Pages

Mar 28, 2013

እስር ቤቶቻችን በሕገ-መንግሥት ወይንስ በ‹‹ሕገ-አራዊት››?




ምንጭ፣ ዞን ዘጠኝ ጦማር
በጌታቸው ሺፈራው
 የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትን እንዲጸድቅ በበላይነት የመሩት አቶ መለስና አቶ ሌንጮ ለታ መሆናቸው ይነገርላቸዋል፡፡ ይህ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ባልሆኑት የተገንጣይ መሪዎች ጠንሳሽነት የጸደቀው ሕገ መንግሥት ለአገር ሉኣላዊነት፣ አንድነትና ታሪክ ክብር የሌለው ቢሆንም ዓለማቀፋዊ የሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አጠቃልሏል፡፡ ሆኖም እነዚህ ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለእርዳታ ማሰባሰቢያ የተቀመጡ እንጂ ወደመሬት ወርደው ተግባራዊ መሆና ባለመቻላቸው የይስሙላህ ሕግ ሆኗል፡፡ ከሕገ መንግሥቱ ይልቅ የገዥዎች ጊዜያዊ ሥልጣን ጥቅም ለማስጠበቅ በየጊዜው ትርጉሙ የሚቀያየረው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ‹‹መርሕ›› ሕዝብ ላይ የተጫነ ገዥ ሕግ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይህን ስርዓት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ‹‹ሕገ አራዊት›› ሲሉ ይገልጹታል፡፡ በዚህ ስርዓት ሕዝብ በሕግ ስም እንጂ በሕግ የሚዳኝበት አጋጣሚ አይታይም፡፡ ብዙዎቹ በዚህ ስርዓት ያለውን የኢትዮጵያን ሕዝብም የታሰረ፣ ታስሮ የተፈታና ለወደፊት የሚታሰር እያሉ በቀልድ መልክ በሦስት የእስራት ምድብ ያስቀምጡታል፡፡ እንደ እኔ ሌላ አራተኛ ምድብም ሊካተት ይገባዋል፡፡ ይኸኛው እንደ ሦስቱ ምድቦች የአካል ጉዳትና ሰብኣዊ መብት ጥሰት የማይደርስበት ሕገመንግሥቱን አጽድቆ ራሱ የሚጥሰው አሳሪው ክፍል ነው፡፡ ይህ አሳሪው የኅብረተሰብ ክፍል በአካል ያልታሰረና ስርዓቱ እስካለ ድረስ በአካል ሊታሰርበት የሚችለው አጋጣሚ ጠባብ ቢሆንም የአዕምሮ እስረኛ ነው፡፡
ኢሕአዴግ እየዘመረለት የሚገኘው አቶ መለስና በእኩል ደረጃ የሚያወግዘው ‹‹አሸባሪው›› አቶ ሌንጮ ያጸደቁት ሕገ-መንግሥት ኢትዮጵያውያን ታሳሪዎች ምቹ ሁኔታ እንዲመቻችላቸው በርካታ አንቀጾችን አስቀምጧል፡፡ ለአብነት ያህል አንቀጽ 19 (2) የተያዙ ሰዎች ላለመናገር መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) ‹‹የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይንም ማንኛውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡›› ቢልም በተለያዩ ጊዜያት የተሰሩ የፕሮፖጋንዳ ፊልሞች ላይ ‹‹እማኝነታቸውን›› የሰጡ ታሳሪዎች የሚሰጡት ቃል በኃይል የተደረገ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
መጋቢት 8/2005
ይህን እውነታ እሁድ መጋቢት 8/2005 ‹‹ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መሰጠት የአባቶቻችንን መስዋዕትነት ማራከስ ነው›› በሚል የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ እኔና ጉዋደኞቼ በታሰርንበት ወቅት ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ አንድ ታሳሪ ከአንድ ጊዜ በላይ ቃል መስጠት እንዳለበት የሚገልጽ የሕግ አሠራር ባይኖርም ከሶስት እስከ አራት ጊዜ ቃል እንድንሰጥ ተደርገናል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ሁሉም ሕገ መንግሥቱ ‹‹ሰጥቶኛል›› ያለውን መብት ተጠቅሞ ‹‹ቃል አልሰጥም›› ብሎ ፊርማውን አስቀምጦ ወጣ፡፡ በዚህ የተደናገጡት መርማሪዎች አንዳንዶቹን ቃል እንዲሰጡ ቢያባብሉም ሊሳካላቸው አልቻለም፡፡ በታጎርንበት ጣቢያም ሆነ በሌሎቹ ጣቢያዎች የፖሊስ አባል መሆናቸው ያልታወቀውና ከመጀመሪያው ጀምሮ ሰልፉን የበጠበጡት ‹‹ኮማንደር›› ግን ‹‹ይህ ፒቲሽን በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል›› በሚል መርማሪዎች የቻሉትን ሁሉ ተጠቅመው ቃል እንዲቀበሉን ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ሆኖም ሁሉም ታሳሪዎች ቃል ሳይሰጡ ቀሩ፡፡ ይህን ተከትሎም የይስሙላህ ሕገ መንግሥቱ ተግባር ላይ የዋለው ለተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ ሆነ፡፡
ቃል አንሰጥም ካልንበት ወቅት በኋላ ለጥቂት ጊዜ ጠፍተው የቆዩት ‹‹ኮማንደር›› ታሳሪዎች በእየተራ ፎቶ ግራፍና ቪዲዮ እየተቀረጹ ሌላ ተጨማሪ ቃል እንዲሰጡ አደረጉ፡፡ ይህን ምርመራ የሚያከናውኑት ፖሊሶች ሳይሆኑ ደህንነቶች በመሆናቸው ቃል አልሰጥም የሚለው መብት አይሰራም፡፡ ተመርማሪው ገና ከመግባቱ ስድብና ዘለፋ ይገጥመዋል፡፡ ከእነኮማንደር በሚደርስ ቅድሚያ ፍረጃ አንዳንዶቹ ለቃል ከመግባታቸው ዱላ ጠብቋቸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ብሄራቸውን ሲጠየቁ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› በማለታቸው ዱላና ዱላ ቀረሽ ስድብና ዘለፋ ገጥሟቸዋል፡፡ አንዲት የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ወጣት ከደህንነቶቹ በደረሰባት ድብደባና አስጸያፊ ዘለፋ እራት መብላት አልቻለችም፡፡የባሰው ደሞ ቅዳሜ መጋቢት 7 ቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩ ወጣቶች የደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ነው፡፡ ተክለሀይማኖት አካባቢ ታስረው የነበሩት መካከል አንደኛው ብሔሩን ‹‹ኢትዮጵያዊ›› በማለቱ ይመረምረው የነበረው ደኅንነት ከመደብደብ አልፎ በሽጉጥ አስፈራርቶ መረጃ እንደጠየቀው አውግቶኛል፡፡
ቃል ስንሰጥ ከተጠየቅናቸው ጥያቄዎች በተጨማሪ የኢሜልና የፌስ ቡክ አድራሻና የይለፍ ቃል በግድ ተቀብለውናል፡፡ ‹‹በምርመራው›› በ1997 ዓ/ም ማንን እንደመረጥን ተጠይቀናል፡፡ መልሱን ከመመለሳችን በፊት ደኅንነቶቹ ራሳቸው ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ መምረጣችንን ያለ ጥርጥር እየነገሩ ‹‹አፍራሽነታችን›› የቆየ መሆኑን ለማስገንዘብ ሞክረዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረገው ለሕዝብ ይቆማል በሚባለው ፖሊስ ተቋም ግቢ ውስጥ ሲሆን ፖሊስ በደኅንነቶች የሚሰጠው ክብር ለታሳሪዎች ከሚሰጠው የሚለይ አይደለም፡፡
የተያዙ ሰዎች አያያዝ በፓሊስ ጣቢያዎች
ተግባር ላይ መዋል ያልቻለው ሕገ መንግሥት አንቀጽ አንቀጽ 17(1) ‹‹ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብኣዊ ከሆነ ወይንም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይንም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው›› ቢልም የሚፈጸመው ግን በተቃራኒው ነው፡፡ ስርዓቱ ለይስሙላህ ከሚጠቀምበት ሕገ-መንግሥት በተቃራኒ ‹‹በሕገ አራዊቱ›› እንደሚመራ በደንብ የተረዳሁት ለማሰላቸት ተብሎም ይሁን ለሌላ ዓላማ ከፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ ጣቢያ ሲያዟዙሩን ካመሹ በኋላ ከለሌቱ አምስት ሰዓት ገደማ ቀጨኔ አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ ከገባን በኋላ ነው፡፡ ከታሰርነንበት ጊዜ ጀምሮ በሆነ ባልሆነው በዚህ የወረዳ 9 ጣቢያ በተደጋጋሚ የታሰሩ የባለራዕይ ወጣት አመራሮች እንደተለመደው ለመቀጣጫ ወደዚሁ ጣቢያ ሊወስዱን እንደሚችሉ በእርግጠኝነት ይናገሩ ነበር፡፡ ማታ ላይ ሁላችንም ወደጣቢያው እንድንሄድ ተፈልጎ የነበረ ቢሆንም ቀድሞ በመሙላቱ የተወሰኑት ጃን ሜዳ አካባቢ ባለው የማዘዣ ጣቢያ እንዲያድሩ ተደርገዋል፡፡
በወረዳ 9 ሦስት በአራት የሆነች ጠባብ ክፍል ውስጥ እድሜያቸው 15 አመት የማይበልጥ ህጻናትን ጨምሮ 37 ሰው እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ በእርግጥ ይህ ክፍል እስከ 50 ሰው የሚይዝበት አጋጣሚ እንዳለ ታሳሪዎቹ ነግረውኛል፡፡ በክፍሉ ወስጥ በተነጠፈው ቆሻሻ የወለል ምንጣፍ ላይ ሰው በሰው ላይ ተኝቷል፡፡ ሙቀቱ ከፍተኛ በመሆኑ ብዙዎቹ ራቁታቸውን ናቸው፡፡ አስተባባሪዎቹ ከፖሊስ ቦታ እንዲፈልጉልን በተላለፈላቸው ትዕዛዝ መሠረት በዚህ መተላለፊያ በሌለው ቤት ውስጥ ለመቀመጫ ያህል ቦታ ሰጡን፡፡ ታሳሪ ወጣቶቹም የያዝነውን ገንዘብ እንድናስረክባቸው ጠየቁን፡፡ ተከትሎም ሳንቲም ሳይቀር ያለንን ገንዘብ በሙሉ ተቀብለውናል፡፡ይህ ታዲያ እኛ ወጣቶቹ ላይ ብቻ ሳይሆን ከእድሜ የገፉትም ላይ ተግባራዊ የሆነ ውስጣዊ የታሳሪዎች ህግ መሆኑን ሰምተናል፡፡እንዳስተዋልኩት ከሆነ ይህ ቤት ሰው እንደሰው የማይቆጠርበት ዘግናኝ ቤት ነው፡፡ በዚህ ሰዎች እንደሰው በማይቆጠሩበት ቤት ውስጥ ሰው ሊማር የሚችለው ጭካኔን ብቻ ነው፡፡
እንደገባንም የገጠመኝ ይህ ነው፡፡ በግድግዳው ላይ የተጻፉት ጽሑፎችም የሚያሳዩት ጨካኝ በሆኑት ታሳሪዎች ላይ የሚደርስባቸውን በደል ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ግድግዳው ላይ የተጻፉ ጽሑፎች እስረኞቹ ያለምንም ጥፋት መታሰራቸውን የሚገልጹ ናቸው፡፡ በተለይ ‹‹አገሬ ሆይ ወንድ አይወለድብሽ››፣ ‹‹በደልን ለማን ይነግሩታል››፣ ‹‹አይ ስቃይ››፣ ‹‹ገሃነብ ከመግባት በምን ይለያል››፣‹‹ሰው እንዴለለኝ›› የሚሉት ግድግዳው ላይ የተጻፉ ጽሑፎች የእስረኞችን ምሬት ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ፡፡ በዚህ በደል የተሞላበት እስር ቤት የሚገኙት አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ከጨካኝነታቸው ባሻገር የአእምሮ ችግርና ተስፋ መቁረጥ የሚስተዋልባቸው ናቸው፡፡ በቀጨኔውና በሌሎቹ በተዘዋወርንባቸው ለሰው የማይመቹ እስር ቤቶች ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በተደጋጋሚ እንደሚታሰሩ በየግድግዳው የተጻፉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስም ዝርዝር ምስክር ነው፡፡
በእነዚህ ጨካኝ ቤቶች የሚገኙ እስረኞች ከስርዓቱ እንደሚሻሉ ግን እየቆዩም ቢሆን አሳይተውናል፡፡ በምን እንደታሰርን በነገርናቸው ወቅት ለእኛ የነበራቸው አመለካከት ተቀየረ፡፡ ቀደም ብለው ተደራርበው ተኝተው የነበሩትን በማስነሳት ሰፋ ብሎ ለማስቀመጥ የሚያስችል ቦታን እንድንተኛበት አመቻቹልን፡፡ እስረኞች ጫማና ልብሳቸውን ጨብጠው ነው የሚተኙት፡፡ አልፎ አልፎ ዘመድ ያመጣላቸውን ምግብም ከልብስና ጫማቸው ጋር መደበቅ የግድ ይላቸዋል፡፡ አንድ እስረኛ ሊቀርብለት የሚገባውን ምግብ ባይቀርብልንም የታሰርንበትን ምክንያት ዘግይተው ያወቁት ያች ጠባብ ቤት ውስጥ የሚገኙ እስረኞች በርህራሄ ከጓደኞቻቸው የደበቁትንና ለራሳቸው የቆጠቡትን ቆሎና ጁስ ለእኛ አቅርበውልናል፡፡ በተለይ እነ ዶክተር ያቆብ በእስረኞች ዘንድ ይታወቁ ስለነበር በሌላኛው ክፍል ውስጥ መታሰራቸውን ስንነግራቸው በስርዓቱ ላይ ያማረሩት ብዙዎቹ ናቸው፡፡
ከአንገቱ በላይ ካለው የሰውነት ክፍሉ ውጭ ቀሪው ሰውነቱ ላይ ጓደኞቹ የተኙበት አንድ ወታደር ዶክተር ያቆብና ኢ/ር ይልቃል በቀጣዩ ክፍል መታሰራቸውን ሲሳማ ‹‹ይች ግፈኛ አገር!›› ብሎ እንደገና ተኛ፡፡ ሌላኛው አዛውንት ‹‹ምሁሮቿን ሞባይል ሰርቀው ከተያዙ ሕጻናት ጋር ወለል ላይ እንደዚህ የምታስር አገር የት ትገኛለች?›› ለሚል ጥያቄያቸው መልስ ሳይጠብቁ ‹‹የኢትዮጵያ ምሁራን ክብር ቦታና ፓስፖርት እንደልባቸው ከሚሰጣቸው የሶማሊያ ስደተኞች ያነሰ ሆነ፡፡ አገራችን የጠላት እንጂ የዜጎቿ መኖሪያ አልሆነችም፡፡›› ብለው ተናገሩ፡፡
በዚህ ክፍል ውስጥ የተሻለ ጥንቃቄ ሲደረግለት ያየሁት ሽንት የሚሸናበት የጀሪካን ቅዳጅ ብቻ ነው፡፡ ይህ ጀሪካን ማንም እንዳይጫነው ጥንቃቄ የሚደረግለት ብቸኛው ታሳሪ ነው፡፡ ይህንም የሚያደርጉት ተደራርበው የተኙት እስረኞች የሽንት ማጠራቀሚያውን በሀይል ሲገፉት አሊያም በእንቅልፍ ልባቸው ሲወጡበት በተደጋጋሚ እየተደፋ ቤቱ ስለሚበላሽ ነው፡፡ የሰው ትንፋሽ እና በየቦታው የሚጨሰው ሲጋራ የክፍሉ ሌላኛው አስከፊ ገጽታ ነው፡፡ አብዛኛው እስረኛ ቀን የተወሰነች ሰዓት ተኝቶ ለሌቱን ሌሎች እስረኞች እንዳይጫኑት እየተከላከለ ቁጭ ብሎ ያድራል፡፡ አንዱ በአንዱ ላይ ተደራርቦ ያደረው አብዛኛው እስረኛ በጠባቧ ግቢ ውስጥ ‹‹ሊዝናና›› ሲወጣ ቁጭ ብለው ያደሩት መተኛት ይጀምራሉ፡፡ ሆኖም በየደቂቃው በቆጠራና በሌላ ምክንያት እስረኞች ወደክፍል እንዲመለሱ ስለሚደረግ ሌሊት ከሚደርስባቸው ያልተለየ ችግር ያጋጥማቸዋል፡፡ አንድ ሰው ከፍ ያለ ድምጽ በማሰማቱ አሊያም የመውጫ ሰዓት ደርሶ ፖሊስ ውጣ ሳይለው ሊወጣ በመሞከሩ ክፍሉ እንደገና በቅጣት ተቆልፎ ቤቱ ወስጥ ያለው ሁሉም ሰው አብሮ ይቀጣል፡፡
ዝቅተኛ ካድሬዎች ከመቶ በላይ እስረኛ ከሚታጨቅበት የቀጨኔው እስር ቤት የተሻለ ስፋት ያለው የቀበሌ ቤት፣ ኮምዶሚኒየምና ቪላ ባለቤቶች ናቸው፡፡ ከፍ ያለ ስልጣን ያላቸው ፖለቲከኞች፣ ዘመዶቻቸው፣ የደኅንነት ኃላፊዎች፣ ወታደራዊ አመራሮችና የመሳሰሉት ደግሞ ከሚኖሩባቸው ዘመናዊ ቤቶች በተጨማሪ በሽዎች ብር የሚያከራዩትን ቤት በሕዝብ ገንዘብ ገንብተዋል፡፡ ለሥልጣኑ ሲል ሰዎችን ማሰቃየት አንዱ ስልት ነውና በህግ ጥፋተኝነታቸው ያልተረጋገጠ ታሳሪዎች ወለል ላይ እግራቸውን ዘርግተው የሚተኙበት እስር ቤት ለመገንባት ፍላጎት ያለው አይመስልም፡፡ልንቃወመው ወጥተን በስርዓቱ ድጋፍ ያገኘው የፋሽስት ስርዓት እንኳ በሞቃዲሾና ሮም ቁም ስቅል ያሳዩትን ወገኖቻችንን ያጉርበት የነበረው እስር ቤት አሁን አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት በተለየ ሰው በቅጡ ሊያስተኛ የሚችል እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡
እንዳያውቅ የተደረገው የሕዝብ ፖሊስ
ፖሊሶች ሕግ እንዲያውቁ አይደረግም፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ ከመበተኑ ጀምሮ እስከተፈታንበት ጊዜ ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት መብት በሕገመንግሥቱ መደንገጉን የሚያውቁ ፖሊሶች አላጋጠሙኝም፡፡ ሁሉም ይህ መብት ከፓርቲው የሚለገስ አድርገው የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ ሕግ እንዳያውቁ ተደርገው እንጂ ለአገራቸው ሕዝብ የተለየ ጥላቻ ኖሯቸው እንዳልሆነ ግን ዓላማውና ሕጉ ሲገባቸው ከእኛ ጎን ቆመው አበረታትተውናል፡፡ በተለይ አመራሮቻቸው ከነገሯቸው በተቃራኒ በፖሊሶች ላይ ግርታ የተፈጠረው በአንድ የፖሊስ መኪና እንደ ሽንኩርት ከሰው ላይ ሰው ጭነው ወደ ጣቢያ ሲወስዱን በመደብደባቸው ይሸማቀቃሉ ተብለው የተገመቱት ወጣቶች፡-
‹‹ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም፣ በአባቶቻችን ደም፣
እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም፣ ያስደፈረሽ ይውደም!››
እያሉ ሲጨፍሩ ነው፡፡ ሰባራ ባቡር አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ባረፍንበት ወቅት ሁሉም ሰው እስረኛ ሳይሆን ለሌላ ዓላማ የተገናኘ ያህል ልዩ ስሜት ውስጥ ነበር፡፡ ፖሊሶችንና ‹‹ኮማንደሩን›› ስለሕግ ያስረዳል፡፡ ስለአገሩ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይዘምራል፡፡ ኢሕአዴግን ይተቻል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን የታሰርነውን ለማየት ወደጣቢያው ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ ፖሊስ ሲያስመልሳቸው ሁሉም ለእርሳቸው ክብር ከመቆም በጭብጨባ ክብራቸውን ገለጸላቸው፡፡ በወጣቶቹ ላይ መሸማቀቅና የጥፋተኝነት መንፈስ መመልከት ያልቻሉት ፖሊሶች ይበልጡት ተደናገጡ፡፡ ‹‹ኮማንደሩ›› እና አንዳንድ አመራሮች ደግሞ በመናደዳቸው ጩኸታችንን እንድንቀንስ በተደጋጋሚ ወቀሳ ያደርሱብን ነበር፡፡ ይህን ባለመሳካቱም በቪዲዮ ቀረጻ ተጀመረ፡፡ በወቅቱ ግን ለማሸማቀቅ በሞከሩት አካላት ላይ ይበልጥ ያናደደና ፖሊሶቹ ከእኛው ጋር እንዲሆኑ ያደረገ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ በወቅቱ ከወጣቱ ተለይተው ተቀምጠው የነበሩት እነ ዶ/ር ያቆብ፣ ኢ/ር ይልቃል፣ አቶ ታዲዮስና ሌሎችም በመጨመራቸው ድምፃችን ከፍ ብሎ መሰማት ጀምሯል፡፡ ለማሸማቀቂያነት የታሰበው ቪዲዮ መቅረጽ ሲጀመርም፡፡
‹‹ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም፣ በአባቶቻችን ደም፣
እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም፣ ያስደፈረሽ ይውደም!›› እንደገና ተዘመረ፡፡
እኛን ለመጠበቅና ለማስቀረጽ ፊት ለፊታችን መሳሪያና ዱላ ይዘው የተኮለኮሉት ፖሊሶች ከመገረም አልፈው በስሜት አብረውን ዘምረዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፖሊሶቹ የጠየቅናቸውን ነገር ለማቅረብ ቀናኢ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ከተነገራቸው ባሻገር ሌላ አዎንታዊ ዓላማ ይዘን መነሳታችንን ማረጋገጥ የሚያስችላቸውን ጥያቄ በጓደኝነት መንፈስ ይጠይቁን ነበር፡፡ በኮማንደሩ ትዕዛዝ ከፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ ጣቢያ ሲያንከራትቱንም ጠባቂ ፖሊሶች ያጅቡን የነበረው ያለ መሳሪያ ነበር፡፡ ስልኮቻችን በመያዛቸው ከቤተሰብ ጋር መገናኘት እንደምንችል በማወቃቸውም ባለ አንስተኛ ደሞዝተኞቹ ፖሊሶች በራሳቸው ጥያቄ ብዙ ሰው ወደቤተሰብ እንዲደውል ተባብረዋል፡፡ እንደኛ ጾማቸውን ውለው የእረፍት ጊዜያቸው ሲደርስ የተለዩን በጓደኛና ዘመድ ስሜት ነው፡፡

