Pages

Jan 9, 2013


‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ብቻ ነኝ››ሲል የአንድነት ፓርቲ አመራሩ አንዷለም አራጌ ገለጸ

ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አንዷለም ይህን ያለው፤የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ እንዲጠይቁት የተፈቀደላቸው የ አንድነት አመራሮች በቃሊቲ ተገኝተው በጎበኙት ጊዜ ነው።

ወጣቱ ፖለቲከኛ በዚሁ ጊዜ ቃሊቲ ለተገኙት  የአንድነት አመራሮች ፦”በፍቅርና በመተሳሰብ የምንኖርባት ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች”በማለት ህያው ራዕዩንና ውስጣዊ ምኞቱን ገልጾላቸዋል።

ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ተመስጌን ዘውዴ፣ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን፣ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና አቶ  ሙላት ጣሰው እና ከአስር በላይ የሚሆኑ አባላትም በመገኘት የአንዷለም የጤና ሁኔታና የእስር አያያዝ ምን እንደሚመስል ጠይቀዋል፡፡

አቶ አንዷለም በበኩሉ ከራሱ ይልቅ የገዥው ፓርቲ አፈናና ጭቆና እንዲሁም በዚህ ሁኔታ እየታገሉ ያሉ ባልደረቦቹ ጉዳይ እንደሚያሳስበው ገልጦ፤ በእሱ በኩል እንደቀረበበት ክስ በማንም ላይ በክፋት ባለመነሳቱ የህሊና ሰላም እንደሚሰማው ተናግሯል፡፡
አሁንም ኢትዮጵያና ፖለቲከኞቿ ስለፍቅርና መተሳሰብ ሊገባቸው አለመቻሉና በፍቅር ተሳስቦ መኖር የሚባለውን  መፍራታቸው ክፉኛ እንደሚያሳስበው ተናግሯል፡፡

በተያያዘም በቃሊቲ ከሚገኙ እስረኞች በተለየ ሁኔታ   በጠባብ ክፍል የታሰረና እንደማንኛውም እስረኛ ዘመድ አዝማድና ጓደኛ እንዳይጠይቀው የተደረገ ብቸኛ ታሳሪ መሆኑን በማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ፊት ለፊት ተናግሯል፡፡

<<ለእኛ ቀርቶብን ለልጆቻችን እንኳን የተሻለ ማረሚያ ቤት ማስተላለፍ አለብን>> ያለው አንዷለም፤በተለየ መልኩ  እሱ ላይ ብቻ ያነጣጠረው የመብት ገፈፋ ተገቢ እንዳልሆነ  ፊት ለፊት ገልጧል፡፡
በዚህ ሃቅ የተበሳጩት ማረሚያ ቤቱ ኃላፊ፦ ‹‹ተነስ ግባ!› የሚል ዘለፋ የአንድነት አመራር አባላት በተገኙበት ፊት በብስጭት ተናግረዋል፡፡
የአንድነት አመራርና አባላትም የተጀመረው ትግል ግቡን እስኪመታና በፍቅርና መተሳሰብ የምንኖርባት ኢትዮጵያ እስከምትፈጠር ከትግሉ ሜዳ እንደማያፈገፍጉ  ለአንዷለም አረጋግጠውለታል፡፡

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ብዙ ተማሪዎች መደብደባቸውና መታሰራቸው ታውቀ


ኢሳት ዜና:-ታህሳስ 29 ቀን 2005 ዓም  በእራት ሰአት ላይ በድሬዳዊ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተን ረብሻ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥራቸው የበዛ ተማሪዎችን ደብድበዋል፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎችን ደግሞ ይዘው አስረዋል።ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
እስከ ምሽት የዘለቀውን ይህንኑ የፖሊሶች  ድብደባ መቋቋም ያቃታቸው ተማሪዎች በምሽት  ግቢያቸውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን  ያመለከተው ዘጋቢያችን፤   የሚያድሩበት ቦታ  በማጣታቸው በቤተክርስቲያኖች እና ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ወደ መስጊድ ሄደው መጠለላቸው ታውቋል።
ፖሊሶቹ በምሽት  ክፍላቸው ዉስጥ ተደብቀው የቀሩ ተማሪዎች ይኖራሉ በማለት  ዶርም ለዶርም አሰሳ ሲያደርጉ ማምሸታቸውን  የጠቀሰው ወኪላችን፤በ አሰሳው  ዶርም ውስጥ ተሸሽገው የተገኙ ተማሪዎች ሲደበደቡ ማምሸታቸውን አጋልጧል።
አብዛኞቹ ተማሪዎች  ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የተደረገው  እራታቸውን  ሳይበሉና  ልብሳቸዉን ሳይወስዱ  ባዶ እጃቸዉን   እንደሆነ  ከወኪላችን ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።
የችግሩ መንስኤ ለተማሪዎች ከሚቀርበው ምግብ ጋር የተያያዘ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። ተማሪዎቹ የተሻለ ምግብ ይዘጋጅልን በሚል ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች ወዲያውኑ ዩኒቨርስቲውን በመውረር በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽመዋል።
ዩኒቨርስቲው ዛሬ መጠነኛ መረጋጋት የታየበት ቢሆንም፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት አሁንም አካባቢውን ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ለማውቅ ተችሎአል።
ሰሞኑን በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል የተከሰተን የብሔር ግጭት ተከትሎ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ በርካታ ተማሪዎች እንደተጎዱና ከመቶ የሚበልጡ እንደታሰሩ መዘገቡ ይታወሳል።

የFBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ – በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው


ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን አንድ የአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (FBI) ግበረሃል ባለፈው ወር መባቻ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደ ቦስተን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተጓዘበት ወቅት የግድያ ወንጀል ለመፈጸም በመዶለትና በማስተባበር ተግባር ላይ ተሰማርቶ የነበረና ለህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሰልል የሚጠረጠር ግለሰብ እና በግብረአበሮቹ ላይ ከፍተኛ ምርመራ መክፈቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጡ።ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
በአሜሪካ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖረውና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ የዘር ድርጅት አባል እና ሰላይ እንደሆነ የሚታመነው ግኡሽ አበራ በመባል የሚጠራው ይሄው ግለሰብ ጋዜጠኛውን ለመግደል በማሴር ሶስት የወንጀሉ ተባባሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን  መመልመሉ ንና ድርጊቱን ለመፈጸም መሰናዶ ማድረጉን የFBI መሪማሪዎች  ደርሰውበት ሴራውን በግዜ ማክሸፋቸው ተረጋግጧል።
ግለሰቡ ወንጀሉን ከመፈጸሙ በፊት የተለዋወጣቸው መልእክቶች የFBI ወንጀል መርማሪዎች እጅ በመግባታቸው ሳቢያ እርሱና አብረው የሚኖሩ ሌሎች አራት ግለሰቦች ላይ ክትትልና ምረመራ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። ከተባባሪዎቹ ጋር  የተለዋወጣቸው መልእክቶች ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደቦስተን የመሄዱን አጋጣሚ በመጠቀም በመሳሪያ ተኩሶ የመግደል እቅድ አውጥቶ ድርጊቱን ለመፈጸም ወይንም ለማስፈጸም ይንቀሳቀስ እንደነበር በግልጽ እንደሚያሳዩ ታውቋል።
የቦስተን ቅርንጫፍ FBI ቃል አቀባይ እና ልዩ መርማሪ ( special agent) የሆኑት ግሬግ ኮምኮዊች በምርመራው ሂደት  ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠቡም፣ FBI እንዲህ አይነት ወንጀሎችን በ ቸልታ እንደማያልፍ ገልጸው በውጭ መንግስታት ሰላዮችም ሆነ ተወካዮች የሌሎችን ሰብአዊ መብቶችን በሚገፍ ህገወጥ ወንጀል የተሰማሩ ካሉ ኢትዮጵያዊያን በቸልታ ማልፍ እንደማይገባቸው እና በአካባቢያቸው ለሚገኙ የFBI  ቅርንጫፎች ጥቆማ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል። መርማሪው አክለውም FBI እንዲህ አይነቱን ጥቆማ በአግባቡ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸዋል። “
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመተቸት የሚታወቁት የጄኖሳይድ ወች ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ግሪጎሪ ስታንተን የግድያ ሴራውን ያከሸፉትን የFBI መርማሪዎች አድንቀው ፣ ህወሃት አሸባሪ ድርጅት መሆኑ ታውቆ ከኢትዮጵያ አልፎ በአሜሪካን ሀገር እንዲህ አይነት ወንጀል ሊፈጽም መንቀሳቀሱ በችልታ አይታይም ብለዋል።
በካምቦድያ በሰው ልጆች ላይ አስከፊ ሰቆቃና ጭፍጨፋ የፈጸሙ የካሜሩዥ ባለስልጣናትን ለፍርድ በማቅረብ አለማቀፍ እወቅና ያገኙት ፕሮፌሰር ስታንተን እንዲህ አይነቱ ወንጀል ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
ግኡሽ አበራን በቅርብ የሚያውቅ አንድ ኢትዮጵያዊ የቦስተን ነዋሪ፣ ግለሰቡ ከከፍተኛ የህወሃት ባልስልጣናት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለውና የቀድሞው አምባገነን መሪ የመለስ ዜናዊ አምላኪ እንደነበር፣ የእርሱ መዋረድና መሞት በጣም ካበሳጫቸው በአሜሪካ የሚኖሩ በርካታ የህወሃት ጀሌዎች አንዱ መሆኑን ገልጿል። በማከልም “ከሁሉ የከፋው ግለሰቡ በዘረኝነት ዛር የተለከፈ ስለሆነ ህወሃቶች እንዲህ አይነቱን ሰው ለእኩይ አላማቸው መጠቀማቸው የተለመደ ነው፣”  በማለት አስረድቷል::
ጋዜጠኛ አበበ ገላው “ህወሃት አሸባሪ የማፊያ ድርጅት መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የነበሩብኝን የጽጥታ ስጋቶች ችላ ባለማለት ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት ከማመልከት አልፌ የቤተሰቤንም ሆነ የራሴን ደህንነት ለማረጋገጥ ቀደም ብዬ እርምጃ ወስጃለሁ ወደ ፊትም እወስዳለሁ” ብሏል።
የFBI መርማሪዎች ወንጀሉ እንዳይፈጸም አስቀድመው እርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ቦስተን ውስጥ ሮክስቤሪ በመባል በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን እና ግኡሽ አበራ ከሌሎች አራት ኢትዮጵያዊን ጋር በጋራ ይሚኖርበትን ቤት የበረበሩ ሲሆን፣  ወደ ሁለቱ የቤቱ ነዋሪዎች ስራ ቦታ ድረስ በመሄድ ምርመራ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።

Jan 8, 2013

ባለሀብቶች ለኢህአዴግ ጽ/ቤት ግንባታ ቃል የገቡትን ገንዘብ ሊሰጡ አልቻሉም ተባለ


ባለሀብቶች ለኢህአዴግ ጽ/ቤት ግንባታ ቃል የገቡትን ገንዘብ ሊሰጡ አልቻሉም ተባለ


ኢሳት ዜና:-በዚህም ምክንያት  የግንባሩ ጽህፈት ቤት ግንባታ መስተጓጎሉን ሪፖርተር ዘግቧል።ታህሳስ  ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ጋዜጣው እንዳለው ከአራት ዓመት በፊት ኢሕአዴግ ሰባት ፎቅ ከፍታ ያለው ሕንፃና ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰንዳፋ ከተማ የካድሬዎች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለመገንባት ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡
አራት ኪሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አካባቢ ይገነባል የተባለው የኢሕአዴግ ፖለቲካ የሚቀመርበት ዋና መሥርያ ቤት ሕንፃ ግንባታ ቢስተጓጎልም፣ እስካሁን ድረስ በተገኘው ገንዘብ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር በሚወስደው መንገድ ላይ በኦሮሚያ ክልል ሱሉልታ ከተማ የካድሬዎች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት እየተገነባ ይገኛል፡፡
በወቅቱ ለ እነዚህ ግንባታዎች 130 ሚሊዮን ብር እንደሚፈልግ የተገለፀ ሲሆን፤ የግንባታዎቹን ዲዛይን በነፃ የሠሩት ኤምኤች ኢንጂነሪንግና አልቲሜት ፕላን ኩባንያዎች ናቸው፡፡
ያንንም ተከትሎ  የአገሪቱ ታላላቅ ባለሀብቶች  ፕሮጀክቱን ፋይናንስ ለማድረግ መንቀሳቀሳቸውና ቃል ገብተው እንደነበር ተመልክቷል።
በአስመጪና ላኪ ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ፣ በኮንስትራክሽንና በሌሎች ዘርፎች   የተሰማሩ ባለሀብቶች እያንዳንዳቸው ከመቶ ሺሕ ብር እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ ለመለገስ ነበር ቃል የገቡት፡፡
ይሁንና  ከአራት ዓመት በኋላ ከባለሀብቶቹ መካከል የተወሰኑት ቃል የገቡትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ አላስገቡም ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በመጪው መጋቢት ወር በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢሕአዴግ ዘጠነኛው ጉባዔ ላይ በእነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሪፖርት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱንም ግንባታዎች በአንድ ወቅት ለማስጀመር ዕቅድ ይዞ የነበረው ኢሕአዴግ፣ ሙሉ ለሙሉ ገንዘቡን ባለማግኘቱ ባገኘው ገንዘብ የካድሬዎች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ላይ ብቻ ትኩረት ለማድረግ መገደዱንም  ምንጮቹ ጨምረው  ገልጸዋል፡፡
ይህ ትምህርት ቤት ቀደም ሲል በሰንዳፋ -በኬ ከተማ እንደሚገነባ የተያዘው  ዕቅድ ተሰርዞ ነው በሱልሉታ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው፡፡

ESAT Ethiopia Breaking News 08 01 13

ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታስረዋል ተባለ


ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታስረዋል ተባለ


ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከስቶ የነበረውን የብሄር ግጭት ተከትሎ ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታሰራቸውን  የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ታስረዋል ያላቸውን የ99 ተማሪዎች ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አብዛኞቹ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ጠቁሟል።
ከታሰሩት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የኦሮሞ ተወላጆች ቢሆንም፣ የአማራና የትግራይ ተማሪዎችም ይገኙበታል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይንስ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረው ብሄር ተኮር ግጭት መንግስት ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት በባህርዳር ከተማ የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ተረጋግጧል በማለት በእየአመቱ የሚያከብረውን የብሄረሰቦች ቀን ባከበረ ወር ባልሞላው ጊዜ ውስጥ የተፈጠረ ነው።

የወያኔ የፖሊስ እና የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሌቦችን በማስተባበር ወንጀል ሲፈጽሙ የሚያመለክት ማህደር


