Pages

Jul 3, 2013

ለጅምላ ጭፍጨፋ ህጋዊ ሽፋን?

ሰሞኑን በጣም እጅግ በጣም አስደናቂ፣ አስገራሚና ዘግናኝ ዜናዎች እየተሰማ ነው።በእስከ ነጻነት

  • በርግጥ ለትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር አዲስ ነገር አደለም ሊሆንም አይችልም።
የህወሃትን ባህርይ ለምናውቅና የነጻውን አለም ህይወትና ሰብአዊ መብት አክብሮት ለቀመስነው ግን በጣም እጅግ በጣም የሚያስገርም፤ የሚያስደነግጥ: ከዚያም አልፎ  ይህን መቀበልና መዚህ መቀጠል አንችልም  ወያኔ ካልጠፋ ስራም: ኑሮም፤ ትምህርትም እምነትም የለም ክተት የሚያሰኝ ነው:
ዜናው እ አ አቆጣጠር ሰኔ 26 2013 በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዠን  (እኔ  የኢትዮጵያ ሳተላይት መገናኛ፣ Ethiopian Satellite media) ብዬ ብጠራው ደስ ይለኛል) ባስተላለፈው ዜና፡ የወያኔው የደህንነት አባላት ለሚፈጽሙት ማንኛውም ጥፋት በወንጀልም ሆነ በፍታብሄር አይጠየቁም የሚል የህግ ረቂቅ ለምክር ቤት መቅረቡን አርድቶን ነበር። ይሁን እንጂ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዴት ጅምላ ጭፍጨፋ የህግ ሽፋን ሊሰጠው ይችላል በሚል ጥርጣሬ ተወጥረን እያለ፡  ነገሩ እኛ ያሰብነው ሳይሆን ወያኔ ያቀደው ሆነና በዛሬው እለት የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ታጣቂዎች ለሚፈጽሙት ጅምላ ጭፍጨፋ ወይም ንብረት ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት በወንጀልም ሆነ በፍታብሄር አይጠየቁም የሚል ህግ ባሻንጉሊት ስብስቦች አስጸድቋል፡ ነፃ  እርምጃ ባገሪቱ ታውጇል፡ ለትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ጸጥ ለጥ ብለህ ካልተገዛህ ባደባባይ ትረሸናለህ፤ ለሞትህም ሆነ ለመቁሰልህ ማንም አይጠየቅም፡የሚል ቀጭን ትዛዝ እና አዋጅ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተጭኗል።
ይህ ማለት ምን ማለት ነው? አብረው እየተከናወኑ ያሉት አባሪ ተግባራትስ ምንድናቸው?
በዝርዝር ሳይሆን ጠቅለልና አጠር ያለ የወያኔ ተግባራትን  ወደሗላ መለስ ብሎ መቃኘት አስፈላጊ ይሆናል፡
ህውሃት ገና የዕኩይ ጥንስሱ ሳይፈላ በስብሃት ነጋ አጋፋሪነት የመጀመሪያ አገራዊ አንድነትን ለመናድ ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያመቻች የበረሃ ሲኖዶስ ማቋቋምና፤ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በእምነቱ በጎለበቱና በጸኑ አባቶች ሳይሆን በህውሃት ካድሬዎች እንዲያዝ በረሃ ስልጠና መሰጠቱንና ካድሬዎች የመነኩሴ ልብስ ለብሰው በየገዳማቱ ያሉትን መናኝ ባሃታዊያን፤ መነኩሳትን፤ አረጋውያን ካህናትን አፍነው፤ ገድለው መጨረሳቸውንና አዲስ አበባም ሲደርሱ ዋናውን ፓትርያርክ ከነባር ካደሬዎች አንዱን አባ ገ/ማርያምን ማስቀመጣቸውን ቤተ ማህቶት እ. አ. አቆጣጠር ጥር 23 2013 ምስጢራዊው የበረሃው ሲኖዶስና የማህ በረ ቅዱሳን ፓትርያርክ፣ ከአብየ አዲ እስከ አዲስ አበባ በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሁፍ በሚገባ ዘርዝረው፤ ዋቤ አጣቅሰው አሰቀምጠውታል:   
በዛ ወቅት እነስበሃት ነጋ  ለእስልምና እምነት ተከታዮች የተሳሳተ ግንዛቤ ነበራቸው ብዬ እገምታለሁ፡  በነስ ቁንጽልና በጥላቻ የተቃኘ ህሊና ኢትዮጵያ የአማራና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ብቻ፤ ስለኢትዮጵያ የሚጨነቁ አማሮችና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ናቸው ብለው ራሳቸው የፈጠሩትን ውሽት አምነው፤ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችንን በቀላሉ መቀየር፤ እንችላለን ከሚል ግምት በመነሳት በረሃ እያሉ ያላሰቡበትን አሁን ግን በቀላሉ ልንተገብረው እንችላለን ከሚል ንቀት ተነሳስተው የሃባሽን እምነት ተከተሉ የሚል በየትም አለም ታይቶና ተሰምቶ የማይታውቅ እኔ የሰጠሗችሁን እመኑ የሚል ትእዛዝ ሊጭንባቸው ሞክረዋል። የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ናቸውና፤ እንደነ ስብሃት፤ መለስና  መሰሎች የባንዳ ቅርንጫፍ አደሉምና፤ ሃገር የመናድ ፍላጎትም ሆነ ተንዳ የማየት ፍላጎት የላቸውምና ዞር በል አሏቸው፡ ተቃውሟቸውንም በሰላማዊ ድምጻችን ይሰማ ሲሉ አቤት ሲሉ ሁለት አመት ሊሞላቸው ጥቂት ወራት ብቻ ቀራቸው።Ethiopian government abusing and torches Ethiopian Muslims.
በእበሪት የተወጠረው ወያኔ ይህን ሁለተኛ አመቱን የያዘውን  እምነቴን አንተ አትመርጥልኝም የሚለውን ሰላማዊ ተቃውሞ በሰላማዊ መንገድ እልባት እንደመሰጠት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በሃሰት ወንጅሎ እንደለመደው በሃይል ለመጨፍለቅ  የእስልምና እምነት ተከታዮች ያልሆኑ ግን ልክ በረሃ ካድሬ መነኩሳትን እንዳስተማረና የኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያንን እንደተቆጣጠረ ሁሉ አሁንም በስለላ የሰለጠኑ አረብኛ ቋንቋን የተማሩና ቁርአንን የቀሩ 987 በእስራኤል የሰለጠኑ የደህንነት አባላት በየመስጊዶቹ ማሰማራቱን እየሰማን ነው። እነዚህ የደህንነት ሰላዮች በየመስጊዱ  የሚሰማሩት መስጊድ ሊያረክሱ፤ ብጥብጥ ሊያስነሱ፤ ከዛም የሚፈልጉትን ለማጥፋት፤ ለመግደል የተዘጋጁ መሆናቸውን የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም፡
ሼሆችን፤ ይማሞችን ቢገሉ፤ መስጊድ ቢያቃጥሉ በወንጀልም ሆነ በፍታብሄር እንደማይጠየቁ በህግ ተረጋግጦላቸዋል፡
የሚገርው ደግሞ  እስራኤል ከሰለጠኑት 987 ሰላዮች መካከል የእሰልምና ተከታዮች 11 ብቻ መሆናቸው ነው፡ (11 ግን ምትሃታዊ ቁጥር ነች እንዴ? የኢኮኖሚ እድገት 11% ሌላም፡ ይቺ  እንኳ ለፈገግታ ነች እልፏት) ከነዚህ ስልጣኞች ውስጥ 613ቱ ደግሞ የትገራይ ተወላጆች ናቸው፡ ራሳቸው ባስቀመጡት ስሌት፤ ብሄር ብሄረ ስቦች ቀመር ቢተነተን  ለአንድ ሚሊየን 11 ሰላይ ሂሳብ ማለት ነው፡ በዚህ ሂሳብ ሲሰላ ትግራይ የሚደርሳት የሰልጣኝ ሰላይ ብዛት 55 ገደማ መሆን ነበረበት፤ አሁን ግን ትግራይ 1115% አንድ ሽህ አንድ መቶ አስራ አምስት በመቶ ድርሻ ወስዳለች ማለት ነው። ከ22 አመት አገዛዝ በሗላ 1115% የደህንነት አባላት ከትግራይ ተመልምለውና ስልጥነው፡ መስጊድ ለመበጥበጥና ስልክ ለመጥለፍ ሲዘጋጁ በምንም መስፈርት አገሪቱን እየገዛ ያለው ኢትዮጵያዊ አገዛዝ ነው የሚል ብዥታ ሊኖር እንዳይችል አድርጎታል፡ የገሃዱ አለም ቁልጭ አርጎ እንዲሚያስረዳው ኢትዮጵያ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር የቅኝ አገዛዝ ለመውደቋ ከዚህ በላይ  ማረጋገጫ የሚያስፈልግ አይመስለኝም።
ዋናው ቁጥሩ አደለም፡ የህውሃት ደህንነቶች በጅምላ ለሚፈጁት (በርግጥ ከዚህ ቀደምም ተጠያቂ ሆኖ የሚያውቅ የለም) ለወንጀላቸው ተጠያቂ እንደማይሆኑ መስጊድ፤ ቤተክርስቲያን ቢያቃጥሉ እንደማይጠየቁ፤ የህግ ሽፋን መሰጠቱ የህውሃትን አገር የማፍረስ፤ ዘር የማጥፋት፤ እና ለምንም ተጠያቂነት ሊወስድ አለመፈለጉንና አለመዘጋጀቱን ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ነው፡
በዚህ አጋጣሚ ግን እስራኤል ለአረብ ሃገራት ያላትን ጥላቻ በኢትዮጵያ የአስልምና እምነት  ተከታዮች ላይ ለመወጣት ስላዮችን ማሰልጠኗ ታሪካዊ ስህተት መፈጸሟን ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም። ወያኔን ስልጣን ላይ ለማውጣትና ስልጣኑ ላይም ለማቆየት እንግሊዝና አሜሪካ የተጫወቱትን ሚና፤ ሰላዮችንና ያፈና ሰራተኞችን በማስልጠንና ማፈኛ መሳሪያ በመሸጥ ህንድ፤ ቻይና እና እስራኤል ተጠያቂ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሊገነዘቡት ይገባል።፡አሁን አቅሙ ላይኖረን ይችላል ግን የቴክኖሎጂ እድገት ሌላውን ለማጥፋት ያመረቱት መሳሪያ በራሳቸው ላይ ሊውል የሚችልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፤ እነዚህ ሃገራት አቶ ገ/መድህን አርአያ እንደጠቀሱት ለ8 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን እልቂት ተባባሪ መሆናቸውን መረዳትና መዝግቦ ለትውልድ ማስተላለፍ የያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ነው።
ስለዚህ በትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ታጣቂዎች ለግንባሩ የማያጎበድዱትን፡ እንቢ አልገዛም ያሉትን ኢትዮጵያውያን፤ በጅምላ እንዲፈጁ፤ ንብረታቸውን እንዲያቃጥሉ፤ እንዲዘርፉ እና ዘር እንዲያጠፉ ትዕዛዝና የህግ ሽፋን ተሰጥቷቸዋል። ዘር በማጥፋታቸው፤ ህዝብን በመጨረሳቸው፤ ንብረት በማውደማቸው ይሸለሙ እንደሆነ እንጂ በወንጀልም በፍታብሄርም እንደማይጠየቁ ግልጽ ሆኗል፡
የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ተግባራዊ ተሞክሮ የሚያስረዳን ደግሞ በጣም ግልጽ ነው፡ በደኖ፤ ወተር፤ አርባ ጉጉ፤ ጋምቤላ፤ አዲስ አበባ፤ አረካ፤ አዋሳ፤ ሸካ ማጂ፤ አሶሳ፤ ጉሙዝ፡ ወልቃይት ጠገዴ ስንቱ ተዘርዝሮ ይዘለቃል፡በነዚህ ቦታዎች ሁሉ ሁሉ ወያኔ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው የፈጸመው። አሁን ይህ በአዋጅ ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መሆኑ ግልጽ ነው፡
የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር በየንዳንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ላይ የሞት ፈርድ አውጆበታል የሚቀረው ተግባራዊ የሚሆንበት ቀን ብቻ ነው።
ስለዚህ የትግሬ ነጻ አውጭ ታጣቂዎች በጅምላ ሲፈጁን ቆመን ሞታችንን እንጠብቅ? እንደ ጅግራ አንገታችንን ሰጥተን እንታረድ ወይስ ይህ ሁሉ ከመድረሱ በፊት እንደ ግብጾች ወያኔ አሁኑኑ ስልጣን እንዲለቅ ህዝባዊ አመጽ እንጀምር፡ አሁን፤ ዛሬ፡ ወያኔ ስልጣን አሁኑኑ ካልለቀቅህ ስራም፤ ትምህርትም፤ ኑሮም፤ እምነትም፤ ሃገርም የለም ብለን እየመከትንና፤ እየተከላከልን እንሙት? ወያኔ ግድያውን ነገ ይጀምራል፡ ጊዜ የለም፡ ያለችው ጊዜ አሁን ይች ቅጽበት ነች።
መልሱን ለያንዳንዳችሁ እተዋለሁ።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
እስከ ነጻነት

“አፍሪኮም ወደ አገርህ ተመለስ” አፍሪኮም ከጀርመን ውጣ - ዛሬውኑ! አፍሪኮም ከአፍሪካ ውጣ- ቶሎ ብለህ!

“አፍሪኮም ወደ አገርህ ተመለስ”

አፍሪኮም ከጀርመን ውጣ - ዛሬውኑ! አፍሪኮም ከአፍሪካ ውጣ- ቶሎ ብለህ!
stop_africom


የአፍሪካ አንድነትን 50ኛ ዐመት የመመስረቻ በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ   የወጣ መግለጫ!