Mar 27, 2013

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ 60 የአማራ ተወላጆችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ 59 ሰዎች ሞቱ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ከአካባቢው ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አደጋው የተፈጠረው፣ ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው መኪና ትክሻ በምትባል ቀበሌ ውስጥ ጀዴሳ በሚባል ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው።
ከትናንት ወዲያ በተፈጠረው አሰቃቂ አደጋ ለሞቱት ሰዎች የደረሰላቸው ሰው አለመኖሩን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገልጽ የፈለጉ ተፈናቃይ አርሶደሮች ተናግረዋል።
ከሞቱት መካከል ህጻናትና ሴቶችም ይገኙበታል። በአደጋው ዙሪያ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
በተመሳሳይ ዜናም በዛሬው እለት በርካታ አርሶ አደሮች በክልሉ ልዩ ሚሊሺያ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
የክልሉ ባለስልጣናት የሚፈናቀሉት ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ ክልሉ የገቡ ናቸው ሲሉ ለአዲስ አድማስ መናገራቸው ይታወሳል።
የዜጐች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብትን በተለከተ አስተያየታቸውን የሰቱት የሕግ ባለሞያ አቶ ግዛው ለገሠ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 32 “የመዘዋወር ነፃነት” በሚል ርእስ ስር ‹‹ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ አገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ፤ በመረጠው የአገሪቱ አካባቢ የመኖርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከአገር የመውጣት መብት እንዳለው መደንገጉን ለጋዜጣው ገልጸዋል።

Mar 26, 2013

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”

ፍኖተ ነጻነት መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም.

የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡
በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ
Interview with Ato Tadiwos Tantu
አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡
ተቃወቅሞውን ለማቅረብ ያነሳሳችሁ ዋነኛ ምክንያት ምን ነበር?
አቶ ታዲዎስ፡- ብዙውን ጊዜ እኔ በጋዜጦች ስለ አርበኞች ታሪክ ያነበብኩትንና ያወቅሁትን እፅፋለሁ፣ እመረምራለሁ፡፡ የጣሊያኑ ፋሽስት ግራዚያኒ ሀገራችንን በመውረር በአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ አሰቃቂ እንደነበር ስለተረዳሁ፤ ያ ሲቆጨኝ ደግሞ አሁን በጣሊያን ሀገር ለእሱ ሙዚየምና ሐውልት የመሰራቱን ወሬ ከኢንተርኔት ምንጮች ስላየሁ በጣም ተናድጄ እንደውም ተቃውሞ ማሰማት አለብን ብዬ ተነሳሁ፡፡ በኋላ ደግሞ እኛም የአንተ ዓይነት ሐሳብ ነበረን ብለው የባለ ዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር አነጋገሩን፡፡ ከዛ በመቀጠል ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንስራ የሚል ጥያቄ አቀረበ፡፡ በዚህ ምክንያት ሶስቱ አካላት በጋራ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን፡፡ ስለዚህ ለኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ጣሊያን ሀገር ጨረቃም ላይ ቢሆን ሀውልት እንዲሰራ አንፈቅደም፡፡
በጊዜው ሩዶልፍ ግራዚያኒ ወንጀለኛ በመሆኑ የነበረው ፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተገፎ ከወታደርነቱ ተባሮ በጦር ወንጀል ተከሶ 19 ዓመት ተፈርዶበት ቅጣቱን ሳይጨርስ ከእስር ቢለቀቅም እ.አ.አ. በ1955 ዓ.ም. ሞቷል፡፡ ታዲያ ይህ በጊዜው ወንጀለኛ ለተባለው ሰው ሐውልትም ሆነ የመታሰቢያ ሙዚየም ማሰራት ኢትዮጵየውያንን መናቅና የአባቶቻችንን ክብር የሚነካ በመሆኑ ሊሰራለት አይገባም፤ እንደውም ለፈፀመው እልቂት ጣሊያን በቂ ካሳ ስላልከፈለች ካሳ መክፈልና በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ይገባታል የሚል አቋም ይዘን ነው የወጣነው፡፡ ስለዚህ ግራዚያኒ ከነ አዳፋ ታሪኩ ሌላው እንዳይደግም ሲወሳ መኖር አለበት እንጂ እንደ ጀግና ሐውልት ሊሰራለት፣ሊወደስና ሊመሰገን አይገባም እንላለን፡፡
በወቅቱ የደረስው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ይቻላል?
አቶ ታዲዎስ፡- በወቅቱ ግራዚያኒ በፊርማው በግፍ ኢትዮጵያውያንን ያስጨፈጨፋቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ከነደብዳቤው አለ፤ የዚህ ቅጂ እኔም ጋር አለ ይታወቃል፡፡ በተለይ የካቲት 12-14 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30 ሺህ በላይ ዜጎቻችንን በግፍ አዲስ አበባ ላይ እራሱ ግራዚያኒ አስጨፍጨፏል፡፡ ከ250 በላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ መነኮሳትን አስጨፍጭፏል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በ1938 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው አለም አቀፍ ጉባኤ ያቀረበው ሰነድ እንደሚያስረዳው 760,300 ሺህ ዜጎች ወዲያው ሲገደሉ 525,000 ደግሞ ከነቤት ንብረታቸው እንዲቃጠሉ ተደርጎ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሁለት ሺህ በላይ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው መነኮሳት ተገድለዋል፣ በርካታ ቅርሶች ተዘርፈው ተወስደዋል፡፡ በርግጥ ከተዘረፉ ቅርሶቻችን መካከል እስካሁን የተመለሰው የአክሱም ሐውልት ብቻ ነው፤ ሌሎቹ ግን አሁንም እዛው ናቸው፤ ሊመለሱልንም ይገባል፡፡ ከዛ ውጭ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶች በወቅቱ ተዘርፈው ተወስደዋል፤ 7 ሺህ ግመሎችም ተገድለውብናል፡፡ ይህም በሰነድ በተደገፈ ማስረጃ ለዓለም አቀፉ የሰላም ጉባዔ የቀረበ ነው፡፡ በወቅቱ ሰነድ ያልቀረበባቸውና ሰፊ ጥናቶች ሊደረግባቸው የሚገቡ በርካታ ጥፋቶች ተፈፅመዋል፡፡
ይህንን ተቃውሞ በዋነኝነት ማቅረብ የነበረበት መንግስት ነበር የሚሉ ወገኖች አሉ፤ እርስዎስ ምን ይላሉ?
አቶ ታዲዎስ፡- እኔም እስማማለሁ፤ ነገር ግን መንግስት ማዘጋጀት ካልቻለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማዘጋጀት ይችላል፡፡ እኔ እንደሚገባኝ መንግስት ተቃውሞ ያላቀረበው ከጣሊያን የሚያገኘው ዕርዳታ ይቀርብኛል በሚል ይመስለኛል፡፡ እኔ እስከማውቀው ይሄ መንግስት ዕለታዊና የፖለቲካ ገበያ ጥቅምን መሰረት ያደረገ እንጂ ወደፊት ትውልድ የሚኮራበትን ስራ የመስራት ዓላማ የለውም፡፡ ከዚህ በፊት የቀደሙ አባቶቻችን የሰሩትን በጎ ታሪኮች ሲያንቋሽሽ የኖረ መንግስት ስለሆነ እንዲህ ዓይነት የአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ታሪክና ክብር የሚያስጠብቅ ስራ ይሰራል ብዬ አላስብም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለው፣ ብሔራዊ ስሜትን የጠበቀ ህዝባዊ መንግስት ቢሆን ኖሮ ህዝቡን አስተባብሮ ይሄንን ስራ በቀዳሚነት መስራት የነበረበት እሱ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ባያደርግም ዜጎች ይህንን ሰልፍ የማድረግ መብት ስላላቸው እኛም ሰልፉን አድርገናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የሀውልት ግንባታውን አለመቃወሙ ምን ያስረዳናል?
አቶ ታዲዎስ፡- ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በእጅ አዙር ለሀውልት ግንባታው እውቅና እንደሰጠ ይቆጠራል፤ ይህንን እኔም አምናለሁ፡፡ ከዚህም በላይ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች የነበሩ ናቸው፡፡ እንደውም ነፃነታችንን ባወጅንበት ሁለት ዓመት ሳይሞላ በአርበኞች ላይ ጦርነት የከፈቱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለግራዚያኒ የጀግና ሐውልት መሰራቱን ባይቃወሙ አይገርመኝም፤ ምክንያቱም እነሱ የማን ልጆች ናቸው? እስኪ በስልጣን ላይ ካሉት (ከኢህአዴግ) መካከል ለሀገሩ እና ለወገኑ ብሔራዊ ስሜት፣ ነፃነትና ክብር የተዋጋ የአርበኛ ልጅ አንድ ሰው ካለ ንገረኝ? አንድም ሰው የለም፡፡ ስለዚህ የባንዳ ልጅ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ በእጅ አዙርም ሆነ በቀጥታ እውቅና በመስጠት ድጋፍ ቢያደርጉ አያስደንቀኝም፡፡
እናንተ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረጋችሁ አንድ ቀን በፊት መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም ስምንት ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ክስተት በሰልፉ ወቅት እስር እንደሚኖር አልጠቆማችሁም?
አቶ ታዲዎስ፡- እሱን አውቀንም ነው ሰልፍ የወጣነው፡፡ አንድ ቀን አስቀድሞ ሌሎች ቢታሰሩም መውጣት አለብን ብለን ነው የወጣነው፤ እኛም ብንታሰር ሌሎችም እንደሚወጡ እናውቃለን፡፡ ችግር ይፈጠራል ብለን አልተውንም ፤መተውም የለብንም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የሀገርና የወገን ጉዳይ ነውና፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሰልፉ ላይ የተገኙትን ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
የታሰራችሁት ምን ወንጀል ሰርታችኋል ተብላችሁ ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- ፍቃድ አልጠየቃችሁም ፣ አላስፈቀዳችሁም በሚል ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ በነበሩ የአጼ ኃይለስላሴ፣ በደርግ ዘመንም ሆነ አሁንም በወያኔ አገዛዝ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ፈቃድ ይጠየቃል የሚል የተፃፈ ህገመንግስትም ሆነ አዋጅ አልነበረም፤የለምም፡፡ ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንደምናደርግ ማሳወቅና አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ ማድረግ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አይደለም፡፡ ይህንንም ለእኛ ጥቅም እንጂ እነሱን ለማስደሰት አይደልም፡፡ እኛ ደግሞ የሀገሪቱን የተፃፈ ህግ ተከትለን ሰልፉን ከማድረጋችን 10 ቀናት አስቀድመን አሳውቀናል፡፡
ኢትዮጵያውያንን በግፍ ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ የተሰራለትን ሐውልት በመቃወማችሁ በኢትዮጵያ መንግስት መታሰራችሁ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ? ለእኛ የበለጠ የተነሳሽነት ስሜት ሰጥቶናል፡፡ ጉዳዩንም አጠናክረን እንድንሄድ ትልቅ የሞራል ድጋፍ ሆኖናል፡፡
ከእስር ሲለቋችሁ ምን ብለው ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- ምንም ሳይሉን ለሁለት ሰው አንዳንድ ዋስ በማስጠራት ለቀውናል፡፡ ምክንያቱን ግን አልነገሩንም፤አላወቅንም፡፡ ከዛ ስትፈለጉ ትመጣላችሁ ብለው በዋስ ለቀውናል፡፡
በታሰራችሁበት ወቅትስ የገጠማችሁ ችግር አለ?
አቶ ታዲዎስ፡- በርግጥ እኔ ላይ ድብደባ አልፈፀሙም እንጂ ተመትተው ፊታቸው በተለይም አፋቸው አካባቢ የደማ ወጣት አይቻለሁ፡፡ ፊታቸው ያባበጠ ወጣቶችንም አይቻለሁ፡፡ ሌሎችንም ወጣቶች እንደደበደቧቸውም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ደህንነቶች ማታ መጥተው በግል እያስጠሩ በቢሮ ያናግሩ ነበር፡፡ ስራው ግን የፖሊሶች እንጂ የደህንነቶች አልነበረም፡፡ በታሰርንበት ዕለት ያለምግብና ውሃ ቀን ሙሉ እንድንውል ተደርገናል፡፡ በተለይ እስር ቤቱን ስቃይ አራዳ ፖሊስ መምሪያና ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ያለውን ስታይ ዕቃ ለማስቀመጥ ሆነ ለሌሎች እንሰሳቶች ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንዲቆዩበት አይመችም፡፡ እስር ቤቱን ስታይ በጣም ያሳዝናል፤ እዛ የገቡ እኮ ጤነኛ ሆነው የመውጣታቸው ዕድል እራሱ አነስተኛ ነው፤ለበሽታ የሚያጋልጡ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ብቻ በጣም ያሳዝናል፡፡ ይሄ ደግሞ የወንበዴ ስራ ነው፤ ይሄንን መንግስት ማረም አለበት፡፡ ሌላው መርማሪ ፖሊሶችና ደህንነቶች ያልተገቡና ከእስሩ ጋር የማይገናኙ የግል ህይወትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፣ የኢ-ሜይል የይለፍ ቃል ይጠይቃሉ፣… ብቻ ብዙ ነው፡፡ በግል እኔን ደግሞ ፊታቸውን በኮፊያ የሸፈኑና ጥቁር መነፅር ያደረጉ ደህንነቶች ዋስ ጠርቼ ከወጣሁ በኋላ አንተ የአርበኞችን ታሪክ እያነሳሳህ ወጣቶችን እያነሳሳህ ስለሆነ ብታርፍ ይሻልሃል፤ በግል ልናናግርህ እንፈልጋለን እያሉ ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ እኔ ግን በህጋዊ ደብዳቤ ያውም ያመንኩበት ካልሆነ ብትጠሩኝ አልመጣም፤ አላናግርም ብያለሁ፡፡
ከዚህ በኋለስ ይህን ተቃውሞ ለመቀጠልስ እቅዱ አላችሁ?
አቶ ታዲዎስ፡- አዎ አለን፡፡ ይህ ተቃውሞ ምላሽ አግኝቶ ያሰብነው እስኪሳካ እንቀጥላለን፡፡ ነገር ግን ዝርዝር ሁኔታውን በተመለከተ እያጠናን ስለሆነ ወደፊት ሀገር ውስጥ ያለነው ውጭ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመመካከር ምን መልክ መያዝ እንዳለበት ስንወስን ይፋ እናደርጋለን፡፡
በመጨረሻም የሚሉት ነገር ካለ ዕድሉን ልስጥዎት
አቶ ታዲዎስ፡- ህዝቡ ዓላማችን ከግብ እንዲደርስ የተለመደ ድጋፉን ከመስጠት ወደ ኋላ እንዳይል አደራ እላለሁ፡፡

ኢህአዴግ ብቻውን እየተወዳደረም አልመረጥም ብሎ ሰግቷል

ላይተቀምጠው ያሉ ካድሬዎችና ደህንነቶች ሠራተኞችንና ነዋሪዎችን በየቀበሌው እንዲሁም በተለያዩ አዳራሾች እየሰበሰቡ ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ እንደሆነ ከዛቻና ከማስፈሪያ ጋር መመሪያ እየሠጡ
መሆናቸውን ምንጮቻችን ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ደህንነቶች በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነዋሪዎች እንዲሰበሰቡ ካስደረጉ በኋላ ስብሰባው
የተጠራበትን አጀንዳ በመተው “ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ ነው፤ ኢህአዴግን አለመምረጥ ፀረ ህዝብነት ነው፡፡”
የሚሉና ሌሎች ማስፈራሪያዎችን እየሰጡ ነው ሲሉ ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ መምህራንና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ከፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር መጋቢት 11 ቀን 2005 ዓ/ም ነዋሪዎችን ስብሰባ ጠርቶ
እንደነበር የሚናገሩት ምንጮቹ “ስብሰባ የተጠራነው ስለአካባቢያችን ልማትና መልካም አስተዳደር ላይ ለመወያየት
ተብለን ነው፡፡ ስብሰባውን የመሩት የወረዳው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አሰግድ (የወረዳው ኢህአዴግ ኃላፊ
ናቸው፡፡) በስብሰባው ላይ ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ ነው፡፡ በሚል መንፈስ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲናገሩ ውለዋል፡፡”
ብለዋል፡፡
ምንጮቻችን አክለውም “ተሰብሳቢው በበኩሉ በየሠፈሩ ያሉትን ችግሮች እያነሳ ተናግሮአል፤ አንዳንዶቻችን እኛ
ጥያቄአችን ምርጫ ሳይሆን የእለት ዳቦ ነው ብንልም ሰብሳቢው ተገቢ ያልሆነ መልስ ሰጥተውናል” በማለት
ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ/ም የመዝናኛ ክበባት ሠራተኞች በክፍለ ከተማ ደረጃ ስብሰባ ተጠርተው ነበር፡፡
ከስብሰባው በኃላ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት “የተጠራነው አገልግሎት አሰጣጥ ጉዳይ ለመወያየት ተብሎ ነው፡፡
ነገር ግን ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ እንደሆነ መመሪያ ተስቶናል፡፡ የፈለግነውን መምረጥ እንደምንችል ወይም ማንንም
አለመምረጥ ህገ መንግስታዊ መብታችን መሆኑን ሊረዱልን አልቻሉም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮ ምርጫ ነዋሪነታቸው ያልተረጋገጠና የቀበሌ መታወቂያ የሌላቸው ሰዎች ሁሉ በግዳጅ እንዲመዘገቡና ካርድ
እንዲያወጡ ተደርጓል፡፡ የሚል ቅሬታዎች ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ በመንግስት ደመወዝ እየተከፈላቸው ሙሉ
ጊዜያቸውን የፓርቲውን ሥራ የሚሠሩና በመንግስት የሥራ ሰዓት ሠራተኛቸውን ለፓርቲው ሥራ የሚያውሉ
የመንግስት ባለሥልጣናት በሙስና ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል የሚሉ አስተያየቶችም እየተሰጡ ናቸው፡፡
በመጪው የአካባቢና የአዲስ አበባ መስተዳድር ምርጫ ብቻውን የሚወዳደረው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ አዲስ አበባ
ላይ ላልመረጥ እችላለሁ በሚል ስጋት ነዋሪዎችንና ሰራተኞችን በስብበሳ ማዋከቡ ብዙዎችን እያስገረመ ነው፡፡
ምንጭ፦ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

Mar 22, 2013

freedom more than food !!!: የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በአብዛኛው ነባር አመራሮቻቸው በስራ አስፈጻሚነት ቀጠሉ

freedom more than food !!!: የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በአብዛኛው ነባር አመራሮቻቸው በስራ አስፈጻሚነት ቀጠሉ

የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በአብዛኛው ነባር አመራሮቻቸው በስራ አስፈጻሚነት ቀጠሉ

ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሰሞኑን በተከታታይ ባካሄዱዋቸውና በመተካካት ረገድ እምብዛም ለውጥ ያልታየባቸውጉባዔዎች በአብዛኛው ነባር አመራሩን ይዘው ሲያስቀጥሉ መጠነኛ የሆነ እርምጃም ወስደዋል፡፡በዚሁ መሰረት ኦህዴድ አቶ አባዱላ ገመዳን፣ ግርማ ብሩን እና ኩማ ደመቅሳን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ሲያሰናብት፤ ብአዴን በበኩሉ የፍትህ ሚኒስትር የሆኑትን አቶ ብርሃን ኃይሉን፣ደኢህዴን ደግሞ አቶ ተሾመ ቶጋን አሰናብቷል፡፡ብአዴን በጤና ችግር መደበኛ ስራቸውን ማከናወን የተሳናቸውና ነባር ታጋይ የሆኑትን አቶ ህላዊዮሴፍን፣ኦህዴድ ወ/ሮ አስቴር ማሞን በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት እንዲመረጡ አድርጓል፡፡በተጨማሪም ኦህዴድ የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽነሩን አቶ ወርቅነህ ገበየሁን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባል እንዲሆኑ መርጧቸዋል፡፡ በሟቹ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዕቅድ መሰረት በመተካካት ሒደቱ እስከ 2007 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ቦታ ይለቃሉ ተብለው ይገመቱ የነበሩት ነባር ታጋዮች ለቀጣይ ሁለት ዓመት ተኩል ጊዜያት እንዲቀጥሉ መደረጉ በተለይ ከፍተኛ አመራሩ የመለስን ራዕይ ለማሳካት በተደጋጋሚ የገባውን ቃል ማጠፉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ተናግረዋል፡፡ በ2003 ዓ.ም በመተካካት ስም የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊነታቸው የለቀቁት አቶ አዲሱ ለገሰን ጨምሮ አቶ በረከት ስምኦን፣አቶ ህላዊ ዮሴፍ፣አቶ አባይ ወልዱ እና የመሳሰሉት ስልጣናቸውን ወደማጠናከር ፊታቸውን ማዞራቸው የመተካካት ዕቅዱ ውሃ እንደበላው ማሳያ ሆኗል፡፡ አቶ አዲሱ ከድርጅቱ በአቶ መለስ አማካኝነት ከተሰናበቱ በሁዋላ ተመልሰው መምጣታቸው አስገራሚ ሆኗል። አቶ አዲሱ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገው እርሳቸው ባልጠበቁበት መንገድ እንደነበር መግለጻቸው ይታወሳል። በመተካካት ስም በ2003 የመንግስት እና ከፓርቲ ኃላፊነታቸው የለቀቁትን እነ አቶ ስዩም መስፍን ጨምሮ ሌሎች 9 የህወሃት አባላት በራሳቸው ፈቃድ በአብዛኛው ከጤና ጋር በተያያዘ ድርጅቱን ለመልቀቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተሰናበቱ ሲሆን የእነዚህ ሰዎች መልቀቅ እንደመተካካት ለማየት እየተደረገ ያለው የማደናገሪያ ፕሮፖጋንዳ አሳዛኝ መሆኑን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡በራሳቸው ፈቃድ ከለቀቁት መካከል አቶ ስዩም መስፍን ፣ አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ አቶ አርከበ ዕቁባይና አቶ ዘርዓይ አስገዶም ይገኙበታል፡፡ የዘጠኝ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማቅረባቸው አጋጣሚ ሳይሆን ከአቶ መለስ ህልፈት በሓላ በህወሃት ውስጥ ከተፈጠረው ልዩነት ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጫችን ቢጠቅስም ይህን በተመለከተ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ብዙዎች እንደሚገምቱት ከአቶ አርከበ እቁባይ ጋር ጤነኛ ግንኙነት ያልነበራቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን በዚህ ጉባኤ በድል አድራጊነት ወጥተዋል። ህወሀት የአቶ አባይ ወልዱን  ባለቤት ወ/ሮ  ትረፉ ኪዳነማርያምንም በስራ አስፈጻሚነት መርጧቸዋል። ድርጅቶቹ ባካሄዱት ምርጫ መሰረት ከህወሃት፡- አቶ አባይ ወልዱ፣ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣አቶ አባይ ጸሐዬ፣ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር፣አቶ በየነ ምክሩ፣አቶ ኪሮስ ቢተው፣አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ፤ከብአዴን፡-አቶ አዲሱ ለገሰ፣አቶ በረከት ስምኦን፣አቶ አያሌው ጎበዜ፣አቶ ገዱአንዳርጋቸው፣አቶ ደመቀ መኮንን፣አቶ አለምነው መኮንን፣አቶ ካሳ ተ/ብርሃን፣አቶ ህላዊ ዮሴፍ፣አቶ ተፈራ ደርበው፤ከኦህዴድ፡-አቶ አለማየሁ አቶምሳ፣አቶ ሙክታር ከድር፣ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣አቶ ወርቅነህ ገበየሁ፣አቶ ሶፊያን አህመድ፣አቶ ድሪባ ኩማ፣አቶ አድልቃድር ሁሴን፣አቶ ኡመር ሁሴን፣አቶ አበራ ኃይሉ፤ ከደኢህዴን፡-አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣አቶ ሬድዋን ሁሴን፣አቶ መኩሪያ ኃይሌ፣አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም፣አቶ አለማየሁ አሰፋ አቶ ደሴ ዳልቼ፣አቶ ተስፋዬ ቢነግዴ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሰሩ በየድርጅቶቻቸው ተመርጠዋል፡፡ ከፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚካሄደው የኢህአዴግ ጉባዔ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን በሊቀመንበርነት፣አቶ ደመቀ መኮንን በምክትል ሊቀመንበርነት በድጋሚ ይመርጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቻን ጠቁመዋል፡፡ የኢህአዴግ ድርጅቶች ያደረጉትን ሹም ሽር በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የቀድሞ የሀወሀት ነባር ታጋይ ፡ ምርጫውን “ውሀ ቢወቅጡት ነው” ብለውታል። “ከእነዚህ ሰዎች ምንም የሚጠበቅ ነገር የለም፣ ምን አዲስ ነገር እንደማይፈጥሩም ይታወቃል። የአፈና ስርአቱ እንደሚቀጥል ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል ታጋዩ።

