Pages

Jul 9, 2013

በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ? ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት?

workneh and bereket
ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የአዲስ የሚኒስትሮችና የ”ከፍተኛ” ባለሥልጣናት ሹመት ተከትሎ ከውስጥም ከውጭም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ሪፖርተር “ምንጮቼ ነገሩኝ” በማለት አቶ በረከት ስምዖንን የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር የሚያደርጋቸው አዲስ ሹመት እንደሚሰጣቸው ዘግቦ ነበር። ይህንኑ ዜና ተከትሎ “ኢትዮጵያ በኦፊሴል በኤርትራ መመራት ጀመረች” በማለት ቅድመ አስተያየት የሰነዘሩ ጥቂት አልነበሩም።
ሚዲያውን መዳፋቸው ስር አኑረው የቆዩት አቶ በረከት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነታቸው ተነስተው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም የፖሊሲና ጥናት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው “በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ከመለስ ህልፈት በኋላ ኢህአዴግ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያሳዩት አቶ በረከት ከድርጅታቸው ይሁንታ ውጪ “አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስትር ይሆናሉ። የሚቀረው የስርዓት ማሟላት ጉዳይ ነው” ማለታቸው  የህወሃትና የኦህዴድ ሰዎችን ክፉኛ አበሳጭቶ እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች “አቶ በረከት አማካሪ ሆነው ወደ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ መዛወራቸው ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር የመገፋት ወይም ስራ አልባ የማድረግና ከቀጥተኛ ተሳታፊነት የመታቀብ ያህል ነው” ባይ ናቸው።
“በዜግነታቸው ብቻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የመሳተፍ መብት የሌላቸው አቶ በረከት ሲፈነጩበት ከነበረው የኢህአዴግ ሚዲያ bereketመሰናበታቸው በራሱ በርካታ ጉዳዮችን የሚያመላክት ነው” የሚሉት ምንጮች “የፖሊሲና የጥናት ጉዳዮች ከፍተኛ የቀለም እውቀትና ልምድ የሚጠይቅ ሃላፊነት ነው። አቶ በረከትም ሆነ አቶ ኩማ ለዚህ አይመጥኑም። ውሳኔው ማቀዝቀዣ ውስጥ የማስገባት ያህል ነው” ሲሉ አቶ በረከት ያላቸው የአደባባይ ሚና ማክተሙን ያወሳሉ።
በሌላ በኩል የተለየ አስተያየት የሚሰነዝሩ ክፍሎች እንደሚሉት “አቶ በረከት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ እለት እለት ሥርስራቸው ሆነው እንዲሰሩ የተሰጣቸው ስልጣን ነው። ይህ የሚያሳየው እሳቸው አሁንም ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቀጠላቸውን ነው” በማለት የሃሳብ ልዩነታቸውን ያስቀምጣሉ።
አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የቀረበ ግንኙነት እንደነበራቸው፣ አቶ መለስ በህይወት እያሉም ቢሆን ሶስቱ እንደማይለያዩ ያመለከቱት ክፍሎች፣ የህወሃት የበላይ አመራርና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር መሪ የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስትር ውስጥ የሚሰይሙት ሚኒስትር፤ ሪፖርትር እንዳለው አቶ በረከት ካልሆኑና የህወሃት ሰው ከተሾመ “በትክክልም አቶ በረከት ወደ ማቀዝቀዣ ክፍል ገብተዋል ማለት ነው” ሲሉ ሁለት ጫፍ ያለው አስተያየት ሰንዝረዋል።
አቶ ኩማ አሁን ባለው ኦህዴድ ውስጥ አንጋፋና ታማኝ፣ በቅጣት ከሶስት ዓመት ማዕቀብ በኋላ ወደ መንግስት ሃላፊነት የተመለሱ፣ kumaኦህዴድን ማጥራት ሲፈለግ በትር የሚጨብጡ፣ በመሆናቸው ከንቲባነቱን ሲለቁ እንዳያፈገፍጉ አዲሱ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው አብዛኞች ይስማማሉ። አቶ ኩማ ካላቸው ልምድና ዕውቀት አንጻር አቶ ሃይለማርያምን በፖሊሲ ጉዳዮችና በጥናት ረገድ ለማማከር የሚችሉ ሰው እንዳልሆኑ ስምምነት መኖሩን የሚጠቁሙ ጥቂት አይደሉም። ከዚህ አንጻር በዓለምቀፋዊ ዋና ከተማነት ከምትታወቀው አዲስአበባ ከንቲባነት ወደ አማካሪነት ኩማ ደመቅሳ “ሲሾሙ” እንደ ሥልጣን ሽረት ከተቆጠረ፤ የበረከት ስምዖን በተመሳሳይ መልኩ መታየት የማይችልበት ምክንያት ሊኖር እንደማይችል የሚከራከሩ አሉ፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሥልጣን በምክትል ጠ/ሚ/ርነት ሲያድግና ኢህአዴግ በምርጫ የመሸነፍ ቅንጣት ችግር ሳይኖረው ኩማን ከከንቲባነት ሥልጣን ማንሳቱ የብቃት ማነስና አለመፈለግ እንደሆነ ተጨማሪ አስተያየቶች አሉ፡፡
ለሶስትና አራት ዓመት ህጻን “ከክልላችን ስለተባረርክ የትምህርት ገበታህ ላይ መቀመጥ አትችልም” የሚል ደብዳቤ የሚጽፉና በሙስና በከፍተኛ ደረጃ የሚታሙት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ትምህርት ሚኒስትርነት የተሻገሩት አቶ ሃይለማርያም ደቡብ ክልል ላይ ያለውን ሰንሰለት ለመበጣጠስ እንዲያመቻቸው እንደሆነ ይገመታል። ሃዋሳ ነዋሪ የሆኑ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ሽፈራው የዘረጉት ድር መበጣጠስ እንዳለበት የታመነው አሁን አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠር የክልል በጀት እንደፈለጉ ከሚያስኬዱበትና ያለገደብ ሥልጣናቸውን ከሚያከናውኑበት የክልል ፕሬዚዳንትነት ወደ ሚኒስትርነት “መሾም”፤ የሥልጣን ሽረት ተብሎ ከመጠራት ውጪ ምንም ሊባል እንደማይችል በሽፈራው ሽጉጤ አመራር የተማረሩ ብቻ ሳይሆኑ ደጋፊዎቻቸውም ያመኑበት ጉዳይ ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስቴርን መምራት ያቃታቸው አቶ ደመቀ በስራ ብዛት ሰበብ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸውን ወንበር ብቻ እንዲይዙshiferaw መደረጉን ያመለከቱት ክፍሎች “አቶ ሽፈራው በሹመቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ ከሚቀርቧቸው ሰምተናል። ሃዋሳ በክልሉ መስተዳድር ውስጥ እሳቸው የሰገሰጓቸውም ስጋት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሃይለማርያም “ታማኛቸውን” በመሾም (“በማስመረጥ”) እውነተኛ የደኢህዴን ሊቀመንበርነታቸውን እንደሚያረጋግጡም ይጠበቃል፡፡
ደመቀ መኮንን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸው ብቻ እንዲቀጥሉ የተደረጉት ምን አልባትም አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስቴር ውስጥ በአማራ ክልል ከነበራቸው “ልምድ” አኳያ ለኮታ ማሟያ ታስበው ነው በሚል ካድሬው በስፋት እንደሚያወራ እየተሰማ ነው። አቶ ደመቀ በአማራ ክልል የደህንነቱ መሪ እንደነበሩና በዚሁ በተግባራቸው “የተመሰገኑ ታማኝ” ለመሆን መብቃታቸውን የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።
ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ልጆቻቸውን በትምህርት ቤት እየሰደቧቸው በመቸገራቸው እንደነበር የሚያስታውሱት እኒህ ክፍሎች “አቶ ደመቀ የአማራው ክልል መሬት ተላልፎ ሲሰጥ አቶ አያሌው ጎበዜ አልፈርምም ሲሉ፣ እሳቸው መፈረማቸው ይፋ ከሆነ በኋላ DemekeM‘ከሃዲ’ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ህጻናት ልጆቻቸውም ትምህርት ቤት መማር ያልቻሉት ለአባታቸው በተሰጠ ስም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቻቸው ስለሚያበሽቋቸው ነው” በማለት አቶ ደመቀ ቀደም ሲል ጀምሮ ከደህንነቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት ታማኝ እንዳሰኛቸው አስታውቀዋል። ከዚሁ ውለታቸውና ልምዳቸው አንጻር በደህንነት መ/ቤት ውስጥ ይካተታሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሰኔ 27 ቀን ለተሰየመው ፓርላማ በቀረበው ሹመት መነጋገሪያ ከሆኑት መካካል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ችግር እንደተጣባው የተመሰከረለትን የትምህርት ሚኒስቴርን እንዲመሩ መመደባቸው፣ አንዲሁም የአቶ ደመቀ በ”ስልጣን በዛባቸው” ሰበብ የሚኒስትርነት ቦታቸውን መነጠቃቸው በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው።

የወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ሹመት

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው ከሚቀርቡት ምክንያቶች መካከል ቀደም ሲል ለረዥም ዓመታት ከደህንነቱና ከሽብር መከላለከል ግብረ ሃይል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ከፍተኛ መሆኑ በግንባር ቀደም ይገለጻል። ለጎልጉልአስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ኢህአዴግ የትራንስፖርቱን ዘርፍ በቅርብ መቆጣጠር ይፈልጋል።
በምርጫ 97 ወቅት ለታየው ህዝባዊ መነቃቃት የትራንስፖርቱ ዘርፍ፣ በተለይም የታክሲና የግል ማመላለሻዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ያስታውሳሉ። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እስከወዲያኛው እንዳይታሰቡ ለማድረግ ዘርፉን ከደህንነቱ ጋር በቅርብ ማጠላለፍ፣ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ እየገነባሁ ነው የሚላቸውን መንገዶች፣ የስልክና የብሮድ ባንድ መስመሮች፣ የባቡር ትራንስፖርት በቅርብ ለመቆጣጠርና የቁጥጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ለማስገባት አቶ ወርቅነህ ሁነኛ ሰው ሆነው መገኘታቸውን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።
አዲሱ ቴሌን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን ከደህንነቱ መዋቅር ጋር በቀላሉ ለማያያዝ ልምዳቸውና የመረቡ አባል ሆነው Workineh-Gebeyehu-መቆየታቸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ያደረጋቸው አቶ ወርቅነህ፣ የጄኔራልነት ማዕረጋቸው ከሳቸው ጋር ይቆይ ወይም ይነሳ የተገለጸ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች አቶ ወርቅነህን በታማኝነት መድበው የተቀበሏቸው ሰው ስለመሆናቸው ጥርጥር የላቸውም።
አቶ ወርቅነህ ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በዚሁ ታማኝነታቸው ስልጣናቸውን ሳይጠቀሙ በፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርነት ለረዥም ጊዜ መቆታቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አቶ ወርቅነህ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሰባት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ተውጣጥቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የ”ደህንነት ኮር” ውስጥ አባል እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህንን ኮር በአዲስ እየተዋቀረ ስለሆነ አቶ ወርቅነህ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት የተዛወሩት ከደህንነቱ የኮር መዋቅር ውስጥ እንዲወጡ ስለተፈለገ መሆኑን ይገልጻሉ።
ዝርዝር ጉዳዩን ለማብራራት እንደሚቸገሩ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ እንዲዋቀር አዋጅ የታወጀለት የደህንነት መ/ቤት ሚኒስትርና የበላይ ሃላፊዎች ይፋ ሲሆኑ ነገሮች ይበልጥ እንደሚጠሩ ተናግረዋል። በኢህአዴግ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረውና አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዳልጠራ የሚነገርለትን ልዩነት ተከትሎ የተሸናፊውን ወገኖች የማጥራት ስራ በተለያዩ ስልቶች እንደሚሰሩ የጠቆሙት እነዚህ ክፍሎች፣ የደህንነት ሚኒስትር ሲቋቋም የሚሾሙት ባለስልጣን ከቀድሞዎቹ መካከል እንደማይሆን ምልክት ማየታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን የአዲስ ሹመትና ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሃሙስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በአንድ ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።በዚህም መሰረት
አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ – የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው አስፋው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ – በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ – የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ በከር ሻሌ ዱሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ – የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር
አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
ሆነው የተሾሙ ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።

Ethiopia Intelligence, Security Services Powers Extended


The Ethiopian government has announced plans to transform the National Intelligence and Security Service (NISS) into an autonomous federal government office.
This is expected to strengthen its ability to act on national security issues and ensure it can respond to issues today and in the future.
The National Intelligence and Security Service (NISS) was established in 1994/95 as the Security, Immigration and Nationality Affairs Authority. Its name was changed to the NISS in 2006/07.
On Tuesday, the plan to re-establish the NISS was presented to the House of People’s Representatives.
Three reasons were given: To strengthen the NISS to allow it to protect and defend the sovereignty of the country, the constitution and constitutional order; to determine the power, duties and accountability of the NISS to promote peace, development, democracy and good governance; and build a modern and strong NISS, loyal and resilient to the constitution and constitutional order of Ethiopia and conscious of national and international interests 
The aim of the NISS is to protect national security by providing quality intelligence and reliable security services. Under the plans presented, it is accountable to the Prime Minister.
The proclamation preventing the establishment of other intelligence and security institutions has given other powers to the NISS.
The agency has a wide permit to lead intelligence and security work both inside and outside Ethiopia, formulate national security and intelligence policies and establish and run intelligence and security training institutions.
Under the new plans, the NISS will also work with foreign intelligence and security organisations to share intelligence and conduct joint operations.
It will also investigate domestic or foreign threats to the constitution and constitutional order, threats to economic growth or governance within Ethiopia and collect intelligence.
It will also lead on national counter-terrorism co-operation and co-ordination and represent the country in international and continental counter-terrorism relations and co-operation.
The service will follow up and investigate terrorism and extremism and collect information. 
Its security role includes providing and controlling immigration and nationality services to Ethiopian and foreigners, studying and submitting to the government service charge rates and implement same upon approval; providing the necessary service for refugees based on the Refugee Proclamation and in co-operation with other appropriate organs; leading aviation security activities, providing aviation security services and coordinating other aviation security stake holders in accordance with the Ethiopian Aviation Security Proclamation; providing security protection to the president and prime minister of the country as well as to heads of states and governments of foreign countries in collaboration with other relevant organs. 
Girma Seifu, the only opposition MP, said that NISS employees should be separate from the civil service, in the interests of professionalism.
He said they should also have different ID cards to distinguish them from support staff. “Other support staff might use the ID to harass people as they might not have the ethics,” he said.
He cautioned that the new NISS should provide security to society and should not intimidate people

Jul 8, 2013

እዩልኝ ሲያቅመኝ፤ “አቤ ወደ ሙርሲ የላካቸው ጀቶች ግጭት” ጎንደር ዘ ኢትዮጵያ (Abe Tokichaw)

