‹‹አዲስ አበባ ውስጥ ግብረ ሰዶማዊነት ተስፋፍቷል፡፡ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎችና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በየመንደሩ፣ በየሥርቻው፣ በየጓዳውና ጉድጓዳው ራሳቸውን ደብቀው ያደፈጡ ሁሉ ቢቆጠሩ ብዛታችን ያደላል፡፡ መጠሪያ ስማችን ጌይ ወይም ግብረ ሰዶማዊ የሚል ሳይሆን ‘ዜጋ’ የሚለው ነው፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ያልገቡ ሌሎች ወገኖችን ደግሞ ‹‹ቀጥ›› በሚል እንጠራቸዋለን፡፡››ይህንን የተናገሩት ከሰባት እስከ 32 ዓመት ድረስ ሕይወታቸውን በግብረ ሰዶማዊነት ያሳለፉት ግብረ ሰዶማውያንና ግብረ ሰዶማውያት (ወንዶችና ሴቶች)፣ ‹‹ዝምታው ይሰበር ትውልድ ይዳን በእኛ ይብቃ›› በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ዶክሜንተሪ ፊልም (ቪሲዲ) ውስጥ ባካሄዱት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው፡፡
በቸርችል ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ ‹‹ስለኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሠራር›› የሚል ታካይ ርእስ ባለውና ለምረቃ በበቃው በዚሁ ፊልም ውስጥ ይህንኑ ቃለ መጠይቅ ካካሄዱት ከእነዚህ ግብረ ሰዶማውያን ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው ሕጋዊና መደበኛ ሚስት አግብተው፣ ትዳር መስርተውና ልጆች ወልደው በሽምግልና ዕድሜያቸው ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ አዛውንቶች አሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ‹‹አባባ መሽቷል እባክዎን ወደ ቤትዎ ሂዱ›› እያሉ ወጣት ግብረ ሰዶማውያን ይቀልዱባቸዋል፡፡ ይሳለቁባቸዋል፡፡ እነዚህም አዛውንቶች ታዋቂነታቸው በ‹‹ዜጎች›› ዘንድ ብቻ ስለሆነና በአካባቢያቸው ማኅበረሰብ ዘንድ የሚታወቁት ባለትዳርና የልጆች አባት ስለሆኑ ከማኅበረሰቡ ዘንድ እንዳይገለሉና ተከብረው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፡፡
የእምነት ቃላቸውን ከሰጡት ግብረ ሰዶማውያን መካከል በቅጽል ስሙ ‹‹ኤሊያና›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ወጣት፣ ግብረ ሰዶም መጀመርያ የተፈፀመበት በሐዋሳ ከተማ የሰባት ዓመት ሕፃን ሳለ ነበር፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ መኖር ከጀመረ 32 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ እስካሁን ባሳለፈው ሕይወት ውስጥ ለወሬም የማይመች፣ ከባህል ውጭ የሆነ፣ ሕይወትን እስከመጥላት የሚያደርስና አሰቃቂ የሆነ ወሲብ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ሲፈጸም እንደኖረ ነው የተናገረው፡፡