ጌታቸዉ ረዳ / December 17, 2008
የወያኔ የፖሊስ እና የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሌቦችን በማስተባበር ወንጀል ሲፈጽሙ የሚያመለክት ማህደር
ከጥቂት ዓመታት በፊት የመቶአለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የተባሉ በወያኔዉ መንግስት በፖሊስ ሰራዊት የመቶአለቅነት ማዕረግ የነበራቸዉ በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ 21 ፖሊስ ሹም እና የምርመራዉ ክፍል ሹም በመሆን አገራቸዉን በቀና ለማገልገል በሙያቸዉ ተሰልፈዉ እንደነበር እና የሗላ-ሗላ ግን የወያኔ ባለስልጣኖች በጎሰኝነት እና በዘረፋ በተራ ስርቆት ሌቦችን አሰማርተዉ ሕዘቡን ሲያሸብሩ እና ሰላም ሲነሱ በመታዘባቸዉ እና በምርመራዉም ላይ ግምባር ቀደም ሚና በ አካልም ዘራፊዎቹ እና አስዘራፊዎቹን የሚያሰማሩ አንዳንድ የደህንነት እና የፖሊስ ከፍተኛ ባለስለጣኖችን ሰለ ፍትሕ እና ስለተማሩበት ሙያ ሲሉ በሙያቸዉ ጸንተዉ ሲጋፈጧቸ እና እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሌቦችን እየለቁቁ ካለ ቦታቸዉ ጣልቃ እየገቡ አላሰራም ስላሏቸዉ የነበራቸዉን ስራ እና የሚወዷት አገራቸዉ እና ቤተሳባቸዉን ጥለዉ ወደ ስደት በማምራት የሻዕቢያ ራዲዮ አሳቸዉን አፈላልጎ ከአዉሮጳ የስልክ ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዉ እንደነበር ይታዋሳል። መኮንኑ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ እና ያጋለጡት ምስጢራዊ ሰነዶችን በዚህ ለናንተ “ከወያኔዎች የገበና ማሕደር” ርዕስ ቀርቧል።
“ምናልባትም ካልተሳሳትኩ” የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን- አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በየትኛዉ የ አርበኞች ግምባር ጦር መሆናቸዉን አላዉቅም እንጂ በኤርትራ መንግስት ሲደገፉት ከነበሩት የአርበኞች ግምባር በአንደኛቸዉ ዉስጥ መሰለፋቸዉ ትዝ ይለኛል። ጽሁፋቸዉም በየትናዉ የህዋ ሰሌዳ እነደሆነ ትዝ አይለኝም እነጂ ስለ ግምባሮቹን በሚመለከት ስለ አንድነት እና መተባበር የጻፉት የ አማርኛ ጽሑፍ አንብቤአለሁ። ምናልባትም ይህ ዝግጅት ማንበብ ከቻሉ በ እኔ እና በ ኢትዮጵያን ሰማይ ዳት ብሎግ ሰፖት.ካም (Ethiopiansemay.blogspot.com) አንባቢዎቼ ስም ከፍተና ምስጋናን አቀርባሉ። ባሉበት ምድ እና ትግልም ተቃና ኢትዮጵያዊ ግዳጅዎ እንዲቃና እመኝለዎታለሁ።አምላክ ከ እርስዎ እና መላ ቤተሰቦ በሰላም ይጠብቀዎት እአልኩ በቀጥታ ወደ ቃለ መጠይቁ ማህደር ወደ ወያኔ የስረቆት እና ዝርፊያ ገበና እናምራ።
በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳዉ ምርመራ ሹም እነደነበሩ እና የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሌቦችን በቡድን እና በግለሰብ በማሰማራት በዘረፋ ስራ እንደተሰማሩና የሚዘርፉበትም መሳሪያ በ ባለስልታኖች ስም ተመዘገበ ማሳሪያ እነደነበር በምርመራዉ እንደረሱበት እና ሌሎች ዝርዝር ታሪኮችን ያጋለጡበት አነሆ፡-
የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን
“በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 21 የፖሊስ ምርመራ ክፍል ሹም እንደመኖሬ መጠን በዛች ወረዳ ብቻ የተፈጸሙትን እኔ የተከታተልኳቸዉ መንግስታዊ ወንጀሎችን ነዉ በማስረጃ አስደግፌ ማቀርበዉ። ካገሬ ብወጣ እና በሰደድም ፖሊስ እንደመሆኔ መጠን ሙያየም ስለሚያስገድደኝ ከሕግ ዉጭ የተፈጸሙ መንግስታዊ ደባዎችን ህዝቡን የማስረዳት ግዴታ አለብኝ።
ለምሳሌ ብጠቅስ፣ በወረዳ 21 ቀበሌ 01 ሳህለስላሴ ህንጻ የሚባል አንድ ህነጻ አለ። ህንጻዉ ዉስጥ “ኢሰመጉ” የሚባል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅት ጽ/ቤት የነበረበት ነዉ።የጽ/ቤቱ በር ተሰብሮ ተዘረፈ።የተሰረቀዉ ምነድ ነዉ!ሰነዶች፤ፋይሎች መጽሐፍቶች እና የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶች ናቸዉ ተሰረቁት።በመሰረቱ ቢሮዉን እንዲዘረፍ የተፈለገበት ምክንያት ሰነዶችን ለመዉሰድ ነበር። እኔ በዛዉ ወቅት የወረዳዉ ሸም ስለነበርኩ፤በአካባቢዉ የተፈጸሙ የወንጀል ድረጊቶችና ፈጻሚዉን ተከታትሎ ወደ ሕግ ማቅረብ ሃለፊነት አለብኝ። ኢሕአዴግ አይደልም ይህነን ሐላፊነት የሰጠኝ።አንደኛ የተማርኩበት ት/ቤት ኮርሴን አጠናቅቄ ስመረቅ ለእዉነት እና ለሕግ ተገዝቼ ሕዘቡን ለማገልገል አስምሎ ነዉ ያስመረቀኝ።ሁለተኛ ሕገ መንግስቱ ራሱ ይህነን እንድከታተል ያስገድዳል።በዚህ መሰረት ክትትል በማድረግ ይሄነን ኢሰመጉን ቢሮ ሰብሮ የሰረቀዉን ሌባ፤ከሌሎች የስራ ባልደረቦቼ ጋር ሆኜ (አሁን ስማቸዉን ለመትቀስ አልፈልግም) ከነሱ ጋር ሆነን ተከታትለን ነዉ ግለሰቡን የያዝነዉ “ኤርሚያስ መብራህቱ” ይባላል።
የኢሰመጉ ጽ/ቤት የያዘዉ የማመለክቻ ፋይል ከተለያዩ ቦታዎች ከደቡብ፤ ከአማራ፤ ከኦሮሚያ ክልል፤ ከትግሬ ክልል እንኳን ሳይቀር ወዘተ ያለ ሕግ ከስራ አባረሩኝ፤ ተደበደቡኩኝ ወዘተ የሚሉ ሰብአዊ ነክ ጉዳዮችን ለዚህ ለኢሰመጉ ቢሮ እሮሯቸዉን ያስገቡበት የግለሰቦች ማመልከቻ ነበር የተዘረፈዉ።የነሱ ፋይል ነዉ የተሰረቀዉ።ኤርሚያስ መብራቱ ፋይሎቹን ዘርፎ ለማን ይሰጠዋል፤ በዞን 2 የኢሕአዴግ ሐለፊ ሆኖ ብዙ መስሪያ ቤቶችን የሚቆጣጠር “ገብረ እግዚአብሔር” ሚባል ከፍተኛ ካድሬ አለ።ሰነዶቹን ለእረሱ ነዉ የሰጠዉ።
ገብረእግዚአብሔር … “ኤርሚያስ መብራህቱ” መያዛችንን ሲሰማ፤ ባስቸኳይ ምርመራዉ እንዲቆም ብሎ ነዉ ትዕዛዝ መመሪያ ለእኔ የሰጠኝ። አይ- ምረመራዉንም እማ አላቆምም! ምክንያቱም ወንጀል ተፈጽሟል።”ወንጀል ከተፈጸመ ደግሞ ፈጻመዉ ወደ ሕግ መቅረብ አለበት” የሚል መልስ በምሰጥበት ሰዓት፤ ከእኔ ጋር ሆኖ ሲሰራ የነበረ የጣቢያ አዛዥ አስጠንቅቀዉ (ለሱ ነበር ማስጠንቀቅአዉ የተሰጠዉ) መዝገቡን ወደ እኛ ባስቸኳይ ላክ ተባለ።መዝገቡ ወደ ክልል እንዲላክ ተደረገ። አሁን በዚህ ሰዓት ላይ እዛዉ ከኔዉ ጋር ሲሰሩ ነበሩ የክፍል ሃላፊዎች አሉ፡አነዚህ በቀጥታ መዝገቡን አንሰጥም ማለት ይችላሉ። ይህ አቋም ከያዙ ደግሞ በቀጥታ ከኢሕአዴግ ጋር ተጋጩ ማለት ነዉ።ምክንያቱም ወንጀሉን የፈጸመዉ ኢሕአዴግ ነዉ (ኤርሚያስ መብራህቱ ነዉ)። ኤርሚያስ መብራህቱ ቃሉን ሲገልጽ ምነድ ነዉ ያለዉ_”ገብረእግዚአብሔር ነዉ ሂድ ስረቅ ያለኝ። ሂድ እና መዝገቦቹን ሰርቀህ አምጣ ያለኝ ምክንያት እኔ ሌባ መሆኔን ያዉቃል።እንዲያዉም ይረዳኛል።መዝገቦቹን ብቻ ስጠን ብሎ መዝገቡን ስጥቼዋለሁ” አለን። የግድግዳ ሰዓቶችን እና ሌላ ሌላ የተዘረፉት ንብረቶች ግን ሄዶ ከመረካቶ ነዉ የሸጠዉ።የሸጠዉን ዕቃ ደግሞ አስመልሰን በእግዚቢት ይዘነዋል።
ጥያቄ፦ የመቶ አለቃ አሁን እርሰዎ ያሉት ያሉት ፤ወያኔ ገንዘብ እየከፈለ ወንጀል ያስፈጽማል ነዉ የሚሉት ።ልከ ነዉ?
የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን- በሚገባ እንጂ! ይሄ ኤርሚያስ መብራሕቱ የምልህ ከወላጅ አባቱ ጋር ተጣልቶ የወጣ ስርዓተ አልበኛ ዱርየ ነዉ።የሚኖረዉ በመስረቅ ነዉ። አበዛኛዉ በዋናነት የቅርብ ጓደነኝቱ ግን ገብረ እግዚአብሔር ካልኩህ ጋር ነዉ። የሚያመሹትም ሚዉሉትም አበረዉ ከገብረእግዚአብሔር ጋር ነዉ።ገብረእዝግዚአብሄር ማለት ደግሞ በዞን ሁለት የኢህአዴግ ባለስልጣን ነዉ።የዞን አስተዳደር፤የዞን የትምህርት የጤና ወዘተ በዉስጡ ብዙ ዘርፍ የያዘ ክፍል ነዉ። ጠቅላላ ኢህአዴግን ወክሎ በእነዚህ እና በመሳሰሉት ሕዝባዊ ነክ ዘርፎች የሚቆጣጠረዉ ይህ ክፍል ነዉ።ይህ ክፍል ደግሞ የሚቆጣጠረዉ “ግብረእግዚአብሔር” ነዉ። ስለዚህ ሂድ እና ይሄነን ተግባር ፈጽም እያለ የሚያዘዉ “ገብረእግዚአብሄር፡ ነዉ።ይህ ልጅ ፍላጎቱ በመሰረቱ የሚሸጥ ነገር መስረቅ ነዉ። ምክንያቱም “ኢሰመጉ” ቦሮ ዉስጥ ገብቶ “ሰነዶችን” ሰርቆ ልሽጥ ቢል ማንም አይገዛዉም።ገንዘብ የሚያስገኝለትን ስርቆት እና ዕቃ አጥንቶ ነዉ የሚሰርቀዉ። አነጋግረነዋል።በሚገባ እንዲሰርቅ ማን እንዳዘዘዉ ግልጹን ነግሮናል። ይህነን የወረዳ 21 መርማሪ ፖሊሶች በሚገባ ያዉቁታል።የሰጠዉም ቃል በወረዳዉ ዕለት ሁኔታ መዝገብ ተመዝግቦ ይገኛል። ኢሕአዴግ ብቃቱ እና ሞራሉ ካለዉ እና ልከታተለዉ ካለ ‘እዛዉ ሄዶ መዝገቡን ማየት ይችላል፤ ዉሸት ከሆነ። ስለዚህ ኢህአዴግ የሚያሰማራቸዉ ወንጀለኞች አሉ።
ሌላዉ ልጥቀስ። አንድ የቀድሞ ሰራዊት አባል በሻምበልነት ማዕረግ የነበረ፤በወረዳ 21 ቀበሌ 22 እና 24 መካከል ስሙን ዘንግቼዋለሁ ማዕረጉን ነዉ የማስታዉሰዉ (ማስታወሳን ስለወሰዱብኝ)።
ጥያቄ፡- ማነዉ መስታወሻዎን የወሰደበዎት? የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን- ኢሕአዴግ።ቤቴን ሰብረዉ ስኖርባት ነበረችዉን አንዲት ክፈል እኔ በሌለሁበት ሰብረዉ ማስታወሻዎቼን ወሰዱት። ይህ ድረጊት የፈጸመዉ “ጀማል” የሚባል መጀመሪያ የአዲስ አበባ የደህንነት ሃለፊ የነበረ በሗላ ደግሞ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል እና መርመራ ክፍል ሹም የነበረ፤- እሱ ነዉ ማስታወሻ ሰነዶቼን በሙሉ የወሰዳቸዉ።
ጥያቄ፦ ይገርማል! በዚህ ጉዳይ ወደ ሗላ እንመለስበታለን እና ስለ ሻምበሉ ጉዳይ አስኪ ይቀጥሉ፦
..ሻምበሉ፤በድሮ ሰራዊት አባል ሰራዊት የነበረ ነዉ። በወረዳ 21 እና በቀበሌ 22 መካከል ከቀኑ ስድት ሰዓት አካባቢ ክላሽ በታጠቀ ግለሰብ ተተኩሶበት ተገደለ።ይሄ ግለሰብ ተገድሎ፤ገዳዩ ሻምበሉን ገድሎ እየሮጠ ወዴት ነዉ የገባዉ (?) በወረዳ 21 ቀበሌ 04 “ገነት ሆቴል” የሚባል አንድ ሆቴል ፊት ለፊት ካለዉ የደህንነት ህንጻ ጸ/ቤት በቀጥታ ሮጦ ገባ። ሕዘቡ ተከተታትሎ ሪፖርት አደረገ። ከዛ እኛም ደረስን። ከዚያ በሗላ ደህንነት ጽ/ቤት አባሎችን በማነጋገር “ሰዉ ገድሎ ከእናንተዉ ቢሮ ዉስጥ ሸሽቶ አምልጦ ገብቶ የተደበቀ ሰዉ አለ እና ስጡን ወይንም እንግባ እና እንፈትሸዉ ብለን ስንል፡ “በቀጥታ ከዚህ ጥፉ!” ነዉ የተባልነዉ።
በሬድዮ “ልዩ ሃይል” ተጠርቶ በነሱ እንድንባረር ተደረገ። “ልዩ ሃይል” የሚባል አለ ስለ እሱ ወደ ሗላ አነሳዋለሁ። ልዩ ሃይል ማለት የሰዉን ጭንቅላት ለመቀጥቀጥ የተሰራ “መዶሻ” ነዉ ማለት ይቻላል። እና ከነሱ ጋር ተጋጭተን ስለነበረ ወዲያዉ ከክልሉ ፖሊስ -ፖሊስ ኮሚሽነር “ተስፋይ አብርሃ” በተባለ ግለሰብ ወደ መ/ቤታችን እንድንመለስ ትዕዛዝ ተሰጠን እናም ወደ ቢሮአችን ተመልሰን ሄድን። ወደ አካባቢዉ ስንሄድ የሰዉየዉ አስከሬን ወደ ሆስፒታል ተላከ።ከዚያ በሗላ በክልል ደረጃ ይጣራል ተባለ እና የሰዉየዉ አስከሬን በምኒሊክ ሆስፒታል ሃኪሞች እንዲመረመር ተደረገ። የነበረዉ መረጃ ወደ ክልል ስጡ ተባለ። እነ መቶአለቃ ተማም ኑር ከኔ ጋር ሲሰራ የነበረ ነዉ፦ ከላይ ክልል ደግሞ እነ መቶ አለቃ ዘላለም የሚባሉ በክለል ነብስ ግድያ ወንጀል ምርመራ ቡድን መሪ ነበሩ፤- ጉዳዩ እነሱ ሁሉ ያወቁታል።ሻምበሉ የተገደለዉ ከፖለቲካ ንክኪ ነዉ።የተገደለዉ ደግሞ በጠራራ ጸሐይ ነዉ። ገድሎት ወደ ደህንነት ገብቶ ገዳዩ ሳይጠየቅ ቀረ።
ሌላዉ የወንጀል ዓይነት ደግሞ ልንገርህ። ቡድን አደራጅቶ ወንጀልን የመፈጸም ድርጊታቸዉን ልግለጽ።
ለምሳሌ አንዴ “ጸሐየ” አንዴ “በየነ” አንዴ “እያሱ”፤አንዴ ገብረእግዚአብሔር አንዴ … በተለያዩ ስሞች የሚጠራ የ“ተስፋይ አብርሃ” የእህቱ ልጅ ነዉ።እሱ ነዉ ቡዱኑን የሚመራዉ።ተስፋይ አብርሃ በዛ ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊስ ፖሊስ ኮሚሽነር ነበር።በሗላ ደግሞ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ግጭት ሲፈጠር “ጌታቸዉ አሰፋ” (የማዕከላዊ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበረዉ) ወደ ጦሩ ሲሄድ የሱን ቦታ ተክቶ ሲሰራ የነበረዉ ነዉ። ተስፋይ አብርሃ የነጌታቸዉ አሰፋ፤የነክንፈ ገብረመድህን ቡድን ነዉ ‘ተስፋይ አብርሃ” ማለት። ተስፋይ አብርሃ የሚታወቀዉ “ተስፋይ አፍረሶም” በመባል የሚታወቀዉ ነዉ።ተስፋይ አፍረሶም ብለዉ በአብዛኛዉ የሚጠሩት “ተስፋይ አብርሃ” ማለት ነዉ። እንግዲህ “በየነ፤እያሱ…ወዘተ በሚል ስም የሚጠራዉ ለተስፋይ አብርሃ የ የእህቱ ልጅ ነዉ። በዚህ ግንኙነት በመሳሪያ ታጥቀዉ ሃብታም ነጋዴ ቤት ወይንም ድርጅቱ ድረስ ሄደዉ እያስፈራሩ “በደህንነት ትፈለጋለህ” “በፖሊስ ትፈለጋለህ” እያሉ እና ሚፈልጉዋቸዉን ሃብታሞች በመኪና ጠልፈዉ ይዟቸዉ ይሄዳሉ። ወያኔ ነጋዴ ስለሆነ የሚጫረቱትን ነጋዴዎች ማስፈራራት ማዋከብ ይፈልገዋል እና ነጋዴዎቹም ይህ ባህሪዉ ስለሚአዉቁት ነጋዴዎቹ ስጋት ላይ ናቸዉ። ሰዎቹ ወደ ንግድ ቦታቸዉ ወይንም ከሆነ ካገኙዋቸዉ ቦታ ተልፈዉ በመኪና ለምሳሌ ወደ ባምቢስ የድህንነት ቢሮ አለ ካዛንቺስ ዉስጥ “አንደር ግራዉንድ” አስርቤት ወዳለበት አንድ ድህንነት ኦፊስ አለ ወደ ማዕከላዊ እ…. ወደ ሜክሲኮ ወዳለዉ ልዪ ኦፊስ አለ …ወደ ተላያዩ ወደ እነዚህ ቦታዎች እየወሰዱ በማሳየት ያስፈራሯቸዋል።
ወደ እነዚህ ደህንነት ጽ/ቤቶች ይወስዱ እና አስፈራርተዉ በሺዎች ብር የሚቆጠር ገንዘብ እተቀበሉ ይለቋቸዋል።ለምሳሌ በኔ በ21 ወረዳ ልዩ ቦታዉ “ባክሻፍት” (?) ተብሎ በሚጠራ አጠገብ አንድ ህንዳዊ ዜጋ ነገዴ ነበር። ያ ሕንድ ነጋዴ በተከታታይ ወደ 60 ሺህ ብር በእነ “ጸሃየ” ተወስዶበታል።ይህ የምርመራ ወንጀል እኔ እና ባልደረቦቼ ደርሰንበታል።ይህ ወንጀል ስናዉቅ ሰዉየዉን ሄደን አነጋገርናቸዉ። እንደዚህ ዓይነት ወንጀል ተፈጽመዎበታል፤ ለምንድ ነዉ ወደ እኛ ድረስ መጥተዉ ወንጀሉን ያላመለከቱበት ምክንያት? ብለን ጠየቅናቸዉ። እንግዲህ ካሁን ወዲህ ወንጀለኞቹ እንደልማዳቸዉ ወደ እርስዎ ሲመጡ እኛኑን ወዲያዉኑ ይጥሩን አልናቸዉ። “ታስገድሉናላችሁ” አሉን። ግዴየለዎትም፣ ብለን ቃል ገባንላቸዉ። በመጨረሻ ኦኬ (እሺ) አሉ።
አሁንም ያ “ጸሃየ” የተባለዉ ሰዉየ ደወለላቸዉ።መደወሉን ለእኔ ነገሩኝ። ሲደዉሉ አኔ እና ባለደረቦቼ ወደ ድርጅታቸዉ ስንሄድ 3ሺህ ብር አስፈራርቶ ካሳቸዉ ተቀበለዉን ገንዘብ ይዞ ሲወጣ ወዲያዉኑ እጅ ከፍንጅ ደጃፋቹ ላይ ያዝነዉ። መሳሪያ ታጥቋል።ፎርጂድ የሆነ የታጋይ መታወቂያ ይዟል። ታጋይም ሁን- ሌላም ሁን ምን የምተሄደዉ መንግሥት ቦታ ነዉ፤ ፖሊስ ጣቢያ ነዉ። እዛ ሄደን እነንጋገራለን፡ እና አንሂድ ብለን ከነ ማሳሪያዉ እና 3ሺህ ብሩን ሁሉ ያዝነዉ። የሚገርመዉ ደግሞ ከኪሱ ደግሞ “ካገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር” የሚል ለነጋዴዉ የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ በማሕተም የታተመ የተጻፈ የማስፈራሪያ ደብዳቤ ይዟል። ሻምበል (የሻምበሉ ስም ይጠቅሳሉ- ከቴፑ ጥራት ግን ስሙን በትክክል መለየት ያስቸግራል) ሻምበል (ጥሃፌ/ጸሀፌ (?) ከተባለ ተወካያችን የተለካ ደብዳቤ ነዉ የሚል ማህተም ያለበት ደብዳቤ ሁሉ ይዟል።ከደህንነቱ ተጻፈ አስመስሎ ማለት ነዉ።ይሄን ሁሉ ያዝን እና ወደ ጣቢያ ሄድን።
እኔ ወደ ቢሮ ገብቼ፤ የዕለት ሁኔታ መዝጋቢዎች የተያዛወን ንብረት እግዝቢት እየመዘገቡ እያሉ፡እኔም ይሄን “ጸሃየ” የተባለዉ ሰዉ እያነጋገርኩት እንደለሁ ወዲያዉኑ ከክልል ምመሪያ “ረዳኢ ገ/አነንያ” የተባለ በፖሊስ ሬንጀር መኪና እበረረ ወደ እኔ ቢሮ መጣ። ማን እንደነገረዉ፤እንዴት እንደሰማም አይታወቅም። መጣ። የታያዘዉ ሰዉ አለ ወይ? አለኝ። አዎ አለ፡ አልኩት። ከዚያ ሲያዉ ሰዉየዉን በትግርኛ ተነጋገሩ። እኔ ትግርኛ አልችልም- ግን ፍሬ ነገሩ የተረዳሁት ምንድነዉ፦ለምን አባትክ በየወረዳዉ ትልከሰከሳለህ! የሚል ነዉ።መጨረሻ ሁለቱም ከተነጋገሩ በሗላ “ይህ ጉዳይ በክልል ደረጃ መታየት ስላለበት በክልል ደረጃ እንዲጣራ እኔ ይዤዉ እሄዳሉ አለኝ። እኔም “አይሆንም” ብየዉ ጭቅጭቅ አድረገን፤ ወዲያዉኑ “በላይ” የሚባል ካገር ዉስጥ ደህንነት “በላይ” እባላለሁ ነኝ ያለኝ፦ደዉሎ “ይሄ አሁን የያዝከዉ ኬዝ እኛም እየተከታተልነዉ የነበረ ስለሆነ እና በስፋት ለማጣራት ስለምንፈልግ ለረዳኢ ስጠዉ፡ ረዳኢ ይዉስደዉ!” አለኝ። ማነህ አንተ? ስለዉ- እኔ ከደህንነት ነኝ እደወልኩ ያለሁት። አለኝ። እንዴ ታድያ ደህንነት ከሆንክ የደህንነት ስራ ስራ እንጂ ይሄ እኮ የፖሊስ ስራ ነዉ፡ እርግጥ ሚያገናኘን ስራ ዘርፍ ቢኖርም፤ይሄ የወጣለት፤የለየለት ደረቅ የማጭበርበር ወንጀል ስለሆነ-ግለሰቡ እና ማስረጃዎች “ኦልሬዲ” የተያዘ ስለሆነ ማስረጃዎች ተጣርቶ ወደ ሚመለከተዉ ሕግ ይቀርባል እንጂ እንዴት ወደ የበላይ ይሂድ ትለኛለህ? ስለዉ “ስጠዉ ማለት – ስጠዉ ነዉ “ስጠዉ ብየሃለሁ! ስጠዉ ብየሃለሁ!” አለኝ።
