Pages

Jun 23, 2013

የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል

ዛሬ ወያኔ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያፈናቀላቸው አማሮች የመጀመሪያዎቹ የወያኔዎች የጥቃት ሰለባዎች አይደሉም። የመጨረሻዎቹም አይሆኑም። ወያኔ ከነ ጸረ አማራ ፖሊሲው በስልጣን እስካለ ድረስና በአማራ ስም አማራውን እያፈኑ፣ እየሰለሉ ከወያኔ ፍርፋሪ እየለቀሙ ለመኖር የቆረጡ ከአማራው መሃል የወጡ ከሃዲዎች አማራውን መቆጠጠር እስከቻሉ ድረስ የአማራ ህዝብ መራቆት፣ ስደት፣ ውርደት፣ ሰቆቃና ሞት የማይለዩት ህዝብ እንደሆነ ይቀጥላል።

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ይህን በእብሪትና በጥላቻ የተሞላ በወያኔ የሚፈጸም በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የባላጌዎች ጥቃት ማስቆም የሚቻለው የወያኔን እብሪት በጠመንጃ እና በተባበረ የህዝብ አመጽ ማስተንፈስ እስከተቻለ ብቻ ነው ብሎ ያምናል። እስካሁን ወያኔ በከንቱ ያፈሰሰውን የንጹሃን አማሮች ደም መፋረድ የሚቻለው ከጠምንጃ አፈሙዝ በሚወጣ እሳት ብቻ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል። ከንፈር መምጠጥ፣ ዋይታ፣ ኡኡታ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰላማዊ ሰልፍና በየፈረንጅ በር ደጅ መጽናት ወያኔ የአማራን ህዝብ ቅስም ለመስበር የወያኔ እንጨት ሰባሪና ውሃ ተሸካሚ አድርጎ፣ ነጻነቱንና ክብሩን ገፎ አዋርዶ ለመግዛት የዘረጋውን መርሃ ግብር እንዲያጥፍ አያደርገውም።
ወያኔ ይሉኝታ ያልዘራበት፣ ትእግስትን እንደፍራቻ፣ አርቆ ሳቢነትን እንደሞኝነት የሚቆጥር በአማራው ላይ ቂምና ጥላቻን ሰንቆ የተነሳ ጨካኝ ድርጅት ነው። ይህን ድርጅት ስለጀግንነቱና ስለወርቅ ዘርነቱ እጅግ የተሳሳተና የተጋነነ ግምት ያለው፣ ማንም ምንም አያደርገኝም በሚል ትምክህት ተወጥሮ የሚኖር ድርጅት ነው። ከእንዲህ አይነቱ በራሱ ፕሮፓጋንዳና ከንቱ ውዳሴ ከሰከረ ድርጅት ጋር የሚደረግ ትግል ያለምንም መወላወል በከፍተኛ እልህና ጭካኔ የሚካሄድ ብቻ ነው። የአማራውን ሰቆቃ ለማስቆም ወያኔ “እዩኝ እዩኝ” እንዳለለ “ደብቁኝ ደብቁኝ” እስከሚል የሚዘምቱበት እና ክንዳቸውን የሚያሳዩት ጀግኖችን ይሻል። ከወያኔ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው ገድለው ለመሞ ት የቆረጡ የወገን ደምመላሾችን ይጠይቃል። ቤታቸውን ዱርና ገደሉን አድርገው፣ “ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል” የሚሉ ቁጡዎችን ይፈልጋል። የአማራውን ህዝብ እልቂት ለማቆም፣ የወንድ ልጅ እናት በገመድ የምትታጠቅበት፣ ልጇን አሞራ እንጂ ሰው የማይቀብርበት ሌላ ታሪካዊ ዘመን መምጣቱን ሁላችንም መቀበል ይኖርብናል።
የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል አባላት ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በሚያሳየው እብሪት ተቃጥለናል። በግነናል። የእዚህ እብሪት ማርከሻ ጠመንጃ ነው፡ እሳትና አርር ብቻ ነው ብለናል። ሌላው ሁሉ አማራጭ ተፈትሿል፣ተሞክሯል፣ታይቷል ሌላ አማራጭ የለም ብለናል። የቀረው አንድ ምርጫ ነው፦:መሞ ት ወይም መግደል ። እኛ ይህን አውቀን ከያለንበት ተጠራርተን የአማራን ህዝብ በቀላሉ ልንደርስበት በምንችልበት ምድር እየተሰባሰብን ነው። የከፋህ፣ የመረረህ፣የተበደልክ በቃኝ ያልክ ና ተቀላቀለን፣ የወገናችንን የአሳርና የመከራ ዘመን ማብቃት በወያኔ ቀብር ላይ እናረጋግጥ ።
ውድመት ለአማራ ህዝብ ጠላት ለዘረኛው ወያኔ!!!!!!!!!
ድል በወያኔ ለሚረገጡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!!!!!!!!!!!!
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ

tplf addis

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::
ደርግ
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::
ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::
ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ ወር 1966 ዓ.ም. ተሰብስበው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው “ኢትዮጵያ ትቅደም ፣ አቆርቋዥ ይውደም” በሚል መርህ ስር ሰፊ ሊባል የሚችል የህዝብ ድጋፍም አግኝተው ነበር::
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የተመሰረተው አስተባባሪ ኮሚቴ ንጉሱን ከስልጣን አውርዶ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” የሚል ስም በመያዝ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀመረ:: ቀስ በቀስም ደርግ የስልጣን ወንበሩን በማመቻቸት የሃገሪቷ መንግስት ለመሆን ቻለ::
በወቅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት ሶሻሊዝም ወይም ህብረተሰባዊነት በሚባል ርዕዮተ አለም እድገት እና ብልጽግና የማይገኝበት “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ስርዓት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና ፕሮፖጋንዳ አለምን እንደማዕበል ሲወዘውዛት የነበረበው ሁኔታ ሆኖ በደርግ የተመሰረተው መንግስት ግራና ቀኙን ሳይመለከት ሶሻሊዝም በኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈጥረውን ቀውስ እና ችግር ሳያጤን እና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ሳያማክር በ1972 ዓ.ም. ኢሰፓአኮን(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) መሰረተ:: ይህንን ምስረታ ተከትሎም ደርግ አንድ እግሩን ገደል ከተተው::
በዚህ ጽሁፍ ሁለት ነገሮችን ለያይቼ በማሳየት ለማለፍ እሞክራለሁኝ፤
  1. ደርግ እንደ ፖለቲካ ተቋም እና ስርዓት
  2. መለዮ ለባሹ እንደ አገር መከላከያ ሰራዊት
ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያዊ የሆነ እና በዘመናዊነቱ በአፍሪካ ጭምር ተወዳዳሪ ያልነበረው እንደነበር ነው:: የደርግ ስርዓት ከወታደሩ በወጡ ሰዎች ቢመሰረትም ሰራዊቱ ግን በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለመሆኑ ከጥያቄ ውስጥ ሊያስግባው የሚችል አንዳችም መከራከሪያ ሊቀርብ አይችልም:: አገራችን ዘመናዊ ጦር ማደረጀት ከጀመረችበት ከሃያኛው ክፍለዘመን መባቻ ጀምሮ በስንት ወጪ እና ጥረት የገነባችውን ጦር የ “ደርግ ጦር” የሚል ቅጽል በመስጠት ከፍተኛ የሆነ የስም እና የሞራል ማጥፋት ዘመቻ የፈጸሙበት ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት ወያኔ እና ሻዕቢያ ናቸው::
ይህ ጦር ደሙን አፍስሶ ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፤ ራበኝ ፣ ደክመኝ ሳይል ወያኔ እና ሻዕቢያን እግር እግራቸውን እየተከታተለ ሲደመሥሳቸው እና ሲያጠፋቸው የነበረ የኢትዮጵያ ብርቅ ልጅ ነው:: የዛሬው የወያኔ ዘረኛ ሰራዊት ግን እንኳን ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሊከላከል ይቅርና ራሱ የወያኔ ሰራዊት ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ የአንድ ጎጠኛና ዘረኛ ታጣቂ ቡድን ነው:: አሁን ያለው በዘር የተደራጀው ቅጥረኛ እና ባንዳ ሰራዊት በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ የለም::
የደርግ መንግስት በስልጣን በቆየበት 17 አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ቀይ ባህርን የጠበቀ ፤ ከገንጣይ እና አስገንጣዮች አገሪቷን እየተከላከለ ሉዓላዊነትን የጠበቀ የኢትዮጵያ ስርዓት ነበር::
በሚከተለው ርዕዮተ አለም ቀስ በቀስ እየተዳከመ በመሄድ እንደነበረው አገርና ህዝብ ለማዳን አልቻለም:: ደርግ በተዳከመ ጊዜም ሰራዊቱ ይዳከማል:: አንድ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከመንግስት የሚቀርብለት ነገሮች ብዙ ናቸው:: ይህ አልሆነም:: ሰራዊቱም መንግስት በመዳከሙ ምክንያት የነበረው አልበገር ባይነት ስሜቱ እና ጀግንነቱ የውጊያ ብቃቱ ተስፋ በመቁረጡ ችግር እየፈጠረለት ሄደ ቢሆንም ግን ወያኔም ሆነ ሻዕቢያ አሁንም ፈቀቅ ሊሉ አልቻሉም:: የማይበገር የኢትዮጵያ ሰራዊት መሆኑን ያውቁታል እና::
ይህ በዚሁ እንዳለ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት መንግስቱ ሃይለማሪያም ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለቀው ዚምባብዌ ሃራሬ ገቡ:: እዛም ጥገኝነት ጠየቁ:: መሆን የማይገባውን ስራ ሰሩ:: በኢትዮጵያ ሃገራቸው ሰርተው ሂወታቸው ቢያልፍ ታላቅ ስምና ክብር ያገኙ ነበር:: ግን አላደረጉትም:: ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሰራዊት ተበተነ::
ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፕሬዚደንት መንግስቱ እግር የተተኩት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን በዜና እወጃ የኢትዮጵያ ሰራዊት የነበርከው በያለህበት ቦታ መሳሪያህን ለህወሃት(ኢህአዴግ) እና ለሻዕቢያ እያስረከብክ ወደ ምትፈልግበት ሂድ፤ ሻዕቢያም ኤርትራን ህወሃትም ኢትዮጵያን እንዲቆጣጠሩ ፈቅደናል በማለት ፍጹም ክህደት በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ እና ህዝብዋን ለደመኛ ጠላቶች አሳልፈው ሰጡ::
ያን በወታደራዊ ሳይንስ እና የጦር ውጊያ የተከማቸ እውቀት እና ችሎታ የነበረውን የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እልም ባለ ገደል ወረወሩት:: ለስንት አመታት የሃገሩን ዳር ድንበር ያስከበረ እና የጠበቀ ጦር ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. ካልምንም መተዳደሪያ እና የአገልግሎት ክፍያ በየበረሃው ተበተነ:: በስንት ሚሊዮን የሚቆጠሩ የምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ አየር ወለድ እና አየር መቃወሚያ አባላት እና ቤተሰቦች ለመከራ እና ለችግር ተዳረጉ::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔና ሻዕቢያ:: ሻዕቢያ ኤርትራን ሲቆጣጠር ወያኔ ህወሃት ደግሞ ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፈንደቀለት ጸሃይ አዲስ አበባን ግንቦት 20 ቀን 1983 ተቆጣጠረ:: ኢትዮጵያም ለፋሺስት መሪዎች ተዳረገች:: ሰራዊቱ እየጫነ ካለምንም ችግር ካለ ምንም ውጊያ ወያኔ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ:: ከግንቦት 20 ቀን ጀምሮ ወያኔ በከፊል የተቆጣጠረው ወሎ ፣ ጎንደር እና ጎጃም ብቻ ነበር:: ቀሪው የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ ደቡብ ምስራቅ-ምዕራብ ወያኔ የገባው ከሶስት ወር በኋላ ነበር እንጂ:: ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠረም:: ወደ አዳዲስ ክፍለ ሃገራት ሲሄድ ብዙ ገንዘብ በመክፈል በነዋሪዎች እየተመራ ነው:: ምክንያቱም ወያኔ ህወሃት ከትግራይ አይወጣም ነበር::
ስለሆነም ለኢትዮጵያ ነጻነትና ዲሞክራሲ ስል ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ የሚለው ከንቱ ውሃ የማይቋጥር መፈክሩ ይህ ትልቅ ምስክርነት የሚያሳየው ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደማያውቃት ነው::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ምን ይዛ መጣች? በግንቦት 20 ኢትዮጵያ አገራችን በጨለማ ጉም ተሸፈነች:: አገርና ህዝብ ጥቁር የሃዘን ልብስ ለበሱ:: ሲጠሏት እና ታሪኳን እና ህዝቧን ሲያዋርዱን ሲያንቋሽሹ በነበሩት ወያኔ ህወሃት ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተዳረገች:: ዘረኛው እና ጎጠኛው ወያኔ ህወሃት በመለስ ዜናዊ የሚመራው የማፍያ ፋሺስት ግልገል እና ግብረ አበሮቹ ጸረ ሀገር እና ጸረ ህዝብ የሆኑትን ለዘመናት የተከበረው የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው የግልገል ፋሺስቶች መንደላቀቂያ ሆነ:: እነሱም ስልጣን እንደጨበጡ ኤርትራን አስገንጥለው የቀይ ባህር ንግስት የነበረችው ኢትዮጵያ ወደብ ወይም የባህር በርዋን አጥታ አንገትዋ የተቆረጠ ዝግ አገር አደረጉዋት::
ወያኔ ህወሃት ከደደቢት ይዞት የመጣውን ህገ ደንቡን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አደረገው:: ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት አጠፋዋለሁ ብሎ ያመጣውን የዘረኝነት ህጉን በኢትዮጵያ ዘረጋ::
ይህ በዚህ እንዳለ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እና ግንቦት 20 ምን ይዞለት መጣ? የኢትዮጵያ ህዝብስ ከግንቦት ሃያ ቀን ምን ተጠቀመ? ምን እድገት አገኘ? ፍትህና ነጻነቱ እንዲሁም ሰብዓዊ መብቱስ እንዴት ሆነ? የሃገሪቷ ሃብትስ በትክክል ለህዝብ ጥቅም ዋለ ወይስ ምን ሆነ? የትምህርት እድገቱስ? የዘመናዊ ቴክኖሎጂስ ለህዝብ ተስፋፋ ወይ? ሌላም ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል:: ለሰው ልጅ አደገኛ ጠንቅ ዕጽ መስፋፋት ለምን? ሽርሙጥና መስፋፋት ለምን? ስራ አጥነት ፣ የወንጀል ድርጊት መስፋፋት እንዴት እና ለምን? የህዝብ መፈናቀል ለምን? የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ ስለምን ተደረገ? ወዘተ ::
ወደ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ከ17 አመታት በፊት ወያኔ ህወሃት እንደተፈጠረ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. የትግራይ ህዝብ የአደረበትን ስሜት ባጭሩ ልዳሥ::
ወያኔ ህወሃት በዚሁ ቀንና ወር ደደቢት በረሃ ሲወጣ የትግራይ ህዝብ የዚሁ እኩይ ድርጅት ማንነቱን አያውቅም ነበር:: ቀስ በቀስም በየቦታው ብቅ ጥልቅ ሲል የትግራይ ህዝብ አልተቀበለውም::በህዝቡ ወያኔ ህወዋት ተቀባይነት በማጣቱ የተነሳ ምክንያት ጭንቀትን ንዴት የተነሳ በሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ:: አስገድዶ ንብረቱን መውረስ እና አስገድዶ እርዳታ እንዲሰጥ ተደረገ:: ምክንያቱም የሚከላከልለት ረዳት የሌለው ህዝብ ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ጀብሃ ሶስቱ በየፊናቸው አስቸገሩት:: የትግራይ ህዝብ ከየቦታው እየተለቀመ ተገደለ::
ከዚህም ቀጠል በማድረግ ወያኔ ህወሃት በሃይማኖት ጣልቃ በመግባት ክርስቲያን ጸረ ክርስትና እስላሙ ጸረ እስልምና ሃይማኖታቸውን እንዲያወግዙ የተቻለውን ቢሰራም አልሆነለትም::
ጸረ ህወሃት እና ጸረ ሻዕቢያ እየተባሉ ያልሆነ ያላሰቡት ብዙ ፣  ብዙ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች ሃለዋ ወያኔ (06) እየገቡ እሱም/እርሳውም ተገድለው ቤት ያፈራው ሃብታቸው ተወርሰው ህጻናት አልባሌ ቦታ ወድቀው ቀርተዋል::
በየከተማው ወያኔ ህወሃት ሽብርተኞች () በማሰማራት በጠራራ ጸሃይ ብዙ ሰው ገድለዋል:: ህወሃት የትግራይን ህዝብ እንደግሉ መሳሪያ አድርጎ የሚናገረው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያ ትግሉ ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ለወደፊትም አልተቀበለውም:: አይቀበለውምም:: ህወሃት የሚቀልደው ያለ ጉልበቱ ተማምኖ ነው:: ለዚሁም ዋና ምስክር ምርጫ 97 ዓ.ም. ትግራይ ወያኔ አልመረጠውም:: ለወደፊቱም ወያኔን አይመርጥም:: ሁለቱ ሊታረቅ የማይችል ቂም አላቸውና::
ወያኔ ህወሃት የትግራይ ወጣት ሴት ፣ ወንድ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት በማያውቁት የኤርትራ በረሃዎች ሞተዋል:: እዛው አጥንታቸው ተበታትኖ መቅረቱ የትግራይ ህዝብ እስከ አሁን ደም እያለቀሰ ያለበት ጊዜ ነው::
በአጠቃላይ በትግሉ ወቅት በትግራይ ህዝብ ወያኔ ህወሃት የፈጸመው ግፍ በከፍተኛ ወንጀል የሚይስጠይቀው ነው:: የትግራይ ህዝብ ወያኔ የተፈጠረባት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. በሚከበርበት ጊዜ በየቦታው የሚጠራበት ስም አለው:: በተምቤን አካባቢ “የተረገመች ቀን” ሲላት በአድዋና አክሱም አካባቢ “የጨለማ ቀን”" ሲለው በሽሬ አካባቢ ደግሞ “የእልቂት ዘመን” ይለዋል::
ወያኔ ህወሃት በለስ ቀንቶት አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ቀን ግንቦት 20,1983  ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በደመኛ ጠላታቸው የወደቁበት እና በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ የመጣበት ቀን ነው::
ከዚሁ ቀን መነሻ በማድረግ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ የነበረው ቂም በቀል በማያቋርጥ ሁኔታ በ22 አመት የወያኔ ህወሃት አገዛዝ የወረደበት ግፍና ሰቆቃ ቀጥለን ባጭር ባጭሩ እንመልከት::
ግንቦት 21 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔ ኤርትራን አስገነጠለ:: ኢትዮጵያንም ካለ ባህር በር አስቀራት::
ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ዝነኛው ምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ ፖሊስ ወዘተ የጠላይ ጦር በማለት ይደርግ ስርዓት በራሱ ሂደት ተመናምኖ በወደቀበት ለብዙ አመታት የሃገሩ ዳር ድንበር ሲያስከብር ከጠላት ሲከላከል የነበረው ካለምንም ጡረታና መተዳደሪያ የ”ጠላት ጦር” በማለት ለልመና እና ለችግር ዳረገው:: የሚይስተዳድራቸው ቤተሰቡ በሚልዮኖች የሚቆጠር ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ተበታትነው ቀሩ:: ከትግራይ ይዟቸው የመጣ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሃገር መከላከያ ሰራዊት አደረገ:: ቀሪዎቹን ታጋዮች ደግሞ ፖሊስ ፣ ደህንነት በማለት ዘረኛ ሰራዊት በኢትዮጵያ አቋቋመ:: ይህም በምንም አይነት ኢትዮጵያን የማይወክሉ ሁሉም ከላይ እስከ ታች ለነዚህ ተሰጠ:: እነዚህም በፊናቸው በኢትዮጵያ ህዝብ አስከፊ ሰቆቃና ግድያ በህዝቡ እየፈጸሙ ይገኛሉ::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማራ:: ዘር ማጥፋቱን ገና ከ1969 ዓ.ም. የጀመረው ሲሆን በበለጠ ደግሞ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አማራው ከያለበት እየተፈለገ ዘሩን ማጥፋት ተጧጧፈ ቀጥሎም ኦሮሞ ፣ ጋምቤላ ፣ አፋር ፣ ቤኑሻንጉል ወዘተ :: በትግራይ ውስጥም አደገኛ ጠላት ናቸው የሚላቸውን በዘዴ አጠፋቸው::
ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የአማራው ቋንቋ ስለሆነ ይህ ቋንቋ የትምህክተኛና የነፍጠኛው ቋንቋ በየትኛውም ክልል እንድይነገር በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ መገናኛው እና ሃሳብ ለሃሳብ የሚለዋወጥበት ለስንት ሺህ አመታት ሲጠቀምበት የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ህወሃት እያጠፋው ይገኛል:: በየትኛውም ክልል አማርኛ መናገር በህጉ ከለከለው::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ሲያበቃ ለዘመናት ኢትዮጵያዊው ህዝብ በፈለገው ቦታ ሲኖርና በጋብቻ በደም የተዋሃደው ህዝብ ከየክልላችሁ ከሌላ ቦታ የመጣውን ተስፋፊ ህዝብ አስወጡ በማለት እርስ በርሱ በማጋጨት ብዙ ሂወት ጠፍቶ ንብረቱም ተዘርፎ በየበረሃው ተበትኖ ግንቦት 20 ቀን 1983 ይዞት የመጣውን መከራ ገፈት ቀማሽ ሆነ:: በተለይ አማራው::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጉ አልበቃ ብሎት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሱዳን በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ በምትደዳርበት ገዳሪፍ በተባለው የሱዳን ግዛት አስተዳዳሪ በነበረው ሻለቃ ጉዌን የወሰን መስመር ለጣልያኖች ይጠቅማል በማለት በ1903 እ.ኤ.አ በህገወጥ መንገድ የነደፈው የመስመር ክልል በአጼ ምኒልክ ኋላም በአጼ ሃይለስላሴ እና በደርግ መንግስት ውድቅ የተደረገው እና ተቀባይነት ያጣውን ወያኔ ህወሃት ከየት እንዳገኘው ሳይታወቅ የኢትዮጵያን የወሰን ድምበር በመጻረር ለወዳጁ ሱዳን ከሰቲት ሁመራ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ወደውስጥ ከ40 እስከ 60 ኪ.ሜ. የሚዘልቅ እና 1,600ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ለሱዳን መንግስት የአንዲት ኢትዮጵያን ሰፊና ለም መሬት የሸጠ ወያኔ የሱዳን መንግስት ለውለታው ከገዳሪፍ እስከ መቀሌ የባቡር መንገድ እንደሚዘረጋ የሃገራችንን ሉአላዊነት በመድፈር ለግል ጥቅሙ ሃገራችን እያወደመ ያለ ስርዓት ነው:: የግንቦት 20 ቀን 1983 መዘዝ::
ወያኔ ህወሃት በተፈጥሮ ባህሪው አምባገነን እና ሽብርተኛ ድርጅት እሱን የሚቃወም እና የሚፈጽመው ግፍ እንዲነሳበት አይፈልግም:: ፍላጎቱ ተሳስተሃል አትበሉኝ:: ስለኔ አትናገሩ ከሚለው ፋሺስታዊ ባህሪው በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ እንዲኖር አይፈልግም:: የህዝቡ በነጻነት መናገር እና ሃሳቡን መግለጽ ለወያኔ እንደ እሳት የሚለበልበው ለመሆን የፕሬስ ነጻነት ያገደው:: ይህም እንደ ገዢ ፓርቲ ህወሃት የታገደ ነው:: በዚሁ ፖለቲካዊ ውሳኔ የነጻ ፕሬስ በማደን ፣ በማሰር ፣ በማንገላታት ሳያበቃ ብዙ የፕሬስ ጋዜጠኞች ሃገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመከራን ስደት ተዳረጉ:: ነጻ ፕሬስ በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ::
ወያኔ ህወሃት የሽግግር መንግስት ብሎ ከሰኔ ወር 1983 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር 1985 ዓ.ም.  በስልጣን በቆየበት ምርጫ በማለት በጸረ ዲሞክራሲያዊ መንገድ በ1987 ዓ.ም. , በ1992 ዓ.ም. , በ1997 ዓ.ም. እና በ2002 ዓ.ም. በማካሄድ በተለይ በ1997ዓ.ም. ቅንጅት በተለያዩ ፓርቲዎች ቀስተ ደመና ፣ መኢአድ ፣ ኢዴሊ ፣ ኢዴአፓ-መድህን ወዘተ በተጠናከረ ማዕከላዊ ፓርቲ “ቅንጅት” ተብሎ እንደተመሰረተ እምነቱ መሰረታዊ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲና እድገት ፣ ብልጽግና ፣ ፍትህ ፣ ነጻነት ፣ ከዘረኝነት የጸዳ በምርጫው ለመወዳደር በቀረበበት ምርጫም ተካሂዶ መሉ በሙሉ አሽንፎ ሲወጣ በአንጻሩ ወያኔ -ህወሃት/ኢህአዴግ በዜሮ ተሸንፎ ከምርጫ የወጣው በጉልበቱ ምርጫውን በመንጠቅ ድምጻችን አይነጠቅም ብለው የወጣውን ሰላማዊ ዜጎች በአግአዚ ቅልብ የመለስ ዜናዊ ጦሮች ግደሉት ብሎ ትዕዛዝ በመስጠት ብዙ ኢትዮጵያውያንን ሲገደሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ በየወህኒ ቤት በማሰር ወያኔ ህዝብ ያጠፋበት ቀን የሌባው አይነ ደርቁ ወያኔ በ2002  ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ እንደልማዱ ኮረጆውን በመገልበጥ 99.6% አሸነፍኩ ብሎ ኢትዮጵያና ህዝብዋን ማውደሙን ቀጠለ:: ይህ ሁሉ ችግርን ግድያ ሰቆቃ የግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. ውጤት ነው::
ወያኔ ህወሃት በፕሮግራም እንዳስቀመጠው የኤርትራ ጥያቄ ያላንዳች ጥርጥር ሃቀኛና ታሪካዊ መሰረት ያለወ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ነው በማለት ወያኔ ያመነበት ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የማያምንበት የኤርትራ ህዝብም ያላመነበት በኢትዮጳዊነታቸእው የማያምኑ መሆናቸው አንዳች ጥርጣሬ የለውም:: ድርጊቱ የወያኔ ብቻ ነው:: ይህ በዚህ እንዳለ አሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኤርትራ ግዛት አልነበረችም ሁሉ ተከታታይ ዘመናት በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሆና ስትተዳደር እንደነበረች ሁሉ ኢትዮጵያ በትክክል የሚያውቀው ሃቅ ነው:: አሰብን በኤርትራ ካርታ ጨምሮ በ1967 ዓ.ም. ያወጣው ወያኔ ብቻ መሆኑን በግልጽ የሚታወቅ ሃቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት ይህን የታሪክ እና የሃገር ክህደት የፈጸመው ሆን ተብሎ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ያደረጉት ኢትዮጵያና ህዝብዋ ጠላት ብለው ስለአስቀመጡት የፈጸሙት ጥቃት ነው:: ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ እንደተቆጣጠረ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የባህር በሯን አጣች::
ይህን በተመለከተ ወያኔ/ህወሃት እና ሻዕቢያ እንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ ከግንቦት 5 ቀን እስከ ግንቦት 9 ቀን 1983 ዓ.ም. የቀድሞው የአሜሪካ  ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የወያኔው መሪ መልስ ዜናዊ ባሉበት ስብሰባ ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ህዝብ ስላለባት የባህር በር ያስፈልጋታል:: አሰብም ከኤርትራ ያልተካለለ በመሆኑ በአጼ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ስርዓትም ከኤርትራ ውጭ ሆኖ በወሎ አፋር የተካለለ ስለነበር ቀደም ሲልም አሰብ ከኤርትራ ውጪ ሆኖ በጣሊያንም ብዙ ያልተደፈረች የኢትዮጵያ የባህር በር እንደነበረች ይታወቃል:: አሰብ የኢትዮጵያ የባርህ በር መሆን አለበት ብለው ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጣም ተናዶ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ የወደቀች ሃገር የነበሩ አመራር አጼ ኃይለስላሴ ሆኑ ደርግ ያስቀመጡት ካርታ ህወሃት አይቀበልም:: አሰብ የኤርትራ መሬት ነው:: እኛ አሁን በኢትዮጵያ ስልጣን የምንቆጣጠረው የወደብ ችግር አይኖረንም:: ችግር አይፈጠርብንም:: ብንፈልግ ጂቡቲን አሊያም የሶማሊያ እና የኬኒያን ወደቦች እንጠቀማለን:: አሰብ የኤርትራ ስለሆነ እምነታችንም ይህ በመሆኑ አሰብ የኤርትራ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም::
ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር እና ሌሎች አደረዳሪዎች አቶ መለስ ዜናዊ አሰብን የኤርትራ ነው ፤ የወደብ ችግር የለብንም ብለው እኛንም ስለአሳመኑን አሰብ በኤርትራ ውስጥ መካተቱን ተቀብለናል በመለት ሲዘጉት ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ታሪካዊና ጥንታዊው የባህር በርዎችዋን አሳጥቶ ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም. አገራችን ኢትዮጵያን በጠላቶችዋ እጅ የወደቀችበት የኢትዮጵያ ህዝብም በድቅድቅ ጨለማ እና ጭቆና ፋሽስት ስርዓት ይዛ የመጣች ይህች ግንቦት የተረገመች ቀን ናት:: በምስራቅ-ምዕራብ-ሰሜን-ደቡብ የሚገኙ ኢትይጵያውያንም እየተረገመች ነው::
ወያኔ ህወሃት በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በለስ ቀንቶት ወሮ በተቆጣጠረበት ወቅት የኢትዮጵያን ሃብት-ንብረት ወያኔና ሻዕቢያ ተባብረው ዘረፉት:: የወላድ መሃን የሆነችው ኢትዮጵያ ተከላካይ የሌላት ሁለት ከደደቢትን ከሳህል በረሃ የመጡት ሙሉ ሰራዊታቸውን በማሰማራት ሃብትዋን ንብረትዋን ዘርፈውታል:: የተለያዩ ተቋማት ተዘርፈዋል:: ጠቅላላ ጥሬ ገንዘብዋ ተዘርፏል:: ጥሬ ህብቶቿ ተዘርፏል:: የቀራት ነገር የለም:: ለውጪ ገበያ ለሺያጭ የሚመረት ቡና ፣ ሰሊጥ ፣ አደንጓሬ ወዘተ አይን ባወጣው ዝርፊያ ቀን እና ሌሊት ተፈጽሞባታል:: ዝርፊያው በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የጀመረው እስከ አሁን ቀጥለውበታል:: ኤርትራ የቡናና የቅባት ምግብ አምራች በመሆን በአለም ገበያ አቅራቢ ሆና ከዓለም 3ኛውን ደረጃ ያዘች:: ከኢትዮጵያ በተዘረፈው ጥሬ ሃብት ዋና ገንዘብ ወያኔ ህወሃት መሪዎች 1. መለስ ዜናዊ እና ባለቤቱ አዜብ መስፍን 2.ስብሃት ነጋ 3.አባይ ጸሃዬ 4.ስዩም መስፍን 5.አርከበ እቁባይ 6.አዲስ አለም ባሌማ 7. አባዲ ዘሙ 8.ጸጋይ በርሄ እና ባለቤቱ ቅዱሳን ነጋ 9.ተክለወይኒ አሰፍ 10.ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወዘተ ሆነው ኢፈርተን አቋቁመው ስልጣኑንም ተቆጣጥረው የናጠጡ ባለብዙ ፋብሪካዎች ትልልቅ ተቋማት መስርተው ቱጃር በለሃብቶች ሆነዋል:: ወያኔ ህወሃት ወደ ስልጣን ባልበቃበት ጊዜ በአጼ ኃይለስላሴና በደርግ ስርዓት ነጻ ተቋም በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያገለግሉ የነበሩትን ብሄራዊ ባንክን ፣ ንግድ ባንክን ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ፣ እርሻ ትራንስፖርት ፣ መአድናት ወዘተ ወያኔን ስልጣን እንደጨበጠ ሁሉን ከህዝብ በጉልበቱ ነጥቆ በመቆጣጠር የሃገርና የህዝብ ሃብት የህወሃት ተቋማት ሆኑ:: ይህም ወያኔ ህወሃት በከፍተኛ ወንጀል የሚጠየቅበት ከዋናዎቹ አንዱ ነው::
ወያኔ ከኢትዮጵያ የዘረፈው ገንዝብ እና ጥሬ ሃብት ኢፈርት በትግርኛ ት.እ.ም.ት የሚል ስያሜ በመስጠት በትግራይ ህዝብ ስም ሲያጭበረብር የትግራይ ህዝብ መነገጃ ማድረጉም ህወሃት በዚሁ ሌብነቱ በወንጀል የሚያስጠይቀው ነው:: በትግራይ ህዝብ ስም የወያኔ መሪዎች ነገዱበት እንጂ የትግራይ ህዝብ ከት.እ.ም.ት ተጠቃሚ አይደለም:: ህዝቡም ራሱ የሚናገረው ሃቅ ይህ ነው::
ወያኔ ህወሃት ድርጅት ነው ስንልም ህወሃት የተመሰረተውና እስከ አሁንም ያለው ህወሃት ግለሰቦች ተደራጅተው የፈጠሩት የማፍያ ስብስብ እንጂ በምንም ተአምር የትግራይ ህዝብን የማይወክል ነው:: በድርጅቱ የተሰባሰቡ ግለሰቦችን ያቀፈ:: ህዝብ ሌላ፤ ህወሃት ሌላ:: ህወሃትን የመሰረቱት ሰዎችም ጸረ ህዝብ እና ጸረኢትዮጵያ ናቸው:: ይህ ህወሃት ተብሎ የሚጠራ በሻዕቢያ የተመሰረተ ኤርትራን ነጻ ለማውጣትና ትግራይም የአማራው ቅኝ ግዛት በማለት የተነሳ ከጥዋቱ ኢትዮጵያዊነቱን የካደ የከሃዲዎች ስብስብ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች የገደለ ጸረ ህዝብ ነው:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ህወሃትን በእውቅና አልተቀበለውም::
ወያኔ ህወሃት ገና በ1968 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መሬት እጠቀማለሁ በማለቱ ከባድሜ እስከ አፋር ቡሬ የመሬት ቆዳ ስፋት 1.ታች አዲያቦ 2. ላይ አዲያቦ 3.ጭላ ወይም አንከረ ባሩካ 4. አሕሰኣ 5.እገላ 6.ዛላምበሳ  በዚሁ ውስጥ የሚጠቃለሉ ኢሮብ ፣ ጻልገዳ ፣ ዓውዳ ፣ አይጋ ፣ ሶቦያ ፣ ወዘተ 7.የአፋር መሬት  እስከ ቡሬ 8. አሰብ የኤርትራ መሆንዋን በዚሁ ፊርማቸው በ1969 ዓ.ም. አረጋግጠዋል:: 1. መለስ ዜናዊ 2.አባይ ጸሃዬ 3.ስብሃት ነጋ በዋናነት የሚጠቀሱ በትክክል የኤርትራን መሬት ነው በማለት ፈርመው የሰጡት ህዳር ወር 1969 ዓ.ም. ነው:: በዚሁ መሰረት የትግራይ ህዝብ 1.በሻዕቢያ 2.በጀብሃ 3.በህወሃት  በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ትተዳደራለህ ብለው በመወሰን ህዝቡም በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ቁም ስቃዩን በማየት ተገደለ:: ንብረት ሃብቱ ተዘረፈ:: አቤት የሚባልበት በማጣት በየስደቱ ተበታተነ:: ወያኔ ይህን ወንጀል እንደፈጸመ በአንጻሩ ከሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ለም ወሬት ነጥቆ ወሰደ::
የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዋና ጦሱ ከላይ እንደተጠቀሰው ነው:: የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መንስኤ   ው በግልጽ የሚታወቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት አመራር የሚያላክኩት በኢኮኖሚ ችግር የተፈጠረነው ሲሉ በተደጋጋሚ በተለይ የወያኔው መሪ ነበር መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳመን ለከት በሌለው ውሸቱ ሲለፋደድ ሃገር ሙሉ ያውቃል:: ቀሪዎቹ የሱ የአመራር አባላቱ ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃየ ፣ ስዩም መስፍን ፣ አርከበ እቁባይ ወዘተ የመለስ ዜናዊን ሃሳብ በማስተጋባት በየውጪ ሃገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማሳመን ብዙ ውጣ ውረድ ቢያደርጉም እስከ ዛሬ ተቀባይነት አላገኙም::
የጦርነቱ መንስዔ በኢኮኖሚ ሳይሆን በትክክለኛው አነጋገር በተጨባጭ ሁኔታው የመሬት ይገባኛል ነው:: ሻዕቢያ የኔ ግዛት ነው:: ከዚህ ቀደምም በ1969 ዓ.ም. ተስማምተን እናንተም የኤርትራ መሬት ነው በማለት ያመናችሁበትን አስረክቡን በማለት ወደ ጦርነቱ ሻዕቢያ እና ወያኔ ገቡ:: እውነቱ ይህ ነው:: ይህ በዚሁ እንዳለም የኢኮኖሚው ጉዳይም አስተዋስኦ ያደረገበት አለ:: ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ከ1983 ዓ.ም. ግንቦት ወር ጀምሮ እስከ 1990ዓ.ም.  የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ የግላችን የኢትዮጵያ ሃብት ደግሞ የጋራችን ተባብለው በህወሃት መሪዎች መጠነ ሰፊ ድጋፍ ሁለቱ ማለት ሻዕቢያና ወያኔ የሃገራችን ኢትዮጵያን ጥሬ ሃብትዋን መዓድኗን እና ሃገሪቱ ያፈራችውን የተለያዩ ፋብሪካዎቸ እና ባንኮችን አብረው ተባብረው ዘርፈዋል:: ኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ኤርትራውያን ጤፍ በየአይነቱ ዳጉሳ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ ወዘተ በርካሽ ዋጋ ኤርትራ ሲሸጥ የኢትዮጵያ ገበያ ባዶ ቀረ:: ስለዚህ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ያ የለመዱት በሰው ሃገር ሃብት ሲንደላቀቁ የቆዩት አሁን ሲያጡት ለጦርነቱ አስተዋጽኦ ያደረገም ነበር:: በጣም ከሚገርሙ ነገሮች እና አሳዛኝ የሆነው ሁለቱ መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በስልክ ጥብቅ ግንኙነት እንደነበራቸው ብዙ ሰዎች ተናግረዋል:: ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃዬ እና ሌሎቹ የወያኔ መሪዎች በጣም የደመቀ ግንኙነት ከጦርነቱ ዋዜማ አንስቶ የወያኔ መሪዎች ይገናኙ እንደነበር ምስጢሩም የሚያውቁ ሰዎች ተናግረውታል::
ኢሳያስ አፈወርቂ ላቀረበው የአንድ ቢሊዮን ብር ላክልን መለስ ዜናዊ ሳያቅማማ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተፈቅዶ ገንዘቡ አስመራ እንደገባ በቀናት የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መቀሌ ውስጥ(ሃይደር) የሚገኘው የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤት በሚግ አውሮፕላን ደበደበው:: ከተዋጊ አውሮፕላኖቹ የተጣለው ክላስተር ቦምብ ወድያውኑ 53 ህጻናትና አስተማሪዎች ሲሞቱ 185 ደግሞ ከባዱ ቁስል ደረሰባቸው:: ለዚሁም ተጠያቂው መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ ናቸው::
የሻዕቢያ ተዋጊ ጀቶች እንደገና ተመልሰው ቦምብ ጭነው 48 ሰላማዊ ሰዎችን 10 ህጻናትን ሲገድሉ 150 ሰዎች አቆሰሉ:: በማለት ቢ.ቢ.ሲ. እና ሲ.ኤን.ኤን. የዘገቡት ዋቢ ነው:: ይህ ጥቃት የደረሰው በግንቦት ወር መጨረሻ 1990 ዓ.ም. ሆኖ አስራት አብርሃም በአሳማኝ ሁኔታ ከ’ሃገር በስተጀርባ’ በሚል መጽሃፉ እንደገለጸው መለስ ዜናዊን ኢሳያስ አፈወርቂ እስከ ታህሳስ ወር 1991 ዓ.ም. ይገናኙ እንደነበሩም ያስረዳል:: መለስ ዜናዊን ግብረአበሮቹ እነ ስብሃት ነጋ ወዘተ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ የባዕዳን ቅኝ ገዢዎች መሆናቸው በግልጽ የሚያሳይ እውነታ ነው::
