Pages

Jan 18, 2013

የኢትዮጵያ አየር መንግድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን አገልግሎት እንዲያቆም አዘዘ


የኢትዮጵያ አየር መንግድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን አገልግሎት እንዲያቆም አዘዘ

ኢሳት ዜና:- እንደ ቢቢሲ ዘገባ በቴክኒክ ችግር ምክንያት  አዲሱ ቦይንግ ድሪምላይነር ለጊዜው  አገልግሎት እንዳይሸጥ በአሜሪካ አቪየሺን ባለስልጣን ታግዷል።ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

በመላው ዓለም ላይ 50 የሚሆኑ ቦይንግ ድሪም ላይነር እንዳሉ ያመለከተው የዜና አውታሩ ዘገባ፤የቴክኒክ ፍተሻ እስኪደረግ ድረስ የሁሉም አገራት ቦይንግ ድሪምላይነር ፍላግሺፖች አገልግሎታቸውን እንዲያቆሙ የዩ.ኤስ ፌዴራል አቪየሺን አሳስቧል።

አዲሱ ድሪም ላይነር ነዳጅ የመትፋት፣ የኮክ ፒት መስኮት መሰንጠቅ፣ የፍሬን እና የኤሌክትሪክ ብልጭታ የመፍጠርችግር እንደተስተዋለበትም ተገልጿል።

የአውሮፕላኑ <<ሊትየም አዮን ባትሪ>> የፍተሻው ዋነኛ ትኩረት መሆኑም ተመልክቷል።
ትናትን ረቡዕ በጃፓን  ቦይንግ ድሪም ላይነር ላይ የባትሪ ችግር አጋጥሞ አውሮፕላኑ ባስቸኳይ እንዲያርፍ መደረጉን <<ኦል ኒፖን ኤር ዎይስ>>የተሰኘው የጃፓን አየር መንገድ ሪፖርት አድርጓል።
በዓለም ላይ ቦይንግ ድሪም ላይነርን የሚጠቀሙ ስምንቱም አየር መንገዶች በዩ.ኤስ አቪየሺን ማሰሰቢያ መሰረት አገልግሎቱን ማቆማቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
እነሱም የጃፓን፣የአሜሪካ፣የቺሊ፣ የህንድ፣የኩዋታር፣የፖላንድና የኢትዮጵያ አየር መንገዶች ናቸው።
በብድር 10 ቦይንግ ድሪም ላይነር የገዛችው ኢትዮጵያ፤ ከአፍሪካ ብቸኛዋ የድሪም ላይነር ባለቤት ነች።
አውሮፕላኖቹ አዲስ አበባ ሲገቡ ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸው እንደነበር ይታወሳል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ  የጃፓን ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ላይ ያጋጠመው የቴክኒክ ችግር በኢትዮጵያዎቹ ላይ አውሮፕላኖች ላይ አለመከሰቱን ገልጾ፣ ለጥንቃቄና ለደህንነት ሲባል ላልተወሰነ ጊዜ በረራ ማቋረጡን ዘግይቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ ህዝብን እያነጋገረ ነው


በኢትዮጵያ የሚገኘው ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ ህዝብን እያነጋገረ ነው

ኢሳት ዜና:-የኢሳት አዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጠው አዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ የሆኑትን ምእመናንን እያነጋገረ ነው።ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ሲኖዶሱ ትናንት ባወጣው መግለጫ በውጭ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር ሲደረግ የነበረው የእርቅ ድርድር ያለውጤት በመጠናቀቁ 6ኛ ፓትሪያሪክ ለማሾም መወሰኑን አስታውቋል።

መግለጫው 4ኛው ፓትሪያርክ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ክብራቸውና ደረጃቸው ተጠብቆ በጸሎት ተወስነው እንዲኖሩ ቢሞከረም እንዲሁም ውግዘት ባስከተለው ሹመት የተሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት ሲኖዶሱን ተቀላቅለው በተመደቡበት ቦታ ሆነው እንዲሰሩ ጥረት ቢደረግም አልተሳካም ብሎአል።

4ኛው ፓትሪያርክ በሙሉ የፓትሪያርክ ስልጣን ቤተክርስቲያን መምራት ያለባቸው እሳቸው ናቸው በማለት በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ አቋም በመያዙ ሽምግልናው ሊሳካ እንዳልቻለ ገልጾ፣ 4ኛውን ፓትሪያርክ ወደ ሀላፊነት መመለስ 20 አመት ሙሉ የተሰራውን ስራ መዘንጋት በመሆኑ አቓም ሊቀበል አለመቻሉን ገልጿል።

መግለጫው በመጨረሻም ከእንግዲህ ቤተክርስቲያኒቱን ያለመሪ ማቆየት ለተጨማሪ ክፍተት የሚዳርግ በመሆኑም የ6ኛው ፓትሪያርክ ምርጫ ሂደት በአስመራጭ ኮሚቴው በኩል እንዲቀጥል ውስኗል።

የአዲስ አበባው ሲኖዶስ መግለጫውን ካወጣው በሁዋላ ምእመናንና ሀይማኖት ሀባቶች የተለያዩ አስተያየቶችን እያቀረቡ ነው።

ወልደ አረጋይ የተባሉ ጸሀፊ ” አንድ ክርስቶስ! አንድ ሲኖዶስ! አንድ መንጋ! በሚል ርእስ በደጀ ሰላም ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ  ”አባቶቻችን ፈረዱብን! እንዲያ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ያስተጋባውን የመንጋው የተማኅጽኖ ጥሪ አልገደዳቸውም ነበር እና “ቅድሚያ ለምርጫ” ማለትን ወደዱ፡፡ እጅግ መራራ ነው፡፡ ይህን መስማትም ሆነ ማሰብ እጅግ ይመራል፡፡ በመለያየት ውስጥም መኖር ከሁሉም በላይ አብዝቶ ይመራል፡፡አባቶቻችን ግን በእኛ በክርስቶስ የአደራ ልጆቻቸው በምንሆን ላይ እጅግ አብዝቶ በሚመረው “የመለያየት ክርስትና” ውስጥ እንድንኖር ዛሬ በድጋሚ ፈረዱብን፡፡ አባቶቻችን አንድ እንዳንሆን በድጋሚ ፈረዱብን!” ብሎአል።

ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑትና በ1983 ዓም በጎንደር አደባባይ እየሱስ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ በርካታ ሰዎች ማለቃቸውን ተከትሎ ህዝቡን ለአመጽ አነሳስተዋል ተብለው ለ 12 ዓመታት በእስር የቆዩት አባ አመሀ እየሱስ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለምልልስ ፣ በአዲስ አበባ ያለው እርቅ ያልተሳካው የሀይማኖት አባቶቹ የመንግስት ቅጥረኞች በመሆናቸው ነው፣ ብለዋል።

ሲኖዶሱ እርቁን ካፈረሰባቸው ምክንያቶች አንዱ ” ባለፉት 20 አመታት በአቡነ ጳውሎስ ዘመን የተሰራው ን ታሪክ ላለመዘንጋት ነው” የሚል መሆኑን ገልጿል፣ እርስዎ ይህን ምክንያት እንዴት ያዩታል ለተባሉት አባ አምሀ እየሱስ “ታሪክ የሚበላሸው በዚህ ሲቀጥሉ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል።

በአዲስ አበባ ግቢ ገብርኤል በሚካሄዱ ጉባኤዎች ላይ መምህር የሆነው ዳንኤል ሞገስ በበኩሉ ሲኖዶሱ ያወጣው መግለጫ አሳዛኝ መሆኑንና እረቁ መቅደም እንደነበረት ገልጿል።

ዳንኤል ሞገስ ከጸሎት በተጨማሪ በአባቶች ላይ ጫና በመፍጠር የእርቁ ጉዳይ ተመልሶ እንዲጀመር መደረግ አለበት በማለት አስተያየቱን ገልጿል።

ወለደ አረጋይ የተባሉ ጸሀፊም በበኩላቸው ” በዚህ የሰላም ኮሚቴ አማካኝነት እዚህ በስደት ያለው ምዕመን የአንድነትና የሰላም መንፈስ ወ  ደ አገር ቤት የሚደርስበትንና እዛም ያለው ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና ለአንድነቱ ተግቶ የሚታገልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል፡፡” በማለት መወሰድ ስላለበት እርምጃ ገልጿል።

Jan 17, 2013

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል


ዛፍ በፍሬው ይታወቃል

በዳዊት መላኩ (ጀርመን)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያስተላለፈው ውሳኔ ሀገራችንና ህዝባችን ምን ያክል አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደገቡ ያሳያል፡፡ሲኖዶሱ በመንፈስ ቅዱስ ይመራል ቢባልም አንዴ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም፤ አንዴ አቶ አባይ ጸሀዮ ፤ሲያስፈልግም አቦይ ስብሃት እና አቶ በረከት ስምኦን እየተፈራረቁ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የጥፋት በትራቸውን እያሳረፉበት ይገኛሉ፡፡እንግዲህ የመንግስት ሰዎች በዚህ መልኩ እየተፈራረቁ ተጽዕኖቸውን ሲያሳርፉ በውስጡ የተሰገሰጉት የወያኔ ወኪል አባቶች ደግሞ ህዝቡ ተደራጅቶ መብቱን እንዳያስከብር ጊዜ ለማግኘትና ውስጥ ውስጡን ለሰላም የቆሙ በመምሰል በሽምግልና እና በጸሎት አማካይነት ይስተካከላል እያሉ ሲያታልሉ ቢቆዩም ዛሬ የመንግስትን አቋም ለማስፈጽም መቆማቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡
የመግለጫው ይዘት ስናየው ለማደናገሪያ ያክል በውስጡ አንዳንድ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችና የግዕዝ ቃላቶች ከመግባታቸው በስተቀር ወያኔ በየሦስት ወሩ እያሳተመ ለአባላቶቹ ከሚያሰራጨው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ውዳሴ መጽሔት ከሆነችው የአዲስ ራዕይ መጽሔት፤ በበረከት ሰምኦን በኩል ከሚለቀቀው የመንግስትን አቋም የሚተነትን ተብሎ በመሰለ ገብረህይወት እየተነበበ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከሚቀርበው ፕሮፖጋንዳ የተለየ አደለም፡፡ከዚህ መገመት የሚቻለው መንግስት አስቀድሞ ተዘጋጅቶበት መግለጫው በሲኖዶስ እንዲነበብ መደረጉን ነው፡፡ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ በ1984 ዓ.ም በአቶ ታምራት ላይኔ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ መባረራቸው ያደባባይ ሚስጢር ሁኖ ሳለ ዛሬም በተለመደው ቅጥፈታቸው በገንዛ ፈቃዳቸው ጥለው ሸሽተዋል፣ስልጣኑን ለፈለጋችሁት ስጡት ብለዋል ተብሎ የተጻፈን ጽሁፍ የሲኖዶስ ውሳኔ ነው ብሎ ማውጣት ምን ያክል አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡ጳጳሱ ወታደር ያላቸው ይመስል የቅድስተ- ማሪያምን ቤተክርስቲይን በታንክና በመትረጌስ አስከብበው የተወሰኑ ካድሬ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ተብየዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያዘጋጁ ተደርጎ በተቀነባበረ ሴራ እንደተባረሩ እየታወቀ በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ ሲባል በተለይ አለም በቃን ካሉ መነኮሳት መስማት ምን ያክል አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡
ማቴ.7፤16-20 ” ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ አያፈራም፡፡እንዲሁም መጥፎ ዛፍ ጥሩ ፍሬ አያፈራም፡፡ዛፍ ሁሉ በፍሬው ያታወቃል፡፡” ባለፉት 38 ዓመታት ወያኔ ያፈራቸው የክህደት ፍሬዎች እንዳይናቸው ብሌን እንዲንከባከቡ ከእግዚያብሄር የተረከቡዋቸውን የመንፈስ ልጆቻቸውን በመበተን ይህን አሳፋሪ ተግባር አሜን ብለው ተቀብለዋል፡፡ዛሬም ቢመሽም ቅሉ ፈጽሞ አልጨለመምና በተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያ ምክንያት ያላመናችሁበትን የፈጸማችሁ አባቶች የእግዚያብሔርን ቃል አስታውሱ፡፡ከቤተ-ክርስቲያንና ከምእምናን ጎን በመሰለፍ የእስልምና እምነት ተከታይ የሀይማኖት መሪዎች እንዳደረጉት እንንተም ለእምነታችሁ መከበርና ለቤተክርሰቲያናችሁ አንድነት ነገቢውን ዋግ ክፈሉ፡፡
ማቴ.10፤26-28 “ እንግዲህ ሰዎችን አትፍሩ፤ምክንያቱም የተሸፈን መገለጡ አይቀርም፤ተሰወረም መታወቁ አይቀርም፤በሹክሹክታ የሰማችሁትንም በከፍታ ቦታ ላይ በይፋ አስተምሩ፡፡ለእናንተ ለወዳጆቼ እንዲህ እላችኋለሁ፤ስጋን ከመግደል አልፈው ነፍስን መግደል የማይችሉትን ሰዎች አትፍሩ፤ ይልቁን ነፍስን እና ስጋን በገሀነም ሊያጠፋ ሚችለውን እግዚያብሄርን ፍሩ፡፡” ይላል የእግዚያብሄር ቃል፡፡
ሉቃ.13፤6-7 “አንድ ሰው በአትክልቱ ውስጥ የተተከለች አንዲት የበለስ ዛፍ ነበረችው፡፡ከዚያችም የበለስ ዛፍ ፍሬ አገኛለፉ ብሎ በተለያዩ ጊዜያት እየሄደ ቢሞክርም ምንም ፍሬ ሳያገኝ ቀረ፡፡ስለዚህ አትክልተኛውን ጠርቶ ከዚች ዛፍ ፍሬ ለማግኘት ሦስት አመት ሙሉ ተመላለስኩ፤ ግን ምንም ፍሬ አላገኘሁባትም፤አሁን ቁረጣት ስለምን የአትክልቱን ቦታ በከንቱ ይዛ ታበላሻለች አለው”፡፡ እንግዲህ ከዚህ ምሳሌ መረዳት ሚቻለው ባለፉት 21 አመታት ፍሬ ያልሰጡትን አቡነ ጳውሎስን እና አቶ መለስ ዜናዊን የአትክልቱ ቦታ ባለቤት በቁጣ ቢነቅላቸውም ከትፋጣቸው መማር የማይችሉት ደቀ- መዛሙርቶቻቸው እነ አቶ አባይ ጸሀዬ እና አቦይ ስብሀት አንዲሁም ሌሎች የወያኔ ቡችሎች በጥፋታቸው ቀጥለውበታል፡፡ይባስ ብሎ በእነሱ ግፍና መከራ በስደት ኑሮዋቸውን መግፋት ሳያናሳቸው ሽብርተኛ በመሆናቸው አቡነ መርቆሪወስ ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ሲሉ “አቫይ ጸሀዬ” ነግረውናል፡፡ወያኔዎች መልካም ፍሬ ለማፈራት የማይችሉ ተሰጣቸውን ሀገርን የማስተዳደር ትልቅ ሀላፊነት በተጠናወታቸው የዘር ልክፍት ምክንያት ህዝቡን ለብጥብጥ፣ ለሞት፣ለችግር እና ለስደት ከመዳረግ በቀር ሌላ ነገር የለም፡፡ውድ ኢትዮጵያውያን የእግዚያብሄርም ቃል የሚነግረን ፍሬ የማያፈሩትን ዛፎች ቆርጦ መጣል እንደሚገባ ነው፡፡የሌሌች ሀገሮችም ተሞክሮ የሚያሳየን ያለ ሀይል አልለቅም ብሎ በግድ የተጣበቀብንን ካናሰር በኃይል ቆርጦ መጣልና ነጻነታችንን ማስመለስ ነው፡፡