996816_481813375244363_822890382_n
እዩልኝ ሲያቅመኝ፤  ”አቤ ወደ ሙርሲ የላካቸው ጀቶች ግጭት”
አንድ አማርኛ መመህር ነበሩን ጺማቸው የጎፈረ ጸጉራቸው የተንጨበረረ ነበር፤ በአንዱ ቀን ታድያ ፊት ለፊታችሁ በምታዩት ነገር ግጥም ጻፉ አሉና አዘዙን፡፡ ሁላችንም አንገታችንን ደፍተን ስንንደፋደፍ አንዱ ሳተና ጨርሻለሁ… ሲል እጁ
ን አወጣ… በል እስቲ አጋራን… አሉና መድረኩን ሰጡት፡፡ እርሱም ጀመረ፤
ያጎፈረው ጢምዎ…
ዝንጀሮ አስመስልዎ…
አቤት የፀጉርዎ…. ብሎ ገና ከመጀመሩ ተማሪው ሳቁን መቆጣጠር አቅቶት ከት…ት ብሎ መሳቅ ጀመረ፡፡ ይሄን ጊዜ መምህሩ ተቆጡ…
ተዉ እንጂ ተማሪዎች… ገና እኮ ነው በደንብ ያቅመኝ እንጂ… አሉን፡፡ ሌላ ሳቅ…
አንድ ወዳጄ ባለፈው ግብጽን አስመልክቶ ያወጋሁትን በእንዲህ መልኩ ይዋጋዋል… ደህና አድርጎ አቅሞኛል፡፡ ለነገሩ እኔም የምለቀው አይመስለኝም…  ስለ ባዕድ ሀገር የማውራት ሞራሌ እስኪሰባሰብ ግን እስቲ እርሱ ያቃመኝን ላልደረሰው ላዳርሰው ብዬ በድረ ገፃችን ላይ ለጥፌዋለሁ፡፡
አንዳንዴ ሁለት ተዋጊ ጀቶች ከአንድ የጦር ሰፈራቸው ቦምብና ሮኬት ወይም ሚሳይል አንግበው ይነሱና በጠላት ወረዳ ደርሰው ከማጥቃታቸው በፊት በሚፈጠር ስህተት እርስ በርሳቸው ተላትመው ቦምቡም፣ ሚሳይሉም፣ ሮኬቱም ለጠላት መሆኑ ቀርቶ ለራሳቸውና ለአብራሪዎቻቸው ይተርፋል። አቤ “ደግሞ በግብፅ እንጣላ እንዴ” በሚል አርእስት የላካቸው ጀቶች (ፌስቡክ ላይ ያሰፈራቸው መልእክቶች) ይህ ዕጣ ገጥሟቸዋል እያልኩ ይህን ከበላይ አካል ፈቃድና እውቅና ያገኘ ፅሑፍ ልጋብዝ።
ግጭቱ እንዲህ ነው፤ አቤ በአንድ በኩል ‘ሙርሲ ዋጋውን አገኘ’ ይልና በሌላ በኩል ‘የተመረጠን የገለበጡትን መቃዎም ተገቢ ነው’ ይለናል። እዚህ ላይ አቤን እንደ ፌስቡከኛ ብቻ በማየት ባለማለፍ በጉዳዩ ላይ መነጋገር አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ። ለምን አቤ ኢሳት ላይም የሰራልና ነገሮችና የነገሮች ሂደት የሚገዙበት ደንብ መጣረስ የለበትምና። መጣረስ ደግሞ አንዱ የኢሳት ችግር ነው፤ ለምሳሌ ኢሳት በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ውስጥ መከራና ችግር በዛ፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተጣሱ፣ አምባገነንነቱ ገደብ አጣ፣ የኢትዮጵያ ጉዞ ወደ ጥፋትና ወደ በመበታተን እየሆነ ነው ወዘተ የሚሉ መልዕክቶችን ያስተጋባል። በሌላ በኩል ደግሞ “ምንም የለም በሉ ከደስታ በቀር … ምንም ችግር የለም… አዲስ ነው ዘመኑ … ኧረ አዲስ ነው! ክፉው ዘመን አልፏል…” የሚለውን ዘፈን ደጋግሞ ይጋብዘን ነበር። የአሁኑን እንጃ በናይል ሳት ላይ በነበረበትና እንደ ልብ እንከታተለው በነበረበት ጊዜ ግን ይህ ነገር በተደጋጋሚ ነበር የሚሰማው። ለመሆኑ ዘፈን የምንጋበዘው ስለ መልዕክቱ ነው ወይስ ስለዘፋኙ ወይስ ስለዘፋኙ ቲፎዞዎች ሲባል? አንድ ጊዜ ‘ኢሳቶች ገና ከመጀመራችን ለትችት ተሽቀዳደሙ’ ሲል ሰምቻቸው ነው እንጅ ይህን መሰል ነገር ቀደም ብሎ ማድረግ ጥሩ ነበር። ‘እናቴ ሆይ በእንቁላሉ … ’ አለ ነው የተባለው በሬ ሰርቆ ለስቅላት የቀረበው ሰውዬ?!
በኢሳት የተላለፉ ተመሳሳይ መጣረሶችንና በደንብ ያልታሰበባቸው የሚመስሉ ዝግጅቶችን ከተለያዩ ፕሮግራሞቹ በመሞነታተፍ ማቅረብ ይቻላል። አንድ ቀን ይህን ማድረግ ተገቢ ነው።
ወደ አቤ እንመለስና በመጀመሪያ ሁለቱን ጀቶቹን እንያቸው።
ጀት ቁጥር አንድ
“እንደኔ እምነት የግብፅ ወታደር ኩዴታ ፈፅሟል የሚያስብል ነገር አላየሁም፡፡ በርካታ ህዝብ አደባባይ ወጣ ተቃውሞውንም አሰማ … ሙርሲ ይሂዱልን ከዚ… አሉት ..። ስለዚህ በእኔ በምስኪኑ እምነት የእነዚህ ብዙሃን አቤቱታ መሰማት አለበት፡፡ ለዚህም ወታደሩ ያደረገው መፈንቅለ መንግስት ሳይሆን አፍቅሮተ ህዝብ ነው ባይ ነኝ፡፡ ለብዙሃኑ ጆሮ ሰጥቷልና!” ጥቅስ አቤ ቶኪቻው።
ጀት ቁጥር ሁለት
“ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ተቃዋሚዎች (የሙርሲ ደጋፊዎች) እየጠየቁ ያለው ጥያቄ ትክክል ነው፡፡ ድምጻችን የት ነው…! የመረጥነውን ሰውዬ የት አደረሳችሁት…! እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ እጅግ በጣም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡… እኔ ይቺን እየተየብኩ ባለበት ሰዓት የወታደሩን ጣልቃ ገብነት በመቃወም በተቀሰቀሰው አዲሱ ተቃውሞ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሊደርስ እየተንደረደረ ነበር፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ተቃዋሚዎች እየጠየቁ ያለው ጥያቄ ትክክል ነው፡፡ ድምጻችን የት ነው…! የመረጥነውን ሰውዬ የት አደረሳችሁት…! እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ እጅግ በጣም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡” አሁንም ጥቅስ ከአቤ ቶኪቻው ነው።
የሁለቱ ጀቶች ፍፃሜ
የአሜ ጥቅስ ሲቀጥል የሚከተለውም ይገኝበታል “መጨረሻ ላይ እንደኔ አስቴየት ያኛውም ትክክል ይሄኛውም ትክክል ሆነ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ዲሞክራሲ አጣብቂኝ ውስጥ የምትገባው ይሄኔ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የሚል ሌላ አስተያየት ልጨምራ!”
አቤ ይቀጥላል፤ “አሁን ከሙርሲ እና ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ማረፊያ ቤት መውረድ በኋላ ተቃዋሚዎቹ (የሙርሲ ተቃዋሚዎች) የልባቸው ደርሶ ወደ ጎጇቸው ሲመለሱ የሙርሲ ደጋፊዎች ደግሞ ይቺን ይወዳል የሙርሲ ልጅ ብለው እየቀወጡት ይገኛሉ፡፡ ይህ ሊመጣ እንደሚችል ተንታኞቹ ድሮውንም ገምተዋል፡፡ ማለቂያው ምን ሊሆን እንደሚችል ግን የሚያውቀው የላይኛው ብቻ ነው፡፡”
የአቤን ጀቶች ይዘት እንመርምራቸው!!
አቤ ጀት ቁጥር አንድን “ብዙሃን” እና “ህዝብ” የሚል ታርጋ በመለጠፍ ጥሩና ትልቅ ጀት አድርጎ ሲያሳየን፤ ቁጥር ሁለት ጀትን ግን “ተቃዋሚዎች” እና “ሰዎች’ የሚል ታርጋ በመስጠት አሳንሰን እንድናያት በዘዴ እየሰራ ነው።
አቤ የሙርሲን ተቃዋሚዎች በወታደራዊ ሃይል መደገፋቸውን እሰየው የሚያስብል፣ በሰዎች ሊደረግ የሚገባው እርምጃ አድርጎ ወሰደውና የመርሲ ደጋፊዎች ወዮታን ግን ከፈለገ የላይኛው ይርዳቸው በሚል ለበጣ አልፎታል።
አቤ እንዳሻኝ እፅፋለሁ ለማለት ‘መቼም ለሙርሲ ሞራል ተጠንቀቅ [አትሉኝም]…’ ሲል ፅፏል። በቀልድ መልክ አስተምራለሁ ብሎ መጣጥፍ የሚያቀርብ ሰው ግን በዚህ ዓይነት አስተሳሰብ መመራት የለበትም እላለሁ። ይህ ፅሑፍ የአበበን አመለካከት ብቻ ሳይሆን አቤ ነገሮችን የሚፈርድበትን ሚዛንም ነው የሚያሳየን። አቤ ስለ ምንም ነገር ሲፅፍ የሱን ፅሑፍ ለሚከታተሉ ሰዎች ስለሚለግሰው እውቀት፣ በልባቸው ሊያኖረው ስለሚችለው ተስፋና ሞራል፣ ዝንባሌና አመለካከት መጠንቀቅ እንደሚጋባው ማሰብ የለበትም ይሆን?
አቤ በድፍረት “እንደኔ እምነት የግብፅ ወታደር ኩዴታ ፈፅሟል የሚያስብል ነገር አላየሁም” ብሏልና ይህ ነገር ብዙ ብዙ ይናገራል።
“በሕዝብ የተመረጠ መሪ አጉራ ዘለል ሆኖ ተገኘ ከተባለ በመጣበት መንገድ ለመሸኘት ድጋሚ ምርጫ ማድረግ ነው የሚገባው ወይስ የአደባባይ ግርግርን መሰረት አድርጎ መዘርጠጥ?” ይህ ለአቤ የማቀርበው ጥያቄ ነው። አቤን የምጠይቀው ሌላም ጥያቄ አለኝ “ይህን ያህል ሃይል ያለው የግብፅ ጦር ለምን ሕዝብ ድምፁን በስነ ስርዓት የሚያሰማበትን ወይም በሕጋዊና ‘ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት’ ባለው የድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርዓት የሚካሄድበትን መንገድ አላመቻቸም?”
ስለ ሰልፍ ካነሳን አይቀር የሙርሲ ደጋፊዎችም ገና ከመጀመሪያው አንስቶ አደባባዮች ላይ ነበሩ። በቢቢሲ መስኮት ያልታየ ሕዝብ “ሕዝብ” አይባል ይሆን? ብየም ልጠይቅ።
ሚዲያንና ድምፅን የማሰማትን ነገር ከወሳን አይቀር ከሐምሌ 5-7/ 2013 ባለው ጊዜ ብዙዎቹ የአውሮፓ ሚዲያዎች ለመጥቀስ ያህልም ቢቢሲ፣ ዩሮ ኒውስ፣ ፍራንስ-24 ወዘተ ገና ከማህፀን ያልወጣው ከእንግሊዛዊ ልዑል ባለቤቷ ኬቲ የፀነሰችውን ልጅ ‘መጣ፣ ደረሰ፣ ቀረበ’ ሲሉና ስለ ህፃን አልጋ፣ ስለ ህፃን ልብስ፣ ስለ አራስ ልብስ ወዘተ ሃተታ ብቻ ሳይሆን የዜናቸው ዋና ክፍልም አድርገውት አይተናል። እንግሊዝ ውስጥ ሌሎች የተወለዱ፣ የሚታዩና እዚህና እዚያ የሚኖሩ ድምፃቸው ሊሰማ የሚገባ ሰዎች የሉምና ነው ለአንድ ‘እጭ’ ይህ ሁሉ ጫጫታ?! Mail On Line የተባለው የእንግሊዝ ድረ ገፅ Royal birth the world is waiting for ሲል ነው ነገሩን የዘገበው። ምን ያህል ሕዝብ ቢጓጓ ነው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው መወለድ ያለው? ሚሊዮን ወይስ ቢሊዮን? ሚዲያ እንዲህ ነው። ለራስ ሲቆርሱ…
ሚዲያዎች የተቋቋሙበት ዓላማ አላቸው። ነገራቸው ሁሉ በዚህ የተቃኘ ነው። የግብፅ ጦር ከሄሊኮፕተር አበባና በመልዕክት የተሞላ ወረቀት እየበተነ ያበረታታው ሰልፈኛ (ሕዝብ) የመኖሩን ያህል በተመሳሳይ ዕለት በታጠቀ ሃይል ከበባ ውስጥ አስገብቶ መንቀሳቀሻና መላዎሻ ያሳጣው ሕዝብም ነበር። አቤ ‘ቢቢሲ ሁለቱን ሰልፎች ጎን ለጎን እያሳየ ነው’ ያለን የሙርሲ ቁርጥ ከታወቀ በኋላ ነው፤ ቢቢሲ ለቀናት የሙርሲን ደጋፊዎች ችላ ብሎቿ ነው የነበረው። የአሜሪካ ባለስልጣናትና የአውሮፓ ጋዜጠኞች የስልጣንና የስራ ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ ችላ ያሉትን ሃቅ ወደ ኋላ ተመልሰው በማስተጋባት ይታወቃሉ። ይህን የሚያደርጉት የህሊና ወቀሳ አላስተኛ ብሏቸው ወይም በዚያ ሚስጢር ቀዳሚ (ብቸኛ) ተጠቃሚ በመሆን ታዋቂነት ወይም ‘ታላቅነት’ ወይም ገንዘብ ለማግበስበስም ሊሆን ይችላል። ቢቢሲም ይህን ባህል በመጠቀም ይታወቃል። ስለ ቦብ ጌልዶፍና እሱ ያሰባሰበው የዕርዳ ገንዘብ የት ገባ በሚል ፕሮግራም የተሰራው ነገሩ ከተፈፀመ ከ25 ዓመታት በኋላ ነው። መጀመሪያ ላይ ይህ ፕሮግራም ለሕዝብ ቀርቧል። ከዚያም ይህ ታሪክ ብዙ ውዝግብ ፈጥሮ ከቢቢሲ ከድረ ገፅ እስከመሰረዝ ደርሷል። ይህ ለአቤ ቅርብ የሆነው ታሪክ ነውና አቤ የሚዲያዎችን አካሄድ በዚህ ሊመዝነው ይችላል። ቦብ ጌልዶፍ በእንግሊዝ ንግስታዊ መንግስት “ሰር” ተብሎ የተሾመ ነውና ቢቢሲን አናውጦታል። ከማናወጥም አልፎ ቢቢሲን አፉን ይይዝ ዘንድ አስገድዶታል። ሌላም ታሪክ እናስታውስ፤ በአጠያያቂ ሁኔታ ሕይወታቸው ስላለፈው ስለ እንግሊዛዊው ዶክተር ኬሊ እና በግድያው (በሞታቸው) ዙሪያ ጉዱን ለማጋለጥ ያስችላል የተባለን አንድ ፕሮግራም ቢቢሲ ለሕዝብ በማቅረቡ አታካራ መፈጠሩንና አታካራው አንድሬ ግሊጋንን (የቢቢሲ ዳይሬክተር የነበረ) ከሓላፊነቱ ስለ ማስነሳቱ ታሪክ ፈተሽ ፈተሽ እናድርግ!!
ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ። ወንድሜ ሚዲያን ማመን ብዙ መርምሮ ነው። ሰሞኑን ኦባማ አፍሪካን ሲጎበኙ “ኦባማ አምባገነን ናቸው ያሏቸውን አገራት አይጎበኙም” እያልን የበኩላችንን ደረት የመንፋትና ክብረ ቢስ ‘ጌቶቻችንን’ የማሸማቀቅ መከራዎችን እያደረግን ነው የሰነበትነው። ለነገሩ ይህን እያልን ሰዎችን እንጎሻሽም እንጅ ኦባማ የአምባገነን አገር አይጎበኝም የሚለው እውነት ሆኖ አይደለም። ኦባማም ይሁን እየተነሳ ያለፈ የአሜሪካ ፕሬዘደንት ሁሉ ከአምባገነን ጋር ሳይላላስ የቀረበት ጊዜ የለም። አዲስ የአሜሪካ ፕሬዘደንት በተመረጠ ቁጥር ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ለገብኝት ይጠራል፣ ይሄዳል፣ የውሻ ሰንሰለት የሚያክል የወርቅ ሃብል ከነ ሜዳሊያ ከሳውዲ ነገስታት እጅ በአንገቱ ተጠልቆለት ይመለሳል። በኔ አመለካከት ሳውዲ ውስጥ የለየለት ኋላቀር፣ የለየለት የምዕራባውያን (በተለይ የአሜሪካ) አሻንጉሊት ወይም ገረድ፣ ሰው አራጅ (ስለ ‘Chop Chop Square’ ማንበብ ጥሩ ነው )፣ ሴቶችን እንደ እቃና እንድ እንስሳ የሚቆጥር ወዘተ ወዘተ መንግስት ነው ያለው። ዕድሜ ሚዲያን በገንዘብ ሃይል ሰለመቆጣጠር በሰሜን ኮርያ ስልጣን የቤተሰብ ‘ቮሊቦል’ ሲሆን የተከፉት ‘ዲሞክራቶችና’ ‘ጋዜጠኞች’ በሳውዲ ስልጣን ብቻ ሳይሆን አገር ‘ቮሊቦል’ ሲሆን ጭጭ ነው።
