Pages

Jun 26, 2013

“መቶ ሚልዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፤ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ሲያስፈራሩት ይታያሉ” – ስብሃት ነጋ (አዲስ ቃለ-ምልልስ)

(በቀጣይ ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ያቀረብነው ቃለ ምልልስ አቶ ስብሃት ነጋ ሰንደቅ ለሚባለው ጋዜጣ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ነው።
ቃለ ምልልሱ ዛሬ በኢትዮጵያ በታተመው ጋዜጣ ላይ ታትሞ ተሰራጭቷል። ጥያቄዎቹ በሰሞናዊዎቹ በሙስና እና በአባይ ጉዳይያተኩራሉ። ለግንዛቤዎ በሚል እንደወረደ አቅርበነዋል”")ሰንደቅ፡- ባለፉት ስርዓቶች ሙስና እንደ አሁኑ ብዙ ጫጫታአይሰማበትም ነበር። ለምን አሁን?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ትክክል ነህ። ምክንያቱም በፊውዳሉ ስርዓትመሬቱም ጉልበቱም የባላባቶቹ ንብረት ስለነበረ ቀጣፊ የሚባለውጭሰኛ ነበር። “ቅጥፈቱም” ለባላባቶች ከሚያርሰው መሬት ትንሽለሆዱ የሚሆን በቆሎ ከዘራበት ለምን ቦሎቄ አልዘራህም ተብሎበቦሎቄ ሂሳብ ይቀጣል። የመንግስት ሰራተኛ የመንግስት ገንዘብከሰረቀ ግን ጐደለበት ነበር የሚባለው። በደርጉ ቢሮክራቲክሶሻሊዝም ስርዓትም ቢሆን የከተማ ንብረት በመሉ በእጁ ስለነበረ የተገኘችው እንደፈለገ ነበር፤ ለራሱም ለቤተሰቦቹምሲጠቀምበት የነበረው። ስለዚህ ሁለቱም ሃብት ፈጣሪዎችም አልነበሩም የተፈጠረው ሃብትም በመሰረቱ የራሳቸው ነበር። አሁንበመንግስትም በገበሬም በግሉ ባለሀብትም በፍጥነት ሃብት እየተፈጠረ እያለ ከስርዓቱ ጋር የማይሄድ ሙስና እያጋጠመ ነው።ሰንደቅ፡- በባህርዳር በተካሄደው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ በኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ ዘመቻ እንዲከፈት ለጉባኤው ጥሪ አቅርበውነበር። ጥሪውን ለማቅረብ የነበረዎት መነሻ ምን ነበር?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ኪራይ ሰብሳቢነት የስርዓታችን አደጋ ነው ተብሎ በትክክል የተቀመጠው ገና ኢህአዴግ ስራ ሲጀምር ነው።ስለዚህ ሙስና ያለቅጥ እየተስፋፋና አደጋ እያደረሰ ሲሄድ ጠ/ሚ/መለስም፤ ጠ/ሚ/ሃይለማርያምም፤ የኢህአደግ ጽ/ቤትኃላፊው አቶ ሬድዋንም፣ ተራው ህዝብም በየመንገዱ በየመስርያ ቤቱ ለአመታት ሲጮሁበት የነበረ ጉዳይ ነው። እኔም እንደሌሎቹ ነው ስለሙስና የተናገርኩት እንጂ የተለየ ነገር የለውም። የተለየ ካለው ሙስና ከውጭ ወራሪ ኃይል የከፋ ጠላት ነውናሙስና የተወራበት ቦታ ካለ የሚመለከታቸው አካላት ለደቂቃም ሳይዘገዩ ማጣራት ግዴታቸው ነው፤ ስል አሳስቤአለሁ።ሰንደቅ፡- አሁንበሀገሪቷ ውስጥ ያለውን አደጋስ እንዴት ያዩታል?አቶ ስብሀት ነጋ፡- በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ሙስና ጠቅላላ የሀገሩና የኀብረተሰቡን ህይወት ወደ ከፍተኛ ምስቅልቅል የሚመራተግባር ነው። በመንግስት፤ በግልና በገበሬው የሚካሄደው ልማት ተገቢውን ውጤት ሳያመጣ ሊቀር ይችላል። በሙስና ምክንያትበመንግስት የሚፈፀሙ እቅዶች በተገቢው ወጪ፤ በተፈላጊው ጥራትና ጊዜ እንደማይፈፀም የአደባባይ ሚስጢር ነው። በዚህ ጉዳይምን ያህል ጉዳት ደረሰ በጥናትና በምርመራ ነው የሚታወቀው። መንግስት የተቀናጀ ሁሉም ዓይነት ድጋፍ በመስጠት በሁሉምየኢኮኖሚ ዘርፎች ልማታዊ የግል ባለሀብት እፈጥራለሁ ነበር ያለው። አሁን በየሴክተሩ ያለው ባለሀብት እውነት የኢትዮጵያንኢኮኖሚ በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል አቅም አለው ወይ ብለን ብንጠይቅ፣ መልሱ አሉታዊ ነው ሊሆንየሚችለው። ጥገኛውን በተቀናጀ ጫና እያዳከምን አቅመ-ቢስ እናደርገዋለን፤ ያልነውስ የት ደረሰ ብለን ብንጠይቅስ መልሱምንድነው? ጥገኛው እየበረታ ልማታዊው ሳይፈጠር የቀረበት ሁኔታ ውስጥ ያለን እንዳንሆን መገመት፤ ከግምት ወጥተንምመገምገም የሚጠይቀን ይሆናል።ሙስና በልማት ብቻ ሳይሆን በመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ግንባታ ላይም የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ ነው። ህገመንግስትን በመጣስ የላይኛው የታችኛውን ኃላፊ እያዘዘ ለዚህ አድርግለት፤ ለዚያኛውም ቀማው፤ እሰረው የሚል አለ። ስልጣንየሚቀማው ለኢኮኖሚው /ሙስና/ ጥቅሙ ነው። ስልጣን እየተቀማ ያለውም በዚያች ወንበር ተቀምጦ ለመቆየትና ትርፍራፊአገኛለሁ ብሎ በማሰብ ነው። በወንበሩ ላይ እስካለ ድረስ ጥቅም ያገኛል። ስልጣን በመንጠቅ በመነጠቅ የሚፈፀም እንዳልሆነከፓለቲካዊ ድርጅት ፈንጠር ብለው የድርጅቶችን አባልነታቸው ስም በመጠቀም የራሳቸው ህገ ወጥ ሰንሰለት ፈጥረው ሊዘርፉሊያዘርፉ የሚኖሩ ግለሰቦችም የተፈጠሩ ይመስለኛል። ፈንጠር ማለቴ በኔትወርክ ማለቴ ነው። ስለዚህ በመንግስትም በፖለቲካዊድርጅቶችም ለስርቆት ተቋማዊ አሰራር ከተጀመረ አደጋ ነው።የሙስና አደጋ በልማትና በዲሞክራሲ የሚያመጣው አደጋ ብቻ ሳይሆን በሃገር ፀጥታና በሰው ልጆች የሚያመጣው የስነ አእምሮጫናና ስጋትም ጭምር ነው። ሌባ የሰላም ሃይል አይደለም። ለውጭ ጠላትና ለሃገር ውስጥ ፀረ ህዝብ ተገዢ ነው። በልማታዊናበፀረ ሙስና ሃይሎች የማይተኛ ፈሪ ጨካኝና ፈጣን አራዊት ነው፤ ሙሰኛ።በመሰረቱ በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፤ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፤ የመንግስት ሰዎችነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚልዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፤ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡትሲያስፈራሩት ይታያሉ ይባላል። ጠቅለል አድርገን ስናየው አሁን ያለው የአንዳንድ የመንግስት፤ የፓርቲና የግል ባለሃብቶችከኢህአደግ መንግስት ስርዓት ፈፅሞ የማይሄድ ፀረ-ልማት፣ ፀረ ዴሞክራሲና ፀረ ሠላም እየሆኑ በመጓዝ ላይ ነው ያሉት።ሙሰኝነት ከኢህአዴግ ስርዓት አኳያ ስናየው ከውጭ ወራሪ ኃይል እጅጉን የከፋ ጠላት ነው። ድንበር የተሻገረ ጠላት ጊዜየሚሰጥና በሁለተኛ ደረጃ የሚታይ አደጋ ነው። ስለዚህም ዋናው አደጋ የውጭ ጠላት ሳይሆን በስርዓቱ የሚደርስ አደጋ ነው።የስርዓቱ ባለቤቶችና ስልጣን እየተረከቡ የሚሄድት ልማታዊ ባለሃብት እና ወዝአደሩ ሳይፈጠሩ እየቀሩ፣ ስርዓቱ እንደ ሌሎቹየአፍሪካ አገሮች የጥገኛው ባለሃብትና የቢሮክራቱ ስርዓት ይሆናል።ሰንደቅ፡- ይህ ስርዓት በኪራይ ሰብሳቢዎች የመጠለፍ አደጋ ይገጥመዋል ብለው ይሰጋሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡-ያለውንየሙስና ሁኔታ የሚመጥን እርምጃካልተወሰደ ስርዓቱ ያለምንም ጥርጥር አደጋ ይገጥመዋል።አደጋውም በልማታዊነት ዴሞክራሲያዊነት ብቻ ላይ አያበቃም።ሰላም በውስጥም ከውጭም አይኖርም። ይህ ሲከሰት ደግሞየሰላም የልማት የዴሞክራሲ ተምሳሌት የተባልነውን ያህል ወደድሮ አሳፋሪ ስማችን እንመለሳለን።ሰንደቅ፡- ሙስናን ለመታገል በመንግስት በኩል የፖለቲካቁርጠኝነት ነበር ብለው ያምናሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- የሙስና መጀመርና እየተስፋፋ መሄድ ከአስርዓመታት በላይ ሲነገርለት የነበረ ጉዳይ ነው። እኔ እስከማውቀውአልፎ አልፎ የሚወሰዱ ሁኔታውን የማይመጥኑ የተናጠልእርምጃዎች ነበሩ። ጥራታቸውን ለሚያውቁ እንተወው።ሰንደቅ፡- የሙስናውደረጃ አሁን ባለበት ደረጃ እስከሚደርስ ለምን ተኛን ብለው ይገምታሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ሙስናውእዚህ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ለምን ተኛን የሚለው የግምገማ ጉዳይ ስለሆነ ቢቆይ ይሻላል።ሰንደቅ፡- አሁን መንግስት በኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ የጀመረውስ እርምጃ ተመጣጣኝ ነው ብለው ያስባሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- አብረን የሰማነው የጠ/ሚ/ኃይለማርያም ቃል ነው የምደግምልህ። “ፀረ ሙስና እንቅስቃሴ ይቀጥላል፤ህዝቡ ይሳተፍበታል፤ እኔ ራሴ በቀጥታ እከታተለዋለሁ” ብለዋል። ይህ የእሳቸው ንግግር የፖለቲካ ቁርጠኝነት ይንፀባረቅበታል።አሁንበሙሰኞች ላይ በተወሰደው እርምጃም ተጠቃሚው ሰፊ ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ እጅግ በጣም የተደሰተ ይመስለኛል።እርምጃ መወሰድ የተጀመረው ህዝቡ ይሳተፋል፤ እኔ እራሴ እከታተለዋለሁ ካሉ በኋላ ነው። ይቀጥላል የሚለው ቃል እርምጃውከተጀመረ በኋላ የተገለፀ ነው። ስለዚህም የጠ/ሚኒስትሩ ቃልና ተግባር ስለተገጣጠሙ አስተማማኝ ጅምር ነው እየሆነ ያለው።መቆም ወደማይችልበት ደረጃ የደረሰ ይመስለኛል።ሰንደቅ፡- ይመስለኛል፤ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ይንፀባረቅበታል ከሚሉ ለምን በእርግጠኝነት ምላሽ አይሰጡኝም?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ጠ/ሚኒስትራችን ያለው እንደማይቀለበስ እርግጠኛ ነኝ። አካሄድ ላይ ግን እርግጠኛ ለመሆን አልቻልኩም።በተለይ ኪራይ ሰብሳቢዎችን ለመዋጋት በህዝብ ተሳታፊነት እንዴት ሊሆን እንደሚችል አላወቅኩም። ህዝብ ያለውኢንፎርሜሽንና በእንቅስቃሲያዊ አካሄድ ያለው ገንቢ አመለካከት ለማን ነው የሚያቀርበው? እንዴት ነው የሚያቀርበው?ካቀረበው በኋላስ በየፈርጁ ተደራጅቶ እንደገና ለውይይት ለጥራት ለህዝቡ እንዴት? መቼ? በማን? ነው የሚቀርበው። ወይስበተናጠል ከቀረበ በኋላ ወደ ማጣራትና ወደ ምርመራ ወደ ክስ ነው የሚኬደው? ባጭሩ የህዝቡ ተሳትፎ አካሄድ የህዝቡ አቅምበሚያዳብር አግባብና ጥራት ያለው ውጤት መሄድ አለበት የሚል እምነት አለኝ።እኔ የሚታየኝ አሁን ያለው የኪራይ ሰብሳቢነት ሁኔታ በአጠቃላይ፤ ስፋቱ፤ ጥልቀቱ፤ በየትኛው የመንግስትና የግል አካላትእንደሚታይ በሚመለከተው አካል አማካኝነት ለህዝቡ መቅረብ አለበት። ሁኔታው ከቀረበ በኋላ ህዝብ ያዳብረዋል። ዋነኛውህዝብ ማለት ደግሞ፣ በአገልጋዩ የመንግስት አካል የሚሰራ ሰራተኛ እና በዚሁ አካል በቀጥታ የሚገለገል ህዝብ ነው። ይህምሲባል፤ ከሁኔታው ጋር በቀጥታ ዝምድና ያላቸው ህዝቦች ማለት ነው። ሌላውም የኅብረተሰብ ክፍል በሚድያ በመድረክ ሊሳተፍይችላል። በዚህ መልኩ ሁኔታው ከታየ በኋላ በቀጣይ መንስኤውን ማስቀመጥ ነው። በሶስተኛ ደረጃ ያስከተለውን ኪሳራ ማየትነው። በአራተኛ ደረጃ መፍትሄውን ማየት ነው። ባጭሩ ሁኔታ፤ የሁኔታው መንስኤ፤ የፈጠረው ጠንቅ እና መፍትሄው ላይ ነውህዝቡ መሳተፍ ያለበት። ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ነበረ ወይ የሚለው በዚህ ሂደት ነው የሚመለሰው።ሰንደቅ፡- ከላይያስቀመጡትን ሂደቶች ማነው የሚያዘጋጀው?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ይህን መነሻ /መንደርደርያ/ ግምገማ ማን ነው የሚያዘጋጀው የሚለው የእኔም ትልቅ ጥያቄ ነው። በፀረሙስና ኮሚሽን ተቋም ውስጥ ያለውን መረጃ ለዓመታት ከአገርም ከውጭም የተጠራቀመ ኢንፎርሜሽን አሉ። በአሁኑ ጊዜምህዝቡ ወደዚያው ነው የሚልከው ይባላል። አሁንም ከድሮውም ጀምሮ በሙስና ኢንፎርሜሽን ጉዳይ ሁሉም ነገር ተቋሙ በእጁያለ ይመስለኛል። በኢንፎርሜሽን ከመታጠቅ ውጭ የሞራል ወዘተ ትጥቅ አለው ወይ? ምንም አላውቅም። የምገምተው ግንአለን። የሆኖ ሆኖ የዚህ ባለጉዳይ የመንግስት አካል ለህዝቡና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የሙስና ሁኔታ በአገሪቱ ውስጥመንስኤው እና ያስከተለውን ጠንቅ ለውይይት ቢያቀርብ ህዝቡ ዋናው ባለጉዳዩ የት ነበርክ? በምን ምክንያት ወዘተ የሚሉጥያቄዎች ማቅረቡ አይቀርም። ስለዚህም ‘ይመስለኛል’ ያልኩት ከመንግስት አቋም ጥርጣሬ ተነስቼ ሳይሆን አካሄዱ እንዴት ነውየሚሆነው? ከሚል መነሻ ነው። አሁንም ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ባለጉዳይ ሆኖ ነው ወይ የሚቀጥለው የሚሉ ጥያቄዎች ስላሉኝነው።ሰንደቅ፡- አሁን ያለው ስርዓት ለዓብይ ሙስና ለGrand Corruption የተጋለጠ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። እርስዎ ምንይላሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- የፌደራልየስነምግባርናፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአገር ውስጥ እንዲሁም ከውጭም በPerception ደረጃ ብዙኢንፎርሜሽን እንደሚቀርብለት እሰማለሁ። የሙስና ኢንፎርሜሽን ለአመታት የተከማቸው እዚያው ተቋም ውስጥ ስለሆነ ከላይእንዳልኩት ህዝቡ በሂደቱ እንዲሳተፍበት ከተፈለገ በትክክል በተገቢው የኢንፎርሜሽን /መረጃ/ አደረጃጀት ይቅረብና እነሱና(ተቋሙ) ህዝቡ ይመልሱታል። እኔ ስገምተው ግን ለGrand Corruption የተጋለጥንና በእሱ የተጨማለቅን ጥቂቶች ብቻአይመስለኝም።ሰንደቅ፡- የፀረ ሙስና ዘመቻው በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ያጠነጠነ ነው ይባላል። የእርስዎ አመለካከት ምን ይመስላል?አቶ ስብሀት ነጋ፡- እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ህጉም ዳኛውም ምስክሩም ይቆጣጠሩና ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲያሰቃዩናሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። እንደዚህ ሲያደርጉ እነ እንትና ከክሱ በስተጀርባ አሉበት ብለው ማስፈራርያ /ትክክልምሊሆን ይችላል/ የፖለቲካ ሰዎች ስም እየጠሩም፣ እየተገናኙም፣ ስልክ እየደወሉም፣ ይፈርዱ ያስፈርዱ ነበር ይባላል። ይህ ትክክልነው አይደለም ራሱ የቻለ ሰፊ ስራ ነው። ሰው ግን አረፍ ብሎ ሰርቶ መብላት መኖር አለበት። ስለዚህ የአሁኑ ፀረ ሙስናእንቅስቃሴ የፍትህ አካላትም የምርመራ አካላትም፤ የዐቃቤ ሕግ ጉዳዮችም እያጠሩ ህዝባዊ ፍትሃዊ እየሆኑ የሚሄዱበት ጉዞናበትልቁ ደግሞ በጠራራ ፀሃይ ማለት ህዝቡ የሚካፈልበት ስለሚሆን ያላጠፉ ግለሰቦችን የማይነካበት ይሆናል። ይሁን እንጂ ሌባናሌባ የሁሉም ብሄሮች ሌቦች በአንድነት እየተደራጁም በተናጠልም የዚህ ብሄር ተጠቃ የዚያኛው ብሄር ያለጥፋቱ ታሰረ ማለታቸውአይቀርም። ትርጉም ግን አይኖረውም።ሰንደቅ፡- የፌደራል ዋና ኦዲት ሪፖርት ለእርስዎ የሚሰጥዎት ትርጉም ምንድነው?አቶ ስብሀት ነጋ፡- በዚህ አገር በዚህ ስርዓት በአሁኑ ጊዜ ትልቁና የማያጠራጥር ተስፋ ሰጪ ሁኔታ የፌደራል ዋና ኦዲተር ጠንከርያለ እንቅስቃሴ መጀመሩና ከሁሉም በላይ ደግሞ የፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዝብ ተወካይነቱ ማረጋገጥ መጀመሩነው። ይህ ከፍተኛ የስልጣን አካል ስራ መጀመሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ የምስራች ነው። የሾማቸውን አስፈፃሚ አካላት ኦዲትሪፓርት መሰረት በማድረግ መቆጣጠር መጀመሩ ብቻ ሳይሆን፤ በቀጥታ በመጥራትም ያለወትሮው የስራ ሂደት ማወቅናማስተካከል ጀምሮዋል። አሁንም ያለወትሮው ወደስራ ቦታው እየሄደ ማጥናትና ማስተካከል ጀምሯል። አሁን የተወካዮች ምክርቤትን በተገቢው ደረጃ የማይፈራ ፈፃሚ አካል የለም። ኦዲት እየጠራ እንዲቀርብለት በሚቀርብለት ኦዲት ተመስርቶም እርምጃእንደሚወስድ ምንም ጥርጥር የለውም። ሌሎች ተጠሪነታቸው ለፓርላማ የሆኑም እንደሚንቀሳቀሱ ምንም ጥርጥር ያለውአይመስለኝም። ሌሎች በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶችም ማለትም የክልል የወረዳ፤ የቀበሌ፣ የከተሞች ም/ቤቶች የፌዴራል ም/ቤት ፈለግ መከተላቸው አይቀርም። ፓርላመንተሪ ሲስተም የእኛን ሲስተም ማለቴ ነው። ቦታውን እየያዘ ነው። ሌላው የዳኝነትስርዓቱ ፅዳት በፍጥነት መድረስ አለበት። የጠቅላላ ስርዓቱ አንድ አካል የሆነው ዳኝነት የሚባለው ያለበት ሁኔታ ዓለም ያወቀውስለሆነ ይስተካከል ከማለት በስተቀር ስለሁኔታው አሁን አለመናገር ይሻላል።ሰንደቅ፡- ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ የግብፅ ፓለቲከኞች የሚሰነዝሩትን ሃሳቦች እንዴት ይመለከቱታል?አቶ ስብሀት ነጋ፡- የግብፅ ፖለቲካ በወሳኝነቱ በአባይ ወንዝ የተመሰረተ ነበር፤ አሁንም ቢሆን። የግብፅ ፖለቲከኞችሃገራዊነታቸው ጀግንነታቸውና በስልጣን የመቆየታቸው ጉዳይ በአባይ የተመሰረተ ነው። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አለመረጋጋት አለ።ስለዚህ ማንኛውም የግብፅ ፖለቲከኛ የግብፅ ብሄርተኝነቱ ማረጋገጫ በአባይ ላይ የሚወሰደው አቋም ነው። ለዚህ ተጨማሪበኢትዮጵያ ህዝቦችና ባለፉት መንግስታት የነበረው ንቀት አለ። ስለዚህ እነዚህ ድክመቶች ተደማምረው እነሱ የፈጠሩትን የህዝቡስሜታዊነት ለመቀስቀስ አካኪ ዘራፍ ማለታቸው አያስገርምም። የሚያስገርመው ግን ስለግድቡ እንደማያውቁ መሆናቸው ነው።የሆኖ ሆኖ ታላቁ ቁምነገር ተሳስተናልና ሁሉም ነገር በጋራ እናየዋለን ማለታቸው ነው።ሰንደቅ፡- በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ጦርነት ይነሳል ብለው ያስባሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ጠ/ሚ/ኃይለማርያም አይመስለኝም ብሎ መልሶታል። የእኛ መንግስት ኃላፊዎች የግድቡ አጀማመር፤አካሄድና ይዘት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ የአካኪ ዘራፍ አቋም አልነበራቸውም። ማብራሪያ ነበር የጠየቁት። በታላቅ ትዕግስት ነበርማብራሪያውን የጠበቁት። በርግጥ አንዳንድ ሰዎች ስለጉዳዩ ምንም አይነት ፍንጭና አጠቃላይ ግንዛቤም ሳይዙ ወደ ወታደራዊአቅም ግምገማ የሄዱት፤ የተመኙት ጦርነት የሚሆንላቸው እየመሰላቸው ነው። ጦርነት የማይነሳው በወታደራዊ አቅም ሚዛን ብቻአይደለም። የግድቡ ፍትሃዊነትና ፍትሃዊነቱም ድፍን ዓለም ያወቀው በመሆኑ ነው። በዋናነት ፍትሃዊነቱ የዓለም ኅብረተሰብ ብቻሳይሆን የማይናቅ የግብፅ ህዝብም አሁን ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ባህሪ የጋራ ጥቅምን ማዕከል አድርጐ እያሰበ የሚሰራ እንጂየህዝብ ተራ ስሜት እየቀሰቀሰ ጐራዴ ታጥቆ በየመንገዱ የሚፎክርና የሚያስፎክር እንዳልሆነ ማወቅ ጀምረዋል። ስለዚህምጥንቃቄ አስፈላጊ ቢሆንም፣ ለጦርነት ምክንያት የለውም።ሰንደቅ፡- ግብፅ፤ ኤርትራና ሶማሊያን እንዲሁም የሃገር ውስጥ ተቃዋሚዎችን ኢትዮጵያ ለማተራመስ መምረጣቸውን እንዴትንይመለከቱታል?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ግብፅ እነዚህን ጐረቤት ሃገሮች ለትርምስ መምረጥዋ አላውቅም። የምትመርጥ አይመስለኝም። ግብፅየሚጠቅማት የኢትዮጵያ ልማትና መረጋጋት ነው። ይህንን በተሟላ ደረጃ ለመገንዘብ ብዙ ጊዜ የሚወስድባቸው አይመስለኝም።ግብፅ፣ ሶማልያ፣ ኤርትራና የአገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለትርምስ አትመርጥም። ብትመርጣቸውም እንደሃገር ለዚህ ጉዳይከግብፅ ጋር የሚሰለፉ አይመስለኝም። አይመስለኝም ያልኩት በሁለት ምክንያት ነው። መጀመርያ ሊያምኑበት አይችሉም።ሁለተኛ እነዚህ ጐረቤቶች አያዋጣቸውም። ዋናው ነገር ግን ግብፅ ይህንን ነገር አትመርጥም። ኢህአዴግ ቢጠሉም ከግብፅ ጋርየሚሰለፉ የሃገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አይኖሩም። አንዳንድ ብስጭታቸው ወደ ህመም ደረጃ የደረሰ ካልሆኑ በቀርየሚሰለፍላቸው የለም። ዋናው ነገር ግን ግብፆች ጥቅማቸውን የሚያዋጣቸውን ሳይገነዘቡ አይቀሩም። እየተገነዘቡም ነው።ሰንደቅ፡- የህዳሴው ግድብ ገዢው ፓርቲ ለራሱ የፖለቲካ ፍጆታ እያዋለው ነው የሚል ክስ ተቃዋሚዎች ያቀርባሉ። በዚህ ላይየእርስዎ አስተያየት ምንድነው?አቶ ስብሀት ነጋ፡- የህዳሴ ግድብ ይዘትና አካሄድ በጉዳዩ በአለማችን ግሩምና የተዋጣለት ከሚባሉ ታሪኮች አንዱ ነው። የጉዳዩውስብስብነት በመረዳት የናይል ተፋሰስ ባለድርሻዎች በማሰለፍ አንዱ ትልቅ የአፍሪካዊነት ኢትዮጵያውነት ህዝባዊነት የፈጠረውብልህነት ነው። የባለድርሻዎች ሰልፍ ነው። የአባይ ግድብ ለሶስታችን ለጋራ ተጠቃሚነት ለመገደብ ሲታሰብ ሊያጋጥሙ የሚችሉፖለቲካዊ፤ ዲፕሎማሲያዊና ቴክኒካዊ ፍተሻና ጥናት እንዲካሄድ ኢትዮጵያ መሪነቱን እየያዘች ቀዳዳ እንዳይገኝ የረጅም ዓመታትወደፊት እያየች በታላቅ ሃላፊነትና ትዕግስት ሞያ ነው ስራውን ስታራምድ የቆየችው። ይህን ያህል ታላቅ የዘመናችን ስራ አሁንምለወደፊትም ለጠላት በር እድል እንደማይሰጥ አድርገህ መሄድ እጅግ በጣም አስደናቂ ታሪክ ነው።በእኛና በታችኛው አባይ የነበረ የዘመናት ውጥረት ወደ ፍቅርና አብሮ የመስራት መንደር የሚከተን ስራ ነው። በአጠቃላይ ለኛለአባይ ተፋሰስ አገሮችና በተለይ ግድቡ ለሶስታችን ብቻ አይደለም፤ ጠቃሚነቱና አስተማሪነቱ። እንደኛ ያሉ ድንበር ዘለል ወንዞችያሉዋቸው አገሮች የእኛ የአባይ ተፋሰስ አገሮች አብሮ ለመስራት መጀመር ታላቅ ትምህርት ነው። ግድቡ ብቻ አይደለም ታላቅየሃገር ስራ። ዋናው የዓባይ ተፋሰስ ሃገሮች ትብብር መጀመሩ ነው። ይህ ጉዳይ በዓለም እየተነገረ ብቻ ሳይሆን የሚኖረው መልካምትምህርት ሆኖ እየተኮረጀ የሚኖር ስራ መስራታቸው ነባሪ ነውና መላው ህዝብ እንደ ሃገር ኩራት መውሰድ አለበት። ለቀጣይሃገራዊ ስራዎች የህሊና ሃይል በሚፈጥር መንገድ መነገር ብቻ ሳይሆን፣ ተፅፎ ለእንደኛ ያሉ ድንበር ዘለል ወንዞች ያሉዋቸውሃገሮች መዘርጋት አለበት።¾(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር407 ረቡዕ ሰኔ 19/2005)

