Pages

Feb 26, 2013

ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል

#Ethiopia #StopCensorship

From  Zone 9  blog
FreddomofSpeech.phpለምዕራባዊያኑ የመጨረሻ  ወር በሆነው ዲሴምበር ወር መጀመርያ በሀገረ አሜሪካ ኢትዮጵያዊውን ጦማሪ እና እስክንድርነጋን ለማሰብ የተዘጋጀ መድረክ ነበር፡፡ በመድረኩ ላይ ሾለ እስክንድር ነጋ የተናገሩት ተዋናይ ሊዬቭ ሽሏ የይበር እና ጸሐፊ ካርል በርንስቴይን ነበሩ፡፡ በርንስቴይን  áŠ¨40 ዓመታት በፊት የዋሽንግተን ፖስት ዘጋቢ ሆኖ በሚሠራት ወቅት ከባልደረባው ቦብ ዉድወርድ ጋር በመሆ ን በአሜሪካ መንግስት ታሪክ ትልቅ የተባለውን እና የዋተርገቱ ቅሌት በመባል ሚታወቀውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ያሳተፈ የሙስና ቅሌት አጋልጠዋል፡፡ በነዚህ ሁለት ዘጋቢዎች ታሪካዊ ማጋለጥ ምክንያት በወቅቱ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ሆኗል፡፡
የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሳሌ ተደርጋ የምተጠቀሰው አሜሪካ በወቅቱ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ አቅም የሚያንሳት ሀገር አልነበረችም፡፡ የፖለቲካ ባህሏም (በጥቅሉ) ተጠያቂነትን የሚያበረታታ እና ሙስናን የመሰሉ ተግባራትን አፀያፊ አድርጎ የሚቆጥር ነበር/ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህም ሥርዓት መሐከል ግን እንክርዳድ አይጠፋውም፡፡ እናም መደበኛው የተጠያቂነት ሥርዓት ያልደረሰበትን ማማ አራተኛው የመንግሥት ክንፍ  (fourth organ of government) በመባል የሚታወቀው ሚዲያ አጋለጠው፡፡
ነጻ የሆኑ መገናኛ ብዙኃን መኖር እና ዜጎች ሐሳባቸውን መግለጽ እና መወያየት መቻላቸው የመንግሥትን እና የባለሥልጣናቱን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሕዝብን ከአደጋ ለመጠበቅ ቁልፍ መሣሪያዎች ናቸው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ ሀገራት እያንዳንዱ የመንግሥት መዋለ ነዋይ ለሚፈለግለት ዓላማ መዋል አጥብቆ የሚፈለግ ነገር ነው፡፡ እውነታው ግን ይሄ አይደለም፡፡ በደሃ ሀገራት áˆľáˆáŒŁáŠ• የሚይዙት ሰዎች/የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን አንድም የራሳቸውን ግለሰባዊ ችግር ከሀገሪቱ ችግር በማስቀደም ወይንም በስግብግብነት አልፎ አልፎም ደግሞ ከብቃት ማነስ ሀገራቸው እጅግ አድርጋ የምትፈልገውን መዋለ ነዋይ ያባክናሉ፡፡ ይባስ ብሎም አብዛኞቹ ደሃ ሀገራት የሚመሩት ሁሉንም ነገር መቆጣጠር በሚፈልጉ እና ለምንም አይነት ነጻነት እና መብት ደንታ በማይሰጣቸው መሪዎች  (totalitarian) ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የሀገር ሃብት ሲመዘበር እና አለአግባብ ጥቅም ላይ ሲውል ለምን ብሎ የሚጠይቅ አካል አይኖርም፡፡ ካለምፍዳው እጅግ ብዙ ይሆናል፡፡
የሕዝብ ውክልና የሌላቸው/የሚጎላቸው የድሃ ሀገራት መሪዎች ስልጣን ላይ በሕይወት እስካሉ ድረስ ለመቆየት ሀገራቸው ላለባት ምጣኔ-ሃብታዊ እና ሌሎችም ችግሮች እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ አብዛኛዎቹ መሪዎች ሕዝብ በከፈለው ግብር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙኃንን የራሳቸውን ተረክ ለመፍጠር ይጠቀሙበታል፡፡ እነሱ ከሌሉ ሀገሪቷ የምትገባበትን ‹áˆ˛áŠŚáˆ›  á‹­áˆ°á‰ĽáŠŠá‰ á‰łáˆ፡፡ ይህ ብቻ አይበቃቸውም፡፡ ምንም ዓይነት የተለየ ተረክ ለሕዝብ እንዲደርስ አይፈቅዱም፡፡ የሐሳብ አሀዳዊነትን በሕዝብ ላይ ለመጫን ይመቻቸው ዘንድ የበይነ-መረብ ማጥለል፣ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ጋዜጦች፣  áˆ˜áŒ˝áˆ”ቜች ይዘጋሉ፤ ጋዜጠኞችን ያዋክባሉ፣  á‹ŤáˆľáˆŤáˆ‰፡፡ በዚህም የተነሳ ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ሀገርን የሚጠቅም ነው ብለው የሚያወጧቸው ምጣኔ-ሀብታዊ (ሌሎችም) ፖሊሲዎችን የተለየ ምልከታ ሰጥቶ ጥቅሞቹን እና ጉድለቶቹን ተንትኖ እና ከሕዝብ ፍላጎት ጋር ያላቸውን መጣጣም አመዛዝኖ ለሕዝብ የሚያቀርብ አማራጭ እንዳይኖር ያደርጋሉ፡፡ እናም ፖሊሲዎች መታረም ከሚችሉት ህፀፆቻቸው ጋር በሰሠሯቸው ሰዎች ተደጋግመው ከተወደሱ በኋላ ወደሥራ ይገባሉ፡፡
እነዚህ መሪዎች አንድ መሠረታዊ የሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮን ዘንግተዋል፡፡ ማንኛውም ጤነኛ ሰው የሚቀበለውን መረጃ እንደተሰጠው አይውጠውም፡፡ ሁልግዜም ባይሆን ባመዛኙ፣  á‹¨áˆ°á‹ ልጆች የሚሰጣቸውን መረጃ ማመዛዘን ይፈልጋሉ –  á‰ á‰°áˆˆá‹­áˆ ድጋፍ መስጠት/አቋም ሊይዙበት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሲሆን፡፡ አማራጭ ትንተና ያጡ ዜጎ ችአንድ አንዳንዶቹ (ጥቂቶቹ) የራሳቸውን ትንተና በመስጠት አቋም ሲወስዱ አብዛኞቹ ለድጋፍም ሆነ ለተቃውሞ የሚበቃ አቋም ለመውሰድ በቂ ትንተና ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡በመጨረሻም ፖሊሲውን ተፈፃሚ ለማድረግ የሕዝብ ተሳትፎ/ድጋፍ አጥሮናል ብለው የሚያማርሩ የመንግሥት ድምፆችን መስማት እንጀምራለን፡፡
ምጣኔ ሃብት እና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት
እ.አ.አ 1989 ድሬዝ እና ሴን የተባሉ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪዎች ባያደረጉት ጥናት ነጻ መገናኛ ብዙኃን ባለበት ሀገር አንድም ግዜ ረሀብ ተከስቶ እንደማያውቅ ጠቁመዋል፡፡ ይህንንም ሲደግፉ ነጻ የሆነ የመረጃ ፍሰት ባለባቸው ሀገራት መንግሥታትን (ዴሞክራሲያዊ ባይሆኑም እንኳን) ከሕዝብ የሚመጣ ጫና ውስጥ ስለሚከታቸው እና ይህንንም ለማስወገድ ሲሉ ቀድመው የሕዝብን ጥያቄ የሚመልስ እርምጃ ስለሚወስዱ እንደሆነ ይተነትናሉ፡፡ ኢሻም፣ ካፍ ማን እና ፕሪቼት የተባሉ ምሁራን እ.አ.አ  1997 ባደረጉት ጥናት መሠረት ደግሞ ግለሰባዊ ነጻነቶች  (ሐሳብን የመግለፅን ጨምሮ) ማክበር በመንግስት ቁጥጥር ሾር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ምጣኔ-ሃብታዊ ውጤት  (Project’s Rate of return) እስከ 20 በመቶ ያክል ድረስ ይጨምረዋል፡፡ እንደነዚሁ አጥኚዎች ትንተና መሠረት ግለሰባዊ መብቶችን  (ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ/የመሰብሰብ ነፃነት፣ áˆáˆłá‰ĽáŠ• በነፃነት የመያዝ እና የመግለጽ፣ áˆ•á‹á‰Łá‹Š ጉዳዮች ላይ በነፃነት የመሳተፍ እና ነፃ ማኅበር ማቋቋም) አለማክበር በእኩል መጠን ከሚከሰት የዓመታዊ ምርት መቀነስ፣ የበጀት እጥረት ወይንም የወጪ እና ገቢ ንግድ ላይ ከሚያጋጥም ንዝረት ባልተናነሰ ሁኔታ በመንግስት የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ውጤታነት ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡
እንደ በመንግስት የሚተዳደሩ ፕሮጀክቶች ባይሆንም በግል ባለሀብቶች እና ተቋማት የሚካሄዱ ንግዶች ሐሳብን በነጻነት መግለጽ በሚቻልበት ሀገር ለገበያ የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች እና አገልግሎቶች የኅብረተሰቡን ደኅንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል እንዳይሆኑ ከፍ አድርገው ይጠነቀቃሉ፡፡ በግድየለሽነት ወይንም በአጭር ጊዜ ለመክበር በሚያደርጉት ሙከራ የህብረተሰቡን ደህንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል ዕቃ ወይንም አገልግሎት ቢያቀርቡ ነፃ መገናኛ ብዙሃን ሁኔታውን በማጋለጥ ህብረተሰቡን ከጉዳት ይጠብቃሉ፡፡
የሳንሱርዋጋ
የሐሳብ ብዝኃነትን በመቆጣጠር ሕዝብ እነሱ የሚሉትን ብቻ እየሰማ እንዲነዳ የሚፈልጉ መንግሥታት ሐሳብን ለማፈን ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ሐሳብ ለማፈን ከከሚጠቀሙባቸው መንገዶች በይነ መረብን ማጥለል እና ጦማሮች እዳይከፈቱ ማገድ፣ በይነመረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ መሰለል እና በሳተላይት የሚተላለፉ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች ሞገዶችን መከልከል ይጠቀሳል፡፡
የአውስትራሊያ መንግስት  á‰ 2009 ዓ.ም ሊተገብረው ያሰበው የበይነ መረብ ማጥለልን በተመለከተ ዴቪድ በርድ የተባለ ጦማሪ እንደጻፈው በበይነ መረብ የሚተላለፉ መረጃዎችን ለማጥለል ጥቅም ላይ የሚውሉት ቴክኖሎጂዎች የበይነ መረብ አገልግሎት ፍጥነትን ከ2 በመቶ እስከ 70 በመቶ ይቀንሳሉ፡፡ የማጥለል ሥራውን  ‹á‰ á‹áŒ¤á‰łáˆ›áŠá‰ľ የሚያከናውኑት› ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ፍጥነቱን በደንብ የሚቀንሱት ናቸው፡፡
ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ደግሞ ኒውዮርክ ታይምስ አንድዜና ለኢትዮጵያዊያን ይዞልን ወጥቶ ነበር፡፡ ፊንፊሸር የተባለ በይነ መረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ ስለላ ለማድረግ የሚያስችል የረቀቀ ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀሙ ከታወቁት  10 ሀገራት አንዷ ሀገራችን መሆኗን፡፡ እንደዘገባው ቴክኖሎጂውን ለመግዛት ከ350ሺህ  á‰ áˆ‹á‹­ የአሜሪካን ዶላር ወጪ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ቁጥር አንድ ጠላቷ ድህነት ለሆነ ሀገር ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ ዜጎች ላይ ለመሰለል ይህን ያህል ወጪ ማውጣት እውነትም አሀዳዊ ተረክ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደሚኬድ ማሳያ ነው፡፡
በሳተላይት የሚተላለፉትን ሬዲዮ እና የቴልቪዥን ስርጭትን ለመደገፍ ምን ያህል የተወሳሰበ ቴክኖሎጂ እንደሚያስፈልግ እና እሱም ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጣ መገመትም ቀላል ነው፡፡
ምንም እንኳን አከራካሪ ቢሆንም ዜጎች በነጻነት ሲያስቡ እና ሐሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ሲችሉ አዳዲስ እና ውጤታማ የንግድ ሐሳቦች ማፍለቅ ቀላል ይሆንላቸዋል፡፡ ይህም ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መንፈግ ከሚያስከፍሉት ቀጥተኛ ያልሆኑት ዋጋዎች ውስጥ ሊካተት ይችላል፡፡