አቤ አንተ እነዚህን ሚዲያዎች ሰምቶ ነው የግብፅ ሕዝብ ሰልፍ ሲባል እነማንን ማሰብ እንደሚገባ የፈረደው። የነፃነትና የዲሞክራሲ ሰባኪ የሆነችው እንግሊዝ ያቋቋመችው የመገናኛ ቢሮ (Office of Communication- OFCOM) ያገዳቸው ወይም አፈና ያካሄደባቸውና በምድረ እንግሊዝ እንዳይሰራጩ የከለከላቸው እነ ፕረስ-ቲቪን ብታይ ደግሞ የተሰለፈው ሕዝብ የሚለው አመለካከትህ ሰፋ ይላል ወይም ይቀየራል ብዬ እገምታለሁ። በእርግጥ እኔ የማምነው ከቢቢሲ፣ ከቪኦኤ፣ ከስካይ ኒውስ፣ ከፎክስ ኒውስ የምሰማውን ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ይህ ግን ወደ ትክክለኛና ሚዛናዊ ፍርድ አያመራም።
አቤ “በርካታ ህዝብ አደባባይ ወጣ ተቃውሞውንም አሰማ… ሀቂቃውን ለመናገር ግን በግብጽ ተቃውሞ የወጡት ብዙሃን አንደነበሩ እድሜ ለቴክኖሎጂ በወቅቱ በቦታው ተገኝተው ሲዘግቡ የነበሩቱ ቀጥታ ሲያነፃጽሩልን ነበርና፤ ሙርሲ ይሂዱልን ከዚ… ያሉት ብዙ እንደነበሩ ድንጋይ ነክሰን ብንምልም አንፈራም” ብሎናል። ይህ አቤ ከምዕራቡ ዓለም ሚዲያዎች የወረደን ነገር እንዳለ የመቀበልና አማራጭ ሚዲያዎችስ ምን ይላሉ ብሎ ቅራና ቀኝ ለማየት እንደማይፈልግ ወይም ለዚህ ጊዜ እንደሌለው ወይም ከቢቢሲ ወዲያ ለአሳር ብሎ የማለ መሆኑን ያሳየናል ለማለት ልድፈር ይሆን? አቤ ለጠቅ አደረገና ሚዛኑን ሲያሳየን በድጋሜ “ወታደሩ ያደረገው መፈንቅለ መንግስት ሳይሆን አፍቅሮተ ህዝብ ነው ባይ ነኝ፡፡ ለብዙሃኑ ጆሮ ሰጥቷልና!” ብሎናል። ለአቤ መረጃ አቀባይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማለት ቢቢሲ እና መሰሎቹ ብቻ ይሆኑን? ብዙ ድረ ገፆችና ነፃ ሚዲያዎች እንደ ልብ በሞሉበት በዚህ ዘመን… ምነው… ምነው… ?
አቤ በዜማ (በግጥም) ይህን ብሏል “ተመረጥኩኝ ብለሽ አትበይ ደንበር ገተር… ከልተመቸው “ንኪው” ይልሻል ባላገር…” የሚል ዘፈን አለ አይደል…። የዚህን ዘፈን ዜማ ባልሰማውም ከ1997 ምርጫ በኋላ የአና ጎሜዝን ሪፖርት ተከትሎ አንድ ጋዜጠኛ ለአንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ‘ምርጫ ተጭበርብሯል እየተባለ የአውሮፓ መንግስታትም ሆኑ የአውሮፓ ህብረት ለምን ጠንካራ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጠቡ?’ ሲል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር። ለዚህ መልስ ነው ብለው የፓርላማ አባሉ ብዙ ነገር ነው የተናገሩት። ዋና ዋና ነጥቦች ለመጥቀስ ያህል “… የአካባቢው (የአፍሪካ ቀንድ) ወታደራዊ ሚዛን ሊዛባና ክልሉ ሊበጣበጥ ብሎም የሽብር መነሃሪያ ሊሆን ይችላል… የመለስ ተቃዋሚዎች ከአዲስ አበባ ውጭ ጠንካራ መሰረት የላቸውምና… ሂትለር ወደ ስልጣን የመጣው በምርጫ ነበር፤ የሰው ልጅ ነገሮችን አስቀድሞ የሚያይ ቢሆንና ያንን የምርጫ ውጤት ቢቀለብሰው ኖሮ ለዓለማችን ትልቅ በረከት በሆነ ነበር። ያ የምርጫ ውጤት ቢገለበጥ ለዓለማችን ትልቅ ጠቀሜታ ነበረው ነገር ግን ይህ ነገር ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ምርጫ ተጭበረበረ እያልን እንተቸው ነበር እንጅ ምርጫው መገልበጡ ያስቀረውን ችግርና መከራ ስለማናውቀው እናመሰግነውም ነበር…” እኝህ ሰው በግልፅ ይናገሩት እንጅ ምዕራባውያን ለጥቅማቸው ሲሉ ከዚህ የከፋ ምክንያትም ሊዘረዝሩ ይችላሉ። የ1997ተን ምርጫ ከታዘበ በኋላ ጂሚ ካርተር ቦሌ ላይ ምን ብሎ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሰጠ ሰምተኸዋል የሚል ግምት አለኝ። ካርተር ሃሳቡን የቀየረው የአና ጎሜዝን መግለጫና ጥንካሬ ካየ በኋላ አልነበረምን?
አቤ! ወደራዊ ጣልቃ ገብነት በለው መፈንቅለ መንግስት ይህ ነገር በቱርክ ቢፈፀ ምን ትለን ነበር? የቱርክ ወታደር አደባባይ የወጡ ቱርካውያንን በመደገፍ ተመሳሳዩን እርምጃ ቢወስድ እነ ኦባማ እነ ሜርክል ምን ይሉ ይመስልሃል? ሚዲያዎችስ?
የሙርሲንና የጓደኞቹን መታሰርም ልትቀልድበት ሞክረሃል። ማንም ሰው በምንም ላይ ቢቀልድ ‘መብቱ’ ሊሆን ይችላል ወይም በማን አለብኝነት መብቴ ነው ብሎ ሊያደርገው ይችላል። ነገር ግን ሁልጊዜም አሳሪ ትክክለኛ ታሳሪ ወንጀለኛ አድርገን ከወሰድን ምርጡ ኢትዮጵያዊ ወንድማችንንና ምርጧን ኢትዮጵያዊት እህታችንን (እስክንድርና ርዕዮት) ከነ ምርጥ የሙያና የአላማ ጓደኞቻቸው እስር ቤት ናቸው። ጊዜ የሰጣቸው ደግሞ ‘አሸባሪዎቹ’ እያሉ ነው የሚያብጠጥሏቸው። ሰው የፈለገው አቋም ሊኖረው ይችላል በሚዲያ ላይ የሚቀርብ ሲሆን ግን ቢያንስ የህሊና ተጠያቂነትን ግምት ውስጥ ያስገባ ስራ ቢሰራና አስተሳሰቡንም በዚሁ ቢቃኝ ጥሩ ነው። ምዕራባውያን ድሮ ለቅኝ ግዛት ሲመጡ እንስረቅ፣ እንግደል ብለው አልመጡም። ክርስትና እናስፋፋ፣ ጣዖት አምልኮና አረመኔነትን እናስወግድ፣ የባሪያ ንግድን እናጥፋ ወዘተ ነበር ያሉት። እዚህ ላይ ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወርር የሰጠውን ምክንያት ለማወቅ ‘The Lion of Judah’ የሚለውን ጥናታዊ ፊልም ልጋብዝ።
ለነገሩ አቤ ባለስልጣናትን አስመልክቶ ለበጣ ይፅፋል ይናገራል፤ ይህን ስለ እንግሊዟ ንግስት ማድረግ የሚቻል ይመስላችኋል? አቤ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለእነሱ በሚገባ ጥሩ እንግሊዝኛ የዚህ ዓይነት ነገር መፃፍ ቢጀምር ከሁለትና ከሶስት መጣጥፍ አያልፍም። ቀልድ አይደለም ወቅቶችን ጠብቀው ንግስቲቱንና የቤተመንግስቱን ቡድን የሚቃዎሙ እንግሊዛውያንን ሰልፍ እየተከታተለ በጥሩ እንግሊዝኛ ቀጥተኛ ዘገባ ቢሰራበት መዘዝ ያለው መሆኑን መርሳት አይገባም። እኛ ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ እንደምንለው በእንግሊዝም “What happens in the Palace Remains in The Palace” የሚል መመሪያ አለ። በደም የጨቀየ ታሪክ ያለው ቤተመንግስት ነው ባኪንግሃም ፓላስ። ስለ ዲያና አሟሟት የተሰራውን ፊልም እንውሰድ። ይህ ፊልም እንግሊዝ ውስጥ ለመታየት ከ80 በላይ ክፍሎች ተቆርጠው መውጣት አለባቸው ተብሎ ታግዷል። ልክ ነው ‘ዘ-ዲክታተር’ የተባለው ልብ-ወለድና በተራ ጭብጥ ላይ ተመርኩዞ የተሰራ ፊልም በአፍሪካና በዓረቡ ዓለም ሲከለከል ብዙ የተጮኸውን ያህል በዲያና ታሪክና በአሟሟቷ ላይ ብዙ መረጃዎችን አጭቆ የተሰራው እውነተኛ ፊልም በምድር እንግሊዝ እንዳይታይ ሲከለከል ሚዲያዎች ብዙ አልደሰኮሩም። ከዚህ ሌላ በቅርቡ ሰሞኑን ብዙ የተወራለት የኬቲ ፅንስ ምርመራ እየተካሄደለት በነበረበት ጊዜ ወደ ሆስፒታሉ ስልክ ተደውሎ ነበር፣ ይህን ተከትሎ ስልኩን ተቀብላ ነበር የተባለችና በዚያ የምትሰራ አንዲት ነርስ ሞታ ወይም ተገድላ መጠነኛ ውዝግብ ተከትሎ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳቀጥል ጭጭ ተብሎ ታልፏል- What happens in the Palace Remains in The Palace። ይህ ደግሞ ገና በፅንስነቱ ማስገደል ጀመረ ያሉ ግን አሉ።
አበበ ሆይ ይህን መሰል (የግብፅንና የመርሲን) ነገር ለሕዝብ የምታቀርብ ከሆነ ግራና ቀኝ ማየት አለብህ ብዬ አልመክርህም። ምክንያቱም ይህን አንተ አታጣውምና። በተጨማሪም የታላላቅ ሚዲያዎችን አሰራር ታውቀዋለህና። አበበ ገላው በዋሽንግተኑ የሬገን አዳራሽ የቃውሞውን ባወረደበት ወቅት በዚያ ወኪሉን (ሪፖርተሩን) ያልላከ የሚዲያ ድርጅት አልነበረም። የአበበ ጩኸት ለሁሉ ተሰምቶ ይሆን የሚል ጥርጣሬ የሚያጭርም አልነበረም። በዚያች ደቂቃ በዚያ አዳራሽ ሁሉም ነገር ሰአቶች ሳይቀሩ የቆሙ የሚያስመስል ተአምር ስለተፈጠረ በዚያ የተገኘ ሁሉ የአበበን ስራ ተግቶታል። “አቶ መለስ ሆይ ንግግርዎ አይሰማም፣ ድምፅ ይጨምሩ” ያለ መስሎን ነው እንዳይሉ ደግሞ በጠራ እንግሊዝኛ ነው መልዕክቱን ያስተጋባው። በዚያ ቦታ በዚያች ዕለት እንግሊዝኛ ቋንቋ የማይሰማ ጋዜጠኛ ወይም ሪፖርተር የላካል ብሎ መገመት ጅልነት ነው የሚሆነው። ነገር ግን ይህ ነገር ዜና ላይ አልተሰማም። ቪኦኤን ጨምሮ በዝምታ ነው ያለፉት። ቪኦኤ ነገሩን የዘገበው ከአድማጮች ብዙ ኡኡታና ተቃውሞ ከገጠመው በኋላ ነው። በተቃራኒው የኢራኑን መሪ በአንድ የአሜሪካ ዩንቨርስቲ ውስጥ አንድ ተማሪ ኢራን የግብረ ሰዶማውያንን መብት አታከበርም ብሎ ዘለፋ ሲሰነዝርባቸው ግን ሚዲያዎች እንዴት እየተቀባበሉ እንዳስተጋቡት እናስታውሰዋለን!!
የግብፅን ነገር ወይም የሙርሲን መውደቅ ብዙ ሰዎች ነገሩን የክርስቲያን-ሙስሊም ቁርቁስ አድርገው ያዩትና ሙርሲ እንኳን ሄደ ሲሉ ይሰማሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ሙርሲና ደጋፊዎቹ ‘እስማለዊ’ ስለሚባሉ በጭፍን እስልምና ተጠቃ የሚሉ ወገኖች ይታያሉ። እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ?
የአሜሪካና የአውሮፓ ሚዲያዎች ለምንድን ነው የሙርሲን ደጋፊዎች ‘ኢስላሚስቶች’ የሚሏቸው?
ይህ ብቻ አይደለም አልሸባብ፣ ቦኮሃራም፣ የማሊ ተዋጊዎች ወዘተ ሲጠቀሱ ይህ ‘እስላማዊው’ የሚለው ቅጥያ ተዘውትሮ ጥቅም ላይ ይውላል። ቪኦኤ የአማርኛና የትግርኛ ክፍለ ጊዜ ‘እስላማዊው’ ሲሉ ቪኦኤ ኦሮምኛ ደግሞ ‘ኢስላሙማ’ ሲል ይሰማል። የቸችኒያ፣ የሶርያ፣ እየኮሰመኑ የመጡት የኢራን መጂሃዲኖችና የመሳሰሉት የአሜሪካ ጠላት የሆኑ መንግስታትን ያጠቃሉ የሚባሉ ተዋጊዎች ሙስሊሞችና የእስልምናን መመሪያ አንግበው የሚዋጉ ቢሆንም ‘እስላማዊ’ ሲባሉ አይሰሙም። በአውሮፓና በአሜሪካ ለእስልምና ጥላቻን ማራመድ እየተስፋፋ ነው፤ ታዲያ ይህ ‘እስላማዊው’ ማለት ‘የምትጠሉት’ ወይም ‘መጠላት ያለበት’ እንደማለት ሆኖ እያገለገለ ነውን? በኡጋንዳ የጌታን ትዕዛዛት ለማስከበርና ይህን መሰረት ያደረገ መንግስት ለመመስረት እዋጋለሁ የሚለው ‘የጌታ ተፋላሚ ጦር (Lord’s Resistance Army- LRA) መኖሩ ይታወቃል። ለምን ይህንን ቡድን ‘ክርስቲያናዊው’ እያሉ ሲጠሩት አልተሰሙም?
እኔ ሙስሊም አይደሁም። ነገር ግን የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ለዘመናት አብረን የኖርን ወንድማማቾች ነንና አንዱ የውስጥ ወይም የውጭ አካል ለራሱ ይመቸው ዘንድ እኛን ሊያጫርስ የሚጭራትን ትንሽ እሳት ገና በእንጭጯ ለማጥፋት ንቁ መሆን እንዳለብን ይሰማኛል።
በመጨረሻም የሙርሲን አባባል ያጋነንከውና ልዩ ትርጉም የሰጠኸው ይመስለኛል። ይህን ያደረግከው ለአገርህ ብለህ ነው ወይስ ሙግትህን ለማጠናከር። አቶ ሙርሲ “ኢትዮጵያውንን እርስ በርስ እናበጣብጣታቸው ብለው ሲዶልቱ” ያልከው የኢትዮጵያን ተቀዋዋሚዎች በመርዳት የኢትዮጵያን መንግስት እናዳክመው ያሉትን ነው? እዚህ ላይ ምን እንደምልህ እንጃ! አንድ ታሪክ ግን ልንገርህ። ዚያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ፣ ከሸፈበት። ዚያድ ባሬ ያልተቋጨ የግዛት ጥያቄ አለውና ኢትዮጵያን እያዳከመ መቆየትና ሌላ ጦርነት ማካሄድ እንዳለበት ተሰማው። ሻዕቢያንና ወያኔን ማገዝ ጀመረ፣ አስታጠቀ፣ ፓስፖርት ሰጥቶ በፈለጉበት እየተንቀሳቀሱ የውጭ ሃይሎችን ድጋፍ እንዲያገኙና ደጋፊዎዎቻቸውን ማደራጀት ይችሉ ዘንድ ሀኔታዎችን አመቻቸ። በዚህ ግዙፍ እገዛ ዚያድ ባሬና ሶማሊያ ባይጠቀሙም ዚያድ ባሬ የረዳቸው በጣም እንደተጠቀሙ፣ ኢትዮጵያችን በእጅጉ እንደተጎዳች እያየን ነው። ይህ ጉዳት ይሽር ይሆን? “የጠላቴ ጠላት…” ሲባል ምን ማለት ነው?
የቪኦኤዋነ አዳነች ፍስሃዬ የሙርሲን ንግግር በዚህ መልኩ ደጋግማ አስተጋብታዋልች። ሙርሲ ሲወድቁም ለውድቀታቸው ድጋፍ የመሰለ ፕሮግራም ሰርታለች። ለኢትዮጵያ አስባ ነው ወይስ በአሜሪካ ሲገደፍ የነበረው የሙባረክ መውደቅ አሳስቧት ወይስ የአሜሪካ አሻንጉሊቶች የሆኑ አምባገነኖችን መገልበጥ አደጋ አለው የሚል ትምህርት ልትሰጠን ፈልጋ?
ቻው!!

