Pages

Mar 13, 2013

Tamagne Beyene: Ethiopian Hero


by MeKonnen H. Birru, PhD

Artist Tamagne Beyene Ethiopian Hero
The thing about a hero, is even when it doesn’t look like there’s a light at the end of the tunnel, he’s going to keep digging, he’s going to keep trying to do right and make up for what’s gone before, just because that’s who he is.
Joss Whedon
A hero is a defender. A hero is a protector. A hero is a rescuer. The legendary Ethiopian writer Dr. Haddis Alemayehu (1902 – 2003) portrayed Gudu Kassa as a ‘hero’ in his classical work Fiqir Iske Meqabir (Love Unto Grave’. Gudu Kassa (Kassa Damte) was a nobleman by birth but refused all for the sake of his progressive ideas. He fought for individual liberty and freedom. He became a defender of his people, not his class, nor his race, nor his family power. He fell in love and married a working class woman while he was a noble because he saw love in her, nothing else. To him and so many millions of Ethiopians, love is the essence of life and the root of every particle, motion, foundation, liberty, freedom and expression. Love is our Ethiopian culture and our norm. And now these three remain; faith, hope, and love. But the greatest of these is love (1 Corinthians 13:13).
In our times too, we have several heroes who believe in such love, liberty, faith, and peace. They are crying for our liberty. They are crying for our believed country: Ethiopia. They cry for love, equality, and fairness. Tamagne Beyene is one among many. Tamagne was born in Ethiopia; grow up in Ethiopia, and becoming Ethiopia. His entire families were from Ethiopia. They all love their country and understand the beauty of love, kindness, respect, and compassion. They are the true faces of Ethiopia.
On the other hand, we have brothers and sisters who decided to be dark and evil. They want us to go back. They want us to count our bones. They want us to be divided in terms of race, power, province, and religion. I tell you such are not from God but evil. ‘Turn from evil; do good; seek peace and pursue it (Psalms 34:14). I tell you again anyone who purposefully tries to deprive our liberty, unity, and one nation for the sake of security are wrong and from evil. Benjamin Franklin stated any society that would give up a little liberty to a gain a little security will deserve neither and lose both.’
Lord Acton wrote, “Liberty and good government do not exclude each other, and there are excellent reasons why they should go together. Liberty is not a means to a higher political end. It is itself the highest political end. It is not for the sake of a good public administration that it is required, but for the security in the pursuit of the highest objects of civil society, and of private life.”
Long live mother Ethiopia.
God be with us.

Mar 11, 2013

ለኢትዮጵያ እንድረስላት ይህን ሳናደርግ የቀረን እንደሆነ ግን ህሊና ቢስ ነን ፍሬ ቢስ ነን ወይም ደግሞ ከሃዲ ነን

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁናቴ ህዝቡ á‹•á‹ľáˆ‰áŠ• አግኝቶ ወደውጭ የወጣ እንደሆነ á‹ˆá‹° ዓገር ቤት ተመልሶ ቢገባ የጭንቅላት በሽተኛ ወይም እንደ እብድ አልያም እንደ ሞተ

autor yared elias Brehane
ያሬድ ኤልያስ
ሰው ተቆጥሮ የህድር ጡሩንባ ተለፍፎ ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ የሚላቀስበት አልያም ደግሞ ከቤተሰብ ትዳር አንስቶ የሰፈር ሰው ትንሽ ትልቁ የስራ ባልደረባ ከታክሲ ሹፌር እስከ ዶክተር እስከ ትልቁ የወያኔ አገዛዝ ሚኒስቴር ድረስ እንደዘመኑ በሽታ ታይቶ የምትገለልበት ወሬው ሁሉ እንትና ደቡብ አፍሪካ ጠፋ በሞያሌ በሱዳን ሊቢያ  áŠĽá‹¨á‰°á‰Łáˆˆ ስንቱ  á‰°áˆľá‹ ቆርጦ የሱሰኛ ተገዢ የሚደረግበትዘመን። áˆŒáˆ‹á‹ ይቅርና  áŠĽá‰ľá‰Ľá‰ą ወደተቀበረበት ሃገር ለመመለሾ እንኳን á‹¨á‹ˆá‹ŤáŠ” ገዢ ፓርቲ 10 ግዜ እንድናስብ የሚነግረን ወቅት  áŠĽáŠ•á‹°áŠáŒˆáˆŠ á‰°á‰ áˆá‰ś አንዲት ለስላሳ ለመጠጣት 20 ግዜ የሚታሰብበት ቢራ ለመጠጣት ዱቤ ለመጠየቅ 40 ግዜ የሚታሰብበት ሃገር።  áˆľáˆˆ እውነት ስለነጻነት ቢጠየቅ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል መልሱን ? ..ለነሱ……… fየሚባለበት ግዜ ።
መቼስ አገሩ ላይ መኖር የሚጠላ ስው ያለ አይመስለኝም ግና ገና አካሉ አገሩ ላይ ቍጭ ብሎ መንፈሱ ውጭ አገር ያለውን ስንቱ ይቍጠረው። በውጭ ሃገር የሚኖረውማ  á‹ˆá‹° ሃገሩ ተመልሶ ሃገሩ ላይ ሃገሩን ወገኑን ለማገልገል የፈለገ ሰው ሃገሪቷ ላይ መኖር የማይችልበትን የጥቂት ዘረኛ ወያኔ አገዛዝ መንግስት የሚኖርባት በመሆኑ ለማድረግ አይችልም። á‰ á‹› ላይ ሰሞኑን ያየሁት የሰለሞን ቦጋለ እና ሳምሶን ቤቢ ፊልም በጣም ሲከነክነኝ ነው የዋለው አዎ የዚህ ደራሲ በፈለገው መልኩ ይጻፈው እኔ በተረዳውት ግን ለዚያች አገር ለዛ ህብረተሰብ ነጻነት ያስፈልገዋል ። መልዕክቱን በፈለጉት መልኩ ያስተላልፉት ግን በደንብ የሚታይ ነገር ነበረበት ስለነጻነት ብሩህ ተስፋ ።
ለነገሩ ወያኔዎች áŠ áŒˆáˆŤá‰¸á‹ áŠ á‹­á‹°áˆáˆ  á‹¨áˆ˜áŒĄá‰ á‰ľáŠ• ዓላማ አሳክተዋል።  á‹¨áˆľáˆŤá‹áŠ• ይስጠውና ሟቹ ስሙን ቄስ ይጥራውና አገሪቷን በዘር በዓይማኖት በብሄር ከፋፍሎ ሰዉ በጎሪጥ እንዲተያይ አድርጎት እሱ ወደማይቀረው ሄዷል ምን አለ የሱ ተከታዮችም ይሄ መኖሩን አውቀው ወደ ህዝቡ በተመለሱ። አገሪቷማ  áˆľáŠ•á‰ąáŠ• አሳድጋ እንጡራ አብቷን አውጥታ ያስተማረችውን á‹¨á‰°áˆ›áˆ¨ ዓይል ስንት ድግሪ ፕሮፌሰር ያደረገችውን ሃገር እየተወ መመለሻም መቀበሪያም ላትሆነው ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተሰድዶ በአሁኑ ሰዓት á‰ áˆľá‹°á‰ľ ላይ ይኖራል ። እንዲህም ሆኖ ለሃገር የተቆረቆሩ የሚመስሉ ከሃዲ ሆዳም እነዚህን ሰዎች ባሉበት ቦታ እንኳን እንዲቀመጡ አያደርጓቸውም እንዲያውም ብለው ወያኔ ለሃገር እንደሚቆረቆር ያወራሉ  ለነገሩ የትኛው á‹¨á‹ˆá‹ŤáŠ” ሃገዛዝ መንግስት ነው ለሃገሩ የሚቆረቆረው በዛ በበረሃ የማንም ተኩስ መለማመጃ ሆነው እነደሻማ ቀልጠው ሲቀሩ ሴት እህቶቻችን ማንም ሳይደርስላቸው እንደበግ መሬት ለመሬት ሲጎተቱ ዝም ብሎ  á‰ á‹°áˆáŠ“ው ሃገር ሃገር ማለት መብራትና ውሃ በሌለበት ሰዉ በፈለገውና በሚታየው መልኩ የራሱን ሃሳብ መግለጽ የማይችልበት ከታክሲ ዳቦና ወዘተ የመሳሰሉት ሰልፍ በስተቀር 3 ሰው እንኳን አብሮ ቆሞ ማውራት የማይቻልበት ወያኔ ለህዝቡ ካልሰረቀና ሙስና ካልሰራ መሻሻል የማይቻልበት ሃገር ለዚች አገር ነው ተቆረቆረ የሚባለው። ውድ ወገኖች áˆľáˆˆá‹šáˆ… ለዘመናት ባአባቶቻችን በጥረታቸው á‹¨á‰°áŒˆáŠá‰Łá‰˝ የገነቧትን ሃገር ወያኔ ደግሞ በግዴለሽነት በዘረኝነት እየፈራረሳት ይገኛል ። ህዝቡንም በትልቅ የሞራል እስር ቤት ውስጥ አስረውት ይገኛል ከዚህ እስር ቤት የሚያወጣው አንዳች አይል ያስፈልገዋል ። የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር በማንኛውም መንገድ ማስመለስ ይኖርብናል ህዝቡ በእየለቱ በሚሰማው ነገር ልቡ  áˆ¸áá‰ˇáˆ ከጥቂት ሆዳሞች በስተቀር ስለዚህ ይኼ የነገዋ ኢትዮዽያ ቀን ነዉ የኔ የእናንተ ብ ቻ ሳይሆን የመላዉ ኢትዮዽያ ጥያቄ ነዉ እንድረስላት ይህን ሳናደርግ የቀረን እንደሆነ ግን ህሊና ቢስ ነን ፍሬ ቢስ ነን ወይም ደግሞ ከሃዲ ነን።  click here more
እግዚሃብሄር ኢትዮጵያንና ተከባብሮ የሚኖረውን በማንኛውም ዓይማኖት ላይያለውን ህዝብ ይባርክ
አሜን
ያሬድ ኤልያስ
nome telemark dagsrud

Mar 9, 2013

you want buy children from ethiopia ?

Every agency defines and lists fees differently, which causes confusion when comparing costs. Despite the wide-ranging variables, we have compiled an estimated total that we hope includes every necessary expense related to the adoption. No additional adoption service fees will be required to be paid in Ethiopia. 