“እኛ እዚህ በአዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ የተሰበሰብነው የአፍሪካ መሪዎችና መንግስታት፣ ማንኛውም አገርና ህዝብ የራሱን ዕድል ወሳኝ መሆኑን እናምናለን፤ በዚህም ምክንያት ነፃነት፣ እኩልነት፣ ትክክለኛ ፍርድና ክብር የአፍሪካ ህዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችና የሚገባውም መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ በመሆኑም የተፈጥሮ ሀብታችን የመጠበቅና፣ ህዝቦቻችንም የተፈጥሮ ሀብታቸውን የመጠቀምና፣ ለሚገባቸው የህብረተሰብና የኢኮኖሚ ዕድገት የማዋል መብታቸው እንደሆነ እናምናለን፤ ለዚህም እንታገላለን።”
እ.አ.አ. በግንቦት 25 1963 ዓ.ም በሞዲቦ ኪዬታና ሲልቫኖስ ኦሊምፒዮ የረቀቀውና፣ በጊዜው ነፃነታቸውን የተቀዳጁት 33 የእፍሪካ መንግስታት ያፀደቁት ስምምነት መልዕክቱና ዋናው መሰረተ-ሃሳቡ ምንድነው? አንድ ነገር ማለት የሚቻለው በተለይም በቻርተሩ ላይ የሰፈረው ቁም ነገር ተግባራዊ አልሆነም፤ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ አንድነት ሊረጋገጥ አልቻለም። ከ50 ዐመት በኋላ የአፍሪካ አንድነት የአፍሪካን አንድነት ድርጅትን ቢተካውም አሁንም ቢሆን ሁሉም የአፍሪካ አገሮች ተፈጥሮ የለገሳቸውን የተትረፈረፈ የጥሬ ሀብት ለመጠቅምና መብታቸውን ለማረጋገጥ በመታገል ላይ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ላይ በተስፋፋው የስራ ክፍፍል አህጉሪቱ በመበደልና ቁራኛ በመሆን ሙሉ መብቷን እንዳታረጋግጥ የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ከፍተኛ እንቅፋት ሆነዋል። እንዲያውም አልፎ ተርፎ በቅርቡ በፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስተር የወጣው መግላጫ እንደሚያረጋግጠው ፓን አፍርካኒዝም የሚለው አስተሳሰብ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሯል በማለት ካለማፈር ይናገራል።
ዛሬ ከሃምሳ ዓመት በኋላ የአፍሪካ አንድነት የተቋቋመበትን በዓል ስናከብር፣ እኛ በጀርመንም ሆነ በአፍሪካ፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የምንገኝና የዓለምአቀፋዊነት ሃሳብ ይዘን የምንታገልና የሚያገናኘን፣ እንደገና የቅኝ አገዛዝን መድህር እንድናገላብጥ ተገደናል። እንደሚታወቀው በ19ኛውና እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የቅኝ አገዛዝ በአፍሪካ ውስጥ ተስፋፍቶና ተንሰራፍቶ እንደነበር ግልጽ ነው። በ1885 በበርሊን ኮንፈረንስ ላይ በተለይም ኮንጎን ዋና የቅኝ ገዢዎች የነፃ ንግድ መድረክ ለማድረግ ስምምነት ሲደረስና ከዚያ በመነሳት ጠቅላላውን አፍሪካ ለመቆጣጠር ጣልቃ መግባት እንደሚያስፈልግ ሲታመን የቅኝ ገዢዎች ወንጀለኛነታቸውን በገሃድ አረጋግጠዋል።
በ2013 ዓ.ም ደግሞ አፍሪኮም አፍሪካን ለመቆጣጠርና ሀብቷን ለመዝረፍ በጀርመን ከተማ ሽቱትጋርት ሲቋቋም የቱን ያህል ትልቅ ወንጀልና፣ አህጉሪቱን በዘለዓለም ውዝግብ ውስጥ ለመክተት እንደታቀደ ማሰብ ይቻላል። በተለም አሁን ባለው ዓለም አቀፋዊ የኃይል አሰላለፍና የጂኦ ፖለቲካ እሽቅድምድሞሽ የአህጉሪቱ ነፃነትና ህዝቦቿም ዕወነተኛ መብታቸውን ለማረጋገጥ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደወደቁ ከአሁኑ መናገር ይቻላል። በተለይም በተደጋጋሚ ጦርነትን በቀሰቀሰና በዚህም አማካይነት ብዙ ጉዳት በደረሰበት በጀርመን አገር ይህ ዐይነቱ የዘረፋ ጦር ሰፈር መቋቋሙ ብዙዎችን ከአፍሪካ ህዝብ ጋር የቆሙትንና የሚተባበሩትን አስቆጥቷቸዋል።
የአፍሪካ የአህጉሩ ኮማንዶ (AFRICOM) በመባል የሚታወቀው የተመሰረተው በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ ሲሆን፣ ዋናው ዓላማውም የምዕራቡን ዓለም የወራሪነት ፖለቲካ ለማረጋገጥና የአፍሪካን ሀብት ለመቆጣጠርና ለመዝረፍ ነው። ለዚህ ሸፋን የሆነው አሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሟን ማስጠበቅ የሚል ሲሆን፣ የአፍሪካ መንግስታትን “የመከላከል ኃይል” በማሳደግ ከውጭ የሚመጣውን አደጋ ለመከላከልና ወደ ውስጥ ደግሞ “ሚዛናዊ ዕድገት” ለማምጣት በሚል ሽፋን ነው።
በአሜሪካ መንግስት ቁጥጥር ስር ያለው አፍሪኮም ወይም የአህጉሪቱ ጦር እ.አ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በሽቱትጋርት የተቋቋመና እዚያው የሚገኝ ነው። የቀድሞው የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር (2005-2009) የነበሩትና የሶሻል ዲሞክራት አባሉ ቫልተር ሽታይንማየርና  የቀድሞው የባደን ቩትንበርጉ የክፍለ-ሀገር አስተዳዳሪ (2005-2010) ሁኔታውንና ጉዳዩን ጠጋ ብለው ሳይመረምሩ ይህ የወራሪ ጦር ሰፈር እንዲቋቋም በፊርማቸው ፤ ተስማምተዋልም። በተጨማሪም በሽቱትጋርት ከተማ በአፍሪካ ውስጥ የጦር ልምምድ ለማድረግ የተዘጋጀ የአሜሪካ የባህር ጦር በተጨማሪ ይገኛል።
በጀርመን ህገ-መንግስት በአንቀጽ 26 መሰረት ማንኛውም በጀርመን ምድር አንድን አገር ለመውረር የሚደረግ የጦርነት ዝግጅትን አጥብቆ ይከለክላል። በተለይም በዚህ አንቀጽ መሰረት በዓለም ህዝቦች መሀከል ሊኖር የሚገባውን ሰላማዊና ተከባብሮ መኖርን የሚያደፈርስ ጦርነት ከጀርመን ምድር መቋቋምና መነሳትም እንደሌለበት ቁልጭ አድርጎ አስፍሯል። በተጨማሪም በህገ-መንግስቱ በአንቀጽ 25 መሰረት  ማንኛውም የዓለምን ሰላምና በህዝቦች መሀከል የሚኖረውን ተከባብሮ መኖር የሚያደፈርስ ሁሉ የጀርመንንም ህግ የሚጥስ ነው ብሎ ያረጋግጣል። እ.አ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ጀርመን የዓለም አቀፍ ህዝብን የሚመለከት የመቀጫ ህግ የያዘች ሲሆን፣ በዚህም መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በህዝቦች ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ግፍና ግድያ፣ እንዲሁም ፀረ-ህዝብ ድርጊት የምትቃወምና ይህም ከራሷ ህግ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ተቀብላለች። የመቀጫው ህግ እንደሚያረጋግጠው ማንኛውንም ፀረ-ህዝብ ድርጊትና ግድያ በየትኛውም ዓለም የሚካሄደውን የሚመለከትና በጀርመን አገር ብቻ ያልተገደበ መሆኑን ያስታውቃል። አንድን የውጭ ጦር በጀርመን ምድር ለማቋቋም እ.አ በጥቅምት 23፣ በ1954 ዓ.ም ስምምነት የተደረሰበት ከ2+4 ውል ነው። ውሉ ግን ሌላን አገር ለመውረሪያ የሚያገለግል አይደለም።
አፍሪኮም(AFRICOM) በተቻለው መጠን ዋናውን መቀመጫውን በአንድ የአፍሪካ አገር ማድረግ ይፈልጋል። አፍሪኮሞን ወደ አፍሪካ ለማዘዋወር ሙከራ ቢደረግም አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ሲቃወሙት፣ ጥቂት የአፍሪካ አገሮች እያሰቡበት ነው። ሊታለሉም እንደሚችሉ ፍንጮች ያመለክታሉ። በተለይም አሁን ባለው የማታለልና የማሳመን ስትራቴጂ፣ በተጨማሪም የአፍሪካ አገሮችን ልትወረሩና ልትከበቡም ትችላላችሁ በሚል ግፊትና ስሜትን መሰባያ ዘዴ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ሊያምኑና በራቸውንም ክፍት ሊያደርጉና መስፈሪያም ቦታ ሊሰጡ ይችላሉ። እንደሚታወቀው እንደዚህ ዐይነቱ ወራሪ ጦር የሰሜን አትላንቲክ ጦር አባል አገሮችን፣ በተለይም አሜሪካንና አንዳንድ ጠንካራ አገሮችን ሲጠቅም፣ ፈረንሳይም የዚሁ ስምምነት ተጋሪናን አንዳንድ የአፍሪካ ዘራፊ መንግስታትም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ግልጽ ነው። የአፍሪኮም ዋናው መቋቋም ዓላማው የአፍሪካን የጥሬ ሀብት ለመቆጣጠርና ለመዝረፍ ሲሆን፣ በተጨማሪም ብሪክ (BRIC) መንግስታት የሚባሉትን እንደ ራሺያ፣ ህንድ፣ ብራዚልና ቻይናን የመሳሰሉትን ለመግታትና ከነሱ ጋር ለመፋለም የተዘጋጀ ነው። ከዚህም በተጨማሪም በአፍሪካ ውስጥ ራስን ለመቻል የሚደረገውንም ትግልና ጥረት በእንጭቹ ለመቅጨትና ለመዋጋት የሚያመች ነው።
ማንኛውም የሰሜን አትላንቲክ የጦር ስምምነት አገሮች እንደዚህ ዐይነቱ የራሴን ጥቅም ማስጠብቂያ የሚል ድርጅትና በአፍሪካ ላይ የተቃጣ የጦር ኃይል በፍጹም አያስፈልገውም። መብቱም አይደለም። ያም ሆኖ አንዳንዶች የሰሜን አትላንቲክ የጦር ስምምነት አገሮች ከአንዳንድ የአፍሪካ መንግስታት ጋር የሁለት አገሮች ስምምነት በማድረግና እንደልባቸው በመፈንጠዝ በአህጉሪቱ ውስጥ የፈለጉትን ነገር ያደርጋሉ። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ መንግስታት የጦር ኃይሎች ከሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት ጋር በመስራትና በመተባበር የአፍሪካን ነፃነት እያዳከሙ ነው። በተጨማሪም የግል ጦሮች በመቋቋም በአፍሪካ ውስጥ እንደልባቸው በመንቀሳቀስ ስራቸውን እየሰሩ ነው። ይህ ሁሉ እያለ አፍሪኮም ለምን አስፈለገ?  በተጨማሪም ሽበረተኝነትን ለመዋጋት በሚል እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱና አፍሪካን እያመሱ ነው። ከዚህ ባሻገር የሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት ከሁለት ዐመት በፊት በሰሜን አፍሪካ የቀሰቀሰውን አብዮትና የህዝቦች የነፃነት ጥማት በእንጭጩ እንዲወድም የማይሰሩት ተንኮል ይህ ነው አይባልም። ይህንንም ለማድረግ በሩቅ ምስራቅና በአካባቢው ያሉትን ፀረ-ዕድገትና ፀረ-ተራማጅ የሆኑ ኃይሎችን በሙሉ እንደሚረዱና እንደሚያስታጥቁ የታወቀ ነው።
የአፍሪካን ህዝቦች ነፃነት የማወደሙና የአፍሪካን ህዝብ ጩኸት ጭጭ የማድረጉ ሁኔታ ስር ሰዷል። ከሰላሳ ዐመት ጀምሮ በአህጉሪቱ የሚካሄደው የመዋቅር መስተካከያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚባለውና በቴክኖክራቶች የሚመራውና ተግባራዊ የሆነው የአፍሪካን ህዝብ ክፉኛ ማዳከሙ ብቻ ሳይሆን፣ ለፖለቲካ ነፃነት የሚያደርገውንም ትግል ደብሳውን አጥፎበታል። አብዛኛውም ህዝብ ለፖለቲካ ያለው ግንዛቤ ጠፍቷል ማለት ይቻላል። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ መንግስታት  መሰረታዊ በሆኑ ጥያቄዎች ላይ ሁሉ በመሀከላቸው  ምንም ስምምነት የላቸውም። በተለይም በጦር በኩል የተዳከሙና  በኮንጎ፣ በአይቮሪ ኮስት፣ በሊብያና በማሊ ላይ የሚደረገውን የውጭ ኃይሎች ወረራና ጣልቃ ገብነት ዝም ብለው እንዲያዩ ተገደዋል። በተጨማሪም እንደ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ናይጀሪያ፣ ቱኔዚያ፣ የማዕከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክና አልጄሪያ ግፊት እየተደረገባቸውና ወደጦርነትም እየተገፉ እንደሆኑ ሁኔታው ያረጋግጣል። ከዚህም በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ለሰሜን አትላንቲክ ጦር መውረሪያ መሳሪያ በመሆን ብዙ አገሮች እንዲወረሩ ሁኔታውን አመቻችቷል፤ እያመቻቸውም ነው። ምናልባትም የአፍሪካ አገሮች በተባበሩት መንግስታት ስር በሚደራጀው ጦርና በኔቶ ውስጥ መሳተፍ እንደሚተባበሩ የሚያሳይ ቢመስልም፣ ይህ ሁኔታ ግን ከዕውነቱ የራቀ ነው። የአፍሪካ መንግስታት ጦሮች በዚህ ዐይነቱ መሳተፍ የግዴታ የኢምፔሪያሊስት አገሮች መሳሪያ እንደሚያደርጋቸው የተረጋገጠ ነው። በሚያዚያ ወር 2013 ዓ.ም 36 የአፍሪካ አገሮች የመጭውን ዘመን አመራር ለማስለጠን በሚል ከእነዚህ አገሮች የተውጣጡ የመኮንን ወጣቶች ወደ ዋሺንግተን ተልከዋል። ይህም ኮርስ በአፍሪካ የማዕከለኛው ስትራቴጅክ ጥናት(African Center for Strategic Studies)(ACSS) የተዘጋጀ ነው። እነዚህ ወጣት መኮንኖች ሰልጥነው ከተመለሱ በኋላ  ቲያትራዊ የመተጋገዝ ተግባራዊ የልምምድ ዕቅድ(Theater Security Cooperation Programs) በሚባለው የአፍሪኮም አንደኛው አካል ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል። የአፍሪካ ተጨማሪ ተግባራዊ የልምምድና የደጋፊ ተቋም(African Contingency Operations Training and Assistance)  እንደዚህ ዐይነቱን የአፍሪካን ምርጥ መኮንኖች የማስለጠኑን ተግባር ያሟላል። በዚህም መሰረት እነዚህ ኃይሎች በተባበሩት መንግስታት የጦር ስልት ውስጥ ይካተታሉ።AFRICOM_GO_HOME
በአለፉት አስር ዐመታት ብዙ የአፍሪካ መንግስታት ወታደሮች በእንደዚህ ዐይነቱ የወረራ ስትራቴጂ ውስጥ በመካተት ተለማምደዋል። በሰሜንና በምዕራብ አፍሪካ በስመ ሽብርተኝነት ፍሊንትሎክ እየተባለ የሚጠራውና የሚካሄደው የጦር ልምምድ፣ ከሩቅ ሆኖ  ሁኔታዎችን ለማጣራት የሚካሄደና የአፍሪካ ኢንዴቨር እየተባለ የሚጠራው የጦር ልምምድ፣ ከትላስ ፈጥኖ ደራሽ የሚባለውን በህንድ ውቅያኖስ አካባቢና በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ የሚካሄደውና በዚህ አካባቢ የሚተላለፈውን የንግድ መርከብ ለመቆጣጠር በሚል ሰበብ ብዙ የአፍሪካ ወታደሮች በልምምዱ ውስጥ ተካተዋል።
ከዚህ ስንነሳ የአፍሪካ የሰላምና የደህንነት ሁኔታ በከፍተኛ አደጋ ላይ ይገኛል። የአፍሪካ መንግስታትና ህዝቦች ያሉበት የተዳከመ ሁኔታ በዚህ ዐይነቱ የማጭበርበር ዘዴ ወደ አለመረጋጋትና ብጥብጥ እንዲያመራ እየተደረገ ነው። በዚያውም አህጉሪቱን ለመውረርና እንደገና ቅኝ ግዛት ለማድረግ ያመቻል። በተለያዩ አገሮች የአሽባሪዎች የህቡዕ ቦታዎች በመቋቋምና በሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት በመደገፍ እንደመግቢያ ቀዳዳነት አመቺ ሁኔታ ፈጥረዋል። ይኸኛው በመጠኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ብዙ የማይታወቅ ምስጢር ወደፊት በጉልህ የሚወጣበት ቀን ይመጣል። የኢምፔሪያሊስት አገሮች በየቦታው የሚደፈርሰውን ግጭት ልንቆጣጠር እንችላለን በማለት ጣልቃ በመግባት ለሰላም ዕጦት ዐይነተኛ ምክንያት ሆነዋል። የጠቡም መነሾና የሰላም መደፍረስ ምንጮች የእነሱ የማያቋርጥ የመስፋፋትና የመስገብገብ ፖለቲካ ነው። በየቦታው የተስፋፋው ድህነት፣ እስካሁን ድረስ በዕድገት ስም የተካሄደው የኢኮኖሚ ፖሊሲና ውጤተ-አልባ መሆን፣ የተደራጀ ወንጀለኝነት፣ እነዚህ ሁሉ ከኢምፔሪያሊስት አገሮች የተሳሳተ ፖሊሲና ህዝቦችን ከማስገደድ ጋር የተያያዙ ናቸው። እንደዚህ ዐይነቱ ድህነት የግዴታ ለሰላም ዕጦትና ለአሸባሪዎች መፈልፈያ ምንጭ ሊሆን ይችላል። በተለይ በብዙ የአፍሪካ አገሮች የጥሬ ሀብትን የሚያወጡት የምዕራብ አገሮች ኩባንያዎች ተባባሪ በመሆን ሁኔታውን በማባባስ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ኩባንያዎች አሸባሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ከእነሱ ጋር እየተጋፉ የሀብት ዘረፋ ያካሄዳሉ። ስለሆነም ይህ ዐይነቱ የተወሳሰበና ለብዙዎቹ ግልጽ ያልሆነ ጉዳይ ለሰላም ዕጦትና በተለይም ደግሞ ጣልቃ ለመግባት ተስማሚ ሁኔታን ፈጥሯል። ብዙዎች የአፍሪካ መንግስታት ይህንን ዐይነቱን ተንኮልና ዘረፋ ባለመረዳት ተባባሪ በመሆን ሁኔታው እንዲባባስ እያደረጉ ናቸው። በነፃ ንግድና በሊበራሊዝም ስም የሚካሄደው ዐይን ያወጣ ዘረፋ የአፍሪካ መንግስታትን ዐናቸውን ሰውሮታል። በቀጥታ በሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት ስትራቴጂ ቁጥጥር ስር እንዲወድቁ ተደርገዋል።
ይህ ዐይነቱ የአፍሪካን ጦር በአፍሪኮም ስትራቴጂና በሰሜን አትላንቲኩ የጦር ስምምነት ውስጥ ማካተቱና፣ የአፍሪኮምንም ማዕከል ወደ አፍሪካ ለማዛወር መሞከር የአፍሪካን ነፃነትና የአፍሪካን ህዝቦች መተባበርና ለጋራ ዕድገት መነሳት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያጨናግፍ ነው። አፍሪኮምና ኔቶ ከመተሳሰራቸው የተነሳ መጀመሪያውንና መጨረሻውን ለማወቅ ያዳግታል። ለምሳሌ በግንቦት ወር የኔቶ ዋና ጸሀፊ የሆኑት ሚስተር ራስሙሰን ዋሽንግተን ላይ ምርጡ መሪ በመባል ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። ስለሆነም ኔቶና አፍሪኮም በአፍሪካ ውስጥ ስር ለመሰደድና ሀብቷን ለመዝረፍ ሲሉ አንድ ላይ ተሳስረዋል። አንዱን ከሌላው የማይለይበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
የአፍሪካ አንድነት ከተቋቋመ ከ50 ዐመታት ጀምሮ ብዙ እንቅፋቶች ገጥመውታል። በተለይም ነፃነታቸውን ተቀዳጀትዋል በሚባሉት የአፍሪካ አገሮች ላይ በስንት ትግል የተቀዳጁትን ድል ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዳያደርጉ ቁጥጥር ተደርጎባቸዋል። ከ60ኛው ዓ.ም ጀምሮ ተራማጅ በነበሩ የአፍሪካ ፕሬዚደንቶች ላይ የተካሄደው የመንግስት ግልበጣና፣ ከስልጣናቸውም እንዲባረሩ ማድረግ ወይም ማስገደል፣ ከአፓርታይድ ለመላቀቅ ይደረግ የነበረውን ትግል ለማክሸፍ መሞከር፣ የአሜሪካ ጦር በሶማሌ ላይ ያደረገው ወረራና፣ በሱዳን ላይም የፈጸመው ተንኮል፣ ከአልካይዳ ጋር የሚያደረገው የውስጥ ለውስጥ ንግግር፣ የመስከረም 11 የአሸባሪዎች ድርጊት ከመፈጸሙ በፊት በጂሃዲስቶች የተፈጸመው ድርጊትና ከዚህ ጋር ተያይዞ አሸባሪዎችን መምታት አለብን ተብሎ የረቀቀው ፖሊሲ ሁሉ፣ እነዚህ ሁሉ በአፍሪካ ህዝብ ነፃነትና፣ በአፍሪካ አንድነት የስራ አፈጻጸም ላይ የራሳቸውን አሉታዊ አሻራ ጥለዋል። እ.አ በ2002 ዓ.ም የፓን ሳህል አገሮች የፀረ-አሸባሪ ስምምነት፣ ከሶስት ዐመታት በኋላ ደግሞ የትራንስ ሳሀራ የፀረ-አሸባሪዎች ስምምነት፣ እንዲሁም ሌሎች አምስት አገሮችን በማካተት የየመንግስታቱን አትኩሮ በዚህ ዐይነቱ ለዕድገት በማያመች ተግባር ላይ እንዲሰማሩ አስገድዷቸዋል።
በኋላ ደግሞ የምስራቅ አፍሪካው የፀረ-ሽብር ዝግጀት ወደ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገሮች በመስፋፋት ስድስት የሚጠጉ አገሮችን አካትቷል። በዚሁ ዐመት እ.አ በ2005 ዓ.ም የአፍሪካ አገሮች ያደረጉትን ጥሪ ኒቶ በመቀበል በዳፉር ውስጥ ጣልቃ መግባት ተቻለ። ከዚህ አልፎ በብርጌድ ደረጃ የሚቋቋም ጦር ከሁለት ዐመት በኋላ እንዲቋቋም የመጀመሪያው ዝግጅት ሲጀመር፣ ስራው በ2015 በመጠናቀቅ የሰላም ጥበቃ በሚለው ስም አፍሪካ ሙሉ በሙሉ ነፃቷን እንድታጣ ትደረጋለች ማለት ነው።
ይህ ማለት ምን ማለት ነው?  የራሳችንን ዕድል በራሳችን የመወሰኑ ጉዳይ እንዳለ ይነጠቃል። የአፍሪካ ህዝቦች ከእንግዲህ ወዲያ የነፃነታቸውን፣ የመብታቸውንና የዕድገታቸውን ዕድል ወሳኝ አይሆኑም ማለት ነው። ኔቶና አፍሪኮም በአንድ የአፍሪካ አገር ውስጥ ጣልቃ ለመግባት በሚፈልጉበት ጊዜ ከነሱ በላይ የተቀመጡትን የሲኒየር ሊይዞን ከመጠየቅ በስተቀር ማንንም መጠየቅ አያስፈልጋቸውም። ይህ ዐይነቱ የሚሊተሪ ሊይዞን የአፍሪካን አንድነት የሚቆጣጠርና የሚከታተል ስልሆነ እንደ አፍሪካ አንድነት ተወካይ ሆኖ የሚሰራ ነው ማለት ይቻላል ። የአፍሪካ መንግስታት ምንም ዐይነት የቁጥጥር መብት የላቸውም ማለት ነው። እኛ የፓን አፍሪካንን አርማ አንግበን የምንታገል ይህንን ወረራ ዝም ብሎ መመልከት ሳይሆን አደገኛነቱን ለዓለም ሰላም ወዳድ ህዝብ በማስታወቅና፣ ለአፍሪካ ህዝብና ለምሁሩም ግልጽ በማድረግ ይህንን ህልምና ዕቅድ እንዲከሸፍ ማድረገ ታሪካዊ ግዴታቸን ነው። አፍሪካን ሚሊታራይዝ ማድረጉ ወደ ጥፋት እንጂ ወደ ሰላም እንደማያመጣን መረዳትና ማስታወቅ ይኖርብናል። አለመረጋጋትን፣ ፀብ መጫርንና ማቀጣጠልንና የባሰውኑ ወደ ከፍተኛ የርስበርስ ዕልቂት ከማምራት በስተቀር ለአፍሪካ አህጉርና ለህዝቦቿ የሚበጅ መንገድ አይደለም። ዘለዓለሙኑ የአፍሪካ ህዝብ በትርምስ ዓለም ውስጥ እንዲኖርና ታሪካዊና የሰለጠነ ስራ እንዳይሰራ የሚያደርግ እጅግ አደገኛ ዕቅድ ነው። ስለሆነም የአፍሪካ ህዝብ ብሄራዊ ነፃነቱ እንዲገፈፍ የሚያደርግ ነው። የአፍሪካ ዕውነተኛ ነፃነት የሚጠበቀው በአህጉሪቱ የተቋቋሙት የውጭ ኃይሎች የጦር ካምፖች ሲፈራርሱና ከእነሱ ጋር የተቆላለፉ የሚሊታሪ ኢንስቲቱሽኖች ሲወድሙ ብቻ ነው። ማንኛውም የአፍሪካ መንግስታት የሚሊታሪና የስለላ ድርጅቶች ከውጭ ኃይሎች ትስስርና ምክር፣ እንዲሁም ስልጠና የፀዱ መሆን አለባቸው። ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ የኢምፔሪያሊስቶች የብጥበጣ ዕቅድና የዘረፋ ስልት መበጠስና መውደም አለበት። ዕምነታችን መሆን ያለበት ዕውነተኛ፣ ከውጭ ኃይሎች ተፅዕኖና የስትራቴጂ ተልዕኮ የተላቀቀ የመላው አፍሪካ የወታደር ተቋም ሲቋቋም ብቻ ነው። ለዚህ ተግቶ መስራት ያስፈልጋል።
የኛው የፓን አፍሪካኒዝም ህልምና ምኞት ጠቅላላው የአፍሪካ ህዝብ ወደ አንድነት እንዲመጣ የሚያደርግና ወደ ጋራ ብልጽግና የሚያመራ መሆን አለበት። የኛ መሰረታዊ ዓላማ የውጭ ኃይሎችን ፍላጎት የሚጻረርና በፍጹም በሰላምንና ዕድገትን ፈላጊነት ላይ የተመሰረተ ነው። የኛው የአፍሪካ ጦር ወራሪ ሳይሆን የአፍሪካን ብሄራዊ ነፃነት የሚያስጠብቅ ነው። ሀብቷንና የህዝቦቿን መብት የሚጠባበቅና የሚከላከል ነው። ስለዚህም በኔቶና በአፍሪኮም የተቋቋመው የወረራ ስምምነት ተፈጥሮአዊውን የሰው ልጅ መብት የሚቃወምና የአፍሪካ ህዝቦች ብቻ ሳይሆኑ የዓለምም ህዝብ በስምምነትና በወንድማማችነት እንዳይኖር የሚያደርግ ነው።
የራሳችንን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ በራስችን አዕምሮ መመራት ያስፈልገናል። ስለዚህም ኔቶና አፍሪኮም ሳይሆኑ የኛን ስራ የሚሰሩልን ራሳችን ለመስራት ከምንግዜውም ታጥቀን መነሳት አለብን። ይህ ብቻ ነው ዕውነተኛውን መንገድ የሚያሳየንና የአፍሪካን አንድነት በማጠናከር ወደ ሰላምና ወደ ተፈለገው ብልጽግና የሚያመራን።
አንድ ላይ በመሆን የአፍሪካን ወጣት በፖለቲካ ረገድ ለማንቃትና ነገሮችን እንዲረዳ ታግተን መስራት አለብን። አፍሪኮም ወደ ቤትህ ተመለስ!! አፍሪካ የአፍሪካውያኖች ብቻ ነው!! ውጭ ሆነ አገር ቤት ውስጥ ያለው ሁሉ መተባበር አለበት። የውጭ አገር ጦር ስፈር መቆም የለበትም፤ አሜሪካ ከጀርመንም ሆነ ከአፍሪካ መውጣት አለበት።
አሸባሪዎችን ማስታጠቁ አሁኑኑ መቆም አለበት። ከጂቡቲ፣ ከትሪፖሊ፣ ከሊብረቪሌ፣ ከሳዖ ቶሜና ከጃሜና መውጣት አለበት።
የዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የአፍሪካን የተፈጥሮ ሀብት መዝረፋቸውን ማቆም አለባቸው። የእርሻ መሬታቸውን መንጠቁ መቆም አለበት። የአፍሪካን የጥሬ ሀብት የሚሸጥና ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ስምምነት የሚያደርግ ማንኛውም የአፍርካ መንግስት በስልጣን ላይ መቆየት የለበትም።
ዲሞክራሲና ህዝባዊ ተሳትፎ ብለን በመነሳት የአፍሪካን አንድነት ድርጊት መቆጣጠርና እንዲሻሻል ማድረግ አለብን።
አፍሪካ እንደገና ነፃ መውጣት አለባት!! ስለዚህም ሴትም ሆነ ወንድ፣ ሸማግሌም ሆነ ወጣት፣ ሁሉም በአንድነት በመነሳት አፍሪካን ከውጭ ወረራና ካማተለል ዘረፋ ማዳን አለብን!!
ስለሆነም ይህንን መግለጫ ከዚህ በታች ስማቸው የሰፈረው ድርጅቶች በሙሉ ይተባበራሉ።
የሶስተኛ ዓለም ፎረም (Samir Amin; Bernard Founou)
ፋውንዴሽን ፍራንዝ ፋኖን (Mireille Fanon-Mendes-France)
ሃንኪሊሶ አፍሪካ (Koulsy Lamko)
አፍሪክ እቬኒር ኢንተርናሽናል
የፓን አፍሪካኒስም የስራ ጠረጴዛ ሚዩኒክ (Dipama Hamado)
ሪቫይቫል ፓን እፍሪካኒዝም ፎረም (Gnaka Lagoke)
የቱኔዚያ የውጭ ግኑኝነት ኢንስቲቱት(Ahmad Manai)
የድሮው የደቡብ ማዕከል ዳይሬክተር(Yash Tandon)
የዲያስፖራ ሙዚካ የሁሩ ራዲዮ
የፓን አፍርካ ኔት ወርክ ትብብር- Ajamu Nangwaya, University oft Toronto
ኤሚራ ውድስ-IPS
የአፍሪካ ፎረም ትብብር
አገራዊ የአፍሪካ የምርምርና የዕድገት ትብብር(ARCADE)
የአፍሪካ የባህል ፕሮጀክት በህግ የተመዘገበ
Dr. Horace Campbell-Syracuse Univeristy
Dr. Saer Maty Ba
Dr. Sanou Mbaye
Dr. Boniface Mabanza(Kirchliche Arbeitsstelle Südliches Afrika KASA)
Dr. Werner Ruf(AG Friedensforschung)
Berliner Postkolonial e.V.(Mnyaka Suru mboro und Christian Kopp)
Dipl.Afrikanistin(Ginga Eichler)
Dr. Lutz Holzinger(Journalist an writer in Vienna)
Ababacar Fall, Dakar Senegal
Dr. Henning Melber, Theo Dag Hammarskjöld Foundation, Uppala/Sweden
የሰው መብትና ደሞክራቲ ኮሚቴ- Wolf-Dieter Narr
Jonanes Louis (Univerite Populaire Kwame Nkrumah)
Werner Kersting, Vorsitzender

