Pages

Dec 26, 2012

ሁለት የአረና አባላት የድርጅቱን ልሳን ሲበትኑ ተያዙ


ኢሳት ዜና:-አረና ፓርቲ በየሶስት ወሩ ማሳተም የጀመረውን የድርጅቱን ልሳን ሲያሰራጩ የተገኙ 2 የድርጅቱ አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የመቀሌ የአረና  ጽህፈት ቤት ተጠሪ የሆኑት አቶ ሱልጣን ህህሸ ለኢሳት እንደተናገሩት አቶ አያሌው በየነና አቶ ተካልኝ  ታደሰ የተባሉት ድርጅቱ አባላት የተሳሩበት ምክንያት የፓርቲውን መታወቂያ አልያዛችሁም ተብለው ነው። ይሁን እንጅ ፓርቲው እስረኞቹ የድርጅቱ አባላት መሆናቸውን ለአካባቢው ፖሊስ መግለጹን አቶ ሱልጣን ተናግረዋል።
ትናንት ሰኞ እለትም በሁመራ አደላይ ቀበሌ ሌላው አባላቸው ወረቀት ሲበትኑ መያዛቸውን ፣ የጽህፈት ቤታቸው ሰንደቅ አላማ የሚውለበለብበት ምሰሶ መሰረቁንም ገልጸዋል።
በአረና ትግራይ አባላት ላይ የሚፈጸመው እንግልት እየጨመረ መምጣቱን ድርጅቱ በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል።
በጉዳዩ ዙሪያ የሽራሮ ፖሊስ አመራሮችን ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

የ40 በ60 የ”ቤት ልማት ፕሮግራም ትግበራ የመንግስት አካላትን ግራ አጋብቷል


ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ ከተማ ተጀምሮ ወደ ክልሎች ይስፋፋል በሚል ትልቅ ተስፋ እየተሰጠበት ያለውና በቁጠባ ላይ የተመሰተረው
የ40 በ60 ቤቶች ፕሮግራም አጀማመር ባለቤቱን አዲስአበባ አስተዳደርን ግራ በማጋባቱ እስካሁን ምዝገባ መጀመር
ባለመቻሉ በተለያዩ የተምታቱ መግለጫዎች ሕዝቡን ግራ እያጋቡት መሆናቸው ተሰማ፡፡
በአቶ መኩሪያ ኃይሌ የሚመራው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አጠናሁት ባለው መሰረት አንድ ቤት ፈላጊ
በስቱዲዮ፣ባለአንድ መኝታ ወይም ባለሁለት መኝታ መርጦ ውል ከፈጸመ በኃላ ለአምስት ዓመታት የቤቱን ግምት 40
በመቶ ቆጥቦ ቀሪው 60 በመቶ ከባንክ በሚገኝ ብድር ተሸፍኖ የቤት ባለቤት የሚሆንበት ዕቅድ ነበር፡፡
ዕቅዱ በተለይ መካከለኛ ገቢ ያለውን የመንግስት ሰራተኖችን ጨምሮ ሌሎች የኀብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል በሚል
ብዙ የተወራለት ቢሆንም በቀላሉ ሥራ ላይ ማዋል ግን አልተቻለም፡፡
ዕቅዱን አስመልክቶ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን፣የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር እና ብድር ያቀርባል የተባለው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች እርስበርስ የሚጣረሱ መረጃዎችን ለሕዝብ ከመልቀቅ ጀምሮ ምዝገባ በዚህ
ቀን ይጀመራል በሚል ከፍተኛ ሁካታና ሰልፍ ያስከተለ መግለጫዎችን ሲሰጡ ቢከርሙም ምዝገባውን ግን መጀመር
አልቻሉም፡፡
ስለዚህ ጉዳይ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን በቅርቡ አስተያየት የተጠየቁት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን
ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ የተሳሳተ መረጃ የሚሰጡ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ እስከመግለጽ የደረሱበት
ሁኔታ መኖሩንም ምንጫችን አስታውሶአል፡፡
ይህም ሆኖ አቶ መኩሪያ ራሳቸው በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም ለፓርላማው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የቤት ፕሮግራሙ ምዝገባ ይጀመራል በማለት ቃላቸውን ቢሰጡም ሁለት ወራት አልፎም ምዝገባው ሊጀመር አለመቻሉም ውዥንብር ከሚነዙት ውስጥ አንዱ አድርጓቸዋል፡፡
የ40 በ60 የቤት ልማት ፕሮግራም ምዝገባ ለመጀመር አስቸጋሪ ያደረገው በርካታ ያልተመለሱ ጥያቄዎች በመኖራቸው
መሆኑን ምንጫችን ጠቅሷል፡፡ከነዚህም መካከል “መዝጋቢው አካል ማንነው?አንድ ሰው ቤት እንደሌለው በምን ተረጋግጦ
ይመዘገባል?አንድ ሰው ለአምስት ዓመታት ቆጥቦ በቀጥታ ቤቱን ማግኘት ይችላል ወይ?የተገነቡት ቤቶች ከቆጣቢዎቹ
ቁጥር በላይ ከሆነ ምን ይደረጋል?በዕጣ የሚለይ ከሆነ አንድ ሰው አምስት ዓመት ሙሉ ተቸግሮ የመቆጠቡን ፋይዳ
ዋጋ አያሳጣውም ወይ? በየጊዜው በዕጣ የሚለይ ከሆነ ሰውየው የቤት ባለቤት የሚሆነው መቼ ነው?እስከዚያስ ገንዘቡ
በባንክ ታስሮ መቆየቱ ምን ያህል ተገቢ ነው?የቤቱን ሙሉ ክፍያ በአንዴ መፈጸም የሚችሉ ቤት ፈላጊዎች እንዴት
ይስተናገዳሉ?አንድ ሰው ቁጠባ ጀምሮ ቢያቋርጥ ገንዘቡን እንዴት ማግኘት ይችላል?ቁጠባውን ያቋረጠው ሰው
የጀመረውን መሸጥ ወይም ለሌላ ማስተላለፍ መብት ይኖረዋል ወይ?” እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ሚኒስቴሩም ሆነ የከተማ
አስተዳደሩ በመመሪያ መመለስ አልቻሉም፡፡
በዚህ ምክንያት አሁንም ሕዝቡን ከነገ ፣ዛሬ ምዝገባው ይጀመራል ፣የቤት ችግራችሁም ይቀረፋል በሚል ተስፋ ከመመገብ ባለፈ በትክክለ ምዝገባው የሚጀመርበት ጊዜ አለመታወቁ እንቆቅልሽ ሆኗል፡፡
ከዚሁ ጋርም ተያይዞ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የኀብረተሰብ ክፍሎች የገነባል የተባለው የ10 በ90 የቤቶች ግንባታም
ተመሳሳይ ችግር ውስጥ በመሆኑ እንዳልተጀመረ ታውቋል፡፡

የህወሀት አባላት የሆኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ በመምጣት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ ሊመክሩ ነው


ኢሳት ዜና:-ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር  ደብረ-ጽዮን ገብረሚካኤል፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሀኖም እና አቶ አባይ ወልዱ በመጪው ጥር ወር አሜሪካ በመምጣት  ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ እንደሚመክሩ ተመለከተ።
የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በ ኢትዮጵያ  ፖለቲካዊ ጉዳይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር እንዲመካከሩ መድረኩን ያመቻቸው የትግራይ ልማት ማህበር ነው።
ደ-ብረብርሀን ብሎግ እንደዘገበው የትግራይ ልማት ማህበር በዲያስፓራ  ራሱን የቻለ የትግራይ መንግስት እየፈጠረ ያለ  ድርጅት ነው።
አንድ የትግራይ ተወላጅ ወደ ውጪ አገር በሚመጣበት ጊዜ ወዲያው በመመዝገብ ታክስ እንደሚሰበስብ የጠቀሰው ብሎጉ፤ ማህበሩ  ከረዥም ጊዜ አንስቶ በዲያስፖራ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸው ለመለየት እየደከመ የሚገኝ ጽንፈኛ ማህበር መሆኑን ጠቁሟል።
ይህ ጽንፈኛ ማህበር ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ የትግራይ ብሄርተኝነትን ለማስፋፋት  እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በማውሳትም፤ በመጪው ጥር ወር ወደ አሜሪካ የሚመጡት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በ አገር ጉዳይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ እንዲሰበሰቡ የግብዣ ጥሪ ያቀረበውና ፕሮግራሙን ያዘጋጀውም ይኸው የትግራይ ልማት ማህበር መሆኑን አመልክቷል።
በሚኒሶታና አካባቢው የሚኒሩ የትግራይ ተወላጆች በተደጋጋሚ ባወጧቸው መግለጫዎች ፦የመንግስት ባለስልጣናት  ወደ ወጪ አገር ሲመጡ የትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ ስብሰባ ማድረጋቸውን በማውገዝ፤ የህወሀት መሪዎች  የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለመለያዬት ከሚከተሉት ጠባብ  የጎሰኝነት መንገድ እንዲታረሙ ማሻሰባቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ ዱባይ ለሥራ እንዳይሄዱ በህግ ታገዱ


ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት  ሴቶች ወደተባበሩት አረብ ኢምሬት(ዱባይ) ለሥራ  እንዳይሄዱ በህግ ማገዱን አስታወቀ።ህገ-ወጥ ጉዞው ግን እንደቀጠለ ነው አለ።
በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሸለመ ፥ በጉብኘትና በግል ቪዛ በቤት ሰራተኛነት ለመቀጠር ወደ ዱባይ የሚያደረገው ጉዞ እንዲቆም የተደረገው ራስን ለከፋ ችግር የሚዳርግ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ዜጎች ህጋዊ ጥቅሞቻቸውና መብቶቻቸው ተጠብቀውላቸው እንዲሰሩ የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ ሀገራት ጋር የንግድ የሰራተኛ ቅጥርና የተለያዩ ውሎች  ስምምነት አለው  ያሉት ዳይሬክተሩ፤ኢትዮጵያ በዚህ መልኩ ስምምነት የተፈራረመችው ከሳውዲ አረቢያና ከኩዌት ጋር ሲሆን ፥ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋርም ተመሳሳይ ስምምነት ላይ ለመድረስ  ገና በሂደት ላይ  ትገኛለች ብለዋል።
<<ወደ ዱባይ   የሚደረግ ጉዞ ለዜጎች ደህነነት ሲባል ቢከለከልም፤ በህገ ወጥ መንገድ የሚደረገው  ጉዞ ግን  አሁንም አልቀረም።>>ብለዋል-አቶ ግርማ።
መንግስት ወደ ዱባይ ለቤት ሰራተኝነት የሚደረገው ጉዞ እንዲቆም ያደረገው ፥ በዚህ ጉዞ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለከፋ እንግልት የሚዳርጉ ውስብስብ ችግሮችን ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግስት ጋር በመመካከር ለመፍታት ነው ሲሉም አክለዋል።
ዜጎች ከሁሉም በላይ በሀገራቸው ባለው የስራ አማራጭ ለመጠቀም መጣር አለባቸው ያሉት አቶ ግርማ ፥ ጉዞ ካስፈለገም ህጋዊ መንገድን ተከትሎ ብቻ በመሄድ መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን የፋና ዘገባ ያመለክታል።
ይሁንና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት ያለው  ከሳዑዲ አረቢያና ከኩዌት መንግስታት ጋር ነው ቢሉም፤  አለ የሚሉት ውልና ስምምነት  በተጠቀሱት አገሮች  ያሉትን ኢትዮጵያውያን ከመከራ ሊታደጋቸው አልቻለም።
በሳዑዲና በኩዌት  በሚገኙ  በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይም  ከዱባይ ባልተናነሰ መልኩ በተደጋጋሚ ዘግናኝ በደልና ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

ወይ “መዓልቲ” አለ ያገሬ ሰው!

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አባል ሀገር ሆና ተመረጠች።
የትኛዋ ኢትዮጵያ!? የትኛው ሰብአዊ መብት!? የትኛው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን!?

እኔ የምለው ኢትዮጵያዊው የዩልኝታ ባህላችን ያለው ህብረተሰቡ ዘንድ ብቻ መሆኑ በጣም አሳሳቢ ችግር አይመስላችሁም? እንዴ መንግስት እኮ ይሉኝታ ቢኖረው ኖሮ “ተመድ የሰባዊ መብት ኮሚሽን አባል አድርጌ መርጨሀለሁ!” ሲለው… “አረ በህግ አምላክ እኔ አልሆናችሁም ሀገር ተሳስታችሁ ነው! ወይ ደግሞ ባታውቁኝ ነው የመረጣችሁኝ…!” ማለት ነበረበት። ነገር ግን መንግስቴ “ምን ይሉኝ” ያልፈጠረበት ነውና አሜን ብሎ መቀበሉ ሲገርመን፤ ጭራሽ በአደባባይ “እንዲህ ነን እኛ ሰብአዊ መብት ጠባቂዎች” ተብሎ ተነገረን!ኢቲቪ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታማሚ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን አማካይነት፤ “ድሮውንም እኛ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ዘብ የቆምን ሰዎች ነን!” ብሎናል።
አቶ ዲና በሚወዱት ይማሉልኝ የሚናገሩት የምርዎትን ነው!? ከማሉልኝ ዛሬ ነገ ሳልል ሀገሬ እመጣለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የሰብአዊ መብት ጥሰቱን ፈርቶ የወጣው ኢትዮጵያዊ ሁሉ “ምን አለኝ ሀገሬ” (“ለ“ን አጥብቆ) ዘፍኖ እንደወጣው ሁሉ፤ “ምን አለኝ ሀገሬ” በሚል “ለ”ን አላልቶ ዘፍኖ ይመለሳል። ግን እርግጠኛ ነኝ በሚወዱት አይምልሉንም! ለመሆኑ የሚወዱትስ አለ…!? ወይስ ነፍስ ይማር እንበልልዎ!?
የምር ግን ሰብአዊ መብት ማለት ምን ማለት ነበረ!?

“ወይ መዓልቲ” አለ ያገሬ ሰው!
የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ የተሳካ እና ውጤታማ ለማድረግ በ አንድነት ተነስተናል

ሰላም ወገኖች
እኛ በኖርዎይ የምንገኝ የኢትዮጵያ ስደተኞች ሃገራችን የሚገኘውን ዘረኛ ፣ አፋኝ እና አምባገነን መንግስት በመቃዎም ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች እያደረግን እንገኛለን ። ከነዚህ እንቅስቃሴዎች መካከል አንዱ የኢትዮጵያን ህዝብ እውነተኛ የሆነ መረጃ እንዲያገኝ ፤ በሃገር ወዳድ የኢትዮጵያ ዜጎች የተቋቋመውን ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን(ኢሳት) መርዳት ነው ።


እንደምናውቀው ተራራውን አንቀጠቀጠን የሚሉትን የማፊያ ቡድን ወያኔን ፤ ኢሳት እውነት ለኢትዮጵያን ህዝብ በማቀበል ብቻ እያንቀጠቀጣቸው ይገኛል ። ኢሳት የኢትዮጵያን ብቸኛ ህዝብ አይን እና ጆሮ ብቸኛ ሳይሆን በተግባርም አንደበት ስለሆነ Feb 10-2013 በ ኖርዎይ ዋና ከተማ በኦስሎ ይካሄዳል ። በዚህ ቀን ሃገር ወዳድ ወንድማችን ታማኙ አርቲስት ታማኝ በየነ ተጋባዥ እንግዳችን ነው ። ለኢሳት ፣ ለአርቲስት ታማኝ በየነ እንዲሁም ለኢትዮጵያን ህዝብ ክብር ስንል በስደት የምንኖርበት ሃገር የሚደረገውን የገቢ ማሰባሰቢያ የተሳካ እና ውጤታማ ለማድረግ በ አንድነት ተነስተናል ።

በዚህ አጋጣሚ በኖርዎይ የምትገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያ ወዳጆች በዚህ ዝግጅት በመገኘት ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን (ኢሳት) ለሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ የራስዎን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በክብር ጋብዘንዎታል ።


ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ሞት ለውያኔ እና ሆድ አደሮች !!!

HISTORIC SPEECH BY ABEBE GELAW

እውነትን ሸሽተን የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ልናመጣ አንችልም






ዘመነ ካሣ ከጀርመን
ለሁለት አሥር ዓመታት ቤ ተ ክርስቲያንን ለሁለትና ብሎም ለሦስት እንድትከፈል አንድነታ ተናግቶ ካሕናትና
ምዕመናን ተለያይተው አሁን ለደረስንበት ጊዜ የቆየው በሕገ ቤተ ክርስቲያን የተሾሙት ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ
አቡነ መርቆሬዎስ ከጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ወንበራቸው ያለአገባብ በሕመም ምክንያት አሳበው በዘረኛውና
በጎጠኛው ወያኔ መንግሥት አማከይነት እንዲለቁ የተደረገ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው አውነት ነው::
ይሁን እንጂ ይህነ ግዙፍ እውነት በመካድ አዲስ አበባ ያሉት የሲኖዶሰ አባላት በሕመም ምክንያት መሥራት አልችልም
ብለው ነው የለቀቁት በማለት መሠረተ ቢስ የሆነ የሀሰት ቃል ሲናገሩ መሰማት ከመነኮሳት አባቶች ያውም ለእውነትና
ለቤተክርስቲያን ቆመናል ከሚሉ ሰዎች ሲሰማ እጅግ የሚዘገንን ነው ማን ነው ታዲያ እውነት ሊናገር የሚችል ??
አባሕዝቅኤል ተብለው የሚጠሩት ጳጳስ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ዓለም የሚያውቀው እውነት በመካድ ሀሰት
ሲናገሩ ትንሽ እንኳን የማይከብዳቸው ሰው ናቸው

ሰሞኑን በፕሬዝዳንት ግርማ የተጻፈውና ወዲያው የተሻረው ደብዳቤ መልካም የሚያሰኝ ነገር እንዳለ አመላክቶ ነበር፡፡
ሆኖም ዋናው ችግር በማን በኩል እንዳለ የፕሬዝዳንቱን ደብዳቤ ተከትሎ የተወሰዱ እርምጃዎች ትልቅ ማሳያ
ሆነዋል፡፡ ቤተክህነቱ በፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ ስላልተደሰተ መንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ እንደገባ በመቁጠር
ፕሬዝዳንቱን መውቀሱና ፕሬዝዳንቱም የጸፉትን ደብዳቤ ለማጠፍ እንደተገደዱ መረዳት ተችሏል፡፡ ቤተክህነቱ
የፕሬዝዳንት ግርማን ደብዳቤ ተቃውሞ ሲነሳ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገቡ በሚል ቢሆንም በዋናነት ግን አቡነ
መርቆሬዎስን ላለመቀበል ትልቅ ሽፋን የነበረውና «እኛ ይመለሱ ብንልም መንግስት አይደግፋቸውም» የሚለው ሰበብ
በፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤ በጥቂቱም ቢሆን መሸርሸሩ ደስ ስላላሰኛቸውና ከዚህ ውጪ የሚያቀርቡት ምክንያት ብዙ
የሚያራምዳቸው ሆኖ ባለመገኘቱ እንደሆነ ተገምቷል፡፡

