Jul 26, 2013
Jul 25, 2013
ሰበር ዜና: ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ
በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው ኩታበር ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ያካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ህዝቡ ሰላማዊ እንዲወጣ ኢህአዴግ እያስገደደ መሆኑን ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
የኩታበር ወረዳ ነዋሪ ሰልፍ እንዲወጣ የተደረገው ነገ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠዋት መሆኑም ታውቋል፡፡ በተለይ ሰፊ የማስፈረሳሪያና የቅስቀሳ ስራ እየተካሄደ ያለው በወረዳው ቀበሌ 05፣06 እና 07 መሆኑንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ካድሬዎች ገበሬውን በግድ ከአቅሙ በላይ የዘር ማዳበሪያ ውሰዱ እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከማስከፈላቸው በተጨማሪ ለአልማ(ለአማራ ልማት ማኀበር)፣ለአባይ፣ ለመሬት ግብር እየተባሉ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው እና ነዋሪዎቹ አቅማቸው እንደማይፈቅድ ሲናገሩ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ በመሆኑ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከአካባቢው እየተሰደዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ ማዳበሪያና ዘር አንወስድም ያሉ ገበሬዎችንም መሬታችሁ ይነጠቃል በሚል የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደምሴን ጨምሮ የወረዳው ሹማምንት እያስገደዱ እንደሆነ ነዋሪዎቹ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
ስለጉዳዩ የዝግጅቱ ክፍሉ የወረዳውን አስተዳደር አቶ ደምሴን እና የወረዳውን ግብርና ጽህፈት ቤትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማናገር ጥረት ቢደረግም አልተሳካም፡፡
ምንጭ፣ ፍኖተ ነጻነት
Jul 24, 2013
“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ” ሃይሌ! ወደ ፓርላማ?
የዛሬ 10 ወር የሻለቃ ሃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ፖለቲካ የመምጣት ሁኔታን አስመልክቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሃተታ አቅርቦ ነበር፡፡ (እዚህ ላይ ይመልከቱት) ሰሞኑን አትሌቱ ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጎቱንና “በምርጫ” ለመወዳደር መፈለጉ ብዙ እየተባለበት ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን ላለው ሁኔታ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ሃተታ በድጋሚ አትመነዋል፡፡
“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው።
ሃይሌ ይህንን የተናገረው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ ም ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ጋር በመንግስት ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) አስተያየት በሰጠበት ወቅት ነበር። የቀድሞውን ስርዓትና ትውልድ “ድንጋይ ዳቦ በነበረበት፣ ፍራፍሬ ከጫካ ያለምንም ድካም ከሚሰበሰብበት” ዘመን ጋር ያወዳደረው ሃይሌ፣ “የአሁኑ ትውልድ” በማለት ያሞካሸውን ስርዓት ከተፈጥሮ ጋር ጦርነት በማካሄድ ለውጥ ማስመዝገበ መቻላቸውን አስምሮበታል።
“የባለ ራዕዩ መሪ” አቶ መለስ ገድል ለመዘከር በተዘጋጀ ቅንብር ላይ በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጥ የታየው ሃይሌ “አሁን የት ነው ያለነው?” በማለት ጠይቆ “አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ለማግኘት ነው የምንጋፋው? አውሮፓ ሄደን እዛው ለመቅረት ነው…” በማለት ስደትን መርጠው ከአገራቸው የሚወጡትን ሸርድዶ አልፏል። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ለስደት የሚዳርግ ጉዳይ የለም ወደ ማለት አዝምሞ ተናግሯል። ሃይሌ ይህን ይበል እንጂ በተቃራኒው እስረኞች እንዲፈቱና የፖለቲካ እርቅ እንዲሰፍን እሰራለሁ ከሚሉት ፕሮፌሰር ይስሃቅ ጋር በሽምግልና እያገለገለ መሆኑ በአገሪቱ ውስጥ የሚታው እስርና እንግልት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቅሱ አስተያየት ሰጪዎች የሃይሌን አስተያየት “ለንብረት ዋስትና የሚከፈል የንግግር ቫት” በማለት አጣጥለውታል።
ከኤርትራ ጋር ከተደረገው በቀር በኢትዮጵያ ይህ ነው የሚባል ጦርነት እንዳልተካሔደ ኢህአዴግን የሰላም አባት አስመስሎ ሃይሌ አመልክቷል። በዚሁም ምክንያት ቀደም ሲል ለጦርነት ይውል የነበረው የአገሪቱ በጀት ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ዞሯል ብሏል። የኢህአዴግ ተወካይ መስሎ አስተያየት የሰጠው ሃይሌ “ይህ አሁን የታየው ለውጥ በአስርና አስራ አንድ ዓመት ውስጥ የታየ ነው። አሁን ባለው አካሄድ ከአስር ዓመት በኋላ እንደርሳለን?” ሲል የራሱን ትንቢት አስቀምጧል።
ተቆራርጦ በሚቀርበው አስተያየት እነ ፕሮፌሰር እንድሪያስን በማጀብ ሃይሌ በመዝገበ ቃላት ላይ ኢትዮጵያን “ረሃብ” በማለት የሚተረጉማት ቃል እንደሚቀየር በልበ ሙሉነት ተናግሯል። “ከሃያ ዓመት በኋላ” አለ ሃይሌ “በመዝገበ ቃላት ላይ የኢትዮጵያ ውርስ ትርጉም ሃብታም በሚል ይቀየራል” ብሏል።
“ድሮ ትረዱን ነበር፤ እናመሰግናለን። አሁን ደግሞ እንረዳችሀዋለን እንላቸዋለን” ሲል አውሮፓና አሜሪካን የመሳሰሉ ታላላቅ አገሮች የኢትዮጵያን እጅ እንደሚናፍቁ ሃይሌ ከምኞት ባለፈ ስሜት ውስጥ ሆኖ ተናግሯል። አገሪቱን ለሃያ አንድ ዓመታት ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ ባልገለጹበት ሁኔታ ሃይሌ ከአስር እስከ ሃያ ዓመት ኢትዮጵያ ሃብታም አገር እንደምትሆን መናገሩ ከምን የመነጨ እንደሆነ ሊገባቸው እንዳልቻለ ብዙዎች እየገለጹ ነው።
“ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል” ሲል ኢህአዴግን የመከረው ሃይሌ የበታች ባለስልጣናት መንግስትን እንዳያሰድቡ መክሯል። “መንግስት ይህንን አድርጉ ላይል ይችላል” የሚለው ሃይሌ የበታች ባለስልጣኖች የሚፈጽሙት ሙስና “መንግስትን ያስወቅሰዋል” በሚል ተቆርቋሪነቱን በይፋ አስታውቋል። ዋናዎቹን የሙስና ተዋናዮች ነጻ በማውጣት የታች ባለስልጣኖችን “እያንገዋለለ” አሳጥቷቸዋል።
“… ለህሊናቸው ሲሉ እንደ መንግስት በማሰብ መስራት አለባቸው” ሲል ትዕዛዝ አዘል ምክርና ማሳሰቢያ ለበታች ባለስልጣናት ያስተላለፈው ሃይሌ የአስተያየቱ መነሻ ከኢህአዴግ ጋር የፈጠረው ዝምድና ውጤት እንደሆነ እየተነገረ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ “ሃይሌ ሃብቱ እየበዛ ሲሄድና የተበደረው ገንዘብ ሲጨምር ኢህአዴግን ወክሎ መናገር ጀመረ” ብለዋል።
አትሌቶችን ሰብስቦ የአቶ መለሰን ሃዘን ሳግ በያዘው ድምጽ እያለቀሰ የገለጸው ሃይሌ ነፍሳቸውን ይማረውና በአቶ መለስ አይወደድም ነበር። በህይወት እያሉም በተደጋጋሚ ያናንቁት ነበር። ሃይሌን እንደሚያደንቁት ተጠይቀው አርቲስት ቻቺን በማሞገስ ጭራሹኑ እንደማያወቁት ዘለውት አልፈውት ነበር። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት ለሃይሌ ቁብ እንደሌላቸው የሚያውቀው ሃይሌ ከአንድ ማስታወቂያ ሰራተኛ ልቆ በፕሮፓጋንዳ ተግባር ላይ መሰማራቱ በቅርብ ጓደኞቹና በአድናቂዎቹ ዘንድ መነጋገሪያ አድርጎታል።
በአዳማው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ በመገኘት ውድ ሽልማቱን ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በማበርከት የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ የታየው ሃይሌ፤ በዚያው ጉባኤ ላይ አቶ መለስንና ኢህአዴግን ማሞገሱ በወቅቱ በርካታ አስተያየት እንዲሰነዘርበት ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም። የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ ያነጋገራቸው እንዳሉት ሃይሌ ወደ ፖለቲካው መንደር በፍጥነት እየተንደረደረ መሆኑን በማስረዳት የሚያውቁትንም ተናግረዋል።
ጣና ሃይቅ ዳርቻ ከልማት ባንክ በአርባ ሚሊዮን ብር የገዛውን ሆቴል ከሁለት ወር በኋላ ሼኽ መሃመድ አላሙዲ በትዕዛዝ እንደነጠቁት በታላቅ ቅሬታ ለህዝብ አስታውቆ የነበረው ሃይሌ የባህር ዳርን ቤተ መንግስት የመጠቅለል ታላቅ ፍላጎት እንዳለው ነው የቅርብ ወዳጁ ለመረጃ አቀባያችንየተናገሩት።
በኦሜድላ ስፖርት ክለብ ውስጥ ሰራተኛ የነበሩትና ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሃይሌ ቅርብ ሰው “ሃይሌ ቤተመንግስትን ይወዳል። ኢትዮጵያንም የመምራት ህልም አለው” በማለት ጭራሽ ተሰምቶ በማያውቀው ጉዳይ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
የአማራ ክልል መንግስት ለሲድኒ ኦሊምፒክ ጀግኖች ግብዣ ባደረገበት ወቅት የባህር ዳር ቤተ መንግስት ጎብኝተው እንደነበር አስተያየት ሰጪው ያስታውሳሉ። ሃይሌ የጃንሆይን መኝታ ክፍል ከተመለከተ በኋላ አሰበ። ከአፍታ በኋላ አልጋቸው ላይ ተቀመጠ። አልጋውን ወደ ላይ ወደታች ካወዛወዘው በኋላ “… ይህንን ቤተ መንግስት…” በማለት እንደሚኖርበት መዛቱን አስታውሰው ተናግረዋል።
ሃይሌ ዝም ብሎ እንደማይናገር ያወሱት እኚሁ በቅርብ የሚያውቁት ሰው ሃይሌ ይህንኑ ህልሙን ተግባራዊ ለማድረግ ዘመቻ የጀመረ እንደሚመስላቸው አስታውቀዋል። በቀጣዩ 2005 ምርጫ ሃይሌ እንደሚሳተፍ በርግጠኛነት ተናግረዋል። ሃይሌ ሁለት ጊዜ በግል ፓርላማ ለመግባት እንደሚወዳደር ካስታወቀ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ራሱን ከምርጫ ዘመቻ ማግለሉን መግለጹ ይታዋሳል።
ሃይሌ ፖለቲከኛ የመሆን የኖረ ህልም እንዳለው ያወሱት ባልደረባው ከተናገሩት በተቃራኒ ሃይሌ የፈለገውን መሆንና ማድረግ የግል ውሳኔው እንደሆነ የሚከራከሩለት አልጠፉም። ሃይሌ ሃብት አለው፣ ከፍተኛ ዝና ገንብቷል። ኢትዮጵያዊያን የማይረዱት እውቅናና ክብር በውጪው ዓለም እንዳለው የሚገልጹት ተከራካሪዎች “አንድ ሰው በተናገረ ቁጥር ለንግግሩ ቀንድና ጭራ መቀጠል ነውር ነው። ሰዎች የመሰላቸውን እንዳይናገሩም የሚገድብ ክፉ ልምድ ነው” ባይ ናቸው። “አያይዘውም ሃይሌ የኢህአዴግ አባል ቢሆን እንኳ አስገራሚ አይሆንም” በማለት ጠርዝ ደርሰው ይሟገታሉ።