ግብረ ሰዶማውያን የሚፈልጉትን ቆንጆ ወንድ አንዲት ሴት ይዛባቸው ከሄደች ወይም ካወጣችው ‹‹ዓይነጥላ›› ወሰደችብን እያሉ እንደሚያማርሩ ያወሳው ኤሊያና፣ በድሬዳዋ፣ በጅቡቲ፣ በየመንና በሳዑዲ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ይህንኑ የግብረሰዶም ሥራ ያከናውን እንደነበርም አልሸሸገም፡፡ ጅቡቲ የገባው ከድሬዳዋ እስከ ደዋሌ ድረስ በባቡር ከዚያም እስከ ጅቡቲ ደረስ በእግሩ ለአምስት ቀን ያህል ከተጓዘ በኋላ ነው፡፡ ከጅቡቲም በአንድ የሞተር ጀልባ ተደብቆ ወደ የመን እንደተሻገረና በመቀጠልም ሳዑዲ እንደገባ አመልክቷል፡፡
‹‹በአገር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የአምስት ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው የግብረ ሰዶማውያን ሠርጎችን አይቻለሁ፡፡ ይህን ዓይነቱንም ሠርግ መንግሥት ወይም ማዘጋጃ ቤትና ባህል አያውቀውም፡፡ እኛው ራሳችን ነን የምንፈጽመው፡፡ ይህም ሆኖ ፍቅርን ስለማናውቅ በጋብቻ ፀንተን አንቆይም፡፡ ጋብቻው ግፋ ቢል የሚቆየው ለሦስት ወራት ያህል ብቻ ነው፤›› ብሏል፡፡
ሚስት የሚሆን ወንድ በሠርግ ሥነ ሥርዓቱ ቀን ቅንድቡን ተቀንድቦ፣ ቻፕስቲክ ተቀብቶ፣ ፊቱ ላይ ማድረግ የሚገባውን ሜክአፕ ሁሉ አድርጎ፣ ፀጉሩን ተሠርቶና ቬሎ ለብሶ ይቀርባል፡፡ በሥነ ሥርዓቱም ላይ ኬክ እንደሚዘጋጅ ነው የተናገረው፡፡
ሠላሳ ሁለት ዓመታት ያህል በግብረ ሰዶም ሕይወት የቆየ፣ ስምንት ጊዜ ድል ባለ ሠርግ አግብቶ የወንድ ሚስት የነበረና በቅጽል ስሙ ‹‹አጠለል›› እየተባለ የሚጠራው ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ግብረ ሰዶማዊነትን መተዳደሪያው አድርጎ የያዘው ሲሆን፣ ይህንንም የጀመረው የስምንት ዓመት ሕፃን ሳለ ነው፡፡ የሴት ሚስት ላለውና በዚህ ላይ ደግሞ 17 የወንድ ሚስቶች ካሉት ግብረ ሰዶማዊም ጋር ትዳር ለመጀመርያ ጊዜ ‹‹17ኛ የወንድ ሚስት ሆኜ ነው ያገባሁት›› ሲል አጠለል ይናገራል፡፡
የግብረ ሰዶማውያን መለያቸው ከአለባበሳቸው እንደሚጀምር ይናገራል፡፡ ሁልጊዜ ቁምጣ ሱሪ እንደሚያደርጉ፣ ጠባብ ስኪኒ እንደሚያዘውትሩ፣ ጠልጠል ያለ ቦዲ ቲ ሸርት በመልበስ እምብርት እያሳዩና ያለ ካልሲ ጫማ እያደረጉ እንደሚሄዱ፣ ፀጉራቸውን ሊሞዚ መቆረጥ፣ ጆሯቸውን በተለየ ቦታ ላይ በመበሳት ጌጣ ጌጥ ማስገባትና ሎቲ ማንጠልጠል ናቸው፡፡ ከውጭ አገር የሚረዷቸውም ሰዎች አሉ፡፡ በተለይ ዳያስፖራዎች የጠለልን አድራሻ ይዘው ነው የሚመጡት፡፡ ሲጠሩት ይቀበላቸዋል፡፡ በኢንተርኔትም የሚገናኙበት መንገድ አለ፡፡ በዚህም የተነሳ ደንበኞቻቸው ሲመጡ አይቸገሩም፡፡ በሚፈልጉበት ቦታ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
‹‹ሪች›› በመባል የምትጠራዋ ሌላው ግብረ ሰዶማዊት (ሌዝቢያን) ወደዚህ ሕይወት ውስጥ የገባችው በጓደኛዋ ግፊት እንደሆነ፣ በዚህም ሕይወት ከገባች ስምንት ዓመት እንደሆናትና መተዳደሪያዋም ይኸው እንደሆነ ገልጻለች፡፡ ሁለት ቋሚ የሴት ደንበኞችም እንዳሏት ተናግራለች፡፡ አንደኛዋ ደንበኛዋ አዲስ አበባ ውስጥ ኦሎምፒያ አካባቢ፣ ሁለተኛዋ ደንበኛዋ ደግሞ በሐዋሳ ከተማ ይኖራሉ፡፡ በጠሩዋት ቁጥር ትሄድላቸዋለች፡፡፡ ጠሪዎቿም በጣም ሀብታሞች እንደሆኑ ነው የተናገረችው፡፡ በዚህም እርካታ እንደምታገኝ፡፡ ከተመሳሳይ ጾታዋ ጋር ካልሆነ በስተቀር ለወንድ ወይም ለተቃራኒ ጾታ ፍላጎት እንደሌላት አስረድታለች፡፡
