Pages

Jan 4, 2013

የለንደኗ ማሪያም ቤ/ክን ወዴት እያመራች ነው? – ከታምሩ ገዳ (ጋዜጠኛ)




የለንደኗ ማሪያም ቤ/ክን ወዴት እያመራች ነው?

ከታምሩ ገዳ (ነጻ እና የግል አሰተያየት)

በምድረ እንግሊዝ በለንደን ከተማ የምትገኘው የርእሰ አድባራት ደብር ጽዮን  ቅድስት ማሪያም  ቤተክርስቲያን ፈታኝ የሆኑ ችግሮችን
በመጋፈጥ  ላይ ትገኛለች፡፡
የቤተክርስቲያኒቱን  ስም በግል ስማቸው  ለማዛወር  ጥረት አድርገዋል የተባሉ ሁለት  ምእመናን   ከአባልነት  ታገዱ፡
የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለመስጠት ወደ ቤተክርስቲያኔቱ  ግቢ ያቀኑ  ሁለት አገልጋዮች  ተቃውሞ ገጠማቸው ፡
የጸጥታ ሃይሎች  በቤተክርቲያኒቱ ጉዳይ   ሰሞኑን ሁለት ጊዜ ተጠርተዋል፡፡
ከተመሰረተች  ከሶስት አስርት አመታት በላይ  ያስቆጠረችው  የደብረ ጽዮን  ቅድስት  ማሪያም  ቤተክርስቲያን   በሺዎች ለሚቆጠሩ
በለንደን እና  በአካባቢዋ ለሚገኙ የኢ/ኦ/ተ/ ቤ/ክን አማኞች  አምባ እና  መጠጊያ  በመሆን  ስታገለግል  ቆይታለች ፡፡የድንግል ማሪያምን
አምላጅነት  አምነው  የተማጸኗት  በርካታ  ምእመናን  አያሌ  ተአምራት ሲሰራላቸው  እንደቆዩ  በተቃራኔው  ድግሞ የማሪያምን  ጥቅሟን
የነኩ   ወገኖች   አይወድቁ አወዳደቅ እንደገጠማቸው  እነዚሁ  ማእመናን  የመሰክራሉ፡፡ ይህቺ ለአብዛኛው ስደተኛ  ማህበረሰብ  በሃዘን
ሆነ በደስታ ጊዜያት መሰባሰቢያ እና  መጽናኛ  የሆነች ቅድስት ቤ/ክን  ከአራት አመት  በፊት  በ1,700, 000 የእንግሊዝ  ፓውንድ
(47,600,000 ብር ) የራሷ የሆነ ህንጻ ቤ/ክን  ግዢ ሲፈጸም  ብዙዎች ህልማቸው እውን መሆኑን በማየታቸው የደስታ  እምባቸውን
አምብተዋል፡፡ ሁኔታውንም በጊዜው  በግንባር  ተገኝቼ ለተለያዩ ድህረ ገጾች ዘግቤዋለሁ ::
ከቅርብ ጊዚያት  ወዲህ ግን  ቤክርስቲያኔቱ በምን  መልኩ ትተዳደር?፡ የ ጊዜ ገደቡ ያለፈው የሰበካ ጉባኤው  መቼ ነው  ወርዶ አዲስ
አባላት የሚመረጡት?  ፡ ቤክርስቲያኔቱ ከየትኛው   ቅዱስ  ሲኖዶስ  ጋር ትሁን ?(በአገር ቤት   ካለው ሲኖዶስ ? ወይስ  በውጪ ካለው
ሲኖዶስ?  ወይስ   አሁን ባለችበት በገለልተኛነት አቋሟ ትጽና?...  ወዘተ) የሚሉ ሃሳቦች ዙሪያ  የተካረሩ እሰጣ ገባዎች በሃሳቦቹ ደጋፊዎች
እና በተቃዋሚዎች  መካከል በአውደ ምህረት ላይ: በኪራይ አዳራሾች  እና  በተለያዩ ደህረገጾች  አማካኝነት ሲንሸራሸሩ   ተስተውለዋል፡፡
ወደ ዋና የጽሁፊ  መነሻ  ወደሆነው  ወቅታዊ የቤተክርስቲያኒቱ ችግሮች  ሰመለስ  አንድ ወር ባልሞላ  ጊዜ ውስጥ  ሰለተከሰቱ አንኳር
የቤተክርስቲያኒቱ  ችግሮች  መካከል በሁለቱ ጉዳዮች  ዙሪያ ትንሽ የግሌን አሰተያየት  ልሰንዝር ፡፡
ባለፈው ታህሳስ 13 ቀን 2005 አ/ም (22 ታህሳስ   2012 እኤአ )የቤተክርስቲያኒቱ አሰተዳደር ጉባኤ  በ Ref DTM 568 Ext-Msl
00568/ 12 ያወጣው  ደብዳቤ  እንደሚያመለክተው  “አቶ ግርማ  ተሊላ  እና  አቶ ጥላዬ የሻነው   የተባሉ ምእመናን በመስከረም 2
2012 እ ኤ አ የቤተክርስቲያኒቱን  ስም በመጠቀም ኩባንያ  ካምፓኔ ቁጥር 8200045 የሚል  በአቶ ግርማ  ተሊላ  የመኖሪያ ቤታቸው
አድራሻ  በማውጣት  ላለፉት  ሶስት  ወራት  ያህል  ጉዳዩን  ደብቀው  አንደቆዩ  በመደረሱ ሁለቱ ግለሰቦች   ከቤተክርስቲያኒቱ
አባልነታቸው  ለጊዜው እነደታገዱ” ይፋ አድርጎ ወደፊትም  በህግ እንደሚጠየቁ  የቤ/ክኗ ማህተም እና ፊርማ  ያዘለው  መግለጫ
ያትታል፡፡  ይህ መግለጫ ባለፈው እሁድ እለት (ከሁለት ሳምንት በፊት ) ለምእመናኑ   በአውደ ምህረት ላይ ይፋ በተደረገበት  ወቅት
“የሁለቱ ግለሰቦች  ሃሳባችው መደመጥ አለበት በሚሉ እና የለበትም” በሚሉ ወገኖች መካከል  የተካረረ አስጣ ገባ  እንደነበር ፡
ሁኔታውንም ለማርገብ የጸጥታ ሃይሎች  ጣልቃ እንደገቡ በእለቱ የተገኙ ምእመናኖች ሁኔታውን በሃዘኔታ አጫውተውኛል ፡፡ጉዳዩም
በህግ የተያዘ በመሆኑ  ለጊዜው  ብዙ  አስተያየት መስጠት ባይቻልም  ሁለቱ  “ተወቃሽ ግለሰቦች” በ 19 ታህሳስ  2012 እኤአ  በ ኤ-ሜል
አማካኝነት አሰተላለፉት የተባለ እና ስማቸው  የሰፈረበት  ነገር ግን ፊርማቸውን ያላካተተ   ጸሁፍ አንዳመለከተው ከሆነ
“ቤተክርስቲያኔቱን  በቻሪተእብሌ  ካምፓኒይ   ሊሚትድ ባይ  ጋራንቲ   ለማቋቋም ወራት የፈጀው  እና  እስከአሁን ድረስ  እልባት  
ያላገኘው ድርድር ባለመቋጨቱ  ለቤተክርስቲያኒቱ  ተገቢው  የሆነውን ሰው ሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት  እንዳይወስድባት  በማሰብ
የቤተክርስቲያኒቱን ስም ተጠቅመናል ፡፡ሁኔታዎች  ሲረጋጉ  ያስመዝገብነውን  ድርጅት በነጻ  ለቤተክርስቲያኒቱ  በቻሪተብል ካምፓኒ
ሊሜትድ ባይ ጋራንቲ  አትመዘገብም   ከተባለ በስማችን  ያስመዘገብነው  ድርጅትን   ወዲያውኑ  እንደምንዘጋ  ለሰበካ አሰተዳደር
ለማስተዋወቅ እንወዳለን::” ይላል፡፡  ሁለቱ ግለሰቦች  እስከ አሁን ድርስ ለምን ዝምታን መረጡ? እነርሱን ይህንን ታላቅ ሃላፊነት በግል

እንዲቀበሉ ማን መረጣቸው? ቤተክርስቲያኒቱ   የውሳኔ መግለጫ ካወጣች በሁዋላ  ለምን የማስተባበያ    ደብዳቤ ማውጣት አሰፈለገ
?ለሚሉት እና  መሰል ጥያቄዎች ተጠቃሾቹ ግለሰቦች ሆኑ በእነርሱ ስም የጻፉት ወገኖች ለጊዜው ያሉት ነገር የለም፡፡  የእነዚህን ሁለት
ግለሰቦች ተግባር “እንደግፋለን”  የሚሉ ነገር ግን ሰማቸውን እና ማንነታቸውን በውል ያልገለጹ ወገኖች ያሰራጩት  መልእክት  በበኩሉ
አንደሚያትተው ከሆነ  “ሁለቱ ግለሰቦች የከፈቱት  ድርጅት  ከለንደኗ ጽዮን  ማሪያም   ቤ/ክን  ጋር አይገናኝም”  የሚል መልእክት ያዘለ
ሲሆን  ይሄው ጽሁፍ  ወረደ ብሎ “ሁለቱ  ግለሰቦች  ( አቶ ግርማ እና አቶ ጥላዮ)  ይህንን አርምጃ የወሰዱት  ሌሎች  ግለሰቦች
የቤተክርስቲያኒቱን   ስም  እንዳይጠቀሙ ወይም እንዳይወስዱ  ለማድረግ  አስበው ነው::” የሚል ድጋፍ  አይነት  መልክት
እስተላልፏል፡፡
ሌላኛው   አራሳቸው የቤተክርስቲያኔቱ  ካህናት እና ምእመናን በሚል ሰም  በኤ-ሜል አማካኝነት  ሰሞኑን የተሰራጨ የቅስቀሳ  እና
ማስጠንቀቂያ   መልእክት  የተሰራጨ ሲሆን የዚህ  ወቀሳ ሰለባዎች መካከል  የደብሩ አሰተዳዳሪ  የሆኑት ቆሞስ አባ  ግርማ ከበደ   አንዱ
ሲሆኑ   ይሄው  ጽሁፍ “የማሪያም ቤ/ክን   ከስላሴ ቤ/ክን ጋር ያላትን የአቋም ልዩነት  ወደ ጎን አደርገው  ከስላሴ ቤ/ክን  እና  ከሌሎች
የሟቹ ፓትሪያርክ አባ ጳውሎስ  ደጋፊዎች  ጋር  በመወገን የቤተክርስቲኗን  ህልውና  አሳልፎ የሚሰጥ  ተግባር  እየፈጸሙ ሲሆን  ይህ
ድርጊታቸው   በቤተክርስቲያኒቱ  አባላት  ፈጥኖ ካልተገታ  ቤተክርስቲያናችንን  ከእጃችን ወጥታ ልትቀር አንደምትችል በሚገባ መረዳት
ያሰፈለጋል… ወዘተ፡፡ “  ይላል፡፡  ይሄው  የቅስቀሳ ኢ-ሜል ጽሁፍ አንገብጋቢ ችግር ነው ያለውን ጉዳይ  ሲያብራራ “ በርእሰ  አድባራት
ለንደን ጽዮን  ማሪያም ቤ/ክን  የሚደረገው ቅዳሴ:  ቁርባን:  ክርስትና  ሁሉ የማይሰራ እና   የተወገዘ ነው በማለት  ቤተክርስቲያናችንን
የኮነነ  እና  ስሟን   ያረከሰ   ዲያቆን  ብርሃኑ  የተባለ ሰባኪን ከስላሴ ቤ/ክን  በ16 ታህሳስ   2012 እኤአ   በማምጣት   ዲ\ን ብርሃኑ የአባ
ግርማ ከበደን  አላማን  ሊያሳካ   የሚችል ስብከት  እንዲያደርግ  አባ ግርማ ጥረት  በማደረግ ላይ ናቸው…  ወዘተ፡፡ “የሚል  ነው
በአጭሩ፡፡
እውን አባ ግርማ ከበደ  360 ዲግሪ ተቀየሩ?
  የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ግርማን እስከ ቅርብ ጊዜ እስከ ማቃቸው ድረስ በኢትዮጵያ ያላውን የሰብአዊ መበት  እና
የሃማኖታዊ ጭቆናን በተመለከተ   በርካታ ወገኖች ከአገዛዙ ጋር ያላቸው የጥቅም እና የቅርርቦሽ ትስስር እንዳይቋረጥቧቸው   ዘምታን
በመረጡበት በአሁኑ ወቅት   አባ ግርማ  ግን ድርጊቱን   በአደባባይ በማውገዝ በተለያዩ ሃዝባዊ የተቃውሞ  ሰልፎች እና ስብሰባዎች ላይ
በመገኘት ለጸረ- የሰባዊ መብት ዘመቻው አጋርነታቸውን  በገሃድ  የገለጹ መነኩሴ ናቸው፡፡  የቤተክርስቲያኒቱን  እንቅስቃሴ  በተመለከተ
ደግሞ መረጃን እንኳን ለዜና ሰዎች ለመስጠት  ሙሉ ነጻነት  የሌላቸው   አባት  ለመሆናቸው  ከአንዲም ሁለት ጊዜ ላነጋግራቸው  ሞክሬ  
“ጥያቄህ ማእከላዊነቱን መጠበቅ  ስላለበት በጽሁፍ አቅርብ…ወዘተ”   ያሉኝ  የቅርብ ጊዜ ትዝታዪ ነው ፡፡ ታዲያ  እኛ በቤተክረስቲያኒቱ
አስተዳደራዊ  ጉዳዮች ዙሪያ እንቅስቃሲያቸው  ሆነ አነጋገራቸው  በአመዛኙ ውሱን መሆኑ የሚታወቀው አባ  ግርማን አንዳንድ ወግኖች
በቅርቡ “አቦይ ግርማ “አስከ ማለት  ደረሰው ሲጠሯቸው  ስሰማ  እውን  ቆሞስ አባ ግርማ  መሰረታዊ የአቋም  ለውጥ አሳዩ?   ወይስ
በታላቁ መጽሃፍ ቅዱስ  ውስጥ  በየዋህነት የተመሰለው በጉ ካመረረ… የሚለውን  ቃል ተግባራዊ አደረጉት?  ስል ከእይምሮዩ ጋር ሙግት
ገጥሜ ስንብቻልሁ፡፡ በነገራችን ላይ አባ ግርማ ፍጹም  ሰው ናቸው የሚል  እምነት የለኝም ፡፡አርሳችውም ቢሆኑ  “ፍጹም  ነኝ “የሚሉ
አይመስለኝም፡፡ ታዲያ  በአበዛኛው የለንደን  ሰላማዊ እና ህዝባዊ ስብሰባዎች እና  የተቃውሞ ሰልፎች  ላይ የማይጠፉት አባ ግርማ  ምን
አይነት “የሚያማልል   አለማዊ”   ነገር አገኙ ተብሎ ነው “ቤተክርስቲያኒቱን እያመሷት ናቸው …ወዘተ” የሚሉ በረካታ ወቀሳዎች
ሰሞኑን የሚሰነዘሩባቸው?
ከላይ የቀረበውን  የኤ-ሜል  ጽሁፍ በመንተርሰስ  በምስራቅ ለንደን ከተማ  ለምተገኘው እና በአብዛኛው የካሪቢያን ተወላጆች    እና
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን  ተከታዮች የሆኑ የ ጸራጼዮን ማሪያም ቤ/ክን  በቅርቡ ለገዙት  አዲስ ህንጻ ቤ/ክን የማስፋፊያ  የገቢ ማሰባሰቢያ
ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ለስበከት ወንጌል  አገልግሎት ተጋብዘው ወደ ለንደን የመጡት ዲ/ን መምህር ብርሃኑ   አድማስ እና ዘማሪ ዲ/ን
ምንዳዮ ብርሃኑ  በአባ ግርማ ከበደ የግል ጥሪ ወይስ  በራሳቸው መንገድ ወደ  ማሪያም ቤ/ክን ሄዱ? የሚል ጥያቄ በአይምሮዬ ውስጥ
ተጭሮ ነበር ፡፡ ለጥያቄዬም ያገኘሁት ምላሽ  ሁለቱ አገልጋዮች (ዲ/ን በርሃኑ እና ዲ/ን ዘማሪ  ምንዳዮ ) በለንደን አና በአካባቢዋ የሚገኙ
የኢትዮጵያ  ፡የካሪቤያን  አና የኤርትራ ተወላጆች የሆኑ የኦርቶዶክስ  ተዋህዶ ቤተክረሰቲያኖች  በመዘዋዋር የስብከተ ወንጌል  ትምህርት
እና አገልግሎት  በመስጠት  እና  ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር በህብረት በማዜም መሰንበታቸውን  የተረዱ  በለንደን  ደበረ ጽዮን ማሪያም
ቤተክርስቲን የሚገኙ  ምእመናን   ለቤተክርስቲያኒቱ የካህናት  ጉባኤው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት አንደተጋበዙ እና  የሁለቱንም አገልጋዮች
ወደ ማሪያም ቤ/ክን   መምጣት በመቃወም ረገድ  መሪ ጌታ   አዲስ  አዱኛ   የተባሉ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ   ብቻ ሲቃወሙ የመሪ
ጌታ አዲስ ተቃውሟቸው ተመዘግቦ  የግብዣ ሃሳቡ በድምጽ ብልጫ  ተቀባይነት ማግኘቱን  ለማወቅ ችያለሁ፡፡