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ሆን ብሎ ያሰናከለው መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ እና አባይ ጸሃዬ መሆናቸው ሲታወቅ ምክንያቱም በ1969 ዓ.ም. ከላይ የተጠቀሰ መሬት የኤርትራ ነው ብሎ ወያኔ የፈረመበት በመሆኑ ይህም በአልጀርሱ ስምምነት ወያኔ መሪ መለስ ዜናዊ አሳልፎ ለኤርትራ መስጠቱ የ1969 ዓ.ም. ትልቁ ማሳያ ነው:: የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት እነማን መሩት? ይህን እንመልከት::
1. መለስ ዜናዊ የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር …………………………………………ኤርትራዊ
2. ጻድቃን ገብረተንሳኤ የጦሩ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ……………………………………………..ኤርትራዊ
3. ሳሞራ የኑስ…ከፍተኛ ጀነራል…………………………………………………………………………………….ኤርትራዊ (በናቱ ከርከበት በአባቱ ሱዳናዊ)
እነዚህ ሶስቱ አመራር በምንም ተአምር ለኢትዮጵያ ይሰራሉ?? ጦርነቱን በትክክል ይመራሉ ብሎ ማሰብ “ላም አለችኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” አይነት ነው:: እነዚህ ትልቁ ምኞታቸው የኤርትራ ሰራዊትና ህዝብ እንዳይጎዳ ኢትዮጵያዊው ሰራዊት ቢያልቅ ምንም የማይሰማቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም የውጊያና ጦርነት አመራር ብቃት የሌላቸው በአጋጣሚ የተገኘው ጠ/ሚኒስቴርነት እና ጀነራልነት ከንቱ ነው:: ጠቅላላ የወያኔ ህወሃት መሪዎች ጀነራሎች እና ወታደሮች ከወታደራዊ ሳይንስ ያላቸው ርቀት ሰማይና መሬት ነው:: በ1991 ዓ.ም. ያለቀው ሰራዊት ተጠያቂም ናቸው::
2ኛው በዚሁ ኢትዮ ኤርትራ ውጊያ ሲመሩ የነበሩ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ታዛዦች ናቸው:: አታድርጉ ከተባሉ አያደርጉም:: በዋናነት ጎልተው የሚጠቀሱም::
1. ሰዓረ መኮንን
2.ዮሃንስ ገ/መስቀል (ቦጅቦጅ)
3.ታደሰ ወረደ
4.አብርሃ ወ/ማሪያም(ኳርተር)
5.ብርሃነ ነጋሽ ወዘተ ሲሆኑ ሌሎችም አሉ::
ስለሆነም በ1991ዓ.ም የደረሰው ውድመት ከ100,000ሺ ሰራዊት የሞተበት ወደ 200,000 የሚጠጋ ሰራዊት አካለ ጎዶሎ የሆነበት ግምቱ አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ ሃብት ንብረት የወደመበት ተጠያቂው ማነው??
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተፈጠረበት ምክንያት እና ሰበቡ ምንድነው?? እነዚህ ሁልቱ ጥያቄዎች መልስ በግልጽ ለማስቀመጥ እፈልጋለሁኝ::
1. በኢትዮ-ኤርትራ ለደረሰው ግድያና በጦርነት የወደመው ሃብትና ንብረት ተጠያቂዎች::
1. መለስ ዜናዊ
2. ስብሃት ነጋ
3.አባይ ጸሃዬ
4. አርከበ እቁባይ
5. ጻድቃን ገ/ተንሳኤ
6. ሳሞራ የኑስ
7. ስዩም መስፍን
እነዚህ በሰው ህይወት ለደረሰው እልቂትና ጉዳት በሃገሪቱ የደረሰው ከፍተኛ ውድመት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው::
በጦርነቱ የወደመው ሃብት እና ንብረት ተጠያቂውስ ማነው? ለሚለው::
1. መለስ ዜናዊ
2.ስብሃት ነጋ
3.ጻድቃን ገ/ተንሳኤ
4.አበበ ተክለሃይማኖት
5.ገዛኢ አበራ
6.ጀነራሉ በባለ ሌላ ማእረግ
7.ስዩም መስፍን
8.ብአዴን, ኦህዴድ እና የደቡብ ህዝብ ንቅናቄ
9. በወቅቱ የነበሩ የፓርላማ አባላት በሙሉ
10. የህወሃት ካድሬና ደጋፊዎች በሙሉ::
እነዚህም ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ሲሆኑ፤
3. የጦርነቱ መንስኤ ለሚለው ጥያቄ የህወሃት አመራር በ1969 ዓ.ም. ሻዕቢያ ላቀረበው የመሬት ይገባኛል በወቅቱ አምነት ተቀብለው በፊርማቸው ባረጋገጡት መሰረት በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት የሌለው የህወሃት ጥቂት የማፍያ ስብስብ በፈጸሙት ነገር ከሃዲዎች ከሻዕቢያ ጥቅም እናገኛለን ብለው የፈጸሙት ሚያዝያ ወር 1991 ዓ.ም. የፈነዳ ጦርነት ነው:: ተጠያቂዎቹም ህወሃቶች ናቸው::
በብዙ በርካታ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ሊከሳቸው ዝግጅቱን አጠናቅቆ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ነው:: ህወሃት እና መሪዎቹ ይከሰሳሉ:: አዎን ለፍርድም ይቀርባሉ::
የአይደ መዋእለ ህጻናት የአየር ጥቃትም የትግራይ ህዝብ ካቀረባቸው ክሾች ውስጥ አንዱ ስለሆነ በዚሁም በዋናነት የሚጠቀሱ መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ መሆናቸው ነው::
ግንቦት 20 ቀን1983 ዓ.ም. ይህን አይነት አሰቃቂ ድርጊቶችን አስከትላ ነው ብቅ ያለችው:: የተረገመችው ይህቺ ቀን ኢትዮጵያ ለምለም አገራችንን ለከሃዲ ባንዳዎች አሳልፋ የሰጠች::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ይዛው የመጣችው ሰቆቃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፈለገው የሃገሩ ግዛት የመኖር ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን መብቱን በህወሃት ከፋፍለህ ግዛ በሚመቸው ሃገራችን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ጠባብ ብሄረተኛ በሆነው መንገድ የዘር ፌደራሊዝም መሰረት ይህ የእቅድ ሃሳቡም አማራውን ለማጥፋት እና ለማክሰም የተቀነባበረ ሴራ ነው:: ይባስ ብሎም ሸዋ ጠ/ግዛት ለሌሎች ብሄራት በመስጠት ጎጃም በጌምድር ጠ/ግዛት ወሎ ጠ/ግዛት በታትነው አማራው መኖሪያ አልባ ተደረገ:: በተለያዩ ጠ/ግዛት ይኖር የነበረው አማራ ውጣ እየተባለ በወያኔ ህወሃት ከህጻን እስክ ሽማግሌ እየተገደለ በየበረሃው ወድቆ የዘሩን ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል:: ቀስ በቀስም ኦሮሞ ጋምቤላ አፋር ወዘተ ተመሳሳይ እጣ ደረሰባቸው:: በጠቅላላው ከተወለደበት ካደገበት ኢትዮጵያዊ ከመሬቱ የተፈናቀለ 24 ሚሊዮን ሲሆን በወያኔ ህወሃት የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ጥናቶች የሚያመለክቱተ 7.9ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ወያኔ ህወሃት እንደገደላቸው ያሳያሉ::
ግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሁለቱ ሃይማኖቶች እስልምናእና ክርስትና በእጁ አስገብቶ ለመቆጣጠር እና ቀስ በቀስም ሃይማኖቶቹን ለማክሰም ተነሳ::
1. የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት ለብዙ ዘመናት ወግና ህግጋቱን ጠብቆ የመጣ በብዙ ሚሊዮን እስልምና ተከታይ ያለው የኢትዮጵያ ቅርስና የምንኮራበት ሃይማኖት ዛሬ በወያኔ ህወሃት ተደፍሮ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሙሉ መብታቸውን ተነጥቀው በእስራት መከራ እየተሰቃዩ በገዛ ሃገራቸው ለክፉ ችግር ተዳርገዋል::
2.የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም በክፉ አደጋ ወድቃለች ቤተ ክርስቲያና እየተቃጠሉ ታሪካዊ ቅርሶችዋን በወያኔ ተዘረፉ::ወያኔ የሚቃወሙ ብጹአን አባቶች ለስደት ተዳርገዋል:: ብዙም ተገድለዋል:: ይህን ሁሉ የፈጸመው የወያኔ አባል የነበረው አባ ገብረመድህን ወይም አባ ጳውሎስ የሚባል በወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ ካደረገው ብዙ ወንጀል በቤተ ክርስቲያናችን ፈጽመዋል::
ለመሆኑ አቡነ ጳውሎስ ማነው??
አቡነ ጳውሎስ ትውልዳቸው ትግራይ አድዋ ያደጉትም እንዳባገሪማ ገጠር ነው:: እንዳባገሪማ የተባለበት ምክንያት በአክሱም ዘመነ መንግስት በንጉስ አልአሜዳ ብ470ዓ.ም. ከመጡት ተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ አባ ገሪማ ሲሆኑ ከአድዋ በስተምስራቅ የ18 ኪሎ ሜትር ርቀት የምተገኘው ተራራማ ቦታ አባ ገሪማ በጣም አስደናቂ ሆኖ የተሰራው ቤተ ክርስቲያናቸው በማነጽ እዛው ሞተው እዛው ስለተቀበሩ በዚሁ ምክንያት እንዳባገሪማ ተብላ ትጠራለች::የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያዋረዱን የቤተ ክርስቲያኗን ህገ ደንብ እና ቀኖናውን የለወጡ እና ያፈረሱ ፣ ለስጋቸው ያደሩ: አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሃይማኖት ለማጥፋት ጸረ ክርስትና የሆኑት ጳውሎስ የአድዋ ልጅ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ህጋዊ ሊቀ ቅዱሳን ፓትሪያርክ በቤተ ክርስቲያኑ ህግና ደንብ የተሾሙት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ወያኔ በሃይል አስወግዶ አባ ጳውሎስን ሾመ:: ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሀይማኖት ወግና ስርዓቱን ለማጥፋት የታቀደ ነው:: የቤተ ክርስቲያኑን ህግና ደንብ የሚጻረርም ነው::
አቡነ ጳውሎስ የወያኔ ህወሃት በአባልነት የመለለመሉት በ1976 ዓ.ም. ነበር:: በወቅቱ የሚነገረው ዶ/ር አባ ገብረመድህን የተባሉ የኛ አባል ስለሆኑ ትግራይ ሃገራችን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነጻ በምትወጣበት እኚሁ የትግራይ ፓትሪያርክ ይሆናሉ በማለት ስብሃት ነጋ በለመደው ወሬ ማዛመት በታጋይ ውስጥ ተሰራጨ:: ቢሆንም ግን ታጋዩ ብዙ ስሜት አልሰጠውም:: ምክንያቱም ሃይማኖት የለሽ የወያኔ አመራር በትግሉ ወቅት እግዚያብሄር የሚባል አማልክት የሚባሉ በፍጹም የሉም:: ይህ ለአማራው አገዛዝ እንዲመችለት የፈጠረው ከንቱ ሃሳብ ነው:: በማለት ስለአስተማሩን የአባ ገብረመድህንም ይህን ድባብ የሸፈነው ነበር::
ንገሩ እንደገና በ1980 ዓ.ም. መጀመሪያ ታድሶ መጣ የህወሃት አባል አባ ገ/መድህን ከአሜሪካ ሱዳን ድርስ መጥተው ስብሃት ነጋ የወቅቱ የህወሃት ሊቀ መንበርና መለስ ዜናዊ ሱዳን ድረስ በመሄድ እንደተገናኙ በድጋፍ መልክም $15,000 የአሜሪካን ዶላር መስጠታቸውን የሄዱት ሁልቱ የወያኔ አመራሮች በድብቅ ሳይሆን በግልጽ የተናገሩት ነበር:: ከዚሁም በተጨማሪ ሱዳን ካርቱም ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው በውስጡ የሚገኙ ቀሳውስት ካህናት ወደ ህወሃት አባልነት መልምለው በሶስተኛው ቀን ወደ መጡበት መመለሳቸም ተነገረ::ስብሃት ነጋ አቡነ ጳውሎስ የህወሃት መሪህ ባህታ(vanguard) ናቸው በማለት ይጠራቸዋል::
እንግዲህ የአቡነ ጳውሎስ ነገር ይህ ሆኖ ትግሬ በመሆናቸው ብቻም በደርግ መታሰራቸውን ብዙ ግፍ ተፈጸመብኝ የሚሉት አቡነ ጳውሎስ የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባላት እውነት ይሁን አይሁን ለነሱ ልተው:: ከሆነም አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንዋ ላይ በቂም በቀል ማወካቸው ከአንድ መናኝ አባት መፈጸም የሌለበት ፈጽመዋል:: ነብሳቸውም ለሲዖል ተዳርጋለች::
አቡነ ጳውሎስ የፓትርያርኩ ስልጣን አግባብ በሌለው መንገድ የተረከቡት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናት በምርጥ ካድሬነታቸው በዋልድባና በተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ብዙ ግፍ ከመፈጸማቸው በላይ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከየቤተ ክርስቲያኑ በማስወጣት ሸጠዋል::
ይህ ሁሉ በእስልምና ሃይማኖትና በክርስትና መዘዙ ይዞት የመጣው ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የተረገመች ቀን ናት::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያውያን እንደተቆጣጠረ ብዙ የዝርፊያ ተቋማት አመቻችቶ ነበር:: አገራችንን የተቆጣጠረው 1. ዋና ኢፈርት 2. ለም የኢትዮጵያ መሬት ለባዕዳን መሸጥ 3. ኢትዮጵያውያን ከተወለዱበትና ካደጉበት መሬት ማፈናቀል 4. ገዢ የሆኑት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተቋማት በህወሃት ቁጥጥር ውስጥ መዋል 5. ኢትዮጵያዊው የሃገሩ ዳር ድንበር ጠባቂ አማራው ማጥፋት ከዚህም ጎን ለጎን አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ማጥፋት እና ማክሰም:: 6.የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀ.አየር ኃይል ለ. ምድር ጦር ሐ.ባህር ሃይል መ.ፖሊስ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ የራሱን የህወሃትን ታጋዮች ከትግራይ የመጡ ሁሉ የኢትዮፕያ ምድር ጦርና አየር ኃይል ለማድረግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በራኡ መዳፍ ውስጥ ለማስገባትና ለመቆጣጠር ደህንነቱም ከላይ እስከ ታች በትግሬዎች ማዋቅር አላማው ነበር::
ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ የወያኔ አመራር መለስና ስብሃት ነጋ ባወጡት እቅድ ተግባራዊ ተደርገዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብ በእርሻ የሚተዳደረው መሬቱን ተቀምቶ ለባዕዳን ሳውዲ አረቢያ ፣ ህንድ ፣ እና ለቻይና ወዘተ ህወሃቶች ሸጡት:: በሽያጭ የተገኘው ገንዘብም ሆነ በነ መለስ ዜንዊና ባለቤቱ ወ/ሮ አዜብ እጅ ሲገባ ከመሬቱ የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በየበረሃው ወድቆ ለክፉ ችግርና መከራ ተዳርገዋል::
ወያኔ ህወሃት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማርቶ ህዝበ ኢትዮጵያዊ እያለቀ ነው:: አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ጠላት ነው ብለው ወያኔዎቹ ፈረጁት:: ለመሆኑ የቋንቋ ጠላት አለን?? ይህ ሁሉ በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የመጣ የኢትዮጵያ ህልውና አጠያያቂም ሆነ:: ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ያፈረሰ ህዝብዋንም ለችግር እና ለመከራ የዳረገ በጥቁር ታሪክ የሚመዘገብ የፋሺስት ወያኔ ህወሃት አገዛዝ ስርዓትና የጨለማ ዘመን በማለት ታሪ ዘግቦታል::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. አንቺ ጥቁር የታሪክ አተላ ቀን የስንቱን ኢትዮጵያዊያን ህይወት በላሽ?! ስንቱን ኢትዮጵያዊ ምሁራን የነጻ ፕሬስ እውቅ ጋዜጠኞች ለስደት ለመከራ ዳረግሽ?! ስንቱን ወጣት ሴት እና ወንድ ከሃገሩ ጠፍቶ የባህር ቀለብ ሆነ:: ስንቱስ በስደት ሂወቱ እየማቀቀ ለክፉ መከራ ተዳረገ:: ስንቱ ቤተ ሰብ አፈናቅለሽ የስንቱን ቤት አፈረሽው:: ወጣት የሴት ህጻናት ሽርሙጥና ዳረግሽ:: አደንዛዥ እጽ እና አሺሽ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ተራ የንግድ ገቢ ሆኖ ወጣቱ ትምህርት ተከልክሎ እቅቀት እና ስልጣኔ በኢትዮጵያ የጠፋበት ዛሬ በኢትዮጵያ ስራ አጥነት የተስፋፋበት የወንጀል ድርጊት በስፋት የሚፈጸምበት ህጻናት በየቆሻሻው የተጣሉ ምግብ አይነት ነክ እየለቀሙ የሚበሉበት የጎዳና ተዳዳሪ ጠዋሪ ማደሪትይ ያጡ ህጻናት ለአቀመ አዳም ያልደረሱ ልጆች ወንድ ሴት ማደሪያቸው በየመንገዱ ሆነ:: ህጻናት በርሃብ በየመንገዱ በየትምህርት ቤቱ አእምሮዋቸውን እየሳቱ የሚወድቁበ እርጉዝ ሴት መኖሪያ አልባ ሆና በየዱር ገደሉ እየወለደች ከተወለዱ ህጻናት ከ10 ህጻናት 6 በ3 እና በ 4 ወራቸው እየሞቱ ህክምና ጠፋ:: ውሃ ጠፋ:: መብራት ጠፋ:: አረ ስንት ጉድ ነው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የወረደው ግፍ::
የወያኔ ህወሃት አባል ድርጅቶች ህወሃት ራሱ የነዚህ ቤተሰብ ልጆች ውጭ አገር እየተንደላቀቁ ሲማሩ ሃገር ውስጥ ያሉ አመራሩ ደጋፊዎች በኑሮ ተንደላቀው በሙስና ተዘፍቀው የሃገር እና የህዝብ ሃብት እየዘረፉ ቀኑ ለነሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ የችግር ጨለማ መብቱ የተረገጠ ባሪያ ጥዋት ማታ በወያኔ ስርዓት የሚሰቃይ ግዞተኛ ባዕድ ሆኖ ያለበት ዘመን ነው::
ይህ ክፉ አረመኔያዊ የህወሃት አገዛዝ በዚሁ መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይቀጥል ሁሉ ኢትዮጵያዊ በአንድነት ይነሳ በህዝባዊ ትግል ወያኔን ከስረ መሰረቱ ነቅለን እንጣለው::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ገብረመድህን አርአያ
አውስትራሊያ

ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሌባ ተባባሪነት ለመደባቸው

ከጥቂት ሳምንታት በፊት(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ በከፍተኛ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ተከሰሱ። ሊቀትጉሃን አስታጥቄ በተመሰረተባቸው ክስ ጠበቆቻቸው ዋስትና ቢጠይቁባቸውም ፍርድ ቤቱ ግን ዋስትና ለመፍቀድ ወይም ላለመፍቀድ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ቢባልም ዘ-ሐበሻ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልደረሳትም።
l። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ
“ፕሬዚዳንት ግርማ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ክስ እንዲቋረጥ ጥሪ ማቅረባቸውን” ያትታል። ዜናውን
ለተመለከተ ከዘራፊው የወያኔ ስርዓት ጋር በመተባበር “አበባ የመትከልና አበባ የመቁረጥ ስልጣን” ብቻ ተሰጥቷቸው
ቁጭ ያሉት ፕሬዚዳንቱ እኚህን በርከት ያሉ አርበኞች አባቶችን ያስለቀሱትን ሊቀትጉሃንን ክሳቸው ተቋርጦ ይፈቱ
ሲሉ በድፍረት መጠየቃቸው የሌባ ተባባሪነቱ ለመደባቸው፤ ወይም ከሌባ ጋር መተባበር ሱስ ሆነባቸው እንዴ?
ያስብላል። የሪፖርተር ዜና እንደሚከተለው ነው። አንብቡትና ትዝብታችሁን ጣሉበት።
በከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው
የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት፣ ዋና ጸሐፊና
የአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ፣ የተከሰሱበት ክስ
እንዲቋረጥላቸው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ለፍትሕ
ሚኒስቴር የጻፉት ደብዳቤ ውድቅ መደረጉን ምንጮች ለሪፖርተር
አረጋገጡ፡፡
የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ
ለፕሬዚዳንት ግርማ በጻፉላቸው የመማፀኛ ደብዳቤ አማካይነት፣ ክሳቸው እንዲቋረጥላቸው ወይም በይቅርታ እንዲታለፉ
ፕሬዚዳንቱ ደብዳቤውን የጻፉት በፍትሕ ሚኒስቴር የሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ለአቶ ብርሃኑ ፀጋዬ መሆኑን
ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡
በከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት ክስ የቀረበባቸው
የኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ፣ ዋና ጸሐፊው ፲ አለቃ ሰጥአርጌ አያሌውና የአስተዳደርና
ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ አቶ በቀለ ሻረው መሆናቸው ይታወሳል፡፡
ፕሬዚዳንት ግርማ ተጠርጣሪዎቹ በአገራቸው የጀግንነት ታሪክ ከፍተኛ ቦታ እንዳላቸው፣ ለአገር ልማትም በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ
እገዛ እያደረጉ መሆናቸውንና ዕድሜያቸውም የገፋ መሆኑን በመግለጽ፣ መንግሥት ይቅርታ አድርጐላቸው ክሳቸው እንዲቋረጥ
በደብዳቤ መጠየቃቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በቁጥር መ/818/2005 የጻፉትን ደብዳቤ የተመለከቱት የፍትሕ ሚኒስቴር
ባለሥልጣናት ጥያቄው ተገቢ አለመሆኑን፣ ግለሰቦቹም የተጠረጠሩበትን የወንጀል ድርጊት ፍርድ ቤት ቀርበው በሚደረግ የግራ
ቀኝ ክርክርና የሕግ ሒደት ብቻ የሚታይ መሆኑን በመግለጽ፣ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረጉት ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
እነ ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ የተጠረጠሩበት ወንጀል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት አቶ አርከበ ዕቁባይ፣
አቅመ ደካማ ለሆኑ አባት አርበኞች የፈቀዱላቸውን 25 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለግል ጥቅም አውለዋል፣ ከሚያከራዩዋቸው
ሕንፃዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ የአከራይ ተከራይ ግብር አለመክፈል፣ ያላግባብ ወጪ ማድረግና በመሳሰሉት ተጠርጥረው
መከሰሳቸውን፣ ዋና ጸሐፊውና የአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊው እያንዳንዳቸው በ25 ሺሕ ብር ዋስ መለቀቃቸውንና
ፕሬዚዳንቱ ባለመቅረባቸው ታስረው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ (ሪፖርተር)

ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ተከሰሱ

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሊቀ
ትጉሃን አስታጥቄ አባተ በከፍተኛ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው
ተከሰሱ። ሊቀትጉሃን አስታጥቄ በተመሰረተባቸው ክስ ጠበቆቻቸው
ዋስትና ቢጠይቁባቸውም ፍርድ ቤቱ ግን ዋስትና ለመፍቀድ ወይም
ላለመፍቀድ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ቢባልም ዘ-ሐበሻ ይህ ዜና
እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልደረሳትም።
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል ችሎት የማታለል ወንጀል
ክስ የተመሰረተባቸው ሊቀ ትጉሃን አብረዋቸው ሁለት የማህበሩ
አመራሮችም ክስ እንደተመሰረተባቸው መንግስታዊ ሚድያዎችም ጭምር
ዘግበዋል። ለዘ-ሐበሻ እንደደረሱት መረጃዎች ከሆነ ሊቀትጉሃን በተለያዩ
ክሶች የተከሰሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል በ1998 ዓ ም ከአዲስ አበባ
ከተማ አሰተዳደር ለአቅመ ደካማ ጀግኖች አርበኞች የተሰጠውን 25 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለግል ጥቅማቸውና ለወዳጆቻቸው
አከፋፍለዋል የሚለው በዋነኝነት ተጠቅሷል።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አንድነት ማህበር ሊቀመንበርና አጋሮቻቸው የማህበሩን ሃብትና ንብረት ያለአግባብ ለግል
ጥቅማቸው እያዋሉትና እየመዘበሩት እንደሚገኙ፣ አንዳንድ የማህበሩ አባላት እንደገለጹለት ጠቅሶ አውስትራሊያ የሚገኘው
ጋዜጠኛ ቅዱስ ሃብት በላቸው ከወራት በፊት ዘገቦ እንደነበር ይታወሳል። ጋዜጠኛው ባጠናቀረው ዜና መሰረት የማህበሩ
ሊቀመንበር የሆኑት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ከጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ቁጥሩ ቀላል የማይባል ጥሬ ገንዘብና
ንብረት ለግል ጥቅማቸው አውለዋል። ከዚህም መካከል በዓመት 800 ሺህ ብር ከሚከራየው ህንፃ 240 ሺህ ብር፣ እንዲሁም
ካሳንቺስ አካባቢ የሚገኘው የማህበሩ ንብረት ከሆነው ቡና ቤት ኪራይ የሚገኘው 150 ሺህ ብር የት እንደሚገባ ተለይቶእንደማይታወቅ የማሕበሩን ም/ፕሬዚዳንት ጨምሮ ሌሎች የማህበሩ አባላት ማስታወቃቸውን፤ ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ መስተዳድር ለአቅመ ደካማ የማህበሩ አባላት እንዲከፋፈል የሰጠው 15 የቀበሌና 30 የኮንዶምኒየም ቤቶች ውስጥም የማህበሩ ፕሬዚዳንትና ጥቂት አመራሮች የግል ቤት እያላቸው ለራሳቸው ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ፤ የተቀረውንም ቢሆን አብዛኛውን ለቤተሰቦቻቸውና እነርሱ ለሚቀርቧቸው ጥቂት አባላት ማከፋፈላቸው ታውቋል ሲል ጋዜጠኛ ቅዱስሃብት በላቸው ዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ማህበር ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ድረስ በዱር በገደሉ ተማርተው የፋሺሽት ኢጣሊያን ጦር ድል
አድርገው ከአገር ባባረሩ አርበኞች የተቋቋመ ማህበር ነው።

Jun 22, 2013

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ? “ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”