ብሩክቱ ሌላዋ ግብረ ሰዶማዊት ናት፡፡ ሪታ የምትባል ክልስ የልጅነትና አብሮ አደግ የሆነች ጓደኛ ነበረቻት፡፡ በልጅነታቸው ትምህርት ቤት ሲገናኙና ከትምህርት መልስ ወደየቤታቸው ለመሄድ ሲለያዩ ይሳሳማሉ፡፡ ይህን ዓይነት ሁኔታ ቢያዘወትሩም የልጅነት ነገር እንጂ ወደ ሌላ ስሜት አይመራቸውም ነበር፡፡ ከዓመት ዓመት እያደጉና ነፍስ እያወቁ ሲመጡ በመካከሉ ሪታ ወደ ኢጣሊያ አቀናች፡፡
ሪታ ከሄደችበት ወደ ኢትዮጵያ ስትመለስ ግን ተለውጣ መጣች፡፡ የመሳሳማቸው ሁኔታ ወደ ልጅነት መንፈስ መሄዱ ቀርቶ ወደ ወሲብ ቀስቃሽነት ተሻገረ፡፡ በዚህም የተነሳ ውለው ሲያድሩ ፍቅር መሠረቱ፤ ‹‹እወዳታለሁ ትወደኛለች፣ ከእሷ ጋር ግንኙነት ሳደርግ ታስደስተኛለች፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ከገባሁ ሰባት ዓመት ሆኖኛል፤›› ብላለች ብሩክቱ፡፡
ሁሉም ወንዶችና ሴቶች ግብረ ሰዶማውያን ኤችአይቪ ፖዘቲቭ እንደሆኑ፣ በዚህ ላይ ደግሞ የሥነልቡና ችግርና የአአዕምሮ ጭንቀት እንዳጋጠማቸው፣ በተለይም ኤሊያና የኪንታሮት በሽታ እንዳደረበት፣ ሁሉም ከዚህ አስከፊና አስነዋሪ ሕይወት ለመውጣት እንደሚፈልጉ በየተራ በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል፡፡
ሰኔ 23 ቀን 2005 ዓ.ም. በተከናወነው የዶክመንተሪ ፊልሙ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የሁሉም እምነቶች ተከታዮች፣ አባት አርበኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በዚህም ጊዜ መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) የማኅበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት ሊቀመንበርና የፊልሙ ዋና አዘጋጅ ዓላማውን ሲገልጹ በአገሪቱ እየተከሰተ ያለው ግብረ ሰዶማዊነት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ትውልድንም ምን ያህል እየጎዳ እንዳለ ለማስገንዘብ ነው ብለዋል፡፡
ሦስት ዓመት በፈጀው ጥናታቸው የተገነዘቡት ነገር ቢኖር ከግብረ ሰዶማውያን መካከል አንዳንዶቹ ይህን ድርጊት ሕጋዊ እናደርገዋለን ብለው የሚዝቱና፤ ከፊሎቹ ደግሞ በተቃራኒ ድርጊቱ ለሕይወት ጎጂ በመሆኑ መውጣት አለብን ብለው የወሰኑ መኖራቸውን ነው፡፡
የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 6/29 ግብረ ሰዶም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፡፡ አንቀጽ 6/32 ደግሞ በዚህ ተግባር የተገኘ ከቀላል እስከ እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ያስቀጣል ይላል፡፡ መምህር ደረጀ እንደሚሉት፣ የወንጀል ሕጉ ግብረ ሰዶምን ቢከለክልም ግብረ ሰዶማዊነት በአገሪቷ በድብቅ እየተስፋፋ ነው፡፡ ራሳቸውን አጋልጠው የሚወጡ ሰዎች ቢኖሩም ራሳቸውን ባላጋለጡት ተፅዕኖ ያደርስባቸዋል፡፡