ሁለቱ አገለጋዮች (ዲ/ን በርሃኑ እና ዲ/ን ዘማሪ  ምንዳዮ )  በግብዣው  መሰረት ወደ ማሪያም ቤ/ክን ሲያመሩ  የጠበቃቸው የዘንባባ
ዝንጣፊ ሳይሆን ሁለቱ አገልጋዮች “ ወደ ቤ/ክኗ ይገባሉ… !! አይገቡም…!!  “የሚሉ የሁለት ወገኖች የከረረ  አለመግባባት የታየበት እና
ሁኔታውን ለማርገብ እና ለምቃኘት የጸጥታ ሃይሎች  ወደ ቤተክርስቲያኒቱ  የጋበዘ  ሁኔታ  ተስተውሏል፡፡ ለሶስት ቀናት ይካሄዳል
የተባለው የስብከተ ወንጌል ፕሮግራሙ ሁለቱ  ሰባኪያኑ ከነበራቸው የተጣበበ  ፕሮግራም የተነሳ ለሁለት ቀናት  ብቻ  ተካሄዷል፡፡
ዲ/ን ብርሃኑ  አድማስ ማናቸው ?
በዚህ ሰብከተ ወንጌል ላይ የተገኙት ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ  “ሰለ ማሪያም  ቤክርስቲያን  መጥፎ  ስብከት  ሰጥተዋል”  ተብሎ   ወቀሳ
የተሰነዘረባቸው ሲሆን   በመሰረቱ  ዲ/ን ብርሃኑ  በአገር ቤት ምን አይነት ስብከት እንደሚሰጡ ለመታዘብ አጋጣሚውን ባላገኝም በባህር
ማዶ ሰብከታቸው  ግን  ዘወትር  በስብከተ ወንጌል ትምህርታች  ላይ   ጥቁሩን  ጥቁር:  ነጩን  ነጭ : ጎባጣውን ጎባጣ :ቀጥ ያለውን
ሸንቃጣ  ብለው በስሙ   ከሚጠሩ ጥቂት የዘመናችን  ወጣት ሰባኪያን መካከል አንዱ እንደሆኑ  እና   በተለያዩ ጉባኤዎች ላይ
አሰረገጠው ሲናገሩ ከሰማሁዋቸው  መልክቶቻቸው  መካከል  “የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን  የራሷ የሆነ ሰርአት እና  ደንብ ያላት :  የማትከፋፈል
ሃይማኖታዊ ተቋም በመሆኗ  ይህንን  ሰርአቷን  በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሚያፈርሱ ወይም  የሚጻረር መንገድ  ላይ የቆሙ
በየተኛውም  ጎራ የተሰለፉ ፖለቲከኞች ሆኑ የሃይማኖት መሪዎች ነን  የሚሉ ወገኖች  አካሄዳቸውን ሊመረምሩ ይገባል  ፡
ቤተክርስቲያኒቱም  የሰላም እና  የፍቅር መድረክ  እንጂ  የጸብ እና የንትርክ ቦታ  ልናደርጋት  አይገባም ፡ በቤተክርስቲያናችን ህግ እና
ደምብ መሰረት   ጳጳስ ካልባረከው በሰተቀር  አንድ ቄስ ተነሰቶ አዲስ ቤ/ክን  ሊከፍት ወይም የድቁና ማእረግ ለአገልጋዩች ሊሰጥ በፍጹም
አይችልም …ወዘተ “ በማለት   አስረግጠው ሲሰብኩ  አዳምጫለሁ፡፡ ይህ ሰብከታቸው   ሁሉንም ምእምናን ሊያስድስት  የችላል ማለት
ባይቻልም ከስርአተ  ቤ/ክን አንዱ አካል በመሆኑ መቀበል አለመቀበለ  በእያንዳንዱ ምእመን  የሃይማኖታዊ ግንዛቤ  ደረጃ  ላይ ይወደቃል
፡፡ ዛሬ አውነታውን ፍርጥርጥ አደርግው ለምናገር የሞራል ብቃቱ ሆነ ብልሃቱ የጎደላቸው  በረካታ  መሪዎች  ሆኑ ሰባኪያን
በተበራከቱበት አለም ውስጥ ስንገኝ  ከወገንተኝነት የጸዳ ስብከት  እና ስርአተ ቤ/ክን ትምህርት  የሚሰጡ ወገኖችን እንዲያው  በደፈናው
ማሳጣቱ ወይም ለወቀሳ መዳረጉ ልዪነቶችን ከማስፋቱ በተጨማሪ  እንዴ ጎብዝ ምን አይነት ዘመን ላይ ደረሰን? ፡ወዴትስ እያመራን ነው?
የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ  አይቀርም ፡፡ይህ ማለት ግን    የአገር እና  የሃይማኖት ጉዳይ የጥቂት  አዋቂዎች ወይም መሪዎች   ብቻ ስለሆነ ዝም
በሉ ወይም  የሚሰጣችሁን  መምሪያ ሆነ ውግዘት አሜን ብላችሁ ተቀበሉ ማለት  ሳይሆን  ለሁለት ሺህ  አመታት ስርአቷን  እና ትውፊቷን
ጠብቃ የቆየች  ሃይማኖትን   “የእነ አባ እገሌ ደጋፊዋች  እና ተቃዋሚዋች  ወይም  ከዚያ ዝቅ ሲል የዚህ እለት  እና  የዚያኛው እለት
ጉባኤተኞች…  ወዘተ”   በሚሉ  ልዩነቶች በመተብተብ  ወደ ማያባራ  ልዩነት ለመውስድ መሯሯጡ   በየትኛውም  መንገድ ሊደገፍ
የሚገባ አይመስለኝም፡፡ ቢቻል ልዩነቶችን  ለማጥበብ  መሞከር ብልህነት  እና የሚያጸድቅ ስራ ሲሆን ካልሆነ ደግሞ ጊዜ ፈቅዶ ወደ
አንድነት እስኪመጣ ድረስ  እንኳን  ላለመነቋቆር  እናኳን  በጨዋ ደንብ ተወያይቶ መለያየት ሲቻል   ነጋ ጠባ  በነገር ቁርቃሶ
መውነጫጨፉ  ጉዳቱ ለተፋላሚ ወገኖቹ ብቻ ሳይሆን ሃይማኖቱን  ሃይማኖቴ ብሎ   ከፈጣሪው ጋር ለመገናኘት ዘወትር ማልዶ  ወደ
ቤተክርስቲያን የሚሄደውን ህዝበ ክርስቲያንን  ማሳዝን እና ከሃይማኖቱ አንዲርቅ  እንደሚያደርገው  መዘንጋት የለብንም ፡፡
ፖለቲካኛ ገዢዎች በተፈራረቁ ቁጥር  የጨፍልቀህ ወይም የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲያቸውን ለማሳካት ሲሉ ዛሬ ድርሰ  እጃቸውን
ያላነሱባት ቅድስት  ቤተክርስቲያንን ከተደቀነባት የመከፋፈል እና የመለያየት አደጋ  ለምታደግ የህዝበ ክርስቲያኑ  የጋራ ጾም ፡ጸሎት እና
ስርአት ያለው የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት  አግባባነት  ያለው እና  ሊደገፍ የሚገባው መንገድ  ለመሆኑ ጥርጥር የለውም ፡፡ ይህ ሳይሆን
ቀረቶ  “አኛ ካልነው  ሃሳብ ውጪ  ምንም አይነት  ሃሳብ  አይበጀንም  ፡ ከየትኛው ወገን ይሁን ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጡ  ወገኖችን
ዘወትር በጥርጣሬ  አይን ማየቱ … ወዘተ “ ቤተክርስቲያን  ከተመሰረተችበት   ሃዋሪያዊ ተልእኮዎች   መካከል አንዱ የሆነው   ጠላትህን
እንደ ራስህ አድርገህ ውደደው  የሚለውን  ከባድ ትእዛዝን  ለመተግበር ቀረቶ  “የገዛ ወንድምህን  እንደራስህ  ለማየት ሞክር “ በሚል
እንኳን ብንተካው  ከፊታችን  በርካታ የቡድን እና የግል ፈተናዎች   የተደቀኑብን  ይመስለኛል ፡፡   ( tamgeda@gmail.com)

በኢትዮጵያ አንድም የፖለቲካ እስረኛ አለመኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በድፍረት ተናገሩ


ስመራ ለመሄድና ለመደራደር ፈቃደኛ ከሆኑ፥ የመድረክ ተወካዮች እርሳቸው ቢሮ ድረስ በመሄድ እንዲደራደሩ እንዲፈቅዱ ተጠይቀዋል። በኢትዮጵያ ያለውን እስርና እንግልት፣እንዲሁም “የውንጀላ” ቅንብር ከንጹህ ህሊና እንዲመረምሩ በትህትና የልመና ያህል ቀርቦላቸዋል። በምትሰጠዋ አጭር የመናገሪያ ደቂቃ መነጋገሪያ የሚሆኑ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል። የእያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ ሰብአዊነትን የሚፈታተን ጥያቄዎች በማንሳት አቶ ግርማ ሰይፉ ተሳክቶላቸዋል። በትህትና ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች በተለይም ዶ/ር ደብረጽዮንን በተደጋጋሚ ሲስቁ እንድንመለከት ከመጋበዙ በላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ነጻነት የተሞላው መልስ አልተሰጠባቸውም። አቶ ሃይለማርያም ቀሪዋን ሁለት ዓመት ለመጨረስ ውለታ አስቀማጭ በመሰሉበት የፓርላማ ውሏቸው ፖለቲካ ውሸትና ክህደት የሚበዛበት የአይነ ደረቆች ጨዋታ ነው ቢባልም፣ እሳቸው ግን ክህደታቸው ከልክ ያለፈና ፖለቲካዊ ቃና የሌለው ሆኖ ታይቷል።

የአቶ ግርማ አካሄድ በምዕራቡ ዓለም በሚካሄድ የፍርድቤት ችሎት አንዳንድ ጊዜ ጠበቆች መናገር የማይገባቸውን ነገር እያወቁ የሚናገሩትን ሁኔታ ይመስላል፡፡ እማኝ ዳኞችን (ጁሪ) እንዲሰሙት የሚያስፈልግ ነገርግን በፍርድቤቱ ውስጥ ለመናገር የማይፈቀድ ሃሳብ/መረጃ ጠበቆች ሆን ብለው ይለቃሉ፡፡ ይህ ልክ እንደተሰማም ተከላካይ ጠበቃ የተቃውሞ ድምጽ ያሰማል፤ ዳኛውም ንግግሩ እንዲሰረዝ ያዛሉ ሆኖም ከሰሚዎቹ እማኝ ዳኞች ጭንቅላት ውስጥ መሠረዝ ማንም አይችልም፡፡ ለአቶ ግርማ መሠረታዊ ጥያቄዎች አቶ ሃይለማርያም እጅግ መስመር የለቀቀ ምላሽ በመስጠት ጥያቄዎቹን ለመሰረዝ ቢሞክሩም የአቶ ግርማን ጥያቄዎች ከህዝብ ጆሮ መልሰው መውሰድ አይችሉም፤ ከህዝብ ልብ ውስጥ ማጽዳት አይችሉም፤ ከአየሩ ውስጥ መምጠጥ አይችሉም፡፡

በንግግር ማጣፈጥ ሳይሆን ባነሱት ቁም ነገር በተለይም በኢትዮጵያ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም ሲሉ መናገራቸው ከዳር አስከዳር የሚወጡባቸውን ሪፖርቶች፣ አገርና ህዝብ የሚያውቁትን እውነት፣ የፈጠራ ክስ ሰለባ የሆኑ ቤተሰቦች ለፈጠራው ክስ ምስክር የሆኑ፣ያቀነባበሩ፣ እንዲከሱ የሚያዙ፣ የሚፈርዱትና ፍርድ የሚያስፈጽሙት ሁሉም ባንድነት የህዝብ ወገኖች ናቸውና ዛሬ አቶ ሃይለማርያም በሰጡት ደረቅ የክህደት መልስ ስቀውባቸዋል። ቢያንስ “በስህተት የተሰራ ስራ ካለ አጣራለሁ” በሚል አውገርግረው ማለፍ ሲገባቸው፣ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት አፋቸውን ሞልተው መናገራቸው በግል የሚያከብሩዋቸውን ሁሉ አሳዝኗል። የሃዋሪያት ቤተክርስቲያንን ስምና ዲሲፒሊንም ገደል ከተውታል። እምነታቸውንና የእምነት ቤታቸውን አስመልክቶ የተሰጠ አስተያየት ቢኖርም ለጊዜው ከማተም ተቆጥበናል።

ቤተሰቦቻቸው ኦነግ ተብለው የታሰሩባቸው፣ በፖለቲካ እምነታቸው በጨለማ ቤት የሚማቅቁ፣ በፈጠራ ክስ የተወነጀሉ፣ የተደፈሩ፣ ሃብታቸውን የተቀሙ፣ ስለመኖራቸው ባደባባይ እየታወቀና በየቀኑ ቶርቸር (torture) ሲደረጉ ሲቃቸው የሚሰማ ዜጎች ቁጥር በሺህ እንደሚቆጠር ይታወቃል። የፈረንጅ እማኝ እንኳን ካስፈለገ ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች የቅርብ ጊዜ ምስክር ናቸው። ሁለቱ ስዊድናዊያን ጋዜጠኞች የማንም ብሄርና የፖለቲካ ድርጅት አባል ባለመሆናቸው “መረጃና ማስረጃ” ስለሚባለው የክስ ድራማ የተናገሩት ከሚታመነው በላይ ነው። እንግዲህ አቶ ሃይለማርያም ይህንን ሁሉ እያወቁ ነው “ድኜበታለሁ” በሚሉት አምላክ ፊት እንዲህ ያለ ጥያቄ ማንሳት “በእሳት የመጫወት ያህል ነው” ያሉት። አናትመውን ካልነው አስተያየት ውስጥ “… ልጆቻቸውና ባለቤቶቻቸው ሳይቀሩ ይታዘቡዋቸዋል” የሚል ይገኝበታል።

ብቸኛው ተቃዋሚ “አንከራከርበትም ህዝብ ይፍረደው”

በኢትዮጵያ አንድም የፖለቲካ እስረኛ አለመኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በድፍረት ተናገሩ። የመንግስታቸውን ፍርድ ቤቶችና የፍርድ ሂደት እንደማስረጃ ጠቅሰዋል። በተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የመድረክ ተወካይ ለጥያቄያቸው የሚሰጣቸውን መልስ አስቀድመው በመገመት “አንከራከርበትም ህዝብ ይፍረደው” ብለዋል። ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ንግግሩን “ፍጹም ቅጥፈት የተሞላበት” በማለት ሲኮንኑት በእስር የሚማቅቁት ከቁጥር በላይ “ስም፣ ቤተሰብ፣ ልጅ … ያላቸው የምናውቃቸው ሰዎች ናቸው” በማለት ተናግረዋል፡፡

ታህሳስ 23 ቀን 2005 ዓ ም በተካሄደው የ10ኛው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የተገኙት ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከመድረኩ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ የቀረበላቸው ጥያቄ ከወትሮው በተለየ ህሊናንና ውስጣዊ ማንነትን በሚፈታተን መልኩ ነበር።

የፖለቲካ እስረኞችን አስመልክቶ “መቼም የታሰረ ዘመድ የለዎትም” በማለት ነገሩን “በኔ ላይ ቢደርስ” ብለው እንዲያስቡ በመማጸን አቶ ግርማ አንድ ሰው ከማያውቀው ቦታና ድርጅት በግል ሞባይሉ መልዕክት ቢላክለት እንዴት አልቃይዳ ሊባል እንደሚችል፣ ከማያውቀው ድርጅት ወይም ከማያውቀው የአልቃይዳ አባል መልዕክት ቢላክለትና መልስ ሳይለዋወጥ የተገኘ ሰው እንዴት ወንጀለኛ እንደሚባልና እንደሚፈረድበት በመግለጽ ጥያቄ ሰነዘሩ።

ከኦነግ ጋር ግንኙንት አለሽ ተብላ ከ3 ለጆችዋ ተነጥላ 10 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደባት ሌሊሴ ወዳጆ

“አልቃይዳ ሞባይላቸውን እንዴት እንደሚያገኘው ባይገባኝም” በማለት ወገኖቻቸውን ባስፈገጉበት መልሳቸው ቀድመው የተናገሩት አቶ ሃይለማርያም፣ “አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም” በማለት ነበር። የፍታብሔርና የወንጀል ጉዳዮችና፣ በዚሁ አግባብ የተፈረደባቸው ካልሆኑ በስተቀር የፖለቲካ እስረኛ የሚባል እንደሌለ አስረግጠው በመግለጽ የመንግስታቸውን የፍትህ አሠራር ደረታቸውን በመንፋት አሞካሽተዋል።

በፖለቲካ ሽፋን ወንጀል የሚሰሩ፣ የአሸባሪ መሳሪያ የሚሆኑ፣ የፖለቲካ መሪና አባል በማስረጃ መከሰሳቸውን የጠቆሙት አቶ ሃይለማርያም “መረጃ ቢኖረንም ማስረጃ ያላገኘንባቸውና ወደ ህግ ሳይቀርቡ የተቀመጡ አሉ” ሲሉ የ“ቢጫ” ካርድ ማስጠንቀቂያ በመሳብ የህሊናን ነገር ወደ ጎን በመተው በደረቁ በመሸምጠጥ አቶ መለስን በልጠው ታይተዋል። በድጋሚ ጥያቄ የመጠየቅና የመሟገት እድል አለመኖሩ ጠቀማቸው እንጂ “የሚፈለጉትን ሰዎች ስልክ ከቴሌ ወይም ከጓደኞቻቸው በመውሰድ በሶማሊያ አገር በተመዘገበ ስልክ ከሽብር ጋር የተያያዘ መልዕክት ኢህአዴግ እንደላከው እናውቃለን በማለት አቶ ግርማ ቢከራከሩ መልሳቸው ምን ሊሆን ይችል ነበር?” በማለት ስርጭቱን ሲከታተል የነበረ አስተያየት ሰንዝሯል።

ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ይህንን የአቶ ሃይለማርያም ምላሽ በተመለከ በተለይ ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስካይፕ ለተጠየቁት ሲመልሱ “በእውነቱ ይህ ፍጹም ቅጥፈት የተሞላበትና አጸያፊ ነው” በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ “እነዚህ እስረኞች እኮ በቁጥር የሚታወቁ ብቻ ሳይሆኑ ስም፣ ቤተሰብ፣ ልጅ፣ ዘመድ፣ ወዘተ አላቸው፡፡ እናውቃቸዋለን፤ ዓለም ያውቃቸዋል፤ እንግዲህ ጠ/ሚ/ሩ ለእነዚህ ልጆችና ቤተዘመዶች ነው አባታችሁ/እናታችሁ/ዘመዳችሁ ወንጀለኛ አሸባሪ ነው እንጂ የፖለቲካ እስረኛ አይደለም እያሉ ነው ያሉት፤ … ሥነምግባር የጎደለው ንግግር ነው” ብለዋል፡፡

አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም “የጋራ ንቅናቄያችን አቶ ሃይለማርያም ሥልጣን እንደያዙ ደብዳቤ ልከን ነበር፤ በደብዳቤውም ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን የሚገባው በዕርቅ ዙሪያ ላይ መሥራት ሲሆን ይህም የሚጀምረው የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት እንደሆነ ጠቅሰን አጽዕኖት ሰጥተን ጽፈን ነበር” በማለት ድርጅታቸው ከሦስት ወራት በፊት ለጠሚ/ሩ በስም የጻፈውን ደብዳቤ አስታውሰዋል፡፡ ሆኖም እስካሁን ምንም ምላሽ ያላገኙ እንደሆነ የጠቀሱ ሲሆን በደብዳቤው ላይ አቶ ሃይለማርያም በአሁኑ ጊዜ የህወሃት/ኢህአዴግ ሥራአስፈጻሚ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪ በመሆናቸው ለሚደግፏቸው ብቻ ሳይሆን ለሚጠሏቸውም ጭምር በቅንነት ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው መጥቀሳቸውን ተናግረዋል፡፡ “ይህ ዓይነቱ ማሳሰቢያና ጥያቄ ግን እንዲሁ ሲቀጥል አይኖርም፤ እኛም ሆነ ሕዝብ በቃኝ የሚልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፤ ለዘመናት አምባገነኖች ተመሳሳይ ጥሪ ሲቀርብላቸው ቆይተው ሁሉም ንቀው በመጨረሻ የውርደት ጽዋ እንደተጎነጩ ታሪክ ምስክር ነው፤ ህወሃት/ኢህአዴግ ከዚህ የታሪክ ክስተት ፍጹም የተለየ ሊሆን አይችልም” በማለት አቶ ኦባንግ የማስጠንቀቂያ ተግሳጽ ሰጥተዋል፡፡