Fees and Estimated Adoption Expenses 
Application $ 300 
Adoption study * $ 2,500 - 2,900 
Dossier fee $ 3,000 
Program Fee $ 11,900 
Documents, Certifications and Notarizations $ 100 – 300 
USCIS fees $ 830 
Post placement * $ 1,200 - 1,400 
Travel cost $ 8,000 - 15,000 
Estimated total $ 25,820 - 33,620
* if provided by Holt International Children's Services 

Adoption Expenses Explained

Application 
Holt will open a file for your family and conduct an preliminary assessment that provides initial assurance that we will be able to place a child with you. Due when first applying. Non-refundable


Adoption Study

Often called a “homestudy,” a professional social worker will help your family understand international adoption and assess your ability to parent a child not born to you. The social worker will prepare a document (the adoption study), which is required by virtually ever
y country in the world in order to adopt.





Holt performs the adoption study if you live in a state served by a Holt branch office (Arkansas, California, Iowa, Kansas, Nebraska, Missouri, New Jersey, Oregon, South Dakota). If you live in another state, the adoption study will be provided and billed by an agency approved by Holt. 

Due before the start of group meetings or adoptive study interviews. 


Dossier fee

This fee covers Holt costs to facilitate your adoption with government officials and our partner agencies both in the United States and abroad, coordinating services with your local social worker, administrative/office expenses and telephone expenses. 

Due when Holt approves your adoption study. Non-refundable if you withdraw.


Program fee

This fees covers costs in your child’s country of birth: 


• background investigation and identification of child
• social services
• legal fees
• accepting legal responsibility for the child
• working with government and agency authorities
• translation
• child care, medical expenses (portions not covered by sponsorship)
• passport and U.S. visa fees in the child's country
• in country travel arrangements and assistance 
A small portion of the fee will help develop Holt Ethiopian childcare projects.

Due when you accept the assignment of a child.

Documents, Certifications and Notarizations 
These are expenses related to obtaining legal and vital documents and getting the necessary certifications and notarizations to complete your dossier. These fees are paid to the appropriate government authority.


Postplacement fee

Several official reports are required after your child is home. This fee pays for social worker visits and documentation. If you live in a state not served by a Holt branch office, postplacement services will be provided and billed by an agency approved by Holt.
 

Travel

Holt staff will guide you through making travel arrangements, and provide assistance throughout your stay in Ethiopia. Airfare, lodging and meal expenses are paid directly to the vendors you select.
you can watch here more

ጥቃት በየተራ እስከመቼ?

ባለፉት 21 የወያኔ የግዛት አመታት አይነቱና መጠኑ ይለያይ እንደሆነ እንጅ ጥቃት፣ ግፍ፣ በደልና እብሪታዊ የመብት ገፈፋ ያልደረሰበት ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ክፍል የለም። ገበሬው፣ የመንግስት ሰራተኛው፣ የፋብሪካ ሰራተኛና በየዘርፉ የእለት ጉርሱን አሳዶ የሚኖረው ሁሉ የወያኔን የሰቆቃ ግፍ በትር በየተራ አይቶታል፣ እያየውም ይገኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት አንጀቱ ለፍቶ ያቋቋማቸው ተቋሞቹ እየፈራረሱ ለወያኔ አገዛዝ እንዲመቹ ሆነው ሲጨፈላለቁም አይተናል።
ወያኔ ይህን ሁሉ ያደረገው “አንዱን በአንዴ” በሚል ስልት ነው። መምህራንን ሲያጠቃ የፋብሪካውን ሰራተኛ ተመልካች ያደርገዋል፤ ገበሬውን ሲያጠቃ ከተሜውን ዝም ይለዋል፤ ከተሜው ላይ ሲዘምት ገበሬው ተመልካች ይሆናል፤ ቤተክርሰቲያን ላይ ሲዘምት ቤተ ሙስሊሙ ይመለከተዋል፤ የቤተ ሙስሊሙ የበደል ተራ ጊዜ ቤተክርስቲያን ተመልካች ትሆናለች። ይህ ወያኔን እስከዛሬ ያደረሰው ስልት ነው።
አራዊታዊው የወያኔ አገዛዝ በተመቸውና ይጠቅመኛል ብሎ በአሰበ ሰአት ሁሉ የውብ ህዝብነት ምልክታችን የሆነውን የባህልና የቋንቋ ስብጥርነታችንን እርስ በርስ ለማናከሻነት ሊጠቀምበትም ሞክሯል፤ በተወሰነ ደረጃ አልሰራላቸውም ማለት ያስቸግራል፡፡
ወያኔዎች ከፋፍሎ መግዛትንና በየተራ ማጥቃትን በኪነ ጥበብ ደረጃ አሳድገነዋል ብለው ያምናሉ። በህዝብ ወገን ያለነውም የዲሞክራሲና የነጻነት ሃይሎች ለዚህ አልተመቸንም ማለት ያስቸግራል፡፡ ይህንን ከፋፍሎ የማጥቃት ግፍ በጋራ ለመመከት ያደረግነው ጥረት ህዝባችን ላይ እየደረሰ ካለው ጥቃት ጋር ቢያንስ የሚመጣጠን አይደለም።
የወያኔ መሪዎች ዛሬ ስልታቸውን በማሻሻል አደገኛ ጭዋታ በቤተ እምነቶቻችን ዙሪያ መጫዎት ጀምረዋል። የቤተክርስቲያን እና የአቢያተ መስጊዶችን አስተዳደር በካድሬዎቻቸው ለመቆጣጠር ከሚያደርጉት ሳይጣናዊ ተግባር በተጨማሪ ህዝቡ ሃይማኖት ለይቶ እንዲባላ ለማድረግ በእጅጉ የሚቀፍ ፕሮፖጋንዳ እያካሄዱ ነው። ፍጹም ምሳሌያዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሲቪል መብት ጥያቄ እንደባዕድ መሳሪያነትና እንደ ሽብርተኝነት ለማሳየት እየሞከረ ይገኛል። በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሙሉ እጁን በማስገባት የተጀመረውን እርቀ ሰላም በማፍረስ የራሱን እንደራሴ ሰይሟል። ይህም አልበቃ ብሎት ለዘመናት በመከባበር የኖረውን ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን እርስ በርስ ለማጋጨት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል።
ዛሬ ከመቸውም በበለጠ ሀገራችን ወደማትወጣው አደጋ እየተገፋች ነው። ይህንን ወያኔ ያዘጋጀልንን የክፍፍልና ግጭት ድግስ ለመመከት ይበልጥ በአንድነት የምንቆምበት እና የምንታገልበት ግዜ ዛሬ ነው፡፡
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለወያኔ የ”ከፋፍለህ በየተራ ቀጥቀጥ” ፖሊሲ መድሃኒቱ አንድ ሆኖ በአንድነት አሻፈረኝ ብሎ መነሳት መሆኑን ያምናል፡፡ ወያኔ ጉልበቱ የኛ መከፋፈልና ለክፍፍሉ መመቸት መሆኑን ያምናል፡፡ እኛ ስንተባበርና ልዩነታችንን ለመጠቀም የሚያደረገውን ሙከራ ስናከሽፍና አንዱ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የሁላችንም ነው ብለን የተነሳን እለት ወያኔ የለም።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ወያኔ በፈቃዱ የማይታረም ፋሺስታዊ አምባገነን መሆኑን ከተረዳ ሰንብቷል። በመሆኑም ወያኔን በማስገደድ ወይም በማስወገድ ነጻነታችንን መቀዳጀትና ነጻ ሀገር እንዲኖረን ማድረግ አለብን ብለን እናምናለን። ለዚህ ትግልም ማንኛውንም መሰዋእትነት ለመክፈል ተነስተናል። ነጻነትና ኮርተህ በነጻነት የምትኖርባት ሀገር እንድትኖርህ የምትወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተቀላቀለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ጋምቤላ አሁንም በወያኔ ወራሪ ሠራዊት እየታመሰች መሆኗ ተሰማ


በ1996 ዓም ከ400 በላይ አኝዋኮችን በግፍ የጨፈጨፈዉ የወያኔ ወራሪ ሠራዊትና ልዩ ኃይል ከሰሞኑ በብዛት ወደ ጋምቤላ በመዝመት ሠላማዊ ዜጎችን በተለይ የአካባቢዉን አርሶ አደሮች እየያዘ ማሰርና መግደል መጀመሩን ከአካባቢዉን እየሸሹ ጫካ የገቡ ዜጎች ለኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን ስልክ እየደወሉ በሚልኩት ዜና ገለጹ። በተለይ ካለፈዉ አርብ ጀምሮ ፌዴራል ፖሊስ፤ መከላከያ ሠራዊትና የደህንነት ልዩ ሀይሎች ተቀናጅተዉ በጋራ በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ ተቃዋሚዎችን ይረዳሉ ወይም ታጣቂዎችን ሊቀላቀሉ ይችላሉ ብለዉ የጠረጠሯቸዉን ሠላማዊ ዜጎች ማሰራቸዉንና እራሳቸዉን ለማዳን የሞከሩ ሰዎችን ተኩሰዉ መግደላቸዉን ከአካባባዉ የደረሰን ዜና ጨምሮ ያስረዳል። በአሁኑ ወቅት የወያኔ ወራሪ ሠራዊት በብዛት ወደ ጋምቤላና አካባቢዉ እየዘመተ ሲሆን የአካባቢዉ ህዝብም እራሱን ለማዳን ጫካ እየገባ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የወያኔ ወራሪ ሠራዊት ካለፈዉ ዐርብ ጀምሮ በወሰደዉ የማጥቃት አርምጃ ከአስራ ሁለት በላይ ሠላማዊ ዜጎችን የገደለ ሲሆን ከሟቾቹ ዉስጥ አንድ የአካባቢዉ ተወላጅ የሆነ የአሜሪካ ዜጋ ይገኝበታል። የግንቦት ሰባት ድምጽ ዝግጅት ክፍል የወያኔ ጦር በአካባቢዉ ያደረገዉ ጭፍጨፋ እንደተሰማ በክልሉ የሚገኙ አንዳንድ ባለስልጣናትን ሰልክ ደዉሎ ሁኔታዉን ለማጣራት ሞክሮ ነበር ፤ ሆኖም የዝግጅት ክፍላችን ያናገረዉ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣን በአካባቢዉ ምንም አይነት ግጭት የለም በማለት በአለም ዙሪያ የተሰራጨዉን እዉነት ለመካድ ሞክሯል። በሌላ በኩል አዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣኖች የጸጥታ ሀይሎች ጋምቤላ አካባቢ የአማጽያንን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በሚል በወሰዱት እርምጃ አንድ የአሜሪካ ዜግነት ያለዉ ሰዉ መገደሉን ለአሜሪካ ኤምባሲ ተናግረዋል።
የአዲስቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ የሆኑት አቶ አባንግ ሜቶ ከኢሳት ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በጋምቤላና በአካባቢዉ ያለዉን ወታደራዊ ዉጥረት ድርጅታቸዉ በቅርብ እንደሚከታተለዉ ተናግረዉ ከሰሞኑ በወያኔ ወታደሮች ተገደለ ስለተባለዉ የአሜሪካ ዜጋ አስፈለገዉን የክትትል መረጃዎች ለአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መስጠጣቸዉን ተናግዋል። ዜጎችዋ በዉጭ አገር በሚደረጉ ወታደራዊ ግጭቶችና አመጾች ሲገደሉ ወይም ደብዛቸዉ ሲጠፋ ክፍተኛ ክትትል የምታደርገዉ ዩ ኤስ አሜሪካ አሁንም ጋምቤላ ዉስጥ በወያኔ ወታደሮች ተገደለ የተባለዉን ዜጋዋን ጉዳይ መከታተል መጀመሯን ለማወቅ ተችሏል። በቅርቡ የኦባማ አስተዳደር ከአሸባሪዎች ጎን ተሰልፈዉ በሚዋጉ የአሜሪካ ዜጎች ላይ የሚወስደዉን አርምጃ በተመለከት ሾልኮ የወጣዉ መረጃ ኮንግሬሱን ጨምሮ አያሌ አሜሪካኖችን እንዳስቆጣ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህ ከሰሞኑ ጋምቤላ ዉስጥ የተገደለዉ አሜሪካዊ ጉዳይ ይበልጥ በተሰማና በታወቀ ቁጥር ወያኔ ላይ መዘዝ ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ።

Mar 8, 2013

እኛም እንድገመዋ… ርዕዮትን እያሰሩ … ቐሽ ገብሩን ቢዘክሩ… “ሼም” የለም በአገሩ…!?