ዶክመንተሪ ፊልሙ በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነት መኖሩን በግልጽ በሚመሰክሩ ሰዎች አማካይነት ለመንግሥትና ለኅብረተሰቡ ማሳወቅና ከድርጊታቸው ይወጡና ይታቀቡ ዘንድ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ ለማቅረብ ነው፡፡
በፊልሙ ወቅታዊ ሞቅታን ፈጥሮ መለያየት እንደማያስፈልግ የሚናገሩት መምህር ደረጀ፣ በሕፃናት ላይ ግብረ ሰዶማዊ ጥቃት የመፈፀም አካሄድ የሚከተሉትን ግብረ ሰዶማውያን ከወዲሁ ለማቆም በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በሥነ ምግባር ማኅበር ተደራጅቶ በቀጣይነት መሥራት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡
በግብረ ሰዶም ሕይወት ለብዙ ዓመታት ማሳለፋቸውን በመጥቀስ የሕይወታቸውን እውነታ ለገለጹት የቀድሞ ግብረ ሰዶማውያን ከችግር የተነሳ መልሰው እንዳይገቡበት ኅብረተሰቡና መንግሥት ሊረዷቸው እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነት እየተስፋፋና ግብረ ሰዶማዊ ጥቃትም እየተፈጸመ ስለሆነ ድርጊቱ ከመስፋፋቱና ‹‹ለኛም መብት ይሰጠን›› የሚል ጥያቄ ከመነሳቱ በፊት መንግሥት ከእንጭጩ ሊገታው ይገባልም ብለዋል፡፡
የምረቃውም ታዳሚዎች ይህ ዓይነቱን እኩይና ትውልድ ገዳይ የሆነውን ድርጊት ለመግታት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የተናገሩ ሲሆን፤ ከታዳሚዎቹም መካከል አርቲስት ተስፋዬ አበበ ግብረ ሰዶማዊነትን ለመግታት የሚያስችል በአዲስ አበባ ደረጃ አንድ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጠይቀው፣ ለኮሚቴውም ሥራ ስኬታማነት ቀስቃሽና ትምህርት አዘል መልዕክት ያላቸውን ልዩ ልዩ መዝሙሮች ለማዘጋጀት ቃል ገብተዋል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለመሠረተው ክስ ያስረዱልኛል ያላቸውን ሁለቱ ተጠቂ ሕፃናትና እናቶቻቸውን፣ እንዲሁም አንድ የሥነ ልቦና አማካሪና አንድ የሕግ ባለሙያ አቅርቦ አስመስክሯል፡፡
የግል ተበዳይ መሆኑ የተገለጸው የአሥር ዓመቱና የአራተኛ ክፍል ተማሪ ሕፃን ለፍርድ ቤቱ የሚያስረዳለትን ዓቃቤ ሕግ በጭብጡ ያስያዘው፣ ተጠቂው ወደ አካዳሚው የተቀላቀለው በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም.፣ የግብረሰዶም ድርጊቱ የተፈጸመበት በገባበት ቀን ነው፡፡ በየካቲት ወር 2005 ዓ.ም. ለሁለተኛ ጊዜ ድርጊቱ እንደተፈጸመበትና ሁሉም መምህራን በመፈራረቅ ድርጊቱን እንደፈጸሙበት እንደሚያስረዳለት አስይዟል፡፡
ሕፃኑ በሲሲቲቪ ለችሎቱ እንደገለጸው፣ አካዳሚውን መቼ እንደተቀላቀለ አያስታውስም፡፡ አራተኛ ክፍል ሆኖ መቀላቀሉን ግን ያውቃል፡፡ ወደ አካዳሚው ሊገባ የቻለው ቤተሰቦቹ ከኮተቤ ወደ ቦሌ ቤት በመቀየራቸው ነው፡፡ በመጀመርያ ትምህርት ቤት ሲሄድ ዳይሬክተሩ ጠርተውት ለምን ወደ አካዳሚው እንደመጣ ሲጠይቁት ‹‹ቀድሞ በነበርኩበት ትምህርት ቤት ተደፍሬ ነው አልኩት፤›› በማለት ተናግሯል፡፡
ዳይሬክተሩ በሌላ ቀን ጠርተውት የግብረሰዶም ጥቃት እንዳደረሱበትና ሌሎቹም መምህራን (ሙሉ ስማቸውን ጠርቶ) ድርጊቱን እንደፈጸሙበት ያስረዳው ሕፃኑ፣ ድርጊቱን የፈጸሙበት በባዶ ክፍል ውስጥ በዕረፍትና በምሳ ሰዓት መሆኑን ተናግሯል፡፡