በርካታ አትሌቶች የኦህዴድ አባላት እንደሆኑ የሚጠቁሙት እነዚህ የሃይሌ ተከራካሪዎች “ሃይሌ ኢህአዴግን ቢቀላቀል መነጋገሪያ የሚሆነው ጉዳይ ብአዴን ወይስ ኦህዴድ ይሆናል የሚለው ነው” ብለዋል። አርሲ የተወለደው ሃይሌ በሩጫ ከተሳካለት በኋላ በተለያዩ ጉዳዮችና መጠነኛ ግንባታ ወደ ባህር ዳር መጠጋጋቱ በትውልድ አካባቢው ተወላጆች ቅሬታ እንዳስነሳበት በተለያዩ ጊዚያቶች መዘገቡ የሚታወስ ነው።
የፓርላማው ውይይት መታፈኑን በይፋ ያጋለጠው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ከሥራ ተባረረ
(በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊነት” በሚል ጥቅምት 23 ቀን
2005 ዓ.ም ያደረገውን ውይይት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኩል ተቆራርጦና ተዛብቶ እንዲተላለፍ
ተደርጓል በሚል አንድ ዜና መዘገቡ ይታወሳል።
ይህን ዜና በሰንደቅ ጋዜጣ የህዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን
ተወቀሰ” በሚል ርዕስ ከቀረበ በኋላ፤ በዚህ ዘገባ ላይ ተመድቦ የሠራው የቀድሞ የኢቲቪ ባልደረባ ጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻ ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ለዝግጅት ክፍላችን ምላሹን ሰጥቷል።
ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ
(ፎቶ ከሰንደቅ ጋዜጣ)
እነዚህ ዘገባዎች ከተስተናገዱ በኋላ፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ለሰንደቅ ጋዜጣ መረጃ እንደሰጠና ሚስጢር እንዳወጣ
ተቆጥሮ የዲስፒሊን ክስ ቀርቦበታል። ኢ.ሬ.ቲ.ድ በዲስፒሊን ክሱ ላይ አራት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በምስክርነት
ዘርዝሮ አቅርቧል። የድርጅቱ የዲስፒሊን ኮሚቴ በከሳሽ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና በጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻ መካከል የክስ ዝርዝር እና የመልስ መልስ ደብዳቤዎች ሲያዳምጥ ከሰነበተ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም
በቁጥር ቴ02.1/131-304/02/8/ በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ከግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ
ከሥራ የሚያሰናብተውን ቅጣት አሳልፏል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለቤትነት በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ
ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደው ስብሰባ በመልካም
አስተዳደር፣ በተጠያቂነት፣ በሙስና ችግሮችና በመሳሰሉት ላይ ልዩ
ትኩረት በመስጠት የተካሄደ ሲሆን በዚህ ውይይት ላይ የኢፌዲሪ
ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣
በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ
ፀሐዬ፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ የእምባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ወ/ሮ
ፎዚያ አሚን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን
ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ምክትል
ከንቲባ አቶ አበባው ስጦታው እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች
ተገኝተው ነበር።
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጠራውና የአስፈፃሚ አካላትና
የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናን በተመለከተ የተደረገው ውይይት፣
በዕለቱ በሥፍራው ባልነበረ ጋዜጠኛ ተገቢ ባልሆነ መልኩ
ተቆራርጦና ተዛብቶ ለሕዝብ መቅረቡ ትክክል እንዳልነበረ በይፋ
በመግለፁ ምክንያት ከሥራ የተሰናበተው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻን ስለሁኔታው ፋኑኤል ክንፉ አነጋግሮታል።
ሰንደቅ፡- የዚህ ዜና መነሻ አንተን አድርገው ለመውሰድ ያስቻላቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህን ምላሽ መስጠት የሚችሉት እነሱ ናቸው። በሰጡኝ የክስ ዝርዝር ላይ ግን ሌላ ምክንያት ነው
ያስቀመጡት። ወይም ደግሞ ላነሳኸው ጥያቄ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችለው የዚህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ብቻ ነው።
ሰንደቅ፡- እንዴት?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” ለሚለው ዜና መነሻ
ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በእኔ በኩል ያልኩትም አንዳች ነገር የለም። እንደማንም አንባቢ ይህ ዜና በሰንደቅ
ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ነው የተመለከትኩት። ስለዚህም መረጃ ከእኔ አግኝታችሁ ከሆነ አግኝተናል፤ ካላገኛችሁ አላገኘንም
ለሚለው ምላሽ መስጠት የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ይመስለኛል።
ሰንደቅ፡- በርግጥ የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ለዚህ ዜና መነሻ መረጃውን ያገኘው ከሌላ ሶስተኛ ወገን መሆኑን
ማረጋገጥ እንችላለን። ሆኖም ግን ይህ ዜና በወጣ በሳምንቱ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም. እርሶ ለሰንደቅ ጋዜጣ
ማስተባበያ መስጠትዎ የሚታወስ ነው። በወቅቱ ከዜናው ጋር በተያያዘ ለምን ማስተባበል ፈለጉ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት ያዘጋጀውን ፕሮግራም የቀረጽኩት እኔ በመሆኔ ነበር። በሰንደቅ ጋዜጣም የተሰራው ዜና “የባለስልጣናት ድምጽ
ታፈነ” የሚል በመሆኑም ጭምር ነው። ከዚህ አንፃር እንደአንድ ጋዜጠኛ ውይይቱን አፈነ ተብሎ መወንጀል በጣም
አደገኛ ነው። እንዲሁም ማንስ አፈነው? እንዴት ታፈነ? ለሚሉት ጥያቄዎችም ምላሽ የሚፈልጉ መሆናቸው ግልፅ
የሆነ ነገር ነው። በተለይ በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ኃላፊነት ታሳቢ
ስታደርግ በእኔ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ድንጋጤ መገመት ከባድ አይደለም። የእነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት
አንደበትን ለማፈን በእኔ በተራ ረዳት አዘጋጅ ቀርቶ በሌላው የተቋሙ ከፍተኛ አመራር የሚሞከር ተግባር ተደርጎ
የሚወስድ አካል ያለ አይመስለኝም።
ይህ ችግር ከተፈጠረ በኋላም ከስራ ባልደረቦቼ ጋር ተወያይቻለሁ። እንዲሁም አንድ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር
ለማግኘት ጥረት ባደርግም አልተሳካልኝም። የሆኖ ሆኖ ከባልደረቦቼ ጋር ከመከርኩ በኋላ ፕሮግራሙ ታፍኗል ብሎ
ለዘገበው ጋዜጣ ማስተባበያ በመስጠት እራሴን ከጉዳዩ ነፃ ማድረግ እንዳለብኝ ተማምነናል። የመንግስት ከፍተኛ
ባለስልጣናቱም እኔ አለማድረጌን ሊገነዘቡ የሚችሉት ፕሮግራሙ ታፍኗል የሚለውን ዜና ባሰራጫው ሚዲያ መሆኑ
አሻሚ አይደለም። ስለዚህም በዚህ ጉዳይ ላይ ንፁህ መሆኔን ለማረጋገጥ ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በጉዳዩ ላይ
ያለኝን መረጃ ለመስጠት ተገድጃለሁ።
ሰንደቅ፡-እርሶ እንደዚህ ቢሉም፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ታህሳስ 01 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ
ደብዳቤ የዲስፕሊን ኮሚቴው “አቶ አዲሱ መሸሻ በየነ በፕሮግራሙ ኢ.ሬ.ቴ.ድ የባለስልጣኖች ድምጽ አፍኗል።
ፕሮግራሙ ቆራርጧል የሚል የተሳሳተና ከኃላፊነት የራቀ እና በሀሰት የተሞላ መግለጫ ለሰንደቅ ጋዜጣ” ሰጥቷል ሲል
ይከሳል። በዚህ ላይ የእርሷ አስተያየት ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት የኢ.ሬ.ቴ.ድ “የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ”
ያለው ሰንደቅ ጋዜጣ እንጂ እኔ አዲሱ አይደለሁም። በወቅቱም በሰጠሁት ማስተባበያ ተቋሙን በተመለከተ ያልኩት
አንዳች ነገር የለም። የማፈን ነገር ተፈጽሟል ከተባለም ግለሰቡ እንጂ ተቋሙ ሊሆን አይገባም በማለት ነበር ተቋሙን
የተከላከልኩት። በሌሎችም ተቋማት ግለሰቦች ከተቋሙ ዓላማ በመውጣት የሚፈጽሙት ስህተት በእኛም ተቋም
በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጽሟል። ይህ ማለት ግን ግለሰቦች ከተቋም በላይ ናቸው ማለት አይደለም። ስለዚህም ግለሰቦች
በሰሩት ጥፋት በግል መጠየቅ አለባቸው እንጂ በተቋም ደረጃ ስህተቱ ሊታይ አይገባም። ስለዚህም አንድ ሰው በራሱ
መነሻ በፈጸመው ተግባር የተቋም አድርጎ መውሰድ ከሕግም ከሞራልም አንፃር የሚያስኬድ አይመስለኝም።
ሰንደቅ፡- የተከሰስክበት የደብዳቤ ይዘት ሚስጥር በማውጣት የሚል ነው። የሰጠኸው ማስተባበያ ከሚስጥር መጠበቅ
ጋር እንዴት ትገልፀዋለህ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ሚስጥር ማባከን ከመጥፎ ፍላጎት (intention) የሚመነጭ ነው። ሚስጥር
የሚባክነው ተቋምን ወይም ግለሰብን ለማጥቃት ከመፈለግ የሚመጣ ክፉ መንፈስ ነው። ከዚህ አንፃር ስትወስደው፣
እኔ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የሰራሁትን ፕሮግራም የሚመለከት ዜና በመሰራቱ ብቻ ማስተባበያ ሰጠው እንጂ ምን
አጠፈሁ። ከእኔ ጋር ተያያዥነት ያለው ዜና ባይወጣ እኔም ባልተናገርኩ፤ እነሱም ክስ ያሉት ክስ ባልመሰረቱብኝ ነበር።
ስለዚህም የጋዜጠኝነት ሙያዬን (integrity) በሚያጠፉ “አፋኝ” ተብሎ በተሰየመ ሁኔታ ስሜ ጠፍቶ፣ ስሜን
ለመመለስ መከላከሌ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ከሚስጥር ማባከን ከመጠበቅ ጋር ምን ያገናኘዋል?