አቡነ ጳውሎስ
በሕይወት
እያሉ በውጭ
ካለው
ሲኖዶስ ጋር
ለሚካሄደው
የእርቁ ሂደት
ትልቅ
እንቅፋት
እንደሆኑ
ተደርጎ
አብረዋቸው
ባሉትና ያኔ
ሲቃወሟቸው
በነበሩትና ዛሬ
የሚሉትላለመታረቅ ወስነው እርቁ 

ጳጳሳት ጭምር ብዙ ሲባል እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ከእርሳቸው ዕረፍት በኋላ ነገሮች ይለወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም
እንዲያውም ብሰው ነው የተገኙት፡፡ ቀድሞስ አቡነ ጳውሎስ ናቸው እንቢ ያሉት እንበል፤ አሁን ግን አቡነ መርቆሬዎስ
ወደመንበራቸው ሊመለሱ አይገባም የሚሉት ጳጳሳት አላማቸው ምንድነው? የሚለው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በተለይም
«5ኛ ብለን ወደ4ኛ አንመለስም፤ 6ኛ ነው የምንለው» የሚለው ምላሽ ለአቡነ ጳውሎስ ክብር ከመጨነቅ የሚመነጭ
እንዳልሆነ ታውቋል፡፡ ይህን መግለጫ የሰጡት አቡነ ህዝቅኤልን ጨምሮ ሲኖዶሱን እያናወጡ ያሉት ጥቂት አስቸጋሪ
ጳጳሳት አቡነ ጳውሎስ የሾሟቸውና የአቡነ ጳውሎስ ተቃዋሚ ሆነው የዘለቁ ናቸው፡፡ ታዲያ ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ
ለምን እንዲህ አሉ? ይህን አቋምስ ለምን ያዙ ቢባል አንዱ ምክንያት ቀጣዩ ፓትርያርክ ለመሆን እየተሻኮቱ ስለሆነና
የአቡነ መርቆሬዎስ ወደመንበራቸው መመለስ ነገሮችን ሊቀይርባቸው ስለሚችል ነው። እነዚህ ጳጳሳት የግል
ጥቅማቸው እንጂ የቤተክርስቲያን አንድነት እንደማያሳስባቸው ግልጽ እያደረጉ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ለ 20ዓመታት በ ሁለት ሲኖዶስ ስተመራ የቆየችው እኮ የቀድሞው ፓትርያርክ በህይወት እያሉ
ለምን ሌላ ፓትርያርክ ተሾመ በሚል የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ነበር። እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ አንደኛው ከዚህ
ዓለም በሞት ተለዩ። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድነት ለመመለስ ግልጽና ትክክል የሆነው እርምጃ በይህወት ያሉትን
ፓትርያርክ ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን መሪ ማድረግ ነው። ይሄ ለምን ድርድር እንደሚያስፈልገውና ከባድ እንደሆነ
ለህዝብ ግልጽ አይደለም።
የዚህች ቤተ ክርስቲያን አንድ መሆን ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ድርሻ ነበረው ይሁንና የቀኖና ቤተክርስቲያንን
መጣስ ወደ ጎን በመተው ላለመታረቅ ሰንካላ ምክንያት በመደርደር የቤተ ክርስቲያን መከራ እንዲራዘም የሚሮጡ
ትንሽ ናቸው ማለት አይቻልም ከአንዳድ የሥልጣን ጥመኞች ጳጳሳት በግለሰብና በማሕበር የተደራጁ ቡድኖች
በስውርና በግልጽ የሚሸርቡት ተንኮል እጅግ አስገራሚነው የማሕበረ ቅዱሳን አባላት ነን የሚሉት እነ ዲያቆን ዳንኤል
ክብረት የሚሰጡት አስተያየት ስድስተኛ ፐትርያርክ ለማስመረጥ ሕግ በማርቀቅ የሚሮጡት አነ ቄስ ሰሙ ምትኩ
በፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴነት ላይ ታች ከሚሉት እነ አአቶ ባያብል ሙላቴ የሚሸርቡት ተንኮል እጅግ አሳፋሪ
ነው ታዲያ ቀደም ሲል በፓትርያርክ ምርጫና ቅስቀሳ ተጠምዶ የነበረው ደጀሰላም አሁን ላይ ስለ እርቅ መስበኩ ረፈደ
ባይባልም ስለ ቀኖና ቤተክርስቲያን መጣስ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዴት ሊፈርስ እነደቻለ እውነቱን ከመጻፍ
ይልቅ ” አቡነ መርቆሬዎስ የት ነው ያሉት ” በማለት የፍለጋ ማስታወቂያ ሲሠራና የምርጫ ደንብ ሲያረቅ እንደሰነበተ
ሊካድ የማይችል እውነት ነው

ስለዚህ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች መፈትሔው አጭርና ግልጽ ነው ችግሩ የቀኖና ቤተ
ክርስቲያን መጣስ እስከሆነ ድረስ መፍትሔው በሕይወት ያሉትን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ማድረግ
ነው ሐቁንም መከተል ሕገ ቤተ ክርስተያንንንም ማክበር ነው
እውነትን በማድበስበስ መግለጫ በመደርደር አንድነት ሊመጣ አይችልም

ESAT Meade Esat Ethiopia Dec 24 2012

Dec 25, 2012

የግንቦት7 ህዝባዊ ሐይል ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ


ኢሳት ዜና:-የድርጅቱ ቃል አቀባይ ታጋይ ዜና ጉታ ለኢሳት እንደገለጠው ከትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወይም ደሚት፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህና እኩልነት ግንባር፣ ከጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከተባሉት ድርጅቶች ጋር በጥምረት ለመስራት አስፈላጊው ዝግጅት አጠናቋል።
ታጋይ ዜና ጉታ ህዝባዊ ሀይሉ በዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ከሚመራው የግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጋር ግንኙነት እንዳለው ጥያቄ ቢቀርብለትም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

ከቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባዔ ምርጫ አዳዲስ አመራሮች አይጠበቁም ተባለ


ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ ጉባዔ በየካቲት ወር በመቀሌ ከተማ የግንባሩን አመራር ይመርጣል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም ምርጫው ግን
ብዙም አዳዲሰ ለውጦች እንደማይኖሩት ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገለጡ
በግንባሩ ሕገደንብ መሰረት ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ የሚካሄደው ይኸው ጉባዔ በየካቲት
ወር 2005 ሲካሄድ ግንባሩን ለቀጣይ ሁለት ዓመት የሚያገለግሉ አመራሮችን ይመርጣል፡፡
በዚሁ መሰረት የግንባሩ አባል ድርጅቶች እስከቀጣዩ ወር የራሳቸውን ጉባዔ በማካሄድ ለኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚነት የሚያገለግሉ
እያንዳንዳቸው ዘጠኝ አባላትን የሚመርጡ ሲሆን እነዚህ በጠቅላላው 36 አባላት የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ በመሆን
ከመካከላቸው የግንባሩን ሊቀመንበር፣ምክትል ሊቀመንበር ምርጫ በጉባዔው ላይ ያከናወናሉ፡፡
ይህ ጉባዔ ከአቶ መለስ ሞት በኃላ በቅርቡ የተሾሙትን የግንባሩን ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርም ደሳለኝ እና ምክትላቸውን አቶ ደመቀ መኮንን ያነሳል ተብሎ እንደማይገመት ታውቋል፡፡
በሕመም ምክንያት ረዥም የሕክምና ክትትል ላይ የሚገኙት የአህዴድ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ በምክትላቸው
አቶ ሙክታር ከድር ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አቶ አለማየሁ ቀደም ሲልም መልቀቂያ ከማቅረባቸው ጋር ተያይዞ በቅርቡ በተካሄደው የሶስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት ውስጥ ኦህዴድን መወከል የሚገባቸው እሳቸው የነበሩ ቢሆንም ምክትላቸው አቶ ሙክታር እንዲሾሙ ኦህዴድ በወከላቸው መሰረት አቶ ኃይለማርያም ካቢኔ ውስጥ መካተታቸው ይታወሳል፡፡
በተያያዘ ዜና በቅርቡ የተካሄደው ሹመት ብዙም ያላስደሰታቸው የህወሃት አባላት የቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
የነበሩትን አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖምን ወደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት እንዲዛወሩ ያደረጉት ከሁለት ዓመት በኃላ
የጠ/ሚኒስትርነትን ቦታ እንዲይዙ ታቅዶ ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶች አሉ።
የአቶ መለስ ሞት ከማንም በላይ ህወሃቶችን ያደናገጠና ሁኔታውንም ተከትሎ የተሰጡ ሹመቶች ነባር የሚባሉ ከፍተኛ
የህወሃት አመራሮችን ጭምር እንዳላረካ የሚጠቅሱት የቅርብ ሰዎች፣  ትልቁ የህወሃቶች ስጋት ከእጃቸው የወጣውን ስልጣን መቼ
መልሰው እንደሚያገኙት እርግጠኛ መሆን አለመቻላቸውና ብዙዎቹ አመራሮች ከፍተኛ ሃብት ከማፍራታቸው ጋር ተያይዞ
ስጋት ላይ በመውደቃቸው ነው ተብሎአል፡፡
ይህ ጉዳይ በህወሃቶች በሚስጢር ተመክሮበት አቶ ቴዎድሮስ ከጠ/ሚኒስትር ኃይለማርም ጋር በቅርበት መስራት በሚያስችላቸው ቦታ በማስጠጋት በ2007 ዓ.ም አገራዊ ምርጫን ተከትሎ በሚደረገው የጠ/ሚኒስትር ሹመት ብቁ ማድረግ የሚለው ዕቅዳቸው በፓርቲያቸው ተቀባይነት አግኝቶ መተግበሩን አስረድተዋል፡፡
እንደ ህወሃቶች ዕቅድ ከሆነ አቶ ኃይለማርያም ከሁለት ዓመት ስልጣን በኃላ መሰናበታቸው ግድ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጅ  ይህ የተባለው ዕቅድ መኖርና አለመኖሩን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልተቻለም።
ኢህአዴግ ባስቀመጠው የመተካካት ዕቅድ መሰረት የብአዴን ጎምቱ የተባሉ አመራሮች በአዲስ መተካት ሚኖርባቸው ቢሆንም እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት እንደ እነአቶ በረከት ስምኦን የመሳሰሉ ነባር አመራሮች ከፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ስለመነሳታቸው ጉዳይ ምንም ዓይነት ፍንጭ አለመኖሩን ጠቁሟል።

