Pages

Dec 29, 2012

በአዲስአበባ አቶ መለስን የሚያወድሱ ፖስተሮች እየተነሱ ነው


ኢሳት ዜና:- “ራዕይህን እናሳካለን”፣“አባይን የደፈረ መሪ”፣“ቃልህን እንጠብቃለን” እና የመሳሰሉ የውዳሴ ቃላት ጋር የአቶ
መለስን ምስል የያዙና በውድ ዋጋ የተሰሩ ፖስተሮች አዲስአበባ ከተማን ጨምሮ ክልሎችን ከማጥለቅለቃቸው ጋር
ተያይዞ ግንባሩ ባልተለመደ ሁኔታ ግለሰብ ወደማምለክ ደረጃ ማሽቆልቆሉ በራሱ አባላት ጭምር ከፍተኛ ትችትን
አስከትሎበታል፡፡
ሰሞኑን በአዲስአበባ በተለይ ከኡራኤል ቤ/ክ እስከ ፍትህ ሚኒስቴር የመኪና መንገድ አካፋይ መሃል ላይ በግምት
በ30 ሜትር ልዩነት ተደርድረው የነበሩ የአቶ መለስ ፖስተሮች እንዲነሱ ተደርጓል፡፡
ስለጉዳዩ አስተያየት የተጠየቀ አንድ የአዲስአበባ ነዋሪ ኢህአዴግ በተለይ አቶ መለስ ራዕይ በሚባለው ጉዳይ እጅግ
ተጃጅሎ ከርሟል፡፡
ስንትናስንት ችግር ባለበት ደሃ አገር በሚሊየን የሚቆጠር ብር ለመፈክር መጻፊያ ፖስተር የመንግስትና
የሕዝብ ገንዘብ ሲባክን መክረሙ እጅግ የሚያሰዝንና የሚያሳፍር ነው ብሏል፡፡
የፖስተሮቹ መነሳት፣አለመነሳት ለእኔ ትርጉም የለውም የሚለው አስተያየት ሰጪው የግንባሩ ካድሬዎች ቀድሞውንም መፈክር በመጻፍ ሥራ የተጠመዱት የሕዝብ ድጋፍ ያገኙ መስሎአቸው የነበረ ሲሆን ሕዝቡ ግን በአድራጎታቸው ማፈሩን ሲረዱ ከፍተኛ ገንዘብ ያወጡበትን ምስል በሚያዋርድ መልኩ እየነቀሉ ለመጣል አላመነቱም ሲል ትዝብቱን ገልጾአል፡፡
የቀድሞ የህወሃት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ ሰሞኑን በአዲስአበባ ለታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ “የመለስ
ራዕይ” የሚለውን አሰልቺ ፕሮፖጋንዳ በሚያጣጥል መልኩ “በግለሰብ ላይ የተቀመጠ ራዕይ ሳይሆን የሁላችንም እሴት
የሆነ የጋራ ራዕይ ነው ያለን” ሲሉ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል

በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ


ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።
40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።
የግጭቱን መንስኤ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንድ ወገኖች ግጭቱ በህወሀት ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ነው ሲሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ በህወሀት ደጋፊ ወታደሮችና በተቀረው ሰራዊት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ይላሉ።  ኢሳት የግጭቱን ትክክለኛ ምንጭ ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው።
ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው። ግጭቱ በዚሁ ስፍራ ይጀመር እንጅ ወደ አራት አጎራባች አካባቢዎች ተሰራጭቶ እንደነበር ምንጮች አመልከተዋል።
ከትናንት በስቲያ እና ትናንት ውጥረቱ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ምናልባትም ግጭቱ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የአካባቢው ሰዎች ቀያቸውን እየለቀቁ ነው።
የቡሬ ግንባር ዋና እዝ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን፣ በሰሜን እዝ አዛዥ ጄነራል ሳእረ መኮንን እንደሚመራ ይታወቃል።
ቡሬ ግንባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከባድመ ቀጥሎ ሀይሉን በብዛት ያሰማራበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል። ኢሳት በቅርቡ በሰሜን ግንባር የተመደበን አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል በማናገር በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ችግር መዘገቡ  ይታወሳል።
በሌላ ዜና ደግሞ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው የአፋር ጋድሌ ሚሊሺያ ሀይል ወጣቶችን ትመለምላላችሁ የተባሉ የሚሊሺያው ወታዳራዊ አዛዥ የሆኑት የኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ 4 የቅርብ ዘመዶች ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና መንግስትም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን ማስፈሩን መዘገባችን ይታወሳል።

መንግሰት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ

ኢሳት ዜና:-አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና
ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡
ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት
አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገር
ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም
የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች
ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“የሃይማኖት አክራሪነት አንድ ስጋት ነው፡፡ከዚያ አልፎ ሽብርተኝነት አለ፡፡ሕዝቡ በስነልቦና እንዲሸበር
ፍርሃት፣ጭንቀት፣አለመተማመን እንዲሰፋ፣ ወጣቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ እንዳይገባ የሚያደርጉ
ኃይሎች አሉ ” ያሉት ብ/ጄኔራሉ  ”ይህን ለመቆጣጠር ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የመከላከያ አቅም መገንባት
ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ብ/ጄኔራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው መረር ብለው “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን
የመቆጣጠር አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁ ይህ ነው፡፡ለኀብረተሰቡ የሰላምና የልማት አጀንዳ እንቅፋት ሊሆኑ
የሚችሉ የመቆጣጠር ብቃት አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡
“ስርዓት ያልተበጀለት ኢንተርኔት ጉዳቱ ሰፊ ነው” የሚሉት ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን “ሕገመንግስቱን ም ሆነ የሕዝቡን ሰላም
የሚጻረሩ እንቅስቃሴዎች ሊፈቀድላቸው አይገባም” ብሎ አስቀምጧል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጽያ መንግስት በኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች ላይ አፈና በማድረግ የዜጎችን ኀሳብን በነጻ የመግለጽ
ነጻነት የሚጻረሩ ሕገወጥ እርምጃዎችን ይወስዳል በሚል የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ክሶች፤ መሰረተ ቢስ ናቸው በሚል
ሲያጣጥል መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

Dec 28, 2012

ነጻነትና ፍትህ ከምግብ በላይ: በቡሬ ግንባር ሰራዊቱ እርስ በእርስ ተዋጋ ፤ ቁጥራቸው የበዛ የሰራዊት አባላት ...

ነጻነትና ፍትህ ከምግብ በላይ: በቡሬ ግንባር ሰራዊቱ እርስ በእርስ ተዋጋ ፤ ቁጥራቸው የበዛ የሰራዊት አባላት ...