ስኳሩን እየላሱ በሞቀ ቤታቸው ስለተቀመጡ “የመንግስት ሌቦች” ለተጠየቁት “ለጸረ ሙስና ኮሚሽን መረጃውን በማቅረብ ቢተባበሩን ራሴው ተከታትዬ ለማስፈጸም ቃል እገባለሁ” የሚል መልስ የወረወሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም፣ መንግስታቸው ማስረጃ ባገኘባቸው ላይ ርምጃ እየወሰደ እንደሆነ አመላክተዋል።

አቶ ሃይለማርያም “ለህሊናቸው ይቀርባሉ” በሚል ይመስላል አቶ ግርማ በየቀበሌው ያሉ የኢህአዴግ ካድሬዎች “ኢህአዴግ ከሌለ አገሪቱ አትቀጥልም” በማለት ስለሚያስፈራሩ ህዝብ የፈለገውን የመምረጥ መብት እንዳለው በግልጽ ማረጋገጫና መመሪያ እንዲሰጡላቸው በተማጽኖ ጠይቀው ነበር።

የአቶ ግርማ ጥያቄ እንደተነሳ አቶ መለስ አማራ ክልል ቡግና ወረዳ በሚገኘው አባላቸው ላይ አቶ ልደቱ ላቀረቡት አቤቱታ የሰጡትን ዓይነት ምላሽ የጠበቁ ነበሩ፤ በ2002 ምርጫ አቶ ልደቱ አዲስ አበባን ለቀው በትውልድ ስፍራቸው ቡግና ለመወዳደር ሲቀሰቅሱ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የስም ማጥፋት ተካሂዶባቸው እንደነበር ጠቅሰው ይከሳሉ። አቶ መለስም “… እንዲህ ያለ ወራዳ፣ እንዲህ ያለ ቆሻሻ… እደግመዋለሁ እንዲህ ያለ ወራዳና ቆሻሻ የድርጅታችን አባል ሊሆን አይገባም…” በማለት የስድብ ናዳ አወረዱ። አራዳው ኢቲቪ አቶ ልደቱ ተደስተው ፈገግ ሲሉና አንጀታቸው መራሱን የሚያሳብቀውን ፊታቸውን አሳየ።

አቶ ሃይለማርያም አቶ ግርማ ላቀረቡት ተመሳሳይ ጥያቄ “አባሎቻችን ይህን አይፈጽሙም” በማለት ባጭሩ መልሰዋል። ህዝብ የሚመርጠውን ስለሚያውቅ እንዲህ አይነቱ ጥያቄ የህዝብን የምርጫ ልምድና ንቃተ ህሊና አሳንሶ የማየት ያህል እንደሚቆጠር በመናገር ቀጥተኛውን ጥያቄ የፖለቲካ እርሾ ለማድረግ ሞክረዋል።

በማተሚያ ቤት ችግር የፓርቲያቸው ጋዜጣ ከህትመት መውጣቱን በመጥቀስ አንድ ከፍተኛ ጉዳይ አንስተው ነበር። ፓርቲያቸው ከአባላቱ፣ ከደጋፊውና ከህዝብ ጋር የሚገናኝበትን ብቸኛ ሳምንታዊ ጋዜጣውን በግል ማተሚያ ቤቶች ለማሳተም ሲሞክር በስልክ በሚሰጥ ማስፈራሪያ አታሚዎቹ እየፈሩ እንደማይተባበሯቸው፣ የህትመት ጥያቄያቸውን ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበሉ በመግለጽ በስልክ ማስፈራሪያ ለሚደርሳቸው የግል አታሚዎች በግልጽ ህዝብ እየሰማ ሳይፈሩ ስራቸውን መስራት እንዲችሉ እንዲነግሩላቸው አሁንም የተማጸኑት አቶ ግርማ ያገኙት መልስ ለጠየቁት የሚመጥን አልነበረም።

አቶ ሃይለማርያም “ማተሚያ ቤቶቹ ስራቸውን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በስልክ ማስፈራሪያ ስራቸውን ያቆማሉ ብዬ አላስብም” በማለት ከደመደሙ በኋላ “ማተሚያ ቤቶቹ ስለመፍራታቸው መረጃ የለኝም። እንደጭራቅ ለምን ፈሩን የሚለውን ራሳችሁን ጠይቁ” የሚል ከጥያቄው ጋር ግንኙነት የሌለው ምላሽ ሲሰጡ ተደምጠዋል። አያይዘውም ችግሩ አጋጥሞም ከሆነ የአታሚዎች ማህበር አለ በዚያ በኩል ሊቀርብ እንደሚችል አመላክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህገወጥ ደላሎች ምክንያት ከአገር ስለሚወጡ ዜጎች ሲናገሩ፣ አንድ ሰው የሚከፍለው 50ሺህ ብር መሆኑን በማመልከት ይህን ገንዘብ በመያዝ አገር ውስጥ በመደራጀት ስራ መፍጠር እንደሚቻል ጠቁመዋል። ይህንን ገንዘብ ራሳቸውን ለማጥፋት ከሚያውሉት ራሳቸውን ወደሚጠቅም ስራ እንዲቀይሩት ሰፊ ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል። ይህን ያህል ብር በመክፈል መሰደድን ስለሚመርጡበት የተለየ ነገር ግን የተናገሩት ነገር የለም። የጠየቀም ወገን አልታየም።

አስመራ በመሄድ ለመደራደር ፈቃደኛ እንደሆኑ ለአልጃዚራ ቴሌቪዥን ተናግረው የነበሩት አቶ ሃይለማርያም፣ ኤርትራን በተመለከተ አስመራ ለመሄድ ፈቃደኛ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በራሳቸው አባል ለቀረበላቸው ጥያቄ ቀደም ሲል የነበረው የኢትዮጵያ ፖሊሲ አልተቀየረም፣ ይህ ኢትዮጵያ የያዘችው የሰላም ፖሊሲ ወደፊትም የሚቀጥል ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል። የኤርትራ መንግስት በተለይም የመሪዎቹ ባህሪ የሚታወቅና የአስመራ መንግስት ኢትዮጵያን የማተራመስ ስራውን እንዳላቆመ የተናገሩት አቶ ሃይለማርያም፣ የኤርትራ መንግስት ለሚፈፅማቸው እኩይ ተግባራት የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም አቀፍ ህግጋትን መሰረት በማድረግ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ የተያዘው አቋም እንደማይቀየር አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የአስመራው መንግስት ለድርድርና ለሰላም ራሱን የሚያስገዛ ከሆነ በሩ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል። በሌላም በኩል የሰላምና ፍላጎት እንደሌለው ለዓለም ማስታወቃቸውን ለጠየቋቸው ገልጸዋል።

የምዕራብ አገሮች በስፋት ኢንቨስትመንት ላይ ያልተሰማሩት በመንግሥት ችግር ሳይሆን በራሳቸው የኢኮኖሚ ቀውስ መሆኑንን በማመልክት አስተያየት ሰጡት አቶ ሃይለማርያም፣ ቻይናና ህንድ በኢትዮጵያ ከፍተኛውን የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንደተቆጣጠሩት፣ በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን የቱርክ ባለሃብቶች እየገቡ መሆኑን ገልጸዋል። ቻይናና ህንድ እያስመዘገቡ ያለው እድገት ከፍተኛ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በስፋት ኢንቨስትመንት ላይ መሳተፋቸውን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት 11.4 በመቶ መሆኑንን የዓለም ባንክ ማመኑንና የተጀመሩት ከፍተኛ የልማት ስራዎች በተያዘላቸው የአምስቱ ዓመት እቅድ መሰረት በርብርብ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። በቤቶች ግንባታ “በአፍሪካ በዓመት 100ሺህ ቤቶች የሰራው ኢህአዴግና ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት በቻ በመሆኑ ልንደነቅ ይገባል” ሲሉ በቤቶች ግንባታና ግንባታውን ለመቆጣጠር የተጀመረው አካሄድ በተጀመረው መልኩ ይቀጥላል ብለዋል። መንግሥታቸው ይህንን “ግንባታ” ሲያደርግ በየጊዜው ስለሚያፈርሰው የዜጎች ንብረትና ህይወት ከእርሳቸው የ“ልማትና ግንባታ” ንግግር ጋር የሚሄድ ባለመሆኑ ሳይጠቅሱት አልፈውታል፡፡

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ሀረር ከተማ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፖሊሶች አንድ ህፃን ልጅ ገደሉ

ሀረር ከተማ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ በተፈጠረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ፖሊሶች አንድ ህፃን ልጅ ገደሉ። (እኔ “አንድ ህፃን ገደሉ” የሚለውን ስፅፈው በምን አይነት ሀዘን ውስጥ ሆኜ አንደሆነ የላይናው ይወቀው… የገደሉትስ ምን ተሰምቷቸው ይሆን…!?)
ጎበዝ መንግስታችን ወዴት እየሄደ ነው…? ባለፈው ቤታችን አለ አግባብ ፈረሰ ብለው አቤቱታ ሊያሰሙ የወጡ የአዲሳባ ነዋሪዎች ላይ ፖሊስ ጥቃት ሰንዝሮ ታዘለች ህፃን ገደለ። ሲባል ሰማን አሁን ደግሞ ሌላ መዓት ሰማን… አልገባንም “የቤተሰብ ምጣኔ” ሲባል የተወለደን መግደል መስሏቸው ይሆን እንዴ!? የት ሄደን እንፈንዳ…! ልል ነበር ለካስ በየሄድንበት ሰዎቻችን እያፈነዱን ነው… አንዴም በሳቅ አንዴም በእንባ… አንዴም በችግር አንዴም በዱላ… አረ መላ መላ…!






ESAT Breaking News Muslim Protest Jan 04, 2013

በአንዋር መስጊድና በአዳማ የተቃውሞ ሰልፉ በሰላም ሲጠናቀቅ በሐረር አንድ ሰው ተገደለ

ፎቶ ከፋይል ለግንዛቤ፡ የሙስሊሙ የትግል መነሾና የጥያቄዎቻቸው እንድምታ

(ዘ-ሐበሻ) በአራት ሳምንታት ተደልድሎ እየተዘከረ ያለው ‹‹365 ቀናት ለእምነት ነጻነት›› የመጀመሪያ ሳምንት የጁምዐ ተቃውሞ መርሐ ግብር በበርካታ
የአገሪቱ ከተሞች የኢትዮጵያ ሙስሊምችን አገራዊ አንድነት በጉልህ ባሳየ መልኩ መካሄዱ ተሰማ። በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ በከፍተኛ ጥበቃ ታጅቦ
በተደረገው በዚሁ የተቃውሞ ሰልፍ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአንድነት ድምጹን ጮክ ብሎ አሰምቷል። በአዳማ ከተማም እንዲሁ በርከት ያሉ ሙስሊሞች
ወጥተው ‹‹365 ቀናት ለእምነት ነጻነት›ን የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ያጠናቀቁ ሲሆን መብታቸው እንዲከበርና የታሰሩት መሪዎቻቸው እንዲፈቱ
ጠይቀው የተቃውሞው ሂደት በሰላም ተጠናቋል።
የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ አካሄድ አስደናቂ መሆኑን የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች መንግስት በአንዋር መስጊድም ሆነ በደሴ ሕዝቡን ለማበጣበጥ
ትንኮሳዎችን ቢያደርግም ሰላም ፈላጊው ሕዝብ ግን ሰላምዊውን ጥያቄውን ወደ ግጭት እንዳያመራ በጥንቃቄ ይዞ የዛሬውን ውሎውን ቢያጠናቅቅም፡ በተለይ
በሃረር ከተማ ግን የሙስሙን እንቅስቃሴ ሰላማዊ “ከአሸባሪነት ጋር ለማስመሰል” መንግስት ሆን ብሎ ባስነሳው የጸጥታ ችግር ተፈጥሮ ሰዎች መታሰራቸውንና
አንድ ወደ ወጣትነት ዕድሜ እየደረሰ ያለ ሙስሊም መገደሉን ከሐረር አካባቢ ለዘ-ሐበሻ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በደሴና በወልዲያም ይህ ተቃውሞ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በተለይ በወልድያ አልበሲጥ መስጊድ ለተቃውሞ ከወጡ ሙስሊሞች መካከል ቁጥራቸው በውል
ያልታወቀ ሰዎች መታሰራቸውን ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ችለናል።
                   
ከድምጻችን ይሰማበአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡- በአወሊያ ሙስሊም ሚሽን ት/ት ተማሪዎችየተጀመረውና ወደ ሀገር አቀፍ ደረጃ ያደገው
‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የኃይማኖት ነፃነት ጥያቄ እና
የመንግስት ጣልቃ ገብነትና የመብት ጥሰት ተቃውሞ
እነሆ አንድ ዓመት ሞላው፡፡ በዚህም አመታዊ ጉዞው
ውስጥ ከደርዘን በላይ ሙስሊሞች ህይወታቸውን
መስዋዕት አድርገዋል፤ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ
አባላትን ጨምሮ 29 ሙስሊሞች ታስረዋል፤
በሽብርተኝነትም ተከሰዋል፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ
ንፁሃን ሙስሊሞች በመላ ሀገሪቱ እስር ቤቶች እየማቀቁ
ይገኛሉ፤ ብዙ ምዕመናን አካላቸውን አጥተዋል፤ ብዙ
ሙስሊሞች የሚወዷት ሀገራቸውንና ቤተሰቦቻቸውን
ትተው ተሰደዋል፤ ብዙ የሙስሊም ልማት ድርጅቶች፣
የገንዘብ፣ ኢኮኖሚና የንግድ ተቋማት፣ የየቲሞች
መረዳጃና ማሳደጊያ ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላት
ተዘግተዋል፣ የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል፣ ገንዘባቸው
ተወርሷል፤ የሙስሊም ጋዜጦችና መፅሄቶች ላይመለሱ
ተከርችመዋል፡፡ የእምነት ማዕከላትና መድረሳዎች
ተዘግተዋል፤ መስጂዶች ፈርሰዋል፤ የግዳጅ ሰልፎች ተስተውለዋል፤ ሰላማዊ ትግሉ የተለያዩ ስልቶችን በመቀያየር ሀገሪቱ ሰፍኗል፤ወዘተ…
የዚህ ምልከታ ዓላማም የትግሉን ጉዞ ሂደት ማለትም መነሻ ምክንያቶች፣ ስኬቶች፣ ድክመቶች፣ ስጋቶችና ተግዳሮቶች እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫዎችን
ለመጠቆም ያለመ ነው፡፡
የችግሩ ቁልፍ መነሻ
የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከ1987ቱ የአንዋር መስጅድ ጭፍጨፋ በኋላ ከመጅሊስ እጁን አንስቶ ባያውቅም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን ይፋዊ የሆነ አስገድዶ
የማጥመቅ ዘመቻ አልጀመረም ነበር፡፡ ከሀምሌ ወር 2003 ጀምሮ ግን አዲስ ጥፋት ተጀመረ፡፡ መንግስት በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በኩል አስፈላጊውን
ቅድመ ዝግጅት ካደረገ በኋላ በዚሁ ወር በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ሀረር ካምፓስ ውስጥ በ1980ዎቹ አካባቢ በሊባኖስ ርዕሰ መዲና ቤይሩት እንደተጀመረ
የሚነገርለት አል-አህባሽ የሚባል እምነት በመንግስትና በመጅሊሱ ቅንጅት ከሊባኖስ በመጡ 200 መምህራን በይፋ ማጥመቅ ተጀመረ፡፡ በዚህም 1300
አካባቢ የሚሆኑ የፌደራልና የክልል የመጀሊስ ቢሮዎች አባላት ተካፋይ ሆነዋል፡፡ ከዚህ በኋላም በተከታታይ ቀጥሎ የነበረው የአስገዳጅ ስልጠና በየአካባቢው
መሰጠቱ ሲቀጥል፣ ስልጠናውን የተቃወሙ ሙስሊሞች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡ የአሸባሪነት ስያሜም እየተሰጣቸው ለማሸማቀቅ ተሞክሯል፡፡
እንዲሁም ሁሉም የመስጂድ ኢማሞችና ሙዓዚኖች በአህባሾች አቀንቃኞች እንዲቀየሩ፣ ሁሉም የሙስሊም ትምህርት ቤቶችና ማዕከላት በአህባሽ አስተምህሮ
እንዲቀየሩ ካልሆነም እንዲዘጉ በሚለው የመንግስት ዕቅድ መሰረት ብቸኛው የሙስሊሞች ኮሌጅ የሆነው አወሊያም እጣው ደርሶት በ2004 ታህሳስ 21 ቀን
የኮሌጁ 50 የአርብኛ መምህራን እና የመስጂዱ ኢማምና ምክትላቸውን ጨምሮ በመጅሊሱ ቀጭን ትዕዛዝ በአንድ ሌሊት እንዲባረሩ ተደረገ፤ በዚህ ምክንያት
ኮሌጆም ተዘጋ፡፡ ይህ ያስቆጣቸው የአወሊያ ኮሌጅና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ታህሳስ 24 ቀን ‹‹ኢማሙና መምህራኖች ይመለሱልን፣ ኮሌጁም
ይከፈት!›› በማለት የተቀውሞ ድምጽ ማሰማት ጀመሩ፡፡ ይህ ችግር በቀላሉ ሳይፈታ ቀርቶ ወደ ሀገራዊ አጀንዳነት በማደጉ ‹‹የመጅሊስ አመራሮች
ይውረዱ!›› የሚል ጥያቄ ተነሳ፡፡ የችግሩ ቁልፍ መነሻ የኃይማኖትና እምነት ነፃነት በሚፃረር፣ የኢትዮጲያን ህገ-መንግስታዊ አንቀፅ 27 እንዲሁም የዓለማቀፍ
የሰብዓዊ መብቶችን በሚጥስ ሁኔታ መንግስት በኃይማኖት ጉዳዩች ጣልቃ መግባቱና አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ መጀመሩ ነበር፡፡ ነውም፡፡