መንግስት የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር አንድ አንጃ ከመንግስት ጋር ለመደራደር አዲስ አበባ ገባ በማለት የገለጸውን ግንባሩ አስተባባለ


ኢሳት ዜና:-ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መደራደር እፈልጋለሁ ህገመንግስቱንም ተቀብያለሁ ሲል በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን መግለጫ የሰጠው ግለሰብ ከድርጅቱ የተባረረ ተራ አባል መሆኑን የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር አስታወቀ::
የኢትዮጵያ መንግስት ከኦብነግ አንድ አንጃ ጋር መደራደሩን ቢያስታውቅም ኦብነግ ሀሰት ነው ሲል አስተባብሎል: በኦብነግ ውስጥም የተፈጠረ  አንዳች አንጃ አለመኖሩን ገልጧል::
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራር አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት በሰጡት  መግለጫ አብዲኑር አብድላሂ ፋራህ በኬኒያ የድርጅቱ የውጭ ግንኙነት ተራ አባል ሆነው ሲሰሩ እንደነበር አመልክተው የድርጅቱ የስለላ ቡድን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ስለደረሰበት በዚ ተገምግመው ኦክቶበር 14 ከድርጅቱ የተባረሩ መሆናቸውን ገልጠዋል::
ይሄ የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊት ለኛ አዲስ አይደለም ያሉት አቶ ሀሰን ከዚ በፊት ከኦብነግ ጋር በሸራተን ሆቴል ፊርማ መፈራረማቸውን በማስታወስ ከግለሰብ ጋር የተፈራረሙት ፊርማ ያመጣው ለውጥም ውጤትም እንደሌለ ተናግረዋል::
የኦጋዴን ነጸ አውጪ ግንባር በ 64 አገሮች የሚንቀሳቀስ ትልቅ ድርጅት ነው ያሉት አቶ ሀሰን በአሁኑ ሰአት በፖለቲካ አንጻር በከፍተኛ ሁኔታ የተጠናከረበት ፡ በውጊያ አውደ ግንባርም በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ወታደሮች በየጊዜው እጃቸውን እየሰጡ ያሉበት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል::
አንጃና መከፋፈል የሚባለው የኢትዮጵያ መንግስት ምኞትና ውቸት ነው ብለዋል አቶ ሀሰን አብዱልላሂ

በህውሀት የብቸኝነት እዝ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ከሚደረጉ ህዝባዊ ትግሎች ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ ቀረበ


ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የትግል አቅጣጫውንና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የደህንነት ሀይሎች ለመንግስት ህዝብን የመጨቆኛ መሳሪያ መሆናቸውን አቁመው ከህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፎል::
ህውሀት ኢህአዴግ በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው በደልና ግፍ ሊያበቃ ይገባል ያለው የሸንጎ መግለጫ በእስር ላይ ያሉት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ባስቸኮይ እንዲፈቱም መንግስትን አሳስቦል::
አፋኝ የሆኑ የሚዲያና የሽብርተኝነት ህጎች በሙሉ እንዲሰረዙ ያሳሰበው የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የመንግስት ሚዲያዎች ለምርጫ ግዜ ብቻ ለፕሮፓጋንዳ ሲባል የሚሰጥ ሽርፍራፊ ሰአት ቆሞ በመደበኛነት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል\::
የዲፕሎማቲክ የበላይነት በአንድ ወይም በሁለት ድርጅት ትግል እንደማይገኝ ያመለከተው የሸንጎ መግለጫ ለዘለቄታ ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት ለመብቃት ጠቃሚ ስትራቴጂዎችን በመቀየስ ከሌሎች ሀይሎች ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አመልክቶል::

አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት በሁሉም የመንግስት መ/ቤት ሰራተኞች ዘንድ በግዳጅ እየተሸጠ ነው


ኢሳት ዜና:-በሞቹ የቀድሞ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ የስራ ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት በሁሉም የመንግስት መ/ቤት ሰራተኞች ዘንድ በግዳጅ በ 100 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተገለጸ::
ከሀገር ቤት የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በጠ/ሚሩ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት ከ 2000 ብር በላይ ደሞዝተኛ የሆነ በአንድ ክፍያ 100 ብር ለመግዛት ይገደዳል ከ2000 ብር በታች ደመወዝ ያለው እንደደሞዙ ልክ በየወሩ ይቆረጥበታል::
የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በስብሰባ ተነግሮቸውና ሳያቁ እንዲፈርሙ ተደርጎ ከደመወዛቸው ለአዲስ ራዕይ መጽሄት 100 ብር መወሰዱን ቢቃወሙም ሰሚ እንዳላገኙ አስታውቀዋል::
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በህይወት ዘመናቸው የሰሩትን ስራ አጉልቶና አኩርቶ ይተርካል በተባለው መጽሄት የግዢ  ድርድር የሚባል ነገር የለም ሁሉም ሰራተኛ በአንድ መቶ ብር የመግዛት ግዴታ እንዳለበት በግልጽ ተነግሮል እንደ ምንጮቻችን ዘገባ::

አቶ በረከት ስምአን ተጽእኖቸው አየቀነሰ የህዋሃት ጡንቻ አየፈረጠመ መምጣቱ ተገለፀ


ኢሳት ዜና:-የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስተር መለሰ  ዜናዊ ማለፋቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ፖለትካ መድረከ ውስጥ  ሚናቸው ጎልቶ የነበረው አቶ በረከት ስምአን ተጽእኖቸው አየቀነሰ የህዋሃት ጡንቻ አየፈረጠመ መምጣቱ ተገለጸ::
የአረና ትግራይ አመራር አባል የሆኑት አቶ አስራት አብርሃም የውስጥ ምንጮችን ጠቅሰው ባሰራጩት ጹሁፍ አንዳመለከቱት አቶ በረከት ስለ ኤርትራ የስጡት መግለጫ  ህዋሃትን አሰተባብሮባቸዋል::
አቶ በረከት ስምኦን የኤርትራ ተቃዋሚዎች ፖልቶክ መድረክ ላይ ባድሜ የኤርትራ ነው በማለት መናገራቸው  እና ኤርትራዊያን ከሃገር አንዲባረሩ ያደረጉት አቶ ስየ አብርሃም ናቸው ሲሉ መደመጣቸው የህዋሃት ሰዎች በአቶ በረከት ላይ አንዲነሱ ምክናየት መሆኑም ተመልክቷል::
አቶ በረከት ኤርትራዊያን ከሃገር አንዳይባረሩ እርሳቸውና አቶ መለስ መሞከራቸውን ሆኖም አቶ ተወልደ ወ/ማረያም : አቶ ስየአብርሃና  አቶ ገብሩ አስራት የማባረሩ ሂደት ዋነኞቹ ተዋናዮች መሆናቸውን መስክረዋል::
አቶ በረከት በዚህ ረገድ የሰጡት መግለጫ የህዋሃትን ሰዎች በማስቆጣቱ ሚናቸው እየተገደበ ፡ተጽኑዋቸው እየቀነሰ መምጣቱን በዚህም የአቶ ሰብሃት ነጋ ቡድን እንዲያንሰራራ እድል መፍጠሩን ከጹሁፉ መረዳት ተችሏል::