አንደኛው መምህር ድርጊቱን ሲፈጽም ሌላኛው መምህር እንደሚይዘው የተናገረው ተጠቂው፣ ድርጊቱን አንዳንድ ጊዜ በቢሮ ውስጥ እንደሚፈጽሙበት አስረድቷል፡፡
የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ለሕፃኑ ‹‹ስንት ጊዜ ተደፈርክ?›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡለት፣ ‹‹ብዙ ጊዜ ቀን ቀን እያሳለፉ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በተከታታይ ደፍረውኛል፤›› ብሏል፡፡ የመምህራኑን ስም እየጠራ በተደጋጋሚ ድርጊቱን እንደፈጸሙበት ገልጿል፡፡
ለቤተሰቡ መጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ለማን እንደሆነ ተጠይቆ ለእናቱ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ከነገራቸው በኋላም ትምህርት ቤት መሄዱን አላማቋረጡን አክሏል፡፡ ለምን ለአባቱ እንዳልተናገረ ሲጠየቅ፣ ‹‹እኔ እንጃ የሰማ አልመሰለኝም›› ብሏል፡፡ በተደጋጋሚ ድርጊቱ ሲፈጸምበት ለእናቱ ቢናገርም ከትምህርት ቤት አለመቅረቱን ገልጿል፡፡ ወደ ሆስፒታል እናቱ እንደወሰዱት ነገር ግን አባቱ ይወቁ አይወቁ የሚያውቀው ነገር እንደሌላ ገልጿል፡፡ ሲደፈር መጮህ አለመጮኹን እንዲያስረዳ ተጠይቆ እንዳልጮኸ ተናግሯል፡፡ አካላዊ ጉዳት እንዳልደረሰበት ግን ትንሽ አሞት እንደነበር ገልጿል፡፡ ሲፀዳዳ አንዳንድ ጊዜ እንደሚያመውም አክሏል፡፡ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ እዚያው ከተደረገበት ቦታ ትተውት ሲሄዱ ወደ ጨዋታው መሄዱንና ብቻውን መጫወቱን ተናግሯል፡፡ ሌላ ጊዜም በተደጋጋሚ ሲደፈር ጊዜ ካለው ወደ ጨዋታ እንደሚሄድ ጊዜ ከሌለው ወደ ትምህርቱ እንደሚገባ ገልጿል፡፡ የትምህርት ቤቱን ሠራተኞች ስለሚፈራም ለማንም አለመናገሩን አስረድቷል፡፡ ሊደፍሩት የሚወስዱት ብቻውን ሲያገኙት መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
ሁለተኛው የግል ተበዳይ የ11 ዓመት ዕድሜ ያለው የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሕፃን ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ ለአንደኛው የግል ተበዳይ ባስያዘው ጭብጥ መሠረት የተፈጸመበትን ድርጊት ለችሎቱ እንዲያስረዳ ጠይቆት ሕፃኑ አስረድቷል፡፡
የሁሉንም ተጠርጣሪዎች ስም ሲጣራ ‹‹ምን አደረጉህ?›› በማለት ዓቃቤ ሕግ ጠይቆት እንዳስረዳው፣ የሚኖረው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ለቡ ነው፡፡ ወደ ትምህርት ቤቱ የገባው በየካቲት ወር ነው፡፡ አምስት መምህራን ገና የገባ ዕለት ድርጊቱን እንደፈጸሙበት ተናግሯል፡፡ ድርጊቱን ለመፈጸም ጣታቸውንም መጠቀማቸውን ሕፃኑ አክሏል፡፡
የተጠርጣሪዎች ጠበቆች ‹‹ድርጊቱን የፈጸሙብህ መጀመሪያ የገባህ ቀን ነው?›› በማለት ለሕፃኑ ላቀረቡለት መስቀለኛ ጥያቄ፣ ‹‹አዎ›› ብሏል፡፡ ለእናቱ እንደነገራቸውና ከሦስት ሳምንታት በኋላ ወደ ትምህርት ቤቱ መመለሱን አስረድቷል፡፡ እናቱ ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩት ሞባይል ስልክ አስይዘውት ‹‹ሲጠሩህ ደውልልኝ›› እንዳሉት የተናገረው ሕፃኑ፣ መምህራኑ ሲጠሩት ሊደውል ሲል ሱፐርቫይዘሩ እንደከለከሉት ገልጿል፡፡