አቤ ቶኪቻው

ተዓምረኛው ኢቲቪ ለማርች ስምንት የሴቶች ቀን መታሰቢያ አንድ ዶክመንተሪ ፊልም አሳይቶናል። ፊልሙ የዛሬ አመት ተላልፎ እኛም የአቅማችንን አስተያየት ሰጥተንበት ነበር። ታድያ ዛሬም ኢቲቪዬ ፊልሙን ደግሞ አሳይቶናል። ታድያ መድገም ብርቅ ነው እንዴ… እኛም አስተያየታችንን እንድገመዋ!
በመጀመሪያ አበሻ እንደመሆኔ መጠን ጭቆናን “እምቢ” ብለው ፋኖን ለዘመሩ ታጋዮች ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ ያለ ሽሙጥ እገልፃለሁ።
ተስፋዬ ገብረ አብ ከተረካቸው ትረካዎች በሙሉ “የቁንድዶ ፈረስ” ትረካ በጣም የመሰጠችኝ ናት። እስቲ ለማስታወስ ልሞክር…
ሐረር አካባቢ፤ የጋሪ ፈረሶች የሚደርስባቸው የስራ ጫና እጅግ በጣም ከባድ ነበር። ከስራ ጫናው እኩል ደግሞ ዱላም አለው። ልክ አሁን አሁን ደሞዛችን አነሰ ብለን “ኡኡ” ስንል “ለአባይ እና ለሌሎች ልማቶች ደግሞ መዋጮ አዋጡ” ተብለን መከራችንን እንደምናየው ማለት ነው። በዚህ ላይ እነዚህ የጋሪ ፈረሶች ስራውና ዱላ የሚደራረብባቸው አንሶ ጌታቸው (አባ ፈርዳው) ቀለባቸውንም በአግባቡ አይሰፍርላቸውም ነበርና ከሰውነት ጎዳና ወጥተው ክስት ጉስቁል አሉ።እኛም እንድገመዋ… ርዕዮትን እያሰሩ … ቐሽ ገብሩን ቢዘክሩ… “ሼም” የለም በአገሩ…!?
ይሄን ግዜ “እምቢኝ” አሉና “ቁንድዶ” ወደተባለ ጫካ ገቡ። ከዛም ባህሪያቸው ተለውጦ እንደፈረስ ሳይሆን እንደ እንደ አውሬ ሆኑ። ማን ወንድ መጥቶ ዳግም ወደዛ የጋሪ ባርነት ይመልሳቸው? ማንም።
ታድያ ፈረሶቹ እዛው ጫካ ውስጥ መሽገው እንዳሻቸው እየበሉ እንዳሻቸው እየቦረቁ አማረባቸው። ወዘናቸውም “ጢም” አለ።
“በአሁኑ ግዜ የሀረር አካባቢ ነዋሪዎች የኦህዴድ አባላትን እስከ መቼ የጋሪ ፈረስ ትሆናላችሁ? አንዳንዴ እንኳን የቁንድዶ ፈረስ ሁኑ እንጂ…! እያሉ ያሽሟጥጧቸዋል።” ብሎናል ተስፋዬ። (ልክ ነኝ አይደል ተስፋዬ…? “ይሄንን እኔ አላልኩም” ካልክ እኔ ለማለት እገደዳለሁ…!(ፈገግታ))
እናም እኔ በበኩሌ የቁንድዶ ፈረስነትን አደንቃለሁ። አላማው ልክ ነው አይደለም የሚለው ጥያቄ በይደር ይቆይ። ነገር ግን በደል ሲበዛ “እምቢ” ማለት ከአባት የወረስነው ነው። ዛሬ የሽብረተኝነት አዋጅ ወጥቶ ሳይከለከል አይቀርም እንጂ አንድ ዘፈን ትዝ ይለኛል…
“ደብቆታል መሰል ሶማ በረሃው
“እምቢ” ያለው ጎበዝ የታል ሽፈራው” የሚል ዘፈን።
በአሁኑ ወቅት፤ ይህንን ዘፈን በይፋ መዝፈን የሚቻል አይመስለኝም። ምክንያቱም በሽብርተኝነት አዋጁ አንድ ግለሰብ፤ በዘፈን በፅሁፍ እና በተለያዩ መንገዶች “ሽብርተኛን” እንኳንስ ሲያበረታታ ተገኝቶ ይቅርና፤ “አበረታቷል” ተብሎ ሲታሰብም “ጉዱ ይፈላል” ይላል። በተጨባጭ እንደምናየው ደግሞ እንኳንስ እምቢ ብለው ሶማ ጫካ ገብተው ይቅርና በከተማው ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸው “አሸባሪ” ስለመሆናቸው መረጃው አለ። ማስረጃው ጠፍቶ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩም እኛም የጨነቀን…! ስለዚህ “ደብቆታል መሰል ሶማ በረሃው እምቢ ያለው ጎበዝ የታል ሽፈራው…” ብሎ ማዜም አይቻልም ማለት ነው።
ለማንኛውም፤ ዘፈኑ ግን “እምቢ” ባይነትን እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙሃን የሀገሬ ሰው እንደሚያደንቅ ያስረዳልኛል። አዎ አንዳንዴም እምቢ ማለት ጥሩ ነው። “እምቢ… እምቢ ለሀገሬ! እምቢ… እምቢ ለክብሪ! እምቢ… ታታታታ” ፉከራው ልሹ ማማሩ።
ስለዚህ ቐሽ ገብሩ፤ አሞራውና ሌሎችም “እምቢ” ባይ ታጋዮች “እምቢ” በማለታቸው አደንቃቸዋለሁ። እንኳንም እምቢ አላችሁ!
ወደ ቐሽ ገብሩ ስንመጣ የዶክመንተሪው አዘጋጆች ልብ ያላሉት ወይም ደግሞ “ምን ታመጣላችሁ” ብለው ችላ ያሉት አንድ ስህተት የፌስ ቡክ ወዳጆቼ አግኝተው ነበር። ልብ በሉልኝ ህውሃት ሆዬ ቐሽ ገብሩን መትረየስ ሲያሸክማት ገና የአስራ ሶስት አመት ልጅ ነበረች። ከፈለጋችሁ አስሉት በአስራ ዘጠኝ ስድሳ አንድ ተወለደች። በአስራ ዘጠኝ ሰባ አራት ወደ ትግል ገባች። ማነው ሂሳብ የሚችል…? በሉ እስቲ አስሉልኝ። ሰባ አራት ሲቀነስ ስድሳ አንድ እኩል ይሆናል፤ አስራ ሶስት። ዘጋቢው ፊልም ሲቀጥልም “…ትግሉን በተቀላቀለች በጥቂት ወራት ውስጥ እጇን ተመታች። እንደዛም ሆና መትረየስ ትሸከም ነበር።” ይላል። ጉድ በል ህውሃት…! አይሉኝም?
በዛ ሰሞን አለም ሲነጋገርበት ከሰነበተባቸው ነገሮች ውስጥ በኡጋንዳ የሚገኘው የሎርድ ሬዚስታንት አርሚ መሪ፤ ጆሴፍ ኮኒ ህፃናትን ጦርነት ውስጥ እየማገደ ነው በሚል ታድኖ ይከሰስ ዘንድ የተጀመረው “ኮኒ ሁለት ሺህ አስራ ሁለት” የሚል እንቅስቃሴ ነው። በአለም አቀፍ ህግ፣ አረ በኢትዮጵያ ህገ መንግስትም ቢሆን ህፃናትን ለጦርነት ማሳተፍ የለየለት ወንጀል ነው። በእግዜሩ ዘንድም ያስጠይቃል።
እና ህውሃት የአስራ ሶስት አመቷን ህፃን ሙሉ “ቐሽ ገብሩ” ን በጦርነት ማሳተፉ ሳያንስ የግፉ ግፍ ደግሞ ለማርች ስምንት የሴቶች መብት ክብረ በዓል ላይ ታሪኳን እንደ ጥሩ ነገር ዘገበልን። እውነቱን ለመናገር ይሄ ትልቅ የወንጀል መረጃ ነው። እንደኔ እምነት ይህንን መረጃ ያጠናከሩ ሰዎች የውስጥ አርበኝነት ሾል እየሰሩ ነው። ይሄ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ገና በርካታ መረጃዎችን ያወጣል። እዝችው ላይ ሙሉ ወይም ቐሽ ገብሩ ገና አስራ ስምንት አመት እንኳ ሳይሞላት አንድ ጎረምሳ በፍቅር ስም አስረግዞ እስከማስወረድ እንድትደርስ እንዳደረጋትም ዶክመንተሪው ይዘግባል። ሰውየው ከሷ ጋር ያሳለፈውን ፍቅርም ሲናገርም በኩራት ነው። እንዴት ነው ነገሩ… እኛ መሀሙድ አህመድ በአንድ ዘፈኑ ላይ “ሸግየዋ ጉብሊቷ… የአስራ አምስት አመቷ እንዴት ነሽ በሉልኝ የምታውቁ ቤቷን” ብሎ ስለዘፈነ አይደል እንዴ ከህፃናት መብት አንፃር ወንጀል ነውና ይቅርታ መጠየቅ አለበት እያልን የምንሟገተው? እንዲህ የባሰውን ነውር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አየነው። ለዚህ ነው አይናችን የተርገበገው…?
ወዳጄ እንዴት ሰነበቱ አይገርምዎትም ይሄ ሁሉ መንደርርደሪያ መሆኑ… ይበሉ ወደ ዋናው ጉዳይ ተያይዘን እናምራ
እናልዎ… ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተለያየ ግዜ የተለያየ ዘጋቢም አወዛጋቢም ፊልሞችን ያቀርብልናል።
በዛ ሳምትን ያየነውም የቐሽ ገብሩ ዶክመንተሪም የዚሁ አካል ነው። እንግዲህ ከላይ ያነሳነውን በቐሽ ገብሩ የተጋለጠውን ህፃናትን ወደ ጦርነት የማሰማራት እና ለአቅመ ህይዋን ያልደረሱ ሴቶችን የማማገጥ ወንጀል እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለሚከታተሉ አካሎች እንተወው እና የፈረደባትን ይቺን ህፃን “እምቢ” እንዳለች ጀግና እንቁጠራት። ቆጠርናት…!
ኢህአዴግ ደርግን ብዙ ግዜ ደርግ በጦርነት የማረካቸውን ታጋዮቼን የማያምኑበትን እንዲናገሩ ያሰቃያቸው ነበር፤ ከዛም እምቢ ሲሉት ያስራቸዋል፤ ይገድላቸዋል። ብሎ ይወቅሳል። ይቀጥልናም ቢሆንም ግን፤ “እንደ አሞራው ሁኑ እንደ ቐሽ ገብሩ ሁኑ ብሎ ይመክረናል። እኛም ምክር የምንሰማ ልባሞች ነንና እሺ ብለን እንደ አሞራው፤ እንደ ቐሽ ገብሩም ለመሆን እንታትራለን ከዛ ውጤቱ ምን ይሆናል አይሉኝም…? ለምን እጠይቅሀለው እያወቅሁት…? አሉኝ እንዴ!?
ሰሞኑን አቶ አንዷለም አራጌ ላይ የሆነውን ነገር ሰምተዋል። አንዷለም አራጌ እንደ አሞራው ሁኑ ከመባሉ በፊትም እንደ አሞራው “እምቢ” ባይ ነበር። ለዛውም ጫካ ሳይገባ ፊት ለፊት እምቢ ብሎ የተጋፈጠ ደፋር የተቃማዊ ፓርቲ አመራር ነው። ምን ዋጋ አለው አንዷለም እንደ አሞራው “እምቢ” ቢልም ኢህአዴግ ደግሞ እንደ ደርግ “እምቢ” ማለት አይቻልም ብሎ አሰረው። ማሰር ብቻ ቢሆን በስንት ጣዕሙ ጎረምሳ አስገብቶ አስደበደበው እንጂ!
ማርች ስምንት የአለም ሴቶች ቀን ነው። በአለም ላይ ያሉ ሴቶች ቀደም ሲል ሲደርስባቸው የነበረ ጭቆና ይብቃ የተባለበት ቀን። ይህ ቀን፤ የህውሃት ሴቶች ቀንም የአንድነት ሴቶች ቀንም፤ የጋዜጠኛ ሴቶች ቀንም፣ የሁሉም ሴቶች ቀን ነው።
ርዕዮት አለሙ አሳሪዎቿ የጠላነውን አብረሽን ከጠላሽ ትለቀቂያለሽ ብለዋት ነበር። ቃል በቃል ሲነገር “ኤልያስ ክፍሌ የተባለው ጋዜጠኛን አሸባሪ ነው መሰስክሪበት እና ትለቀቂያለሽ” ተባለች። እርሷም እኔ “በወንጀለኝነት አላውቀውም” ብላ ድርቅ አለች። እንግዲያስ ብሎ ኢህአዴግም አስራ አራት አመት ፈረደባት። ቐሽ ገብሩን ደርግ የያዛት ግዜ “የህውሃት ሰዎችን ወንጀለኛ ናቸው ብለሽ መስክሪባቸው” አላት እምቢኝ ብላ ድርቅ አለች ሞት ፈረደባት። እንግዲህ ቐሽ ገብሩ እና ርዮት አለሙ አንድ ናቸው “እምቢኝ” ብለዋልና። ደርግ እና ኢህአዴግስ…? የመጣው ይምጣ ደፍሬ ልናገር ነው..! አዎ ደርግ እና ኢህአዴግም አንድ ናቸው። እምቢ ያላቸው ላይ ሁሉ ይፈርዳሉና። በነገራችን ላይ የደርግ ፕሮፖጋንዳ ሰራተኞች ቐሽ ገብሩን ለማናገር መከራቸውን ሲያዩ የነበረውን ያህል የኢህአዴግ ጋዜጠኞችም በተደበቀ ካሜራ ሳይቀር ርዮትን ለማናገር አበሳቸውን ሲያዩ ነበር። ነገር ግን ቐሽ ገብሩም ርዮትም አለሙም ፍንክች የአባ ቢላው ልጅ ብለዋል። ወይ መገጣጠም…! አይሉልኝም?
እና ታድያ የሴቶች ቀን ክብረ በዓል ሲዘከር መንግስት ርዕዮትን አስሮ ሾለ ቐሽ ገብሩ ሲተርክ የአራዳ ልጆች ሰሙ። ሰምተውም ጠየቁ “ሼም የለም እንዴ በአገሩ!?” አሉ ዝርዝር ያለው የስራ ሂደት ካለ መልስ ያምጣ…!
በጥቅሉ መንግስት እነ ርዕዮትን፣ እነ እስክንድርን፣ እነ ውብሸትን፣ እነ ሂሩትን፣ እነ አንዷለምን እነ ናትናኤልን፤ ስንቱን ጠርቼ እዘልቀዋለሁ? በጅምላው እምቢ ያሉትን ሁሉ እያሰረ እና እየገረፈ “ደርግ ታጋዮቼን አሰረ፣ ገረፈ፣ ገደለ” ብሎ ዋይ ዋይ ማለት ውሃ የማያነሳ ወቀሳ ነው። መፅሐፉም ይላል “የሌሎችን ጉድፍ ከማየትህ በፊት በአንተ አይን ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ተመልከት…”
በመጨረሻም
ያወጋነውን ለፍሬ ይበልልን
አማን ያሰንብተን!