Dec 24, 2012

Ethiopia 2012: Human Rights and Government Wrongs By Alemayehu G Mariam

Groundhog Year
In December 2008, I wrote a weekly commentary lamenting the fact that 2008 was "Groundhog Year” in Ethiopia:
It was a repetition of 2007, 2006, 2005, 2004... Everyday millions of Ethiopians woke up only to find themselves trapped in a time loop where their lives replayed like a broken record. Each "new" day is the same as the one before it: Repression, intimidation, corruption, incarceration, deception, brutalization and human rights violation… They have no idea how to get out of this awful cycle of misery, agony, despair and tribulation.
So, they pray and pray and pray and pray... for deliverance from Evil!
It is December 2012. Are Ethiopians better off today than they were in 2008, 2009, 2010, 2011? 
Does bread (teff) cost more today than it did in 2008…, a year ago? Cooking oil, produce, basic staples, beef, poultry, housing, water, electricity, household fuel, gasoline...?
Are there more poor people in Ethiopia today than there were in 2008? More hunger, homelessness, unemployment, less health care, fewer educational opportunities for young people?
Is there more corruption and secrecy and less transparency and accountability in December 2012 than in December 2008?
Are elections more free and fair in 2012 than in 2008?
Are there more political prisoners today than in 2008?
Is there less press freedom and are more journalists in prison today than in 2008?  
Is Ethiopia more dependent on international handouts for its daily bread today than it was in 2008?
Is there more environmental pollution, habitat destruction, forced human displacement and land grabbing in Ethiopia today than 2008?
Is Ethiopia today still at the very bottom of the U.N. Human Development Index?
The Evidence on Government Wrongs in Ethiopia in 2012
Human rights violations in Ethiopia continue to draw sharp and sustained condemnation from all of the major international human rights organizations and other legal bodies. In 2012, the ruling regime in that country has become intensely repressive and arrogantly intolerant of all dissent and opposition. The regime continues to trash its own Constitution, sneer at its international legal obligations and thumb its nose at its critics. Though some incorrigible optimists hoped a post-Meles regime would open up the political space, reach out to opposition elements and at least engage in human rights window dressing, the nauseating litany of those who are falling head over heels to fit into Meles’ shoes has been “there will be no change. We will (blindly) follow Meles’ vision…” In other words, 2013, 2014, 2015… will be no better than 2012 or 2008.
The evidence of sustained and massive official human rights violations in Ethiopia is overwhelming and irrefutable. Let the evidence speak for itself. 
The U.S. State Department Country Reports on Human Rights Practices in Ethiopia (May 2012) concluded:
The most significant human rights problems [in Ethiopia] included the government’s arrest of more than 100 opposition political figures, activists, journalists, and bloggers… The government restricted freedom of the press, and fear of harassment and arrest led journalists to practice self-censorship. The Charities and Societies Proclamation (CSO law) continued to impose severe restrictions on civil society and nongovernmental organization (NGO) activities… Other human rights problems included torture, beating, abuse, and mistreatment of detainees by security forces; harsh and at times life-threatening prison conditions; arbitrary arrest and detention; detention without charge and lengthy pretrial detention; infringement on citizens’ privacy rights, including illegal searches; allegations of abuses in connection with the continued low-level conflict in parts of the Somali region; restrictions on freedom of assembly, association, and movement; police, administrative, and judicial corruption…
Ethiopian authorities continued to severely restrict basic rights of freedom of expression, association, and assembly. Hundreds of Ethiopians in 2011 were arbitrarily arrested and detained and remain at risk of torture and ill-treatment. Attacks on political opposition and dissent persisted throughout 2011, with mass arrests of ethnic Oromo, including members of the Oromo political opposition in March, and a wider crackdown with arrests of journalists and opposition politicians from June to September 2011. The restrictive Anti-Terrorism Proclamation (adopted in 2009) has been used to justify arrests of both journalists and members of the political opposition…
Freedom House concluded:
Ethiopia is ranked Not Free in Freedom in the World 2012, with a score of 6 for both political rights and civil liberties.  Political life in Ethiopia is dominated by the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), which was led by Prime Minister Meles Zenawi from 1995 until his death in August 2012. May 2011 federal and regional elections were tightly controlled by the EPRDF; voters were threatened if they did not support the ruling party, and opposition meetings were broken up while leaders were threatened or detained.  The EPRDF routinely utilizes the country’s anti-terrorism laws to target opposition leaders and the media.  Parliament has declared much of the opposition to be terrorist groups and has targeted journalists who cover any opposition activity.  Media is dominated by state-owned broadcasters and government-oriented newspapers.  A 2009 law greatly restricts NGO activity in the country by prohibiting work in the area of human and political rights and limiting the amount of international funding any organization may receive.  This law has neutered the NGO sector in the country.  The judiciary is independent in name only, with judgments that rarely deviate from government policy.
Amnesty International urged that the “government of Ethiopia should see the succession of Meles as an opportunity to break with the past and end the practice of arresting anyone and everyone who criticizes the government.”
A group of U.N. Special Rapporteurs (an independent group of investigating experts authorized by the United Nations Human Rights Council) in 2012 issued public statements condemning the ruling regime for its indiscriminate use of the so-called anti-terrorism law to suppress a broad range of freedoms and for flagrantly perpetuating and sanctioning human rights violations.  
Maina Kiai, the U.N. Special Rapporteur on the rights to freedom of peaceful assembly and of association, concluded, “The resort to anti-terrorism legislation is one of the many obstacles faced by associations today in Ethiopia. The Government must ensure protection across all areas involving the work of associations, especially in relation to human rights issues.”
Ben Emmerson, the U.N. Special Rapporteur on counter-terrorism and human rights warned that “the anti-terrorism provisions should not be abused and need to be clearly defined in Ethiopian criminal law to ensure that they do not go counter to internationally guaranteed human rights.”
Frank La Rue, the U.N. Special Rapporteur on freedom of expression stated that “Journalists play a crucial role in promoting accountability of public officials by investigating and informing the public about human rights violations. They should not face criminal proceedings for carrying out their legitimate work, let alone be severely punished.”
Margaret Sekaggya, the U.N. Special Rapporteur on human rights defenders criticized that “journalists, bloggers and others advocating for increased respect for human rights should not be subject to pressure for the mere fact that their views are not in alignment with those of the Government [of Ethiopia].”
Gabriela Knaul, the U.N. Special Rapporteur on the independence of judges and lawyers argued that  “Defendants in a criminal process should be considered as innocent until proven guilty as enshrined in the Constitution of Ethiopia… And it is crucial that defendants have access to a lawyer during the pre-trial stage to safeguard their right to prepare their legal defence.”
On December 18, 2012, 16 members of the European Parliament issued a public letter to Prime Minister Hailemariam Desalegn “expressing grave concern over the continued detention of journalist and blogger Eskinder Nega”. In the letter, the members reminded Desalegn to comply with his “government’s obligation to respect the right to freedom of expression as established under customary international law and codified in Article 19 of the International Covenant on Civil and Political Rights, to which Ethiopia is a party.”
The Regime Must Cease and Desist All Unlawful Interference in the Exercise of Religious Freedom
Article 11 of the Ethiopian Constitution  mandates “separation of state and religion” to ensure that the “Ethiopian State is a secular state” and that “no state religion” is established. Article 27 prohibits “coercion by force or any other means, which would impair his freedom to have or to adopt a religion or belief of his choice.”
Despite clear legal obligations to respect the religious liberties of citizens, the ruling regime in Ethiopia has played fast and loose with the rights of Muslim citizens to select their own religious and spiritual leaders. According to the U.S. Commission on International Religious Freedom, an independent body constituted by the Congress and the President of the United States to monitor religious freedom worldwide:
Since July 2011, the Ethiopian government has sought to impose the al-Ahbash Islamic sect on the country’s Muslim community, a community that traditionally has practiced the Sufi form of Islam.   The government also has manipulated the election of the new leaders of the Ethiopia Islamic Affairs Supreme Council (EIASC).  Previously viewed as an independent body, EIASC is now viewed as a government-controlled institution.  The arrests, terrorism charges and takeover of EIASC signify a troubling escalation in the government’s attempts to control Ethiopia’s Muslim community and provide further evidence of a decline in religious freedom in Ethiopia. Muslims throughout Ethiopia have been arrested during peaceful protests: On October 29, the Ethiopia government charged 29 protestors with terrorism and attempting to establish an Islamic state.
The regime must conform its conduct to the requirements of its Constitution and international legal obligations and cease and desist interference in the free exercise of religion of Muslim citizens. All citizens unlawfully arrested and detained in connection with the peaceful protest of unlawful deprivation of religious liberty must be released forthwith.
All Political Prisoners Must be Released
The number of political prisoners has yet to be fully documented in Ethiopia today. While human rights organizations have focused on multiple dozens of high profile political prisoners, there are in fact tens of thousands of ordinary Ethiopians who are held in detention because of their beliefs, open opposition or refusal to support the ruling regime. All political prisoners must be released immediately.
In a broader sense, there are two types of political prisoners in Ethiopia today. There are prisoners of conscience  and prisoners-of-their-own-consciences. The prisoners of conscience are imprisoned because they are dissidents, opposition party leaders and journalists. They have done no legal or moral wrong. In fact, they have done what is morally and legally right. They have told the truth. They have spoken truth to power. They have stood up to injustice. They have defended freedom, democracy and human rights by paying the ultimate price with their lives and liberties. They can be set free by the stroke of the pen.
The prisoners-of-their-own-consciences became prisoners by committing crimes against humanity in the first degree with the lesser included offenses of the crimes of ignorance, arrogance and  petulance. These prisoners are numbed by the opiate of power. They live in fear and anxiety of being held accountable any given day. They dread the day the wrath of the people will be visited upon them. They know with certainty that they will one day be judged by the very scales they have used to judge others. 
The prisoners-in-their-own-conscience can free the prisoners of conscience and thereby free themselves. That is their only salvation. In the alternative, let them heed Gandhi’s dire warning: “There have been tyrants and murderers, and for a time they seem invincible, but in the end they always fall—think of it always.” 
Stop Repressing the Press
Napoleon Bonaparte said, “Four hostile newspapers are more to be feared than a thousand bayonets.” That rings true for the ruling regime in Ethiopia. Last week three imprisoned and one exiled Ethiopian journalists received the prestigious Hellman/Hammett Award for 2012 “in recognition of their efforts to promote free expression in Ethiopia, one of the world’s most restricted media environments”. The recipients included Eskinder Nega, an independent journalist and blogger and recipient of the 2012 PEN International freedom to Write Award;  Reeyot Alemu, one of the few Ethiopian female journalists associated with the officially shuttered weekly newspaper Feteh and recipient of the 2012 International Women’s Media Courage in Journalism Award; Woubshet Taye, editor of the officially shuttered weekly newspaper Awramba Times and Mesfin Negash of Addis Neger Online, another weekly officially shuttered before going online. The four were among a diverse group of 41 writers and journalists from 19 countries to receive the Hellman/Hammett Award.According to Human Rights Watch: 
The four jailed and exiled journalists exemplify the courage and dire situation of independent journalism in Ethiopia today. Their ordeals illustrate the price of speaking freely in a country where free speech is no longer tolerated.  The journalistic work and liberty of the four Ethiopian award-winners has been suppressed by the Ethiopian government in its efforts to restrict free speech and peaceful dissent, clamp down on independent media, and limit access to and use of the internet. They represent a much larger group of journalists in Ethiopia forced to self-censor, face prosecution, or flee the country.  
All dictators and tyrants in history have feared the enlightening powers of the independent press. Total control of the media remains the wicked obsession of all modern day dictators who believe that by controlling the flow of information, they can control the hearts and minds of their citizens.  But that is only wishful thinking. As Napoleon realized, “a journalist is a grumbler, a censurer, a giver of advice, a regent of sovereigns and a tutor of nations.” Like Napoleon, the greatest fear of the dictators in Ethiopia is the “tutoring” aspect of the press -- teaching, informing, enlightening and empowering the people with knowledge. They understand the power of the independent press to effectively countercheck their tyrannical rule and hold him accountable before the people. Like Napoleon, they have spared no effort to harass, jail, censor and muzzle journalists for criticizing and exposing their criminality, use of a vast network of spies to terrorize Ethiopian society, shining the light of truth on their military and policy failures, condemning their indiscriminate massacres of unarmed citizen protesters in the streets and for killing, jailing and persecuting their  political opponents. 
All imprisoned journalists must be released immediately.
“Those who make peaceful change impossible will make violent revolution inevitable.” JFK
Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino and is a practicing defense lawyer.