ማነዉ ፈሪዉ ተቀዋሚ ወይስ ህወሃት/ ኢህአደግ?


ሰላም ፍቅሬ / ከጀርመንሰሞኑን በ20/06/2013 በአሜሪካ ኮንግረስ በኮንግረስማን የተከበሩ ሚስተር ስሚዝ ኢትዮጵያ ከመለሰ በኋላ፦የወደፊት ዲሞ ክራሲና የሰበአዊ መ ብት በሚ ል ርዕስበተደረገዉ የም ስክርነት ቃል ላይ የተከበሩ አም ባሳደርያማ ማ ቶ በተቃዋሚ ዎች ዙሪያ ሲናገሩ በራሳቸዉስለማይተማ መኑና ስለሚፈሩ ነዉ ብለዉ መናገራቸዉንአድምጠናል።በዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ይቻላል ፤ ይሁንና ለዛሬ በቅርብየሆኑትንና በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ላተኩር።እዉነት አምባሳደር ያማማቶ እንዳሉት ፍርሃት ያለዉ በተቀዋሚ ጎራ ነዉ ፤ በህወሃት አካባቢ ነዉ ፤ ወይስ አሜሪካየኢትዮጵያ ጉዳይ እያስፈራት መጣ ?ጉዳዩን ለፖለቲካ ጠበብቶች እተወዋለሁ ።እድሜ ለሰማያዊ ፓርቲ አምባሳደር ያማማቶ ከመናገራቸዉ በፊት ቀደማቸዉ እንጂ ሁሉንም ፈርታችሁ ነዉ ይሉነበር። አንድ ነገር አምባሳደር ያማማቶን ልጠይቃቸዉ ለመሆኑ ፍርሃት ዝም ብሎ ይመጣል? ከ1997 ዓ.ም ምርጫበኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ግንባር ግንባሩን እየተባለ ሲገደል ባያዩ እንኳን አልሰሙም ?ታዲያ አሁንስ ህወሃትጥቅሞቹ እንዳይነኩበት ለ39 ዓመታት ያከማቸዉን የጭካኔ ልምድ የሰማና ያየ ለምን አይፈራ ?ግን እኮ አምባሳደር ያማማቶ እዉነታቸዉን ነዉ፤ ከፍርሃት ዉጡና ታገሉ ማለታቸዉ እንደሆነስ? ካለ ትግል ድልየለምና ከፍርሃት ወጥቶ መ ታገል የድል መሰረት በመሆኑ ጥቆማቸዉ ዋናና ጠቃሚ ጉዳይ ነዉና በጥሩ ጎኑ ብናየዉስ?የኢትዮጵያ መንግስት ለ8ዓመታት በግዳጅና በማስፈራራት ይዞት የቆየዉን የሰላማዊ ሠልፍ ፍቃድ ክልከላ ሳይወድበግድ መፍቀዱን መንግስትና ሰማያዊ ፓርቲ ባሳዩት እንቅስቃሴ ለማወቅ ችያለሁ።ሠማያዊ ፓርቲ የተከበሩ አምባሳደር ያማማቶ በዚሁ የምስክርነት ቃል ላይ የተናገሩትን አስቀድሞ ያወቀ ይመስላል።ምክንያቱም ፓርቲዉ ምንም ፍርሃት ሳይገባዉ ህወሃት/ ኢህአደግን ብቻ እያስፈራራ ሰላማዊ ሰልፉን አድርጓል።ከሰልፉም ፍርሃቱ የቱጋ እንዳለ አሳይቷል።ህወሃት/ ኢህአደግ ግን ይፈራል?።አዎ ይፈራል። ህወሃት ለምን ይፈራል? የስንቶች የንጹሃን ደም በእጁ አለ፣ሰንቶችንአስለቅሷል፣ ስንቶችን አሳብዷል፣ ስንቶችን የአልጋ ቁራኛ አድርጓል፣ ስንቶችን ንጹሃን ከመቃብር በታች አድርጓል።ስንቶችን በዘር መሰረታቸዉ አሳድዷል ፣ ከቦታቸዉ አፈናቅሏል፣ንብረታቸዉን ነጥቋል፣አለጥፋታቸዉ አስሯል። ስንትበኢትዮያውያን ህዝብ ስም የመጣ ሃብትና ንብረት ተበዝብዟል፤በዚህም ሰንቶች ህወሃቶች ሃብት አጋብሰዋል።እነዚህብቻ አይደሉም ህወሃት የሰራቸዉ ሃጥያቶችና ወንጀሎች ብዙ ናቸዉ ።ሌላ ህወሃት የሚፈራበት ነገር አለ ወይ? አዎ። ምን?ይህ ዘመን አምባገነኖችን ያንቀተቀጠ ዘመ ን መሆኑናአምባገነኖችን እረፍት መንሳቱ አንድ ቀን ለእነሱም እንደማይቀር ስለገባቸዉ ፤ በአረቡ አለም የወደቁት አምባገነኖችየነበራቸዉ ትጥቅ ከህወሃት ትጥቅ በላይ መሆኑና ያላዳናቸዉ መሁኑን ህወሃት ጠንቅቆ ስለተረዳ፤ በሌሎችም አገሮችለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በብራዚል እና በቱርክ ህዝብ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ስለሚያስረዳቸዉና የህዝብን ብሶትመሳሪያ እንደማይገድበዉ ህወሃት ስለተማረ።ታዲያ ምን ያስፈረዋል? ለምን አያስፈራ? ህዝቡ ትግሉን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ካደረሰዉ ለህወሃት ትልቅ አደጋ ስለሆነነዉ ።ህወሃትን አሁን የሚያስፈራዉ የኢትዮጵያ መኖር አለ መኖር ሳይሆን ፤ የዘረፉት ንብረት ፣ በፓርቲያቸዉ ስር ያለዉግዙፍ የንግድ እንቅስቃሴና ሌሎች ሊያስጠብቋቸዉ የፈለጋቸዉን ፤ስዉር ዓላማዎቻቸዉን ሁሉ የሚጠራርግ ማዕበልእየመጣ መሆኑ ስለገባቸዉ ለምን አይፈሩም?አንዳንድ ተቀዋሚ ፓርቲዎች ሰማያዊ ፓርቲ አብረን ሰላማዊ ሰልፍ እንውጣ ባለ ጊዜ ምክንያት እየደረደሩ አስቸግረዉነበር ይባላል።ይሁንና አሁን ከሰልፉ በኋላ ፦ይህም አለ እንዴ ? ያሉ ይመስላል።አሁንም ትግሉን መደገፋቸዉናመጀመራቸዉ ይበል የሚያሰኝ ጅምር በመሆኑሊበረታታ ይገባል።መነሻዉ የትም ይሁን የት መጀመሩ በራሱ አበረታችነዉ ።ከፍርሃት ወጥተዋል ማለት ነዉ።አንድነት ፓርቲ የሚሊዬኖችን ድምጽ ለማስጠበቅ በሚል መነሳታቸዉን እየሰማን ሲሆን ይህም ማነዉ ፈሪዉየሚለዉን ለማወቅ ጊዜዉ እየደረሰ መ ሆኑንና ሰላማዊ ትግሉ ሊቀጥል እንደሆነ ይታያል። እንግዲህ ህዝቡ ወደጨዋታዉ ሜዳ በመጠጋት ድጋፉን እንደሚሰጥ የሚጠበቅ ሲሆን፤መሪ አጣን ለሚሉም ቀጥተኛ መልስ መገኘቱታዉቋል።ትግሉን ከግብ ለማድረስ ከፍርሃት ዉጭ ሆኖ ስራን መፈጸም ይጠይቃልና ከሰማያዊ ፓርቲ ትምህርት መዉሰድየበታችነት ሳይሆን ብልህነት ነዉ።ትምህርት ትልቅ ጉልበት ይፈጥራል፤ተጨማሪም የሞራል ዝግጅት ማድረግያስችላልና፤በዚህ ዙሪያ ቆራጥነትንና ሌሎች የልምድ ግብአቶችን መጋራት ጠቃሚ ነዉ እላለሁ።ለራሳችን መ ፍትሔ የምናመጣዉ በእርግጥ እራሳችን ነን፤ አንድ ትልቅ ነገር ለተቀዋሚ ዎች እመክራለሁ ። እርሱምከየዋህነት እንድንወጣ ። በየዋህነት ህወሃትን ማሸነፍ አይቻልም ። የህወሃትን የክፋት መጠን የሚመጥን እናየሚቋቋም የትግል ስልትና አቋም ይዞ መነሳት ህወሃትንም ላይቀርለት ወደ ፍጻሜ ያቀርበዋል።የኢትዮጵያ ህዝብም ፤ በአገር ዉስጥም ሆነ ከሃገር ዉጭ ያሉ ሁሉ ተገቢዉን ድጋፍ ለትክክለኛና ለእዉነተኛተቃዋሚዎች በመ ስጠት ህወሃትን ከጫንቃችን ላይ እናዉርድ ፤በዚህም የእፎይታ ዘመናችንን እናፋጥን ። ካልሆነ ግንመንግስትም የራሱን ጥላ ባየ ቁጥር ሰዉ ከሚገልና ቃሊቲ ከሚወረዉር፤ተቃዋሚም ፈርቶ በመንግስት ከሚያላክክ ፤ህዝብም ፈርቶ የሚመራን አጣን እያለ ከሚያዝን፤ ትግሉ ይጀምር፣ይቀጥል፥ ለጥያቄዉ መ ልስ ይገኝ። ሁሉምከፍርሃት ይዉጣ ።ኢትዮጵያ የነጻነት ፣የዲሞክራሲና የብልጽግና አገር ትሁን።ለራሳችንና ለትዉልዳችን ጥቅም ሲባል ቢያንስ ተቃዋሚዉከፍርሃት ይውጣ ። በመጨረሻም ፈሪዉ ማን እንደሆነ ይታወቅ።አም ላክ ኢትዮጵያን ይባርክ !

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን” “ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”


tesfaye


“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር አሰሩኝ ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር ዝዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መታሰርህን ለቤተሰብ ተናግረሀል?
ወጣት ተስፋዬ:- ለማንም ሰው እንድናገር አልፈቀዱልኝም፤ መስሪያ ቤቴ አልጠየቀኝም፣ ደሃዋ እናቴ ያለችው ናዝሬት ነው እሷም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አባቴ አቶ ተካልኝ አስተማሪ ነበር አርባ ጉጉ ላይ ነው በ1985 ዓ.ም በነበረው ግጭት ነው የተገደለው፡፡ ማንም ሳይጠይቀኝ፣ፍ/ቤት ሳልቀርብ 23 ወር ታሰርኩ ልብስ ምግብም የሚያመጣልኝ ሰው አልነበረም፡፡ እናቴም መታሰሬን እንኳ አታውቅም መስሪያ ቤቴም ስኮላርሽፕ አግኝቷል፤ ወደ ውጪ ሃገር ሊማር ሊሄድ ነው የሚባል ነገር ስለነበረ አልጠየቁኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የት ነበር ስኮላርሺፕ ያገኘኸው?
ወጣት ተስፋዬ:- የዛሬ 2 ዓመት አካባቢ የራስመስ ሙንደስን ስኮላርሽፕ አግኝቼ ነበር፡፡ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያና ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶክዮ ባሉ ምሁራን ሪኮመንድ ተደርጌ በጣሊያኑ ፌራሪ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ እንደተፈታሁ ሄጄ ስጠይቃቸው ብዙዎቹ ጓደኞቼ በጣም ደነገጡ፡፡ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ቅማል ተወርሬ … ባካችሁ ተውኝ … ምንም የሌለ ነገር የለም በጣም ተጎድቻለሁ፡፡ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ እናቴ ጋ ስሄድ በጣም ደነገጠች፣ በሕይወት ያለሁ አልመሰላትም 23 ወር ሙሉ ከቤተሰብ ስለተለየሁ ግራተጋባች፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- በእስር ወቅት የደረሰብህ ድብደባና ማሰቃየት ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ በኤሌክትሪክ ጀርባዬ ላይ አቃጥለውኛል፣ በብልቴ ላይና በኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱብኝ ሽንት ችዬ አልሸናም፣ ሽንቴን መቆጣጠርም አልችልም፡፡ ኩላሊቴንም በጣም ያመኛል፡፡ ውሃ ውስጥ እየነከሩ በጣም ደብድበውኛል፡፡ አሁን ስናገር ያመኛል ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደው ስታስበው ለእስር ያበቃህ ወይም ከመንግስት ጋር ያጋጨህ አጋጣሚ ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- መስሪያ ቤቴ ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፤ በጣም ይከታተሉኛል፡፡ በቢ.ፒ.አር ላይ ስብሰባ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ እኔም ሠራተኛ ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ነገሮች ሲመጡ እኔ አልቀበልም በግልፅ እናገር ነበር፤ ሠራተኛውም እኔን ይደግፋል፡፡ ከመታሰሬ ጥቂት ጊዜ በፊት ገነት ሆቴል ስብሰባ ነበረን፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ በጣም ተከራከርኩ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አቶ ፀጋዬ ማሞ የሚባሉ አሰልጣኝ፣ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከንግድና ኢንዱስትሪም የመጡ ነበሩ ስማቸውን የማላስታውሳቸው ባለስልጣን ነበሩ፤ እዛ ላይ ሀሳብ አንስቼ ተከራክሬ ነበር፡፡ “የሠራተኛን ሀሳብ ዳይቨርት ያደርጋል” ይሉኝ ነበር፡፡ መቼም ግን ሀሳቤን በመናገሬ ይህን የመሰለ ስቃይ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ “አሸባሪ፣ ግንቦት ሰባት” እያሉ እኔ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ያለምንም ፍርድ በርሜል ውስጥ ውሃ ጨምረው እያስተኙ አሰቃዩኝ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደዚህ ያሰቃዩህ ምን አይነት ምንም አይነት መረጃ ሳያገኙ ነው?
ወጣት ተስፋዬ:- እኔን ጥፋተኛ የሚያስደርግ ምንም መረጃ አላገኙም፣ እኔን አስረው ወደ መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ይደውሉ እንደነበር ይነግሩኝ ነበር፡፡ የኢሜይል አድሬሴንም ተቀብለው በርብረዋል ግን ምንም አላገኙም፡፡ እኔ ከማንም ጋር ሊንክ የለኝም ኢሜሌ ላይ የስኮላርሺፕ መልዕክት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለውም፡፡ በመስሪያ ቤቴ ሪሰርቸር ነበርኩ፣ በሶሲዮሎጂ ነው የተመረኩት፡፡ ሉሲ የተገኘችበት ሣይት ላይ አፋር፣ ጋምቤላ ብዙ ሳይቶች ሰርቻለሁ፡፡ ከአለቆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሰላማዊ ነው እነሱ ናቸው ስኮላርሽፕ ሪኮመንድ ያደረጉኝ፡፡ አንደኛው ፕሮፌሰር 25 ዓመት ሙሉ እዚህ አገር ሰርቷል፣ አርዲን ያገኘው እሱ ነው፡፡ ሄነሪ ጊልበርት ይባላል፤ እሱም ሪኮመንድ አድርጎኛል፡፡ እኔ በጣም የሚቆጨኝ ደሃዋ እናቴ አረቄና ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ ምን ብዬ ልንገራት እንደዚህ አትጠብቀኝም ከበደኝ፣ አሁን እሷ የምትሰጠኝ ምግብ ራሱ ደምደም አለኝ… (ረጅም ለቅሶ)፡፡ ልጄ በደህናው አይደለም የጠፋው ሞቷል ወይም መኪና ገጭቶታል ብላ ነበር የምታስበው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የከመታሰርህ በፊት ፖለቲካ ተሳትፎ ነበረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- 1997 ዓ.ም የቅንጅት ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ በ97 የነበረው ሁኔታ ስንት ሰው አለቀ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር ታውቃላችሁ ምንም የምናደርገው ነገር አልነበረም ፡፡ በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል ተረዳሁኝ፡፡ ከ1997 ዓ.ም በኋላ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልሆንኩም፡፡ ከዚህ በኋላ ከምንም ነገር የተገለልኩ ሆኛለሁ፡፡ አንድ ብርጭቆ ሳትሰብር አሸባሪ ስትባል አስብ እንግዲህ አንድ ብርጭቆ እንኳን ሰብሬ አላውቅም ባለኝ እውቀት እንደውም ለእውቀት ነው የምጓጓው እውቀቴን አሳድጌ አገሬን ለመለወጥ ነው የማስበው እኔን ምንም የሚመለከተኝ ነገር የለም አሸባሪም ግንቦት ሰባትም አይደለሁም፡፡ስትደበደብ፣ ስትሰቃይ ያላደረከውን አድርጌያለሁ ትላለህ፤ በርሜል ውሃ ሞልተው ይከቱሃል ያሰቃዩሃል፡፡ አያሳዝንም ይሄ? እንዴት አድርጎ እዚህ አገር ይኖራል? 23 ወር ሙሉ አስረው ማሰቃየታቸው ሳያንስ የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም ብዬ ነው የነገርኳችሁ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን የት ነው የምትኖረው?
ወጣት ተስፋዬ:- መኖሪያ የለኝም … (ረጅም ለቅሶ)
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝን ለመርዳት የምትፈልጉ አንባብያን ከፍኖተ ነፃነት መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ (ምንጭ ፍኖተ ነጻነት)