ጀርመን፣ ፍራንክፈርት አውሮፕላን ማረፊያ፣ መነገር ያለበት (ቁጥር አራት)


ጀርመን፣ ፍራንክፈርት አውሮፕላን ማረፊያ፣ መነገር ያለበት (ቁጥር አራት)

ከበልጅግ ዓሊ
Beljig.ali@gmail.com
ጉዳዩ – እሁድ ጃንዋሪ 13 ጠዋት ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በምገኝበት ወቅት ነው የተከሰተው። የዜጎቻችንን ቁጥር ስለበዛ (አበሻ የሚለውን ቃል መጠቀም ስለሚደብረኝ) ምን ይሆን ምክንያቱ ብዬ አካባቢውን እየቃኘሁ ፓስፖርቴን አሳይቼ ወደ ውስጥ ገባሁ። ሰሌዳው ላይ የጀርመን አየር መንገድ የሆነው ሉፍታንዛ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እንዳለውና መግቢያውም በበር ቁጥር 22 እንደሆነ ይገልፃል። በተጠቀሰው በር በኩል ሳልፍ  በርከት ያሉ ተሳፋሪዎች ተመለከትኩ። አንድ አውሮፕላን ይህን ሁሉ ሰው ይዞ ይጓዛል? ራሴን በራሴ ጠየቅሁ። መልሱ ብዙም ሰላላስጨነቀኝ ወደ ፊት ቀጠልኩ። እዚህ አካባቢ የተመለከትኩት የዜጎቻችን ኮተት ማብዛት ፈገግ እያስደረገኝ ወደ ፊት ገሰገስኩ። የፍራንክፈርት አውሮፕላን ማረፊያ ለንደንን አያክል እንጂ ትልቅ ነው። በተለይ ኮተት ለተሸከመ ሰው አድካሚ የውስጥ ለውስጥ ጉዞ ይጠብቀዋል።
ለንደን የሚጓዘው አውሮፕላን መግቢያው በር ቁጥር 47 ላይ ስለነበረ ጉዞዬን ቀጠልኩ። በመንገድ ላይ ተጨማሪ ዜጎቻችን ነበሩ። አንዳንዶቹ የያዙትን ኮተት መጎተት አቅቷቸው እረፍት ለመውሰድ ኮተታቸውን ከራሳቸው ላይ አራግፈው ቆመዋል። ከተጓዦቹ ማህል አንዷ እንዲውም በጣም ገርማኛለች። ከፍ ያለ ታኮ ጫማ ተጫምታለች። ቦርሳ አንግታለች፣ ላፕ ቶፕ ተደግሟል፣ አነስ ያለ ቦርሳ ይጎተታል፣ ከውስጥ የተገዛ ውስኪ በከረጢት ተደርጎ ተይዟል። ልብ ብሎ ለተመለከታት ቤት የምትለቅ ትመስላለች። ይህ ዓይነት ሸክም በብዙው ተሳፋሪ ላይ የሚታይ ነው።
ሁሉንም መርዳት ሰለማይቻል ጉዞዬን ቀጠልኩ። በመንገድ አንደ ጠና ያሉ ሴት አገኘሁና መርዳት አለብኝ ብዬ ተጠጋሁ። በትግሪኛ አነጋገሩኝ። እንደማልችል ገልጽኩላቸው። አማራ ነህ አሉኝ። ዘር መቁጠር ሰለማይጥመኝ ዝም አልኩ። ዘር መቁጠር ብጀምርም ማንነቴን ለመግለጽ እስከ ሰባት ቤት ድረስ መዘዘር አለብኝ።  ሸክሙ ሲቀላቸው አፋቸውን ቀለለው መሰለኝ ጥያቄውን ያዥጎደጉት ጀመር። እኔ ደግሞ ሸክሙ ስለበዛ ለመልሱ ቦታም አልሰጠሁት።
- አዲስ አበባ ነው እንዴ የምትሄደው ?
- አይደለም። እርስዎ አዲስ አበባ ነው የሚሄዱት?
- አዎ።
- ከሆነ ቦታ ተሳስተዋል። በር ቁጥር 22 ነው’ኮ መግቢያው።
- እሱ ሉፍታንዛ ነው። የእኛ አውሮፕላን 48 ቁጥር ላይ ነው።
- አሁን ግራ ገባኝ ወደ አስመራ የሚሄድ ሌላ አውሮፕላን ያለ መሰለኝ። <<የኛ>> ማለት ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም።
ወደ መሳፈሪያው በር ላይ ስደርስ ነገሩ ግልጽ እየሆነልኝ መጣ። አዲሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ  787(Boeing 787 Dreamliner) ፊቱን ወደ መስታወቱ አዙሮ ቆሟል። ከውጭ ሲያዩት ደስ ይላል። ወደ ሃገሬ ምድር የቀረብኩ መሰለኝ። እቃውን አስረክቤ ሴትየዋን በሉ በሰላም ይግቡ አልኩና ተለያየሁ።
Ethiopian Airlines Germanyበነገራችን ላይ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የጀርመን ቅርንጫፍ ሳነሳ አንድ የማይረሳኝ ነገር አለ። የፍራንክፈርት ባቡር ጣቢያ የሚገኘው መሃል ከተማው አካባቢ ነው። ከባቡር ጣቢያው ፊት ለፊት የታወቀው ካይዘር (Kaiserstraße)በመባል የሚታወቀው ሴተኛ አዳሪዎች የሚገኙበት መንገድ ነው። ከዚህ መንገድ ጎን ደግሞ ሙንሽነር መንገድ የሚባል አለ። በሁለቱ መንገዶች መሃል አንድ ሕንጻ አለ። ድሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ የነበረው በዚህ ሕንፃ ላይ ነው። በሕንጻው ላይ በትልቁ Ethiopianየሚል ተጽፎ ነበር። እሱን ባየን ቁጥር ዜጎች የሃገራችን ስም በፍራንክፈርት እምብርት ላይ በመለጠፉ እንደሰት ነበር። አየር መንገዱ በደከመ ዘመን እንኳን ይህንን ቢሮ ይዞት ከርሟል። አሁን ግን በወያኔ ዘመን ይህ ጽሁፍ ከቦታው ወርዷል። የአየር መንገዱም ሥራ ለወያኔ ደጋፊዎች ተበታትኗል። ቢሮውን ተለቋል ። ያ እንደ ትልቅ የምንኮራበትም ጽሁፍ አሁን የለም። እዚያ ሕንጻ ላይ መለጠፉ ትልቅ አየር መንገዱን ማስታወቂያ ስለነበር ገርሞኛል። ( ፎቶው የተጠቀሰው ሕንጻ ነው)
ወደ ቦታዬ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ  ዞር ከማለቴ ፍራንክፈርት አውቀው የነበረ ሰው አሁን የአየር መንገዱ ቢሮ ከፈረሰ በኋላ ሥራውን ተረክቦ ይራወጣል። በእሱ እድገት እየተገረምኩ መንገደኛውን አንድ በአንድ መመለክት ጀመርኩ። ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ ሰው ከውጭ እንጂ ከውስጥ አጋጥሞኝ ስለማያውቅ ብዙ የሚያሰገርም አዳዲስ ክስተቶች በዜጎቻችን ላይ ተመልክቻለሁ።
ከሁሉ በፊት የተረዳሁት የሴት ዜጎቻችንን ፀጉር ረጅም መሆኑን ነበር። አንድም ቀምቀሞ ላገኝ አልቻልኩም። ሹርባም የለም። ኢትዮጵያውያን ሴቶች የጸጉር ቀለማቸው ምን ዓይነት ነው? ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ሊከብድ ይቻላል። ብሎንድ፣ ቢጫ፣ ነጭ፣ ቀይ ፣ ጥቁር  በየዓይነቱ ጸጉር ተሰክቶል። ግሩም ማማር!መሽቀርቀር እንዲህ ነው። የሚገርመው ሁሉም ሴቶች አንድ አይነት የአንገት ሰበቃ ይዘዋል። ፈረንጆች ጸጉራቸውን ንፋስ አምጥቶ ፊታቸው ላይ ሲጥልባቸው ጸጉሩን ለመመለስ እንደሚደርጉት ዓይነት። የኛዎቹ ግን ጸጉር ወደ ፊት ቢመጣም ባይመጣም አንገት መስበቅ እንደ ልምድ አድርገውታል። እንደ ሥልጣኔ!  እንደ ፈረንጅነት!
ጸጉሩን ተወት አድርጌ ወደ ታች ስመለከት የአለባበሱን ጉዳይ መናገር ያቅታል። ጉዞ ጀምሮ፣ ታኮ ጫማ አድርጎ መደናቀፉ የሚገርም ነው። የዝነጣው ዓይነት ግማሾቹ ከአውሮፕላን ሲወርዱ ሙሽራ የሚሆኑ ይመስላሉ። ማጥናቴን ቀጥዬ የእጅ ጥፍር ላይ ስደርስ ግን ግራ የሚያጋባ ነው። ሁሉም አዲስ ጥፍር አስክተዋል። ረጅም ለምንም ሥራ የማይመች።  ያ ጥፍር ደግሞ ዜጎች ለለመድነው  ምግብ ተስማሚ አይደለም። እንጀራን በሹካ ካልሞከርነው በቀር። ችግር የለም ለካ ክትፎ በቀንድ ማንኪያ መሆኑን ረስቼው ነው። ጥፍሩን ከማስነቀል እንጀራም በፈሳሽ መልክ ቢዘጋጅ ምን ነበረበት። ለቅምጥል ሲያንስ ነው።
ወደ ወንዶቹ ስዞር ደግሞ ጥቁር የቆዳ ጃኬት የታደለ ይመስላል። <<የተከበሩ>> ኢንቨስተሮቻችን መዳፈር አይሁንብኝ እንጂ የእጃቸው ስልክ አስሬ ነው የሚጮኸው። ዶላር ስንት ሆነ? ኢሮስ? መኪናው ደረሰ ወይ? ጠዋት ነው የምደርሰው መኪና ይጠብቀኝ? መኪናውን ለምን ሸጣችሁት ? አሁን በምን ልጠቀም ነው? ኮንቴነሮችን እስቶር አስገቧቸው! እኔ ስመጣ ነው የሚከፈቱት! ሆቴል ያዝልኝ! ። ጨኸት በጩኸት! ንግግሩ ለኛ ይሁን ለሌላው አይገባኝም። ግን ሁሉም እየጨኸ በሞባይል ያወራል። እድሜ አዲስ ጀርመን ለገባው የስልክ ካርድ – ላይካ። ስልክ እንደሆነ ረክሷል። ብዙዎቹ  መነጽራቸው ወደ ላይ ወደራሳቸው ገፋ ተደርጓል። እዚህ እንደሁ ክረምት ነው ፀሐይ የለም።  ምን አልባት ለአዲስ አበባ ይሆን ? ይሁን መቼስ።
ከሁሉ የገረመኝ አብረው የሚሄዱት ፈረንጆች ናቸው። ቱታ ለብሰው፣ አሮጌ የቴንስ ጫማ ተጫምተው ዘና ብለው ለመንገድ ተዘጋጅተዋል። ጥፍርም አላስተከሉ፣ አዲስ ልብስ አልገዙ፣ በታኮ ጫማም አልተደናቀፉ። ዜጎቻችን የሰባቱን ሰዓት ጉዞ የለበሱት፣ የተቀቡት፣ እንዳይበላሽ ሲጨነቁ ፈረንጆቹ በሰላም ሊደርሱ ነው። እንዲውም አንዱ ከላይ የሃገራችን መስቀል የተጠለፈበት ሸሚዝ ነው ያደረገው። ወይ እንደ ፈረንጅ መሆን።
ከተጓዦቹ ማህል አንዳንዶቹን በዓባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ወቅት ፍራንክፈርት (Nordweststadt saalbau) በተደረገ ወቅት እየተንደረደሩ ሲገቡ በውጭ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ነበርንና  ሰልፈኛው ሆዳም ሆዳም ብሎ ሲሰድባቸው አይቻቻዋለሁ። እነርሱም ሰላዩኝ ይህንን ካነበቡ ማንን ማለቴ እንደሆን ይገባቸዋል።
ወደ አውሮፕላኑ ሲገቡ የተለያየ ሁኔታ መገንዘብ ቻልኩ። አንዱ የባለቤትነት፣ ሌላው ደግሞ የእንግድነት። ቀደም ፣ ቀደም ብለው በድፍረት የሚሄዱ አሉበት፣ እንደ እንግዳ እየተሽኮረመሙ የሚገቡ አሉበት፣ እንደ እውነተኛ ነጋዴ የሚዝናኑ አሉበት፣ አስመሳይ ኢንቬስተሮችም አሉበት፣ ለመዘነጥ የሚሄዱ አሉበት፣ እውነተኛ የሃገር የቤተሰብ ፍቅር አንገብግቦት የሚሄድ አለበት፣። ሁሉም ድብልቅልቅ ያለ ነው። ስንቱ ይሆን ሱሱን ለማርካት የሚሄደው? ዋናው ጥያቄዬ እሱ ነበር።
ባለፈው ሳምንት በድረ ገፆች እየተዘዋወርኩ ሳነብ <<አዲስ አበባበ ህገወጥ ልማዶችና የወሲብ ድርጊቶች እየተናጠች ነው !!! >> በሚል እርዕስ ያነበብኩት ትዝ አለኝ። እንዲህ ይላል፡ -
ግብረሰዶም ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋ ነውአብዛኞቹ የከተማዋ ማሳጅ ቤቶች የወሲብ ንግድ እንደሚያጧጡፉ ታውቋል። ከ3600 በላይ ህገወጥ ልማዶችና የወሲብ ድርጊቶች የሚፈፀምባቸው ቤቶች አሉ። ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ፖሊሶችና ነጋዴዎች የአነቃቂ እፆች ተጠቃሚ ናቸው።በእርቃን ጭፈራ ቤቶች ደጃፍ ከሚቆሙ መኪኖች አብዛኛዎቹ የመንግስትና የንግድ ታርጋ የለጠፉ ናቸው። በአዲስ አበባ ህገወጥ ተግባራት የሚከናወኑባቸው ቤቶች በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ ምጣታቸውንና ከተማዋ አደጋ ላይ እንደሆነች ሰሞኑን ይፋ የተደረገ ጥናት አረጋገጠ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት ይፋ የተደረገው ጥናት “መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም በወጣቶችና ሴቶች ላይ እያስከተሉት ያለው አሉታዊ ተጽእኖ” በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን ከ3600 በላይ ህገወጥ የወሲብ ድርጊት የሚፈፀምባቸው ቤቶች እንዳሉ ጠቁሟል፡፡
ይህ ሁሉ አስከፊ ድርጊት ወደ ሃገሪቱ እንዴት እንደተዛመተ መገመት ይቻላል። ጥናቱም <<መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች>> በሚል አስቀምጧቸዋል። አንዳንድ ዜጎቻችንን ከውጭ እየያዙ የሚገቡትን አንዳንድ መጥፎ ተግባራት በአላቸው ገንዘብ በመጠቀም በእርካሽ አገር ውስጥ ስሜታቸውን አርክተው ግን ወጣቱን ትውልድ ወደ ውጭ እናወጣኻለን በሚል አበላሹት። ፈረንጆቹም ቢሆኑ ከእንደዚህ ዓይነት ተግባር የጸዱ አይደሉም። ወያኔ ደግሞ እንዲዚህ ዓይነት ብኩን ዜጎች መብዛታቸው ያስደስተዋል እንጂ አያስከፋውም። ሊያምጽ የሚችለውን ወጣት በሱስ ማደነዝ ቀዳሚ ተግባሩ ነውና።
እነዚህ ሁሉ ሲመለሱ ደግሞ የሃገሪቷን ሁኔታ በተለያ መነጽር መመለከታቸው አይቀርም። ለመዘነጥ የሄደው ፣ስለዘናጩ ብዛት ይነግረናል፣ ነጋዴው ስለነጋዴው የተሳካ ኑሮ፣ ኢንቨስተሩም እንዲዚሁ። የዛችን ሃገር ፣ የዛን ሕዝቡ ሰቆቃ ለማየት ያልፈለገ አያየውምና ተንጋግተው እንደሄዱ፣ ተንጋግተው ይመለሳሉ። ይህ መንጋ እውነቱን እንዳያይ፣ አዲሱ ጸጉሩ ፣ አዲሱ ጥፍሩ ፣ አዲሱ እሱነቱ የጥንቱን ማንነቱ ይሸፍንበታል። ችግር ከሃገሪቱ ጠፍቷል ብሎ ይቀደዳል። የተቃዋሚዎችን ስህተት እያጎላ ይሰብካል። ይህ በወያኔ የተሰጠው ሃገርን የማጥፋት ፍቃድ እንዳይቀርበት በሚያምበት ሁሉ ይሳላል።
ይህ ዝርክርክ፣ ግትልትል ዜጋ  ትንሽ አፍ እላፊ ከተናገረና የወያኔን ማንነት ካጋለጠ ይህ ኑ እንታያይ የዝንጣ ኑሮ ሊቀርበት ሰለሆነ እንደ ዘመኑ ቋንቋ ጎመን በጤና! እያለ እየዘፈነ ይኖራል። ከዛም አልፎ የግድብ ቦንድ ገዥ፣  ለመለስ ሞት በየኤምባሲው ደረት መቺ ቢሆን አይደንቅም። ወያኔም ይህ ሽቅቅርቅር የዲያስፖራ ቡድን የተቃዋሚውን ትግል ለማዳከም መርዙን ለመርጨት ይጠቀምበታል።
ወገን እስከመቼ ነው እንደዚህ የምንኖረው?
እነርሱ ከገቡ በኋላ የእኔም ተራ ደረሰና ወደ አውሮፕላናችን ገብተን የለንደን ጉዞ ። እና የስደት ኑሮ ቀጠለ ! አውሮፕላኑ ውስጥ በእውቀቱ ስዩምን አስታወስኩ። ቆዳ ጃኬትና መነጽር አጥቶ ይሆን? የሃገር ልብስ ለብሶ ለንደን ውስጥ ለኦለምፒክ የተጋበዘ ጊዜ በየስብሰባው የሚሄደው። በሚቀጥለው ሳገኘው እስቲ እጠይቀዋለሁ።
ሰለዛች ሃገር የሚያስብ ሁሉ በሰላም ይክረም!
ፍራንክፈርት
ጃንዋሪ 13/2013