Mar 7, 2013

Watch and share. Two young Ethiopian immigrants physically abused by Arab human traffic smugglers

Watch and share. Two young Ethiopian immigrants physically abused by Arab human traffic smugglers




“ድህነታቸውን ህዝቡ ላይ አራግፈው ለራሳቸው ባለፎቆች ሆነዋል” ስማቸው ያልተገለጸ እናት

ከሉሉ ከበደ

ሰሞኑን ከአገር ቤት አንዲት እናት ልጃቸውን ሊጠይቁ መተው ነበር። ልጃቸው የባለቤቴ ጓደኛ ነች።..የኔም ጓደኛ!…እኒህ አናት አንደበተ ርቱእና ተደምጠው የማይጠገቡ ጨዋታ አዋቂ ቀልደኛም ናቸው። ሑሉም ነገር የገባቸው ፍጹም ፖለቲካ አዋቂ ብሩህ እናት ናቸው። ጨዋታቸው ንግግራቸው ሁሉ ይማርካል። ሰማንያ አመት አይሞሉም። ጥንክር ያሉ፤ የነቁ ፍጹም ጤናማ እናት ናቸው።

ወይን ቢጤ ገዛሁና ባለቤቴ ድፎ ዳቦ ጋግራ (እናቶች አዚህ አገር ሲመጡ ድፎ ዳቦ ሲቀርብላቸው ደስ እንደሚላቸው ታውቃለች) እንኳን ደህና መጡ ልንል ሄድን።
ለሁለት ሰአት ያህል አብሬ ስቆይ ከናታችን የገበየሁት ትምህርትና ቁም ነገር በቀላል የሚገመት አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ እየጠላቸው ዛሬ ስልጣን ላይ የተጣበቁት የወያኔ ደናቁርት፤ addis-ababa-2013የኢትዮጵያን ህዝብ ምንም አያውቅም ብለው፤ የሚገምቱትና የሚንቁት፤ወደ ታች ወደ ህብረተሰቡ ዝቅ ብለው፤ስለነሱ አገዛዝ፤ ሾለ መልካም አስተዳደር ያለውን ግንዛቤ ቢረዱ ምን ያህል ከህብረተሰቡ ኋላ ኋላ እየሄዱ እንመራሀለን እንደሚሉ በተረዱና ባፈሩ ይበጃቸው ነበር።
እኒህ እናት ድህነትን እኩል ያካፈለን ደርግ ተሻለ ነው ነው የሚሉት፤ “እነዚህ ድህነታቸውን ህዝቡ ላይ አራግፈው ለራሳቸው ባለፎቅ ሆነዋል። ደርግ አንዱን ልጅ አንዱን እንጀራ ልጅ አላደረገንም። ቢበድለንም አልለያየንም።”
ጎዳና ላይ ለፈሰሱ ለማኝ ህጻናትና ወላጆች ዘወትር ያለቅሳሉ። ኑሮአቸውን የከተማው ቆሻ ክምር ላይ የመሰረቱ ወላጆችና ልጆች ያስለቅሷቸዋል። “ይሄ ሁሉ ፎቅ ይገነባል። የእያንዳንዱን ፎቅ ባለቤት አስር አስር ልጅ ከጎዳና ወስዶ እንዲያሳድግ ቢያስገድዱት ጽድቅ ነበር። ላለው ሰው ምንም ማለት አይደለም” ይላሉ።
ስለቤተሰብ ስለዘመድ አዝማድ፤ስአየርንብረትና ሌላ ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ ወዲያው ነበር ሾለ ሀገር ጉዳይ የተነሳው።
“ኑሮ አንዴት ነው?.. እትዬ… አገር ቤት ” አልኩ ።
“…አየ… ልጄ .. ምን ኑሮ እንዴት ነው ትለኛለህ? …ወያኔው እንዴት አደረጋችሁ በለኝ እንጂ? …”
አነጋገራቸው ያስቃል። ሁላችንም ሳቅን። ሳቄን ገታ አደረኩና.. “ወያኔው ምን አደረገ?.. እስቲ ያለውን ነገር ያጫውቱኝ…” አልኩ።
“ከየቱ ጋ እንደምጀምርልህ አላውቅም ልጄ….ያላየነው ታሪክ የለም …በነዚህ ሰዎች ዘመን ያየነው ጉድ ብዙ ነው።”
“ ምን ጉድ አለባቸው?”
“ደግ ጠይቀኸኛል ልጄ…ምን ጉድ አለባቸው አልከኝ? …. ይሔውልህ እኔ ያንተ እናት… ሶስቱንም መንግስት በልቻለሁ።.. አንድ ነገር ልንገርህ ..ጃንሆይን ክፉ …አድሀሪ ስትሉ.. ክፉ መንግስት ስትሉ …ደርግ መጣና ክፉ መንግስት ምን አይነት እንደሆነ አሳየን.. ደርግን ክፉ ስንል ስንጠላ..ስንጠላ..እነዚህ መጡና የባሰ ክፉ መኖሩን አሳዩን..” ድንገት አቁዋረጥኳቸውና…
“የነዚህ ክፋት ምንድንው?”
“ደግ ብለሀል ልጄ… የነዚህ ክፋት.. ደርግ ወንበሬን ቀና ብላችሁ አትዩ ብሎ ነበር ያን ሁሉ ሰው የፈጀው፤…አማራ አላለም፤… ትግሬ አላም። እስላም ክርስትያን አላለም። ደርጉ ይል የነበረው፤ አገራችሁን ጠብቁ፤ ተስማምታችሁ አንድ ሆናችሁ ኑሩ፤ ወንበሬን ግን ቀና ብላችሁ አትዩ…”
ፊቴን ትኩር ብለው እያዩ
“..ያኔ እናንተም በየከተማው ጦርነት ከፈታችሁበት..እሱም ጦርነት ከፈተ…ያሁሉ በልቶ ያልጠገበ ልጅ አለቀ። ቀድሞውንም ያኔ ወይ ጫካ ሂዳችሁ በተዋጋችሁት ደግ… ወይ አርፋችሁ በተቀመጣችሁ… ያንን ሁሉ የልጅ ሏሳ አናይም ነበር..በኢሀፓ ጊዜ…”
“..እነዚህ መጡ …ያገሬ ሰው ተረተ። … ‘ምንሽር ልገዛ ወይፈኔን  ሳስማማ፤መጣ የትግሬ ልጅ በነጠላ ጫማ’… ገና ሲመጡ ጀምሮ የወደዳቸውም የለ… እግዚአብሄር ያመጣውን ፍርጃ መቀበል እንጂ  የሚደረግ የለም… መጡልህና ወንበራችንንም ቀና ብላችሁ እንዳታዩ፤ ለራሳችሁም እንዳትትያዩ… በየዘራችሁ ተበታተኑ አሉ። ለሁሉም በየዘሩ ማህበር አበጀለትና ሁልህም በዚህ ቀንበር ውስጥ ትገባለህ..ግባ አለው።”
“ማን ነው ያለው?’’
“ሟቹ…”
“አልገባም ያለ፤ እነሱን የሞገተ፤ የጥይት እራት ይሆን ጀመር። አንድም ሰው ጠመንጃ አንስቶ የተኮሰባቸው የለም። በያለበት ሰው መግደል ሆነ ስራቸው። አንዱን ካንዱ ማባላት፤ አሉባልታ ውሸት በራዲዮን፤ በቴሌቭዥን ሲነዙ መዋል ሆነ። እንዲህ እንዲህ አድርገው ሰዉን ሁሉ አደናግረው ሲያበቁ፤ አስፈራርተው ሲያበቁ፤… የራሳቸውን ሰው ሁሉ  ቦታቦታውን አስያዙ። ዛሬ ያለነሱ ነጋዴ የለም። ያለ እነሱ የቢሮ አለቃ የለም። ያለነሱ የቀበሌ አለቃ የለም። ያለ እነሱ ፎሊስ የለም። ሰው ሁሉ ሀሞቱ ፈሶ እነሱን እየፈራ መኖር የዟል። ….ወንዱም ሴቱም….ታዲያ ልጄ ደርጉ እንደዚህ ባይተዋር አድርጎናል?” አሉና በንዴት እራሳቸውን እየነቀነቁ ጠየቁኝ።
“ልማቱስ እትየ?…አገሩን አልምተዋል ይባል የለ እንዴ?”
“ሀሰት!.. ሀሰት ልጄ!…አገር ቢለማ፤ አገሬው ሁሉ ከነልጁ ለልመና ጎዳና ላይ ይፈስ ነበር?…ልማቱንስ ቢሆን እነሱ እንጂ ሌላው ሰው የታለ?..የታለ ጉራጌ ባለፎቅ ?..የታለ አማራ?..የታለ ኦሮሞ?….ያ ፎቅ የማነው ስትል… እነሱ….ያፎቅ የማነው ስትል እነሱ…..ልጄ ከየት አመጡት ያሰኛል እኮ? እነሱና አላሙዲ እንጂ ሀብታም አለ እንዴ ዛሬ?..”