በመጨረሻ ተስፋይ አብርሃ (አፍረሶም) (ቅድም የፀሃየ የእህቱ ልጅ ነዉ ብየ የጠቀሰውኩት ባለስልጣን ደዉሎ ለረዳኢ አስረክበዉ ብየሃለሁ ብሎ ደዉሎ አሱም ከኔ ጋር ንትርክ አድርጎ የተያዘዉን መሳርያ እና የመሳሪያዉ መለያ ቁጥር፤ እንደዚሁም 3ሺህ የተያዘዉ ገንዘብ ረዳኢ ይዞት ሄደ። ለታሪክም መዝገቡ ካልጠፋ ወይም ካልቀደዱት በወረዳ 21 የዕለት ሁኔታ መዝገብ አስከ እነ ቁጥሩ ቀን ዓ/ም ይገኛል።መሳሪያዉ ቁጥር፤ የሐሰት የደህንነት ደብዳቤ ከነ ሸኚ ቁጥሩ ሳይቀር ሁሉ ተመዝግቦ ይገኛል።ተጠያቂዉም አብሮ ከነ መዝገቡ ይዞት ሄደ። አንድ ሰዓት አልቆየም ይሄ ይዞት የሄደዉ ‘በየነ’ ‘እአሱ’ ‘ጸሃየ…እገሌ እገሌ እያለ በተለያየ ስም የሚያጭበረብረዉ ወንጀለኛ ስልክ በቀጥታ ወደ እኔ ደወለ። ደዉሎ ምንድ ነዉ ያለኝ- “ከማን ጋር እየታገልክ እንደሆንክ እወቅ! ለምድነዉ አርፈህ እንጀራህን በሰላም እየበላህ የማትኖር? ካስፈለገ እኮ የአንተ ጉዳይ የደቂቃ ስራ ጉዳይ ነዉ! ብሎ በስልክ ደዉሎ አስጠነቀቀኝ። እኔም ስመልስ_ አንተ ምትችለዉን አድርግ እኔም አለሁኝ! አልኩት እና በዚህ ተለያን።
አንግዲህ በነ ተስፋይ አብርሃ በእነ ረዳኢ ገብረአነንያ በኩል ነዉ መሳሪያዉን የሚያገኘዉ። ይዞት የነበረዉን ያጭበረበረበትን መሳሪያ ፈቃድ አሳየን ብለን ስንጠይቀዉ የማሳሪያዉ መለያ ፈቃድ የሚያሳየዉ “”ረዳኢ ገብረአነንያ” ይላል።ረዳኢ ገብርአነንያ ማለት ደግሞ ‘የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ሃለፊ” ነዉ። ሌሎች ትግሬ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን ግን በሆነ አጋጣሚ መሳሪ ይዘዉ ከተገኙ ተይዘዉ ይታሰራሉ።ወይ ኦነግ ነዉ ወይ መኢአድ ነዉ ወይ የኦሮሞ ኮንግረስ ወይ የደቡብ ህዝቦች አባል ነዉ የሚል የፖለቲካ ስም ይለጠፍበት እና “ጀርባዉ ይጣራ” የሚሉት ቋንቋ አላቸዉ። ይሄ ጸረ ኢሕአዴግ ነዉ፡መሳሪያ ከየት ሊያመጣ ይችላል? ተብሎ ስቃዩን ያያል። የትግራይ ተወላጆች ግን 3 አራት ማሳርያ አላቸዉ። ይሄ የሚደረግዉ እንግዲህ ወያኔ ራሱ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” እንደሚባለዉ “ራሱ ዳኛ ነዉ” ራሱም “ይዘርፋል ወይም ያስዘርፋል” ።ስለዚህ በቡድን በእጅ አዙር በመንግስት ባለስልታኖች የሚሰራ የወንጀል መተባበር ተግባር እና ትስስር ተለመደ ነዉ።
ሌላ ዓይነት ቡድን ደግሞ አለ።
አንድ ቀን ታጋይ ሐዱሽ፤ታጋይ ጀማል፤ታጋይ ዜናዊ የተባሉ በቀን መኪና አስቁመዉ ከዛዉ ከእነ ተስፋይ አበርሃ ቢሮ ትንሽ ዝቅ ብሎ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ (የተስፋይ አበርሃ ቢሮ ነዉ) ከዚየዉ ዝቅ ብሎ ከጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ጀምሮ አስከ መክሲኮ ድረስ በአንድ መኪና እየበረሩ መጥተዉ፤ ክላሽን ጠመንጃ ይዘዋል፤ሽጉጥ ታጥቀዋል፤የመከላከያ ደምብ ልብስ ዩኒፎረም ነዉ የለበሱት፤ሦስት ናቸዉ፡ አንዱ ሾፌር ነዉ-ከደጅ ሆኖ ይጠብቃል፤ ሁለቱ በመደዳ በወቅቱ ክፍት በነበሩ ቡናቤቶች ገብተዉ ለመዝናናት የመጡ ደምበኞችን ሁሉ ወለል ላይ በሆዳቸዉ አስተኝተዉ -ሰዓት ያለዉ ሰዓቱን፤ወርቅ ያለዉ ወርቁን፤ የቡና ቤቱ ቴፕ ሪኮርደር እና ከመጠጥ ሽያጭ የተገኘዉ የቡና ቤቱ ባለቤት ገንዘብ ካለም ገንዘቡን ዘርፈዉ መኪናቸዉ ይሰወራሉ። እንግዲህ እንደዚህ እያደረጉ ከላይ ከ እዛ… እንግዲ አዲስ አበባ ለሚያዉቅ ሰዉ ግልጽ ነዉ፤-ከፕያሳ ጀምረዉ በቴድሮስ አደባባይ አድርገዉ በመስቀል አደባባይ አድርገዉ እንደገና እየዞሩ አስከ ሜክሲኮ አደባባይ ድረስ ሲመጡ መደዳዉን ስላዳረሱት ህዝብ ተዘርፏል እና ለእርዳታ ድረስ ተብሎ ለክልሉ በስልክ ሲነገር_ የክልሉ ተረኛ ፖሊሶች ይህነን ይሰማሉ።-
ድርጉቱ ሲፈጸም አጋጣሚ ምሽት ስለነበር፤-የበላይ አለቆች በእዛ ሰዓት በየአረቄ ቤቱ ስለነበሩ ከወገንተንነቱ ነጻ የሆኑ ፖሊሶቹ ይህነን ሃላፊነት ለመወጣት ጥሩ አጋጣሚ አግኝተዉ የዘረፋዉ ዜና በየወረዳዉ በስልክ ስያስተላልፉልን፤ጥበቃ ማድረግ ጀመርን። በዘረፋዉ ወቅት ዘራፊዎቹ የተጠቀሙባት የታክሲ መኪናዋ ልዩ መለያ ምልክት ተነግሮን ስለነበር እመክሲኮ አደባባይ ስትደርስ ታክሲዋን አየናት። ተከታተልንባቸዉ። እነሱን ተከታትለን ወደ ልደታ አቀናን ቀጠሉና ሄዱ፡ ከልደታ ወደ…(የቴፑ ድምጹ ጥራት በደምብ አይሰማም) ሲሄዱ እዛዉ ደረስንባቸዉ። ከመኪና ሲወርዱ አስቆምናቸዉ። ስናያቸዉ የለበሱት ልብስ የመከላከያ ነዉ፡ሽጉጥ ይዘዋል፤ክላሽ አነግተዋል፡ ይገርማል! ይሄነን ለተመለከተ ሰዉ እነኚህ ሰዎች ዘራፊዎች ናቸዉ ብሎ ደፍሮ ለማለት የስቸግራል። መጨረሻ እጃችነን አንሰጥም አሉን። እኛም አግባብተን “አይ ሌሎች ሰዎች መስላችሁን እኮ ነዉ፣ ለካ እናንተም ታጋዮች ናችሁ’ ብለን አዘናጋናቸዉ እና በመጨረሻ የተጠቀምነዉ ስልት አለ፦አያነጋገርን ያዝናቸዉ።መሳሪያቸዉንም የዘረፉት ንብረትም ገንዘቡንም ሁሉ አነሱንም ይዘን ወደ ጣቢያ ሄድን።
ታክሲዋ/መኪናዋም ጭምር ወረዳዉ ፖሊስ ጣቢያ ታግታ ለብዙ ጊዜ ቆማ ነበር። ሾፌሩ “እኔ ተገድጄ አስገድደዉኝ ነዉ እንጂ በዚህ ስራ ወድጄ አልተሰማራሁም” ስላለ ዳኛዉም ዉሳኔ መስጠት አቅቶት ነገሩ ሲጎትተዉ መኪናዋ ለብዙ ጊዜ ቆማ ተገትራ እዘዉ ነበረች። በመጨረሻ ላይ ምርመራ ተደርጎላቸዉ ሲጠየቁ “ዛሬ ብታስሩን -ነገ እነፈታለን”እያሉ ያሾፉብን ነበር። የዉም የሚገርመዉ “መታሰራችን ሳይሆን የሚቆጨን የዘረፍነዉን ገንዘብ ሳንጠቀምበት መቅረቱ ነዉ”-አለን ‘የማነ’ የሚባለዉ ከዘረፉት ንብረት ጋር ፎቶግራፍ ሳስነሳዉ።”እኔን ዘረፍክ ትሉኛላችሁ-የተዘረፍኩት ግን እኔ ነኝ” አለን የዘረፉት ንብረት ባንድነት ተቀምጦ ሲያየዉ አሳሳዉ/አስጎመጀዉ። “ይሄ ሁሉ ይዤ ብሄድ ኖሮ ነበር “ዘረፍክ የምባለዉ፤ነገር ግን የተዘረፍኩት አኔ ነኝ እያለ ሲቀልድብን ነበር።
በመጨረሻ ተጣርቶ ለሚመለከተዉ ስናስረክብ በዋስ እንዲለቀቁ ተደረገ። መሳሪያን ተጠቅሞ በሰላም የሚዝናናን በሰላም በየጎዳናዉ እና በየ አደባባዩ ወደ ቤቱም ወደ ስራም የሚንቀሳቀስ ሰላማዊ ዜጋን መዘርፍ እና ሽብርን መልቀቅ በጣም ከባድ ወንጀል እና አስከ 15 ዓመት በእስር የሚያስቀጣ የወንጀል ድርት ነዉ።ዜጎች እንደልብ እንዳይንቀሳቀሱ በየመንገዱ እና በንግድ ተቃሟት እገባ የሚያስጨንቅ በፍርሃት ሚገድብ ሚያሸማቅቅ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚዎች በወቅቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት የነበሩት የትግራይ ሰዉ “አቶ ሐጎስ” የሚባሉ እንዲለቀቁ አደረጓቸዉ።
አብዛኛዉ እንደዚህ ያለ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ አለበት ከተማ ዘረፋ ሽብር ላያዉቀዉ ወይንም ሰምቶት የማያዉቅ ብዙ ሰዉ ሊኖር ይችላል።ለዚህም ነዉ እኔ በፖሊስ ሞያነቴ ተሰማርቼ እንደዚህ ዓይነቶቹ መንግስታዊ ወንጀሎች ሲፈጸሙ በማየቴ ያየሁትን መረመርኩትን ለህዝብ ምስጢሩ ተደብቆ እንዳይቀር የማጋለጥ ሃለፊነት ሙያየ ስለሚያስገድደኝ ህዝቡ እንዲያዉቀዉ ይገባል በሚል ነዉ።በመንግሥት የተቀነባበረ ግድያ (ለምሳሌ ሻምበሉን እንደገደሉት ዓይነት)፤በቡድን እና በግለሰብ በባለስልጣኖች የተቀነባበረ ዘረፋ፤ነጋዴ ሕብረተሰቡን ማስጨነቅ ማስፈራረት የመሳሰሉት ከመንግስት ባለስልጣኖች ጋር እተመሳጠሩ የወንጀል ድረጊቶች ተፈጽመዋል። ኢሕአዴግ ነጋዴ በመሆኑ ፤ነጋዴዎችን በማስፈራራት እንዲሸማቀቅ እና ከጨዋታዉ ዉጭ ሊያደረግዉ ይፈልጋል። ወደደም ጠላም ከፍራቻ ነፃ ለመሆን (እንዳይዘረፍ) ከኢሕአዴግ ባለስልጣን ቢያንስ አንድ ወዳጅ እንዲይዝ እንዲሞዳሞድ ሰላም በዉስጡ እንዲሰማዉ ጀርባዉን እንዲተማመን ያደርጉታል። ስለዚህ በሕዘብ ላይ የሚደረግ መንግሥታዊ ደባ ህዝቡ ማወቅ አለበት።
ይህ ተቀነባበረ የዘረፋ እና የፖለቲካ ወንጀል ፖሊስ ኮሚሽነረሩ አቶ ተስፋይ አብርሃ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወንጀል መከላከል ሃለፊ የአቶ ረዳኢ ገብረአነኒያ እጅ እንዳለበት ከላይ የገለጽኩት በወረዳችን በወረዳ 21 ሲካሄድ የነበረዉ የተቀነባበረዉ ዘረፋ ወደ ወረዳ 20 ሽፍት አድረጎ ወደ ወረዳ 20 አዞሩት። ወረዳ 20 ማለት በዞን ሁለት ቄራ አካባቢ የሚገኘዉ ወረዳ ማለት ነዉ። እና በሌሎች ወረዳዎች በወረዳ 19 17 20 23 24 ወረዳዎች እየተዘዋወረ የሚዘርፍ ቡድን ነበረ። ከነዚህ ቡድኖች ዉስጥ አሁንም ዜናዊ ነበረበት። ዜናዊ ማለት ቅድም ስጠቅስ ከነ ጀማል ጋር የነበረ ነዉ። እንደገና ከዚህ ቡድን ጋራ አስቀድሞ ሲዘርፍበት በነበሩት ወረዳዎች ትቶ በእነዚህ በተጠቀሱት አዳዲስ የዘረፋ ወረዳዎች መዝረፍ ጀመሩ። እነዚህ በተከታታይ በጦር መሳሪያ በመደገፍ በየመንደሩ በየቤቱ እየገቡ እያሰሩ ዘረፋቸዉን ያካሂዱ ነበር። ይህ ድርጊት በጊዜዉ ጉዳዩን ሲከታተሉት የነበሩት እነ መቶ አለቃ ክፍሉ እነ መቶአለቃ ስሞኦን እ… እራሱ የወያኔዉ ሹም የነበረዉ የዞን አዘዥ “አጋዓዚ” እ…… እነ ወታደር ማዕርጉ እ….. ምሕረታብ የሚባሉ ይህነን ነገር ያወቁታል። ምክንያቱም እነሱ ነበሩ እንዲመረምሩ ትዕዛዝ ተሰጣቸዉ።
ከላይ የጠቀስኳቸዉ የምርመራ ባልደረቦች በምርመራዉ ላይ ጥሩ አልሰራችሁም ተብለዉ ከስራ አገዷቸዉ።ሜርኲሪ የሚባል የማጭበርበሪያ ስልት አለ፡ የተጣራዉ ዝርዝር ምርመራ በእዛኛዉ በሜሪኩሪ ኮሚቴ አልፎ ወደ ደህንነት ከዛዉ ወደ ትላልቆቹ ባለስልጣኖች ቢሮ ሲሄድ የነበራቸዉ አማረጭ ምርመራዉን ማስቆም ነዉ። ምርመራዉን ለማስቆም ደግሞ ሲመረምሩ የነበሩትን ልጆች ምርመራ አሳጥታችሗል/አጋልጣችሗል፤ሰብአዊ መብት ረግጣችሗል በሚል እነ ወታደር ማዕረጉ እነ ምሕረታብ እነ መቶአለቃ ክፍሉ እራሱ “አጋዓዚ” ሳይቀር ይመሰክሩታል። አጋዓዚ ራሱ በዚህ ምክንያት ከስራዉ ታግዶ ነበር። መርማሪዎቹ ከስራ ሲባረሩም ሁኔታዉ በጣም ስለገረማቸዉ “ ሰራቂዉ ትግሬ፤ዓቃቤ ሕጉም ትግሬ፤ዳኛዉም ትግሬ፤ ታዲያ ይሄ ከሆነ የኛ በቦታችን ሆነን ጉዳዩን መመርመር ፋይዳዉ ምንድነዉ? ብለዉ በምሬት ስለተናገራቸዉ -ከስራ ተባረሩ። ምክንያቱም በተጨባጭ የተረጋገጠ እና የምናዉቀዉ ሲዘርፉ የነበሩት ትግሬዎች ናቸዉ፤
ጉዳዩ ተጠርቶ ለከፍተኛ ሲላክ ጉዳዩን በአጋጣሚ የተላለፈለት የተረከበዉ አቃቤ ሕግም ትገሬ ነዉ፤ አሱ ጋር ሲደርስ አሱም በዋስ ልቀቁዋቸዉ አለ። ዳኞች ጋር ቀርበዉ ሲያመለክቱ “አይ እኛ አናስርም” አሉ። አናስራቸዉም ብሎ ትዕዛዝ የሰጠዉ ዳኛ ደግሞ ትገሬ ነበር። በዚህ ተበሳጭተዉ ነበር “እንዴ! ዘራፊዉ ትግሬ ፤ዓቃቤ ሕጉም ትግሬ ዳኛዉም ትግሬ ስለዚህ በማሃል ገብተን መዳከራችን ምን ዉጤት አመጣ?” በማለታቸዉ “መንግሥትን ነቅፋችሗል የመንግስት ወገኖች ሳትሆኑ መንግስት ጠላቶች ናችሁ” ብለዉ እንዲባረሩ ተደረገ። አሁን ስራ የላቸዉም እነዚህ ሰዎች። አጋዓዚን የዞኑን አዛዥ የነበረ በዚህ ረገድ የኢሕአዴግን ጥቅም አላስጠበቅክም ተብሎ አሱንም ከ ሌሎቹ ቅን መርማሪዎች ጋር አግደዉት ለወራቶች ካንከራተቱት በሗላ ይመስለኛል መልሰዉ ከዞን አዘዥነት ስልጣኑን አዉርደዉ በወረዳ 28 አካባቢ በጣም ትንሽ ደካማ ጣቢያ በሆነች የወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ አድርገዉ መለሱት። የተቀሩት ስራ አጥ ሆነዉ ተንከራትተዉ ነበር። ዛሬ በምን ሁኔታ ላይ አንዳሉ አላወቅኩም። እና እነዚህ የመሳሰሉት ወንጀሎች፤ባለስልጣኖቹ የፖሊስ ሃይል ጽ/ቤቶችን የደህንነት ስለጣኖችን በመጠቀም ያስዘርፋሉከዘራፊዎችም ጋር ጥቅም ይካፈላሉ።
ሌላዉ በጣም ልብ ብሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊገነዘበዉ የምፈልገዉ ነገር ለየት ያለ የአገሪቱን ከኢኮኖሚ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የዘረፋ ድርጊት ልግለጽ። አንድ ባገሪቱ ዉስጥ በግምባር ቀደም የሚጠቀስ ድረጅት አለ፡ እና በጥሞና እንድታዳምጡኝ እጠይቃለሁ። የድርጅቱ ስም “የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን” የሚባል መረጃዉ እንደሰማሁት ምናልባትም ካገሪቱ በጀት ግማሹን ለዚህ ድርጅት ተመድቧል። በዚህ መ/ቤት ዉስጥ ሚደረግ ምዝበራ አስመልክቶ አንድ ማስረጃ ላቅርብ። የህ ድርጅት በወረዳ 021 ቀበሌ 24 ልዩ ቦታዉ መክሲኮ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ነዉ የሚገኘዉ።ትልቅ ህንጻ ነዉ። እ…. መስርያቤቱ በማዕከልነት ለመምራት የተቋቋመ መስርያቤት ነዉ። ሌሎች የክልሎች ባለስልጣኖች አሉ። ይሄ የጠቅላላ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ነዉ።ግዙፍ ነዉ። ስራዉ መንገድ መስራት ነዉ። ሁለት የመንገዶች የስራ ዘርፎች አሉት። አንዱ በመንግስት የሚከናወን ሌላዉ የግል ኮንትራክት ተጫራቾች የሚያከናዉኑት አሰራር ነዉ። ኮንትራክተሮቹ ከዚህ ድርጅት ጋር ተፈራርመዉ የሚሰሩ ተዋዋየች ናቸዉ።
እኔ አስከ ማዉቀዉ ድረስ በ1989 ዓ/ም አካቢ ጀምሮ በዚህ መስርያቤት ዉስጥ በተከታታይ ዘረፋዎች ሲካሄድ እኔ የማዉቀዉ በተጫባጭ የደረስኩበት ምርመራ ነዉ።ዘረፋዉ ሚካሄደዉ ምንድ ነዉ? የመስሪያቤቱ ንብረት ይሰረቃል፤ በወረዳ 21 እና ቤሎችም ንበረቶች የሚቀመጥበት ግምጃ ቤት አለ።ሌሎችም በወረዳ 18 እና ሌሎች ግምጃቤቶች አሉት። ግን እኔ መግለጽ የምፈልገዉ በእኔ ወረዳ በነበረዉ ጉዳይ ነዉ። ምረመራዎች በሂደት እየተደረጉም እያሉ፤ አሁንም በተደጋጋኒ ያለማቋረጥ ሌላ ስርቆት ይካሄዳል። ዕቃዎች ይጠፋሉ ይዘረፋሉ። ዘራፊዉ አይታወቅም። መቸ ተዘረፈ? በማን ተዘረፈ? የሚል አይታወቅም።የመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ለይስሙላ ብቻ መሰረቁን ደብዳቤዎች ይጽፉ ነበር። የሚጽፉት ለማን ነዉ_ለማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራ ማስተባበሪያ ለእነ “ታደሰ መሰረት”፤ ታደሰ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ነዉ። ለነሱ ይጻፋል። ቀጥሎ የሚጽፉት ለአዲዩስ አበባ ፖሊስ ነዉ። “ተስፋይ አብረሃ” ሳይቀር ያዉቀዋል።ኮሞሽነር በነበረበት ጊዜ በተከታታይ ደብዳቤ ተጽፎለታል።
ይሄ መስርያቤት በእኛ ወረዳ በወረዳ 21ፖሊስ ጸ/ቤት ክልል በመሆኑ ለተጠቀሱት መ’ቤቶች ሲጻፍ ለእኛ በግልባጭ ያመለክቱን ነበር። እኔ ጋር ይመጣል፡ ቢሮ ዉስጥ ተመዝግቦ ይቀመጣል። ሁኔታዉን አያለሁ።ከስድስት ወር በፊት የተጻፈዉ ደብዳቤ መለስ የለዉም፤ዘረፋዉ አሁንም ቀጥሏል፤ አሁንም አዲስ የዘረፋዉ አመላካች ደብዳቤ በተከታታይ ይጎርፋል። በክልሉ የምርመራ ሃለፊ የነበሩ መቶ አለቃ አስፋ አየለ የሚባሉ ይሄን ነገር ጠየቅካቸዉ።እንዴ! ይሄ መስሪያ ቤት ተከታታይ ደብዳቤዎች ለናንተ ይጽፋል፡ ለኛም በግልባጭ ያስታዉቀናል፤የተካሄደ ምርመራም የለም። ይሄ ብሔራዊ ወንጀል/ናሺናል ክራይም ነዉ እና እንዴት ነዉ መቶ አለቃ አሰፋ የምታዉቀዉ ነገር አስቲ አካፍለኝ፤ይሄ ጉዳይ አሳሳቢ ነዉ፤አገሪቱን ይጎዳል ብየ አወያየሁት። መቶ አለቃ አሰፋ አየለ ጥሩ አዋቂ የፖሊስ መኮንን ነዉ። አይ! “አበረ” ይሄን ነገር ባታነሳብኝ ጥሩ ነዉ አለኝ። የተወሰኑ ሦስት የመስሪያ ቤቱ ዘበኞች ምርመራዉን ለማጣራት አስሮ አንደነበር ነገረኝ። በሁለተኛዉ ቀን ልቀቁዋቸዉ ተብሎ ተለቀቁ። እንዴት? ለምን? ሲባል -በስረቆቱ ጉዳይ ብዙ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣኖች እጅ ስላለበት እነኚህ ዘበኞች ለትንሽ ጊዜ በእስር ቢቆዩ ምስጢሩን ስለሚያወጡ እና ባለስልጣኖቹ እና ንክኪያቸዉ አብረዉ ስለሚጋለጡ በዚህ ስለሰጉ እንዲለቀቁ ተደረገ። ይቀጥላል…….