ማሳሰቢያ፣

ይህ ጥሪ ካናዳ ውስጥ በሚኖሩና በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር በሆኑት በሚስተር አዚዝ ሳልሞን ፋል የሚመራ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የተዘጋጀ ጽሁፍ ነው። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሚስተር አዚዝ በምኖርበት ከተማ እኔና የአፍሪካ ሀውስ በመተባበር የአፍሪካ አንድነትን ጉዞ፣ ውጤትና ችግር እንዲሁም የወደፊቱ ሁኔታ ላይ በሴሚናራችን ላይ ተገኝተው ከተሳተፉና፣ እሳቸውም በአፍሪካ ላይ የተጣለውን አደጋ በሰፊውና በሚያመረቃ መንገድ ካቀረቡ በኋላ፣ የሃሳብ ልውውጥ ካደረግን በኋላ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ስለሚሄዱ ይህንን ጽሁፋቸውን እንድተረጉም ስለጠየቁኝ በዚህ መልክ አቅርቤዋለሁ። አቶ አዚዝ ጽሁፉን ይዘው በመሄድ ኢትዮጵያ ውስጥም ለሚመለከቷቸው ባለስልጣናት እንደሚሰጡ አውስተውኛል። ይህም ማለት ይህ ጽሁፍ በሳቸው ፈቃድ የተተረጎመ ነው ማለት ነው። ይህንን ዕድል ስለሰጡኝ በጣም አመሰግናለሁ።
ተርጓሚ፤ ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

Jul 2, 2013

ግብጦች ምን ነካቸው…!?abetokichaw

ግብጦች ምን ነካቸው…!?
እስቲ ጠይቁልኝ ግብጦች ምን ነካቸው…
ኡኡታ ሚያሰሙት ካደባባይ ወጥተው…
ከፍቷቸው ነው አሉ ከመንግስት ተኳርፈው…
ታድያ ለምንድን ነው… ካገር የማይወጡ…
“ከነገሩ ጦም ይደሩ” ብለው የማያመልጡ…
ምን አሟገታቸው
ምን አስጨነቃቸው
ምንስ አስጮሃቸው
ዝም ብለው አይሄዱም ሀገሪቱን ጥለው…
እሺ እርሱም ይቅር ሀገር ጥሎ መሄድ እንደ አፍ አይቀልም፡፡
ለምን ዝ…….ም አይሉም ለበጎ ነው ብለው… ለምን ፀጥ አይሉም
“…ካለፈው ይሻላል የባሰ አታምጣ
አምላኬ ተመስገን አናበዛም ጣጣ…”
       ብለው  …ጫ! አይሉም ምን አስጨነቃቸው….
                                                                                                                    አደባባይ ወጥተው እንዲህ መጮሃቸው
                                                                                                                    እስቲ ጠይቁልኝ ግብጾች ምን ነካቸው…!

በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የቦንድ ምንተፋ በተቃዋሚዎች የድምጽ ማእበል እየታመሰ ነበር

ሳዲቅ አህመድ

አትላንታ ጆርጂያ፥አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን የሚያዉለበልቡ ብቻ ሳይሆንየለበሱም ነበሩ።የኢትዮጽያ መንግስት አባይን ለመገደብ በሚልስም ቦንድን ለመመንተፍ የሚያደርገዉን ሴራ እንቃወማለን አባይከመገደቡ በፊት ነጻነት፣ዲሞክራሲ፣ፍትህ ለመላዉ ኢትዮጵያንያሻል በማለት በዘር በሃይማኖት ሳይለያዩም ድምጻቸዉንያሰማሉ።ቁጥራቸዉ የተመናመነ ግለሰቦች ሃፍረት በተሞላበት መልኩ ወደአዳራሹ ቢያመሩም ከመካከላቸዉ አንዳንዶቹ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የሟቹን መለስ ዜናዊ ቲሸርት በመልበስ ቢንጎማለሉምበፍርሃት እየነፈሩ መሆናቸዉ ግን ያስታዉቅ ነበር። “ተከብረሽ የኖርሽዉ ባባቶቻን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም”በማለት ኅብረ-ዜማን የሚያሰሙት ኢትዮጵያዉያን “ተመልከቱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዝግጅት ቢያዘጋጁም የኢትዮጵያንባንዲራን ለማዉለብለብ ግን ፍላጎቱ የላቸዉም! እኛ ግን በአባይ ስም አትነግዱ ስንላችዉ የኢትዮጵያን ባንዲራ እያዉለበለብንነዉ” ይላሉ።“እኛ ኢትዮጵያዉያን ነን ወደ አዳራሹ ለመግባት የዘር መለዮ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት ነዉ የሚያሻን” ብሉዉ ለመደራደርቢሞክሩም አዘጋጆቹ የአባይ ጉዳይ በዘር የተደለደለ እንዲመስል አድርገዉታል። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ከሰላሳ የሚያንሱ የቦንድተመንታፊዎች በሰአት 400 ዶላር በሚከፈልበት አዳራሽ ዉስጥ ሲገቡ ተስተዉሏል። በአዳራሹ ዉስጥም መዝጋቢ ሰዉ እንደሌለ፣እንኳን ደህና መጣቹ ባይ እንዳልነበረ አንድ በተክለ-ሰዉነቱ የስብሰባዉን አዘጋጆች የዘር መስፍርት የሚያሟላ ልቦናዉ ግንለኢትዮጵያዊነቱ የጸና ግለሰብ ዉስጥ ገብቶ የታዘበዉን ገልጿል።በተገቢዉ መልኩ ጥናት ያልተደረገበት አባይን የመገደቡ ሙከራ የዲፕሎማሲና የደህንነንት አደጋ አለዉ፤ ስልጣንን ለማራዘምናአቅጣጫን ለማስቀየር በሚደረግ ደፋ ቀና ነዉ አባይን መገደብ በሚል ስም የኢትዮጵያ መንግስት የሚንቀሳቀሰዉ የሚሉ ተቺዎችብዙ ናቸዉ። ባንጻሩ አባይ አሁን አይገደብ የሚሉት ፖለቲካውዊ ክፋት የተጠናወታችዉ ናቸዉ በማለት የኢትዮጵያ መንግስትለማጣጣል ይሞክራል። አንድ የጋራ እዉነታ ግን አለ፤ በአባይ የመገደብ ጉዳይ ኢትዮጵያዉያን የተለያየ ሃሳብ የላችዉም! ህዝባዊዉክልና የሌዉ ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት “ያላዋቂ ሳሚ ምን ይለቀልቃል” ግድቡን አያርገዉ ባዮች ቢኖሩ እንጂ…ጁን 30 በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የአትላንታ ጆርጂያ የቦንድ ምንተፋ ሂደት ክዉ ድንግጥም ያለ ነበር።

Jun 28, 2013

የትኛው ነው ሊያስጨንቀን የሚገባው ከያሬድ ኤልያስ nome telemark

ከሰሞኑ በአብዛኛው ሶሻልሚዲያ ላይ የምንመለከተው ወይም የምናነበው ቤቴልሄም አበራ(ቤቲ) የተባለች ወጣት ኢትዮጵያዊት በቢግ ብራዘር አፍሪካ ትእይንት (show) ላይ ከሴራሊዮኑ ቦልት ጋር ፈጸመችው ስለተባለው ወሲብ በተለየዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች እና መገናኛ ብዙሃን የሚሰጠው አስተያየት እንደቀጠለ ነው እሷም ከውድድሩ ከተባረረችም  በኋላም የምታደርገው ቃለ ምልልስ እንደቀጠለ ነው የሷም መልሷም እንደዛው አገሬን ወክዬ ነው የሄድኩት ብዙም ነገር ስለአገሬ ተናግሬሃለሁ ከዛ በተረፈ ደግሞ የራሴ ህይወት አለኝ እንደፈለግኩ መሆን እችላለው ስዎም ደግሞ ይሄን ነገር ማስብ ያለበት እንደጌም ነው አለችን ።


አዉን እኔ ለማለት የፈለግኩት ነገር ቢኖር እንደሚከተለው ነው 
 እውን ከዚህ በላይ ስለዚች ልጅ የምንናገረው ሆነ የምንጽፈው ነገር ማብቃት አለበት ባይ ነኝ  እንደማንኛውም ሰው ለመጀመሪያ ግዜ ይህንን ቪዲዮ እንዳየሁት እኔም ሌላው ሰው እንደሚሰማው መጥፎ  ስሜት ተስምቶኛል እንደሌላውም ሰው አስተያየቴን ስጥቻለው በአውን ሰዓት ግን ይህንን ነገር ከሌላም ሰው ጋር ላለማውራትም ሆነ  አስተያየት ላለመጻፍ መቆጠቤን እና  ለዝችም ልጅ ምንም ማሰቢያ ግዜ  እንደሌለኝ ይህንን የቪዲዮ ፊልም  እስካየሁበት ቀን ዕለት የተባለችውን ልጅ በመልክም ሆነ በአካል እንደማላውቃት ሁሉ አሁንም ለራሴ ይችን ልጅ እንደ ኢትዮጵያዊነቷ እንደማላውቃት ማናችንም ብንሆን ደግሞ ስለሷ በምናስብበት ግዜ ሰለአገራችን ማስብ እንደሚበጅ እንድናውቅ።
በዚህ ወቅት ስንት ነገር ነው በህይወታችን ሆነ በአገራችን  እያስጨንቀን ያለው  በዚህ በኩል አገራችን ከደረሰባትና  እየደረሰባት ካለው ነገር እንዴት ነው የምናላቅቃት ብለን በምናስብበት ሁኔታ ላይ እንደመሰናክል ሆኖ የዚች ልጅ ነገር እንደዚህ ሊያደናቅፈን የሚገባ አይመስለኝም ። እውን ነው ባአሁን ሰዓት ሊያስጨንቀን የሚገባው ነገር የዚች ልጅ ጉዳይ አይመስለኝም ይልቁንስ በነጻነት ናፍቆት አሳሩን ለሚበላው ህዝብ ያለ ፍትህ ያለምንም ጥፋት በእስር ለሚማቅቁት ለውድ ወንድሞቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በስደት ላይ ጉዳት እየደረሰበት ላለው ወገን በዓረብ አገራቱ ለሚሰቃዩት ሴት እህቶቻችን በየቀኑ እያየነው ባለው ነገር በዚህ ላይ ነው መጨንቅ ያለብን ።
በኔ በኩል ለአንዴም ለመጨረሻም ይህን ነገር ብያለሁ ማነው ስሟ ቤቴልሄም ነው አይደል እኔ ለአንቺ ለዚህ ተርካሻ ስራሽ ግዜ የለኝም ላንቺ በማስብበት ግዜ ለሌላው በበረሃ ላይ ለሚንገላቱት ሴት እህቶቼ  ማስቡ ይቀለኛል  ለቤተሰቦችሽ ግን  ብርታቱን ይስጣቸው 




-የፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጎርጊስ ደብዳቤ ተቀባይነት አጥቷል ፕሬዝዳንቱ በከባድ የማታለል ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሊቀትጉሀን አስታጥቄ አባተ ትላንት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ፡፡ ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ከቀኑ8፡00ልደታ የሚገኘው ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል ችሎት ይቀርባሉ፡፡ፕሬዝዳንት ሊቀትጉሀን አስታጥቄ አባተ ሶስት የወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ከክሱ ይዘት መካከል ቤት ለሌላቸው አርበኞች ከተሰጠው የኮንደሚኒየም ቤተች ውስጥ ቤት እያላቸው እንሌላቸው አድርገው በመውሰዳቸው 2ኛ እህታቸውን ጨምሮ አርበኛ ላልሆኑና ለማይመለከታቸው ግለሰቦች “አርበኛ ናቸው” ብለው በመስጠታቸው እንዲሁም ከማህበሩ ከፍተኛ መጠን ያለው የብር ጉድለት መታየቱ ይጠቀሳል፡፡ፕሬዝዳንት ሊቀትጉሀን አስታጥቄ አባተ ላይ የተመሰረተው ክስ እንዲቋረጥ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጎርጊስ ለፍትህ ሚኒስቴር የጻፉት ደብዳቤ ተቀባይነት አጥቷል፡፡ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በተለያየ ጊዜ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት በሆኑት በሊቀትጉሀን አስታጥቄ አባተ ተፈፅመዋል ስለተባሉ የተለያዩ የአስተዳደር በደልና የሙስና አቤቱታዎች መዘገቧ አይዘነጋም፡፡


ኢሳት (በደረጀ ሀብተወልድ) ከሁለት ሣምንት በፊት ሲቪሊቲ ፓልቶክ ባዘጋጀው የጋዜጠኞችና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ውይይት

ኢሳት (በደረጀ ሀብተወልድ)

