርግጠኛ አይደለንም።

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን እንታገላለን የሚሉ ተቃዋሚዎች ሁሉ የብርሃኑ ነጋ ግንቦት 7 ጭምር ከኔ ወድያ ላሳር ነው ከሚል ነባር ተአብዮ(ትዕቢት) ነጻ ሁነው የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድምጽ እንዲሰማ እንደጉምዞች ባህል "እኔንም አድምጡኝ" ለሚል ክብርና ዋጋ መስጠትን ባህል ማድረግ አለባቸው። ለድርጅቶች ሆነ ለግለሰቦች ማንነት መስካሪው የሚያቀርቡት እውነትና ተግባራቸው በህዝብ መመዘንና መዳኘ ሲገባው ራሳቸው ዳኛ፣ ራሳቸው እውነት ለህዝብ መራጭ ሆነው ሊቀርቡ አይገባም።

በቶሮንቶ የኢሳት የድጋፉ ዓላማ ተሳክቶ ጥረቱን በማደናቀፍ በተንቀሳቀሱት ወግኖች ላይ የበለጠ ጽሁፌን ትኩረት ማድረጌ ያለምክንያት አይደለም። እነዚህ ወገኖች የኢትዮጵያውያን ተስፋ ባበበበት ሁሉ እየተገኙ ዋግ እንዲመታው ከህዝቡ ግልጽ ጠላቶች ይበልጥ ስለሚተጉ ነው። ስራቸውን ባደባባይ እያወጡ ለፀሃይ ማብቃት ተገቢ ይመስለኛል። የመለስን በውሸት የተገነባ ስብዕና የሰበረው የሰላሳ ሰከንድ እውነት የነዚህንም ተንኮል ይሰባብረዋል ብዬ አምናለሁ። እውነት ኃያል ነው።

የኢሳት ዋና ዓላማ ለህዝቡ እውነትን ማሳወቅ ነው። እውነተኛ መረጃ የሚያገኝ ህዝብ ሃይል ይኖረዋል። ፈረንጆች እንደሚሉት (ኢምፓወር) ወይም የጉዳዩ ባለቤት ያደርገዋል። አምባገነኖች መረጃን ለማፈን የሚራወጡትም ይህንን በራሱ ጉዳይ ባለቤት መሆኑን ለመንጠቅ ነው።

የሞስሊሞች እንቅስቃሴ፣ የጉራ ፈርዳና የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች፣ የኦጋዴኖች አበሳ፣ የኦሮሞዎች እንግልት፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚዎች ስቃይ፣ የጋምቤላ መፈናቀልና እልቂት፣ የተለያዩ ምሁራን ሃሳብ፣ የብዙ ኢትዮጵያውያን ብሶት፣ የወያኔ ደጋፊዎችም ሃሳብ ሳይቀር በሚገባ በኢሳት ተስተናግዷል። ኢሳት በሚችለው ሃቅም የሁሉንም አስተሳሰብ መድረክ በመስጠት ኢትዮጵያዊ ሁሉ በተጨባጭ ያለውን እውነታ እንዲያውቅ በማድረጉ ህዝቡን የመረጃ ኃይል ሰጥቶታል። ይህንን ሃይል ለመንጠቅ ነው ወያኔም ሆነ ሌሎች የሚፍጨረጨሩት። ያሁኑ መፍጨርጨር ከንቱ ይመስላል። የኢትዮጵያውያን ትኩረት ኢሳትንና ሌሎችንም የሚድያ ተቋማት የሚጎለብቱበትን መንገድ ወደማጠናከሩ ነው የሚሆነው።

የሁሉም የሆነች ኢትዮጵያ በነፃነት ትኑር!

ለተጨማሪ ሃሳብ ጸሃፊውን በamerid2000@gmail .com ማግኘት ይችላሉ።

Total Pageviews

Translate