በአፋር ህጻነት በርሀብ እየረገፉ ነው

ኢሳት ዜና:-በክልሉ ካለፉት አራት ወራት ጀምሮ የተከሰተው ከፍተኛ ረሀብና የውሀ እጥረት የበርካታ ህጻናትን ህይወት መቅጠፉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።ምንም እንኳ 60 በመቶ በሚሆነው የአፋር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሀ እጥረት ቢከሰተም ፣ ችግሩ ከሁሉም ወረዳዎች አስከፊ ሆኖ በቀጠለበት የእዳ ወረዳ 6 ህጻናት በአንድ ወር ውስጥ ሞተዋል። ይህ አሀዝ በአንድ ሰፈር ብቻ የተጠናከረ እንጅ በአጠቃላይ በወረዳው በተከሰተው ረሀብና የውሀ እጥረት የሟቾች ቁጥር በብዙ መቶዎች ሊደርስ እንደሚችል የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል።አንድ ጀሪካን ውሀ በ60 ብር ለመግዛት መገደዳቸውን የገለጹት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የእዳ   ወረዳ ነዋሪ፣ የአካባቢው ነዋሪ ፍየሎቹና ግመሎቹ አልቀውበት ወደ አሳይታ ስደት መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ አሳይታ በሰላም የደረሱት በህይወት ሲትረፉ ሌሎች ደግሞ በመንገድ ላይ አልቀዋል ።የመንግስት እርዳታ እንዳልመጣላቸው የተነጋሩት ነዋሪዎቹ ፣ አስቸኳይ እርዳታ ካልደረሰ አስከፊ እልቂት ይፈጠራል ብለዋል።በአካባቢው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘው የአፋር ጋድሌ ሊ/መንበር ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ለኢሳት እንደገለጡት ከፍተኛ ረሀብ በአካባቢው መግባቱን ድርጅታቸው እንደሚያውቅ ገልጸዋል።በዚህ አመት ከአፋር ሌላ በሶማሊና በተለያዩ የአማራ፣ የደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች ድርቅ መግባቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።በአዲስ አበባ ህጻናት በምግብ እጦት ትምህርታቸውን መከታተል እንዳልቻሉ ሸገር ኤፍ ኤምን በመጥቀስ ኢሳት ትናንት መዘገቡ ይታወሳል።በግብርናው መስክ ከፍተኛ እመርታ እንዳገኘ ከመናገር ተቆጠቦ የማያውቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ፣ ላለፉት 21 አመታት ኢትዮጵያን በምግብ ራሱዋን እንደሚያስችል ቢናገርም እስካሁን ድረስ የታየ ለውጥ የለም። በቅርቡ ይፋ ሆነ አንድ ጥናት እንዳለመከተው ከ7 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በምግብ ለስራ ታቅፈው ከአለም ባንክና ከአውሮፓ ህብረት በሚለገስ ስንዴ እየተደጎሙ ነው። በዚህ አመት የአስቸኳይ ምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።በመላው አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የውሀ እና የምግብ እጥረት ቢከሰተም ገዢው ሀይል በቅርቡ 200 ሚሊዮን ብር በማውጣት የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አክብሮአል። ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ደግሞ የመከላከያ ቀንን አክብሮአል።

የወያኔ/ኢህአዴግ ጉባኤ ውሃ ቢወቅጡት እሞቦጭ

ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይና በተለምዶ ተለጣፊ እየተባሉ የሚጠሩት ሎሌ ድርጅቶቹ ሰሞኑን በጉባኤ ሽርጉድ ላይ ተጠምደዋል። የድግሱ፣ የፌስታውና የካርኔባሉ አይነትና ብዛት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች በቀን አንድ ጊዜ ለመብላት በሚቸገሩበት ሀገር ውስጥ የሚደረግ አይመስልም። ይሔው የፈረደበት የኢትዮጵያ ድሃ ግብር ከፋይ ይህን በብዙ መቶ ሚሊየኖች ብር የሚቆጠር ወጭ ይሸፍናል። ማን ከልካይና ጠያቂ አለ? ሌሎች በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች ለአንድ ደቂቃ እንኮን በአጠገቡ ዝር እንዳይሉ የሚከለክለው የመንግስት ሚዲያ ይህንን የግፈኞች የውሸት ዲስኩርና ፌሽታ በቀን 24 ሰአት ያጋፍራል። እንጨት እንጨት የሚል ፕሮፖጋንዳ ሊግተን፣ ሊያደነቁረን ይታገላል፡፡ ልብ ብሎ ለተመለከተው ጠቅላላው የወያኔ የጉባኤ ሽርጉድ ከጆርጅ ኦርዌል “የእንስሳት እርሻ” (Animal Farm) የስላቅ ድርሰት ተወስዶ የሚሰራ ትያትር ይመስላል።
የወያኔ መሪዎችና ሎሌዎቻቸው ለሆድ አደሮች እግዚያብሄር እንደ ፀጋ ሰጥቷቸዋል። እፍረትና ይሉኝታ የሚባል ነገር ከልክሎ ፈጥሯቸዋል። ትዝብት አይፈሩም። ህዝቡ አንጀቱ እያረረ እብሪታቸውን ሲመለከት በደስታ ፈንድቆ የሚጨፍር ይመስላቸዋል። ኢትዮጵያን ወደ ፖሊሲያዊ መንግስትነት ቀይሮ የሞተውን አለቃቸውን ለአፍሪካና ለአለም የሚያጎድል መሪ ነው ይሉናል። መለስ በምን ህመም እንደሞተ እንኩዋን አጣርተው የማያውቁ ጀሌዎች ትግል ላይ የተሰዋ ኣርበኛ ኣስመስለው ሲያወሩ አያፍሩም።
ይህንኑ እንዲመሰክርላቸው ከዚህ ቀደም በሙሁር ሸቃጭነት (intellectual prostitution) የገዛ ጎደኞቻቸው ሙሁር ከከሰሳቸው የኮሎምቢያ ሙሁራንም  አንዱን አስመጥተዋል። በነዚህ ሰዎች ግምት መለስ ዜናዊ በግፍ የጨፈጨፋቸው ወገኖቻችን፣ የዝምብ ያህል ክብር የላቸውም።   በእስር የታሰሩት ንጹሃንና ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ወገኖቻችን በነሱ ቤት ሰዎች አይደሉም። እናም ጉባኤው አይናችሁን ጨፍኑልንና እናሞኛችሁ ከሚል  ቡዋልት የተለየ አይደለም።
እንዳለፉት ጉባኤዎች ሁሉ የዚህንም ጉባኤ ተብዬ  ውጤት አስቀድሞ መናገር ይቻላል።አሁንም አይናቸውን አጥበው ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር እየሰራን ነው የሚል መግለጫ ያወጡልናል። መለስ ዜናዊ ቀድሞውኑ ራሱን አዋቂ አድርጎ በመሳል ከሱ የተቀራረበ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ጠራርጎ በደካሞች ራሱን ከቦ ከበሮ እያስደለቀ መቆየቱ ለከንቱ የሙት ውዳሴ ጠቅሞታል። እነዚህ ደካማ ጀሌዎች አሁንም ምንም የራሳቸን እውቀት ስለሌለን በሞተው መለስ ራእይ በሚሉት ነገር እንደሚመሩ በጉባኤው መጨረሻ የአዞ እንባ ያለበት መግለጫ ያወጣሉ።
እድገትና ትራንስፎርሜሽን የሚባለው ነገር ከሁለት አመት በኋላ ህብስተመና ከሰማይ ይወርዳል የሚል የጉባኤ ውሳኔም እንሰማለን። መብታቸውን የሚጠይቁ ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራራትና አስጎንብሶ ለመግዛት ይጠቅማሉ የተባሉ መግለጫዎችም በጉባኤው መጨረሻ ይጠበቃሉ። አሸባሪ፣ ጸረ-ልማት፣ አክራሪ፣ ወዘተ ወዮላችሁ ይሉናል። ስልጣንና ስልጣንን መከታ በማድረግ የዘረፉት ሀብት ይቀርብናል የሚል የሚያባንን ፍርሃት ስላደረባቸው ባስፈራሩን ቁጥር ሰላም ያገኙ ይመስላቸዋል። በህዝብ መሃል ልዩነት መፍጠርና አንዱን በአንዱ ላይ ማነሳሳት ሰላም ይሰጠናል ብለው ስለወሰኑ እርስበርሳችን እንድንጋጭ ጥሪ ያቀርቡልናል።
ዛሬም እንዳምና ካቻምናው የነሱ ምቾት ስለጨመረና ስለተመቻቸው ኢኮኖሚው እየተመነደገ ነው እንደሚሉን ይጠበቃል። የህዝባችን ኑሮ የከዘራ ያህል እንኳን ቀና እንዳላለ ህዝቡ ራሱ ያውቀዋል።
ወገን ይሄ ግፍ ለከቱን አልፏል። ከወያኔ አገዛዝ በጎ ነገር መጠበቅ ከእባብ እንቁላል ርግብ መጠበቅ  መሆኑን ካወቅን ውለን አድረናል።
ግንቦት 7 የፍትህ የነትጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ  በሀገራችን ዴሞክራሲ ሰፍኖ በገዛ ሀገር ተዋርዶ መኖር ቆሞ፣ በኩራትና በሰባአዊ ክብር ሁላችንም የምንኖርበት ሀገር ወያኔና ሎሌዎቹ ሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው ብሎ ያምናል ። በመሆኑም የወደፊቱ እጣችንና ተስፋችን ያለው በራሳችን መዳፍ  ውስጥ ብቻ  እንደመሆኑ   ለነጻነቱና ለክብሩ ቀናዕ የሆነ ሁሉ በራሱ   አነሳሽነት ትግሉን ለማቀጣጠል መነሳት ያለበት ጊዜው አሁን ነው ።
ከወያኔ በጅጉ የተሻለ ስርዓት የሚገባን ህዝብና ሀገር እንደመሆናችን ህዝባችን  በወያኔ አገዛዝ ላይ በቃኝ በማለት ዛሬውኑ እንዲነሳና ! በየአቅጣጫው ለነጻነት የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን እንዲቀላቀል ግንቦት 7 የፍትህ የነትጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ  የትግል ጥሪውን ያቀርባል!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Mar 18, 2013

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ታሠሩ (የታሰሩትን 34 ሰዎች ስም ዝርዝር ይዘናል)

ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል
ተነሳሽነት ማህበር፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን
“ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን
መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ
መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ
ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፣ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች
እና በርካታ ወጣቶች ማሰሩ ታወቀ። አሁንም የታሳሪዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል
የሚሉት የዜና ዘጋቢዎች የቀድሞውን የቅንጅት አመራር ዶ/ር ያዕቆብ
ኃይለማርያምን ጨምሮ 34 ሰዎች መታሰራቸው በወጣው ስም ዝርዝር ላይ
ተገልጿል፡፡ ትላንት እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ
አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን በማሰር የተጀመረው ይህ የማሰር
ተግባር ዛሬ ቀጥሎ የታሳሪዎቹ ቁጥር 34 ደርሷል።
ለጊዜው ስማቸው የታወቀና የታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው።
1. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
2. አቶ ታዲዎስ ታንቱ
3. አቶ ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ሊቀመንበር)
4. ስለሺ ፈይሳ (የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር)
5. ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
6. ሀና ዋለልኝ (የሰማያዊ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ)
7. ጌታነህ ባልቻ (የሰማያዊ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ)
8. ብርሀኑ ተክለያሬድ (የባለራዕይ ወጣቶች ተ/ምክትል ሊቀመንበር)
9. ያሬድ አማረ (የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጸሀፊ)
10. ኤልሳቤጥ ወሰኔ
11. ሰለሞን ወዳጅ
12. ወይንሸት ንጉሴ
13. እየሩሳሌም ተስፋው
14. ለገሰ ማሞ
15. ትዕግስት ተገኝ
16. አማኑኤል ጊዲና
17. አለማየሁ ዘለቀ
18. አገኘሁ አሰገድ
19. ሻሚል ከድር
20. አሸብር ኪያር
21. ጌታቸው ሽፈራው
22. ግሩም አበራ
23. አቤል ሙሉ
24. ዩሀንስ ጌታቸው
25. ስማቸው ተበጀ
26. ፍቃዱ ወንዳፍራው
27. ባህረን እሸቱ
28. ሄኖክ መሀመድ
29. እንቢበል ሰርጓለም
30. አለማየሁ በቀለ
31. ዩናስ
32. የመኪናው ሹፌር
33. ዮዲት አገዘ
34. ጥላዬ ታረቀኝ

Mar 17, 2013

ውድ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች ሁሉ ይህ አልባሌ የቅስቀሳ ወረቀት ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ መልዕክት ስለሆነ በጥሞና አንብባችሁ ተረዱ።

ሕዝብ ሃብትና ጉልበት የቆመችው ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ለኢትዮጵያ መንግሥት (ኢህአዲግ) ለማስረከብ የተወሰኑ ካህናት ከኤምባሲ ጋር ድርድር እያደረጉ ነው።

አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው የእግዚአብሔር ቤት የሆነውንና ሕዝብ በሃብቱና በጉልበት ገዝቶ ያቆመውን ቤተ ክርስቲያን በአብይ ጾም ሕዝብ እንዳይጸልይበት ከ11/03/2013
London Ethiopian Orthodox Church
ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን
ጃምሮ ከዘጉ በኋላ ለንደን ወደሚገኘው የኢትዮጵያ (የኢህአዲግ) ኤምባሲ በስውር በመሄድ በኤምባሲው አደራዳሪነት ቤተ ክርስቲያኑን የኢትዮጵያ (ኢህአዲግ) መንግሥት እንዲረከበው ለማድረግ ድርድር መጀመራቸውን በተጨባጭ ማረጋገጥ ተችሏል።
አባ ግርማ ከበደ፤ መሪ ጌታ አለማየሁ ደስታና ድቁናውን ያፈረሰው የቀድሞ ሊቀ ዲያቆን ዳዊት ገ/ዮሐንስ በመሆን ከአሁን በፊት የማርያም ቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በመዝረፉ፤ ከዛም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1998 ዓ/ም ቤተ ክርስቲያኗን ለኢህአዲግ አሳልፎ ለመስጠት ሲል አገልግሎቷን አቋርጣ እንድትዘጋ አድርጎ የነበረውና ከዚህም ሁሉ በላይ ደግሞ የኦርቶዶክስ እምነቱን ክዶ ጴንጤ በመሆን ጴጤ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ የኦርቶዶክስ እምነት የበሰበሰና የገማ ነው በማለት ምሥክርነት መሥጠቱ የሚታወቀው ሙሉጌታ አሥራትን በኤምባሲ ውስጥ በማግኘት ለተንኮል ሥራቸው እንዲተባበራቸው ማድረጋቸው ታውቋል።
ከሃገሩ ኢትዮጵያ ተሰድዶ በUK የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ባደረገው 40 ዓመታትን ያስቆጠር ድካምና ጥረት በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ሃብትና ጉልበቱን አስተባብሮ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን በመግዛት ሁለተኛ ኢትዮጵያ የምትሆነውን ቤተ ክርስቲያን ካቆመ ብዙም ሳይቆይ ቤተ ክርስቲያኑን ከእጁ ነጥቀው አሳልፈው በመሥጠት መሾሚያና መሸለሚያ ለማድረግ የሚጥሩ አባ ግርማ ከበደን የመሰሉ ባላንጣዎች ተነሱበት።
ሕዝብ ሃብትና ጉልበቱን አስተባብሮ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን መግዛት ብቻ አይደለም የካህናቱን ደምወዝና አበልም ሆነ የቤተ ክርስቲያኑን ጥገናና እድሳት ጨምሮ እያንዳንዱን የቤተ ክርስቲያኑን የዕለት ተዕለት ወጪ ከኪሱ እያወጣ በሚሰጠው ገንዘብ ሸፍኖ የሚያኖረው ይኸው ሕዝብ ሆኖ ሳለ አባ ግርማ ከበደ በመጀመሪያ የምእመኑ ተወካይ የሆኑትን 4 የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በተጽዕኖ ሥራቸውን እንዲለቁ አደረጉ። ቀጥሎም የምእመኑ ተወካዮች በሌሉበት ተከታዮቻቸው የሆኑትን ከህናት በመያዝ ሕዝብ አንዳችም ነገር ሳያውቅና ምንም ዓይነት ፍንጭ ለሕዝብ ሳያሳዩ 15 ሕዝብ የመረጣቸውን የኮሚቴ አባላትና ቤተ ክርስቲያንን ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ የቤተ ክርስቲያን አባላትን ቅጥር ግቢው ውስጥ እንዳይደርሱ ብለው በደብዳቤ አባረሩ። ይህንን በመሰለ ሁኔታ ከቤተ ክርስቲያን ምንም አይነት ጥቅም ሳይፈልጉ የሚያገለግሉና ለእውነት የቆሙ የምእመናኑን ተወካዮች ካስወገዱ በኋላ እነሆ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው ብቻ የቤተ ክርስቲያኑ ሃብትና ንብረትም ሆነ የወደፊት እጣ ፋንታዋ ወሳኞቹና ፈላጭ ቆራጮቹ እኛ ነን ብለው በመቅረብ ቤተ ክርስቲያኗን ከነ ንብረቷ ለኢህአዲግ መንግሥት በማስረከብ በምትኩ ሹመትና ሽልማት ይሰጠን በማለት ከኤምባሲ ጋር በመደራደር ላይ ይገኛሉ።
ይህ ለማመን የሚያዳግት ሕዝብንም ሆነ እግዚአብሔርን የተዳፈረ ተግባር በሕዝብ ላይ ሲፈጸም የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤትና ባለንብረት የሆነው ሕዝብም ሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዝም ብሎ ስለማያይ አጠቃላይ ሕዝቡ በአንድነት ተንቀሳቅሶ ሕዝብን ከነ ቤተ ክርስቲያኑ ለመሸጥ በማስማማት ላይ የሚገኙትን የአባ ግርማ ከበደና የተከታዮቻቸውን ደባ በማስቆም የጥፋት ዓላማቸውን ሊያከሽፍባቸው ይገባል።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ሕዝብ በፈራ ተባና በመዘናጋት ለአባ ግርማና ተከታዮቻቸው ጊዜ ከሰጣቸው “ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆሞ ማውረድ ያቅታል” ነውና ዓይናችን እያየና ጆሮአችን እየሰማ ቤተ ክርስቲያን ከሕዝብ እጅ ወጥታ የማትሄድበት ምክንያት ስለሌለ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ከምንግዜውም በበለጠ በመነሳት ቤተ ክርስቲያንህን ለመከላከልና ለማዳን ከአስተባባሪ ኮሚቴው በሚሰጥህ መረጃና መመሪያ መሠረት በአስፈላጊው ቦታ ሁሉ በመገኘት የሚጠበቅብህን ሁሉ እንድታደርግ በማርያም ስም ጥሪአችንን እናስተላልፋለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አስተባባሪ ኮሚቴው

ሰንሰለቱም ይጠብቃል፤ እርግጫውም ይከፋል …ካልተነሳን!

ሉሉ ከበደ

አስተዳደር በየፈርጁና በየደረጃው፤ ከብሄራዊ መንግስት እስከ ታች የቀበሌ አመራር በመጥፎም ይሁን በደግ መልኩ በዜጎች ህይወት የለት ተለት እንቅስቃሴና አኗኗር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ እንደሚኖረው ሁሉም ሰው እየኖረው ስለሚያየው ማስረጃ መደርደር ላያስፍልገው ይችላል።
በሀገርና በህዝባዊ ጉዳዮች ውሳኔ አሰጣጥ ላይ እናም ውሳኔውን በማስፈጸም ሂደት ላይ ዋናው ተዋናይ በመንግስትነት የተሰየመው አካል ሲሆን፤ እንደየ ሀይላቸውና ቅቡልነታቸው፤ በመንግስት ውሳኔ ላይ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉ ወገኖች መኖራቸው የተለመደ ነው። ለምሳሌ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የሰራተኛ ማህበራት፤ የገበሬ ማህበራት፤ የሙያ ማህበራት፤ ተደማጭ ግለሰቦች እናም አለም አቀፍ ሀይላት፤ የመገናኛ ብዙሀን፤ የገንዘብ ተቋማት፤ ወዘት……ከሁሉም  በላይ ደግሞ ሕዝብ!!..ዲሞክራሲ ባለበት ሀገር ውስጥ በመንግስት ውሳኔ ላይ ተጽእኖ ማሳደር ይችላሉ።
ወደእኛ ሀገር ጉድ የመጣን እንደሆነ በተለይም በደርግና በዘረኛው የወያኔ አስተዳደር ዘመን ፍጹም በሆነ ወደር ያልተገኘለት አንባገነንነት ስር በመውደቃችን፤ የምንታገልለትና የምንመኘው ዲሞክራሲ ጭላንጭሉም እስከወዲያኛው በመጥፋቱ፤ እንኳን የፖለቲካ ድርጅት፤ እንኳን የሙያ ማህበር፤ ህዝብ በነቂስ ከቤቱ ወጥቶ አደባባይ ውሎ አድሮ አቤቱታ፤ሮሮም ሆነ ተቃውሞ ቢያሰማ ወያኔ ከጥፋት አቋሙ ፍንክች እንደማይል ለኢትዮጵያ ህዝብ በተግባር አሳይቷል። ሙስሊም ወንድሞቻችን ከአመት በላይ በሰላም እየታገሉለት ያለው የሀይማኖት ነጻነት ምላሽ ማግኘት ቀርቶ ጭራሽ ይህን አንገብጋቢ ህዝባዊ ሰብአዊ ጥያቄ ወደ ወንጀልነት ቀይሮ፤ ንጹሀን ዜጎችን ወህኒ መቀመቅ ለማጎር ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እየተመለከትን ነው አዲስ ነገር ባይሆንም።
የሙስሊም ወንድሞቻችን ትግል አርአያነቱ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በእልህና በድንቁርና ለሚታመሰው ለሚተራመሰው አለም በሀገራችን ቢሳካም ባይሳካም እየሞቱ እንዴት ሰላምን ማምጣት እንዴት መብትና ንጻነትን ማስከበር እንደሚቻል የሚያስተምር አጋጣሚ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ይህንን የሙስሊማን ወርቃማ የትግል ስልት ለመቀላቀል የዘገየበት ምክንያቱ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ሰላማዊ ትግል መርጠናል የሚሉን የፖለቲካ ድርጅቶች ደጅም ሆነ እቤት ያሉት፤ ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ትግል ምን አለ ብለው ይሆን የራሳቸው አንሶ ህዝቡንም ይዘው የተኙት? ኢትዮጵያ የሙስሊምና የክርስቲያን ሀገር አይደለችም እንዴ? ፖለቲከኞች እስላም ወይ ክርስቲያን አይደሉም እንዴ?…ጥያቄው እኮ የመብት የነጻነት ነው?….የአምልኮ ነጻነት… የፖለቲካ ነጻነት….የኢኮኖሚ ነጻነት….የመኖር ነጻነት… የመደራጀት…..የመሰብሰብ….ሁሉም ልንታገልላቸው የሚገባ ሊኖሩን የሚገቡ የህይወት እሴቶች፤ እስትንፋሶች ናቸው።
መልካም አስተዳደር የሚባለው የአመራር አይነት ቢያንስ ሊኖሩት የሚገቡ ግብአቶች  በግልጽ ተቀምጠው እያለ፤ የተባብሩት መንግታት ድርጅትም ሆነ የአለም ገንዘብ ድርጅት፤ የአለም ልማት ድርጅቶች፤ ሀያላን መንግስታት እነ አሜሪካም ሆኑ እንግሊዞች በተለይም ከአፍሪካ አገሮች መንግስታት ጋር የሚኖራቸው የእርዳታና የልማት ትብብር የሚወሰነው የመልካም አስተዳደር መስፈርቶችን ማሟላት ሲችሉ ነው ቢሉም የግል ጉዳያቸውንና ጥቅማቸውን እስከጠበቁላቸው ድረስ ከማንኛውም ዘረኛና ጨፍጫፊ ቡድን ጋር እንደሚተባበሩ በተግባር አሳይተውናል።
ለዚህም አንድ ቁልጭ ያለ ማስረጃ አሜሪካ በየአለሙ ያሉ አንባሳደሮቿ በሚስጥር ለመንግስታቸው የሚያስተላልፉትን መረጃ ያዝረከረከው ዊኪሊክ  ይፋ እንዳደረገው፤ አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኢንባሲ እለት በእለት ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽማቸውን ወንጀሎች፤ ሰባዊ መብት ረገጣዎች፤ ግድያዎች፤ በአዲስ አበባ ያካሄዱትን ፍንዳታዎች ሁሉ በየእለቱ ለአሜሪካ መንግስት ያስተላልፍ ነበር። ያ ማለት እለት በእለት የምትሰራዋን ወንጀል በሙሉ ያውቁ ነበር። ያውቃሉም። ነገር ግን ባካባቢው የራሳቸውን ጥቅምና ፍላጎት ስለሚጠብቅላቸው ብቻ፤ በሀገሩና በህዝቡ ላይ ይህን አደረሰ ብለው፤ ትብብራቸውንና እርዳታቸውን አላቋረጡም። አያቋርጡምም። እንግሊዝ በቅርቡ በብዙ ሚሊዮን ዶላር ወጪ በሱማሌ ክልል ሀዝቡን የሚያሰቃዩበት ፖሊስ በብዛት አሰልጥኖላቸዋል።
ለውስጥ ችግራችን መፍትሄ ወደ እነሱ መመልከት ሳይሆን እኛው የጉዳዩ ባለቤቶች የችግሩ ገፈት ጨላጮች፤ በመናበብ፤ በመደማመጥ፤ በመተያየት፤ ከየትኛውም የሀገሪቱ ጥግ የበደል ጩኸት ሲሰማ፤ እንደ ንብ አብሮ መቀስቀስና ባንድ ድምጽ በመጮህ የወያኔን ዘረኛ አጥፊ ቡድን መታገልና ከስልጣን ማስወገድ ያስፈልጋል።
በሀገራቸው ፖለቲካና ኢኮኖሚ እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ዜጎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሙሉ የተሳትፎ መብትና እድል ሲኖራቸው፤ የመደራጀት ነጻነት ያለገደብ፤ ኢንፎርሜሽን የማግኘት ነጻነት ያለገደብ ሲኖራቸው፤ በሚወከሉበት ድርጅትም ሆነ በግላቸው በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ደህንነታቸውን፤ ሀብታቸውን፤ ግዛታቸውን፤ መንግስታቸውን፤ በተመለከተ ሊናገሩ ሊደመጡና ውሳኔም ሊያስተላልፉ ሲችሉ፤ ሊሾሙና ሊሽሩ ሲችሉ፤  ቢያንስ መሰረታዊ መብት አላቸውና ወደው ወይም መርጠው ስለተቀበሉት ስርአት የሚያስጨንቅ ነገር የለም፤ ካልበጃቸው ያንኑ መብታቸውን ተጠቅመው ይለውጡታልና!
አለመታደል ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያንስ ለግማሽ ምእተ አመት ለዲሞክራሲና ለተሻለ መልካም አስተዳደር ትግል ቢያደርግም ባለፉት ሁለት አጋጣሚዎች ድሉን እየተነጠቀ ለእኩይ አላማና ግብ የተነሱ፤የሀገርና የህዝብ  የውስጥ ጠላቶች አሸናፊ ሆነውበት፤ ለባሰ ውድመትና መከራ ዳርገውት፤ ሀገራዊ ህልውናውንም ማጥፋት በሚያስችል የታሪክ አዘቅት አፋፍ ላይ አቆሙት። ዲሞክራሲው ቀርቶ የአንዲት ኢትዮጵያ ህዝብነታችን፤ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ባለቤትነታችን በቀጭን ክር ላይ የተንጠለጠለ እጣፈንታ ሆኖ አረፈው። ዜጎች ተወልደው ካደጉበት አገር እንደ ባእድ ስደተኛ ሀብትና ንብረታቸውን እየተቀሙ ሲባረሩ፤ በተፈጠሩባት ምድር መድረሻ እንዲያጡ ተደርገው በየጎዳናው ሲወድቁ እያየን ምንም ማድረግ ተስኖን አፍጠን ተቀምጠናል።
በደቡብ ኢትዮጵያ፤ አማራ የተባለ ዜጋ፤ በሶማሌ ክልል  ጂጂጋ ሱማሌ ያልሆነ ሁሉ ንብረቱ እየተቀማ፤ እየታሰረ ቶርች እየተደረገ፤ እዚያው ተወልደው ያደጉ አማሮችና ሌሎች ብሄረሰቦች ግፍ እየተፈጸመባቸው ይህንን ተከታታና የማይቆም በእቅድ የተያዘ ጥቃት ማስቆም የቻለ የፖለቲካ ድርጅትም ሆነ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ብቅ ባለማለቱ የኢትዮጵያውያኑ ሰቆቃ እየባሰ በመሄድ ላይ ይገኛል። ወያኔና የክልሉ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ  የሱማሌ ባለስልጣናትና ፖሊሶች በመተባበር ይህን ዘመቻ ሲያንቀሳቅሱ፤ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ አለም አቀፍ ሰብአዊ ድርጅቶች ድርጊቱን ለማስቆም ያንቀሳቀሱት ሁለገብ ዘመቻ የለም። የህውሀትና የክልሉ ቅጥረኞቻቸው ዘመቻ ግን አላቋረጠም። ባጠቃላይ ወያኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለውን ህዝብና ኢትዮጵያን የማጥፋት ቀጣይ ተግባሩን ያለምንም እንቅፋት ማከናወኑን ቀጥሏል።  እራሳችንንና ሀገራችንን ለማዳን መነሳት ያስፈራን በሚምስል መልኩ የወያኔ መንጋ መጨፈሪያ መሆናችን ቀጥሏል።
ያለ ህዝብ ምክርና ዝክር መላውን የሀገራችንን መሬት ለባእዳን አሳልፎ መስጠቱ ቀጥሏል። ነገ ልጆቻችንን በገዛ ምድራቸው ላይ እያሳደዱ እሚገሏቸው ባእዳንን በብዛት እያስገቡ ማስፈሩ ቀጥሏል። በፍርሀት ተውጠን፤ ሀሞታችን ሸንቶ፤ እኛ አባቶቻቸው፤ ወንድሞቻቸው ተቀምጠን የልጆቻችንን ቅርስ ምድር ኢትዮጵያን ወያኔ ሲቸበችበው ዝም ብለናል።
ጀግና ህዝብ ታግሎ ዜጎች ነጻ ዳኝነት የሚያገኙበት ሉአላዊ የሆነ የፍትህ ተቋም ይገነባል። ዜጎች ሁሉ በህግ ፊት እኩል የሚዳኙበት፤ መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ ከሙስናና ከወገንተኝነት በጸዳ የፖሊስ ሰራዊት የአካልና የህግ ጥበቃ የሚያገኙበት፤  ስርአት ይገነባል። ዳኞች ከሙስናና ከአንድ ወገን ጉዳይ አስፈጻሚነት በጸዳ ህሊና ለዜጎች ደህንነት የቆሙ  መሆኑን ያለ ማንም ባለስልጣን ጣልቃ ገብነት በሚሰጡት  ነጻ ፍትህ ያረጋግጣሉ። ይህ በትግላችን እውን ሊሆን የሚገባው ስርአት ሀገራችንን እንደሰማይ እየራቃት፤ በመሄድ ላይ ይገኛል። በራሳችን ደካማነትና ፍርሀት።
በሀገርና በህዝብ ጉዳይ ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎች፤ የሚተገበሩ እርምጃዎች፤ ህግና ደንብን የተከተሉ መሆናቸውን እርግጠኛ ለማድረግ፤ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ህዝብ እያያቸው፤ እየሰማቸው፤ እየተነገረው፤ እየተነጋገረባቸው ሲሆን ፍትሀዊነት ይሆናል። በመንግሰትነት የተሰየመው አካል ያስተላለፈው፤ የሚያስተላልፈው ውሳኔ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካው የህብረተሰብ አካል፤ ቀጥተኛ ኢንፎርሜሽን ቀድሞ ሲያገኝና የሀሳቡ ተካፋይ ሲሆን፤ ጥቅሙንም ደህንነቱንም ለመጠበቅ እድል ያገኛል። በህብረተሰብ ህይወት ላይ የሚተላለፍ ውሳኔ ሰፊና ጥልቅ ምክክር ያስፈልገዋል።
ልንታገሰው የሚገባ መንግስት፤ አስተዳደር፤ ከህዝብ ለሚመጡ ሮሮዎችና አቤቱታዎች የመብት ረገጣ፤ የፍትህ ጉድለት፤ የመሳሰሉ ችግሮችን ፈጥኖ መስማትና መፍትሄ ለመሻት መንቀሳቀስ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል። በንቅዘት የበሸቀጡ ባለስልጣናት ከደሞዛቸው ጋር የማይመጣጠን ኑሮና ንብረት ሲያደረጁ ያየ ህዝብ፤ የሀገር ሀብት ለግል ጥቅም እየዋለ ነው ብሎ ቢያመለክት፤ መንግስት ውሎ ሳያድር እነዚያን ግለሰቦች የሀብታቸው ምንጭ ምን እንደሆነ እንዲያስረዱ ለዳኝነት የሚቆሙበትን የህግ ተቋም ማደራጀትና ጉዳያቸው ታይቶ ለጠያቂው ህዝብ ምላሽ የሚሰጥበትን ሂደት እውን ያደርጋል። ሌባውና ወንጀለኛው፤ ሙሰኛው እራሱ መንግስት ነኝ ብሎ ስልጣን ላይ የተጣበቀው ወገን በሆነበት ሀገር ከላይ የጠቀስኩት ነገር የማይታሰብ ነው። ብቸኛው አማራጭ አንባገነኑን ቡድን ከስልጣን አስወግዶ፤ በከርሰ መቃብሩ ላይ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት ነው።
ቀጣይነት ላለው የህብረተሰብ እድገትና ሰላም አስፈላጊ የሚሆነው፤ የህዝብን ታሪክ፤ ባህል፤ ማህበራዊ አኗኗርና መስተጋብር፤ የለት ተለት ያኗኗር ዘይቤን ግንዛቤ ውስጥ የሚያካትት ውሳኔና እርምጃ የሚያራምድ አስተዳደር መኖር ነው።