በቡሬ ግንባር ሰራዊቱ እርስ በእርስ ተዋጋ ፤ ቁጥራቸው የበዛ የሰራዊት አባላት ተገድለዋል የቆሰሉም ብዙ ናቸው ፤ ውጥረቱም አሁንም እንደቀጠለ ነው:: በምሽቱ የዜና ዘገባ ዝርዝር ይኖረናል::

ESAT DC Daily News 27 December 2012 Ethiopia

የቤተሰብ ምሽት በቶሮንቶ በደማቅ ሁኔት ተከበረ


ኢሳት ዜና:-በቶሮንቶ ከተማና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢሳት የቤተሰብ ምሽትን ቅዳሜ ዲሴምበር 22 ቀን 2012 ዓ ም የዕለቱ ይክብር እንግዳ ታማኝ በየነ ከባለቤቱና ከቤተሰቡ ጋር እንዲሁም ከኦተዋ፣ ከተለያዩ የካናዳ ከተሞችና ከአሜሪካ የመጡ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።
በየዓመቱ የኢሳት የቤተሰብ ምሽትን ለማዘጋጀት ያቀደው የቶሮንቶ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው የቤተሰብ ምሽቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ በጎና ጉልህ አስተዋጾ እያደረጉ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እውቅና የሚሰጥበትና በስራቸውም እንዲገፉበት የሚያበረታታበት ነው።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆነው ታማኝ በየነ ለሃገሩና ለወገኑ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የቤተሰቡንና የግል ህይወቱን መስዋዕት በማድረግ ፍትህና ርትዕ በጠፋባት ኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ የአገሩ ሉዓላዊነት እንዲከበር አምባገነኖችን በማጋለጥ፣ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለመብታቸውና ለአገራቸው ነጻነት ቆርጠው እንዲታገሉ በመቀስቀስና በማስተማር እየተጫወተ ላለው ጉልህ ሚና ማበረታታት የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን የበአሉ አዘጋጆች አስታውቀዋል።
በዚህ የቤተሰብ ምሽት ታማኝን ያሳደጉት ቤተሰቡና ህብረተሰብ እሱን በመቅረጽ ትልቅ ሚና ያላቸው መሆኑን ያብራራው የበአሉ ዝግጅት ኮሚቴ የታማኝ ቤተሰብ በተለይም ባለቤቱ ፋንትሽ በቀለና ሶስቱ ልጆቻቸው እየከፈሉ ያለው መስዋዕት ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ታማኝን በአሁኑ ማንነቱ እንዲገፋበት ለሚያደርጉት ጥረት አርዓያ ቤተሰብ በመሆናቸው የበአሉ የመጀመርያ የክብር እንግዶች ሆነዋል ብሏል።
ለኢሳት ቤተሰብ ምሽት በቀጥታ በስልክ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የታማኝ እናት ልጃቸው ከድሮውም በራሱና በሌሎች ላይ ጥቃት ሲደርስ የማይወድ መሆኑን አስረድተው ለዚህ ጥሩ ተግባሩ እውቅና የሰጡትንና የሚደግፉትን ከልብ አመስግነዋል።
የበአሉ ዝግጅት ኮሚቴና ወጣቶቹ ለሱና ለቤተሰቡ ያበረከቱትን ስጦታ ከተረከበ በሁዋላ ታማኝ ባደረገው ቀስቃሽ ንግግር የተደረገለትን ከበሬታና ስጦታ አመስግኖ እሱ እንደዜጋ ለአገሩ ያደረገው አስተዋጾ ከሌሎቹ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት መሆኑን በማስረዳት “ብዙዎቹ ምንም ያላገኙባት ኢትዮጵያን ለአንድነቷ በገበያ ላይ በገመድ ተሰቅለዋል፣ ለባንዲራዋ በፈንጅ ላይ ተረማምደዋል፣ ለሉዐላዊነቷ ባምባገነኖች ተረሽነዋል። እኔ ያደግሁት ይህን እየሰማሁና እያየሁ በመሆኑ የማውቀውን እውነት በመናገሬ አክብራችሁኛል። ህይወትንም የሚጠይቅ መስዋዕት ቢመጣ በጸጋ እቀበላለሁ” ሲል አረጋግጧል።
በበአሉ የልጅ አለማየሁ ቴዎድሮስ፣ የአሉላ አባነጋና የአቡነ ጴጥሮስ ምስሎች በጨረታ ቀርበው ገቢ አስገኝተዋል።

ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ተጽዕኖ የጸዳች፤ በUK ለሚገኘው ስደተኛ የእምነቱ ማዕከልና ኢትዮጵያው ጭምር ናት!! አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች


የዘመናት ታሪክ ባለቤትና ከትውልድ ወደ
ትውልድ
በመተላለፍ፤ ወደፊትም ለዘለዓለም የምትኖር
የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ
የክርስቶስ
ማደሪያ የምትባለው ዛሬ ኖሮ ነገ ለማይኖረው
አምባ ገነንና
ዘረኛ አገዛዝ መሣሪያ ሳትሆን ከተበደለውና
መብትና
ነጻነቱን ከተገፈፈው የኢዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆም
የቻለች
እንደሁ ብቻ ነው።ደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች -(Erope-Churchደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች

ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ተጽዕኖ 
የጸዳች፤ በUK ለሚገኘው ስደተኛ የእምነቱ ማዕከልና ኢትዮጵያው ጭምር ናት!! 
አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች
የዘመናት ታሪክ ባለቤትና ከትውልድ ወደ ትውልድ
በመተላለፍ፤ ወደፊትም ለዘለዓለም የምትኖር የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ የክርስቶስ
ማደሪያ የምትባለው ዛሬ ኖሮ ነገ ለማይኖረው አምባ ገነንና
ዘረኛ አገዛዝ መሣሪያ ሳትሆን ከተበደለውና መብትና
ነጻነቱን ከተገፈፈው የኢዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆም የቻለች
እንደሁ ብቻ ነው።
ላለፉት 21  ዓመታት ይህንን እውነተኛ ክርስቲያናዊ ሥራ
ተግባራዊ በማድረግ ከወያኔ ተጽዕኖ ነጻ በመሆን በዓለም
ሁሉ ተዘርቶ ለሚገኘው ኢትዮጵያዊ መኩሪያና መመኪያ
ተበለው ከሚጠቀሱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን ውስጥ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን
ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አንዷ ነች።
ኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ የበላይ፤ ሕግ
አውጪና ወሳኝ የሆነው የቅዱስ ሲኖዶስን መንፈሳዊ ዓላማና ውሳኔ በሥራ ላይ እንዳይውል፤ እውነት የሚናገሩ አባቶችን
በማስፈራራት፤ በማስደብደብ፤ በጠመንጃና በደህንነት ኃይል በማስገደድ በሃገሪቱ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ እንደሚፈጸመው
ሁሉ በቤተ ክህነትም ሆነ በየአብያተ ክርስቲያኑ ወሳኝ በተባሉ ቦታዎች ሁሉ የአገዛዙን የጎሳ አባላትና ደጋፊዎች በመሰግሰግ ቤተ
ክርስቲያንም የዘረኛ አገዛዝን ሥርዓትን ተከትላ እንድትዋቀር አድርጓት እንደሚገኝ ይፋ ከሆነ ወራትና አመታት ተቆጥረዋል።
የዘረኛው ቁንጮ የሆኑት መለስ ዜናዊና አባ ጳውሎስን ሞት ቢወስዳቸውም ዘረኛው ሥርዓት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ
የሚያደርገው ተጽዕኖና መከፋፈል በከፋ ሁኔታ ቀጥለ እንጂ ሲሻሻል አልታየም።
ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 21 ዓመታት በአባ ጳውሎስ አማካኝነት የተቃጣባትን የወያኔን አገዛዝ
ጣልቃ ገብነት በሙሉ በመመከትና በመከላከል በዘረኛው አገዛዝ አቀነባባሪነት በጅማ፤ በአሩሲ፤ በአሰቦትና በሌሎችም ቦታዎች
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በተከታዮቿ ላይ ጥቃት ሲደርስ ማንንም ሳትፈራ በነፃነት ድርጊቱን አጋልጣለች፤
ተቃውሞዋን ለዓለም አሰምታለች፤ አቅም በፈቀደም ለተጎዱት ክርስቲያኖች ድጋፍ አድርጋለች።
በቅርቡም የዋልድባ ገዳም በአገዛዙ ሲደፈርና ሲጠቃ፤ መነኮሳት ሲታሰሩና ሲሰቃዩ ሌሎች እንግሊዝ ሃገር ያሉ በወያኔ አገዛዝ ጫና
ሥር ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት ፀጥ እረጭ ሲሉ ቤተ ክርስቲያናችን ግን በድፍረትና በነፃነት ታላቅ
ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ አገዛዙ በእምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የሚፈጽመውን በደል አጋልጣለች ተቃውሞዋንም ለዓለም
አሰምታለች።
ይህ የቅርቡ ትዝታ ሲሆን እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ2005 ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ወንድ ሴት ሳይለይ ህጻን ወጣት፤ ጎልማሳና
አዛውንት ሳይቀር በአሰቃቂ ሁኔታ በጨፈጨፈበት ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ተቃውሞ ከማሰማት ባሻገር በአገዛዙ
የተገደሉት ኢትዮጵያኖች እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ውሻ ተቆጥረው ፍትሐትም ሆነ ጸሎት አይደረግላቸው ተብሎ በአባ ጳውሎስ
አማካኝነት ሲታገድ ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ግን በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያኖች መሉ ጸሎት
አድርጋለች።
ከዚህም በማስከተል ብጹ ወቅዱስ በማለት የአባ ጳውሎስ ሥም በቤተ ክርሲያኗ ውስጥ አይጠራም በማለት ቤተ ክርስቲያኗ
የወሰደችውን የጠራ የአቋም ባሉት ሚዲያዎች ተጠቅማ ለዓለም ሁሉ አሳውቃለች። ይህንን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ
የነበሩ የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ደጋፊዎች ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ለሞቱት መጸለዩንና በአባ ጳውሎስ ላይ የተወሰደውን አቋም
በመቃወም ከቤተ ክርስቲያኗ ተለይተው ስላሴ ቤተ ክርስቲያንን ሊያቋቁሙ ችለዋል።
የተፈጠረው የአቋም ልዩነት እንጂ የሃይማኖት ልዩነት ባለመሆኑም በአንድ ሃይማኖት ጥላ ሥር ሆኖ በአቋም ልዩነት ሕዝብ ከህዝብ
ከሚቃቃርና ከሚናቆር ተለያይቶ ማምለኩ መፍትሔ ሰጪ ሊሆን ችሏል።

በእርግጥ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እ.አ.አቆጣጠር በ1993 የዘረኛ ሥርዓት አራማጅ
ተወካይ የሆኑት አባ ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ሳይጋብዟቸው መጥተው በማሳፈርና በማዋረድ መልሳ አባራቸዋለች ያም
ሆኖ ግን የአባ ጳውሎስን ስም ብጹዕ ወቅዱስ ብላ ትጠራ ስለነበር መልሰን በእጃችን እናገባታለን በሚል ተስፋ የተለያዩ የተንኮል
ሙከራዎች ይደረግባት ነበር እንጂ በለየለት ጠላትነት ተፈርጃ የከፋ ጥቃት ሳይሰነዘርባት ቆይታ ነበር።
እ.አ.  አቆጣጠር ከ2005  በኋላ ግን ቤተ ክርስቲያኗ በመንበረ ፓትርያርኩኗ በአባ ጳውሎስ በለየለት ጠላትነት ተፈርጃ በርካታ
ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቃት የደረሰባት ሲሆነ ከዚህም ውስጥ የማይዘነጋው ቤተ ክርስቲያኗ የምትገለገልበትን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን
ለመግዛት ሕዝበ ክርስቲያኑ ገንዘብና ጉልበትን በማስተባበር ደፋ ቀና ሲል በአባ ጳውሎስ የተፈረመና ከመንበረ ፓትሪያርክ
ለእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን በተጻፈ ደብዳቤ ቤተ ክርስቲያኑ በእንግሊዝ ሃገር በስደት ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን
እንዳይሸጥላቸው የወጣው ማገጃ ነው።
ይህንን ማገጃ ግን በስደት ላይ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲሻር በማድረግ የቤተ ክርስቲያኑንና በግቢው ውስጥ የሚገኘውን
የቪካሬጅ ህንፃ በ£1.700.000 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ፓውንድ) በመግዛት የስደተኛው ኢትዮጵያዊ ዘላለማዊ ሃብትና
ቅርስ እንዲሆን አድርጎታል።
ይህንን ሕዝብ ጥሮና ግሮ ያፈራውን ቅርስ ነው ዛሬ አባ ግርማ ከበደና (በግራ)
መሪጌታ ዓለማየሁ ደስታ (በቀኝ) በተባሉ ካህናት አስተባባሪነት ቤተ
ክርስቲያኗም ሆነች ሃብትና ንብረቷ የቅዱስ ሲኖዶስና የመንበረ ፓትርያርክ ነው
በማለት በቅዱስ ሲኖዶስ ስም ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ሥርዓት አራማጆች
በኤምባሲ አማካኝነት ለማስረከብ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኙት።
ይህንን የክህደት ተግባራቸውን የቤተ ክርስቲያኗ አባላት እንዳማይደግፉት ሲረዱ
የወያኔ ሥርዓት ደጋፊ የሆኑ ሰዎችን በተለያየ ዘዴ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ በመጥራት
የቤተ ክርስቲያኗ አባላት በብዛት እንዲዋጡና እየተስፈራሩ ከቤተ ክርስቲያን እንዲባረሩ በማስደረግ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊ መብቱ በወያኔ ተረገጠ፤ ፍትሕ በኢትዮጵያ ጠፋ፤ ዘረኝነትና የአንድ ጎሳ የበላይነት በኢትዮጵያ ነገሰ፤
የሃገር ሃብትና ንብረት በዘረኞች እጅ ወደቀ እያልክ የምትቆረቆርና ድምጽ ለሌለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጽ የሆንክ ሁሉ ዘረኛው
ወያኔ ከኢትዮጵያም አልፎ በጥቂት ካህናትና ደጋፊዎቻቸው አስተባባሪነት እዚህ እንግሊዝ ሃገር የሚገኘውን የስደተኛው
ኢትዮጵያዊ ንብረትና ቅርስ  ሊወርስ እየጣረ ነውና አንዳችም ማመንታት ሳታደርግ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመምጣት በተለመደውና
በምትታወቅበት ወኔ ወያኔን አዋርደህ እንድታባርር ቅድስት ማርያም ጠርታሃለችና አታሳፍራት!!
ላለፉት 21 ዓመታት ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ተጽዕኖ ነፃ አድርገህ በነፃነት እንዳኖርካት ዛሬም ቤተ ክርስቲያንህ በጥቂት የግል
ጥቅም አሳዳጅ ካህናት አማካኝነት በወያኔ ደጋፊዎች እጅ እንዳትወድቅ መጥተህ ታገልላት።
የፊታችን አሑድ 30/12/12  ክቀኑ ሰምንት ሰአት፤ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ዓዲስ አመራር ኮሚቲ ለመምረጥ ስብስባ 
ጠርተዋል። ስሞኑን ብዙ የማናውቃቸው ስወች ወደ ቤተ ክርስቲያናችን መምጣት ጀምረዋል። ይህም ‘አባላትን”  ሕጋዊ ባልሆነ 
መንገድ በማብዛት፤ ቤተ ክርስቲያናችንን፤ ንብርተዋንና አስትዳደርዋን፤ አሳልፎ፤ ለወያኔ፤ ለመስጠት ነው። ስለዚህ፤ በእለቱ 
ተገኝታችሁ፤ ቤተ ክርስቲያናችሁን አድኑ። ወደፊትም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥም ሆነ ከቤተ ክርስቲያናችን ውጭ በሚደረጉ 
ስብሰባዎች ላይ ተገኝታችሁ፤ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያምን አድኑ!!!
ኃይልም ድልም የእግዚአብሔር ነው!!ent/uploads/2012/12/Church-Under-Attack1.pdf