Feb 24, 2013

ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ

ድምፃችን ይሰማ

በእርግጥ ግለሰቡ የባለስልጣን ግብር አላቸው?
ባሳለፍነው ሳምንት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ዲኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ኢትዮ ቻናል ከተባለው ጋዜጣ ጋር አንድ ቃለመጠይቅ አድርገው ነበር፡፡ ጋዜጣው የመንግስት ፕሮፓጋንዳ መንዣ መሳሪያ ከሆኑ ‹‹á‹¨áŒáˆ›› ጋዜጣዎች ውስጥ አንዱ እንደመሆኑ ምን አይነት ይዘት ያለው ነገር እንደሚያወጣ ለብዙዎች ድብቅ አይደለም፡፡ ያወጣውም ብዙዎች ከሱ የሚጠብቁትን ፕሮፓጋንዳ አይነት ጽሁፍ ነበር፡፡ ኢቲቪ የፍርድ ቤት ትእዛዝን ጥሶ ባስተላለፈው አሳፋሪ ‹‹á‹śáŠŠáˆ˜áŠ•á‰łáˆŞ›› ፊልም የተነሳ የደረሰበትን ውግዘት እና የፕሮፓጋንዳውን መክሸፍ ሊያስተባብሉ ነበር አቶ ሽመልስ ከማል በኢትዮ ቻናሉ ቃለ መጠይቅ ብቅ ያሉት፡፡ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ
ቃለ መጠይቁ ከአንድ ትልቅ የመንግስት ባለስልጣን እንደመምጣቱ ጨዋነትን የተላበሰና ደረጃውን የጠበቀ መሆን በተገባው ነበር፡፡ ያ ግን አልሆነም፡፡ አስገራሚ በሚባል ደረጃ ከቃላት አጠቃቀሙ ጀምሮ በሁለመናው ዝቅ ያለ እና የወረደ ነበር፡፡ ቃላቶቹ ተራና ‹‹á‹¨áˆ˜áŠ•á‹°áˆ­›› ከመሆናቸውም ሌላ ግለሰቡ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የሻቸውን የሚናገሩ እንደሆኑ ያሳብቁ ነበር፡፡ አንድ የመንግስት ባለስልጣን የሚናገራቸውን ነገሮች የኋላ ውጤት ያለምንም ማገናዘብ እንዳመጣለት መናገሩ አገራችን ውስጥ በመንግስት እና በግለሰብ መካከል ያለው ለውጥ ከነጭራሹ እየጠፋ መምጣቱን እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡
ግለሰቡ በረዥሙ ቃለ መጠይቃቸው በርካታ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡ ሁሉንም እዚህ እያነሳን ልንነጋገርባቸው ባንችልም የተወሰኑትን ብቻ ጠቀስ ጠቀስ እያደረግን ምልከታችንን እንሰጥባቸዋለን፡፡
አቶ ሽመልስ በቃለ መጠይቃቸው እጅግ አብዝተው ያነሱት ሾለ ‹‹áˆ˝á‰Ľáˆ­á‰°áŠáŠá‰ľ›› ነው፡፡ የተለያዩ ፖለቲከኞች ስለሽብርተኞች እና አልቃይዳን ስለመሳሰሉ ድርጅቶች የተናገሯቸውን አንዳንድ ጥቅሶች እየጠቀሱ፣ ስለፈንጂ ጉዳት እያነሱ ከኛው ሰላማዊ እንቅስቃሴ መሪዎች ጋር ለማገናኘት ይሞክራሉ፡፡ ሁለቱ የሰማይና ምድርን ያህል የሚራራቁ ነገሮች እንዴት እንደተገጣጠሙላቸው ግልጽ አይደለም፡፡ ‹‹… ይሄ ሴል ተግባራዊ ሆኖ ቢሆን ኖሮ በበርካታ ንፁኃን ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ኑሮ ላይ፣ በህይወታቸው፣ በንብረታቸው ላይ በግምት ሊሰፈር የማይችል እጅግ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል እሙን ነው፡፡ ስለዚህ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ከፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ጋር ባደረገው ክትትል ይሄንን ሴል ገና በእንጭጩ ለማምከን ችሏል›› ሲሉም የማይመስል ነገር ይናገራሉ፡፡ አመት ያለፈው እንቅስቃሴያችን ሰላማዊ ብቻ መሆኑ አይደለም ለአገራችን ይቅርና ለዓለምም ተረጋግጧል፡፡ መንግስት በየጁሙአው ‹‹á‹ľáŠ•áŒ‹á‹­ ይወረወራል›› በሚል ተስፋ እንዲሰባበሩ አንዋር መስጊድ በተቃውሞ ሰአት የሚያስቆማቸው አንበሳ አውቶቡሶች እንኳን አንድም ቀን የመሰበር እጣ አላጋጠማቸውም፡፡ አቶ ሽመልስ ግን በኢቴቪ የተላለፈውን መረጃ አልባ ዶኩመንተሪ ‹‹á‰ŁáŠ“áˆłá‹¨á‹ ኖሮ አገሪቷ ትፈርስ ነበር›› ለማለት ይዳዳቸዋል፡፡ ይህንኑ ‹‹á–áˆŠáˆľ በምርመራው አረጋግጧል›› የሚለውን ንግግር ከመደጋገም ባለፈ አንዳችም ማስረጃ ያላቀረበውን ፊልማቸውን እየጠቆሙም ሌላ አስገራሚ ነገር ይነግሩናል፡-
‹‹áŠĽáŠá‹šáˆ… ሰዎች ከኃይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን መነሻቸውም፣ ማምሻቸውም፣ ግባቸው ፖለቲካዊ መሆኑን እነሱ የሚፈልጉትን የአንድ እምነት ህግጋት እና ይሄንን ህግጋት የሚያስፈፅም አምባገነናዊ ኃይማኖታዊ መንግስት የመገንባት ዓላማ ያላቸው መሆኑን የሚያጋልጡ በርካታ ሰነዶች እየወጡ ነው፡፡ የዚህ ሰነድም አንደኛው የዶክመንተሪው ዓላማም ይሄ ነበር›› ይሉናል፡፡ ፊልሙ ላይ ሕዝቡ እንደተመለከተው ከኮሚቴዎቻችንም ሆነ ከሰላማዊ እንቅስቃሴያችን ጋር የተያያዘ በርካታ የሰነድ ማስረጃ ይቅርና አንድ እንኳ ሰነድ ሊቀርብ አልቻለም፡፡ ይህንን ፊልሙን ያየ ሁሉ አይቶታል፡፡ በተመልካቹ ዘንድ ዜሮ ተቀባይነት ያገኘውም በዚሁ እንደሆነ የዘነጉት ይመስላሉ – አቶ ሽመልስ፡፡
ወረድ ብለው ደግሞ ግለሰቡ ሌላ አስገራሚ ነገር ጠቅሰዋል፡፡ ኮሚቴዎቻችንን አስመልክቶ የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥተዋል፡- ‹‹…እነዚሁ የምናውቃቸው ዛሬ የሙስሊም መሪዎች ነን ምንትሴ ነን እያሉ የወጡ አክራሪዎች ናቸው – እነሱ ናቸው ይሄንን ስብከት የሚያሰራጩት – ይሄን መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም አበጥሮ ያውቀዋል፡፡ በዚህ የሚታለል የለም – ዓላማው ይሄ እንዳልሆነ ይታወቃል›› ብለዋል፡፡
ቃለ መጠይቁን የሞሉትን ‹‹áˆáŠ•á‰ľáˆľ…. ቀጣፊ›› … ወዘተ አይነት ቃላቶች አቶ ሽመልስ ለተቀመጡበት ወንበር እንኳ የማይመጥኑ አሳፋሪ መሆናቸውን ለጊዜው ትተነው ሀሳቡ ግን እጅግ ከእውነታ የራቀ መሆኑን ማስግዘብ ያሻል፡፡ ‹‹áˆ˜áˆ‹á‹ የኢትዮጵያ ሙስሊም አበጥሮ ያውቀዋል›› ማለታቸው በተለይ ትልቅ ሹፈታቸው ነው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙማ ከማን ጋር እንደሆነ በበቂ ሁኔታ አሳይቷል፡፡ ‹‹áˆ˜áˆŞá‹Žá‰ťá‰˝áŠ• ይፈቱ!›› የሚል ድምጹን በኢድና በአረፋ ሚሊዮኖች ሆኖ፣ በሌሎችም በርካታ የጁምአ ስግደቶች በተደጋጋሚ አረጋግጧል፡፡ ግለሰቡ ‹‹áŠ áŠ­áˆŤáˆŞá‹Žá‰˝›› ሲሉ ያንጓጠጧቸውን ኮሚቴዎች ህዝበ ሙስሊሙ ‹‹á‰Ľáˆ­á‰…á‹Ź የሰላም አምባሳደሮቻችን›› እያለ ነው የሚጠራቸው፡፡ በጥር ወር 2005 ብቻ በአገር አቀፍ ደረጃ 35 ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተደርገዋል፡፡ ሕዝቡ ወደ አደባባይ የወጣው ለምን እንደሆነም መንግስትና ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፉ ማህበረሰብም ጭምር ያውቀዋል፡፡ መንግስት አመቱን ሙሉ በዚህ ጉዳይ ተወጥሮ የቆየውኮ ጉዳዩ የህዝብ እንጂ ‹‹á‹¨áŒĽá‰‚ቾ አክራሪዎች›› ስላልሆነ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ አቶ ሽመልስ ሳያውቁት ቀርተው አይደለም – የፖለቲካ ሾል ሆኖባቸው እንጂ፡፡
ሌላ ንግግራቸውን እንመልከት፡- ‹‹á‹¨áˆ˝á‰Ľáˆ­á‰°áŠáŠá‰ľ ዋና ዓላማ ህብረተሰቡን ተከታታይ የሆነ የፍርሀትና የሥነ ልቦናዊ ሰቀቀን ውስጥ መክተት ነው፡፡ የፖሊስ ሼል ደግሞ ከወንጀል ሼል እና ፍርሀት፣ ከወንጀል ሥጋት ነፃ ማውጣት ነው›› ይሉናል፡፡ ይህን በመርህ ደረጃ መቀበል ለማንም አይቸግርም፡፡ ለሽብርተኝነት ጥሩ ገለጻ ነው የሰጡት አቶ ሽመልስ፡፡ እስቲ ራስዎ ባወጡት መስፈርት እያሸበረ ያለው ማን እንደሆነ እንመልከት፡፡
ሰሞኑን በውድቅት ሌሊት የታጠቁና ፊታቸውን በጭምብል የሸፈኑ ፖሊሶች በየሰፈሩ የሙስሊሞችን ቤት ያለምንም የፍርድ ቤት ማዘዣ ዘልለው እየገቡ፣ እየደበደቡና ያገኙትን ውድ ንብረት (ወርቅና ብር) በግድ እየዘረፉ፣ ከዚያም አልፈው በቤቱ የሚገኘውን ቅዱስ ቁርአንና አረብኛ የሀዲስ መጽሀፍት ‹‹á‹­á‰°áˆ¨áŒŽáˆ›áˆ‰›› በሚል እየወሰዱ ነው የሚገኙት፤ ልክ እንደ ደርግ ዘመን! ሙስሊሙ በየቤቱ ስጋት ውስጥ ነው ያለው፤ ሽብር ውስጥ!!! እያሸበረው ያለው ደግሞ እርስዎ ‹‹áˆĽáˆŤá‹ ህዝቡን ከወንጀል ሼል እና ፍርሀት፣ ከወንጀል ሥጋት ነፃ ማውጣት ነው›› ሲሉ ያንቆጳጰሱት ‹‹á–áˆŠáˆľ›› ነው፡፡ በየጁምአው የሰላማዊውን ሙስሊም ድምጽ ለማፈን ጠመንጃውን ወልውሎ ቆመጡን እየወዘወዘ የሚወጣው የእርስዎና የባልረቦችዎ ታዛዥ የፖሊስ ሀይል ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ተገለባብጧል… እርስዎ ደግሞ የሚነግሩን ሌላ እኛ የማናውቃት ኢትዮጵያ ያለች እንዲመስል አድርጎናል…. መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ የማይገባባት…. ፖሊስ ህዝቡን ከስጋት የሚጠብቅባት…!!!
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
አላሁ አክበር!

Feb 23, 2013

Ethiopian Minister Junedin seeks Asylum in Kenya


EthioChannel’s cover story on Junedin
EthioChannel, pro regime “private” Saturday Newspaper has today reported that
top ruling party official and “the Minister of Civil Service” has sought asylum in
neighboring Kenya. A political scientist with a close knowledge of the former
Minister that De Birhan talked to said that Junedin’s family couldn’t confirm the
Report and that he was not contactable.
Junedin Sado’s wife, Habiba Mohammed, is one of 29 people facing terrorism
charges related to protests by Muslims. Junedin last year published a letter in the
same newspaper defending his wife and criticizing the federal prosecutor’s charges.
In the letter, Mr. Junedin said that he had approached the Saudi Arabian Embassy
in his personal capacity to raise money to build a mosque to fulfil the wishes
expressed in the will of his late mother. The money recovered from his wife, Mr.
Junedin said, was meant for the mosque and not to fund terrorist activities.
Habiba was charged in October 2012 with funneling money from the Embassy of
Saudi Arabia to Islamist terror groups, at a hearing at the Ethiopian Federal High

Court.
Jundein was president of the Oromia Region from 28 October 2001 until 6 October
2005. He subsequently was appointed Transport and Communication Minister,
which is the office he was holding when Prime Minister Meles Zenawi moved him to
the Science and Technology Ministry October 2008. Following the 2010 general
election, Junedin was appointed Minister of Civil Service until November 2012
Prime Minister Hailemariam replaced him with another Minister in his Ministerial
reshuffle. The Oromo People’s Democratic Organisation (OPDO), a constituent of
the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front, the ruling coalition had also
expelled him from the Organisation. It was reported that after “self criticism he was
readmitted and secured his posts”. He previously served as the president of the
OPDO. Although the Ethiopian Parliament had the plan of “removing Junedin’s
immunity” it in its agenda, it was not implemented to that effect. Junedin has also
been the Board Chairman of Addis Abeba University (AAU).
Junedin was one of the “most powerful” ruling Party officials who represented the
regime in various international and local duties. He was also one of the few Ministers
that represented the ruling Party in the Ethiopian General election debates. A close
confident and loyal of the late Prime Minister Meles Zenawi, Junedin was one of the
ardent critics of Ethiopian opposition and Muslim critics/protesters, sources who
knows the Minister closely at the Oromia regional Council recount.
The paper also stated that it was not established how Junedin left for Kenya, so far.
Some sources close to De Birhan had informed us that Junedin had absconded to
Kenya with eight senior members of OPDO and colleagues. There are no details on
the whereabouts of his three underage children

Ethiopia: TPLF cadre exposed in Norway

Feb 22, 2013

ሰመጉ የተላለፈው ዘጋቢ ፊልም የተከሰሱ ሰዎችን ሕገመንግስታዊ መብት የጣሰ ነው ባወጣው መግለጫ አስታወቀ

የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰመጉ በዚሁ መግለጫው በፌዴራል ፖሊስና በብሄራዊ ደህንነት እና ጸጥታ ባለስልጣን ተዘጋጅቶ በኢቲቪ እንዲቀርብ የተደረገው ፊልም ተጠርጣሪዎቹ በሕገመንግስቱ መሰረት በተከሰሱበት ወንጀል ከፍርድ በፊት እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር መብታቸውን የጣሰ መሆኑን ጠቁሞ ይህ በመሆኑም ከአሁን በኋላ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤት የመከላከያ ምስክሮችን የማቅረብ አቅማቸው አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቅሶአል፡፡
የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ ደህንነት እና ጸጥታ ባለስልጣን እንደ ህገመንግስት ተቋምነታቸው በአሁኑ ሰአት በፍትህ ሚኒስቴር የፌደራል ማእከል አቃቢ ህግ በነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ በከፈተው የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ በምርምራ ያገኙትን ማስረጃ እንደሚያቀርቡ ቢጠበቅም፣ ተቛማቱ በህገመንግስቱ አንቀጽ 20 የተደነገገውን ዜጎች ፈርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር መብታቸውን በመጣስ ፣ ተከሳሾች ወንጀል ስለመፈጸማቸው አውጅዋል ሲል አስታውሷል።
ዘጋቢ ፊልሙ ፍርድ ቤቶች በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት የሚያዛባ ይሆናል ያለው ሰመጉ፣ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በመንግስት በኩል የተወሰደውን ድርጊት ከማውገዝ ባተጨማሪ ዘጋቢ ፊልሙን ያዘጋጁት እና እንዲሰራጭ ያደረገው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሚመለከተው የመንግስት አካልም ድርጊቱን በማውገዝ አስፈላጊውን ማስተካከያ  áŠĽáŠ•á‹˛á‹Ťá‹°áˆ­áŒ ጠይቋል።

በአጋሮ በርካታ ሙስሊሞች መደብደባቸው ታወቀ

የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የጁመአን ስግደት ተከትሎ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ ቢሞክሩም የፌደራል ፖሊስ አባላት የሀይል እርምጃ ወስደዋል።
በርካቶች መታሰራቸውን፣ መደብደባቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል::
ከፍተኛ ተቃውሞ ከታየባቸው ከተሞች መካከል ሻሸመኔ አንዱ ሲሆን፣ በርካቶች በ04 መስጊድ ተገኝተው ድምጻችን ይሰማ መሪዎቻችን ይፈቱ ማለታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
ተመሳሳይ ተቃውሞዎች በበደሌ፣ መቱና ድሬዳዋ መካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሙስሊሙን ተቃውሞ ለማስቆም የተለያዩ ሙከራዎችን ቢያደርግም ተቃውሞው ከአዲስ አበባ ውጭ አድማሱን እየተስፋፋ ከመሄድ በስተቀር የመቀነስ ሁኔታ አይታይበትም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሜሪካ የሞኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ነገ ፌብሩዋሪ 23 በዋይት ሀውስ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ያደርጋሉ።
ድምፃችን ይሰማ ዋሺንግተን ዲሲ እንዳስታወቀው፤ ሰልፉ የተዘጋጀው የ ኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሞች ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማውገዝና ረዥም ጊዜ ላስቆጠረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ትግል አጋርነትን ለመግለጽ ነው።
የ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላነሱት የመብት ጥያቄ መንግስት ቀና ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ካለመሆኑም በላይ ህግን በሚፃረር ሁኔታ በመብት ጠያቂዎቹ ላይ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን የጠቆመው ድምፃችን ይሰማ፤ ከዚያም አልፎ በሙስሊሙ መሪዎች ላይ የእስር፣የግርፋትና የማንገላታት ድርጊት መፈፀሙን አመልክቷል።
ጥቂት የማይባሉ ሙስሊሞችም በደህንነት ሀይሎች ታፍነው ተወስደው እስካሁን ያሉበት ስፍራ አለመታወቁንም ኮሚቴው በመግለጫው ጠቅሷል።
እንዲሁም ከ 1000 በላይ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በእምነታቸው ሳቢያ ከትምህርታቸው መታገዳቸውን ኮሚቴው ኢሳትን በዋቢነት በመጥቀስ በመግለጫው አስፍሯል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናልም፤እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከሐምሌ 12 ጀምሮ 17 ዋነኛ የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል መሪዎችን ጨምሮ በርካታዎች እንደታሰሩ፣እንደተገረፉ እና እንደተሰቃዩ ሪፖርት ማውጣቱን ድምፃችን ይሰማ አስታውሷል።
ከፊል መንግስታዊ የሆኑ ተቋማትን ጨምሮ ዓለማቀፍና አገር አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የ ኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሞች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና በደል በተከታታይ ማውገዛቸውን ኮሚቴው አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና በእስር ላይ የሚገኙት መሪዎቻቸው በፖለቲካ ተጽጽኖ ሾር ከወደቀ ፍርድ ቤት ፍትህን ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎ ፈጽሞ እንደማይጠበቅ ዓለማቀፉ ማህበረሰብና ለጋሽ ሀገራት ሊያውቁት እንደሚገባም ድምፃችን ይሰማ ዲሲ ጠቁሟል።
በመሆኑም የ ኢትዮጵያ መንግስት በራሱ ህዝቦች ላይ እየፈጸመ ያለው የመብት ጥሰትና ወንጀል እጅግ ሳይዘገይ በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት ያገኝ ዘንድ ኮሚቴው ጠይቋል።
የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድሞቻችንም በመንግስት የተለያዩ አፋኝ ፖሊሲዎችና አሠራሮች ተጠቂ መሆናቸውን እንደሚገነዘቡ ጠቀሰው የድምፃችን ይሰማ ዲሲ መግለጫ፤በመሆኑም ክርስቲያን ወንድሞቻቸው ነገ በዋይት ሀውስ ፊት ለፊት ሙስሊሞች በሚያካሂዱት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አብረው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል

የካቲትን የምንዘክረው ከሀገር በቀል ወራሪው ህወሃት ጋር በመፋለም ነው!!