ከዕርቀ ሰላም ይልቅ ለ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ቅድሚያ የሰጠው የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ተስፋዎችን አጨላሚ ሆነ


ከዕርቀ ሰላም ይልቅ ለ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ቅድሚያ የሰጠው የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ተስፋዎችን አጨላሚ ሆነ

ደጀ ሰላም፤ ጥር 8/2005፤ ጃኑዋሪ 16/2013/
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና ከመነሻውም በውጪ ተጽዕኖ ሥር የወደቀው የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ እንደተፈራውም ዕርቀ ሰላሙን አሽቀንጥሮ ወርውሮ 6ኛ ፓትርያርክ በመፈረሙ ላይ ጸንቷል። በብፁዕ አቡነ አብርሃም በተነበበው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው ቅ/ሲኖዶሱ ያደረገው ሙከራ ያልተሳካው በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች ባቀረቧቸውና ከዕርቁ ጋር በማይገናኙ ሌሎች ምክንያቶች የተነሣ ነው። ይህ “ከእርቁ ጋር የማይገናኝ” የተባለው ምክንያት አሜሪካ ያሉ አባቶች የሚያነሧቸው “ፖለቲካዊ ጥያቄዎች” መሆናቸውን ደጀ ሰላም ትረዳለች። በተለይም ለብዙዎቹ የቅ/ሲኖዶስ አባላት የተነገራቸው ምክንያት “አገር አቀፍ ዕርቅ” ይውረድ ይላሉ፤ ውጪ አገር አሉት ፖለቲከኞችም አብረውን ካልገቡ ይላሉ የሚለው መልዕክት ነው።ከዕርቀ ሰላም ይልቅ ለ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ቅድሚያ የሰጠው የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ተስፋዎችን አጨላሚ ሆነ
ዛሬ በቅ/ሲኖዶሱ ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሳይሆን ከሰሞኑ በተለያዩ ዜናዎች ስማቸው ተደጋግሞ ሲጠቀስ በሰነበተው በብፁዕ አቡነ አብርሃም የተነበበው መግለጫ የብዙዎች ምእመናንና ካህናትን ተስፋ እንደሚያጨልምና ወደ ቀቢጸ ተስፋም እንደሚከታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ጥበብና አስተዋይነት በጎደለው፣ ከሃይማኖታዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ በሚሰማው በዚህ ውሳኔ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከ20 ዓመታት በኋላ ድጋሚ ልታገኘው ትችል የነበረውን የአንድነት መንፈስ ተኮላሽቷል። ለዚህም ከታዋቂ ሰባኪ ነን ባዮች እስከ አንዳንድ “ልጅግር” ጳጳሳት፣ ተሰሚነት አለን ከሚሉ ጦማርያን እስከ ፖለቲከኞች ያደረጉት ርብርብ በርግጥም ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድ እንዳትሆን የሚሠራው አካል እስከ ደም ጠብታ እንደተዋደቀ አሳይቷል፤ የብዙዎችንም አሰላለፍ በርግጥ ተረድተንበታል። የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይፈርዳል!!
አንዳንዶቹ ጳጳሳትና ብሎገሮች እንዳሉት በርግጥ ለጳጳሳቱ ደሞዛቸውን የሚከፍላቸው አሜሪካና አውሮፓ፣ አረብ አገርና በሌሎች ዓለማት በስደት የሚገኘው ምእመን አለመሆኑ ብቻ የሚያስንቀው ከሆነ አገር ቤትም እያለ ጠቀም ያለ ገንዘብ መክፈል የማይችለው ደሃ ምእመን በእነርሱ ዘንድ ሞገስ የለውም ማለት ነው? በዚህ ደሃ ሕዝብ ገንዘብ ቤታቸውን አልሰሩምን? የሚንደላቀቁትስ በዚሁ ደሃ ምእመን ጥሪት አይደለምን? በሌላ ጊዜ ለዕረፍትም ለመዝናናትም የሚሆዱባቸው የአሜሪካና አውሮፓ አገራት ምእመናን አይሰሙ/ አይሰማቸው መስሏቸው ይሆን? ለማንኛውም በዚህ ውሳኔ አንድነምታ ዙሪያ ተከታታይ “ምልከታዎች” ማቅረባችን ይቀጥላል። ደጀ ሰላማውያንም ሐሳባችሁን እንድትሰጡ ከወዲሁ እንጋብዛለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።