በህብረተሰብ ውስጥ እጅግ የተለያዩና አንዳንዴም የተራራቁ ፍላጎቶች አመለካከቶች መኖራቸው የተፈጥሮ ህግ ነው። እያንዳንዱን የህብረተስብ ክፍል እኩል ማስደሰት አይቻል ይሆናል። እስላምና ክርስቲያን በጋራ በሚኖሩባት ሀገር ውስጥ የክርስትያኑን ህዝብ ፍላጎትና መብት ከግምት ውስጥ ባለማስገባት አንድ ገዢ ቡድን ተነስቶ በሸሪአ ህግ ነው መተዳደር ያለብን በሚል፤ የእስላም መንግስት ቢያውጅ፤ በአንዲት የጋራ ሀገር ውስጥ ያንዱ ወገን ፍላጎትና ጥቅም የሌላውን ወገን ጉዳትና ቅሬታ አስከተለ ማለት ነው ። ለእንዲህ ያለ ህዝብ ሁሉንም የሚያስማማው አለማዊ መንግስት ይሆንና ሁሉም የማምለክ ነጻነቱ ተከብሮለት ሲኖር ማለፊያ አሰራር ይሆናል።
የህብረተሰብ ደህንነት የሚረጋገጠው፤ እያንዳንዱ ክፍል ከህዳጣን እስከ ብዙሀን ሕዝቡን የገነቡ ብሄረሰቦች  እኩል መብትና ነጻነት ሲኖራቸው፤ በሀገራቸው እኩል የባለቤትነት ስሜት ሲኖራቸው፤ በባህላቸው፤ በቋንቋቸው፤ በሀይማኖታቸውና በኑሮ ደረጃቸው ምክንያት ያለመገፋት፤ ያለመገለል፤ መኖሩን በተጨባጭ ማየት ሲችሉ ነው።
በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ቀና ብሎ እንደልቡ እየተናገረ መኖር የያዘ ዜጋ ወያኔ ብቻ ሆኗል። ሰፊው ህዝብ ተሸማቆ በመኖር ላይ ነው። በግል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ እንኳ እንደፈለገ የፈለገውን ጮክ ብሎ ማውራት እያስፈራው መቷል። የወያኔ ጆሮ ጠቢዎች በየሰዉ ጣራ ስር ጨለማ ለብሰው እየተለጠፉ ዜጎች የሚያወሩትን ወሬ እየሰበሰቡ ለቅርብ ሀላፊያቸው ያቀርባሉ። ፈጥኖ ፈጥኖ ከውጭ አገር ስልክ የሚደወልላቸው ሰዎች ይተኮርባቸዋል። አንዳንዶች በቤታቸው ዙሪያ ማንም እንዳይቆም ስልክ ሲደወልላቸው ልጆቻቸውን አሰማርተው ነው እንደልብ የሚያወሩት።
ተጠያቂነት የጤናማ መንግስት ያስተዳደር ስራ ደንብ ነው። የመንግስት ተቋማትና  ባለስልጣናት ብቻም አይደሉም፡ የግል ድርጅቶች ማህበራትና ተቋማት ጭምር የሀይማኖት የእምነት እና የሙያ ማህበራት ጭምር ሀላፊነት ለጣለባቸው ወገን፤ ለሚያገለግሉት ህዝብና ለሚተዳደሩበት ህግ ተጠያቂ ናቸው። ተጠያቂነት ግልጽነትንና ለህግ ተገዥነትን ያካትታል። ተጠያቂነት የዲሞክራሲ ስርአት አንኳር ግብአት ነው። የመንግስት ባለስልጣናትና ሀላፊዎች እንደየደረጃቸው በህግ የሚሰጣቸው ስልጣንና ሀላፊነት አለ። ያ ህጋዊ ስልጣንና ሀላፊነት ለሚያስተዳድሩት ህዝብ አገልግሎት የሚሰጡበት ልክና ደረጃ ነው። ተጠያቂነቱ ስልጣናቸውን ባግባቡ እየተጠቀሙ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድዳቸው ያሰራር ፈርጅ ነው።
አሁን በሀገራችን ጥያቄው ተጠያቂነት አለ ወይስ የለም አይደለም። በሀገራችን ተጠያቂነት የለም። ስርአቱን ሙሉ ለሙሉ እከምናስወግድ ድረስ እንኳን ቢሆን እስካሁን ለፈጸማቸው ወንጀሎች ይህን ገዢ ቡድን እና ባለ ስልጣናቱን እንዴት ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል? ተቆጥሮ ከማያልቀው ወንጀላቸው የቅርቡን “ጂሀዳዊ ሀረካት” እንውሰድና የዜጎችን መብትና ነጻነት፤ ሰብአዊ መብት በእጅጉ የረገጠ፤ ለይስሙላ አለ የተባለውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር፤ በፍርድ ሂደት ላይ ያለን ጉዳይ በመገናኛ ብዙሀን በማሰራጨት ተራ የፖለቲካ ጠቀሜታ ለማግኘት መንግስት ነኝ ያለ ቡድን  የፈጸመው ወንጀል ነው። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ማስታወቂያ ሚኒስትሩን በተዋረድ የተሳተፉትን በሙሉ ለፍርድ ማቅረብ ያስፈልጋል። ይህ ፊልም የታለመለት ወንጀል የሙስሊም ወንድሞቻችንን ሰብአዊ መብትና  የሀይማኖት ነጻነት መጋፋት ብቻ ሳይሆን ህዝብን ከህዝብ፤ ክርስትያንን ከሙስሊም ለማጋጨት ሆን ብሎ ይህ ስልጣን ላይ ያለው ማፊያ ቡድን ያዘጋጀው ወንጀል ነው። የህውሀት ምግብ ለስራ ሰራተኞች የተሰበሰቡበት ምክር ቤት፤ ስልጣኑ የሚፈቅድለትን ነገር ባለማድረጉ፤ የዚህን ወንጀል ፈጻሚዎች ለጥያቄ ባለማቅረቡ ለራሱም መጠየቅ የሚገባው፤ መበተን የሚገባው የመንጋ ጥርቅም ነው።
የወያኔው ተረት ተረት ህገመንግስት አንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 2 ማንኛውም ሀላፊና የህዝብ ተመራጭ ሀላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ ይሆናል ይላል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪዎች ናቸው። ሚኒስትሮችም በውሳኔአቸው ተጠሪዎችና ተጠያቂዎችም ናቸው። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ወንጀል ይፈጸማል። ጠያቂም ተጠያቂም የለም። ወያኔን ከስልጣን በማስወገድ ለፈጸሙት ወንጀል ሁሉ ሁሉንም ለፍርድ በማቆም ተጠያቂነትን ማስተማር ይገባናል። ፖሊስ የህሊና እስረኞችን ቶርች በማድረግ፤ ያልፈጸሙትን ወንጀል እንደፈጸሙ አድርጎ በስቃይ እንዲናገሩ በማድረግና ያንን በቴፕ በመቅዳት፤ ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ፤ ህዝብ በመገናኛ ብዙሀን እንዲሰማውና መቀጣጫ አድርጎት አርፎ እንዲቀመጥ ለማድረግ፤ ወደር የማይገኝለት ግፍ በንጹሀን ዜጎች ላይ በመፈጸሙ፤ የደህንነቱ ክፍል የዜጎችን የግል ሚስጢር ለመሰብሰብ፤ የስልክ፤ የኢሜል፤ የፖስታ መልክቶችን በመጥለፍ፤ በመስረቅ፤ በከፍተኛ ወጭ አንድ ሰላይ ለአምስት ዜጋ በመመደብ ህዝቡ የህሊና ሰላም አቶ እንዲኖር፤ በጭንቀት ተወጥሮ ስለግሉ ደህንነት እየሰጋ በወያኔ ገዢ ቡድን ላይ እንዳይነሳ ለራሱ ተሸብሮ እንዲኖ ሴራ በመኖንጎን፤ ዳኞች ህሊናቸውን ለጥቅም በመሸጥ የሀሰት ምስክርና የውሸት ክስ፤ የሀሰት ማስረጃ ተቀነባብሮ ሲመጣላቸው ህሊናቸው እያወቀ፤ የአረመኔዎቹ መንግስት ጠባቂና ተንከባካቢ በመሆን ንጹሀን ዜጎችን በሞትና በእድሜልክ እስራት ፍርድ በመቅጣታቸው፤ ሁሉም የጃቸውን ማግኘት ይገባቸዋል። ለፍርድ መቅረብ ይገባቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን በጉልበት ስልጣን ላይ ተጣበቀው፤ እየገደሉ፤ እያፈኑ፤ ወህኒ እያጎሩ፤ እያሸበሩ ስልጣን ላይ ለመዝለቅ የቆረጡ የህውሀት  አመጸኞችን በአመጽ አስወግዶ፤ እውነተኛው ፍትህ ርትእ የሚነግስበትን ስርአት ገንብቶ፤ ዛሬ ግፍ እየፈጸሙበት ያሉትን ወያኔና ቅጥረኞቻቸውን ሁሉ እግር ተወርች አስሮ ለዳኝነት ማቆም ያስፈልጋል።
የጊዜ ጉዳይ ነው። እድሜልኩን ተኝቶ ሲረገጥ የኖረ ህዝብ በአለም ላይ የለም።  የኢትዮጵያ ህዝብም ተረግጦ ለመኖር አይደለም የተፈጠረው:: ታፍኖ፤ ተረግጦ፤ ተገድሎ በዚህች በሰለጠነች አለም ውስጥ ለምእተ አመት ያህል በመኖር ሁሉንም መከራ አጣጥሞታል። ብዙ የግፍ ጽዋ ተጎንጭቷል፤ እየተጎነጨም ነው። አሁን የቀረው ነገር ማንንም ሳይጠብቅ አንድ ቀን መገንፈል። የቀረው ነገር…. በቃ! ብሎ በአንድ ድምጽ፤ አንድ ቀን መፈንዳትና እነኚህን የወረሩትን ትንኞች ከትከሻው ላይ ማርገፍ…. ማውረድ ብቻ ነው!
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!…ሞት ለዘረኞች!
lkebede10@gmail.com