June 27, 2013
 
ከሁለት ሣምንት በፊት ሲቪሊቲ ፓልቶክ ባዘጋጀው የጋዜጠኞችና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ውይይት 
በደረጀ ሀብተወልድላይ ኢሣትን በመወከል ተሳትፌ ነበር። በክፍሉ ታዳሚ ከነበሩት ከ 500 በላይ ተሳታፊዎች መካከል በጣም የሚበዙት የኢሳት ደጋፊዎች መሆናቸውን ሳይ ደስታ ሳይሰማኝ አልቀረም። ከደስታው ባሻገር የተሰማኝ ሌላ ስሜት ግን፦” ሰው እንደዚህ ሲደግፋችሁ፤ የበለጠ በርትቻችሁና ጠንክራችሁ  መሥራት አለባችሁ” የሚል አደራዊ ሸክም ነው።
ደጋፊዎቻችን የመብዛታቸውን ያህል ታዲያ ከጥቂት ሰዎችም ቢሆን  ቅሬታ አዘል ጥያቄዎች መሰንዘራቸው አልቀረም።ኢሳትን በተመለከተ የተሰነዘሩት እነዚህ ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች ሲጨመቁ፦” ኢሳት የግንቦት 7 ነው፣ ግንቦት 7 እና መሪዎቹ  ከሌሎች ፓርቲዎች በተለየ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ያገኛሉ፣ ጭራሽ የሚዲያ ሽፋን የማትሰጧቸው ፓርቲዎች አሉ” የሚሉ ናቸው።
ለሦስቱም ጥያቄዎች ለመስጠት የሞከርኩትን መልስ ነው እዚህ  በመልኩ ለማስቀመጥ የሞከርኩት፦
1-      ኢሳት የግንቦት 7 ነው የሚለውን በተመለከተ፦
ይህ ጥያቄ መነሳት የጀመረው ከኢሳት ምስረታ ጊዜ አንስቶ መሆኑ ይታወቃል።በወቅቱ ይህን ወሬ ከሰሙት መካከል  አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አንዱ ነበር። ታማኝ  የኢሳት 1ኛ ዓመት በዋሽንግተን ዲሲ ሲከበር ለጥያቄው መልስ የሰጠው፦” አይደለም እንጂ ቢኾንስ !?”በማለት ነበር። ቀደም ባሉት ዓመታትም ራዕይ ያላቸው አገር ወዳድ ዜጎች የቤት ካርታቸውን ሳይቀር እያስያዙ ከባንክ በተበደሩት ገንዘብ ያቋቋሙት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኔትወርክ(ኢቲኤን) ይሰኝ የነበረው ተወዳጅ   የቴሌቪዥን ጣቢያ “አንዴ የ ሲ. አይ. ኤ ነው ሌላ ጊዜ የ እነ እገሌ ነው” ከሚል ሀሜት ሊያመልጥ ያለመቻሉን ታማኝ በማውሳት፤ ሰው እየወጣ ለሚናገርበትና ሀሳቡን ለሚገልጽበት  ጣቢያ ህልውና-  የድጋፍ ጥያቄ ሲቀርብለት ምላሽ ባለመስጠቱና የጣቢያውን ህልውና ማስቀጠል ከነዛ ጥቂት ሰዎች አቅም በላይ በመሆኑ ሊዘጋ መቻሉን አብራርቷል።Ethiopian Satellite Television, ESAT TV
“በጣም የሚያሳዝነው ኢ.ቲ.ኤን ተዘጋ ሲባሉ  እሠይ! ደግ ሆኑ!” ያሉ ሰዎች መሰማቱ  ነው።”ሲልም ታማኝ አክሏል።አዎ!ጣቢያው መዘጋቱ የሁሉም መናገሪያ አፍ መዘጋቱ ቢሆንም፤ በዚህ የተደሰቱ  <<ሰዎች>> እንደነበሩ ታማኝ ልምዱን አካፍሎናል።
በወቅቱ ኢሳት በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ መሆኑን የገለጸው ታማኝ፤ ይህን እውነት የማይቀበሉ- የማንም ይሁን የማን የባለቤትነቱ ጉዳይ ሊጨንቃቸው እንደማይገባ፣ ኢሳትን ሊጠይቁትና ሊተቹት የሚገባው እየሠራው ባለው ሥራ ሊሆን እንደሚገባው፣ የዚህ ዓይነት ሥራ የሚሠራ ሚዲያ አይደለም ግንቦት 7- ኢህአዴግም ቢሆን ካቋቋመ ሊመሰገን እንጅ ሊነቀፍ  እንደማይገባው በመንገር ነበር ምላሹን የቋጨው።
-የዩኒቲ ኮሌጅ ባለቤትና ፕሬዚዳንት በነበሩት በዶክተር ፍስሀ እሸቱ “ዕለታዊ አዲስ” የተሰኘ ዘወትር የሚታተም ጋዜጣ ሲቋቋም በፕሬስ ተቋሙ ታቅፈው ከሠሩት ጋዜጠኞች መካከል- ይህ ፀሀፊ አንዱ ነበር። ያኔ ዕለታዊ አዲስ ይታማ የነበረው “ሲ.አይ.ኤ ያቋቋመው ነው” እየተባለ ነበር። ጋዜጣው በርዕሰ-አንቀጹ  በሰጠው ምላሽም ፦”አረ በፍፁም! የሲ.አይ. ኤ አይደለሁም”የሚል ሙግት ውስጥ አልነበረም የገባው-ይልቁንም፦ “ሲ.አይ. ኤ ይህን ጋዜጣ፤ እየሠራ ላለው ተግባር አቋቁሞ ከሰጠ ሊመሰገን ይገባዋል” የሚል ነበር ምላሹ።ሁሌም አዲስና ተልቅ ነገር ከትችት  ሊያመልጥ እንደማይችል ያለፉ ልምዶቻችን ሁሉ ምስክሮች ናቸው።
በኢሳት ዙሪያ ለተነሳው ተመሣሳይ ጥያቄም በበኩሌ ከዚህ ውጪ ምላሽ የለኝም። ኢሳት በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ነፃ ሚዲያ መሆኑን እረዳለሁ።  እኔ የምናገረው፤ የማውቀውን ያህል ነው። ይህን ስነግረው <“አይ ተሣስተሀል ፤ኢሣት የግንቦት 7 ነው”  የሚለኝ ካለ ምላሼ፦”እና? ቢሆንስ?” የሚል ነው።ግንቦት 7ቶች ራሳቸውን የሚተቿው ሰዎች ሰይቀሩ በተደጋጋሚ  የሚስተናገዱበትን ነፃና ገለልተኛ ሚዲያ ካቋቋሙ በእውነት  ልናደንቃቸው ይገባል። አዎ!እንደሚወራው ኢሳት የግንቦት 7 ነው ብለን የምናምን ከሆነ፤ የየግንቦት 7 መሪዎች  ዲሞክራቶች መሆናቸውን በተግባር ከማስረገጥ ውጭ ሌላ የሚሰጠን ትርጉም ሊኖር አይችልም።
2-ግንቦት 7 እና መሪዎቹ በኢሳት የተለየ ሽፋን ያገኛሉ የሚለውን በተመለከተ፦
ይህ አባባል  በመረጃ ላይ ሳይሆን በግምት የተወሰደ ድምዳሜ እንደሆነ ተረድቻለሁ።ግምት ሁልጊዜ ህሊናዊ(ሰብጀክቲቭ) ነው። ይሆናል ብለን የገመትነው ነገር በመረጃ ሲመረመር ከግምታችን ውጪ የሚሆንበት አጋጣሚ ጥቂት አይደለም። ግንቦት 7 ሰፊ ሽፋን ያገኛል የሚለውን ወሬ ለመጀመሪያ ጊዜ  የሰማን ሰሞን ለማወቅ ያህል ” ለየትኛው ፓርቲ ብዙ ሽፋን ሰጥተናል?” በሚል -ዜናና ፕሮግራም ቆጠራ ድረስ ገብተናል።ያኔ አንድነት ፓርቲ ጥሩና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ የሚያደርግበት ጊዜ ነበር(እነ አንዷለም ሳይታሰሩ ማለቴ ነው)  በወቅቱ ባደረግነው ቆጠራ ሰፊ ሽፋን አግኝቶ የነበረው አንድነት ፓርቲ ነው። ዶክተር ነጋሶ፣ አቶ አንዷለም፣አቶ አስራት ጣሴ… ሌሎችም  የአንድነት አመራሮች በተደጋጋሚ ቃለ-ምልልስ የሰጡበትና ያወጧቸው የነበሩት መግለጫዎች በሙሉ ሽፋን ያገኙበት ጊዜ ነበር።
-ግንቦት 7 በነጀነራል ከማል ገልቹ ከሚመራው የኦነግ አንድኛው ክንፍ ጋር ትብብር በመሰረተ ሰሞን ደግሞ- ከፍ  ያለ ሽፋን አግኝቶ ነበር።
-የሙስሊሞች መብታችን ይከበር ጥያቄ የተነሳ ሰሞን ደግሞ ጉዳዩ ከሁሉም የበለጠ ከፍተኛ ሽፋን አግኝቶ ነበር።
-የዋልድባም እንደ ችግሩ መጠን ሰፊ ሽፋን አግኝቷል።
-ከሳምንታት በፊት ሰማያዊ ፓርቲም እንዲሁ  ትርጉም ያለውና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ማድረግ ሲጀምር ሰፋ ያለ ሽፋን አግኝቷል። ወዘተ..
-በግለሰብ ደረጃም የዓባይ ወንዝ ግድብ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እነ ዶክተር ጌታቸው በጋሻው እንዲሁም በአውስትራሊያ፣ በአውሮፓና በደቡብ አፍሪካ የ ኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ሲያካሂዱ እነ  ታማኝ በየነ፣ በተለያዩ ጉዳዩች ፖለቲካዊ ትንታኔያቸውን እንዲያጋሩን ስንፈልግ  ደግሞ እነ ጃዋር መሀመድ… ወዘተ በተደጋጋሚ በኢሳት ላይ ቀርበዋል። ይህ ማለት ጋዜጠኞቹ ለምንሠራቸው ዘገባዎችና ቃለምልልሶች  በአመዛኙ እየተመራን ያለነው በክስተቶች (Events) ነው ማለት ነው።
አንዳንዶቻችን ግን ይህን አልተገነዘብንም ወይም ላለመገንዘብ አስቀድመን የራሳችንን መስመር አስምረናል። ከተጠቀሱት ድርጅቶችና ግለሰቦች ጎልቶ ሚታየን፤ እነ ዶክተር ብርሀኑ ኢሳት ላይ መናገራቸው ብቻ ነው።እደግመዋለሁ ሁላችንም ሳንሆን አንዳንዶቻችን።
ስለዚህ በዚህ ዙሪያ የምንወቀስበት ነገር ካለ ወቀሳው መቅረብ ያለበት ከላይ በአብነት  እንደተጠቀሱት ያሉ  ትኩረት ሳቢ(የዜና ዋጋ ያላቸውን) እንቅስቃሴዎች አድርጎ ሽፋን ያልሰጠንለት ድርጅት ካለ፤ ያን በማሳየት  ቢሆን ይመረጣል። “ጥሩ አንቀሰቃሴ(የዜና ዋጋ ያለው) አደርጌ ሽፋን አልሰጣች ኝም”የሚል ድርጅት ካለ በተጫባጭ በማሳየት ሊወቅሰንም፣ በአደባባይ ሊከሰንም ይችላል።ያ ሲሆን እኛም ያላየናቸውን ስህተቶች ዐይተን ለማስተካከል ዕድል ይኖረናል።እስካሁን ባለው ሂደት በማንም ይደረጉ በማን፤ ያየናቸውን ክስተቶች በሙሉ ያለምንም አድሎ ባለን አቅምና የሰው ሀይል ለመሸፈን ሞክረናል።ከዚህም አልፎ(ብዙዎቹ መረጃ ለመ ጠት ፈቃደኛ አይሁኑ እንጂ) በተለያዩ ጉዳዩት ዙሪያ የመንግስትን  ሀላፊዎች ለማነጋገር ብዙ ጊዜ ሙከራ ተደርጓል።
ይህን ስል  የተሟላ ሥራ እየሠራን ነው እያልኩ አይደለም።ብዙ በሚሠራ ተቋም አልፎ አልፎ ለስህተት መዳረጉ የሚጠበቅ እስከሆነ ድረስ ፤ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። እኛ ራሳችን የምናያቸውና የምንነጋገርባቸውም ነገሮች አሉ።በየጊዜው ግን ድክመቶቻችንን ለማሻሻል ጥረት እያደረግን ነው። አሁንም የምለው ነገር ቢኖር፤  በዚህ ረገድ ድክመቶች ተስተውለውብን ከሆነ፤ልንመከርና ልናስተካክል ዝግጁ ነን።
በ3ተኛ ደረጃ የተነሳውን ጥያቄ የማየውም ከዚሁ አንፃር ነው። እስከዛሬ የሚዲያ ሽፋን ያላገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ይኖራሉ። ያ የሆነው ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት በአመዛኙ በክስተቶች እየተመራን በመሥራታችን እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም። ወደፊት እነዚህን ጉዳዮች በዕቅዳችን በማካተት ያሉብን ጉድለቶች ለማሻሻል እንጥራለን። ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐይንና ጆሮ ነው የምንለው ለመፈክር ብቻ አይደለም። ከልብ በማመን ነው።
በመጨረሻም፦
ሰሞኑን  በፌስ ቡክ በተሰራጨው የዶክተር ብርሀኑ ንግግር ዙሪያ አስተያየት እንድሰጥ የጠየቃችሁኝ በርካታ ናችሁ።የተሟላና የጠራ መረጃ ባላገኘሁበት ሁኔታ አስተያዬት መስጠት ስላልፈለግኩ ነበር ዝም ያልኩት። አንዳንዶቻችሁ ግፊታችሁን ባለማቆማችሁ በአጭሩ የምለውን ልበል፦
ዶክተር ብርሀኑ በንግግራቸው የጠቀሷቸው ሁለት ተቋማት አሉ-ግንቦት 7 እና ኢሳት። በሚመለከተኝ በኢሳት ጉዳይ ላይ  ባ’ጭሩ የምለው ነገር ቢኖር ፦የኢሣትን ህልውና  ለማረጋገጥና ቢያንስ አሁን በሚያደርገው መጠን ስርጭቱን ለማስቀጠል  ከተፈለገ ፤ ዲሞክራሲ በአገሬ እንዲያብብ እሻለሁ የሚሉ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ሁሉ ኢሣትን የመርዳት ሀላፊነት ጭምር አለባቸው የሚል ነው። ኢሣት ከምስረታው ድረስ እስካሁን ድረስ “እባካችሁ እርዱኝ” እያለ እንደሚገኝ  በግልጽ የሚታወቅ ነው ።  ይሁንና እንደ ኢሣት ያለን -ከነ ኢቲቪ የተለየ ድምጽን የመጠበቅ  ሀላፊነቱ- የግለሰቦችና የድርጅቶች ብቻ አይደለም።  ስላልታደልን ነው እንጂ በዋነኝነት ኢሣትን  ሊረዳ የሚገባው የኢትዮጵያ መንግስት ነበር።
እዚህ ላይ ሊነሳ የሚገባው ዋነኛ ጥያቄ፦” ኢሳት ከግለሰቦችም ሆነ ከተለያዩ አካላት የሚያገኘው ድጋፍ የኢዲቶሪያል ነፃነቱን አያሳጠውም ወይ?” የሚል መሆን ነው ያለበት። አዎ! የገንዘብ ድጋፍ መቀበልን- የሚዲያን ነፃነትና ገለልተኝነት አሳልፎ ከመስጠት ጋር በማያያዝ ስጋታቸውን የሚገልጹ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ተገቢ ስጋት ነው።
ይሁንና ኢሣት የተመሰረተበት ጊዜ፣ ቦታ(በስደት)፣ዓላማ፣ የተቋሙ አወቃቀር፣የሚገኝበት ሁኔታ ወዘተ..ለተጠቀሰው ስጋት የሚያጋልጠው አይደለም። ይነስም ይብዛም በተለይ በውጪ አገር የሚገኙ በርካታ  ኢትዮጵያውያን  በቋሚነት ሳይቀር ኢሣትን እየደገፉ ይገኛሉ። እነዚህ ወገኖች ኢሳትን እየደገፉ ያሉት ለራሳቸውና ላ’ገራቸው ሲሉ ነው። የድጋፍ መነሻቸውም ይህ አመለካከታቸው ነው። ሰዎቹ ኢሳትን በቋሚነት ስለሚደግፉ በግላቸው ያገኙት ወይም የተደረገላቸው ነገር የለም።ሊኖርም አይችልም። ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶችም ጉዳይ  ከዚህ በተለየ መልኩ ሊታይ አይችልም።አንድ ድርጅት ኢሳትን ሊረዳ የሚገባው የኢሳት መኖር ለማደርገው (ለሚደረገው) ዲሞክራሲን የማምጣት ትግል ጠቃሚ ነው በሚል አመለካከት እንጂ- ባደረገው ድጋፍ ምክንያት በተለየ መልኩ በሚዲያው ለመስተናገድ በማሰብ  አይደለም። ግንቦት 7ትም አንደተበለው አሣትን ደግፎ ከሆነ  ከዚህ እሣቤ ውጪ  ይሆናል ብዬ ፈጽሞ አልገምትም።  “በታገልነው ልክ የስልጣን ደመወዝ ይገባናል “ የሚሉ ገዥዎችን አምርረው የሚኮንኑ ሰዎች ይህን ያስባሉ ማለት በጣም ይከብዳል።     እስካሁን ያሉት የኢሣት አሠራሮችም ይህን አያመለክቱም።
ላብራራ፦  በኢሣት ጋዜጠኞች የኤዲቶሪያል ስብሰባ ላይ አንድም ቀን ከሌሎች በተለየ መልኩ ለእገሌ ፓርቲ ወይም ድርጅት  ይሄ ይሠራለት የተባለበት ጊዜ  ፈጽሞ የለም-ሊኖርም አይችልም።እስካሁን ድረስ የኢዲቶሪያል ነፃነታችን  የተጠበቀ እንደሆነ በድፍረት መናገር እችላለሁ። አልዋሸሁም።ይህን ፅሁፍ  ጓደኞቼ ሊያነቡት እንደሚችሉ አውቃለሁና ቢያንስ እነሱ እንዲታዘቡኝ አልፈልግም።ከዚያም በላይ ህሊና አለ። ማንም ጣልቃ የማይገባበት የኤዲቶሪያል ነፃነት አለን። ሥራችንን እና እንግዶቻችንን የምንወስነው  በኤዲቶሪያል ስብሰባችን  በነፃነት እየተነጋገርን፣እየተከራከርን፣እየተሟገተን ነው።   በምን ምክንያት  ካ’ገራችን ተሰደድን?  …… <<አሳልፈን አንሰጥም!>> በማለታችን ምክንያት ለእስር እና ለስደት የተዳረግንበትንና ስንት ያየንበትን መክሊታችንን/ሀብታችንን/ ነፃነታችንን፤ እዚህ ለምን ብለን የምንጥለው ይመስላችሁዋል? ለገንዘብ? ለጥቅም? ወይስ ለዝና?  በፍጹም!!!  እንዳትሣሳቱ።  ቢያንስ ለራሳችን ክብር  አለን።               ሀቁ ይኸው ነው፦  ነፃና ገለልተኛ የሆነ የኤዲቶሪያል ነፃነት አለን። አምላክ ዕድሜና ጤናውን ይስጠን እንጂ – ይህ ሙያዊ ነፃነታችን ተጠብቆ እስከቀጠለ ድረስ ከኢሣት ጋር እንቀጥላለን።እደግመዋለሁ፦ደመወዝ እስከተከፈለን ድረስ ሳይሆን ፤አሁን ያለን ሙያዊ ነፃነት እስከተጠበቀ ድረስ።    በዚህ አጋጣሚ  እንዲህ ያለ ሙያዊ ነፃነቱ የተጠበቀ የሚዲያ ተቋም ለመሰረቱ ሰዎች ያለኝን ታላቅ አክብሮት ሳልገልጽ ባልፍ፤ ንፉግ እሆናለሁ።
እናም… አስተያዬቴን የጠየቃችሁኝ ሰዎች፣ እንደተባለው ግንቦት 7- ለኢሳት ድጋፍ አድርጎ ከሆነ፤ የግንቦት 7 መሪዎችን- በባልደረቦቼና በኢሳት ወዳጆች ስም ከልብ አመሰግናለሁ ከማለት ውጪ ሌላ ምን ልል እችላለሁ?ሌላ ማለት ካለብኝ ልል የምችለው፦  “ ሌሎችም ድርጅቶች ሆናችሁ ግለሰቦች በምትችሉት አቅም በልጅነት ዕድሜ ላይ የሚገኘውን ኢሳትን በመርዳት በአገራችን  ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ታግዙ ዘንድ አደራ!” ነው ።
ኢሣት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንደበት፣ ዓይን እና ጆሮ ነው!!!