በሌላኛው ሕፃን ላይ ጥቃት መፈጸሙንና እንዴት እንዳወቀ ጠበቆች ሲጠይቁት እናቶቻቸው ተገናኝተው ሲነጋገሩ መስማቱን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በስልክ ሲያወሩ መስማቱን፣ በመቀጠል ደግሞ ተጠቂ ነኝ ያለው ልጅ እንደነገረው አስረድቷል፡፡
ለቤተሰቦቹ ለምን እንዳልተናገረ ሲጠየቅ ደግሞ፣ ተጠርጣሪዎቹ እንደሚገድሉት ስላስፈራሩት መሆኑን ሲናገር፣ ‹‹ታዲያ እንዴት ለእናትህ ተናገርክ?›› ሲባል ከንፈሩ በልዞ ተመልክተው ‹‹ካልነገርከኝ ራሴን መኪና ውስጥ ከትቼ አጠፋለሁ›› ስላሉት ፈርቶ መናገሩን አስረድቷል፡፡
ከተደፈረ በኋላ ወዴት እንደሚሄድ ተጠይቆ ወደ ጨዋታ እንደሚሄድ ተናግሯል፡፡ እናቱ ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩት ቲሸርቱንና የሱሪውን ወገብ ሰፍተው መሆኑን፣ ነግር ግን ድርጊቱን የሚፈጽሙበት ስፌቱን ቀደው መሆኑን አስረድቷል፡፡ መፀዳጃ ቤት እንዴት እንደሚጠቀም ሲጠየቅ፣ ‹‹ጠዋት ቤት ከተፀዳዳሁ ስመለስ ነው የምጠቀመው፤›› ብሏል፡፡
ሆስፒታል ስለመወሰዱ ተጠይቆ፣ የመጀመርያው ቀንና የመጨረሻው ቀን ጋንዲና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንደተወሰደና ድርጊቱ የተፈጸመበት ለሦስት ቀናት መሆኑን ገልጿል፡፡
የመጀመርያው ተጠቂ እናት በሰጡት ምስክርነት እንደገለጹት፣ መምህራኑ በልጃቸው ላይ ተፈራርቀው ጥቃት አድርሰውበታል፡፡ በሌላ ትምህርት ቤትም ተደፍሮ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ከነበረበት ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ካራክተር ሆልማርክ አስገቡት፡፡ በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም. መጀመርያ ቀን ዳይሬክተሩ ከየትና እንዴት እንደመጣ ከጠየቀው በኋላ፣ እንደደፈረውና ሌሎቹም ደጋግመው እንዳደረጉት እንደነገራቸው አስረድተዋል፡፡
ለአካዳሚው የቦርድ አባል ለሆኑ ግለሰብ ሲደውሉላቸው፣ ተደፈረ የሚባለው ነገር ሊደረግ እንደማይችልና ስህተት መሆኑን ሲገልጹላቸው፣ ለሌሎች የአካዳሚው ሰዎች ቢናገሩም ምንም ዓይነት ዕርምጃ እንዳልተወሰደ ገልጸዋል፡፡
ጠበቆች እንዴት ከሌላ ትምህርት ቤት ሊያስወጡት እንደቻሉ ሲጠይቋቸው፣ በነበረበት ትምህርት ቤት ሌሎች ሲደፈሩ በማየቱ በቀጣይ እሱም ጋ ይደርሳል የሚል ሥጋት ስላደረባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህንን አካዳሚም የመረጡት በግብረሰዶማውያን ዙሪያ የሚያስተምሩትንና የአካዳሚው የቦርድ አባልን አግኝተዋቸው ሲያስረዷቸው፣ ‹‹አምጭው እኛ ጋ ይማር›› ስላሏቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ ትምህርት ቤት ጥቃቱ ደርሶበት ወንጀለኞቹ እንደተፈረደባቸውም ተናግረዋል፡፡