hearing3
አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ “ክፉ ጠረን” አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ። አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” የዛሬ 22ዓመት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ከተናገሩት፡፡
“አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ (የነጻነት መንገዱን አትዝጉብን)። ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ … እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ አለ … እሱም እርቅ ነው … ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚው በኩል ዓመኔታ የሚጣልባቸው አሉ … ” አቶ ኦባንግ ሜቶ፡፡
“የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ የማይቀር ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። … ሕዝብ በጭቆና አገዛዝ እየተገዛ ዝም ብሎ የማይኖርበት ደረጃ ላይ ደርሷል … ዝም ብሎ ግን አይቀመጥም … ይፈነዳል … ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፡፡
አቶ መለስ “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው … እንደነበር አዲስ አበባ ሄጄ ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጫለሁ” ክሪስ ስሚዝ፡፡
“እድሜ ልካችሁን አትገዙም ብለን መክረናቸዋል” ዶናልድ ያማሞቶ፡፡
 hearing1የምክክሩ መድረክ
“ኢትዮጵያ ድኅረ መለስ፤ የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች የወደፊት ዕጣ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ፤ ከኢትዮጵያ ሁለት ተናጋሪዎች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ጸሐፊ ዶናልድ ያማሞቶ፣ የአሜሪካ የዓለምአቀፍ የልማት ተራድዖ የአፍሪካ ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ ኤሪል ጋስት፤ የማይክል አንሳሪ የአፍሪካ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ፒተር ፓሃም እንዲሁም በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግሥት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አዶቴ አክዌ የተጋበዙበት የምክክር ሸንጎ ላይ የቀረቡት ሃሳቦች በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ነበሩ። ሰብሳቢው በአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት በአፍሪካ፣ በዓለምአቀፍ ጤናና ሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ንዑስኮሚቴ ሰብሳቢ ክሪስቶፈር ስሚዝ ደግሞ ኢህአዴግ ከፍተኛ ገንዘብ አፍስሶ ያኮላሽው ኤችአር2003 የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረቂቅ ህግ ከሟቹ ዶናልድ ፔይን ጋር በማዘጋጀት በምክርቤት ለማስወሰን ያስቻሉ ነበሩ።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ እንዲሁም በበክኔል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት የግንቦት 7 ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደ እምነታቸው ንግግር አድርገዋል። ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። በምክክር ሸንጎው ላይ ከተጋበዙት መካካል ኢህአዴግ በቀጥታ ባለመወከሉ “ያለመመጣጠን (ያለመወከል)” ችግር አልነበረም፡፡ ኢህአዴግም ተገኝቶ ቢሆን ኖር ሊናገረው ከሚችለው በላይ ተናጋሪና ተከራካሪ ስለነበረው የኢህአዴግ መኖር አስፈላጊ አልነበረም የሚል አስተያየት ስብሰባውን በአካል ተገኝተው ከታዘቡና በቀጥታ ስርጭት ከተከታተሉ ወገኖች  ተደምጧል።
ያም ሆኖ ግን ምክክሩ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የበላይ ሰው ክሪስ ስሚዝ ቢሮ በመገኘት አሉ የሚሏቸውን መከራከሪያዎች አቅርበው ነበር። የጎልጉል ምንጮች ለማረጋገጥ እንደቻሉት ኢህአዴግ ምክክሩን ተከትሎ ኤች አር 2003 ረቂቅ ሕግ እንዳይጸድቅ የተጠቀመበትን መንገድ ገና ካሁኑ በድጋሚ ጀምሯል።
ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እያደር የእግር እሳት ሆኖ ያለፈውን የ1997 ምርጫ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት ከኢህአዴግ መሪ አቶ መለስ ጋር በርካታ ዲፕሎማቶች ተነጋግረዋል። አንዱ ከኒውጀርሲ ጠቅላይግዛት የአሜሪካ ም/ቤት ተወካይ ክሪስ ስሚዝ ነበሩ። “ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል የተዘጋጀውን የምክክር ሸንጎ በመሪነታቸው ሲከፍቱ አቶ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው …” በማለት ነበር የገለጹዋቸው። የርሳቸው ገለጻ ታዲያ ከሁለት ዓስርተ ዓመታት በፊት ኢህአዴግ እንዲነግስ ሲወሰን ከቃል በላይ እሳት እየተፉ ንግግር ያደረጉትን ኢትዮጵያዊ አስታወሰ – የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው የኢትዮጵያን ተላልፎ መሰጠት በዚሁ በሰኔ ወር ከ22ዓመት በፊት አስረግጠው በማስረጃና በማስጠንቀቂያ በመቃወመ፣ በማሳሰብ፣ እንደማይሆን በመምከር፣ አድሮ እንደሚያቃጥል በማስጠንቀቅ፣ ላቀረቡት ንግግር የክሪስ ስሚዝ ገለጻ በማረጋገጫነት የሚቆም እውነት ይሆናል።
አሜሪካ ራስዋ ቀብታና ባርካ በትረ ሹመት የሰጠቻቸውን ሰዎች ከ22ዓመት በኋላ መልሳ “ገምግሙልኝ” ማለቷ አስገራሚ የሚሆንባቸው ጥቂት አይደሉም። ሰብሳቢው በመግቢያቸው የተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት ወቅታዊ መገለጫ፣ ቀደም ሲል ሚ/ር ያማሞቶን በመጥቀስ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረጋቸውን መረጃዎች ለተከታተሉ “አሜሪካኖቹ ምን የማያውቁት ነገር አለና ነው የሚጠይቁት ያሰኛል” በሚል የሚገረሙ በርካታዎች ናቸው።
obang at hearingለዚህ ይመስላል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ታሪካዊውን የኮሎኔል ጎሹ “ትንቢትና የኢትዮጵያ ህዝብን የሚወክል የምልጃ መቃተት” በማስታወስ ቀዳሚ የሆኑት። አስከትለውም “አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት። (ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ)” የሚል መልክት አስተላለፉ።
የጋራ ንቅናቄው መሪ በድርጅታቸው መርህ ላይ ተመሥርተው በሰጡት የምስክርነት ቃል “ህወሓት እስካሁን በነጻአውጪ ስም አገር እየመራ እንደሆነ፤ መለስ ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) ዓይነት መሪ እንደነበሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 22ዓመታት በመከራ ውስጥ ያለና የዛሬ 8ዓመት በዚሁ ቦታ ላይ ያማሞቶ ኢትዮጵያ በአቋራጭ መንገድ (ክሮስሮድ) ላይ እንደምትገኝ” መናገሩ አቶ ኦባንግ ካስታወሱ በኋላ “መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከስምንት ዓመት በኋላ አሁም አንሻገርም ወይ፤ አናቋርጠውም ወይ” በማለት ተሰብሳቢውን ያስደመመ ለሰብሳቢዎቹ ግልጽ ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡
አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም “ኢትዮጵያውያን የምንጠይቀው በጣም ቀላል ጥያቄ ነው፤ አሜሪካኖች የሚመኩበትን ሰብዓዊ መብት እኛ ተነፍገናል፤ የራሳችን ክሪስ ስሚዝ ይኑሩን ብቻ ነው የምንለው” ካሉ በኋላ በኃይለሥላሴም ሆነ በመንግሥቱ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ዕድላቸውን እንደተነፈጉ አስታውሰዋል፡፡ በወቅቱም በዚሁ ም/ቤት የዛሬ 22ዓመት በወርሃ ሰኔ ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ የዛሬዋን ኢትዮጵያን መተንበያቸውን አቶ ኦባንግ በንግግራቸው አስታውሰዋል፡፡ አሁንም የኢትዮጵያውያንን ቁርጠኛ አቋም ምን እንደሆነ ለአሜሪካውያኑ ግልጽ አድርገዋል “አሜሪካ እንድታድነን አይደለም የምንጠይቀው፤ ራሳችንን ማዳን እንችላለን፤ በነጻነት መንገዳችን ላይ ግን ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ ራሳችንን ነጻ እናወጣለን፤ ኦባማ ለፕሬዚዳንትነት ሲወዳደር በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሚያገኙት ጥቂት ደመወዝ ለምርጫው ዘመቻ ረድተው ነበር፤ ከኦባማ ግን የሰማነው ነገር እስካሁን ምንም የለም፤ ነጻነታችንን እየለመንን አይደለም፤ ራሳችንን ነጻ እናወጣለን” በማለት የበርካታ ኢትዮጵያውያንን የነጻነት መንፈስ የቀሰቀሰ ንግግር አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲ ለውጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ሰጥቻለሁ እንደሚል ከጠቀሱ በኋላ “ይህ ሁሉ ገንዘብ የት ነው የገባው፤ የት ነው የሄደው” በማለት ኢህአዴግ ከቀበሌ ጀምሮ እስከላይ ሥልጣኑን እንደተቆጣጠረ፤ ሙስሊሙ መሪውን እንምረጥ ሲል አሸባሪ ተብሎ እንደሚፈረጅ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር አገርና መሬት ብቻ ሳይሆን የምንጋራው በደም የተሳሰርን መሆናችን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ አንድ ጊዜም እንኳን ጦርነት ሰብከውም ሆነ መሳሪያ አንስተው የማያውቁ መሆናቸውን የተናገሩት ኦባንግ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት “አሸባሪ” መባላቸውን በመናገር የኢህአዴግን አሸባሪነት አጋልጠዋል፡፡ እስካሁን በአገራችን ላይ የፈሰሰው ደም በቂ እንደሆነ የጠቆሙት የጋራ ንቅናቄው መሪ፤ በኤድስና ምግብ በማጣት የረደሰብን ዕልቂት በቂ እንደሆነና ከእንግዲህ ወዲህ መጋደል እንደሌለብን ሆኖም ከኢህዴግም ሆነ ከተቃዋሚ በኩል አመኔታ የሚጣልባቸው ሰዎች ስላሉ እስካሁን ያልተሞከረውን የዕርቅ መንገድ (ሥራ) በኢትዮጵያ መከናወን እንዳለበት አቶ ኦባንግ ሜቶ በሚመሩት ድርጅት መርህና በሚታገሉለት የማዕዘን ሃሳብ ላይ ተተርሰው ሃሳባቸውን አጠቃልለዋል፡፡
በምክክር ሸንጎው ላይ የተገኙት የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው የንግግራቸውና የማሳሰቢያቸው ማሳረጊያ ሊባል የሚችል መልዕክት አስተላልፈዋል። ዶ/ር ብርሃኑ “አስተውሉ፣ ልብ ብላችሁ ተገንዘቡ” በማለት ያሳሰቡት ዛሬ ኢትዮጵያን የሚወዱ ሁሉ የሚጠበቡበት፣ እንዲከሰት የማይፈልጉትን የመጨረሻው ስጋት ነው።nega
በምክሩ ላይ በቀዳሚነት ምልከታቸውን ያብራሩት ዶ/ር ብርሀኑ ኢህአዴግ የዘረጋው የአፈና ስርዓት ያስመረረው ህዝብ፣ ኢህአዴግ ሆን ብሎ የሚያንኮታኩታቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሆን ብሎ የሚተናኮለው ህዝብ፣ ያለው ብቸኛ አማራጭ ብረት ማንሳት ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል። በቅርቡ የኢህአዴግ የአፈና ስርዓት ፈተና እንደሚገጥመው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አለመረጋጋት ቀጣናውን በሙሉ እንደሚረብሽና የአሜሪካንን ጥቅም በእጅጉ እንደሚጎዳ ዶ/ር ብርሃኑ በግልጽ በማስረዳት አሜሪካ ገንዘቧን በተገቢው ቦታ ላይ ማዋል እንዳለባት ምክር ሰጥተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተቃዋሚ ኃይሎች አማራጭ ከማጣት የተነሳ ብረት ማንሳታቸውን የጠቆሙት የግንቦት 7 ሊቀመንበር፤ ሕዝብ ዝም ብሎ በአስከፊ አገዛዝ ሥር እየኖረ እንደማይቀጥል አስጠንቅቀዋል፡፡ በመሆኑም አማራጭ ሲጠፋ ባገኘው መንገድ ሁሉ መብቱን ወደማስጠበቅ እንደሚገፋና በአሁኑ ወቅትም የተቃዋሚ ኃይሎች በመተባበር በኢህአዴግ ላይ ጥቃት መሰንዘር የሚስችላቸውን ብቃትና ኅብረት እንደፈጠሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለውም ኢህአዴግ በምንም መልኩ የማይሰማና በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን ለማስረከብ የማይችል መሆኑን በተለይ በ1997 ምርጫ ካስታወቀ ወዲህ በግልጽ የሚከተለው መርህ በራሱ ማስረጃ እንደሆነ ዶ/ር ብርሃኑ በጥያቄ መልክ ለቀረበላቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኢህአዴግ የደምሥር የውጭ ዕርዳታ እንሆነ የተናገሩት የግንቦት 7 መሪ አሜሪካ ከአውሮጳውያን ጋር በመተባበርና ለእያንዳንዱ የተሃድሶ ዕርምጃ ቀነ ገደብ በመሥጠት በተሰጠው ገደብ ውስጥ እስረኞች ካልተፈቱ፤ የምርጫ ኮሚሽን ካልተቀየረ፤ ወዘተ በማለት ዕርዳታው እንደሚቆም በማስጠንቀቅ አሜሪካውያኑ ለኢህአዴግ መመሪያ ቢሰጡ ለገንዘብ ሲል ኢህአዴግ ሊታዘዝ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም በድጋሚ የሰብሳቢውን ስም በመጥራት ትኩረት የጠየቁት ዶ/ር ብርሃኑ “የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ብለዋል።
ከክሪስ አንደበት
ሰብሳቢው ክሪስ ስሚዝ በምክርቤት ስብሰባ ላይ ድምጽ መስጠት በሚገባቸው ረቂቅ ህጎች ላይ ሲሳተፉ ስለነበር ምክከሩ የጀመረው ከታቀደው ሰዓት 1፡30 ያህል ዘግይቶ በመሆኑ ይቅርታ በመጠየቅ ነበር መንበራቸው ላይ ተሰይመው ንግግር ጀመሩት። የምክክሩ ሊቀመንበር አቶ መለስ የዘረጉት አገዛዝ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ልዩ ባህሪው እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ምክከሩን ከፈቱ። ምክክሩ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶችና የዴሞክራሲ ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩርና የአሜሪካ መንግሥት ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያመላከት ምክር የሚካሄድበት እንደሆነ አስገነዘቡ።
ኢትዮጵያ እስላማዊ አሸባሪነትን በቀጣናው በመዋጋት የአሜሪካ ደጋፊ አገር ሆና መቆየቷን፣ ሆኖም ግን በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚፈጽመው ተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥት ተጠያቂ ማድረግ እስካሁን አለመቻሉን ሳይሸሽጉ ተናገሩ።smith3
የፖለቲካ ድርጅቶች በነጻነት መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን፣ መንግስታዊ ባልሆኑ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች (መያዶች) ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ፣ ጋዘጠኞች እንደሚታሰሩ፣ በርካታ ዜጎች ከመሬታቸው እንደሚፈናቀሉ ወዘተ በመዘርዘር አስረዱ።
የአሜሪካ የዕርዳታ ድርጅት – ዩኤስኤይድ እንደሚለው ከሆነ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ግልጽ ግንኙነት ማድረግ ወደፊት የዴሞክራሲና የለውጥ ሂደቶችን ለማሳካት ይረዳል ተብሎ ቢታሰብም፣ በክሪስ ስሚዝ አመለካከት ግን እምነቱ ሊተገበር የሚችል ቢመስልም እስካሁን ምንም ፍሬ እንዳላመጣ ሳይሸሽጉ ተናግረዋል።
እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ስልታዊ አፈናና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ለሌሎች አገራት መጥፎ ምሳሌ እየሆነ መሄዱን ሊቀመንበር ስሚዝ ጠቅሰዋል፡፡ ንጹሃን ዜጎች ስቃይ፣ ድብደባ እንደሚደርስባቸው፣ በኤሌክትሪክ እንደሚጠበሱና የግዳጅ ወሲብ እንደሚፈጸምባቸው፣ የአምነስቲ ሪፖርት መዘገቡን ክሪስ ስሚዝ በእማኝነት ተናግረዋል፡፡
ራሳቸው ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ረቂቅ ህግ አዘጋጅተው እንደነበርና በወቅቱ የነበረው የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ግን ኢትዮጵያን በአሸባሪነት ላይ ወዳጅ በማድረጉ ምክንያት በነበረው ቸልተኝነት የተነሳ ተፈጻሚ ሳይሆን መቅረቱን አስታውቀዋል። ሚ/ር ስሚዝ እነዚህን ጉልህ ህጸጾች በመጠቆም ምክክሩ ላይ ተናጋሪ እንዲሆኑ የተጋበዙትን ክፍሎች በየተራ በማስተዋወቅ ጋብዘዋል። ከንግግሩ በኋላም ጥያቄዎችን ጠይቀዋል። ሌሎች ተሳታፊዎችም ጥያቄ በመሰንዘር ማብራሪያ እንዲወስዱ ተደርጓል።
ያማማቶ ምን አሉ?
ያማሞቶ በመግቢያ ንግግራቸው መለስን አወድሰዋል። አፍሪካን በዓለም መድረክ ከፍ እንድትል ያደረጉ መሪ በማለት አመስግነው ኢትዮጵያ ተሰሚነቷ እንዲጨምር ያደረጉ፣ ተሟጋችና ጎበዝ ተናጋሪ እንደነበሩ መስክረዋል። ኢኮኖሚውን አሳድገዋል፣ ኢትዮጵያን በቀጣናውና በዓለም ታዋቂ አድርገዋል፣ በሶማሊያ ተሟጋች፣ በሱዳን አስታራቂ፣ በአፍሪካ የአየርንብረት ጉዳይ ደግሞ አንደበተ ርዕቱ አፈቀላጤ ነበሩ በማለት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ከሚደረድረው በላይ ቃል አከማችተው ምስጋና ቸረዋቸዋል።
ያማማቶ በማያያዝ እንደ አምባሳደርነታቸው በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ አስመልክቶ አቶ መለስን ማነጋገራቸውን ጠቁመዋል። በሰብዓዊ መብቱን መጓደል ዙሪያም በተመሳሳይ መነጋገራቸውን  አክለዋል።
ካሊፎርኒያ ሎሳንጅለስ “ትንሿ ኢትዮጵያ” ወረዳ ተወካይ የምክርቤት አባል ሚስዝ ባስ፤ ያማሞቶን መስቀለኛ ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር። ጠያቂዋ “የኢህአዴግ መንግሥት ዋናው ችግር ምንድነው? ለምንድነው ይህንን ሁሉ መከራና አፈና የሚያካሂደው” በማለት የመገረም የሚመስል ጥያቄ ጠይቀዋል። ያማሞቶ እንደ መንተባተብ ሲሉ “ችግሩ ምንድ ነው?” በማለት ባስ በድጋሚ ጥያቄያቸውን ወረወሩ። “ችግሩ እንዳለ ነው” ሲሉ ደግመው መልስ የሰጡት ያማሞቶ “ጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም አፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ እንዳሉት ነው፣ የዴሞክራሲ እሴቶች አስፈላጊ ናቸው፣ መጥፎ ህጎች መወገድ አለባቸው፣ እንስራ፣ እንሞክር ብለዋል” አሉና መለሱ።
ኮንግሬስማን ሜዶውስ በኢትዮጵያ ኢህአዴግ ሁሉን ተቆጣጥሮዋል፤ እኛ አሜሪካኖች ምን ልናደርግ እንችላለን? እንዴት ነው ልናስተካክለው የምንችለው? የሚል ጥያቄ ለያማሞቶ ወረወሩ። ያማሞቶም  “ከምርጫው በኋላ ደስተኞች አለመሆናችንን ተናግረናል፡፡ ከበስተጀርባና በፊትለፊት እየሰራን ያለነው ነገር አለ፡፡ ጊዜ የሚወስድ ነው፡፡ ለምሳሌ በሴቶች ላይ የሚደረግ የመብት ጉዳይ አለ እናም ይህንን ከዩስኤድ ጋር እየሰራን ነው” አሉ፡፡
ሜዶውስ የረኩ አይመስልም “እና ያለው ፍርሃት ምንድርነው?” ሲሉ በድጋሚ መልስ መፈለጋቸውን አመለከቱ። “ነግረናቸዋል ፣ ለዘላለም ልትገዙ አትችሉም። ስለዚህ የተቃዋሚውን ተሳትፎ ማበረታታት አለባችሁ ። እነዚህ ተቃዋሚዎች አንድ ቀን መንግሥት ይሆናሉ። ስለዚህ ዝግጅት መደረግ አለበት ብለናቸዋል” የሚል የደፈና መልስ ከያማሞቶ ተሰጠ።
ጋንት፤ የዩኤስ ኤይድ ረዳት ዳይሬክተር
የሴፍቲኔት ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑንና በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እየተረጋጋች እንደሆነ፣ ከዚህም ጋር በማከል ኢኮኖሚው እያደገ እንደሆነ ልክ የኢህአዴግ ወኪል መስለው ተናገሩ። ሰብሳቢው ስሚዝ “ቶርቸር በየቦታው አለ እና ይህንን እንዴት ነው ለማስታረቅ ወይም ለማቆም የሚቻለው?” ሲሉ ማብራሪያ ጠየቁ። ሚ/ር ጋንት “አስቸጋሪ ነገር ነው። ቶርቸር እንዳለ እናውቃለን ግን ዋናው ሥራችን መልካም ነገሮችን ለማበረታታት ነው የምንሞክረው” የሚል ምላሽ ሰጡ።
በሚ/ር ጋንት ንግግር ላይ ተንተርሰው ተጨማሪ ጥያቄ ያቀረቡት ክሪስ ስሚዝ፣ ኢትዮጵያ ትምህርትን አስመልክቶ የሚሊኒየም ጎል ተሳክቷል ማለታቸውን ጠቅሰው “ጋንት ግን እኮ ጥራቱ በጣም የዘቀጠ እንደሆነ ነው ሪፖርቱ የሚያሳየው” ሲሉ ሞገቱዋቸው። የዩኤስ አይዲው ዳይሬክተር ጋንት “አዎ ችግር አለ ግን በርካታ መምህራን ተሰማርተዋል በትምህርቱ በኩል ዕድገት አለ” የሚል መልስ መመለሳቸው ለግንዛቤ ያህል የሚጠቀስ ሆኖ አግኝተነዋል።
ያማሞቶና ጋንት ያቀረቡትን ንግግርና ምስጋና ያደመጡ፣ በአካል ተገኝተው የተከታቱተሉ እንዳሉት በምክክሩ ላይ ኢህአዴግ ቢገኝም የሚጨምረው ምንም ነገር ሊኖር እንደማይችል አመልክተዋል።
ዳግም HR2003
የዛሬ አስር ዓመት፤ ኤች አር 2003 በምክር ቤት ደረጃ ከፍተኛ የሸንጎ (ኮንግሬስ) አባላትን ድጋፍ ካገኘ በኋላ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) አጽድቆት በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ ፖሊሲ ሆኖ እንዲጸድቅ ባለመደረጉ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች መከኑ። የህጉ መርቀቅና እንዲጸድቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያስበረገገው ኢህአዴግ ጡረተኛ የሴኔት አባላት ከሚመሩት ዲኤልኤ ፓይፐር ከተባለ የጎትጓች (ሎቢ) ቡድን ጋር ከፍተኛ በጀት በጅቶ ታገለ። ባፈሰሰላቸው መጠን ጎትጓቾቹ ባልደረቦቻቸውን ጠመዘዙና ህጉ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለው አዲስ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ህግ እንዳይሆን ተደረገ። ይህንኑ ህግ በማዘጋጀት ከሟቹ የምክርቤት አባል ዶናልድ ፔይን ጋር በወቅቱ ብዙ ደከሙት ክሪስ ስሚዝ የወቅቱን የቡሽ አስተዳደርን በንዝላልነት መድበው አሁን ይሀንኑ ህግ ተግባራዊ የሚደረግበትን አግባብ እንደሚገፉበት አመልክተዋል።
እንዴት እዚህ ተደረሰ?
የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድረጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና የሚነፈገው ራሱን በነጻ አውጪ (ህወሓት) የሰየመ መንግስት ስለሆነ ነው። ነጻ አውጪ እየተባለ አገር መምራቱ አቅዶ፤ ተልሞና መድረሻውን አስልቶ የሚጓዝ ስለመሆኑ ያሳብቅበታል። ለዚህም ይመስላል ስርዓቱ በሙስና የሸተተ፣ በግፍ የገለማ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያሰቃ፣ መንግስት ሆኖ  የሚሰርቅ፣ ብሔራዊ ክብርን የሚጠላ፣ ህብረትንና አንድነትን የሚጠየፍ፣ ጎሳና ጠባብ አመለካከት ላይ የተቀረጸ፣ በተራና በወረደ ተግባሩ ለመንግስትነት የማይመጥን መሆኑን የተረዱት አጋሮቹ አሁን ያመረሩበት ደረጃ ስለመዳረሳቸው ምልክቶች እንዳሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረዋል።
ይህ የምክክር ሸንጎ እንዴት ሊዘጋጅ ቻለ ለሚለው ጥያቄ በርካታ ጥረቶች መካሄዳቸውን በመግለጽ ዝርዝር ያላቀረቡት አቶ ኦባንግ ሐሙስ በተካሄደው ምክክር በመካከል ላይ ሚ/ር ስሚዝና ሌሎቹ ተወካዮች በምክርቤት ድምጽ መስጠት ስለነበረባቸው ምክክሩ ተቋርጦ እንደገና ሲጀመር ያልታዩበትን ምክንያት ተናግረዋል። ምክክሩ በተባለው ሰዓት ተጀምሮ ያልቃል የሚል እምነት ስለነበራቸው ሌላ ተደራራቢ የጉዞ መርሃግብር አመቻችተው እንደነበር አመልክተዋል።
“አሁን ስራ ላይ ነኝ” ያሉት አቶ ኦባንግ “እስራኤል አገር ለሁለት ከፍተኛ ጉዳዮች መጓዝ ነበረብኝ። አንዱ የወገኖቻችን ጉዳይ ነው። ሌላኛው ደግሞ የአገራችን ጉዳይ ነው። ከጉዞዬ በኋላ ማብራሪያ ለመስጠት እችላለሁ” በማለት ሁለተኛው ስብሰባ ሲካሄድ እርሳቸው ወደ እስራኤል ለሥራ እየተጓዙ እንደነበር አስታውቀዋል።

ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ስራቸውን እየሰሩ ነው ማለት ነው!