አቶ መለስ ዜናዊ ለትውልድና ለሀገራችን ጥለውት ያልፉት እኩይ፣ መራራና አሳዛኝ ሀቆች

ከፊሊጶስ

የአቶ መለስ፣ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ግንኙነት ሁሌም ይደንቀኛል። በሀገርና በትውልድ ላይ የፈጸሙትንና
ጥለውት የሄዱትን ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሚትላልፍ መርዝ ሳስብ፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን የነበራቸውን
ጥላቻ ስቃኝ ፤ በ’ርግጥ የሰው አዕምሮ ተመራምሮ ይደርስብት ይሆን? እላለሁ። አሁንም ከኢትዮጵያና ከዚች ዓለም
ተለይተው ሄደው ግፋቸውን ሳስታውስ እጅግ አድርጎ ይገርመኛል ። ዘፋኙ ምን ነበር ያለው?……
’’….ግርም ያደርገኛል ያሰበኩት እንደሆን
ሰው በገዛ ሀገሩ ስደተኛ ሲሆን።….”
እስቲ ባለፉት አመታት አቶ መለስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ የሰሩትንና የፈጸሙትን መራራ ሀቆችና ለዚህ
ትውልድ ጥለውት ያለፉትን ታሪክ እጅግ ባጭር ባጭሩ (የውቅያኖስን ውሀ በጭልፋ ጨለፎ ለመጨረስ እንደመሞከር
ይቆጠራል።) እናስታውስ።
1ኛ/ አቶ መለስ፣ኢትዮጵያና
ኢትዮጵያዊነታቸው፤
አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵም ሆነ
በኢትዮጵያዊነታቸው አያምኑም ነበር። ”ኢትዮጵያዊ
ነኝ” ወይም ”ኢትዮጵያ ሀገራችን” ወይም ”ሀገሬ”
ሲሉ ተሰምተው አያውቁም።
አቶ መለስ የድሮው ለገሰ ዜናዊ ሚያዚያ 30/1947
በኢትዮጵያ በትግራይ ክፍለ ሀገር በአደዋ ተወለዱ።
ገና ከጅምሩ አቶ መለስ ለኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን
አልታገሉም። የወላጆቻቸው ክፍለ ሀገር፤ “ኤርትሪያና
ትግራይ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛቶች ናቸውና።”
እሳቸውም በኢትዮጵያዊነታቸው አያምኑም ነበር።
ሕወሓትን እንደተቀላቀሉ፤ ላልተወሰነ ግዜ ጠፍተው
ወደ ኤርትራ፣ ወደ እናታቸው መንደር አዲቋላ ነበሩ። ከዚያም ተመልስው ለሕወሓትን እጅ ሰጡ። የሻአቢያን ትግል
ለመቀላቀል ፈልገው ግን ስላልተመቻቸላችው ወይስ ተቀባይነት ስላጡ? ይህ መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው። ትውልድ
እውነቱን እንዲያውቅ። (‘’ኤርትራ ከየት ወዴት” የሚለውን የራሳቸውን ድርሳን ይመልከቱ) ታዲያ ”ኢትዮጵያዊ
ያልሆኑና በኢትዮጵያ ቅኝ ተገዥ የሆኑት” አቶ መለስ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመት የቻሉትን ያህል ከፋፍለውና አፈራርሰው
ገዙ። ሸጡ። በታሪካችንና በትውልድ ላይ ቀለዱ።
2ኛ/ አቶ መለስ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸው ግንዛቤ፤
አቶ መለስ ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ታሪክ ያላትና በአጼ ምኒሊክ የተቆረቆረች ሀገር ናት ብለው የራሳቸውን የፈጠራ
ታሪክ ያምናሉ። ማመን ብቻ አይደለም፤ እምነታቸውን ባገኙት መድረክና አጋጣሚ ሁሉ ሌላውን ወገን፣ በተለይም
ለአፍሪካዊያንና ለምዕራባዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ የበታችነትና የንቀት ስሜት እንዲያሳድሩ ከማስረዳትና ታሪክን
ከማዛባት ቦዘነው አያውቁም። ደጋፊዎቻቸውንም በዙ ድርሳናት እንዲደርሱ አድገዋል። የክህደትና የፈጠራ ታሪካቸውን
ለፓለቲካ ግባቸው ተጠቀሙበት። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ”ኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ያላትና ታላቅ ሀገር ነች።” ለማለት
ሲከጅሉ ተሰምተዋል። ዋይ!…..ንሰሀ ሊገቡ አስበው ነበር ይሆን? ወይስ አዲሱ የፓለቲካ አክሮባት? ግን ተቀደሙ።
3ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ባንዲራ፤
አቶ መለስ ለኢትዮጰያ ባንዲራ ያላቸው ጥላቻ እጅግ የከፋ ብቻ ሳይሆን “ከጨርቅ ጉዳይ የለንም!” በማለት
የራሳቸውን ባንዲራ ሰርተው፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳይፈልግ ”እንዲቀበል” አድርገውታል።
4ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ሠራዊት፤
አቶ መለስ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ጥላቻና ማን አለበኝነት ካሳዮበት መንገድ አንዱ በብዙ ድካምና
ወጭ ሲገነባ የኖረውን የኢትዮጵያን ሠራዊት በአንድ ጀምበር በመበታተንና በማፈራረስ የጎዳና ተዳዳሪ አደረጉት።
የባህርና የጦር መርከቦቻቸን ከፊሎቹን ለሻአቢያ ሰጡ፤ ሻአቢያ የማትፈልጋቸውን ደግሞ ለታሪካዊ ጥላቶቻችን ተሸጡ።
5ኛ/ አቶ መለስ፣ የኢትዮጵያ ለዕልናና ዳር ድንበር፤
በ1983 አቶ መለስ ከደርግ ጋር በሚደራደሩበት ወቅት፤ የሳቸው አሸናፊነተ ሲረጋገጥ፤ አሜሪካዊ አደራዳሪ ኸርማን
ኮኸን ለንደን ላይ ‘’የባህር በር ጉዳይ እንዴት ነው? መቼም ቢሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል።’’ ሲሏቸው፤
የአቶ መለስ መልስ “ስለ ባህር በር ጉዳይ ከሻአቢያ ጋር እንነጋገርበታለን” ነበር ያሉት። እናም ታሪካዊ ጥላቶቻችን
ዘመናት ሙሉ ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት የማድረግ ህልም አቶ መለስ እውን አደረጉላቸው። በእርግጥ አቶ መለስ
ሌላም ዓላማ ነበራቸው። ኢትዮጵያን ከቻሉ አፈራርሰው፣ ካልቻሉ ደግሞ ደካማና የተከፋፈለ ህዝብ በመፍጠር፣
ታላቋን ትግራይን በመመስረት ከኤርትራ ጋር በመስማማት አሰብን የትግራይ ማድረግ ነበር። ይህን ህልማቸውን እውን
ሳያደርጉ አቶ መለስ አለፉ። ግብረ-አበሮቻቸው ግን ”ትግላችን ይቀጥላል” በማልት ሲፎክሩ ይሰማሉ።
6ኛ/ አቶ መለስና የኤርትራ ተውኔት፤
ተውኔት-1፡ አቶ መለስ “ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች።” በማለት፤ ይህን ቋንቋ ሊገጸው፣አዕምሮ ሊያስበው
የሚከብደውን ዓይን አውጣ የክፍለ ዘመኑን የክህድት ታሪክ ለመስበክና ለማስተማር ያላቸውን ሀይል ሁሉ ተጠቀሙ።
በታሪክና በትውልድ ላይ አፌዙ።
ተውኔት-2፡ ”ኢትዮጵያዊያን ስለ ኤርትራ ምንም የሚመለከታቸው ነገር የለም።” በማለት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ
የዳር ተመልካች ሆኖ ቀረ። ለሺ’ ዘመናት ሙሉ ሲከፈል የነበረው የደምና የአጥንት መሰዋዕትነት ትርጉም የሌለውና
”የትምህክተኞች” እንደነበር በመግለጽ፤ በጀግኖች ሙታን ወገኖቻችን ላይ ሲደነፉ ኖሩ።
ተውኔት-3፡ ‘’ነጻነት ወይም ባርነት’’ ለሚጠይቀው ህዝበ ውሳኔ ህጋዊ እውቅና በመስጠት ኢትዮጵያን የመበታተኑን
የጥላቶቻችንን ሴራ ተገበሩ:: አቶ መለስ በዚህም አድራጎታቸው በጣም ይመኩ ነበር።
ተውኔት-4: “ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነበረች።” በማለት “ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነጻ መውጣቷን” ለተባበሩት
መንግሥታትና ለአፍሪካ አድነት ድርጅት ደበዳቤ በመጻፍ እውቅና እንዲሰጧት ተማጸኑ፤ አቶ መለስ። ባለስልጣናቱ
ከዓለም ህግ አንጻር እንደማይቻል ሊያስረዷቸው ቢሞክሩ (ከቡትረስ ቡትረስ ጋሊ ውጭ፤ እሳቸው ያገራቸውን
የግብጽን ዓላማ ማስፍጸም ነበረባቸው።) ”ባገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትግቡ” አሏቸው።
ተውኔት-5: በኤርትራ ምድር ከአሁን በኋላ ጥይት አይጮህም። ወ.ዘ.ተ.
አቶ መለስ ኤርትራ ከኢትዮጵያዊ እንድትገነጠል ሳይሆን ገንጥለዋል። አቶ ኢሳያስ አፈወርቂም የአቶ መለስን ያሀል
የደከሙ አይመስለኝም። አቶ መለስ ኤርትራን ገንጥለውና አስገንጥለው ከጨረሱና ሁሉንም ካመቻቹ በኋላ፤ የኤርትራ
ተወላጅ ወገኖቻችን ኢትዮጵያን እንዲገዙ ይፈልጉ ነበር። (በእርግጥ ፍታዊ በሆነ መንገድ ከሆነ አቶ ኢሳያስም
የኢትዮጵያ መሪ ቢሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስተኛ በሆነ። ችግራችን ከሚከተሉት ዓላማ እንጅ።) ለዚህም ሲሉ
በሻአቢያ የወርቅ ጥርሳቸውን ሳይቀር እየተወለቀ ለተባረሩት ዜጎች፤ ”ይህም ሲያንስ ነው፣ እንዲያውም ኢትዮጵያ ካሳ
መክፈል ነበረባት” ነበር ያሉት። እናም ቀጠሉ… ለሻቢያዎች ኢትዮጵያዊያኖችን የሚያስሩብት ከርቸሌ አዘጋጅተው
አሳሰሩ፣ አስገርፉ፣ አስገደሉ። ሻአቢያዎች የሀሰት ገንዘብ አሳትመው የፈለጉትን ነገር ሁሉ እንዲሸጡ፣ እንዲገዙ፣
እንዲለውጡና እንዲያግዙ ተደረገ። እናም ሻአቢያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ቡና ላኪ ሆኑ።
7ኛ/ መሬት ለሱዳንና ኢትዮጵያን መግዛት ለሚፈለጉ ሁሉ፤
አቶ መለስ ኤርትራን ገንጥለውና አስገንጥለው ከወገኖቻችን ለያይተውን ብቻ አልቀሩም። ስልጣናቸው መደላደሉን
ሲያረጋግጡ፣ ሱዳኖች ጫካ በነበሩበት ወቅት ለዋሉላቸው ውለታና ተቀናቃኝ ጠላት ቢነሳባቸው አሳልፈው
እንዲሰጧቸው የኢትዮጵያዊያን ገበሬዎችን በማባረር የኢትዮጵያን ክቡር መሬት ቆርሰው በገጸ-በረከትነት አበረከቱ።
አቶ መለስ በዚህ አላቆሙም….. የሀገሪቱን አንጡራ መሬትና ማዕድን ዜጋውን እያፈናቅሉ ለባዕዳንና ለታሪካዊ
ጠላቶቻችን ቸበቸቡ። እስከልተ ሞታቸው ድረስ እንግሊዝን የሚያክል ሀገር እንደሸጡ ይገምታል። አላማውም
ኢትዮጵያ ማፈራረስ ቀላሉ መንግድ በመሆኑ ነው።
8ኛ/ የአቶ መለስና ኢትዮጵያዊያን ምሁራን፤
አቶ መለስ የስልጣን ኮርቻቸውን እንደተፈናጠጡ፣ አ’ዱና ዋና ስራ አድርገው የያዙት ኢትዮጵያዊ ስብእናና ለኢትዮጵያ
ክብርና አንድንት ሊታገሉ ይችላሉ ያሏቸውን ምሁራንን ከየትምህርት ትቋሞት አሳደዋል። አባረዋል። ገለዋል።
የትምህርት ተቋማቱንም ለሆዳቸው ባደሩ ሆድ አምላኪ ‘’ምሁራንን’’ ተኩበት። ዓላማቸውም ተጠራጣሪ፣
የማይትማምን፣ ለኢትዮጵያ አንድንትና ለክብሩ ብዙም የማይጨነቅ፣ እንደገዥዎቻችን በአፍቅሮ ንዋይ የታወረ፣
ገንዝብ (ሀብት) የሁሉም ነገር መጀመሪያና መጨረሻ ነው ብሎ የሚያምን ለውጭ አለም ማንነቱን ያስረከበ ትውልድ
ለማፍራት የታቀደ ነበር። ነውም።
9ኛ/ የአቶ መለስ የዘር ጥላቻ፤
አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ያፈራረሳል ብለው የተጠቀሙበትና ዋና መሳሪያ ያደረጉት ኢትዮጵያዊያንን
በተቻለ መጠን በዘርና በቋንቋ በመከፋፈል፤ ከትውልድ ትውልድ የሚተላልፍ ጥላቻንና ቂምን በማሰራጨት፤”የክልል
ይገባኛል” የርስ-በ’ርስ እልቂት እንዲኖር ማድረግ ነው። ” ከወርቅ ዘር መወልዴ፣ ለወላይታው አክሱም ምኑ ነው፣
ወዘተ. የመሳሰሉትን አባባሎቻቸውን ስናሰብ፣ አቶ መለስ የጥላቻና የበታችነት ስሜታቸውን ለመወጣት፤የኢትዮጵያን
የህዝብ እልቂት እንደማለዳ ጸሀይ ይናፍቁና ሌት ተቀን ይደክሙ ነበር።
10ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ሃይማኖት፤
አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አዳክሞ ያፈራርሳታል ብለው ካምኑበት ውስጥ አንዱ በሃይማኖት ከፋፍሎ
እርስ በ’ርስ ማናቆርና ማበጣብጥ ነው። በተለይም የኦርቶዶክሳዊያንን ዶግማ እምነት በማፈራረስ፤ ጳጳሱን በማባረር
ከራሳቸው መንደር የሚወልዱ “ጳጳስ” አስቀመጡ። ቤተክርስቲያንን ለሁለት ከፈሉ። እስልምናንም ከክርስቲያኑ ጋር
ማበጣበጡ እንደፈለጉት አልሆን ሲል እርስ-በርስ ለማነካከስ ብዙ ጥረዋል። ሞት ቀደማቸው እንጅ።
11ኛ/ የአቶ መለስ ሰባአዊ ‘ረገጣዎች፤
አቶ መለስ ገና ጫካ እያሉ ከ’ርሳቸው የተለየ ሀሳብ ያራምዳሉ ወይም ያስባሉ ብለው የጠርጠሯቸውን፤ በተለይ ደግሞ
ኢትዮጵያዊነትን በሚያንጸባርቁና ትግላችን የመደብ ትግል ነው በሚሉ ታጋዮችን ያለ ‘ርኅራሄ ‘ረሽነዋል።
አስረሽነዋል።
መሀል ሀገር ከገቡም በኋላ በተለያዮ የሀገሪቱ ክፍሎች ዜጎች በቀለማቸው፣ በቋንቋቸውና በአመለካከታቸው ብቻ
ከገደል ከነ ነፍሳቸው ተወርውረዋል። ቤታቸው ተዝግቶባቸው እንዲቃጠሉ ተደርጒል። ተረሽነዋል። ተሳደዋል።
ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ በጥይት ተደብድበዋል። ታስረው ተገርፈዋል። ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ስደተኛና እንደሁለትኛ ዜጋ
ተቆጥረዋል።
አቶ መለስ ከወዳጃቸው ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂም ጋር በኢትዮጵያን ሀብትና ንብረት አዘራረፋ ላይ አለመስማማት
ሲፈጠር “አማራ ለያይቶን እንጅ፤ እኛ እኮ በአንድ ሳንባ መተንፈስ የምንችል አንድ ህዝቦች ነን!” እንዳልተባለ
ሁሉ፤በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ማግደው አቃጠሉ። ብዙ ዜጎችንም ተወልደው ካደጉበትና በስጋም በነፍስም
ከተሳሰሩበት ወገናቸው ለይተው አባረሩ።
ለአሜሪካ ተላለኪ በመሆንም በሱማሊያ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ሬሳቸው በመቋድሾ
ጎዳናወች እንዲጎተትና የዓለም መሳለቂያ በማድረግ ከትውልድ ትውልድ የሚተላልፍ ጥላቻና ቂም በቀል ዘሩልን።
12ኛ/አቶ መለስ፣ የሀገር ሀብትና ሙስና፤
በአጠቃላይ ማለት ይቻላል፤ የሀገሪቱ ሀብት በሳቸው አካባቢ ባሉ ሰዎች፣ ለስልጣናቸው ታማኝና ለኢትዮጵያን
ኢትዮጵያዊያን ደንታ በሌላቸው ባባእዳን የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑ ዜጎች እጅ እንዲገባ አደረጉ። ሀገሪቱን የግል
ሀብታቸውና ንብረታቸው በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የበይ ተመልካች ሆነ። ከፊሉ ተሰደደ። ከፊሉንም በርሀ፣
ባህርና ውቅያኖስ በላው። ወጣት እህቶቻችን ለዝሙትና ለአረብ ግርድና አደሩ። አንዳንዶቹም እራሳቸውን አጠፋ።
በፈላ ውህ ተቀቀሉ። ህጻናት ለስዶማዊያን ሳይቀር በጉዲፈቻ ተቸበቸቡ። ኢትዮጵያዊ ከዓለም ዜጋ ሁሉ የተጠላና
የተዋረደ ሆነ።
አቶ መለስ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያን ከምድረ-ገጽ መጥፋት ከሚፈልጉ ምእራባዊ አጋሮቻቸው ቢያንስ በአመት 4
ቢልዮን ዶላር ያገኙ ነበር። ግን ለሀገሪቱ ልማት የዋለው 14% ብቻ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት አረጋግጦላቸዋል።
ቀሪው ግን የአቶ መለስንና የመሰሎቻቸውን ካዝና እያጣበበ፣ኢትዮጵያኖችን ግን እያራቆተ ነው። ከ11.4 ቢሊዎን
ዶላር በላይ በውጭ ሀገር ባንኮች አስቀምጠዋል። በቀርቡ ደግሞ ገዥዎቻችን በያዝነው ዓመት ብቻ ከ3 ቢሊዎን ዶላር
በላይ ከሀገር አሽሽተዋል። እንገዲህ ይህ ጸሀይ የሞቀው ዓለም ያወቀው ነው። በድብቅ፣ በቤተሰብ ስምና በንግድ ስም
21 ዓምት ሙሉ የተዘረፈውን እሱ ይቁጠረው። ሙስናማ በአቶ መለስ ዘመን አዲሱ ባህላችን አድርገውልናል።
13ኛ/ አቶ መለስና ፍትህ፤
የአቶ መለስ ፍርድ ቤቶች አስቂኝና አሳዛኝ ቲያትር ቤቶች ናቸው። የፈለጉትን ሰው በፈለጉት መንገድ በአንድ ቀን
ውስጥም ቢሆን ህግ አርቅቀው የማሰር፣ የመወንጀል፣ የመግደልና የመፍረድ መብት በእጃቸው መዳፍ ውስጥ ነው።
በአሁኑ ወቅት ብዙ ዜጎች በእስር ቤት በፍትህ እጦት ይሰቃያሉ።
14ኛ አቶ መለስ፣ ተሳዳቢነትና ውሸታምነት፤
አቶ መለስ የበታችነት ስሜታቸው ሲገነፍልባቸውና የተደፈሩ ሲመስላቸው፤ አንድ አዕምሮው የተነካ ሰው እንኳን
ቢናገረው ሊቀፈን የሚችል የስድብና የንቅት ቃላቶችን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከመለደፍ ቦዝነው አያውቁም ነበር።
ውሸታምነታቸው ግን አገርን ሲያፈርስና ህዝብን ሲያበጣብጥ ከመኖሩ አልፎ፤ ተከታዮቻቸው ሞታቸውን እንኳን
ሲዋሹን ከርመዋል።
ማጠቃለያ፤
አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስና የማጥፋት ተግባራቸውን እስከመጨረሻ እስትንፋሳቸው ድረስ
ሰርተው በጽናት አልፈዋል። ስለዚህም ተከታዮቻቸው ‘’ሳያርፍ ያረፈው መለስ” ቢሏቸውና ሌላም ሌላም የመወድስ
ስም ቢያወጡላቸው ያንሳቸዋል እንጅ አይበዛባቸውም። በእርግጥ አላማ አድርገው የተነሱበትን ሙሉ በሙሉ
አላሳኩም። ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ዜጋ አሁንም አለና። እንዲያውም ይህ ትውልድ አቶ መለስና ባልደረቦቻቸው
ለፈጸሙብን ግፍና በደል፤በኢትዮጵያዊነታችን ላይ ላደረሱብን ውርደትና ከፋፍልህ ግዛው የበለጠ ግንዛቤ እያገኘን
መ’ተናል።
-4-
አዎ…አቶ መለስ ላይመለሱ ሄደዋል። ነገር ግን ላለፉት ዓመታት የደከሙበትና የለፉበት የጥላቻ፣ የዘረኝነት፣ የስደት፣
የክህደትና የሙስና በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስና የማጥፋት ዓላማቸውን ለተከታዮቻቸው
ጥለው አልፈዋል። አዲሱ ገዥዎቻችን ደግሞ የአቶ መለስን ዓላማ ተከትለው እስከመጨረሻው እንደሚጓዙ አበክረው
ገልጸውልናል። ታዲያ እኛስ አሁንም እንዳለፈው በዚሁ በተገዥነት ጉዞ እንቀጥላለን? ወይስ ካለፈው ተምረን፣ አዲስ
የትግል ስልት ቀይሰን ኢትዮጵያን ከመፈራረስ አድነን፣ ሁሉም ዜጎቿ በፍትህና በእኩልነት የሚኖሩባት የሁላችን ሀገር
እገነባለን? ጥያቄውና ጠሪው ለሁላችንም ነው።
——————-//——————
ፊልጶስ / ጳጉሜ 3/2004 ኢ-ሜል፡philiposmw@gmail.com
(በዚህ አጋጣሚ ይህችን የመለስን ምግባር እንድጽፍ ሀሳቡን ላቀረብክልኝና ለገፈፋህኝ ለያደቴ ሙሉጌታ የከበረ
ምስጋና ይድረስህ።)