ይቅርታ የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም” ቴሌኮም ቀመስ ልቦለድ!


ይቅርታ የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም” ቴሌኮም ቀመስ ልቦለድ!

ናፍቃው ናፍቃው አሁንም ናፍቃው ደወለችለት።
ነግሯታል። በእርሱ ውስጥ የተሾመች ባለስልጣን እርሷ ነች። ና ስትለው ይመጣል ሂድ ስትለው ይሄዳል። ግባ ስትለው ይገባል ውጣ ስትለው ይወጣል።
ለዚህም ነው የወደደችው ታዛዥነቱን ትህትናውን “ጠብ እርግፍ” ማለቱን አይታ ነው  በፍቅሩ “ጠብ እርግፍ” ያለችው።
ናፍቃው ናፍቃው አሁንም ናፍቃው ደወለችለት።
“ይቅርታ የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይሉም!”  በተስረቅራቂ ድምፅ ከወዲያኛው መስመር የሆነች ሴትዮ መለሰችላት። ቅናት አይሉት አንዳች ሰይጣናዊ ስሜት ሲሰማት ታወቃት። ሰውነቷ በበስጭት ጋለ። ከዛም ምን ነካኝ… ብላ በሀፍረት ሳቅ ብላ…
ደግማ ደወለች…
ቴሌዎች በየስኩ ላይ ያስቀመጧት ሴትዬ የሰዉን አባወራ ሁሉ “ይቅርታ የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም” ስትል “ከኔጋ የሚቆይበት ጉዳይ አለው” የምትል ትመስላለች፤ እንጂ ምክንያቱን አትገልፅም። አነጋገሯ ደግሞ ከሌሎቹ የተለየ ቅላፄ አለው። “ያልዎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው…” ከምትለው እና ቀልቀል ባለ ድምፅ “The network is busy now” ከምትለው ሴትዬ የተለየች ናት። ማሽን ላየ የተገጠመች ሳይሆን ከሰዉ ወዳጅ ጋር አጓጉል የገጠመች ነው የምትመስለው።
የገዛ ፍቅረኛዋን ያለ በቂ ምክንያት “አሁን ማግኘት አይችሉም” መባሏ እያብከነከናት ደግማ ደወለች…
ከዛኛው መስመር ቆጣ ያለ የሴት ድምፅ ሰማች፤
“ሁለተኛ በዚህ ስልክ ባትደውይ ደስ ይለኛል ነገርኩሽ አይደል እንዴ!”
ተሳስታ የደወለች መስሏት ስልኳን አየት አደረገችው። በፍፁም አልተሳሳተችም። የእርሱን ስልክ መሳሳት ስሙን የመሳሳት ያክል ከባድ ነው።
ማናት ይቺ…?
እንደቅድሙ ማሽኗ በሆነች… ስትል እየተመኘች… ቀሰስ ባለ ድምፅ “ሃ…ሎ” አለች፤ ቅስሟ ስብር ሲል ታወቃት። ቅስም የቱጋ ነበር…? እንጃ ብቻ ከወገብ ስብራት የበለጠ ያማል። ታመመች…
በተሰበረ ቅስም እና በተሰበረ ድምፅ ድጋሚ “ሃ…ሎ” አለች። የእርሱን ድምፅ ሰማቸው። ግን አልገባትም… “በቃ እንደነገረችሽ አድርጊ የኔ እመቤት”
ራሷ ሊፈነዳ ነው።
————————————————————————————-
“በቃ እንደነገረችሽ አድርጊ የኔ እመቤት” አለና፤
ተጣድፎ ስልኩን ዘጋው። አንዳንድ ደንበኞች ይገርሙታል  ከሰራተኞች የተሰጣቸውን መረጃ ድጋሚ ከእርሱ ካልሰሙ ደስ አይላቸውም። እርሱም “እነርሱ እንደነገሯችሁ አድርጉ” ብሎ ይሸኛል።
ስልኩን ገና ሳይዘጋው ሌላ ጥሪ መጣ… ውዱ ናት። ገብረክርስቶስ ደስታ ከገጠመላት በላይ ሚካኤል በላይነህ ካዜመላት የበለጠ የሚወዳት ውዱ…
“የኔ ናፍቆት…” ብሎ ሲጀምር፤ “ማንነቷን ብቻ ንገረኝና እዘጋልሃለሁ።” የሚል የተሰበረ ድምፅ የእንባ ሳግ እየተናነቀው ከጆሮው ደረሰ።
አልገባውም…
“እሷ እንደነገረችኝ አደርጋለሁ… ግን ማናት…!?”
የት ነበርሽ…? ይሄ ቃል እርሷ ከመደወሏ በፊት የተናገረው ነው…! የት ሆና ሰማችው… ደግሞስ ምን ክፋት አለው… የስራ ጉዳይ ነው… “እርሷ እንደነገረችሽ አድርጊ የኔ እመቤት…” እመቤት ማለቴ ይሆን ያስከፋት…
እያሰበ እያለ ሃይሏን አሰባስባ አምባረቀችበት።
“ማናት?”
“ደንበኛችን ናት…” አለ። ከዛኛው ጫፍ ውዱ ከምትገኝበት ጫፍ ስቅስቅታ… ተሰማው… አዎ አለቀሰች ሆዷ ባባ… ስልኩንም ዘጋችበት።
———————————————————————-
ግራ ተጋብቶ በተቀመጠበት አንድ ወዳጁ ቢሮውን ላመል ያህል “ኳኳ..” አድርጎ ገባና… “ሰሞኑን ቴሌ የሰዎችን የፍቅር ተቋማት ለማፈራረስ ቆርጦ ተነስቷል” አለው።
“እንዴ….ት” አለ ሙትት ባለ ድምፅ፤
“የአንዱን ስልክ ለአንዱ እያጠላለፈ የሰዉን ፍቅር እያናጋው ነዋ” አለው።
ይሄኔ “ከትክት ብሎ ሳቀ” ወዳጁ የነገረው ነገር ይሄን ያህል የሚያስቅ መሆኑ አልገለጥልህ አለው። ጭራሽ ተነስቶ፤ “ተጠልፎ ነው ተጠልፎ ነው… ተጠልፎ ነው” እያለ እንደቀውስ ብቻውን እየጮኸ በሩጫ ወደ “ውዱ” ሄደ አንገቷን ደፍታ አይኗ ቀልቶ አገኛት…
“ተጠልፎ ነው! ተጠልፎ ነው! ተጠልፎ ነውኮ…”