ሁለተኛው፣ “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የተካሄደው ውይይት ዋናው ዓላማው፣ ውይይቱ ለሕዝብ እንዲቀርብ ነበር። ተደራሽነቱም ለሕዝቡ ነው። ለሕዝቡም
ግልፅ መረጃ ለማቅረብ የተዘጋጀ ውይይት ነበር። ከሁሉ በላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው የስብሰባ ይዘት፣
የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ በዚህች ሀገር ውስጥ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ ለሕዝብ ማሳየት ነበር። ሕዝቡም አደጋውን
በመረዳት ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግንዛቤ ለማስጨበት ያለመ ስብሰባ ነበር። ይህ ታዲያ
ምን ሚስጥር አለው? ሚስጥር ከሆነ መጀመሪያውኑ ሚዲያውን አይጋብዙም ነበር። በወቅቱም ፕሮግራሙ ሲቀረጽም
ሚስጥር ነው ያለ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አልነበረም።
ሌላው በዚህ ተቋም ውስጥ በቆየሁበት የስራ ዘርፎች ሚስጥር ተብለው የሚቀረፁ ስራዎችን ጠንቅቄ አውቃለሁ።
በሚስጥር ደረጃ የተቀረፁ ስራዎችንም ሰርቼ አውቃለሁ። በዚህ ደረጃ የሰራኋቸውን ስራዎች እንኳን ለሶስተኛ ወገን፣
በተቋሙ ውስጥ ማወቅ ከሚገባቸው ሰዎች ውጪ ዉይይት አድርጌም አላውቅም። አለቆቼም ይህን ጠንቅቀው
ያውቁታል።
ሰንደቅ፡- የዲሲፕሊን ኮሚቴው እንደሚለው ከሆነ “በስሜት ያደረኩት ነው” ሲሉ አቶ አዲሱ በኢዲቶሪያል ስብሰባ
ላይ ገልጸዋል ይላል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በነገራችን ላይ የነበረው ኢዲቶሪያል ስብሰባ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ብዙ ርቆ የሄደ ነው። ግልፅ
የፖሊስ ምርመራ ነበር የተደረገብኝ። አስራ አራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባሉበት የተደረገ ስብሰባ ሲሆን አውጣ፣
አታውጣ የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ። እኔ ለማስፈራራት፣ ለማሸማቀቅ የተደረገ ኢዲቶሪያል ስብሰባ ነበር። የቀረበብኝ
ውንጀላ እስከሀገር ክህደት የሚደርስ መሆኑ ነበር የተነገረኝ። የፖለቲካ ይዘት ፈጥረውለት እኔ አንገት ለማስደፋት
በአደባባይ ውጣና ማስተባበያ ስጥ ብለውኛል። የሚገርመው እኔ ነኝ ፕሮግራሙን የቆረጥኩት ያለው አመራር በዚህ
ስብሰባ ውስጥ አንዱ ወቃሽ ሆኖ የተገኘበት ነበር።
ሰንደቅ፡-በዚህ ስብሳባ ደረሰብኝ የሚሉት ጉዳት አለ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- አለ እንጂ። ከዚህ በፊት የኢዲቶሪያል ስብሳባ የምናደርገው አየር ላይ የዋሉ ፕሮግራሞችን ጠንካራና
ደካማ ጎናቸውን ለመገምገም ነው። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የተደረገው ኢዲቶሪያል ግን መንፈሱን የተለየ ነው። የአንድ
ተቋም ኃላፊዎች ተሰብስበው የፖሊስን ስራ በመተካት ያን ሁሉ ወከባ ማስፈራራት ሲፈጥሩ መመልከት በጣም አሳዛኝ
ተግባር ነው። በእኔ ውስጥ የፈጠረው ስሜት ለረጅም ጊዜ ውስጤን ጎድቶታል። በተለይ የኢ.ሬ.ቴ.ድ ተጠሪነቱ ለህዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ይታወቃል። የምክር ቤቱን ውይይት መቁረጡን በግልፅ መናገሩን ሳይፈራ፣ ለምን እኔን
ውይይቱ ተቆርጧል ብልሃል ብሎ ከስራ ሊያሰናብተኝ እንደፈለገ አልገባኝም።
ሰንደቅ፡-በታህሳስ 01 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው ወጪ በሆነው ደብዳቤ ላይ “ፕሮግራሙን ያዘጋጁት
ባልደረባችን አቶ አዲሱ መሸሻ” የሚል ሲሆን፣ በጥር 20 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው የወጣው ደብዳቤ
በበኩሉ “ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ” ናቸው ይላል። ከዲሲፕሊን ኮሚቴው በዚህ
መልኩ ደብዳቤዎቹ ሊዘጋጁ ቻሉ? ፕሮግራሙን የሰራው ማነው ሊባል ይችላል?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ዲሲፕሊን ኮሚቴው ያወጣው ደብዳቤ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው። ለክሱ እንዲረዳቸው አንድ
ደብዳቤ በእኔ አዘጋጁ። ለመከላከል እንዲረዳቸው ደግሞ ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ
ናቸው የሚል ደብዳቤ አዘጋጅ። ይህ በራሱ የሚነግርህ ነገር አለ። በማኛውም ዋጋ እኔ መክሰስ እና ከስራ ማፈናቀል
ለዲሲፕሊን ኮሚቴው የተሰጠው ተልዕኮ ነው። አቶ ሳሙኤል በወቅቱ ትምህርት ላይ ነበሩ። እንዴትም እንደመጡ
አላውቅም።
እውነቱ ግን ጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅዳሜ ፕሮግራሙን ሰርቼ ሙሉ ዝግጅቱ እሁድ ጥቅምት 25 ቀን
2005 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ዜና በኋላ የሚቀርብ መሆኑ ነው። በዚህ ዕለት የሚተላለፍ መሆኑን የሚገልፅ
ከውይይቱ የተወሰዱ አጫጭር ንግግሮች የሚያሳይ ማስታወቂውን /ስፖት/ የሰራሁትም እኔው እራሴ ነኝ።
ሰንደቅ፡- አሁን በዚህ መልስ በእርሶ ላይ የተወሰደው እርምጃ በሌላው ሰራተኛ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን
ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህ ጥያቄ ከነሳህልኝ በውይይቱ ላይ አንድ የተሰነዘረ ነጥብ ልንገርህ። በዚህ ውይይት ከተሳተፉት
ተሳታፊዎች መካከል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዓሊ ሱሌማን አንዱ ናቸው። እሳቸው
ከገጠማቸው አስቸጋሪ የፀረ-ሙስና ትግል ሲገልፁ፤ “የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚታገሉ እና የሙስና
ተግባራትን የጠቆሙና ያጋለጡ ሰዎች በአለቆቻቸው የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እየተወሰዱባቸው ቤሰቦቻቸው
ተበትነዋል። በዚህም የተነሳ እነዚህ ግለሰቦች ምነው ይህን ባልተናገርኩ እያሉ አንገታቸውን ደፍተው ተሸማቀው
እየሄዱ ነው። እነዚህ ሃይሎች ገነው ወጥተው ለፀረ-ሙስና ትግል የተሰለፉ ኃይሎች ግን አንገታቸውን ደፍተው
ይገኛሉ” ነበር ያሉት።
ሰንደቅ፡- አሁን እርሶ ላይ የደረሰውን ነገር ከዚህ ከአቶ አሊ ሱሌይማን አባባል ጋር እንዴት ያስታርቁታል?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የኮሚሽነሩን አስተያየት በእኔ ላይ መፈጸሙን ስመለከት በጣም አስገርሞኛል። ምክንያቱም
በውይይቱ ላይ ተገኝቼ የቀረጽኩት ውይይቱን ለሕዝብ ለማቅረብ እንጂ፣ በዚህ የውይይት ፕሮግራም መቆራርጥ መነሻ
እና በመልካም አስተዳደር ዕጦት ሰለባ ለመሆን አልነበረም። የሆነው ግን በእውነት አስገራሚ ነው። ከስራ
ተፈናቅያለሁ። ልጆቼን ለጊዜው ለወላጆቼ ሰጥቻለሁ። ባለቤቴን ከፍዬ ነው፤ የማስተምረው። የፓርላማውን ውይይት
በፈለጉት መንገድ የቆረጡት ግን ደረታቸውን ነፍተው ለእኔ የስንብት ደብዳቤ ፅፈው ሰጥተውኛል። ኮሚሽነሩም ያሉት
ከላይ የዘረዘርኳቸውን ሂደቶች ነበር። ለእሳቸው አስተያየት ከእኔ በላይ ማረጋገጫ ማን ሊያቀርብ ይችላል?
እዚህ ላይ ማወቅ ያለብህ በጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ይህን እድል አግኝቼ ለመናገር ቻልኩ እንጂ ስንቶቹ የሆዳቸውን
ይዘው የቢሮክራቶች ሰለባ ሆነው ቁጭ ማለታቸውን መዘንጋት የለብንም።
ሰንደቅ፡- ተጠሪነታችሁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። አሁን ደርሶብኛል የምትለውን የመልካም አስተዳደር
ችግር በአካል ሄደህ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል፣ የቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
ያመለከትከው ነገር የለም?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ የወሰድኩት እርምጃ እራሴን ማረጋጋት ነበር። በዚህ ጉዳይ አንተ ሶስተኛ ወገን ስለሆንክ
እንጂ የተፈጠረው ሁኔታ እጅግ ድፍረት የተሞላበት ነው። መዋሸት የማልፈልገው ከስራ ተሰናብተሃል የሚለውን
ውሳኔ ስሰማ ደንግጫለሁ።
ሰንደቅ፡- ለምን?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠራው ስብሳባ ታማኝ ባለመሆኑ ይቅርታ መጠየቅ
የነበረበት ኢ.ቴ.ሬ.ድ ነው። ይህን የምለው የእኛ ተቋም አስፈፃሚ መስሪያቤት በመሆኑ ተጠሪ ለሆነበት ተቋም በሰራው
ስህተት ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል የሚል እምነት ስለነበረኝ ነው። የሆነው ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት
በአግባቡ አልተስተናገደም የሚል መከራከሪያ ባነሳሁት ግለሰብ ላይ፣ የስራ ስንብት ደብዳቤ ሲሰጥ ምን ሊሰማህ
ይችላል። እንደዚህ ዓይነት ድፍረት የተሞላበት እርምጃ እንዴት ይወስዳሉ ብለህ ትገምታለህ። ስለዚህም ግራና ቀኙን
ለመመልከትና የተፈጠረብኝን ጫና ለመርሳት ወደ ሆነ ቦታ ዞር ማለትን ነበር የመረጥኩት።
ሰንደቅ፡- ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ምን ትጠብቃለህ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ከእኔ ስራ መፈናቀል በላይ አጀንዳ ያለው
ይመስለኛል። ምክንያቱም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ተቋም፣ በምን ምክንያት ውይይቱን ሊቆርጠው
ይችላል? ውይይቱ መቆረጡንም ምክር ቤቱ ያውቃል። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ምክር ቤቱ ውይይቱ እየተቆራረጠ
መቅረቡን እንደሚያውቅ እየታወቀ፣ ለምን የሃሰት መረጃ እንዳቀረብኩ ተቆጥሮ ከስራ ገበታዬ እስናበታለሁ?
የፓርላማው ውይይት በትክክል አለመዘገቡን በመቃወም ምላሽ መስጠቴ ዋጋው ከስራ መሰናበት ከሆነ፣ ከእኔ የስራ
ዋስትና በላይ ፓርላማው ሊመለከተው የሚገባ ጉዳይ ነው። ይህን መሰል ብልሹ የመልካም አስተዳደር ከተለመደ
ተቋሙም ወዴት እየሄደ እንደሆነ ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል።¾
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 411 ሀምሌ 17/2005)

አ.አ በግድግዳ ጽሁፎች (ግራፊቲ) ተሸፍና አደረች
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው እሁድ ምሽት ለሰኞ አጥቢያ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ቦታዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄዎች
በሚያንጸባርቁ ጥቅሶች ተጽፎባቸው አደሩ፡፡ በከተማዋ የተለያዩ መንገዶች፣ የመንገድ አካፋዮች እና አጥሮች ላይ
መንግስት ሕገ መንግሰቱን እንዲያከብርና በእምነት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም የሚጠይቁ ጽሁፎች በትላልቅ ቁመት
ለህዝብ በሚታይ መልኩ ተጽፈው የተገኙ ሲሆን ይህ በተጻፈባቸው ቦታዎችም ሰዎች ሁኔታውን በትኩረትና በግርምት
ሲመለከቱ እንደነበር ታውቋል፡፡
በካዛንቺስ፣
በጦርሀይሎች በውንጌት አስኮ መንገድ እንዲሁም ገና በውል ባልታወቁ ቦታዎች ደምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ ሕገ
መንግስቱ ይከበር፣ ጥያቄያችን ይመለስ፣ በእምነታችን ጣልቃ
ግቡብን የሚሉ ጽሁፎች ተጽፈው የታዩ ሲሆን በካባቢው የሚገኙ የወረዳ አስተዳደሮችም በተፈጠረው ነገር
በመደናገጥ ጽሁፎቹን ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡ የጎዳና እና የግድግዳ ጽሁፎች በአለም የታወቁ የመቃወሚያ
ዘዴዎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ መልእክቱን ለሚመለከተው አካል ለማድረስ የሚጠቀምባቸው ናቸው፡፡
ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎቹን አግባብ ባለው መልኩ ለመንግስት ሲያቀርብ እንደነበር የሚታወቅ
ሲሆን አሁንም በዚህ እርምጃው በመቀጠልና ወደ ሌላ ሂደትም በመሸጋገር መንግስት ለሚወስዳቸው ማንኛውም
እርምጃዎች እጅ እንደማይሰጥ በማሳየት ላይ የሚገኝ መሆኑን ይህ የዛሬ ክስተት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ መንግስት
የሙስሊሙን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ሙስሊሙን በአክራነትና አሸባሪነት በመፈረጅ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ሙስሊሙ
ህብረተሰብ በተገኙት አጋጣሚዎች ሁሉ ድምጹን ለማሰማትና መንግስት ምላሹን እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረቶች
በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ አይነቱስልትም ሆነ በሌሎች ሰላማዊ መንገዶችና የመታገያ ስልቶች የሙስሊሙን ህብረተሰብ ሕጋዊ ጥቄዎች ብቻ
የሚያንጸባርቁና ከትግሉ መንፈስ ያልወጡ መልእክቶች ሊተላለፉበት እንደሚችሉ ይታሰባል፡፡

Jul 23, 2013
የመለስ ፋውንዴሽን ቦርድ ሰበሳቢ የሆኑት ሴትዮ ምን አሉ (yared elias)
እውነት እኮ ነው ሴትየዋ ወ/ሮ አዜብ ምን ነካቸው መለስን በህብረተሰቡ ውስጥ ይበልጥ ለማስተዋወቅ በመጽሃፍ፣ በዶክመንተሪ እና መሰል መንገዶች እንደሚሰራ ተናገሩ።
እንዴ ቆይ ቆይ ሌላ መለስ ዜናዊ አምጥተው ሊያስተዋውቁን ነው ወይስ ያ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ልጆች ላይ ታንክ በማሰማራት በአልሞ ተኳሾች ሕይወታቸው የነጠቀውን ወይም ያስነጠቀውን መለስ አልያስ መጉላላት ስቃይ እስራትና በዘር ላይ የተመሠረተውን ሥርዓታቸውን ያቆየውን መለስ ወይንስ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በከንቱ የስንቱ ወንድማማች ህይወት ደም ያስፈሰሰውን መለስ እንደገና ደግሞስ የበደኖውንና የጋምቤላውን እልቂት ዘር ከዘር እንዲለያይ ያደረገውን መለስ የትኛውን ነው የሚሉት ሴትየዋ ? መቼም አብደው ካልሆነ በስተቀር ስለ መለስ ዜናዊ አስቀያሚ ኢፍትሃዊ አገዛዝ አይደለም 22 ዓመት ሙሉ በውስጡ ኢሳት የሚንቦገቦገው ኢትዮጵያዊ ህዝብ ይቅርና መላው አለም መለስ ምን ሰርቶ እንዳለፈ ያውቃል ።
እሺ የሙስና እናት ከዚህ ሌላ የሚሉት ነገር ይኖር ይሆን ? ሴትየዋ ይህ አባባሏ ምን ያህል ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላትን ንቀት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ይመስለኛል ማን ነው የሷን ወሬ የሚያዳምጠው ምን አለ የሰዉን ቁስል ባትነካካው ህዝቡ የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ የሞተ ሰው አይወቀስም ብሎ መሰለኝ ዝም ያለው የሴትየዋ ንቀት ግን የአቶ መለስን አስክሬን ከመቃብር ውስጥ አውጥቶ በ22 ዓመት ታሪክ ኢትዮጵያ ውስጥ ለደረሰው ህዝብ እልቂት እስራት እንግልት ስደት ዘር ከዘር በመከፋፈል የኑሮ ውጣ ውረድ በዚህ ሁሉ ነገር ለፍርድ እንዲቀርብ ባለማድረጉ የተናደደች ነው የሚመስለው እውነት እውነት አቶ መለስ በህይወት ቢኖሩ እኮ የኢትዮጵያ እናት እንባ በቁማቸው ነበር የሚጨርሳቸው ምነው እያለቀም ነበር እኮ የመጨረሻ ሰሞን የነበረው ፎቶ ይናገር ነበር እኮ ለመሆኑ ግን ይሄንን ዘነጉት እንዴ እንደወም ተመስገን ማለት የነበረባት እንኳን ከዚህ ሁሉ ጭንቀት አቶ መለስ ተገላገሉ እኔንም እንደሱ የያዘኝ ነገር ቶሎ ይውሰደኝ ብሎ መጸለይ ነው የሚያዋጣው ወየው ለራሴ ማለት አውን ነው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንዳላገጡ አይቀሩም ።
በመጨረሻም እኚው ሴትዮ እንደገና በሙስና የሰረቁት ነገር አልበቃ ብሎሃቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ድጋሚ በግልጽ ሊሰርቁት ይኧው የፈረደበት ፋውንዴሽን ላይ ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ ለመሳተፍ የሚፈልጉ እንዳሉ በማሰብም በ ኤስ ኤም ኤስ መልእክት ከ2 ብር ጀምሮ እስከ 1መቶ ብር ድረስ ወዲ በሉ እንዲሁም ከዚህ በላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ደግሞ በአዲስ አበባና ክልል ከተሞች የባንክ አካውንት በመክፈት እንዲሳተፉ ለማድረግ ታስቧል እያሉ ነው። ግና እንደው ማን ይሙት እርሳቸው ያላቸው ብር ለተባለው ነገር እሃ እሃ እሃ እረስቼው ለካስ አቶ መለስ እራሱ በፔሮል ነበር ብር የሚወስዱት ብለዋል ነበር ሁለት አፍ ሆነው የኢትዮጵያን ህዝብ እንዳያስቀየሙት ግን እኔ ለወይዘሮዋ የምመክራቸው ያው የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ በዚህ 22 ዓመት ውስጥ የነደደው ኢሳት የጠፋ መስሎት ያለ የሌለ ቢዘላብዱ የሚጠቅም ነገር አይኖርም አውንም በዚህ ኢትዮጵያ እናት ውስጥ የሚንቦገቦገው ኢሳት የርሶን አይደለም የግብርሃበርሆን ሁሉ በቁም አቃጥሎ ምን አቃጥሎ ብቻ አሳርሮ ይጨርሳቸዋል ። አሁንም ግን ሞት ለእናንተ እና ለእናንተ ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች ትኑር
yared elias
telemark
(yayazuf@gmail.com)

Jul 21, 2013
ቅዳሜ ‹‹ፋክት›› በተሰኘ መፅሄት ይዋጃል “ተመስገን ደሳለኝ”
ተመስገን ደሳለኝ
‹‹ሲመቸኝ ዝም ብል፣ ዝም ያልኩ መስሎታል፣
ሲታሰብ ነው እንጂ ዝም ማለት የታል፡፡››
ሲታሰብ ነው እንጂ ዝም ማለት የታል፡፡››
እነሆም ይህ የዮፍታሔ ንጉሴ ስንኝ ‹‹የት ጠፋህ?›› ብለው ለተጨነቁልኝ ወዳጅ ዘመድ መላሽ ይሆን ዘንድ ወደድኩ፤
የነገው ቅዳሜ ‹‹ፋክት›› በተሰኘ መፅሄት ይዋጃልና አንባቢያኖቻችን ሆይ ደስታችን ደስታችው ይሁን! ይህ መፅሄት ባለፈው ዓመት ለሶስት ጊዜ ያህል ከታተመ በኋላ በኪሳራ የተዘጋ ነበር፤ አሁን ትንሳኤው ሆኖለት የሚከተሉትን አምደኞች አሰባስቦ ተመልሷል፡፡
1.ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፡-
ሀ/ የመንግስትን ስም ማጥፋት፤ ክቡርነታቸው ናቸው መንግስት?
ለ/ ምንም ይሁን ምን፣ የትም ይሁን የት አበሻ መናገር ይወዳል
(ሁለት የተለያየ ፅሁፍ)
ለ/ ምንም ይሁን ምን፣ የትም ይሁን የት አበሻ መናገር ይወዳል
(ሁለት የተለያየ ፅሁፍ)
2.ተመስገን ደሳለኝ፡-
ሀ/ ብርቱው ሰው! /The Iron Man/
ለ/ ኢህአፓና የገሀነም ቅፅሩ!
(ሁለት የተለያየ ፅሁፍ)
ለ/ ኢህአፓና የገሀነም ቅፅሩ!
(ሁለት የተለያየ ፅሁፍ)
3.ሙሉነህ አያሌው፡- ለውጥ አለ ወይንስ…?
4.ሐይለመስቀል በሸዋምየለ፡- በብሄርተኛ ልሂቃን የምትታመስ አገር
5.ዳዊት ታደሰ፡- ኡጃማ፡ የብርቱካን መንገድ
6.አቤ ቶኪቻው፡- ሀገራችንን ኢህአዴግ አክራሪነት እንደሚያሰጋት ተሰጋ!
7.ደ/ር በድሉ ወቅጅራ፡- ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል አራት)
8.ብርሃኑ ደቦጭ፡- የመለስ ውርሶችና ለሀልዮት የማይመቸው የኢህአዴግ ተፈጥሮ
9.እንዳለጌታ ከበደ፡- ቆራሌው፡- ነባር ልሂቃንን ፍለጋ
10.ቴውድሮስ ተ/አረጋይ፡- ለጌኛዎቹ ሳር ስጧቸው
እና የተለያዩ ፀሀፊያን ተሳትፈውበታል፡፡ ከዚህ በኋላም ዘውትር ቅዳሜ በየሳምንቱ አንባቢያን እጅ ትደርሳለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ማስታወሻ ለሪፖርተር ጋዜጣ
ሐምሌ አስር ረቡዕ በወጣው ህትመት ላይ ‹‹‹የነፃነት ዋጋ ስንት ነው?› ዥንጉርጉርነት›› በሚል ርዕስ በተለይ ደግሞ ‹‹ያላነበቡ ገምጋሚዎች›› በምትለው ግልገል ርዕስ ስር የተካተተው ሃሳብ ቅንነት የጎደላው ብቻ ሳይሆን ፍፁም በሬ ወለደ መሆኑን ስገልፅ ከጥልቅ ሀዘን ጋር ነው፡፡ በዕለቱ አቶ ግርማ ሰይፉ ‹‹የነፃነት ዋጋ ስንት ነው?›› በሚል ርዕስ ያሳተመው መፅሀፍ የምረቃ ፕሮግራም በውሃ ልማት አዳራሽ መካሄዱ እውነት ቢሆንም እኔ የተገኘሁት የመፅሀፉ ገምጋሚ ተደርጌ እንደሆነ የተገለፀው ግን ውሸት ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ድርሻ ከመፅሀፉ ውጪ ያለውን የግርማን ስራዎችና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መናገር ብቻ መሆኑን አስቀድሜ ከአዘጋጆቹ ጋር ስምምነት ላይ ደርሼአለሁ፡፡ የመድረክ መሪውም መፅሀፉ ትላንት ማታ እንደደረሰኝና እንዳላነበብኩት ተናግሮ ነው ወደ መነጋገሪያው የጋበዘኝ፤ እኔም መፃሀፉ ትላንት ምሽት እንደደረሰኝና ለማንበብ እንዳልቻልኩ ከተናገርኩ በኋላ፤ ምንም እንኳ ከመፅሀፉ ውጪ ባሉ ጉዳዮች ላይ ተናጋሪ ሆኜ ብጋበዝም፣ በቂ ምክንያት ቢኖረኝም ሳለናበው በመምጣቴ እናንተን ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ሆኖ ስላገኘሁት ‹‹ይቅርታ እጠይቃለሁ›› በሚል መግቢያነው ንግግሬን የጀመርኩት፡፡
ታዲያ ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ ሪፖርተር ጋዜጣ ከየት አምጥቶት ይሆን ‹‹ይህንን መፅሀፍ የገመገሙት ዶ/ር ኃይሉ አርዓያና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ናቸው›› ያለው? ስለቀጣዩ ምርጫ ዋጋ ቢስነትም የተናገርኩት መፅሀፉን ጠቅሼ ሳይሆን ከስርዓቱ ጉልበተኝነት ተነስቼ መሆኑንም ሪፖርተር እንዴት ሊሳተው እንደቻለ ግራ አጋቢ ነው፡፡ ‹‹ተቃዋሚዎች ለመሞት እንጂ ለመግደል አልተዘጋጁም›› የሚል ቃል እንዳልወጣኝም በአዳራሹ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ የሚያውቀው ነው፤ (በነገራችን ላይ ይህንን የምለው ከፍርሃት አይደለም፤ ውሸት ስለሆነ ብቻ ነው) እኔ በዕለቱ የተናገርኩት ‹‹ለስርዓት ለውጥ ምርጫን የግድ ጠብቁ የሚል ህግ የለም፤ አገዛዙ ካልተመቸን አደባባይ ወጥተን ቤተ-መንግስቱን ነቅንቀን ለውጥ ማምጣት አለብን፤ ይህ ማንም የማይሰጥን፣ ማንም የማይነሳን መብታችን ነው፤ መልካምነቱ ደግሞ በሰላማዊ ትግል ውስጥ መሞት እንጂ መግደል የለም፤ መታሰር እንጂ ማሰር የለም፤ አካል መጉደል እንጂ አካል ማጉደል የለም፤ መዘረፍ እንጂ መዝረፍ የለም…›› ነው ያልኩት፡፡ ከሁሉም የሚገርመው የጋዜጣው ነጭ ውሸት ‹‹‹በ2006 ዓ.ም ተቃዋሚዎችን ከውጪ ሆነን ከማየት ወጥተን ትግሉን እናፋፍመው› የሚለው ንግግሩ በከፍተኛ ጭብጨባ የታጀበ ነበር፡፡ በማጠናቀቂያ አስተያየቱም ‹መፅሀፉን ባላነበውም ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ እንደነገሩን…› ሲል ሲያጨበጭቡለት የነበሩትን ታዳሚዎች ያሳዘነ ነበር፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎችም ይህንን ቅሬታ ነው የገለፁት›› የሚለው ነው፤ መቼም እነዚህ ሰዎች ኢቲቪ ‹‹አንዳንድ ነዋሪዎች…›› እያለ የሚጠቅሳቸው ስም፣ ፆታ፣ አድራሻ፣ ዜግነት ያሌላቸው፣ እነዛ የማይጨበጡት፣ የማይዳሰሱት፣ የማይናገሩት… ሰዎች ካልሆኑ በቀረ ዕድምተኞቹ የተናገርኩትን በሚገባ ሰምተዋል፡፡
በመጨረሻም ስለማይመቸኝ መከራከሪያ፡-
ሪፖርተር በወቅቱ ያነጋገራቸው ሰዎች ‹‹ተቃዋሚ ነው ወይስ ጋዜጠኛ?›› የሚል ግርምት የሚያጭር ጥያቄ እንዳቀረቡለት ገለጿል፡፡ ይህ ግን ምን ማለት ነው? ጋዜጠኛ ሀገር የለውም፣ የፖለቲካ አቋም የለውም ያለውስ ማን ነው? እሺ! ሌላው ይቅር ይህ ሁሉ የመንግስት እና ‹‹ቅምጥ›› ጋዜጠኛ ‹‹ኢህአዴግ ጌታ ነው›› ሲል መዋሉን ስለምን ሪፖርተርን አላሳሰበውም? ወይስ ጋዜጠኛ የስርዓቱ ደጋፊ ብቻ ነው መሆን የሚችለው የሚል አመክንዮ አለ?