Jun 25, 2013

ስለኢሳት ለኢትዮጵያውያን የተላከ መልእክት! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ


ኢትዮጵያ ሀገራችን የለየላት የዜጎቿ እሥር ቤት ከሆነች በጥቂቱ 22 ዓመታት አለፉ፡፡
ከ22 ዓመታት በፊት የነበረው ሥርዓተ መንግሥቷ አሳሪና ገዳይ ቢሆንም
እንደሥርዓትና የገዢዎቹም ማንነት እንደሀገራዊ ስብዕና ሥርዓተ መንግሥቱ
በኢትዮጵያዊ ወገናዊነቱ የማይታማ፣ የመንግሥት አገልጋዮችም በሀገር
ወዳድነታቸው ጥያቄ ውስጥ የማይገቡ ከደነዝነታቸውና ድንቁርናን መሠረት
ካደረገው ዕብሪታቸው በስተቀር ሌላ ጠላት የሌላቸው ገልቱ ሥርዓትና ጨካኝ
ኢትዮጵያውያን ባለሥልጣናት እንደነበሩን የምናስታውሰው ነው፡፡ የአሁኖቹ ግን
ስንዴ መሃል እንደበቀሉ እንክርዳዶች የሚመሰሉ የታሪክ አሽክቶች እንደመሆናቸው
አዘናግተውና አንድን የታሪካችንን ስብራት አጋጣሚ ተጠቅመው ሥልጣነ
መንግሥቱን ከያዙ በኋላ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊውያን ነን የሚሉ ወገኖችን
ጠራርገው ለማጥፋት የተነሱ በጭካኔ ወደር የማይገኝላቸው የራሳችን ወገኖች
ናቸው፡፡ በበቀልና በጥላቻ መንፈስ የሚነዱት እነዚህ ወገኖቻችን የሰበቀቡን ጦር
ወደሰገባው የሚመለስበት ዘመን እየራቀ በመምጣቱ በተለይ በአሁኑ ወቅት የሕዝቡ ሁለንተናዊ ሕይወት ከድጡ ወደማጡ ሆኖ
ኢኮኖሚያዊ ሕይወቱ ይቅርና መንፈሳዊ ሕይወቱ ራሱ ከዓለም ሕዝቦች በተለዬ አሰቃቂ ሁኔታ ወደ መቀመቅ እየወረደ ነው፡፡
መብላት መጠጣት፣ መልበስና ማማር ሊቀር የሚችል ተራ ነገር ነው፡፡ ማጣትና ማግኘት ተፈራራቂ በመሆናቸው ዛሬን ያጣ ነገ
ያገኛል ተብሎ ይገመታልና ይህም ምንም ማለት አይደለም፡፡ አሁን እያስፈራን የሚገኘው ትልቁ መርዶ ግን አንድ ሕዝብ በዜግነት
ማንነቱ፣ በባህሉ፣ በሃይማኖቱ፣ በትምህርት አቋሙ፣ በማኅበራዊ ሥነ ልቦናው፣ በአጠቃላይ የግንዛቤና ዓለምን የመረዳት
የአስተሳሰብና የአመለካከት አድማሱ… በነዚህና በመሳሰለው አእምሮኣዊና መንፈሣዊ ኅልውናው ላይ አሁን የተጋረጠበት አደጋ
ሊያስከትለው የሚችለው የትውልድ ምክነትና የኅልውና ቀጣይነት ችግር ነው፡፡ ይህ ዓይቱ ችግር ነው ብዙዎቻችንን እንቅልፍ
እየነሳን የሚገኘው፡፡ ይህ ዓይነቱ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀስ ሞራለቢስና በሀገሩ ላይ ሀገር አልባ የሆነ ትውልድ በብዛት
የሚያመርት ሀገራዊ ችግር ነው ጥቂት የማንባል የቀደመው ትውልድ አባላትን የኅሊና ዕረፍት እያሳጣን የሚገኘው፡፡ ይህ ዓይነቱ
ሀገር ያለች እየመሰለች ነገር ግን ሁለመናዋ የጠፋና እንደፀጉራም ውሻ አለች ሲሏት የሞተች ሀገር ውስጥ የመኖር አደጋ ነው
እየተንሰራፋ ያለው፡፡
ከቁሣዊው ሕይወት አንጻር ዛሬ ቢርበንና ቢጠማን ምንም አይደለም፡፡ ዛሬን ብንታረዝ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ዛሬን ብንከሳና
ብንጠቁር፣ ብንኮስስና ብንገረጣ ብንታመምም ምንም አይደለም፡፡ ጦርነትና ርሀብ ተከስቶ የተመሰቃቀለ ችግር ቢፈጠርም አላፊ
ነውና ምንም ማለት አይደለም፡፡ በጥቅሉ ዛሬን ተፈጥሯዊ ችግርን ብንቸገር በኛ ብቻ ስላልሆነ ምንም አይደለም፡፡ ይህ እንግዲህ
በሥጋዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ብዙ የዓለም ሀገሮችም በዚህ ሂደት አልፈዋል፤ ዛሬ የሥልጣኔና የቅንጦተኛ ኑሮ ቁንጮ የሆኑት
እነአሜሪካና (ቻይና?)፣ እነጃፓንና ከሞላ ጎደል ሁሉም የአውሮፓ ሀገሮች በጠኔና የርስ በርስ ጦርነትን ጨምሮ በአሰቃቂ ችግሮች
ውስጥ አልፈው ነው (በአንጻራዊ ሁኔታ የአሁኑ) ምድራዊ ገነት ውስጥ ሊገቡ የቻሉት፡፡ በታሪክ አንቀልባ ታዝሎ መኖር ለማንም
አልጠቀመም እንጂ ኢትዮጵያም አንድ ወቅት ለተቸገሩ ሀገሮችና ሕዝቦች የምትረዳ ርህሩሂት ሀገር እንደነበረች የቅርብ ጊዜው
ታሪካችን የሚዘክረውና ፈረንጆችና ሌሎች የውጪዎች ሊያምኑት የሚቸግራቸው ተኣምር ነው፡፡ ለጃፓን፣ ለኮርያ፣ ለካናዳና ለብዙ
የአፍሪካ ሀገሮች ፍጡነ ረድኤት የነበረች ሀገራችን ዛሬ ሌሎችን መርዳት ይቅርና ቅን አሳቢ ሰው የማይወጣባት፣ መጭና ወበሎ
የሚበቅልባት፣ ጅቦችና ዓሣማዎች የሚራቡባት (የሚፈለፈሉባት ለማለት እንጂ ርሀቡስ ሲያልፍም አይነካቸው!) እጅግ አሳዛኝ
ሀገር ሆናለች፡፡ ጤናማ ዜጎቿ እግር ባወጣ እየተሰደዱ፣ በሀገር ቤት ያሉትም በፍርሀት ተሸብበው አንገታቸውን እየደፉ፣ ብዙዎች
“ምሁራኗ” ወያኔ የቀደዳለቸውን ቦይ በመከተል በዘርና በጎሣ ተከፋፍለውና በአጥፊና ጠፊ አማሳኝ ጎራዎች ተቧድነው
ኃይላቸውን በልማትና በችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ ሳይሆን በጉንጭአልፋ ንትርክ የሚያባክኑ፣ በውጤቱ ደግሞ
ታሪካዊ ጠላቶቿ ያሰማሯቸው የውስጥ የጠላት ቅጥረኞችና ሸማቂዎች ያገኙትን ወርቃማ ዕድል ተጠቅመው ሀገሪቱ ዳግም
እንዳታንሰራራ የሚቀጠቅጡበት ሁኔታ ተመቻችቶላቸው ሳንወድ በግዳችን በታሪክ ጠማማ ፍርድ እየተንገፈገፍን እንገኛለን፡፡
ቅጥቀጣው ቁሣዊ ብቻ ቢሆን እንደገለጽኩላችሁ ብዙም ባልከፋ፡፡ የቅጥቀጣው መሠሪነትና አሰቃቂነት ግዘፍ ነስቶ የሚታየው ነገ
ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዳይኖር ሆን ተብሎ ታቅዶ በሚደረገው ሁልአቀፍ ጥረት አማካይነት እየታዘብነው በምንገኘው
ወደርየለሽ ጭካኔ የተሞላት ዕኩይ ድርጊት አማካይነት ነው፡፡ ለአብነት በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የትምህርት ተቋም የሚመረቅ
ወጣት – አብዛኛው ማለት በሚቻል ሁኔታ – ስሙን በእንግሊዝኛ አስተካክሎ የሚጽፍ ስለመሆኑ በርግጠኛነት መናገር
አይቻልም፤ ይህ የተደረገውና እየተደረገ ያለውም ሆን ተብሎ በተጫነ ትውልድ ገዳይ የመማር ማስተማር ሂደት ነው፡፡ በአሁኑ
ወቅት ከየትኛውም የትምህርት ተቋም የሚመረቅ ወጣት ሀገርህ የት ነው ተብሎ ቢጠየቅ ‹ኦሮምያ፣ ትግራይ፣ደቡብ፣
ሶማሌ፣አፋር…› ከማለት ውጪ ‹ኢትዮጵያ ናት› የሚል ለማግኘት በጣም የምንቸገርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ይህ ዓይነቱ
ወያኔያዊ ከፋፍሎ የመግዛት ዘዴ ሀገራችንን እያጠፋት ነው – የፈጣሪ ሥራ ካልተጨመረበት በስተቀር በቀላሉ ልታገግም
በማትችልበት ሁኔታ እየወደመች ናት፡፡
በየቀኑ እንደ አሸን የሚፈላውን የሕዝብ ቁጥር ስትመለከቱ ደግሞ ደንብራችሁ ገደል ልትገቡ ትችላላችሁ – እንዲህም የምትሆኑት
ስለነገዋ ኢትዮጵያና ሥራ አጥቶ በየባቡር መንገዱ ካለሥራ የሚርመሰመሰውን ሕዝብ ተመልክታችሁ የምትጨነቁ ከሆናችሁ እንጂ
ወያኔን ይመስል እንደመጋዣ ያገኛችሁትን እያሞነዠካችሁ የምትኖሩ እንስሳት ከሆናችሁ ምንም ላይሰማችሁ ይችላል – ወያኔዎች
እኮ ከሕዝብ መፈጠራቸውን ረስተው በሕዝብ ስቃይ የሚፈነጥዙ በሩቅ ሀገር ሰውነት የሚፈረጁ ጥፉዎች ናቸው፡፡ ሰውን ወደ
እንስሳነት መለወጥ ደግሞ የወያኔ አንዱና ትልቁ የአገዛዝ ስትራቴጂው ነው፡፡ የሕዝቡ ብዛት እንግዲህ በእጅጉ የሚያስደነግጥ
የወቅቱ ወረርሽኝ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እውነት ነው – የሕዝብ ብዛት በራሱ ችግር ሊሆን እንደማይችል ቻይናውያን
አመላክተዋል፡፡ ግን ግን ከዘመኑ ጋር የተገናዘበ ሀገራዊ የሥነ ሕዝብ ፖሊሲ እንደሚያስፈልግ፣ የሕዝቡ ብዛት ከሀገሪቱ የተፈጥሮ
ሀብትና የታህታይና ላዕላይ መዋቅሮች አኳያ መመጣጠን እንደሚገባው፣ የሕዝብ ብዛት መጨመር ወይም መቀነስ ለሕዝብ
ከሚቆረቆርና ለሕዝብ ከሚሠራ መንግሥት ጋር የቀጥታ ግንኙነት እንዳለው፣ የሕዝብን ብዛት ወደ ተጨባጭ የሀብት ምንጭነት
ሊለውጥ የሚችል መንግሥት በአንድ ሀገር ሊኖር እንደሚገባ … መጠቆሙ ጊዜ ያለፈበት አስተያየት ሊባል የሚችል
አይመስለኝም፡፡ በነገራችን ላይ እኛ በሕዝብ ብዛት የምንጨነቀውን ያህል ወይም ከኛውም በበለጠ ‹የሀገራችን የሞትና የወሊድ
ምጣኔ በዚህ መልክ ከቀጠለ በዚህን ያህል ዓመተ ምሕረት የዚህች ሀገር ዜጎች ከምድረ ገጽ ይጠፋሉ› ብለው የሚጨነቁና
ጋብቻንና ወሊድን በስፖንሰርነት የሚደግፉ የአውሮፓ ሀገሮች እንዳሉ እንሰማለን፡፡ …
በዚህ የጭንቅ ዘመን የሕዝቡን አንድነት ሊያስተባብርና የጋራ የትግል መድረክ ሊፈጥር የሚችል የተስፋ ጭላንጭል ከወደ አሜሪካ
ተከስቷል፡፡ ይህ የሕዝቡን ተስፋ በማለምለም ላይ የሚገኘው ዕፁብ ድንቅ ክስተት የኢትዮጵያ ሣተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን
ጣቢያ (ኢሳት) አየር ላይ መዋል ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ባብዛኛው መንቀፍን እንጂ ማበረታታትን የማንወድ፣ ማቀጨጭን
እንጂ ማወፈርን የምንጠላ፣ መውለድን እንጂ ተንከባክቦ በማሳደግ ለወግ ለማዕረግ ማብቃትን የምንጠየፍ፣ በምቀኝነት ታውረን
የሌሎችን ስኬት ማንቋሸሽ እንጂ በመንፈሣዊ ቅናት ተመርተን የማንተባበር፣ እንደድመትና ጥንቸል ወልዶ የመብላት ሾተላይ
የተጣባው ጠባያችን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ጅል ዐመል ያከናነበን በመሆናችን እንጂ በተስፋ መቁረጥ የጽልመት ማዕበል
ተውጦ እየተንገላታ የመከራ ኑሮ ለሚኖረው ምሥኪን ሕዝባችን የምናስብ ብንሆን ኖሮ ይህን አዲስ ተስፋ – ይህን የጋራ የመረጃ
ማዕከል ካላንዳች የመቋረጥ ሥጋት ቀጥ አድርገን መያዝ በቻልን ነበር፡፡ ግን እባብ የልቡን አይቶ እንዲሉ የየልባችን ሃሳብና
ናፍቆት ለየቅል በመሆኑ ይመስላል ከመተባበር ይልቅ ተለያይተን ለጥገናም በሚያስቸግር መልክ ተሰባብረን መኖርን መረጥንና
ስደትና እንግልት የተመቸን ያህል በየሀገሩ የሰው ጫማ ሥር ወድቀን የምናገኛትን ሣንቲም ከቁም ነገር ጥፈን ውርደትንም
እንደክብር ቆጥረን ለመኖር ያህል ብቻ እንኖራለን – ምን የመሰለች ቆንጆና የ13 ወር ፀጋ የፈሰሰባት ገነት ምድር እያለችን የሌሎች
ባርያ መሆን አማረን፡፡ አያናድድም? መቼ ይሆን ሰው እምንሆን? መቼስ ይሆን የሚቆጨን? መቼ ይሆን ከእልህና ከቂም በቀል
ልክፍት ተፈውሰን ለጋራ ቤት በጋራ የምንነሳው?
በመሠረቱና እንደኔ ኢሳት የገንዘብ ልመና ውስጥ መግባት አያስፈልገውም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይና ለሀገር
በሚጠቅም ኢሳትን በመሰለ የዜና መድረክ ላይ የገንዘብ ልመና ሲደረግ በበኩሌ አዝናለሁ፤ አፍራለሁም፡፡ ብዙዎቻችን የዜግነት
ግዴታን ምንነት ለማወቅ ባለመቻላችንም እንዲሁ አፍራለሁ፡፡ ማን ለማን ገንዘብ ይለምናል? ጤናማ የእምነት ተከታይና ጤናማ
ሀገር ወዳድ ሰው የሃይማኖትና የዜግነት ግዴታውን ሳይለመንና ነጋ ጠባ ሳይጎተጎት መወጣት ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ብዙ
ሊያናግረኝ የሚችለውን የዐውደ ምሕረቱን ነገር ለጊዜው ልተወውና ኢሳት ላይ ላተኩር፡፡ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ኢሳትን
ከጠላት ጎልያዳዊ ጦር መጠበቅ ነውና፤ በኃይል ሚዛን ብቻ ሳይሆን በጠባይም እንደጎልያድ የሚመሰሉት ወያኔዎች ኢሳትን ከአየር
ለማውረድ ያደረጉትን ቀጣይነት ያለው ሙከራና ስኬት እናውቃለን – ሊያውም በራሳችን ገንዘብና በራሳችን የፖለቲካና
የዲፕሎማሲ መስመር፡፡ እኔን መሰሉ ድሃ የኢሳት ተመልካች እንኳን ያቺው ኢትዮጵያዊነትን የምታስታውሰን የጋራ ተስፋ
እንዳትቀርብን ብለን ከመቶ ብር የማስተካከያ ክፍያ እስከ ዲሽ መለወጥና አልኤንቢ መጨመር ድረስ ሄደን ስንትና ስንት ወጪ
ማውጣታችንም ይታወቃል፡፡ ይህ ሁሉ እልህ ውሸት ነግሦብን ለምን የወያኔን ቅርሻትና ትውከት ብቻ እንድንጋት እንገደዳለን፤
የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ከሌላ አቅጣጫስ ለምን አናገኝም ከሚል ቁጭት ነው፡፡ ይህን ወርቃማ ዕድል ማጣት ለኔ ዓይነቱ ዜጋ
ትልቅ የልብ ስብራት ነው፡፡ ታዲያን የዳዊትን ወንጭፍ ለማስታጠቅ ሁላችንም በያቅማችን ጠጠር ካላዋጣን ጎልያድ ማጥቃቱን
ይቀጥላል፤ ነጻነታችንም በቶሎ አይመጣም – በቦሌም በባሌም መምጣቱ ባይቀርም፡፡ ግን ግን ልብ በሉ! በባሌ የሚመጣ ነጻነት
ባፍንጫችን ቢወጣ ይሻለናል! በቦሌ እንዲመጣ ነው መትጋና ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ያላንዳች ማመንታት በፍቅርና በውዴታ
ማድረግ የሚኖርብን፡፡ ይህን ስል ቅኔየ የማይገባው ካለ በቦሌ ስል በሁላችን ፈቃድና የደምም ይሁን የገንዘብና የዕውቀት አስተዋፅዖ
የሚመጣ ሕጋዊ ነጻነት ማለቴ ነው፡፡ በባሌ ስል ከወያኔ የተሻለም ይሁን የከፋ ግን ልክ እንደወያኔዎቹ የደም ዋጋ የሚያስከፍለን
አደገኛ የማፍያ ቡድን ማለቴ ነው፡፡ በጦር የሚገባን የንቅናቄ ጎራ አጥብቆ መፍራት ይገባል፤ ‹የአበራሽን ጠባሳ ያዬ በእሳት
አይጫወትም›፡፡ ከሚገባን በላይ ተቀጣን፡፡
ኢሳትን በገንዘብ ስናጠናክር ግን መጠንቀቅ የሚኖርብን ነገር አለ፡፡ መጽሐፉ ግራህ ስትሰጥ ቀኝህ አትይ እንደሚለው ሳይሆን የኛ
መስጠት አደጋ ሊያስከትል የሚችልበት ሁኔታ በመኖሩ መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ ዋናው ፈቃዳችን ነው እንጂ ኢሳትን መርዳት
ከፈለግን ከየትም ሆነን መርዳት እንችላለን፤ ቃል ስላጣሁ ነው ‹መርዳት› የምለው- (በግላቸው የኢኮኖሚ ችግር በሌላቸው ደህና
ኗሪ ኢትዮጵያውያን ዜጎች የተቋቋመው ኢሳት እኔን ሊረዳ ቆሞ ሳለ ኢሳትን እኔ ስረዳው አልታይህ ስለሚለኝ ነው ቃሉ
የሚከብደኝ – ጭንቀቴን ተረዱልኝ – ምናልባት መደገፍ፣ ማገዝ፣ መተባበር… ሊሆኑ ከቻሉ አላውቅም፡፡ ግን ለጋራ የሀገር ጉዳይ
አንዱ ረጂ ሌላው ተረጂ አይሆኑም ብዬ አምናለሁ – በትክክል ተረድታችሁኝ ከሆነ፡፡)
ኢሳት ከተቋቋመ ሦስት ዓመታት ያህል ሆኑት፡፡ በግል ገንዘባቸውና ጥረታቸው ይህን ውድ ገጸ በረከት ለሀገራቸው ሕዝብ
ያበረከቱትን ወገኖች እግዚአብሔር ይባርካቸው፤ ዘራቸውንም ያለምልምልን፡፡ ለጓደኛው የአንድ ብር ዳቦ ገዝቶ ወስፋቱን
በመሸንገል ሰኞን ማክሰኞ ማድረግ የሚያቅተው ገብጋባ ነገር ግን በምሽት ክበባት እየደነሰና ከታዳጊ ሕጻናት ጋር በወሲብ ዳንኪራ
ልቡ እስኪወልቅ እየጨፈረና እየደነሰ በሺዎች የሚገመት ገንዘብ አላግባብ የሚያባክነው ዜጋ ቁጥር ቀላል ባልሆነባት ሀገራችን
ውስጥ እንደዚህ ያለ ታላቅ ቁም ነገር መሥራት በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ ታላቅ ገድል ነውና እነዚህን ሰዎች በሞትም ሆነ
በሕይወት ዘመናቸው ፈጣሪ በፀጋው ይገብኝልን፤ እንደሃይማኖተኝነቴ ኅያው እግዚአብሔር የመንግሥቱ ወራሽ አድርጎ
እንዲመዘግብልኝ ዘወትር እጸልያለሁ፡፡ የሆኖ ሆኖ ‹ጓደኛህ ማር ቢሆን ጨርሰህ አትላሰው› ይባላልና እንደገናም ‹ፈረስ ያደርሳል
እንጂ አይዋጋም› እንላለንና ጅምራቸውን ከዳር ማድረስ ያለብን ሁላችንም ተጋግዘንና ተባብረንም ሊሆን ይገባል እንጂ ‹በገቡበት
ይወጡት፤ እኛን ምን አገባን፤ ሺም ታለበ መቶ ያው በገሌ፤ ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቅ…› ብለን ለነሱ ብቻ የምንተወው ጉዳይ
አይደለም፡፡ እንደዚያ ካልን ፈሪዎች ብቻ ሳንሆን ሀገር የለሾች ነን፡፡ እንደዚያ ካልን ለልጆቻችን ማፈሪያና መጠቋቆሚያ የሚሆን
መጥፎ ታሪክ መተዋችንን አንርሳ፡፡ እንደዚያ ካልን ‹እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል› ካለችው እንስሳ የማንሻል አሞስኪ ወይም
ሰልቃጭ እንስሳ እንደሆንን አንዘንጋ – ይህን እያልኩ ያለሁት አባታችሁ ወይም ወንድማችሁ የምሆን እኔ ምሥኪኑ ዜጋ ዳግማዊ
እንጂ የኢሳት የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ እንዳልሆነ እዚህችው ላይ ማስታወስ እፈልጋለሁ፤ ለሀገሬና ስለሀገሬ የሚሰማኝን ሳልፈራና
ሳላፍር የመናገር መብት አለኝ፡፡ መከራውን ለጥቂቶች ደስታውን ለሁሉም የማድረግ የቆዬ ፈሊጥ ማስቀረት አለብን፡፡ ነገ
ይታዘበናል፤ ነገ ማለት ደግሞ ታሪክ ማለት ነው፡፡ እንዲህ የምለው ለስብከት ሳይሆን ለጋራ የአሁንና የወደፊት ጥቅም ነው፡፡
እየቻልን አለማድረግ መረገም ነው፡፡ መረገምን ማስወገድ ደግሞ ይቻላል፤ ቶሎ መንቃትና መፍትሔ ሥራዩን ማፈላለግ ነው፡፡
የተኛንበት ምክንያት ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡ አንድም አለማወቅ ወይም የግንዛቤ እጥረት ሊሆን ይችላል፡፡ አንድም ግዴለሽነት
ሊሆን ይችላል፡፡ አንድም በዓላማ ደረጃ ሲታይ የአጥፊዎች ወገን ሆኖ መገኘትም ሊሆን ይችላል፡፡ አንድም ገብጋባነት ሊሆን
ይችላል፡፡ ብዙ ነው ጣጣው፡፡ የዞረ ድምሩ ግን አንድ ነው፡፡ ማገዝ የሚገባህን ክቡር ዓላማ ማገዝ በሚገባህ ጊዜ ሳታግዝ ቀርተህ
ቆይቶና ሌላ ጊዜ ወደኅሊናህ ትመለስና ልታግዘው የምትፈልግበት ሌላ ፍላጎት ቢያድርብህና ያኔ ከእልህ ሳይሆን ከእውነት እገዛህ
ሳያስፈልገው የሚቀርበት አጋጣሚ ቢፈጠር ያኔና ከዚያም በፊት ተጎጂዎቹ አንተና በአስፈላጊ የችግሩ ወቅት ልታግዘው የሚገባህ
አካል ናችሁ – ሁልጊዜም መዘንጋት የሌለብን ሃቅ ድርጊትና ቁጭት/ፀፀት ጓደኛሞች መሆናቸውን ናው፡፡ የተምታታ ነገር ተናጌሬ
ሊሆን ይችላል፤ ግን እውነት ነው፡፡ ዳሩ ዛሬ ማን ያልተምታታበት አለና፡፡
መራር አነጋገሬ የሚገባው ይግባው፡፡ የማይገባው ቢኖር ልብ ይስጠው ከማለት ውጪ ረቂቅ ነገርን በጥብጦ መጋ ስለማይቻል
ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ማወቅ ያለብን ነገር ግን አለ – ያም ማንኛውም የሕይወት እንቅስቃሴ በደግም ሆነ በክፉ ዋጋ
የሚያስከፍል መሆኑን ነው፡፡ ክርስቶስ እንዲህ አለ፡- ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ ያለ ሁሉ መንግሥተ ሰማይ አይገባም፤ አጭር ቃል፡፡ ዛሬ
ብዙዎቻችን ብቻችንንም ሆነ ከጠላቶች ጋር ወግነን እንደፈለግን በሕዘብ ላይ ብንፈነጥዝና ብናሸካንን ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነውና
ላያችን ላይ የሚያሻካንን ነገር ከላይ ወይም ከታች ይላክብናል – የላዩ ግዴለም፤ መፍራት የታቹን ነው – የሰውን(መርምረህ
ድረስበት!)፤ ዓለም ዘወርዋራ ናት – ለማንም አትሞላም አትጎድልምም፡፡ ዛሬ ያለህና ሞልቶ የፈሰሰ የሚመስልህ ነገር ምናልባት
ትናንት ያጣኻውን ባንተ በጭብጧ ሕይወት ግን ሲደርስ ያላስተዋልከውን ወይ ከናካቴው ያልደረሰብህን ሊሆን ይችላል፤ ምድር
የዕዳ ክፍያ መድረክ መሆንዋን አንርሳ – የአባባ ተስፋየን እረኞች ያሳድዱት የነበረውን ነብርና ከአደጋ ያዳነውን ሚዳቆ ይሁን
ድኩላ ታሪክ አስታውስ – ቀን ሰጠኝ ብለህም በሰውና በሀገር ላይ አትፏልል፤ ሁሉም ነገር እንደጤዛ ረጋፊና እንደጉም በናኝ ነው
– ነገ ጥርኝ አፈርና ብናኝ አቧራ የሚሆን ሰው ደግሞ ቆሻሻ ታሪክ ትቶ ላለማለፍ መትጋት ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ ዋናው ሰው
የመሆን መፍትሔ ወደኅሊና መመለስ ነውና ከጥፋት ጎዳና በአፋጣኝ ወጥተን ዒላማችንን ወደ ሀገራችን እናቀጣጭ፡፡ ከየገባንበት
የግል ዓለም ስንወጣ ደግሞ ኢሳትንም ባይሆን ሌላ ለሀገር የሚሠራ ጤናማ ተቋም ፈልገንና አፈላልገን በከንቱ ከምንምነሸነሽበት
ገንዘብም ሆነ አለመላው ከምናባክነው ጊዜ፣ ጉልበትና ዕውቀት ቀነስ አድርገን ለታሪካችን ማማር እንዲሁ በነጻ እናውል፤ ለገንዘብ
በገንዘብ ስለገንዘብ ብለንም ገደል አንግባ፤፤ ሁሉንም ነገር ከገንዘብ አንጻር፣ ከወጪና ቀሪ ሥሌት አኳያ ካየነው በዓለም ላይ
ስንዝር አንራመድም፡፡ እንዲህ አድርጌ ምን አተርፋለሁ የሚባለው በሀገር ጉዳይ ሳይሆን በተለይ በዘመናችን ብዙም ሰብኣዊነትና
ርህራሄ በማይታይበት በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ፡፡ እንጦርጦስ እየወረድክ ባለህበት ቅጽበት ከዚያ አዘቅት እንዲያወጣህ
ከመጣ ኃይል ጋር የሒሣብም ይን የሥልጣን ድርድር ማድረግ ሞኝነት ነው – ቀድመህ ከሞት መውጣትህን አስብ እንጂ ሰው
ሠራሹ ወረቀትና እልቅና ሊያብከነክንህ አይገባም፡፡ ለወገንህና ለሀገርህ ፈጥነህ መድረስህ ከገንዘብ በላይ ዋጋ አለው፡፡ ለማረፊያ