ኢህአዴግ ደንግጧል!! በአዲስ አበባ የአንድነት አባላትን ማሰር ተጀምሯል

Image
በአዲስ አበባ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት የበተነ የአንድነት አባል በአደራ ታሰረ፡፡


አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ መንግስት የማደናቀፍ ተግባሩን በአዲስ አበባም ጀምሯል፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ሙሉጌታ ተፈሪ የተባለውን የአንድነት ፓርቲ የወረዳ 15 አባል ካዛንችስ አካባቢ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስሯል፡፡... ሙሉጌታ ካዛንችስ አካባቢ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጭ መታሰሩን ፖሊስ ተናግሯል፡፡

የአባሉን መታሰር የሰሙት የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ ግርማ ሰይፉና አቶ በላይ ፍቃዱ ካዛንችስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው ሙሉጌታ በህገወጥ መንገድ መታሰሩን በማስረዳት ተከራክረዋል፡፡ የጣቢያው ፖሊሶች ግን “ሙሉጌታን ያሰረው ፖሊስ ስለሌለ እሱ ሳይመጣ አይፈታም” በማለት “የአደራ እስር” ከጎንደር በተጨማሪ በአዲስ አበባም መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ አመራሮቹም “እኛም ወረቀቱን እየበተንን በመሆኑ እሰሩን” በማለት ተሟግተዋል፡፡

ዘግይቶ በደረሰን ዜና የአንድነት አመራሮች የታሳሪውን ጉዳይ መከታተላቸውን ተከትሎ ሙሉጌታ ተፈሪ ክቤ በተባለች ፖሊስ “ተመርምሮ” ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሊወሰድ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን አባላት ዛሬ ጠዋት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በመገኘት ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ህዝባዊ ንቅናቄውን በአዲስ አበባ ተደራሽ የማድረግ ተልዕኮ ተቀብለው ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ100ሺ በላይ የሆነ በራሪ ወረቀትም በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ ፍ ኖተ ነፃነት

Jul 7, 2013

የግብረ ሰዶማውያኑ ኑዛዜ በኢትዮጵያ

‹‹አዲስ አበባ ውስጥ ግብረ ሰዶማዊነት ተስፋፍቷል፡፡ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎችና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በየመንደሩ፣ በየሥርቻው፣ በየጓዳውና ጉድጓዳው ራሳቸውን ደብቀው ያደፈጡ ሁሉ ቢቆጠሩ ብዛታችን ያደላል፡፡ መጠሪያ ስማችን ጌይ ወይም ግብረ ሰዶማዊ የሚል ሳይሆን ‘ዜጋ’ የሚለው ነው፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ያልገቡ ሌሎች ወገኖችን ደግሞ ‹‹ቀጥ›› በሚል እንጠራቸዋለን፡፡››ይህንን የተናገሩት ከሰባት እስከ 32 ዓመት ድረስ ሕይወታቸውን በግብረ ሰዶማዊነት ያሳለፉት ግብረ ሰዶማውያንና ግብረ ሰዶማውያት (ወንዶችና ሴቶች)፣ ‹‹ዝምታው ይሰበር ትውልድ ይዳን በእኛ ይብቃ›› በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ዶክሜንተሪ ፊልም (ቪሲዲ) ውስጥ ባካሄዱት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው፡፡
በቸርችል ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ ‹‹ስለኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሠራር›› የሚል ታካይ ርእስ ባለውና ለምረቃ በበቃው በዚሁ ፊልም ውስጥ ይህንኑ ቃለ መጠይቅ ካካሄዱት ከእነዚህ ግብረ ሰዶማውያን ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው ሕጋዊና መደበኛ ሚስት አግብተው፣ ትዳር መስርተውና ልጆች ወልደው በሽምግልና ዕድሜያቸው ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ አዛውንቶች አሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ‹‹አባባ መሽቷል እባክዎን ወደ ቤትዎ ሂዱ›› እያሉ ወጣት ግብረ ሰዶማውያን ይቀልዱባቸዋል፡፡ ይሳለቁባቸዋል፡፡ እነዚህም አዛውንቶች ታዋቂነታቸው በ‹‹ዜጎች›› ዘንድ ብቻ ስለሆነና በአካባቢያቸው ማኅበረሰብ ዘንድ የሚታወቁት ባለትዳርና የልጆች አባት ስለሆኑ ከማኅበረሰቡ ዘንድ እንዳይገለሉና ተከብረው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፡፡ 
የእምነት ቃላቸውን ከሰጡት ግብረ ሰዶማውያን መካከል በቅጽል ስሙ ‹‹ኤሊያና›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ወጣት፣ ግብረ ሰዶም መጀመርያ የተፈፀመበት በሐዋሳ ከተማ የሰባት ዓመት ሕፃን ሳለ ነበር፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ መኖር ከጀመረ 32 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ እስካሁን ባሳለፈው ሕይወት ውስጥ ለወሬም የማይመች፣ ከባህል ውጭ የሆነ፣ ሕይወትን እስከመጥላት የሚያደርስና አሰቃቂ የሆነ ወሲብ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ሲፈጸም እንደኖረ ነው የተናገረው፡፡ 
ግብረ ሰዶማውያን የሚፈልጉትን ቆንጆ ወንድ አንዲት ሴት ይዛባቸው ከሄደች ወይም ካወጣችው ‹‹ዓይነጥላ›› ወሰደችብን እያሉ እንደሚያማርሩ ያወሳው ኤሊያና፣ በድሬዳዋ፣ በጅቡቲ፣ በየመንና በሳዑዲ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ይህንኑ የግብረሰዶም ሥራ ያከናውን እንደነበርም አልሸሸገም፡፡ ጅቡቲ የገባው ከድሬዳዋ እስከ ደዋሌ ድረስ በባቡር ከዚያም እስከ ጅቡቲ ደረስ በእግሩ ለአምስት ቀን ያህል ከተጓዘ በኋላ ነው፡፡ ከጅቡቲም በአንድ የሞተር ጀልባ ተደብቆ ወደ የመን እንደተሻገረና በመቀጠልም ሳዑዲ እንደገባ አመልክቷል፡፡ 
‹‹በአገር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የአምስት ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው የግብረ ሰዶማውያን ሠርጎችን አይቻለሁ፡፡ ይህን ዓይነቱንም ሠርግ መንግሥት ወይም ማዘጋጃ ቤትና ባህል አያውቀውም፡፡ እኛው ራሳችን ነን የምንፈጽመው፡፡ ይህም ሆኖ ፍቅርን ስለማናውቅ በጋብቻ ፀንተን አንቆይም፡፡ ጋብቻው ግፋ ቢል የሚቆየው ለሦስት ወራት ያህል ብቻ ነው፤›› ብሏል፡፡
ሚስት የሚሆን ወንድ በሠርግ ሥነ ሥርዓቱ ቀን ቅንድቡን ተቀንድቦ፣ ቻፕስቲክ ተቀብቶ፣ ፊቱ ላይ ማድረግ የሚገባውን ሜክአፕ ሁሉ አድርጎ፣ ፀጉሩን ተሠርቶና ቬሎ ለብሶ ይቀርባል፡፡ በሥነ ሥርዓቱም ላይ ኬክ እንደሚዘጋጅ ነው የተናገረው፡፡ 
ሠላሳ ሁለት ዓመታት ያህል በግብረ ሰዶም ሕይወት የቆየ፣ ስምንት ጊዜ ድል ባለ ሠርግ አግብቶ የወንድ ሚስት የነበረና በቅጽል ስሙ ‹‹አጠለል›› እየተባለ የሚጠራው ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ግብረ ሰዶማዊነትን መተዳደሪያው አድርጎ የያዘው ሲሆን፣ ይህንንም የጀመረው የስምንት ዓመት ሕፃን ሳለ ነው፡፡ የሴት ሚስት ላለውና በዚህ ላይ ደግሞ 17 የወንድ ሚስቶች ካሉት ግብረ ሰዶማዊም ጋር ትዳር ለመጀመርያ ጊዜ ‹‹17ኛ የወንድ ሚስት ሆኜ ነው ያገባሁት›› ሲል አጠለል ይናገራል፡፡ 
የግብረ ሰዶማውያን መለያቸው ከአለባበሳቸው እንደሚጀምር ይናገራል፡፡ ሁልጊዜ ቁምጣ ሱሪ እንደሚያደርጉ፣ ጠባብ ስኪኒ እንደሚያዘውትሩ፣ ጠልጠል ያለ ቦዲ ቲ ሸርት በመልበስ እምብርት እያሳዩና ያለ ካልሲ ጫማ እያደረጉ እንደሚሄዱ፣ ፀጉራቸውን ሊሞዚ መቆረጥ፣ ጆሯቸውን በተለየ ቦታ ላይ በመበሳት ጌጣ ጌጥ ማስገባትና ሎቲ ማንጠልጠል ናቸው፡፡ ከውጭ አገር የሚረዷቸውም ሰዎች አሉ፡፡ በተለይ ዳያስፖራዎች የጠለልን አድራሻ ይዘው ነው የሚመጡት፡፡ ሲጠሩት ይቀበላቸዋል፡፡ በኢንተርኔትም የሚገናኙበት መንገድ አለ፡፡ በዚህም የተነሳ ደንበኞቻቸው ሲመጡ አይቸገሩም፡፡ በሚፈልጉበት ቦታ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ 
‹‹ሪች›› በመባል የምትጠራዋ ሌላው ግብረ ሰዶማዊት (ሌዝቢያን) ወደዚህ ሕይወት ውስጥ የገባችው በጓደኛዋ ግፊት እንደሆነ፣ በዚህም ሕይወት ከገባች ስምንት ዓመት እንደሆናትና መተዳደሪያዋም ይኸው እንደሆነ ገልጻለች፡፡ ሁለት ቋሚ የሴት ደንበኞችም እንዳሏት ተናግራለች፡፡ አንደኛዋ ደንበኛዋ አዲስ አበባ ውስጥ ኦሎምፒያ አካባቢ፣ ሁለተኛዋ ደንበኛዋ ደግሞ በሐዋሳ ከተማ ይኖራሉ፡፡ በጠሩዋት ቁጥር ትሄድላቸዋለች፡፡፡ ጠሪዎቿም በጣም ሀብታሞች እንደሆኑ ነው የተናገረችው፡፡ በዚህም እርካታ እንደምታገኝ፡፡ ከተመሳሳይ ጾታዋ ጋር ካልሆነ በስተቀር ለወንድ ወይም ለተቃራኒ ጾታ ፍላጎት እንደሌላት አስረድታለች፡፡ 
ብሩክቱ ሌላዋ ግብረ ሰዶማዊት ናት፡፡ ሪታ የምትባል ክልስ የልጅነትና አብሮ አደግ የሆነች ጓደኛ ነበረቻት፡፡ በልጅነታቸው ትምህርት ቤት ሲገናኙና ከትምህርት መልስ ወደየቤታቸው ለመሄድ ሲለያዩ ይሳሳማሉ፡፡ ይህን ዓይነት ሁኔታ ቢያዘወትሩም የልጅነት ነገር እንጂ ወደ ሌላ ስሜት አይመራቸውም ነበር፡፡ ከዓመት ዓመት እያደጉና ነፍስ እያወቁ ሲመጡ በመካከሉ ሪታ ወደ ኢጣሊያ አቀናች፡፡ 
ሪታ ከሄደችበት ወደ ኢትዮጵያ ስትመለስ ግን ተለውጣ መጣች፡፡ የመሳሳማቸው ሁኔታ ወደ ልጅነት መንፈስ መሄዱ ቀርቶ ወደ ወሲብ ቀስቃሽነት ተሻገረ፡፡ በዚህም የተነሳ ውለው ሲያድሩ ፍቅር መሠረቱ፤ ‹‹እወዳታለሁ ትወደኛለች፣ ከእሷ ጋር ግንኙነት ሳደርግ ታስደስተኛለች፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ከገባሁ ሰባት ዓመት ሆኖኛል፤›› ብላለች ብሩክቱ፡፡
ሁሉም ወንዶችና ሴቶች ግብረ ሰዶማውያን ኤችአይቪ ፖዘቲቭ እንደሆኑ፣ በዚህ ላይ ደግሞ የሥነልቡና ችግርና የአአዕምሮ ጭንቀት እንዳጋጠማቸው፣ በተለይም ኤሊያና የኪንታሮት በሽታ እንዳደረበት፣ ሁሉም ከዚህ አስከፊና አስነዋሪ ሕይወት ለመውጣት እንደሚፈልጉ በየተራ በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል፡፡ 
ሰኔ 23 ቀን 2005 ዓ.ም. በተከናወነው የዶክመንተሪ ፊልሙ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የሁሉም እምነቶች ተከታዮች፣ አባት አርበኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በዚህም ጊዜ መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) የማኅበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት ሊቀመንበርና የፊልሙ ዋና አዘጋጅ ዓላማውን ሲገልጹ በአገሪቱ እየተከሰተ ያለው ግብረ ሰዶማዊነት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ትውልድንም ምን ያህል እየጎዳ እንዳለ ለማስገንዘብ ነው ብለዋል፡፡
ሦስት ዓመት በፈጀው ጥናታቸው የተገነዘቡት ነገር ቢኖር ከግብረ ሰዶማውያን መካከል አንዳንዶቹ ይህን ድርጊት ሕጋዊ እናደርገዋለን ብለው የሚዝቱና፤ ከፊሎቹ ደግሞ በተቃራኒ ድርጊቱ ለሕይወት ጎጂ በመሆኑ መውጣት አለብን ብለው የወሰኑ መኖራቸውን ነው፡፡ 
የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 6/29 ግብረ ሰዶም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፡፡ አንቀጽ 6/32 ደግሞ በዚህ ተግባር የተገኘ ከቀላል እስከ እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ያስቀጣል ይላል፡፡ መምህር ደረጀ እንደሚሉት፣ የወንጀል ሕጉ ግብረ ሰዶምን ቢከለክልም ግብረ ሰዶማዊነት በአገሪቷ በድብቅ እየተስፋፋ ነው፡፡ ራሳቸውን አጋልጠው የሚወጡ ሰዎች ቢኖሩም ራሳቸውን ባላጋለጡት ተፅዕኖ ያደርስባቸዋል፡፡ 
ዶክመንተሪ ፊልሙ በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነት መኖሩን በግልጽ በሚመሰክሩ ሰዎች አማካይነት ለመንግሥትና ለኅብረተሰቡ ማሳወቅና ከድርጊታቸው ይወጡና ይታቀቡ ዘንድ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ ለማቅረብ ነው፡፡ 
በፊልሙ ወቅታዊ ሞቅታን ፈጥሮ መለያየት እንደማያስፈልግ የሚናገሩት መምህር ደረጀ፣ በሕፃናት ላይ ግብረ ሰዶማዊ ጥቃት የመፈፀም አካሄድ የሚከተሉትን ግብረ ሰዶማውያን ከወዲሁ ለማቆም በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በሥነ ምግባር ማኅበር ተደራጅቶ በቀጣይነት መሥራት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡ 
በግብረ ሰዶም ሕይወት ለብዙ ዓመታት ማሳለፋቸውን በመጥቀስ የሕይወታቸውን እውነታ ለገለጹት የቀድሞ ግብረ ሰዶማውያን ከችግር የተነሳ መልሰው እንዳይገቡበት ኅብረተሰቡና መንግሥት ሊረዷቸው እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ 
በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነት እየተስፋፋና ግብረ ሰዶማዊ ጥቃትም እየተፈጸመ ስለሆነ ድርጊቱ ከመስፋፋቱና ‹‹ለኛም መብት ይሰጠን›› የሚል ጥያቄ ከመነሳቱ በፊት መንግሥት ከእንጭጩ ሊገታው ይገባልም ብለዋል፡፡ 
የምረቃውም ታዳሚዎች ይህ ዓይነቱን እኩይና ትውልድ ገዳይ የሆነውን ድርጊት ለመግታት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የተናገሩ ሲሆን፤ ከታዳሚዎቹም መካከል አርቲስት ተስፋዬ አበበ ግብረ ሰዶማዊነትን ለመግታት የሚያስችል በአዲስ አበባ ደረጃ አንድ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጠይቀው፣ ለኮሚቴውም ሥራ ስኬታማነት ቀስቃሽና ትምህርት አዘል መልዕክት ያላቸውን ልዩ ልዩ መዝሙሮች ለማዘጋጀት ቃል ገብተዋል፡፡ 