የሆነ ሆኖ አዎ! እኔ ጋዜጠኛ ነኝ፤ አዎ! የስርዓት ለውጥ የሚፈልግ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ነኝ-ሀገሬን እየገዳለት ነውና፤ አዎ! አደባባይ መውጣት ከምርጫም ይሁን ከሌላ በላይ ቅድሚያ እንደሚሰጠው ደጋግሜ እናገራለሁ፤ በ2007 ዓ.ም ለሚደረገው ምርጫም (ምን አልባት ኢህአዴግ በእኛ ድክመት እስካዛ ድርስ ከቆየ ማለቴ ነው) ፕ/ር መርጋ በቃና የሚመራውን ምርጫ ቦርድ ተማምኜ በፍፁም የምርጫ ካርድ አልወስድም፡፡ ምክንያቱም አደባባይ በመውጣት መሬት አርድ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሮ ለውጥ ለማምጣት እንጂ ለመምረጥና ለመጭበርበር አልተዘጋጀውምና፤ በአናቱም እውነት እውነት እላቸኋላሁ ከዚህ በኋላ ታሪክ ለመቀየር ብዙ እንጠብቅም፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
Jul 19, 2013
Ethiopian Australian 15 Years old Obsa shot and killed 13-year-old Fenet Dinku by accident
Mother fears for teenage son held in a distant prison
Caroline Zielinski, TheAge.com.au
When 15-year-old Obsa Paulos Gudina traveled to Ethiopia in January, he expected to spend time reconnecting with his family. Instead, he finds himself in an adult prison facing a long jail sentence for what his mother says was a tragic accident.
Invited by his older sister to stay at her home while he completed a three-month photography course, Obsa, an Australian citizen, was excited to see his birth country again and to spend time with his nephews and nieces. However, just as he was preparing to return to Australia, his holiday went horribly wrong.
On April 16, Obsa and a friend were getting ready for a birthday party while his nieces, nephews and the housekeeper watched television in the main bedroom. Obsa's mother, Tsehai Atomsa, told Fairfax Media through an interpreter that her son had entered the room to search for his phone charger and found a gun in the drawer of a bedside table.
''He just started handling it, playing with it. My son was pointing the gun at the wall … and then, by accident, the gun shot off and hit my granddaughter in the neck,'' Ms Atomsa said through tears at her western suburbs home. Despite being taken immediately to hospital, 13-year-old Fenet Dinku died 45 minutes later.
After Fenet's death, Obsa's family informed the Australian embassy in Addis Ababa that he had been arrested for homicide. Ms Atomsa said that John Newman, the Australian deputy head of mission and counsellor, visited her son every Tuesday.
''My son is getting support from him and food, because there's no good food there,'' she said.
Ms Atomsa said it was impossible to contact her son as access to prisoners in Ethiopia was restricted. ''We have no right to contact him by telephone, either in Ethiopia or from Australia. If I was in Ethiopia, I would be standing behind the fence of the prison trying to speak to him like that.''
Until recently, Ms Atomsa's only contact with Obsa was through Mr Newman's secretary. However, she can now speak to Obsa's lawyer in Ethiopia, Taffesse Gebremedhin.
She said she was very worried about her son as ''in Ethiopia, the legal system is different to here''.
''For example, the right to be represented and considered innocent until proven guilty is not like in Australia,'' she said. ''I appreciate the [Australian government's] help, and they are trying their best. This is not a criminal act, I believe, just an accident.''
Mr Gebremedhin agrees, saying Obsa had no motive to kill his 13-year-old niece.
''He came from Australia to pass the Christmas vacation period with family. He was living in his sister's house the whole time, and they ate dinner, lunch and sat at the same table every day. They were friendly and played together all the time,'' he said.
Mr Gebremedhin said he was sure the witnesses would not testify against Obsa.
''There are four witnesses - the children, the housekeeper and the father, even though he was not there at the time - but I am sure that not one of them will give the testimony that Obsa did it intentionally,'' he said.
''I strongly believe there is no negligence. An accident is an accident in any jurisdiction - it is not a criminal offence.''
Ms Atomsa said her family was deeply concerned about Obsa's wellbeing. ''He has suffered a severe depression and is regretting what happened. We are concerned about him committing suicide,'' she said tearfully.
But Mr Gebremedhin said Obsa's mental and physical health had improved since his mother visited Ethiopia earlier in the year.
''Previously he was in a very bad, overcrowded cell, and he was depressed. But now [since he has been moved to a different cell] his state of mind has improved.''
Obsa was granted a session with the prison counsellor on June 21 after consular officials lodged a request. They have also attended two hearings, on April 23 and May 17, but were denied access to a hearing on April 30.
Fenet's mother, Obsa's older sister, has not been in contact with Ms Atomsa throughout the ordeal. ''She's in Washington DC and we haven't heard from her - no contact by telephone or anything,'' Ms Atomsa said
She said the family had all ''forgiven each other'' and everyone was sure ''it wasn't deliberate, but a terrible accident''.
Obsa is being held in the federal prison in Kaliti after being charged with ordinary homicide, which carries a sentence of five to 20 years' imprisonment.
New Hope Foundation settlement co-ordinator Heidi Zwick said the organisation hoped to raise funds to help Ms Atomsa return for her son's court hearing on July 31.
''We hope to raise money for the flight initially, and then for legal fees,'' she said.
Ms Zwick said the legal fees would be about $10,000, and it would cost almost $2000 for Ms Atomsa - who lives in public housing and is on a disability support payment - to travel to Ethiopia. Other obstacles include her failing health, which is ''deteriorating and has been exacerbated'' by the ordeal.
This is not the first tragedy that Ms Atomsa has suffered. Migrating to Australia as a widow with four children in 2006, she had experienced torture, imprisonment and the loss of her husband and other children in Ethiopia.
In Australia she had to cope with being a single parent while navigating a foreign language and culture and struggling with the mental and physical anguish from torture.
Anyone wishing to donate money to Ms Atomsa can do so via the New Hope Foundation atwww.newhope.asn.au, or on 9510 5877.

Jul 18, 2013
ኢትዮጵያን ለ3 ቀናት የጎበኘው የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብት ልዑካን ቡድን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የተያዙበትን እስርቤት እንዳይጎበኝ ተከለለ ።
ፀረ ሽብር የተባለውን ደንብ ነቅፈናል። አንቀጹ የሚያሻማ፣ ግልጽ ባልሆኑ አንቀጾች የተቀመጠ ነው። ሰዎች በዚህ ሳቢያ ራሥረዋል። ስለሆነም የህግ አውጪው ፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ዘርፍ ፤ ነጻነት በተሃድሶ ለውጥ ሊቀየር ብለን እናስባለን ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች የታሣሪዎች ይዞታ እንዲታይ የሚል አቋም ነው ያለው ።
ኢትዮጵያን ለ3 ቀናት የጎበኘው የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብት ልዑካን ቡድን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የተያዙበትን እስርቤት እንዳይጎበኝ ተከለለ ። ከአዲስ አበባ የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ቡድኑ እስር ቤቱን እንዲጎበኝ ፈቃድ አግኝቶ ነበር ። የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የታሰሩትን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈታ ጠይቋል ። በጀርመን የአረንጓዴ ፓርቲ አባልና የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ወ/ት ባርባራ ሎህቢላር የተመራው ይኽው የልዑካን ቡድን ከትናንት በስተያ እሰከዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ከአፍሪቃ ህብረት ባለሥልጣናት ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፓርላማው አፈ ጉባኤ እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጋር በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ተወያይቷል ። በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ እንዳነጋገረ አለ። በኢትዮጵያ የሚሆነው ነገር ሁሉ በውጭ መንግሥታት ዐይንም ያታያል።
በመሆኑም፤ የአውሮፓ ፓርላማ የሰብአዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ፤ በጀርመናዊቷ ባልደረባቸው ባርብራ ሎህቢለር መሪነት አዲስ አበባ ውስጥ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተነጋግሯል። ሎህቢለር፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በኤኮኖሚ፤ ማኅበራዊ ኑሮ፣ ባህል፣ በተለይ ትምህርትን በመሳሰሉት መሻሻል መታየቱን ተገንዝበናል ነው ያሉት። አዎንታዊ ያልሆነውን ገጽ ስንመረምር ፣ብዙዎቹ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች በተለይ በልማትና ሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ ያተኮሩት ፣ አሳሪ በሆነ ድንጋጌ ፍጹም መሥራት በማይቻልበት ሁኔታ መገፋታቸውን ለመመሥከር ችለናል ብለዋል። ደንቡን ይለውጡት ዘንድ ለባለሥልጣናቱ ነግረናቸዋል። ከሰብአዊ መብት ኮሚሽኑም ጋር ተነጋግረናል። ግን ነጻ መሆኑ አጠያያቂ ነው። ነጻው መገናኛ ብዙኀን፣ችግር እንዳጋጠመው ነው። የመንግሥትን አመራር ዘይቤ ለሚተቹ ጋዜጠኞችም አደጋ አለው። የተለያዩ ሥርጭቶችን ፣ የ DW ን መታፈን ጭምር አንስተን ተነጋግረናል። ፀረ ሽብር የተባለውን ደንብ ነቅፈናል። አንቀጹ የሚያሻማ፣ ግልጽ ባልሆኑ አንቀጾች የተቀመጠ ነው። ሰዎች በዚህ ሳቢያ ራሥረዋል። ስለሆነም የህግ አውጪው ፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ዘርፍ ፤ ነጻነት በተሃድሶ ለውጥ ሊቀየር ብለን እናስባለን ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች የታሣሪዎች ይዞታ እንዲታይ የሚል አቋም ነው ያለው ። እንዲሁም ፍጹም ፍትሃዊ ያልሆነ የፍርድ ቤት ምርመራ ተካሂዶ እሥራት የተበየነባቸው ዜጎችም እንዲለቀቁ መጠየቃቸውን ነው የጠቆሙት ። በውይይቱ ወቅት ባለሥልጣናት ስለ ህገ መንግሥት ባያወሱም አከራካሪው ነጥብ ምን እንደነበረ ባራባራ ሎህቢለር ገልፀዋል
ባርብራ ኦኽቢለር
«ጥያቄው እና የሐሳብ ልዩነት ያለን ከአንዳንድ የህገ-መንግሥቱ አንቀጾች አተረጓጓም(በተግባር የማዋል ጉዳይ ነው ። እነርሱ የመንግሥት ስላልሆኑ ድርጅቶች ሲወሳ ሐቀኛ ነፃ ድርጅቶች አይደሉም ። በህብረተሰቡ ውስጥ አክራሪ አመለካከት ከሚያራምዱ ጋር ግንኙነት ያላቸው በመሆናቸው እንታገላቸዋለን ነው ያሉት ። ከሲብሉ ማህበረሰብ ጋር በዛ ያሉ ስብሰባዎች ማድረግ ችለናል እነርሱም ያደረግነውን ዓይነት ጉብኝት እንድንገፋበትና የኢትዮጵያን ጉዳይ ተመልሰን ለአውሮፓ ህብረትና በአጠቃላይ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እንድናሳውቅ ጠይቀውናል ። » የተቃውሞ ፓርቲ ደጋፊዎች ለሠላማዊ ሠልፍ ሲዘጋጁ የማዋከብ እርምጃ እንደሚወሰድ እንቅፋትም እንደሚያጋጥማቸው ሲናገሩ ተሰምቷል ። ያም ሆኖ በሳምንቱ ማለቂያ ላይ ሰልፋቸውን አካሂደዋል ። ይህ መንግሥት የዴሞክራሲውን በር ገርበብ ማድረጉን የሚያሳይ ወይስ የማስመሰል ተግባር ነው ? ከርስዎ ግንዛቤ በመነሳት ምን ይላሉ ? « የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የሆኑ ሰዎች በራሪ ወረቀቶችን በማሰራጨታቸው አርባው ተይዘው መታሠራቸው ተነግሯል እርግጥ ነው መንግሥት በር ለመክፈት ትንሽ ገርበብ ማድረጉ አዎንታዊ እርምጃ ነው ነገር ግን እንደ ሰብዓዊ መብት ፖለቲከኛ ህጎች የተጣሱበትንና አዎንታዊነት የማይታይባቸውን ሂደቶች ልብ ብለህ ታስተውላለህ። ከዚህ በተጨማሪ ሳልጠቅስ የማላልፈው ጉዳይ ያነጋገርናቸው በሰብዓዊ መብት ዙሪያ የሚሠሩ ሰዎችና ለዚህ መብት የሚታገሉት ወገኖች እንዳሉት ሁኔታው በርግጥ የበር መከፈትን ሳይሆን የበር መዘጋትን ሁኔታ ነው የሚያሳየው ። »
ምዕራባውያን መንግሥታት የልማት እርዳታን ከመልካም አስተዳደር ከፕሬስ ነፃነት ከህግ የበላይነትና ከዴሞክራሲ ጋር ለማቆራኘት ፍላጎት እንዳላቸው ቢገልጹም ተግባራዊ ሲሆን አልታየም ። ፀረ-ሽብር የተሰኘው አዋጅ የመንግሥት ባልሆኑ ድርጅቶች የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር ማድረጉ በፕሬስ ነፃነትም ላይ ብርቱ እርምጃ መወሰዱ እንደቀጠለ መሆኑ ይነገራልና ፣ የጀርመንና የአውሮፓ ህብረት የልማት እርዳታ እንዳለፈው ጊዜ ሁሉ አሁንም ያለ አንዳች ሳንክ ይቀጥላል ይላሉ ? «የኔ ተስፋ ፖለቲከኞቹ ሁሉ በልማት ዘርፍ የሚሰሩትን የሰብዓዊ መብትን ይዞታ ሳያገናዝቡ ተግባራቸውን እንደማያከናውኑ ነው ። የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዲሻሻል አጥብቀው መጠየቅ ይኖርባቸዋል። በትምሕርት በባህልና በመሳሰሉት አስመስጋኝ ተግባር ፈጽመዋል ላሏቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጠቃሚ የሚሰኙ መልዕክቶችን ሳያስተላልፉ አልነበረም የልዑካኑ ቡድን አባላት ውይይታቸውን የደመደሙት ። «መልዕክታችን በተጨማሪ ፀረ ሽብር ህጉን ፣ የፀጥታ ስጋት ያልሆኑ በዛ ያሉ ሂስ አቅርቢ ሰዎችን እየያዛችሁ ለማሰር አታውሉት ። የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች ትርጉም ያለው ሥራ እንዳያከናውኑ የሚገታውን መመሪያ ደንብም አንሱት ። በመጨረሻም የጠየቅነው በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ በማሳየታቸው ብቻ ወይም በአንድ መልክ ወይ በሌላ መንግሥትን በመተቸታቸው የታሰሩትን ሰዎች በነፃ እንዲለቋቸው ነው ።»
ተክሌ የኋላ
Jul 17, 2013
ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!
ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።
አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡
በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
የጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።
በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል ጃዋር ሙሃመድ እና ዘረኝነት
- Sirage De Tango
የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል ጃዋር ሙሃመድ እና ዘረኝነት
ሁለት ዓመት እየያ'ዘ ባለው የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል የዲያስፖራው ድርሻ ቀላል የሚባል' አይደለም ። ሀገር ውስጥ ያለን ሰዎች እንደተከታተልነው እና በአሁኑ ሰዓት እስር ቤት በሚገኙት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግረ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ምስጋና እንደተቸረው ከሆነ በውጭ የሚገኘው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤ/ን አባላት ጳጳሱን ጨምሮ ይሄን እንቅስቃሴ በቀናነት እና በፍፁም ኢትዮጲያዊነት ሲደግፉ ተስተውሏል። ይህም የሆነበት ዋና ምክኒያት የሙስሊሙ ጥያቄ የፍትህ የህግ መንግስት ይከበር ስለነበር ነው። በእርግጥ እነዚህ ጥያቄዎች ተነስተው ንፅሁ ህሊና እና አስተዋይ አዕምሮ ላለው ሰው ከመደገፍ ውጭ ምን አማራጭ አለው?ኢትዮጲያውያንም የደረጉት ይሄንኑ ነው ለዚህም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል። በመቀጠል የጃዋርን ንግግር ከሙስሊሙ ጥያቄ እና ከእስልምና መርህ ጋር ለማየት እንሞክራለን….
#የሙስሊሙ ጥያቄ
ሙስሊሙ ማህበረሰብ አሁን እያደረገ ያለውን ሠላማዊ የመብት ትግል የጀመረው ሁላችንም እንደምናውቀው ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማንገብ ነበር። ለማስታዎስ ያክል
1. የመጂሊሱን(የኢትዮጲያ እስልምን ጉዳዮች ምክር ቤት አመራር) አመራሮች በራሳችን እንምረጥ
2. አወሊያ በቦርድ ይተዳደር
3. አህባሽ የተሰኘ ከእስልምን ውጭ የሆነ አስተሳሰብ በሃይል አይጫንብን።
እነዚህ ጥያቄዎች ሲጠቃለሉ ህገ መንግስቱ ይከበር ወደ ሚል አንድምታ ይወስዱናል በእርግጥ በኋላ ላይ ሌሎች ጥያቄዎች ቢመጡም ልክ የታሰሩትይፈቱ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ ሁሉም ነገር የሀገሪቱ የህግ የበላይየሆነው ህገ መንግስት ይከበር ከሚል አያልፍም ።
#ስለጃዋር
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጃዋር ያለው ነገር ሳይሆን የሚያሳስበው ስንትጃዋሮች አሉ የሚለው ነው የሚያስጨንቀን ሲል ጽፏል።
እኔ ደግሞ እውን ጃዋር የኢትዮጲያ ሙስሊሞችን እና ኦሮሞዎችን ይወክላልን እላለሁ? ወንድም ፋሲል በመላምት ደረጃም ቢሆን ኦሮሞን ጠቅልሎ የጃዋር ሃሳብ አቀንቃኝ አድርጎ የማሰብ ነገር ይታያል(ቢሆን እንኳ ስሌት ይጠቀማል )ይሄ ደግሞ ጨርሶ ስህትት ነው ምክኒያቱም የኦሮሞ ህዝብ የጃዋርን ሃሳብ ከጥንቱም አይደግፍው ቢደግፈው ሃሳቡ እንዲህ ባልተንኮታኮተ ነበር።
ወደ ጥያቄየ መልስ ስመጣ ጃዋር ሙስሊሙንም ሆነ ኦሮሞውን አይወክልም ባይ ነኝ። እንደ አንድ ግለሰብ የመሰለውን ተናግሯል ። መብቱ ነው። እኛም ተው ይሄ ሃሳብ ትክክል አይደላም እንላለን ። ታዲያሀገር ሲፈርስ ዝም እንበል እንዴ!?
ይህ ሲባል ግን ጃዋር ለሙስሊሙ ትግል አስተዋጽኦ አላበረከተም ማለቴ አይደለም ብዙ ነገር አድርጓል እናመሰግናለን ደግሞ መታወቅ ያለበት ጃዋር ወይም ሙስሊሙ ዲያስፖራ ብቻ አይደለም እየታገለ ያለው ከነ ታማኝ ጀምሮ ሁሉም የኢሳት ጋዜጠኞች እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውያን ዲያስፖራ ተሳትፈዋል ለምን ህገ መንግስት ይከበር ስለነበረ ጥያቄው።
አሁን አሁን ጃዋር ጥያቄውን ጠቅልሎ ወዴት እየወሰደው ነው ያስብላል እንዲህም ይላል “የኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር የሙስሊሙ መብት መከበርነው” ምክኒያቱም አብዛኛው ሙስሊም ኦሮሞ ስለሆነ እንቀጥል….
የኦሮሞ ትግል Vs የሙስሊሙ ትግል
እዚህ ላይ ስለ ኦሮሞ ትግል ብዙ ማለት አልፈልግም ግን ትግላቸው እነ ጃዋርም ሆኑ ሌሎች የኦሮሞ ታጋዮች ለፍትህ ለዴሞክራሲ እና ለህግ የበላይነት ከሆነ አዎ ከኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል ጋር አንድ ነው። ካልሆነ ጃዋር እንደሚለውን የኦሮሞን የበላይነት ለማረጋገጥ ከሆነ የሙስሊሙ ትግል አላማው እሱ አይደለም እንለዋለን። እዚች ላይ የማዲባ ንግግር ትምጣ ታዋቂው የፀረ አፓርታይድ ታጋይ ማዲባ ማንዴላ እንዲህ ይላሉ “ እኛ የምንታገለው የነጭን የበላይነት አስወግደን የጥቁሩን የበላይነት ለማምጣይ አይደለም፤ እኛ የምንታገለው ነጩም ጥቁሩም በእኩል የሚኖርባት ደቡብ አፍሪካን ለመፍጠር ነው” እኛም እንዲህ እንላለል ‘እኛ የምንታገለው የኦሮሞን እና የሙስሊሙን የበላይነት ለማንገስ ሳይሆን በኢትዮጲያ የህግ የበላይነትን ለማስፈን ነው!”
#ኢትዮጲያችን ወዴት ወዴት
የሰው ልጆች ታሪክ እንደሚያስረዳው የጭቆናና የበደል መዓት አንደኛው በአንደኛው ላይ ሲጭን እንደነበረ ነው። ነጩ በጥቁሩ፤ብዝሃው በዓናሳው፤ካቶሊኩ በፕሮቴስታንቱ(በአውሮፓ የሆነ ነው) ግልባጩም ሰርቷል አጼዎቹ በሙስሊሙ እና በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች (በኛ ሀገር) ይሄ ግን በህዝቦች እና ጨቋኞች በሚከተሉት እምነት ቡራኬ የተሰጠው አልነበረም በትቂት ግለሰቦች እና ለሆዳቸው ባደሩ የእምነቱ መሪዎች እንጂ። እነደዚህ አይነት የታሪክ ጠባሳ ያረፈባቸው የዓለማችን ህዝቦች ችግሩን የፈቱት በእርቅ እና በሰላም እንጂ ታሪኩን እየመዘዙ ለበቀል በመነሳሳት አይደለም። ከእርቅ እና ይቅር ከመባባል የተሻለም ትክክልኛ መንገድ ሊኖር አይችልም ምክኒያቱም በጊዜው የነበሩትን ጨቋኞች በአሁኑ ዘመን አግኝቶ መጠየቅ እና ለፍርድ ማቅረብ ሰለማይቻል። አክቲቪስት ታማኝ በየነ በአንድ ንግግሩ (ሁሉም ማህበረሰብ የትም ሃገር በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተጨቁኗል እኛም ሀገር እንዲሁ በጊዜው ብንኖር እና ብናስተካክለው ደስ ባለን ግን አልሆነም እኛም አልነበርነም )ብሏል ስለዚህ ፍቅር ይሻለናል። የሁለቱም እምነቶች መጽሃፍ ይህንኑ ሃሳብ ያጠናክሩልናል።
ቅዱስ ቁርዓን በምዕራፍ 17፤15 “….Nor can the bearer of a burden bear the burden of another… “ (ተሸካሚም ነፍስ የሌላኛውን ሃጢያት አትሸከምም)
መፅሃፍ ቅዱስ በዘዳግም 24፤16” The fathers shall not be put to death for the children neither shall the children be put to death for the fathers every man shall be put to death for his own sin” (አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ ልጆችም ስለ አባቶች aይገደ..
ለኔ ይሄ ትግላችን ለማደናቀፍ የሚደረግ ጥረት ነውና ድምጻችን ይሰማ (አሚራችን) ተገቢወን መግለጫ መስጠት አለበት ብዬ አምናለው ፡፡ እንተስ??