“ቅድሚያ ለእርቀ ሰላም!” (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ)




ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

የተከበራችሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን፣ በቅድሚያ ቡራኬያችሁ ይድረሰን። ቤተ ክርስቲያናችን ለሁለት
አሥርት ዓመታት በፈተና ውስጥ እንድትቆይ ያደረገውን የልዩነት ግድግዳ አፍርሶ አንድ ሲኖዶስ፣ አንድ
ፓትርያርክ፣ አንድ አስተዳደር እንዲኖራት ለማድረግ የተጀመረውን የእርቀ ሰላም ዓላማ በመደገፍ ልዑካንን
በመሰየም የጀመራችሁት ሂደት አስደስቶናል። ነገር ግን የእርቀ ሰላሙ ሂደት ሳይጠናቀቅ ወደ ፓትርያርክ ምርጫ
ጉዞ መጀመሩ በእጅጉ እንድናዝን አድርጎናል።
እንደሚታወቀው በአሁኑ ወቅት በሰንበት ት/ቤት ውስጥ የምንገኝ ወጣቶች አብዛኛው ዘመናችንን ያሳለፍነው
ቤተክርስቲያናችን በሁለት ሲኖዶስ ተከፍላ የልዩነት፣ የውግዘት እና የመራራቅ ባዕድ ሥርዓቶችን ስናስተናግድ
ነው። ይህም በሰንበት ት/ቤት ተሳትፎ ለቤተክርስቲያናችን የሚገባውን አገልግሎት እንዳንሰጥ ትልቅ መሰናክል
ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ጊዜው ደርሶ የተጀመረው የእርቀ ሰላም ሂደት ትልቅ ተስፋ ሰጥቶን ነበር። ነገር ግን
በተቃራኒው እየተከናወነ ያለው የፓትርያርክ ምርጫ ጉዞ የተቀረ ዘመናችንን በተስፋ እና በበለጠ መነሳሳት
እንዳንጓዝ እያደረገን ይገኛል።
በተለይም እኛ በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የምንገኘው የቤተክርስቲያን ልዩነት በእጅጉ
ገዝፎ በሚታይበት አኅጉር በመሆኑ የእርቀ ሰላሙ ሂደት መደናቀፍ የቤተክርስቲያናችንን ችግር ወደ ባሰ አዘቅት
ውስጥ እንደሚጨምረው ለመገመት አያዳግተንም። በእርቀ ሰላም ጉባኤያቱ ምክንያትም የተጀመረውን ወደ
አንድነት የመምጣቱን የተስፋ ጭላንጭልን አክስሞ ለሚቀጥሉት የማይታወቁ አያሌ ዘመናት የምእመናንን
አንገት የሚያስደፉ ሁኔታዎችን ሊፈጥር እንደሚችልም ግልጽ ነው።
የቤተ ክርስቲያን አንድነት ወደ ተሻለ የአገልግሎት ምዕራፍ አሸጋግሮን በልዩነት ምክንያት ያልተነኩ ዘርፈ ብዙ
ተልዕኮዎችን ለመፈጸም እየተሰናዳን ባለንበት ወቅት ከእኛ አልፎ ለልጆቻችን የምናወርሰው የመከፋፈል እና
የመለያየት ሥርዓትን በድጋሚ የምናስተናግድበት አቅም ለማግኘትም እንቸገራለን።
ስለዚህ ፍጹም በሆነ የልጅነት መንፈስ የሚከተለውን መልእክት ለማስተላለፍ እንወዳለን፦
1) የተጀመረው የእርቀ ሰላም ሂደት ሳይጠናቀቅ ወደ ፓትርያርክ ምርጫ ጉዞ በመጀመሩ በእጅጉ አዝነናል።
የቀጣይ የአገልግሎት ዘመናችንንም በተስፋ እንዳንጓዝ እንቅፋት ሆኖብናል። ስለዚህ ለተተኪ ልጆቻችሁ ስትሉ
የእርቀ ሰላሙ ሂደት እንዲጠናቀቅ እንድታደርጉ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እንጠይቃለን።
2) እንደ ቀደሙት አባቶቻችን ለቤተክርስቲያን እና ለመንጋችሁ ስትሉ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ከሆነ ተፅዕኖ
በጸዳ ሁኔታ መክራችሁ የእርቀ ሰላሙን ሂደት ለውሳኔ እንድታበቁ እንማጸናለን።
3) የተፈጠረው የአስተዳደር ልዩነት ተወግዶ ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድነት ሊያመጣ የሚችል ጥንቃቄ
የተሞላበት የመፍትሄ ውሳኔ እንድትወስኑም አደራ እንላለን።
አምላካችን እግዚአብሔር የተፈጠረውን መለያየት አስወግዶ እና የቤተ ክርስቲያን አንድነትን ወደ ቀድሞ ቦታው
መልሶ በአንድነት እንድናመሰግነው ያበቃን ዘንድ መልካም ፈቃዱ ይሁንልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።
ህዳር 13/2005 ዓ. ም
በሰሜን አሜሪካ አኅጉረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ
ሰሜን አሜሪካ
ግልባጭ:
ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
ለሰሜን አሜሪካ አኅጉረ ስብከት
ለሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት በያሉበት ፣
ለኢትዮጵያ የሰንበት ት/ቤቶች ኅብረት ፣
ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች ኅብረት ፣
በካናዳ፣ በአፍሪካና አና በአውሮፓ ለሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች ፣
ለሰላም እና አንድነት ጉባኤ፣
ለመገናኛ ብዙኃን በሙሉ።