Jan 7, 2013

የሙስሊም ሓበሾች የነጻነት ትግል ከግንቦት20 እስከ ግንቦት 20

የሙስሊም ሓበሾች የነጻነት ትግል ከግንቦት20 እስከ ግንቦት 20
አቡ ዘኪያ
ከምድረ-አናቶሊያ
“እስላም እሚያርድ እንጅ እሚወድ አይመጣም፣
የፈራህ ሰው ውጣ እኔ መልስ አላጣም
ይዘገያል እንጅ ሰው የጁን አያጣም”ሸህ ሑሴን ጂብሪል
እነሆ እስልምናና ሀገረ-ሐበሻ ከተዋወቁ አስራ አራት ክፍለ ዘመናት ተቆጠሩ::በነዚህ ዘመናት ዉስጥ  ሙስሊም
ሐበሾችን ያስደሰቱና ያሳዘኑ  ብዙ መስዋዕትም ያስከፈሉ በዚች አጭር ጦማር  ተዘርዝረው የማያልቁ በርካታ
ክስተቶች ተከስተዋል:: በዛሬው ጽሑፌ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በሙስሊም
ሐበሾች ላይ የተጋረጡ  ዋና ዋና ጋሬጣዎችንና እነሱን ለማስወገድ የተደረገውን ትግል አጠር አድርጌ ለመዳሰስ
እሞክራለሁ::
በወርኃ የካቲት 1847  ደጃዝማች ካሳ ኃይሉ በረዥሙ የሀገራችን ታሪክ ዉስጥ ዘመነ መሳፍንት በመባል
የሚታወቀውን ነገሥታት የተዳከሙበትንና መሳፍንታት የገነኑበትን ዘመን ፍጻሜ  በማብሰር ራሳቸውን ዳግማዊ
አፄ ቴዎድሮስ  ብለው አወጁ::በጎጥ ተከፋፍላ ያገኟትን ኢትዮጵያን ማዋሀድ ከአፄ ቴዎድሮስ ርዕዮች አንዱና
ዋነኛው ነበር::ኃይማኖታዊ አንድነት የሀገራዊ ዉህደት አንዱ መሰረት ነው በሚልም በእሳቸው ቁጥጥር በነበረው
የሰሜን ኢትዮጵያ ግዛት ዉስጥ ይኖሩ የነበሩ ሙስሊሞችን እንደ ባላንጣ በማየት ለአስከፊ ስቃይ ዳርገዋቸው
እንደ ነበር ይታወሳል::
ግንቦት 20 ቀን 1870...
ግንቦት 20 ቀን 1870 በሙስሊም ሐበሾች ታሪክ ዉስጥ ልዩ ስፍራ ይዞ የሚገኝ እለት ነው::አፄ ቴዎድሮስ
ራሳቸውን መቅደላ አምባ ላይ በገደሉ በአራተኛ ዓመታቸው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆነው የነገሡት አፄ
ዮሐንስ አራተኛ የአፄ ቴዎድሮስን ኃይማኖታዊ መሰረት ያለው ሀገራዊ አንድነት ግንባታ መርህ እጅግ በከፋ
መልኩ የተገበሩ ንጉሥ ነበሩ::የዚህ ፖሊሲያቸው ሰለባም የሰሜን ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ነበሩ::
ግንቦት 20 ቀን 1870 በኢትዮጵያ ክርስቲያናት መካከል ለዘመናት ለዘለቀው(ቅባት፣ጸጋና ካራ ቡድኖችን
ያስታውሷል) ቀኖናዊ ዉዝግብ  እልባት ለመስጠትና ሙስሊሞችን ለማጥመቅ ከደሴ ከተማ በስተሰሜን 10 ኪሎ
ሜትር  ርቀት ላይ በሚገኘው ቀለም ሜዳ(ቦሩ ሜዳ)በአፄ ዮሐንስ  ዋና ወምበርነት አንድ ኃይማኖታዊ የክርክር
መድረክ ተከፈተ::ያ ለቀናት የዘለቀና የሸዋውን ንጉሥ ምኒሊክንና ሌሎች ስመጥር መኳንንትና ካህናትን ያሳተፈ
ስብሰባ  የተረቱ ክርስቲያን ሊቃውንትን  እግር፣እጅና ምላስን በማስቆረጥና የሐበሻ ሙስሊሞች ህልውናን አደጋ
ላይ የሚጥል አስደንጋጭ ዉሳኔን በማሳለፍ ነበር የተጠናቀቀው::
የሰሜን ኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንዲጠመቁ ወይም ሀገር እንዲለቁ በይፋ ተነገራቸው::ተጠመቅ ወይ አገር
ልቀቅ የሚለው የአፄ ዮሐንስ አዋጅ ለኃይማኖታቸው ቀናዒ ለነበሩት የሰሜን ኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚዋጥ
አልነበረም::እርግጥ ነው ከመሞት መሰንበት ያሉ ከእምነት ይልቅ ሹመትን የመረጡ የኢማምሙሐመድ ዓሊ

ወይም ራስ ሚካኤል(በኋላ ንጉሥ ሚካኤል)ዓይነት ግለሰቦችም ነበሩ::እስኪያልፍ ያለፋል እንዲሉ አንዳንዶችም
ለይስሙላ በመጠመቅ ቀን ቀን ክርስቲያን ማታ  ማታ ሙስሊም መሆንን መርጠው ነበር::ሌሎች
ተሰደዱ::እምነቴን ወይ ሞቴን ያሉ ደግሞ ጂሐድ አወጁ::
ጂሐዱ ሁለት መልክ ነበረው ማለት ይቻላል::ሰላማዊና ብረታዊ ::ሰላማዊ ዘርፉ እምቢተኝነትን በሰላማዊ መልክ
በግጥምና በእንጉርጉሮ  መግለጽ ላይ ያተኮረ ነበር::የሰላማዊው ዘርፍ  ዋና መሪ  በዘመን ተሻጋሪ አስደማሚ
ግጥሞቻቸውሙስሊሞችን ሲያበረታቱና አፄ ዮሐንስን ሲመክሩና ሲያስጠነቅቁ የነበሩት ኢትዮጵያዊው
ኖስትራዳመስ ሸህ ሑሴን ጂብሪል ነበሩ::ዛሬም ድረስ በሙስሊም አምሐራዎች ዘንድ በስፋት የሚታወሱትና
የሰላማዊው ጂሐድ ስንቅና ትጥቅ ከነበሩት የሸህ ሑሴን ጂብሪል ግጥሞች  ዉስጥ እንዲህ የሚሉ ይገኙባቸው
ነበር:-
ዓባይ በጣና ላይ መሄዱ ለምን ነው?
ትንሹ ሲያጠፋ ትልቁ ሊችል ነው፣
ቢያከፋም ቢያበጅም ዓባይ ማለፉ ነው
ሰውን በግዴታ የሚገዛው ማነው?
ከምክር በስተቀር የቀረው ከንቱ ነው::
ማረዱ ከፋ እንጅ ጀግንነት አያጣም
እስላም እሚያርድ እንጅ እሚወድ አይመጣም፣
የፈራህ ሰው ውጣ እኔ መልስ አላጣም
ይዘገያል እንጅ ሰው የጁን አያጣም
መተማ ከሄደ ተመልሶ አይመጣም::
አንተም እድሜህ አጭር ወይ ዘርህ አይገዛ
ጎርፍ ደርሶ አይወስድም አለቅጥ ካልበዛ
እንጨት ከደረቀ ቢቀቡት አይወዛ
ሐበሻ ክፉ ነው አይምሰልህ ዋዛ
መተማ እስቲጠራህ በብልሃት ግዛ::
እመክርህ ነበረ መች እሺ ትላለህ
ሀሳብህ ብዙ ነው መንገድ ታበዛለህ
መተማ ለመዝመት አሁን ትሄዳለህ

መመልስክን እንጃ እዛው ትቀራለህ
በድርቡሽ ጎራዴ ራስህን ታጣለህ::
አንድ ዓመት ሲቀረው ምኒልክ ሊነግሥ
አላህ መተማ ላይ ይስላል መቀስ
በደም አጨማልቃ የምትቆራርስ
እራስ የምትቆርጥ ያውም የንጉሥ
አንደዜ ተመታች የማታላውስ::
በወቅቱ ከፍ ያለ ተሰሚነት በነበራቸው ሸህ ሑሴን ጂብሪል ይነገሩ የነበሩት መሳጭና ተስፋ ሰጭ ዜማዊ
መልእክቶች ጋራ ሸንተረሩን ተሻግረው ከጎጥ ጎጥ  በፍጥነት ይደርሱ እንደነበር አበው ይተርካሉ::እነዚህ ዉብ
ስንኞች ሕዝበሙስሊሙ ተስፋ ሰንቆ በእምነቱ ጸንቶ እንዲቆይ የተጫወቱት ሚና ቀላል አልነበረም::
ከላይ እንደ ተጠቀሰው ሁለተኛው የትግል ግንባር ወታደራዊ ጂሐድ ነበር::የጂሐዱም መሪዎች በሕብረተሰቡ
ለሕብረተሰቡ የተመረጡ የኃይማኖት መሪዎች ነበሩ::ወታደራዊው ጂሐድ በርካታ መሪዎች ነበሩት::ከግንባር
ቀደም ወታደራዊ አዛዦች አንዱ ሸህ ዓሊ አደም  ነበሩ::ሸህ ዓሊ አደም በአሁኗ የደሴ ከተማ ደቡባዊ ጫፍ
የሚገኘውና  ልዩ ስሙ ቢለን የሚባለው መንደር  ተወላጅ ነበሩ::ቤተሰቦቻቸው ከጂሩ-መንዝ የፈለሱ
በመሆናቸው ሸህ ዓሊ ጅሩም ተብለው ይጠራሉ::
ሸህ ዓሊ አደም የአፄ ዮሐንስን ጦር ለመጀመሪያ ጊዜ ግንባር ለግንባር የተጋፈጡትሙጃሒዲኖች መሪ
ነበሩ::የመጀመሪያው ታሪካዊ ዉጊያም የተካሄደው  በቀለም ሜዳው አዋጅ  ማግስት ከዛሬዋ ሀይቅ ከተማ
በስተሰሜን ምዕራብ ዋሄሎ በተሰኘ ቦታ ላይ ነበር::በውጊያውም የሸህ ዓሊ ጦር ለሽንፈት ሲዳረግ ሸህ ዓሊም
በውጊያው ላይ ተሰው::በውቅቱ ዋሄሎ ላይ አርፎ የነበረው የሸህ ዓሊ አስከሬን ከስድስት ዓመት በኋላ ወደ
ትውልድ ቦታቸው ቢለን የተዛወረ ሲሆን ቀብራቸውም  የጎብኝዎች መስህብ የሆነ ታሪካዊ ቦታ ለመሆን በቅቷል::
ሌላው የወታደራዊ ጂሐድ ዝነኛ መሪ የአርጎባው ተወላጅ ሸህ ጠልሃ ቢን ጃዕፈር ነበሩ::ሸህ ጠልሃ የአፄ ዮሐንስንና
የሸዋው ንጉሥ ምኒሊክን ጣምራ ጦር ለዓመታት በመመከት አይበገሬነታቸውን አስመስክረዋል::ሸህ ጠልሃ
በባላንጦቻቸው ሳይቀር:-
ጠላት ማወደስ እንዳይሆን እንጅ
ማንም አያህለው ጠለሃ ሐጅ
ተብሎ የተገጠመላቸው ድንቅ የጦር ሰው ነበሩ::ወታደራዊው ጂሐድ ደቡብና ሰሜን ወሎን፤ሰሜን ሸዋንና ደቡብ
ትግራይን ያካለለ የአምሐራ ፣አርጎባ ፣አፋር ፣ኦሮሞና ትግራይ ተወላጆችን ያሳተፈ ህብረ-ብሐራዊ የነጻነት
ተጋድሎ ነበር::ጂሐዱ ለዓመታት የዘለቀና ብዙ መስዋዕትነትም የተከፈለበት ነበር::

የአፄ ዮሐንስን መተማ ላይ መቀላት ተከትሎ የንጉሠ ነገሥትነቱን ስልጣን የተቆጣጠሩት ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ
ከአፄ ዮሐንስ ስህተት የተማሩ ይመስላሉ:: "አመልክን በጉያ ስንቅህን በአህያ"  ተብሎ በሚታወቀው የኃይማኖት
ፖሊሲያቸው መሰረት ከኦሮቶዶክስ ኃይማኖት ዉጭ ላሉ ዜጎቻቸው መለስተኛ የእምነት ነጻነት መፍቀዳቸው
ለዚህ ዓይነተኛ ማስረጃ ነው::
አፄ ምኒሊክን የተኩትና ተራማጅ ርዕያቸው በልጅነት የተቀጨባቸው ልጅ ኢያሱ በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ
ሙስሊሞችን ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር እኩል ለማድረግ የጣሩ ብቸኛ ተራማጅ መሪ ነበሩ::ድህረ-ኢያሱ
ኢትዮጵያን መጀመሪያ በአልጋወራሽነት  በኋላም በንጉሠ ነገሥትነት የመሯት ቀዳማዊ ኃይለ  ሥላሴ በሙስሊም
ሐበሾች ዘንድ በበጎ ዓይን ከማይታዩ ነገሥታት ወገን ይመደባሉ::በተለይም ከ1909 እስከ  1928 በነበረው የግዛት
ዘመናቸውሙስሊሞችን በጣም መጫናቸው ይታወሳል::ከ1928 እስከ 1933 በነበሩት ዓመታት ሀገራችን ወሮ
ፋሽስታዊ ስርዓት መስርቶ የነበረውሙሶሎኒ ለከፋፍለህ ግዛ አላማው ይረዳው ዘንድ ለሐበሻ ሙስሊሞች
ከአብዛሃኞቹ ሰለሞናዊያን ንጉሦቻቸው ሻል ያለ የእምነት መብት ሰጥቶ ነበር::
ከስደት መልስ አፄ ኃይለ ሥላሴ የጣሊያንን እርምጃ ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባትሙስሊም ዜጎቻቸውን
አስመልክቶ ከወትሮ ሻል ያለ ፖሊሲ ስራ ላይ ለማዋል ሞክረዋል::በ1936 በንጉሠ ነገሥቱ የታወጀው የናኢባና
ሸሪዓ ፍርድ ቤት አዋጅ ለዚህ እንደማስረጃ ሊጠቀስ ይችላል::ኤሪትሪያ በ1944 ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን
መጣመሯና በኋላም የኢትዮጵያ አንድ ጠቅላይ ግዛት ሆና መጠቃለሏም ንጉሠ ነገሥቱ ሙስሊሞችን
አስመልክቶ አንዳንድ አዎንታዊ እርምጃዎች እንዲወስዱ የራሱን ተጽእኖ አስድሯል::በ1960ዎቹ አካባቢ ሁለት
ሙስሊም ሚኒስትሮች መሾማቸውም የዚህ ተጽእኖ ውጤት ነበር::
ትግሉ ቀጥሏል..."በኢትዮጵያ የሚገኙ ሙስሊሞች"በመባል በሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ይታዩ የነበሩትሙስሊሞች
በየካቲት 1966 አብዮት ፍንዳታ ማግሥት ማለትም ሚያዝያ 12 ቀን 1966 "የዜግነት መብቶቻችን
ይጠበቁ..."በማለት 300,000 ራሳቸውን ሆነው በአዲስ አበባ ግዙፍ ታሪካው ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ::ይሁን እንጅ
የአፄ ኃይለ ሥላሴ ስርዓት የሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ ሳይመልስ ተገረሰሰ::
መስከረም 2 ቀን 1967 ንጉሠ ነገሥቱን ከዙፋን አውርዶ ጊዜያዊ መንግሥት ያቋቋመው ግራ ዘመም ወታደራዊ
ጁንታ  ስልጣን በያዘ በማግስቱሙስሊሞች "በኢትዮጵያ የሚገኙ ሙስሊሞች" መባላቸው ቀርቶ
"ኢትዮጵያዊያንሙስሊሞች"እንዲባሉ ፣የዒድ አልፍጥር፣ ዒድ አል አድሀ(አረፋ)እና መውሊድ በዓላት
በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩና ሙስሊሞች ኃይማኖታዊ ጉዳዮቻቸውን የሚከውኑበት "የኢትዮጵያ እስልምና
ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባዔ"የተሰኘ መሪ ድርጅት እንዲያቋቁሙበመፍቀድ የሙስሊም ሐበሾችን ቀልብ በተወሰነ
ደረጃ መሳብ ያስቻሉ ታሪካዊ  እርምጃዎችን ወሰደ::
ግንቦት 20 ቀን 1983...
የአስራ ሰባት ዓመታት የጭቆና ቀንበር በሕዝባዊ ትግል ተሰባብሮ አዲስ ምእራፍ ተጀመረ::በሰኔ 1983
የተመሰረተው የሽግግር መንግሥትም ዜጎች የእምነትና የመደራጀት መብት እንዳላቸው በይፋ ደነገገ::ይህን
ተከትሎም በዘመነ ደርግ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲሙስሊም ተማሪዎች ተጠንስሶ የነበረው የኢትዮጵያሙስሊም
ወጣቶች ድርጅት(ኢ.ሙ.ወ.ድ.) እና ሌሎች እስላማዊ ማሕበራት በሕጋዊ መልክ ተመዝግበው እንቅስቃሴ

ጀመሩ::የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባዔም(መጅሊስ)በአዲስ መልክ ማንሰራራት ጀመረ:: ከጥቅምት
5 እስከ ጥቅምት ስምንት 1985 ለአራት ቀናት በተደረገ  ጉባዔም መጅሊሱ በአዲስ መልክ ተዋቀረ::ሳይውል
ሳያድርም የስልጣን ሽኩቻው ተጀመረ::ያ ዉስጣዊ ትርምስም ለየካቲት 14 ቀን 1987 ትራዤዲ መንገድ ጠረገ..
የካቲት 14 ቀን 1987 በአንዋር መስጅድ በግለሰቦችመሀል በተፈጠረ ግርግር ፖሊስ 10 ሙስሊሞችን መስጅዱ
ዉስጥ ገደለ::የአስር ሰዎች ደምና የሚሊዮኖች እምባ ፈሰሰ::ኢ.ሙ.ወ.ድ. እና መሰል እስላማዊ ማሕበራት
ከሰሙ::የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን መሪ ድርጅት የነበረው መጅሊስም ፈረሰ::ከዚያች እለት ጀምሮ መጅሊሱ
ከሙስሊሞች ወኪልነት ወደ  የኢሕአዴግ "እስላማዊ"ክንፍነት ተሸጋገረ::ግንቦት
ሃያዊያንና(ኢሕአዴግና)ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንም ሆድና ጀርባ ሆኑ::
ታኅሳስ 24 ቀን 2004...
ልክ የዛሬ ዓመት በዚች እለት "ድምጻችን ይሰማ"የሚል  ድምጽ በኢትዮጵያዋ ታህሪር አደባባይ ማለትም አወሊያ
ቅጥር ግቢ ተሰማ::የጩኸቱም  ምክኒያት  ከሰኔ 2003 ጀምሮ መጅሊሱን የተቆጣጠረው ሊባኖስ በቀል አህባሽ
የተሰኘ አንጃ ታሪካዊው የአወሊያ መድረሳ ላይ እጁን ማሳረፉ ነበር::የአወሊያ ተማሪዎች ተቃውሞም ተዳፍኖ
የነበረውን የሙስሊሙን ብሶት ለአደባባይ አበቃው::አወሊያን ማእከል ያደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴም በፍጥነት
በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ መስጂዶችን አዳረሰ::የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ተቋቋመ::በሕዝበሙስሊሙ  ለሕዝበ
ሙስሊሙ  የተቋቋመ መጅሊስ እንሻለን፣ መንግሥት ሕዝብ ሙስሊሙላይ የአህባሽን አንጃ በግድ ለመጫን
የሚያደርገውን ትግል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያቁም እና አወሊያ በሕዝበሙስሊሙበተመረጡ ክህሎቱ
ባላቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚሉ ሦስት አበይት ጥያቄዎችም  ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት
ቀረቡ::
በሰላማዊ መልክ ለቀረበው የመብት ጥያቄ በመንግሥት በኩል የተሰጠውና እየተሰጠ ያለው ምላሽ ባያስገርምም
አሳዛኝ ነው::በሕዝባዊ እንቅስቃሴውና መሪዎቹ ላይ  የተለያዩ ታርጋዎችን በመለጠፍ ኢ-ሰብዓዊ እርምጃዎችን
በመውሰድ ላይ ይገኛል::በሚያዝያ 19 ቀን 2004  አርሲ አሳሳ ላይ የተካሄደውን ጭፍጨፋ፣በወርኃ ሐምሌ
የመፍትሄ አፈላላጊውን ኮሚቴ አባላት ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ታፍሰው የታሰሩ ሙስሊሞችን
ጉዳይና በጥቅምት 10 ቀን 2005 በገርባ ከተማ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ለአብነት ያህል ማንሳት ይቻላል::
ወደ ግንቦት 20 ቀን 1870 እየተጓዝን ይሆን?ወደ ኋላ መለስ ብለን ግንቦት ሃያዊያንን.:-
ሰውን በግዴታ የሚገዛው ማነው?
ከምክር በስተቀር የቀረው ከንቱ ነው::
የምትለዋን ዘመን ተሻጋሪ የሸህ ሑሴን ጂብሪልን መልእክት ልናስታውሳቸው እንወዳለን::አዎ!በእርግጫ ሕዝብን
ለዘመናት ለመግዛት ማሰብ እንደነ ጋዳፊ በሕዝባዊ ጡጫ መዋረድን ማስከተሉ አይቀሬ ነው::እናም
እንደማመጥ::ለመደመጥ ማዳመጥ ፤ለመሰማት መስማት የግድ ነው::መሰማማትና መስማማት  አለብን
...እንመካከር "ከምክር በስተቀር የቀረው ከንቱ ነው::"አበቃሁ::

ትግሉ ይቀጥላል...
ታኅሳስ 24 ቀን 2006 በሰላማዊቷና ዴሞክራሲያዊቷ ኢትዮጵያ በሰላም ለመገናኘት ያብቃን!