የሰላማዊ ትግሉ ህጋዊ አካሄድ
ይህ የተማሪዎች ጥያቄ ወደ ሀገራዊ አጀንዳነት ከተቀየረ በኋላ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የተቃውሞ ድምፃቸውን ማሰማት ሲጀምሮ ህገ-መንግስቱ
በሚፈቅደው መሰረት ከሁለት ሳምንታት በኋላ ጥር 11 ቀን ወኪሎችን በመምረጥ 17 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተዋቀረ፡፡ ይህ ኮሚቴም ዘርፈ-ብዙ ከሆኑት ከህዝቡ
ከተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ውስጥ ሶስት ጥያቄዎችን ብቻ በመለየት ለመንግስት ለማቅረብ ተሰናዳ፡፡ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ከህዝብ ከቀረቡ ጥያቄዎች እነዚህ
ሶስቱ ሲመረጡ በርካታ ነጥቦችን ከግንዛቤ በማስገባት ነበር፡፡ በቀጥታ ተቃውሞው እንዲነሳ ምክንያት የሆኑት ላይ ብቻ በማተኮር፣ ከእምነት ነፃነትና
የህገመንግስታዊ መርህን ሙሉ ድጋፍ የሚያገኙትን፣ በሃይማኖታችንና በመንፈሳዊ ተቋማችን ብቻ የታጠሩትን፣ መንግስት ከመመለስ ውጭ ምክንያት ሊያቀርብ
እድል የማያሰጡትን፣ በፅንሰ ሃሳብና አሻሚ በሆኑ ነገሮች ላይ የተገነቡ ሳይሆን ግልፅና በተግባር መመለሳቸው ሊረጋግጥ የሚችሉ፣ ቀላሎቹን፣ አፋጣኝ መፍትሄ
የሚሹትን፣ ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያሳምኑትን፣ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ባህሪ ያላቸውን፣ 3 ጥያቄዎችን በመለየት ነበር የመንግስት ባለስልጣናትን ለማስረዳትና
መፍትሄ ለማፈላለግ ስራውን የጀመረው፡፡
ሦስቱ መሰረታዊ የትግሉ ጥያቄዎችም፡-
1. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አመራሮች በሙሉ የሕዝበ ሙስሊሙ ውክልና የሌላቸው በመሆኑ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ በነጻነት
በሚመረጡ አመራሮች ይተኩልን
2. በመጅሊሱ አማካኝነት በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ በግድ እየተጫነ ያለው የአሕባሽ የማጥመቅ ዘመቻ ይቁምልን እና
3. አወሊያ የህዝበ ሙስሊሙ ነጻ ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል መጅሊስ እጁን ከአወሊያ ያንሳ የሚሉ ነበሩ፡፡
በዚህም መሰረት የሰላማዊ ትግሉ ዓላማና ግብ ከመንግስትና መጅሊስ እጅ ነፃ የሆነና ህትሃዊ ምርጫ ይካሄድ፤ እንዲሁም ሙስሊሙ ተቋማት በራሱ
በሙስሊሙ ፍላጎት ይመሩ የሚል ማለትም የኃይማኖታዊ ተቋማትን የማደራጀት፣ ኃይማኖታዊ የመምረጥና የመመረጥ መብቶች መከበር ላይ የሚያተኩር
ነበር፡፡ ሌላኛው ደግሞ አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻው ይቁም ሲል የኃይማኖት፣ የእምነትና የአስተሳሰብ መብትና ነፃነት ይከበር፣ መንግስት እጅህን አንሳልን
የሚል ትልቅ እንድምታ ያለው ነበር፡፡ የትግሉም ውጤትና ስኬት የሚለካው ከዚሁ ዓላማና ግብ አንፃር ነው፡፡
ኮሚቴውም እነዚህን ጥያቄዎች ይዞ ከመንግስት አካል ከሆነው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋር ባደረገው ከሶስት ያላነሱ ውይይቶች መሰረት የካቲት 26
መንግስት ‹‹መልሴ ነው›› ያለውን የመጨረሻ አቋሙን እንደሚከተለው አሳወቀ፡-
1. የመጅሊስ ምርጫ በቅርቡ ይካሄዳል፤ እንዴት በማንና በምን መስፈርት የሚሉት ግን ዝግ ነበሩ
2. አወሊያና መሰል የሙስሊሙ ማዕከላት በመጅሊሱ በሚመረጥ ቦርድ ይመራሉ እና
3. የአህባሽ ስልጠናም ይቀጥላል የሚሉ ነበሩ፡፡
ምንም እንኳን ጥያቄዎቹ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት፣ በዓለማቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች በግልፅና በማያሻማ መልኩ የተቀመጡ ቢሆንም የመንግስት ምላሽ
ግን ሰብዓዊነትን የሚጋፋ፣ የኃይማኖት ነፃነት መብትን በእጅጉ የሚጥስና ኢትዮጲያ የፈረመቻቸውን ዓለማቀፋዊ ስምምነቶች በሙሉ ቅርቃር ውስጥ የሚከት
ነበር፡፡ ኮሚቴውም ሰላማዊነትንና ህጋዊነትን ብቻ በመላበስ የፌደራል ጉዳዮች የሰጠው ምላሽ ትክክለኛና ጥያቄዎቹን በደንብ ያላገናዘበ መሆኑን በፅሁፍ ጭምር
በማሳወቅ ወደ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ድረስ በደብዳቤ በማስረዳት እንዲሁም ለውይይት በመጋበዝ ብዙ የተጓዘ ቢሆንም
ሳይሳካና ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡
ከየካቲት 26ቱ ምላሽ በኋላ መንግስት በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን ሰላማዊ ትግሉንና ጥያቄውን በአክራሪነትና በአሸባሪነት በመፈረጅ የማጠልሸት
ፕሮፓጋንዳውን በይበልጥ ተያያዘው፡፡ ኮሚቴውም ለወቅታዊ ክስተቶች ማብራሪያዎችን እየሰጠ እንዲሁም በየክልሉ የትግሉንና የጥያቄዎቹን ምንነት በህዝብ
ዘንድ ለማስረፅ እንዲሁም የህዝብን አንድነትና ሰላማዊ አካሄድ ብቻ ለማስረፅ ብዙ ተጉዟል፡፡ መንግስት የመጅሊስ አመራሮችን ለመቀየር ቢፈልግም
ምርጫወውን ግን ለራሱ ቁጥጥር በሚያመቸው መልኩ በመንግስት አስተዳደራዊ ቦታዎች ማለትም በቀበሌ እንዲሆን በማድረጉ ምክንያት ህዝበ-ሙስሊሙ
‹‹ምርጫችን በመስጅዳችን›› እያለ ቢቃወምም በእምቢተኝነት ህዝብ ያልተሳተፈበት የምርጫ ድራማ በመስከረም ወር አድርጎ በአዲስ የመንግስት ካድሬዎች
ተክቷል፡፡ እስካሁንም በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን መስጅዶችና መድረሳዎች በመጅሊሱ ቁጥጥር ስር ለማስገባት ሩጫውን እንደቀጠለ ነው፡፡ የተቃወሙትን እስር
ቤቶች በማጎር ላይ ይገኛል፡፡
ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላነሳቸው ጥያቄዎች ከ 365 ቀን በኋላ ዛሬም ፍትሓዊ መልስ ይጠብቃል፡፡ መስማት የነበረባቸው አካላት ጆሮ ዳባ ልበስ ቢሉም
ለመስማት እስኪገደዱና መልስ እሰከሚያገኝ ድረስ ያለ መሰልቸት ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፡፡ ድካሙም ከንቱ እንደማይቀር በአላህ ላይ ሙሉ እምነት ጥሎ
ወደፊት ይጓዛል፡፡ መሰረታዊ መብቱ እየተጣሰ እንዳላየ ሆኖ ዝም የሚልበት ጊዜ በአላህ ፈቃድ ላይመለስ ተሸኝቷል፡፡

ዳዉሮ ህዝብ አመጽ እንደገና ሊያገረሽ ነው

“እውነትና ፍትህ በሌለበት ሀገር ኑር አትበሉኝ!”