ሀገርህ ገንዘብህንና ዕውቀትህን ብቻ ሳይሆን እንደነኢንጂኔር ቅጣው እጅጉና አሰፋ ማሩ… ሕይወትህንም ብትሰዋ ለአንተና
ለትውልድህ ታላቅ ክብር ነው – እስኪ አስበው – ጋዜጠኛና እክቲቪስት እስክንድር ነጋ እኮ በአሥሮችና ከዚያም በላይ የሚሆኑ
እኔን መሰል የቀን ሠራተኞችን ሊቀጥርና ሊያሠራበት የሚችል ወረት ነበረው፡፡ ግን ‹ለማን ብሎ ከርቸሌ ወረደ?› ብለህ አስብ –
ሌሎችም የታሠሩት ለሌላ ሥውር ጉዳይ ሳይሆን ለሕዝባዊ ዓላማ ነው፡፡ ይህን ስልህ ሕይወትን ለሀገር መስጠት ቀላል ነው፤
ማንም በቀላሉ ያደርገዋል ለማለት ፈልጌ ሳይሆን ይህን ያደረጉና እያደረጉም ያሉ ወገኖች ስላሉ ለእነዚያ ድንቅ ዜጎች ያለኝን
አክብሮትና ፍቅር ለመግለጽና የቻለ ሁሉ አርአያነታቸውን እንዲከተል ለመጠቆም ነው፡፡ አለበለዚያ ‹የሚጠሩ ብዙዎች፤
የሚመረጡ ጥቂቶች› መሆናቸውን ዘንግቸቼ እንዳልሆነ ተረዳልኝ፡፡ ገንዘብም ሆነ ስምና ዝና አላፊ ጠፊ ናቸው፡፡ የማይጠፋና
የማይጠወልግ ለሀገር የሚያደርጉት መልካም አስዋፅዖና ሱታፌ በረከት ነው፡፡ እንደሃይማኖታዊ ስብከት አትውሰዱብኝ፡፡ ሃቁን
እየተናገርኩ ነው – ሊመርር ይችል ይሆናል፡፡ እውነታው ግን ይውና ይሄው ብቻ ነው፡፡ አጥፊና ጠፊ፣ እንዲሁም መሀል ሠፋሪና
በሀገር ጉዳይ የማይሞቀን የማይበርደን ግዴለሾች ሆነን እስከመቼም አንዘልቅም፡፡ ደግሞም ይህን ልብ እንበል፡- የጓሸው
የሚጠራበት፣ የጠራው የሚደፈርስበት ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡
ስለራሴ አንድ ምሳሌ እንድናገር ይፈቀድልኝ፡፡ እኔ ኢሳትን መደገፍ የሚያስችለኝ አንዳች አቅም ባገኝ አሁኑኑ አደርገው ነበር፡፡ ግን
አልችልም፡፡ የአለመቻሌ ምክንያት ደግሞ የወር ገቢየ የወቅቱን ገበያ ከመሸከም አቅም በእጅጉ ያነሰና ለራሴም የማይበቃ በመሆኑ
ነው – ለገንዘብ ስል ለልጆቼና ለቀሪው ትውልዴ መጠቋቆሚያ የሚሆን መጥፎ ነገር ውስጥ አለመዘፈቄና በንጹሕ ድህነት መኖሬ
ራሱም ትልቅ ነገር ነው – ድህነታቸውን ለማስወገድ ብዙ ወንጀልና ኃጢኣት የሚሠሩ ወገኖች እንዳሉ እረዳለሁና፡፡ ይህን ስል
ደግሞ ለሀገሬ ምንም አልሠራሁም አልሠራምም ማለቴ እንዳልሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ የሚጨበጥና የሚዳሰስ ነገር ባልሠራም
ቢያንስ በሃሳብና በጭንቀት ከሚዋትቱ ወገኖች ውስጥ እመደባለሁ ብዬ ስለማስብ ያ ብቻውን ያስደስተኛል፡፡ ከአጥፊዎቿ የስም
ዝርዝር ውስጥ አለመገኘቴ ራሱ ለኔ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ሁለንተናዊ ትግሉን የሚያግዝ ዕድል ቢኖረኝ ክብርና ሞገሱ ለኔ
እንጂ ለማንም አይደለምና አቅምና ችሎታየ በፈቀደ የምሳተፍበት ዕድል ቢፈጠር አላፈገፍግም፡፡ እማምላክን – አሁን አሁን
በማየውና በምሰማው በሚደርስብኝ የሕይወት እንግልትም ክፉኛ እየመረረኝ ነው፤ በሌላ አንጻር ግን በርካታ ዜጎችን ስናይ ብዙ
የሚያሳዝንና የሚያስተዛዝብ ነገሮችን እየታዘብን ነው – “ ‹ሀ› ራስን ማዳን” በሚሉት ፈሊጥ፡፡
ቀደም ብዬ ለመጠቆም እንደሞከርኩት ለአልባሌ ነገር ስንትና ስንት ገንዘብ የሚያወድሙ ሰዎች ቆም ብለው ቢያስቡና ለዚህ
ለተቀደሰ ተግባር – ለግብር ይውጣና ለታይታ ሳይሆን – ለዓላማ ብለው በቋ ሚነት አንዳች ነገር ቢመድቡ ኢሳት በቀላሉ እያደገና
እየተመነደገ ይሄዳል፡፡ በቁጥ ቁጥ የልመና ገንዘብ አንድን የመረጃ ተቋም ማሳደግ ግን አይቻልም፡፡ መስዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡
እርግጥ ነው እስካሁንም ቆሞ ያለው መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ በሆኑ ጥቂት ዜጎች አማካይነት መሆኑን እናውቃለን፡፡ እኔ
እያልኩ ያለሁት ግን ለጋራ ዓላማ አንዱ ለማኝ ሌላው ተለማኝ እንድንሆን መጠበቅ እንደማይገባንና ሁሉም ተባብሮ ይህን በወያኔ
መንደር ሽብርና ብርክ የለቀቀ የመረጃ ማዕከል መደገፍ እንደሚገባ ነው፡፡ ‹ወንድሜ ታሟል እባካችሁን የቻላችሁትን ዕርዱኝና
ላሳክም› ማለት አንድ ነገር ነው – ከዚያ ይሠውር እንጂ ይቻላልም፡፡ ‹በሀገራችን ላይ የሚፈጸምን ግፍና በደል ለሕዝባችንና
ለዓለም እናጋልጥ፤ ይህን ግፍና በደል በጋራ ተቋቁመን ነጻ ሀገር እንፍጠር…› ለማለት ግን ልመና በጭራሽ አያስፈልግም፡፡
እንደዘመነ ኢሕአፓ ለሞት ተልእኮም እንኳን ቢሆን በእኔ እቀድም እኔ እቀድም ዕድሉን ለማግኘት መሽቀዳደም ሲገባን የሁላችን
ጉዳይ ለተወሰኑ ዜጎች የተጣለ ያህል ቸልተኛና ግዴለሾች መሆን አይጠበቅብንም፡፡ የሀገራችን ጉዳይ ለአንዱ ሸክም ለሌላው
ከመጤፍ የማይቆጠር ገለባ ሆኖ ማየትም ያሳፍራል፡፡
አንድ እውነት ልንገራችሁ ደግሞ፡፡ ይህን ሁሉ ማስፈራሪያም በሉት ዛቻ ለእንቅልፋሞች የምወረውረው ኢሳት ቢቋረጥ
የሚከተለውን አደጋ ከግምት በላይ ስለምረዳ ነው፡፡ ሕዝቡ በአሁኑ ወቅት ኢሳትን የሚመለከተው እንደመሲሕ ነው፤ የብዙ ሰው
መጽናኛ ሆኗል፡፡ መሲሕ ማለት በዚህ በኔ ዐውድ የአንድን ነገር መምጣት የሚያበስር እንደመንገድ ጠራጊ የሚቆጠር በጎ መፃኢ
ነገርን አመላካች ማለት ነው፡፡ ወያኔ እንደጦር የሚፈራውም አለምክንያት አይደለም፡፡ ወያኔዎች የሚፈሩትን ነገር ለምን
እንደሚፈሩ ጠንቅቄ አውቃለሁ፤ በፈሩት እንደሚጠፉም ያውቃሉ፡፡ ስለዚህም ነው ኢሳትንና እነእንቶኔን የሚፈፈሩት –
ስማቸውም ሲጠራ ገደል እስከመግባት በሚያደርስ ድንጋጤ የሚዋጡት፡፡ ለዚህም ነው እኔም ኢሳትን የወደድኩትና ከጎኑ
ለመቆም የቆረጥኩት፡፡ ለዚህ ነው ለኢሳት የማልሆነው የሌለኝ – ምን ማለታችሁ ነው፡- 450 ብር ሆጭ አድርጌ እኮ ነው በዚያን
ሰሞን ለስንተኛ ጊዜ ኢሳትን ያስገባሁት፡፡ …
ኢሳት ጉደለት አለው የለውም የሚለው የዘበናዮች አነጋገር ለጊዜው የሚያነጋገር አይደለም – እየየም ሲዳላ ነው ጌቶቼ፡፡ ጉድለት
እንኳንስ በችሮታና በቡገታ ገንዘብ የሚተዳደር አንድ አፍሪካዊና ኢትዮጵያዊ ታዳጊ የዜናና መረጃ ማዕከል ይቅርና ቢቢስና
አልጀዚራን በመሳሰሉ በቢሊዮኖች ዶላርና በሺዎች ዕውቅ ባለሙያዎች የሚተዳደሩ ዕድሜ ጠገብ ጣቢያዎችም ስንትና ስንት
ጉድለትና እንከን አለባቸው፡፡ ይህን እውነት የኢሳት ኃላፊዎችም የሚያጡት አይመስለኝም፡፡ ዐይን ውስጥ ያረፈች ትንኝን በለስላሳ
ነገር በብልሃት እንደማውጣት በወስፌና በጉጠት የሚደነቁል ሰው ካለ ስህተቱ የትንኟ ወይም የዐይኑ ሳይሆን ትንኚትን አወጣለሁ
ብሎ የሚነሳው ጀብደኛና አቅለቢስ ሰው ነው፡፡ በሌላ በኩል ኢሳታውያን፣ ኢሳትን ሕዝብ ስለወደደውና ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን
ሥርጭትን በሚመለከት ብቸኛ የሕዝብ አለኝታና ዋስ ጠበቃ የመሆናቸው አጋጣሚ አንዳች ግርዶሽ አጥልቶባቸው ‹እኛ ፍጹማን
ነን፤ ለትችት የሚያጋልጠን አንዳችም ነገር አንሠራም፤ የሚተቸን ሰው ካለም ወያኔ ነው…› የሚሉ አይመስሉኝም – እንደዚህ
ዓይነት ነገር በግልጽ አይደለም በምልክትም እንኳን ቢያሳዩ ሌላውን ተውት እኔና ምሥኪን ብዕሬም በቻልነው ሁሉ
እንታገላቸዋለን፡፡ ምክንያቱም የሕዝብ ተስፋ መጨለም የለበትም፡፡ ተራርመን፣ ተወቃቅሰን፣ ተማምረን ይህችውን ያለችንን
ብቸኛ መድረክ በመጠቀም ለሀገራችን ነጻነት መብቃት ይኖርብናል፡፡ የሦስት ብር ገመድ የሁለት መቶ ብር ዶሮ ይዞ መጥፋት
የለበትም ባይ ነኝ፡፡ (የስሙኒ ዶሮ የብር ገመድ … ይባል ነበር ዱሮ!)
እርግጥ ነው – ይህ ሲባል እዚህም ሆነ እዚያ ኮሽ አይበል ማለት አይደለም፤ ይሄኛውም አንዱና ሌላው መጥፎ ጫፍ ነው፡፡
መወቃቀስና መተቻቸት አንዱ የዴሞክራሲ ባህል በመሆኑ መለማመድ ያስፈልጋል፡፡ በነባሩ ኢትዮጵያዊ የመኮራረፍና የመጠላለፍ
ባህል በትንሹም በትልቁም እጅጌያችንን አንሰብስብ እንጂ ስህተት በመሰለ ነገር ላይ በጨዋነት መነጋገሩ ተገቢ ነው – መጥፎው
እንዲያውም እየተፈራሩ አለመነጋገሩና ቅሬታን እንደቁስል እየሸፋፈኑ ለበለጠ የማይድን ምርቀዛ መዳረጉ ነው፤ እናም በሰለጠነ
መንገድ እንወቃቀስ፣ ስንወቃቀስም በግል ስብዕና ውስጥ እየገባን “እንዲህ ነህ፤ እንዲህ ነበርክ፤…” ከማለት ተቆጥበን በወቅቱ
ጉዳይ ላይ ብቻ እናተኩር እንጂ ወደሽመልና ግላዊ የሽሙጥና አግቦ ዘመቻ አንግባ፡፡ ከዚህ በተያያዘ እንደፌንጣ እየዘለሉ
በዶንኪሾታዊ ምናብ አከል የጠብ ያለሽ በዳቦ ልክፍት መጠመድ ጤናማነት አይደለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ሰው መለየትና
ማስተማር፣ መገሰጽና ካልተቻለም በጊዜ ማራቅ በሥራውም ተቀይሞ አጉል እልህ ውስጥ አለመግባት እንደሚያስፈልግ መረዳት
ጠቃሚ ነው – በዚህ ዓይነቱ ሸውራራ አካሄድ በውነቱ ብዙ ተጎድተናል፤ ብዙ ሰውና ብዙ ጥረትም ባክኖብናል፡፡ በዚህ ዓይነቱ
የማይጠቅም የሃሳብና የተግባር ግጭት ውስጥ መግባት የጊዜ፣ የገንዘብ፣ የጉልበትና የትኩረት ‹ሪሶርስ›ን አላግባብ እያባከኑ ትግልን
ማቀጨጭ ያስከትላል – ልክ እንደ እስካሁኑ፡፡
ከጀመርኩት ሃሳብ እንዳልወጣ እንጂ ቅሬታዎችን በተመለከተ አንድ ሃሳብ አለኝ፡፡ እንዲህ ቢሆንስ – ከታወቁና ከታላላቅ
የሁሉም ክልሎቻችን ሰዎች አንድ ትልቅ ኮሚቴ እናቋቁም – ከተቻለ ከሀገር ውስጥም ካልተቻለ ግን በውጪ ከሚኖሩ፡፡ ይህ
ኮሚቴ በታወቁ የሃይማኖት ሰዎች እንዲመራ እናድርግ፡፡ የዚህ ኮሚቴ ዋና ተግባርም የሀገራችንን ፖለቲካ በሚመለከት የሚፈጠሩ
ግጭቶችንና አለመግባባቶችን በሰከነ ሁኔታ እየመረመረ ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን የሚያስታርቅና ወደመግባባት የሚያመጣ
ይሁን፡፡ የዚህ ኮሚቴ ቢሮም በግድ የታወቀና የተወሰነ ቦታ ላይ ሊሆን አይጠበቅበትም፡፡ ዘመኑ የቴክኖሎጂ ስለሆነ በያሉበት
በኢሜይልና በመሰል የቴክሎጂ ውጤቶች ሊካሄድ ይችላል፡፡ ይህ ኮሚቴ እያጣራ አጥፊን የሚገስጽበትና ከማኅበር እንዲገለል
የሚያወግዝበት ብልሃት እንዲኖረው ይደረግ፡፡ ኮሚቴው ተዓማኒነትና ተፈቃሪነት ካገኘ በዚህ ኮሚቴ ሥር በባህልና
በሃይማኖታዊ ትዕዛዛት እየተዳኘ አፈንጋጭ የሚስተካከልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ሃሳቡን ‹የሚገዛኝ›
ባገኝ በ‹ነጻ› እሸጣለሁ፡፡ ተጨነቅን እኮ ጎበዝ! አዳሜ እየተነሣ ‹እንዲህ ካልሆነ እንዲህ እሆናለሁ/አደርጋለሁ!› ይላል፤ ገና
በሳይጋገር ተቦካ እምቡር እያለ በረት እንደሚበጠብጥ ፊጋ በሬ ስብስቦችን ስለሚያውክ የጋራ ትግል ጥረቶች ከመጀመራቸው
እየመከኑ የጠላት መጫወቻና መሣለቂያ ሆነን ቀረን፤ እኛም ለሀፍረትና ለውርደት እንዲሁም ለትዝበት እንደተዳረግን መኖር ዕጣ
ፋንታችን ሆነ፡፡ ይሄ ‹ታዋቂ ግለሰቦች› የሚሉት ፈሊጥ ደግሞ አንዱ የጠመሰን ነገር ነው፡፡ ታዋቂነትን እኛው እንፈጥረውና መልሶ
እኛኑ ይጨቁነናል፡፡ ምን ዓይነት ፍርጃ ነው? እኛው ቁጭ ብለን ሰቅለን ቆመን ማውረድ ያቅተናል፡፡ እኔ ታዋቂነትን የምረዳው
ከትህትናና ከጥበብ ጋር ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲገባ ትርጉሙ የማይለወጥ ወይ ቢያንስ የማይጣመም ነገር ጠፋና የኛ ሀገር
ታዋቂዎች ሥልጣኑም ምኑም ምናምኑም ‹ከኛው ግዛት አይውጣ› ከሚል ይመስላል አሽርጋጅና አከንፋሽ ቲፎዞም ከጎናቸው
በማሰለፍ ጭምር ብዙ የፖለቲካና ሲቪክ ማኅበራትን ሲያውኩ ይስተዋላል ይባላል፡፡ ይሄ ታዋቂነትና ዝና የሚሉት አስካሪ መጠጥ
ናላን ከሚያዞር እንክርዳድ የሚጠመቅ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ማን ነው ያ አንድ የቀድሞ ‹ወዳጄ› በታዋቂነት መርዝ ጭንቅላቱ ዞሮ
በየስብሰባው ሲኮፈስ ባጅቶ አሁን እንደፈሳች ጅንጀሮ ብቻውን ይንከላወሳል ሲሉ ሰማሁ፡፡ አሁን የሚያስፈልገን ሐኪም ለዚህ
ዓይነቱ በገንዘብም ይሁን ወይ በትምህርት ልሂቅነት ወይም በአንድ የታሪክ አጋጣሚ ዕውቅና የሚያገኝ ሰው ያገኘው ስመጥርነትና
የሕዝብ ፍቅር ራሱን እንዳያዞረውና ወደመታበይ እንዳያመራ የሚረዳው መድሓኒት መፍጠር የሚችል ብልህ ሰው ነው፡፡ በዚህም
ክፉኛ ተጠቅተናል ጎበዝ፡፡ የፈረንጅ ታዋቂ አይታበይም ይባላል – የኛ ግን ገና ከመታወቁ አናቱ ላይ ቂብ የሚልበት ዛር ቢጤ አለ
አሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ሌሎችን በዐይኑ እንትን ማየት ይጀምራል፤ ከእርሱ በላይ ሰውም ላሳር ነው፡፡ ትልቅ መረገም!
ለመሆኑ መቼ ነው ሰው መሆናችንን ለዓለምና ለኛው ለራሳችን የምናሳየው? መቼ ነው ታላቆች እንደነበርን፣ አስታራቂዎች
እንደነበርን፣ ምራጮች ሳንሆን መራጮችና ተመራጮች እንደነበርን የምናስመሰክረው? መቼ ነው ከታጥቦ ጭቃነት የምንወጣው?
መቼ ነው ቀፍድዶ ከያዘን የምቀኝነትና የተንኮል አባዜ የምንፈወሰው? መቼ ነው በስኬታማ ወገኖች ዐይን ላይ ሚጥሚጣና በርበሬ
መነስነሳችንን የምናቆመውና ‹ኦ! ጥሩ ሠራህ! እባክህን ወንድሜ እኔም እንዳንተ እንዲሳካልኝ ምከረኝ!› እያልን እርስ በርስ
የምንደናነቀውና በልበ ቀናነት የምንመካከረው ? መቼ ነው ከባንጠጣው እናደፍርሰው የጠነዛና የገለማ ባህል ራሳችንን ነጻ
የምናወጣው? መቼ ነው ራሳችንን ከቀፍዳጅ አመለካከትና አስተሳሰብ ነጻ ወጥተን ሀገራችንን ነጻ የምናወጣው? በሀገር ውስጥና
በውጪ በስደት የሚንገላታው ወገናችን ችግር የሚገባን መቼ ነው? ከግል የሥልጣንና የሀብት ማጋበስ ፍላጎት ወጥተን መቼም
ለማይሞት የሀገር ክብርና የወገን ፍቅር የምንማረከው መቼ ነው? የወገናችን ቁስል እንደራሳችን የሚሰማንና ሌት ከቀን
የሚጠዘጥዘን መቼ ነው? ወያኔ ካጠመደብን የክፍፍል የፈንጂ ወረዳ ራሳችንን ነጻ የምናወጣው መቼ ነው? ከሥልጣን ሱስና
አራራ የምንላቀቀው መቼ ነው? ከአፍ እስካፍንጫችን ማሰቡን አቁመን ሰፊ የአስተሳሰብ አድማስ ባለቤቶች የምንሆነውና
ከመሳቂያነት የምንወጣው መቼ ነው? መቆሚያና ሁነኛ ምላሽ የሌላቸውን እነዚህን መሰል ብዙ ጥያቄዎች መጠየቅ ይቻላል፡፡
እባካችሁን ጊዜ እየቀደመን ነውና አሁኑኑ እናስብበት፡፡
ኢሳትን በሚመለከት ግን በኢትዮጵያ ሕዝብ በዐይኑ በብረቱ እንደመምጣት ነውና በዚህ ተቋም ላይ እጃችሁንና ሁለንተናችሁን
ያነሳችሁ ወገኖች ሶብሩ – አደብ ግዙ፡፡ በጥፋት መንገዳችሁ የምትጓዙ ከሆነ ወያኔ ባትሆኑም እንኳን የሕዝብ ችግርና ብሶት
የማይገባችሁ ደናቁርት ወይም ግዑዛን ድንጋዮች ናችሁና የታሪክ ፍርድ በእናንተና በትውልዳችሁ ላይ ይውረድ፡፡ ኢትዮጵያን
እያጠፉ ያሉ ወገኖቻችን የእርግማን ውጤቶች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ የእናንተ የተረገመ ትውልድ ግና ሌላ የመከራ አዙሪት
በሀገራችን ሕዝብ ላይ ሳያስከትል በእንጭጩ እንደጤዛ ይርገፍ፡፡ በሀገርና በሕዝብ የሚቀልድ ከአሁን በኋላ የዶግ አመድ ይሁን፡፡
ሳትፈሩ አሜን በሉ፤ ምናባቱ ሊጠቅመን፡፡
ኢሳት ውስጥ በግሌ የማልወደው ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ያ ግን ከኢሳት አጠቃላይ ተልእኮ ጋር በአጋም በቀጋ አይገናኝም፡፡ በዚያ
ላይ ተነስቼ ኢሳት ላይ የምዘምት ከሆነ ሳልወለድ ብጨነግፍ ይሻለኛል – እንዲህ ዓይነቱ ነገር የሚያመለክተኝ ከጤፉ ይሁን
ከበርበሬው እንደምናገኘው የሚጠረጠረው የምቀኝነት ጄኔቲክ ንጥረ ነገር የሚያሳድርብን አፍራሽ ኃይል እንደተጠናወተን ነውና
በዚህ ራቁቱን በወጣ ሰይጣናዊ መንገድ መሄዱ ይቅርብን፡፡ መወቃቀስ ካለብን በየግል የኢሜል አድራሻዎቻችን እየተነጋገርን
አለመግባባታችንንም ቢሆን በዚያው እልባት እንስጠው እንጂ ሁሉንም ተራ የመንደር ጠብና የጓደኝነት ዘመን ንትርክ ወደ ሀገር
አናምጣው፤ አሉቧልታና የግል ቅያሜ ወደሥራው ዓለም ሲዛነቅ እጅግ ጎጂ ነው፤ ያለማደግና በዚያው በአነስተኛ የአስተሳሰብ
ደረጃ ተወስኖ የመቅረትም ምልክት ነው፡፡ እንኳንስ የአሠርት ዓመታት ጠብና ቅራኔ ይቅርና አደጉ የተባሉ ሰዎች በደቂቃዎች
ውስጥ ተነታርከው በደቂቃዎች ውስጥ ቅራኔያቸውን አስወግደው በደቂቃዎች ውስጥ ሰላማዊ ግንኙነታቸው አድሰው
እንደቀድሟቸው ይሆናሉ – ማደግ ሲባል ደግሞ በአካል መንጀርገግ ወይም በሀብት የባንክ አካውንትን ማስጨነቅ አይደለም፤
እንደዚያ ዓይነቱ እንዲያውም የዕድገት ፀር እንጂ ከዕድገት ዐበይት መገለጫዎች የሚመደብ አይደለም (ከፈለጋችሁ የረጂሙ
አሥራትን ሞኝነትና የቱጃሩ እንትናዬን አጠቃላይ ብልግና ታዘቡና የአባባሌን ደርዘኝነት አመሳክሩ፤ ቁመትና ሀብት ሲበዛ
በሞኝነትና በትዕቢት ያናፍላል እንጂ አስተዋይነትን አይጨምርም – አንዳንድ በስተቀሮችን ግን ከዚህ በተቃራኒ በሚገኝ ታሳቢነት
ያዙልኝ)፡፡ እኛ ታዲያ ጅሎች ፍጡራን የሆንን ይመስል የአርባ ዓመት ጠብ እየቀሰቀስን እንደአዲስ ስንነቋቆርና ሌሎችን ሰላም
ስንነሳ እንገኛለን – ሥራ እንደሌለው ሰው፡፡ የምንገርም ፍጡራን ነን! ደግሞም ‹ኢትዮጵያውያን አስተዋይና በመቻቻል የሚኖሩ
ትግስተኞች ናቸው›ይባልልናል –‹ዶሮን ሲያታልሏት ዳይኖሰር ነሽ አሏት አሉ –እነሱ ባይሉም እኔው ብልስ፡፡ ወገን፤
ግዴላችሁም ጓዳችንንና ጉዳችንን አንደ በአንድ እንፈትሽ፡፡ ትክክለኛውን ራሳችንን ዕንወቅ፡፡ የአሁኑን ዘመን ዜጎች ከጥንቶቹ ጋር
እንናወዳድርና ጉድለት ካለብን እናስተካክል፤ መልካም ጎንም ካለን አጠናክረንና አሻሽለን እንቀጥል፡፡ የሆነው ቢሆን ታዲያ
ኢሳትን ለቀቅ እናድርግና ይልቁናስ በተቻለን መጠን በመላው አቅማችን ተረባርበን ቀጥ አድርገን እናቁመው፡፡ የግል ጠብና ቅራኔን
ከጋራ የሀገር ጉዳይ እንለይ፡፡ ደግሞም በብዙኃን የአብላጫ ድምፅ የመገዛትን ባህል እናዳብር እንጂ የኛ ሃሳብ ብቻ ተቀባይነት
ካላገኘ ‹ወዮልሽ!›እያልን በአምባገነንነት እምቡር አንበል‹ጥረታችን ነሁሉ አምባገነንነትን ለማፈራረስ እንጂ በእስካሁኑ
ማኅበረሰብኣዊ ሕይወታችን ቋቅ ያለንን ፈላጭ ቆራጭነት በአንድ ወይ በሌላ መልክ ለመመለስ መሆን የለበትም፡፡ የማያዋጣ
ጸሎት ለብራቅ እንደሚዳርግ ከኛ በላይ የሚያውቅ የለምና ጅልነታችንን በአስተዋይነት እንለውጥ፡፡ …ጋን በጠጠር ይደገፋል፤
ሃምሳ ሎሚም ለአንድ ሰው ሸክም ለሃምሳ ሰው ጌጥ ነው፡፡ እናም ኢሳትን በእግሩ ለማቆም በምንችለው ሁሉ ከልብ እንረባረብ፡፡
ልብ ይስጠን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አሁኑኑ በልዩ ጥበቡ ይባርክ፡፡ ሰውም ይላክልን፡፡ አሜን፡፡
ma74085@gmail.com
 ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ጋዜጠኛ ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳንን እንኳን ደስ ያለህ ማለት እፈልጋለሁ፤ ይህን ወረቀት ጽፌ ጨርሼ
አርትዖት ላይ እያለሁ ኢቲቪ ሦስት ላይ አንድ የቀይ መስቀል ሎተሪ ማስታወቂያ ስመለከት በሞባይል በሚላክ የሁለት ብር ሎተሪ
አማካይነት ባለ 65000(ስድስት መቶ ሃምሣ ሺ ብር)ዳብል ጋና ፒክኣፕ መኪና እንደደረሰው አየሁ –ዕድልን እግዜር
ይስጣት፤ ልጅም ይውጣላት፡፡ ደስታየ ወሰን አልነበረውም፤ እሰይ!!ለዕድገቱ ያድርግለት!በተለይ በኢትዮ.የጋዜጠኛ ኑሮ
ያሳዝናል፡፡
 ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጋዜጠኛ አሰግድ ተፈራን ሲያነጋግር የተጠቀመውን የአንቱታና የአንተታ ድብልቅ አነጋገር
አልወደድኩለትም፡፡ ጋዜጠኛና አርቲስ ባብዛኛው አንተ እንጂ አንቱ በመባል አይታወቅምና በዚህ ረገድ ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም
ነው፡፡ ሌላ አጋጣሚ ካላገኘሁ የተሰማኝን ቅሬታ በዚሁ ልተንፍሳት ብዬ ነው፡፡
 ኢሳት ፕሮግራሞቹን በጣም መደጋገሙ ላይ በጣቢያው በሚተላፍ የሕዝብ አስተያየት ሳይቀር በስፋት ትችት እየቀረበበት
ነው፡፡ በግሌ ችገሩ ይገባኛል፡፡ ይህ ችግር ሊቀረፍ የሚችለው ደግሞ ኢኮኖሚያዊ አቅሙ ሲዳብርና አጋዥ ኃይል ሲበራከት
በመሆኑ መታገስ እንደሚኖርብን ይሰማኛል፡፡ የጣቢያው የሥራ ኃላፊዎችም የሚያስቡበት ይመስለኛል፡፡ በዚህ ግን ብዙም ባንከፋ
ደስ ይለኛል፤ በመሠረቱ የፕሮግራምና የዜና መደጋገም በሌሎችም ላይ ያለ ነው –እየመረጡና ሰዓትን እየለዩ መከታተል ደግሞ
የአድማጭና ተመልካች ድርሻ ነው፡፡ ለነገሩ ጣቢያውም ለዚህ ተገቢ ቅሬታ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይመስለኛል –ለዚህ ግን
የሁሉም ዜጎችና በተለይም የባለሀብቶች ትብብር ወሳኝ ነው፡፡