must watch tplf (deferewenal neqewenal)

በኢትዮዽያ ‹‹ግብረ ሰዶማዊነት›› ስር ሰዷል – (ከዳንኤል ክብረት)

zz
ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት!?
አሁን ያለንበት ወቅት አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ልጆቻችን ቤት ውስጥ መዋል የጀመሩበት፣ ወይም የክረምት መክረሚያ ነገሮችን ማከናወን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ በበጋ ከነበረው የወላጆች ወከባ ዐረፍ ብለናል፡፡ ልጆችን ትምህርት ቤት ማድረስ፣ የቤት ሥራ ማሠራት፣ ግዙ፣ አምጡ፣ ኑ፣ ሂዱ ከሚሉ የትምህርት ቤቶች ትእዛዞች ዐረፍ ያልንበት ሰሞን ነው፡፡ አሁን ልጆቻችንን ስለሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ለመነጋገር ምቹ ጊዜ ነው፡፡ እኔ ሁለት ጉዳዮችን መርጫለሁ፤ ዛሬ አንደኛውን እናንሣው፡፡
ጉዳይ አንድ
ባለፈው ሰሞን አንዲት እናት ወደ ቢሮዬ መጥተው እንዲህ አወጉኝ፡፡ ‹‹ልጄ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅና የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የማይበት ጠባይ ግራ የሚያጋባኝ እየሆነ ተቸግሬ ነበር፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የእኔን ሽቱ ይቀባል፡፡ እኔም ይህን ሳይ የልጅ ነገር አድርጌ ትቼው ነበር፡፡ በኋላ ግን ከሌላው ነገር ጋር ሲደረብብኝ ነው ግራ የተጋባሁት፡፡ ፀጉሩን እንደ ሴቶች ማስተኛት ይፈልጋል፡፡ ጥብቅ ያለ ሱሪ ካልገዛሽልኝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት አድርሼው መኪናዬን አዙሬ ልመለስ ስል ከኋላ ያለውን መኪና እንዳልነካው ዞር አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ያየሁትን ነገር ዓይኔ ሊያምን አልቻለም ነበር፡፡ ከአንድ ሌላ ወንድ ልጅ ጋር ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ከኋላዬ የነበረው መኪና በጡሩንባ እየጮኸብኝ እንኳን የማየውን ተጠራጥሬ ለረዥም ሰዓት ፈዝዤ ነበር፡፡
ሥራ ከገባሁ በኋላ እጅግ ፈዝዤ ነበር፡፡ የቢሮ ሰዎች ሁሉ እየደጋገሙ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ግን ለማን ምን ብዬ ልንገረው? ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ወደ አንዲት ጓደኛዬ ባለቤት ጋር ደወልኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነበርና ምናልባት ከረዳኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ በስልክ አነጋገሬ አደጋ የደረሰብኝ ይመስል ስለነበር እየከነፈ ቢሮዬ መጣ፡፡ ከእርሱ ጋር ተያይዘን ወጣንና አንድ ቦታ ቁጭ አልን፡፡ በልጄ ላይ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኩት፡፡ እርሱም ከሌሎች የሰማቸውን የባሱ ነገሮች እየነገረ አጽናናኝ፡፡ ከዚያም የበለጠ ርግጠኛ ለመሆንና ችግሩንም በሚገባ ለመረዳት ልጄ በማይኖርበት ሰዓት የልጄን ዕቃዎች እንድፈትሻቸው ነገረኝ፡፡ አንድ ቀን አባቱ ወደ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደው ነገርኩትና እኔ ዕቃዎቹን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ ያኔ ነው የልጄን ጉዳይ በጥልቀት የተረዳሁት፡፡ እኔ ያልገዛሁለት አንድ ቀይ ቲሸርት አገኘሁ፡፡ ቲሸርቱ ላይ በእንግሊዝኛ ‹I am a gay› የሚልተጽፎበታል፡፡ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋው ላይ ተቀምጬ ለረዥም ጊዜ አለቀስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ልጄን እንዳጣሁት ገባኝ፤ ልጄን እንደማላውቀው ገባኝ፤ ልጄና እኔ በተለያዩ መንገዶች እየተጓዝን መሆኑ ገባኝ፡፡
የጓደኛዬ ባለቤት በጉዳዩ ላይ እንዴት ከልጄ ጋር ልወያይ እንደምችል መንገዶችን አመላከተኝ፡፡ አንድ ቀን ከልጄ ጋር ከአዲስ አበባ ወጣ አልን፡፡ አብሬው ስጫወት ዋልኩና ለሻሂ ዐረፍ ስንል አንድ ስልክ አነሣሁ፡፡
አሁን ያለንበት ወቅት አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ልጆቻችን ቤት ውስጥ መዋል የጀመሩበት፣ ወይም የክረምት መክረሚያ ነገሮችን ማከናወን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ በበጋ ከነበረው የወላጆች ወከባ ዐረፍ ብለናል፡፡ ልጆችን ትምህርት ቤት ማድረስ፣ የቤት ሥራ ማሠራት፣ ግዙ፣ አምጡ፣ ኑ፣ ሂዱ ከሚሉ የትምህርት ቤቶች ትእዛዞች ዐረፍ ያልንበት ሰሞን ነው፡፡ አሁን ልጆቻችንን ስለሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ለመነጋገር ምቹ ጊዜ ነው፡፡ እኔ ሁለት ጉዳዮችን መርጫለሁ፤ ዛሬ አንደኛውን እናንሣው፡፡
ጉዳይ አንድ
ባለፈው ሰሞን አንዲት እናት ወደ ቢሮዬ መጥተው እንዲህ አወጉኝ፡፡ ‹‹ልጄ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅና የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የማይበት ጠባይ ግራ የሚያጋባኝ እየሆነ ተቸግሬ ነበር፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የእኔን ሽቱ ይቀባል፡፡ እኔም ይህን ሳይ የልጅ ነገር አድርጌ ትቼው ነበር፡፡ በኋላ ግን ከሌላው ነገር ጋር ሲደረብብኝ ነው ግራ የተጋባሁት፡፡ ፀጉሩን እንደ ሴቶች ማስተኛት ይፈልጋል፡፡ ጥብቅ ያለ ሱሪ ካልገዛሽልኝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት አድርሼው መኪናዬን አዙሬ ልመለስ ስል ከኋላ ያለውን መኪና እንዳልነካው ዞር አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ያየሁትን ነገር ዓይኔ ሊያምን አልቻለም ነበር፡፡ ከአንድ ሌላ ወንድ ልጅ ጋር ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ከኋላዬ የነበረው መኪና በጡሩንባ እየጮኸብኝ እንኳን የማየውን ተጠራጥሬ ለረዥም ሰዓት ፈዝዤ ነበር፡፡
ሥራ ከገባሁ በኋላ እጅግ ፈዝዤ ነበር፡፡ የቢሮ ሰዎች ሁሉ እየደጋገሙ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ግን ለማን ምን ብዬ ልንገረው? ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ወደ አንዲት ጓደኛዬ ባለቤት ጋር ደወልኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነበርና ምናልባት ከረዳኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ በስልክ አነጋገሬ አደጋ የደረሰብኝ ይመስል ስለነበር እየከነፈ ቢሮዬ መጣ፡፡ ከእርሱ ጋር ተያይዘን ወጣንና አንድ ቦታ ቁጭ አልን፡፡ በልጄ ላይ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኩት፡፡ እርሱም ከሌሎች የሰማቸውን የባሱ ነገሮች እየነገረ አጽናናኝ፡፡ ከዚያም የበለጠ ርግጠኛ ለመሆንና ችግሩንም በሚገባ ለመረዳት ልጄ በማይኖርበት ሰዓት የልጄን ዕቃዎች እንድፈትሻቸው ነገረኝ፡፡ አንድ ቀን አባቱ ወደ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደው ነገርኩትና እኔ ዕቃዎቹን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ ያኔ ነው የልጄን ጉዳይ በጥልቀት የተረዳሁት፡፡ እኔ ያልገዛሁለት አንድ ቀይ ቲሸርት አገኘሁ፡፡ ቲሸርቱ ላይ በእንግሊዝኛ ‹I am a gay› የሚልተጽፎበታል፡፡ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋው ላይ ተቀምጬ ለረዥም ጊዜ አለቀስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ልጄን እንዳጣሁት ገባኝ፤ ልጄን እንደማላውቀው ገባኝ፤ ልጄና እኔ በተለያዩ መንገዶች እየተጓዝን መሆኑ ገባኝ፡፡
የጓደኛዬ ባለቤት በጉዳዩ ላይ እንዴት ከልጄ ጋር ልወያይ እንደምችል መንገዶችን አመላከተኝ፡፡ አንድ ቀን ከልጄ ጋር ከአዲስ አበባ ወጣ አልን፡፡ አብሬው ስጫወት ዋልኩና ለሻሂ ዐረፍ ስንል አንድ ስልክ አነሣሁ፡፡
አሁን ያለንበት ወቅት አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ልጆቻችን ቤት ውስጥ መዋል የጀመሩበት፣ ወይም የክረምት መክረሚያ ነገሮችን ማከናወን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ በበጋ ከነበረው የወላጆች ወከባ ዐረፍ ብለናል፡፡ ልጆችን ትምህርት ቤት ማድረስ፣ የቤት ሥራ ማሠራት፣ ግዙ፣ አምጡ፣ ኑ፣ ሂዱ ከሚሉ የትምህርት ቤቶች ትእዛዞች ዐረፍ ያልንበት ሰሞን ነው፡፡ አሁን ልጆቻችንን ስለሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ለመነጋገር ምቹ ጊዜ ነው፡፡ እኔ ሁለት ጉዳዮችን መርጫለሁ፤ ዛሬ አንደኛውን እናንሣው፡፡
ጉዳይ አንድ
ባለፈው ሰሞን አንዲት እናት ወደ ቢሮዬ መጥተው እንዲህ አወጉኝ፡፡ ‹‹ልጄ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅና የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የማይበት ጠባይ ግራ የሚያጋባኝ እየሆነ ተቸግሬ ነበር፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የእኔን ሽቱ ይቀባል፡፡ እኔም ይህን ሳይ የልጅ ነገር አድርጌ ትቼው ነበር፡፡ በኋላ ግን ከሌላው ነገር ጋር ሲደረብብኝ ነው ግራ የተጋባሁት፡፡ ፀጉሩን እንደ ሴቶች ማስተኛት ይፈልጋል፡፡ ጥብቅ ያለ ሱሪ ካልገዛሽልኝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት አድርሼው መኪናዬን አዙሬ ልመለስ ስል ከኋላ ያለውን መኪና እንዳልነካው ዞር አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ያየሁትን ነገር ዓይኔ ሊያምን አልቻለም ነበር፡፡ ከአንድ ሌላ ወንድ ልጅ ጋር ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ከኋላዬ የነበረው መኪና በጡሩንባ እየጮኸብኝ እንኳን የማየውን ተጠራጥሬ ለረዥም ሰዓት ፈዝዤ ነበር፡፡
ሥራ ከገባሁ በኋላ እጅግ ፈዝዤ ነበር፡፡ የቢሮ ሰዎች ሁሉ እየደጋገሙ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ግን ለማን ምን ብዬ ልንገረው? ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ወደ አንዲት ጓደኛዬ ባለቤት ጋር ደወልኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነበርና ምናልባት ከረዳኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ በስልክ አነጋገሬ አደጋ የደረሰብኝ ይመስል ስለነበር እየከነፈ ቢሮዬ መጣ፡፡ ከእርሱ ጋር ተያይዘን ወጣንና አንድ ቦታ ቁጭ አልን፡፡ በልጄ ላይ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኩት፡፡ እርሱም ከሌሎች የሰማቸውን የባሱ ነገሮች እየነገረ አጽናናኝ፡፡ ከዚያም የበለጠ ርግጠኛ ለመሆንና ችግሩንም በሚገባ ለመረዳት ልጄ በማይኖርበት ሰዓት የልጄን ዕቃዎች እንድፈትሻቸው ነገረኝ፡፡ አንድ ቀን አባቱ ወደ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደው ነገርኩትና እኔ ዕቃዎቹን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ ያኔ ነው የልጄን ጉዳይ በጥልቀት የተረዳሁት፡፡ እኔ ያልገዛሁለት አንድ ቀይ ቲሸርት አገኘሁ፡፡ ቲሸርቱ ላይ በእንግሊዝኛ ‹I am a gay› የሚልተጽፎበታል፡፡ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋው ላይ ተቀምጬ ለረዥም ጊዜ አለቀስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ልጄን እንዳጣሁት ገባኝ፤ ልጄን እንደማላውቀው ገባኝ፤ ልጄና እኔ በተለያዩ መንገዶች እየተጓዝን መሆኑ ገባኝ፡፡
የጓደኛዬ ባለቤት በጉዳዩ ላይ እንዴት ከልጄ ጋር ልወያይ እንደምችል መንገዶችን አመላከተኝ፡፡ አንድ ቀን ከልጄ ጋር ከአዲስ አበባ ወጣ አልን፡፡ አብሬው ስጫወት ዋልኩና ለሻሂ ዐረፍ ስንል አንድ ስልክ አነሣሁ፡፡
እንደ ደነገጠ ሰው ሆኜ ነበር የማወራው፡፡ ልጄም ድምፄን እየሰማና ሁኔታዬን እያየ ተደናገጠ፡፡ ስጨርስ ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ፡፡ ‹‹አንዲት ጓደኛዬ ከባድ ነገር እንደ ደረሰባት፡፡ ልጇ ግብረ ሰዶማዊ እንደሆነባት፡፡ በዚህም ምክንያት በሕግ ሊጠየቅ መሆኑን›› ነገርኩት፡፡ እጅግ ደነገጠ፡፡ ‹‹የእኔ ልጅ መቼም እንዲህ ያለ ነገር አያደርግም›› ብዬ ተውኩት፡፡ አፍጥጦ ዓይን ዓይኔን ያየኝ ነበር፡፡ ‹‹በጣም ከባድ ነገር ነው የገጠማት፤ ግብረ ሰዶማዊ ማለትኮ በሃይማኖታችንም ትክክል አይደለም፤ እግዚአብሔር ግብረ ሰዶማውያንን አጥፍቷቸዋል፡፡ ከዚያም በላይ ግብረ ሰዶማውያን በኅሊናቸውም ሆነ በማኅበራዊ ኑሮአቸው ላይ ችግር እንደሚገጥማቸው፤ ከሕዝቡም እንደሚገለሉ፤ አኗኗራቸውም ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ እንደሆነ፤ ወንድ ከሴት ጋር ሴትም ከወንድ ጋር እንጂ ወንድ ከወንድ፣ ሴትም ከሴትጋር የሚደረገው ግንኙነት እንስሳት እንኳን የማይፈጽሙት መሆኑን፡፡ የወሲብ ግንኙነት ማንኛውም ወንድ ከ ተፈቀደለት ሴት ጋር ብቻ፣ ባህሉና እምነቱ፣ ሕጉም በሚፈቅደው እድሜና ሁኔታ የሚፈጸም መሆኑን›› እየዘረዘርኩ መግለጥ ጀመርኩ፡፡ ዝም ብሎ ነበር የሚያዳምጠኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ልጆቻቸውን ግብረ ሰዶማውያን እንደሚያደርጓቸው፤ እነዚህ ልጆችም ሌሎችን ልጆች አባብለው ወደዚህ እንደሚያስገቧቸው፤ እንዲያውም ‹I am a gay› የሚል ልብስ የሚለብሱ እንዳሉ ነገርኩት፡፡
ግራ ሳይገባው አልቀረም፡፡ ስለ እርሱ እንደምናገር ገምቷል፡፡ ስጨርስ ‹‹የኔ ልጅ አንተ ግን እንደዚህ አታደርግም አይደል?›› አልኩት፡፡ ምንም አላለኝም፡፡ ዝም አለኝ፡፡ መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡ ‹‹ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ እንዴ›› አልኩት፡፡ ዝም አለ፡፡ ‹‹አደራህን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልጆች ሌሎች ልጆችን ሳያውቁት ወደዚህ ነገር እያስገቧቸው ነውና ተጠንቀቅ›› አልኩት፡፡ እሺምእምቢም አላለኝም፡፡ ‹‹አንተ ይህንን ስታደርግ ካየሁ፤ እኔ ዲያው ነው የምሞተው›› ስለው ተስፈንጥሮ መጥቶ ጭኔ ላይ ተደፋ፡፡ ሲያለቅስ ይሰማኛል፡፡ ዕንባውም እግሬን ሲያሞቀው ይታወቀኛል፡፡ እኔም እያለቀስኩ ነበር፡፡ ከብዙ የዝምታ ልቅሶ በኋላ ‹‹እማዬ እኔኮ ጌይ ሆኛለሁ›› አለኝ፡፡ ቀድሜ ባውቅም ያ ሰዓት ግን መብረቅ የመታኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከልጄ አንደበት ይህንን ስሰማ ኩምሽሽ ብዬ ትንሽ የሆንኩ መሰለኝ፡፡ የማደርገው ጨነቀኝ፤ ምን ልመልስለት? ምንልበለው? ግራ ተጋባሁ፡፡ ‹‹ለምን ልጄ? ለምን?›› አልኩት፡፡ ከእኛ ራቅ ብለው የሚያዩን ሰዎች ሁኔታዬ ግራ አጋብቷቸው ሁሉም እኔን ያያሉ፡፡
‹‹እኛ ትምህርት ቤትኮ ብዙ ልጆች አሉ›› አለኝ፡፡‹‹ምን ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት‹‹ሽቱ ተቀብተው ይመጣሉ፤ ደግሞ አንድ ዓይነት ማስቲካ ነው የምንበላው፤ ‹I ama gay› የሚል ቲሸርት እንለብሳለን›› አለኝ፡፡‹‹ቲሸርቱን ማን ነው የሰጣችሁ?›› አልኩት‹‹አንድ ልጅ ነው ያመጣልን፤ ለሁላችን ሰጠን፡፡ ግን ከዩኒፎርማችን ሥር እንድንለብሰው ነግሮናል››‹‹ሌላስ?››‹‹ደግሞ አንድ ልጅ የጌይ ፊልም በዕረፍት ጊዜ ያሳየናል››‹‹የት ነው የሚያሳያችሁ?›› ‹‹በኪሱ የሚያመጣው ሞባይል አለ፡፡ እናቴ ናት የምትጭንልኝ ብሏል››የምሰማውን እንዴት ልመነው?‹‹እርሱኮ [የልጁን ስም እየነገረኝ] አባቱ ትምህርት ቤት ሲሸኘው ሁልጊዜ ከንፈሩን ይስመዋል›› አለኝ፡፡ ይኼኔ ነቃሁ፡፡ አስታወስኩ፡፡ ሰውዬውንም ዐወቅኩት፡፡ እኔም ደስ አይለኝም ነበር፡፡ አባት ወንድ ልጁን፣ እናትም ሴት ልጇን ከንፈራቸውን መሳም እዚህ ትምህርት ቤት የማየው ነገር ነው፡፡ ይህ ነገር ልጆቻችን ይህንን መሰሉን ተግባር ከዕድሜ ቀድመው እንዲለምዱት ያደርጋል፡፡ ከዚያም አልፎ ነገ ሌሎች ግብረ ሰዶማውያን በልጆቹ ላይ ይህንን መሰል ተግባር ሲፈጽሙባቸው ምንም እንዳይመስላቸውና የፍቅር መግለጫ አድርገው እንዲወስዱት ያደርጋቸዋል፡፡ ከባህላችን ያፈነገጡ ነገሮችን በልጆቻችን ላይ ማድረግ እነዚህ ነገሮች በልጆቻችን ላይ በሌሎች አካላት ሲደረጉባቸው እንዳያስተውሉት እንዳይጸየፉትም ያደርጋቸዋል፡፡‹‹ለመሆኑ አብራችሁ ስትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት፡፡‹‹አንዳንድ ወንዶች ልጆች ይሳሳማሉ፤ እኔ ግን ይደብረኛል፤ ደግሞ ይተሻሻሉ›› አለኝ፡፡ ከገጽታው የመቅፈፍ ስሜት አየሁበት፡፡ ይህንን ስሜት ስመለከት ወደ ችግሩ ውስጥ ዘልቆ እንዳልገባበት ተረዳሁ፡፡ እኔ የማዝነው በባህላችን ተከብሮ የኖረውን የወንድም ለወንድም፣ የእኅት ለእኅት ግንኙነት ግብረ ሰዶማዊነት እያጠፋብን በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ከአክስቶቼ ልጆች ጋር አብሬ እየተጫወትኩ፣ አብሬእየተኛሁ ነው ያደግኩት፡፡ ልጆቻችን ግን እንዲህ ማድረግ ላይችሉ ነው፡፡ ከአጎታችን፣ ከአክስታችን ጋር መተኛት ለኛ ደስታችን ነበር፡፡ ዛሬ ግን ዘመዶች በዘመዶች ላይ እንዲህ የሚፈጽሙ ከሆነ ዝምድናችን ሊጠፋብን ነው፡፡ መምህሮቻችንን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የቤት ሠራተኞችን፣ የጥበቃ ሠራተኞችን እየተጠራጠርን ልንኖር ነው፡፡ ግብረ ሰዶምነት ባህላችንን እጅግ አድርጎ ነው የሚያበላሸው፤ ማኅበራዊ ግንኙነቶቻችንን ነው የሚበጣጥሰው፤ እንዴት ያለ ችግር ውስጥ ነው የገባነው በእግዚአብሔር? በኋላ ከአንዳንድ የሕክምና ባለሞያዎች ጋር ስንነጋገር ብዙ ነገር ሰማሁ፡፡ በከተማችን ውስጥ የግብረ ሰዶማውያን ማዘውተሪያዎች የታወቁ ናቸው፡፡ የራሳቸው የመግባቢያ ‹ቋንቋም› አላቸው፡፡ ትልልቆቹ ግብረ ሰዶማውያን ድራግ በመውሰድ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ለሕፃናቱ ድራጉን በከረሚላ መልክ ይሰጧቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ለመደበቅ ሲሉ ልጆቹ ግለኛነትን ይመርጣሉ፡፡ ከሌሎች ልጆች ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ከመጨዋት ይልቅ ከጌምና ከቴሌቭዥን ጋር ብቻ መሆንን ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ፌስ ቡክን በሚገባ ለዚህ አስተሳሰብ ማራመጃ ይጠቀሙበታል፡፡ ወላጆች ኢንተርኔትን ልጆቻችን ያለእድሜያቸው እንዳይጠቀሙበት ማድረግ አለብን፡፡ ስለ ኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ስለ ጥቅምና ጉዳቱ ሳንነግራቸው ነው የምንፈቅድላቸው፡፡ ይኼኔ ከበጎው ይልቅ ክፉውን የመያዝ ዕድላቸው ይሰፋል፡፡ በቤታችን ውስጥ ያስገባናቸውን የቴሌቭዥን ቻነሎችንም መቆጣጠር አለብን፡፡ ልጆቻችን ክፉውንም ደጉንም ዝም ብለው እንዲያዩ ማድረግ የለብንም፡፡ ግብረ ሰዶምን የሚያበረታቱ ቻነሎች አሉ፡፡