ረ/ሳጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ
የዳውሮ ዞን ፖሊስ ባልደረባ
(ዋካ ከስዊድን)
መግቢያ
የዳውሮ ሕዝብ የደረሰበትን የመልካም አስተዳደር እጦት፤ በአቅራቢያው ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት አለመቻል፤ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ሕዝቡ ለሚያቀርበው የመብትA memorial service for Yenesew Gebre የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ያለመስጠት፤  በየወቅቱ በሚፈራረቁ የሥልጣን ተረኛ በሆኑት የህወሐት/ ደኢህዴን ካድሬዎች የግል ፍላጎትና ውሳኔ ብቻ የወረዳ ማዕከል እየተወሰነ ከመንደር ወደ መንደር በመዘዋወሩ የተነሳ ማሕበራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት አለመቻል አበሳጭቶት ወደ አምጽ ማምራቱን በመዘርዘር ከዚህ በፊት በሦስት ክፍሎች ያዘጋጀሁትን ጽሑፍ ማስነበቤ ይታወሳል።
አሁንም በሕወሃት/ ደህዴን ካድሬዎች ተንኳሽነት የተነሳ የሕዝቡ ቁጣ እንደገና እያገረሸ መጥቷል። እስሩ ማንገላታቱ ከሥራ ማባረሩ ተጀምሯል። የሕዝቡ ጥያቄ የሚታወቅና ግልጽ ነው። ከሚዲያና ከካድሬዎች የሚነገረውን የሀገሪቱን  የኢኮኖሚ የልማትና እድገት ፕሮፓጋንዳ ባሻገር ድርሻውን ማግኘት ቀርቶ በአይኑ ለማየት አለመቻል፤ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለማግኘት ያለመቻላቸውና የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየናረ መምጣት፤ አንድ አርሶ አደር ወደ ወረዳ ማዕከል ለመድረስ ከአንድ ቀን በላይ ለሚፈጅ ጊዜ በእግሩ መጓዝ የግድ እየሆነበት ስለመጣና ይህም ስላሰለቸው፤ ያላግባብ እንዲርቀው የተደረገው የወረዳ ማዕከል በሚፈልገውና ወደ ሚቀርበው ሥፍራ እንዲዛወርለት ያቀረበው ተደጋጋሚ አቤቱታ ሰሚ ሊያገኝ አለመቻሉ፤ ጥያቄውን ለመንግሥት በየደረጃው  በተደጋጋሚ አቅርቦ መፍትሄ አለማግኘቱ ሕዝቡን በጣም አሳዝታል። በዚህም የተነሳ የዳውሮ ዋካን ሕዝብ ጥያቄ ያነገበው ጀግናው ሰማዕት መምህር የኔሰው ገብሬ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና የመልካም አስተዳደር እጦት በመቃወምና ድርጊቱን በማውገዝ ራሱን በእሳት በማቃጠል መስዋዕትነት መክፈሉ ይታወቃል። ይህም ሆኖ የዳውሮ ሕዝብ በደል መፍትሄ እስካሁን ሊያገግኝ አልቻለም።
የተቃውሞው እንደገና መቀስቀስ ምክንያት
ህወሐት/ ደኢህዴን በደቡብ ክልል በአንዳንድ ዞኖች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚነሳበትን የህዝብ ተቃውሞ መቀነስ ስለሚችልበት ሁኔታ ተወያይቶ ነበር። በዚህ ውይይት ላይ በዋናነት የተነሳውና የታመነበት ነጥብ የተጨማሪ ወረዳ ጥያቄና የወረዳ ማዕከል ጉዳይ ሆኖ በውይይቱ ጎልቶ ወጣ። በመቀጠልም እንዴት አድርገው የህዝቡን ቁጣ ማርገብ እንደሚቻልና ምንም ተጨማሪ ወረዳ ሳይሰጥ ሕዝቡን የማሳመን ሥራ መሥራት እንደሚገባ ታምኖበት ለአፈጻጸም ለሚመለከተው የፖለቲካ ኃላፊዎች እንዲያስፈጽሙት ስልጠና ተሰጥቶ ወደ ሕዝቡ እንዲወርዱ ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ በአንክሮ የተነሳው የቀድሞው ሰሜን ኦሞ ዞን ሥር የነበሩት ዞኖች መካከል የጋሞጎፋና የዳውሮ ዞኖች ህዝብ ጉዳይ ነበር። በዚህ መነሻነት የዞን አመራሮች ሕዝባቸውን የማሳመን ሥራ እንዲሰሩ የሚያስገድድ መመሪያ ለዞኑ የፖለቲካ አመራርች ይወርዳል። አመራሮቸ እንዲያስፈጽሙ ታዘዙ። በዚህ መነሻነት ነው እንግዲህ   በእስርና በእንግልቱ ሳቢያ ዝም ያለና ጊዜ የሚጠብቅ፤ ግን ውስጥ ውስጡን እየፋመና እየጋመ የነበረን የህዝብ ብሶት እንደገና ቀሰቀሱት።
የዳውሮ ህዝብ ያቀረበው የፍትና የመብት ጥያቄ በመሆኑ ከዛሬ ነገ ይመለስልኛል ብሎ በሚጠበቅበት ወቅት  መንግሥትና ገዢው ፓርቲ ጥያቄውን ለማድበስበስና ከሕዝቡ የተሻለ ለሕዝቡ አሳቢ በመምሰል ወረዳ ምን ያደርግላችኋል? ልማት ነው የሚያስፈልጋችሁ! ከልማትና ከወረዳ ምረጡ! ተጨማሪ ወረዳ አይጠቅማችሁም! የወረዳ ርእሰ ከተማ ቢርቅባችሁም ራቀብን አትበሉ! ዝም በሉ! እንዲያውም ፍትህ ፍለጋ ስንቅ ተሸክማችሁ በእግራችሁ ረጅም ሰዓት በመጓዛችሁደስ ደስ ሊላችሁ ይገባል! የሚል ስሜት ያዘላ አድራቂ ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን ለማወናበድ እየተሞከረ ይገኛል። የመንግሥት ሠራተኛው የህዝብ ልጅ እንዳልሆነና የሕዝብ በደልን የማይረዳ በማስመሰል ከሕዝቡ ሓሳብ በተቃራኒው ከአመራሮች ጎን እንዲቆም ለማድረግ በየወረዳው ካድሬ ተመድቦ ተግቶ እንዲሰራ ይደረጋል።
ካድሬዎች በሕዝቡ መካከል እጅግ የሚገርምና ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ጀመሩ። የማረቃ ዋካ ወረዳ ዋና ከተማ ዋካ ይሁንልን የሚልን የህዝብ ጥያቄ ለማፈን የማይቻል መሆኑ ግልጽ ነው። በማሰር በማፈን በሐሰት በመክሰስና በመወንጀል በማስፈራራት ጥያቄውን ምላሽ እንዳያገኝ ማድረግ አምና ተችሏል። ይህ ማለት ግን ሕዝቡ ጥያቄውን ትቶታል ወይም መልስ አግኝቷል ማለት አይደለም። የወረዳው ማዕከል አያማክለንም የሚለውን የሕዝብ ጥያቄ ለማፈንና ምላሽ ላለመስጠት ሲባል ለዘመናት አብሮ የኖረንና ቤተሰብ የሆነውን የማሪና አካባቢውን ሕዝብ በመቀስቀስና በዋካ ከተማ ሕዝብ ላይ ለማነሳሳት መቀስቀስ ቀጠሉ።
የማረቃ ወረዳ ሕዝብ ከቆዳ ስፋቱና ከሕዝብ ቁጥር አንጻር እንዲሁም ጂኦግራፊያዊ አቀማመጡ የተነሳ ሁለት ወረዳ ሊሆን ይገባል የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢነት ያለው ነው። በዚህ የተነሳ ዋካና ማሪ ሁለት የተለያዩ ወረዳዎች መሆን ይገባቸዋል የሚል ሐሳብ ይዞ መነሳት ነው የተጨማሪ ወረዳ ጥያቄ ማለት። ነገር ግን ቀድሞ የነበረን ወረዳ የወረዳው ማዕከል ይርቀናል አያማክለንም የሚልን ጥያቄ ለማፈን ሌላ ተገቢ ያልሆነ ቅስቀሳ ሕዝብ ውስጥ መርጨት ተጀመረ።
በምንም ዓይነት ሁኔታየኢትዮጵያ ዋና ከተማ ኬንያ ጠረፍ የሚገኝ ቀበሌ ሊሆን አይችልም። የትግራይ ክልል ዋና ከተማ ደሴ አልተደረገም። ዳውሮ ውስጥ ብትመለከቱ ግን ሁኔታው የተለየ ነው። የሎማዲሳ ወረዳ  ዋና ከተማ ገሳ ጨሬ ይባላል። ይህ አዲስ የተቆረቆረ ከተማ ያለው በአጎራባቹ የጌና ቦሳ ወረዳ ውስጥ ነው። የሎማ ዲሳ ወረዳ ሕዝብ የጠየቀው የወረዳችን ዋና ከተማ ከአጎራባች ወረዳ ወጥቶ ቢያንስ እንደቀድሞው ወደ ወረዳችን መሐል አካባቢ ተመልሶ በሚያማክለን ሥፍራ ይደረግልን ነው። ይህንን ጥያቄ አይቶና ሰምቶ መፍትሔ የሚሰጥ አመራር የለም።
በመንግሥት ውሳኔ የተጣመሩ ወረዳዎች ዳግም በመንግሥት ውሳኔ ተለያይተው ቀድሞ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ሲደረግ የወረዳው ማዕከል ጉዳይ ወደ ሕዝቡ ወርዶ ውይይት ተደርጎበት ሊወሰን ሲገባ ይህ ሳይሆን ቀርቷል። ታዲያ ይሄ ስህተት የማነው? የሕዝቡ ነው ወይስ የአመራሩ ነው? ከዲሳ አካባቢ ለምሳሌ ቃኢ ጌሬራና ከዚያ ርቆ የሚኖር አንድ አርሶ አደር የወረዳውን አስተዳደር ፍለጋ አንድ ቀንና ከዚያ በላይ መጓዝ አለበት የሚል የወረዳና የዞን አመራር እውነት ለህዝቡ የቆመ ነው? አመራሩ ለምንድነው የሚመራውን ሕዝብ  የማይሰማው? እውነት አሁን የዲሳ አካባቢ ህዝብ ወደ ገሳጨሬ እንዲመላለስ ተገቢ አይደለም ያለ የመንግሥት ሠራተኛ ሊዋከብ ሊታሰርና ከሥራ ሊታገድ ተገቢ ነው?
የዳውሮ ህዝብ የወረዳ ማዕከል ለአቤቱታ ሲሄድ እንደ ዘመነ ምንሊክ ከቤቱ ስንቅ ቋጥሮ በእግሩ ከአንድ ቀን በላይ በመጓዝ ላይ ይገኛል። በሎማ ወረዳ ዲሳ አካባቢ አገልግሎት ማለት ጋሞ ጎፋ ዞን አዋሳኝ አካባቢየሚገኝ ቀበሌ ማለት ነው። ከዚያ ተነስቶ አንድ አርሶ አደር የወረዳው ማዕከል ወደተሰደደበት ሌላ ወረዳ ማለትም ጌና ቦሳ ወረዳ ከአንድ ቀን በላይ መጓዝ ግድ ይለዋል። ከዚያ በኋላ ተጨማሪ የመኪና ጉዞ አድርጎ ነው ገሳ ጨሬ የሚደርሰው። ይህ ነው እንግዲህ እውነቱ። ልዩነቱ ጥቂት የእግር ጉዞ ሰዓታት ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ችግሩ በቶጫም ሆነ በማረቃ ወረዳዎች ተመሳሳይ ነው።
የሎማን ወረዳ ምሳሌ አነሳሁ እንጂ የቶጫ ወረዳም ቢሆን ተመሳሳይ ነው። ተርጫ አጠገብ ዋራ አካባቢ የሚኖርን አንድ አርሶ አደር ከጪ ድረስ ተጉዞ ፍትህ እንዲያገኝ ማስገደድ ምን ይባላል? ከጪ ኢሰራ ወረዳ አጠገብ ነው። ቀደም ሲል ኢሰራና ቶጫ ወረዳዎች እንዲጣመሩ በተደረገ ጊዜ ሁለቱን ወረዳዎች እንዲያማክል በሚል የተመሰረተ ከተማ ነው። ወረዳዎች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ሲወሰን የኢሰራ ወረዳ ከተማ ወደ ቀድሞው ማዕከል ሲመለስ ቶጫ ወረዳ ግን ቀደም ሲል ወደ ነበረበት ሥፍራ ሳይመለስ እዚያው እንዲቀጥል ተደረገ።
ይህ የሕዝብ ጥያቄ ሕብረተሰቡን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ያስተባበረና እያጠናከረው የመጣ ሲሆን በገዢው ፓርቲ  ላይ ያለው ጥላቻ እያደገና እየከረረ መጥቷል። ለዚህ አስተዋጽኦ ያደረጉት ካድሬዎች ናቸው። ጀግናው የነጻነት ታጋይና ሰማዕት የሆነው መምህር የኔሰው ገብሬም “ የወረዳና የልማት ጥያቄ በማቅረቡ ወህኒ ቤት ሲያስሩት ጤነኛ የነበረ፤ ሲፈቱት ያልታመመና በሳምንቱ ራሱን በብሶት በቤንዚን አቃጠለ። በተቃጠለ በሦስተኛው ቀን ሞተና ከሞተ በኋላ ደግሞ ፖለቲከኞቹ እንዲሉት ታዘውና ተገደው እብድ ነበር አሉት።  የከፈለው መስዋዕትነት የዚሁ ትግል አካል ነበር።  ሌሎችም ለሚዲያ ያልበቁ በየወረዳው ፍትህና መልካም አስተዳደር እጦት ለችግራቸው መፍትሄ የሚሰጥ አካል አጥተው በተለያየ መንገድ ራሳቸውን ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም። ጊዜና ወቅት ሲፈቅድ የሚታወሱበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል።
እኛ አመራሮቹ የምንፈልገውን አስተጋቡልንም? የወረዳ ጥያቄ ለህዝቡ አይጠቅምም እያላችሁ ሕዝቡን ቀስቅሱልን! የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን ከገዢው ፓርቲ ጋር ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ መተባበር ግዴታው ነው! ይህን ካላደረግህ ጥገኛ ነህ!  በሌላ አባባል ህዝቡን ለማፈን መብቱን ለመንፈግ ተነስተናልና የመንግሥት ሠራተኛውም ከእኛ ይተባበር የሚል አስገዳጅ ውሳኔ ወስነው ለመንግሥት ሰራተኛው ጥሪ አደረጉ። ለዚህ ያልተባበረውን የመንግሥት ሠራተኛ ከሥራ በማገድ በማባረር በማሰር ወዘተ ለማስገደድና አንገቱን ለማስቀርቀር ብሎም ዝም ለማሰኘት ይቻላል በሚል እርምጃ መውሰድ ጀመሩ።ይህም የሕዝቡን ቁጣ እየቀሰቀሰው ይታያል። ረዳት ሳጅን ሽታዬ ወርቁም ታህሳስ 17/ 2005 ዓ.ም በገሳ ጨሬ ከተማ የተደረገው የመንግሥት ሠራተኞች ስብሰባ ላይ አካሄዱን ያወገዘው። ሕዝቡን ማፈን ተገቢ አይደለም ያለው።
የረዳት ሳጅን ሽታዬ ወርቁ ጥያቄና ላቀረበው ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ የተሰጠው ምላሽም የዚሁ ውሳኔ አካል ነው። በደረሰበት ጫናና እስራት የተነሳ ነው ነጻነት በሌለበት ሁኔታ ለመኖር መቸገሩን ያስታወቀው። ይህንን የሚያደርጉ ካድሬዎች ነገ ከሕዝቡ ጋር የሚኖሩ ናቸው ወይስ አይደሉም? እያልኩ ራሴን ስጠይቅ ምላሽ አጣለሁ። መንግሥትም የዳውሮ ሕዝብ ችግርን በመናቅ ጉዳዩ ለስልጣኑ ምንም የሚያሰጋው ስላልሆነ ይመስላል እስከዛሬ እያስለቀሰው ይገኛል።
ይህንን የዳውሮን ሕዝብ በደል ለማስቆም ትልቁ ጉልበት ያለው በመንግሥት እጅ መሆኑ ግልጽ ነው። መንግሥት ግን ስለ ሕዝቡ መበደል አልተገነዘበም ወይም ንቆታል አሊያም ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና ዳውሮ ውስጥ ከፈጠራቸው አሽከሮቹ የሚቀርበውን የሐሰት መረጃ በመቀበል ሕዝቡን እንደጠላቱ ፈርጆታል ብዬ እገምታለሁ። በመሆኑም ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመለወጥና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የሚመለከታችሁ የሕብረተሰቡ አካላት የየድርሻቸውን መወጣት እንደ አለባቸው በማመን መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
መልዕክት ለሕወሀት አመራሮች
የዳውሮ ሕዝብ በደል እጅግ ተባብሷል። ለመንግሥት ያቀረበው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ያገኛል ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር። የሕዝቡ ጥያቄ በአጭሩ፤ የወረዳ ማዕከል ቦታ እንዲሆን የተመረጠው ሥፍራ የወረዳውን ሕዝብ አያማክልም፤ የወረዳ ዋና ከተማ ዝውውር የተወሰነውና የተከናወነው በአንድና ሁለት ካድሬዎች የግል ፍላጎትና መነሻነት ነው፤ ስለዚህ በሕዝቡ ፍላጎትና ሕዝቡን በሚያማክል ሥፍራ ይደረግልኝ ነው። ቅን መሪ ቢኖርና የመወሰን ኃላፊነት ከተመጣጣኝ ሥልጣን ጋር የተሰጠው ዜጋ ይህን ጥያቄ ለመመለስ እንደማይቸገር ግልጽ ነው። ይህ ባለመሆኑ ሕዝቡ ተበደለ።
የሕወሀት/ ደህዴን ኃላፊና የአሁኑ “ ጠቅላይ ሚንስትር ” የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሰሩትና የሚያከናውኑት ድርጊት የዳውሮ ሕዝብ ጥላቻቸው እስካሁን እንዳልበረደላቸው ያሳያል። የዳውሮ ሕዝብ እምነት ያለውን ጠንካራ አመራር ጠራርገው አስወግደው፤ በቀጣይም ሌላ የተሻለ መሪ እንዳይፈጠር አምክነው በግል አሽከሮቻቸው ተክተውታል። እሳቸው በስልጣን እስካሉ ድረስ የዳውሮ ሕዝብ ለማንኛውም ፍትሐዊ ጥያቄው ምንም ምላሽ እንደማያገኝ እሳቸውም ያውቃሉ፤ አሽከሮሻሸውም ለዚሁ ሳይታክቱ ይሰራሉ፤ የዳውሮ ሕዝብም ይህንኑ በሚገባ ያውቃል። ይቃወሙናል በሚል የዳውሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች በተለያየ ሰበብ ከሥራ ገበታቸው እየተወገዱ ይገኛሉ።
የእርሳቸው ዓላማ የዳውሮ ሕዝብን ጥቅም ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ነጥቀው የራሴ ነው ለሚሉት ብሔር አሳልፈው የመስጠትና የመጥቀም ራዕይ ነው። ለምሳሌ ያህል በዳውሮ ውስጥ የተካሄደውን የሰፈራ ፕሮግራም የሥራ ክንውን፤ በግልገል ግቤ ቁጥር ሦስት የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ ግንባታ ሥራ ከባለሙያና ከአስተዳደር ሠራተኞች ቅጥር ጀምሮ ከኃይል ማመንጫው ሥራ ጋር በተያያዘ የሚከናወኑ የተከላ ሥራ እንቅስቃሴዎች ድርጊቱን መመልከት በቂ ማስረጃ ነው። በወላይታ በኩል ብቻ ግንኙነት እንዲኖረው በማሰብ የዳውሮ ጠንባሮን የገጠር መንገድ ፕሮጀክት ሥራ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው አስዘግተውበታል። የዳውሮ ሕዝብ የወረዳ ጥያቄም እስከ አሁን መፍትሔ እንዳያገኝ ያደረጉ እሳቸው ለመሆናቸው የዳውሮ ሕዝብ ጥርጥር የለውም።አሽከሮቻቸውም ለሚቀርባቸው ሁሉ ይህችን ለሕዝቡ አረጋግጠዋል።አቶ ሺፈራው ሽጉጤ የደቡብ ክልል አስተዳዳሪ በዋናነት በዳውሮ የወረዳ ጥያቄ ጉዳይ አቶ ኃይለማርያም ያሳረፉትን በደል ጠንቅቀው ያውቃሉ። ለሕዝቡ ወረዳ በመስጠት ችግሩን ለመፍታት እንኳ እንዳይችሉ ተደርገዋል።
ህወሀቶች ከአቶ ኃይለማርያምና ከግል አሽከሮቻቸው ጡጫና በደል የዳውሮን ሕዝብ ታደጉ አላቅቁትም። ታግላችሁ የደማችሁት እናንተ ናችሁና እናንተው ብትበድሉት ይሻላል እሳቸው ከሚበድሉት። በደልን ማንም በደለ ያው ነው። ግን የእሳቸው በደል ባሰበትና ነው። እርሳቸው እንደሚሉት የዳውሮ ሕዝብ አሸባሪ፤ ጥገኛና ጸረ ልማት አይደለም። የሚጠቅመውንም የማያውቅ ሕዝብ አይደለም። የወረዳና የልማት ጥያቄን ልዩነትና አንድነት ጠንቅቆ ያውቃል። ለወላይታ ሕዝብ አምስት ተጨማሪ ወረዳ ሲሰጡት አቶ ኃይለማርያም የወላይታን ሕዝብ ጥገኛ ነው አላሉም። ጭቁን ሕዝብ ነው ብለው ነበር የሰጡት። ዛሬ የዳውሮ ሕዝብ የወረዳ ጥያቄ ከወላይታ ሕዝብ ቀድሞ ያቀረበ መሆኑን እያወቁ የተዛባ ሥም ሊሰጡት አይገባም። ይህንን ለምን ታደርጋለህ? የሚል ሰው የለም! እርሳቸውና የአሽከሮቻቸው የግፍ አገዛዝ ዘመን በዳውሮ ምድር ሊያበቃ ይገባልና የዳውሮን ሕዝብ ከእሳቸው ጡጫ አውጡት።
የወረዳ ጥያቄን ለማምከን ሲባል ወረዳውን በሁለትና በሦስት መንደር ከፋፍሎ የአንዱን መንደር ሕዝብ በሌላኛው ላይ ጥገኛ ሕዝብ ነው ታገሉት ብሎ መቀሰቀስ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው አካሄድ ነው። ሕዝብ ሁልጊዜ አብሮ የሚኖር ነው። መንግሥት እንደነባራዊ ሁኔታው ሊቀያየር ግድ ነው። የሚቀየርና የሚያልፍ መንግሥትና ገዢ ፓርቲ ለዘመናት የኖረንና ወደፊትም አብሮ የሚቀጥል ሕዝብን ጥገኛ ነው፤ የጥገኛ ሐሳብ ተሸካሚ ነው፤ ጠላትህ ነው! ወዘተ በሚል ሕዝብን በጥላቻ እንዲተያይ ማድረግ አይጠቅምም። ይህንን ኃላፊነት ለጎደላቸው ከፍተኛ አመራሮች ንገሯቸው።
መልዕክት ለዳውሮ ዞንና ለየወረዳዎቹ ካድሬዎች