Dec 27, 2012

ለእርቅ ጉባኤ አሜሪክ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አባቶች በሽምግልና ኮሚቴ ላይ ጠንከር ያለ መግለጫ አወጡ


ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባና በውጭ ሀገር የሚገኙ አባታቶችን በሶስት ዙር ሲያደራድር የቆየውና ለአረተኛ ዙር ቀጠሮ ይዞ የተነሳው የሽምግልና ቡድን ባለፈው አርብ ያወጣው መግለጫ እንዳስቆጣቸው የገለጹት አባቶች ይቅርታ ካልተጠየቁ በተያዘው የእርቅ ንግግር እንደማይቀጥሉ አረጋግጠዋል::
በቤተክርስትያኒቱ መካከል እርቅ ለማውረድና ሰላምን ለማውረድ ሲንቀሳቀስ የቆየው አስታራቂ ቡድን አዲስ ፓትሪያርክ ለመምረጥ ኮሚቴ መሰየሙን በመቃወም ባለፈው አርብ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል::
ለእርቅ ንግግር ወደአሜሪካ የተጎዙት ልኡካን ባልተመለሱበትና  ቀጣይ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ በያዙበት ወቅት በአንዳንድ አባቶች ግፊት እ  እርምጃ ተገቢአይደለም ሲል ነበር ሸምጋዩ ቡድን መግለጫ ያወጣው::
እንደ ሽምግልና ቡድኑ ሁሉ ፓትርያርክ ለመምረጥ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙን በመቃወምና እንደማይቀበሉ በማረጋገጥ ለአሜምጽ ሬዲዮ የአማሪኛው አገልግሎት መግለጫ የሰጡት አባቶች አዲስ አበባ ከደረሱ በሆላ ሸምጋዮቹን በመውቀስ ያወጡት መግለጫ አነጋጋሪ ሆኖል::
በሸምጋዩ ቡድን አርብ ታህሳስ 23/2005 መግለጫውን ሲያወጣ በአሜሪካ የነበሩትና ታህሳስ 15/2005 ወደ ኢትዮጵያ የተጎዙት አባቶች ከአዲስ አበባ ያወጡትን መግለጫ አሜሪካ በነበሩበት ቀን ታህሳስ 13/2005 እንደሆነ መደረጉ ግልጽ አልሆነም::
የልኡካን ቡድኑ አባላት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ገሪማ፡ ብጹእ አቡነ አትና ቲዎስ ፡ ብጹእ አቡነ ቀውስጦስ ፡ ንቡረ እድ ኤሊያስ አብርሀ ባወጡት መግለጫ ሸምጋዩ ቡድን ቅዱስ ሲኖዶሱን ተዳፍሮል በማለት ወቅሶል:: በሽምግልናውም ሂደት ወገንተኝነት ይንጸባረቅበት ነበር ሲሉ አክለዋል::
የሽምግልናው ኮሚቴ ይህንን ስህተቱን አምኖ ይቅርታ ካልጠየቀ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት በሚደረግ ንግግር አንሳተፍም ብለዋል::
ለሰላም ያለን ፍላጎት ግን አይታጠፍም ሲሉም አጠቃልዋል::

ያለው አማራጭ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ብቻ ነው ሲሉ አንጋፋው የሕውሀት ታጋይ አቶ ስብሐት ነጋ ገለጹ


ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሐት ነጋ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ከተማ ለንባብ ለበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ የመለስ ራዕይ የሚባለው ነገር ትክክል እንደማይመስላቸውና ያለው የጋራ ራዕይ መሆኑን ገልጠዋል::
ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሾም ያስፈለገው ክፍት የአመራር ቦታ ስለነበር እንደሆነ ያወሱት አቶ ስብሐት ነጋ: መደረግ የነበረበት ነገር መከናወኑን አስረድተዋል::
ይህ እርምጃ ሕገ-መንግስቱን ይጥሳል በሚል የሚነሳውን ተቃውሞ በተመለከተ እኔ የማውቀው ነገር የለም ያሉት አቶ ስብሐት ነጋ ሕገ-መንግስቱ ከተጣሰም ያለው አማራጭ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ወይንም ሌላ አማራጭ መፈለግ እንጂ አዲሱ አደረጃጀት መቀጠል አለበት ብለዋል::
ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕውሀት)ን ከ1971 እስከ1981 በመሪነት ያገለገሉትና አሁን ይፋዊ የሆነ የፓርቲ አመራር ስፍራ የሌላቸው አቶ ስብሐት ነጋ በሐገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኗቸው የጎላ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል:: በተለይ የአቶ በረከት ሥምዖን ሚና ከቀነሰ ወዲህ ይበልጥ እያንሰራሩ መሆናቸው የተገለጸው አቶ ስብሐት ነጋ በዚህ ረገድ ለተነሳባቸው ጥያቄ እኔ ተራ አባል ነኝ ያለ ሃላፊነቴ ምንም የምሰራው ነገር ያለም ብለዋል::
እኔ ሥርዓት ከጣስኩ ከግንቦት 7: ኦብነግ እና ኦነግ በምን እለያለሁ:: በማለት ጠይቀው ምንም ሚና የለኝም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል::
የአቶ መለስ ራዕይ በሚል የሚነሳውን በተመለከተም “በግለሰብ ብቻ የተቀመጠ ራዕይ ሳይሆን የሁላችንም ዕሴት የሆነ የጋራ ራዕይ ነው” በሚል ምላሽ ሰጥተዋል:: ሆኖም አቶ መለስ ወሳኝ ሰው እንደነበሩ በቃለ ምልልሱ አንስተዋል::
በድርጅቱ ውስጥ ክፍፍል ስለመፈጠሩ ለተነሳባቸው ጥያቄ “እስከአሁን በኢሕአዲግ ውስጥ ይሁን በአባል ድርጅቶቹ መከፋፈል የሚባል ነገር  ገጥሞ አያውቅም:: በዚህ ሂደት በተለያዩ መለኪያዎች ለኢሕአዲግ ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ተባረዋል ወይንም በራሳቸው ለቀው ወደ ሚመጥናቸው ድርጅት ሔደው ይወድቃሉ” ያሉት አቶ ስብሐት ነጋ “አሁን በኢሕአዲግ ውስጥ የሚታይ የሚሰማ የፖለቲካ ጥያቄ ያለ አይመስለኝም ብለዋል:: ካለም እንዳለፈው ጸጋ ነው:: በአፈጻጸም ዙሪያም ጥያቄዎች ሊኖሩ ይችላሉ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል::

በደቡብ ክልል የዳውሮ ወረዳ ዞን ም/ቤት አባላት ዛሬ ከጠሩት ስብሰባ 1500 ሰራተኞች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተገለጠ


ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች  ከዞኑ እንዳመለከቱት የክቢኒ አባላቱ የምረጡን ስብሰባ አድርገው በነበረ ጊዜ ህዝቡ የኔሰው ገብሬ የተሰዋበትን የሎሜ ከተማ ዋና ከተማ ዋካ ትሁን ጥያቄ ሳይመለስ ስለምርጫ  አናወራም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተመልክቶል::
የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በየኔ ሰው ገብሬና በህዝቡ ዘንድ ዋካ መሆን ይገባታል የሚል የነበረ ሲሆን የዞኑ የዴህዴን አመራር አባላት ዋካ መጤ ነዋሪ የመጣባት ከተማ በመሆኖ አይቻልም ሲሉ መቆየታቸው ተገልጦል::
ዛሬ በሎሜ ወረዳ የዞኑ የካቢኔ አባላት ሰራተኞችን ሰብስበው በቅርቡ በሚደረገው የወረዳ ምርጫ ደኢህዴን ኢህአዴግን ምረጡን ለመስበክ ሰራተኞችን ሰብስበው የነበረ ቢሆንም የዋካ ዋና ከተማነት ካልጸደቀ ከናንተ ጋር አንወያይም ሲል ነው 1500 ሰራተኛ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት::
ምንጮቻችን ከሎሜ ወረዳ ባደረሱን ዘገባ መሰረት የዞኑ የካቢኔ አባላት መከፋፈላቸውንም ለማወቅ ተችሎል::

ESAT New Frequency advert

በኩዌት፣ በሳዑዲ ዓረቢያና ጅዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰው ኃይልን በርካሽ ዋጋ ሊያቀርብ እንደሚችል በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያው እያስነገረ ነው



ከሔለን ዘውዱ
ሰው በፈለገበት ቦታና አገር የመዘዋወር መብቱ በሕገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በኮንትራት በቤት ሠራተኝነት ወደ
አረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይሰማል። ኢትዮጵያውያኑ
ላይ ከፍተኛ የሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እየደረሰ ነው። ለዚህም በዋነኛነት ማሳያ የሚሆነው በተለያዩ የዓረብ
አገሮች በቤት ሠራተኛነት በሚሄዱት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የመደፈርና ያለደመወዝ
ማባረር ጥቂቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት እንኳን ከዓለም ደቻሳ ጀምሮ በድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን ለከፍተኛ
የአካል ጉዳት የተዳረጉትን የተደፈሩትን ከፎቅ የተወረወሩትን ለአእምሮ መቃወስ የተዳረጉት የትየለሌ ናቸው
ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪወቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ
በዝርዝር እየዘገቡት ነው፡፡
የወገኖቻችን እንግልት የሚጀምረው አገራቸው ላይ ነው፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያንም
በዜጎቻችን ላይ ክብራቸውን ጭምር የሚነካ ተግባር የሚፈጽሙ አሉ፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በደላላዎች
እየተደለሉ ከየቀያቸው እየተፈናቀሉ ዜጎቻችን ለጉዳት እየተዳረጉ ነው፡፡ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ እንደሆነና ወርቅ
ተነጥፎ እንደሚጠብቃቸው በመስበክ ወጎኖቻችንን እያስጨረሱ ነው፡፡ ከእነዚህ ደላሎች በስተጀርባ የመንግስት እጅ
አለበት መንግሥት ዜጎችን ከመጠበቅና ካለበት ኃላፊነት አንጻር እሱም ተጠያቂ ነው፡፡ ዕድሜያቸው እንዳልሞላ
እየታወቀ ከ13-15 ዓመትን ልጅን 23-26 ዓመት በማለት በማጣራትና አይቶም መገመት ሲቻል ፓስፖርት
ይሰጧቸዋል የሚያስደነግጥ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ ሳዑዲና ኩዌት ለመሄድ የሚመጡት መጻፍ፣ ማንበብ የማይችሉና
መታወቂያና ፓስፖርት መሆኑን መለየት የማይችሉ ናቸው፡፡ ፓስፖርት እስከሚያወጡና የሕክምና ምርመራ
እስከሚደረግላቸው ድረስ ብዙ ችግሮችን ያሳልፋሉ ሁሉም ነገር ተሳክቶላቸው እስከሚሄዱ ድረስ የደላሎቹ የወሲብ
መፈጸሚያ ይሆናሉ፡፡ የጤና ምርመራ ሲደረግላቸውም የHIV ተጠቂ ሆነው ይገኛሉ ውጤታቸው ሲነገራቸው እንደ
ውርደት ስለሚቆጥሩት ተመልሰው ወደቀያቸው መግባትን ይተዉና ራሳቸውን በመሸጥ ለመተዳደር ይሞክራሉ፡፡
በሽታውንም ያስተላልፋሉ ላልተፈለገ እርግዝና ለ አደንዛዥ ዕፆች ተጋላጭ እየሆኑ ነው፡፡
የጤና ምርመራ ውጤቱን አግኝተው ከተጓዙ በኋላ በተቀባይ አገሮችም ችግር ይደርስባቸዋል፡፡ እዚያ ሲመረመሩ ብቁ
አይደላችሁም ተብለው እንዲመለሱ ይገደዳሉ ወይም የት እንዳሉና ማን እንደቀጠራቸው፣ ስንት ቤተሰብ ያለበት ቤት
እንደሚገቡ በስንት እንደተቀጠሩ፣ ቀጣሪዎች ለሕገወጦች ከፍለናል የሚሉት ገንዘብ ስንት እንደሆነና ከሄዱ ከስንት
ጊዜ በኋላ ደመወዛቸውን እንደሚያገኙ አያውቁትም፡፡ ዱባይ ከደረሱ በኋላ ወደ አፍጋኒስታንና ኢራን ሳይቀር ለቤት
ሠራተኝነት ያግዟቸዋል፡፡ ወይም ዱባይ አየር መንገድ ደርሰው የሚቀበላቸው ሰው ባለማግኘት አየር ማረፊያው አካባቢ
ሜዳ ላይ ለመዋልና ለማደር፣ ለምኖ ለመብላትም የተገደዱ በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች ወዴት እንደሚሄዱና
ለምን እንደሚሄዱ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ መንግሥት ራሱ ማወቅ ነበረበት፡፡ የዜጎቹን መብት የሚያስከብር መንግስት
የለንም በዚህ የተነሳ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች በሕገወጥ መንገድ እየወጡ ነው፡፡ የሚደርስባቸውን አደጋ መንግሥት
ጠንቅቆ ያውቀዋል፡
የዚህ ምክንያት ብዙ ነው፡፡ አንዱና ዋነኛው ቁጥጥሩና ክትትሉ በአግባቡ አለመቃኘቱ ነው፡፡ ዜጎች በየትኛውም ቦታ
የመዘዋወር ሕገመንግሥታዊ መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን በተለይ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚደረገው ጉዞ ለሥራ
መሆኑን መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ጉዞው በህጋዊ መንገድ መሆን ሲገባው፣ በተለያየ መንገድ የሚመጣላቸውን
ቪዛ ሕጋዊ ሳያስደርጉና ሳይመዘገቡ ዝም ብለው ነው የሚሄዱት፡፡ ይኽ ደግሞ በውጭ አገር ያሉ ሕገወጦች ቪዛዎችን
እያወጡ ወደ ኢትዮጵያ ሲልኩ እዚህ ያሉት ሕገወጦች ተቀብለውና በሕገወጥ መንገድ ለመለመሏቸው ዜጎች