በደቡብ አፍሪካ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ባንዲራና ቲቨርት አሳትመው በነፃ እየበተኑ ነው

(ዘ-ሐበሻ) ለአፍሪካ ዋንጫ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚሄደውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ቡድን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ እየተሯሯጠ የሚገኘውን የደቡብ አፍሪካ
የኢትዮጵያ ኢምባሲን ሴራ ለማክሸፍ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሰፊው
እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የደቡብ አፍሪካ የዘ-ሐበሻ ወኪል ገለጸ። እንደ ወኪላችን ገለጻ
የኢትዮጵያ ኢምባሴ የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ የያዘ ቲቨርትና የወያኔን ኮከብ
ያለበትን ባንዲራ ለመሸጥ ከፍተኛ እንስቃሴ እያደረገ ቢሆንም፤ ሕዝቡ የአንባገነኑን አቶ
መለስ ዜናዊን ፎቶ ያለበትን ቲቨርት እንዳይለብስና የወያኔን ባንዲራ እንዳይዝ በማሰብ
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ እና የቤተ ኢትዮጵያውያን ማህበር በጋራ
ቲሸርቶችን እና ምንም ዓይነት ኮከብ የሌለበትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ
አሳትመው በነጻ እየበተኑ መሆኑ ታውቋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት “በዘርና በሃይማኖት መከፋፈሉ በቃን፤ አንድ ኢትዮጵያዊ
ነን በሚል” ደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች ለሚሄደው ድጋፍ ለመስጠት
ከፍተኛ ርብርቦሽ እያደረጉ ሲሆን ከወዲሁም ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር የምታደርገው
ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ትኬት ተሽጦ ማለቁን ወኪላችን ከደቡብ አፍሪካ
ዘግቧል። ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጨዋታውን ለመመልከት ትኬት
ገዝተዋል ተብሏል; እንደወኪላችን ዘገባ በደቡብ አፍሪካ ከ200 ሺህ በላይ የሚመቱ
ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኢምባሲ የመንግስት አመራሮችን
በተለይም ሃይለማርያም ደሳለኝን ጋብዞ ህዝባዊ ስብሰባ ቢጠራም ሕዝቡ ቦይኮት
በማድረግ የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካ ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ከዛም በኋላ ታማኝ
በየነን ጋብዘው ስታዲየም ሙሉ ሕዝብ በመገኘት አንድነታቸውንና ሃገር
ወዳድነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለስፖርታዊ ጨዋታዎች የሚሄደውን
ብሔራዊ ቡድናችንን ከስፖርታዊው ትኩረቱ ውጭ አቶ መለስ ዜናዊ ሌጋሲ ላይ እንዲያደርግ ከፍተኛ ሥራ እየሰራ መሆኑን የጠቁመው የዘሐበሻው ወኪል የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ደጋፊዎችን
ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊዎች ወደ አንድነት በመምጣት የመንግስትን ሴራ ለማክሸፍ እየተሯሯጡ ይገኛሉ። በተለይም በእምነት ውስጥ ጣልቃ እየገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤ/ክ እና ሙስሊሞችን እያስጨነቀ የሚገኘውን የኢትዮጵያ መንግስት ስታዲየሙ ውስጥም ሆነ ከስታዲየሙ ውጭ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ “መንግስት እጁን ከሃይማኖቶች ላይ
እንዲያነሳ” ለመጠየቅ ሥራ እየተሰራ ይገኛል ያለው ዘጋቢያችን በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የወያኔን ባለኮከብ ባንዲራ ይዞ እንዳይገኝ ጥሪ መተላለፉን በአንጻሩ ሃገር ወዳድ
ኢትዮጵያውያን በተለይ በጆሐንስበርግ ከተማ በነፃ እየበተኑት ያለውን ባንዲራ ይዘው ለብሄራዊ ቡድናችን ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ እየተላለፈ ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጆሐንስበርግ ሲገባ ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

(ሰበር ዜና) ሲኖዶሱ አቡነ መርቆርዮስን እንደማይቀበል፤ 6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ እንዲደረግ ወስኖ ተበተነ (መግለጫውን ይዘናል)

6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ይደረግ ሲል ወሰነ
– መግለጫው ላይ የቅዱስ ሲኖዱሱ ዋናጸሐፊ ማህተምና ፊርማ የለበትም፤ ሕጋዊ ሊባል
ይችላል ወይ?
– መግለጫውን ያነበቡት አቡነ አብርሃም ናቸው
ለ3 ቀናት ሲደረግ የቆየው ኢትዮጵያ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ትናንት ዘ-ሐበሻ እንደገለጸችው ዛሬ መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ። ቅዱስ ሲኖዶሱ ያወጣው መግለጫ ፕሮቶኮሉን
ያልጠበቀ መሆኑን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ሲኖዶሱ በመጨረሻም የደረሰበት ውሳኔ አቡነ መርቆርዮስን እንደማይቀበል ሲሆን መግለጫውን ማንበብና ማህተምና ፊርማ ማኖር የነበረባቸው የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሕዝቄል
የነበሩ ቢሆንም ትናንት የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አልቀበልም በማለታቸውና ስብሰባውን ረግጠው በመውጣታቸው መንግስት ባስቀመጣቸው የሃረርጌ ሊቀጳጳስ አቡነ አብርሃም አማካኝነት
እንዲነበብ መደረጉንም የዘ-ሐበሻ ምንጮች አረጋግጠዋል። አባቶች የመንግስትን አቋም አሜን ብለው መቀበላቸው ሕዝበ ክርስቲያኑን አሳዝኗል።
ደብዳቤውን የጻፉት የሕወሐት አባሉ ንቡረ ዕድ ኤሊያስ መሆናቸ




“ፍቅረኛሞቹ” አዜብና ብርሃነ – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

አዜብ መስፍንን ከሱዳን አምጥቶ ሕወሓትን እንዲቀላቀሉ ያደረገ ነው። የፍቅር
ግንኙነትም ነበራቸው። ይህ ሰው ብርሃነ ኪዳነማርያም (በቅፅል ስሙ ብርሃነ-ማረት)
ነው። አዜብና ብርሃነ ድርጅቱን ሲቀላቀሉ የተቀበሏቸው አቶ አስገደ ገ/ስላሴ (አሁን
የአረና አባል) ነበሩ። ጥቂት የበላይ አመራሮች በሁለቱ የፍቅር ግንኙነት ዙሪያ መከሩ።
ከዛም የብርሃነና የአዜብ ግንኙነት እንዲቋረጥ በማድረግ ከለያዩዋቸው በኋላ ከመለስ
ዜናዊ ጋር አዜብ እንዲጠቃለሉ ሆነ። (በነገራችን ላይ አንዳንድ ወገኖች አዜብና ሟቹ
ክንፈ ገ/መድህን በጫካ ግንኙነት እንደነበራቸው ተደርጎ የሚነገረው ከእውነት የራቀ
እንደሆነ የቅርብ ታማኝ ምንጮች ይገልፃሉ፤)
ወደ ዋናው ርዕሰ ጉዳይ እናምራ፥ በሕወሓት ውስጥ አድፍጠው መሰሪ ተግባር
ከሚፈፅሙት አንዱ ነው ተብሎ በፓርቲው ወገኖች የሚፈረጀው ብርሃነ ኪ/ማርያም
(ብርሃነ-ማረት) ማንነትና አደገኛ አካሄድ ምን እንደሚመስል ከላይ የተገለፀውን
መንደርደሪያ ያስቀደሙ ታማኝ ምንጮች ተከታዩን ይላሉ።
ፓርቲው ወደ ስልጣን ሲመጣ አቶ ብርሃነ የተመደበው በመቀሌ ማዘጋጃ ሃላፊ ተደርጎ
ነበር፤ መንግስት የከተማውን አስፋልት መንገድ ለማሰራት እንዲውል የመደበውን
አምስት ሚሊዮን ብር « ቅርጥፍ» ያደርጋል። በወቅቱ የክልሉ ፕ/ት የነበሩት ገብሩ
አስራት በወሰዱት እርምጃ ብርሃነ እንዲባረር ሲደረግ፥ ሁለት ግብረ-አበሮች የተባሉ
ደግሞ ይታሰራሉ። የተባረረው ብርሃነ አዲስ አበባ ይመጣል። አዜብን ለማግኘት ብዙ
ጥረት ካደረገ በኋላ ተሳካለት። ከዚያም አዜብ የቀድሞ « ፍቅረኛቸው»ን ለመታደግ
ሲሉ ብርሃነ በሲቪል ሰርቪስ ኰሌጅ እንዲገባ ያደርጋሉ። ለረጅም አመት ድምፁን
አጥፍቶ በኰሌጁ ቆየ። የኢትዮ- ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ ለብርሃነ «ጥሩ» አጋጣሚ
ፈጠረለት። ከቤተ መንግስት የማይጠፋ ሆነ፤ ከመለስ ጋር ቀን-ከሌሊት ምስጢራዊ
ምክክሩ ቀጠለ። ታማኝና ቀኝ እጅ መሆኑን ለማሳየት በተግባር ተንቀሳቀሰ።
በ1993ዓ.ም ፓርቲው ለሁለት ከመሰንጠቁና ይፋ ከመውጣቱ በፊት « ጥንስሱን » ያውቁ የነበሩት አቶ መለስና ብርሃነ ነበሩ። ብርሃነ ታህሳስ 1993ዓ.ም ከፍተኛ ባጀት ተመድቦለት ወደ
አሜሪካ መጣ፤ በወቅቱ በፓርቲው ውስጥ ገና ክፍፍል አልተፈጠረም፤ በተባራሪዋቹም በኩል የታወቀ ነገር አልነበረም። ብርሃነ በአሜሪካ ፥ ላስቬጋስ፡ ቴክሳስ፡ቦስተን፡ አትላንታ፡ ሲያትል…
ከተሞች እየተዘዋወረ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ በማካሔድ በሕወሓት መከፋፈል መፈጠሩን በይፋ ለድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች ገለፀ። ጎን ለጎን ሰዎችን በመመልመል ከአቶ መለስ ጎን
እንዲቆሙ አደረገ። በኢምባሲ የተመደቡትን ሳይቀር እያስፈራራና እየዛተ ድጋፍ እንዲሰጡ አዘዘ። በቅስቀሳው ላይ የሚባረሩትን፡ የሚታሰሩትን አመራሮች በስም እየጠቀሰና በስድብ
እያብጠለጠለ ነበር ቅስቀሳውን ያካሂድ የነበረው። በተለይ የገብሩ አስራትን ስም በማንቑዋሸሽ… ዘመቻ አካሂዶዋል።« ግዳጁን » በአግባቡ በመፈፀሙ…የፓርቲው ማ/ኰሚቴ አባል ተደርጎ
የተመረጠው ወዲያው ነበር።
በሙልጌታ አለምሰገድ ይመራ የነበረውንና በፓርቲው መሰንጠቅ ማግስት የተቋቋመው የፌደራል ደህንነት ቢሮን ከጀርባ እንዲመሩ ከተመደቡት አንዱ የሆነው ብርሃነ፥ ተግባሩን
ሲጀምር..የአፈናና ስቃይ ሰለባ ያደረጋቸው ከፓርቲው የተወገዱ አመራሮች – ጠባቂዎችን ነበር። የገብሩ አስራትን ጠባቂዎች (ታጋይ የነበሩ) ጨምሮ በጅምላ እንዲታሰሩ አደረገ። ግርማይ
(ማንጁስ) ከተባለ የፌዴራል ፖሊስ ኮማንደር ጋር በቅንጅት ሆነው ጠባቂዎቹን በደም እስኪታጠቡ አሰቃዩዋቸው፤ እነ ገ/መስቀል የተባሉ የቀድሞ ታጋዮች እጅና እግራቸው በብረት ሰንሰለት
ታስሮ ከተሰቃዩ በኋላ ወደ ትግራይ ተወስደው..በአደገኛ ቦዘኔነት ክስ እንዲመሰረትባቸው አደረጉ። በስቃይ ብዛት ገ/መድህን የተባለ ህይወቱ አለፈ። ለረጅም ወራት ታስረው ከተፈቱ በኋላ
በመቀሌና ማይጨው የቁም እስረኛ ተደረጉ። ምንም ስራ መስራት አይችሉም፤ ወደየትም ስፍራ መንቀሳቀስና ሌላ አካባቢ መሄድ አይችሉም፤..ይህ ሁሉ በብርሃነ የተፈፀመ ነበር።
በሌላ በኩል ደግሞ የዚህን ሰው አደገኛና መሰሪ አካሔድና ተግባሩን ከማንም በተሻለ ጠንቅቀው የሚያውቁና የእርሱ ወጥመድ «ሰለባ» የሆኑ የቀድሞ የፓርቲው አመራር አባላት ምንም ትንፍሽ
አለማለታቸውና አለማጋለጣቸው አስገራሚ ነው። ምክንያቱም እነዚህ አካላት በአገር ውስጥ እንዴት እንደታፈኑ ብቻ ሳይሆን ..በዚህ ሰው እንዴት እንደተሰቃዩ ያውቁታል፤ ያስታውሱታል…
ሲሉ ምንጮቹ ትዝብታቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።..
በውጭ አገራት የሚኖሩ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች ማንነትና የሚያራምዱት አቋም በተመለከተ መረጃ አለው። በተመሳሳይ በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች ዙሪያ
መረጃ ማነፍነፍ የየዕለት ተግባሩ ነው። በተለያዩ አገራት የሚመደቡ አምባሳደራት በዚህ ሰው ጥብቅ ክትትል ይካሄድባቸዋል። ሲፈልግ አምባሰደራቱን በስድብ እያብጠለጠለ ያስፈራራል።
አንዳንዶች ደግሞ የፈጣሪያቸው ያክል « ጠብ እርግፍ » እያሉ ይሰግዱለታል። በአውሮፓና አሜሪካ ሲዘዋወር በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዩሮና ዶላር ተመድቦለት ነው የሚንቀሳቀሰው።..(
በነገራችን ላይ አሜሪካ-ዲሲ የከተሙ የብርሃነ ጋሻ ጃግሬዎች አሉ፤ አንዳንዶቹ በፖለቲካ አሳበው ጥገኝነት የጠየቁ ናቸው። ግን ስራቸው ፓርቲውን በምስጢር ማገልገል፡ በየጊዜው
ኢትዮጲያውያንን እየሰለሉ ለብርሃነ መረጃ ማቀበል ነው፤ የአሜሪካ ዜግነት ወስደው ይህን እየሰሩ የሚገኙትን በተመለከተ በቀጣይ እመለስበታለው፤ ማንነታቸው ይጋለጣል።)…
.አደገኛው የፓርቲው ሰላይ ብርሃነ ከወራቶች በፊት በአሜሪካ በተከሰተው ሁኔታ ውስጥ ነበር፤ ይኸውም አቶ መለስ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ጠ/ሚ/ሩን ሲቃወም …
ብርሃነ በአዳራሹ ነበር። ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ በመነሳት ለጠ/ሚ/ሩ አጃቢዎች ትዕዛዝ ይሰጥ ነበር። ..
ከፓርቲው ሊቀመንበር ህልፈት በኋላ፥ ብርሃነ የፓርቲው የጀርባ « አጥንት » በመሆን ማሽከርከሩን ተያይዞታል። በተጨማሪ ከአሁኑ ጠ/ሚ/ር ጀርባ አድፍጦ የመሪነት ሚና መጫወቱን
ቀጥሎበታል። በሌላም በኩል ሽማግሌው ስብሃት ነጋ በየመድረኩ የሚፈነጩት ያለምክንያት አይደለም፤ ይህን ሰው ይዘውና ተማምነው ነው። ምስጢሩ ደግሞ ሁለቱ ማለትም ብርሃነና ስብሃት
በጋብቻ የተሳሰሩ በመሆናቸው ነው። በተጨማሪ የፌዴራል ደህንነት በፀጋይ በርሔ ነው የሚመራው ይባል እንጂ ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው ብርሃነ ነው። ሁለቱም ከስብሃት ጋር በጋብቻ
የተሳሰሩ ናቸው። …ሽማግሌው ስብሃት በአዜብ ዙሪያ « መፈንቅለ ኤፈርት » ደግሰው « ጥንስሱን » ተግባራዊ ለማድረግ ሩጫቸውን ገፍተውበታል። ..ብርሃነ በቀድሞ « ፍቅረኛው » ላይ
የሽማግሌውን የሴራ በትር ያሳርፋል?…በቀጣይ የሚታይ ይሆናል፤..ብለዋል ምንጮች።
በሚቀጥለው መጣጥፍ.. በ40 ሚሊዮን ብር ህንፃ ስለተገነባለት የአዜብ ውሽማ…የምንለው ይኖራል፤