ፍጥረታዊ ፍትሕ ወይስ ዘረኛ ፍርደገምድልነት?


ፍጥረታዊ ፍትሕ ወይስ ዘረኛ ፍርደገምድልነት?

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት
ተበዳዩን  እንደ  ወንጀለኛ!
Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino.
ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የመርገጫ ማህተም የሆነውን ፓርላማ ግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ መለስ ዜናዊ ተገደው ከደቡብ ኢትዮጵያ  ‹‹የተፈናቀሉትን›› የአማራዎች (አንዳንዶች‹‹በተንኮል ዘዴ ዘር ማጥፋት›› ብለውታል) በተመለከተ፤ በጉዳዩ ላይ ተቃውሞ ያሰሙትንና ፤ ዜናውን እንዲሰራጭ ያደረጉትን፤ በደፈናው ሃላፊነት የሌላቸው በማለት በማዉገዝና እውነቱን ሸምጥጦ በመካድ ጨርሶ መፈናቀል እንዳልተካሄደ ለማሳመን ሲፈላሰፍ ታይቷል፡፡  መለስ  ስለመፈናቀሉ  ማሳሳቻውን ማስረጃ ሲያቀርብ አንዳችም መፈናቀል ያልተካሄደ በማስመሰል  አንዳንድ  ሕገወጥ ከሰሜን ጎጃም የፈለሱ (‹‹ሰፋሪዎች›› ይላቸዋል) ከደቡብ መኖርያቸው የተነሱበት ምክንያት ቦታው የአካባቢ ደንና ፊጥረታዊ  ሃብት ጥበቃ ነው ሲል ሊሞግት ሞክሯል፡፡ እንዲያውም ለምን ያሉትንና የጋራነት መታወቂያችን ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት የቆሙትን ድርጅቶች በተመለከተ፤ መለስ በጠራራ ጸሃይ ሲሰብክ:
….. ባለፉት አሰርት ዓመታት በታሪክ አጋጣሚ፤በርካታ ሰዎች፤… ወደ ሰላሳ ሺህ የሚጠጉ ሰፋሪዎች፤ ከሰሜን ጎጃም (የፈለሱ) በቤንጅ ማጂ ዞን (በደቡብ ኢትዮጵያ)ሰፍረዋል፡፡ በጉራ ፈርዳ 24.000 ሰፋሪዎች አሉ፡፡ ቦታው ጫካማ ስለሆነ ብዙ ሰው አይኖርበትም፡፡በተለያየ ሰበብና አጋጣሚ ሁሉም የድርሻውን ያገኛል የሚጎዳ አይኖርም፡፡እነዚህ ህገወጥ ሰፋሪዎች ባልተቀናጀ መልኩ ነው የሰፈሩት፡፡ እነዚህ ህገ ወጥ ሰፋሪዎች በተናጠልና በተመሰቃቀለ መንገድ፤ የአካባቢውንም የዓየር ሁኔታ በሚበክል መልኩነው የሰፈሩት፡፡ይህ ደሞ አጥፊና ጎጂ ነው፡፡
ሰፈራው የአካባቢውን ዓየር ሁኔታ ባገናዘበ፤ የጫካውን መጥፋት ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ታስቦ የተከናወነ አይደለም፡፡ድንግል የሆነው ጫካ መጠበቅ አለበት፡፡ሰፋሪዎቹበቀላሉ ሊለማ የሚችልና አፍሪ ቦታ ነው የፈለጉት፡፡ደን ሆነ አልሆነ ደንታ የላቸውም፡፡ደኑን እየጨፈጨፉ ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ከሰል ያከስላሉ፡፡ በዚህ የተነሳም በርካታየአካባቢ ብክለትና ጉዳት ተፈጽሟል፡፡…… ሰፋሪዎች ወደፈለጉበት ቦታ ሄደው በመስፈር የአካባቢውን ደን በማጥፋት መኖር አይችሉም፡፡ሕገ ወጥ በመሆኑ ሊቆምይገባዋል፡፡ ይህን እውነታ ለማጭበርበር የሚጥሩ ሁሉ ሃላፊነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ ዕውነትን አጥርቶ ማየት ያስፈልጋል፡፡የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብት በእኩል ደረጃሊጠበቅ ይገባል፡፡ አማሮች ተፈናቀሉ ለስደት ተዳረጉ በማለት የሚጮሁት ማንንም የማይጠቅም ቅስቀሳ ነው በማድረግ ላይ ያሉት፡………..
መለስ በቀላሉ ሲያስቀምጠው፤ እነዚህ ‹‹የሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› የአካባቢውን የደን ሁኔታ ያጠፉ ወንጀለኞች ናቸውና ተገደው መነቀልና መሰደድ አለባቸው፤ እንዲያውም በወንጀል ባለመጠየቃቸው እድላቸውን ሊያመሰግኑ ይገባል፡፡
የአፍሪካ  የከባቢ ዓየር  ዋና  ሹም
ስለአካባቢ ዓየር ሲነሳ በአፍሪካ ካሉት ከማንኛቸውም በበለጠ እውቀትና  ችሎታ ያለው ሰው ቢፈለግ ከመለስ ሌላ ጨርሶ የት ሊገኝ?! ምንስ ቢሆን የአፍሪካ ዋና የከባቢ ዓየር መኮንን ተብሎ የለም እንዴ!   በ2009 መለስ በኮፕንሃገን በተካሄደው ስብሰባ ላይ የአፍሪካዊያንን ተደራዳሪዎች በመምራት ተገኝቶ ነበር፡፡  በዚህ ቦታ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች መገኘት መንስኤውም፤የምእራቡ ዓለም እያጠፋና እያዛባ ያለውን የተፈጥሮ ዓየር፤ ደግሞም የተከተለውን የአየር ለውጥ፤በዓለም የሙቀት ሁኔታው መባባስን፤እና ሌላውንም በተመለከተ የሞራል ካሳና የገነዘብ መቀጫ ለመጠየቅ ነበር ዘራፍ ብሎ የተነሳው፡፡ በዚህም 40 ቢሊዮን ዶላር ካልተፋ ስብሰባውን  እንደሚያጨናግፈው ረግጦ እንደሚወጣ ደንፍቶ ነበር፡፡
እኛ በአናሳው የምናቀርበው ስምምነት ተቀባይነት ካጣ፤ ቁጥራችንን በመጠቀም ውሳኔው ውድቅ እንዲሆን እናደርጋለን…….እንዲያውም አካሄዳቸውና ውሳኔያቸውአህጉራችንን አስገድዶ የሚዳፈር ከሆነ ስብሰባውን ረግጠን እንወጣለን፡፡……..ከዚህ ቀደም ይደረግ እንደነበረው የአፍሪካ ፍላጎትና አቋም ሊታፈን አይችልም አይገባምም፡፡……. አፍሪካ፤የአፍሪካ ሕብረት አባላትን ሀገራት የሚወክልና ሙሉ ስልጣን ያለው አንድ ብቸኛ ተደራዳሪ ቡድን ትሰይማለች፤…. ለኔ ዋነኛው ቁልፍ ጉዳይ፤አፍሪካ የዓለምን አየር መዛባት አስመልክቶ በተፈጠረው ጉዳት ልትካስ ተገቢ ነው፡፡ በርካታ ኢኒስቲቲዩሽኖች ይህን በቁጥር ለማስቀመጥ ሞክረው የተለያየ ተመን አስቀምጠዋል፡፡ከዚህ በመነሳትም ማእከላዊው ቀመር በዓመት 40 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል፡፡
ስብሰባው በተጀመረ በማግስቱ ፤ መለስ ከ‹‹አፍሪካ አስገድዶ ደፋሪዎች›› ጋር በ10 ቢሊዮን ዶላር ውለታ ለመፈጸም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ሆነ፡፡ አፍሪካውያን ወንድሞቹንም ጥሬ ብር ከአርቲ ቡርቲ ቃላት ይሻላል በማለት አሳመነ፡፡
……እርግጥ ይሄ የኔ ሃሳብ ምናልባትም ከሕግ አኳያ ለደረሰብን በደልና ጥፋት፤ በልማታችን ላይ ለደረሰብን በደል ሙሉ ካሳ ይገባናል በማለት ሃሳብ ያቀረቡትንአፍሪካውያንን ቅር ሊያሰኝ ይችላል፡፡ የኔ ሃሳብ ቀስ በቀስ ወደ ተነሳንበት ቁጥር ያደርሰናል፡፡ ይህን ፈንድ መቆጣጠርና በዚህም የአስተዳደር ስልጣን ማግኘትና በወሳኝነት መቀመጥ ዋነኛ መሳርያችንና አስተማማኝ የፋይናነስ ፍሰት ማግኛችን ነው፡፡
በኦክቶበር 2011 መለስ በአፍሪካ ኤኮኖሚ ኮንፍራንስ ላይ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር፡-
……..በአህጉራችን ያለው መሬት፤ከመሬቱ መሳሳትና ከማለቁ የተነሳ ዛፎቹ ሁሉ ወድመዋል፤በአፈሩ መሸርሸር፤ለድርቅና ለጎርፍ፤በዓለም ላይ በመከሰት ላይ ባለው የዓየርመዛባት ሳቢያም ከዚህ ቀደም ታይቶ ወደማይታወቅ የጎርፍና የድርቅ ሁኔታ ተዳርገናል፡፡የአርሻዎቻችን መሰረትም እጅጉን አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡
ስለዚህም በመለስ አተማመን ወደ አውሮፓውያን አስገድዶ ደፋሪዎቻችን በመመለስ በድጋሚ ተጨማሪ የገንዘብ ካሳ ማግኘት ይኖርብናል፡፡
በኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊ ፍጥረታዊ ተሰጥኦዎችi ተንከባካቢነት
በአፍሪካ የዓየር ለውጥና የዓለምን የሙቀት ሁኔታ በተመለከተ መለስ ዜናዊ አዋቂ የሚል የለበጣ ስያሜ አግኝቷል፡፡ ይሁንና ግን በኢትዮጵያ ውስጥ በመካ ሄድ ላይ ስለአለው የአካባቢ ብክለት፤በተለይም በኢትዮጵያ የደኖችን መጨፍጨፍና መጥፋት በተመለከተ ግንዛቤ አለውን? የኢትዮጵያ የእርሻ ምርምር ኢኒስቲቲዩት (በሃገሪቱ ያለው ግንባር ቀደም የእርሻ ኢኒስቲቲዩት) ዘገባ እንደሚያመላክተው በ2020 ኢትዮጵያ ጠቅላላ ደኖቿን ታጣለች ብሏል፡፡
ባለፈው የምዕተ ዓመት ለውጥ ላይ የኢትዮጵያ ደን 40 በመቶ ነበር፡፡ በወታደራዊው አገዛዝ ዘመን በ1987 ላይ ወደ 5.5 በመቶ አዘቀዘቀ፡፡ በ2003 ወደ 0.2 ወረደ፡፡የትዮጵያ የእርሻ ምርምር ኢኒስቲቲዩት ኢትዮጵያ በየዓመቱ 200.000 ሄክታር ደን እንደምታጣ ይናገራል፡፡ በ1990 እና በ2005 መሃል ኢትዮጵያ 14.0 በመቶ የደን ሽፋኗንአጥታለች፡፡(2.114.00 ሄክታር) በተጨማሪም 3.6 ከመቶ የዛፍ ተክሎችን አጥተናል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በመጪው 11 ዓመታት ኢትዮጵያ በ2020 ደን አልባ ሃገር ወደመሆኑ ትሸጋገራለች፡፡
በ 2004 የተደረገ ጥናት እንደሚያስረዳው፤ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ሄክታር መሬቷ በደን በቀል ዛፎች የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 7 በመቶው የደን እርሻ ነው፡፡63 በመቶ ገደማው ጫካማው ቦታ ደሞ በኦሮሚያ ክልል ያለ ሲሆን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ደግሞ በ19 በመቶ ተከታይ ሲሆን፤ጋምቤላ 9 በመቶውን ያካትታል፡፡ በጣም የሚያስገርመውታዲያ መለስ ዜናዊ  የደን እንክብካቤን አስመልክቶ ትኩረት የሰጠው ለቤንች ማጂ/ ጉራ ፈርዳ መሆኑና፤ በ2012 በእጅጉ መጠን ያጣው ችግር፤ ስርአት አልባ የሆነው የውጪ የንግድሁኔታ በአካባቢው መዳበሩ መሆኑን ነው፡፡ ከዚሁ ጋርም የደኖችን መጨፍጨፍ ሰበብ ያደረገው እንቅስቃሴው በዘር ላይ የተመሰረተ ማሳደድና ነዋሪዎችን በትውልድ ሀረጋቸው ብቻ ለማፈናቀል መወሰኑ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን፤መለስ ለአካባቢ ደህንነት ተቆርቋሪ ለመምሰል ‹‹የሰሜን ጎጃሞችን ሰፋሪዎች›› በማስረጃ የተደገፈ መፈናቀል አወዛጋቢውን ርእስ ለመሸፈንና ከወቀሳና ከትችት ለመዳን በማታለያነት ተጠቀመበት?
መለስ ዜናዊ ስለአካባቢ ዓየር መቆርቆርን፤በሃሳብ መባዘንን ስለደኖች እንክብካቤ መቆጨትን፤ በማስመሰያነት ከመጠቀም ውጪ አንድም የእውነት ፍንጭ የሌለው ነው፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት፤መለስ ዜናዊ  በጣም ፍሬያማ የሆኑትን ለም የደን መሬቶች  ለሳውዲዎች ለሼሆቹ፤ለህንዶች፤ለቻይናዊያን፤ለኮርያውያኖችና የዶላርን ስም ለጠሩና ቁጥር ለጠቀሱ ሁሉ በሊዝ ስም ሸጦላቸዋል፡፡  እንደ የተከበረው የኦክላንድ ኢኒስቲቲዩት  [OI]  ግንዛቤ ከ2008 ጀምሮ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ
በትንሹ 3.619.509  ሄክታር  መሬት ለውጪ ኢንቬስተሮች (ቁጥሩ ሊበልጥም ይችላል) አስተላልፏል፡፡….የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት በመሬቶች ላይ ስለተከናነው ድርድር ሁሉ በውይይት መግባባት ተደርሶበት ነው፡፡ አንድም የተፈናቀለ ነዋሪየለም፡፡ የተሰጠው መሬትም በጥቅም ያልዋለ ጦም አዳሪ የነበረ ነው በማለት ቀልመድመድ ቢያደርግም የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ግን ከነዋሪዎች ጋር ተካሄደ ስለተባለው ውይይትአንዳችም ማረጋገጫ አላገኘም፡፡ ………..በውሃ አጠቃቀም ላይ አንዳችም ገደብ አልተደረገም፤በአካባቢው ዓየር ላይ ሊያደርስ ስለሚችለው ብክለት(EIA)  ምንም የተወሰደ ጥናት  አልነበረም፤ቁጥጥርም አልተደረገም፡፡ ኢንቬስተሮች ውሃን ያላንዳች ገደብ እንዲጠቀሙበት መፍቀድ እጅጉን የሚያስገርምና አሳዛኝ ደንታ ቢስነት ነው፡፡ የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ከኢንቬስተሮች በተደረገት ገለጻ፤ ምንም አይነት ቁጥጥርና ገደብም ስለሌባቸው የአካባቢውን ወንዝ በመገደብ ሊገለገሉበት እንዳቀዱና በአካባቢ የዓየር ቁጥጥርም አንዳችም ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን ገዢው መንግስትና ባለስልጣኖቹ የአካባቢ ዓየር ጥበቃ ይደረጋል በማለት ቢናገሩም  ከመንግስት በኩል አንድም የማስረጃ ማሳመኛ ሊያቀርቡ፤ ጥናትና ቁጥጥር ለመኖሩና ለመከበሩም ቢሆን አንድም የመንግስት ባለስልጣን ወይ ም የየአካባቢው ሹም በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ቦታው ደርሶ እንደማያውቅ ነዋሪዎች ሲመሰክሩ፤ ኢንቬስተሮችም ይህ ሁኔታ ለመከናወኑ አንዳችም ማስረጃ የላቸውም፤ የጠኝውም ሃገር ደግሞ ይህን አይነት ሁኔታ ተካሂዶበት አይውቅም፡፡………… ከአርሻ ይዞታ ላይ መፈናቀል በሰፊው የሚካሄድ የእለት ተእለት ሂደት ነው፤ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮችም ተገቢውን ማካካሻ አልተከፈላቸውም፤ከመኖሪያና እርሻቸው ሲነቀሉም በሌላ አካባቢ የእርሻ ቦታ እንዲፈልጉ በመደረግ በመሆኑ ከሌሎች የአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በቦታ ሰበብ ውጥረት እንዲፈጠር እየተደረገ ነው፡፡
በመጨረሻውም ሼሆቹ፤ሳውዲዎች፤ህንዶች፤ቻይናዊያን፤ ኮርያዎች (ሼሳህቻኮ)  ለሙን  መሬት በማቃጠል ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማብቀልና ለመክበር የተሰባሰቡትና መሬቱንም በሻጩ መንግስት የተከፋፈሉት ኢንቬስተሮች ሲባሉ፤ ለእለት ጉርስና ቤተሰቡን ለማኖር በማለት ኩራማን በምትሆን መሬት ላይ ኑሮውን ለማሸነፍ የሚጥረው ዜጋ ግን፤ ሕገወጥ ኗሪ (‹‹ሰፋሪ››) ይባላል፡፡ እነዚህ ስብስቦች (ሼሳህቻኮ) ለ‹‹ልማት›› በሚል የማደናገርያ ቃል፤በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር መሬት ለ99 ዓመታት ተሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከሞነርያ ቀያቸው በጉልበት በመፈናቀል የእርሻና የመኖርያ ቦታቸውን ለነዚህ ሼሳህቻኮች እንዲያስረክቡ ተፈርዶባቸዋል፡፡  ሼሳህቻኮች ከግምት በማይገባ ገንዘብ ያሻቸውን ያህል የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ ሲፈቀድላቸው፤ ኢትዮጵያውያን ግን የባለቤትነት ይዞታቸውን አንዳችም የገንዘብም ሆነ የቦታ ትክ ሳይደረግላቸው እንዲባረሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡  ሼሳህቻኮ  በብርሃን በግላጭ በአክብሮት የደስታ አቀባበል ሲደረግላቸው፤ ዜጎች ግን ጸሃይ ከመጥለቋ በፊት አካባቢውን ጥለው እንዲሰደዱ ይደረጋሉ፡፡ ሼሳህቻኮ የመሬት ባለቤትነት መብት ሲኖራቸው ኢትዮጵያውያን ደግሞ ለመሬት አልባነት ይዳረጋሉ፡፡  ሼሳህቻኮ የነገስታታነት ከበሬታ ሲሰጣቸው፤ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዱላ መባረርን ይቸራሉ፡፡ እንደ ኦክላንድ ኢኒስቲቲዩት ጥናት  ከሁሉም በላይ የሚያሳፈረው በ ሼሳህቻኮ እርሻዎች ላይ ለመስራትና ኑሮን ለመታገል የፈቀዱትም ኢትዮጵያውያን በመጤዎቹ እንደ እንስሳ በመቆጠር ለግፍ መዳረጋቸው ነው፡፡
ወደ ሼሳህቻኮ ግዛት እንኳን በደህና መጣችሁ!
የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› ሊያከብሩትና ሊከተሉት የሚገባ የአካባቢ ዓየር ሕግ አለን?
የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› ከይዞታቸው መነቀል አስፈላጊ መሆኑን መለስ ሲያስረዳ፤ ‹‹ሰፋሪዎቹ›› ሕገወጥ፤በዘፈቀደ ቦታውን የያዙ፤ እና የአካባቢ ዓየርንም ደህንነት የሚያበላሹ ናቸው በማለት ይወነጅላቸዋል፡፡ ለመሆኑ የመለስ ገዢ መንግስት፤ሕጋዊነትን የሚጠይቅ፤ ስርአት የተቀመጠለት፤የገጠር አሰፋፈር ደንብ አለው? ለምሳሌ በጉዳዩ ላይ የተቀመጠው ወሳኙ ሕግ፤ ‹‹የገጠር መሬት አስተዳደርና አጣቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/2005›› በእርሻ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ሁሉ፤ መሬትን ያለምንም ገደብ ይፈቅዳል እንጂ አሰፋፈርን በተመለከተ እንዴት መከናወን እንደሚገባው የሚለው አንዳችም ነገር የለም፤ ስለአስተዳደሩም የሚገልጸው ስርአት የለም፡፡ አተገባበሩን በተመለተ ሙሉ መብቱን ሙያው፤ብቃቱ፤ችሎታውም ለሌላቸው ‹‹የአካባቢው ባስልጣናት›› ትቶታል፡፡ በእርግጠኝነት አዋጅ ቁጥር 456 ስለ ደን መሬት ጥበቃ፤አስተዳደር አንዳችም የሚለው ቃል የለውም፡፡በደፈናው የግብር ይውጣ ያህል፤ ደን፣የደን መመናመን፤እና የደን መሬት በማለት ይዘጋዋል፡፡
የተሸሻላና አዋጅ ቁጥር 456ን የተካውም አዋጅ ቁጥር 106/2007 ቢሆን፤ እንዲያው በይሆናል ግምት፤የታወጀ እንጂ  ክልሉ የአካባቢ ዓየር ጥበቃ ኤጀንሲ የለውም፡፡ አዋጅ ቁጥር 456ን ተግባራዊ የማድረጉ ሃላፊነት በእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ ስር የተጣለ ሚንቀሳቀሰው ግን የተፈጥሮ ሃብትንና የዱር አራዊትን በመጠበቁ ላይ እንጂ  የደን ጥበቃውን በተመለከተ ጨርሶ የተጣለበትን ሃላፊነት አልተረዳውም ወይም ከጉዳይ አላስገባውም፡፡ የመሬት አጠቃቀም ገደብን በተመለከተ በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ድንጋጌ ቁጥር 66/2007 ከጫካማ ቦታዎች ወይም ደኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ግንኙነቱ ከውሃማ ቦታዎችን ከተንሸራታች መሬቶች ጋር ነው፡፡ በደፈናው ብቻ ደኖችን ስለማመናመን ወይም ስመጨፍጨፍና ለእርሻነት ስለማዋል የሚጠቅስ አንዳችም ክልላዊ ሕግ የለም፡፡ እና ታዲያ ‹‹ሰፋሪዎች›› ምን አድርጉ ነው የሚባሉት?
የፌዴራሉ ‹‹የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 542/2007›› ቢሆንም ዝም ብሎ የእቅድ አቅጣጫ ጠቋሚ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡አዋጁ የመንግስትንና የግል ደኖችን ያከብራል ይላል እንጂ፤ደኖች እንዴት ሊለሙ እንደሚችሉ የሚየሳየው አካሄድ አለያም ደግሞ ግለሰቦች በስራው ለመሰማራት ፈቃዱን ከየት እንደሚያገኙ አይገልጽም፡፡ አዋጁ የግል ደኖች አልሚዎችን ግዴታ ሲደረድር ስለመብታቸው ግን ምንም አይልም፡፡ የአዋጁ ብዘው ቦታ የተሞላው ወደፊት ምን ሊደረግ ይገባል በሚል የምኞት እቅድ ላይ ነው፡፡
መለስ የቤንች ማጂ ‹‹ሰፋሪዎች›› ከአስፈላጊው የአካባቢ ዓየር መመርያ አዋጅ ቁጥር 299/2002 ጋር በሚጋጭ ሁኔታ ነው በማለት ሊያሳስት ይሞክራል፡፡ ይህ አዋጅ አስቀድሞ የተባለው ፕሮጄክት ተግባራዊ ከመሆኑ አስቀድሞ ሊጠናና ሊመረመር ይገባዋል፡፡ የዚህ አዋጅ ቁጥር 299 አባባልና አተረጓጎም ‹‹ሰፋሪዎቹ››  የአካባቢን ዓየር ሁኔታ ከሚመለከተው ሕግ ተጠያቂነት ውጪ ናቸው፡፡ከዚያ ይልቅ ለአዋጅ ቁጥር 456 (የገጠር መሬቶች አስተዳደርና ጥቅም) ተገዢ ይሆናሉ፡፡ይህ ሁሉ የሕጋ ቃልና የቴክኒክ አጠራርና አላስፈላጊው ክርክር ሁሉ ይቀርና ጉዳዩ በሙሉ የፖለቲካ ጥያቄና የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ይሆናል፡፡  በጊቤ ግድብ 3 ሂደት ላይ የቀረበው የከባቢ ዓየር አስተያየት በግልጽ የሚያሳየው ሁኔታ የፖለቲካ ጉዳይ ሲሆን የሚያስከትለውን ነው፡፡
የዘር ጥሰት ወይስ የደን እንክብካቤ?
ከደቡብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ/ጉራ ፈርዳ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች በግዴታ መፈናቀላቸው አያጠያይቅም፡፡በአሜሪካ ድምጽ ላይ የተስተናገዱት ቃለ መጠይቆች፤ በግዳጅ መባረራቸውን በግልጽ ያስረዳል፡፡ስለዚህም ቸል የማይባለውንና ሊታለፍ የማይገባውን ጥያቄ ልንጋፈጠው የግድ ነው፡፡ይህ አስገድዶ ከቀዬ ማፈናቀል የዘር ጥላቻ ነው ወይስ የተለመደ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅ ነው? መለስ ዜናዊ ይህን አስገድዶ ማፈናቀልን በተመለከተ ማሳመኛ አድርጎ የሚያቀርበው  የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› የተፈናቀሉበት ምክንያት ደኑን በማጥፋታቸውና አሰፋፈራቸውም በተለምዶ እንደሚያደርጉት ስርአት ያጣና ከህግ ውጪ በመሆኑ ነው ሲል፡  የደቡቡ ገዢ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩሉ ደሞ  መለስ ስላነሳው ‹‹ሰፋሪዎች›› ስላደረሱት የደን መጨፍጨፍ፤ አንድም ቃል አልወጣውም፡፡ የፈጣሪ ያለህ ታዲያ ማን ሊታመን ነው?
ዘር ማጥፋት እንዲህ ነው ሊባል የሚችል ህጋዊ ትርጉም የለውም፡፡በ1993 የተባበሩት መንግስታት ኮሚሽን ቃሉን ሲተነትነው ‹‹ሆን ተብሎ ታቅዶ ከተወሰነ አካባቢ የተወሰነ ዘር ተወላጆች የሆኑትን በጉልበት፤ በማስፈራራት አፈናቅሎ ቦታውን ለሌሎች ዘሮች ለመስጠት የሚፈጸም››  ይለዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት ሴኪውሪቲ ካውንስል የባለሙያዎች ኮሚሽን ድንጋጌ 780 የዘር ማሳደድን ሲተነትንም በሰብዊ ፍጡሮች ላይ የሚፈጸም ወንጀል በመሆኑ እንደጦር ወንጀል ይቆጠራል ይላል፡፡የተለያዩ ድንጋጌዎችና ትንታኔዎች ወንጀልነቱን በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ ያረጋገጡት ነው፡፡የነዚህም ‹‹ሰፋሪዎች›› መፈናቀል ሆን ተብሎ በተመረጡ ብሄሮች ላይ የተፈጸመ ነዋሪውን የማግለል ደባ መሆን አለመሆኑ በተጠናቀሩት ማስረጃዎች ሊረጋገጥ የሚችል፤ጉዳይ ነው፡፡
ማካካሻ አይገባምን?
‹‹ሰፋሪዎቹ›› የተፈናቀሉት  የሃገሪቱን ደን ከጥፋት ለማዳን ነው ተብሎል የሚለውን የመለስ ሰበብ አምነን የምንቀበል ከሆነ፣ የተፈናቀሉትና ርስታቸውን፤ መኖርያ መንደራቸውን፤ ንብረታቸውን ያጡት ከፍ ላለ የሀገር ጥቅም መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ አባባሉ የሚታመን ሆኖ ፤በአዋጅ ቁጥር 456 ‹‹ሰፋሪዎቹ›› መሰረት መብታቸው ሊከበርላቸው የግድ ነው፡፡ በአዋጁ ላይ ‹‹የገጠር መሬት ይዞታው ለሕዝባዊ ጠቀሜታ የተወሰደበት ሰው፤ በነበረበት ቦታ ላይ ባለማውና ባፈራው ሃብት መሰረት ተመጣጣኝ ማካካሻ ሊያገኝ አለያም ተመጣጣኝ የሆነ ትክ ሊሰጠው ይገባል›› ይላል፡: እነዚህ ሰፋሪዎች ግን ለተዘረፉት ቦታ፤ እንስሳትና ንብረት እንዲሁም ላደረጉት የልማት ውጤት አንዳችም ማካካሻ አልተደረገላቸውም፡፡ ጸሃይ ስትጠልቅ በድቅድቅ ጨለማ አካባቢያቸውን ለቀው፤ በጀርባቸው የለበሱትን ጨርቅ ብቻ ይዘው: ሕጻናት ልጆቻቸውን አዝለው እንዲጠፉ ብቻ ነበር የተገደዱት፡፡ ሌላው ቢቀር ከሕጉ አባባል  አኳያ ማካካሻ ሊደረግላቸው አይገባም?
እረ የህግ ያለህ!     እረ የህግ ያለህ!