ቀደምቶቻችንን የምናስታውስበት፣ ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ እና አንድነቷን ለማስጠበቅ ያደረጉትን  ተጋድሎ ከምንዘክርበት እለት አንዱ የካቲት 12 ነው። በዚህ ግዜ ይህንን ታሪክ ገልብጦ ለማበላሸትና ለመጻፍ የሚጥረውን፣ የአሁኑን የግራዚያኒ ትንሽ ወንድም ሀገር በቀል ዘረኛ መንግስት  á‹¨áˆ†áŠá‹áŠ• ህወሃት/ኢህአዴግን ሀይማኖት፣ ዘርና ጾታ ሳይለየን የምንታገልበት ሁነኛ ወቅት ላይ እንገኛለን።
የቀድሞዋ የአፍሪካ ሀገራት የነጻነት ተምሳሌት የሆነችው እማማ ኢትዮጵያ፤ ዛሬ ሀገር በቀል በሆኑ የዘረኛ መዥገሮች ስብስብ ተጣብቃ የአበው መሰዋእትነት ከንቱ ይሆን ዘንድ ወያኔዎች እየሰሩ ነው። ጥንታዊ ታሪክን በመፋቅ፣ ባልተደረገና ባልተፈጸመ ታሪክ ለመተካት ወያኔ/ኢህአዴግ እያንዳንዱን የአበውን የታሪክ ማህደር በማጥፋት፣ እንደ አቡነ ጴጥሮስ የመሳሰሉ የጀግኖችን ሀውልት አሻራ በማፍራረስ ርካሽ የሆነ ግዚያዊ የፖለቲካ  áŒĽá‰…ም ማስገኛ ሾል ላይ በመሰማራት ሀገራችንን ወደኋለዮሽ እድገት እየጎተቷት ይገኛሉ።
ሁለቱን ገዳዮች የሚያገናኛቸው፤ የግራዚያኒ ወታደር አበው ለነጻነታቸው ለአንድነታቸው ሲያደርጉት የነበረውን ተጋድሎ ለማስቆም፤ የህዝቡን የትግል ሞራል ለመግደል የአዲስ አበባን ነዋሪ ቁጥሩ 30ሺ የሚሆን ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ ፋሽስትነቱን ለማሳየት ያደረገው ያልተሳካ ሙከራ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያውያን ለነጻነታቸው የሚያደርጉትን ትግል ይህ አልገታቸውም። በተመሳሳይ ደግሞ ዘመን አመጣሹ የየካቲት አስራ አንዱ ወያኔም፤ እንደፋሽስቱ ሁሉ በንጹሃን ህዝባችን ላይ በጎንደር ስላሴ፣ በምርጫ 97፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ፣ በኦሮምያ፣ በአዋሳ፣ በሀረር አሁን ደግሞ በሙስሊሙ ወገናችን ያደረሰው ጭፍጨፋ፣ እስርና ግድያ ከግራዚያኒ ጋር ያመሳስለዋል። ልዩነታቸው ይሄኛው ሀገር በቀል ወራሪ መሆኑ ነው። ምን አልባትም ወያኔ ልደቴ ብሎ የሚጨፍርበት የካቲት 11 ለሹ የድል ቀን ሲሆን፤ ለእኛ ደግሞ አባቶቻችን የምናስታውስበት የመከራ ቀን ነው።
በየካቲት12 የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ፣ ለአንድነቱ፣ ለሀገሪቱ ከብር የፋሽስቱን ወራሪ ሃይል በመመከት፤ ልጅ አዋቂ ሳይለይ ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን በማስጨነቅ እየሞቱም አልበገርነታቸውን ያስመሰከሩበት ልዩ ቀን ነው። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት ሀገር እንድትሆንም በማድረግ፤ ወርሃ የካቲት ታሪካዊ ወርና በድል አጥቢያነት በሀገራችን እንዲሁም በአሁጉራችን አፍሪካ ዘለአለም እንዲታወስና እንዲዘከር አድርገው  አበው አልፈዋል። ይህን የማስጠበቅ ታሪካዊ የሞራል ግዴታ የማን ነው?
አበው የፋሽስቱን የግራዚያኒ ወራሪ ጦር ድባቅ በመምታት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ አድነው አስረክበውናል። በዚህ ታሪካዊ ገድል በሆነው በወርሃ የካቲት የተሰዉት ጀግኖች፣ የኢትዮጵያ ልጆች አጥንትና ደም መሰዋእትነት ከቶ ከታሪክ ማህደር የማይጠፋ ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። ይህ ትውልድ ይህን የማስጠበቅ የታሪክ ባለተራ ነው እንላለን።
ግንቦት 7፣ የአባቶቻችንን ጀግንነትና ወደር የሌለውን የሀገር ፍቅር፣ የሀገር ክብር፣ የቁርጠኝነት መንፈስና የአደረጉት መሰዋእትነት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ይታገላል። በቁርጥ ቀን ልጆች በቁርጥ ቀን ሰዓትም ለመድረስ፤ እስከመጨረሻው በመታገል ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣትና ይህን ድል ለማስመለስ፤ አስመልሶ ለትውልድ ለማስረከብ፣ ለማስጠበቅ እያንዳንዷን ደቂቃ ሊጠቀምባት ቆርቶ ተነስቷል።እርሰዎስ?
የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡- የኢትዮጵያ ጀግኖች እነ አጼ ሚኒሊክ፣ የበላይ ዘለቀ፣ እነ አብዲሳጋ፣ እነ ዘራይደረስ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አፄ ዮሃንስ፣ እንደ ቋራው ካሳ እና ሌሎችም በበቀሉበት፣ በተፈጠሩበት በጥቁር አፈር ምድር፤ ፀረ-ኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዘረኛ ሃይሎች መፈጠራቸው አሳዛኝ ታሪክ መሆኑን እኛም እንመሰክራልን። ይሁን እንጅ፣ ቅሉ ይህንን በሁለት ትውልድ መካከል የተፈጠረውን የሰማይና የምድር ልዩነት ቁጭ ብለን በማየት ከንፈራችንን እየመጠጥን የምንቀመጥበት ሰአት ላይ አይደለንም። ጥሪ ከወዲያ ማዶ እየተበራከተ ነው። የድረሱልን ጥሪ!
ስለዚህም መላው የሀገራችን ህዝብ ወያኔን ለማስገደድ አሊያም ለማስወገድ አቅሙ በፈቀደ ሁሉ በገንዘብ፣ በእውቀት በጊዜና ጉልበቱ በመርዳት ታግለን የካቲትን የመሰዋእትነት መንፈስ እያስታወስን፣ ግንቦት 7ን የህዝብ ድምጽ ለማስከበር ይህ ትውልድ ሞራላዊ ግዴታ አለበት እና እንነሳ! እንሂድ።
በአንጻሩ በወያኔ መንደር በአጋጣሚም ሆነ በጥቅም ምክንያት ያላችሁ፡- እንደ ጠዋት ጤዛ ብን ብለው ከሚጠፉ አምባገነኖች ጋር በመለጠፍ ህዝባችንና ሀገራችንን መበድልና ማሰቃየት ለታሪክ ተጠያቂነት ይደርጋል። በወንጀል ተባባሪነት ስለሚያስጠይቅ ከወዲሁ መንገድን በማስተካከል እምቢ ለህወሃት፣ በቃኝ ባርነት፤ በሚል የህዝብ አጋርነትና ድጋፍ ወደ አለው የነጻነት ትግል በመቀላቀል ከማይሻር፣ ከማይጠፋ የታሪክ ማህደር ውስጥ ራስዎትን ያስገቡ ዘንድ የካቲት ጥሩ አጋጣሚ ነው።
በተለይም ኢትዮጵያውያን አርበኞች በጠላት ላይ የወሰዱት የማያዳግም እርምጃ ለመድገም እና ኢትዮጵያን ከሀገር ውስጥ ጠላት ከሆነው ህወሃት ለመታደግ፤ ነፃነታችንን አሳልፎ ላለመስጠት፣ ብርቱ ክንዳቸውን በአኩሪ መሰዋእትነት ለማሳረፍ እና ሕያው ምስክር ለመሆን ከተነሱት ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ጋር ሆነን በጋራ በተባበረ ሃይል የምንታገልበት ጊዜ ዛሬ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

The Muslim Brothers Poem on ESAT Fundraising Program with Tamagne Beyene...

መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫልበአለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ችግሮችን መፈልፈያ መሣሪያ ሆናለች፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት ይዘናቸው (ምናልባትም አቅፈናቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ስንንከባለል የቆዩ ችግሮች ሞልተውናል፤ እያሰብን እነዚያን የቆዩ ችግሮቻችንን በመፍታት ፋንታ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈልን የተቆላለፉና የተወሳሰቡ፣ ውላቸው የጠፋ ችግሮችን ፈጥረናል፤ እየፈጠርንም ነው፤ አሁን በመፈጠር ላይ ያለው አዲስ ችግር እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚል ነው፤ እስቲ እንመልከተው፡፡
በሩቁ እንጀምር፤ እስላማዊ መንግሥታት ያቋቋሙ አገሮች አሉ፤ አንዳቸውም ሰላም የላቸውም፤ እስላማዊ ቡድኖች በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአረብ አገሮች በተጀመረው የፖሊቲካ እድገት ለውጥ በቱኒስያና በግብጽ እስላማዊ ቡድኖች አሸንፈው ሥልጣን ይዘዋል፤ በዚህም ምክንያት በቱኒስያና በግብጽ የለውጥ ጥያቄ አገርሽቶ አንደገና ሰዎች እየሞቱ ነው፤ በነዚህና በሌሎችም አገሮች የሚገኙት ወጣቶች የሚፈልጉት የሰው ልጆች ሁሉ መብቶች የሚከበሩባቸውና በሙሉ የግለሰብ ነጻነት የተረጋገጡባቸው አገሮች እንዲኖራቸውና በእኩልነት ኩሩ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ነው፤ የአንድ አገር ዜጎች የተለያየ ዘር፣ የተለያየ የቆዳ ቀለም፣ የተለያየ ቁመትና ውፍረት፣ የተለያየ ጾታና ዕድሜ፣ የተለያየ ቋንቋ፣ የተለያየ ሃይማኖት፣ የተለያየ የፖሊቲካ አመለካከት፣ የተለያየ ትምህርት፣ የተለያየ ሙያና የተለያየ ገቢ ሊኖራቸው ይችላል፤ የጋራ ማንነታቸው ዜግነት ነው፤ እኩልነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ አንድነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ እኩልነታቸውንና አንድነታቸውን የሚያረጋግጥላቸውና ሚዛኑን የሚጠብቅላቸው ከበላይ ሆኖ ሁሉንም የሚገዛው ሕግ ነው፡፡
በቡድን ወይም በጅምላ የሚያስቡ ሰዎች የሕግን ባሕርይ አያውቁትም፤ ‹‹áŠ­áˆ­áˆľá‰˛á‹ŤáŠ–ች እስላሞችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ ወይም እስላሞች ክርስቲያኖችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ በሚል አሉባልታ ላይ ክስ ተመሥርቶ ሕጋዊ ፍርድ መጠበቅ አይቻልም፤ በየትም ሆነ በማንኛውም ጊዜ ጽንፈኛ እምነትና አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ፤ እነዚህ ግለሰቦች ሕልማቸውንም ሆነ ቅዠታቸውን በስውርም ሆነ በአደባባይ ይገልጻሉ፤ ለምሳሌ በአሜሪካ ጥቁሮችንና ይሁዲዎችን ከአገሩ ጠራርገን እናወጣና ንጹሕ የነጮች አገር እንፈጥራለን የሚሉ ግለሰቦች አሉ፤ ይህ እምነት ለአሜሪካ ማኅበረሰብ መርዝ ነው፤ አሜሪካ የነጻነት አገር ነው፤ የነጭ ዘረኞቹ መርዛቸውን ለመንዛት መብት አላቸው፤ የዘረኞቹን መብት ለማፈን የሚወሰድ የጡንቻ እርምጃ ሁሉ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ይሽራል፤ ከዚያም በላይ የአሜሪካ መንግሥት በሚከተለው ዘዴ ከነጭ ዘረኞቹ የተሻለ አይሆንም ነበር፤ ስለዚህም ነጭ ዘረኞችን ለመቋቋም የሚወሰደው አርምጃ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ሳይሽርና ነጭ ዘረኞቹም እምነታቸውን የመግለጽ መብታቸው ሳይደፈጠጥ መሆን አለበት፤ የነጻነት ትርጉሙ ይህ ብቻ ነው፡፡
በሥልጣን ወንበር ላይ ስለተቀመጡ ብቻ አንድ ዓይነት የፖሊቲካ እምነት ብቻ ይዞ ሌላውን መደፍጠጥ፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የኦርቶዶከስ ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የእስልምና ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን ልማድና የአሠራር ባህል እየሆነ ሲሄድ ሁሉንም ነገር አንድ ዓይነት ብቻ ለማድረግ የሚታየው ጥረት የኢትዮጵያን ጉራማይሌ ባሕርይ የሚቃረን በመሆኑ ሾር አይኖረውም፤ ይህ ሁሉም ሰው ሊያስብበት የሚገባው አንዱ ነገር ነው፤ ሁለተኛው አንድ ወይም ጥቂት ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እናቋቁማለን ቢሉ አገር የሚሸበርበት ምንም ምክንያት የለም፤ ኢትዮጵያን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አገር ለማድረግ የሚመኙም አሉ፤ ኢትዮጵያን ሃይማኖት-አልባ የጉግማንጉግ አገር ለማድረግ የሚፈልጉ አሉ፤ ኢትዮጵያ በአንድ አጋጣሚ ወንበሩ ላይ የወጣ ጉልበተኛ የሚያትምባትን እምነትም ሆነ ሃይማኖት የማትቀበል አገር መሆንዋ ተደጋግሞ የታየ ነው፤ ኢትዮጵያን የይሁዲ አገር ለማድረግ ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የክርስቲያን አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የእስላም አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ሁሉም አልሆነም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ሆና ዘልቃለች፤ ይህንን በማክሸፍ ለማንም ምንም ጥቅም አይገኝም፤ በአንጻሩ ደግሞ የሥልጣን ወንበሩ ላይ የወጡ ጉልበተኞች ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀውን የነጻነት ጮራ እያዳፈኑ የነጻነትን፣ የእኩልነትንና የሕግ የበላይነትን ዓላማ ለማክሸፍ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፡፡
የነጻነትና የሕጋዊነት መክሸፍ የሰላም ጠንቅ ነው፤ የሰላም መክሸፍ የልማት ጠንቅ ነው፤ የልማት መክሸፍ ደሀነት ነው፤ ደሀነት የሞት አፋፍ ነው፤ ይህንን ለመገንዘብ የሚያዳግተው ሃያ አንድ ዓመት የሞላው ሰው አለ? ኢትዮጵያን ለመምራት የሚደናበሩት ሰዎች ሁሉ ሃያ አንድ ዓመት አልፎአቸዋል፤ ነገር ግን ከላይ የተገለጸው የመክሸፍ ጉዞ ጭራሽ አይታያቸውም፤የሚታየውም ሲነግራቸው የተበለጡ ስለሚመስላቸው አይሰሙትም፤ ስለዚህም የሚታየውን ሳያዩ፣ የሚሰማውን ሳይሰሙ ጊዜ የሚበላውን ጉልበታቸውን ብቻ ተማምነው በጭፍን እንምራችሁ የሚሉትን ተከትለን ለእኛ በሚታየንና ለእነሱ በተሰወረባቸው ገደል ውስጥ ለምን አብረን እንግባ? አብረን ገደል በመግባት አንድነታችንን የምንጠብቅ የሚመስላቸው ሰዎች በሁለት በኩል ይሳሳታሉ፤ አንደኛ ከአገዛዙ መሪዎች ዘንድ የሎሌ ተከታይነትን እንጂ የአኩልነት አንድነትን አያገኙም፤ እኩልነት በሌለበት አንድነት አይፈጠርም፤ ሁለተኛ ወደገደል የሚጨምር አንድነትን መምረጥ ሕይወትን ትቶ ሞትን መምረጥ ነው፡፡
በሃያ አንድ ዓመት ውስጥ መክተፍ-መከታተፍ ሙያ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችና ድርጅቶች ሠለጠኑበት፤ መክተፍ-መከታተፍ አብሮ የመኖር ጸር ነው፤ አብሮ የመኖር ጸር የሚሆነው በፍቅር ፋንታ ጥላቻን፣ በሰላም ፋንታ ጠብን፣ በመረዳዳት ፋንታ መጋጨትን፣ በልማት ፋንታ ጦርነትን በመንዛት ነው፤ አንዳንድ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በግልጽም ሆነ በስውር እንደጠላት መቁጠርና በእነሱ ላይ ቂምን እንዲቋጥሩ ማድረጉ የማንንም የፖሊቲካ ቡድን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ይጎዳል እንጂ አይረዳም፡፡
አሁን ደግሞ በአንድ በኩል በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ በየገዳማቱና ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃትና በሊቀ ጳጳሳት ምርጫው ላይ አገዛዙ እያሳየ ያለው ጣልቃ-ገብነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን እያስቀየመና እያስኮረፈ ነው፤ በሌላ በኩል በእስልምና ሃይማኖት ላይም የሚታየውን ጣልቃ-ገብነት ተከታዮቹ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በርትተው በመቋቋማቸው እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ለጆሮ እየቀፈፈና በጣም አሳፋሪ እየሆነ ነው፡፡
ይህ በሃይማኖቶች ላይ የተጀመረው ዘመቻ ውጤት ይኖረዋል፤ ውጤቱ በአገዛዙ የውስጥም ሆነ የውጭ አመራሩ ላይ ከባድ ተጽእኖ ይኖረዋል፤ የሃይማኖቶቹ ጉዳይ እንደጎሣዎች መከታተፍ በኑሮ ላይ ብቻ ጫናውን የሚያሳርፍና በምድር የሚንከላወስ አይደለም፤ ወደሰማይ ያርጋል፤ የሰማይ ሠራዊትን ይጠራል፤ ያንን ኃይል እንኳን የኢትዮጵያ የጦር ኃይልና የአሜሪካውም አይችለውም፤ ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ ልብ ያለው ያስተውላል፤ ዶላር ነፍስን አይገዛም፤ ክብርን አይገዛም፤ ወዳጅንም አይገዛም፡፡
ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም፤ የካቲት 2005