ባለቤታቸው ትልቅ ቦታ ያሉ በመሆናቸውና ታማሚ በመሆናቸው እንዲሁም ልጁ አንድ ልጃቸው በመሆኑ ፈርተው እንዳልነገሯቸው ገልጸዋል፡፡ ከጥቅምት እስከ መጋቢት ድርጊቱ እንደተፈጸመበት እየነገራቸው ትምህርት ቤት እንደወሰዱት አስረድተዋል፡፡ ለምን ወደ ሕግ እንዳልወሰዱት ተጠይቀው፣ ከአባቱ ጋር ካልተስማሙ የማስቀረት አቅም እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ ባለቤታቸው ቢነግሯቸውም ‹‹ሊሆን አይችልም›› እንደሚሏቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጀመርያው ቀን ስድስቱም አስተማሪዎች እንደደፈሩት እንደነገራቸው ገልጸዋል፡፡ ገና እንደገባ እንዴት ሊያውቃቸው (ስማቸውን) እንደቻለ ሲጠየቁ፣ ሁሉንም ከነስማቸው እንደሚያውቃቸው ጠቁመዋል፡፡
የሁለተኛው ተጠቂ እናትም በልጃቸው ላይ ጥቃቱ እንደደረሰ ያወቁት ከሦስት ሳምንታት በኋላ መሆኑን ተናግረው፣ ድርጊቱን የፈጸሙበት ግን ትምህርት ቤቱ በገባ ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አምስት መምህራን እንደደፈሩት ለትምህርት ቤቱ ቦርድና ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን፣ ካሜራ ለመግጠም ቢሞከርም መነቀሉን፣ ጋንዲና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወስደው ማስመርመራቸውንም መስክረዋል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወስደው ለሥነ ልቡና ባለሙያዎች ማማከራቸውንም አክለዋል፡፡
ልጃቸው ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ አምስተኛው ትምህርት ቤቱ መሆኑን የገለጹት የተጠቂው እናት፣ በአራቱም ትምህርት ቤቶች መደፈሩን አስረድተዋል፡፡ የትምህርት ቤቶቹን ስምም ጠቅሰዋል፡፡ ለፖሊስ እንዲደውል ስልክ አስይዘው ቢልኩትም ዳይሬክተሩ እንደነጠቁት፣ እናቱ ስልኩን ሲያዩት መደወሉን አይተው ‹‹ተደፈርክ?›› ሲሉት ‹‹አልተደፈርኩም›› ቢላቸውም፣ ‹‹እውነቱን ካልነገርከኝ መኪና ውስጥ እገባለሁ›› በማለታቸው በድጋሚ መደፈሩን እንደነገራቸው አስረድተዋል፡፡
ጠበቆች እውነቱን እየነገራቸው ለምን እንዳስጨነቁት ሲጠይቋቸው፣ ‹‹ስለፈራ እንጂ እንደተደፈረማ አውቃለሁ፤›› ብለዋል፡፡ ሌላዋ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠራተኛ የሆኑ ግለሰብ ሲሆኑ፣ ልጆቹ እሳቸው ዘንድ የመጡ ቢሆንም ያነጋገሯቸው ከ20 ደቂቃ የማይበልጥ በመሆኑ ሙያዊ ማብራሪያ ሊሰጡ እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡
የመጨረሻዋ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የሕግ ባለሙያና የሕፃናት የሕግ ከለላ ማዕከል ኃላፊ ሲሆኑ ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውን፣ ነገር ግን ጉዳዩ ስለሚቀፍ መስማት እንዳልፈለጉ፣ ነገር ግን ተጠቂዎቹ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ቃላቸውን ሲሰጡ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተገኝተው መስማታቸውን መስክረዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃልንና ክሱን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