‹አሁን ልጅዎ ከችግሩ በሚገባ ወጥቶልዎታል?›› አልኳቸው፡፡‹‹ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ወጥቷል ማለት አልችልም፤ አሁንም እጠራጠራለሁ፡፡ ፍርሃቱ ገና አልለቀቀኝም፡፡ ነገር ግን ክትትሌን አላቆምኩም፤ ከልጄ ጋር ያለኝን ቀረቤታም ጨምሬያለሁ፤ ስለ ብዙ ነገሮችም እንነጋገራለን፤ የሃይማኖት ትምህርት እንዲማርም እያደረግኩ ነው፡፡ አንድ የማውቀው የሥነ ልቡና ባለሞያ ስለ ግረ ሰዶም ጉዳት በሚገባ ነግሮታል፡፡ በተለይ በዚህ ክረምት የተለየ ነገር ለማድረግ እየሞከርኩ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶቻችንን ግን ከትምህርት ጥራትና ከክፍያቸው ባለፈ ወላጆች መከታተል አለብን፤ ልጆቻችንም የተለየ ነገር ሲያዩ እንዲነግሩን ማሳሰብ ይገባል፡፡ ዘመኑ ወላጅነት ከባድ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ ›› አሉኝ፡፡ወላጆች ሆይእስኪ በጉዳዩ ላይ እንምከርበት፡፡ ከልጆቻችንም ጋር እንነጋገር፤ መምህራን በተማሪዎች ላይ ይህንን ነገር ፈጽመዋል ተብለው የሚከሰሱበት ጊዜ ላይ ነንና ልጆቻችን እንዳይታለሉ እንንገራቸው፤ ከሃይማኖት፣ ከሥነ ምግባር፣ ከባህል፣ ከጤናና ከማኅበራዊ ኑሮ አንጻር የሚያስከትለውን ችግር እንንገራቸው፡፡ እኛም ስለዚህ ጉዳይ መረጃ እንዲኖረን እንጠይቅ፣ እናንብብ፣ እንመካከር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ከምሰማው አንጻር በተለይ በከተሞች ውስጥ ችግሩ ሳይታሰብ ሥር እየሰደደ ነው፡፡ ሰሞኑን የቀረበ አንድ ይፋ ያልሆነ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ 2000 ተማዎች ላይ በተደረገ ጥናት 48% ተማሪዎች የጌይና ሌዝቢያን ደጋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ እኒህ እናት እንዳሉት በዚህ ዘመን ወላጅነት ፈተና ውስጥ ገብቷል፡፡ ኃላፊነቱ ሰፍቷል፡፡ መሰናክሉ በዝቷል፡፡ እስኪ የፈጣሪን ርዳታ እየጠየቅን ይህንን ነገር የሰሞኑ የቤተሰብ አጀንዳ እናድርገው፡፡

Weyane to Export Ethiopian Girls to Qatar as Domestic Workers


Ethiopia sets terms for sending maids to Qatar
DOHA: Ethiopia has agreed to send domestic workers, including maids, to Qatar but said it would need monthly reports about salary payments to them and that their work timings should not exceed that agreed upon in their job contracts.
The dignity and rights of Ethiopian workers must be protected in Qatar, the country’s Minister of State for Labour and Social Affairs, Dr Zerihun Kebede, told a visiting delegation of Qatar Chamber, representative body of the private sector.
He said requests to recruit Ethiopian domestics will need to be submitted to the country’s embassy in Doha, and it would be sent to manpower agencies in Ethiopia for approval.
However, an extensive mechanism is being put in place for the recruitment process to take off based on terms and conditions agreed on by both sides, local Arabic daily Al Watan reported yesterday.
The Chamber delegation led by Ali Hamad Al Marri held discussions with the Ethiopian labour ministry for two days beginning June 30.
The wages paid to the Ethiopian domestics will be uniform, the Qatari delegation told Ethiopian officials. There are 120 manpower agencies in Qatar while the number of recognised recruitment agencies in Ethiopia is 380.
Those shortlisted for recruitment will have to undergo medical tests in Ethiopia, and later on here. If a worker is sent home on health grounds, all costs would be borne by the Ethiopian agency concerned.