“ዛሬ አንድ ሺህ ብር ይዘህ ገበያ ወተህ….. አንዲት ዘንቢል ሞልተህ አትመለስም እኮ!…ልማት ማለት ድህነትና እራብ ነው እንዴ?… ጦሙን የሚያድረው ህዝብ ተቆጥሮ አያልቅም እኮ…. እዚችው አዲስ አበባ…..”
“…ጭራሽ ጥጋባቸው… ቤት ዘግተው፤ ዊስኪ አውርደው ሲጨፍሩ የሚያድሩ እነሱ… ጠግበው በሽጉጥ ሲታኮሱ የሚያድሩ እነሱ… መጠጥ ቤት የፈለጋቸውን ደብድበው አድምተው የሚሄዱ እነሱ….”
“…የኛ ሰፈር መደዳውን ቡና ቤት ነው።…አንድ ቀን ጠዋት ወደ ክፍለ ሀገር አውቶብስ ተራ ልሄድ አስር ሰአት ተነስቼ ታክሲ ስጠብቅ….አንዲቷን ድሀ ጸጉሩዋን ይዞ መሬት ለመሬት እየጎተተ በግንባሯ ያዳፋታል፤ ከቡና ቤት አውጥቶ አስፋልት ላይ ይረግጣታል።..ኡ ኡ እያለች…ገደለኝ እያለች…ሊገላግላት የመጣ ወንድ ጠፋ። ሰው ሁሉ ሰምቶ እንዳልሰማ እየሆነ ብቅ አላለም። በስካር መንፈስ እንኳ እነዚህን ሰዎች የሚደፍር ጠፋ? አልኩና እንባዬን እርግፍ አድርጌ አለቀስኩ። ልጄ ድሮ ሴት ልጅ ድረሱልኝ ብላ ስትጮህ እንዲህ  ነበር እንዴ?..”
“..ወዲያውኑ አንድ ታክሲ ሲበር መጣ… አስቆምኩና ገብቼ… እንዳው ልጄ ይህን ሰውየ እላዩ ላይ ንዳበት!…ንዳበት!…ገደላት እኮ…ንዳበት! አልኩት። ለካንስ ያም ባለታክሲ የነሱ ሰው ኖሯል…አንዳንድ ደግ መቸም አለ…ሽርርር አደረገና መኪናዋን እላዩ ላይ  áŠ á‰áˆž፤ ወርዶ፤ እንደብራቅ ጮኸበት አልኩህ።ተጯጯሁ..ተጯጯሁ..ተሰዳደቡ፤ተሰዳደቡ..በግርግር እሷ እመር አለችልህና ደሟን እያዘራች ተነስታ አመለጠች…ያም ከባለታክሲው ጋር እየተሰዳደበ ወደ መሄጃየ አቀናን …”
“..ዛሬ አሁን የፈለገ ነገር ቢመጣ የአዲስ አበባ ሰው ቤት ለነሱ አያከራይም….”
“ለምን?” አልኩ።
“ለምን ማለት ደግ..ይኽውልህ ልጄ ቤት ታከራያቸው የለም?…ልቀቁ ስትል አይለቁም፤ …ወደየትም  áˆ„ደህ ከሰህ አታስለቅቃቸውም።…አንዲቷ እንዳደረገችኝ ልንገርህ..”  አሉና ፎቴው ላይ እየተመቻቹ፤ የተደረበላቸውን ብርድ ልብስ ወደላይ እየሰበሰቡ፤ “… እግዚአብሄር ብድሩን ይክፈላቸውና ልጆቼ ቤት ሰሩልኝ ብየህ አልነበር?…”
ውድ አንባቢያን ወደጨዋታችን መጀመሪያ ላይ ልጆቻቸው ቤት እንደሰሩላቸው ነግረውኝ  ነበር። አምስት ልጆች አሏቸው። ሁሉም በየአለሙ ተበትነው ይገኛሉ። ኖርዌይ፤ ጀርመን፤ አሜሪካ፤ካናዳ..እና ሁሉም እንደየአቅሙ አዋቶ አራት ዋና ዋና ክፍሎች ከየመኝታ ቤት ያላቸው ባለ አንድ ፎቅ ሰርተውላቸው ነበር። እሳቸው አሮጌው ቤት እየኖሩ ይህን ቤት አከራይተው በሚያገኙት ገቢ ስድስት የእህት የወንድም ልጅ ከገጠር አስመጥተው እያስተማሩ ያሳድጋሉ። እናም ልጆቻቸው እንደገና ገንዘብ እንስጥሽ ብለው እንዳይቸገሩ በማለት ለነሱ ያልነገሯቸው፤ ነገር ግን ከቤቱ ኪራይ ቆጥበው ምድር ቤት ባንዱ ክፍል ምግብና መጠጥ ሊነግዱ ሀሳብ አላቸው። ዛሬ ነገ እጀምራለሁ ሲሉ አንዱን ቤት አላከራዩትም ነበር። ኋላ ላይ ግን ለማከራየት ወሰኑ።
“…ቤት ሰሩልኝ ብየህ አልነበር?…ታዲያ ያችን አንዷን የቀረችውን ለአምስት ወርም ቢሆን ላከራይ አልኩልህና….አንዱ ደላላ አንዲቷን ወያኔ ሴት ይዞ መጣ። ቤቱ መንገድ ዳር ነው ለንግድ ይመቻል …አንባሻና ሻይ ቡና ልሸጥ ነው አለችኝ።…..አይ ልጄ እኔም እንዲህ፤ እንዲህ ላደርግ ሀሳብ አለኝ። …ባከራይሽም ለአምስት ለስድስት ወር ነው። ከፍተሽ የምትዘጊው ንግድ ምንም አያደርግልሽም። ሌላ ብትፈልጊ ይሻልሻል አልኳት።”
“…ሞቼ እገኛለሁ። ልቀቂ ባሉኝ ቀን እለቃለሁ። እንደው እትዬ..እትዬ..” አለች።
“ኮሎኔል ወንድም አላት አሉ። እሱ ነው ካገሯ ያስመጣት። ላገሩም እንግዳ ነች። አይ እንግዲህ እለቃለሁ ካለች ትግባ ብየ በሰው ፊት ተዋውለን ገባች።”
“እርግጥ ጎበዝ ሴት ናት። የኛ ሰፈር አላፊ  áŠ áŒá‹łáˆšá‹ ይበዛል። በጠዋት ተነስታ ቄጠማውን ጎዝጉዛ፤ አጫጭሳ፤ ቡናውን አቀራርባ፤ ሞቅ ሞቅ ስታደርገው፤  መንገደኛው ሁሉ ቁርሱን በልቶ ቡናውን ጠጥቶላት ወደየስራው ይሰማራል።”
“..እንዲህ እንዲህ እያለ ያች አምስት ወር ደረሰች። አይ ይች ሰው አሁን እንዲህ ገበያው ደርቶላት ልቀቂ ብላት ትቀየመኝ ይሆን? አልኩልህና እኔው ተጨንቄ አረፍኩት። …እሷም ቤት ልፈልግ አላለች፤ እኔም ትንሽ ትቋቋም ብየ ሶስት ወር ጨመርኩላት። ከዚያ በኋላ ደሞ ሶስት ወር አስቀድሜ ቤት እንድትፈልግ ነገርኳት። እሺ አለች። ወር አለፈ። ሁለተኛውም አለፈ። ሶስተኛው ተገባደደ። እየፈለኩ ነው ትላለች። ወሩ አለቀ። ቤቴን መልቀቅ የፈለገች አትመስልም። …በይ እንግዲህ ካጣሽ እኔው እፈልግልሻለሁ አልኩና ከኔ ቤት ወረድ ብሎ ሌላ አገኘሁላትና በይ በዚህ ወር  መጨረሻ ላይ ቤቱን እፈልገዋለሁ አልኳት። ወሩ ሲሞላ ደህና የነበረችው ሴትዮ ድንገት ተለዋወጠችብኝና አልወጣም ሂጂ ክሰሽ አትለኝ መሰለህ?…አበስኩ ገበርኩ…አልኩና ያዋዋሉንን ሰዎች ጠራሁና ይችን ሽፍታ ገላግሉኝ አልኩ። ጭቅጭቋን ቀጠለች። አንድ አስራ አምስት ቀን ስታምሰን ከረመች አልኩህ…በኋላ አንድ ቀን ጠዋት ወደዚሁ ቤት ስመጣ ሌሊት እቃ ታግዝ ነበር ሲሉኝ አምላክ በሰላም ሊገላግለኝ ነው አልኩና ገብቼ ቤቴን አየዋለሁ….ልጄ አፍርሳዋለች አልኩህ…ግርግዳውን ሁሉ ቧጣ፤ቧጣ ቧጣ…..እንደው ልጄ በምን ይሆን ስትቧጥጠው ያደረችው?…ሸንትራ፤ሸንትራ፤ ግርግዳውን ልጅ ያረሰው መጫወቻ ደጅ አስመስላዋለች። ሽንት ቤቱን ሰባብራ አግማምታ፤ አበስብሳው፤ የአንድ ወር የቤት ኪራይ ሳትከፍለኝ ኮተቷን ሰብስባ ውልቅ አለች። ክሰሻት አሉኝ። ማን ላይ ነው የምከሳት?…ጭራሽ አሸባሪ ትብየ እኔው ልታሰር?…”
የእናታችን ጨዋታ ፈርጀ ብዙ ነበር። አንዱን ጨርሰው ወደ ሌላው ሲያልፉ አንደበተ ርቱእነታቸውና ለዛቸው አፍ ያስከፍታል።