ሰበር ዜና የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት የኢሚግሬሽን ሕጉን አሣለፈ

አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡

ዋሺንግተን ዲ.ሲ. — 


አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡ በምክር ቤቱ ውስጥ ዛሬ በተሰጠው ድምፅ 68 ሴናተሮች የድጋፍ ድምፃቸውን ሲሰጡ 32 ሴናተሮች ደግሞ ተቃውመውታል፡፡ ይህ ሕግ አያይዞም ዩናይትድ ስቴትስ የተጠናከረ የወሰን ጥበቃ እንዲኖራት የሚያዝዝ ሲሆን ከሜክሲኮ ጋር ባላት ድንበር ላይ ሃያ ሺህ ተጨማሪ የወሰን ቃፊሮች እንዲሠማሩ እና የአንድ ሺህ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አዲስ አጥር እንዲሠራ ይፈቅዳል፡፡
የተበላሸውን የሃገሪቱን የኢሚግሬሽን ሥርዓት ለመጠገን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ነው ሲሉ የሕጉ ደጋፊ የሆኑት በአፍሪካ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለዛሬው የሴኔቱ ውሣኔ አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡ ሕጉ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለተወካዮች ምክር ቤቱ የሕግ መምሪያው እንደራሴዎች ለድምፅ ይቀርባል፡፡ ሕግ ለጣሱ ምህረት የሚሰጥ ነው የሚሉትን ማንኛውንም እርምጃ እንደሚቃወሙ ወግ አጥባቂ ሪፐብሊካኖች ይናገራሉ፡

Jun 26, 2013

“መቶ ሚልዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፤ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ሲያስፈራሩት ይታያሉ” – ስብሃት ነጋ (አዲስ ቃለ-ምልልስ)