ይሰጣሉ፡፡ በዚህ መካከል ሕገወጦቹ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ የኩዌት ኤምባሲ ከሚሠሩ የበታች ሠራተኞች ጋር በሚደረግ የምስጢር ግንኙነት ሕጋዊ ሥርዓቱን
በሚቃረን መልኩ እየተሠራ ነው፡፡ በመሆኑም ሕጋዊዎቹ ኤጀንሲዎች ሥራቸው እየተዳከመ ነው፡፡ መንግስት ባለበት
አገር ሕግ እየተጣሰ በሕጋዊ መንገድ በሚላከው ቪዛ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ እየሄዱ ነው፡፡
በሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ የኢትዮጵያ ቆንስላዎች ወደ ሳዑዲ የሚላኩ ሠራተኞች ስለሚያገኙት ደመወዝ መወሰን
የሚችሉት እነሱ እንደሆኑና እጅግ በወረደ ደመወዝ እንደሚያስቀጥሩ መረጃ አለ፡፡ በኩዌትና በሳዑዲ ዓረቢያ በተለይ
ጅዳ ላይ ኤምባሲው የሰው ኃይልን በርካሽ ዋጋ ሊያቀርብ እንደሚችል በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እያስነገረና በጋዜጣ
ላይ ማስታወቂያው እየወጣ ነው፡፡ ተልዕኮአቸውና ኃላፊነታቸው አይደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ የሚሳተፉ የኤምባሲ
ሠራተኞች አሉ፡፡ በኩዌት አካባቢም ከአሠሪዎቻቸው ሸሽተው ከለላ ለማግኝት ወደ ኤምባሲ ለመጠለል ስሄዱ
ኤምባሲው ውስጥ ባሉ ሰራተኞች አማካይነት ለሌላ አሠሪ አሳልፈው እንደሚሸጧቸው ነው መረጃዎች
የሚያመለክቱት፡፡ ይህንን ጉዳይ ለማስቆም የተንቀሳቀሱትን ወገን ወዳድ ዜጎች በመንግስት ባለስልጣናት ታፍነዋል፡፡
በአሁኑም ጊዜ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በቀን ከአንድ ሺሕ እስከ አንድ ሺሕ አምስት መቶ ይሄዳሉ፡፡ ተቀባይ አገሮች
ከሌሎች ሠራተኛ አቅራቢ አገሮች ጋር ያላቸው ግንኙነት ጥሩ ስላልሆነ ፊታቸውን መሪና መንግስት ወደ ሌላት
ኢትዮጵያ አዙረዋል ምክንያቱም ሌሎች አገሮች የዜጎቻቸውን መብት እያስከበሩ ሰለሚልኩ በአሁኑ ጊዜ ብዙ አገሮች
ወደ መንግስት አልባዋ ኢትዮጵያ ትኩረት እያደረጉ ነው፡፡
ለምሳሌ ፊሊፒንን ብንወስድ በዱባይ የሚገኘው ኤምባሲያቸው ጉዟቸውን ሳያፀድቅ አገራቸውን ለቀው አይወጡም፡፡
የአገራቸው መንግሥትም ማንኛውም የቤት ሠራተኛ ሆኖ የሚሄድ ዜጋው ከ450 ዶላር በታች ተከፋይ ሆኖ
እንዳይጓዝ በሕግ ደንግጓል፡፡ ችሎታና የትምህርት ደረጃቸውን በሚመለከት የሚሞሉት የቅጥር ፎርም ትክክለኛና
እውነተኛ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ለሚያጋጥሟቸው አስከፊ ችግሮች፣ ለሚደርስባቸው ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት
ረገጣና የጉልበት ብዝበዛ መነሻ የሴቶቹ የአገሩን ባህልና አኗኗር ዘይቤ አለማወቅና ለሥራቸው የሚያስፈልጋቸውን
ሥልጠና አለማግኘት ነው፡፡ እንደ ልብስ ማጠቢያ ወይም ምግብ ማብሰያ ባሉ ማሽኖች ግራ ይጋባሉ፡፡
ስለሚቀጠሩበት ቤት ሁኔታ፣ የቤተሰብ ብዛት ሌላም ሌላም አንድም የሚያውቁት ነገር ሳይኖር ከአገር ይወጣሉ፡፡
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚታየው ወደ አረብ አገሮች በመሔድ ላይ ያሉት ለአዲስ አበባ እንኳ እንግዳ የሆኑ
ከገጠር አካባቢ የሚመጡ ልጆች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል የሚቀጥራቸው እንዲገኝ ሲባል የኢትዮጵያውያኑ የቅጥር ፎርም ችሎታቸው ምንም ይሁን ምን ሁሉንም
ዘመናዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ማሽን መጠቀም እንደሚችሉ፤ ማንኛውንም ሥራ ለመሥራትም ብቃት እንዳላቸው
ተደርጎ ይሞላል፡፡ ይህን ከፍተኛ ቁጥር የተመለከቱ ዱባይ ውስጥ የሚገኙ ህንድና ፓኪስታናዊ ደላሎች አማርኛ
ለምደው ሥራቸውን እያቀላጠፉ ኢትዮጵያውያኑ በወር የሚከፈላቸው 135 ዶላር ሲሆን፣ ኤጀንሲዎች አንዲት
ኢትዮጵያዊትን በማስቀጠር የሚያገኙት 500 አልያም 550 ዶላር ነው፡፡ በተቃራኒው አንዲት ፈሊፒን የቤት
ሠራተኛን በማስቀጠር ኤጀንሲዎች ከ2700 ዶላር በላይ ያገኛሉ፡፡ ‹‹አንዲት ፊሊፒን ለሚቀጥር ኢትዮጵያዊ
ይመረቅለታል›› የሚሉ ማስታወቂያዎች በተለያዩ የሥራ ማስታወቂያ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ላይ መመልከትም
የተለመደ ሆኖአል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
ከዚህ በፊት በዘ-ሐበሻ ላይ ተለጥፎ የነበረና አረቦች ኢትዮጵያዊቷን ሲያሰቃዩ የሚያሳየውን ቪድዮ በድጋሚ






ኢትዮጵያ ምዕመን በዘማሪት ዘርፌ ከበደ “አለው ነገር” መዝሙር ስሜቱን እየገለጸ ነው


ሐበሻ) ዘማሪ ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል፣ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን እና ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ከወራት በፊት
ያወጡት አዲስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር ሲዲና ካሴት በመላው ኢትዮጵያ እየተደመጠ ሲሆን በተለይ የዘማሪት
ዘርፌ ከበደ “አለው ነገር እግዚአብሄር እንዲህ አብዝቶ ዝም ካለ” የሚለው መዝሙርን ከወቅታዊ የቤ/ክ ሁኔታ ጋር
ይያያዛል በሚል በርከት ያሉ ሰዎች ስሜታቸውን በዚህ መዝሙር እየገለጹ እንደሚገኙ የዘ-ሐበሻ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎች
አስታወቁ። እንደ ዘጋቢዎቻችን ገለጻ ከሆነ በሕዝብ ማመላለሻ ታክሲዎችና በየቦታው ሕዝቡ ይህን መዝሙር
እየደጋገመ እንደሚከፍትና ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር በማያያዝ ይነጋገርበታል። አነጋጋሪው የዘማሪት ዘርፌ ከበደ
መዝሙር ከነግጥሙ ይኸው፦