“..አንድ ጉድ ደሞ ላጫውትህ….ሾል አጥተው ችግርርርር ያላቸው አስር የሚሆኑ የሰፈራችን ወጣቶች ተሰበሰቡልህና ሾል ፈጠሩ። ምንድነው ስራው ብትለኝ…ሆቴል ቤቶች ሞልተዋል ብየሀለሁ ሰፈራችን….ከባለቤቶቹ ጋር ይነጋገሩልህና  በቀን ሶስት ጊዜ ቆሻሻ መድፋት፤ በቀን አንድ ጊዜ ግቢ መጥረግ፤ ይህን ለመስራት ተዋውለው ….ባለ ሆቴሎቹም ሁሉ ደስ ብሏቸው….ሲሰሊ የሚለብሱት ልብስም ገዝተውላቸው…ጋሪም ገዝተውላቸው ሾል ጀመሩ። የሰፈሩ ሰው ሁሉ ደስ አለው። ልጆቹ ገንዘብ አገኙ፤ እናትና አባታቸውን ማልበስ ለራሳቸውም ደህናደህና ነገር መልበስ ጀመሩ። ስራቸውንም እያስፋፉ በቁጥር አስራ አምስት ደርሰው፤ በሰላም ተረጋግተው በመስራት ላይ እንዳሉ፤ ህገ ወጥ ሾል ነው የምትሰሩት አቁሙ ይላቸዋል አንዱ…”
“ማን? “
“እዚያው ቀበሌ ውስጥ ….የምንትስ ሀላፊ ነው ያሉት ትግሬ…”
“ለምን አስቆማቸው?”
“ስራውን ቀበሌው ሊሰራው በእቅድ የያዘው ስለሆነ በቀበሌ ታቅፋችሁ ነው መስራት ያለባችሁ። ቀበሌ ለናንተ ይከፍላል። ግብር ለመንግስት መክፈል አለባችሁ፤ ፍቃድ ያስፈልጋችኋል….አለና አስቆማቸው። ልጆቹም ለምንድነው እኛ የፈጠርነውን ሾል የምንከለከለው ብለው ሲጨቃጨቁ ሁለቱን አስረው፤ የቀሩትን አስፈራርተው በተኗቸው።”
“…ትንሽ ቆየት ይሉልህና… ልጆቹን አደናግረው አስፈራርተው ከበተኗቸው በኋላ ያንኑ ሾል በቀበሌው የማይኖሩ የራሳቸውን ወጣቶች ሰብስበው ….”
“የራሳቸውን ወጣቶች ማለት?” አቋርጨ ጠየኩ።
“ትግሬዎቹን… ሰበሰቡና ከመጀመሪዎቹ ሁለቱን ቀላቅልው ሾሊ አሏቸው …እነዚያ ሁለቱ ደሞ ጓደኞቻችን ተባረው እኛ አንሰራም ብለው ትተውላቸው ሄዱ። ባለሆቴሎቹ ቀድሞ የሚያስጠርጉትን ልጆች ሲያጡ፤ ምንድነው  ነገሩ ብለው ቢያጠያይቁ፤ የመጀመሪያዎቹ ልጆች የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው። ባለሆቴሎቹም አደሙ ። ቆሻሻችንን እኛው እንደፋለን እንጂ አናስጠርግም አሉ። የተተኩትን ልጆች ሾል የለንም እያሉ መለሷቸው። ”
“ያ አለቃ ተብየው ቀበሌ ሰዉን ሰብስቦ አሉ… ጸረ ልማት ሀይሎች እያለ ሲሳደብ ከረመ አሉ። ባለ ሆቴሎቹም እንዳደሙ ቀሩ። ሗላ ላይ ሥሰማ በመጀመሪያ ያጸዱላቸው የነበሩትን ልጆች ሁሉንም ተከፋፍለው ቀጠሯቸው አሉ። እነዚያም ጋሪያቸውንና ጓዛቸውን ይዘው ወዴት እንደሄዱ አላውቅም እልሀለሁ …..ልጄ..ወያኔ እንዲህ እያመሰን ነው እልሀለሁ…..” እንደ መተከዝ አይኖቻቸውን ወለሉ ላይ ተክለው ለአፍታ ዝምም አሉ።
ውድ አንባቢያን የህብረተሰብ ደህንነት የሚረጋገጠው፤ እያንዳንዱ ክፍለ ህዝብ ከህዳጣን እስከ ብዙሀን ምልአተ ህዝቡን የገነቡ ብሄረሰቦች ሁሉ እኩል መብትና ነጻነት ሲኖራቸው፤ በሀገራቸው እኩል የባለቤትነት ስሜት ሲኖራቸው፤አንባ ገነንም ይሁን ዲሞክራሲያዊ ..ያለውን መንግስት የኛ ነው ሲሉት፤ በባህላቸው፤ በቋንቋቸው፤ በሀይማኖታቸው፤ የተነሳ ምንም አይነት መገፋት እንደሌለ ሲያረጋግጡ ዜጎች ደህንነት ይሰማቸዋል።
የናታችንን ጨዋታ ለማጫር ይችን ጥያቄ ጣል አደረኩ።
“ወያኔ..ወያኔ ይባላል… ኢህአደግ ነው መባል ያለበት… አይደለም እትየ?”
ከት አሉና ሳቁ ። ሳቃቸው አስቆን ሁላችንም ፍንድት አለን።
“አየህ ልጄ…በቆሎ እሸት ታውቃለህ አይደል?..በቆሎ እሸት..” አሉ እጃቸውን ቀና ቀጥ አድርገው፤ “..በቆሎ እሸት የምትሸለቅቀው ልባሱ አለ። ያ ልባሱ ገለባ ነው። ይጣላል። ዋናው በቆሎው ነው። ፍሬው። እነዚህ ኢህአደግ  ያልካቸው ገለባ ናቸው (ሶስቱን የወያኔ ፍጡራን ድርጅቶች ማለታቸው ነው፡ ኦህዴድ፤ ብአዴን….) ዋናዎቹ ትግሬዎቹ ናቸው። ገባህ ልጄ…”
በአዎንታ ራሴን ነቀነኩ።
“..የአማራው ነን፤ የኦሮሞው ነን፤ ማነው ይሄ ደሞ የበየነ ጴጥሮስ አገር…ብቻ ሁሉም ከነሱ ጋር ያሉት ገለባዎቹ አሽከሮቻቸው ናቸው። ማፈሪያዎች ናቸው፤…..እንዳይመስልህ ልጄ…ጌቶቹ ትግሬዎቹ ናቸው፤….የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም እነዚህ ኢህአደግ ያልካቸው ከምንም አያስጥሉንም……”
ውድ አንባቢያን ያለፈ አንድ አመት አካባቢ አንዲት ሌላ እናት እንዲሁ መተው ለመጠየቅ ሄጄ ዘጠና በመቶ ማለት ይቻላል ተመሳሳይ አይነት ጨዋታ አጫውተውኝ ነበር። ካንድ ሰው ብቻ የተገኘ ኢንፎርሜሽን ለሌላው ማስተላለፍ ያስቸግራል፡፡ ሁለት ይማይተዋወቁ ሰዎች፤ የተለያየ አካባቢ የሚኖሩ፤ በተለያየ ጊዜ አንድ አይነት ነገር ከተናገሩ እውነትነት ያለው ጉዳይ አለ ማለት ነው።
ይህ ስርአት መለወጥ እንዳለበት ዜጎች ይስማማሉ። ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚታሰብ ነገር አልሆነም።  እንዴት ነው እነዚህን ሰዎች ከስልጣን የምናስወግደው ነው ጥያቄው፤ መላ መምታት የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታና ፈንታ ነው። እናታችንን ጠይቄአቸው ነበር።
“ይህንን መንግስት ለመለወጥ ምን ቢደረግ የሚበጅ ይመስሎታል እትየ?”
“መተኮስ….መተኮስ ነዋ!…እነሱ ተኩሰው አይደል ለዚህ የበቁት?…..ግን እኮ ልጄ… ወንዱ ሁሉ ሀሞቱ ፈሰሰ…በጥቁር አህያ ነው አሉ ያስደገሙብን…የሱዳን መተት ቀላል እንዳይመስልህ ልጄ…ሱዳን አልነበረ የሚኖሩት…ያኔ አሉ…. ሲገቡ፤ ሕዝቡ ሁሉ እንዲፈዝላቸው……ወንዱ ሁሉ ወኔው እንዲሰለብ…. በጥቁር አህያ አድርገው አስደግመው ገቡ አሉ። ይኸው ሀያሁለት አመት….አገር መሬቱን ሲሸጡ፤ እስላም ክርስቲያኑን ሲያምሱ፤ ሲገሉ ….ቤት ሲያፈርሱ.. ንብረት ሲቀሙ…ማን ወንድ ሸፍቶ አስደነገጣቸው?…..ሀያ ሁለት አመት…ሀያ ሁለት ዓመት… መተኮስ … መተኮስ ነው ልጄ…”  lkebede10@gmail.com