Jun 24, 2013

አቶ ገብረመድህን አርአያ የዘማናችን አሉላ አባ ነጋ ተብለው በከፍተኛ ክብር ተሰየሙ

በምእራብ አውስትራሊያ በፐርዝ ከተማና አካባቢዋ ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ጁን 23 ቀን 2013 ባደረጉት ልዩ ዝግጅት ታዋቂውንየነፃነት ተፋላሚና የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ አቶ ገብረመድህን አርአያን የዘመናችን አሉላ አባ ነጋ በማለት በክብር ሰይመዋቸዋል።በዚህ ለእርሳቸው ታስቦ በተደረገው ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ እንግዶቹለአቶ ገብረመድህን አርአያ ያላቸውን ልዩ ክብርና አድናቆት በየተራ እየተነሱ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በዚሁ መሰረትም አቶገብረመድህን ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይዞ የተነሳውን እኩይ አላማና ተግባር በማጋለጥ ያደረጉት ጉልህ አስተዋጽኦ፣ በተለያዩየሚዲያ ዘርፎች በመረጃ የተደገፉ መግለጫዎችን እና ትምህርቶችን በመስጠት የከወኗቸው ሥራዎች፤ እንዲሁም ለእሩብ ምእተዓመታትያህል በጽኑነት፤ በቆራጥነትና በሕዝብ ወገናዊነት መቆማቸው በምሳሌነት በጉልህ ተጠቅሰዋል።ለአቶ ገብረመድህን ማህበረሰቡ በጋራ ባዘጋጀው በዚሁ ስነስርዓት ላይ በአረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ቀለማት በደመቀ የኢትዮጵያ ሙሉ ካርታላይ የጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ምስል የተቀመጠበት የታሪክ ማስታወሻ ከታላቅአክብሮት ጋር ተበርክቶላቸዋል። እንዲሁም ግለሰቦች በራሳቸው አነሳሽነትያዘጋጁላቸው የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል።በዚሁ ደማቅ ስነስርዓት ላይ አቶ ገብረመድህን ባደረጉት ንግግር ለሳቸው ተብሎየተደረገውን ይህን ታላቅ ዝግጅት ያልጠበቁት እንደነበር ገልጸው ለዚህ ክብርያበቃቸውን ወገናቸውን እጅግ አድርገው እንደሚወዱ፣ እንባ እየተናነቃቸውየታዳሚውን ስሜት በጥልቅ በሚነካ አኳኋን ገልጸዋል። ይህ ለርሳቸው የተደረገውየክብር ዝግጅት የበለጠ ለወገናቸውና ለሃገራቸው ሌት ተቀን ተግተውእስከመጨረሻው ለመታገል ብርታት እንደሚሰጣቸውም ተናግረዋል። እያንዳንዱኢትዮጵያዊ በርትቶ በመታገል የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ በአጽንኦትአሳስበዋል። “አገራችን የጋራ ናት፣ በመሆኑም ችግሩ የጋራችን ነው፣ እንዲያ በመሆኑም የጋራ መፍትሄ ያስፈልገዋል” በማለት ወያኔን ከስሩነቅለን እስካልጣልነው ድረስ በጥገናዊ እርምጃ መፍትሄ የማይገኝ መሆኑን አቶ ገብረመድህን አስገንዝበዋል። ለዚህም ሴት፣ ወንድ፣ሽማግሌ፣ ህፃን ሳይል ሁላችንም ተዋናይ በመሆን ቆርጠን መነሳት አለብን ብለዋል።(http://www.youtube.com/watch?v=v7FoKwDqZaY&feature=youtu.be)አቶ ገብረመድህን በተለይ አማራ በተባለው ነገድ ላይ በህወሓት እየተደረገያለው የዘር ማጥራት ድርጊት በዚሁ ከቀጠለና በአስቸኳይ እንዲቆምካልተደረገ ይህ ሕዝብ የሚደርስበት ጉዳት መመለሻ የሌለው ሊሆንእንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። ለዚህ ማስረጃም በዋናነት ሟቹየህወሓት መሪ መለስ ዜናዊ ለይስሙላ ባዋቀረው ፓርላማ ላይ እንዳመነውከ2.5 ሚሊዮን በላይ አማራ መጥፋቱን እንደገለጸ አውስተው፣ እሳቻውባላቸው መረጃ መሰረት ግን በህወሓት ምክንያት የጠፋው አማራ ከ5ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን አመልክተዋል። ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስቀላሉ ዘዴ አማራውን ማጥፋት ነው በሚለው እስትታተጂው ገፍቶእንደቀጠለበት በገሃድ እየታየ መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡም አስገንዝበዋል።በአማራው ላይ የሚደረገው የከፋ ጭፍጨፋ ሌላውን ወንጀል አደበዘዘው እንጂ ብዙ ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን እንዳለቁናእንደተሳደዱም አቶ ገብረመድህን መስክረዋል። በአፋር፣ በሲዳማ፣ በሱማሌ፣ በጉራጌ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚካሄደውጭፍጨፋ የከፋ መሆኑንም ገልጸዋል። ስለዚህም ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን ጎሰኛና ጨፍጫፊ ስርዓት በአንድነት ተነስተውታግለው በመጣል የሁሉም መብት የሚከበርበት የራሳቸው የሆነ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማምጣት እንደሚገባቸው በአጽንኦትአስገንዝበዋል።ታዳሚው በበኩሉ ለአቶ ገብረመድህን ያለውን አድናቆት ከምግለጹም በተጨማሪ፣ የሳቸውን ጥሪ እንደተቀበለው ኢትዮጵያዊ ወኔበተሞላበት ስሜት አረጋግጧል። እኚህን የኢትዮጵያዊ አርበኝነት ምሳሌ የሆኑትን ጀግና አቅፎና ደግፎ እስከመጨረሻውእንደሚንከባከባቸውም ታዳሚው ገልጿል። ምክራቸውን እና ምሳሌነታቸውን በመቀበልም ተግቶ እንደሚንቀሳቀስም አረጋግጦላቸዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘም ወያኔና የወያኔ ጥቅም አስከባሪዎች በአቶ ገብረመድህን አርአያ ላይ የሚሰነዝሩትን ማንኛውንም ትንኮሳ አምርሮእንደሚዋጋ ታዳሚው በአንድ ድምጽ ገልጿል። ለምሳሌም በቅርቡ በአቶ አብርሃም ያየህ በአውራ አምባ ድረገጽ ላይ የተሰነዘረባችውንየሃሰት ዘመቻ በመጥቀስ ይህን አይነት ተግባር የሚፈጽሙ ወገኖች ከዚህ አይነቱ አጸያፊ ተግብራቸው ተቆጥበው ለወግን እና ለሃገርበሚበጅ ተግባር ላይ ቢሰማሩ የተሻለ እንደሚሆን ታዳሚው አሳስቧል።በመጨረሻም ታዳሚው ለአቶ ገብረመድህን አርአያ የሚመኝላቸው ብዙ መስዋእትነት የከፈሉላትን እና የሚወዷትን የእናት ሃገራቸውንየኢትዮጵያን ትንሳኤ ከሕዝቡ ጋር በጋራ ድል ለማየት የሚያበቃ ረጅም እድሜና ጤንነት ፈጣሪ እንዲያድላቸው መሆኑን በከፍተኛ ስሜትገልጿል።ኢትዮጵያ በክብር ለዘለዓለም ትኑርየፕርዝና አካባቢዋ ኗሪ ኢትዮጵያውያን

“አሜሪካ አቋማን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ ናት” ክሪስ ስሚዝ "አሸባሪነትን መዋጋት የግፍ ማከናወኛ ሽፋን አይሆንም"