የዳውሮ ወረዳዎች የማዕከል ጥያቄ የተነሳው አሁን በእናንተ ዘመነ ሥልጣን አይደለም። አሁን በስልጣን ላይ ያሉት አመራሮችም ሆኑ ካድሬዎች ለችግሩ መነሻዎች እንዳይደላችሁ እረዳለሁ። የችግሩ ምንጭ ቀደም ሲል የወረዳዎች መታጠፍና እንደገና መዘርጋት ጥሎ ያለፈው ችግር እንደሆነም አስተውላለሁ። ችግሩን ለመፍታት ከጪ፤ ገሳ ጨሬና ተርጫ ቤት የሠሩና የንግድም ሆነ ሌሎች የግል ድርጅቶችን የመሰረቱ ከፍተኛ ካድሬዎች የሚያሳርፉት ቀጥተኛ ያልሆነ ግፊትና ጫናም እንዳለ ይሰማኛል። በየወረዳው ማዕከል የተሰሩ የአመራሮችና የካድሬዎች የግል መኖሪያ ቤቶች፤ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለዚህ የወጣው ወጪ ወዘተ ቀላል እንዳይደለም አልዘነጋም። ይህ ሁሉ ግን ከምንመራው ህዝብ መብት የሚበልጥ አይደለም።ተጠቃሚው ሕዝብ አይመቸኝም ሲል ያለው አማራጭ መቀበልና በሕዝብ ውሳኔ መገዛት ይገባችኋል።
ይህንን የቤት ሥራና የዳውሮ የወረዳዎችን የማዕከል ጥያቄ በቀላሉ መመለስ ሲችል የሰሜን ኦሞ ዞን መዋቅር ፈርሶ በ1993 ዓ.ም መግቢያ አካባቢ ዳውሮ እንደ ዞን ሲዋቀር በወቅቱ የነበሩ የፖለቲካ አመራሮች ይህንን ችግር በሚገባ አስተውለው መወሰንና በቀላሉ ማስተካከል ሲገባቸው ይህንን ችግር ተክለው እንዳለፉ ይሰማኛል። ይህ የዛሬው የዳውሮ የአያማክለኝም ጥያቄና ችግር በሂደት ሊመጣ እንደሚችል አስቀድመው ማየት የቻሉ የዳውሮ ምሁራንና ባለሙያዎች ነበሩ። አስተያየታቸውን አቅርበው እንደነበር አውቃለሁ። ወረዳዎች እንዴት በአዲስ መልክ ቢካለሉ የተሻለ ሊሆን እንደሚችል አጥንተው ያቀረቡት ነገር ነበር። ይህንን ጥናት አስፍቶ ሕዝብን ማወያየትና የተሻለ መፍትሄ ማምጣት አልተቻለም። የዚያኔ  አስፈላጊ የነበረው ወረዳና የወረዳ ማዕከል ጉዳይ እንደተራ ነገር ታይቶ መፍትሄ ሳያገኝ ቀርቷል። ሕዝብ ተንቋል።
የቶጫ ወረዳ ሕዝብ የመኪና መንገድ በመቆፈር ግንኙነት መቁረጡን አትዘነጉትም። ይህን  ያደረገ ህዝብ አቅም ቢኖረው ኖሮ ለደረሰበት በደል የተሻለ እርምጃ አመራሩ ላይ ይወስድ እንሰነበር ለመገመት የሥነ ልቡና ትምህርት አይጠይቅም። ተቃውሞውን አሳይቷል። በተመሳሳይ የዋካንና አካባቢውን  ሕዝብ የወረዳ ማዕከል ጥያቄ ባለፈው ዓመት አይታችሁታል። የዲሳን ሕዝብ ብሶት ደግሞ ሰሞኑን እያያችሁት ነው።
ጋሞ ጎፋና ዳውሮ የተለያዩ ናቸው። አቶ ታገሰ ጫፎ ወደ ደጋማው የጋሞ አካባቢ ተንቀስቅቅሶ የሕዝብ ፍላጎት የነበረውን የተጨማሪ ወረዳ ጥያቄ ለማምከን ባደረገው ጥረት ውጤታማ ሥራ ሰርቷል በሚል ተሞክሮ ይህ ሂደት በዳውሮ ሕዝብም ላይ ይሞከር በሚል የዳውሮ ሕዝብ እንደላቮራቶሪ እንዲሞከርበት አሥራ አንድ ገጽ ወረቀት ለውይይት የቀረበ ሰነድ በሚል ተዘጋጅቶ ተሰጥቷችሁ የሕዝቡን ጥያቄ ለማፈን እየሰራችሁ ትገኛላችሁ። ለዚሁም አፈጻጸም እንዲመች አስተያየት እንዲሰጥ የመናገር ዕድል ለማን እድል መስጠት እንዳለባችሁ ጭምር ተነግሯችሁ በነጻነት መናገር ለሚችሉ አርሶ አደሮች የመናገርና ሀሳባቸውን መግለጽ እንዳይችሉ በሕዝብ ስብሰባው ላይ እድል በመከልከል፤ እንቢ ብለው ከተናገሩ አቅራቢያችሁ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በማሰር ማፈን፤ የመንግሥት ሠራተኛ ከሆነ ደግሞ በተጨማሪ ማስፈራራት ከሥራ ማገድ እንዲሁም ከሥራ ማባረር ወዘተ ተግባራዊ በማድረግ የህዝብን ጥያቄ መቀልበስ እንደሚገባ ከሰነዱ ላይ ሰፍሯል። እየሰራችሁ ያላችሁትም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ነው። በዋናነት የጋሞጎፋ ሕዝብ ጥያቄ የተጨማሪ ወረዳ ጭምር እንጂ በጉልህ የወረዳ ማዕከል ጥያቄ አልነበረም።
ባለሙያዎች የሆናችሁ አመራሮችና ካድሬዎች በሙያችሁ ሰርታችሁ በቀላሉ መኖር የምትችሉት ዜጎች ናችሁ። እውነትን ሰርቶ ማለፍ የህሊና ቁስል የለውም። እስቲ የሚከተሉትን ጥያዌዎች ልጠይቃችሁ። ሲዳማ ዘጠኝ፤ ወላይታ አምስት፤ ቤንች ማጂ ሦስት፤ ስልጢ ሁለት፤ ጎፋም እንደዚሁ አዳዲስ ወረዳዎች ለሕዝቡ ሲሰጥ ለምን የነዚህ ዞንና ወረዳዎች አመራሮች ህዝቡን ወረዳ አያስፈልገውም ልማት ይጠቅመዋል ብለው ወረዳውን ያላስከለከሉትና ሕዝባቸውን ያልቀሰቀሱት ለምንድነው? ምናልባት አመራሩ ጥገኛ ስለሆነ ነው ትሉኝ ይሆናል። ለሲዳማ አቶ ሺፈራው፤ ለወላይታ አቶ ኃይለማርያም፤ ለስልጢ አቶ ሬድዋን፤ ለቤንች ማጂ አቶ ጸጋዬ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት ለሕዝባቸው አዳዲስ ወረዳዎችን ሰጧቸው። እርግጠኛ ነኝ እነዚህን አመራሮች ጥገኛ ናቸው እንደማትሉ! ታዲያ ዳውሮ ውስጥ ተጨማሪ ወረዳ መጠየቅ ይቅርና የወረዳ ማዕከል ይስተካከልልኝ ብሎ ማሰብ መናገርና መጠየቅ ምነው ጥገኝነት በሚል ፍረጃ ውስጥ የሚያስገባ ሆነ? የዳውሮ የወረዳ ማዕከል ጥያቄ ለምን ከልማት ጋር ይያያዛል? እናንተ ለህዝባቸው ወረዳ ከሰጡት ባለስልጣናት የምታንሱት ሕዝባችሁን ስለማትወዱና ራሳችሁንና የሥልጣን ዘመናችሁን ለማስረዘም ብላችሁ ነው የሚል ጥያቄ ቢነሳባችሁ መልሳችሁ ምን ይሆን? ቀድሞውኑ ማን ጠይቋችሁ!
በቀድሞዎቹ የንጉሡና የደርግ መንግሥታት ዘመን ያገለገሉትና ሕዝብን በድለዋል ተብለው ብዙ ባለስልጣናት ታስረዋል ተቀጥተዋል። እነዚህ ባለሥልጣናት አብዛኛዎቹ ያገለገሉበት መንንግሥት የሰጣቸውን ሥራ በሕዝቡ ላይ አስገድደው አስፈጽመዋል። ትልቁ በደላቸውና ስህተታቸው ይህ እንደሆነ ሲገለጽ ሰምተናል። የመንግስትን ዕቅድና ፍላጎት በጉልበት ማስፈጸም፤ የግለሰብን የመናገርና የማሰብ ነጻነት መንፈግ፤ ያለምንም ጥፋትና በደል ሰውን በመናገሩ ብቻ እንደወንጀለኛ ማሰር ማንገላታት ከሥራ ማባረር ወዘተ ማድረግ ከቻላችሁ ታዲያ እናንተ ከእነርሱ የምትለዩት በምንድነው? እናንተስ ነገ ተመሳሳይ ጥያቄ እንደማትጠይቁ እርግጠኞች ናችሁ?
አትቀበሉኝ ይሆናል ግን ልምከራችሁ።‘‘ጻድቃን ሥልጣን ሲይዙ ሕዝብ ሐሤት ያደርጋል፤ ክፉዎች ሲገዙ ግን ሕዝብ ያቃስታል፡፡’’ ምሳሌ 29፡2  እናንተንን ክፉዎች ናችሁ ለማለት ባልደፍርም የዳውሮ ሕዝብ እያለቀሰ ነው። እውነቱን ደግሞ ውስጣችሁ ያውቀዋል። እናንተም ነገ ታልፋላችሁ። ለሚያልፍ ሥልጣን ብላችሁ የማያልፈውን ወገናችሁን በዋናነት ዳውሮንና ሕዝባችሁን አትበድሉ። የመሰለውን ስለተናገረ ሰውን አላግባብ ጎትታችሁ አትሰሩ። የደርግ ባለሥልጣናት እንኳን እንደናንተ ለሕዝብ እንዲዋሽ ትብብር ጠይቀው እንቢ አልተባበርም ያላቸውን ግለሰብ ስለማሰራቸው እርግጠና አይደለሁም። የእናንተ ባስ እኮ!
የመንግሥት ሠራተኛ የግል ሠራተኛችሁ አይደለም። እንደእናንተ ሕዝብን አልዋሽም ስላለ ከሥራም አንዲባረር እንዲጎሳቆል አታድርጉ። ቢቻላችሁ የህዝቡን ጥያቄ በምትችሉት ሁሉ መልሳችሁ ምኑም ቀርቶባችሁ በሰላምና በፍቅር ከወገኖቻችሁ ጋር ብትኖሩ ይሻላችኋል። ነገ ከስልጣን ስትወርዱ የምትኖሩት ከዳውሮ ሕዝብ ጋር ነው። ብትሞቱ የሚቀብራችሁ ይህ ህዝብ ነው። ቃሉን አክብራችሁ ብትሰሩ ይጠቅማችኋል። ወደዳችሁም ጠላችሁ የህዝብ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ አይቀርም። አሁን በሥልጣን ያላችሁት ግለሰቦች የሕዝቡን ጥያቄ በተገቢው መልሳችሁ ምርቃቱ ቢቀርባችሁ እንኳ ሳትረገሙ ብታልፉ ይሻላችኋል። ነገ ከነገወዲያ እግዚአብሄር ሲፈቅድለት በእናንተ ማግስትም ቢሆን የህዝብ ጥያቄ በተገቢነት መመለሱ እንደማይቀር ለማየት ዕድሜ ያድላችሁ!
ለመንግሥት ሠራተኞች
ረዳት ሣጅን ሽታዬ ወርቁ በሎማ ዲሣ ወረዳ አካባቢ የዲሣ ከተማ ፖሊስ በመሆን ለዓመታት ማገልገሉንና በቅርቡ ወደ ሎማ ገሣ መዛወሩን፤  በዲሣ አካባቢ ቆይታዉ ወቅት የዲሣን ወረዳ ጥያቄ የሚያንቀሳቅሱ ሦስት ግለሰቦችን እንዲያስር ከዳዉሮ ዞን የፖለቲካ ጉዳዮች ሀላፊ መመሪያ ተሰጥቶት ያለ አንዳች በቂ ማስረጃና ጥፋት ሰዉ እንዲሁ ከሜዳ አላስርም በማለቱ በዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሁኔታው አልተደሰቱም ነበር፡፡ የዲሣን ወረዳ ጥያቄ ያንቀሳቅሳሉና መታሰር አለባቸዉ ተብለዉ ከዞኑ ፖለቲካ ኃላፊ ትዕዛዝ የተላለፈባቸዉ ግለሰቦች አቶ አባቴ አሰፋ የትምህርት ባለሙያ፤ አቶ መስፍን ማሞ አርሶ አደር፤ እና አቶ ደስታ ቶልባ የግብርና ባለሙያ ነበሩ። አሁን እዚህ ላይ የፖለቲካ ኃላፊውንና ፖሊሱን አወዳድሩ። የትኛው ነው ለሕዝብ የቆመውና እውነተኛ የህዝብ ጥቅምና መብት የታገለው? ልዩነቱን ተመልከቱ።
ይህንን ያነሳሁት በየወረዳው እየተደረገ ያለው  የሕዝብን እውነተኛ የተጨማሪና የወረዳ ማዕከል ይስተካከልልኝ ጥያቄ የመንግሥት ሰራተኛው እንዳይደግፈው ለማድረግ እየተካሄደ ያለውን ሁኔታ ለማመላከት ነው። የመንግሥት ሠራተኛው የራሱም ሆነ የቤተሰቡ ህይወት መንግሥት በሚከፍለው የወር ደመወዙ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ካድሬዎች ይህችን እንጀራውን እንደማስያዣ ዕቃ ቆጥረው አንድን የመንግሥት ሠራተኛ እነርሱ የፈለጉትን እንደ ቴፕሪከርደር ሲዲ ያሻቸውን ሞልተው ለማናገር የወሰኑ ይመስላል።ልጅን በአባቱና በቤተሰቡ ላይ ለመቀስቀስ እየሰሩ ነው።
ኃላፊነት የጎደለው ሥራ እያተሰራ ይስተዋላል። የህዝብን ጥያቄ ለማፈን ለመንግሥት ከባድ አይደለም። እንደተለመደው ማሰር ማንገላታት ማስፈራራትና ጥያቄህን አንመልስም እንቢ ምን ታመጣለህ? በሚል በተለመደው መንገድ ማስቆምና መግታት ይቻላል። ተችሏልም። ነገር ግን አንድ ወረዳ ውስጥ ያለን የኖረንና የሚኖርን ሕዝብ እርስ በራሱ ለማጋጨት በአንድ ወረዳ ውስጥ የዋካንና ዙሪያውን ህዝብ ጥያቄ የማሪ ዙሪያ ህዝብ እንዲቃወመው ሕዝብን ማነሳሳትና መቀስቀስ፤ የዲሳን አካባቢ ሕዝብን የወረዳ ማዕከል ጥያቄን ለመቀልበስ የገሳጨሬ አካባቢ ሕዝብን መቀስቀስ፤ የቶጫ አካባቢን ሕዝብ ጥያቄ ለማፈን የከጪ አካባቢ ሕዝብን መቀስቀስ የዛሬን የሕዝብን የወረዳ ጥያቄ ለመግታት እየተሰራ ያለው ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ለነገ አብሮነታቸው የሚያሳድረው የነገር ቁርሾ እንዳይኖር በተማሩትና አርቀው ማስተዋል የሚችሉት የሕብረተሰቡ ወገኖች ሊያስቡበትና ሊነቁበት ይገባል። ካድሬዎቻችን ምን እንደነካቸው አላውቅም። እኛ በስልጣን ላይ ዛሬን እንቆይ እንጂ የሕዝብ ጉዳይ የነገ ጉዳይ ወዘተ አያገባንም ያሉ ይመስላልና እንድናስብ አደራ እላለሁ። እነርሱ ለሕዝባቸውና ለዳውሮ ጥሩና የሚችሉትን አድርገው ለማለፍ የታደሉ አይደሉም።
በ1998 ዓ.ም እና በ1999 ዓ.ም የሌሎች አካባቢዎች የዞንና የክልል አመራሮች የነበሩ ለህዝባቸው ልማትና ዕድገት ሲሉ የራሳቸውን ጥቅም የማያስቀድሙ፤ ህዝባቸውን የሚወዱና የሚያከብሩ፤ በተሰጣቸው የስልጣን ክልል የህዝባቸውን የልማትና የወረዳ ጥያቄ አንግበው የታገሉና ጸንተው የቆሙ፤ የወከለኝ ህዝብ ጥያቄ የእኔም ጥያቄ ነው ያሉ አመራሮች በሌሎች ዞኖችና አካባቢዎች በተለያየ ቦታና ደረጃ አሉ። የሲዳማን የስልጢን የጎፋን የቤንችንና የወላይታ አመራሮችን የሥራ ተግባር ማየት እንችላለን። እነዚህ ህዝባቸውን ጠቅመዋል። የወከላቸውን ሕዝብ ጥያቄ በሆዳቸው አልለወጡትም። በዚህ የተነሳ ከፍተኛ የሞራል የበላይነት ሊሰማቸው ይገባቸዋል። ሕዝባቸውና አካባቢያቸው ሲዘክራቸው ይኖራል።
ለጊዚያዊ የግል ጥቅማቸው የቆሙ፤ ነገ ሳያውቁትና ሳይመሰገኑበት አሊያም ታስረው ወይም ተባርረው ለሚጥሉት ሥልጣን ትኩረት የሰጡ፤ ለጊዜው  የያዙትን ሥልጣን ማጣት የሚያስጨንቃቸው፤ ራስ ወዳዶች፤ ጥሩ ነገር ለህዝባቸው ሰርተው ለማለፍ ያልታደሉና አድርጉ የተባሉትን ለማድረግ ተሽቀዳድመው ከመሮጥ ባሻገር ቆም ብለው ይህ ሕዝባችንን አካባቢያችንን ይጠቅማል ወስ አይጠቅምም? ሕዝቡስ ምን ይላል ማለት የማይችሉ የህዝብ ተቃራኒዎች ደግሞ አሉ።። የዳውሮ ዞን አመራሮችን በዚህ ቡድን አስገብቶ መውቀስ ተገቢ ነው። ጠንካራ አመራሮች ለህዝባቸውና ለዞናቸው ተጨማሪ ወረዳ ታግለው አስገኙ። እኛ ለህዝብ የቆመ አመራር በዞን ደረጃ ስላልነበረን የዳውሮ ህዝብ እያነባ እያለቀሰ ይገኛል። ከእሱ የተሰበሰበው ግብርና ታክስ እየተከፈለው የሚሰራ አመራርና ካድሬ ህዝቡ ወረዳ አያስፈልገውም አልጠየቀም እያለ እየዋሸ እኛም የሱን ግጥምና ዜማ ተቀብለን እንድናዜም ሊያስገድደን ይታገለናል። አለመታደል እኮ ነው ወገኖቼ! በፍጹም እንቢ ልንል ግድ ይለናል። ተቃውሟችሁን በግልጽ አድርጋችሁ ጥቂቶችን ሰለባ ማድረግ ባያስፈልገንም የሕዝብ አጋርነታችንን በምንችለው ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተቃራኒ መግለጽ የሞራል ግዴታችን ነው።ይህ አመራር ጥቅሜ ከሚጓደልና የመኪና ጋቢና ከሚቀርብኝ ከዳውሮ ሕዝብ ምኑም ይቅርበት ብሎ የወሰነ ይመስላልና ያቅማችንን የማበርከት ግዴታ ይጠብቀናል።
ለዳውሮ አርሶአደሮች፤ ነጋዴዎችና ሌሎች የየከተማው ነዋሪዎች
ለዳውሮ ዞን ሕዝብ መንግሥት ተገቢውን  ምላሽ እንደሚሰጣችሁ በተስፋ ስትጠብቁ ቆይታችኋል። ነገሩ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ የሚታወቅ ቢሆንም የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል የሚል የፖለቲካ አመራር በየደረጃው ባለማኖሩ እስካሁን ተገቢውን ምላሽ ማግኘት አልተቻለም። እንዲያውም እያደር ጥያቄው የጥገኞች ነው፤ የጥቂቶች ነው፤ የብዙኋኑ የዳውሮ ሕዝብ ጥያቄ አይደለም፤ ሕዝቡ ልማት እንጂ ወረዳ አይጠቅመውም በሚል የሕዝቡን ጥያቄ ለመቀልበስና አቅጣጫውን ለማስቀየር ብሎም ህዝቡ ተጨማሪ ወረዳ እንዲያጣና የሚሻውን የወረዳ ማዕከል ወደሚቀርበው ሥፍራ የማዛወር መብት እንዳይኖረው ለማድረግ ተግተው እየሰሩ ይገኛሉ።
የገዛ ልጆችህ ናቸው ጥያቄህን ለመድፈቅ አሲረው አንተን ለማፈን ተግተው እየሰሩ የሚገኙት። የሚናገረውን ለማስፈራራትና እንዳይናገር በማድረግ እድል በመከልከልና በማሸማቀቅ፤ ለምን መብታችንን ትነኩብናላችሁ ብለው የሚጠይቁ ከተገኙ ለማስፈራሪያነት በማሰር ለማስፈራራት ዕቅድ ተሰጥቷቸው ይህንን ለመተግበር ይሰራሉ። በመንደርና በአገልግሎት በመከፋፈል ጥያቄህን ለማሳነስና የጋራ ጥያቄ አይደለም የጥቂቶች ነው ለማለት እየተባበሩ ነው። ስለዚህ በአገልግሎትና በመንደር መከፋፈል አያስፈልግህም። ልማትና ወረዳ አይነጣጠልም።
አንድ ምሳሌ ላንሳላችሁ። የወረዳ ማዕከል ጥያቄ የእኛ አይደለም የጥቂቶች ነው እኛ ወረዳ አንፈልግም በሉ፤ እንቢ ካላችሁ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቱን ከዚህ እናነሳለን፤ የጤና ጣቢያ ሥራ አይከናወንም ወዘተ የሚል ተራ ማስፈራሪያ አንድ ሆድ አደር ካድሬ ሲናገር ሰምተው ከተሰብሳቢዎቹ መካከል አንዱ አርሶ አደር (በማረቃ ወረዳ ጌንዶ አገልግሎት አካባቢ ውስጥ ነዋሪ ናቸው ) ካድሬውን በሚያሳዝን መልኩ ረግመውት አሁን የእኛን ወረዳ ጥያቄ ለማስጨንገፍ ብለህ ለሆድህ አድረህ ህሊናህን ሽጠህ በል የተባልከውን እያልክ ነው ብለዉት ይህንን ተራ ወሬ ይዞ ወደ መጣበት እንዲመለስና እሳቸውም ሆነ ሕዝቡ የሚሻለውን ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆኑን አስተምረውት አሳፍረውት መልሰውታል።
ይህንን የተናገሩት አርሶ አደር በፖለቲካዊ ንቃተ ህሊና አንጻር ከካድሬው ጋር አነጻጽራችሁ የቱ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዳለ አስተውሉ። ማነው የህሊና ነጻነት ያለው? ልማትና ወረዳ አይነጣጠሉም። ወረዳ ሲመጣ ከወረዳው ጋር አብሮ ልማትም ይመጣል። ዳውሮ ዞን ባይሆን አሁን የደረሰበት የልማት ደረጃ ላይ ይደርስ ነበር የሚል ካድሬ ሊመጣ እንደሚችል አትጠራጠሩ ግን አትመኑት። የሰሞኑ ካድሬ ድንጋይ ዳቦ ነው ለማለት የሚታቀብ ስለመሆኑ ያጠራጥራል። እያከናወነ ያለው ክብሩን ህሊናውን ሞራሉን ሁሉ ትቶት ነው።
የዳውሮ ሕዝብን የወረዳና የልማት ጥያቄውን ለመቀልበስ የሚሰሩ ሁሉ የዳውሮ ልማትና የዳውሮ ህዝብ ጠላቶች ናቸው! ሕዝብ የሚበጀውንና የሚሻለውን ያውቃል። የካድሬ ሰበካና የሐሰት ቀላጤ አያስፈልገውም። የካድሬው ዓላማ የህዝብን ጥያቄ ወደ ጥቂቶች ጥያቄነት ለመቀየርና ጥያቄውን ለማምከን ነውና ሁላችንም በምንም ሳንከፋፈል አብረን ቆመን ጥያቄያችንን በጋራ በአንድ ድምፅ ማስተጋባት ይጠበቅብናል።
የዳውሮ ምሁራን የሆናችሁ በሙሉ!
ከላይ በዝርዝር ያስቀመጥኩትን እውነታ ተመልክታችኋል። የዳውሮ ዞን አመራሮች ከክልል አመራሮች ተጭነው የመጡትን የሕዝቡን የወረዳና የወረዳ ማዕከል ጥያቄ ለማምከን ምን ያህል ተግተው እየሰሩ እንዳለ ተመልከቱ። ከራሳቸው አልፈው የወረዳ አመራሮችንና ካድሬዎችን አስገድደው የተጫኑትን መልሰው ጭነውባቸው ከህዝቡ ጋር እያላተሟቸው ይገኛል። እኔ በግሌ የወረዳ አመራሮች ላይ ብዙ አልፈርድም። ለአብዛኛዎቹ የእንጀራ ጉዳይም ሆኖባቸው ሳይወዱ በግድ የተጫኑትን ማራገፊያ አጥተው እንደሚሰቃዩ ይሰማኛል። ከሕዝቡም እየደረሰባቸው ያለው ነገር እያሰቃያቸው ነው። በድርጊቱ ከዞን ጀምሮ ያለው አመራር በሕዝባችን ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም በደልና እንግልት ተጠያቂ መሆናቸውን ልብ ልንል ይገባል።
ምሁሩ የሕዝብ ወገን አመራሩ ለምንድነው እንዲህ የሚያደርጉት? ምን ይሻሻል? ከእኔ ምን ይጠበቃል? በሚል ማሰብ እንደሚገባችሁና እንቅስቃሴውንም በአንክሮ መከታተል እንደሚጠበቅባችሁ አሳስቤ ጽሁፌን በዚሁ እቋጫለሁ።