Dec 26, 2012

“የኦርቶዶክ ቤ/ክርስቲያን አመራር ለሃይማኖቱም ሆነ ለአጠቃላይ ሥርዓቱ አደጋ ወደመሆን ተቃርቧል” – ስብሃት ነጋ (ቃለምልልስ)



• በግለሰብ ላይ የተቀመጠ ራዕይ ሳይሆን የሁላችንም እሴት የሆነ የጋራ ራዕይ ነው
ያለን፣
• የኦርቶዶክ ቤ/ክርስቲያን አመራር ለሃይማኖቱም ሆነ ለአጠቃላይ ሥርዓቱ አደጋ
ወደመሆን ተቃርቧል፣
• ኢህአዴግ በታሪክ እያላዘነ፣ ታሪክ እየረገመ፣ ታሪክ እያደነቀ አይኖርም፣
• ሥርዓት ከጣስኩ ከግንቦት ሰባት፣ ከኦብነግ እና ከኦነግ በምን እሻላለሁ፣
• ለኢህአዴግ ብቁ ያልሆኑ ሰዎች በልካቸው አዲስ “ድርጅት ይፈጥራሉ”
Read full story in PDF  http://www.zehabesha.com/wp-content/uploads/2012/12/sibehat-nega.pdf

ተወካዮች ምክርቤት አባላት በአዲስ አበባ ለኢህአዴግ የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስል ጉብኝት አደረጉ


የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ አልተጋበዙም
ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በአዲስ አበባ የተወካዮች ም/ቤት አባላት በአራት ተከፍለው የአዲስ አበባ መስተዳድር
ሰራሁዋቸው ያላቸውን ተለያዩ ስራዎች እንደጎበኙ የደረሰን መረጃ አመለከተ፡፡ የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ብቸኛ የተቃዋሚ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ሳይጋበዙ እንቀሩ መረጃው ይጠቁማል፡፡
ከጉብኝቱ በሁዋላ በሂልተን ሆቴል ከፍተኛ የምሳ ግብዣና ፌሽታ ያደረጉት የምክር ቤት አባላቱ ለጉብኝታቸው
ምክንያት የሆነው ሚያዚያ ውስጥ የሚካሄደው የአዲስ አበባና የወረዳ ምርጫ ሳይሆን እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡
አሁንም ያለተወዳዳሪ በሽፍንፍን ምርጫ አሸናፊ ሆኖ መውጣት የሚፈልገው ኢህአዴግ የምክር ቤት አባላቱ
ሰራሁዋቸው ለሚለው ልማት ዕውቅናና አድናቆት እንዲሰጡ በማድረግ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ በማካሄድ የምርጫ
ቅስቀሳው አካል እንዳደረጋቸው አስተያየት የጠየቅናቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ነግረውና፡፡

ESAT Daily News Amsterdam 25 December 2012 Ethiopia

አፋሮች በብዛት እየታሰሩ ሴቶቻቸውም እየተደፈሩ ነው ተባለ


ኢሳት ዜና:-ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ በአፋር አካባቢ የሚደርሰው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መጨመሩን የአካባቢው ተወላጆች ተናግረዋል።
ህዳር 20 ቀን 2005 ዓም በዱብቲ ወረዳ ቀይ አፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ፋጡማ ኡህመድ ገዶ የተባለች የ11 አመት ልጅ ተደፍራ መሞቷን የልጂቱ አጎት ለኢሳት ገልጸዋል። ልጂቷን የደፈሩት ሰዎች መንግስት ለስኳር ልማት ስራ ብሎ ያመጣቸው ሰራተኞ ች ይሁኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት  ለማወቅ እንዳልቻሉ የልጂቷ አጎት ገልጸው፣ ይሁን እንጅ የአፋር ተወላጆች እንዲህ አይነት ድርጊት እንዳልፈጸሙ በእርግጠኝነት ተናግረዋል።  የአካባቢው ባለስልጣናት ጉዳዩን ይፋ ቢያወጡ እርምጃ እንደሚወስዱባቸው እንደዛቱባቸው የልጂቷ አጎት ገልጸው፣ በድርጊቱ የተበሳጩ የጎሳው አባላት ተቃውሞ እንዳያሰሙ  የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው እንዲሰፍር መደረጉን ተናግረዋል።
በአካባቢው ምንም ሰላም እንደሌለ የተናገሩት ነዋሪዎች ፣ ለስኳር ልማቱ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ተጠይቀው ፈቃደኛ ያልሆኑ በርካታ ሰዎች ወደ እስር ቤት መጓዛቸውንም ገልጸዋል።
በቅርቡ ደግሞ ሩቢ ኢብራሂም አሊ የተባለች የ8 አመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ ወደ አዲስ አበባ ጦር ሀይሎች ሆስፒታል መላኩዋን እስካሁን ድረስ ሊሻላት እንዳልቻለ አንድ በአፋር ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ እናት ተናግረዋል። ግለሰቡዋ ኢሳት ችግራቸውን ለመዘገብ ስለደረሰላቸውም ምስጋና አቅርበዋል
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሃለፊ የሆኑት አቶ ገአስ አህመድ ለኢሳት እንደተናገሩት ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ በአካባቢው ያለው ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ገልጸዋል።
በክልሉ ያለውን ችግር ለአለማቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ድርጅታቸው እየሰራ መሆኑንም አቶ ገአስ ገልጸዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ የአፋር ገድሌ እየተባለ የሚጠራው ታጣቂ ሀይል በአፋር አካባቢ መንቀሳቀሱ መሰማቱን ተከትሎ ዞን 1 እዳር ወረዳ አካባቢ ያለው ሰራዊት ተንቀሳቅሶ ህዝቡ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ እና ታጣቂው ሀይሉን እንዳይቀላቀል ኬላዎች መዘርጋታቸውን የአፋር ጋድሌ ወታደራዊ ጉዳይ ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል  መሀመድ አህመድ ተናግረዋል

ሁለት የአረና አባላት የድርጅቱን ልሳን ሲበትኑ ተያዙ


ኢሳት ዜና:-አረና ፓርቲ በየሶስት ወሩ ማሳተም የጀመረውን የድርጅቱን ልሳን ሲያሰራጩ የተገኙ 2 የድርጅቱ አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የመቀሌ የአረና  ጽህፈት ቤት ተጠሪ የሆኑት አቶ ሱልጣን ህህሸ ለኢሳት እንደተናገሩት አቶ አያሌው በየነና አቶ ተካልኝ  ታደሰ የተባሉት ድርጅቱ አባላት የተሳሩበት ምክንያት የፓርቲውን መታወቂያ አልያዛችሁም ተብለው ነው። ይሁን እንጅ ፓርቲው እስረኞቹ የድርጅቱ አባላት መሆናቸውን ለአካባቢው ፖሊስ መግለጹን አቶ ሱልጣን ተናግረዋል።
ትናንት ሰኞ እለትም በሁመራ አደላይ ቀበሌ ሌላው አባላቸው ወረቀት ሲበትኑ መያዛቸውን ፣ የጽህፈት ቤታቸው ሰንደቅ አላማ የሚውለበለብበት ምሰሶ መሰረቁንም ገልጸዋል።
በአረና ትግራይ አባላት ላይ የሚፈጸመው እንግልት እየጨመረ መምጣቱን ድርጅቱ በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል።
በጉዳዩ ዙሪያ የሽራሮ ፖሊስ አመራሮችን ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

Total Pageviews

110536

Translate