ሰበር ዜና – አስመራጭ ኮሚቴው ለዕጩነት የለያቸው አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!

ሐራ ዘተዋሕዶ

  • ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አልተካተቱም
  • ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው አጠራጣሪ ኾኗል
  • የፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱ ከዕጩዎች ማንነት ጋራ በአግባቡ ይረጋገጥ
  • ‹‹á‹•áŒŠá‹Žá‰šáŠ• ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ››› /ሰሞንኛ አባባል/
የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩ ፓትርያሪክነት አጣርቶ የለያቸውን አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ማቅረቡ ተሰማ፡፡ ከየካቲት ዘጠኝ ቀን ጀምሮ የዕጩዎች ልየታ ሲያካሂድ የቆየው አስመራጭ ኮሚቴው÷ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ስም ዝርዝር፡-
1)  á‰Ľáá‹• አቡነ ማትያስ – በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ
2)  á‰Ľáá‹• አቡነ ማቴዎስ – የወላይታ ዳውሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3)  á‰Ľáá‹• አቡነ ዮሴፍ – የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4)  á‰Ľáá‹• አቡነ ሕዝቅኤል – የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
5)  á‰Ľáá‹• አቡነ ኤልሳዕ – የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡
የአስመራጭ ኮሚቴው አጣርቶ ሊያቀርባቸው ከሚችላቸውና የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አባቶች አራቱ በኮሚቴው የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ኮሚቴው በሚያቀርባቸው ዕጩዎች ውስጥ ያልተጠበቁ አባቶች ሊታዩ እንደሚችሉም አስቀድሞ የተገመተ ነበር፡፡
ነገር ግን በብዙ ሺሕ የካህናትና ምእመናን ድምፅ የተጠቆሙትና በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ አንቀጽ 5 የተዘረዘረውን የዕጩ ፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱን ያሟላሉ ተብለው የታሰቡት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል (ከ9000 ያህል ጠቅላላ ጠቋሚዎች 7200 አግኝተዋል)
እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከዕጩዎቹ ሳይካተቱ መቅረታቸው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካላትን መስገረሙ አልቀረም፡፡ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ቀድሞም ከዕጩዎች ዝርዝር እንዳይጨመሩ በአንዳንድ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትና በተለይም ‹‹áˆ˜áŠ•áŒáˆĽá‰ľ የሚፈልጋቸውን ብፁዕ አቡነ ማትያስን እናስመርጣለን›› á‰ áˆ›áˆˆá‰ľ በመራጮች ላይ ሽብርና ስጋት ሲፈጥሩ በሰነበቱት÷ የእነ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ ወ/ሎ እጅጋየሁ በየነ፣ መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም፣ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ፣ መ/ር አባ ገብረ መድኅን ኀይለ ጊዮርጊስ እና መ/ር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተ ቡድን ከፍተኛ ጫና ሲፈጠር መሰንበቱ ተዘግቧል፡፡
ኮሚቴው ዕጩዎቹን የለየበትን ሂደት ወደፊት በዝርዝር ለማወቅ የሚጠበቅ ቢኾንም ሾለ ተግባርና ሓላፊነቱን አስመልክቶ÷ á‰ áŠ áŠ•á‰€áŒ˝ 6/ሐ – ጥቆማ ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከካህናትና ምእመናን እየተቀበለ እንደሚሠራ፤ á‰ áŠ áŠ•á‰€áŒ˝ 6/ሰ – የዕጩዎችን ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ ለ15 ቀናት ይፋ በማድረግ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን እንደሚቀበል፤ á‰ áŠ áŠ•á‰€áŒ˝ 6/ሸ – በተቀበላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች መሠረት ዕጩዎቹን ከቅ/ሲኖዶስ ጋራ መርምሮና አጣርቶ የሚቀበለውን ከተቀበለ፣ የማይቀበለውንም ከጣለ በኋላ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ዕጩዎች ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ እንደሚያሳውቅ በግልጽ የተደነገገ በመኾኑ ቀጣይ አካሄዱ ከእኒህ á‰ á‰°áŒ¨á‰ŁáŒ­ መሸራረፍ ከጀመሩ áŠ áŠ“á‰…áŒ˝ አኳያ የሚመዘን ይኾናል፡፡
ሐራዊ áˆáŠ•áŒŽá‰˝ ከወዲሁ ስለኹኔታው ለመረዳት ባደረጉት ጥረት ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው ጥርጣሬ ያላቸው ሲኾን ከዚህም በመነሣት ውሳኔውን በፊርማቸው ስለማረጋገጣቸውም አበክረው ይጠይቃሉ፡፡
‹‹á‹•áŒŠá‹Žá‰šáŠ• ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ›› የሚለው ሰሞንኛ አባባል ቋጠሮው ሊፈታ እነኾ ቀኑ ቀርቧል፡፡

Feb 20, 2013

በሚኒሶታ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ

“የኢቲቪ ጀሃዳዊ ሀረካት የፈጠራ ድራማ የመብት
ትግላችንን አይገታም” ሲሉ በሚኒሶታ የሚገኙ
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ባወጡት ባለ5 ነጥብ
የአቋም መግለጫ ላይ አስታወቁ።
ሙሉ መግለጫው የሚከተለው ነው። ( መግለጫውን
)pdf ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በቅርቡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጀሀዳዊ ሀረካት በሚል
ስያሜ ተራ የፈጠራ ተራኪ ፊልም ለህዝብ መተላለፉ
ይታወቃል። በማናቸውም መመዘኛ ቅንጣት እውነታን
ያላዘለ አግባብነት የሌለው ውንጀላ የሞላበት ለመሆኑ
ለመረዳት አያዳግትም፤ የፊልሙ አዘጋጆች ምን ያህል
የወረደ የሞራል ዝቅጠት ደረጃ ላይ እንደ ደረሰ
የሚያመላክት ነው።
በዚህ ዓይነት የፈጠራ ተውኔት የሙስሊሙ የመብታችን ይከበር ጥያቄ ለማዳፈን ከንቱነት ነው። ሙስሊሙ
ሕብረተሰባችን ትግሉን በስፉት ከጀመረበት ከ፩ አመት በላይ ፍጹም ሰላማዊ ጥያቄውን እያቀረበ ያለበት ስልት
የሰለጠነና ሕግና ስርአትን የተከተለ ለመሆኑ የማያሻማ እውነታ ነው። በተገላቢጦሽ የመንግስትን ስልጣን የያዘው አካል
ግን ሙስሊሙን ማሸበር፣ ማሰርና መግደል የእለት ተግባር አድርጎታል። በእስር ላይ በሚገኙ በመፍትሔ አፈላላጊ
ኮሚቴ አባላትም ላይ እየደረሰ ያለው የአካል ጉዳትና የአእምሮ ሰቆቃ እጅግ ከፍተኛ ነው።
ይባስ ተብሎም ቅጥ ያጣው የመንግስት ድርጊት የሚያሳየን በፍርድ ቤት ለህዝብ እንዳይታይ እገዳ የተጣለበትን
የኢቲቪ የፈጠራ ፊልም በግለሰብ ቀጭን ትእዛዝ ተሽሮ መቅረቡ ታውቋል። ይሕም ገዢው መንግስት ራሱን ከሕግ
በላይ ማድረጉ እና ልሹ ህግን እንደፈለገው የሚያዘው መሆኑን ነው።
ሪሳላ ኢንተርናሽናል ከዚህ በታች የሚገለጸው አቋም ላይ መድረሱን ለሁሉም አበክርን እንገልፃለን።
፩ኛ. በእስርና በእንግልት

፫ኛ. በግፍ በእስርና በእንግልት የሚገኙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና በየእስር ቤቱ የተሰሩ ሙስሊሞች በሙሉ
ያላ ምንምቅድመ ሁኔታ በነፃ እንዲላቀቁ እንጠይቀለን።
፬ኛ. በሃገሪቱ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎችን አፍኖ ማሰር ከትምህርት ገበታቸው
ያለአግባብ ማገድና ማሸማቀቅ በአስቸኳይ እንዲገታ እንጠይቃለን።
፭ኛ. በሙስሊሙ ህብረተሰባችን የቀረበው ግልፅና መሰረታዊ የመብት ጥያቄ አሁንም ምላሽ የሚሹ በመሆኑ ለዚሁ
ሰላማዊ ትግል ሙሉ ድጋፋችን እንገልፃለን ።
ኢስላም የሰላም ሃይማኖት ነዉ!!
እምነትን በነፃነት መተግበር ሰባዊ መብት ነዉ!
አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! አላሁ አክበር!

Feb 19, 2013

በጂሃድ ሃረካት ፊልም ላይ ከ33ቱ ፔቲሺን ፈራሚዎች የተሰጠ መግለጫ

ንብረትነቱ የሕዝብ ቢሆንም አገልግሎቱ የኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሆነው ኢቲቪ በሰሞኑ የፍርድ ቤት ዕግድ ወደጎን በመግፋት ከተለያዩ ፊልሞች በመቀነጫጨብ ‹‹áŒ‚áˆƒá‹łá‹Š ሃረካት›› በማለት ጉዳያቸው በፍርድቤት እየታየ ባለው በእሥር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ያነጣጠረ ፊልም በተደጋጋሚ አሰራጭቶ ተከታትለናል፡፡ከሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ጭንቀት የፈጠረበት ዝዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በትናንትናው እለት ሞባይል ኔትወርክ አቋርጦ እንደነበር ታወቀ


ላለፈው አንድ አመት በጽናት የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ የሚገኙት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የፈጠሩበት ጭንቀት ያደናበረው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ  áŠ¨áŒáˆáŠ  ጸሎት ስርዓት ጋር ረብሻና ከፍተኛ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት ትናንት ማለዳ በአዲስ አበባ የሞይባል አገልግሎት ከአምስት ሰዓታት በላይ እንዲቁአረጥ አድርጎ እንደነበር ዘጋቢያችን በላከልን ሪፖርት ገለጸ፡፡
እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ከጊዜ ወደጊዜ በጽናት ድምጻቸውን የሚያሰሙት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በመደበኛ የጁምአ ፕሮግራማቸው እርስ በእርስ በመጠራራት እና አጫጭር የስልክ መልዕክቶችን በመለዋወጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊያደርጉብኝ  á‹­á‰˝áˆ‹áˆ‰ በሚል ፍርሃት ሐሙስ ለዓርብ አጥቢያ በግምት ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የተወሰኑ የሞባይል ሰልክ ቁጥሮችን ከግንኙነት ውጪ የማድረግና ኔትወርክ የማቋረጥ እርምጃንም ወስዱአል፡፡
የህዝብ መንገላታት ደንታ የማይሰጠው የወያኔ አገዛዝ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ያነጣጠረ ርምጃው በበርካታ ግለሰቦችና የቢዝነስ ተቋማት ላይም ተመሳሳይ ተጽእኖ በማሳደሩ የእርስ በርስ ግንኙነት ማድረግ ሳይችሉ ለማርፈድ መገደዳቸውን ዘጋቢያችን አያይዞ ገልጹአል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ሁሉም የሞይባል አገልግሎት ያልተቋረጠበት ዋንኛ ምክንያት ምን እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ባገኘው መረጃ የተወሰኑ የደንበኛ ጭነት ያለባቸው መስመሮች ግንኙነት ከተቋረጠ ያልተቋረጠባቸው ስልኮች ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም ማለታቸውን ገልጹአል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ቁጥሮች አለመቋረጣቸው ቴሌ ለሚነሳበት ቅሬታ የኔትወርክ መጨናነቅ ነው በሚል ጉዳዩን ለማስተባበል ስለሚረዳው ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑን እነኝሁ ምንጮች መጥቀሳቸውንና የዚህ ዓይነቱ አሰራር ሲፈጸም የመጀመሪያው አለመሆኑን ማመልከታቸውን ኢሳት ገልጹአል፡፡
በስፋት እንደሚታወቀው ካሁን ቀደምም  áˆ˜áˆˆáˆľ ዜናዊና ሌሎች የአገር መሪዎች በከተማ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ ሲገቡና ሲወጡ መንገዶችን ከመዝጋት ባሻገር ሸብርተኝነትን አስቀድሞ ለመከላከል በሚል የተወሰኑ የሞይባል ግንኙነቶች ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሲቋረጡ መቆየታቸውን ሲዘገብ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በአፋኙ የወያኔ ስርአት በሞኖፖል የተያዘው የቴሌኮም ዘርፍ ለግሉ ዘርፍ ክፍት እንዲሆን ከማይፈለግባቸው ምክንያቶች አንዱ አገዛዙ ባሻው ጊዜ ስልኮችን የማቋረጥ፣የመጥለፍና የመሳሰሉ ህገወጥ ድርጊቶችን ለመፈጸም እንዲረዳው በማሰብ መሆኑን ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ደህንነት መ/ቤት “ጀሃዳዊ ሃራካት” በሚል ርዕስ በሕግ ጥላ ሾር የሚገኙ ሙስሊም እስረኛችን በማስገደድ የተጠናቀረ ፊልም ጥር 28 ቀን ምሽት በኢቴቪ ካሰራጨ በኋላ እንደገና ከዳር እስከዳር የተቀጣጠለውን የሙስሊሞች ተቃውሞ ለማዳፈን ዜጎች በነፍስ ወከፍ ኮንትራት ገብተው እያገኙ ያሉትን የሰልክ አገልግሎት ከፈቃዳቸው ውጪ በማቋረጥና በማስተጓጎል ሼል ውስጥ መጠመዱ አገዛዙ አሁን ያለበትን ገደብየለሽነት ፍርሃት በግልጽ የሚያመላክት ነው፡፡