በሁለት ሕፃናት ተማሪዎቻቸው ላይ የግብረሰዶም ጥቃት ፈጽመዋል በተባሉ ስድስት መምህራን ላይ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ስድስት ምስክሮች፣ ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ በሚባል ትምህርት ቤት ውስጥ፣ የአሥርና የ11 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የአራተኛና የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የግብረሰዶም ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ኃይለየሱስ፣ ሱፐርቫይዘሩ አቶ የኔዓለም ጌታቸው፣ መምህር አለማየሁ ገብሬ፣ መምህር ደበበ ጥሩነህ፣ አቶ መልካሙ ቀለብና አቶ ሳምሶን መኩሪያ ሲሆኑ፣ አካዳሚው ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚም በክሱ መካተቱ ይታወሳል፡፡ 
ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለመሠረተው ክስ ያስረዱልኛል ያላቸውን ሁለቱ ተጠቂ ሕፃናትና እናቶቻቸውን፣ እንዲሁም አንድ የሥነ ልቦና አማካሪና አንድ የሕግ ባለሙያ አቅርቦ አስመስክሯል፡፡ 
የግል ተበዳይ መሆኑ የተገለጸው የአሥር ዓመቱና የአራተኛ ክፍል ተማሪ ሕፃን ለፍርድ ቤቱ የሚያስረዳለትን ዓቃቤ ሕግ በጭብጡ ያስያዘው፣ ተጠቂው ወደ አካዳሚው የተቀላቀለው በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም.፣ የግብረሰዶም ድርጊቱ የተፈጸመበት በገባበት ቀን ነው፡፡ በየካቲት ወር 2005 ዓ.ም. ለሁለተኛ ጊዜ ድርጊቱ እንደተፈጸመበትና ሁሉም መምህራን በመፈራረቅ ድርጊቱን እንደፈጸሙበት እንደሚያስረዳለት አስይዟል፡፡ 
ሕፃኑ በሲሲቲቪ ለችሎቱ እንደገለጸው፣ አካዳሚውን መቼ እንደተቀላቀለ አያስታውስም፡፡ አራተኛ ክፍል ሆኖ መቀላቀሉን ግን ያውቃል፡፡ ወደ አካዳሚው ሊገባ የቻለው ቤተሰቦቹ ከኮተቤ ወደ ቦሌ ቤት በመቀየራቸው ነው፡፡ በመጀመርያ ትምህርት ቤት ሲሄድ ዳይሬክተሩ ጠርተውት ለምን ወደ አካዳሚው እንደመጣ ሲጠይቁት ‹‹ቀድሞ በነበርኩበት ትምህርት ቤት ተደፍሬ ነው አልኩት፤›› በማለት ተናግሯል፡፡ 
ዳይሬክተሩ በሌላ ቀን ጠርተውት የግብረሰዶም ጥቃት እንዳደረሱበትና ሌሎቹም መምህራን (ሙሉ ስማቸውን ጠርቶ) ድርጊቱን እንደፈጸሙበት ያስረዳው ሕፃኑ፣ ድርጊቱን የፈጸሙበት በባዶ ክፍል ውስጥ በዕረፍትና በምሳ ሰዓት መሆኑን ተናግሯል፡፡ 
አንደኛው መምህር ድርጊቱን ሲፈጽም ሌላኛው መምህር እንደሚይዘው የተናገረው ተጠቂው፣ ድርጊቱን አንዳንድ ጊዜ በቢሮ ውስጥ እንደሚፈጽሙበት አስረድቷል፡፡ 
የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ለሕፃኑ ‹‹ስንት ጊዜ ተደፈርክ?›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡለት፣ ‹‹ብዙ ጊዜ ቀን ቀን እያሳለፉ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በተከታታይ ደፍረውኛል፤›› ብሏል፡፡ የመምህራኑን ስም እየጠራ በተደጋጋሚ ድርጊቱን እንደፈጸሙበት ገልጿል፡፡ 
ለቤተሰቡ መጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ለማን እንደሆነ ተጠይቆ ለእናቱ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ከነገራቸው በኋላም ትምህርት ቤት መሄዱን አላማቋረጡን አክሏል፡፡ ለምን ለአባቱ እንዳልተናገረ ሲጠየቅ፣ ‹‹እኔ እንጃ የሰማ አልመሰለኝም›› ብሏል፡፡ በተደጋጋሚ ድርጊቱ ሲፈጸምበት ለእናቱ ቢናገርም ከትምህርት ቤት አለመቅረቱን ገልጿል፡፡ ወደ ሆስፒታል እናቱ እንደወሰዱት ነገር ግን አባቱ ይወቁ አይወቁ የሚያውቀው ነገር እንደሌላ ገልጿል፡፡ ሲደፈር መጮህ አለመጮኹን እንዲያስረዳ ተጠይቆ እንዳልጮኸ ተናግሯል፡፡ አካላዊ ጉዳት እንዳልደረሰበት ግን ትንሽ አሞት እንደነበር ገልጿል፡፡ ሲፀዳዳ አንዳንድ ጊዜ እንደሚያመውም አክሏል፡፡ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ እዚያው ከተደረገበት ቦታ ትተውት ሲሄዱ ወደ ጨዋታው መሄዱንና ብቻውን መጫወቱን ተናግሯል፡፡ ሌላ ጊዜም በተደጋጋሚ ሲደፈር ጊዜ ካለው ወደ ጨዋታ እንደሚሄድ ጊዜ ከሌለው ወደ ትምህርቱ እንደሚገባ ገልጿል፡፡ የትምህርት ቤቱን ሠራተኞች ስለሚፈራም ለማንም አለመናገሩን አስረድቷል፡፡ ሊደፍሩት የሚወስዱት ብቻውን ሲያገኙት መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
ሁለተኛው የግል ተበዳይ የ11 ዓመት ዕድሜ ያለው የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሕፃን ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ ለአንደኛው የግል ተበዳይ ባስያዘው ጭብጥ መሠረት የተፈጸመበትን ድርጊት ለችሎቱ እንዲያስረዳ ጠይቆት ሕፃኑ አስረድቷል፡፡ 
የሁሉንም ተጠርጣሪዎች ስም ሲጣራ ‹‹ምን አደረጉህ?›› በማለት ዓቃቤ ሕግ ጠይቆት እንዳስረዳው፣ የሚኖረው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ለቡ ነው፡፡ ወደ ትምህርት ቤቱ የገባው በየካቲት ወር ነው፡፡ አምስት መምህራን ገና የገባ ዕለት ድርጊቱን እንደፈጸሙበት ተናግሯል፡፡ ድርጊቱን ለመፈጸም ጣታቸውንም መጠቀማቸውን ሕፃኑ አክሏል፡፡ 
የተጠርጣሪዎች ጠበቆች ‹‹ድርጊቱን የፈጸሙብህ መጀመሪያ የገባህ ቀን ነው?›› በማለት ለሕፃኑ ላቀረቡለት መስቀለኛ ጥያቄ፣ ‹‹አዎ›› ብሏል፡፡ ለእናቱ እንደነገራቸውና ከሦስት ሳምንታት በኋላ ወደ ትምህርት ቤቱ መመለሱን አስረድቷል፡፡ እናቱ ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩት ሞባይል ስልክ አስይዘውት ‹‹ሲጠሩህ ደውልልኝ›› እንዳሉት የተናገረው ሕፃኑ፣ መምህራኑ ሲጠሩት ሊደውል ሲል ሱፐርቫይዘሩ እንደከለከሉት ገልጿል፡፡ 
በሌላኛው ሕፃን ላይ ጥቃት መፈጸሙንና እንዴት እንዳወቀ ጠበቆች ሲጠይቁት እናቶቻቸው ተገናኝተው ሲነጋገሩ መስማቱን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በስልክ ሲያወሩ መስማቱን፣ በመቀጠል ደግሞ ተጠቂ ነኝ ያለው ልጅ እንደነገረው አስረድቷል፡፡ 
ለቤተሰቦቹ ለምን እንዳልተናገረ ሲጠየቅ ደግሞ፣ ተጠርጣሪዎቹ እንደሚገድሉት ስላስፈራሩት መሆኑን ሲናገር፣ ‹‹ታዲያ እንዴት ለእናትህ ተናገርክ?›› ሲባል ከንፈሩ በልዞ ተመልክተው ‹‹ካልነገርከኝ ራሴን መኪና ውስጥ ከትቼ አጠፋለሁ›› ስላሉት ፈርቶ መናገሩን አስረድቷል፡፡ 
ከተደፈረ በኋላ ወዴት እንደሚሄድ ተጠይቆ ወደ ጨዋታ እንደሚሄድ ተናግሯል፡፡ እናቱ ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩት ቲሸርቱንና የሱሪውን ወገብ ሰፍተው መሆኑን፣ ነግር ግን ድርጊቱን የሚፈጽሙበት ስፌቱን ቀደው መሆኑን አስረድቷል፡፡ መፀዳጃ ቤት እንዴት እንደሚጠቀም ሲጠየቅ፣ ‹‹ጠዋት ቤት ከተፀዳዳሁ ስመለስ ነው የምጠቀመው፤›› ብሏል፡፡ 
ሆስፒታል ስለመወሰዱ ተጠይቆ፣ የመጀመርያው ቀንና የመጨረሻው ቀን ጋንዲና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንደተወሰደና ድርጊቱ የተፈጸመበት ለሦስት ቀናት መሆኑን ገልጿል፡፡ 
የመጀመርያው ተጠቂ እናት በሰጡት ምስክርነት እንደገለጹት፣ መምህራኑ በልጃቸው ላይ ተፈራርቀው ጥቃት አድርሰውበታል፡፡ በሌላ ትምህርት ቤትም ተደፍሮ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ከነበረበት ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ካራክተር ሆልማርክ አስገቡት፡፡ በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም. መጀመርያ ቀን ዳይሬክተሩ ከየትና እንዴት እንደመጣ ከጠየቀው በኋላ፣ እንደደፈረውና ሌሎቹም ደጋግመው እንዳደረጉት እንደነገራቸው አስረድተዋል፡፡ 
ለአካዳሚው የቦርድ አባል ለሆኑ ግለሰብ ሲደውሉላቸው፣ ተደፈረ የሚባለው ነገር ሊደረግ እንደማይችልና ስህተት መሆኑን ሲገልጹላቸው፣ ለሌሎች የአካዳሚው ሰዎች ቢናገሩም ምንም ዓይነት ዕርምጃ እንዳልተወሰደ ገልጸዋል፡፡ 
ጠበቆች እንዴት ከሌላ ትምህርት ቤት ሊያስወጡት እንደቻሉ ሲጠይቋቸው፣ በነበረበት ትምህርት ቤት ሌሎች ሲደፈሩ በማየቱ በቀጣይ እሱም ጋ ይደርሳል የሚል ሥጋት ስላደረባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህንን አካዳሚም የመረጡት በግብረሰዶማውያን ዙሪያ የሚያስተምሩትንና የአካዳሚው የቦርድ አባልን አግኝተዋቸው ሲያስረዷቸው፣ ‹‹አምጭው እኛ ጋ ይማር›› ስላሏቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ ትምህርት ቤት ጥቃቱ ደርሶበት ወንጀለኞቹ እንደተፈረደባቸውም ተናግረዋል፡፡ 
ባለቤታቸው ትልቅ ቦታ ያሉ በመሆናቸውና ታማሚ በመሆናቸው እንዲሁም ልጁ አንድ ልጃቸው በመሆኑ ፈርተው እንዳልነገሯቸው ገልጸዋል፡፡ ከጥቅምት እስከ መጋቢት ድርጊቱ እንደተፈጸመበት እየነገራቸው ትምህርት ቤት እንደወሰዱት አስረድተዋል፡፡ ለምን ወደ ሕግ እንዳልወሰዱት ተጠይቀው፣ ከአባቱ ጋር ካልተስማሙ የማስቀረት አቅም እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ ባለቤታቸው ቢነግሯቸውም ‹‹ሊሆን አይችልም›› እንደሚሏቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጀመርያው ቀን ስድስቱም አስተማሪዎች እንደደፈሩት እንደነገራቸው ገልጸዋል፡፡ ገና እንደገባ እንዴት ሊያውቃቸው (ስማቸውን) እንደቻለ ሲጠየቁ፣ ሁሉንም ከነስማቸው እንደሚያውቃቸው ጠቁመዋል፡፡ 
የሁለተኛው ተጠቂ እናትም በልጃቸው ላይ ጥቃቱ እንደደረሰ ያወቁት ከሦስት ሳምንታት በኋላ መሆኑን ተናግረው፣ ድርጊቱን የፈጸሙበት ግን ትምህርት ቤቱ በገባ ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 
አምስት መምህራን እንደደፈሩት ለትምህርት ቤቱ ቦርድና ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን፣ ካሜራ ለመግጠም ቢሞከርም መነቀሉን፣ ጋንዲና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወስደው ማስመርመራቸውንም መስክረዋል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወስደው ለሥነ ልቡና ባለሙያዎች ማማከራቸውንም አክለዋል፡፡ 
ልጃቸው ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ አምስተኛው ትምህርት ቤቱ መሆኑን የገለጹት የተጠቂው እናት፣ በአራቱም ትምህርት ቤቶች መደፈሩን አስረድተዋል፡፡ የትምህርት ቤቶቹን ስምም ጠቅሰዋል፡፡ ለፖሊስ እንዲደውል ስልክ አስይዘው ቢልኩትም ዳይሬክተሩ እንደነጠቁት፣ እናቱ ስልኩን ሲያዩት መደወሉን አይተው ‹‹ተደፈርክ?›› ሲሉት ‹‹አልተደፈርኩም›› ቢላቸውም፣ ‹‹እውነቱን ካልነገርከኝ መኪና ውስጥ እገባለሁ›› በማለታቸው በድጋሚ መደፈሩን እንደነገራቸው አስረድተዋል፡፡ 
ጠበቆች እውነቱን እየነገራቸው ለምን እንዳስጨነቁት ሲጠይቋቸው፣ ‹‹ስለፈራ እንጂ እንደተደፈረማ አውቃለሁ፤›› ብለዋል፡፡ ሌላዋ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠራተኛ የሆኑ ግለሰብ ሲሆኑ፣ ልጆቹ እሳቸው ዘንድ የመጡ ቢሆንም ያነጋገሯቸው ከ20 ደቂቃ የማይበልጥ በመሆኑ ሙያዊ ማብራሪያ ሊሰጡ እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡ 
የመጨረሻዋ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የሕግ ባለሙያና የሕፃናት የሕግ ከለላ ማዕከል ኃላፊ ሲሆኑ ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውን፣ ነገር ግን ጉዳዩ ስለሚቀፍ መስማት እንዳልፈለጉ፣ ነገር ግን ተጠቂዎቹ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ቃላቸውን ሲሰጡ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተገኝተው መስማታቸውን መስክረዋል፡፡ 
ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃልንና ክሱን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት በሚኒስቴር ደረጃ ሊቋቋም ነው

     የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት በሚኒስቴር ደረጃ ሊቋቋም ነው

-የደኅንነት ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለሚወስዱት ዕርምጃ በሕግ አይጠየቁም
-ማንኛውም ሰው መረጃ መጠየቁንና መስጠቱን በሚስጥር የመያዝ ግዴታ አለበት
ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ተቋምን በሚኒስቴር ደረጃ እንደገና የሚያቋቁም ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በ1987 ዓ.ም. በወጣ አዋጅ የተቋቋመ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ በርካታ አገራዊ፣ አካባቢያዊ፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ላይ ለውጦች መታየታቸውና እነዚህ ለውጦች በኢትዮጵያ ደኅንነት ላይ ያላቸውን ፋይዳ ባገናዘበ ሁኔታ በተቋሙ ላይ ለውጥ መፍጠር በማስፈለጉ፣ ማሻሻያው እንዲደረግ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አባሪ ያደረገው መግለጫ ያስረዳል፡፡
በዚህም መሠረት የአገር መከላከያን፣ የአገር ደኅንነትንና ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ ሥልጣንና ተግባር የፌዴራል መንግሥት እንደመሆኑ መጠን፣ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በአገር ደረጃ የሚዋቀር ብቸኛ ተቋም ሆኖ ክልሎች መሰል ተቋም ሊኖሯቸው እንደማይችል በማመልከት አዋጁ ተረቋል፡፡
አገልግሎቱ ካለበት ሕገ መንግሥታዊና አገራዊ ኃላፊነት እንዲሁም ካለው ሰፊ ሥልጣንና ተግባር አንፃር በሚኒስቴር ደረጃ እንዲዋቀር በረቂቅ አዋጁ ተካቷል፡፡
ተቋሙ ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን የሒሳብ መዛግብትና ሌሎች የሥራ መረጃዎችን እጅግ ብርቱ ሚስጥር ብሎ በመሰየም ለሌሎች አካላት (የፈዴራል ኦዲተርንም ቢሆን) ሊከለክል እንደሚችል በረቂቁ ላይ ተካቷል፡፡
ይህ ሥልጣን ቢኖረውም በውስጥ ኦዲተርና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚቀርብ ሪፖርት መነሻነት ክትትልና ቁጥጥር ስለሚደረግበት፣ የተጠያቂነት ሥርዓቱ ላይ ጥያቄ የማያጭር መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አባሪ መግለጫ ያስረዳል፡፡
በመሆኑም ተቋሙ ከውጭ አገር የሚያስገባቸውን የመረጃ ደኅንነት መሣሪያዎች ወይም ዕቃዎች ለጉምሩክ ሳይገለጹ እንዲገቡ ማድረግ ሲችል፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ተመሳሳይ መሣሪያዎች ሚስጥራዊ ባህሪያቸው እንደተጠበቀ እንዲንቀሳቀሱ አዋጁ ይፈቅዳል፡፡
የተቋሙ የደኅንነት ሠራተኞች ማንነትና የሀብት መጠን ሚስጥራዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጠበቅ የማድረግ ኃላፊነትም በረቂቁ ተካቷል፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ ከአገር ውስጥ የሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በፀጥታ ዙሪያ በቅንጅት እንዲሠራ ትብብሩና መደጋገፉ በአጋር አካላት በጐ ፈቃደኝነት ላይ የተሠረተ ሳይሆን፣ ግዴታን የጣለ ረቂቅ አንቀጽ ተካቷል፡፡
የአቪዬሽን ደኅንነትን በበላይነት የመምራት፣ ብሔራዊ የመታወቂያ ካርድ የመስጠት ሥራን በበላይነት የመምራት፣ እንዲሁም ለግል ጥበቃ ድርጅቶችና ሠራተኞች የማረጋገጫ ሠርተፊኬት የመስጠት ኃላፊነቶች ተሰጥተውታል፡፡
የተቋሙ የደኅንነት ሠራተኛ ኃላፊነቱን በአግባቡ በሚወጣበት ወቅት በነበሩ አስገዳጅ ሁኔታዎች ለሚወስደው ዕርምጃ በወንጀልም ሆነ በፍትሐ ብሔር ወንጀል እንደማይጠየቅ ረቂቁ ያስረዳል፡፡
የደኅንነት ሠራተኞች በሥራ ላይም ሆነ ከተሰናበቱ በኋላ በሥራ አጋጣሚ የሚያውቋቸውን ሚስጥሮች የመጠበቅ ግዴታ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ማንኛውም ሰው በተቋሙ መረጃ ተጠይቆና ሰጥቶ ስለመሆኑ በቸልተኝነት እንኳን ለሌሎች ቢያሳውቅ በወንጀል እንደሚጠየቅ ረቂቅ አዋጁ ይገልጻል፡፡
በተጨማሪም የተቋሙ ሠራተኛ ያልሆነ ግለሰብ በተቋሙ፣ በኃላፊው ወይም በደኅንነት ሠራተኞች ስም በቃል ወይም በድርጊት ለማታለልና ለማስመሰል የሞከረና የተቋሙን ተግባር ያወከ ግለሰብ፣ በወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች እንደሚቀጣ በረቂቁ ተካቷል፡፡ ረቂቁ ለዝርዝር ዕይታ ለሕግና ፍትሕ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዋናነት ተመርቷል፡፡ 

ሰበር ዜና

የሰሜን ጎንደር የአንድነት ሰብሳቢ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው
——————————————————
የሰሜን ጎንደር የአንደነት አመራሮችን ማሰር ቀጥሏል ዛሬ ዞኑ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ አለላቸው አታለለ ህገወጥ እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የክልሉ መንግስት በሚፈፅመው ህገወጥ እስርና እንግልት አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን እንደማያስሰርዘው ገልጧል፡፡
አንድነት በጎንደር የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የክልሉ መንግስት የሰሜን ጎንደር አንድነት የፓርቲውን አመራሮች የማሰር ዘመቻ ጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ አቶ አለላቸው አታለለ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡
አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን በመንግስት ህገወጥ እርምጃ እንደማይቀለበስ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከፍተኛ አመራሮቹም በንቅናቄው ላይ ግምባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን የሚመጣውን መስዋዕትነት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡



Total Pageviews

Translate