እንደ “ጠቅላይ ሚንስትሩ” አባባል ዋጋ ግሽበቱን ያባባሱት “አዳዲሶቹ ጤፍ በላተኛ” ሃብታሞች ናቸው


እንደ “ጠቅላይ ሚንስትሩ” አባባል ዋጋ ግሽበቱን ያባባሱት “አዳዲሶቹ ጤፍ በላተኛ” ሃብታሞች ናቸው

ዶ/ር ዘላለም ተክሉ
01/05/2013
በቅርቡ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች “ጠቅላይ ሚንስትር” ሃይለማርያም ደሳለኝ የሰጡትን ምላሽ በጥሞና አዳምጬው ነበር1:: በዚህ ምላሻቸው ከዳሳሷቸው ጉዳዮችEthiopian PM Hailemariam Dessalege chauvinism ideology ውስጥ ስለሃገሪቱ ሁለት አሃዝ ዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አፈጻጸም፣ የኑሮ ውድነት በተለይም የምግብ እህል ዋጋ ግሽበት፣ መራሩን የሃገር ቤት ኑሮ በመሸሽ ወደ ዓረብና አፍሪካ ሃገራት በሚሰደዱ ወገኖቻችን ላይ ስለሚደርሰው ሞትና ዘግናኝ ስቃይ፣ ስለፖለቲካ እስረኞች፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር ስላላት ግንኙነት፣ እንዲሁም በቅርቡ በአልጀዚራ ቃለምልልስ አስመራ ድረስ በመሄድ ከኤርትራ ጋር ያለቅድመ ሁኔታ ስለመደራደር ዋና ዋናዎቹ ነበሩ::
በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካውና በውጭ ግንኙነቱ ዘርፍ በአጠቃላይ የሰጡዋቸው ምላሾች  “ባለራዕዩ” የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ከነበራቸው ብልጣብልጥነትና ለዛ በስተቀር በይዘታቸው መቶ በመቶ ተመሳሳይ ነበሩ::  ምላሾቹ ባብዘኛው የኢህአዴግ የተለምዶ ማደናበሪያዎች ስለመሆናቸው ከዚህ በፊት በተለያዩ አካላት የተብራሩና ወደፊትም ምላሽ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ይሆናሉ ብዬ አምናለሁ:: ለኔ  በተለይ ትኩረቴን የሳበው ግን ስለ ዋጋ ግሽበት (Inflation) ትርጓሜና በተለይ የጤፍ ዋጋ እየናረ የመጣበትን ምስጢር በተመለከተ የሰጡት ትምህርት (Lecture) መሳይ ነገር ነበር::
ከሙያ አንጻር ስመለከተው የዋጋ ግሽበቱን በሚመለከት የሰጡት ትርጓሜ በግርድፉ ሲታይ “አማካሪዎቻቸውን” በመያሳማ መልኩ ያስረዱ ይመስላል:: የጤፍ ምርት ዋጋ እየናረ መምጣትንም ከገቢ ማደግ፣ ምርትና ፍጆታ መጨመር ጋር ለማያያዝ መሞከራቸው  በግኡዙ(Rubber Stamp) የኢትዮጵያ ፓርላማ ተቀባይነት ሊያገኝ ይችል ይሆናል ብዬ እገምታለሁ:: ነገር ግን የኑሮ ውድነቱ በየቀኑ እየተባባሰ በመምጣቱ የመራብና የመታረዝ ገፈቱን በተጨባጭ እየቀመሰ ላለው ህዝባችን ይህ ትምህርት (Lecture) ድራማና ስላቅ እንጂ ምንም ተብሎ ሊገለጽ አንደማይችል ላሰምርበት እወዳለሁ:: የዚህ ጽሁፍ ዋና ዓላማም ይህንኑ አይን ያወጣ ሽወዳ አይሉት መደናበር ከኔ እይታ ለመፈንጠቅ ነው::
የዋጋ ግሽበት ስለመቀነሱ የተፈጠር ብዥታ
አቶ ሃይለማርያም በመጀመሪያ ሲያስረዱ የሃገሪቱ ከፍተኛ ዋጋ ግሽበት ከወር ወር እየቀነሰ መምጣቱን ከጠቆሙ በኋላ ስለቀመሩ አሰላል ሲያስረዱ የአለፈውን ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ጋር በማነጻጸር የሚገኝን ልዩነት በማስላት እንደሆነ ገልጸዋል:: በመቀጠልም ይህ ቀመር አጠቃላይ የእርሻና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በአንድ ቅርጫት ውስጥ በማስገባት (Composite Good) እንጂ ለእያንዳንዱ ምርትበተናጠል ማስላት እንደማይቻል ደጋግመው አስረድተዋል:: የ“ጠቅላይ ሚንስትሩ” የትርጉም ግድፈት እንግዲህ የሚጀምረው ለተናጠል ምርቶች የዋጋ ግሽበት ቀመር ማስላት አይቻልም ከሚለው ይሆል:: አይቻልም የሚሉት ስሌት ላይ አጽዕኖት መስጠታቸው ከወር ወር እየቀነሰ መጥቷል ለሚሉት የዋጋ ግሽበት ሪፖርት መከላከያ ግድግዳ (Fire Wall) ለማቆም ፈልገው ነው ብዬ በመከራከር እንደሚከተለው ለማስረዳት እሞክራለሁ::
በአንድ ቅርጫት ውስጥ ሁሉንም ምርቶች በማስገባት ቀመሩን በምናሰላበት ጊዜ የእርሻ፣ የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ምርቶችን እንደ አንድ ምርት (Composite Good) እንዲሁም የእርሻ፣ የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዋጋዎችን እንደ አንድ ዋጋ (Composite Price) ስለምንቆጥራቸው በውስጣቸው ያለውን ልዩነት እንሸፍናቸዋለን:: ይህንን ልዩነት ነጥሎ ለማውጣት እንዲያስችል የገበያና ዋጋ ተንታኞች (Market & Price Analyst) በምርት ዘርፎች የተከፋፈለ የዋጋ ቀመር (Disaggregated Price Index) መስራታቸው የተለመደ አካሄድ (approach) ነው:: በዚህ አካሄድ መሰረት የግብርናውን ምርት በአንድ ቅርጫት ውስጥ፣ የኢንዱስትሪውና የአገልግሎት ምርቶችን ደግሞ በሌሎች ሁለት ቅርጫቶች ውስጥ በማስገባት የዋጋ ግሽበቶችን በተናጠል ማስላት ዓለም ያወቀውና ፀሃይ የሞቀው እውነታ ነው::
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከወር ወር እየቀነሰ መጥቷል እየተባለ የሚለፈልለትን የዋጋ ግሽበት ከላይ በተገለጸው መልኩ በምርት ዘርፎች በተከፋፈለ መልኩ ተሰልተው ቢቀርቡ ምን ያህል የተጋነነ (spurious) እና የተዛባ (flawed) እንደሆነ ማሳየት ይቻላል:: እስኪ አስቡት የአብዛኛው የግብርና ምርቶች ዋጋ ባለፈው ዓመት አይደለም ካለፉት ጥቂት ወራቶች በፊት እንኳን ከነበረው በላይ እየጨመረ በመጣበት ሁኔታ ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት መኖሩ ምን አጠያያቂ ያደርገዋል:: አቶ ሃይለማርያም የጠቀሱት ጤፍ ብቻ ሳይሆን የሽሮ እሆሎቹና ጥራጥሬዎች፣ ለቂጣና ዳቦ የሚሆኑት ስንዴና ገብስ፣ ለማጣፈጫ የሚሆኑት ቅመማ ቅመምና በርበሪ፣ የእንስሳ ምርቶችና ተዋጽኦዎች በሙሉ ዋጋቸው ጨምሯል:: በዚህ ዘርፍ በተናጠል የታየውን የዋጋ ንረት መንግስትም ቢሆን እንደማይክደው እርግጠኛ ነኝ:: አብዛኛዎቹ የኢንዱስትሪ ውጤቶችም ከዓመት ዓመት እየተወደደ በሚመጣው የውጭ ምንዛሪ ተገዝተው የሚገቡ በመሆናቸው የዋጋ ግሽበቱን የማባባስ አስተዋጽኦዋቸው ከፍተኛ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም:: ከኢንዱስትሪው ዘርፍ ምናልባት መሰረታዊ ፍላጎት የሆኑት ስኳርና ዘይት ናቸው እንግዲህ ዋጋቸው የቀነሰው:: ያም ለውጥ የታየው በአገር ውስጥ ያሉ አግሮ ኢንዱስትሪዎች ምርት በመጨመሩ ሳይሆን መንግስት ከውጭ አስመጥቶ በተቋማቱ አማካኝነት በአነስተኛ ዋጋ በማከፋፈል በወሰደው የማረጋጋት እርምጃ እንደሆነ ይታወቃል:: ትንሽ የሚታይና  የሚጠቀስ ለውጥ የተመዘገበው በአገልግሎት ዘርፉ ላይ ከመጣው ዕድገት ጋር የተያያዘ ነው ብሎ መገመት ይቻላል:: ብዙ ሆቴሎችና መንገዶች በመገንባታቸው፣ ተጨማሪ የስልክና የኤሌክትሪክ መስመሮች እንዲሁም የውሃ ቧምቧዎች በመዘርጋታቸው፣ በየገጠሩ የጤና ጣቢያዎችና ኬላዎች በመከፈታቸው የነዚህ ማህበራዊ አገልግሎቶች ዋጋ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ሊወርድ እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለኝም::
ነገር ግን አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደድህነቱ ከ 60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ገቢውን በምግብ ፍጆታ ላይ የሚያጠፋ ከሆነ፣ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ሲሰላ በአንድ ቅርጫት ውስጥ ከተካተቱት ምርቶች ውስጥ ከ 60 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት የምግብ ምርት ውጤቶች ናቸው ማለት ነው:: እንግዲህ አስቡት ከቅርጫት ውስጥ ከተካተቱት ሸቀጦች ውስጥ ከ 2/3ኛ በላይ የሆነው የምግብ ዋጋ መጨመርና 1/3ኛ የሚሆነው የአገልግሎት ኢንዱስትሪ ዋጋ መቀነስን ሁሉም በተስማማበት ሁኔታ እንዴ አድርጎ ነው የአጠቃላይ ምርት ዋጋ ግሽበቱ ቀንሷል ማለት የሚቻለው:: የትምህርት ጥራቱ “እንደሚወራለት ካልወረደ” በስተቀር የ4ኛ ክፍል ተማሪ እንኳን 2/3 ሲደመር -1/3 ይሆናል 1/3 እንጂ -1/3 ብሎ ይሳሳታል ብዬ አልጠረጠርም::
የጤፍ ዋጋ እየናረ መምጣት ሚስጥር
የዋጋ ግሽበት ስሌቱ ከወር ወር ቀንሷል እየተባለ የምግብ ዋጋ ለምን ጨመረ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ጤፍን እንደ ምሳሌነት ተጠቅመዋል::  ከላይ እንደተገለጸው የእያንዳንዱን ምርት የዋጋ ግሽበት ማስላት እንደማይቻል በማከላከል ይህንን መሰረታዊ ጥያቄ ሳይመልሱ አድበስብሰው አልፈውታል:: እርሳቸው እንዳሉት የጤፍ ምርት በብዙ ክልሎች ከ 20 እስከ 30 በመቶ ቢያድግም ዋጋው የበለጠ  እየናረ የመጣበት ምክንያት በኢኮኖሚ ዕድገቱ ሳቢያ ገቢያቸው ያደገ ነገር ግን ከዚህ በፊት ጤፍ በልተው የማያውቁ የህብረተሰብ ክፍሎች መመገብ በመጀመራቸው እንደሆነ አስረድተዋል:: ይህ ምላሽ ምንም ስሜት የማይሰጥና አስገራሚ ንጽጽር መስሎ  ስለታየኝ የኢኮኖሚክስ ግንዘቤዬን ወደኋለ ሄጄ እንድመረምር ተገደድኩኝ:: ካደረኩት አነስተኛ ምርመራም በጣም ጠቃሚ ምላሽ በማግኘቴ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ::
በኢኮኖሚክስ ንድፈሃሳቦች ውስጥ ዋነኛ በሆነው የፍላጎት ህግ (the Law of Demand) መሰረት (ሌሎች ነገሮች ሳይለወጡ Ceteris Paribus) የአንድ ሸቀጥ ዋጋ ሲጨምር ፍላጎት እንደሚቀንስና ዋጋው ሲቀንስም ፍላጎት እንደሚጨምር ይታወቃል:: ይህንን ህግ ከተከተልን እንግዲህ የጤፍ ዋጋ እየጨመረ በመጣበት ባሁኑ ወቅት ፍላጎቱና ፍጆታው መቀነስ ነበረበት:: በሃገራችን የተከሰተው ግን ከፍላጎት ህጉ በተቃራኒው ነው:: ኢኮኖሚስቶች እንደሚያስረዱት ይህን የተለየ ክስተት የሚፈጠረው እየተነጋገርንበት ያለው ሸቀጥ ጊፍን ሸቀጥ(Giffen Good) ሲሆን እንደሆነ ይገልጻሉ:: እነዚህ ጊፍን ሸቀጦች ሁለት ዓይነት ሊሆኑ ይችላሉ:: አንደኛው ዓይነቶች ዕለት ከዕለት በዋናነት አስፈላጊ (Necessary staples) የሆኑ እንደ ዳቦ፣ ስኳር፣ ዘይት፣ የምግብ ዕህሎች (ጤፍ፣ስንዴ፣ ሌሎች)፣ አትክልቶች(ሽንኩርት፣ቃሪያና ሌሎች) እና የመሳሰሉትን የሚያካትት ሲሆን እነዚህን ሸቀጦች ህዝቡ በየቀኑ ማግኘት ስላለበት ዋጋቸው ቢጨምርም እንኳን ሌሎች ፍላጎቶቹን (ልብስ፣ ጤና፣ትምህርት፣መዝናኛና የመሳሰሉት) በማቀብ በከፍተኛ ዋጋም ቢሆን የሚገዛቸው ናቸው:: ሌሎቹ ጊፍን ሸቀጦች ደግሞ  በዝቅተኛ ደረጃ ተፈላጊ (Inferior Good) ቁሳቁሶች ሲሆኑ ህብረተሰቡ ገቢው ሲያድግ በሌላ የተሻለ ጥራት ባላቸውና ውድ በሆኑ ሸቀጦች የሚተካቸው ናቸው::
እንግዲህ ከላይ በተዘረዘረው የኢኮኖሚ ንድፈ  ሃሳብ መሰረት አቶ ሃይለማሪያም በምሳሌነት የጠቀሱት ጤፍ  እንደ ጊፍን ሸቀጥነት መውሰድ ይቻላል:: ጤፍ በአስር ሚሊዮኖች ለሚገመተው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት የዕለት ከዕለት ምግብ (Necessary Staples) በመሆኑ ዋጋው እየጨመረ ቢመጣም እየገዛ መገበመገቡን የማያቆመው የእህል ዓይነት ነው:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በሥርዓቱ ተጠቃሚ የሆኑና ከዚህ በፊት ጤፍ ተመግበው የማያውቁ ጥቂት የህብረተሰብ ክፍሎች ቀድሞ ይመገቡት የነበረውን የእህል ዓይነት (Inferior Food) በመተው ወደጤፍ አመጋገብ ተሸጋግረዋል ማለት ነው:: ከሳቸው አባባል በመነሳት እነዚህ በቅርቡ ገቢያቸው የጨመረላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ኑሮዋቸው በመሻሻሉና ለቅንጦት ምግቡ ጤፍ ፍላጎታቸው በመጨመሩ በዋጋ ንረቱ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ማለት ነው:: ይህ ማለት ደግሞ በአስር ሚሊዮኖች የሚገመቱ ወገኖቻችን ዋና የዕለት ምግባቸውን በከፍተኛ ዋጋ ክፍያ ለማግኘት እየተንገታገቱ ባሉበት ወሳኝ ወቅት ውስጥ ጥቂት የህብረተሰብ ክፍሎች የዋጋ ንረቱ ሳያስጨንቃቸው ጤፍን እየተመገቡ በደስታና በድሎት እየኖሩ ነው ማለት ነው::
አገዛዙ ካላበቃ ድራማው ይቀጥላል
ከተለያዩ ወገኖች በተደጋጋሚ እንደሚተቸው ወያኔ በፕሮፓጋንዳ እንደሚለፍፈው ሳይሆን ለጥቂት ታጋዮችና የቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ጥቅመኛ ነጋዴዎች፣ የሥርዓቱ ተላላኪዎችና አጎብዳጆች ሃብት ፈጣሪ ቡድን እንደሆነ ይታወቃል:: የ”ጠቅላይ ሚንስትሩ” የፓርላማም ንግግር ይህንኑ የሚያጠናክር ይመስላል:: በአስር ሚሊዮኖች የሚገመተው ጤፍን በዋና የዕለት ምግብነት የሚጠቀመው ህዝባችን የዋጋ ግሽበቱ መከራውን እያበላው ባለበት ባሁኑ ወቅት፣ እንደቅንጦት ምግብነት በውድ ዋጋ ገዝተው የሚመጋቡ ጥቂት አዲስ ሃብታሞች መፈጠራቸውን አብስረውናል:: መቼስ በየቀኑ በኢትዮጵያ የሚሰማው ጉድ ማለቂያ የለውም:: ነገ ደግሞ የምንሰማው ተአምር ምን ይሆን? መቼም ይህ አገዛዝ የሚያበቃበት ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ድራማው መቀጠሉ አይቀሬ ነው!