Jan 16, 2013

በእርሶ ድጋፍ ኢሳት የኢትዮጵያዊያን ዓይንና ጆሮ ሆኖ ይቀጥላል!!!!

Add caption


ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ልትሆን እንደምትችል ተጠቆመ

ኢሳት ዜና:-በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ በሚካሄደው    የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የህብረቱ ሊቀ-መንበር ለማድረግ ኢትዮጵያ  ቀደም ካለ ጊዚ ጀምሮ ጥረት ስታደርግ መቆየቷ ተገልጿል።ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር  ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት ኢታዮጵያ በመጪው ሳምንት 20ኛውን የ አፍሪካ ጉባኤ ታስተናግዳለች።
ከህብረቱ 50ኛ ዓመት የምስረታ በ ዓል ጋት ተጣምሮ ይካሄዳል በተባለው በዚህ ጉባኤ ላይ፤የሁለቱ ሱዳኖች ፣ የሶማሊያ ፣ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎና የሰሞኑ የማሊ ሁኔታ አበይት ትኩረት አግኝተው ይመከርባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ።
በጉባኤው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የወቅቱ ሊቀመንበርነትንም ስፍራ ቤኒን ለባለተራው አገር ታስረክባለች።
እንደ አምባሳደሩ ገለፃ የሊቀመንበርነቱ ተራ የምስራቅ አፍሪካ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ይህን ቦታ ለማግኘት የተለያዩ ጥረቶችን ስታደርግ ቆይታለች።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ከ አንድ የውጪ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ የ አፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆኖ የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ባለው የስኳር ፕሮጀክት ዙሪያ ቅሬታቸውን ገለጹ

ኢሳት ዜና:-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጡት ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም አቶ አባይ ጸሐየ ወደ አካባቢው በመሄድ ነዋሪዎችን ማነጋገራቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች በፕሮጀክቱ ደስታቸውን እንደገለጡ ተደርጎ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን የቀረበው ትክክል አይደለም።ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የጅንካ ከተማ ነዋሪ እንደገለጡት “አቶ አባይ ጸሀየ ነዋሪዎች ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ የተገባላቸው ቃል ባለመከበሩ ተቃውሞ አስነስተዋል በሚል ምክንያት” ወደ አካባቢው በመሄድ ህዝቡን ቢያነጋግሩም ፣ በስብሰባው ወቅት የኢህአዴግ አባላት ብቻ ተመርጠው አስተያየት እንዲሰጡ በመደረጉ ህዝቡ ቅሬታውን በይፋ እንዳይገለጥ ተደርጓል።” የአካባቢው ነዋሪዎች ቃል የተገባላቸው ግንባታዎች እንደተሟሉላቸው ተደርጎ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን የቀረበው ዘገባ ህዝቡን ማስቆጣቱን ነዋሪው ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ሀሳባቸውን የጠየቅናቸው የደቡብ ኦሞ የአንድነት ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው ” መንግስት የህዝቡን ችግር አድበስብሶ ለማለፍ ሙከራ ማድረጉን ይሁን እንጅ ችግሩ ተመልሶ መምጣቱን” ገልጸዋል።
ከወራት በፊት የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ በማሰማታቸው 13 ወጣቶች ታስረው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ወጣቶቹ ከ20 ቀናት በሁዋላ በዋስ ከእስር እንደሚለቀቁ ለማወቅ ተችሎአል።
በአካባቢው ከሚደረገው የስኳር ልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በቦዲዎች እና በመንግስት መካከል ግጭት ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል። ችግሩ አሁንም ድረስ አለመፈታቱ ታውቋል።
በተመሳሳይ ዜናም በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚደረገውን የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ጋር ይቃወማሉ የተባሉ 4 መኖከሳት ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል።
አባ ገ/ ሕይወት ጉራጌ፣ አባ ኃይለማርያም ፣ አባ ገብርኤልና ባህታዊ ታዲዎስን የተባሉት መነኮሳት መታሰራቸውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ባህታዊ ተናግረዋል። ባህታዊያኑ በማይጸብሪ እስር ቤት ውስጥ መታሰራቸውን ባህታዊው ገልጸዋል። መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።
የአሜሪካ ፌደራል በረራ መስሪያ ቤት በቦይንግ ድሪም ላይነር 787 አይሮፕላን ላይ መርምራ ሊያደርግ ነው

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የፌደራል መስሪያ ቤቱ ዋና ሃላፊ ሚሸል ሁሬታ አንዳስታወቁት በአውሮፕላኑ ላይ በደረሰው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የአውሮፕላኑን ዲዛይና ኣመራረቱ ምርመራ ይደረግበታል።

አውሮፕላኑ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የጃፓን ኣየር መንገድ ቦስተን ላይ ከቶኪዮ ተመልሶ በሚያርፍበት ሰአት እሳት ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ባለፈው አርብ የጃፓን ኦል ኒፖን አየር መንገድ ሪፖርት አንዳደረገው በሚበርበት ሰኦት በፓይለቱ በኩል ያለው መስኮት በመሰንጠቁ የመመለሻ በረራውን ለመሰረዝ ተገዷል።

ይኸው አየር መንገድ ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላን በሞተሩ ውስጥ ዘይት በማፍሰሱ በረራውን ለማቋረጥ ተገዶ እንደነበርና የፍሬን ችግርም በማጋጠሙም ከያማጉቺ ወደ ቶኪዮ ያደርግ የነበረውን በረራ መሰረዙን ገልፆአል። እንዲሁም አውሮፕላኑ 151 ሊትር የሚሆን ነዳጅ በማፍሰሱ ምክንያት ማክሰኞ ከቦስተን ወደ ቶኪዮ ያደርግ የነበረውን በረራ ኣቋርጧል።

ባለፈው አመት በዩናይት ኤር ላይንስ በተፈጠረ የኤሌትሪክ ችግር ምክኒያት አውሮፕላኑ በድንገት አንዲያርፍ የተደረገ ሲሆን የካታር ኣየር መንገድም በዲሴምበር ወር ኣንዱ አውሮፕላኑ በደረሰበት የቴክኒክና የኤሌክትሪክ ችግር ምክኒያት ከበረራ አንዲቆም አድርጎታል የቦይንግ ካምፓኒ በሰጠው መግለጫ የአውሮፕላኑ ዲዛይን አስትማማኝና ለበረራም ከአደጋ ነፃ የሆነ ነው ብሎታል

ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላን የተሰራው ካርቦን ከተባለውንጥረ ነገር ሲሆን በቴክኖሎጂም አጅግ ዘመናዊ የተባለለት ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኣፍሪካ የመጀመሪያ በመሆን 10 ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላኖች ከ ቦይንግ የገዛ ሲሆን ባለፈው ነሐሤ የመጀመሪያውን አውሮፕላን ተረክቦ ወደ ሃገር ቤት በከፍተኛ የአቀባበል ስነስርአት አስገብቷል

በገበያ ላይ ውሎ ውጤቱ ያልተመሰከረለትን አዲስ አውሮፕላን መግዛት ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል በሞያው ላይ የተሰማሩ የኤሮኖቲክ ኢንጅነሮች ያስጠነቅቃሉ።