የሚያስቅና የሚያሳቅቅ የፍርድ ቤት ውሎ



ዕለቱ “በእነ ኤልያስ ክፍሌ የፍርድ መዝገብ” ምስክርነት ይሰጣል የተባለበት ዕለት ነበር። በዚህ መዝገብ ውብሸት ታዬ፣ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር፣ ሂሩት ክፍሌ እና ርዮት አለሙ ክስ ተመስርቶባቸዋል።
እነ ውብሸት ታዬ መጀመሪያ ሲታሰሩ በቴሌቪዥን የሰማነው “የቴሌ እና የመብራት ሃይል ተቋማትን ማፈራረስ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ መሞከር” የሚል ነበር። ከዛ እያደር እያደር አቃቤ ህግ በምን እንደከሰሳቸው ረሳው መሰለኝ፤ ለምስክርነት በሄድንበት ጊዜ የሰማነው አንድም ከመብራት ሃይልና ቴሌኮሚዩኒኬሽን ጋር የሚያያዝ ነገር አልነበረውም። አረ ልብ ብለን ካየነውማ ከህገ መንግስቱም ጋር የሚጋጭ ነገር አላየንበትም።  
ለማንኛውም፤ በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና በአቶ ዘሪሁን ላይ ለምስክርነት የቀረቡ ሶስት ልጆች ነበሩ። ሶስቱም  የምንመሰክረው እውነት ካልሆነ አቡነ ገሪማ ይገልብጡን ብለው ማህላ ፈፀሙ።
በነገራችን ላይ አቡነ ገሪማ አድዋ ውስጥ የሚገኙ ቁጡ ፃድቅ ናቸው። ከየት ትዝ አሉኝ…? ሌላ ጊዜ እርሳቸውን የሚመለከት ጨዋታ ይኖረን ይሆናል… እድሜ እና ማሳታወሱን ከሰጠን!
ወደ ማስታወሻችን ስንመለስ፤ መስካሪዎቹ ከአድዋው አቡነ ገሪማ ይልቅ የአድዋውን መለስ የሚፈሩ እና የሚያከብሩ መሆናቸው ያስታውቅባቸዋል። እንዴት ማለት ጥሩ ጥያቄ ነው… ይከተሉኝማ፤
የመጀመሪያው መስካሪ መጣ፤ የመኖሪያ አድራሻውን ሲጠየቅ የጎዳና ተዳዳሪ ነኝ አለ። ወዘናው ግን አይመስልም። እሺ ይሁንለት… ቀጥል ተባለ…
“ቦና ታከለ ከተባለ የቡቲክ አስተናጋጅ ጋር ሆነን ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ “በቃ!” የሚል ፅሁፍ ፅፈናል አለ።
ሁለተኛው መስካሪ መጣ የመኖሪያ አድራሻ ተጠየቀ። ድንቡሽቡሽ ያለው ልጅ ሞልቀቅ ብሎ፤ “ቦሌ” ይላል ብለን ስንጠብቅ ምስኪን ለመምሰል እየሞከረ የጎዳና ተዳዳሪ ነኝ አለን። ይሄኔ እውነቱን ንገረኝ ካሉኝ የጎዳና ተዳዳሪ መሆን ተመኘሁ። የጎዳና ተዳዳሪነት እንዲህ የሚያሳምር ከሆነ ከቤታችን ውስጥ ምን እየሰራን ነው? ስል ራሴን ጠየኩ። ለማንኛውም ምስክርነቱን እንስማ፤
“ቦና ታከለ ከሚባል ሊስትሮ ሰራተኛ ጋር በመሆን “በቃ” የሚል ፅሁፍ ፅፈናል” አለ። ቆይ ቆይ ቆይ የመጀመሪያው ልጅ የቦና ታከለን ስራ ምን ነበር ያለው…? ማስታወሻዬን ገለጥ ገለጥ ሳደርጋት “የቡቲክ አስተናጋጅ” ይላል። ይሄኛው ደግሞ በአንድ ጊዜ ሊስትሮ አደረገው። “እሺ… ስንት ሰዓት ላይ ነበር የፃፋችሁት?” “ከሌሊቱ አስራ አንድ ሰዓት።” ልብ አድርጉልኝ የመጀመሪየው መስካሪ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ነበር ያለው። ገድ ፈላ…
ቀጥሎ ቦና ታከለ ራሱ መጣ። እሰይ አሁን እውነቱን ከዋናው ሰው ልንሰማ ነው። ቦና ለመሆኑ ስራህ ምንድነው?፡”ሶፍት ነጋዴ ነኝ!” (ያዝ ቀበሌ ይላሉ የኛ ሰፈር ልጆች የማይሆን ነገር ሲሰሙ።) የቦና ታከለን ስራ አንደኛው ጓደኛው የቡቲክ አስተናጋጅ ሲለው ሲለው ሌላኛው ደግሞ ሊስትሮ አለው። ራሱ ሲመጣ “ሶፍት ነጋዴ ነኝ” አለን። እነዚህ ጓደኛማቾች ሳይሆኑ ጉደኛማቾች ናቸው! እያልኩ በሆዴ እያንሰላሰልኩ ምስክርነቱን መስማት ቀጠልኩ…
አቶ ዘሪሁን ባዘዘኝ መሰረት “በቃ” የሚል ፅሁፍ በየአደባባዩ ፅፈናል። ይሄኔ ዳኛው የጠየቁት ነው የማይረሳኝ “ምንድነው የበቃው…?” አሉት። ልጁ ፈራ… ትንሽ ቁልጭ ቁልጭ አለ። ደግመው ጠየቁት “ምንድነው የበቃው?” “መ… መለስ በቃ” ይሄኔ በፍርድ ቤቱ ውስጥ የታፈኑ ሳቆች ከዚህም ከዛም ሹልክ ሹልክ እያሉተሰሙ። ዳኛው ቆጣ ብለው ስነ ስርዓት! አሉ እና ቦና ቀጠለ…
ስንት ሰዓት ነበር የምትፅፉት? ሲባል ምን አለ መሰልዎ…? “ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ” አለ። ግራ ተጋባን እንዲህ ያለ ሃራምባ እና ቆቦ፣ ባሌ እና ቦሌ ጉለሌ እና ሰላሌ… አረ እንደውም እነዚህ ይቀራረባሉ እንደነ ቦታ ታከለ አይነት የተራራቀ ምስክርነት ሰምቼ አላውቅም። ለዛውም መፅሐፍ ተይዞ ተምሎ ይገልብጠኝ ተብሎ የተገለባበጠ ምስክርነት… ብዙዎቻችን “ምንድነው ጉዱ” በሚል ርስ በርስ እየተያየን ቀጠልን!
ሂሩት ክፍሌ ላይ ምስክር ሊሆን የቀረበው አንድ ወጣት ነበር። በነገራችን ላይ ሂሩት ክፍሌ በጣም የሚገርም አይነት የእስር እድል ነው ያላት። መንግስት ደንገጥ ባለ ቁጥር ዘሎ ነው የሚያስራት። ለምሳሌ በቅንጅት ጊዜ ታስራለች። ከዛም ቀጥሎ ደግሞ፤ “ከአርበኞች ግንባር ጋር አብራችኋል” ተብለው ወደ አርባ የሚጠጉ ሰዎች ሲታሰሩ ታስራለች። አሁንም ደግሞ አሸበርሽ ተብላ ነው የታሰረችው። በአንድ ወቅት በቃሊቲ እስር ቤት ሄጄ ስጠይቃት እንደውም “መጣ የተባለ ፋሽን አያልፋትም” እንደሚባሉ ፋሽነኛ ሴቶች፤ አንቺ ደግሞ መጣ የተባለ እስር አያልፍሽም ማለት ነዋ…? ብዬ ልቀልድ ሙከራ አድርጌያለሁ።
በሂሩት ላይ ምስክርነት የቀረበው ወጣት “መካኒክ ነኝ” አለን። እሺ እስቲ ቀጥል መካኒኩ፤ ሂሩት ክፍሌን የማውቃት በ97 ዓ.ም አብረን ታስረን በነበረ ጊዜ ነው። አለ። ወንድ እና ሴት አስር ቤት የመተዋወቅ እድላቸው ምን ያህል ጠባብ እንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል።
እንኳን ሌላ ቀርቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት ውስጥ የተወለደ የገዛ ልጁንም ሆነ ባለቤቱን ማየት ባለመቻሉ ነበር የልጁን ስም “ናፍቆት” ያለው።   
ለማንኛውም “ምስክሩ” ቀጠለ። “እርሷ ባለችኝ መሰረት ሃዋሳ ከተማ ሄጄ አመፅ የሚቀሰቅስ ወረቀት ለጥፊያለሁ” አለ። ለዚህም ገንዘብ ተቀብያለሁ። ሲል ጨመረልን። ገንዘቡ የምንድነው? ቢባል… “የእኔ ክፍያ እና ለቀለም መቅዣ ነበር” አለን።  ጥሩ… ከዛስ…? “ከዛ…” አለና ትንሽ አሰብ አድርጎ… “ከዛ… እኔ በዘጠና ሰባትም ዓመተ ምህረትም በዚሁ ጉዳይ ታስሬ ስለነበር፡ ከዚህ በኋላ እንዲህ ያለ ወንጀል መስራት ስላልፈለኩ ለፖሊስ ጠቆምኩ” ብሎን እርፍ…!
አረ በህግ አምላክ መካኒኩ… ሀዋሳ ሄጄ ወረቀት ለጥፊያለሁ ብለሃልኮ… ብዬ ጮኬ ልናገር ምንም አልቀረኝም።   
ምስክርነቱ ቀጥሏል። በርዮት አለሙ ላይ የቀረበችው ምስክር የርዮት ጓደኛ ነበረች። እሺ እንዴት መጣሽ…? ተባለች። “ፖሊስ አስገድዶኝ!” በሆዳችን አይዞሽ አልናት። ግና ፖሊስ አስገዳጆችን ይከላከል እንጂ ያስገድድ ዘንድ ደግ ነውን…? ይህንንም በሆዳችን የጠየቅነው ነው…!
“ምንድነው የምትመሰክሪው?”
“ለርዮት ካሜራ አውሻት አውቃለሁ እና እርሱን ትመሰክሪያለሽ ተብዬ ነው የመጣሁት” እሺ ቀጥዬ… “ጓደኛዬ ስለሆነች ካሜራም ሆነ ሆነ እስክርቢቶ እንዋዋሳለን፤ ካሜራው እርሷ ስትፈልግ እርሷ ጋር እኔ ስፈልግ ደግሞ እኔ ጋር ይሆናል” አለች። ከዛም በቃ ይህንኑ እንድትናገር ነው የመጣችውና ጨረሰች።
ታድያ ይሄ ወንጀሉ ምንድነው? ካሜራ የተዋዋስን በሙሉ ልንታሰር ነው ማለት ነው? ግራ የሚያጋባ ምስክርነት ነበር። ቴሌን መብራት ሃይል እና ህገመንግስቱ የሚናዱት በፎቶ ካሜራ ነው? እንኳን ሌላው ቀርቶ “በቃ” የሚል የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት ቴሌን እንዴት የወድመዋል? መብራት ሃይልንስ እንደምን ያፈርሰዋል? (ስንል ጠይቀን መልስ ስናጣ ራሳችን በሳቅ ፈረስን!)
እዝችጋ አንድ የዘጠና ሰባት ቀልድ ትምጣ…
ያኔ አሉ ሁለት ፖሊሶች አብረው እየሄዱ ነበር። በወቅቱ፤ አብዛኛዎቹ፤ የአዲሳባ ከተማ ፖሊሶች በመንግስት አመኔታን አጥተው ታማኝ ካድሬ የሆኑ ፖሊሶች ብቻ ከፌደራል ፖሊስ ጋር እየተጣመሩ ነበር ጥበቃ የሚያደርጉት። ታድያ አንድ ካድሬ ፖሊስ እና አንድ ፌደራል ፖሊስ አብረው እየሄዱ ሳለ፤ የፌደራል ፖሊሱ አንድ ጥያቄ ካድሬ ቀመሱን ፖሊስ ይጠይቀዋል።፡
“ባለፈው ወጣቶቹ አውቶብስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ የነበረው ለምንድነው?” ብሎ ጠየቀ። ካድሬ ብጤውም “ያው ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ ነዋ!” አለው በርሱ ቤት ጨዋታ ማሳመሩ ነው። ይሄኔ ፌደራሉ ትንሽ አሰብ አደረገና እንግዲያስ መንግስት ነው ጥፋተኛ…! አለ። ካድሬው የአዲሳባ ፖሊስ ደንገጥ ብሎ እንዴት…? ቢለው ግዜ “ህገመንግስቱን ለምን በአውቶብስ ይዞት ይዞራል…?” ብሎ ጠየቀው አሉ።
እናላችሁ ወዳጆቼ… በአሁኑ ሰዓት በነገርኳችሁ አይነት የተጣረሱ የሚያስቅና የሚያሳቅቅ የፍርድ ቤት ምስክርነቶች ሁሉም ተከሳሾች ከአስራ አራት አመት በላይ ተፈርዶባቸዋል። ርዮት አለሙ ብቻ ይግባኝ ጠይቃ ወደ አምስት አመት ዝቅ ተደርጎላታል።
እውነቱን ለመናገር መንግስታችን ጣጣ የለውም “አንጥሴ” የሚሉትን ራሱ ህገመንግስቱን እና ተቋማትን በሀይል ለመናድ እንደማሴር አድርጎ ሊያስመሰክርብዎ ይችላል። ግን ማስነጠሳችንን አንተውም! (ሃሃ..ተቀኘን ማለት ነው!?)    