#የጃዋር ሞሀመድ እብደት "እኔ ባለሁበት 99% ሙስሊም ነው ማንም ሰው ደፍሮ ቀና አይልም #በሜንጫ ነው አንገቱን የምንለው " በአሜሪካ በተደረገ ስብሰባ ላይ ከተናገረው(ሜንጫ የማጭድ ቅርፅ ያለው ረዘም ያለ ባለስለት የቁጥቋጦ መቁረጫ መሳሪያ ነው)
እንደ አባባሉ ከሆነ ሆድ ያባውን ብቅል ነበር የሚያወጣው የጃዋር ነገር ግን ግራ የሚያጋባው አድማጭ እና መድረክ ባገኘ ቁጥር ነው ከውስጡ ደብቆ የኖረውን ለማንም የማይጠቅም መርዘኛ አስተሳሰብ አደባባይ እያወጣ ያለው።የነ ኢሳያስ አፈወርቂና የሟች መለስ ዜናዊ የመንፈስ ልጅ ለመሆን እየተንደረደረ የሚገኘው ጃዋር የጎሳና የዘር ፖለቲካ ኋላቀርና ተቀባይነቱ እጅግ እየደከመ መሆኑን ሲረዳ ብዙ ለውጥ ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ልቡ ሲደግፈው የነበረውን እንዲሁም ዘረኝነት የሌለበትን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተቃኘውን የሙስሊሞች ትግል ላይ ተፈናጦና አቅጣጫውን አስቶ ፀሐይ የጠለቀችበትን የወረደ የፖለቲካ አስተሳሰቡን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለመጫን እይተፍጨረጨረ ይገኛል በስመ መሐል ሰፋሪነት የጃዋርን ደም አፋሳሽ እብደት መታገስ ግብዝነት ነው ብዙሀን ሙስሊሙም ጃዋርን በስማችን አትነግድ ሊለው ግድ ይላል።እኔ በበኩሌ እንደ ጃዋር ያሉ ግልገል መለስ ዜናዊና ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያችንን በደም ለማጨቅየት ሲቋምጡ እያየሁ ዝም አልልም።እውነትም ትምህርት ቀናን እንጅ ጠማማን እንደማያቀና ጃዋር አብይ ምስክር ነው።
- የኮሌጁን መዘጋት የተቃወሙ አባቶች እንደዚህ ቀደሙ ትደበደባላችሁ የሚል ማስፈራሪያ ደረሳቸው - አሁንም ቤተክህነቱ በድህንነቶች እንደተከበበ ነው
ተማሪዎቹ ከኮሌጁ ውጭ ሆነው
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በተቃውሞ ላይ
(ዘ-ሐበሻ) ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ለቀው እንዲወጡና ኮሌጁ ትምህርት ተቋርጦ እንዲዘጋ
ፓትሪያርኩ አቡነ ማቲያስ ማዘዛቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚገኙት የቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች “አቡነ ማቲያስ
ኮሌጁን የመዝጋት ሥልጣን የላቸውም፤ ውሳኔያቸውም ሕገ ወጥ ነው” በሚል ተቃወሙ።በኮሌጁ ላይ የሚሰጡ
ማናቸውም ውሳኔዎች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መሆኑን በመጥቀስ የሲኖዶሱ ዋናፀሐፊ አቡነ ሉቃስ በይፋ
መቃወማቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል።
አቡነ ሉቃስ ፓትርያርኩን በኮሌጁ መዘጋት ዙሪያ በማነጋገር “አቡነ ጳውሎስ ከዚህ የበለጠ ምን አደረጉ?” በሚል
ከአቡነ ጳውሎስ በበለጠ የቤተክርስቲያኗን ቀኖና እንደጣሱ ወቅሰዋቸዋል ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች መንፈሳዊ ኮሌጁን
በራሳቸው ፈቃድ ማዘጋታቸውና ተማሪዎቹንም
እንዲወጡ ማደረጋቸው በሲኖዶሱ የሃሳብ ልዩነት
እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ብለዋል። በአቡነ ገሪማ
የተፈረመውና በአቡነ ማቲያስ ትዕዛዝ የተጻፈው
ይኸው ተማሪዎቹን ከኮሌጁ እንዲወጡ የታዘዘበት
ደብዳቤ የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣
የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣
የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እና የቅድስት
ሥላሴ ሥራ አመራር ቦርድ ደብዳቤው በግልባጭ
እንዲደርሳቸው ሲደረግ የቅዱስ ሲኖዶሱ ጽህፈት ቤት
ግን የደብዳቤው ግልባጭ ውስጥ አለመካተቱ
የተፈጠረውን መከፋፈልና በተለይ በአንድ ብሄር ሥር
የበላይነት የያዙት ወገኖች በማስፈራራት ቤተክርስቲያኗን የራሳቸው ለማድረግ የሚያደርጉትን ሩጫ የሚያሳይ ነው
ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ።
ኢትዮጵያ በሚገኘው ሲኖዶስ ስር ያሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ጳጳስ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት “አሁን
ጉዳዩን እያቀጣጠሉት ያሉት አቡነ ጢሞጢዎስ ናቸው። አቡነ ጢሞጢዎስ ማለት ፓትርያርኩ ውጭ ሃገር እያሉ በሃገር
ቤቱ ሲኖዶስ ይከፈላቸው የነበረውን ደመወዝ ፈርመው በመውሰድ የሚጠቀሙበት ሰው ናቸው። እኚህ ሰው
ከፓትርያርኩ ጋር የቅርብ ወዳጅነት ስላላቸው እንዲመረጡም በአስመራጭነት ውስጥ ገብተው ትልቅ ሥራ ሰርተዋል።
በዚህ በገንዘብ ላይ በተመሠረተ ስር የሰደደ ወዳጅነት የተነሳ የአቡነ ማቲያስን ት ዕዛዝ በማስፈጸም ሌሎች አባቶችን
በማስፈራራትና በአባቶች መካከል ቡድን በመፍጠር በውስጣችን ውስጥ መከፋፈል እንዲኖር አድርገዋል” ሲሉ
ይወቅሳሉ። ዘ-ሐበሻ አቡነ ጢሞጢዎስን አግኝታ ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት ባይሳካም ከቅርብ ምንጮች
እንደሰማነው የአቡነ ጢሞጢዎስ ግሩም በዘር ላይ የተመሠረተ ከመሆኑም በላይ የሌላ ብሔር ተወላጅ የሆኑ አባቶችን
በመግፋት የስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መዘጋትንና የተማሪዎቹን ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀልን ከሕግ ውጭ
አስፈጽመዋል በሚል እየተወቀሱ ነው።
በተለይም በሲኖዶሱ ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው በሚባለው የዘር ሐረግ ውስጥ የሌሉት የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ
ተብለው የተፈረጁት አባቶች ይህን ውሳኔ በመቃወማቸው ወይም ባለመደገፋቸው ሳቢያ እንደከዚህ በፊቱ
ትደበደባላችሁ የሚል ማስፈራሪያ እንደሚደርሳቸው እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋልጠዋል። ከዚህ በፊት አቡነ
ጳውሎስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት አባቶች ቤታቸው ተሰብሮ እንደተደበደቡ በተለያዩ ሚድያዎች ተዘግቦ እንደነበር
የሚያስታውሱት እነዚሁ ምንጮች ይህን በማስታወስ አባቶች እንዲፈሩና አርፈው እንዲቀመጡ ለማድረግ እየተሠራ
ነው ይላሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአቡነ ጳውሎስ ሕልፈት በኋላ አዲሱ ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ለውጥ ያመጣሉ በሚል ተስፋ
የነበራቸው ወገኖች ተስፋ መቁረጥ ጀምረዋል። አሁንም ቤተክህነቱ በደህነንቶች የተከበበ ከመሆኑም በላይ
ቤተክርስቲያኒቷን ከበላይ ሆነው የሚመሯት የሕወሓት ካድሬዎች እንጂ የ እምነት ሰዎች አይደሉም ሲሉ
ትዝብታቸውን የሚገልጹት ምንጮቻችን አባቶች አሁንም በደህንነቶች በብሄራቸውና ባለመደገፋቸው ብቻ
እንደሚገፉና እንደሚዋከቡ ተናግረዋል።
ዘ-ሐበሻ በቅድሥት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዙሪያና በቅዱስ ሲኖዶሱ መከፋፈል ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን
እንዳገኘች ትመለሳለች።

ፖሊስ ማሰሩን የአንድነት አባላትም ወረቀት መበተኑን ገፍተውበታል (ዛሬ የታሰሩት 4 ደረሱ)
(ሰበር ዜና ከፍኖተ ነፃነት) ዛሬ ሐምሌ 9, 2005 ዓ.ም የታሰሩት አባላት 4 ደርሰዋል፡፡
ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የታሰሩ 3 የአንድነት አባላትን ለማስፈታት ወደ ስፍራው የሄደውን
የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የሆነው አዲሱ ካሳሁንን ከታሳሪዎቹ ጋር ቀላቅለውታል፡፡
ከአንድነት አዲስ አበባ ዞን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ
የተሰማሩት አባላት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች በተሳካ ሁኔታ ወረቀት የመበተን
ተልዕኳቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል፡፡ በትላንትናው እለት 42 የአንድነት አባላትና ለአንዱ
ታሳሪ ዋስ ለመሆን የሄደ ግለሰብ መታሰራቸው አይዘነጋም፡:
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረሽብር ህጉ እንዲሻርና በሌላ እንዲቀየር እያሰባሰበ
ስለሚገኘው ፊርማ የሚያብራራ በራሪ ወረቀት በመበተን ላይ የነበሩት ባይሳ ደርሳ፣ አለማየሁ
በቀለ፣ ግርማ ሹቤ የተባሉትን የአንድነት አባላት ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም በፖሊስ ታስረዋል፡፡ የአንድነት
ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቀው በዛሬው ዕለት ሁለት መቶ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት በተለያዩ
የአዲስ አበባ የክፍሎች በራሪወረቀቶችን በመበተን ላይ ናቸው፡፡

Jul 16, 2013
በዋልድባ ገዳም የሚገኝው የሥኳር ፕሮጀክት ነዳጅ ማራገፊያ የመሬት መንሸራተት አጋጠመው ::
(አንድ አድርገን ሐምሌ 8 2005 ዓ.ም)፡-መንግሥት በአምስት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዘመኑ ውስጥ በ32 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ አስር የሥኳር ፋብሪካዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እገነባለሁ ብሎ በእቅድ መያዙ ይታወቃል ፤ መንግሥት ከፍተኛ አትኩሮት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ በኋላ የሥኳር ፕሮጀክቶቹ በሁለተኝነት ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው ፤ ብዙ ዋጋ ያስከፈለው አሁንም እያስከፈለ ካለው የሥኳር ፋብሪካ ውስጥ በዋልድባ ገዳም የሚገነባው አንዱ ነው፡፡ እነዚህን ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚመራው መቀመጫው መሀል ካሳንቺስ ያደረገው በአቶ አባይ ጸሀዬ የሚመራው የስኳር ኮርፖሬሽን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቶቹ አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የዋልድባን የስኳር ፋብሪካ ግንባታን በመቃወም ብዙ መነኮሳት ከበአታቸው በመሰደድ በያሉበት ሆነው ስራውን እየተቃወሙ ይገኛሉ ፤ ፕሮጀክቱን ለመስራት በየጊዜው የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የመጡ ኮንትራክተሮች ውል በመቋጠር እንደገና በመፍታት አሁን ላይ ሶስተኛው ስራ ተቋራጭ ስራው እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
መንግሥት በትላልቅ ፕሮጀክቶች ስራቸው እንዳይተጓጎል ለማድረግ ከየትኛውም ፕሮጀክቶች በተለየ መልኩ ከብሔራዊ ነዳጅ ማከማቻ ጋር የተለየ ውል መያዙን የውስጥ ሰዎች ይገልጻሉ ፤ ለአንድም ቀን ይሁን እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሰሩ መኪናዎችና የተለያዩ በነዳጅ የሚሰሩ መሳሪያዎች ስራቸው እንዳይስተጓጎል በመጀመሪያ ደረጃ በተለየ ምልከታ የነዳጅ ፍላጎታቸው በየጊዜው እንደሚቀርብላቸው ምንጮች ያስረዳሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ከሳምንታት በፊት በዋልድባ ገዳም እየተሰራ ለሚገኝው የሥኳር ልማት ፕሮጀክት አንድ ከነተሳቢው ነዳጅ የጫነ መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ዋልድባ የጫነውን ነዳጅ ለማራገፍ ወደ ቦታው ያመራል ፤ ቦታው ላይም ነዳጅ የጫነው መኪና በጊዜው መድረስ ችሎ ነበር ፤ ነገር ግን ነዳጅ የጫነው መኪና በጊዜው ቢደርስም ነዳጁን ለማራገፍ በሚሞክርበት ጊዜ ከመሬት ስር የተቀበረው ነዳጅ ማራገፊያ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ከዋናው ቦታ መሸሹን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ምክንያትም ነዳጁን የያዘው መኪና በመሬት መንሸራተት ምክንያት ቦታውን ያጣውን ነዳጅ ማከማቻ ወደ ቦታው የመመለስ ስራ እስኪሰራ እና ለመገልበጥ ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ድረስ ለ21 ቀናት በቦታው ላይ መቆሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል ፤ በዋልድባ ከፕሮጀክቶቹ ጋር ተያይዙ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ይገኛሉ ፤ ላስተዋለ አንድም ምልክት በቂ ነበር ላላስተዋለ እንደ ፈርኦን አስራ አንድ ምልክት ቢከታተል ልቡ ደንድኗልና የመጨረሻውን ምልክት እስከሚያይ ድረስ ፤ ባሕረ ኤርትራ ተከፍቶ እስኪውጠው ድረስ ከጥፋት ስራው ሊመለስ አይችልም ፤ መጽሀፉ ‹‹ ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ›› ይላል፡፡
እግዚአብሔር ዋልድባ ገዳምን ይታደግልን፡፡
Jul 15, 2013
ሆድ ያባውን ሰላማዊ ሰለፍ ያወጣዋል (Abe Tokichaw)
ባለፈው ጊዜ አዲስ አበባ በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጎ ነበር፡፡ በሰልፉ ላይም ለገዢው ግንባር ኢህአዴግ ተነግሮታል፡፡ የምጠራጠረው መስማቱን ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ሟች ጠቅላ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲናገሩ እንደሰማነው አንዲት እንስሳ አለች ትልልቅ አይን አላት ግን አታይም ትልልቅ ጆሮ አላት ግን በቅጡ አትሰማም… ብለውን ነበር፡፡ ይቺን የሰማቻቸው ጊዜ የአብዬን ወደ እምዬ ብላቸው ነበር አሉ… እስንስሳዋን ብዙዎቻችን እናውቃታለን… ለደህንነቷ ስንል ስሟን እንዝለለው…
ኢህአዴግዬ ትልልቅ መስሚያ ጆሮዎች ትልልቅ መመልከቻ ኤኖች አሏት ብዙ ጊዜ ግን በቅጡ ስታይ በቅጡ ስትሰማ አላየናትም፡፡ (የኔ እናት… እግዜር ቀላሉን ያደርግልሽ ብዬ ተቆርቋሪነቴን እገልፃለሁ)
ለማንኛውም እንዲህ የመስማት እና የማየት ችግር ያላለበት ሰው እንዲሰማን እና እንዲያየን ደመቅ ብሎ መታየት እና ጮክ ብሎ መጮህ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡
ትላንት በደሴ እና በጎንደር ህዝቡ ደምቆ ታይቷል ጮክ ብሎም ተናግሯል፡፡ አሁንም ኢህአዴግዬ መስማቷን አንጃ… ስለዚህ ዳግም ድምፃችንን ከፍ ማድረግ አለብን ማለት ነው፡፡
አንድነቶች እንደነገሩን በቀጣይም፤ በሃያ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰልፎች ይደረጋሉ፡፡
የሀገሬ ሰው፤ ሆድ ያባውን ሰላማዊ ሰልፍ ያወጣዋል! ኢህአዴግ እስክትሰማን ድረስ ደጋግመን የሆዳችንን ልንነግራት ይገባል ያለ ይመስላል፡፡
ኢህአዴግ ሆይ ስሚ…!
በዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ የኢቲቪ የሀሰት ዘገባ ሲጋለጥ
ከብስራት ወ/ገብርኤል
ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከአራዳ የአንድነት ፓርቲ ጽህፈት የጀመረው የአንድነት ፓርቲ
የጠራው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በፒያሳ አድርጎ መዳረሻውን በሆጤ ስታዲየም በማድረግ ከቀኑ 6 ሰዓት
በሰላም ተጠናቋል፡፡
የህዝቡም ጨዋነት እጅግ የሚያስገርም ሲሆን በሰልፉ ላይ የተገኙት ከደሴ ከተማ፣ ከሐይቅ ከተማ፣ ከኮምቦልቻ
ከተማ እንዲሁም ከወረባቡ እና ኩታበር ወረዳ የመጡ ተሳታፊዎችንም ማግኘት ችለኛል፡፡ በሰልፉ መርሃ ግብር ፍፃሜ
ላይም የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ሰብሳቢ አቶ ብስራት አቢ፣ የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ተፈራ በመጨረሻም በፓርላማ ብቸኛው የህዝብ
ተወካይና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግርማ ሰይፉ ንግግር ካደረጉ በኋላ መርሃ ግብሩ በሰላም
ተጠናቋል፡፡
በመቀጠልም የሰልፉ ተሳታፊዎች የፀረ-ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቀውን ሰነድ ሲፈርሙ መታዘብ ችያለሁ፡፡
በሰልፉ ላይም በግምት ከ50ሺህ ሰው በላይ የተገኘ ሲሆን ከደሴ፣ከኮምቦልቻና ከሐይቅ ከተማ እንዲሁም ከወረባቡ
እና ከኩታበር ወረዳ የመጡ እንደነበሩ አንዳንዶቹን ታዳሚዎች ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጠውልኛል፡፡ የሰልፉ
ታዳሚዎችም ሰላማዊ ሰልፉን ላዘጋጀው አንድነት ፓርቲ ምስጋና እና አድነቆት ሲቸሩም ተመልክቻለሁ፡፡
በሰላም የተጠናቀቀውን ሰለማዊ ሰልፍ ለመዘገብ የመጡ ከሀገር ውስጥ ሚዲያዎች መካከል ፍኖተ ነፃነት
ጋዜጣ፣ኢቴቪ፣ የአማራ ክልል መገናኛ ብዙኃን፣ የፖሊስ ሚዲያ፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ የኢትዮጵያ ዜና
አገልግሎት እና ለጊዜው ከየትኛው ሚዲያ እንደመጡ ያላረጋገጥኳቸው የሀገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞችን ማየት
ችያለሁ፡፡
ይሁን እንጂ ኢቴቪ ሰላማዊ ሰልፉ ከተጠናቀቀ ከ 40 ደቂቃ በኋላ ተመርጠው የተዘጋጁ ግን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ
ያልተገኙ ሰዎችን ሰብስቦ በሰልፉ ላይ የተገኙትም ሆኑ አንድነት ፓርቲ ያላንፀባረቀውን ጥያቄ እንደተንፀባረቀ አድርጎ
ጋዜጠኛው ቃለመጠይቅ ሲያደርግ እጅከፍንጅ በመያዝ እኛም የቀረበውን ቃለመጠይቅ ቀርፀናል፡፡ እኔ እንደሚገባኝ
ከሆነ ኢቴቪ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተንፀባረቀውን የህዝቡን ጥያቄ አንሻፎ በማቅረብ ሌላ የሀሰት ዘጋቢ ፊልም ሊያዘጋጅ
መሆኑ ነው፡፡ ቃለመጠይቁን ጠያቂውንና ተጠያቂውን ምስላቸውን በ”Millions of voices for Freedom”
ዩቲዩብ ላይ ለቀነዋል ተመልከቱ፡፡
በተጨማሪም ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው አቶ ጌታቸው እባላለሁ ያሉን ግለሰብ የኢቴቪ ጋዜጠኛ ያቀረበሎት ጥያቄ
ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተንፀባርቋል ወይ? ስል ላቀረብኩላቸው ጥያቄ መቅረፀ ድምፁን ዝጋውና ካሉ በኋላ እኔ በሰላማዊ
ሰልፉ ላይ አልተገኘሁም የጠየቀኝን ነው የመለስኩት ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በምስሉ ላይ የምታገኙት ስሙን
የማልገልፅላችሁ የኢቴቪ ጋዜጠኛንም በሰልፉ ላይ አንድነት ፓርቲም ሆነ ህዝቡ ያላንፀባረቁትን እንዴት እንዳንፀባረቁ
አድርገህ ትጠይቃለህ? ስለው የሚመልሰው አጥቶ ሲንተባተብ ከቆየ በኋላ እንደማለቀው ሲያውቅ እኔ የሰማሁትን ነው
በሚል ብቻ ጭንቀቱ ስለገባኝ በመቅረፀ ድምፅ ምላሹን አኑሬ ልገላገለው ችያለሁ፡፡
ያው እኔም ለህዝቡ፣ለሀሩና ለዓለም ይጠቅም ዘንድ እንደሰለጠነ ለእውነት እና ለሙያው እንደቆመ ነፃ ጋዜጠኛ ያየሁት
ነግር አስገርሞኝ ከካሜራ ባለሙያ ባልደረባዬ ያሬድ ጋር ከምንሳፈርበት ታክሲ በፍጥነት ወርደን በመቅረፅ ኢቴቪ
የተለመደውን የውሸት ዘገባና ዘጋቢ ፊልም ከማሰራጨቱ በፊት እውነታውን ህዝብ እንዲረዳ እንዲሁም የደሴ እና
የአካባቢው ህዝብ ጥያቄ እንዳይዳፈን በማሰብ ለመልቀቅ ተገደናል፡፡
ቻይናዊያን ኢትዮጵያን ሊያለሟት ወይንስ ቅኝ ሊገዟት…?
ቻይናውያን ለስራ የተንቀሳቀሱባቸውና ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ገንብተው የሰፈሩባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሁሉ ሰላምና መረጋጋት የላቸውም፡፡ በተለይም የችግሩ ዋነኛ ገፈት ቀማሽ ደግሞ ድሃው ገበሬ ነው፡፡
ከራሳቸው ከዜጎቿ አንደበት ወጥቶ አንደተረጋገጠው ኮምዩኒስቷ ቻይና በዋነኝነት ለኮንስትራክሽን ስራ ወደ አፍሪካ አገሮች በተለይም ወደ ኢትዮጵያ የምትልካቸው ወጣቶች ከአስራ አምስት ዓመት እስከ እድሜ ይፍታሽ እስር የተፈረደባቸው ከባድ ጥፋት የፈፀሙ ወንጀለኞችና ወሮበሎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ድሃዋ አገራችን ኢትዮጵያ ለሀብታሟ ቻይና በእስር ቤትነት እያገለገለች ነው ማለት ነው፡፡
ጣሊያን ቅኝ ሊገዛን በመጣበት ዘመን ለፍርፋሪ ያደሩ የንጉሱ ሹማምንት የሆኑ መኳንት፣ የኃይማኖት፣ የዘመናዊ ትምህርትና የስነ-ጽሁፍ ልሂቃን የፋሽስት ጉዳይ አስፈፃሚና ተላላኪ በመሆን በገዛ አገራቸውና ድሃ ወገናቸው ላይ መቸም ቢሆን ታሪክ የማይረሳው ክህደት ፈፅመዋል፡፡ ከጻኅፍት አፈወርቅ ገ/ኢየሱስንና ብርሃኑ ድንቄን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡
ዛሬም በዚህ ዘመን በተመሳሳይ ሁኔታ የወያኔ ኢህአዴግ ካድሬዎች ከቻይናዊያን ጋር በመመሳጠር የአገራቸውን ብሄራዊ ማንነትና ጥቅም አሳልፈው በገንዘብ በመሸጥና የጎስቋላ ወገናቸውን ሰብአዊ መብት በማስረገጥ ባቋራጭ እየበለጸጉ ይገኛሉ፡፡
ከጎንደር ባህር ዳር ያለው ጎዳና የአስፋልት ግንባታ ሲሰራ በጎንደር ማክሰኝት ከተማ ውስጥ ይገኙ የነበሩት የወያኔ ኢህአዴግ ካድሬዎች ከአካባቢው ህብረተሰብ ሲነፃፀር ያማረና የዘነጠ መኖሪያ ቤት ከመስራት አልፈው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በባንክ እስከማከማቸት ደርሰው ነበር፡፡ አንዳንዶቹማ ጭራሽ ሃፍረታቸውን ሽጠው በልተው በአየር ባየር የሲሚንቶ፣ የብረታብረት፣ የድንጋይ፣ የአሸዋና የነዳጅ ንግድ ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡ በዚያ ዓይን ያወጣ ስርቆትና ዝርፊያ ጥልፍልፎሽ መረብ ውስጥ የነበሩ ጥቂት የማይባሉ ግለሰቦችም ለጥቅም ሲሉ አርስበርሳቸው በጥይት ተገዳድለዋል፤ በጩቤ ተራርደዋል፡፡ በተጨማሪም የማክሰኝትና አካባቢዋ ህብረተሰብ የዕለት ከዕለት ኑሮ መንገዱ ተገንብቶ እስኪያልቅ ድረስ መረጋጋት ያልሰፈነበትና ስጋት የተጋረጠበት ሆኖ ቆይቷል፡፡
በጎጃም መርጦ ለማርያም አከባቢ የሚገኙ የወያኔ ኢህአዴግ ካድሬዎች ደግሞ ከቻይናዊያን መሃንዲሶች ጋር በስውር በመዋዋል የጥራት ደረጃው በእጅጉ የወረደ የአስፋልት መንገድ አንዲገነባ ሲያደርጉ ስራው በሚመለከተው ኢትዮጵያዊ መሃንዲስ ተደርሶባቸው ኢትዮጵያዊዩ መሃንዲስ ሴራውን በማጋለጥ አስፋልቱን ለማስፈረስ ሞክሮ በካድሬዎቹ ዛቻና ማስፈራሪያ አገሩን ኢትዮጵያን ጥሎ ለመሰደድ በቅቷል፡፡
አሁንም በዚያው በጎጃም አዴት ዙሪያ በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ቻይናዊያን እሳት በውስጡ በቋጠረ የኤሌክትሪክ ሽቦ አንገቷን አንቀው በማንጠልጠል አንዲትን ሴት ህይወቷን በመቅጠፋቸው የአካባቢ ገበሬ ለተቃውሞ ሲወጣ በካራቴ እየዘረሩ ጨርሰውታል፡፡
ባጠቃላይ ቻይናዊያን ለግንባታ ስራ ተሰማርተው ወንጀል ያልፈፀሙባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሉም፡፡ አሁንም በነቀምቴ ባኮ መንገድ ስራ ሳይት አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን የዚሁ እጣ ነው እየደረሰባቸው የሚገኙት፡፡ የአሰላና አካባቢዋ ነዋሪዎችም በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ መቼም ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አንድ ቻይናዊ የገልባጭ መኪና ሾፌር የጫናቸውን ኢትዮጵያዊ የቀን ሰራተኞች ልክ አንደማይጠቅም ቆሻሻ መንገድ ዳር ላይ ገልብጦ እንደደፋቸውም ተሰምቷል፡፡ ቻይናዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ ግፍ የሚፈፅሙት በጥቅማጥቅም ያሰሯቸውን “የመንግስት” ካድሬዎች መከታና ከለላ በማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ምንም አይነት ወንጀል በህብረተሰቡ ላይ ፈፅመው ይከሰሱ ወንወጀላቸው ተድበስብሶ ይቀራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህብረተሰቡ ጥቃቱን በራሱ መንገድ እንዳይከላከል በጥቅም ምክንያት ከቻይናዊያን ጋር ባበሩ ፌደራል ፖሊሶችና የአካባቢው ታጣቂ ሚሊሻዎች የሚደርስበትን አፀፋ ይፈራል፡፡ ደግነቱ ዘውዱ ታድያ ይህ ሁሉ ልማት ወይንስ ቅኝ ግዛት…?

Subscribe to:
Posts (Atom)