መሪ አልባዉ የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በስንዴ ግዢ ጉዳይ ሲጨቃጨቅ መክረሙ ተሰማ


ከዘረኛዉ መለሾ ዜናዊ ሞት በኋላ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ መሪ የሌለበት የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተብየው መፈራራትና መከባበር የሚባል ነገር ርቆት አባላቱ “ፕሮፓጋንዳ ይሻለናል” ወይስ “ሀቁን ተጋፍጠን መፍትሔ እንፈልግ” በሚሉ ሁለት ቡድኖች ተከፍሎ በየቀኑ ሲጨቃጨቅ እንደሚዉል ለካቢኔዉ ቅርበት ያለቸዉ የታመኑ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩልን ዜና ገለጹ። የስንዴው ፖለቲካ በሚል አርዕስት ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰዉ ዜና መሰረት የወያኔ አገዛዝ አገሪቱ ዉስጥ በኤኮኖሚዉና በማህበራዊ ዘርፎች እየደረሰ ያለዉን ቀዉስ መቆጣጠር አቅቶት አሁን ስራዬ ተብሎ የተያያዘዉ የእህል ውድነት በህዝቡ ላይ በተለይ ወያኔ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ብሎ በሚፈራዉ በከተማዉ ህዝብ ላይ ያስከተለውን ቀውስ በአስቸኳይ “ለማረጋጋት” ምን ያህል ስንዴ ከውጭ እንግዛ በሚል ጭቅጭቅ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮቹ አክልዉ በላኩልን ዜና ገልጸዋል ።

በዚህ ሳምንት ከወያኔ ጓዳ በደረሰን ዜና መሰረት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር በሚል በያዝነዉ ወር 850 ሺህ ኩንታል ስንዴ አገር ውስጥ ገብቷል። የዚህ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ወጥቶበት የተገዛዉ ስንዴ ጉዳይ ቀድሞዉንም በቋፍ የነበረዉን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጭራሽ ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ ዉስጥ እንዲዘፈቅ አደርጎታል። በአንድ በኩል ግዢዉ የሚፈጥረዉ የዉጭ ምንዛሬ ጉድለት የባሰዉኑ የዋጋ ግሽበቱን ያባብሰዋል የሚሉ የካቢኔዉ አባላት ሲኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ “ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ከ1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ስንዴ ከውጭ አምጥተን አከፋፍለናል ሆኖም ምንም አይነት ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣት አልቻልንም ብለዉ የሚከራከሩ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ቁጥራቸዉ ትንሽ ቢሆንም ከእነዚህ ሁለት ቡድኖች ለየት ያለ አስተሳሰብ ያለቸዉና የአገሪቱ ችግር የገባቸዉ አንዳንድ የካቢኔዉ አባላት ደግሞ ችግራችን ስንዴ መግዘት ወይም ማምረት ሳይሆን የገዛነዉን ወይም ያመረትነዉን ስንዴ ለተጠቃሚዉ ህዝብ በሚገባ ማከፋፈል አለመቻላችን ነዉ የሚሉም አልታጡም። ለምሳሌ የወያኔ አገዛዝ እራሱ በሰጣቸዉ መግለጫዎች “በ1.5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ይመረታል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከ3 ሚሊየን ቶን በላይ ስንዴ ኢትዮጵያን ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በስንዴ ምርት ቀዳሚ ያደርጋታል፤ ችግሩ ግን ይህ ብዛት ያለዉ ስንዴም ሆነ ከዉጭ አገር ተገዝቶ የሚመጣዉ ስንዴ ዬት እንደሚገባ አይታወቀም።

ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን በተገኘዉ መረጃ መሰረት ገበያ ለማረጋጋት በሚል ሰበብ ስንዴ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገዛ አየር በአየር ወደ ሌላ አገር እየተዛወረ በመሸጥ ላይ ሲሆን ግዢውን የሚፈቅዱት፣የሚያስፈጽሙት፤ የሚያጓጉዙትና ብሎም ወደ ደቡብ ሱዳንና አረብ አገሮች እያወጡ የሚሸጡት፣ በዘርና በስጋ ዝምድና የተሳሰሩ የህወሀት ሰዎች መሆናቸው በገልጽ ይታወቃል።

መለሾ ዜናዊ በህይወት በነበረባቸዉ ግዜ ማንም ሰዉ ደፍሮ የማያነሳቸዉ ይንንና ይህንን የመሳሰሉ ጉዳዮች ዛሬ የመወያያ አርዕስቶች እየሆኑ በመምጣታቸዉ ስልጣን ከእጃችን ሊወጣ ይችላል በሚል ፍራቻ ብዙ የወያኔ ባለስልጣኖች አገሪቱን ባዶዋን እያስቀሯት መሆኑን ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ፤ በተለይ ከአገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት የሚኮበልለዉ የዉጭ ምንዛሬ ብዛት ያሰጋቸዉ አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ አዳራ ያሉን የገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የህወሀት አባላት ዝርፍያ በዚህ ከቀጠለ በቅርብ ግዜ ዉስጥ የኢትዮጵያ የዉጭ ምንዛ ካዝና ባዶ ይሆናል ብለዋል።

ታስሮ የነበረው ኤርሚያስ አመልጋ ተፈታ

(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት መልሚ የኢትዮጵያ አስተዳደር በሃገሪቱ ውስጥ የሕወሓት ነጋዴዎች ካልሆኑ በስትቀር ሌሎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው በሃገራቸው ነግደው እንዳይበሉ ከፍተኛ ምቀኝነት እንዳለበት በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም። ከዚህ ቀደም በንግድ ብልጠት የሕወሃት የንግድ ድርጅቶችን እርቃናቸውን በኪሳራ አስቀርተው የነበሩት የስታር ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤቶች የሕወሓትን ክፍፍል ተከትሎ በተፈጠረ ድንጋጤ በሙስና ሰበብ ታስረው ከንግዱ ዓለም እንዲወጡ መደረጉ አይዘነጋም።
- የኮካ ኮላ ከፍተኛ ባለ አክሲዮን አቶ ንጉሴም ከአቶ ታምራት ክስ ጋር ተያይዘው በኪሳራ ከሕወሃት ድርጅቶች ተፎካካሪነት ወጥተዋል።
- የሃግቤስ ኢንተርናሽናል ባለቤት ሚ/ር ህራየር ቤንሰን (አርመናዊ ናቸው) እርሳቸውም በሙስና ሰበብ ከአቶ ስዬ አብርሃና ወንድሞቻቸው ጋር እንዲታሰሩ በመደረግ ከሕወሓት ንግዶች ጋር እንዳይፎካከሩ ተደርገው ግማሽ ደርዘን ዓመታትን እስር ቤት እንዲያሳልፉ ተደርገዋል።
- የመስቀል ፍላወር ባለቤት አቶ እስክንድርም በሕወሓት ተመትተዋል
- እነ አቶ ክቡር ገና በተፎካካሪነት ላይ አይደሉም
- በአቢሲኒያ ባንክ ላይ የደረሰውን ከአንባቢዎቻችን እንተወዋለን
- እንደ አቶ ብርሃነ መዋ ያሉ ነጋዴዎች ንግዳቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ተደርገዋል
- ጣይቱ ሆቴልን የገዙትና የዘሞኒተር የ እንግሊዘኛ ጋዜጣ አዘጋጅ አቶ ፍጹም ዘ-አብ አስገዶም እህታቸው የአቶ ስዬ አብርሃን ወንድም አቶ አስፋ አብርሃን ስላገቡ ብቻ ሕወሃት ለሁለት ሲሰነጠቅ “አቶ አሰፋ በአምቻ ጋብቻ ተይዘው ጣይቱ ሆቴልን በቅናሽ ለአቶ ፍጹም እንዲሸጥ አድርገዋል” በሚል ተከሰው ከገበያ እንዲወጡ ተደርጓል
ምን ይሄ ብቻ? ሌላም ሌላም
አዲሱ የወያኔ ሰለባ ደግሞ ኤርሚያስ አመልጋ ናቸው።
ከዚህ ቀደም ቡሬ የተሰኘውን ውሃ በጎጃም ክልል ውስጥ ፋብሪካ ከፍተው ሲያቀርቡ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ “በደረቅ ቼክ ማጭበርበር ወንጀል” ታስረው ተፈትተዋል። መለሾ ሞተዋል የሚል ዜና በኢሳት በተነገረበት ወቅት “አልሞቱም አዲስ አበባ ገብተዋል” እያለ በማስተባበል ሼል ላይ የከረመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ኤሚያስ ታሰሩ ብሎ በሰበር ዜና ቢዘግብም ሪፖርተር ደግሞ ታስረው ተፈቱ ብሏል። የሪፖርተር ዜና እንደወረደ ይኸው፦
የዘመን ባንክና የአክሰስ ሪል ስቴት መሥራች የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከደረቅ ቼክ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው አንድ ቀን በቁጥጥር ሼር ውለው ባለፈው ዓርብ ተለቀቁ፡፡
አክሰስ ካፒታል ግን በአቶ ኤርሚያስ ላይ የተጀመረው ምርመራ መቋረጡን አስታውቋል፡፡
አቶ ኤርሚያስ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ካዛንቺስ (ስድስተኛ) ማዘዣ ጣቢያ አንድ ቀን ካደሩ በኋላ ተለቀዋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ችግሩ የተፈጠረው ባለመግባባት መሆኑን ገልጸው፣ አሁን ግን ምርመራው ተቋርጦ ወደ ሼል መመለሳቸውን አስታውቀዋል፡፡
አቶ ኤርሚያስ የተጠረጠሩበት ምክንያት የአክሰስ ሪል ስቴት ኩባንያ አንድ ደንበኛ ኩባንያው እሠራለሁ ያለውን ቤት ሠርቶ በወቅቱ አላስረከበኝም በማለት ገንዘባቸው እንዲመለስ ሲጠይቁ፣ አቶ ኤርሚያስ የ350 ሺሕ ብር ቼክ ይፈርሙላቸዋል፡፡
እኝህ ደንበኛ ዘመን ባንክ ሄደው በቼክ የተጻፈላቸውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ ክስ በመሄዳቸው ነው አቶ ኤርሚያስ በቁጥጥር ሼር የዋሉት ተብሏል፡፡
ምንጮች እንደሚገልጹት ግን፣ አካውንቱ ውስጥ ገንዘብ ነበር፡፡ ነገር ግን ሌላ የሪል ስቴቱ ደንበኛ አካውንቱን በፍርድ ቤት በማሳገዳቸው ገንዘቡን ማንቀሳቀስ አልተቻለም፡፡ አክሰስ ካሉት አካውንቶች ውስጥ በአንደኛው ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ እንደነበር ሪፖርተር መረዳት ችሏል፡፡ ይህም መረጃ ለመርማሪዎቹ ቀርቦ የይከፈለኝ ጥያቄ ላነሱት ግለሰብ ገንዘቡ ተከፍሏቸዋል፡፡ ግለሰቡም ወዲያው ክሱን በማንሳታቸው ምርመራው ተቋርጦ አቶ ኤርሚያስ ተለቀዋል፡፡
አክሰስ ሪል ስቴት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአካውንቱ ውስጥ በቂ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጧል፡፡ የተፈጠረው ክስተትም በቢዝነስ እንቅስቃሴ ውስጥ በየጊዜው የሚያጋጥም መሆኑን የገለጸው አክሰስ፣ መርማሪዎቹ ይህንኑ ተረድተው ምርመራውን ማቋረጣቸውን አስታውቋል፡፡
በዘመን ባንክ በአካውንቱ ውስጥ ገንዘብ መኖሩን ተረጋግጦ፣ ችግሩ ሊፈጠር የቻለው በአካውንቱ ውስጥ ገንዘብ ባለመኖሩ ሳይሆን በፍርድ ቤት ውሳኔ በመታገዱ መሆኑን የሚገልጹ አሉ፡፡
ችግሩ የተፈጠረውም በዘመን ባንክ ስህተት መሆኑን የሚገልጹት ምንጮች፣ ባንኩ በጉዳዩ ሳይጠየቅ እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡ የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሚያስ እሸቱን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ብንሞክርም፣ ‹‹á‰ á‰ŁáŠ•áŠŠ ፖሊሲ መሠረት በደንበኞች ጉዳይ ላይ አስተያየት አንሰጥም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ወደተለመደው የሥራ ገበታቸው መመለሳቸውን ያስታወቀው አክሰስ ሪል ስቴት፣ በቀጣይ ሳምንታት ሥራውን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃዎችን ለደንበኞቹ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡
አቶ ኤርሚያስ በኢትዮጵያ ቢዝነስ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ሰዎች ተርታ የሚመደቡ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ባንኮች ውስጥ በመሥራት የሚታወቁት አቶ ኤርሚያስ ኃይላንድ በመባል የሚታወቀውን ውኃ፣ ዘመን ባንክን፣ አክሰስ ሪል ስቴትና ሌሎች ተዛማጅ ቢዝነሶችን በመመሥረት ይታወቃሉ፡፡

አበበ ገላው ተጫማሪ የግድያ ዛቻ ደረሰው


(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተጨማሪ የግድያ ሙከራ ዛቻ እንደደረሰው በጎግል ቮይስ በኩል በድምጽ ማስረጃ አቀረበ። “አበበ ደምህን እንጠጣዋለን ፤ከኛ የትም አታመልጥም”ሲል አስፈራሪው ሰው ይሰማል። ይህን ተከትሎ አበበ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “የህወሃቶች ዛቻ እና የዘረኝነት ፉከራ ቀጥሏል። እስከ አሁን ያልተገለጠላቸው ሃቅ እንኳን ዛቻ ሞት ከትግላችንም ሆነ ከቁርጠኛ ጉዞአችን ፈጽሞ አይገታንም። ነጻነት ወይንም ሞት
ብሎ የተነሳን ህዝብ ማንም አንባገነን አያስቆመውም። እኔ ብሞትም በዛ በታላቅ አደባባይ ላይ የተናገርኩት እውነት ግን
ፈጽሞ አይሞትም፣ ምክንያቱም በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የታመቀ ሃቅ ነውና። ሃቅ ሲታፈን ፈንድቶ
መውጣቱ ያለ እና ወደፊትም የሚኖር ነው።”
ማስፈራሪያውን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ

Feb 17, 2013

በሙኒክ የተሳካ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሄደ

ኢሳት ዜና:-እውቁ የሰብአዊ መብቶች ተማጓች አርቲስት ታማኝ በየነ እና ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው በተገኙበት የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢ ዝግጅት ከተጠበቀው ሰው በላይ በመምጣቱ ቦታ መጥበቡን አዘጋጆች ለኢሳት ገልጸዋል።
የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆነው አቶ አበበ መለሰ እንደተናገረው በጀርመን የኢትዮጵያውያን ዝግጅት ታሪክ ይህን ያክል ህዝብ ሲሳተፍ ማየቱ የመጀመሪያው ነው።
ነገ እሁድ ፌብሩዋሪ 17 ደግሞ አርቲስት ታማኝ በየነ በኢሳት መቀመጫ አምስተርዳም ከተማ ተገኝቶ በሆላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያል። በዚህ ዝግጅት የሀይማኖት አባቶች እና  የሰብአዊ መብት ተማጓቾች ንግግር ያደርጋሉ።
የኢሳት የሆላንድ የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረሀይል በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ ላይ  እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ከዚህ ቀደም በኖርዌይ፣ በስዊድንና በስዊዘርላንድ ደማቅ እና ውጤታማ የድጋፍ ማሳባሰብ ዝግጅት ተካሂዷል።
ተመሳሳይ ዝግጅቶች በለንደን፣ በብራሰልንስና በፍራንከፍርት እንደሚካሄዱ የአውሮፓ የኢሳት ግብረሀይል አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ምርጫ ከ99 በመቶ በላይ በእጩነት የተመዘገቡት ኢህአዴግ ናቸው