ኢትዮጵያ፤ የመዳኛ ወቅትና፤ የዕረቀሰላም ጊዜ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
የረፖርተር ድሕረ ገፅ ሲዘግብ:
በጎሳ ላይ የተመሰረተ ግጭት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል በመጸዳጃ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍትና በመኝታ ቤት  ግድግዳ ላይ፤የተጻፉ አስፀያፊ ክብረነክ ጸሁፎች ከስድስት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ለከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ተጠቂ ዳርጓቸዋል:: በርካታዎችንም ለእስር አብቅቷል፡፡ ለላለፉት አሰርት ዓመታት፤በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል ግጭቶችን ሲያስነሱ ከርመዋል፡፡ ይህም መሰረታዊ ችግሩና መንስኤው አስተዳደራዊ ድክመት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተመሳሳይ ባለፈው በእለተ ዕረቡ ጃንዋሪ 2 2013 የተቀሰቀሰው ግጭትም በተለይ በሁለት ጎሳዎች በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መሃል የተከሰተ ነበር፡፡ ምስክሮች እንደሚሉት፤ግጭቱ የተቀሰቀሰው የትግራይ ተወላጅ የሆነው ተማሪ፤ በመጸዳጃ ቤት፤ በቤተመጻህፍትና በተማሪዎች መኝታ ቤቶች  ግድግዳዎች ላይ የጎሳን ክብር የሚነካ ጽሁፍ በመጻፉ ነበር፡፡
እንደ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለስልጣን አባባል ‹‹ግጭቱ የተቀሰቀሰው ያንን የጎሣ ክብር የሚነካ ክብረነክ ጽሁፍ በተመለከቱት ተማሪዎች  መሆኑን ነው::›› በዚህም የተነሳ 20Addis Ababa University, Ethiopia ተማሪዎች መቁሰላችውንና 3ቱ የጠናባቸው ወደ ሆስፒታ፤ል መወሰዳቸውን በተጨማሪ ሁለቱ የቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡ ሌሎች 20ዎችም በፖሊስ ባልለየለት ውንጀላ ለእስር ተዳርገዋል፡፡
ስለኢትዮጵያ ‹‹የብልሆች መፍለቂያ ከነበረው ዩኒቨርሲቲ›› ይህን ሁኔታ ሳነበው ያደረብኝ ግብታዊ አስተያየት፤ ማመን እስኪያቅተኝ ነበር፡፡ ሳስበዉም ‹‹ይህ ፈጽሞ ሊታመን የሚችል ጉዳይ አይደልም፡፡ ይህ ከኢትዮጵያ አነሮች ትውልድ (ወጣቱ ትውልድ) በዚህ ፈሪነትና የማያስፈራራ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ መግባት ተግባራቸው አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚህ ቆሻሻ እና እጣቢ አተላ የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ከመንደፋደፍ የተሸለና የበለጠ ተግባር ማከናውን ይችላሉ›› አልኩኝ :: ይህን የመሰለ የረከሰ የጥላቻ ምግባር፤የወዲፊቶቹ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን፤የቀጣዩ ትውልድ መምህራን፤ ሳይንቲስቶች፤ እና የፈጠራ ሰዎች ምግባር እንዳልሆነ ነበር እራሴን ማሳመን የሞከርኩት፡፡
ነገሩን የበለጠ ሳጤነው አምአሮ የሚነካና የሚአስቀፍፍ ሆኖ አገኘሁት፡፡ እራሴንም ጠየቅሁ፡፡ ምናልባትስ ይህ የጎሳ ክብር የሚነካ ጽሁፍ በሌሎች የአ አ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  የተፈጠረ ቢሆንስ? ይህን የመሰለው ዝቃጭ፤ወኔቢስ፤ባለጌ ተግባር ስለነዚህ ተማሪዎች ምን ይላል? ስለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችስ? ስለአጠቃላዮቹ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችስ? ስለ መላው የኢትዮጵያ ወጣቶችስ?
ከዚህ ጥየቄ ጋር በመታገል ላይ እንዳለሁ፤ ሊገታ የማይችል ሃፍረትና ውርደት ሰሜት ወረረኝ፡፡ እራሴን ደጋግሜ መረመርኩት፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አእምሮ ያለቸው ተማሪዎች—- የኢዮጵያ አነሮች —- ይህን በመሰል ኋላ ቀር፤ አረመኔያዊ፤ ጨካኝና አሰቃቂ፤ ተናካሽ፤ ተንኮል የተመላበት፤ተግባር አንዴት ሊሰሩ ይችላሉ?  በምን መንስኤ ነው፤ አንድ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ስብስብ ሌላውን ወገን ስብእና ለመድፈር፤ የጋኔን ተግባር ለመፈጸም፤ ዝቅ አድርጎ ለመመልከት፤ አውሬ በማስመሰል፤ አካሄድና ተግባር የሚሰማሩት? ለምን? እኮ ለምን? ለነዚህ ጥያቄዎች አንዳችም ምክንያታዊ ምላሽ ላገኝ አልቻልኩም፡፡
ይህ የ ጎሳ  ጥላቻ ወንጀል የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሰለ አትዮጴያ ወጣቶች ክብርና ወደፊት ላገራቸው ሰለምተበቀባቸው ግዴታ በመፅፈበት ወቅት ነበር :: ሆነ በተባለው የጎሳ ጥላቻ ወንጀል የበለጠ ግራ እየተጋባሁ ሄድኩ፡፡ ይህን አስጠያፊና አስፈሪ፤ ቀፋፊ ሁኔታ በምክንያታዊነት በጥልቀት ለመረዳትና በዚህ አስገራሚ ትርኢት ውስጥ አንዳንድ የኢትዮጵያ አነሮች እንደ ጉማሬዎቹ በመንቀሳቀስ እንደጅቦቹ ለመሆን መከጀላቸው አስገረመኝ፡፡ አሳፈረኝ፡፡ አሳዘነኝ፡፡
ያን ግልብ ስሜቴን ወደ ጎን አልኩና ረጋ ብዬ ማሰብ ጀመርኩ:: ከምር ጠንክሬ አሰብኩ፡፡ ይህ በዩኒቨርሲቲው የተከናወነው ‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተውን አልመግባባት›› ድርጊት ከጥሩ እምነት ካላቸው ሁነኛ መደበኛ ተማሪዎች ተጠንስሶ በስራ ላይ የዋለ ነው  ለማለት ምን ማስረጃ ሊቀርብ ይችላል? በእውነትስ  የተባለውና በዚህ በየግድግዳው ላይ የሰፈሩትን ክብረ ነክ ጽሁፎች የጻፈው ‹‹ተማሪ›› ማነው?  በዚህ ዩኒቨርሲቲ የሙዚቃ ሸክላ አጫዋች መሰል የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ተቀምሞ የተበተነውን መሸንገያ አባባል ማመን አለብን? እንዴት ነው የዩኒቨርሲቲ አስተዳዳሪዎች  ‹‹ለአሰርት ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች ሲከናወኑ የነበሩትን የጎሳ ግጭቶች” ያሳለፏቸውና አሁንም ሲቀጥሉ  አጃቸዉን አጣጥፈው  መመልከት የቻሉት? በዩኒቨርሲቲውስ ውስጥ ምራቃቸውን የዋጡና የበሰሉ፤ችግሮችን ለማክሸፍና ለማግባባት ፈቃደኛ የሆኑ አመራሮች የሉም?
ጥርጣሬ ቀስ እያለ፤ድንጋጤዬንና ሃፍረቴ  መተካት ስለጀመረ፤ የዚህ ‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተ ብጥብጥ›› በገዢው መንግስት ጀብደኛ ባለማዕረግ የተዋቀረና፤ የተተለመ እንደሆነስ የሚለው ጥያቄ አያፈጠጠ ያየኝ ጀመር፡፡ በኋላም የወንጀል መመርመርያ ማስረጃ ማፈላለጊያ “መነጽሬን” ሳደርገው፤ እንደገና በመሹለክለክ ድምጽዋን አጥፍታ ጨለማና ወቅትን መከለያ በማድረግ አንዲት መናጢና ቆሻሻ አይጥ ተንኮሏን ከፈጸመችና ተልእኮዋን ከፈጸመች በኋላ ሳትታይ ጥላው  የሄደችውን የእጇንና የእግሯን አሸራ በግድገዳ ላይ ከተጻፈው አስጠያፊ ጥሁፍ አግርጌ ታትሞ አየሁት፡፡
በሜይ 2010 ጃዋር ሲራጅ ሞሃመድ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሐተታ ሰጪ እንዲሁም የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ እንደዘገበው  በዩኒ ቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ከተማሪዎች ጋር በርካታ ውይይት ካካሄደ በኋላ እንዲሁም በሁለት ክፍል በሃራማያና፤በአዳማ  ዩኒ ቨርሲቲ በ2006 የተከናወነውን ድርጊት  ሰበቡን የአካዳሚክ ነጻነት ማጣትና በኢትዮጵያ የደህንነት ሚስጥራዊ ተቀጣሪዎች ተማሪ በመምሰል ሰርገው በመግባት የግጭቱ መሰሪ ጠንሳሾች መሆናቸውን ለማመን በቅቷል፡፡
ደግሞም በሴፕቴምበር 2011 ላይ በይፋ የዎጣው ማስረጃ አንዳሳየው በሴፕቴምበር 16 2006 “ የኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ 3 ፈንጂዎች መቅበራቸውንና በመፈንዳቱና፤ በወቅቱም የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ የሚካሄድበት ስለነበረ ከረር ያለ ጥያቄ ያስነሳውን  ፍንዳታም ኤርትራንና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባርን ተጠያቂ እንዳደረጉ ነበር::” በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን መንግስት ኤምባሲ ባካሄደው ‹‹የሚስጢር ዘገባ›› በጉዳዩ ላይ የመርማሪዎቹ ጣት  ወደ ኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የደህንነት አባላትን በመጠቆም ለዚህ የወንጀል ድርጊት ተጠያቂ አድርጓቸዋል፡፡
በሌላም በኩል በ2006 የተገኘው ሚስጥራዊው ባለ 52 ገጽ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተዘጋጀው ሰነድ፤ የዲያስፖራው ዳይሬክቶሬት በዲያስፖራው ያሉትን የተቃዋሚ ሃይላትና አባሎቻቸውን የሚነዘንዝ፤ በሃይማኖት፤ በዘር፤ በፖለቲካ ጥላቻ የሚከፋፍልና ማንኛቸውንም ገዢውን ፓርቲ የሚቃወሙትን ለመከፋፈልና በመሃላቸው መግባባት እንዲጠፋ ያደረገው ጥረትና ዝግጅት ተጋልጦ ነበር ፡፡ ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጋጣሚ በይበልጥ ባሰብኩ ቁጥር፤የገዢው መንግስት ተቃዋሚዎችን ለማስጠላት ለመከፋፈል ለመበታተን ለማክሸፍ ብሎ የሚዘራውን ቆሻሻና የብልግና ባህሪ ያጋልጡት ጀምረዋል፡፡
በተጨባጭ ምርምሬ አንደተርዳሁት ‹‹በጎሳ ላይ ለተመሰረተው ግጭት›› ወንጀል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  ተጠያቂው ማን እንደሆነ ግልጽ የሆነው ማስረጃ  የሚጠቆመው ወደ ተለመዱት ወንጀል ፈጻሚ የገዢው መንገስት ወንጀለኞች ነው፡፡
ሊታለፍ የማይችለው መደምደሚያም፤ (ሌላ ተቃራኒ  ማስረጃ  እስካልቀረበ ድረስ) በጃንዋሪ 2 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለተፈጸመው ወንጀላዊ  ተግባር ተጠያቂዎቹ፤ በግቢው ውስጥ በድብቅ የተቀመጡት መዘዝ ፈጣሪዎችና ምግባረ ብልሹ ሕሊና ቢስ  ወኪል ተንኳሾችና ደባ ፈጻሚዎች እንጂ ጨርሶ ለጥሩ ዕምነት የተፈጠሩት ወጣት አቦሸማኔዎቹ የነገ የሃገር አለኝተ ዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የማጠቃለያው ግምገማም ይህንን መደምደሚያ የማያጠያይቅ ማስረጃ በመሆን ያረጋግጠዋል፡፡ ያለዉን ማስረጃ በጥቂቱ ብንመለከተው: በመጀመርያ እንድ ብቸኛ “ተማሪ”ብቻ ነው ድርጊቱን በመተንኮሱ  የተወነጀለው፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪዎች በአንድ ጎሳ ስር ተቧድነው ለዚህ ድርጊት መንቀሳቀሳቸውንና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላም ለማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም፤ መደራጀታቸውን ተአማኒነት ያሳጣዋል፡፡  ይህን እንቅሳቃሴ ለመጀመርና መነሻ ሆነ የተባለውም ብቸኛ “ተማሪ” የየት ጎሳ አባል እንደሆነ በግልጽ አልተረጋገጠም፡፡ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት: ስምና መለያው ያልታወቀ፤ አንድ ተማሪ በማለት ወንጀለኛ ብለውታል፡፡ ይሁንና ይህ ‹‹ተማሪ›› ዓላማ ያለው እርገግጠኛ  መደበኛ “ተማሪስ” ነው? ወይስ ተቀጣሪ ነገር ቆስቋሽ የስለላ ድርጅት ወኪል ግን እንደተማሪ ተመሳስሎ ተወሻቂ አባል (የቀበሮ መንኩሴ በግ መሃል ይጸለያል አንደሚባለው ሁሉ ) ነው? ይህስ ተማሪ በዘር ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ባሕሪ ግለ ታሪክስ ያለው ነው?
ሶስተኛ፤ በሶስት ቦታዎች ማለትም በላይብረሪ፤ በመጻሕፍት ቤትና በተማሪ  መኝታ ቤት ይህን መሰሉን የጎሳን ክብር የሚያዋርድና የሚያንቋሽሽ ጽሁፍ ለመጻፉ ምንም የተጠቀሰ ማስረጃ የለም፡፡ በጥላቻ ወንጀል ድርጊት፤ እንዲህ መሰሎች የጥላቻና የማዋረድ ተግባር ያለባቸው ጽሁፎች ሲጻፉ ዓላማቸው አንድን የጎሳ አባል የሚመለከቱ ሲሆኑ፤ ኢላማ የተደረጉት ግለሰብም ይሁን ቡድኖች ሊደርሱበትና ሊያዩት በሚችሉት ስፍራ ይሆናል እንጂ የግል ጥላቻውንና ብሶት ጣውን  ከተለያዩ ብዙ ጎሳዎች የመጡ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ የማይመለከታቸውም እንዲመለከቱት ለምን ይደረጋል?
አራተኛ፤ ከዚህ አስቀያሚ  የግድግዳ ጽሁፍ ሌላ ማስረጃ ሊሆን የሚችል አንዳችም ነገር ከዚህ የችግሩ ጠንሳሽ በተባለው ‹‹ተማሪ›› ላይ አልተገኘም፡፡
አምስተኛ፤ በጃንዋሪ 2 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመው ደባ የተለየ ሁኔታ ሆኖ ሊታይ አይችልም፡፡ ላለፉት በርካታ አሰርት ዓመታት ይህን መሰል በጎሳ ላይ ተመሰረተ አምባጓሮ ይነሳ እንደነበር የማያጠያይቅ ነው፡፡ ለምንስ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት ጉዳዩ ሲያቆጠቁጥ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ለዚህ ከመብቃቱ ቀደም ብለው አላከሸፉትም፡፡ ድርጊቱ በአስከፊና ሊቀለበስ ወደማይችልበት ሁኔታ ከደረሰና አዳገው ሁሉ ከተከናወነም በኋላ በሌሎች ተማሪዎች ላይ አመጹ ተስፋፍቶ እንዳይቀጥልም ባለስላጣናቱ የወሰዱት እርምጃ የለም፡፡
ስድስተኛ፤ በነጻ አካላት ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ከመጣራቱስ አስቀድመው የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት “አመጹ የተጀመረው በግድግዳዎች ላይ የተጻፈውን ምግባረ ብልሹና ጎሳን የሚያንኳስስ ጥሁፍ ያዩት ተማሪዎች ነው በማለት ለምነስ መግለጫ አወጡ? ጉዳዩን ከመሰረቱ አንስተው የሚያጣሩ ገለልተኛ ወገኖች በማዋቀርና በመመርመር ለወዲቱ ይህን መሰል ድርጊት በድጋሚ እንዳይከሰት ማድረግ የሚቻልበትን ዘዴ ለምን አልቀያሱም? የዩኒቬርሲቲው ባለስልጣናት ጉዳዩን እራሳቸውን ከተጠያቂነትና ከሃላፊነት በማግለል ለፖሊስ ሙሉ በሙሉ ለምን አስረከቡት? ምናልባት በዩኒቨርሲቲው የሚከሰተውን የጎሳ ጥላቻ ወንጀል ቸል ያሉት አይታችሁ እንዳላየ ሁኑ የሚል መመርያ ስለተሰጣቸው ይሆን?
ሰባተኛ፤ የዚህ የጥላቻ ብጥብጥ ወንጀል ተጠቂ የሆኑትስ በፖሊስ ለመደብደብ ለመያዝና ለመታሰር ለጉዳት ለምን ተዳረጉ?
በአጭሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመው የጥላቻ ወንጀል የቀረበው ሁኔታና ማስረጃ ጨርሶ ወደ ተከሳሾቹ ተማሪዎች ጣት አያመላክትም፡፡ ይልቁንስ ያአመልካች ጣት በወንጀለከኝነት የሚጠቁመው ወደ ከሳሾቹ ነው፡፡ የዚህን የጥላቻ ወንጀል ፈጻሚዎች ለማጣራትና ለመያዝ የሚያስፈልገው፤ ያንን የግድግዳ ላይ ጽሁፍ የከተቡትን የማይታዩ ጣቶች ብቻ ሳይሆን  እነዚያን ተማሪዎቹን እስኪጠወልጉ ድረስ የቀጠቀጡና ያሰቃዩ፤ ከዚያም በረጩት የአመጽ ነዳጅ ላይ እንዳይጠፋና የበለጥ እንዲቀጣጠል ንዳድ የረጩበትንና የጎሳ ግጭቱን ያቀጣጠሉትን፤በተማሪዎች መሃል ጥላቻ  ንትረክና ዉዝግብ አንድፈጠር የሚዶልቱ ወንጀል ጠንሳሶች ነው፡፡
ያም እንዳለ ሆኖ፤አሁን ወቅቱ ነው፤ አስፈላጊው ወቅት ነው፤ትክክለኛው ጊዜ ……..
የማገገሚያጊዜ፤የመቀበያውየመተቃቀፊያ  የእርቀሠላምጊዜ አሁን ነው
በክዱስ ጽሁፍ እንደሰፈረው፤ ‹‹ለማንኛውም ሁኔታ ወቅት አለው፤ከሰማይ በታች ላሉት ነገሮች ሁሉ  ለየምክንያቱ ጊዜ አለው::›› ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለሃዘንም ወቅት አለው፤ ድንጋይ ለመወርወርም ጊዜ አለው፡፡ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፡፡ እንዲሁም ለመተቃቀፍም ጊዜ አለው ለሠላምና ለማገገምም ጊዜ አለው፡፡ ለእርቀሰላምም  የራሱ ጊዜ አለው፡፡
አሁን ነው ጊዜው፤ — ትክለኛው ጊዜ– ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በትምህርት ቤቶች፤ በዩኒቬርስቲዎች፤ በስራ ቦታዎች፤ በአጎራባች መንደሮችና በመንገድም ላይ  የማገገሚያው ወቅት፡፡ ጊዜው—– ትክክለኛው ጊዜ—- የኢትዮጵያ ወጣቶች በወንድማማችነት በአህትማማችነት ስሜት መተቃቀፍ  መተሳሰብ እጅ ለእጅ በመያያዝና አንድ በመሆን ብዛታቸውን  ለቅድመአያቶቻቸው ክብርና ለታሪካቸው መከበርያ ማድረግ የሚገባቸው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የጎሳ ጥላቻን  የብጥብጥን አዙሪት የመበጠሻ ጊዜው አሁንነው:: አላስፈላጊውን የቅሬታ ልምድ የማክተሚያ፤ የፍርሃትን ባህል፤ ጥላቻን፤ አውልቆ የመጣያው ትክክለኛው ጊዜው አሁን ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጣቶቻቸውን በማቆላለፍ እጅ ለእጅ በመያያዝ የፍርሃትን እከክ ማራገፊያቸው፤ ጥላቻን፤ግጭትን፤ከልባቸው ፤ ከሕሊናቸው፤ ከመንፈሳቸው አውጥተው መጣያ ጊዜያቸው አሁን ነው፡፡ ጓደኞቻቸውንና የትምህርት ባልደረቦቻቸውን እንደጠላትና  ባላጋራ መመልከትን ማቆሚያቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡
ሰላም ፈጥረው እርስ በርሳቸው እንደወንድምና እህት የሚተቃቀፉበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብልህና ምርጦች አንድ ላይ በመስራትና በመተጋገዝ የተሸለን ነገ ለመፍጠር የሚችሉበት፤በረጋና ጠንካራ በሆነ የሕግ የበላይነት ላይ፤ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ የተከበሩበት አማራጭ ሂደቶች ያሉበት መትለሚያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት ‹‹ከጠላት ጋር ሠላምን መፍጠር ካስፈለገህ፤ከጠላትህ ጋር ተጓድነህ መስራት አለብህ፤ ያን ጊዜ ጠላትህ ወዳጅህ ይሆናል::›› እነዚያን ጠላት የምንላቸውን ወንድምና አህት አብሮ ተማሪዎች  ና ወዳጅ ማድረጊያ ጊዜው አሁን ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ግቢያችን ውስጥና ከግቢያችንም ውጪ ጥላቻንና የጥላቻ ወንጀልን ለማጥፋት መተባበርያው ጊዜ አሁን ነው፡፡
ከሕሊናችንና ከመንፈሳችን ውስጥ የጥላቻ ቋጠሯችንን ማጥፊያው፤ የፍርሃትን ሰንሰለትና ካቴና መበጠሸውጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫና እራሳቸውን ለማላቀቅና ነጻ ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ቆንጨራውን በመቅበር ለአንድዬና ለመጨረሻው ጊዜ ‹‹አሻፈረን! አንዳችን ሌላውን የዚህ ወይም የዚያ ጎሳ ስለሆንን ለመጠላላት አሻፈረን፤ እምቢ! መባያችን ጊዜው አሁን ነው፡፡ አሻፈረን! ምክንያቱም ሁላችንም በተለያየ ስም በምንጠራው የጋራችን በሆነው አምላክ ስር አለያም የሁላችን በሆነችው ሀጋራችን የተለያየ ማእዘን ነዋሪዎች ነንና፡፡ እምቢ! በምንም መልኩ ለመጠቀሚያነትና እንደ አሻንጉሊትነት ሆነን በሚጠቀሙብን ለጥላቻ ለእርስ በርስ መቆራቆስ መጠቀሚያ አንሆንም፤ እምቢኝ! የሠለጠንን ነንና ለጥላቻ አንሰለፍም፡፡ አዳኝ እንደሚያሳድደው የሚታደን አውሬ ለመሆን እምቢኝ!
ከአንድጉማሬጥቂትቃላትለበርካታዎቹአቦሸማኔዎች
በርካታ አቦሸማኔዎች ምናልባትም ጉማሬውን ትውልድ ማዳመጡ ያስገርማቸው ይሆናል፡፡
እኛ ጉማሬዎች ‹‹በዕውቀት የተጋረድን›› ‹‹ራዕይ የጎደለን››  ‹‹የራሳችን ምንጭ እስካልደረቀብን ድረስ ጠቅላላው ሃገር ቢደረማመስ ደንታ የሌለን ›› ነን ተበለን አነታወቃለን:: ያም ሆኖ ወጣቱን ትውልድ  በአክብሮት እባካችሁ ጆሯችሁን አውሱኝና ለመደመጥ እድል ስጡኝ እላለሁ፡፡
ጀግኑ!
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ እራሳችሁን ከሰንሰለቱ ነጻ በማድረግ ካለፈው የጫና ሰቆቃ እኛንም አራሳችህሁንም ለማላቀቅ ብቁ፡፡
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ ታሪካዊ ጥላቻን፤ ቅሬታን በማጥፋት፤ መግባባትንና መቻቻልን በማምጣት አዲስ እርቀሰላም በኢትዮጵያ ታሪክ ጀምሩ፡፡
የጥላቻን ቁስል ለማዳን የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ለዘመናት ያመረቀዘውን በማጥፋት ለመጪው ትውልድ ያለፈው ትውልድ ስህተትና ጥፋት እስረኞች እንደማይሆኑ አረጋግጡላቸው፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ሁላችንም በእኩልነት የሰው ዘር አባላት በመሆናችን ይህንንም በጎሰኝነት ለማቀደም ብለን አዘቅት አንውረድ ::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አንደኛችን ለሌላው ይቅርታን በመቸር ለአንድዬና ለመጨረሻ ጊዜ ቆንጨራውን በመቅበር፤ ጣቶቻችንም የጠመንጃ  ቃታና ምላጭ ለመሳብ፤ጣቶቻችን የጥላቻ መነሾ የሆኑ ቃላትን በየግድግዳው ላይ ለመለቅለቅ ሳይሆን እጆቻችን የሚዘረጉት የመግባባት የመተሳሰብ ሰላምታ ለመለዋወጥና ለችግርም ይሁን ለደስታ እጅ ለመዋዋስ ብቻ አንድሆን ማረግ ያሻል፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የተለያዩት እምነቶቻችን መለኮታዊነታቸውን ማረጋገጥ እንቻል::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አሻፈረኝ! አምቢ! በማለት ውስጥ ውስጡን ከሚበላን የጎሳ የሃይሞነት የጻታ ልዩነት በተቃርኖ እንቁም::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን በመኝታ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍት፤በመጸዳጃ ቤቶችም ያሉትን አስነዋሪና በታታኝ፤ ጎሰኝነትን የሚያቅራሩ ቃላታን በእርቀሰላም፤ በመግባባት፤ በውህደት፤ በፍቅር አሰባሳቢ ቃላቶች እንሸፍናቸው፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የወደፊቷ ሃገራችን መሪ ሻምበሎች እናንት ኩሩ አቦሸማኔዎችእንጂ፤ የደከሙት፤ሙሰኞቹ፤ ምግባረብልሹዎቹ፤ እራሳቸውን የሚያስተናግዱ ጉማሬዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን  ለመሆን የምትመኘውን ሁሉ በመሆን፤ለመሆንም ለማሰብ ቀደምት አንሁን፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን  የትላንቱን የመረረ ስሜት በዛሬውና በነገው ጣፋጭ እርቀሰላም፤ መግባባት፤ አንድነት፤ መሰረት ላይ መልሳችሁ አዋቅሩት፡፡
የሃቅ ወቅቱ ደርሷል፡ አቦሸማኔዎቹ እራሳቸውን በማዳን ለእኛም መድህን ይሆኑን ይሆን ?
ለኢትዮጵያ ምርጡና ብሩሁ የሃቅ ወቅት ደርሷል!
የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫናና መከራ እራሳቸውን በማዳንና የጎሳ መጎጃጃ፤ የሃይሞነት አክራሪነትን  የጨቋኝ ስጦታ በመጣል እራሳቸውን ማዳን ይችሉ ይሆን?
እነዚህ አቦሸማኔዎች ተጠራጣሪዎቹን፤ የመሸጉትን ምስኪን ጉማሬዎች ከራሳቸው ነጻ ያወጧቸው ይሆን?
ከጎሳ መቆራቆስ ወደ ጎሳ ፍቅር፤መቻቻል አንድነት፤ መግባባትን ያበቁን ይሆን?
አቦሸማኔዎቹ ስብእናችንን ከጎግፍ ማነቆና ከአውሬ አስተሳሰብ ያላቅቁን ይሆን?
አቦሸማኔዎች የእርቀ ሰላምን ጥበብ ያስተምሩን ይሆን? በእርቀሰላም ቋንቋ ያናግሩን ይሆን?
የኢትዮጵያ ብልህና ብሩሆች አንድ የወጣት ግብረሃይል በመሆን 2013ን የአቦሸማኔዎች ዓመት ያደርጉት ይሆን? አንድ ላይ በመቆም የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ በመስበር የወገንተኛነትን ጎራዴ በማቅለጥ የእርቀሰላምን ሙሉነት ያስመርቱን ይሆን?
የአላንዳች ጥርጥር አዎን ይቻላቸዋል!
ባለፈው ሳምንት 2013 የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ዓመት ብዬ ስተነብይ፤  የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ ለማዳረስ፤ለማሳመን ቃል ገብቼ ነበር፡፡ አኛ ጉማሬዎች አቦሸማነዎችን አናስተመራለን የሚል አምነትም ነበረኝ:: ጉማሬዎችን አቦሸማኔዎችን ያስተምራሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር::  ለዚህ ነው እኛ ጉማሬዎች ግራ የተጋባ ሸውራራ (የተዛባ አመለካከት) ቅርብ አዳሪነት፤ጠባብ አስተሳሰብ፤ የምያጠቃን::  ለአቦሸማኔዎች የማስተማርያ ወቅት ሊኖር ስለመቻሉ ጥርጣሬዬ የመጣው::
ስለዚህም የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና ጉማሬዎች በርካታ ግብግቦች የሚገጥሟቸው፡፡ የአቦሸማኔዎቹ ፈታና ጉማሬዎቹን የእርቀሰላምን ጥበብ ማስተማሩ ላይ ነው፡፡ የጉማሬዎቹ ፈተና ደግሞ ከአቦሸማኔዎች የእርቀሰላምን ጥበብ መማሩ ላይ ነው፡፡
አቦሸማኔዎች ታሪካዊ ገድል የመፈጸም እድል ቀርቦላቸዋል፡- ይሄዉም በምሳሌነት ማስተማር፡፡
በአዲስ አበባው ዩኒቨርሲቲ አጋጣሚ የተሳተፉትን፤ ወዳዳጆቻቸውንና ሌሎቹም ጭምር በግቢያቸው የተፈጸመውን አስጸያፊ የግጭት ሁኔታና ሁከት አስመልክቼ የማቀርበው ጥሪ ሁኔታውን ወደ ውብና ያማረ ፍቅርና ሰላም የሞላበት ፍሬያማ ውጤት ለማምጣት የአንድነት አውድማ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ወደ ሌላው በመቅረብ ይቅርታን እንዲጠይቁና እንዲቀባበሉ እጠይቃለሁ፡፡ አንዲት በጣም ትንሽ የሆነችውን ‹‹ይቅርታ›› የምትለውን ቃል ለመተንፈስ ወኔ ይጠይቃል፡፡
በራሳቸው ውህደት እንዲፈጥሩ እጠይቃለሁ—-አንድ ለአንድ፤ በትንሹና በበርካታው ስብስብ—–ልዩነታቸውን ይወያዩበት ይነጋገሩበት ይምከሩበት፡፡ አንደኛቸው የሌላው ጉዳትና ግፍ ይሰማው፡፡ አንዱ የሌላው ፍርሃትና ጥርጣሬ ይሰማው:: አንዱ ለሌላው እንባ ንቀት አይኑረው፡፡