Jan 3, 2013

Breaking News: Protest erupts at Addis Ababa University

                                                                       Addis Ababa University main campus

Awramba Times (Addis Ababa) – Protest sparked at the College of Natural Sciences, Arat Kilo Campus of the Addis Ababa University. According to our sources in Addis Ababa, The main cause of the protest is due to an ethnic derogatory poster against Oromo-ethnic students placed at the College’s main Library and two other places.
So far, more than 20 students from the conflicting ethnic groups were wounded and were taken to government hospitals. On the other hand Police have accused several students of causing damage to university property, including broken windows and doors. More details to come…

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያቀረበውን የመነጋገርና የመታረቅ ጥያቄ ውድቅ አደረጉ


ኢሳት ዜና:-ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ቃል የተመላለሱት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኤርትራ ስልጣን ላይ ካሉ ግለሰቦች መቀያየር ጋር የምታያይዘው አንዳችም ነገር የለም ካሉ በሆላ ዝንባሌው እራሱ ከኤርትራ ባህልና እሴት የሚቃረን መሆኑን ገልጠዋል::
እንነጋገር የሚለው አባባል ምንጩ ከየት እንደሆነ እንረዳልን ያሉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይህ አይነት አካሄድ ትኩረት ከማስቀየር በቀር ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለውና ኤርትራም የምትገባበት ድራማ እንዳልሆነ አመልክተዋል::
የድንበር ኮምሽኑ ውሳኔ ተግባራዊ ላለመሆኑ የአሜሪካ መንግስት ተጠያቂ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን ከሀገራቸው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስታውቀዋል::
ፕሬዚዳንቱ የአሜሪካ መንግስት በሀገራቸው ላይ የጣለውን መአቀብ በመቆቆም አንድነቱንና እድገቱን በማጠናከር መዝለቁንም በዚሁ ቃለምልልስ ገልጠዋል::
ከአልቃይዳና ከአልሸባብ የተሰጣቸውን ግዳጅ ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል የተባሉ 10 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ ::  አንዱ በነጻ ተለቀቀ::
በተያያዘ ዜና በሱማሊያ ከሚገኙ እስላማዊ ሀይሎች ጋር ያላቸውና በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የተዘጋጁ ያላቸውን 15 ተጠርጣሪዎች  የኢትዮጵያ መንግስት መያዙን ሮይተርስ ዘገበ:፡ የፌደራል አቃቢ ህግ ክስ የመሰረተባቸውና በዕስር ላይ ሆነው ክሳቸውን ሲከታተሉ ከነበሩት መካከል በሽር ሀጂ እስማኤል የተባለው ተከሳሽ ነጻ ሲወጣ ሌሎች 10 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብልዋል::
አቃቢህግ የወንጀሉ ጠንሳሽ የአልቀኢዳና የአልሸባብ ዋና ተላላኪ ያለውን ነዋሪነቱ በሶማሊያ ሞቃዲሾ የሆነውን ሀሰን ጋርሶ ስቶላ ክሱ እንዲከብድና በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣለት ጠይቆል::
ጥፋተኛ የተባሉት 10 ተከሳሾች በህቡ በመደራጀትና በመንቀሳቀስ በኢትዮጵያ የፖለቲካና የሀይማኖት አላማ ለማራመድ በማሰብ በመንግስት ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ህብረተሰቡን በማስፈራራት ህገመንግስታዊ ስርአቱን ለማፈራረስ በአሸባሪነት ከተፈረጁት ከአልቃይዳና ከአልሸባብ ጋር ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አቃቢ ህግ በክሱ ላይ አስረድቶል::
በዚህ መሰረት ግለሰቦቹ ሊፈጽሙት የነበረው ወንጀል ከባድ እንዲባል አቃቢ ህግ ፍርድ ቤቱን ጠይቆል::
በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ የደህንነትን የጸጥታ አገልግሎት 20 ሰአት በፈጀ ዘመቻ በሀገሪቱ ላይ ጥቃት ለመፈጸምምያቀዱ 15 ሰዎችን መያዙን ሮይተርስ ዘግቦል::
እንደዘገባው ከሆነ ተጠርጣሪዎቹ በሱማሊያ ከሚገኝ እስላማዊ ቡድን የተቀጠሩ፡የሰለጠኑና በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ የተሰማሩ ናቸው ብሎል  የኢትዮጵያ የደህንነትን የጸጥታ አገልግሎት:፡
የተያዙት 15 ሰዎች ዜግነት አልተገለጠም ያለው ሮይተርስ ከሱማሊያና ከኬኒያ አቆርጠው ኢትዮጵያ መግባታቸውን ግን ዘግቦል:፡

በመቀሌ ከተማ የግል ጋዜጣና መጽሄት አዞሪዎችና ሻጮች ስራቸው ህገወጥ በመሆኑ ከስራ መታገዳቸው ተገለጠ




ኢሳት ዜና:- በከተማዋ በቆሚነት ደርድረውና እያዞሩ ጋዜጣና መጽሄት የሚሸጡ በመከልከላቸው ህዝቡ ጋዜጣ ማግኘት አለመቻሉን የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችና የቅርብ ምንጮች ያላቸውን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቦል::
ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁና በአካባቢው ጋዜጣና መጽሄት በመሸጥ የሚተዳደሩ ወጣቶች የጠቀሰው ዘገባ የከተማዋ ወያኔ ወረዳ ንግድና ኢንዱስትሪ አስተዳደር ስራው ህገወጥ መሆኑ ተገልፆላቸው ከታህሳስ 5፣2005 ጀምሮ በአካባቢው የገል ጋዜጣና መጽሄት የመሸጥ ስራ እንዳይሰራ መታገዱን አመልክቶል::
ይህንን ትእዛዝ ተላልፋችሁ ጋዜጣና መጽሄት እያዞራችሁ ተገኝታችሆል የተባሉ አምስት ወጣቶች በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው የታወቀ ሲሆን ሲያዞሩት የነበረው ጋዜጣና መጽሄት መወረሱ ተዘግቦል::


ESAT Daliy News-Amsterdam Jan. 03 2013 Ethiopia

Ethiopian woman in Kuwait died after falling from a building


KUWAIT CITY (Arabtimes) — An Ethiopian woman died when she fell from the window of a domestic employment agency in Hawally.
According to security sources, when the Operations Room of Ministry of Interior received information from the building guard about a woman lying on the ground and bleeding, police and paramedics rushed to the location and found the woman bleeding profusely from the head.
Paramedics examined her and discovered she had succumbed to severe head injury.
Officers from General Department for Criminal Evidences rushed to the location and referred the corpse to the Forensics Department.
Preliminary investigations by authorities revealed that the victim fell from the window of a domestic employment agency in the building. They also noticed that the victim was wearing ‘abaya’ without any underclothes. They were informed that the woman was at the agency with three other Ethiopian women.
Police summoned the three women and the owner of the agency to the police station where they said that they were sleeping at the time of the incident and were not aware of her death until the police notified them about it.
A case was registered for further investigations.

ኢሳያስ አፈወርቂ በጦር ወንጀለኝነት ሊጠየቁ ይገባል ተባለ


ር ያ ዕቆብ ኃይለማርያም ኢሳያስ አፈወርቂ “በጦር ወንጀለኝነት ሊጠየቁ ይገባል” አሉ። የፖለቲካ ኢኮኖሚ
ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ በበኩላቸው “የኢትዮጵያ መንግስት ኢሳያስን እና የጦር ጀኔራሎቹን በጦር
ወንጀለኝነት ሊከሰው የሚችልበት ዕድል አለ” ይላሉ።

በፋኑኤል ክንፉ
የኤርትራው ፕሬዝደነት ኢሳያስ አፈ ወርቂ ያቀረቡት የሰላም ድርድር ጥያቄ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ያለቅድመ ሁኔታ እደራደራለሁ ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
በተለይ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጋር በተያያዘ በሃይደር ት/ቤት ላይ የተፈፀመው የቦንብ ድብደባ እና በምርኮ በተያዙት በኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ላይ የተፈፀመው ሰብዓዊነት የጎደለው አያያዝ በጀኔቫ የጦር ወንጀል ስምምነት መሠረት ኢሳያስ አፈወርቂና የጦር ጀኔራሎቻቸው በጦር ወንጀለኝነት የሚያስጠይቅ መሆኑ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች እየጠየቁ ነው፡፡
በዓለም አቀፉ ሕግ ከፍተኛ ባለሙያና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለጽት፤ “የጦር ወንጀለኝነትን በተመለከተ በጄኔቫ ኮንቬንሽን የሠፈሩ ሁለት ፕሮቶኮሎች አሉ፡፡ በእነዚህ ፕሮቶኮሎች ትንታኔ ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የሚያስከትለው ክስ በፍትሐብሄርና በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑ፣ ከጦርነት ቀጠና ውጪ ስለሆኑ ሰዎች እንዲሁም የጦር ምርኮኞችን በተመለከተ በዝርዝር ሰፍሯል፡፡ ከፕሮቶኮሎቹ ስንነሳ በሃይደር ት/ቤት በአስመራ መንግስት የተፈፀመው የቦምብ ድብደባ በግልፅ ከጦርነት ቀጠና ውጪ የተፈፀመ የጦር ወንጀል መሆኑ ግልፅ ሆኖ እናገኛዋለን፡፡”
አያይዘውም “የኰሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የጦር ምርኮኛ ሆነው ከተያዙ በኋላ የተፈፀመባቸው ሰብአዊነት የጐደለው አያያዝ የጄኔቫ የጦር ምርኮኞች ፕሮቶኮል መሠረት በጦር ወንጀል የሚያስከስስ ነው፡፡ ፕሮቶኮሎቹ ወንጀልና ካሳን ለይተው ነው የሚያስቀምጡት፡፡ ካሳን በተመለከተ የአልጀርሱ የድንበር ኮሚሽን ስምምነት እና የሄግ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥተውበታል፡፡ ለኢትዮጵያ 110 ሚሊዮን ዶላር ሲቆረጥላት፣ ኤርትራ 100 ሚሊዮን ዶላር ተወስኖላታል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለሃይደር
ት/ቤት ተብሎ የተሰጠ የካሳ ክፍያ አለ፡፡ ይህ ግን በፍትሐብሔር የተፈፀመ የካሳ ክፍያ እንጂ በተማሪዎቹ ላይ ስለተፈፀመው የጦር ወንጀል የተሰጠ ብይን አይደለም፡፡ የፍርድ ውሣኔ ግን በፍትሐብሔር ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ሃይደር ት/ቤትን በተመለከተ የተከፈለ የገንዘብ ክፍያ መኖሩን የፍርድ ውሣኔ ሰነድ ቢያሳይም፤ የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ያለው አንዳች ነገር የለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወንጀል በቅጣት እንጂ በካሳ አይታለፍም፡፡ በእስር ያስቀጣል፡፡ ስለዚህም ኢሳያስና የእሱ የጦር ጀነራሎች የፈጸሙት የጦር ወንጀል በመኖሩ ሊጠየቁ ይገባል” ብለዋል፡፡ “ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አባል ሀገር አይደለችም፡፡ ይህን መሰል ክስ የት ልትመሰርት ትችላለች ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤
“ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አባል ባትሆንም የተፈፀመውን የጦር ወንጀል የሚያሳይ መረጃ ለፀጥታው ም/ቤት በማቅረብ በኢሳያስ ላይ የጦር ወንጀል ክስ ምርመራ ማዘዣ ማስወጣት ትችላለች፡፡ ምክንያቱም የፀጥታው ም/ቤት የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤትን የማዘዝ ስልጣን አለው፡፡ ቁም ነገሩ ግን፤ ይህን የጦር ወንጀል ድርጊት በባለቤትነት የያዘውም የጠየቀውም በኢትዮጵያ በኩል አለመኖሩ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን አሁንም በጦር ወንጀል ኢሳያስን ለመክሰስ የሚቻልበት እድል ተዘግቷል ማለት አይደለም፡፡ አሁንም ኢሳያስ አፈወርቂ በጦር ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግራዋል፡፡”
የፖለቲካ ኢኮኖሚ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ በበኩላቸው፤ “የኢትዮጵያ መንግስት ኢሳያስን እና የጦር ጀኔራሎቹን በጦር ወንጀለኝነት ሊከሰው የሚችልበት ዕድል አለ፡፡ ከዓለም አቀፉ ረጅም ቢሮክራሲ አንፃር ምን ያህል ያስኬዳል የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አሁን ያለው ነገር በአልጀርሱ ስምምነት መሠረት  ወደ ሁሉን አቀፍ የሠላም ድርድር ውስጥ ለመግባት የታሰበው መስለኝ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የምትቀበለውም የምትሰጠውም ነገር ይኖራል፡፡ ችግሩ ሁለቱም ሀገሮች
የአልጀርሱን ስምምነት አለመቀበላቸው ነው፡፡ ቁምነገሩ ድርድሩ ቢጀመር በምንድነው የሚጀመረው? የድንበር ኮሚሽኑ ውሣኔ ትክክል ነው? የኢትዮጵያ መንግስት ባድመን ለኤርትራ አሳልፎ ቢሰጥ በቀጣይ ምን ዓይነት የፖለቲካ ሁኔታ ሊገጥመው ይችላል? ከ70 ሺ በላይ የሰው ህይወት የቀጠፈው ጦርነት ለምን ተጀመረ?  ለሚሉት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ሊሰጥባቸው” ይገባል ብለዋል፡፡
ዶክተሩ አያይዘውም ፤ “የጦርነቱ መጀመር የባድመ ጉዳይ አይደለም፡፡ ናቅፋ የኤርትራ ገንዘብ ሆኖ መቅረቡ ነበር፡፡ በኤርትራ ውስጥ ሶስት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ነበር፡፡ ይህን ገንዘብ የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት በዶላር እንዲከፈል ጥያቄ ቢያቀርብም ውድቅ ተደረገበት፡፡ ሌላው፤ የኢትዮጵያ መንግስትም ኤርትራን ለማቋቋም የሰጠው ሶስት ቢሊዮን ብር እና ለኤርትራ ንግድ ባንክ ማቋቋሚያ ተብሎ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በብድር ሰጥቶ የነበረበት ሁኔታ ነበር የነበረው፡፡ በወቅቱ ኤርትራ ትጠቀምበት የበረውን የኢትዮጵያን ብር ወደ ናቅፋ ስትቀይረው፤ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ነባሩን ብር በአዲስ ብር ተክቶ ስራ ላይ አዋለ፡፡ ስለዚህም ኤርትራ ውሰጥ የነበረው የኢትዮጵያ ብር ከአገልግሎት ውጩ ሆነ፡፡ ይህ በመሆኑ የኤርትራ መንግስት ንዴት ውስጥ ወደቀ፡፡ የነበራቸው ግምት  በነበረው ግንኙነት በመጠቀም ወይም በጉልበት ፍላጐታቸውን ማሳካት የሚቻል መስሏቸው ነበር፡፡ የሆነው ግን ከጠበቁት ውጪ ነው፡፡ ጠብ የተጀመረው ከዚህ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራን የሚያክል መሬት ከሰጠ በኋላ 20 ኪሎ ሜትር ለማይሞላ በባድመ መሬት ጦርነት ውስጥ ሊገባ
አይችልም፡፡ አሁንም ሊደረግ የታሰበው ድርድር ባድመን ማዕከል ያደረገ ነው ተብሎ መውሰድም ከባድ ነው የሚሆነው፡፡ ኤርትራዊያን ባድመን ቢወሰዱትም የቻይና ግንብ አይሰሩበትም፡፡ ባድሜ ያለውም ሕዝብ ኤርትራዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ቢሆን ኖሮ፤ እስካሁን የድንበር ውዝግቡ መቋጫ ያገኝ ነበር፡፡ መሬቱን ኤርትራ ትጠይቃለች፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ ይላል፡፡ እዚህ ላይ ነው ጨዋታው ያለው፡፡›› ብለዋል፡፡ የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ቁርሾ በእርቅ ለመጨረስ በደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫኪር በኩል በይፋ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ የኢትዮጵያ
መንግስት አዎንታዊ ምላሽ መስጠቱ የተለያዩ ምንጮች መዘገባቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

ኢህአዴግ የአ.አ. መራጮችን A, B, C በሚል መክፈሉ አንድነት ፓርቲን አስቆጣ


በዘሪሁን ሙሉጌታ

በመጪው ሚያዚያ ወር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ የአካባቢ ምርጫ መካሄዱን ተከትሎ ኢህአዴግ የአዲስ አበባ መራጮችን በሦስት
መክፈሉ የአንድነት ፓርቲን አስቆጣ።
ኢህአዴግ በበኩሉ ከ2002ቱ የተለየ አዲስ የምርጫ ስትራቴጂ ግብ እንደሌለው አስታውቋል። ምርጫው በሕዝቡ ዘንድ ተአማኒነቱን ጠብቆ እንዲሄድ አባላቱን
በተለያየ መንገድ እያነቃነቀ መሆኑን ግን አልካደም።
ቀደም ሲል ለ2002ቱ ምርጫ ኢህአዴግ የገነባው የምርጫ ሰራዊት (አንድ ለአምስት) አደረጃጀት እንዳለ ቢሆንም ግንባሩ በተለይ የአዲስ አበባ መራጮች በሦስት
ደረጃ በመክፈል ለአባላቱ አዲስ ቅፅ አሳትሞ ማሰራጨቱ ታውቋል። በየቀበሌው የተበተነው ቅፅ መራጮቹን ‘‘ኤ’’፣ ‘‘ቢ’’ እና ‘‘ሲ’’ በሚል በመክፈል የምርጫ
ቅስቀሳው በዚሁ ቅደም ተከተል የሚፈፀም መሆኑን የሚያመለክት ነው።
‘‘ቅፁ በእጃችን ገብቷል’’ ያሉት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ አስራት ጣሴ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ቅፁ የኢህአዴግ አርማ
ያለበት ሆኖ የቀበሌውን ስም፣ መዝጋቢውን፣ የመራጩን ስምና የሚኖርበትን ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር የተመዘገበበት ቀን የመሳሰሉትን መጠይቆች የያዘ መሆኑን
ገልፀዋል። ቅፁን በመያዝ የኢህአዴግ አባላት ሕዝቡን መመዝገብ መጀመራቸውን ገልፀዋል።
በቅርቡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ሆነው የተመረጡት አቶ ሙክታር ከድር በስራቸው የሚገኙ 22 የመንግስት ሚኒስቴር
መስሪያ ቤቶችንና ኤጀንሲዎች ላይ ግምገማ ካካሄዱ በኋላ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች አንድ ለአምስት መደራጀት እንዳለባቸውና አደረጃጀቱም በሦስት
ዘርፎች እንደሚሆን መግለፃቸው፣ እነዚህም ሶስት ዘርፎች የኢህአዴግ ዘርፍ፣ የመንግስት ዘርፍ እንዲሁም ሶስተኛው አንድ ለአምስት ከሚያደራጀው መስሪያቤት
ወይም ከኤጀንሲው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የህብረተሰብ ክፍል እንዲሆን መወሰኑ አቶ አስራት አስታውሰዋል።
ለምሳሌ የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በአንድ ለአምስት አደረጃጀት በኢህአዴግ ዘርፍ፣ በመንግስት ሰራተኛ ዘርፍ ከተደራጁ በኋላ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር
ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ተማሪዎችና ወላጆች መሆናቸው በመጥቀስ ኢህአዴግ የአደረጃጀት አካሄድ ሀገሪቱን የአንድ ፓርቲ ስርዓት ከማድረግ ባለፈ በመንግስትና
በኢህአዴግ መዋቅር መካከል ያለው ልዩነት ተደምስሷል ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል።
ኢህአዴግ በሚያዚያ ወር በሚካሄደውም ምርጫ መሰረት በማድረግ መራጮችን በሶስት መክፈሉ ምርጫውን ይበልጥ ያወሳስበዋል ያሉት አቶ አስራት ‘‘ኤ’’፣ ‘‘ቢ’’
እና ‘‘ሲ’’ የሚለው መዋቅራዊ አካሄድም የመራጩን ስነ-ልቦና የሚነካ እንደሆነም ነው የገለፁት።
በስትራቴጂው መሰረት በ‘‘ኤ’’ ስር የሚመደቡ መራጮች በአስተማማኝ ኢህአዴግን የሚመርጡ በመሆኑ ከእነዚህ መራጮች ላይ ብዙ መስራት አያስፈልግም፣
በ‘‘ቢ’’ ስር የተፈረጁ ደግሞ በኢህአዴግ እና በተቃዋሚ መካከል የሚዋልሉና መጠነኛ ቅስቀሳ የሚካሄድባቸው ሲሆን በ‘‘ሲ’’ ስር የተፈረጁ መራጮች ደግሞ ሙሉ
በሙሉ ተቃዋሚ የሚመርጡ በመሆኑ የበለጠ መስራት የሚል እንደሆነ ተጠቁሟል።
የኢህአዴግ የውጪ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተመስገን ጥላሁን ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው ግንባሩ ለአዲሰ አበባ አስተዳደር እና በመላው ሀገሪቱ ለሚካሄደው የአካባቢው
ምርጫ የተለየ የምርጫ ስትራቴጂ እንደሌለው ተናግረዋል። ምርጫው በሕዝቡ ዘንድ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በሕዝቡ ዘንድ ተአማኒ እንዲሆን ግንባሩ እየሰራ
እንደሆነም አረጋግጠዋል። ግንባሩ በምርጫው ስኬታማ ለማድረግ ነባር መዋቅሩን መሰረት በማድረግ አባላቱን እያነቃነቀ መሆኑን በመግለፅ ስብሰባ እየመሩ
በመሆኑ በቀጣይ ጊዜ ወስደው በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንደሚሰጡበት ገልፀዋል።