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ወኪል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች= በመዘዋወር ያጠናቀረው ዘገባ እንደሚያመለክተው በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባ የወረዳና የአካባቢ ምርጫ፣ ተወዳዳሪ ሆነው በእጩነት የቀረቡት 99 በመቶ የሚሆኑት የኢህአዴግ አባላት ናቸው።
አብዛኞቹ ተመራጮች የመንግስት ሰራተኞችና በጥቃቅንና አነስተኛ ሾል ተመድበው የሚሰሩ ናቸው። በእጩዎች ስም ዝርዝር ላይ እንደሚታየው ከ40 በመቶ በላይ ተመራጮች ከ3ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል የሚሸፍን የትምህርት ደረጃ አላቸው። 40 በመቶ የሚሆኑት ተወዳዳሪዎች ደግሞ ከ10ኛ ክፍል እስከ ዲፕሎማ የሚደርስ የትምህርት ደረጃ አላቸው። ከ20 በመቶ በላይ ተወዳዳሪዎች  á‹¨áˆ˜áŒ€áˆ˜áˆŞá‹Ť ደግሪ እንዳላቸው ለማወቅ ተችሎአል።
ከ99 በመቶ በላይ በሆኑት  ጣቢያዎች በእጩነት የቀረቡት ኢህአዴጎች ሲሆኑ፣ የተቃዋሚ አባላትን ፈልጎ ማግኘት በእጅጉ አስቸጋሪ ነው።
33 የተቃዋሚ ድርጅቶች በምርጫው ላለመወዳደር የያዙት ጠንካራ አቋም ገዢው ፓርቲ የዘንድሮውን የአካባቢና አዲስ አበባ ምርጫ ብቻውን እንዲሮጥ አስገድዶታል።
በ1997 ዓም ምርጫ ቅንጅት በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ካሸነፈ በሁዋላና ገዢው ፓርቲ ውጤቱን በጉልበት ከቀማ በሁዋላ፣ በአዲስ አበባም ሆነ በመላ አገሪቱ በቂ ፉክክር የታየበት ምርጫ አልተካሄደም።
የገዢው ፓርቲ አባላት እስካሁን ድረስ ምርጫ ካርድ ላልወሰዱት ሰዎች ካርድ እያደሉ እንደሚገኙ በተለያዩ

Feb 16, 2013

ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደረገ ምሽት እንዳለ ጌታነህ ከኖርዌ እንደተመለከተው



የዳመነው ችግር፣ ሰማዩ እስኪጠራ፤ ካገር ተሰደድን በተራ በተራ። አንድ ቀን ይታየኛል፡ ታብሶ የኛ ዕንባ፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን አገር ቤት ስንገባ። ይህ ዜማ በአንድ ወቅት ቴዲ አፍሮ በአሜሪካ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በአገር ፍቅርና ናፍቆት ለሚሰቃየው አገር ወዳድ እጅ ለእጅ አያይዞ ያላቀሰበት ዘፈን ነበር። እኛም ዛሬ በፎቶው እንደሚታየው ለኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ በመሆን የሚያገለግለውን የእሳትን መለያ ካኔተራ በመልበስ በእሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት ላይ በኖርዌ የምንገኝ ስደተኞች ከአጭር ድራማ በኋላ የዘመርነው መዝሙር ነው።
ልቀጥል በዝግጅቱ ላይ የተገኘውን ህዝብ ስመለከት አንድ ነገርአሰብኩኝ፤ደግሞም ተመኘሁኝ፤ማሰብም መመኘትም መብቴ ቢሆንም ምናልባት እኔ እንዳሰብኩት ይህንን ጽሁፍArtist and activist Tamagne Beyene in Norway, Oslo  ESAT á‹¨áˆšá‹ŤáŠ•á‰Ľ ሰው ሃሳቤን ይጋራል ብዬ ልገምት፤ሀሳቤ ምን መሰላችሁ፤በፕሮግራሙ ላይ ታዳሚ የነበረው ዕድምተኛ በሙሉ ለሁሉም አገራዊ ጥሪ ህብረቱ፤አንድነቱ፦ትብብሩና በጋራ መስራቱ ሁል ጊዜ እንዳሁኑ ቢሆን፤ልክ የድራማው መጨረሻ ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን መዝሙሩን በአንድነት ከልብ ከስሜት እንደዘመርን ፤በእምነታችንና በዘራችን ሊለየን ፤የንግግር፦የመጻፍና በሰላም የመኖር መብታችንን ያሳጣንን፤አገራችንን ለባዕድ እየሰጠ ገበሬውን መሬትና አገር አልባ አድርጎ በአገሩ ላይ ስደተኛ እንዲሆን የሚያደርገውን ጨቋኝና ከፋፋይ የሆነውን የወያኔ መንግስት በጋራ ለማጥፋት፤ህብረታችን እንዲቀጥል፤የእርስ በርስ መናቆራችንን በመተው ላገርና ለወገን የሚበጀውን ቅድሚያ በመስጠት በህብረት ብንቀሳቀስ; ብዬ ተመኘሁ። ደግሞ ቀደም ብዬ ተናግሬአለው መመኘት መብቴ ነው ብዬ።
እስኪ ይታያችሁ እኔ የተመኘሁት ከመጀመሪያው ቢሆን ኖሮ አይደለም 21 ዓመት አንድም ዓመት አይቆዩም ነበር። እረ የምን አንድ ዓመት አመጣህ ያኔ ገና ሰባት እንዳሉ በአንድ ቦምብ እምሽክ ነበር እንዳለው ይሆን ነበር። ትሉኝ ይሆናል፤ ግን ነበርን ትተን ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራም ለሚመጣው ይታሰባል የሚለውን አገርኛ አባባል ተቀብልን ወደፊት በሉለት ይለይለት የሚለውን የጥላሁንን ዘፈን ለአንባቢዎቼ ስመርጥላችሁ፤ ለቃሉ ታማኝ በመሆን ከእሳትና ከውሃ እሳትን በመምረጥ የእናት አገሩና የህዝቡ መጠቃት ዘወትር የሚያገበግበው እንደ ሌሎቹ አርቲስት ነን ባዮች ምሳሌ ከርሳሙ ሰለሞን ተካልኝ እና መሰሎቹ ለጥቅም ሳይገዛ ወያኔ አገሪቱን ከተቆጣጠር ጀምሮ ቃል የእምነት እዳ እንጂ የእናት አባት አይደለም በማለት ብዙ መከራና ችግር በመቀበል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለእኛም ከኢትዮጵያ ውጭ ላለነው ምሳሌ በመሆን እንድንሰባሰብና በደስታና በፍቅር እንድንገናኝ ላደረገው፤ አንድዬና ብርቅዬ ልጃችን፤ ወንድማችንና፡ አባታችን ለሆነው የሰባዊ መብት ተሟጋች፤ አክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ በየን እረጅም እድሜና ጤና ለእሱና ለመላው ቤተሰብ እየተመኘው ጥቁር ሰው የሚለውን ዘፈን በታማኝ ስም አዳምጡልኝ በማለት ነው።
በዕለቱ ሾለ ነበረው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ትንሽ ነገር ልበል፤ፕሮግራሙ የሚፈለግበትን አላማ አሟልቷል። ማለትም የሚፈለገው ገንዘብ ማግኘት ነው አዎ ገንዘቡ ተገኝቷልArtist and activist Tamagne Beyene in Norway, Oslo for ESAT fundraising ።ቅድመ ዝግጅቱ በጣም ጥሩ ነበር ። አብዛኛው ሰው በተለያየ ኮሚቴ ውስጥ በመግባት ያደረገው እርብርብ በትንሹ የሚገመት አይደለም። በአስራ አምስት ቀን እንዳይሞት ለምግብ ብቻ የሚሰጠውን 900 ክሮነር በመቆጠብ ከተለያዩ ቦታ ለትራንስፖርት ወጪ በማድረግ ለማረፊያ እንኳን ሳይጨነቁ ባላቸው ጉልበት ለኢሳት ያላቸውን ፍቅር በተለያዩ ስራዎች ላይ በመሳተፍ አስተዋጽኦ ያደረጉ በካምፕ ያሉ የኢትዮጵያ ስደተኞች በጣም ሊመሰገኑ ይገባል።
የውያኔ ሰራዊት ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ስቃይና እንግልት የሚያሳይ ተመልካችን በእንባ ያራጨና ወደ ኋላ በትዝታ ወስዶ ለካ እንደዚህም ተደርጓል ብሎ ከልብ ያሳዘነ በስደተኛው ተጽፎ የተዘጋጀ አጭር ተውኔት ለዕይታ ቀርቧል። ተውኔቱን የጸፉትም ለምለም ሀይሌ እና ያሬድ ኤሊያስ ሲሆኑ እንዳለ ጌታነህ ተውኔቱ በማዘጋጀት ተሳትፈዋል። በድራማው ላይ ሳላነሳ ያማላልፋቸው እናት በመሆን የተጫወቱት ወይዘሮ መዓዛሽ መኮንን እና ልጅ በመሆን የታጫወተው ያሬድ በትክክል ባህሪው የሚፈልገውን ካራክተር ከልብ በመጫወታቸው ሰውን በእንባ አራጭተውታል።
ላልፈው ወይም ልተወው የማልችለው ችግር ትንሽ ልበል ፤በርግጥ በትንሽ ወጪ ብዙ ብር ማግኘት ቢሆንም አላማው ምንም አይሰራም ያልነው ሃሳብ ችግር ሲሆን አይተናል ምሳሌ ፕሮግራምን በተመለከት፦የቅደም ተከተል ችግር ነበር።የድምጽም መሳሪያን በተመለከት፤ ዋናውና ሰው በአንክሮ ሊከታተለው የሚገባ የታማኝ ዝግጅትን በድምጽ ምክንያት ለመከታተል ሲቸገርና ታማኝም በትክክሉባለማቅረቡ ሲበሳጭ በቅርብ ሁሉም ያየው ነው።ሾል ሲሰል ስተት መፈጠሩ አይቀርም ጥሩ ትምህርት ሆኖ ያልፋል ግን ይህንን የተፈጠረውን ትንሽ ስህተት ቀድመን ስለተነጋገርን ቢያንስ ብንሰማማ ኖሮ ችግሩ ባልመጣ ነበር ፤እንደዚ ዓይነት ብዙ ሰው የሚያሳትፍ ዝግጅት ሲኖር ቢያንስ ሙያው የሚመለከተውን ሾል ለሙያው ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ከተቻለ ሀላፊነቱን መስጠት ካልተቻለ ማማከር ተገቢ ነው ብዬ አምናለው።ሃሳቡን እናንሳው እንጂ ዋናው ነገር በኖርዌ የምንገኝን ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደረገ ጥሩ ምሽት ሆኖ አልፏል።ላሁኑ ላብቃ ሰላም ያገናኘን ደህና ሰንብቱልኝ።
http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6119

በ”ጀሃዳዊ ሃረካት” ትረካ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ ማዳፈን አይቻልም! ከአንድነት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

በ‹‹áŒ€áˆƒá‹łá‹Š ሃረካት›› ትረካ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ ማዳፈን አይቻልም!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
     ይሄንን መግለጫ ስናወጣ ሀገራዊ ራዕይ እንዳለው ፓርቲ በገዥው ፓርቲ እያፈርንና እያዘንን ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ ዜጎች በማንኛውም መንገድ የሚያነሱትን ጥያቄ በግልጽና በውይይት መፍታት ያለመፈለጉ ግልጽ ሀገራዊ አደጋ እየሆነ መምጣቱን እያየን ነው፡፡
በኢትዮጵያ ሕዝብ ግብር የሚተዳደረው ነገር ግን የገዥው ፓርቲ መሳሪያ በመሆን የሕዝብ ጥያቄዎችን ለማፈን ተባባሪ መሳሪያ በመሆን እያለገለ ያለው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ‹‹áŒ€áˆƒá‹łá‹Š ሃረካት›› በሚል የተሰናዳና እንደተለመደው የሙስሊሙን ህዝብ ጥያቄን ለማዳፈን የተዘጋጀ አይነት ትረካ (ዶክመንተሪ) ሲያቀርብ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከዚህ በፊትም ከፍርድ ቤት ፍርድ በፊት ፍርድ የሚሰጡ ‹‹áŠ áŠŹáˆá‹łáˆ›››áŠ• የመሳሰሉ ዶክመንተሪዎች በማቅረብ የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ ክብር በሚጥስ ሁኔታና ከህግ በላይ በሆነ አካሄድ እየወነጀሉ አቅርበዋል፡፡ ዶክመንተሪዎች የሚሰጣቸው ርዕስ ግዝፈትና የአጽመ ታሪካቸው ትረካ ልልነት ከተራ ድራማም ያነሰ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ ሀገር እያስተዳደረ ባለ መንግሥት አዝነናል የምንለው፡፡
በ28/05/05 ምሽት ላይ ‹‹áŒ€áˆƒá‹łá‹Š ሃረካት›› በሚል የቀረበው ትረካም የቀረበበት አብይ ምክንያት፡-
1. የሙስሊሙን አንድ ዓመት የዘለቀ ግልፅ ጥያቄ ፊት ለፊት ተወያይቶ በመመለስ ፋንታ በእጅ አዙር ለማድበስበስ የተሰራ መሆኑ፤
2. በዜጎች ላይ የስነ-ልቡና ጫና በመፍጠር በፍርሓት ውስጥ አድርጎ ለመግዛት በማለም እና
3. መንግሥት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አልገባም ቢልም እጁን አስረዝሞ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የሚያደርገውን የአድራጊ ፈጣሪነት ሾል ‹‹áˆ•áŒ የማስከበር›› የሚል ሽፋን በመስጠትና ትንሹን ጉዳይ በማግዘፍ የማደናገር ሾል ለመስራት ያለመ ነው፡፡ እንደ ፓርቲም ይህንን መቃወም ብቻ ሳይሆን ኃላፊነት የጎደለውና፣ አርቆ አስተዋይነት ያጣ ተግባር ስለሆነ በአስቸአኩዋይ እንዲገታ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ሌላው አሳፋሪ ጉዳይም እንደተለመደው የፍርድ ቤቶች ገለልተኛ ውሳኔ ‹‹áˆ›áŠ• አለብኝ›› በሚሉ አምባገነን ግለሰቦች እየተጣሰ እንደሆነ ‹‹áŒ€áˆƒá‹łá‹Š ሃረካት›› አሳይቶናል፡፡ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ይህ ዶክመንተሪ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት የዕግድ ትእዛዝ ቢተላለፍበትም በማናለብኝነትና ሥልጣንን ካለአግባብ በመጠቀም ያለምንም ይግባኝ በከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ተሽሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡ የመንግሥትን ህግ ጣሽነት በግልጽ ያሳያል፡፡ ልሹ ህግ የሚጥስ ገዢ ፓርቲስ እንዴት የሌሎችን ህግ ሊያስከብር ይችላል?
ፓርቲያችን አሁንም ስጋት አለው፤ አሁንም የገዥውን ፓርቲ አፋኝ አካሄድን እንቃወማለን፣ አሁንም የመንግሥትን በኃይማኖት ጣልቃ ገብነት እናወግዛለን፣ ጥሪያችንም የዜጎች ጥያቄ በግልጽና በአደባባይ ይመለስ የሚል ነው፡፡ የህዝብ ጥያቄ ይከበር ነው፡፡  áˆľáˆˆá‹šáˆ… ‹‹áŒ€áˆƒá‹łá‹Š ሃረካት›› የሚል ትረካ በማቅረብ የሙስሊሙን ጥያቄ ማዳፈን አይቻልም፡፡ ዶክመንተሪው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ መልስ ሊሆንም አይችልም፡፡


ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
ጥር 29 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ግፍ ሲበዛ ማስፈራት፤ እስርም ሲበዛ ማሸማቀቁ ይቀራል