ለዚች አገር የሚገባት እውን ይሄ ነውን !!!!!

yared elias
(nome telemark dagsrud)
ዘረኛው ወያኔ አገዛዝ መንግስት ስልጣን ከያዘበት ግዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ድረስ እየሰራ ያለው ነገር በውነት ከሌላ አገር  áŠ˘á‰ľá‹ŽáŒľá‹ŤáŠ• ቅኝ ግዛት ለመያዝ የመጡ ሰዎች እንጂ እውነት ኢትዮጵያኖች ናቸው ለማለት እያጠራጠረ መጥቷል።
ሃገራችን ኢትዮጵያ አውን በምትገኝበት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ምስቅልቅል የፖለቲካው ነጸብራቅ መሆኑን ማንም ሊመሰክር ይችላል áˆˆá‹šáˆáˆ áŠ áŠ•á‹ą ማሳያ ከፍተኛ የሆነ የዜጎች ስደት ነው።ከሁለት ዓመት በፊት ጋሎፕ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት መሰረት የኢትዮጵያ ዜጎች ለኑሮ የማይመርጧት ሃገር እንደሆነች ተዘግቧል። ጥናቱ እንዳመለከተው ከሆነ እድሉን ካገኙ፣46 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደውጭ የመውጣት ፍላጎት አላቸው ።ያው ይሄን ያደረገው ?
ይገርማል ግን! ኢትዮጵያዊያንን ከአገራቸው ያውም ወደ አረብ አገራት ያለምንም ማስተማመኛ በዓመት 500 000 ያውም ሳውዲ ዓረቢያ ብቻ  á‹˛á–áˆ­á‰ľ ያደርጋሉ ያው ዲፖርት ማለት አደለምን ። áŠ¨á‹›áˆ› ስለነሱ ማን ይጠይቃል እንዲህ እያለ የወያኔ ጠባብ ብሄርተኛ ዘረኛው á“áˆ­á‰˛ ለተከታታይ ዓመታት ባለሁለት አሀዝ ኢኮኖሚዊ ዕድገት እንደተመዘገበ፣ ድህነት በገጠርና በከተማ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸነፈ መምጣቱን እየነገረን ይገኛል፡፡ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመጨረሻ የትግበራ ዓመት ከድህነት በታች የሚገኙ ዜጎች 22 በመቶ ብቻ እንደሚሆን ተነግሮናል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ በሆኑ ችግሮች ውስጥ ተተብትባ ትገኛለች፡፡ ገዥው ፓርቲ በሚያራምዳቸው ጠርዝ የያዙና ስልጣንን ከሀገር ጥቅም በፊት የሚያስቀድሙ አመለካከቶችና አሰራሮች ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል፡፡ አገዛዙ የሚከተላችው ጥራዝ ነጠቅና የዜጎችን ጥቅም ያላማከለ አካሄድ ሀገርን እየጎዳ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ፖሊሲዎች አንዱ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ዘላቂ የሀገርን ጥቅም ባላገናዘበ  áˆ˜áˆáŠŠ ለባዕዳን የመስጠት ጉዳይ ነው፡፡መንግስት ልሹ ባቀረበው መረጃ መሠረት ከ380 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች  áˆ˜áˆ°áŒ á‰ąáŠ• ተገልጿዋል፡፡ የአዲስ አባባን 54 ሺ ሄክታር የቆዳ ስፋት በግምት ውስጥ ስናስገባ፣ ኢህአዴግ  áˆˆá‹áŒ­ ባለሃብቶች የሰጠው መሬት የመዲናችንን ሰባት እጥፍ በላይ ነው፡፡ መንግስት የፊሊፒንስን ቆዳ  áˆľá‹á‰ľ የሚያክል መሬት (3 ሚሊየን ሄክታር) ለውጭ ባለሃብቶች ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን  áŠĽáŠ•á‹°áŒˆáˆˆá€ ይታወቃል፡፡  á‰ áŒ‹áŠ•á‰¤áˆ‹ ክልል ብቻ 1.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለሰፋፊ እርሻ እንደተዘጋጀ መንግስት ገልጸዋል፡፡ ይህ ማለት ከጋንቤላ አጠቃላይ ስፋት 37 በመቶ በላይ መሬት በእርሻ ኢንቨስትመንት ስም ለውጭ ባለሃቶች  áˆˆáˆ˜áˆľáŒ á‰ľ ኢህአዴግ እየሰራ ነው፡፡ ለዚሁ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ ኢህአዴግ በጋንቤላ ሰፊ የሰፈራ ፕሮግራም
 áŠĽá‹ŤáŠŤáˆ„á‹° ይገኛል።
ይቀጥልና ዘረኛው ወያኔ መንግስት ይሄ አስመሳይ በሃሪውን ቀየሮ ለስልጣን መቆያ ይሆነው ዘንድ በሃይማኖት በኩል ዞሮ መጥቶ በተለይ በመላው ኢትዮጵያ መስኪዶች ስፍር ቁጥር የሌለው ህዝብ በአይነቱ የተለየ እና ግዙፍ ተቃውሞ ያደረገ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብም ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መንግስት በሙስሊሙ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ እንግልት በሃይማኖቱ ላይ የሚያደርገውን ግልጽ ጣልቃ ገብነትና እንዲሁም የህዝብ ሙስሊሙ ተወካዮች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን ንቀት የተሞላበት ከፍተኛ ስቃይ እና አምባገነናዊ ተግባር እረ እስከ መቼ ነው የሚጠበቀው ? ምንስ ነው ዝም ያስባለው ብዬ ሳስብ á‰ áŠ áŠ•á‹ľ ወቅት  áŠ áŠ•á‹ľ ተናጋሪ á‰Łá‹°áˆ¨áŒ‰á‰ľ ንግግር ላይ የተናገሩት ነገር ትዝ አለኝ ለካስ ትክክል ነበር ለማለት ወደድኩ  " አገር ቤት ውስጥ ያለው ህዝብ ሁሉንም ነገር ሰለለመደው ለሹ አዲስ ነገር አደለም  á‹¨áŠáŒťáŠá‰ľáŠ• ትንፋሽ የሚባለውን አያውቅም ምክንያቱም አንድ ትልቅ ነገር ሲነሳ ለዛ ለተነሳው ነገር አንድ ሳምንት ሆይ ሆይ ይልና ወዲያው ይለምደዋል" ሌላም እንድህዚሁ አይነት ሲገጥም ለአንድ ወር ያህል ሰው ያለቅሳል ያዝናል ወዲያውም ይለምደዋል ስለዚህ ምንም አይነት ነገር ይፈጠር ነጻነት የምትባለዋን ነገር እንዳለችው ባለችው ነገር ላይ ተላምዶዋት ቍጭ ብሏል ነገር ግን የነጻነት ትንፋሽን የሚያውቀው ያው ወደውጭ አገር ወጥቶ የነጻነትን ትንፋሽ አጣጥሞ ወደ አገር ቤት á‹¨áˆšáŒˆá‰Łá‹ ሰው ብቻ ነው እንደገባም የህዝቡ á‹¨áŠáŒťáŠá‰ľ ትንፋሹ በትንሽና ጠባብ ብሄርተኛ ዘረኛ ወረኛ መንግስት ታግቶ ሲያይ ምንኛ እንደሚያሳዝን ያሳያል ።
ይህው እንዳየነው ሙስሊሙ ህብረተሰብ በቤታቸው እንኳን ቍጭ ማለት እንዳልቻሉ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ይገኛሉ በአንድ ቴሌቪዠን ለ80_90 ሚልዮን ህዝብ ማስፈራሪያ ይነገረዋል አልፎ ተርፎ የ 1000 አመት ታሪክ ያላቸውን እነዛ ተከባብረው የሚኖሩ አጥር ብቻ የሚለያቸው ሁለቱ ወንድማማቾቹን ሙስሊምና ክርስትያኑን ሊያባሉ ስንት ይዘይዳሉ ። ለነገሩ ነው እንጂ ማን ይሰማቸዋል። ንጹህ የነጻነት ትንፋሽ እንዲተነፍስ እናድርገው ።
እግዚሃብሄር  áŠ˘á‰ľá‹ŽáŒľá‹Ť ይባርክ!!