(በቀጣይ ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ያቀረብነው ቃለ ምልልስ አቶ ስብሃት ነጋ ሰንደቅ ለሚባለው ጋዜጣ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ነው።
ቃለ ምልልሱ ዛሬ በኢትዮጵያ በታተመው ጋዜጣ ላይ ታትሞ ተሰራጭቷል። ጥያቄዎቹ በሰሞናዊዎቹ በሙስና እና በአባይ ጉዳይያተኩራሉ። ለግንዛቤዎ በሚል እንደወረደ አቅርበነዋል”")ሰንደቅ፡- ባለፉት ስርዓቶች ሙስና እንደ አሁኑ ብዙ ጫጫታአይሰማበትም ነበር። ለምን አሁን?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ትክክል ነህ። ምክንያቱም በፊውዳሉ ስርዓትመሬቱም ጉልበቱም የባላባቶቹ ንብረት ስለነበረ ቀጣፊ የሚባለውጭሰኛ ነበር። “ቅጥፈቱም” ለባላባቶች ከሚያርሰው መሬት ትንሽለሆዱ የሚሆን በቆሎ ከዘራበት ለምን ቦሎቄ አልዘራህም ተብሎበቦሎቄ ሂሳብ ይቀጣል። የመንግስት ሰራተኛ የመንግስት ገንዘብከሰረቀ ግን ጐደለበት ነበር የሚባለው። በደርጉ ቢሮክራቲክሶሻሊዝም ስርዓትም ቢሆን የከተማ ንብረት በመሉ በእጁ ስለነበረ የተገኘችው እንደፈለገ ነበር፤ ለራሱም ለቤተሰቦቹምሲጠቀምበት የነበረው። ስለዚህ ሁለቱም ሃብት ፈጣሪዎችም አልነበሩም የተፈጠረው ሃብትም በመሰረቱ የራሳቸው ነበር። አሁንበመንግስትም በገበሬም በግሉ ባለሀብትም በፍጥነት ሃብት እየተፈጠረ እያለ ከስርዓቱ ጋር የማይሄድ ሙስና እያጋጠመ ነው።ሰንደቅ፡- በባህርዳር በተካሄደው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ በኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ ዘመቻ እንዲከፈት ለጉባኤው ጥሪ አቅርበውነበር። ጥሪውን ለማቅረብ የነበረዎት መነሻ ምን ነበር?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ኪራይ ሰብሳቢነት የስርዓታችን አደጋ ነው ተብሎ በትክክል የተቀመጠው ገና ኢህአዴግ ስራ ሲጀምር ነው።ስለዚህ ሙስና ያለቅጥ እየተስፋፋና አደጋ እያደረሰ ሲሄድ ጠ/ሚ/መለስም፤ ጠ/ሚ/ሃይለማርያምም፤ የኢህአደግ ጽ/ቤትኃላፊው አቶ ሬድዋንም፣ ተራው ህዝብም በየመንገዱ በየመስርያ ቤቱ ለአመታት ሲጮሁበት የነበረ ጉዳይ ነው። እኔም እንደሌሎቹ ነው ስለሙስና የተናገርኩት እንጂ የተለየ ነገር የለውም። የተለየ ካለው ሙስና ከውጭ ወራሪ ኃይል የከፋ ጠላት ነውናሙስና የተወራበት ቦታ ካለ የሚመለከታቸው አካላት ለደቂቃም ሳይዘገዩ ማጣራት ግዴታቸው ነው፤ ስል አሳስቤአለሁ።ሰንደቅ፡- አሁንበሀገሪቷ ውስጥ ያለውን አደጋስ እንዴት ያዩታል?አቶ ስብሀት ነጋ፡- በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ሙስና ጠቅላላ የሀገሩና የኀብረተሰቡን ህይወት ወደ ከፍተኛ ምስቅልቅል የሚመራተግባር ነው። በመንግስት፤ በግልና በገበሬው የሚካሄደው ልማት ተገቢውን ውጤት ሳያመጣ ሊቀር ይችላል። በሙስና ምክንያትበመንግስት የሚፈፀሙ እቅዶች በተገቢው ወጪ፤ በተፈላጊው ጥራትና ጊዜ እንደማይፈፀም የአደባባይ ሚስጢር ነው። በዚህ ጉዳይምን ያህል ጉዳት ደረሰ በጥናትና በምርመራ ነው የሚታወቀው። መንግስት የተቀናጀ ሁሉም ዓይነት ድጋፍ በመስጠት በሁሉምየኢኮኖሚ ዘርፎች ልማታዊ የግል ባለሀብት እፈጥራለሁ ነበር ያለው። አሁን በየሴክተሩ ያለው ባለሀብት እውነት የኢትዮጵያንኢኮኖሚ በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል አቅም አለው ወይ ብለን ብንጠይቅ፣ መልሱ አሉታዊ ነው ሊሆንየሚችለው። ጥገኛውን በተቀናጀ ጫና እያዳከምን አቅመ-ቢስ እናደርገዋለን፤ ያልነውስ የት ደረሰ ብለን ብንጠይቅስ መልሱምንድነው? ጥገኛው እየበረታ ልማታዊው ሳይፈጠር የቀረበት ሁኔታ ውስጥ ያለን እንዳንሆን መገመት፤ ከግምት ወጥተንምመገምገም የሚጠይቀን ይሆናል።ሙስና በልማት ብቻ ሳይሆን በመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ግንባታ ላይም የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ ነው። ህገመንግስትን በመጣስ የላይኛው የታችኛውን ኃላፊ እያዘዘ ለዚህ አድርግለት፤ ለዚያኛውም ቀማው፤ እሰረው የሚል አለ። ስልጣንየሚቀማው ለኢኮኖሚው /ሙስና/ ጥቅሙ ነው። ስልጣን እየተቀማ ያለውም በዚያች ወንበር ተቀምጦ ለመቆየትና ትርፍራፊአገኛለሁ ብሎ በማሰብ ነው። በወንበሩ ላይ እስካለ ድረስ ጥቅም ያገኛል። ስልጣን በመንጠቅ በመነጠቅ የሚፈፀም እንዳልሆነከፓለቲካዊ ድርጅት ፈንጠር ብለው የድርጅቶችን አባልነታቸው ስም በመጠቀም የራሳቸው ህገ ወጥ ሰንሰለት ፈጥረው ሊዘርፉሊያዘርፉ የሚኖሩ ግለሰቦችም የተፈጠሩ ይመስለኛል። ፈንጠር ማለቴ በኔትወርክ ማለቴ ነው። ስለዚህ በመንግስትም በፖለቲካዊድርጅቶችም ለስርቆት ተቋማዊ አሰራር ከተጀመረ አደጋ ነው።የሙስና አደጋ በልማትና በዲሞክራሲ የሚያመጣው አደጋ ብቻ ሳይሆን በሃገር ፀጥታና በሰው ልጆች የሚያመጣው የስነ አእምሮጫናና ስጋትም ጭምር ነው። ሌባ የሰላም ሃይል አይደለም። ለውጭ ጠላትና ለሃገር ውስጥ ፀረ ህዝብ ተገዢ ነው። በልማታዊናበፀረ ሙስና ሃይሎች የማይተኛ ፈሪ ጨካኝና ፈጣን አራዊት ነው፤ ሙሰኛ።በመሰረቱ በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፤ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፤ የመንግስት ሰዎችነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚልዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፤ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡትሲያስፈራሩት ይታያሉ ይባላል። ጠቅለል አድርገን ስናየው አሁን ያለው የአንዳንድ የመንግስት፤ የፓርቲና የግል ባለሃብቶችከኢህአደግ መንግስት ስርዓት ፈፅሞ የማይሄድ ፀረ-ልማት፣ ፀረ ዴሞክራሲና ፀረ ሠላም እየሆኑ በመጓዝ ላይ ነው ያሉት።ሙሰኝነት ከኢህአዴግ ስርዓት አኳያ ስናየው ከውጭ ወራሪ ኃይል እጅጉን የከፋ ጠላት ነው። ድንበር የተሻገረ ጠላት ጊዜየሚሰጥና በሁለተኛ ደረጃ የሚታይ አደጋ ነው። ስለዚህም ዋናው አደጋ የውጭ ጠላት ሳይሆን በስርዓቱ የሚደርስ አደጋ ነው።የስርዓቱ ባለቤቶችና ስልጣን እየተረከቡ የሚሄድት ልማታዊ ባለሃብት እና ወዝአደሩ ሳይፈጠሩ እየቀሩ፣ ስርዓቱ እንደ ሌሎቹየአፍሪካ አገሮች የጥገኛው ባለሃብትና የቢሮክራቱ ስርዓት ይሆናል።ሰንደቅ፡- ይህ ስርዓት በኪራይ ሰብሳቢዎች የመጠለፍ አደጋ ይገጥመዋል ብለው ይሰጋሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡-ያለውንየሙስና ሁኔታ የሚመጥን እርምጃካልተወሰደ ስርዓቱ ያለምንም ጥርጥር አደጋ ይገጥመዋል።አደጋውም በልማታዊነት ዴሞክራሲያዊነት ብቻ ላይ አያበቃም።ሰላም በውስጥም ከውጭም አይኖርም። ይህ ሲከሰት ደግሞየሰላም የልማት የዴሞክራሲ ተምሳሌት የተባልነውን ያህል ወደድሮ አሳፋሪ ስማችን እንመለሳለን።ሰንደቅ፡- ሙስናን ለመታገል በመንግስት በኩል የፖለቲካቁርጠኝነት ነበር ብለው ያምናሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- የሙስና መጀመርና እየተስፋፋ መሄድ ከአስርዓመታት በላይ ሲነገርለት የነበረ ጉዳይ ነው። እኔ እስከማውቀውአልፎ አልፎ የሚወሰዱ ሁኔታውን የማይመጥኑ የተናጠልእርምጃዎች ነበሩ። ጥራታቸውን ለሚያውቁ እንተወው።ሰንደቅ፡- የሙስናውደረጃ አሁን ባለበት ደረጃ እስከሚደርስ ለምን ተኛን ብለው ይገምታሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ሙስናውእዚህ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ለምን ተኛን የሚለው የግምገማ ጉዳይ ስለሆነ ቢቆይ ይሻላል።ሰንደቅ፡- አሁን መንግስት በኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ የጀመረውስ እርምጃ ተመጣጣኝ ነው ብለው ያስባሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- አብረን የሰማነው የጠ/ሚ/ኃይለማርያም ቃል ነው የምደግምልህ። “ፀረ ሙስና እንቅስቃሴ ይቀጥላል፤ህዝቡ ይሳተፍበታል፤ እኔ ራሴ በቀጥታ እከታተለዋለሁ” ብለዋል። ይህ የእሳቸው ንግግር የፖለቲካ ቁርጠኝነት ይንፀባረቅበታል።አሁንበሙሰኞች ላይ በተወሰደው እርምጃም ተጠቃሚው ሰፊ ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ እጅግ በጣም የተደሰተ ይመስለኛል።እርምጃ መወሰድ የተጀመረው ህዝቡ ይሳተፋል፤ እኔ እራሴ እከታተለዋለሁ ካሉ በኋላ ነው። ይቀጥላል የሚለው ቃል እርምጃውከተጀመረ በኋላ የተገለፀ ነው። ስለዚህም የጠ/ሚኒስትሩ ቃልና ተግባር ስለተገጣጠሙ አስተማማኝ ጅምር ነው እየሆነ ያለው።መቆም ወደማይችልበት ደረጃ የደረሰ ይመስለኛል።ሰንደቅ፡- ይመስለኛል፤ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ይንፀባረቅበታል ከሚሉ ለምን በእርግጠኝነት ምላሽ አይሰጡኝም?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ጠ/ሚኒስትራችን ያለው እንደማይቀለበስ እርግጠኛ ነኝ። አካሄድ ላይ ግን እርግጠኛ ለመሆን አልቻልኩም።በተለይ ኪራይ ሰብሳቢዎችን ለመዋጋት በህዝብ ተሳታፊነት እንዴት ሊሆን እንደሚችል አላወቅኩም። ህዝብ ያለውኢንፎርሜሽንና በእንቅስቃሲያዊ አካሄድ ያለው ገንቢ አመለካከት ለማን ነው የሚያቀርበው? እንዴት ነው የሚያቀርበው?ካቀረበው በኋላስ በየፈርጁ ተደራጅቶ እንደገና ለውይይት ለጥራት ለህዝቡ እንዴት? መቼ? በማን? ነው የሚቀርበው። ወይስበተናጠል ከቀረበ በኋላ ወደ ማጣራትና ወደ ምርመራ ወደ ክስ ነው የሚኬደው? ባጭሩ የህዝቡ ተሳትፎ አካሄድ የህዝቡ አቅምበሚያዳብር አግባብና ጥራት ያለው ውጤት መሄድ አለበት የሚል እምነት አለኝ።እኔ የሚታየኝ አሁን ያለው የኪራይ ሰብሳቢነት ሁኔታ በአጠቃላይ፤ ስፋቱ፤ ጥልቀቱ፤ በየትኛው የመንግስትና የግል አካላትእንደሚታይ በሚመለከተው አካል አማካኝነት ለህዝቡ መቅረብ አለበት። ሁኔታው ከቀረበ በኋላ ህዝብ ያዳብረዋል። ዋነኛውህዝብ ማለት ደግሞ፣ በአገልጋዩ የመንግስት አካል የሚሰራ ሰራተኛ እና በዚሁ አካል በቀጥታ የሚገለገል ህዝብ ነው። ይህምሲባል፤ ከሁኔታው ጋር በቀጥታ ዝምድና ያላቸው ህዝቦች ማለት ነው። ሌላውም የኅብረተሰብ ክፍል በሚድያ በመድረክ ሊሳተፍይችላል። በዚህ መልኩ ሁኔታው ከታየ በኋላ በቀጣይ መንስኤውን ማስቀመጥ ነው። በሶስተኛ ደረጃ ያስከተለውን ኪሳራ ማየትነው። በአራተኛ ደረጃ መፍትሄውን ማየት ነው። ባጭሩ ሁኔታ፤ የሁኔታው መንስኤ፤ የፈጠረው ጠንቅ እና መፍትሄው ላይ ነውህዝቡ መሳተፍ ያለበት። ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ነበረ ወይ የሚለው በዚህ ሂደት ነው የሚመለሰው።ሰንደቅ፡- ከላይያስቀመጡትን ሂደቶች ማነው የሚያዘጋጀው?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ይህን መነሻ /መንደርደርያ/ ግምገማ ማን ነው የሚያዘጋጀው የሚለው የእኔም ትልቅ ጥያቄ ነው። በፀረሙስና ኮሚሽን ተቋም ውስጥ ያለውን መረጃ ለዓመታት ከአገርም ከውጭም የተጠራቀመ ኢንፎርሜሽን አሉ። በአሁኑ ጊዜምህዝቡ ወደዚያው ነው የሚልከው ይባላል። አሁንም ከድሮውም ጀምሮ በሙስና ኢንፎርሜሽን ጉዳይ ሁሉም ነገር ተቋሙ በእጁያለ ይመስለኛል። በኢንፎርሜሽን ከመታጠቅ ውጭ የሞራል ወዘተ ትጥቅ አለው ወይ? ምንም አላውቅም። የምገምተው ግንአለን። የሆኖ ሆኖ የዚህ ባለጉዳይ የመንግስት አካል ለህዝቡና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የሙስና ሁኔታ በአገሪቱ ውስጥመንስኤው እና ያስከተለውን ጠንቅ ለውይይት ቢያቀርብ ህዝቡ ዋናው ባለጉዳዩ የት ነበርክ? በምን ምክንያት ወዘተ የሚሉጥያቄዎች ማቅረቡ አይቀርም። ስለዚህም ‘ይመስለኛል’ ያልኩት ከመንግስት አቋም ጥርጣሬ ተነስቼ ሳይሆን አካሄዱ እንዴት ነውየሚሆነው? ከሚል መነሻ ነው። አሁንም ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ባለጉዳይ ሆኖ ነው ወይ የሚቀጥለው የሚሉ ጥያቄዎች ስላሉኝነው።ሰንደቅ፡- አሁን ያለው ስርዓት ለዓብይ ሙስና ለGrand Corruption የተጋለጠ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። እርስዎ ምንይላሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- የፌደራልየስነምግባርናፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአገር ውስጥ እንዲሁም ከውጭም በPerception ደረጃ ብዙኢንፎርሜሽን እንደሚቀርብለት እሰማለሁ። የሙስና ኢንፎርሜሽን ለአመታት የተከማቸው እዚያው ተቋም ውስጥ ስለሆነ ከላይእንዳልኩት ህዝቡ በሂደቱ እንዲሳተፍበት ከተፈለገ በትክክል በተገቢው የኢንፎርሜሽን /መረጃ/ አደረጃጀት ይቅረብና እነሱና(ተቋሙ) ህዝቡ ይመልሱታል። እኔ ስገምተው ግን ለGrand Corruption የተጋለጥንና በእሱ የተጨማለቅን ጥቂቶች ብቻአይመስለኝም።ሰንደቅ፡- የፀረ ሙስና ዘመቻው በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ያጠነጠነ ነው ይባላል። የእርስዎ አመለካከት ምን ይመስላል?አቶ ስብሀት ነጋ፡- እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ህጉም ዳኛውም ምስክሩም ይቆጣጠሩና ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲያሰቃዩናሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። እንደዚህ ሲያደርጉ እነ እንትና ከክሱ በስተጀርባ አሉበት ብለው ማስፈራርያ /ትክክልምሊሆን ይችላል/ የፖለቲካ ሰዎች ስም እየጠሩም፣ እየተገናኙም፣ ስልክ እየደወሉም፣ ይፈርዱ ያስፈርዱ ነበር ይባላል። ይህ ትክክልነው አይደለም ራሱ የቻለ ሰፊ ስራ ነው። ሰው ግን አረፍ ብሎ ሰርቶ መብላት መኖር አለበት። ስለዚህ የአሁኑ ፀረ ሙስናእንቅስቃሴ የፍትህ አካላትም የምርመራ አካላትም፤ የዐቃቤ ሕግ ጉዳዮችም እያጠሩ ህዝባዊ ፍትሃዊ እየሆኑ የሚሄዱበት ጉዞናበትልቁ ደግሞ በጠራራ ፀሃይ ማለት ህዝቡ የሚካፈልበት ስለሚሆን ያላጠፉ ግለሰቦችን የማይነካበት ይሆናል። ይሁን እንጂ ሌባናሌባ የሁሉም ብሄሮች ሌቦች በአንድነት እየተደራጁም በተናጠልም የዚህ ብሄር ተጠቃ የዚያኛው ብሄር ያለጥፋቱ ታሰረ ማለታቸውአይቀርም። ትርጉም ግን አይኖረውም።ሰንደቅ፡- የፌደራል ዋና ኦዲት ሪፖርት ለእርስዎ የሚሰጥዎት ትርጉም ምንድነው?አቶ ስብሀት ነጋ፡- በዚህ አገር በዚህ ስርዓት በአሁኑ ጊዜ ትልቁና የማያጠራጥር ተስፋ ሰጪ ሁኔታ የፌደራል ዋና ኦዲተር ጠንከርያለ እንቅስቃሴ መጀመሩና ከሁሉም በላይ ደግሞ የፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዝብ ተወካይነቱ ማረጋገጥ መጀመሩነው። ይህ ከፍተኛ የስልጣን አካል ስራ መጀመሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ የምስራች ነው። የሾማቸውን አስፈፃሚ አካላት ኦዲትሪፓርት መሰረት በማድረግ መቆጣጠር መጀመሩ ብቻ ሳይሆን፤ በቀጥታ በመጥራትም ያለወትሮው የስራ ሂደት ማወቅናማስተካከል ጀምሮዋል። አሁንም ያለወትሮው ወደስራ ቦታው እየሄደ ማጥናትና ማስተካከል ጀምሯል። አሁን የተወካዮች ምክርቤትን በተገቢው ደረጃ የማይፈራ ፈፃሚ አካል የለም። ኦዲት እየጠራ እንዲቀርብለት በሚቀርብለት ኦዲት ተመስርቶም እርምጃእንደሚወስድ ምንም ጥርጥር የለውም። ሌሎች ተጠሪነታቸው ለፓርላማ የሆኑም እንደሚንቀሳቀሱ ምንም ጥርጥር ያለውአይመስለኝም። ሌሎች በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶችም ማለትም የክልል የወረዳ፤ የቀበሌ፣ የከተሞች ም/ቤቶች የፌዴራል ም/ቤት ፈለግ መከተላቸው አይቀርም። ፓርላመንተሪ ሲስተም የእኛን ሲስተም ማለቴ ነው። ቦታውን እየያዘ ነው። ሌላው የዳኝነትስርዓቱ ፅዳት በፍጥነት መድረስ አለበት። የጠቅላላ ስርዓቱ አንድ አካል የሆነው ዳኝነት የሚባለው ያለበት ሁኔታ ዓለም ያወቀውስለሆነ ይስተካከል ከማለት በስተቀር ስለሁኔታው አሁን አለመናገር ይሻላል።ሰንደቅ፡- ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ የግብፅ ፓለቲከኞች የሚሰነዝሩትን ሃሳቦች እንዴት ይመለከቱታል?አቶ ስብሀት ነጋ፡- የግብፅ ፖለቲካ በወሳኝነቱ በአባይ ወንዝ የተመሰረተ ነበር፤ አሁንም ቢሆን። የግብፅ ፖለቲከኞችሃገራዊነታቸው ጀግንነታቸውና በስልጣን የመቆየታቸው ጉዳይ በአባይ የተመሰረተ ነው። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አለመረጋጋት አለ።ስለዚህ ማንኛውም የግብፅ ፖለቲከኛ የግብፅ ብሄርተኝነቱ ማረጋገጫ በአባይ ላይ የሚወሰደው አቋም ነው። ለዚህ ተጨማሪበኢትዮጵያ ህዝቦችና ባለፉት መንግስታት የነበረው ንቀት አለ። ስለዚህ እነዚህ ድክመቶች ተደማምረው እነሱ የፈጠሩትን የህዝቡስሜታዊነት ለመቀስቀስ አካኪ ዘራፍ ማለታቸው አያስገርምም። የሚያስገርመው ግን ስለግድቡ እንደማያውቁ መሆናቸው ነው።የሆኖ ሆኖ ታላቁ ቁምነገር ተሳስተናልና ሁሉም ነገር በጋራ እናየዋለን ማለታቸው ነው።ሰንደቅ፡- በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ጦርነት ይነሳል ብለው ያስባሉ?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ጠ/ሚ/ኃይለማርያም አይመስለኝም ብሎ መልሶታል። የእኛ መንግስት ኃላፊዎች የግድቡ አጀማመር፤አካሄድና ይዘት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ የአካኪ ዘራፍ አቋም አልነበራቸውም። ማብራሪያ ነበር የጠየቁት። በታላቅ ትዕግስት ነበርማብራሪያውን የጠበቁት። በርግጥ አንዳንድ ሰዎች ስለጉዳዩ ምንም አይነት ፍንጭና አጠቃላይ ግንዛቤም ሳይዙ ወደ ወታደራዊአቅም ግምገማ የሄዱት፤ የተመኙት ጦርነት የሚሆንላቸው እየመሰላቸው ነው። ጦርነት የማይነሳው በወታደራዊ አቅም ሚዛን ብቻአይደለም። የግድቡ ፍትሃዊነትና ፍትሃዊነቱም ድፍን ዓለም ያወቀው በመሆኑ ነው። በዋናነት ፍትሃዊነቱ የዓለም ኅብረተሰብ ብቻሳይሆን የማይናቅ የግብፅ ህዝብም አሁን ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ባህሪ የጋራ ጥቅምን ማዕከል አድርጐ እያሰበ የሚሰራ እንጂየህዝብ ተራ ስሜት እየቀሰቀሰ ጐራዴ ታጥቆ በየመንገዱ የሚፎክርና የሚያስፎክር እንዳልሆነ ማወቅ ጀምረዋል። ስለዚህምጥንቃቄ አስፈላጊ ቢሆንም፣ ለጦርነት ምክንያት የለውም።ሰንደቅ፡- ግብፅ፤ ኤርትራና ሶማሊያን እንዲሁም የሃገር ውስጥ ተቃዋሚዎችን ኢትዮጵያ ለማተራመስ መምረጣቸውን እንዴትንይመለከቱታል?አቶ ስብሀት ነጋ፡- ግብፅ እነዚህን ጐረቤት ሃገሮች ለትርምስ መምረጥዋ አላውቅም። የምትመርጥ አይመስለኝም። ግብፅየሚጠቅማት የኢትዮጵያ ልማትና መረጋጋት ነው። ይህንን በተሟላ ደረጃ ለመገንዘብ ብዙ ጊዜ የሚወስድባቸው አይመስለኝም።ግብፅ፣ ሶማልያ፣ ኤርትራና የአገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለትርምስ አትመርጥም። ብትመርጣቸውም እንደሃገር ለዚህ ጉዳይከግብፅ ጋር የሚሰለፉ አይመስለኝም። አይመስለኝም ያልኩት በሁለት ምክንያት ነው። መጀመርያ ሊያምኑበት አይችሉም።ሁለተኛ እነዚህ ጐረቤቶች አያዋጣቸውም። ዋናው ነገር ግን ግብፅ ይህንን ነገር አትመርጥም። ኢህአዴግ ቢጠሉም ከግብፅ ጋርየሚሰለፉ የሃገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አይኖሩም። አንዳንድ ብስጭታቸው ወደ ህመም ደረጃ የደረሰ ካልሆኑ በቀርየሚሰለፍላቸው የለም። ዋናው ነገር ግን ግብፆች ጥቅማቸውን የሚያዋጣቸውን ሳይገነዘቡ አይቀሩም። እየተገነዘቡም ነው።ሰንደቅ፡- የህዳሴው ግድብ ገዢው ፓርቲ ለራሱ የፖለቲካ ፍጆታ እያዋለው ነው የሚል ክስ ተቃዋሚዎች ያቀርባሉ። በዚህ ላይየእርስዎ አስተያየት ምንድነው?አቶ ስብሀት ነጋ፡- የህዳሴ ግድብ ይዘትና አካሄድ በጉዳዩ በአለማችን ግሩምና የተዋጣለት ከሚባሉ ታሪኮች አንዱ ነው። የጉዳዩውስብስብነት በመረዳት የናይል ተፋሰስ ባለድርሻዎች በማሰለፍ አንዱ ትልቅ የአፍሪካዊነት ኢትዮጵያውነት ህዝባዊነት የፈጠረውብልህነት ነው። የባለድርሻዎች ሰልፍ ነው። የአባይ ግድብ ለሶስታችን ለጋራ ተጠቃሚነት ለመገደብ ሲታሰብ ሊያጋጥሙ የሚችሉፖለቲካዊ፤ ዲፕሎማሲያዊና ቴክኒካዊ ፍተሻና ጥናት እንዲካሄድ ኢትዮጵያ መሪነቱን እየያዘች ቀዳዳ እንዳይገኝ የረጅም ዓመታትወደፊት እያየች በታላቅ ሃላፊነትና ትዕግስት ሞያ ነው ስራውን ስታራምድ የቆየችው። ይህን ያህል ታላቅ የዘመናችን ስራ አሁንምለወደፊትም ለጠላት በር እድል እንደማይሰጥ አድርገህ መሄድ እጅግ በጣም አስደናቂ ታሪክ ነው።በእኛና በታችኛው አባይ የነበረ የዘመናት ውጥረት ወደ ፍቅርና አብሮ የመስራት መንደር የሚከተን ስራ ነው። በአጠቃላይ ለኛለአባይ ተፋሰስ አገሮችና በተለይ ግድቡ ለሶስታችን ብቻ አይደለም፤ ጠቃሚነቱና አስተማሪነቱ። እንደኛ ያሉ ድንበር ዘለል ወንዞችያሉዋቸው አገሮች የእኛ የአባይ ተፋሰስ አገሮች አብሮ ለመስራት መጀመር ታላቅ ትምህርት ነው። ግድቡ ብቻ አይደለም ታላቅየሃገር ስራ። ዋናው የዓባይ ተፋሰስ ሃገሮች ትብብር መጀመሩ ነው። ይህ ጉዳይ በዓለም እየተነገረ ብቻ ሳይሆን የሚኖረው መልካምትምህርት ሆኖ እየተኮረጀ የሚኖር ስራ መስራታቸው ነባሪ ነውና መላው ህዝብ እንደ ሃገር ኩራት መውሰድ አለበት። ለቀጣይሃገራዊ ስራዎች የህሊና ሃይል በሚፈጥር መንገድ መነገር ብቻ ሳይሆን፣ ተፅፎ ለእንደኛ ያሉ ድንበር ዘለል ወንዞች ያሉዋቸውሃገሮች መዘርጋት አለበት።¾(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር407 ረቡዕ ሰኔ 19/2005)

ማነዉ ፈሪዉ ተቀዋሚ ወይስ ህወሃት/ ኢህአደግ?