ቦሌ ለሚ ኮብልስቶን በሚሰሩ ሰዎችና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 8 ሰዎች ሞቱ

  በአዲስ አበባ ከተሰሩ የኮብልስቶን ሥራዎች መካከል (ፎቶ)
አዲስ አበባ በሚገኘው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ ቦሌ ለሚ በሚባል አካባቢ ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን
2005ዓ.ም. ኮብልስቶን በሚሰሩ ሰዎችና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 8 ሰዎች መሞታቸውንና
በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ተጠቆመ፡፡
በፍኖተ ነፃነት ዘጋቢዎች የተጠናቀረው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ የግጭቱ መንስኤ የሞባይል መጥፋት
እንደሆነ እና በዚህም ኮብልስቶን ትሰራ የነበረችን የአንዲት የአካባቢው ነዋሪ ሴት ጡት ሌላው ሰራተኛ በመቁረጡ
ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ በአካባቢው ነዋሪዎችና በኮብል ስቶን በአዲስ አበባ ከተሰሩ የኮብልስቶን ሥራዎች መካከል(ፎቶ)ሰራተኞቹ መሀከል ግጭት ተነስቷል፡፡ በዛው ዕለት
ፀቡን ለማረጋጋት የሞከረ ፖሊስም በኮብልስቶን ተመቶ ወዲያው ህይወቱ ማለፉን ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት ተለውጦ ፀቡ እስከ ሐሙስ መጋቢት 5 ቀን መዝለቁንና ህይወቷ
ያለፈው ወጣት የአካባቢው (ኦሮሚያ) ተወላጅ በመሆኗ ጉዳዩ ወደ ማኀበረሰቡ በመድረሱ በርካታ የአካባቢው ሰዎች
ከአያት ኮንዶሚኒየም እስከ ቦሌ ለሚ ድረስ ከበባ በማድረግ በሰራተኞች መካከል የኢህአዴግ አደራጅና ሰላይ
ናቸው የተባሉ 6 የወላይታ ተወላጆችን በመግደልና በርካታ ሰዎችን በማቁሰላቸው በአካባቢው ከ3 ተሸከርካሪ ያላነሱ
የፌደራል ፖሊሶች ግጭቱን ለማረጋጋት ቢገኙም ለማረጋጋት እንዳልቻሉ ሆኖም በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችን
ወስደው እንዳሰሩ የዓይን እማኞች ገልፀዋል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ከፖሊስ ወገን የተሰጠ ማረጋገጫ
የለም፡፡
የዝግጅት ክፍሉ ጉዳዩ በቀጥታ ይመለከተዋል ወደ ተባለው ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መረጃ ክፍል ስለጉዳዩ
ለማረጋገጥ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ዘገባው ወደ ህዝብ እንዲደርስ እስከተደረገበት
መጋቢት 7 ቀን 2005ዓ.ም. ድረስ ቀደም ሲል በርካታ ሰዎች የኮብልስቶን ስራ ይሰሩበት የነበረው አያት ጨፌ እና
ቦሌ ለሚ
የሚባል አካባቢ ማንም ሰው እንዳይገባ የተደረገ ሲሆን ከሰራተኞች ጋር እዛው በሚገኝ ቀበሌ ለጊዜው ማንነታቸው
ያልታወቁ የመንግስት ባለስልጣናት እያወያዩ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
ችግሩ እስኪፈታም በአካባቢው እስከ ሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2005ዓ.ም. ድረስ ስራ እንደለሌም ምንጮቻችን
ከስፍራው ጠቁመዋል፡፡

(ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ)

“ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ” – የ67 አመቷ እናት

“ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ ሲሉ አንዲት የ67 አመትባልቴት በተለይ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ አስታወቁ፡፡
ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የሚባሉት እኚሁ እናት የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት ባለቤታቸውም እንደ እሳቸው ሁሉ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘጋቢ
ከዕንባቸው ጋር እየታገሉ አስረድተዋል፡፡
“በሐረር ከተማ ቀበሌ 17 ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ኖሬ፤ ሀብትና ንብረት አድርቼ እኖር ነበር አሁን ግን በአካባቢው
እንዳልኖር ተደርጌያለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ “ከ30 ዓመት በላይ የኖርኩበትን ቤቴን የወረዳው
አስተዳዳሪ እና የወረዳው ፓሊስ አዛዥ አስጠርተው ቤትሽን ለወ/ሮ አኒሳ መሐመድ ሸጠሽ ግቢውን
እንድታስረክቢያት አሉኝ፡፡ እኔ ቤቴን የመሸጥ ሐሳብ የለኝም፡፡ ቤቴን ሸጪ የት እወድቃለሁ? አልሸጥም አልኳቸው
እንቢ ካልሽ ከአገራችን እናባርራሻለን በገንዘብ አልሸጥም ካልሽ በባዶሽ ተባረሽ ወደ አገርሽ ትሄጃለሽ አሉኝ፡፡ እኔ ሌላ
አገር የለኝም የምሄድበትም ቦታ የለኝም መንግስት ባለበት አገር ቤትሽን ተቀምተሽ ውጪ የሚለኝ የለም ብዬአቸው
ተመለስኩኝ” በማለት የችግሩ መነሻ ነው ያሉትን ጉዳይ ወደኋላ መለስ ብለው ያስረዳሉ፡፡ ጎስቋላዋ የ67 ዓመት
ባልቴት በመቀጠልም “በማግስቱ እኔ ቡና አፍልቼ፣ ባለቤቴም ጫማውን አውልቆ ፍራሽ ላይ አረፍ ብሎአል፤ አንድ
ፓሊስ በሩን በሰደፍ እና በእርግጫ መቶት በሩን በረገደው፡፡ ምንድነው? ብለን ስንወጣ ከ30 በላይ ፓሊሶች
ቤታችንን ከበውታል፡፡ ይህች ናት፡፡ ነይ ውጭ! ብሎ ለሁለት ሶስት ሆነው ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምን አደረኩ ብዬ
ስለምናቸው አንቺ ለህግ አልገዛ ያልሽ አመጸኛ ነሽ! ወንጀለኛ ነሽ እያሉ መሬት ለመሬት ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምንም

የሰራሁት ወንጀል የለም ብዬ ጮኩኝ፡፡ ጎረቤት ተሰበሰበ ምንድነው ብሎ ጠየቀ ማንም ምላሽ አልሰጠም” የሚሉት ወ/
ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ሟች ልጃቸውን በሀዘን ተውጠው እያስታወሱ ይቀጥላሉ “ልጄ ባል አግብታ የምትኖረው ሌላ ቦታ
ነው፡፡ ቀን ቀን ምግብ እየሰራች ትሸጣለች ፓሊሶች እናትሽን ከበው እየደበደቡ ናቸው ብሎ ጎረቤት ሲደውልላት ሮጣ
መጣች፡፡ ደርሳ ምን አድርጋ ነው ብላ ብትጠይቅ ቤቱን አስረክቢ ስትባል እንቢ ብላ ነው አሏት፡፡ የተወለድንበትና
ያደግንበትን ቤት ከህግ ውጭ እንዴት እንነጠቃለን ብላ ስትጮህ ጥላው ሄዱ” በማለት በለቅሶ ያስረዳሉ፡፡
ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ በመቀጠልም “ያንለቱኑ ማታ ልጄ ምግብ የምትሸጥበት ቦታ ሁለት ሰዎች ተመጋቢ መስለው
ከገቡ በኋላ (ረመዳን የተባለ ፓሊስና እንዳለ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ(ከሀረር ጠሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸው
የተባረሩ አዛውንት) ግርማ የተባለ ወጣት) ቤቱን አስረክቡ ስትባሉ አናስረክብም የምትሉት ለምንድነው ብለው
ረመዳን ልብሷና ሰውነቷ ላይ ጋዝ ሲደፋባት እንዳለ ግርማ የተባለው ላይተር ለኩሶ አቃጥለዋታል፡፡ ሳትሞት ሆስፒታል
ደርሳ ነበር፡፡ በማግስቱ አዲስ አበባ አምጥቼ ላሳክም መኪና ተከራይቼ ይዤ ስወጣ ፓሊስ እዚህ ትታከም እንጂ ከሐረር
አትወጣም ብሎ ከለከለኝ፡፡ እኔም ገንዘብ ካለኝ እንኳን አዲስ አበባ አሜርካን ወስጄ ባሳክም ለምን እከለከላለሁ ብዬ
ብጮህ ባለቅስ ማንም ሊደርስልኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ህክምና አጥታ ሞተች፡፡” ብለዋል፡፡ ባልቴቷ ከልጃቸው ሞት በኋላ
የደረሰባቸውን በምሬት ያወጋሉ “እኔንም ከቤቴ አስወጥተው ቦታውን ሺጭላት ላሏት ሴት ሰጧት፡፡ አሁን ቦታዬ ላይ
ፎቅ እየተገነባ ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ ግን ጎዳና ተጣልን፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ አዋጥቶ የሰጠኝን 3ሺ ብር እንድ
ፓሊስና አንድ ደላላ መጥተው ነጠቁኝ፡፡ ሐረር ውስጥ አደሬ ወይም ኦሮሞ ካልሆንክ አቤት የሚባልበት ቦታ የለም፡፡
አማራ ነው ከተባለ ሁሉም ባለስልጣን በደረሰበት ግፍና ስቃይ ይስቅበታል፡፡ በደርግ ጊዜ የሐረር ፓሊስ አዛዥ ትግሬ
ነበር፤ የማረሚያ ቤት አዛዥም ትግሬ ነው፡፡ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ትግሬ ነው፡፡ ለምን ትግሬ ሆነ ያለ አንድም ሰው
የለም፡፡ ዛሬ በሀረር በየትኛውም መስሪያ ቤት አማራ ባለስልጣን የለም፡፡ ባለቤቴ ኦሮሞ ነው፡፡ ልጆቼም ኦሮሞ ናቸው፡፡
እኔ አማራ በመሆኔ ብቻ ይህ ሁሉ ጉዳት ተፈጸመብን፡፡” የሚሉ ወይዘሮዋ የተፈፀመባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት
ዘራቸውን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አክለውም “አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቃ ተቋም አመለከትኩኝ፡፡
ፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም እንዴት እንዲህ ይፈጸማል ብለው ይዘውኝ ሐረር ተመለሱ፡፡ የቤቴ ካሳ እንዲከፈለኝ
ተወሰነልኝ፡፡ የክልሉ ባለስልጣናትም እሺ ይፈጸምሎታል ብለው ቃል ገቡልኝ፡፡ እንባ ጠባቂዎቹ ወደ አዲስ አበባ
ተመልሱ፡፡ እነሱ ከተመለሱ በኋላ ግን ምንም መፍትሄ አልሰጡኝም፡፡ በድጋሚ አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቂ
ተቋም ባመለክት እነሱም ውሳኔያቸውን እንደ አጀማመራቸው ሊያስፈጽሙልኝ አልቻሉም፡፡ ጉዳዬንም ለመስማት
ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡” በማለት የበደላቸውን ስፋት ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
“ዛሬ እኔ አዲስ አበባ ላይ ባለቤቴ ደግሞ ሐረር ላይ ጎዳና ላይ ነን፡፡ መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም” ሲሉ ተስፋ
መቁረጥና ምሬት ተሞልተው በለቅሶ የመንግስት ያለህ … የህዝብ ያለህ በማለት ጥያቸውን ያቀርባሉ፡፡
የወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማን ጉዳይ አስመልክቶ የፌደራሉ እንባ ጠባቂ ተቋም ለሐረሪ ክልላዊ መንግስት ጸጥታ ቢሮ
የጻፈውን ደብዳቤ እንደተመለከትነው ደብዳቤው ከዚህ በፊት ስለጉዳዩ ተጠይቆ መልስ አለመስጠቱን በማስታወስ
አሁን በድጋሚ በ 15 ቀን ውስጥ መልስ እንዲሰጥ ያለበለዚያ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ
እንደሚወስድ የሚገልጽ ነው፡፡ ሆኖም የእምባ ጠባቂ ተቋም ውሳኔ ባልቴቷንና ባለቤታቸውን ከጎዳና ተዳዳሪነት
የሚታደግ አልሆነም፡፡ በጉዳዩ ላይ የፊደራል እንባ ጠባቂ ተቋም አስተያየት እንዲሰጥበት ወደ ተቋሙ ህዝብ ግንኙነት
ክፍል በማምረት ባለሙያዎችንም አነጋግረን ነበር፡፡ በቅድሚያ ያነጋገርናቸው የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ጉዳዩን
ከስሙንና በእጃችን ያለውን መረጃ ከተመለከቱ በኃላ ወደ ሌላው የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ መሩን፡፡እሳቸውም
በተመሳሳይ ሁኔታ ማስረጃችንን ከተመለከቱ በኃላ ይህንን ጉዳይ የሚያውቁት ዋና አማካሪው አቶ ቀነአ ሶና ናቸው፡፤
እሳቸውን አነጋግሩ አሉን፡፡ አቶ ቀነአን በወቅቱ ማግኘት አላቻልንም፡፡ በሌላ ጊዜ ተመልሰን ቢሮአቸው ያሉትን
የተቋሙን ሰራተኛ አቶ ቀነአን እንደምንፈልግ አስረዳናቸው፤ አቶ ቀነአን ወደ መስክ ወጥተዋል፡፡ ሰሞኑን ቢሮ
አይገቡም አሉን፡፡ በዚህ ምክንያት የፌደራሉን እንባ ጠባቂ ተቋም አስተያየት ማካተት አልቻልንም፡፡ ጉዳዩ ተከቷል
ወደ ተባለለት ወረዳ ፖሊስ ደወልን የሐኪም ወረዳ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ሀላፊ የሆኑትን ሳጂን ተሾመ ሰይፉን
አግኝተናቸዋል፡፡ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ደረሰብኝ የሚሉትን በደል ወቅቱን ጠቅሰንም አስረድተናቸዋል፡፡ ሆኖም
ሳጂን ተሾመ ሲመልሱ ‹‹እኛ ፖሊሶች በየሁለት ዓመቱ እንቀያየራለን፡፡ አሁን በዚህ ወረዳ ያለነው ከሁለት ዓመት
ወዲህ ተዛውረን የመጣን ነን፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት በወረዳችን ሮመዳን የሚባል
ፖሊስ የለም፡፡ ምናልባት የወረዳው መስተዳድር የሚያውቁት ነገር ካለ እነሱን ብትጠይቁ ይላል፡፡›› በማለት
መልሰውልናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያሉትን የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ኢስማኤልንም ስለጉዳዩ ጠይቀን በሰጡን መልስ
‹‹እኔ በቅርብ ጊዜ ነው የመጣሁት ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፡፡ የሚያውቁት ነገር ካለ ከእኔ በፊት የነበሩትን
ጠይቋቸው›› ብለውናል፡፡ ከእሳቸው በፊት የወረዳው አስተዳዳሪ የነበሩትን አቶ ጀማል አህመድን አፈላልገን
ጠየቅናቸው፡፡ “እኔ ድርጊቱ ተፈፀመ በምትለኝ ወቅት እዚያ ወረዳ አልሄድኩም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር
የለም፡፡ ከእኔ በፊት የነበረውን ሰው አፈላልጋችሁ ጠይቁ ብለውናል፡፡” ከእሳቸው በፊት የነበሩትን አስተዳዳሪ ማንነትና
አድራሻ ማግኘት ባለመቻላችን ዜናውን በተገቢው ሁኔታ ሚዛናዊ ማድረግ አልቻልንም፡፡
ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ

Mar 16, 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ መቱ፤ ኮሌጁ በፖሊስ ተከቧል

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እየታመሰ መሆኑ ተሰማ። ኢሳት ራድዮ ዛሬ እንደዘገበው ተማሪዎቹ የአስተዳደር
ጥያቄ በማንሳት ረቡዕ እለት የተጀመረው የትምህርት ማቆም አድማ እስከዛሬ አርብ ድረስ ዘልቋል። የመንፈሳዊ ኮሌጅ
ተማሪዎች ለዚህ ዓመት ካነሳሳቸው ምክንያቶች መካከል ከአስተዳደር ጥያቄ፣ ከምግብ ጥራት፣ ከአስተማሪዎች ብቃት
በተጨማሪ የአዲሱ ፓትርያርክ ጉዳይም ሊያያዝ እንደሚችልም ኢሳት ዘግቧል። ተማሪዎቹ ምግብ ተከልክለዋል።
የኢሳትን ዘግባ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።












ዜናውን ላልሰማ ያካፍሉ

Mar 15, 2013

ትግላችን ይቀጥላል

ድምፃችን ይሰማ

አንዋር መስጊድ ነገ ጭር ይላል!
የድምጻችን ይሰማ ሕዝባዊ መነሳሳትና ተቃውሞ በግፍ ለእስር በተዳረጉት መሪዎቹ ቃል ኪዳን ታስሮ የስኬት ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ትግላችን ድንበሮችን አቋርጦ ክልሎችን ከክልሎች፣ ከተሞችን ከከተሞች እንዲሁም ሕዝቦችን ከሕዝቦች ከምንም በላይ ልቦችን ከልቦች ጋር አስተሳስሮ እየነጎደ ነው፡፡ አልሀምዱሊላህ! ይህን ክብር እና ስኬት ያሳየን አላህ (ሱ.ወ) ምስጋና ይገባው፡፡ በዚህ ሳምንት በሚደረጉ ሁሉን አይነት ተቃውሞዎች የምናንጸባርቀዉ ዋነኛ ሀሳብም ትግላችን እያደገ፣ መስዋእትነታችንም እያየለ ግን ደግሞ ጥንካሬያችንና ስኬታችን በአስተማማኝ መሰረት ላይ እየተገነባ መሆኑን ማሳየት እና ትግላችንም እንደሚቀጥል ማስገንዘብ ነው፡፡ትግላችን ይቀጥላል
በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ የሚኖረው ተቃውሞ ወደ ታላቁ አንዋር መስጊድ ባለመሄድና መስጊዱን ጭር በማድረግ የሚገለጽ ነው፡፡ ዘወትር ለተቃውሞም ሆነ ለጁምአ ሰላት የምንሄድ ሁሉ የነገውን የጁምአ ሰላት በሌሎች አማራጭ መስጊዶች በመስገድ ብቻ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
ተቃውሞአችን በድምጽ በሚደረግባቸው ከተሞች የሚኖረው ጠንከር ያለ ተቃውሞ ዝርዝር የአፈጻጸም መርሐ ግብሩ ይህን ይመስላል፡፡
ኢማሙ የጁመዓ ሰላት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በአንድ ከፍ ያለ ድምፅ:-
• የአላህን ታላቅነት ለማሳየት ለሦስት ደቂቃ ‹‹አላሁ አክበር!››
• የተቃውሞችንን መሪ ቃል እና የተቃውሞችንን መንፈስ ለመግለጽ ለሦስት ደቂቃ ‹‹ድምፃችን… ይሰማ!››
• መንግስተ የመብት ጥያቄ ሂደታችንን ከሽብር ተግባር ጋር በማያያዝ ሕዝቡን አሸባሪ ለማለት ደፍሯል እኛ ግን ሰላም መርሁ የሆነው የኢስላም ተከታዮች መሆናችንን ለማስገንዘብ ለሦስት ደቂቃ ‹‹ኢስላም… ሠላም!››
• መሪዎቻችንን ጨምሮ ያለጥፋታቸው ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ ታስረው በመላዋ አገሪቱ ወህኒ ቤት የሚገኙ ሁሉ እንዲፈቱ ለሦስት ደቂቃ ‹‹የታሰሩት….ይፈቱ!››
• ብሄራዊ ውሸታቸውን በየእለቱ እየጋቱን ላሉት መንግስት ብዙሀን መገነኛዎች ከሀሰተኛ ዘገባዎች እንዲቆጠቡ ለመንገር ለሦስት ደቂቃ ‹‹ውሸት …. በቃን!››
• ጥያቄዎቻችን በማያዳግም መልኩ እስካልተመለሱ ድረስ ትግላችን እንደማይቋረጥ እና ሕዝባዊ መሰረት ላይ የተገነባ መሆኑን ለማመልከት ለሦስት ደቂቃ ‹‹ትግላችን….ይቀጥላል!››
• በመጨረሻም ሁላችንም ባለንበት ለሦስት ደቂቃ ወደ አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ የመጣብንን በላእ እንዲያነሳልን ዱዓ በማድረግ የዕለቱ ተቃውሞ ይጠናቀቃል-ኢንሻ አላህ፡፡
ይህን በቁጥር በርካታ በሆኑ ከተሞች የሚደረገው ተቃውሞ ላይ ሁሉም በተጠቀሱት ከተሞች ላይ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ሁሉ በነቂስ ወጥቶ እንደሚሳተፍበት ጥርጥር የለንም፡፡ ይህ እለት ዳግም አንድነታችንን፣ ጥንካሬያችንና ለመሪዎቻችን ያለንን ታማኝነት የምናሳይበት ነው፡፡
አላሁ አክበር!

Mar 13, 2013

Tamagne Beyene: Ethiopian Hero


by MeKonnen H. Birru, PhD

Artist Tamagne Beyene Ethiopian Hero
The thing about a hero, is even when it doesn’t look like there’s a light at the end of the tunnel, he’s going to keep digging, he’s going to keep trying to do right and make up for what’s gone before, just because that’s who he is.
Joss Whedon
A hero is a defender. A hero is a protector. A hero is a rescuer. The legendary Ethiopian writer Dr. Haddis Alemayehu (1902 – 2003) portrayed Gudu Kassa as a ‘hero’ in his classical work Fiqir Iske Meqabir (Love Unto Grave’. Gudu Kassa (Kassa Damte) was a nobleman by birth but refused all for the sake of his progressive ideas. He fought for individual liberty and freedom. He became a defender of his people, not his class, nor his race, nor his family power. He fell in love and married a working class woman while he was a noble because he saw love in her, nothing else. To him and so many millions of Ethiopians, love is the essence of life and the root of every particle, motion, foundation, liberty, freedom and expression. Love is our Ethiopian culture and our norm. And now these three remain; faith, hope, and love. But the greatest of these is love (1 Corinthians 13:13).
In our times too, we have several heroes who believe in such love, liberty, faith, and peace. They are crying for our liberty. They are crying for our believed country: Ethiopia. They cry for love, equality, and fairness. Tamagne Beyene is one among many. Tamagne was born in Ethiopia; grow up in Ethiopia, and becoming Ethiopia. His entire families were from Ethiopia. They all love their country and understand the beauty of love, kindness, respect, and compassion. They are the true faces of Ethiopia.
On the other hand, we have brothers and sisters who decided to be dark and evil. They want us to go back. They want us to count our bones. They want us to be divided in terms of race, power, province, and religion. I tell you such are not from God but evil. ‘Turn from evil; do good; seek peace and pursue it (Psalms 34:14). I tell you again anyone who purposefully tries to deprive our liberty, unity, and one nation for the sake of security are wrong and from evil. Benjamin Franklin stated any society that would give up a little liberty to a gain a little security will deserve neither and lose both.’
Lord Acton wrote, “Liberty and good government do not exclude each other, and there are excellent reasons why they should go together. Liberty is not a means to a higher political end. It is itself the highest political end. It is not for the sake of a good public administration that it is required, but for the security in the pursuit of the highest objects of civil society, and of private life.”
Long live mother Ethiopia.
God be with us.

Mar 11, 2013

ለኢትዮጵያ እንድረስላት ይህን ሳናደርግ የቀረን እንደሆነ ግን ህሊና ቢስ ነን ፍሬ ቢስ ነን ወይም ደግሞ ከሃዲ ነን

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁናቴ ህዝቡ ዕድሉን አግኝቶ ወደውጭ የወጣ እንደሆነ ወደ ዓገር ቤት ተመልሶ ቢገባ የጭንቅላት በሽተኛ ወይም እንደ እብድ አልያም እንደ ሞተ

autor yared elias Brehane
ያሬድ ኤልያስ
ሰው ተቆጥሮ የህድር ጡሩንባ ተለፍፎ ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ የሚላቀስበት አልያም ደግሞ ከቤተሰብ ትዳር አንስቶ የሰፈር ሰው ትንሽ ትልቁ የስራ ባልደረባ ከታክሲ ሹፌር እስከ ዶክተር እስከ ትልቁ የወያኔ አገዛዝ ሚኒስቴር ድረስ እንደዘመኑ በሽታ ታይቶ የምትገለልበት ወሬው ሁሉ እንትና ደቡብ አፍሪካ ጠፋ በሞያሌ በሱዳን ሊቢያ  እየተባለ ስንቱ  ተስፋ ቆርጦ የሱሰኛ ተገዢ የሚደረግበትዘመን። ሌላው ይቅርና  እትብቱ ወደተቀበረበት ሃገር ለመመለስ እንኳን የወያኔ ገዢ ፓርቲ 10 ግዜ እንድናስብ የሚነግረን ወቅት  እንደነገሩ ተበልቶ አንዲት ለስላሳ ለመጠጣት 20 ግዜ የሚታሰብበት ቢራ ለመጠጣት ዱቤ ለመጠየቅ 40 ግዜ የሚታሰብበት ሃገር።  ስለ እውነት ስለነጻነት ቢጠየቅ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል መልሱን ? ..ለነሱ……… fየሚባለበት ግዜ ።
መቼስ አገሩ ላይ መኖር የሚጠላ ስው ያለ አይመስለኝም ግና ገና አካሉ አገሩ ላይ ቍጭ ብሎ መንፈሱ ውጭ አገር ያለውን ስንቱ ይቍጠረው። በውጭ ሃገር የሚኖረውማ  ወደ ሃገሩ ተመልሶ ሃገሩ ላይ ሃገሩን ወገኑን ለማገልገል የፈለገ ሰው ሃገሪቷ ላይ መኖር የማይችልበትን የጥቂት ዘረኛ ወያኔ አገዛዝ መንግስት የሚኖርባት በመሆኑ ለማድረግ አይችልም። በዛ ላይ ሰሞኑን ያየሁት የሰለሞን ቦጋለ እና ሳምሶን ቤቢ ፊልም በጣም ሲከነክነኝ ነው የዋለው አዎ የዚህ ደራሲ በፈለገው መልኩ ይጻፈው እኔ በተረዳውት ግን ለዚያች አገር ለዛ ህብረተሰብ ነጻነት ያስፈልገዋል ። መልዕክቱን በፈለጉት መልኩ ያስተላልፉት ግን በደንብ የሚታይ ነገር ነበረበት ስለነጻነት ብሩህ ተስፋ ።
ለነገሩ ወያኔዎች አገራቸው አይደልም  የመጡበትን ዓላማ አሳክተዋል።  የስራውን ይስጠውና ሟቹ ስሙን ቄስ ይጥራውና አገሪቷን በዘር በዓይማኖት በብሄር ከፋፍሎ ሰዉ በጎሪጥ እንዲተያይ አድርጎት እሱ ወደማይቀረው ሄዷል ምን አለ የሱ ተከታዮችም ይሄ መኖሩን አውቀው ወደ ህዝቡ በተመለሱ። አገሪቷማ  ስንቱን አሳድጋ እንጡራ አብቷን አውጥታ ያስተማረችውን የተማረ ዓይል ስንት ድግሪ ፕሮፌሰር ያደረገችውን ሃገር እየተወ መመለሻም መቀበሪያም ላትሆነው ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተሰድዶ በአሁኑ ሰዓት በስደት ላይ ይኖራል ። እንዲህም ሆኖ ለሃገር የተቆረቆሩ የሚመስሉ ከሃዲ ሆዳም እነዚህን ሰዎች ባሉበት ቦታ እንኳን እንዲቀመጡ አያደርጓቸውም እንዲያውም ብለው ወያኔ ለሃገር እንደሚቆረቆር ያወራሉ  ለነገሩ የትኛው የወያኔ ሃገዛዝ መንግስት ነው ለሃገሩ የሚቆረቆረው በዛ በበረሃ የማንም ተኩስ መለማመጃ ሆነው እነደሻማ ቀልጠው ሲቀሩ ሴት እህቶቻችን ማንም ሳይደርስላቸው እንደበግ መሬት ለመሬት ሲጎተቱ ዝም ብሎ  በደፈናው ሃገር ሃገር ማለት መብራትና ውሃ በሌለበት ሰዉ በፈለገውና በሚታየው መልኩ የራሱን ሃሳብ መግለጽ የማይችልበት ከታክሲ ዳቦና ወዘተ የመሳሰሉት ሰልፍ በስተቀር 3 ሰው እንኳን አብሮ ቆሞ ማውራት የማይቻልበት ወያኔ ለህዝቡ ካልሰረቀና ሙስና ካልሰራ መሻሻል የማይቻልበት ሃገር ለዚች አገር ነው ተቆረቆረ የሚባለው። ውድ ወገኖች ስለዚህ ለዘመናት ባአባቶቻችን በጥረታቸው የተገነባች የገነቧትን ሃገር ወያኔ ደግሞ በግዴለሽነት በዘረኝነት እየፈራረሳት ይገኛል ። ህዝቡንም በትልቅ የሞራል እስር ቤት ውስጥ አስረውት ይገኛል ከዚህ እስር ቤት የሚያወጣው አንዳች አይል ያስፈልገዋል ። የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር በማንኛውም መንገድ ማስመለስ ይኖርብናል ህዝቡ በእየለቱ በሚሰማው ነገር ልቡ  ሸፍቷል ከጥቂት ሆዳሞች በስተቀር ስለዚህ ይኼ የነገዋ ኢትዮዽያ ቀን ነዉ የኔ የእናንተ ብ ቻ ሳይሆን የመላዉ ኢትዮዽያ ጥያቄ ነዉ እንድረስላት ይህን ሳናደርግ የቀረን እንደሆነ ግን ህሊና ቢስ ነን ፍሬ ቢስ ነን ወይም ደግሞ ከሃዲ ነን።  click here more
እግዚሃብሄር ኢትዮጵያንና ተከባብሮ የሚኖረውን በማንኛውም ዓይማኖት ላይያለውን ህዝብ ይባርክ
አሜን
ያሬድ ኤልያስ
nome telemark dagsrud

Total Pageviews

Translate