ኢህአዴግ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም ከአሜሪካ ጋር የመሰረተውን ግንኙነት አስታክኮ የሚፈጽመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ተገለጸ። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ የምትመረምርበት ወቅት ላይ ትገኛለች ተባለ። ኢህአዴግ ጸረሽብርተኝነትን ለአፈናና ለበጀት ማሟያ እየተጠቀመበት እንደማይቀጥል ተመለከተ።
gear 1አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው እንደራሴ (ኮንግረስማን) ክሪስ ስሚዝ ያስታወቁት ሽብርተኛነትን አስመልክቶ ጠንካራ ማሳሰቢያ በማስቀመጥ ነው።
እንደራሴ ስሚዝ የኢትዮጵያ ጉዳይ የተደመጠበትን የምክክር ሸንጎ ከዘጉ በኋላ በተለይ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት “አሜሪካ በኢህአዴግ ላይ ያላትን አቋም የምትመረምርበት ወቅት ላይ ትገኛለች” ብለዋል።
አሜሪካ ከሰብአዊ ርዳታ ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግና በተለይም ኢትዮጵያና አሜሪካ አሸባሪነትን በመዋጋት በኩል አብረው እንደሚሰሩ ያመለከቱት እንደራሴው፣ “ሽብርንና ሽብርተኛነትን የመታገል ትብብር ግን የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመርገጥ ፍቃድ ማግኛ አይደለም። የመብት ረገጣ ሽፋን ሊሆን አይገባም” በማለት የኢህአዴግና የመሪዎቹን ተግባር ኮንነዋል።
“አንድ አገር ገና ለገና ሽብርተኛነትን ለመዋጋት ከአሜሪካ ጎን ስለቆመ ብቻ የህዝብ ሰብአዊ መብቶችና የዴሞክራሲ አተገባበር ላይ ዝም ሊባል አይገባም” በማለት አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ስሚዝ፣ ሽብርን መዋጋት የኢትዮጵያ የራስዋም ፍላጎት አንደሆነ አመልክተዋል።
“ስለዚህ” አሉ ክሪስ ስሚዝ፣ “ስለዚህ የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል”
“ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በአዲስ አበባው መንግስት ላይ የማያወላውል ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ማሳየት አለባቸው” ሲሉ የተደመጡት ክሪስ ስሚዝ “ከዚህ ቀደም አርቅቄ፣ አስተዋውቄ፣ ለውይይት አቅርቤው የነበረውን ኤች አር 2003 ህግ እንደገና በማሻሻል ለድምጽ አቀርበዋለሁ” ብለዋል።
“የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ህገደንብ” የሚል ስያሜ ያለው ህግ፣ ኢትዮጵያን የሚመራው ኢህአዴግ ከአሜሪካ መንግስት ለሚፈልገው ማናቸውም ድጋፍ መሟላት የሚገባቸውን የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብት ግብአቶችን በቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ነው። እንደራሴ ክሪስ እንደገና ለድምጽ እንደሚያቀርቡት ደጋግመው የገለጹት ይህ ህግ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ አፍስሶ በአሜሪካን ጎትጓቾች (ሎቢዪስቶች) ዘመቻ ያካሄደበት ነው።
መለስን ”አሮጋንት/ዕብሪተኛ/“ በመለት የገለጹት ክሪስ ስሚዝ “ከመለስ ሞት በኋላ ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ አቅጣጫ ታመራለች” የሚል እምነት እንደነበራቸው በመናገር “የሰማሁት ምስክርነት ከዚህ የተለየ፣ ተስፋ ከተደረገው ተቃራኒ ነው” ብለዋል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ “ብዙዎች” ሲሉ በጥንቃቄ የገለጹዋቸው አካላት ከመለስ ሞት በኋላ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ መንግድ ታመራለች የሚል እምነት እንደነበራቸው ሳይሸሽጉ ተናግረዋል። በውል የተየው ነገር ኢትዮጵያዊያን ወደ ባሰበት ችግርና የመብት ረገጣ የመዘዋወራቸው ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል። ይህም አሳሳቢ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በማብቂያቸውም “አሁን ፖሊሲያችንን ዳግም የመፈተሽያ ጊዜ ላይ ነን። ቁም ነገሩ ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር መቆሙ ላይ ነው። ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር እንቆማለን” የሚል ከተለመደው የአሜሪካ አቋም የተለየ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ኦባንግ ሜቶና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የተገኙበትን የምክክር ሸንጎ ተከትሎ እስካሁን ድረስ የኢህአዴግ አቋምና ምላሽ አልታወቀም። ይሁን እንጂ ቀደምሲል ኤች አር 2003 ህግ ሆኖ እንዳይጸድቅ ኢህአዴግና ወዳጅ ባለሃብቶች ተመሳሳይ ተግባር ለማከናወን ሩጫ መጀመራቸው ተሰምቷል። በተጨማሪም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዲፕሎማሲ ጅምናስቲክ መጀመሩ ታውቋል።
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በተለያየ ወቅት መለስ በሽብርተኛ ትግል ሰበብ አሜሪካንንና የምዕራቡን ዓለም እያምታቱ እንደሆነ በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል። ሆን ተብሎ በተሽከርካሪዎች ላይ የተቀነባበረ የፈንጂ ማፈንዳት፣ ህዝብን የማሸበር ተግባር እንደሚፈጸም በማመልከት ተቃዋሚዎች ሲጮሁ ሰሚ አልነበራቸውም። የሹልክዓምድ (ዊኪሊክስ) መረጃ ይህንኑ ይፋ ማድረጉና ኢህአዴግ ራሱ ፈንጂ አፈንድቶ “አሸባሪዎች ፈንጂ አፈነዱ” በሚል እንደሚያምታታ ማጋለጡ ይታወሳል።
አቶ መለስ አሜሪካና ምዕራባዊያን ሰብአዊ መብትን፣ ምርጫንና የዲሞክራሲ መብቶችን አስመልክቶ ጥያቄ ሲያቀርቡላቸው “ጦራችንን ከሶማሊያ እናስወጣለን፣ ቀጠናው ቢተራመስ ተጠያቂ አይደለንም” የሚል ምላሽ  እየሰጡ ያስፈራሩ እንደነበር የሚጠቁሙ የጎልጉል ምንጮች “ኢህአዴግ ብር ሲፈልግና ካዝናው ሲጎድል ዘወትር የሚያነሳው የሽብርና አሸባሪዎችን የመታገል ውለታ ድርጎ ነው” ብለዋል። በ1997 ምርጫ ወቅት የተሸነፈው ኢህአዴግ በወቅቱ አሜሪካን ጫና ልታደርግ ስትሞክር “ሰራዊታችንን ይዘን ወደ ክልላችን እንገባለን። ተቃዋሚዎች ጦር የላቸውም። በቀጣናው ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ አይደለንም” በማለት አቶ መለስ አሜሪካን ጫናዋን አቁማ ከህወሃት ጎን እንድትቆም ማድረጋቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ይናገራሉ። ያም ሆነ ይህ እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ ኢህአዴግ የውጪውን ዓለም የሚጋልብበትን የፖለቲካ “ጆከሩን” ወይም “ሽብርን መታገል” መርጠው ” ካሁን በኋላ በዚህ ሂሳብ መጫወት አይቻልም” ማለታቸው ቀጣዩን የፖለቲካ ጨዋታ እንደሚያከረው ተገምቷል።

Ethiopia: Committee organised for preparation of hero welcome ceremony of Ethiopia Betty [Satire]

Satire (Joke) News, Written by Sodere Team
A committee under the name "Million Betty's" is organised to prepare for welcome ceremony of Ethiopia's Betty upon
her return from Big Brother Africa reality show.
According to sources, the committee has allocated 1 million birr to welcome Betty after a successful run on the show.
The committee organizer Atetegeb Behageru said "Betty has inspired millions during the show and we can't wait to welcome
her at Addis Ababa bole Airport."
Here is the tentative schedule of the welcome ceremony
1. Police Band plays Aster Aweke "Sebebu" at Bole International Airport
2. Government officials and invited guests welcome Betty
3. Betty will speak about her experience at Big Brother and how she plans to inspire millions of Ethiopians
4. Men-only event with Betty.
In completely unrelated news, Alemneh Wasse is planning to interview Betty when she arrives.
Email Alert: With our e-mail alerts, you will get everything from breaking news about Ethiopia to the days most popular videos, drama and stories sent straight to your inbox. Sign up for email alerts.

Jun 23, 2013

የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል

ዛሬ ወያኔ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያፈናቀላቸው አማሮች የመጀመሪያዎቹ የወያኔዎች የጥቃት ሰለባዎች አይደሉም። የመጨረሻዎቹም አይሆኑም። ወያኔ ከነ ጸረ አማራ ፖሊሲው በስልጣን እስካለ ድረስና በአማራ ስም አማራውን እያፈኑ፣ እየሰለሉ ከወያኔ ፍርፋሪ እየለቀሙ ለመኖር የቆረጡ ከአማራው መሃል የወጡ ከሃዲዎች አማራውን መቆጠጠር እስከቻሉ ድረስ የአማራ ህዝብ መራቆት፣ ስደት፣ ውርደት፣ ሰቆቃና ሞት የማይለዩት ህዝብ እንደሆነ ይቀጥላል።

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ይህን በእብሪትና በጥላቻ የተሞላ በወያኔ የሚፈጸም በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የባላጌዎች ጥቃት ማስቆም የሚቻለው የወያኔን እብሪት በጠመንጃ እና በተባበረ የህዝብ አመጽ ማስተንፈስ እስከተቻለ ብቻ ነው ብሎ ያምናል። እስካሁን ወያኔ በከንቱ ያፈሰሰውን የንጹሃን አማሮች ደም መፋረድ የሚቻለው ከጠምንጃ አፈሙዝ በሚወጣ እሳት ብቻ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል። ከንፈር መምጠጥ፣ ዋይታ፣ ኡኡታ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰላማዊ ሰልፍና በየፈረንጅ በር ደጅ መጽናት ወያኔ የአማራን ህዝብ ቅስም ለመስበር የወያኔ እንጨት ሰባሪና ውሃ ተሸካሚ አድርጎ፣ ነጻነቱንና ክብሩን ገፎ አዋርዶ ለመግዛት የዘረጋውን መርሃ ግብር እንዲያጥፍ አያደርገውም።
ወያኔ ይሉኝታ ያልዘራበት፣ ትእግስትን እንደፍራቻ፣ አርቆ ሳቢነትን እንደሞኝነት የሚቆጥር በአማራው ላይ ቂምና ጥላቻን ሰንቆ የተነሳ ጨካኝ ድርጅት ነው። ይህን ድርጅት ስለጀግንነቱና ስለወርቅ ዘርነቱ እጅግ የተሳሳተና የተጋነነ ግምት ያለው፣ ማንም ምንም አያደርገኝም በሚል ትምክህት ተወጥሮ የሚኖር ድርጅት ነው። ከእንዲህ አይነቱ በራሱ ፕሮፓጋንዳና ከንቱ ውዳሴ ከሰከረ ድርጅት ጋር የሚደረግ ትግል ያለምንም መወላወል በከፍተኛ እልህና ጭካኔ የሚካሄድ ብቻ ነው። የአማራውን ሰቆቃ ለማስቆም ወያኔ “እዩኝ እዩኝ” እንዳለለ “ደብቁኝ ደብቁኝ” እስከሚል የሚዘምቱበት እና ክንዳቸውን የሚያሳዩት ጀግኖችን ይሻል። ከወያኔ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው ገድለው ለመሞ ት የቆረጡ የወገን ደምመላሾችን ይጠይቃል። ቤታቸውን ዱርና ገደሉን አድርገው፣ “ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል” የሚሉ ቁጡዎችን ይፈልጋል። የአማራውን ህዝብ እልቂት ለማቆም፣ የወንድ ልጅ እናት በገመድ የምትታጠቅበት፣ ልጇን አሞራ እንጂ ሰው የማይቀብርበት ሌላ ታሪካዊ ዘመን መምጣቱን ሁላችንም መቀበል ይኖርብናል።
የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል አባላት ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በሚያሳየው እብሪት ተቃጥለናል። በግነናል። የእዚህ እብሪት ማርከሻ ጠመንጃ ነው፡ እሳትና አርር ብቻ ነው ብለናል። ሌላው ሁሉ አማራጭ ተፈትሿል፣ተሞክሯል፣ታይቷል ሌላ አማራጭ የለም ብለናል። የቀረው አንድ ምርጫ ነው፦:መሞ ት ወይም መግደል ። እኛ ይህን አውቀን ከያለንበት ተጠራርተን የአማራን ህዝብ በቀላሉ ልንደርስበት በምንችልበት ምድር እየተሰባሰብን ነው። የከፋህ፣ የመረረህ፣የተበደልክ በቃኝ ያልክ ና ተቀላቀለን፣ የወገናችንን የአሳርና የመከራ ዘመን ማብቃት በወያኔ ቀብር ላይ እናረጋግጥ ።
ውድመት ለአማራ ህዝብ ጠላት ለዘረኛው ወያኔ!!!!!!!!!
ድል በወያኔ ለሚረገጡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!!!!!!!!!!!!
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ

tplf addis

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::
ደርግ
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::
ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::
ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ ወር 1966 ዓ.ም. ተሰብስበው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው “ኢትዮጵያ ትቅደም ፣ አቆርቋዥ ይውደም” በሚል መርህ ስር ሰፊ ሊባል የሚችል የህዝብ ድጋፍም አግኝተው ነበር::
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የተመሰረተው አስተባባሪ ኮሚቴ ንጉሱን ከስልጣን አውርዶ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” የሚል ስም በመያዝ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀመረ:: ቀስ በቀስም ደርግ የስልጣን ወንበሩን በማመቻቸት የሃገሪቷ መንግስት ለመሆን ቻለ::
በወቅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት ሶሻሊዝም ወይም ህብረተሰባዊነት በሚባል ርዕዮተ አለም እድገት እና ብልጽግና የማይገኝበት “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ስርዓት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና ፕሮፖጋንዳ አለምን እንደማዕበል ሲወዘውዛት የነበረበው ሁኔታ ሆኖ በደርግ የተመሰረተው መንግስት ግራና ቀኙን ሳይመለከት ሶሻሊዝም በኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈጥረውን ቀውስ እና ችግር ሳያጤን እና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ሳያማክር በ1972 ዓ.ም. ኢሰፓአኮን(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) መሰረተ:: ይህንን ምስረታ ተከትሎም ደርግ አንድ እግሩን ገደል ከተተው::
በዚህ ጽሁፍ ሁለት ነገሮችን ለያይቼ በማሳየት ለማለፍ እሞክራለሁኝ፤
  1. ደርግ እንደ ፖለቲካ ተቋም እና ስርዓት
  2. መለዮ ለባሹ እንደ አገር መከላከያ ሰራዊት
ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያዊ የሆነ እና በዘመናዊነቱ በአፍሪካ ጭምር ተወዳዳሪ ያልነበረው እንደነበር ነው:: የደርግ ስርዓት ከወታደሩ በወጡ ሰዎች ቢመሰረትም ሰራዊቱ ግን በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለመሆኑ ከጥያቄ ውስጥ ሊያስግባው የሚችል አንዳችም መከራከሪያ ሊቀርብ አይችልም:: አገራችን ዘመናዊ ጦር ማደረጀት ከጀመረችበት ከሃያኛው ክፍለዘመን መባቻ ጀምሮ በስንት ወጪ እና ጥረት የገነባችውን ጦር የ “ደርግ ጦር” የሚል ቅጽል በመስጠት ከፍተኛ የሆነ የስም እና የሞራል ማጥፋት ዘመቻ የፈጸሙበት ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት ወያኔ እና ሻዕቢያ ናቸው::
ይህ ጦር ደሙን አፍስሶ ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፤ ራበኝ ፣ ደክመኝ ሳይል ወያኔ እና ሻዕቢያን እግር እግራቸውን እየተከታተለ ሲደመሥሳቸው እና ሲያጠፋቸው የነበረ የኢትዮጵያ ብርቅ ልጅ ነው:: የዛሬው የወያኔ ዘረኛ ሰራዊት ግን እንኳን ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሊከላከል ይቅርና ራሱ የወያኔ ሰራዊት ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ የአንድ ጎጠኛና ዘረኛ ታጣቂ ቡድን ነው:: አሁን ያለው በዘር የተደራጀው ቅጥረኛ እና ባንዳ ሰራዊት በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ የለም::
የደርግ መንግስት በስልጣን በቆየበት 17 አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ቀይ ባህርን የጠበቀ ፤ ከገንጣይ እና አስገንጣዮች አገሪቷን እየተከላከለ ሉዓላዊነትን የጠበቀ የኢትዮጵያ ስርዓት ነበር::
በሚከተለው ርዕዮተ አለም ቀስ በቀስ እየተዳከመ በመሄድ እንደነበረው አገርና ህዝብ ለማዳን አልቻለም:: ደርግ በተዳከመ ጊዜም ሰራዊቱ ይዳከማል:: አንድ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከመንግስት የሚቀርብለት ነገሮች ብዙ ናቸው:: ይህ አልሆነም:: ሰራዊቱም መንግስት በመዳከሙ ምክንያት የነበረው አልበገር ባይነት ስሜቱ እና ጀግንነቱ የውጊያ ብቃቱ ተስፋ በመቁረጡ ችግር እየፈጠረለት ሄደ ቢሆንም ግን ወያኔም ሆነ ሻዕቢያ አሁንም ፈቀቅ ሊሉ አልቻሉም:: የማይበገር የኢትዮጵያ ሰራዊት መሆኑን ያውቁታል እና::
ይህ በዚሁ እንዳለ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት መንግስቱ ሃይለማሪያም ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለቀው ዚምባብዌ ሃራሬ ገቡ:: እዛም ጥገኝነት ጠየቁ:: መሆን የማይገባውን ስራ ሰሩ:: በኢትዮጵያ ሃገራቸው ሰርተው ሂወታቸው ቢያልፍ ታላቅ ስምና ክብር ያገኙ ነበር:: ግን አላደረጉትም:: ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሰራዊት ተበተነ::
ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፕሬዚደንት መንግስቱ እግር የተተኩት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን በዜና እወጃ የኢትዮጵያ ሰራዊት የነበርከው በያለህበት ቦታ መሳሪያህን ለህወሃት(ኢህአዴግ) እና ለሻዕቢያ እያስረከብክ ወደ ምትፈልግበት ሂድ፤ ሻዕቢያም ኤርትራን ህወሃትም ኢትዮጵያን እንዲቆጣጠሩ ፈቅደናል በማለት ፍጹም ክህደት በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ እና ህዝብዋን ለደመኛ ጠላቶች አሳልፈው ሰጡ::
ያን በወታደራዊ ሳይንስ እና የጦር ውጊያ የተከማቸ እውቀት እና ችሎታ የነበረውን የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እልም ባለ ገደል ወረወሩት:: ለስንት አመታት የሃገሩን ዳር ድንበር ያስከበረ እና የጠበቀ ጦር ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. ካልምንም መተዳደሪያ እና የአገልግሎት ክፍያ በየበረሃው ተበተነ:: በስንት ሚሊዮን የሚቆጠሩ የምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ አየር ወለድ እና አየር መቃወሚያ አባላት እና ቤተሰቦች ለመከራ እና ለችግር ተዳረጉ::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔና ሻዕቢያ:: ሻዕቢያ ኤርትራን ሲቆጣጠር ወያኔ ህወሃት ደግሞ ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፈንደቀለት ጸሃይ አዲስ አበባን ግንቦት 20 ቀን 1983 ተቆጣጠረ:: ኢትዮጵያም ለፋሺስት መሪዎች ተዳረገች:: ሰራዊቱ እየጫነ ካለምንም ችግር ካለ ምንም ውጊያ ወያኔ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ:: ከግንቦት 20 ቀን ጀምሮ ወያኔ በከፊል የተቆጣጠረው ወሎ ፣ ጎንደር እና ጎጃም ብቻ ነበር:: ቀሪው የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ ደቡብ ምስራቅ-ምዕራብ ወያኔ የገባው ከሶስት ወር በኋላ ነበር እንጂ:: ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠረም:: ወደ አዳዲስ ክፍለ ሃገራት ሲሄድ ብዙ ገንዘብ በመክፈል በነዋሪዎች እየተመራ ነው:: ምክንያቱም ወያኔ ህወሃት ከትግራይ አይወጣም ነበር::
ስለሆነም ለኢትዮጵያ ነጻነትና ዲሞክራሲ ስል ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ የሚለው ከንቱ ውሃ የማይቋጥር መፈክሩ ይህ ትልቅ ምስክርነት የሚያሳየው ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደማያውቃት ነው::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ምን ይዛ መጣች? በግንቦት 20 ኢትዮጵያ አገራችን በጨለማ ጉም ተሸፈነች:: አገርና ህዝብ ጥቁር የሃዘን ልብስ ለበሱ:: ሲጠሏት እና ታሪኳን እና ህዝቧን ሲያዋርዱን ሲያንቋሽሹ በነበሩት ወያኔ ህወሃት ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተዳረገች:: ዘረኛው እና ጎጠኛው ወያኔ ህወሃት በመለስ ዜናዊ የሚመራው የማፍያ ፋሺስት ግልገል እና ግብረ አበሮቹ ጸረ ሀገር እና ጸረ ህዝብ የሆኑትን ለዘመናት የተከበረው የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው የግልገል ፋሺስቶች መንደላቀቂያ ሆነ:: እነሱም ስልጣን እንደጨበጡ ኤርትራን አስገንጥለው የቀይ ባህር ንግስት የነበረችው ኢትዮጵያ ወደብ ወይም የባህር በርዋን አጥታ አንገትዋ የተቆረጠ ዝግ አገር አደረጉዋት::
ወያኔ ህወሃት ከደደቢት ይዞት የመጣውን ህገ ደንቡን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አደረገው:: ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት አጠፋዋለሁ ብሎ ያመጣውን የዘረኝነት ህጉን በኢትዮጵያ ዘረጋ::
ይህ በዚህ እንዳለ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እና ግንቦት 20 ምን ይዞለት መጣ? የኢትዮጵያ ህዝብስ ከግንቦት ሃያ ቀን ምን ተጠቀመ? ምን እድገት አገኘ? ፍትህና ነጻነቱ እንዲሁም ሰብዓዊ መብቱስ እንዴት ሆነ? የሃገሪቷ ሃብትስ በትክክል ለህዝብ ጥቅም ዋለ ወይስ ምን ሆነ? የትምህርት እድገቱስ? የዘመናዊ ቴክኖሎጂስ ለህዝብ ተስፋፋ ወይ? ሌላም ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል:: ለሰው ልጅ አደገኛ ጠንቅ ዕጽ መስፋፋት ለምን? ሽርሙጥና መስፋፋት ለምን? ስራ አጥነት ፣ የወንጀል ድርጊት መስፋፋት እንዴት እና ለምን? የህዝብ መፈናቀል ለምን? የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ ስለምን ተደረገ? ወዘተ ::
ወደ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ከ17 አመታት በፊት ወያኔ ህወሃት እንደተፈጠረ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. የትግራይ ህዝብ የአደረበትን ስሜት ባጭሩ ልዳሥ::
ወያኔ ህወሃት በዚሁ ቀንና ወር ደደቢት በረሃ ሲወጣ የትግራይ ህዝብ የዚሁ እኩይ ድርጅት ማንነቱን አያውቅም ነበር:: ቀስ በቀስም በየቦታው ብቅ ጥልቅ ሲል የትግራይ ህዝብ አልተቀበለውም::በህዝቡ ወያኔ ህወዋት ተቀባይነት በማጣቱ የተነሳ ምክንያት ጭንቀትን ንዴት የተነሳ በሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ:: አስገድዶ ንብረቱን መውረስ እና አስገድዶ እርዳታ እንዲሰጥ ተደረገ:: ምክንያቱም የሚከላከልለት ረዳት የሌለው ህዝብ ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ጀብሃ ሶስቱ በየፊናቸው አስቸገሩት:: የትግራይ ህዝብ ከየቦታው እየተለቀመ ተገደለ::
ከዚህም ቀጠል በማድረግ ወያኔ ህወሃት በሃይማኖት ጣልቃ በመግባት ክርስቲያን ጸረ ክርስትና እስላሙ ጸረ እስልምና ሃይማኖታቸውን እንዲያወግዙ የተቻለውን ቢሰራም አልሆነለትም::
ጸረ ህወሃት እና ጸረ ሻዕቢያ እየተባሉ ያልሆነ ያላሰቡት ብዙ ፣  ብዙ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች ሃለዋ ወያኔ (06) እየገቡ እሱም/እርሳውም ተገድለው ቤት ያፈራው ሃብታቸው ተወርሰው ህጻናት አልባሌ ቦታ ወድቀው ቀርተዋል::
በየከተማው ወያኔ ህወሃት ሽብርተኞች () በማሰማራት በጠራራ ጸሃይ ብዙ ሰው ገድለዋል:: ህወሃት የትግራይን ህዝብ እንደግሉ መሳሪያ አድርጎ የሚናገረው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያ ትግሉ ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ለወደፊትም አልተቀበለውም:: አይቀበለውምም:: ህወሃት የሚቀልደው ያለ ጉልበቱ ተማምኖ ነው:: ለዚሁም ዋና ምስክር ምርጫ 97 ዓ.ም. ትግራይ ወያኔ አልመረጠውም:: ለወደፊቱም ወያኔን አይመርጥም:: ሁለቱ ሊታረቅ የማይችል ቂም አላቸውና::
ወያኔ ህወሃት የትግራይ ወጣት ሴት ፣ ወንድ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት በማያውቁት የኤርትራ በረሃዎች ሞተዋል:: እዛው አጥንታቸው ተበታትኖ መቅረቱ የትግራይ ህዝብ እስከ አሁን ደም እያለቀሰ ያለበት ጊዜ ነው::
በአጠቃላይ በትግሉ ወቅት በትግራይ ህዝብ ወያኔ ህወሃት የፈጸመው ግፍ በከፍተኛ ወንጀል የሚይስጠይቀው ነው:: የትግራይ ህዝብ ወያኔ የተፈጠረባት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. በሚከበርበት ጊዜ በየቦታው የሚጠራበት ስም አለው:: በተምቤን አካባቢ “የተረገመች ቀን” ሲላት በአድዋና አክሱም አካባቢ “የጨለማ ቀን”" ሲለው በሽሬ አካባቢ ደግሞ “የእልቂት ዘመን” ይለዋል::
ወያኔ ህወሃት በለስ ቀንቶት አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ቀን ግንቦት 20,1983  ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በደመኛ ጠላታቸው የወደቁበት እና በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ የመጣበት ቀን ነው::
ከዚሁ ቀን መነሻ በማድረግ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ የነበረው ቂም በቀል በማያቋርጥ ሁኔታ በ22 አመት የወያኔ ህወሃት አገዛዝ የወረደበት ግፍና ሰቆቃ ቀጥለን ባጭር ባጭሩ እንመልከት::
ግንቦት 21 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔ ኤርትራን አስገነጠለ:: ኢትዮጵያንም ካለ ባህር በር አስቀራት::
ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ዝነኛው ምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ ፖሊስ ወዘተ የጠላይ ጦር በማለት ይደርግ ስርዓት በራሱ ሂደት ተመናምኖ በወደቀበት ለብዙ አመታት የሃገሩ ዳር ድንበር ሲያስከብር ከጠላት ሲከላከል የነበረው ካለምንም ጡረታና መተዳደሪያ የ”ጠላት ጦር” በማለት ለልመና እና ለችግር ዳረገው:: የሚይስተዳድራቸው ቤተሰቡ በሚልዮኖች የሚቆጠር ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ተበታትነው ቀሩ:: ከትግራይ ይዟቸው የመጣ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሃገር መከላከያ ሰራዊት አደረገ:: ቀሪዎቹን ታጋዮች ደግሞ ፖሊስ ፣ ደህንነት በማለት ዘረኛ ሰራዊት በኢትዮጵያ አቋቋመ:: ይህም በምንም አይነት ኢትዮጵያን የማይወክሉ ሁሉም ከላይ እስከ ታች ለነዚህ ተሰጠ:: እነዚህም በፊናቸው በኢትዮጵያ ህዝብ አስከፊ ሰቆቃና ግድያ በህዝቡ እየፈጸሙ ይገኛሉ::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማራ:: ዘር ማጥፋቱን ገና ከ1969 ዓ.ም. የጀመረው ሲሆን በበለጠ ደግሞ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አማራው ከያለበት እየተፈለገ ዘሩን ማጥፋት ተጧጧፈ ቀጥሎም ኦሮሞ ፣ ጋምቤላ ፣ አፋር ፣ ቤኑሻንጉል ወዘተ :: በትግራይ ውስጥም አደገኛ ጠላት ናቸው የሚላቸውን በዘዴ አጠፋቸው::
ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የአማራው ቋንቋ ስለሆነ ይህ ቋንቋ የትምህክተኛና የነፍጠኛው ቋንቋ በየትኛውም ክልል እንድይነገር በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ መገናኛው እና ሃሳብ ለሃሳብ የሚለዋወጥበት ለስንት ሺህ አመታት ሲጠቀምበት የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ህወሃት እያጠፋው ይገኛል:: በየትኛውም ክልል አማርኛ መናገር በህጉ ከለከለው::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ሲያበቃ ለዘመናት ኢትዮጵያዊው ህዝብ በፈለገው ቦታ ሲኖርና በጋብቻ በደም የተዋሃደው ህዝብ ከየክልላችሁ ከሌላ ቦታ የመጣውን ተስፋፊ ህዝብ አስወጡ በማለት እርስ በርሱ በማጋጨት ብዙ ሂወት ጠፍቶ ንብረቱም ተዘርፎ በየበረሃው ተበትኖ ግንቦት 20 ቀን 1983 ይዞት የመጣውን መከራ ገፈት ቀማሽ ሆነ:: በተለይ አማራው::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጉ አልበቃ ብሎት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሱዳን በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ በምትደዳርበት ገዳሪፍ በተባለው የሱዳን ግዛት አስተዳዳሪ በነበረው ሻለቃ ጉዌን የወሰን መስመር ለጣልያኖች ይጠቅማል በማለት በ1903 እ.ኤ.አ በህገወጥ መንገድ የነደፈው የመስመር ክልል በአጼ ምኒልክ ኋላም በአጼ ሃይለስላሴ እና በደርግ መንግስት ውድቅ የተደረገው እና ተቀባይነት ያጣውን ወያኔ ህወሃት ከየት እንዳገኘው ሳይታወቅ የኢትዮጵያን የወሰን ድምበር በመጻረር ለወዳጁ ሱዳን ከሰቲት ሁመራ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ወደውስጥ ከ40 እስከ 60 ኪ.ሜ. የሚዘልቅ እና 1,600ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ለሱዳን መንግስት የአንዲት ኢትዮጵያን ሰፊና ለም መሬት የሸጠ ወያኔ የሱዳን መንግስት ለውለታው ከገዳሪፍ እስከ መቀሌ የባቡር መንገድ እንደሚዘረጋ የሃገራችንን ሉአላዊነት በመድፈር ለግል ጥቅሙ ሃገራችን እያወደመ ያለ ስርዓት ነው:: የግንቦት 20 ቀን 1983 መዘዝ::
ወያኔ ህወሃት በተፈጥሮ ባህሪው አምባገነን እና ሽብርተኛ ድርጅት እሱን የሚቃወም እና የሚፈጽመው ግፍ እንዲነሳበት አይፈልግም:: ፍላጎቱ ተሳስተሃል አትበሉኝ:: ስለኔ አትናገሩ ከሚለው ፋሺስታዊ ባህሪው በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ እንዲኖር አይፈልግም:: የህዝቡ በነጻነት መናገር እና ሃሳቡን መግለጽ ለወያኔ እንደ እሳት የሚለበልበው ለመሆን የፕሬስ ነጻነት ያገደው:: ይህም እንደ ገዢ ፓርቲ ህወሃት የታገደ ነው:: በዚሁ ፖለቲካዊ ውሳኔ የነጻ ፕሬስ በማደን ፣ በማሰር ፣ በማንገላታት ሳያበቃ ብዙ የፕሬስ ጋዜጠኞች ሃገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመከራን ስደት ተዳረጉ:: ነጻ ፕሬስ በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ::
ወያኔ ህወሃት የሽግግር መንግስት ብሎ ከሰኔ ወር 1983 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር 1985 ዓ.ም.  በስልጣን በቆየበት ምርጫ በማለት በጸረ ዲሞክራሲያዊ መንገድ በ1987 ዓ.ም. , በ1992 ዓ.ም. , በ1997 ዓ.ም. እና በ2002 ዓ.ም. በማካሄድ በተለይ በ1997ዓ.ም. ቅንጅት በተለያዩ ፓርቲዎች ቀስተ ደመና ፣ መኢአድ ፣ ኢዴሊ ፣ ኢዴአፓ-መድህን ወዘተ በተጠናከረ ማዕከላዊ ፓርቲ “ቅንጅት” ተብሎ እንደተመሰረተ እምነቱ መሰረታዊ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲና እድገት ፣ ብልጽግና ፣ ፍትህ ፣ ነጻነት ፣ ከዘረኝነት የጸዳ በምርጫው ለመወዳደር በቀረበበት ምርጫም ተካሂዶ መሉ በሙሉ አሽንፎ ሲወጣ በአንጻሩ ወያኔ -ህወሃት/ኢህአዴግ በዜሮ ተሸንፎ ከምርጫ የወጣው በጉልበቱ ምርጫውን በመንጠቅ ድምጻችን አይነጠቅም ብለው የወጣውን ሰላማዊ ዜጎች በአግአዚ ቅልብ የመለስ ዜናዊ ጦሮች ግደሉት ብሎ ትዕዛዝ በመስጠት ብዙ ኢትዮጵያውያንን ሲገደሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ በየወህኒ ቤት በማሰር ወያኔ ህዝብ ያጠፋበት ቀን የሌባው አይነ ደርቁ ወያኔ በ2002  ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ እንደልማዱ ኮረጆውን በመገልበጥ 99.6% አሸነፍኩ ብሎ ኢትዮጵያና ህዝብዋን ማውደሙን ቀጠለ:: ይህ ሁሉ ችግርን ግድያ ሰቆቃ የግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. ውጤት ነው::
ወያኔ ህወሃት በፕሮግራም እንዳስቀመጠው የኤርትራ ጥያቄ ያላንዳች ጥርጥር ሃቀኛና ታሪካዊ መሰረት ያለወ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ነው በማለት ወያኔ ያመነበት ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የማያምንበት የኤርትራ ህዝብም ያላመነበት በኢትዮጳዊነታቸእው የማያምኑ መሆናቸው አንዳች ጥርጣሬ የለውም:: ድርጊቱ የወያኔ ብቻ ነው:: ይህ በዚህ እንዳለ አሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኤርትራ ግዛት አልነበረችም ሁሉ ተከታታይ ዘመናት በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሆና ስትተዳደር እንደነበረች ሁሉ ኢትዮጵያ በትክክል የሚያውቀው ሃቅ ነው:: አሰብን በኤርትራ ካርታ ጨምሮ በ1967 ዓ.ም. ያወጣው ወያኔ ብቻ መሆኑን በግልጽ የሚታወቅ ሃቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት ይህን የታሪክ እና የሃገር ክህደት የፈጸመው ሆን ተብሎ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ያደረጉት ኢትዮጵያና ህዝብዋ ጠላት ብለው ስለአስቀመጡት የፈጸሙት ጥቃት ነው:: ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ እንደተቆጣጠረ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የባህር በሯን አጣች::
ይህን በተመለከተ ወያኔ/ህወሃት እና ሻዕቢያ እንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ ከግንቦት 5 ቀን እስከ ግንቦት 9 ቀን 1983 ዓ.ም. የቀድሞው የአሜሪካ  ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የወያኔው መሪ መልስ ዜናዊ ባሉበት ስብሰባ ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ህዝብ ስላለባት የባህር በር ያስፈልጋታል:: አሰብም ከኤርትራ ያልተካለለ በመሆኑ በአጼ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ስርዓትም ከኤርትራ ውጭ ሆኖ በወሎ አፋር የተካለለ ስለነበር ቀደም ሲልም አሰብ ከኤርትራ ውጪ ሆኖ በጣሊያንም ብዙ ያልተደፈረች የኢትዮጵያ የባህር በር እንደነበረች ይታወቃል:: አሰብ የኢትዮጵያ የባርህ በር መሆን አለበት ብለው ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጣም ተናዶ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ የወደቀች ሃገር የነበሩ አመራር አጼ ኃይለስላሴ ሆኑ ደርግ ያስቀመጡት ካርታ ህወሃት አይቀበልም:: አሰብ የኤርትራ መሬት ነው:: እኛ አሁን በኢትዮጵያ ስልጣን የምንቆጣጠረው የወደብ ችግር አይኖረንም:: ችግር አይፈጠርብንም:: ብንፈልግ ጂቡቲን አሊያም የሶማሊያ እና የኬኒያን ወደቦች እንጠቀማለን:: አሰብ የኤርትራ ስለሆነ እምነታችንም ይህ በመሆኑ አሰብ የኤርትራ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም::
ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር እና ሌሎች አደረዳሪዎች አቶ መለስ ዜናዊ አሰብን የኤርትራ ነው ፤ የወደብ ችግር የለብንም ብለው እኛንም ስለአሳመኑን አሰብ በኤርትራ ውስጥ መካተቱን ተቀብለናል በመለት ሲዘጉት ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ታሪካዊና ጥንታዊው የባህር በርዎችዋን አሳጥቶ ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም. አገራችን ኢትዮጵያን በጠላቶችዋ እጅ የወደቀችበት የኢትዮጵያ ህዝብም በድቅድቅ ጨለማ እና ጭቆና ፋሽስት ስርዓት ይዛ የመጣች ይህች ግንቦት የተረገመች ቀን ናት:: በምስራቅ-ምዕራብ-ሰሜን-ደቡብ የሚገኙ ኢትይጵያውያንም እየተረገመች ነው::