የወያኔ ልብ ወለድ “ደራሲዎች” ተደራሲ በሌለበት  áŠ áˆˆáˆ  ሆነው የገሃዱን  አለም  áŠáŒ¸á‰ĽáˆŤá‰…  ያልሆነውን የቀን ቅዠታቸውን በመርዛማና በዶለደመ መቃቸው ዛሬም እንደትላንቱ በቆሸሸው ኢቲቪ አማካይነት የጥጋብ ግሳታቸውን ማግሳት ቀጥለዋል፡፡  እኛም ግሳታቸውን በተራበ አንጀት እነሆ ለ21 አመት እየተጋትነው አለን።
የወያኔ ዘረኞች ቀደም ሲል በግንቦት 7 እና በሌሎቸም ደርጅቶች ላያ ያነጣጠሩ አኬልዳማን የመሰሰሉ የዉሸት ድራማዎችን በማቀነባበርና ሀአዲስ አበባን እንደ ባግዳድ የእልቂት ቀጠና ሊያደርጓት ነዉ የሚል የሞት ዜና ለህዝብ በማሰማት የታጋዮችን ቅስም ለመስበርና  á‹¨áˆ…á‹á‰ĽáŠ•  á‹¨á‰°áŠáˆłáˆł የትግል ስሜት ለማቀዝቀዝ ከፍተኛ ሙከራ አድርገዋል።
እነዚህ ዘረኞች  በባህላችንም ሆነ በሀይማኖታችን እንዲሁም በኢትየጵያዊ ትውፊቶቻችን ላይ ሲያላግጡ ገና ከመጀመርያው በቃቸሁ በለመባላቸው ዛሬም እንደትናንቱ “የምን ትሆናላችሁ” ንቀታቸዉንና  ለህዝብና ለአገር ያላቸዉን ጥላቻ ትውፊቶች ያላቸውን ጥላቻና ንቀጅሃዳዊ ሃረካት፡ በሚል የዘግናኝ ፈልም እያሳዩንነው ። ጅሃዳዊ ሃረካትን ከአኬልዳማ የሚለየዉ ነገር ቢኖር፤ ጅሃዳዊ ሃረካት፡  ለዘመናት ተከባብረው በኖሩት የሀገራችንን  የእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ነው፤ ይህ የወያኔ ጭፍን ተግባር የሚያሳየን ወያኔ ስልጣኑን እስካራዘመለት ድረስ ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ተከባብሮ የኖረን ህዝብን፣ እምነትንና አገራችንንም ጭምር ለማጥፋት እንደማይመለስ ነው።
የኢትዮጵያ  ህዝብ  áŠĽá‹áŠá‰łá‹áŠ• ወይም ሀቁን ለይቶ የሚረዳና የሚያገናዝብ ህዝብ በመሆኑ እንጅ የወያኔ ቆሻሻ መልቀቂያ በሆነው በኢቲቪ የሚተላለፉትን ድራማዎች ወይም ውሸቶች፣ ከንቱ ትረካዎችና አንድን ህዝብ በሌላው ላይ እንዲሁም አንዱ ሃይማኖት በሌላው ሃይማኖት ላይ እንዲነሳ ለማድረግ ያደረጋቸዉ ሙከራዎች  áŠ áŒˆáˆŤá‰˝áŠ• ኢትዮጵያን የት ሊያደርሳት ይችል ነበር ብለን  ስንገምት በኢትዮጵያ ህዝብ ጽናትና አርቆ አስተዋይነት  ህዝብ እንድንኮራና እንድንተማመን ያደርገናል፡፡
በተቃራኒው ወያኔ እራሱ አገር ምድሩን እያሸበረ ሌሎች ለመብታቸው የሚታገሉ ወገኖቻችንንችን በተለይም የአስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችንን ሽብርተኞች ናችሁ እያለ በማሰሩ አፍረንበታል።
ወያኔ ይህንን የሚደርገው የታጋዮችን ቅስም ለመስበር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወጣቶች የታጋዮችን አርአያ ተከትለው ትግሉን እንዳይቀላቀሉና የስልጣን እድሜውን እንደያሳጥሩበት ለመቀጣጫ እንዲሆንና ወጣቱን ከትግሉ መንደር ለማራቅ ቢሆንም እውነታው ግን የሚያሳየው የተገላቢጦሽ ነው፡፡ ግፍ ሲበዛ ማስፈራቱ፣ እስርም ሲበዛም ማሸማቀቁ ይቀራል፡፡ በዛሬዬቱ ኢትዮጵያ እስርም ሆነ ግርፋት የማይፈራበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። ዛሬ የኢትዮጵያ ወጣቶች እኔ አቡበከር ነኝ እኔ አንዷለም ነኝ እያሉ ተነስተዋል፤ ይህም የወያኔ መውደቀያ ቀን አብይ ምልክት ነው
ህወሃት አሸባሪ ድርጅት ነው። ህወሃት የማህበረሰባችን የእምነት ነጻነት፤ ክብርና መብት የሚገፍ፣ የሚያዋርድ፣ የሚያፈናቅል ጤነኛ ያልሆነ ስርአት በመሆኑ መብታችንና ነጻነታችንን  ለማስከበር ማናቸውንም አይነት የትግል ስልት ተጠቅመን  á‹ˆá‹ŤáŠ”ን በመፋለም ህዝባችንን ከእርስበርስ ግጭት፤ አመጽና ትርምስ የማዳን ግዜው አሁን ወይም ዛሬ ነው ይላል ግንቦት 7።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነት የዲሞክራሲ ንቅናቄ ትላንት እንዳልነው ዛሬም ለመብታቸው ሲሉ በወያኔ  እጅ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ያለንን ጥልቅ አክብሮት ይገልጻል፡የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ፣ ለማንነቱ፣ ለእምነቱ፣ የሚያደርገው መልል ትግል ይቀጥላል። የህወሃት መርዘኛ አፈ ሙዞች ወይም  á‹¨áŒ…ል ፕሮፖጋንዳ ድራማዎች ትግሉን ለደቂቃም ቢሆን አይገቱትም ያጠናክሩታል እንጂ፡፡  á‹ˆá‹ŤáŠ” የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ጠያቂዎቹን በሀሰት የሚወነጅል ጀሃዳዊ ሀረካት ብሎ ያረበዉን ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያወግዛል፡፡
የድራማው ሌላኛው መልእክት በኢትዮጵያ ውስጥ የፍትህ ስርአት ሞቶ የተቀበረና የማይነሳ መሆኑን ቀባሪው ወያኔ የቀብሩን ስነስርአት በቲቪ መስኮት እነ አኬልዳማን፣ ጀሃዳዊ ሀረካትን ካለ ከልካይ እርሱ የሚጮኸው ጩኸት ትክክል መሆኑን ያሳየናል፣ ደጋግሞም ይነግረናል። ልብ ይበሉ የአሻንጉሊቱ የፍርድ ቤት ዳኞች የተባሉት በዚህ የቀብር ስነስርአት በየትኛው የአስለቃሽ  ቦታ ላይ  መሆናቸውን ግን ድራማው አያሳየንም።
ህግ የሚወጣው መንግስት የዜጎችን መብት ለመጠበቅ ነው፤ በወያኔ ግን “ህግ” ማለት የመንግስት መሳሪያ ዜጎችን መጨፍለቂያ ስልጣንን ማሰንበቻ ነው። በሀገራችን የመናገር መብት ተገፎ እያለ የማምለክ መብት ሊፋፋ አይችልም፤ ወይም ደግሞ ፍትሃዊ ዳኝነት የማግኘት መብት ተጥሶ እያለ የማምለክ መብትን የሚያስከብር ተቋም ሊኖር አይችልም።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የዛሬ ሁለት አመት ወያኔዎች አኬልዳማ የተሰነውን አማተርና ደካማ ድራማቸውን እንደፈለጉ በሚቆጣጠሩትና በሚያዙት የውሸት መፈብረኪያ ቴሌቪዥናቸው ሲያሰራጩ እንዲህ አይነቱን ንቀትና ውርደት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆምና የዘረኛ አምባገነኖችን ትእቢት ለማስተንፈስ ትግሉን አጠናክሮ በመቀጠል ወያኔን ለማስገደድና ለማስወገድ ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ ይገኛል። ስለዚህም ሙስሊሙ ወገናችንም ሆነ ህዝበክርስትያኑ ሰብአዊ መብቶች ሳይከበሩ የሃይማኖት ነጻነት ብቻውን ሊከበር የማይችል መሆኑን ተረድቶ ህውአትን ለማስወገድ በምናደርገው መልል ትግል ግንቦት 7ን እንዲቀላቀል አለያም ከጎናችን እንዲቆም ወገናዊ ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Feb 13, 2013

የኢሕአዴግ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለአ.አ. አስተዳደር ለመወዳደር መታጨታቸው አነጋጋሪ ሆኗል


በሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር
ገዢው ፓርቲን በመወከል በተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተመርጠው ሲያገለግሉ የነበሩ ከፍተኛ መንግስት
ባለስልጣናት ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አስተዳደር ለመወዳደር እጩ ሆነው መቅረባቸው በተለያዩ ሕብረተስብ ክፍሎች
ውስጥ የተደበላለቀ ስሜት ፈጥሯል።
በተለይ ገዢው ፓርቲ ካለው የአባላት ብዛት አንፃር እና ከተማረ ሕብረተሰብ ክፍልም ከያዘው አንፃር ከከፍተኛ
የመንግስት ስልጣን አውርዶ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት እንዲወዳደሩ መደረጉ ገዢው ፓርቲን የመተካካት
ፖሊሲ ፍሬያማነትን ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል። ፓርቲውም በተወሰኑ ሰዎች ትከሻ ላይ ያረፈ እንዳልሆነ እየታወቀ ለምን
ይህን መሰል አማራጭ ገዢው ፓርቲ መውሰድ እንደፈለገ ለመገመት እንኳን አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ መፈጠሩን አንድ
ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ገልፀዋል።
አዲስ አበባን በአዲስ መልክ ለማጠናከር በሚል መነሻ የተሰጠ ሹመት መሆኑ ቢነገርም፤ በአዲስ አበባ አስተዳደር
ውስጥ ያለው ዋነኛ ችግር የአመለካከት እንጂ የከፍተኛ እና የዝቅተኛ አመራር ችግር አለመሆኑ ነው የሚነገረው።
በአዲስ አበባ አስተዳደር ውስጥ ከማሕፀን ኪራይ ሰብሳቢ እስከ መሬት ኪራይ ሰብሳቢነት የተንሰራፋው ሙስና ለያዥ
ለገናዥ አስቸጋሪ መሆኑ ይታወቃል። አሁን አስተዳደሩን ለማጠንከር በራሳቸው ፈቃድ የተወካዮች ምክር ቤትን
የተሰናበቱት ከፍተኛ ባለስልጣናት በሚያስተዳድሩት የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ምን ያህል ኪራይ ሰብሳቢነትን
ተዋግተዋል? ራሳቸውስ ከኪራይ ሰብሳቢነት ምን ያህል የፀዱ ናቸው? በሕዝቡና በድርጅቱ ካድሬዎች በግልፅ
ተተችተዋል ወይ? ለሚለው ግልፅ የመንግስት ምላሽ ያስፈልጋል ብለዋል ምሁሩ።
በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡና ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሌላ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር በበኩላቸው፤ ገዢው ፓርቲ
የሰለጠነ የፖለቲካ ዱላ እያሳረፈባቸው ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። ይህም ሲባል፤ በአንድ ጊዜ ከሚወሰድ እርምጃ ደረጃ
በደረጃ የመጨረስ የፖለቲካ ጨዋታ ሳይሆን አይቀርም ነው የተባለው።
በሌላ ወገን ያለው አስተያየት የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሚኒስትር መስሪያ ቤት የበለጠ አስቸጋሪ በመሆኑ ችግሩ
የሚፈታው መዋቅራዊ ለውጥ በአስተዳደሩ ላይ ሲደረግ እንጂ አዲስ ተሿሚዎች በማምጣት አይደለም የሚል ነው።
ስለዚህም መንግስት ለምን እነዚህን ከፍተኛ አመራሮች ማምጣት እንደፈለገ በግልፅ ምክንያቱን ሊያስቀምጥ እንዲገባ
ምሁሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።¾

Feb 6, 2013

ትግሉ የሚጠይቀውን መሰዋእትነት ለመክፈል እኛም ዝግጁዎች ነን!

ቅኝ ገዥዎችን በማሳፈር በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ተጋድሎ ነጻነቷን ጠብቃ የኖረችውና በባርነት ሾር ለቆዩ ሀገራት ፋና ወጊ የሆነችው ውድ ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ዛሬ በሀገር ውስጥ ወራሪ በሆነው ህወሃት/ወያኔ መዳፍ እጅ ገብታ በሁሉም ረገድ ከኢኮኖሚ እስከ ሰበአዊ መብት አያያዝ በአለም የመጨረሻዋ የሰው ልጅ መብት ረገጣ የሚፈጸምባት ተስፋ አልባ ሀገር ተብላ ተመድባ ትገኛለች።
ይህችው የቀድሞዋ ኢትዮጵያ በክብርና በኩራት የአፍሪካ የነጻነት ፋናወጊ ተብላ የሚነገርላት፤ በዚህ ዘመን በባርነት አረንቋ እየኖረች፣ ህዝቧ የነጻነት ያለህና የትውልድ የድረሱልኝ ጥሪ ኤሎሄ ለወጣት ልጆቿ  እያቀረበች፣ እየተማጸነች አለች።
ይህን ተከትሎ በሁሉም ግንባር ሀገር በቀል ወራሪ ህወሃት/ወያኔን ታግሎ ለማስወገድ እየተደረገ ያለው ትብብር የሚበረታታ ቢሆንም የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ ና የአንድ ዘር የበላይነት ርዕዮተ ዓለምን አስወግዶ ነፃነት ከናፈቀው ህዝብ ጎን በመሰለፍ በሀገራችን የሰላም አየር በሁሉም ከተሞች እንዲሰፍን ለሚደረገው እልህ አስጨራሽ ጉዞ የምናደርገው እገዛ በቂ ነው ብለን አናምንም።
ትውልዱ ለውጥ አያመጣም በሚል እስከአሁን የተደላደለውን ወያኔ፤ ከመንበሩ ፈንቅለው ሊጥሉት ዛሬ ራሳቸውን መሰዋእት ለማድረግ ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ፣ በታሪክ ማህደር ኢትዮጵያዊ ገድላቸው እንዲቀለምላቸው ቆርጦው የተነሱት የህዝባዊ ሃይል ታጋዮች ፤ የእማማ ኢትዮጵያን እንባ በእንባቸው ሊጠርጉ መከራና ስቃይን መርጠው መሰደዳቸውን ሰሞኑን በድጋሜ አስታውቀዋል።
ህዝባዊ ሃይሉ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “ኢትያጵያዊነት እንደ ሸቀጥ የተሸጠበት የክፉ ቀን ውረደት ላይ እንገኛለን እና ከገባንበት የውረደት አዘቅት የመውጫ ጊዜው አሁን ነው፤ ነገም ሳይሆን ዛሬ ነው። ዛሬ በሃገራችን በወያኔ አምባገነናዊ እብሪት ያልታፈነ፣ ያልተዋረደና ያልተዘረፈ የሃገሪቱ ዜጋ አይገኝም። የወያኔ ሹማምንት በሃብት ላይ ሃብት፤ በድሎት ላይ ድሎት ሲጨምሩ፣ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እጣ ፈንታ ግን መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መንገላታት፣ መታሰር፣ መደብደብና መገደል ሆኗል” ብለዋል ። ታዲያ እኛ ምን እንጠብቃለን?
ሀገራችን ሀገር ሆና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ግንቦት 7 ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ከማንኛውም ሃይል ጋር ሆኖ ለድረሱልኝ ሀገራዊ ወገናዊ ጥሪ ደራሽ በመሆን በዛች ሀገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔን በማስወገድ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታን ለማምጣት አምርሮ በመስራት ፍትህና ነፃነትን ከተጠማው ሕዝብ ጋር አብሮ ሊታገል ቃል በመግባት ለጥሪው ምላሽ ይሰጣል፡፡
የማንኛውም የፖለቲካ/የሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ወጣቱ፤ በተለይም አደገኛ በረሃዎችንና ባህሮችን በማቋረጥ ለመሰደድ ልብህ እየከጀለ ያለው የሃገራችን  ወጣት ሆይ! የመተባበሪያው ጊዜ አሁን ነው።  á‰ á‹áˆ­á‹°á‰ľ እስከ መቼ ? ማንስ መጥቶ ሊታገልልን ይችላል? ስለዚህ በከንቱ ክቡር ህይወትን ከማጣት ስደትን አቁሞ ዘላለማዊ ክብር ወደ ሚያሰገኝለት የትግል ጥሪ ይቀላቀል ዘንድ ግንቦት 7 ንቅናቄም ጥሪውን ያቀርባል።
በርግጥም ነው ድሎት ሳይሆን የህዝብ ስቃይ ጣርን፣ የሀገር ውርደትን ማየት አላስችል ያላቸው የህዝባዊ ሃይሉ የቁርጥ ቀን ወጣቶች፤ የጥቁር ደም ጥቁር አፈር የሰራቸው የአበው ልጆች የውርደትን ወላፈን፤ በማይቆምና በሚያቃጥል የትግል ወላፍን ሊመክቱት፣ ሊያስወግዱት፤ ተራራ፣ ጋራ ሸንተረሩን መርጠው ወያኔንን በሚገባው ቋንቋ ሊያናግሩት ሊጋፈጡት ቀናትን እየቆጠሩ ነው።
የህዝብ ልጆች የከፈሉትና ወደፊትም የሚከፍለው ውድ መስዋእትነት የሌላ አምባገነናዊና ግፈኛ ሥርዓት መቋቋሚያ እንዳይሆን ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ተግባር በተናጠል ይሁን በ ጋራ በመሆን መሰዋእት በመክፈል አብሮ መስራት የግድ ነው ሲል ግንቦት 7 ንቅናቄም ያምናል።
አምባገነኖች መውደቂያቸው ሲደርስ ሁሉም ነገር በቁጥጥራቸው ሼር ያለ ለማስመሰል መቅበጥበጣቸው የተለመደ ነው። የወያኔም መቅበጥበጥ ምክንያቱ መሠረቱ እየተናደ  በመሆኑ ነው። ቢቻለው የተፈጥሮ ቀመርን ሳይቀር በሱ መልካም ፈቃድ የሚከናወን መሆኑን ብናምለት ደስታው ነው። ይህ የሁሉም አምባነኖች የመውደቂያ ወቅት መለያ ባህርይ ነው።
ስለዚህ ወያኔ ከሥልጣን ሳይባረር አንዳችም በጎ ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሰብ አይቻልም። ስርአቱ ከገባበት የምቾት ማጥ ውስጥ በስብሶ ስለተቀመጠ ከቶ ጀሮዎቹ ለሰላማዊ ጥሪ ጮኸት የተደፈኑ ስለሆኑ፤ እያንዳንዷን ደቂቃ ሳንዘናጋ በንቃት ሁሉንም የተቃዋሚ ሃይላትን በማስተባበር ትግሉን የማቀጣጠያ ሰአት ላይ ነን።
እኛ ግንቦት 7 ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ከማንኛውም ሃይል ጋር ሆነን  ለድረሱልኝ ሀገራዊ፣ ወገናዊ ጥሪ ደራሽ በመሆን፤ በዛች ሀገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔን በማስወገድ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታን ለማምጣት አምርሮ በመስራት ፍትህና ነፃነትን ከተጠማው ሕዝብ ጋር በመቆም ለመታገል ዝግጁ መሆኑን ዛሬም ያሳውቃል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Feb 4, 2013