ሰላም ፍቅሬ / ከጀርመንሰሞኑን በ20/06/2013 በአሜሪካ ኮንግረስ በኮንግረስማን የተከበሩ ሚስተር ስሚዝ ኢትዮጵያ ከመለሰ በኋላ፦የወደፊት ዲሞ ክራሲና የሰበአዊ መ ብት በሚ ል ርዕስበተደረገዉ የም ስክርነት ቃል ላይ የተከበሩ አም ባሳደርያማ ማ ቶ በተቃዋሚ ዎች ዙሪያ ሲናገሩ በራሳቸዉስለማይተማ መኑና ስለሚፈሩ ነዉ ብለዉ መናገራቸዉንአድምጠናል።በዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ይቻላል ፤ ይሁንና ለዛሬ በቅርብየሆኑትንና በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ላተኩር።እዉነት አምባሳደር ያማማቶ እንዳሉት ፍርሃት ያለዉ በተቀዋሚ ጎራ ነዉ ፤ በህወሃት አካባቢ ነዉ ፤ ወይስ አሜሪካየኢትዮጵያ ጉዳይ እያስፈራት መጣ ?ጉዳዩን ለፖለቲካ ጠበብቶች እተወዋለሁ ።እድሜ ለሰማያዊ ፓርቲ አምባሳደር ያማማቶ ከመናገራቸዉ በፊት ቀደማቸዉ እንጂ ሁሉንም ፈርታችሁ ነዉ ይሉነበር። አንድ ነገር አምባሳደር ያማማቶን ልጠይቃቸዉ ለመሆኑ ፍርሃት ዝም ብሎ ይመጣል? ከ1997 ዓ.ም ምርጫበኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ግንባር ግንባሩን እየተባለ ሲገደል ባያዩ እንኳን አልሰሙም ?ታዲያ አሁንስ ህወሃትጥቅሞቹ እንዳይነኩበት ለ39 ዓመታት ያከማቸዉን የጭካኔ ልምድ የሰማና ያየ ለምን አይፈራ ?ግን እኮ አምባሳደር ያማማቶ እዉነታቸዉን ነዉ፤ ከፍርሃት ዉጡና ታገሉ ማለታቸዉ እንደሆነስ? ካለ ትግል ድልየለምና ከፍርሃት ወጥቶ መ ታገል የድል መሰረት በመሆኑ ጥቆማቸዉ ዋናና ጠቃሚ ጉዳይ ነዉና በጥሩ ጎኑ ብናየዉስ?የኢትዮጵያ መንግስት ለ8ዓመታት በግዳጅና በማስፈራራት ይዞት የቆየዉን የሰላማዊ ሠልፍ ፍቃድ ክልከላ ሳይወድበግድ መፍቀዱን መንግስትና ሰማያዊ ፓርቲ ባሳዩት እንቅስቃሴ ለማወቅ ችያለሁ።ሠማያዊ ፓርቲ የተከበሩ አምባሳደር ያማማቶ በዚሁ የምስክርነት ቃል ላይ የተናገሩትን አስቀድሞ ያወቀ ይመስላል።ምክንያቱም ፓርቲዉ ምንም ፍርሃት ሳይገባዉ ህወሃት/ ኢህአደግን ብቻ እያስፈራራ ሰላማዊ ሰልፉን አድርጓል።ከሰልፉም ፍርሃቱ የቱጋ እንዳለ አሳይቷል።ህወሃት/ ኢህአደግ ግን ይፈራል?።አዎ ይፈራል። ህወሃት ለምን ይፈራል? የስንቶች የንጹሃን ደም በእጁ አለ፣ሰንቶችንአስለቅሷል፣ ስንቶችን አሳብዷል፣ ስንቶችን የአልጋ ቁራኛ አድርጓል፣ ስንቶችን ንጹሃን ከመቃብር በታች አድርጓል።ስንቶችን በዘር መሰረታቸዉ አሳድዷል ፣ ከቦታቸዉ አፈናቅሏል፣ንብረታቸዉን ነጥቋል፣አለጥፋታቸዉ አስሯል። ስንትበኢትዮያውያን ህዝብ ስም የመጣ ሃብትና ንብረት ተበዝብዟል፤በዚህም ሰንቶች ህወሃቶች ሃብት አጋብሰዋል።እነዚህብቻ አይደሉም ህወሃት የሰራቸዉ ሃጥያቶችና ወንጀሎች ብዙ ናቸዉ ።ሌላ ህወሃት የሚፈራበት ነገር አለ ወይ? አዎ። ምን?ይህ ዘመን አምባገነኖችን ያንቀተቀጠ ዘመ ን መሆኑናአምባገነኖችን እረፍት መንሳቱ አንድ ቀን ለእነሱም እንደማይቀር ስለገባቸዉ ፤ በአረቡ አለም የወደቁት አምባገነኖችየነበራቸዉ ትጥቅ ከህወሃት ትጥቅ በላይ መሆኑና ያላዳናቸዉ መሁኑን ህወሃት ጠንቅቆ ስለተረዳ፤ በሌሎችም አገሮችለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በብራዚል እና በቱርክ ህዝብ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ስለሚያስረዳቸዉና የህዝብን ብሶትመሳሪያ እንደማይገድበዉ ህወሃት ስለተማረ።ታዲያ ምን ያስፈረዋል? ለምን አያስፈራ? ህዝቡ ትግሉን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ካደረሰዉ ለህወሃት ትልቅ አደጋ ስለሆነነዉ ።ህወሃትን አሁን የሚያስፈራዉ የኢትዮጵያ መኖር አለ መኖር ሳይሆን ፤ የዘረፉት ንብረት ፣ በፓርቲያቸዉ ስር ያለዉግዙፍ የንግድ እንቅስቃሴና ሌሎች ሊያስጠብቋቸዉ የፈለጋቸዉን ፤ስዉር ዓላማዎቻቸዉን ሁሉ የሚጠራርግ ማዕበልእየመጣ መሆኑ ስለገባቸዉ ለምን አይፈሩም?አንዳንድ ተቀዋሚ ፓርቲዎች ሰማያዊ ፓርቲ አብረን ሰላማዊ ሰልፍ እንውጣ ባለ ጊዜ ምክንያት እየደረደሩ አስቸግረዉነበር ይባላል።ይሁንና አሁን ከሰልፉ በኋላ ፦ይህም አለ እንዴ ? ያሉ ይመስላል።አሁንም ትግሉን መደገፋቸዉናመጀመራቸዉ ይበል የሚያሰኝ ጅምር በመሆኑሊበረታታ ይገባል።መነሻዉ የትም ይሁን የት መጀመሩ በራሱ አበረታችነዉ ።ከፍርሃት ወጥተዋል ማለት ነዉ።አንድነት ፓርቲ የሚሊዬኖችን ድምጽ ለማስጠበቅ በሚል መነሳታቸዉን እየሰማን ሲሆን ይህም ማነዉ ፈሪዉየሚለዉን ለማወቅ ጊዜዉ እየደረሰ መ ሆኑንና ሰላማዊ ትግሉ ሊቀጥል እንደሆነ ይታያል። እንግዲህ ህዝቡ ወደጨዋታዉ ሜዳ በመጠጋት ድጋፉን እንደሚሰጥ የሚጠበቅ ሲሆን፤መሪ አጣን ለሚሉም ቀጥተኛ መልስ መገኘቱታዉቋል።ትግሉን ከግብ ለማድረስ ከፍርሃት ዉጭ ሆኖ ስራን መፈጸም ይጠይቃልና ከሰማያዊ ፓርቲ ትምህርት መዉሰድየበታችነት ሳይሆን ብልህነት ነዉ።ትምህርት ትልቅ ጉልበት ይፈጥራል፤ተጨማሪም የሞራል ዝግጅት ማድረግያስችላልና፤በዚህ ዙሪያ ቆራጥነትንና ሌሎች የልምድ ግብአቶችን መጋራት ጠቃሚ ነዉ እላለሁ።ለራሳችን መ ፍትሔ የምናመጣዉ በእርግጥ እራሳችን ነን፤ አንድ ትልቅ ነገር ለተቀዋሚ ዎች እመክራለሁ ። እርሱምከየዋህነት እንድንወጣ ። በየዋህነት ህወሃትን ማሸነፍ አይቻልም ። የህወሃትን የክፋት መጠን የሚመጥን እናየሚቋቋም የትግል ስልትና አቋም ይዞ መነሳት ህወሃትንም ላይቀርለት ወደ ፍጻሜ ያቀርበዋል።የኢትዮጵያ ህዝብም ፤ በአገር ዉስጥም ሆነ ከሃገር ዉጭ ያሉ ሁሉ ተገቢዉን ድጋፍ ለትክክለኛና ለእዉነተኛተቃዋሚዎች በመ ስጠት ህወሃትን ከጫንቃችን ላይ እናዉርድ ፤በዚህም የእፎይታ ዘመናችንን እናፋጥን ። ካልሆነ ግንመንግስትም የራሱን ጥላ ባየ ቁጥር ሰዉ ከሚገልና ቃሊቲ ከሚወረዉር፤ተቃዋሚም ፈርቶ በመንግስት ከሚያላክክ ፤ህዝብም ፈርቶ የሚመራን አጣን እያለ ከሚያዝን፤ ትግሉ ይጀምር፣ይቀጥል፥ ለጥያቄዉ መ ልስ ይገኝ። ሁሉምከፍርሃት ይዉጣ ።ኢትዮጵያ የነጻነት ፣የዲሞክራሲና የብልጽግና አገር ትሁን።ለራሳችንና ለትዉልዳችን ጥቅም ሲባል ቢያንስ ተቃዋሚዉከፍርሃት ይውጣ ። በመጨረሻም ፈሪዉ ማን እንደሆነ ይታወቅ።አም ላክ ኢትዮጵያን ይባርክ !

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን” “ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”


tesfaye


“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር አሰሩኝ ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር ዝዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መታሰርህን ለቤተሰብ ተናግረሀል?
ወጣት ተስፋዬ:- ለማንም ሰው እንድናገር አልፈቀዱልኝም፤ መስሪያ ቤቴ አልጠየቀኝም፣ ደሃዋ እናቴ ያለችው ናዝሬት ነው እሷም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አባቴ አቶ ተካልኝ አስተማሪ ነበር አርባ ጉጉ ላይ ነው በ1985 ዓ.ም በነበረው ግጭት ነው የተገደለው፡፡ ማንም ሳይጠይቀኝ፣ፍ/ቤት ሳልቀርብ 23 ወር ታሰርኩ ልብስ ምግብም የሚያመጣልኝ ሰው አልነበረም፡፡ እናቴም መታሰሬን እንኳ አታውቅም መስሪያ ቤቴም ስኮላርሽፕ አግኝቷል፤ ወደ ውጪ ሃገር ሊማር ሊሄድ ነው የሚባል ነገር ስለነበረ አልጠየቁኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የት ነበር ስኮላርሺፕ ያገኘኸው?
ወጣት ተስፋዬ:- የዛሬ 2 ዓመት አካባቢ የራስመስ ሙንደስን ስኮላርሽፕ አግኝቼ ነበር፡፡ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያና ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶክዮ ባሉ ምሁራን ሪኮመንድ ተደርጌ በጣሊያኑ ፌራሪ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ እንደተፈታሁ ሄጄ ስጠይቃቸው ብዙዎቹ ጓደኞቼ በጣም ደነገጡ፡፡ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ቅማል ተወርሬ … ባካችሁ ተውኝ … ምንም የሌለ ነገር የለም በጣም ተጎድቻለሁ፡፡ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ እናቴ ጋ ስሄድ በጣም ደነገጠች፣ በሕይወት ያለሁ አልመሰላትም 23 ወር ሙሉ ከቤተሰብ ስለተለየሁ ግራተጋባች፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- በእስር ወቅት የደረሰብህ ድብደባና ማሰቃየት ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ በኤሌክትሪክ ጀርባዬ ላይ አቃጥለውኛል፣ በብልቴ ላይና በኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱብኝ ሽንት ችዬ አልሸናም፣ ሽንቴን መቆጣጠርም አልችልም፡፡ ኩላሊቴንም በጣም ያመኛል፡፡ ውሃ ውስጥ እየነከሩ በጣም ደብድበውኛል፡፡ አሁን ስናገር ያመኛል ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደው ስታስበው ለእስር ያበቃህ ወይም ከመንግስት ጋር ያጋጨህ አጋጣሚ ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- መስሪያ ቤቴ ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፤ በጣም ይከታተሉኛል፡፡ በቢ.ፒ.አር ላይ ስብሰባ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ እኔም ሠራተኛ ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ነገሮች ሲመጡ እኔ አልቀበልም በግልፅ እናገር ነበር፤ ሠራተኛውም እኔን ይደግፋል፡፡ ከመታሰሬ ጥቂት ጊዜ በፊት ገነት ሆቴል ስብሰባ ነበረን፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ በጣም ተከራከርኩ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አቶ ፀጋዬ ማሞ የሚባሉ አሰልጣኝ፣ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከንግድና ኢንዱስትሪም የመጡ ነበሩ ስማቸውን የማላስታውሳቸው ባለስልጣን ነበሩ፤ እዛ ላይ ሀሳብ አንስቼ ተከራክሬ ነበር፡፡ “የሠራተኛን ሀሳብ ዳይቨርት ያደርጋል” ይሉኝ ነበር፡፡ መቼም ግን ሀሳቤን በመናገሬ ይህን የመሰለ ስቃይ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ “አሸባሪ፣ ግንቦት ሰባት” እያሉ እኔ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ያለምንም ፍርድ በርሜል ውስጥ ውሃ ጨምረው እያስተኙ አሰቃዩኝ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደዚህ ያሰቃዩህ ምን አይነት ምንም አይነት መረጃ ሳያገኙ ነው?
ወጣት ተስፋዬ:- እኔን ጥፋተኛ የሚያስደርግ ምንም መረጃ አላገኙም፣ እኔን አስረው ወደ መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ይደውሉ እንደነበር ይነግሩኝ ነበር፡፡ የኢሜይል አድሬሴንም ተቀብለው በርብረዋል ግን ምንም አላገኙም፡፡ እኔ ከማንም ጋር ሊንክ የለኝም ኢሜሌ ላይ የስኮላርሺፕ መልዕክት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለውም፡፡ በመስሪያ ቤቴ ሪሰርቸር ነበርኩ፣ በሶሲዮሎጂ ነው የተመረኩት፡፡ ሉሲ የተገኘችበት ሣይት ላይ አፋር፣ ጋምቤላ ብዙ ሳይቶች ሰርቻለሁ፡፡ ከአለቆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሰላማዊ ነው እነሱ ናቸው ስኮላርሽፕ ሪኮመንድ ያደረጉኝ፡፡ አንደኛው ፕሮፌሰር 25 ዓመት ሙሉ እዚህ አገር ሰርቷል፣ አርዲን ያገኘው እሱ ነው፡፡ ሄነሪ ጊልበርት ይባላል፤ እሱም ሪኮመንድ አድርጎኛል፡፡ እኔ በጣም የሚቆጨኝ ደሃዋ እናቴ አረቄና ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ ምን ብዬ ልንገራት እንደዚህ አትጠብቀኝም ከበደኝ፣ አሁን እሷ የምትሰጠኝ ምግብ ራሱ ደምደም አለኝ… (ረጅም ለቅሶ)፡፡ ልጄ በደህናው አይደለም የጠፋው ሞቷል ወይም መኪና ገጭቶታል ብላ ነበር የምታስበው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የከመታሰርህ በፊት ፖለቲካ ተሳትፎ ነበረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- 1997 ዓ.ም የቅንጅት ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ በ97 የነበረው ሁኔታ ስንት ሰው አለቀ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር ታውቃላችሁ ምንም የምናደርገው ነገር አልነበረም ፡፡ በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል ተረዳሁኝ፡፡ ከ1997 ዓ.ም በኋላ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልሆንኩም፡፡ ከዚህ በኋላ ከምንም ነገር የተገለልኩ ሆኛለሁ፡፡ አንድ ብርጭቆ ሳትሰብር አሸባሪ ስትባል አስብ እንግዲህ አንድ ብርጭቆ እንኳን ሰብሬ አላውቅም ባለኝ እውቀት እንደውም ለእውቀት ነው የምጓጓው እውቀቴን አሳድጌ አገሬን ለመለወጥ ነው የማስበው እኔን ምንም የሚመለከተኝ ነገር የለም አሸባሪም ግንቦት ሰባትም አይደለሁም፡፡ስትደበደብ፣ ስትሰቃይ ያላደረከውን አድርጌያለሁ ትላለህ፤ በርሜል ውሃ ሞልተው ይከቱሃል ያሰቃዩሃል፡፡ አያሳዝንም ይሄ? እንዴት አድርጎ እዚህ አገር ይኖራል? 23 ወር ሙሉ አስረው ማሰቃየታቸው ሳያንስ የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም ብዬ ነው የነገርኳችሁ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን የት ነው የምትኖረው?
ወጣት ተስፋዬ:- መኖሪያ የለኝም … (ረጅም ለቅሶ)
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝን ለመርዳት የምትፈልጉ አንባብያን ከፍኖተ ነፃነት መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ (ምንጭ ፍኖተ ነጻነት)

Total Pageviews

Translate