ወያኔ ህወሃት በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በለስ ቀንቶት ወሮ በተቆጣጠረበት ወቅት የኢትዮጵያን ሃብት-ንብረት ወያኔና ሻዕቢያ ተባብረው ዘረፉት:: የወላድ መሃን የሆነችው ኢትዮጵያ ተከላካይ የሌላት ሁለት ከደደቢትን ከሳህል በረሃ የመጡት ሙሉ ሰራዊታቸውን በማሰማራት ሃብትዋን ንብረትዋን ዘርፈውታል:: የተለያዩ ተቋማት ተዘርፈዋል:: ጠቅላላ ጥሬ ገንዘብዋ ተዘርፏል:: ጥሬ ህብቶቿ ተዘርፏል:: የቀራት ነገር የለም:: ለውጪ ገበያ ለሺያጭ የሚመረት ቡና ፣ ሰሊጥ ፣ አደንጓሬ ወዘተ አይን ባወጣው ዝርፊያ ቀን እና ሌሊት ተፈጽሞባታል:: ዝርፊያው በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የጀመረው እስከ አሁን ቀጥለውበታል:: ኤርትራ የቡናና የቅባት ምግብ አምራች በመሆን በአለም ገበያ አቅራቢ ሆና ከዓለም 3ኛውን ደረጃ ያዘች:: ከኢትዮጵያ በተዘረፈው ጥሬ ሃብት ዋና ገንዘብ ወያኔ ህወሃት መሪዎች 1. መለስ ዜናዊ እና ባለቤቱ አዜብ መስፍን 2.ስብሃት ነጋ 3.አባይ ጸሃዬ 4.ስዩም መስፍን 5.አርከበ እቁባይ 6.አዲስ አለም ባሌማ 7. አባዲ ዘሙ 8.ጸጋይ በርሄ እና ባለቤቱ ቅዱሳን ነጋ 9.ተክለወይኒ አሰፍ 10.ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወዘተ ሆነው ኢፈርተን አቋቁመው ስልጣኑንም ተቆጣጥረው የናጠጡ ባለብዙ ፋብሪካዎች ትልልቅ ተቋማት መስርተው ቱጃር በለሃብቶች ሆነዋል:: ወያኔ ህወሃት ወደ ስልጣን ባልበቃበት ጊዜ በአጼ ኃይለስላሴና በደርግ ስርዓት ነጻ ተቋም በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያገለግሉ የነበሩትን ብሄራዊ ባንክን ፣ ንግድ ባንክን ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ፣ እርሻ ትራንስፖርት ፣ መአድናት ወዘተ ወያኔን ስልጣን እንደጨበጠ ሁሉን ከህዝብ በጉልበቱ ነጥቆ በመቆጣጠር የሃገርና የህዝብ ሃብት የህወሃት ተቋማት ሆኑ:: ይህም ወያኔ ህወሃት በከፍተኛ ወንጀል የሚጠየቅበት ከዋናዎቹ አንዱ ነው::
ወያኔ ከኢትዮጵያ የዘረፈው ገንዝብ እና ጥሬ ሃብት ኢፈርት በትግርኛ ት.እ.ም.ት የሚል ስያሜ በመስጠት በትግራይ ህዝብ ስም ሲያጭበረብር የትግራይ ህዝብ መነገጃ ማድረጉም ህወሃት በዚሁ ሌብነቱ በወንጀል የሚያስጠይቀው ነው:: በትግራይ ህዝብ ስም የወያኔ መሪዎች ነገዱበት እንጂ የትግራይ ህዝብ ከት.እ.ም.ት ተጠቃሚ አይደለም:: ህዝቡም ራሱ የሚናገረው ሃቅ ይህ ነው::
ወያኔ ህወሃት ድርጅት ነው ስንልም ህወሃት የተመሰረተውና እስከ አሁንም ያለው ህወሃት ግለሰቦች ተደራጅተው የፈጠሩት የማፍያ ስብስብ እንጂ በምንም ተአምር የትግራይ ህዝብን የማይወክል ነው:: በድርጅቱ የተሰባሰቡ ግለሰቦችን ያቀፈ:: ህዝብ ሌላ፤ ህወሃት ሌላ:: ህወሃትን የመሰረቱት ሰዎችም ጸረ ህዝብ እና ጸረኢትዮጵያ ናቸው:: ይህ ህወሃት ተብሎ የሚጠራ በሻዕቢያ የተመሰረተ ኤርትራን ነጻ ለማውጣትና ትግራይም የአማራው ቅኝ ግዛት በማለት የተነሳ ከጥዋቱ ኢትዮጵያዊነቱን የካደ የከሃዲዎች ስብስብ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች የገደለ ጸረ ህዝብ ነው:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ህወሃትን በእውቅና አልተቀበለውም::
ወያኔ ህወሃት ገና በ1968 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መሬት እጠቀማለሁ በማለቱ ከባድሜ እስከ አፋር ቡሬ የመሬት ቆዳ ስፋት 1.ታች አዲያቦ 2. ላይ አዲያቦ 3.ጭላ ወይም አንከረ ባሩካ 4. አሕሰኣ 5.እገላ 6.ዛላምበሳ  በዚሁ ውስጥ የሚጠቃለሉ ኢሮብ ፣ ጻልገዳ ፣ ዓውዳ ፣ አይጋ ፣ ሶቦያ ፣ ወዘተ 7.የአፋር መሬት  እስከ ቡሬ 8. አሰብ የኤርትራ መሆንዋን በዚሁ ፊርማቸው በ1969 ዓ.ም. አረጋግጠዋል:: 1. መለስ ዜናዊ 2.አባይ ጸሃዬ 3.ስብሃት ነጋ በዋናነት የሚጠቀሱ በትክክል የኤርትራን መሬት ነው በማለት ፈርመው የሰጡት ህዳር ወር 1969 ዓ.ም. ነው:: በዚሁ መሰረት የትግራይ ህዝብ 1.በሻዕቢያ 2.በጀብሃ 3.በህወሃት  በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ትተዳደራለህ ብለው በመወሰን ህዝቡም በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ቁም ስቃዩን በማየት ተገደለ:: ንብረት ሃብቱ ተዘረፈ:: አቤት የሚባልበት በማጣት በየስደቱ ተበታተነ:: ወያኔ ይህን ወንጀል እንደፈጸመ በአንጻሩ ከሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ለም ወሬት ነጥቆ ወሰደ::
የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዋና ጦሱ ከላይ እንደተጠቀሰው ነው:: የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መንስኤ   ው በግልጽ የሚታወቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት አመራር የሚያላክኩት በኢኮኖሚ ችግር የተፈጠረነው ሲሉ በተደጋጋሚ በተለይ የወያኔው መሪ ነበር መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳመን ለከት በሌለው ውሸቱ ሲለፋደድ ሃገር ሙሉ ያውቃል:: ቀሪዎቹ የሱ የአመራር አባላቱ ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃየ ፣ ስዩም መስፍን ፣ አርከበ እቁባይ ወዘተ የመለስ ዜናዊን ሃሳብ በማስተጋባት በየውጪ ሃገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማሳመን ብዙ ውጣ ውረድ ቢያደርጉም እስከ ዛሬ ተቀባይነት አላገኙም::
የጦርነቱ መንስዔ በኢኮኖሚ ሳይሆን በትክክለኛው አነጋገር በተጨባጭ ሁኔታው የመሬት ይገባኛል ነው:: ሻዕቢያ የኔ ግዛት ነው:: ከዚህ ቀደምም በ1969 ዓ.ም. ተስማምተን እናንተም የኤርትራ መሬት ነው በማለት ያመናችሁበትን አስረክቡን በማለት ወደ ጦርነቱ ሻዕቢያ እና ወያኔ ገቡ:: እውነቱ ይህ ነው:: ይህ በዚሁ እንዳለም የኢኮኖሚው ጉዳይም አስተዋስኦ ያደረገበት አለ:: ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ከ1983 ዓ.ም. ግንቦት ወር ጀምሮ እስከ 1990ዓ.ም.  የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ የግላችን የኢትዮጵያ ሃብት ደግሞ የጋራችን ተባብለው በህወሃት መሪዎች መጠነ ሰፊ ድጋፍ ሁለቱ ማለት ሻዕቢያና ወያኔ የሃገራችን ኢትዮጵያን ጥሬ ሃብትዋን መዓድኗን እና ሃገሪቱ ያፈራችውን የተለያዩ ፋብሪካዎቸ እና ባንኮችን አብረው ተባብረው ዘርፈዋል:: ኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ኤርትራውያን ጤፍ በየአይነቱ ዳጉሳ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ ወዘተ በርካሽ ዋጋ ኤርትራ ሲሸጥ የኢትዮጵያ ገበያ ባዶ ቀረ:: ስለዚህ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ያ የለመዱት በሰው ሃገር ሃብት ሲንደላቀቁ የቆዩት አሁን ሲያጡት ለጦርነቱ አስተዋጽኦ ያደረገም ነበር:: በጣም ከሚገርሙ ነገሮች እና አሳዛኝ የሆነው ሁለቱ መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በስልክ ጥብቅ ግንኙነት እንደነበራቸው ብዙ ሰዎች ተናግረዋል:: ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃዬ እና ሌሎቹ የወያኔ መሪዎች በጣም የደመቀ ግንኙነት ከጦርነቱ ዋዜማ አንስቶ የወያኔ መሪዎች ይገናኙ እንደነበር ምስጢሩም የሚያውቁ ሰዎች ተናግረውታል::
ኢሳያስ አፈወርቂ ላቀረበው የአንድ ቢሊዮን ብር ላክልን መለስ ዜናዊ ሳያቅማማ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተፈቅዶ ገንዘቡ አስመራ እንደገባ በቀናት የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መቀሌ ውስጥ(ሃይደር) የሚገኘው የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤት በሚግ አውሮፕላን ደበደበው:: ከተዋጊ አውሮፕላኖቹ የተጣለው ክላስተር ቦምብ ወድያውኑ 53 ህጻናትና አስተማሪዎች ሲሞቱ 185 ደግሞ ከባዱ ቁስል ደረሰባቸው:: ለዚሁም ተጠያቂው መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ ናቸው::
የሻዕቢያ ተዋጊ ጀቶች እንደገና ተመልሰው ቦምብ ጭነው 48 ሰላማዊ ሰዎችን 10 ህጻናትን ሲገድሉ 150 ሰዎች አቆሰሉ:: በማለት ቢ.ቢ.ሲ. እና ሲ.ኤን.ኤን. የዘገቡት ዋቢ ነው:: ይህ ጥቃት የደረሰው በግንቦት ወር መጨረሻ 1990 ዓ.ም. ሆኖ አስራት አብርሃም በአሳማኝ ሁኔታ ከ’ሃገር በስተጀርባ’ በሚል መጽሃፉ እንደገለጸው መለስ ዜናዊን ኢሳያስ አፈወርቂ እስከ ታህሳስ ወር 1991 ዓ.ም. ይገናኙ እንደነበሩም ያስረዳል:: መለስ ዜናዊን ግብረአበሮቹ እነ ስብሃት ነጋ ወዘተ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ የባዕዳን ቅኝ ገዢዎች መሆናቸው በግልጽ የሚያሳይ እውነታ ነው::
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ሆን ብሎ ያሰናከለው መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ እና አባይ ጸሃዬ መሆናቸው ሲታወቅ ምክንያቱም በ1969 ዓ.ም. ከላይ የተጠቀሰ መሬት የኤርትራ ነው ብሎ ወያኔ የፈረመበት በመሆኑ ይህም በአልጀርሱ ስምምነት ወያኔ መሪ መለስ ዜናዊ አሳልፎ ለኤርትራ መስጠቱ የ1969 ዓ.ም. ትልቁ ማሳያ ነው:: የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት እነማን መሩት? ይህን እንመልከት::
1. መለስ ዜናዊ የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር …………………………………………ኤርትራዊ
2. ጻድቃን ገብረተንሳኤ የጦሩ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ……………………………………………..ኤርትራዊ
3. ሳሞራ የኑስ…ከፍተኛ ጀነራል…………………………………………………………………………………….ኤርትራዊ (በናቱ ከርከበት በአባቱ ሱዳናዊ)
እነዚህ ሶስቱ አመራር በምንም ተአምር ለኢትዮጵያ ይሰራሉ?? ጦርነቱን በትክክል ይመራሉ ብሎ ማሰብ “ላም አለችኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” አይነት ነው:: እነዚህ ትልቁ ምኞታቸው የኤርትራ ሰራዊትና ህዝብ እንዳይጎዳ ኢትዮጵያዊው ሰራዊት ቢያልቅ ምንም የማይሰማቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም የውጊያና ጦርነት አመራር ብቃት የሌላቸው በአጋጣሚ የተገኘው ጠ/ሚኒስቴርነት እና ጀነራልነት ከንቱ ነው:: ጠቅላላ የወያኔ ህወሃት መሪዎች ጀነራሎች እና ወታደሮች ከወታደራዊ ሳይንስ ያላቸው ርቀት ሰማይና መሬት ነው:: በ1991 ዓ.ም. ያለቀው ሰራዊት ተጠያቂም ናቸው::
2ኛው በዚሁ ኢትዮ ኤርትራ ውጊያ ሲመሩ የነበሩ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ታዛዦች ናቸው:: አታድርጉ ከተባሉ አያደርጉም:: በዋናነት ጎልተው የሚጠቀሱም::
1. ሰዓረ መኮንን
2.ዮሃንስ ገ/መስቀል (ቦጅቦጅ)
3.ታደሰ ወረደ
4.አብርሃ ወ/ማሪያም(ኳርተር)
5.ብርሃነ ነጋሽ ወዘተ ሲሆኑ ሌሎችም አሉ::
ስለሆነም በ1991ዓ.ም የደረሰው ውድመት ከ100,000ሺ ሰራዊት የሞተበት ወደ 200,000 የሚጠጋ ሰራዊት አካለ ጎዶሎ የሆነበት ግምቱ አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ ሃብት ንብረት የወደመበት ተጠያቂው ማነው??
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተፈጠረበት ምክንያት እና ሰበቡ ምንድነው?? እነዚህ ሁልቱ ጥያቄዎች መልስ በግልጽ ለማስቀመጥ እፈልጋለሁኝ::
1. በኢትዮ-ኤርትራ ለደረሰው ግድያና በጦርነት የወደመው ሃብትና ንብረት ተጠያቂዎች::
1. መለስ ዜናዊ
2. ስብሃት ነጋ
3.አባይ ጸሃዬ
4. አርከበ እቁባይ
5. ጻድቃን ገ/ተንሳኤ
6. ሳሞራ የኑስ
7. ስዩም መስፍን
እነዚህ በሰው ህይወት ለደረሰው እልቂትና ጉዳት በሃገሪቱ የደረሰው ከፍተኛ ውድመት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው::
በጦርነቱ የወደመው ሃብት እና ንብረት ተጠያቂውስ ማነው? ለሚለው::
1. መለስ ዜናዊ
2.ስብሃት ነጋ
3.ጻድቃን ገ/ተንሳኤ
4.አበበ ተክለሃይማኖት
5.ገዛኢ አበራ
6.ጀነራሉ በባለ ሌላ ማእረግ
7.ስዩም መስፍን
8.ብአዴን, ኦህዴድ እና የደቡብ ህዝብ ንቅናቄ
9. በወቅቱ የነበሩ የፓርላማ አባላት በሙሉ
10. የህወሃት ካድሬና ደጋፊዎች በሙሉ::
እነዚህም ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ሲሆኑ፤
3. የጦርነቱ መንስኤ ለሚለው ጥያቄ የህወሃት አመራር በ1969 ዓ.ም. ሻዕቢያ ላቀረበው የመሬት ይገባኛል በወቅቱ አምነት ተቀብለው በፊርማቸው ባረጋገጡት መሰረት በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት የሌለው የህወሃት ጥቂት የማፍያ ስብስብ በፈጸሙት ነገር ከሃዲዎች ከሻዕቢያ ጥቅም እናገኛለን ብለው የፈጸሙት ሚያዝያ ወር 1991 ዓ.ም. የፈነዳ ጦርነት ነው:: ተጠያቂዎቹም ህወሃቶች ናቸው::
በብዙ በርካታ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ሊከሳቸው ዝግጅቱን አጠናቅቆ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ነው:: ህወሃት እና መሪዎቹ ይከሰሳሉ:: አዎን ለፍርድም ይቀርባሉ::
የአይደ መዋእለ ህጻናት የአየር ጥቃትም የትግራይ ህዝብ ካቀረባቸው ክሾች ውስጥ አንዱ ስለሆነ በዚሁም በዋናነት የሚጠቀሱ መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ መሆናቸው ነው::
ግንቦት 20 ቀን1983 ዓ.ም. ይህን አይነት አሰቃቂ ድርጊቶችን አስከትላ ነው ብቅ ያለችው:: የተረገመችው ይህቺ ቀን ኢትዮጵያ ለምለም አገራችንን ለከሃዲ ባንዳዎች አሳልፋ የሰጠች::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ይዛው የመጣችው ሰቆቃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፈለገው የሃገሩ ግዛት የመኖር ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን መብቱን በህወሃት ከፋፍለህ ግዛ በሚመቸው ሃገራችን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ጠባብ ብሄረተኛ በሆነው መንገድ የዘር ፌደራሊዝም መሰረት ይህ የእቅድ ሃሳቡም አማራውን ለማጥፋት እና ለማክሰም የተቀነባበረ ሴራ ነው:: ይባስ ብሎም ሸዋ ጠ/ግዛት ለሌሎች ብሄራት በመስጠት ጎጃም በጌምድር ጠ/ግዛት ወሎ ጠ/ግዛት በታትነው አማራው መኖሪያ አልባ ተደረገ:: በተለያዩ ጠ/ግዛት ይኖር የነበረው አማራ ውጣ እየተባለ በወያኔ ህወሃት ከህጻን እስክ ሽማግሌ እየተገደለ በየበረሃው ወድቆ የዘሩን ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል:: ቀስ በቀስም ኦሮሞ ጋምቤላ አፋር ወዘተ ተመሳሳይ እጣ ደረሰባቸው:: በጠቅላላው ከተወለደበት ካደገበት ኢትዮጵያዊ ከመሬቱ የተፈናቀለ 24 ሚሊዮን ሲሆን በወያኔ ህወሃት የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ጥናቶች የሚያመለክቱተ 7.9ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ወያኔ ህወሃት እንደገደላቸው ያሳያሉ::
ግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሁለቱ ሃይማኖቶች እስልምናእና ክርስትና በእጁ አስገብቶ ለመቆጣጠር እና ቀስ በቀስም ሃይማኖቶቹን ለማክሰም ተነሳ::
1. የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት ለብዙ ዘመናት ወግና ህግጋቱን ጠብቆ የመጣ በብዙ ሚሊዮን እስልምና ተከታይ ያለው የኢትዮጵያ ቅርስና የምንኮራበት ሃይማኖት ዛሬ በወያኔ ህወሃት ተደፍሮ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሙሉ መብታቸውን ተነጥቀው በእስራት መከራ እየተሰቃዩ በገዛ ሃገራቸው ለክፉ ችግር ተዳርገዋል::
2.የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም በክፉ አደጋ ወድቃለች ቤተ ክርስቲያና እየተቃጠሉ ታሪካዊ ቅርሶችዋን በወያኔ ተዘረፉ::ወያኔ የሚቃወሙ ብጹአን አባቶች ለስደት ተዳርገዋል:: ብዙም ተገድለዋል:: ይህን ሁሉ የፈጸመው የወያኔ አባል የነበረው አባ ገብረመድህን ወይም አባ ጳውሎስ የሚባል በወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ ካደረገው ብዙ ወንጀል በቤተ ክርስቲያናችን ፈጽመዋል::
ለመሆኑ አቡነ ጳውሎስ ማነው??
አቡነ ጳውሎስ ትውልዳቸው ትግራይ አድዋ ያደጉትም እንዳባገሪማ ገጠር ነው:: እንዳባገሪማ የተባለበት ምክንያት በአክሱም ዘመነ መንግስት በንጉስ አልአሜዳ ብ470ዓ.ም. ከመጡት ተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ አባ ገሪማ ሲሆኑ ከአድዋ በስተምስራቅ የ18 ኪሎ ሜትር ርቀት የምተገኘው ተራራማ ቦታ አባ ገሪማ በጣም አስደናቂ ሆኖ የተሰራው ቤተ ክርስቲያናቸው በማነጽ እዛው ሞተው እዛው ስለተቀበሩ በዚሁ ምክንያት እንዳባገሪማ ተብላ ትጠራለች::የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያዋረዱን የቤተ ክርስቲያኗን ህገ ደንብ እና ቀኖናውን የለወጡ እና ያፈረሱ ፣ ለስጋቸው ያደሩ: አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሃይማኖት ለማጥፋት ጸረ ክርስትና የሆኑት ጳውሎስ የአድዋ ልጅ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ህጋዊ ሊቀ ቅዱሳን ፓትሪያርክ በቤተ ክርስቲያኑ ህግና ደንብ የተሾሙት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ወያኔ በሃይል አስወግዶ አባ ጳውሎስን ሾመ:: ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሀይማኖት ወግና ስርዓቱን ለማጥፋት የታቀደ ነው:: የቤተ ክርስቲያኑን ህግና ደንብ የሚጻረርም ነው::
አቡነ ጳውሎስ የወያኔ ህወሃት በአባልነት የመለለመሉት በ1976 ዓ.ም. ነበር:: በወቅቱ የሚነገረው ዶ/ር አባ ገብረመድህን የተባሉ የኛ አባል ስለሆኑ ትግራይ ሃገራችን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነጻ በምትወጣበት እኚሁ የትግራይ ፓትሪያርክ ይሆናሉ በማለት ስብሃት ነጋ በለመደው ወሬ ማዛመት በታጋይ ውስጥ ተሰራጨ:: ቢሆንም ግን ታጋዩ ብዙ ስሜት አልሰጠውም:: ምክንያቱም ሃይማኖት የለሽ የወያኔ አመራር በትግሉ ወቅት እግዚያብሄር የሚባል አማልክት የሚባሉ በፍጹም የሉም:: ይህ ለአማራው አገዛዝ እንዲመችለት የፈጠረው ከንቱ ሃሳብ ነው:: በማለት ስለአስተማሩን የአባ ገብረመድህንም ይህን ድባብ የሸፈነው ነበር::
ንገሩ እንደገና በ1980 ዓ.ም. መጀመሪያ ታድሶ መጣ የህወሃት አባል አባ ገ/መድህን ከአሜሪካ ሱዳን ድርስ መጥተው ስብሃት ነጋ የወቅቱ የህወሃት ሊቀ መንበርና መለስ ዜናዊ ሱዳን ድረስ በመሄድ እንደተገናኙ በድጋፍ መልክም $15,000 የአሜሪካን ዶላር መስጠታቸውን የሄዱት ሁልቱ የወያኔ አመራሮች በድብቅ ሳይሆን በግልጽ የተናገሩት ነበር:: ከዚሁም በተጨማሪ ሱዳን ካርቱም ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው በውስጡ የሚገኙ ቀሳውስት ካህናት ወደ ህወሃት አባልነት መልምለው በሶስተኛው ቀን ወደ መጡበት መመለሳቸም ተነገረ::ስብሃት ነጋ አቡነ ጳውሎስ የህወሃት መሪህ ባህታ(vanguard) ናቸው በማለት ይጠራቸዋል::
እንግዲህ የአቡነ ጳውሎስ ነገር ይህ ሆኖ ትግሬ በመሆናቸው ብቻም በደርግ መታሰራቸውን ብዙ ግፍ ተፈጸመብኝ የሚሉት አቡነ ጳውሎስ የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባላት እውነት ይሁን አይሁን ለነሱ ልተው:: ከሆነም አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንዋ ላይ በቂም በቀል ማወካቸው ከአንድ መናኝ አባት መፈጸም የሌለበት ፈጽመዋል:: ነብሳቸውም ለሲዖል ተዳርጋለች::
አቡነ ጳውሎስ የፓትርያርኩ ስልጣን አግባብ በሌለው መንገድ የተረከቡት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናት በምርጥ ካድሬነታቸው በዋልድባና በተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ብዙ ግፍ ከመፈጸማቸው በላይ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከየቤተ ክርስቲያኑ በማስወጣት ሸጠዋል::
ይህ ሁሉ በእስልምና ሃይማኖትና በክርስትና መዘዙ ይዞት የመጣው ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የተረገመች ቀን ናት::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያውያን እንደተቆጣጠረ ብዙ የዝርፊያ ተቋማት አመቻችቶ ነበር:: አገራችንን የተቆጣጠረው 1. ዋና ኢፈርት 2. ለም የኢትዮጵያ መሬት ለባዕዳን መሸጥ 3. ኢትዮጵያውያን ከተወለዱበትና ካደጉበት መሬት ማፈናቀል 4. ገዢ የሆኑት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተቋማት በህወሃት ቁጥጥር ውስጥ መዋል 5. ኢትዮጵያዊው የሃገሩ ዳር ድንበር ጠባቂ አማራው ማጥፋት ከዚህም ጎን ለጎን አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ማጥፋት እና ማክሰም:: 6.የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀ.አየር ኃይል ለ. ምድር ጦር ሐ.ባህር ሃይል መ.ፖሊስ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ የራሱን የህወሃትን ታጋዮች ከትግራይ የመጡ ሁሉ የኢትዮፕያ ምድር ጦርና አየር ኃይል ለማድረግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በራኡ መዳፍ ውስጥ ለማስገባትና ለመቆጣጠር ደህንነቱም ከላይ እስከ ታች በትግሬዎች ማዋቅር አላማው ነበር::
ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ የወያኔ አመራር መለስና ስብሃት ነጋ ባወጡት እቅድ ተግባራዊ ተደርገዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብ በእርሻ የሚተዳደረው መሬቱን ተቀምቶ ለባዕዳን ሳውዲ አረቢያ ፣ ህንድ ፣ እና ለቻይና ወዘተ ህወሃቶች ሸጡት:: በሽያጭ የተገኘው ገንዘብም ሆነ በነ መለስ ዜንዊና ባለቤቱ ወ/ሮ አዜብ እጅ ሲገባ ከመሬቱ የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በየበረሃው ወድቆ ለክፉ ችግርና መከራ ተዳርገዋል::
ወያኔ ህወሃት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማርቶ ህዝበ ኢትዮጵያዊ እያለቀ ነው:: አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ጠላት ነው ብለው ወያኔዎቹ ፈረጁት:: ለመሆኑ የቋንቋ ጠላት አለን?? ይህ ሁሉ በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የመጣ የኢትዮጵያ ህልውና አጠያያቂም ሆነ:: ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ያፈረሰ ህዝብዋንም ለችግር እና ለመከራ የዳረገ በጥቁር ታሪክ የሚመዘገብ የፋሺስት ወያኔ ህወሃት አገዛዝ ስርዓትና የጨለማ ዘመን በማለት ታሪ ዘግቦታል::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. አንቺ ጥቁር የታሪክ አተላ ቀን የስንቱን ኢትዮጵያዊያን ህይወት በላሽ?! ስንቱን ኢትዮጵያዊ ምሁራን የነጻ ፕሬስ እውቅ ጋዜጠኞች ለስደት ለመከራ ዳረግሽ?! ስንቱን ወጣት ሴት እና ወንድ ከሃገሩ ጠፍቶ የባህር ቀለብ ሆነ:: ስንቱስ በስደት ሂወቱ እየማቀቀ ለክፉ መከራ ተዳረገ:: ስንቱ ቤተ ሰብ አፈናቅለሽ የስንቱን ቤት አፈረሽው:: ወጣት የሴት ህጻናት ሽርሙጥና ዳረግሽ:: አደንዛዥ እጽ እና አሺሽ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ተራ የንግድ ገቢ ሆኖ ወጣቱ ትምህርት ተከልክሎ እቅቀት እና ስልጣኔ በኢትዮጵያ የጠፋበት ዛሬ በኢትዮጵያ ስራ አጥነት የተስፋፋበት የወንጀል ድርጊት በስፋት የሚፈጸምበት ህጻናት በየቆሻሻው የተጣሉ ምግብ አይነት ነክ እየለቀሙ የሚበሉበት የጎዳና ተዳዳሪ ጠዋሪ ማደሪትይ ያጡ ህጻናት ለአቀመ አዳም ያልደረሱ ልጆች ወንድ ሴት ማደሪያቸው በየመንገዱ ሆነ:: ህጻናት በርሃብ በየመንገዱ በየትምህርት ቤቱ አእምሮዋቸውን እየሳቱ የሚወድቁበ እርጉዝ ሴት መኖሪያ አልባ ሆና በየዱር ገደሉ እየወለደች ከተወለዱ ህጻናት ከ10 ህጻናት 6 በ3 እና በ 4 ወራቸው እየሞቱ ህክምና ጠፋ:: ውሃ ጠፋ:: መብራት ጠፋ:: አረ ስንት ጉድ ነው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የወረደው ግፍ::
የወያኔ ህወሃት አባል ድርጅቶች ህወሃት ራሱ የነዚህ ቤተሰብ ልጆች ውጭ አገር እየተንደላቀቁ ሲማሩ ሃገር ውስጥ ያሉ አመራሩ ደጋፊዎች በኑሮ ተንደላቀው በሙስና ተዘፍቀው የሃገር እና የህዝብ ሃብት እየዘረፉ ቀኑ ለነሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ የችግር ጨለማ መብቱ የተረገጠ ባሪያ ጥዋት ማታ በወያኔ ስርዓት የሚሰቃይ ግዞተኛ ባዕድ ሆኖ ያለበት ዘመን ነው::
ይህ ክፉ አረመኔያዊ የህወሃት አገዛዝ በዚሁ መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይቀጥል ሁሉ ኢትዮጵያዊ በአንድነት ይነሳ በህዝባዊ ትግል ወያኔን ከስረ መሰረቱ ነቅለን እንጣለው::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ገብረመድህን አርአያ
አውስትራሊያ

Total Pageviews

Translate