የመጨረሻህ መጀመሪያ


የመጨረሻህ መጀመሪያ

በዚህ በውጭው ዓለም ለምንገኘው ለብዙዎቻችን ፥በተለይ ባለፉት 7 እና 8 ዓመታት ላቋቋምናቸው አጥቢያ አቢያተ
ቤተክርስቲያናት፥ ምርጫችንን እናት ቤተክርስቲያናት አድርገን ስንጓዝ፥ መንገዱ እንደዚህ እንደ ዛሬው ቀላል አልነበረም፥ የተለያዩ
ቅጥያ ስሞች እየተለጠፉብንና በአደባባይም ስንት ነቀፋ እየተቀበልንም ነበር። የወያኔ ቅጥረኞች እና የአባ ጳውሎስ አሽከሮች የሚሉት
በተደጋጋሚ የሚዘወተሩ ሲሆኑ አጥቢያ አቢያተ ቤተክርስቲያናቱን ለማህበረ ቅዱሳን አባላት ብቻ  እንደ ተቋቋመ የሚመለከቱንም
ቁጥራቸው ትንሽ አልነበረም። የሆነው ሆኖ ቅዱስ ሲኖዶስ አይሰደድም (ፓትርያርክ እና ሊቃነ ጳጳሳት ሊሰደዱ ይችላሉ)፣ የቅዱስ
ሲኖዶስ መንበሩ አዲስ አበባ ነው፣ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያናችን የመጨረሻው ወሳኝ የበላይ አካል ነው (ከፓትርያርኩም በላይ) ፣
እና የቅዱስ ሲኖዶስ መሪው መንፈስ ቅዱስ ነው የሚሉትን መሰረታዊ ሃሳቦች በማንገብ ነበር፥ ቅዱስ ሲኖዶስን ለውጭው ዓለም
በድጋሚ ያስተዋወቅነው። ዛሬ ፥በተደጋጋሚ እየመጡ ያስተምሩን የነበሩ መምህራን ሳይቀር፥ ይህ የሰላም ድርድር፥ በአውሮፓና
በአሜሪካ ለምንገኝ የቤተክርስቲያኗ ልጆች ብቻ የሚደረግ፥ አገር ቤት ያሉ ቅጠል ሸጠው ያስተማሩን ወላጆቻን ከእኛ የተለየ ፍላጎት
እንዳላቸው አድርገው፥ ሲናገሩና በየብሎጋቸው ሲጽፉ የተስተዋሉት። አዝነንባችኋል! አንድ  ለወደፊቱ  የምንገባላችሁ ቃል ቢኖር ፥
ውሎአችሁ ከማን ጋር እንደሆነ በስፋት እናጠናለን!! ነው። ወደ ዋናው ቁም ነገር እንገባ።
የተከበራችሁ የተዋሕዶ ልጆች ፥ የዛሬ ሃያ ዓመት፥ እንኳን እናት ቤተክርስቲያናችን ፥ ኢትዮጵያ ሀገራችን የወደ ፊት
ዕጣዋ ምን ሊሆን መገመት በማይቻልበትና ማለቂያ ለሌለው የእርስ በርስ ጦርነት ልትዳረግ ጫፍ ላይ ባለችበት ወቅት፥ የተፈጸሙ
ታሪካዊ ስህተቶችን ፥ ዛሬ በሰከነ አእዕምሮ ስንመለከተው ሊያስቆጨን ጀምሮአል። ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ለምትቸገርባቸው አብዛኛዎቹ
ችግሮች መነሻው ፥ ከጫካ የመጣው እንግዳው መንግስት ብቻ ሳይሆን ፥ ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ አባልነት ያሉ አረጋውያን አባቶቻችን፣
በውጭው ዓለም የሚገኙትም አረጋውያን አባቶች፣(ሙት ወቃሽ አትበሉኝ እንጂ ከሁለቱም ወገን ፥ወደ እውነተኛው ቦታ የሄዱትን
አባቶች) ጨምሮ፥ የሚፈለግባቸውን ኃላፊነታቸውን ባለ መወጣታቸው ነው። አንዳንዶቹም ልክ እንደ ዛሬዎቹ ጥቂት ጳጳሳት መንበረ
ፕትርክናው ቃል ስለተገባላቸው ነበር፥ በአንድ ልብ ፥ቅዱስ ፓትርያርኩ ለቅዱስ ሲኖዶስና ለመንግስት የጻፉትን ደብዳቤ ወደ ጎን
ገፍተው የወደዱትን ያደረጉት። አንድ ትልቅ  ቁርጠኛ የተዋሕዶ አባት አቡነ በርተሎሜዎስ ግን በይፋ ተቃውመው፥ << እኔ በዚህ ነገር
አልስማማም >>። ብለው በማለታቸው፥ ድምጻቸው በድምጸ ተዓቅቦ ተመዝግቦላቸው፥ ለታሪክ ትዝታ ጥለው አርፈዋል።
ከባለፈው ታሪክ << ጥሩ>> ልምድ የቀሰመው የኢሕአዲግ መንግስት እንደ ልማዱ የገዛ አባቶቻችንን አሰልጥኖ
ለምርጫ አዘጋጅቶልናል። ለቤተክርስቲያናችንና ለብጹአን አባቶቻችን ያላቸውን ንቀት በአደባባይ << ጳጳሳቱ አይረቡም >> ሌላም
ሌላም እያሉ ሲናገሩ እንኳን የማያፍሩ፥ በእውነቱ ከቤተክህነቱም ሆነ ከሌላ ጠያቂም የሌለባቸው << ነጻ ዜጎች ናቸው>>።  መንግሥት
በልዑካኑ ተጠቅሞ፥ የስድስተኛ ፓትርያርክ ማስመረጫ ደንቡንም በሚስፈልገው መልኩ ቀርጾ ፥ ለቤተ መንግስቱ ያልተጠቀመበትን
የዕድሜ ገደብ (ለፕሬዝዳንቱ ማለቴ እንደሆነ ይታወቅልኝ)፥ በመጀመሪያ አረጋውያኑን ከጨዋታ ውጪ አስስወጣ። ብልጣ ብልጦቹ
አባቶቻችን ደግሞ በድርብ ዜግነት ሽፋን ዋናውን የመንግስት ዕጩ ጨምሮ፥ አንድ አራቱን አባቶች፥ ከምርጫ ውጭ አደረጉበት።
ለጊዜው መንግስትም ከእነርሱ መካከል በሁለተኛና ሶስተኛ ዕጩዎች እንዲረጋጋና፥ እንዲገፋበት ተገዷል። ባለፉት ሁለት ሶስት
ድርድሮች፥ልክ እንደ ዲፕሎማት ያዝ ለቀቅ እያደረጉ የተደራደሩት አባቶቻችንም፥ ድርድሩ ከመልካም ፍጻሜ የመድረስ ዕድሉ
እየጨመረ ሲመጣ ያለ ይሉኝታና ፍርሃት፥ የሰላሙን ሂደት ለማደናቀፍ የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ ምክንያታቸውን በመደርደር ላይም
ይገኛሉ።
የሰላምና አንድነት ኮሜቴው የቅዱስ ሲኖዶስ አካሄድን ተመልክቶ ባወጣው መግለጫ ያልተደሰቱትና፥ የፕሬዚዳንቱ
ደብዳቤ ያደናገጣቸው የቤተክህነትና የመንግስት ባለሥልጣናት ድርድሩ እየተካሄደ የሰጧቸው ቃለ ምልልሶች የመጀመሪያዎቹ
አመላካች ማስረጃዎች ናቸው። ከዚያም በእነ ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስና በ<<ንቡረ ዕድ>> ኤልያስ የሚወከለው መንግስት በጥሩ መንፈስ
የሰላም ድርድሩን ሲካፈሉ የነበሩትን የቅዱስ ሲኖዶስ ሰላም ልዑካን አስፈራርተው የሚያሳዝን መግለጫ ማውጣታቸው ሌላው
ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ከዚያማ በውጭው አለም የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን ቁጣው ሲገነፍል፥ መንግስት በግልጽ ርምጃ ወደ
መውሰድ ገባ። የሰላም ልዑኩን ሊቀ ካህናትን አስሮ አንገላታ፥አቋማቸውን እንዲለውጡ በግልጽ ጠየቀ። ሌላው የሰላም ልዑክም ከዚያ
ያልተናነሰ ወከባ አጋጥሟቸዋል፥ ለእስርም ሊዳርጓቸው ዝግጅታቸውን ጨርሰው ሲያበቁ በእግዚአብሔር ቸርነት ወደ መጡበት
ተመለሱ። ይህ ሁሉ ወከባ ለምን አስፈለገ?
እጅግ የምንወዳቸውና የምናከብራቸው  አባቶቻችን ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብጹዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ ብጹዕ አቡነ
ቄርሎስ፣ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብጹዕ አቡነ እንድርያስ ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ እንዲሁም ሌሎች፤ ታህሳስ 23 በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ
ስብሰባ ላይ ያሳያችሁት ቆራጥነት መንፈሳዊ ኩራት ሆኖናል። በርቱ!! እኛ በውጭም በሀገር ውስጥ ያለን ልጆቻችሁ እስከ መጨረሻው
ከእናንተ ጋር አብረን እንቆማለን። እዚህ ላይ አንድ አስተያየቴን መስጠት የምፈልግበት ጉዳይ አለ። ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላምና አንድነት
ኮሜቴው በሌላ እንዲተካና ኮሜቴው ለሌሎችአደራዳሪዎች ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ያለፈ ሚና እንዳይኖረው የተፈለገው ለምንድን
ይሆን??

ለመሆኑ በእናት ቤተክርስቲያናቸው ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያደጉ፥በክፉም በደጉም ሰዓት ለቤተክርስቲያናቸው
መስዋዕትነትን የከፈሉትን፥ ስንቱን የቤተክርስቲያን ገመና ሸፍነው የያዙ አባቶችን የሚያስመርጥ ሌላ አደራዳሪ ተገኝቶ ነው? ምንድን
ነው፥ የሰላምና አንድነት ኮሚቴ ያጎደለባችሁ? ዕርቅ አውርዱ ስድስተኛ ፓትሪያርክ ለመምረጥ የምታደርጉትን ሩጫ አቁሙ
ስለተባላችሁ ነውን? በምትካቸውስ የታሰቡት የቤተክርስቲያኗ ልጆች ይሆኑ? ወይስ የቤተመንግስቱ? ቤተክርስቲያን መዳኘት ያለባት
በዓለማውያን እጅ ይሆን? ወይስ እነ ፓስተር እከሌ ወይም ፕሮፌሰር እከሌ ወይም እነ አትሌት ወይም ራስ፥ ደጃዝማች ስላልገቡበት
ይሆን ቅር ያላችሁ? ጥቂት የመንበረ ፕትርክና አላሚዎች የሰላሙን ሂደት ከመንግስት ጋር በመሆን ሊያበላሹት ስለሆነ እባካችሁ
አባቶቻችን ድካማችንንና የቤተክርስቲያንን ልጆች ጩኸት አሁንም አዳምጡ እላለሁ።
ሌላው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ፥ በግልጽ ቋንቋ ለመናገር ፥ መንግስትም ሆነ የመንበረ ፕትርክና አላሚዎች መቼም
ቢሆን  ያሰቡትን ከማድረግ አይተኙም። እናንተም እኛም ልጆቻችሁ ለረጅም ጉዞ እንዘጋጅ። ብጹአን አባቶቻችን ከመካከላችሁ ማን