በብሩህ ህሊና፤ በንጹህ ልቦና፤ አእምሮና መንፈስ ሊነጋገሩ ግድ ነውና ይህንንም እጠይቃለሁ፡፡
እያንዳንዳቸው የሌላውን ስሜትና ጥርጣሬ እንዲረዱ እጠይቃለሁ፡፡ በጓደኞቻቸው ጫማ ውስጥ ሆነው ለኪሎሜትር  እንዲራመዱ እጠይቃለሁ:: በመጫሚያም ይሁን በባዶ እግራቸው ፈገግ ሊያሰኛቸው የሚችል ሁኔታ ያጋጥማቸዋል፡፡
የኢትጵያ አቦሸማኔዎችን 2013ን የእርቀሰላምና የሰላም ዓመት እንዲያደርጉት እጠይቃለሁ፡፡
ጃንዋሪ 2 1013 በታሪክ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ፤የሃይሞነት ወገንተኝነት፤ የጾታ ልዩነት የተቀበሩበት ዕለት ሆኖ ዘወትር አንድታሰብ ይሁን፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው አስጸያፊ ሁኔታ ለሕዝብ ማስተማሪያነት ያገልግል፡፡
ጥንካሬን ከችግር ወልዳችሁ፤ አንድነትን ከከፋፋይ ተምራችሁ፤ ከጓደኞቻችሁ ተማሪዎች ጋር ለመደማመጥና የመግባባትን፤ የመቻቻልን፤ የውህደትን ዘር ለማፈስ እንድትበቁ እማጸናችኋለሁ፡፡
የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ጉማሬዎችን እንደመሩ እጠይቃለሁ፡፡ እኛን አትከተሉን፤መሄጃችንን አናውቀውምና፡፡እኛ የጠፋው የጉማሬ ትውልዶች ነን፡፡
ይህን ግብግብ በመቀበል፤ትክክለኛውን እንደትክክል፤ስህተቱንም ወደ ትክክለኛነት ካልለወጣችሁት፤ አቦሸማኔዎች በስልጠና ላይ ያሉ ደካማ ጉማሬዎች ናቸው የሚል ትችት ላይ መውደቅ ይመጣል::
ለሁሉም ጊዜ አለው::   ለኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች፤ ለማገገምና ለእርቀሰላም ሰዓቱ አሁን ነው፡፡
የኔ ጥያቄ ለእዮጵያ ወጣቶች  ይህ ነው:-  አሁን ስንት ሰአት ነው!?!
የተባበሩት የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ፈጽሞ ለውድቀትና ለሽንፈት አይዳረጉም!