የባህርዳር ሹማምንት በከፍተኛ ሙስና ተዘፍቀዋል ተባለ


ኢሳት ዜና:-ለአቶ በረከት ስምኦን የተጻፈ ሚስጢራዊ ደብዳቤ እንዳመለከተው በባህርዳር ከተማ ከንቲባ በአቶ ፋንታ ደጀን አማካኝነት በርካታ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ናቸው።
ደብዳቤው በብአዴን ውስጥ ሁለት በጥቅም የተሳሰሩ ቡድኖች መፈጠራቸውን ያመለክታል። አንደኛው ቡድን ደጀኔ ሽባባው በተባለው የብአዴን ጽሀፈት ቤት ሀላፊ የሚመራ ሲሆን በዚህ ቡድን ውስጥ የገቢዎች ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆነው ክብረት ሙሀመድ፣ የከተማ አግልገሎት የቴክኒክ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅር መኮንን፣ የቤቶች ልማት ስራአስኪያጅ አቶ ክንድይሁን እገዘው፣ የንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መንግስቴ አምሳሉ እና የጥቃቅን ምክትል ሀላፊ አቶ ሙላቱ ጸጋየ ይገኙበታል።
አቶ ስማቸው ወንድማገኘሁ በተባለው ሰው በሚመራው ቡድን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ቢያድግልኝ አድምጠው፣ የጥቃቅን ጽህፈት ቤት ሃለፊ አቶ ንበረት ታፈረ፣ የገንዘብ ጽ/ቤት ሃለፊ አቶ ፍትሀነገስት በዛብህ፣ የከተማ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሲል ሙሉ፣ የትምህርት ጽ/ቤት ሃለፊ አቶ ሙሉቀን አየሁ፣ የፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ነጋ ተመስገን፣ የከንቲባ ጽ/ቤት ሃለፊ አቶ አላዩ መኮንን፣ የጤና ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ወርቅነህ ማሞ፣ የትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ሃለፊውን አቶ ሙለጌታ ካሳ እና የከተማዋ ም/ቤት ም/ል አፈ ጉባኤዋ ወ/ሮ አበባ ካህሊው ይገኙበታል።

ሁለቱ ቡድኖች የዘጌና የደቡብ ጎንደር በሚል የሚታወቁ ሲሆን በቡድኖቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ የጥቅም ትስስር መኖሩ ተገልጿል።በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው በ2004 በተደረገው ግምገማ አቶ ሰማቸው ወንድማገኘው ያለአግባብ በተለያዩ እህቶቹና ወንድሞቹ ስም  ሁለት ኮንዲሚኒየም ቤቶችን መግዛቱ ፣   ሁለት ቪላ ቤቶች መስራቱ ፣  በደብረታቦር ከተማ ውስጥ በራሱ ስም አንድ ቤት እያለው በተሳሳተ መረጃ  200 ካ.ሜ ቦታ መውሰዱ፣ በባህርዳር ከተማ 200 ካ.ሜ ቦታ ወስዶ በት መስራቱ ተጠቅሷል።ፀረ ሙስና ኮሚሽን በግለሰቡ ላይ ምርመራ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በከንቲባው በአቶ ፋንታ ደጀን ጫና ምርመራውና ክትትሉ እንዲቆም መደረጉ ተጠቅሷል።  መረጃውን ያጋለጡ ግለሰቦችም አደገኛ በሆነ መንገድ ክትትል እየተደረገባቸው ከመሆኑም ባሻገር በግልፅ እረፉ አየተባሉ የማሳደድ ስራ እየተሰራባቸው እንደሚገኝ ተመልክቷል።

አቶ ፋንታና አቶ ስማቸው በከተማው  ውስጥ የዝርፊያና የአፈና የአመራር ቡድን እንዳደራጁ የተጠቀሰ ሲሆን ፣ ከከተማው አመራር በስተጀርባ ሆነው የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ፣ የዲፕሎማሲ ስራ የሚሰሩና የበላይ ጠባቂ  ሆነው ቡድኑን የሚያጠናክሩ ነጋዴዎች፣ የክልል አመራሮች እና ስራቸውን የረሱ የሚመስሉ የፌዴራል ደኅንነቶች እንዳሉበት ደብዳቤው ይጠቅሳል።
በብአዴን አባላት የተጻፈው ደብዳቤ በመጨረሻም “በክልሉ የሚታየው አካሄድ  ስርዓቱንም ሆነ ህዝቡን እየጎዳ ያለና የሰማዕታትንም ደም ከንቱ የሚያስቀር በመሆኑ . ፍትህ የጠፋበትንና ዝርፊያ የተበራከተበትን ከተማ ለህዝባችን ነፃነትና ጥቅም መከበር ሲሉ በተሰውት አእላፋት ጓዶቻችንና ከሁሉም በላይ በቅርብ ቀን ባጣነው ባለራዕይውና ቁርጠኛ ክቡር መሪያችን ስም ችግሩን በመፈተሽ ነፃ እንደምታወጡትና የህዝባችንንም ጩኸት እንደምትመልሱት ተስፋ በማድረግ ነው” በማለት ገልጿል።
ሚስጥራዊ ደብዳቤውን ሙሉ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ21-12-2012 ሚስጢራዊ ደብዳቤ

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ነገ ድምፃቸውን ያሰማሉ


ኢሳት ዜና:-<<ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት እርቅና ሰላም ይቅደም>>በሚል መሪ ሀሳብ የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በመጪው እሁድ ከቅዳሴ በሁዋላ የተቃውሞ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ ቀረበ።
ደጀ ሰላም እንደዘገበው ላለፉት 20 ዓመታት በውግዘት የተለያዩ አባቶች አንድ እንዲሆኑ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ አስተዳደርና አንድ ቅ/ሲኖዶስ እንዲኖር ለማድረግ ሲካሄድ የሰነበተው የእርቀ-ሰላም ሂደት በመልካም ውጤት ሊጠናቀቅ ጫፍ ላይ በደረሰበት ጊዜ፤ የታየውን የተስፋ ጭላንጭል በሚያዳፍን መልኩ በጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ግፊት 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም “አስመራጭ ኮሚቴ” ተቋቁሟል።
“የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል” የሚሉ ምእመናን በሙሉ ውሳኔውን በጽኑዕ በመቃወም ላይ ይገኛሉ>> ያለው ድረ-ገጹ፤ይህንን “ከኮምፒውተር ጀርባ” እና በስልክ የሚደረግ የኢንተርኔት ተቃውሞን መልክ ለመስጠት፤ በመጪው እሑድ፣ ቅዳሴ ካለቀ በኋላ በየአጥቢያችን በመሰባሰብ  ሐዘናችንንና መከፋታችንን እንዲሁም በውሳኔው ማዘናችንን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለመግለጽ መሰባሰብ ይኖርብናል>>ብሏል።
<<ሰንበት ት/ቤቶች፣ ማኅበራት፣ ሰንበቴዎች እና ምእመናን በሙሉ ከሚያውቋቸው ሰዎች በመጀመር ለእሑዱ ቀጠሮ መያዝ እና የመሰባሰቡን ሁናቴ መልክ መስጠት መጀመር ይኖርባቸዋል>>ያለው ደጀ ሰላም፤ << ዓላማችን አንድ ነው። እርሱም <<ስብስባችንን የሚጠሉ ሰዎች በፖለቲካ በማሳበብ በመንግሥት ዱላ ለማስደብደብ የሚያደርጉት ሙከራ እንደሚኖር ስለምናውቅ ከወዲሁ ለሚመለከተው ሁሉ ዓላማችንን መግለጽ እንፈልጋለን። መነጋገር የምንፈልገው ከቅ/ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አባቶች ጋር ነው።>> ብሏል።
<<ባልመረጥነው መጂሊስ አንተዳደርም፣ መንግስት የማንቀበለውን የ አህባሽ አስተምህሮ በሀይል አይጫንብን!>> በማለት  እጅግ በርካታ የ እስልምና እምነት ተከታዮች ያነሱት ተቃውሞ መፍትሔ ሳያገኝ  አንደኛ ዓመቱን እያስቆጠረ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ከፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ  መንግስት  በቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥም ጣልቃ መግባቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮችን ለተመሣሳይ ተቃውሞ እንዳይጋብዛቸው ተፈርቷል።
በስደት የሚገኙት አራተኛው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከነ ሙሉ ስልጣናቸውና ክብራቸው ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ በፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ አማካይነት ደብዳቤ ከተፃፈ በሁዋላ፤ ውሳኔው እንደገና እንዲቀለበስ መደረጉና መንግስት አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ሆነው እንዲመጡ ፍላጎት የለውም መባሉ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ በ ኢዮሩሳሌም የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ የሆኑትን አቡነ ማትያስን ለማስሾም እየተንቀሳቀሰ  እንደሆነ በተለያዩ ብዙሀን መገናኛዎች ተዘግቧል።
በዚህም ሳቢያ ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድ ለማምጣት የተጀመረውናታላቅ ተስፋ የታየበት የእርቀ-ሰላም  ጥረት እየተደናቀፈ ነው መባሉ ብዙዎችን የቤተክርስቲያኒቷን ምዕመናን እጅግ ያሳዘነ ሆኗል።
<<ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት እርቀ-ሰላም ይቅደም >>በሚል መሪ ሀሳብ እሁድ ከቅደሴ በሁዋላ ለሚደረገው ተቃውሞ በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ጥሪዎች እየተላለፉ ነው።

Total Pageviews

Translate