Mar 6, 2013

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ

የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (http://www.goolgule.com/)
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።Gambella
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።
ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።
አቶ ኡሞት በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነትም አላቸው። ኢህአዴግ ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ በክልሉ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ አጥብቀው በግልጽ የሚቃወሙ ሰው መሆናቸውን የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አቶ ኡሞት ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ህዝብን የሚያስተባብሩና ለዓመጽ የሚያነሳሱ ናቸው በሚል ኢህአዴግ ቢወነጅላቸውም ውንጀላውን በማስረጃ ማቅረብ እንደማይችል እነዚሁ ክፍሎች ይገልጻሉ። ስለተፈጸመው ግፍ የተሞላበት ግድያና ከግድያው በኋላ ስለተከናወነው “አረመኔያዊ የእንስሳ ተግባር” ሲያስረዱ በቁጣ ነው።
በተጠቀሰው ቀን ቤተሰቦቻቸውን ቀበሌያቸው ድረስ በመሄድ በመግረፍና በማስፈራራት ወደ አብሌን ለከበባ በጠቋሚ የመጡት የመከላከያ አባላት ሰዎቹን እንደተመለከቱ ተኩስ ከፈቱ። በድንገት የተከበቡትና ዛፍ ሼር ተቀምጠው የነበሩት አንዳችም ጥያቄ ሳይቀርብላቸው በጥይት የተደበደቡት ሰዎች የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል ቢያደርጉም አልሆነም። ተደራጅቶ በሶስት የወታደር ካሚዮን ከባድ መሳሪያ ታጥቆ የመጣው ሰራዊት ጨፈጨፋቸው። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደተናገሩት ወዲያው ህይወታቸው ካለፈው ስድስት ንጹሃን መካከል አቶ ኡሞት መሞታቸው ሲታወቅ የሰራዊቱ አባላት አውካኩ፤ በደስታ ጨፈሩ። አስከሬኑንን ጭነው ፉኙዶ ወደሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በመሄድ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ደስታቸውን አበሰሩ።
አስከሬን በመኪና በመጫን ከተማ እየዞሩ ደስታቸውን ገለጹ። በማግስቱ በጋምቤላ ከተማ ስታዲየም አስከሬኑን ህዝብ እንዲመለከተው ታዘዘ። ህዝብ ስታዲየም ተገኝቶ የአቶ ኡሞትን አስከሬን እንዲሳለም፣ ኢንቨስተሮችም ያለስጋት የመሬት ነጠቃቸውንና “ልማታቸውን እንዲቀጥሉ”፣ መሞታቸውን አይቶ ሕዝቡ እንዲያምንና ሞራሉ እንዲጎዳ የተላለፈው ውሳኔ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተስተጓጎለ። ለጎልጉል መረጃውን ያስተላለፉ እንዳሉት አቶ ኡሞት አሜሪካዊ መሆናቸው ሲታወቅ ማዕከላዊ መንግስት ከአዲስ አበባ አስቸኳይ ትዕዛዝ አስተላለፈ። አስከሬኑን ባስቸኳይ እንዲቀብሩ መመሪያ ሰጡ። ሁሉም ነገር በመመሪያው መሰረት ተጠናቀቀ። የአቶ ኡሞት አስከሬን ባልታወቀ ቦታ ተቀበረ። አስከሬኑንን ለማየት በግዳጅ ተሰባሰበው ህዝብም ምንም ነገር ሳይመለከት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ሁኔታውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመረጋጋት የኢህአዴግ ሠራዊት በጎክ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የጋምቤላ ተወላጆች በተለይም ወንዶችን እያሠሩና እያሰቃዩ እንደሆነ ከሥፍራው የደረሰን ዜና ያረጋግጣል፡፡
የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት ጉዳዩን ለአሜሪካ መንግስት እንዳሳወቀና የአሜሪካ መንግስት ጉዳዩን ከስር መሰረቱ ጀምሮ እንደሚመረምረውና እስከ መጨረሻው የመንግሥት አካል እንደሚደርሱ ማረጋገጡ ታውቋል። ኢህአዴግ አቶ ኡሞትን የገደለበትን ምክንያት በማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅበትም አስታውቀዋል። አቶ ኡሞት የሚጠረጠሩበት ድርጊት እንኳን ቢኖር በቁጥጥር ሾር አውሎ በህግ መጠየቅ እየተቻለ እንዲገደሉ መደረጋቸው ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ የሚከራከሩላቸውና ጉዳያቸውን ይፋ ያደረጉት ክፍሎች ይናገራሉ።
በወቅቱ ህይወታቸው ያለፈው ንጹሃንና የደረሱበት ያልታወቀው ሰዎች ስም ዝርዝር ከስፍራው የደረሰን ሲሆን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
  1. ጎጎ ኦቻላ
  2. ቻም ኦቻላ
  3. ዑከች አቻው
  4. አኳይ ኦሞት
  5. ኦሞት ኦባንግ
  6. አጂባ አኳይ
  7. ኦሞት ኡጁሉ ኦጎታ
  8. አንበሳው ኡጁሉ
  9. ቱወል ኦሎክ
  10. ኦችዋል ኦባንግ
  11. ኦዋር ቻም
  12. ኒሙሉ አጎሌ
  13. አብራች ኒሙሉ
  14. አኩኔ ኦሞት
  15. አግዋ ቻም
  16. ኦዋር ኒግዎ አጋክ
  17. ኦሞት ኡዶል (አሜሪካዊው)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውሳኔ ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው ተባለ


በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረን ግጭት ተከትሎ 10 የኦሮሞ ተወላጆች ከትምህርታቸው እንዲታገዱ መደረጋቸውን የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብዓዊ መብት ሊግ አጥብቆ ያወገዘው ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ውሳኔም ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው ብሎታል።
የሰብዓዊ መብት ሊጉ ከትምርታቸው የታገዱትን ተማሪዎች ፎቶ አስደግፎ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው የታገዱት የመጀመሪያ ሴሚስተር ፈተናቸውን አጠናቅቀው የሁለት ሳምንት እረፍት ወስደው ከተመለሱ በሁዋላ ነው ብሏል።
ሊጉ ከውስጥ የደረሱትን መረጃዎች ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው ይህ በግልጽ ፖለቲካዊ የሆነውና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረው ውሳኔ የተላለፈው “ዲሲፕሊን ኮሚቴ” ተብሎ በሚጠራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አካል ሲሆን፤ኮሚቴው ለዚህ ውሳኔ ምክንያት የሆነውም ባለፈው ጥር ወር በኦሮሞና በትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ነው።
በሁለቱ ብሔረሰብ ተወላጆች መካከል ግጭቱ ሊፈጠር የቻለውም ጥቂት የትግራይ ተወላጆች የኦሮሞ ብሄረሰብን አስመልክቶ ተገቢ ያልሆነና ቆስቋሽ ጽሁፍ ጽፈው በመለጠፋቸው ምክንያት እንደሆነ ማረጋገጡን ሊጉ አውስቷል።
ይህን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ በግጭቱ ሳቢያ ከ10 በሚበልጡ ተማሪዎች ላይ የ እስራት፣የግርፋትና የድብደባ እርምጃ መወሰዱን፤ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ የ ኦሮሞ ተወላጆች እንደሆኑ ይፋ ማድረጉንም ሊጉ አስታውሷል።
በግጭቱ ምክንያት ከትምህርታቸው እንዲታገዱ የተደረጉት አስሩም ተማሪዎች ኦሮሞዎች መሆናቸውን እና ከመካከላቸው አንዷ ሴት መሆኗን ያመለከተው ሊጉ፤ ሁሉም ለአንድ ወር ያህል ታስረው በዋስ ከተለቀቁ በሁዋላ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው እንደነበር ጠቅሷል።
ከትምህርታቸው የታገዱት የኦሮሞ ተማሪዎች ከወለጋ ነቀምት የመጣው የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ታደለ ታረቀኝ፣ ከደቡብ ሸዋ ኦሮሚያ የመጣው የ3ኛ ዓመት ተማሪ አበጀ ቱጂ ጫላ፣ የ4ኛ ዓመቱ ተማሪ ገመቹ ደለቶ ዳፎ፣ የ 4ኛ ዓመት ተማሪ መልካሙ ሙሉጌታ፣ የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ፈቃዱ መሰል፣ የ4ኛ ዓመቷ ሴት ተማሪ አዲስ ጋቴራ ያደሳ፣የ 4ኛ ዓመቱ ተማሪ በቃሉ ስዩም ተሻለ፣ የ3ኛ ዓመቱ ተማሪ ቀጀላ አድማሱ ደሬሳ፣የ 2ኛ ኣመት ተማሪው ኢሳያስ ኢታና እና የ 4ኛ ዓመት ተማሪው አራርሳ ዋቅቶላ ኦልጅራ መሆናቸው ይታወሳል።
ግጭቱን ከቀሰቀሱትም ሆነ በግጭቱ ከተሳተፉት የትግራይ ተወላጆች አንድም ተማሪ ላይ እርምጃ አለመወሰዱ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተብየውን ውሳኔ በግልጽ ፖለቲካዊና ዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ያሳያል ሲል የሰብዓዊ መብት ሊጉ አመልክቷል።
ይህ ውሳኔ ከሰብዓዊ መብት ሊጉ ባሻገር ብዙዎችን ያስገረመ እና ጥቂት በማይባሉም ታዛቢዎች ዘንድ፦ “በ እርግጥም ይህች አገር የማናት?” የሚልን ጥያቄ ያጫረ ሆኗል።

Mar 3, 2013

ተጋዳላይ ማትያስ ሹመት ያዳብር!

click here for pdf
እንዳይነቀሳቀስ አጁን በስንሰለት ጠፍረህ አሰረኸው፡
ሽጉጥክን ደግነህ ተናዘዝ ብትለው፡
በእምነቴ አትምጣ ከፈለክ ያውልህ ደረቴን ለጥይት፡
ከቶ አልበገርም በባዶ ድራማ አድማጭ የለሽ ተረት፡
ሞቴን ከነምነቴ ብሎ በመጽናቱ ግራ የተጋባህ፡
ደንባራ ወያኔ ፊልም መቆራረጥ መቀጣጠል ገባህ፡፡
አንተ አቡ በከር አንድ ጎኔን ሞቀው በጣም አኮራኸኝ ፡
አኩል አልሞቅ አለኝ አንዱ ጎኔ ሳስቶ ክፉኛ በረደኝ ።
እንኳንስ ተከታይ፤ አስተማሪው ካህን መነኩሴው ጳጳሱ፡
ለምነት አልቆም አለ አሳሳችው ነፍሱ።
ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መሆኗ ቀረና የእምነት ማህደር፡
ታጋይ ተፈራርቆ ይሾምባት ጀመር።
የሃይማኖት መሪ በግዜር ይመረጣል ተብይ አድጌ፡
አገር በጾም ጸሎት ትጸናለች ሲባል ተምሬ አድጌ፤
ታጋይ ጳጳስ ሲሆን ስተቱ የማን ነው? መልስ አጣሁ ፈልጌ።
በመርዝ በጥይት ወገኑን ጨርሶ የመጣ ሹመኛ ደብሩን ቢረከበው፡
እግዜር የሾመው ነው በሚል አጉል ባህል መስቀል ልሳለም ነው?
ወይስ
አንተ እርኩስ መንፈስ ተጣልቼሃለሁ፡
መስቀልህ ይቅርብኝ ቤቴ ጸልያለሁ፡
ገንዘቤም በኪሴ ለምን ጦርሃለሁ፡
ብዬ ላሳርፈው?
ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን የምትሆነው ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው የሃይማኖት መሪ ሲኖራት እንጂ የፖለቲካ ስልጣን በተቆጣጠሩ ባለስልጣናት የሚሾም ካድሬ ቁጥጥር ሾር ሆና አደለም ፡ ስለዚህ ለተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ ማስተላለፍ የምፈልገው ምልእክት፡ ስርዓት እሰኪከበር ድረስ ጸሎታችሁን በቤታችሁ ገንዘባችሁን በኪሳችሁ እንድታረጉት እንዲሆን ነው፡ በገዛ ገንዘባችሁ ወያኔን የምታዳብሩበት ምክንያት አይኖርም፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
እስከ ነጻነት

Total Pageviews

Translate