ሰበር ዜና፡ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል

(ከአዘጋጁ፡ ውድ የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አንባቢዎች በቤተክርስቲያን ሰላም እና አንድነት እንዲመጣ የተለያዩ ዘገባዎችን
ስናቀርብ ቆይተናል። በርከት ያሉ አንባቢዎቻችን በምናቀርባቸው ዘገባዎች ያላቸውን ማበረታቻ ስለለገሱን
እናመሰግናለን) ከሁለት ሰዓት በፊት በሰበር ዜናችን አቶ አባይ ጸሐዬ በስደት ያለውን ሲኖዶስ በአሸባሪነት
መንግስታቸው እንደሚከስ መናገራቸውንና የቅዱስ ሲኖዶሱም አስቸኳይ ስብሰባ ለሰላምና ለአንድነቱ መፍትሄ
የማይሰጥ ውሳኔ በማሳለፍ የዛሬውን ውሎ ማጠናቀቁን መዘገባችን ይታወሳል። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አሁንም በዚህ
ዙሪያ ጠለቅ ያለ መረጃ እንዲኖራቸው በማሰብ ወደ ሃገር ቤት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎችን ወደ ምንጮቻችን
ስናደርግ ቆይተናል። ምንጮቻችን ያደረሱን አዲስ መረጃ ቢኖር “የሰላምና የአንድነት ፍጻሜው እልባት ካገኘ በኋላ
ውጭ ሃገር ከሚገኙት አባቶች ጋር በጋራ የፓትርያርክ ምርጫውን እናድርግ በሚለው አቋማቸው የጸኑት የቅዱስ
ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል (ፎቶ) አባይ ጸሐዬና ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም የተገኙበትን ስብሰባ
ረግጠው መውጣታቸው ነው። የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ እዝቅኤል ስብሰባውን ረግጠው ለምን እንደወጡና
የልዩነት አቋማቸውን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንደሚናገሩ ዝተዋል የተባለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት
በከፍተኛ የደህንነቶች ክትትል ሥር እንደሆኑ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።)
ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን አሁንም ተከታትላ አዳዲስ መረጃዎችን ለአንባቢዎቿ ታቀርባለች።

Marathon runner Shumye dies in car crash


(Iaaf News ) Ethiopian marathon runner Alemayehu Shumye died
in a car crash on Friday (11). He was 24.
His marathon career began in 2008 with much promise and in his
first three races at the distance he won in Vercelli, Warsaw and
Beirut.
His lifetime best, 2:08:46, was set at the 2009 Frankfurt
Marathon where he finished fifth. His most recent Marathon
victory came at last year’s Gold Coast Marathon.
Shumye competed just six days before the car crash, finishing
10th in Xiamen with a time of 2:12:57.

አምባሳደር ስዩም መስፍን ቻይና በአካባቢ ውድመት ላይ የሚቀርብባትን ክስ መከላከል አያስፈልጋትም አሉ


አምባሳደር ስዩም መስፍን ቻይና በአካባቢ ውድመት ላይ የሚቀርብባትን ክስ መከላከል አያስፈልጋትም አሉ

ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የቻይና አምባሳደር ስዩም መስፍን ከሲሲቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ቻይና በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ማእድናትን በምታወጣበት ጊዜ የአካባቢ ውድመት ታደርሳለች እየተባለ በአፍሪካውያንና በምእራባዊያን ዜጎች የሚደርስባትን ወቀሳ መከላከል አያስፈልጋትም ብለዋል።ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
አምባሳደሩ ይህን መልስ የሰጡት የሲሲቲ ጋዜጠኛ ” ብዙውን ጊዜ አገራችን በሌሎች አገሮች ማእድናትን ስታወጣ የአካባቢውን ህዝቦች ታፈናቅላለች፣ በአካባቢውም ላይ ውድመት ታደርሳለች እየተባለች ትወቀሳለች፣ ይህ ችግር በኢትዮጵያም ውስጥ አለ?’ የሚል ጥያቄ ካቀረበላቸው በሁዋላ ነው።
አምባሳደር ስዩም መስፍን ሲመልሱ ” ቻይና የአፍሪካን ማእድን ለማልማት እዚህና እዛ ለሚቀርብባት ወቀሳ ራሱዋን መመከላከል አያስፈልጋትም፣  የእኛ ነባር ወዳጆች እኮ ይህንኑ ለዘመናት ሲያካሂዱ ነበር” ብለዋል።
“የምእራባዊያን ኩባንያዎች ማእድናትን በአፍሪካ ውስጥ አውጥተው በተወሰነ ደረጃ ቀይረው ወደ ወደ አውሮፓ ሲልኩ ቀረጥ ይከፍላሉ፣ ማእድናትን እንዳለ ሲልኩ ግን ቀረጥ አይከፍሉም ይህ በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ እንዱስትሪ ላይ እድገት እንዳይኖር አድርጓል” የሚሉት አምባሳደር ስዩም  ቻይና ይህንን እስካልኮረጀች ድረስ በአካባቢ ውድመት ዙሪያ ለሚደርስባት ክስ ትኩረት መስጠት እንደማይገባት መክረዋል።
ጋዜጠኛው ” ቻይናዎች ጥሩ ምክር ከእውነተኛ ወዳጅ ይገኛል ይላሉ” በማለት በአምባሳደር ስዩም መስፍን መልስ መርካቱን ገልጿል።
ቻይና በአፍሪካ ውስጥ ማእድናትን ፍለጋ በምታካሂደው እንቅስቃሴ በአካባቢ ላይ ጉዳት ታዳረስላች ለህዝብ መፈናቀልና ችግር ትኩረት አትሰጥም በማለት ወቀሳ እንደሚቀርብባት ይታወቃል።

Total Pageviews

Translate