ምን እንደሆነ ታውቁታላችሁ። እኛ ምዕመናኑ እንኳን በሚገባን መጠን ገብቶናል። ከመሀክል ያሉትን ጊዜና ሁኔታዎች በሚፈቅዱበት
አካሄድ የሚገባውን ዕርማት ማድረግ ትችላላችሁ። ከሁሉ በፊት ግን ከዘበኛው ጀምሮ የቤተክርስቲያኒቷን ጥሪት እየተመገበ ታማኝነቱ
ለውጭ የሆነውን ሁሉ (የመንግስት ቅጥረኛም ሆነ የሌሎች) ፥የሥራ ስንብት ወረቀቱን ስጡት። ቅዱስ ሲኖዶሱ ነጻ አየር እንዲተነፍስ
አድርት። እነ አቶ ብርሃኔ እነ ማን ናቸው ? ማን ቀጠራቸው? ከዚህ ቀደም አቡነ ጳውሎስ በሰጡት ይሁንታ ተጠቅሞ፥ መንግስት
በደህንነት ክፍሉና በእነዚሁ << ዘበኞቻችን>> በእናንተ ብጹአን አባቶቻችን ላይ ያደረሰው ጉዳት ይረሳል ወይ? ለምን መንገዳችሁ ላይ
እንቅፋት ተቀምጦ እያያችሁ ታልፉታላችሁ?  በአጠቃላይ ሕብረታችሁና አንድነታችሁ እንዳይሳሳ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ።
በውጭውም ዓለም የምትገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች እንዲሁ ለረጅሙ ጉዞ ተዘጋጁ። አቋማችሁ ግልጽ ይሁን።
ስድስተኛ ፓትርያርክ ቢሾም አንቀበልም ብሎ ለማለትን አትፍሩ። ከእናት ቤተክርስቲያን መለየት ሳይሆን እናት ቤተክርስቲያን በስልጣን
ወዳጆችና በአደር ባዮች መንገዷን እንዳትስት መርዳት ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ሊመራ የሚገባው ከመንግስት ምክር ቤት በሚወጣ
መመሪያ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው። በመንፈስ ቅዱስ የማይመራ ሲኖዶስ የእናት ቤተክርስቲያን የበላይ አካል ተብሎ ሊጠራ
አይገባም። ፍርሃታችሁን አስወግዱ፥ ቢያንስ በውጭው ዓለም ያላችሁን የመናገር መብት ለበጎ ነገር ተጠቀሙበት። ከእናንተ ጋር አብሮ
ተሰዶ ያለ የመንግስት ሰላይ አያስፈራራችሁ። አጋልጣችሁ ላላችሁበት መንግስት አሳልፋችሁ ስጡት። ሽፍንፍን ይቅር። እዚህ ላይ፥
ሀገር ቤት ንብረቴ ይወረስብኛል፣ የኢሕአዲግ መንግስት፥ ሀገሬ አያስገባኝም ፥ብለው የሚፈሩትን አይጨምርም። እነዚህ ወገኖች
መቼም ለራሳቸውም፥ ለቤተክርስቲያናቸው አይሆኑም። እሾሁ አንቋቸዋልና!
ትልልቆቹ እና ትንንሾቹ ማህበራት፣ የሰንበት ትምህርትቤት ተማሪዎች ለቤተክርስቲያናችሁና ለአባቶቻችሁ እንደ
አጥር ሁኑ። ዝምታችሁ ይብቃ። ይህ ወቅት ለእኛ መፈተኛ ጥያቄ አቅርቧል። መልስ ያሻዋል። አሁን!!
እስከ አሁን የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሀሳብ ያልሰጣችሁ አቢያተ ክርስቲያናት እባካችሁ ትልቅ ወንዝ የብዙ ጠብታ
ውሃ ጥርቅም መሆኑን አስታውሱ። መንግስትም ሆነ እኒህ <<አባቶቻችን>> በሰሙትና ባዩት ተቃውሞ ምንኛ እንደተረበሹ
ከሚወስዷቸው ርምጃዎች ተረዱ። ያላችሁን ሃሳብም ይሁን ድጋፍ ግለጡ። አሁን የማይጠቅም ነገር የለም።
ሲሆን ሲሆን ቤተክርስቲያን ጠንክራ ባላት ምዕመናን ብዛትና መዋቅር ጥቅሞቿን ለማስከበር መንግስትንና ፖሊሲዎቹ
ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ደረጃ ላይ ብትደርስ ምኞቴ ነበር። አሁን ግን መንግስት አጥር አልፎ የቤተክህነቱን ደንብ ቁጭ ብሎ እስከ ማርቀቅ
ደረሰ። ትልቅ ድፍረትና ንቀት ነው። ይህ በዚህ መቀጠል የለበትም። የኢሕአዲግ መንግስት እኛ አልደረስንብህም እባክህ ልብ ግዛ።
ሕዝበ ምዕመናኑን ወደ አልተፈለገ መንገድ አትምራው። ያለበለዚያ የመጨረሻህ መጀመሪያ መሆኑን እወቅ። የእኛ ጥያቄ
የቤተክርስቲያናችንን ዕጣ ፈንታ እኛ ብቻ እንድንወስን ተወን!! ምነው የራስን ጉዳይ በራስ መወሰን መብት የአንድ ወቅት መፈክር ብቻ
ሆኖ ቀረ?
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልዕክተ ተዋሕዶ -ዘ ሮኪ ነኝ

አዉራ የሌለዉ ትግል፤ እረኛ የሌለዉ መንጋ ነዉ - እኔ መሪዩን መርጫለሁ እናንተስ? ከፍስሃ እሸቱ (ዶ/ር)




በቅርቡ ከዳር ቆሞ ለዉጥን መጠበቅ የህልም እንጀራ በሚል በትግሉ ጎራ ላይ ያለኝን የግሌን አመለካከት የሚገልፅ
ፅሁፍ ለወገኖቼ ማቅረቤ ይታወሳል። ይንንኑም ተከትሎ የተለያዩ አስተያቶች ከበርካታ አንባብያን ደርሰዉኛል።
ወገኖቼም በቀረበዉ ሀሳብ ላይ ተነስታችሁ ለሰጣችሁኝ ገንቢ አስተያቶች የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁኝ። ከበርካታ
ወገኖችም በፅሁፉ የተዘረዘሩትን ችግሮችና የመፍትሄ ሀሳቦች በመገምገም በቀጣይነት ምን ማድረግ አለብን ትላለህ
የሚሉ በርካታ ጥያቄዎችም ቀርበዉልኛል። በበኩሌም ለጥያቄዉ ከፍተኛ ትኩረትን በመስጠት የላይና የታቹን
በማሰላሰል፤ የግራና የቀኙን በማመዛዘን፤ በልቤ የሚሰማኝን ከህሊናዩ ጋር በመሟገት ለዉይይትና ለተግባራዊነቱ በጋራ
እንድንቀሳቀስ አዲስ ሀሳብ (thesis) አቀርባለሁኝ።
ባለፈዉ አንድ አመት ጨቅላ የትግል ተመክሮዬ፤ በነፃነት ትግሉ ጎራ ዉስጥ ከበርካታ ወገኖች ደግሞ ደጋግሞ
የሚነሳዉና አብዛኛዉ ህብረተሰብ የሚስማማበት ጉዳይ የህወሃት/ኢህአዴግ ስርአት ለሃያ አንድ አመታት በላያችን ላይ
እንደፈለገዉ እየጨፈረብን፤ ህዝባችንንና አገራችንን እያመሰ፤ ወገኖቻችንን እያሰቃየ፤ ከሃገር እያሰደደ፤ እያሰረ ሲሻዉም
እየገደለ፤ ተንሰራፍቶ አገራችንና የኢትዮጵያዊነትን ስሜት እያጠፋ ያለዉ በስርዓቱ ጥንካሬ ሳይሆን ባንፃሩ በተቃወሚ
ጎራዉ አንድነት መጥፋትና መዳከም ነዉ። የህዙቡንም ስሜት ባጭር ቃላት ስናስቀምጠዉ አሰባሳቢ መሪ ወይንም
አዉራ መታጣቱ ነዉ።
በትግሉ ጎራ ሁሉም ስርዓቱን የመለወጥ በምትኩም ፍትህ የሰፈነባት፤ ህዝቦቿ በእኩልነት፤ በነጻነት፤ በክብርና፤
በአንድነት የሚኖሩናት፤ በፍፁም ዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጦ ህዝቡን የሚገዛ ሳይሆን የሚያገለግል መንግሥት
የሚመሰረትባት ኢትዮጵያን መመስረት አንድ ቋንቋ ይናገራሉ። ሆኖም ይህንን አንድ ቋንቋ እየተናገሩ፤ እንደ ባቢሎን
ቋንቋ ተቃዋሚዉ መደማመጥ፤ መከባበር፤ መተባበር፤ መቻቻል፤ አቅቶት፤ ህብረተሰቡም ማንን መደገፍ እንዳለበት ግራ
ተጋብቶ ሁሉም ዉጥንቅጡ ባለበት ሁኔታ ዉስጥ እንገኛለን። ጉዳዩ ባጭሩ ሲጠቃለል የሚያስተባብረን፤ ምክር
የሚሰጠን፤ አቅጣጫ የሚያሲዘን፤ ስንጣላ የሚያስታርቀን፤ ስንደክም ሚያበረታታን፤ የአንድነታችን፤ የጥንካሬያችን
የተስፋችን ምልክት መሪ ማጣታችን ትልቅ ኪሳራ ላይ ጥሎናል።
እኛ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለእኩልነት፤ ለዲሞክራሲ፤ ለአንድነት፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ክብር ከምንም በላይ
ሁላችንንም የሚያኮራ የትግል አላማ ይዘን መሪ አጥተን እየተንከራተትን ሳለን፤ ባንፃሩ ገዳዮች፤ ጨቋኞች፤ ዘረኞች፤
ከፋፋዮች፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በእርኩስ ተግባራቸዉ እያጠፉ ያሉች የስርዓቱ አቀንቀኞች ግን በህይወት
ብቻም ሳይሆን ሞቶም እንኳን አንድ አድርጎ እስተባብሮ የሚመራቸዉ ማግኘታቸዉ ብርታትንና ጥንካሬን ሰጥቷቸዉ
የመሪን፤ የመተባበርንና ያንድነትን አስፈላጊነት በተግባር እያስተማሩን ይገኛሉ።
የእራኤል ልጆች በፈርኦኖች አገር ሲማቅቁ መሪያቸዉ ሙሴ ነፃ አወጣቸዉ፤ አርባ አመትም በበረሃ ሲንከራተቱ
የብርታታቸዉ፤ የጥንካሬያቸዉ፤ የአንድነትና የተስፋቸዉ ምሰሶ ሆናቸዉ፤ ጥቁሮች በነጮች ጭቆና ሲዳክሩ ማርቲን
ሉተር ኪንግ የአንድነታቸዉና አቅጣጫ ጠቋሚያቸዉ ሆኖ በእርሱ ራእይ ጥቁሮች ነፃ መዉጣት ብቻ ሳይሆን ዛሬ ታላቋ
ሀገር አሜሪካ በጥቁር መመራት ጀምራለች፤ በደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች አገራቸዉን ተነጥቀዉ እንደ እንስሳ ሲገዙ ማንዴላ
የትግላቸዉ ምልከትና አስተባባሪያቸዉ በመሆን ነፃ እንዲወጡና በአለም ላይ የነፃነት ተምሳሌት ለመሆን በቅቷል።
ሌሎችም እንደ ጋንዲ፤ አን ሳን ሱቺ፤ የመሳሰሉ የነፃነት አዉራዎችን በዚሁ አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል። አኛ የነፃነት
ትግል እያከናወንን የመገኘታችን ያክል ከነዚህ አገሮች የመሪን አስፈላጊነት የምንማር ይመስለኛል።
ጊዜዉና ትግላችን የራሳችን ማንዴላ፤ የራሳችን ማርቲን ሉተር ኪንግ፤ የራሳችን ጋንዲ እንዲሁም የራሳችን አን ሳን ሱቺን
የመሰለ የሚያስተባብረን፤ ያንድነታችን፤ የነፃነታችን፤ የአልሸነፍ ባይነታችን፤ ምልክት የሚሆን መሪን እየጠየቀ ይገኛል።
ብዙዎቻችን የአሰባሳቢም ሆነ የመሪ አስፈላጊነት ላይ የምንስማማ ቢሆንም ዋናዉ ጥያቄ ግን ለመሆኑ እንዲህ አይነት
መሪ በሀገራችን ይገኛል ወይ የሚለዉ ሆኗል። ለጥያቄዉ ያለኝ አጭር ምላሽ ያለመጠራጠር በትክክል ይገኛል ነዉ።
ከዚህ አንጻር ሌላዉ የሚነሳዉ ጥያቄ የምንፈልገዉ መሪ ምን ምን መስፈርቶችንና ባህሪዎችን መላበስ ይኖርበታል
የሚለዉ ይሆናል። በኔ እምነት መሪዬ ብዬ የምከተለዉ ፍፁም የአገር ፍቅር ያለዉ፤ ለሀገሩና ለቆመለት መርህና አላማ
ለመሰዋት ወደሗላ የማይል፤ አርቆ አሳቢ፤ በሚያወራዉ ሳይሆን በተግባር የተፈተነ፤ በትግሉ ሳያሰልስ ለአመታት

በመታገል መስዕዋትነትን እየከፈለ የሚገኝ፤ እንደወርቅ በእሳት የተፈተነ፤ ለማንም የፖለቲካ ቡድን የማይወግን፤ ለሰዉ
ልጆች ክብር ያለዉ፤ መልካም ስብእና ያለዉና፤ ሀገራዊና አለማቀፋዊ እዉቅናና ተቀባይነት ያለዉ እንዲሆን
እመርጣለሁ።
መቼም ነብይ በሀገሩ አይከበርም ሆኖብን ነዉና ኢትዮጵያ በታሪኳ የእንደዚህ አይነት ጀግኖች መካን ሆና አታዉቅም።
ሀገራችን ታሪካቸዉንና ገድላቸዉን በኩራት የምንዘክርላቸዉ በርካታ ብርቅዬ ልጆች ያፈራች ስትሆን በዘመናችንም
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ልንኮራባቸዉና ሊመሩን የሚችሉ የጊዜአችን ጀግኖች አሉን። ከነዚህ
ብርቅዬ የሀገራችን ልጆች መካከል አንዱን መርጠን በማክበርና ልንሰጠዉ የሚገባንን ድጋፍ በመስጠት ከልባችን
የምንከተለዉ መሪያችን በማድረግ አሁን በየአቅጣጫዉ የተበታተነዉን ትግል ማሰባሰብ ይጠበቅብናል። ትግሉ
ከተሰባበሰ፤ ከተቀነባበረና፤ አቅጣጫና ግብ ኖሮት ከተከናወነ ጥንካሬ በማግኘት ዉጤታማ መሆኑ አይቀርም። ስለዚህ
ምርጫዉ የሁላችንም ነዉ። በዘመነ መሳፍንት በታሪካችን እንዳሳለፍነዉና በወቅቱም ትግል እንደምናደርገዉ ሁላችንም
የየራሳችንን ትንንሽ ዘዉዶች ደፍተን እርስ በእርሳችን እየተናቆርን ትናንሽ የሃሳብ ጉልቶችን ይዘን መቀመጥ። ወይም
ፈረንጆቹ እንደሚሉት ከጊዜዉ ጥያቄ ጋር አድገን፤ ከራሳችን በላይ ሀገራችንና ህዝባችንን አስቀድመን በአንድ መሪ ዙርያ
በግልም ሆነ በድርጅት ተሰባስበን ትግላችንን ማከናወን።
የኔ፤ የግሌ ምርጫ ግልፅ ነዉ። መሪ እፈልጋለሁ። የራሴን ኢትዮጵያዊ ማንዴላ እፈልጋለሁ። አስተባባሪ፤ መካሪ፤
አቅጣጫ ጠቋሚ፤ አስታራቂ፤ የተስፋ፤ የአላማና የኢትዮጵያዊነት ምልክት። ወያኔ ሟቹን መሪያቸዉን ታላቁ መሪ
ብለዉ እንዳመለኩት፤ እኔም የኔ የምለዉ መሪ እፈልጋለሁ። ለመሪዬም የሚገባዉን ክብርና፤ ድጋፍ፤ ለመስጠት
እሻለሁ። በመሪና በኢትዮጵአዊነት ካምፕ ዙርያ ተሰባስበን ዘላቂ፤ መሰረታዊና እዉነተኛ ለዉጥ እንዲመጣ እሻለሁ
ለተግባራዊነቱም እታገላለሁ። በዚሁም የልባዊ ፍላጎትና ጽናት በመነሳት መሪዬን ከጀግኖች መካከል መምረጥ
ጀመርኩኝ። የህሊና ምርጫዉም እጅግ አስቸጋሪ ነበር። ሁሉም ጀግኖቻች በተለያ ደረጃ የራሳቸዉ የሚከበር ባህሪና
የከፈሉት መስእዋትነት ቢኖርም የግድ አንድ መምረጥ ስለሚኖርብኝ ሁሉምን ሚገባቸዉን ክብር በመስጠት ምርጫዬ
ግን አንዱ ላይ አመዘነ።
የኔ ኢትዮጵያዊ ማንዴላ ማነዉ በምንስ መመዘኛ ተመረጠ? ለሚለዉ የኔ ኢትዮጵዊዉ ማንዴላ
1. በትግሉ ከሃያ አመታት በላይ ተፈትኖ እስካሁን ያለማመንታት በፅናት እየታገለ ያለ፤
2. ለኛ ነፃነት፤ ለፍትህ፤ ለመናገር መብት ለእኩልነት በመቆሙ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ በፋሽሽቱ ስርዓት ለእስር
የተዳረገና አሁንም ለበርካታ አመታት ተፈርዶበት ወህኒ እየማቀቀ ያለ፤
3. ሀብትና ንብረቱን ለሀገሩና ለወገኑ ክብር አሳልፎ የሰጠ፤
4. ለሀገሩና ለወገኑ ነፃነት እስከ መሞት ለመታገል በቃልኪዳኑ የፀና፤
5. እንደሌላዉ ከሀገር ተሰዶ መኖር ሲችል ባርነትንና ጭቆናን ለመታገል ሀገር ቤት በመቅረት እየታገለ ያለ፤
6. በበሳል አንደበቱና በሰላ ፅሁፎቹ ስርዓቱን በፍፁም ጀግንነት ያንገዳገደ፤
7. በፀባዩ፤ በበሳልነቱ፤ ባጠቃላይ በስብእናዉና ለሰዉ ልጆች ባለዉ አመለካከት ፈፅሞ የተከበረ፤
8. የተከበረ የቤተሰብ አስተዳዳሪ፤
9. የሀገሩን ፍቅር ከልጁ ያስበለጠ፤
10. እኛ የሚገባዉን ድጋፍና እዉቅና ባንሰጠዉም በአለም አቀፍ ደረጃ እዉቅናና በርካታ ሽልማቶችን ያገኘ፤
11. በርካታ ፅሁፎችን የፃፈና ለኛ የታገለ እንዲሁም ትምህርቶችን ያስተማረ ሲሆን ሌሎችም እጅግ በርካታ ነጥቦች
ማስቀመጥ ቢቻልም በኔ እምነት እንደወርቅ አንድ የሰዉ ልጅ ሊቀበለዉ የሚችለዉን ፈተና በእሳት የተፈተነና
አሁንም ድረስ እየተፈተነ ያለ ነዉ።
ከዚህ አንጻር በኔ ፍፁም የማያወላዉል እምነትም ተበታትኖ ያለዉን የትግል ጎራ አሰባሳቢ ሊሆን የሚችል መሪ
ከጀግናዉ እስክንድር ነጋ የተሻለ የኛ የዘመናችንና የራሳችን ማንዴላ ይኖራል ብዬ አላምንም። በኔ አመለካከትም እንደ
እስክንድር ያለ አለም አቀፍ እዉቅና ያለዉ ጀግና በመካከላችን ማግኘታችን እድለኞች ነን። ጊዜዉ ያለፈበትን በእጅ ያለ
ወርቅ፤ ወይም ነብይ ባገሩ የሚለዉን ሗላ ቀር ብሂልና አለመካከት ጥለን በወርቃችን በመኩራት፤ በሱ ዙርያ መሰባሰብ
እንጀምር ብዬ ጥሪዬን አቀርባለሁኝ። ስምን መላዕክት ያወጡታል እንዲሉ በታላቁ በእስክንድር ትግላችን መሪ፤
አሰባሳቢ፤ ክብር  ያግኝ። የኛ የምንለዉ፤ የምናከብረዉ፡ የምንኮራበት መሪ ይኑረን። በሱ ዙርያ ሰላምን፤ ተስፋን፤
አንድነትን፤ ጥንካሬንና፤ ዉጤትን እናግኝ። ይህንንም ካደረግን በኔ እምነት የምንመኘዉን ለዉጥ እንጎናጸፋለን።

በእስር ላይ ያለና ፖለቲከኛ ያልሆነ ጋዜጠኛ ባለሙያ እንዴት ይህንን እልህ አስጨራሽ ትግል ይመራዋል የሚል ጥያቄ
ሊቀርብ ይችላል። ለዚህም በአጭሩ በአለም ላይ የነበሩትና አሁንም ያሉትን የታላላቅ ለዉጥ መሪዎች ማንነትን መለስ
ብለን ስናጤን፤ ስንቶቹ ፖለቲከኞች ነበሩ የሚለዉ አፀፋዊ ጥያቄ ምላሹን ይሰጣል ብዬ አምናለሁኝ። ብዙዎቹ ለእዉነት
የቆሙና በአርአያነትና በቁርጠኝነት የታገሉ ምሁራን፤ የህግ፡ የሀይማኖት፤ አልፎም ተራ ሰዎች ሆነዉ እናገኛቸዋለን።
መሪ በሚያሳየዉ የአላማ ፅናት፤ በመርሁ፤ በተግባር መፈተኑና ሌሎችን ለትግል ለማነሳሳት ባለዉ ፋና ወጊነት
ስለሚመረጥ እንዲህ አይነት ጥያቄ እስክንድርን በተመለከተ ሚዛን አይደፋም።    
እኔ ምርጫዬን አደረኩኝ። እናንተስ? መሪ አሰባሳቢ ፈላጊዎች ከሆናችሁና እርሱ ምርጫችሁ ከሆነ እንሰባሰብ። በሱ
ዙርያ የኢትዮጵያዊነት አንድነት መድረክ እንፍጠርና ተሰባስበን በጋራ እንዲመራን እንጠይቀዉ። ከእስር እንዲፈታም
ታላቅ አለም አቀፋዊ ዘመቻ እንጀምር። በዘመቻዉና በሱም አመራር ለትግላችን አለም አቀፋዊ ድጋፍን እናሰባስብ።
በዚህም ጥንካሬን በማግኘት አገራችንና ህዝባችንን እንታደግ። ያለዉን የሰጠ እንደሚባለዉ ይህ ለኔ የተሻለዉ አማራጭ
ይመስለኛል። ከዚህ በፊትም ደጋግሜ እንዳቀረብኩት ትግል ያለ አቅም አይታሰብምና ተበታትነን ከምንጓዝ አዉራችንን
በመምረጥ እንሰባሰብ። በመሰባሰባችንም አቅምን አጎልብተን የኢትዮጵያ ልጆች ይሰባሰባሉ፤ ሀገራችንም አጆቿን ወደ
አምላኳ ትዘረጋለች፤ ታላቅም ሀገር ትሆናለች የተባለዉን ትንቢት በኛ ግዜ አዉን እናድርገዉ። እንደ ምናደርገዉም
ጥርጣሬ የለኝም!!!
አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

Total Pageviews

Translate