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

Dec 30, 2012

Brutal Killings Inside Mosques Will Not Deter The Resolve Of The Ethiopian Muslim Community


Ginbot 7 Press Release
In the twenty one years of the TPLF rule, the Ethiopian people and the world at large have witnessed mass killings, targeted killings, and indiscriminate killings of the young, old, women and children as young as 8 years old. In 2005, the mass killing in Ethiopia reached its climax when special security forces under the direct order from the late Prime Minister Meles Zenawi savagely killed over 200 people as the world watched quietly. When Deputy PM Haile Mariam Desalegn took the oath of office and promised to walk on the same path as his predecessor, many Ethiopians lowered their expectation of witnessing a free, just and democratic Ethiopia in their life time.
 In just a little over a month in office, PM Haile Mariam Desalegn has kept his promise of staying the course of his predecessor in gunning down peaceful demonstrators on the streets of Ethiopian cities. On Sunday, October 21, 2012, Haile Mariam Desalgen mercilessly took the lives of his first four victims in a standoff that started inside a Holy Mosque in the Amhara zone. Two of his young victims were frog marched by security forces and shot execution style at the nearby police station while the other two were shot and killed inside the Mosque compound. According to reliable local sources, there are many people who are seriously wounded and the death toll may increase by two fold.
Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy categorically denounces the barbaric killing of innocent civilians and holds Haile Mariam Desalegn and his associates accountable for the lives lost. Ginbot 7 acknowledges that the Muslim community in Ethiopia has been waging a legitimate struggle in Ethiopia for the past 11 months. The demands are simple and crystal clear – they have asked the regime for freedom of worship and for the right to elect their religious leaders in their own way and place of their own choosing. These rights are protected by the Ethiopian constitution which the regime is obligated to respect.
Ginbot 7 urges Ethiopians inside and outside of Ethiopia to stand together with our Muslim brothers and sisters in this difficult time. Ethiopians of Muslim and Christian faith must stand together as a community to continue the struggle for freedom, justice, democracy and equality understanding and believing that we live in the context of each other, and acknowledging that the source of our freedom is our collective struggle.
We ask that donor nations and international organizations get their act together and start holding the brutal regime in Ethiopia accountable for its heinous crimes and its wanton disregard for the sanctity of life. All civilized nations should strongly condemn this act of terror against the Muslim community in their place of worship.
In Solidarity!

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የትግል ሜዳ መሃል አገርን ጨምሮ ወያኔ ባለበት ሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች መሆኑ ተዘገበ


የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል በሚል ስያሜ መመስረቱን ድርጂቱ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ያሳወቀ ሲሆን ይህን መግለጫ ተከትሎም በርካታ የዜና አውታሮች ሲዘግቡት መቆያታቸው ይታወሳል። ከዚሁ ዘገባ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት በትናንትናው እለት ስርጪቱ ከግንቦት 7 ሃይል ቃል አቀባይ  ታጋይ ዜና ጉታ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ ቃል አቀባዩ እንደገለጹት  የዝባዊ ሃይሉ  ራእይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት  ጠንካራ ኢትዮጵያን እውን ሆና ማየት ነው ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት የንቅናቄው ስም ግንቦት ሰባት የተባለበት ዋነኛ ምክንያት በ1997 ምርጫ ወቅት ግንቦት ሰባት ቀን የኢትዮጵያዊያን ድምጽ ባደባባይ በጉልበት የተነጠቀበት በመሆኑ፣ ቀኑ በኢትዮጵያዊያን ልዩ ቦታ የሚሰጠውና እለቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ዘረኛውን የወያኔ አገኣዛዝ ፍጹም እንደማይፈልግ የገለጸበት እንዲሁም ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ዝግጁነቱን ያረጋገጠበት  ቀን በመሆኑ ነው ብለዋል።
የግንቦት ሰባት ሃይልን አሁን መመስረት ለምን አስፈለገ በሚል የኢሳት ጋዜጠኛ ለታጋይ ዜና ጉታ ላቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል።
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ታጋይ ዜና ጉታ ወያኔን በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በምድር ላይ እየተንቀአሳቀሱ ካሉ  ሃይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆኑንና፣  ከነኝሁ ሃይሎች ጋር በጋራ ለመስራት አስፈላጊዉን ቅድመ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን እንዲሁም የዚህ ሃይል የትግል ሜዳ መሃል አገርን ጨምሮ ወያኔ ባለበት ሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ነው በማለት፣ በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ አብራርተዋል። ቃል አቀባዩ ለኢሳት እንደገለጡት የግንቦት 7 ሃይል ከትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወይም ደሚት፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህና እኩልነት ግንባር፣ ከጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከተባሉት ድርጅቶች ጋር በጥምረት ለመስራት አስፈላጊው ዝግጅት አጠናቋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መመስረት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባቱና፣ የዘረኛነት አባዜ መርዙን በመርጨት ስራ ላይ መጠመዱ ትግራይ ኦን ላይን በመባል በሚታወቀው ድረ ገጽ ላይ ባወጣው ጽሁፍ ገልጹአል። የዚህን የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል መመስረት ተከትሎ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ዲሴምበር 22 ቀን በዚሁ ድረ ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ እንደሚያመለክተው የግንቦት 7 ሃይል በተለይም በትግራይ ህዝብ ላይ ለመዝመት የተነሳ ሃይል ነው ያለ ሲሆን፣ የትግራይ ህዝብ እሰከ አፍንጫው ድረስ በጦር መሳሪያ የታጠቀ፣ የተደራጀና፣ ወታደራዊ ስልጠናም የወሰደ በመሆኑ ይህን የግንቦት ሰባት ሃይል እሰከ ደም ጠብታው ድረስ ይፋለመዋል፣ ካለ በሁአላ የትግራይ ተወላጆች ይህን ሃይል እንዲፋለሙ ጥሪ አቅርቡአል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በትግራይ ህዝብ ስም መነገድ የጀመረው ገና ወደ ስልጣን ወምበር ከመምጣቱ ቀደም ብሎ  እንደነበር በስፋት የሚታወቅ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ የስልጣን ወምበርን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ወዲህ የትግራይን ህዝብ ከሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ የመነጣጠልና እርስ በርስም ጥላቻ እንዲፈጠር በማድረግ ስራ ተጠምዶ እንደቆየ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ አይዘነጋም።
ይህ የመከፋፈል አባዜ የተጠናወተው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ አሁንም፣ ይህን ርካሽ ስልቱን በመጠቀምና የትግራይ ተወላጆችን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ነጥሎ በማውጣት እስካፍንጫቸው የታጠቁና በወታደራዊ ስልጠናም ብቃት ያላቸው በመሆኑ እስከደም ጠብታ ይፋለማሉ በማለት መርዘኛ ፕሮፓጋንዳውን መንዛቱን ቀጥሉአል።

ህወሃትን ፈጣሪም ሰውም ተፀይፎታል !


ህወሃት ጭካኔውን እንደ ጀግንነት፤ ድንቁርናውን እንደ እውቀት ቆጥሮት እኔ ብቻ ጀግና! እኔ ብቻ አዋቂ! ብሎ በትዕቢት አብጦ በማን አለበኝነት ታብዮ የኖረ ዘረኛ ቡድን ነው። የዚህ ቡድን ትዕቢት ልክና ወሰን የለውም። የትዕቢታቸው መገለጫም ብዙ ነው።”እኛ ከሌለን ኢትዮጵያን እንበትናታለን ብለው የሚዘባትሉትን ማስታወስ ብቻ በቂ ነው። ይሄ የጨካኞች መገለጫ እንጂ የጀግና ጠባይ አይደለም። ጀግና አገር ይገነባል እንጂ አገር አይበትንም። ጀግና ለአገሩ አንድነትና ለህዝቡ ክብር ይዋደቃል እንጂ እኔ ከሌለው አገሪቷን አፈርሳታለው ብሎ አይዘባትልም። ህወሃቶች ከትእቢታቻው ላይ በወንድማማቾች መካከል ጥላቻን የመዝራት የረከሰ ስብዕናቸው ታክሎበት በሰውና በፈጣሪ ፊት የተጠሉ እንዲሆኑ ሁነዋል።መጽሃፍ ቅዱስም እግዚአብሄር ትዕቢተኞችን ይቃወማል በወንድማማቾች መካከል ጥላቻ የሚዘራውንም ነፍሱ አጥብቃ ትፀየፈዋለች ይላል። ህወሃቶች የሚገለጹት በዚህ መልኩ ነው።ከዚህ ሌላ መልክ የላቸውም።
በእነዚህ በሰውና በፈጣሪ ፊት በተናቁና በተጠሉ ቡድኖች አማካኝነት በኢትዮጵያችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም። አዎን በደል አይረሳም። በህወቶች የተፈፀመው በደል የማንረሳው የታሪካችን ህያው አካል ነው።ህወሃቶች በአገራችን ላይ የፈፀሙትን በደል ያላካተተ የኢትዮጵያ ታሪክ ጎዶሎ ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ መጥፎ ገጽታዋ መገለጫ ነው።
የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ! አገራችን እንዲህ ያለ መከራ ውስጥ የገባችው በህወሃቶች ክፋት ብቻ አይደለም፤ የእነርሱን ክፋት እያዩ ዝም በሚሉ ቅን ዜጎችም ጭምር ነው። ከሃያ ዓመት በላይ ፈረጀ ብዙ የሆኑ ግፎችን ተሸክመን ዝም በማለታችን አህያ” ተብለን ተሰደብን እንጂ ያተርፍነው በጎ ነገር የለም። ዝም ማለት የህወሃቶችን እድሜ አራዝሞ ብዙሃኑ ጥቂቶችን ተሸክመው፤ ጥቂቶቹም ብዙሃኑን ተጭነው የሚኖሩባት አገር እንድትሆን ከማገዝ በቀር ለነፃነታችን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የለም። እኛ ከአያት ቅደም አያቶቻችን የወረሰነውን በነፃነት የመኖር ልማድን ለዘረኞች አሳልፈን ሰጥተን ዝም የምንል አልባሌ ሰዎች ልንሆን አይገባም። የህወሃቶችን ግፍና በደል ተሸክመን እንኖር ዘንድ እኛ እርግማን ያለብንም ዜጎች አይደለንም።
ህወሃት ማለት በአገራችን ላይ የተተከለ መርገምት ማለት ነው።የመርገምትነቱም መገለጫ በዜጎች መካከል መለያየትንና አለመተማመንን ማስፈኑ፤ በሃይማኖቶች መካከልም እየገባ ግጭት ፈጥሮ የንጹሃን ደም በከንቱ እንዲፈስ ማድረጉ፤ንጹሃን ዜጎችን በሃሰት ከሶ ምናምንቴ ግለሰቦችን ምስክር አቁሞ የእድሜ ልክ እስራትና የሞት ፍርድ ፈርዶ ዜጎችን ማሰቃየቱ ጥቂቶቹ የመርገምትነቱ መገለጫዎች ናቸው። እርግጥ ነው ይህን እርግማን ተሸክመው ለመኖር የማይጎረብጣቸው እና የሂሊና ጥያቄ የሌለባቸው ደካማ ግለሰቦች ይኖራሉ። እነዚህ ትርፍራፊ ለቃቀመው ሆዳቸውን ከሞሉ፤ ጭላጭ አግኝተው ከተጎነጩ ሁሉም ሰላም ነው የሚሉ ሰው የመሆን ነገራቸውን ረስተው፤ ራሳቸውን አራት እግር ካላቸው አሳሞችና ፈረሶች ጋር ማመሳሰልን የመረጡ ናቸው። ይህ ምርጫ ግን ትክክል አይደለም። ይህም በራሱ ሌላ መርገምት ነው። ትግል የሚያስፈልገውም እንደነዚህ ዓይነቶቹ ራሳቸውን ከሰው ተራ ያወረዱትን ሰው ወደመሆን ደረጃ ከፍ ብለው እንደ ሰው እንዲያስቡ ለማደረግም ጭምር ነው።
እንግዲህ ለራሱ ክብር የሚሰጥ ዜጋ ይህን መርገምት ተሸክሞ ለመኖር እሺ አይልም። እንዲያውም መርገምቱን ከሥሩ ነቅሎ ወዲያ ለመጣል በሚደረገው ትግል ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊም መሪም ይሆናል። ይህን መርገምት መዋጋት ግዜው የሚጠይቀው የቅን ዜጎች የሞራል ግዴታ ነው። በሌላ በኩል ህወሃትን እንደ መንግስት አይቶ ትዕዛዙን ለመቀበል እሺ ማለት ዘረኝነትንና ግፍን በጣም ጥሩ አድርጎ ማጠናከር ነው። ህወሃትን ለመሰለ ዘረኛ እና ዘራፊ ቡድን መታዘዝ ማለት የዘረኝነቱና የጥፋቱ ተባባሪ መሆን ማለት ነው። ማንኛውም መልካም ሰው ዘረኝነትንና ግፍን በሙሉ እስትንፋሱ የመቃወም የሞራል ግዴታ አለበት። ህወሃትን ሰው ብቻ ሳይሆን ፈጣሪም ተፀይፎታል።ፈጣሪ የተፀየፈውን አለመፀየፍ ከጥሩ ሰው ተርታ የሚያስቆም አይደለም።
በህወሃቶች አማካኝነት የብዙ ንጹሃን ዜጎች ደም በከንቱ ፈሷል። በእነዚህ ዘረኞች አማካኝነት አማሮች ናችሁ ተብለው ከኖሩበት ተነቅለው ወደ አገራችሁ ሂዱ ተብለው ሜዳ ላይ የተበተኑ ዜጎች ብዙ ናቸው። በኢትዮጵያችን ውስጥ ከታች እስከ ላይ እርከን ያሉ የመንግስት ስልጣኖች በሙሉ መሃይማን በሆኑ ህወሃቶች ተይዟል። በህወሃቶች አማካኝነት በጋምቤላ እና በኦጋዴን  የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል፤በእነዚህ ቡድኖች አማካኝነት ከድሆች ጉሮሮ ተነጥቆ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ በውጭ አገር ባንኮች ውስጥ ተደብቋል። እንግዲህ እንዲህ ዓይነቶቹን የዘመኑ መርገምቶችን በሙሉ እስትንፋስ ለመቃወም አለመነሳት አሳፋሪ ነው።
በእነዚህ ዘረኞች አማካኝነት ሲፈፅሙ የኖሩ በደሎችን መቃወም የወቅቱ ትክክለኛ ተግባር ነው። ከሰሞኑ የግንቦት ሰባት ኃይል የሚባል ቡድን ካሁን ወዲያ ልቅሶው ያብቃ፤ የሚሰደዱ በአገራቸው ረግተው በሰላም ይኑሩ፤ ወጣቱ ተምሮ ድንጋይ ፈላጭ አይሁን፤ ዜጎች በብሄራቸው ብቻ ተለይተው ከኖሩበት ቀየ ተነቅለው ሜዳ ላይ አይጣሉ፤ በልማት ስም ዜጎች መድረሻ አይጡ ብለው ጋሻና ጦራቸውን አንስተዋል። የግንቦት ሰባት ንቅናቄም አገራችን ላይ የተተከለውን ህወሃት የተባለ መርገምት ነቅሎ ለመጣል በሚደረገው ትግል ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል። ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያችን ውስጥ ታሪካዊ እለት ነች። ኢትዮጵያዊያን በድምፃቸው መንግስታቸውን መምረጥ የሚችሉ መሆናቸውን ያሳዩበት እና የነፃነት ጎህ የፈንጠቀበት ዕለት ግንቦት ሰባት ነበረች። በሌላ በኩልም ግንቦት ሰባት ቃየላዊያን የብዙ አቤሎችን ደም ሊያፈሱ የተማማሉበት ዕለትም ነች። በዚህች ዕለት በተሴረው ሴራ የፈሰሰው ደም፤የወረደው እንባ፤ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው ግፍ ትግላችንን ለመሰብሰብ በቂ ምክንያት ነው። ከዚያም ከዚህም ተጠራርቶ በዚህች እለት ዙሪያ ተሰባስቦ ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ ማካሄድ ግዜው የሚጠይቀው የትግል ስልት በመሆኑ ከሰሞኑ የግንቦት ሰባት ህዛባዊ ኃይል ያስተላለፍውን ጥሪ ንቅናቄያችን አድንቆ ተቀብሎታል።
ህወሃቶች ከሃያ ዓመት በላይ አገሪቷን ሰባብረዋል፤ዜጎችን አዋርደዋል። ይሄን ሁሉ ዘመን ከዛሬ ነገ ይሻላሉ፤ ከዛሬ ነገ እንደ ሰው ልጅ ማሰብ ይጀምራሉ፤ ከዛሬ ነገ ከስህተታቸው ተምረው ይመለሳሉ በሚል እሳቤ ታግሰናል። እነርሱ ግን ትዕግስታችንን እንደ ፍርሃት፤ አርቆ አስተዋይነታችንንም እንደ ሞኝነት ቆጥረው የጭካኔ እጃቸውን ከጫንቃችን ላይ ለማንሳት እምቢ ብለው ቆይተዋል። ይሄ ግን ማብቃት አለበት።ማብቃት አለበት ስንል ደግሞ በማንኛውም መንገድ እየሄድን፤ እየወደቅንና እየተነሳን አስቸጋሪውን ጉዞ በአጭር ግዜ ጨርሰን ነፃነታችንን ለማወጅ የሚከፈለውን መሥዋእትነት ለመክፈል ዝግጁዎች መሆናችንን እያሳወቅን ነው።
የተከበራችሁ ወገኖቻችን! ኢትዮጵያችን የምትዋረደው ህወሃቶች በሚፈፅሙት ግፍ ብቻ አይደለም፤ የሚፈፀመውን ግፍ እያዩ ዝም በሚሉ ቅን ዜጎችም ጭምር ነው። ህወሃት የሰው ልጅ ይቅርና ፈጣሪ የተፀየፈው ቡድን ነው። ፈጣሪ የተፀየፈውን ትፀየፉት ዘንድ ግዜው ደርሷል፤ ዝምታው ይብቃ፤ፍርሃቱም ይሰበር። ዛሬውኑ ትግሉን ተቀላቀሉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

Total Pageviews

Translate