በገንዘብዎ ሳይሆን በጊዜዎ የሚገዙት ሎተሪ በኢሳት !

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን / ኢሳት / በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን፣ በድህረ ገጽ፣ በፌስ ቡክና በትዊተር የሚዲያ ዘርፎቹ  á‰ á‹ˆáˆ­ ከ7.6 ሚሊዮን በላይ ጎብኚ ያለው ነው። ይህ ከፍተኛ አድማጭና ተመልካች ያለው የሚዲያ ተቋም በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ተቀባይነት ጠብቆ ለመቆየት፤  áˆľáˆŤá‹áŠ• እያሳደገና ወደ ኢትዮጵያ የሚያድርገውንም የቴሌቪዥንና ሬዲዮ ስርጭት አስተማማኝ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። በሚያስተላልፈው ፕሮግራምም የተለያየ የህብረተሰብ ክፍልን ፍላጎት ለማሟላት በየጊዜው ያልተቋረጠ ፕሮግራሞችን የማስፋፋት ስራም እያከናወነ ነው። ከዚህም ውስጥ አንዱ ለንግዱ ማህበረሰብ የገበያ ምንጭ የሆነው ሸማች ተሰባስቦ የሚገኝበት ብቸኛ የጋራ ቦታ በሆነው የኢሳት ሚዲያ የማስታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል። የመጀመሪያውን የማስታወቂያ አገልግሎትም ኢሳትን ከገንዘብ ድጋፍ አንስቶ ገንቢም ሆነ ነቃፊ አስተያየት በመስጠት የአንድ ወገን ሚዲያ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ አንዲሆን ላደረገው ህዝብ  áŒŠá‹œáŠ• አንጂ ገንዘብን የማይጠይቅ የሎተሪ እጣ በማዘጋጀት  የንግዱ ማህበረሰብ ምርትና አገልግሎቱን በማስተዋወቅ ከሸማቹ ጋር እንዲገናኝ ጋብዟል።
ከማስታወቂያው የሚገኘውም ገቢ  áŠ˘áˆłá‰ľ ለኢትዮጵያ ህዝብ እየሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት ለማስፋፋትና  á‰ áŠ áŒˆáˆ­ ቤትም ስርጭቱን በአስተማማኝነት ለማስቀጠል ለሚያስችለው ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ነው።
ስለዚህ ገንዘብዎን ሳይሆን የሁለት ደቂቃ ጊዜዎትን በመክፈል የሎተሪ ቅጹን ይሙሉና የሎተሪው ተሳታፊ ይሁኑ። በሎተሪው የሚያገኙት እጣ ለ15 ቀናት የሚቆይ፣ በሳምንት ለ3 ቀናት፣ በቀን ለ30 ሰከንድ የንግድ ድርጅትዎን ምርትም ሆን አገልግሎት ለማስተዋወቅ የሚያስችል እጣ አሸናፊ የሚያደርግዎት ይሆናል። የእጣውም ብዛት 5 ሲሆን ፤ ከዚህ ውስጥ የአንዱ እጣ ባለ እድል  á‰ áˆ˜áˆ†áŠ• ምርትዎንም ሆነ አገልግሎትዎን በኢሳት ሬዲዮን አማካኝነት በሚሊዮኖች  ጆሮ እንዲገባ ለማድረግ እጣውን ሞልተው  advert@ethsat.com á‰ áˆšáˆˆá‹ የኢሜል አድራሻ ለኢሳት የአየር ሰዓት ሽያጭና ማስታወቂያ ክፍል  ይላኩ።
ሎተሪው የሚወጣበት ቀን ማርች 03/2013 ነው።
ምርትዎንም ሆነ አገልግሎትዎን የኢትዮጵያውያን አይንና ጆሮ በሆነው ኢሳት ያስተዋውቁ !
Lottery Form
Business Name………………………………………………………..        Country………………………………………………………
Email address………………………………………………………………      City……………………………………….
Business phone No…………………………………………
Cell phone No…………………………………………..

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ


ኢሳት ዜና:-ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ በትናንትናው እለት በደህንነት ሀይሎች ታፍነው የተወሰዱት 2ቱ ጓደኞቻቸው የት እንዳሉ ዩኒቨርስቲው እንዲያሳውቃቸው ጠይቀዋል።
የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች ከተማሪዎች ለቀረበው ጥያቄ ” ተማሪዎቹ በደህንነት ሀይሎች ተፈልገው የተወሰዱ በመሆኑ እኛ ምንም ማድረግ አንችልንም፣ ለወደፊቱም የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘው ከመጡ  áŠ áˆłáˆáˆáŠ• እንሰጣለን” በማለት መልስ መስጠታቸው ታውቋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች እንደገለጡት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ እየጨመረ በመምጣቱ ትምህርታቸውን ተረጋግተው ለመማር አልቻሉም።
በደህንነት ሀይሎች የተወሰዱት  ሰይድ እና ኡመር የተባሉት ተማሪዎች በዚህ አመት ይመረቃሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። በሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።
በተመሳሳይ ዜና በሐረር ኢማን መስጂድ ዘበኛ የነበሩት ስማቸው ለጊዜው ያልታወቀው ግለሰብ  በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታውቋል። ግለሰቡ ከመገደላቸው በፊት በአካባቢው  áˆ˜á‰ĽáˆŤá‰ľ ጠፍቶ የነበረ ሲሆን፣ ሁኔታው ከተረጋጋ በሁዋላ መብራት ተመልሶ መምጣቱ ታውቋል።
መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን የሰጠው መልስ የለም።

ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው የህወሃት ጀሌ ተጋለጠ (አዲስ ቮይስ) በጋዜጠኛ አበበ ገላው እና በቤተሰቡ ላይ ህገወጥ በሆነ መንገድ በተከታታይ ስልክ በመደወል ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው ግለሰብ ማንነት ተጋለጠ። ጋዜጠኛ አበበ ገላው የግለሰቡን ማንነት ለማጣራት ለበርካታ ሳምንታት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትልና ምርመራ መደረጉን እና ድምጹም ልምድ ባላቸው የፎረንሲክ ኤክስፐርቶች የተመረመረ መሆኑን ገልጾ በዚሁ መሰረት ይህን ህገወጥ የሆነ ድርጊት ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ ሙሉጌታ ካህሳይ የተባለ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ጀሌ መሆኑእንደተደረሰበት ገልጿል።

Feb 1, 2013

ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል

ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይን ለመስጠት የተሰየመ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ቀጠሮ ሰጥቷል።

የችሎቱ ዳኛ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እና አሳታሚው ማስተዋል የህትመት ሾል ድርጅት ዋና ሾል አስኪያጅ የነበረው አቶ ማስተዋል ብርሀኑ መኖራቸውን ካረጋገጡ በሁዋላ ብይኑን ለመስጠት ለየካቲት አንድ ቀጠሮ ሰጥተዋል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቆች በችሎቱ ላይ አልተገኙም። በችሎቱ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የጋዜጠኛው ቤተሰቦች፣ አድናቂዎችና ሾል ባልደረቦች ተገኝተዋል።

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አንዲት ተማሪ ራሱዋን መጸዳጃ ውስጥ በመግባት አጠፋች

ኢሳት ዜና:-ገነቴ ጌታቸው የተባለችው ተማሪ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ራሱዋን በመወርወር ያጠፋቸው ባለፈው ሳምንት ነው። በትምህርቷ ከፍተኛ ውጤት የነበራት ተማሪ ገነቴ ራሱን ለማጥፋት ለምን እንደወሰነች በትክክል ለማወቅ ባይቻልም ተማሪዎች እንደሚሉት ከሶስት ሳምንት በፊት የግቢው ተማሪዎች የውሀ፣ የመጸዳጃ እና ሌሎች አገልግሎቶች አልተሟሉልንም በሚል ተቃውሞ ከማስነሳታቸው ጋር ሊያያዝ ይችላል። ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸውን በማስቸገር በሚላክላቸው ገንዘብ የፕላስቲክ ውሀ ሲገዙ መቆየታቸውን ያወሱት የሟቿ ባልደረቦች፣ ይሁን እንጅ ተማሪዋ የመጣችበት ቤተሰብ ይህን ለሟሟላት ባለመቻሉ ተማሪዋ በችግር ውስጥ ትገኝ ነበር ብለዋል። አሟሟቷንም ከገንዘብ ችግር ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ትምህርታቸውን አቁመው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ግቢያቸው ተመልሰው መደበኛ ትምህርት የጀመሩ ቢሆንም፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግን አሁንም በዩኒቨርስቲው አካባቢ በብዛት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አስተዳዳሪዎችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ለአባይ ግድብ ቃል ከተገባው ገንዘብ ውስጥ የተሰበሰበው ከ35 በመቶ በታች ነው

ኢሳት ዜና:-የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ይፋ ከተደረገበት ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች እና ግለሰቦች ቃል ከተገባው 600 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም 11 ቢሊዮን ብር ውስጥ እስካሁን ለመሰብሰብ የተቻለው ከ200 ሚሊዮን ዶላር ወይም 4 ቢሊዮን ብር ሊበልጥ አልቻለም።

መንግስት ሰራተኞችን እንዲሁም የንግድ ድርጅቶችን በማስገደድ እስካሁን ያሰባሰበው ገንዘብ ፕሮጀክቱን ለማሰራት ከሚፈጀው ገንዘብ ጋር ሲተያይ እጅግ አነስተኛ ነው። በየጊዜው የሚጨምረው የእቃዎች ዋጋ ባለበት ቢቆም እንኳ ግድቡን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማስጨረስ የሚያስፈልገው ከ90 ቢሊዮን ያላነሰ ገንዘብ ለመሰብሰብ እጅግ አዳጋች እንደሚሆን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ሲያስጠነቀቁ ቆይተዋል።

በፕሮጀክቱ ላይ በተለያዩ ሞያዎች የሚሳተፉ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት በማኔጅመንቱና ስራውን በሚሰራው የጣሊያኑ ሳሊኒ የአስተዳደር ችግር ምክንያት ስራው በተፈለገው ፍጥነት እየሄደ አይደለም። ግንባታው በታቀደለት በአራት አመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደማይችል ሰራተኞች በእርግጠኝነት ይናገራሉ። መንግስት የግድቡ 14 በመቶ ተጠናቋል በማለት ቢያስታውቅም፣ በተያዘለት የጊዜ ገድብ ያልቃል የሚለውን በእርግጠኝነት ከመናገር ባለቀበት ጊዜ ይለቅ የሚል ቅስቀሳ ማካሄድ ጀምሯል።

መንግስት ህዝቡ ለግድቡ ያለው ስሜት መቀዛቀዙን እና መዋጮውም እያነሰ መምጣቱን በመመልከት አዳዲስ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን ለመዘርጋት አቅዷል።

ግድቡን ለመስራት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ይጠበቅ የነበረው በውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ቢሆንም፣ የኢህአዴግ ደጋፊ ከሆኑ የዲያስፖራው አባላት በስተቀር አብዛኛው ገንዘብ ለማዋጣት ፈቃደኛ አለመሆኑ ገዢውን ፓርቲ ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል።

የአባይ ግድብ የአረቡ አብዮት በተነሳ ማግስት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

አብዛኞቹ የተፈናቀሉ የጉራፈርዳ ነዋሪዎች የደረሰቡት እንደማይታወቅ መኢአድ ገለጠ

ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ” በጭቆናና በአፈና ስልጣንን ለማራዘም የሚካሄደው ዘመቻ ቀጥሏል” በሚል ርእስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ በጉራፈርዳ ወረዳ የሚፈናቀለው አርሶአደር ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑንና የተወሰኑትም በሚዛን ተፈሪ፣ በጅማ፣ በአንቦ እና በአዲስ አበባ ያለመጠለያ ለልመና መዳረጋቸውን ገልጿል።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አርሶአደሮች መሬታቸውን ተነጥቀው የአካባቢው ታጣቂዎች በጨረታ ስም እየተቀራመቱት መሆኑን የገለጠው መግለጫው፣ ወ/ሎ ስንዴ ስጦታው የተባሉ የስምንት ልጆች እናት በጥይት ተደብድበው በመሞታቸው ልጆቻቸው ያለአሳዳጊ መቅረታቸውን አብራርቷል።

ጥር 21 ከሌሊቱ 8 ሰአት ከወረዳው መስተዳደር የተላኩ አራት ወታደሮች ወደ አቶ ኢበሉ ማሞ ጊቢ በመግባት ሁለት በሬዎችና ሶስት በጎችን መውሰዳቸውን የጠቀሰው ድርጅቱ መግለጫ፣ 32 ሰዎችም እንዲሁ በእስር ቤት ያለምንም ፍርድ እየተሰቃዩ መሆኑን ገልጿል።

መኢአድ ” በጉራፈርዳ ህዝብ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ እየተካሄደ ያለው ወከባ እስራትና እና ግድያ በአገራችን ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊ ረገጣና የአንድን ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብን የማጥፋት ዘመቻ አካል ነው ” በማለት ገልጾ፣ ነዋሪዎቹ ከአካባቢው መልቀቅ እንዳለባቸው አለበለዚያ ግን ሁሉንም እንደሚገድሏቸው የወረዳው አስተዳዳሪዎች እና የፖሊስ ሀላፊዎች መግለጻቸውንም ይፋ አድርጓል።

በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ የተካሄደውን የሌሎች አገራት የዘር ማጥፋት ወደ አገራችን መግባቱን፣ በጉራ ፈርዳ የተፈጸመው ድርጊት እንደሚያመላክት የገለጸው መኢአድ፣ ድርጊቱን ኢትዮጵያውያን ተረባርበው እንዲያስቆሙት ጥሪ አቅርቧል።

በደቡብ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተባባሱ መምጣታቸው ይነገራል።

Total Pageviews

Translate