June 21, 2013

Bucknell University Professor of Economics Berhanu Nega
ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር።
ሰሞኑን ከኢህአዴግ ጋር የስጋ ዝምድና አላቸው እየተባሉ የሚጠረጠሩ ወዳጆቻችን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከአንዳች ሀይል ኢህአዴግን ለመገዳደሪያ የሚሆን ገንዘብ እንዳገኙ የሚያሰማ ድምፅ አጋርተውናል፡፡ ችግሩ ግን ይህ ገንዘብ ከየት እንደተገኘ እርስ በርሳቸው ስምምነት ላይ አልደረሱም፡፡ አንዳቸው ከኤርትራ ነው ሲሉ ሌላኛው ደግሞ ከግብፅ ነው ይላሉ፡፡ በደንብ ጆሮ ጣል ብናደርግ ከኢህአዴግ መንግስት ነው የሚልም አይጠፋም፡፡
ወዳጆቻችን ያጋሩን ድምፅ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከሆነ ቦታ የተገኘውን ብር፤ ለእንትን ይሄን ያህል፣ ለእንትና ይሄን ያህል እያሉ ሲናገሩ ያስደምጣል፡፡ በዚህ ላይ ያስደነቀኝን ልናገር እና እመለሳለሁ ቆይ አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ፡፡
ዶክተሩ የሆነውን ብር እዛው ለመከላከያ እና ደህንነቱ የተበጀተ ነው፤ ሲሉ ሰማናቸው፡፡ ይሄኔ በተለይ እንደኔ በኢህአዴግዬ ፍቅር የተለከፈ ሰው ክው!!! ማለቱ አይቀርም፡፡ ደህነነት እና መከላከያችን ከመንግስት ከሚመደብለት በጀት ውጪ በግንቦት 7 ደግሞ ሌላ በጀት አለው ማለት ነው፡፡ ይቺን ነው መፍራት፤ ዶክተሩ ስራቸውን ቀጥ ለጥ አድርገው እየሰሩ ነው ማለት ነው፡፡
ታድያ ለዚህ ነዋ የኢህአዴግዬ ገመናዋ ሁሉ ቀድሞ አደባባይ የሚሰጣው!!! እኔ ልሰጣ … ልበል ወይስ አልበል! (በቅንፍም ይቅርብኝ እነ እንትና ሳይሉ እኔ ቀድሜ ልሰጣ… ብል እነሱን ማሳጣት ሆንብኛል!) ከቅንፍ ስንወጣም ለኢሳትም የሆነ ብር ይሰጣል ሲሉ ዶክተሩ መናገራቸውን አዳመጥኩ፡፡ በእውነት ዶክተርዬ የተባረኩ ኖት፡፡ … እንዴ… በአሁኑ ጊዜ ማን እንደዚህ ያደርጋል… የምር እኮ ኢሳትን ሁሉም መርዳት አለበት፡፡ ግንቦት 7 ከረዳው በጣም ጥሩ ጅምር ነው፡፡ እንኳን ሌላ ቀርቶ ግንቦት 20 ም ራሷ ኢሳትን መርዳት አለባት፡፡ እንዴ ኢቲቪ የማይሰራውን በሙሉ የሚሰራው ኢሳት አይደለ እንዴ…! ታድያ እንዲህ እንዲተጋገዙ ሁሉም የአቅሙን ቢያዋጣ ምን ችግር አለበት!
ወደ ዋናው መስመር ስመለስ ወዳጆቻችን “ፈልፍለው” ይፋ ባደረጉት መረጃ ዶክተሩ ለካስ አልተኙም ብለናል፡፡ እና ይበርቱ ልንላቸው ይገባል፡፡
ገንዘቡ ከግብጽ ነው፤
ግብፅ የምር ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ገንዘብ የምትረዳ ከሆነ ተጃጅላለች ማለት ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ኢህአዴግ እንኳ ያንን ሁላ አድርጋለት አልተመለሰላትም፡፡ በእውኑ ሌሎቹማ ከኢህአዴግ የበለጠ ለሀገራቸው ተቆርቋሪ አይደሉምን…!
ገንዘቡ ከኤርትራ ነው፤
ወይ…. ኤርትራ….!!! አሁን ማን ይሙት ኤርትራዬ ከራሷ አልፋ ለሌላ ሰው ይሄንን ያክል ብር መስጠት ትችላለች…! ይሄንን ሃሳብ የሰነዘሩ ሰዎች በእርግጠኝነት ኤርትራዊያን ናቸው፡፡ አላማውም የኤርትራም መልካም ገፅታ ለመገንባት ሳይሆን አይቀርም ብለን እኛ ጠርጣሮቹ እንጠረጥራለን!
የትም ፍጪው ኢህአዴግን አስወጪው፤
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ግንቦት 7 የሚባል ተቃዋሚ ፓርቲ መስርተው ሁለገብ በሆነ ዘዴ ኢህአዴግን ወግድ እለዋለሁ ብለውናል፡፡ ግንቦት 7 ይህ ከሆነለት የዘመናት ብሶት የወለዳቸው ሁሉ ተሰባሰበው ዋንጫ እንደበላ ሰው “የእርግብ አሞራ” እያሉ የሚጨፍሩለት ደስታ የሚሆን ይመስለኛል፡፡ ታድያ ለዚህ አላማ ገንዘብ ከየትስ ቢያመጡ እኛ ምን አገባን…!?

Jun 21, 2013

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ለኢትዮጵያ የሚገባትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሸራረፍ
በሰላማዊ የትግል መስመር ለማረጋገጥ ትግል ከጀመረ አራት ዓመታት አሳልፏል፡፡ በነዚህ ዓመታትም ፓርቲያችን ወደ ፍፁም
አምባገንነት እየነጎደ ያለውን ገዥ ፓርቲ የፖለቲካ አካሄድ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ነጠቃ እንዲቆም
አጥብቆ ታግሏል፡፡ በትግሉ ሂደትም ስርዓቱ በግልፅና በስውር ፓርቲያችን ላይ ጥቃት ፈፅሟል፤ እየፈፀመም ይገኛል፡፡
አመራሮቻችንና አባሎቻችንም ስለ ቁርጠኛ ዓላማቸው ያለምንም ማፈግፈግ የሚከፈለውን መስዋእትነት ከፍለዋል፣ እየከፈሉም
ይገኛሉ፡፡ ስለ ዴሞክራሲና ነፃነት ሲሉ ጨለማ ክፍል ውስጥ የተጣሉትን ወጣት አመራሮች አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን
እና ሌሎችንም፤ ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ እስር ቤት የተጣሉ ጉምቱ ጋዜጠኞችና የዕምነት ጣልቃ ገብነትን ስለተቃወሙ
ለእስር የተዳረጉ ኢትዮጵያውያንን መጥቀስ ይቻላል፡፡
አንድነት በሆደ ሰፊነት የፖለቲካ ለውጦች እንዲደረጉ፣ ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ እንዳይታሰሩ፣ እንዳይገረፉ፣
እንዳይሳደዱ፣ መንግስት በኃይማኖት ጣልቃ እንዳይገባና የኃይማኖት ነፃነት እንዲረጋገጥ ስለጠየቁ በጅምላ የድራማ ክስ
እየተመሰረተ ወደ እስር ቤት እንዳይጋዙ፣ ጋዜጠኞች ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ እንደ መደበኛ ጠላት ተቆጥረው ሰብዓዊ
መብታቸው ተገፍፎ እንዳይታሰሩና ለስደት እንዳይዳረጉ በተደጋጋሚ ገዥውን አካል ያለመታከት መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡
የሀገሪቱ ችግሮች በገዥው ፓርቲ ብቻ የሚፈቱ አለመሆናቸውን በመገንዘብ በሃገራዊ ጉዳዮችና የፖለቲካ መፍትሄዎች ላይ
ከተቃውሞ ኃይሎች ጋር ድርድር እንዲያደርግ፣ የዘጋውን በር ለውይይት ክፍት እንዲያደርግ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ
ኢትዮጵያውያንን ያሳተፈ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር በተደጋጋሚ ጠይቀናል፡፡ ለነዚህ ዓብይ ጥያቄዎቻችን የተሰጠን መልስ
እስራት፣ መፈረጅና ማዋከብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ገዥው ፓርቲ ለጭቆናው ሕጋዊ ከለላ ለመስጠት ጨቋኝና አፋኝ ህጎችን
በማውጣት፤ የረጅም ዓመት የስልጣን ቆይታን በመናፈቅ ዜጎችን በየማጎሪያ ቤቱ እያሰቃየ ይገኛል፡፡ እኛም ይሄንን ዓብይ ችግር
ለመፍታት ሰላማዊ በሆነ የትግል ስልት ህዝባዊ ንቅናቄ መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ አምነናል፡፡
ስርኣቱ ዜጎች ካላግባብ ከየመኖሪያ ቀያቸው በገጠርም ሆነ በከተማ በግፍ እንዲፈናቀሉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሄው ሀገራዊ ይዘት
ያለው ማፈናቀል ሦስት አይነት መልክ ያለው ሲሆን በዘር ላይ ተመሰረተ ማፈናቀል፣ በልማት ስም ማፈናቀልና ለመሬት ወረራ
ማፈናቀል ናቸው፡፡ ዘርን መሰረት ያደረገው ማፈናቀል በቅርቡ ብቻ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ፣ በቤኒሻንጉል ክልልና ሌሎችም
አካባቢዎች የተከሰተው ነው፡፡ በልማት ስም የሚከናወነው ማፈናቀል በአብዛኛው በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በስፋት
የሚታይ ነው፡፡ ዋናው መሰረቱ የገዥው ፓርቲ የመሬት ፖሊሲ ነው፡፡ መሬት በባለቤቱ ፈቃድ የሚሸጥና የሚለወጥ ባለመሆኑ
ያለበቂ ካሳና ማስጠንቀቂያ ለማህበራዊ ትስስር ቁብ ሳይኖረው ልማት በሚል ስም ብቻ በማንሳት ዜጎች የሚፈናቀሉበት ነው፡፡
ሌላው የማፈናቀል አይነት ደግሞ ከመሬት ወረራ ጋር በእጅጉ የተቆራኘና በእርሻ መሬት ሰበብ ዜጎች እየተፈናቀሉ ለውጭና ለሀገር
ውስጥ ባለሀብቶች በጥቂት ሳንቲም የሚሰጥ ነው፡፡ ይሄም በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች በስፋት የታየና እየታየ ያለ ነው፡፡
ፓርቲያችን ይህንን ጉልህ ሀገራዊ አደጋ ለማስቆምም የሚጠበቅበትን ትግል ለማድረግ ህዝባዊ ንቅናቄ አስፈላጊ መሆኑን ያምናል፡፡
ከመፈናቀሉ በተጨማሪም ቅጥ ያጣ የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት በሰፊው ተንሰራፍቷል፡፡ የኑሮ ውድነቱን ጣሪያ ያስነካው የዋጋ
ግሽበት ዋና መንስኤው ስርዓቱ የሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ የወለደው ነገር ቢኖር ሀገራችን በታሪኳ አይታ
የማታውቀው ስደት ነው፡፡ ዜጎች ከፊት ለፊት ሞት እንደሚጠብቃቸው እያወቁ ተጋፍጠው ለስደት የመነሳታቸው መንስኤ ስራ
አጥነትና የኑሮ ውድነት ነው፡፡ ከዚህ ጋር የነፃነት እጦት ሲታከልበት የችግሩን መልክ ውስብስብ አድርጎታል፡፡
የንግዱን ማህበረሰብም ስንመለከት ከመቼውም በባሰ ሁኔታ ነጋዴ መሆን ወንጀለኛ መሆን የሚል ትርጉም ይዟል፡፡ በተጨማሪም
ገዥው ፓርቲ በአንድ በኩል ህግ አውጪና አስፈጻሚ፣ በሌላ በኩል ነጋዴ በሆነበት ሁኔታ ፍትሀዊ የንግድ ውድድር የሚታሰብ
አይደለም፡፡ ይህም የግሉ ሴክተር በሀገሪቱ ዕድገት ውስጥ ሊኖረው የሚገባውን ሚና እጅግ አቀጭጮታል፡፡ ካላግባብና በግምት
የሚጣል ታክስ መክፈል ሃገራዊ ግዴታ የመሆኑን ለዛ አሳጥቶታል፡፡ አንዳንዱ በብልጣብልጥነት ስርዓቱን እንደመታወቂያና ከለላ
በመጠቀምና ከባለስልጣናት ጋር በመሻረክ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሀብት ማማ ላይ ሲወጣ እንመለከታለን፡፡ ይሄም በንፁህ ንግድ
ላይ ለተመሰረቱ በርካታ ዜጎች አደጋ እየሆነ መጥቷል፡፡ ከዚያም ልቆ ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ስለዚህ ፍትሃዊ የንግድ አሰራር
እንዲኖርና የግሉ ሴክተር በኢኮኖሚ ውስጥ የሚገባውን ቦታ እንዲኖረው እንጠይቃለን፡፡
በዚህም መሰረት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እንዲሳተፍ ለማድረግ በአዲስ አበባና በመላ ኢትዮጵያ ህዝባዊ ውይይትና ሰላማዊ ሰልፍ
እናደርጋለን፡፡ ህዝቡንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያሳትፍ፣ አባሎቻችንንና ደጋፊዎቻችንን ያሚያቅፍ፣ አፋኝና ጨቋኝ ህጎችና
አዋጆች እንዲሰረዙ ጫና የሚያደርጉ፣ በመሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ለማካሄድ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች
በፍጥነት መደረግ እዳለባቸው እናምናለን፡፡ በዚህም መሰረት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት (MILLIONS OF VOICES
FOR FREEDOM) በሚል መሪ ቃል ተከታታይነት ያለው የሕዝባዊ ንቅናቄ ዕቅድ ይፋ አድርገናል፡፡
የዕቅዳችን ዋና አላማ ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነንነትን ማስፉት፤ በአንፃሩ ደግሞ ዴሞክራሲዊና ሰብዓዊ መብትን እየገፈፈ፣ ዜጎችን
በፍርሃት ተዘፍቀው በምንደኛነት እንዲኖሩ ያደረገውን ስርዓት መቃወም፤ መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ስልጣን የህዝብ
እንዲሆን፣ ግለሰቦች በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ በዕምነታቸውና ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸው የማይታሰሩባት ሃገር
መፍጠርና ፍትሃዊነትን ማስፈን ነው፡፡ ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ የሚሊዮኖችን ድምፅ በመሰብሰብ ከህገ-መንግስቱ ጋር
የሚጋጨውንና ፍፁም ነፃነት ነጣቂ የሆነውንና ማሰብ እንኳን የሚከለክለውን የፀረ ሽብርተኝነት ህግ እንዲሰረዝ ማድረግ ነው፡፡
ሚሊዮኖች የፀረ ሽብር አዋጁን በመቃወም የሚፈርሙበት ሰነድም እነሆ ይፋ አድርገናል፡፡ ሚሊዮኖችም የተቃውሞ ፊርማቸውን
እንደሚያኖሩ ሙሉ እምነት አለን፡፡ ይንንም መሰረት በማድረግ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና የሃይማኖት ነፃነት
ጠያቂዎች እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የተቀየሰው የሠላማዊ ስልት በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች ህዝባዊ የአዳራሽ ስብሰባዎችን፤
የአደባባይ ስብሰባዎችንና የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን ያካትታል፡፡ በአዲስ አበባ ስድስት ህዝባዊ ስብሰባዎችን፣ በክልል
ደግሞ ለመጀመሪያ ዙር ብቻ አስር ስብሰባዎችን እናደርጋለን፡፡ በሚሊዮኖች ድምፅ ነፃነትን ለማረጋገጥ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ
ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚሳተፉበት ይሆናል፡
የህዝባዊ ንቅናቄው ዓላማ
1. የፀረ-ሽብር ህጉ የኢትዮጵያውያንን በርካታ መብቶች የሚገፍ በመሆኑና ከሕገ-መንግስቱ ጋር የሚፃረር በመሆኑ
በሚሊዮኖች የሚቆጠር የተቃውሞ ድምፅ በማሰባሰብ በአስቸኳይ እንዲሰረዝ ጥያቄ እናቀርባለን፡፡ የድጋፍ ፊርማ
(ፔቲሽን) እናስፈርማለን፡፡ ይህንንም በሰላማዊ ሰልፍ እንጠይቃለን፡፡ የሚሊዮኖችን ድምፅ በመያዝ ወደ ክስ እንሄዳለን፡፡
2. በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው በገጠርና በከተማ የዜጎች መፈናቀልና የመሬት ቅርምት እንዲቆምና መፍትሄ
እንዲያገኝ እንጠይቃለን፤
3. የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት እንዲቀረፍ፤ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ርምጃዎች እንዲወሰዱ እንጠይቃለን፤
4. የንግዱ ማህበረሰብ ውስጥ ፍትሃዊ ውድድር እንዲኖር፤ ማጥላላትና ማዋከብ እንዲቆም፤ ገዥው ፓርቲ ህግ አውጭና
ነጋዴ የሚሆንበት ስርዓት እንዲያበቃና የግሉ ሴክር በልማቱ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዲኖረው እንጠይቃለን፡፡
ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ መሳካት ሕዝቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያው፣ በውጭ የሚኖሩ
ኢትዮጵያውያን፣ ለሀገር ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያንና የሀገርን ጥቅም ለማስቀደም የሚፈልጉ የኢህአዴግ አባላት እንዲሳተፉ ሀገራዊ
ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሰኔ 12 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Jun 19, 2013

የጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሀቢባ መሐመድን ጨምሮ የ32ቱ ሰዎች ክስ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆን ጠበቆቹ ጠየቁ

በዘሪሁን ሙሉጌታ
.ዐቃቤ ሕግ 197 የሰው ምስክር ለማቅረብ ጠይቆ 89 ምስክሮችን ብቻ አሰማ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌድሪየወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣38(1) እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅቁጥር 652 /2001 አንቀፅ 3(1) (4)(6) እና 4 ስር የተመለከቱትንድንጋጌዎች በመተላለፍ የተከሰሱትንየቀድሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርየነበሩት የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮሀቢባ መሐመድን ጨምሮ ሌሎች 32ሰዎች ክስ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆንጠበቆቹ ጠየቁ።ቀደም ሲል ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹላይ የሰው ምስክር በሚያሰማበት ወቅትለምስክሮቹ ደህንነት ሲባል ችሎቱ በዝግእንዲካሄድ ፍርድ ቤቱ በመወሰኑ ችሎቱበዝግ ሲካሄድ ቆይቷል። ዐቃቤ ሕግ ለክሱ ዝርዝር ያስረዱልኛል ያላቸውን 197 የሰው ምስክሮች እንደሚያሰማ አስቀድሞለፍርድ ቤቱ ያመለከተ ቢሆንም 89 ምስክሮችን ካሰማ በኋላ ማጠናቀቁን ተከትሎ የፍርድ ሂደቱ ለጋዜጠኞችና ለዲፕሎማቶችእንዲሁም ጠበቆቹ ለተጠርጣሪዎቹ ዘመድ ወዳጆች ክፍት እንዲሆን ጠይቀዋል።ከተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች አንዱ የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በመጪው ሐሙስ ሰኔ 13ቀን 2005 ዓ.ም የሚሰየመው ችሎት ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ክፍት እንዲሆንና በቀጣይ በተከሳሾቹ ላይ ዐቃቤ ሕግአቀርበዋለሁ ያለው የኦዲዮና ቪዲዮ ቅጂ ለጠበቆች ቅድሚያ ሊደርስ ይገባል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ እየታየ ያለው የቀድሞ ቅንጅቶች ጉዳይ ይታይበት በነበረው በቃሊቲ ወረዳ 8 አዳራሽ ውስጥሲሆን፤ ጉዳዩ እየታየ ያለው በፌዴራል አራተኛ ወንጀል ችሎት ነው።በሌላ በኩል ከዚህ በፊት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት “ጅሃዳዊ ሀራካት” በሚል የቀረበው ዘጋቢ ፊልም በአሁኑ ወቅትጉዳያቸው እየታዩ ካሉ 12ቱ ተጠርጣሪዎች አለአግባብ ስማቸው መጥፋቱን በመግለፅ፤ በጠበቆቻቸው አማካኝነት በፕሬስ ሕጉአንቀፅ 43 መሠረት ፎቶና ምስሎችን አለአግባብ ታይቷል በሚል 8 ሚሊዮን ብር የካሳ ክስ አቅርበው እንደነበር ጠበቃ ተማምገልፀዋል። ነገር ግን የዳኝነት 83 ሺህ ብር ከፍለው ክሱን በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ለመክፈት ሲሞክሩ፤ ሬጅስትራሩ የክስፎርማሊቲ አልተሟላም በማለት ለዳኛ ሳይመራ፣ አቤቱታ አቅራቢዎች ሳይከራከሩ፣ ተከራካሪ ወገኖች መጥሪያ ሳይሰጣቸውአላግባብ በመዘጋቱ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቤቱታ ሰሞኑን እንደሚያቀርቡ አያይዘው ገልፀዋል።በተጨማሪም የመጅሊስ ምርጫውን በተመለከተ መጅሊሱ የተመረጠበት አካሄድ ሕገ-መንግስቱን፣ የኢትዮጵያ ፍትሐብሔርሕግን እና የመጅሊስ ሕገ-ደንብን የጣሰ ነው በሚል ያቀረቡትን ክስ የሥር ፍርድ ቤቶች ውድቅ ቢያደርጉም፤ ጉዳዩ ሰበር ሰሚመድረሱንና ለሰኔ 27 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱንም ጨምረው ገልፀዋል።
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

Egypt and Ethiopia: The war of two morons

June 18, 2013

by Abebe Gellaw
Just like the proverbial bald men fighting over a comb, two unpopular regimes in Cairo and Addis Ababa have lately ended up being ridiculed and jeered across the world for their absurdities. With that melodrama, the long standing loveless relationships between Egypt and Ethiopia have hit rock bottom. It appears that the root cause of the recent debacles by the two beleaguered regimes appears to have little to do with water security but the maddening internal crises that both wanted to divert attention from.
The comedy was started by none other than the foolhardy TPLF that sent out its poodle Demeke Mekonen and the Eritrean-born Amhara leader “Bereket Simon” (aka Comical Simon) to openly declare a top “secret” undertaking. On the occasion of the 22ndanniversary of the fall of a brutal military junta and the rise of TPLF’s apartheid, Comical Simon and his colleagues came up with the most absurd idea that triggered an absurd war of words. Following a carelessly crafted bravado, the officials declared that the TPLF regime had “diverted” the Nile. But it turns out that the bravado was far from the truth and extremely misleading. The blazing propaganda claimed that Abay was now totally harnessed and diverted from its natural course. And yet, given the sensitivity of the Nile waters, the unnecessary spin was a total madness.
The news in English released by state-run media outlets and distributed globally reads: “The diversion of the course of Abay (Nile) River was successfully undertaken on Tuesday to make way for the construction of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD).Relationships between Egypt and Ethiopia have hit rock bottom.
“Speaking at the a ceremony held at Guba, site of the GERD in Benishangul Gumuz State, President of the GERD Construction Public Coordination Council and Deputy Prime Minister Demeke Mekonnin said the diversion of the River has been successfully done to utilize the resource for national interest…. Demeke said the government would remain focused to realize the vision of the late Great leader Meles Zenawi and martyrs, thereby promoting the Ethiopian Renaissance.” (ERTA May 28, 2013)
Ethiopia, being the major source of the Nile that generates 85 percent the total water flow, has every right to utilize its water. The monopoly that Egypt and Sudan exercise over the Nile is based on archaic myths and an unacceptable colonial era fraud committed by Britain to water its cotton plantations. Ethiopia was not part of the fraudulent arrangement. It is clearly not only unacceptable but also unsustainable. Nonetheless, TPLF’s bravado of declaring “the successful diversion of Abay” is quite obviously a moronic act.
One could notice that the clumsy spin doctor Comical Simon and his collaborators attained nothing but notoriety that defies the norms of modern diplomacy and international relations. On May 30, Comical Simon even appeared on Al Jazeera, which also happily amplified the TPLF-generated news. “The River Nile has been a source of life for millions over the centuries. Now Ethiopia is diverting water to build a giant dam pushing those downstream who depend on the river to wonder when and whether this issue can be resolved peacefully,” David Foster, the presenter of Inside Story, said adding emphatically that the issue can lead to “death on the Nile.”
Foster exaggerated the dam’s impact using data from the Egyptian misinformation campaign.  He said that the loss of water for Egypt, as a result of the construction of the dam, is estimated between 11 to 19 billion cubic meters. “An idea of what that means, a four million cubic meters of loss could turn a million acres of land into a desert…An expert says that would cause two million Egyptian families to lose their livelihoods. The Ethiopian dam could also affect Egypt’s electric supply by 25 to 40 percent, it is argued, which would leave upper Egypt in darkness.”
It was in this context that the inarticulate Comical Simon, who seemed clueless like a sloth, appeared on Al Jazeera to “refute” the root cause of the problem, i.e. his own bravado that Ethiopia diverted the Nile. The background Comical Simon also chose was also as provocative as pornography. He loomed large over an artist’s impression of the so-called Renaissance Dam.
Comical Simon inarticulately and unconvincingly explained that the dam would result in “more flow of water of the Nile River to downstream riparian countries.” But he obviously failed to show his magic wand.
“We believe in Ethiopia we are doing a lot of conservation works [sic], environmental improvement works whereby we are enriching the underground water of the country [sic]. We will have more water in our streams,” says the Minister of Miscommunication cryptically in a way that even himself can hardly understand.
In Cairo, a different kind of bravado followed. A “secret” war plan was broadcast live on TV confirming to the world that the contention over the Nile is more of a comedy than an issue that calls for a serious dialogue and diplomacy. President Morsi, the leader of the Muslim Brotherhood that is in trouble for hijacking and diverting the popular revolution that toppled Hosni Mubarak, convened a secret meeting with political leaders from other parties including the opposition. But he and his advisers felt that it was an issue to exploit for a populist cause in order to divert attention from the critical internal crisis the regime is facing. But the decision to broadcast the “secret” meeting live on TV was not communicated to those convened at the palace. The politicians were unaware that the secret meeting was on live TV. Their nonsensical discussion rather exposed the lack of leadership in Cairo, as much as in Addis.
Younes Makhioun, Chairman of Al-Nour Party, focused on a conspiracy theory and concluded that Israel and the U.S. were behind the dam. He proposed that Egypt should use rebel groups and, if that fails, the security service should destroy the dam.
The founding chairman of the Ghad El-Thawra Party put forward the idea of spreading rumors that Egypt had obtained advanced aircraft refueling capability that enables her to bomb the dam. One participant was advising everyone that the meeting should be kept top secret, when it was announced a minute or so later to the room that the secret meeting was actually live on TV. Embarrassed with their own folly, the politicians had no choice but to giggle and chuckle.
The Egyptians know full well that insisting on a colonial era fraud never helps their case. When the colonial masters, British officials, were asked if they could help resolve the “dispute” they suggested that the best way forward would be to have a dialogue among the riparian states in the Nile basin. It is quite obvious that no one will be able to monopolize an international river like the Nile as long as equitable share is the only acceptable solution.
It is quite Quixotic on the part of Egyptian politicians to quote an ancient saying attributed to Herodotus now and again: “Egypt is the gift of the Nile.”
“If Egypt is ‘the gift of the Nile,’ then the Nile is God’s gift to Egypt,” President Morsi declared at a recent all-Islamic conference that was aimed at creating more illusion than helping Egyptians live in the 21st century. “We will defend each drop of Nile water with our blood if necessary,” he warned.
Rhetoric aside, Morsi knows the reality that Egypt can do little to stop Ethiopia from drinking its water and quench its perennial thirst and hunger. For most Ethiopians, the issue of the Nile is not a matter of dispute. Ethiopians have a long established consensus that the problem is to do with their moronic regimes that incite tension for little political ends while doing so little to protect our national interests. After all, this is a regime that has willfully made the country one of the biggest landlocked countries in the world.
There are two fundamental issues that remain unanswered. First of all, building a mega dam without even mobilizing enough resources is like putting all eggs in one basket. It is estimated that the dam would cost around five billion dollars. So far between 10 to 15 percent of the total cost has been collected. The regime has no idea where the remaining 85 percent of the outlay would come from.
Ethiopia needs micro-dams across the country not only for hydroelectric power generation but also irrigation to ensure food security for its hunger-stricken population. While starting from small scale projects is a wiser approach, investing all resources and subcontracting EFFORT companies along with their foreign accomplices will not bring about the construction of a mega-dam. It will only sustain TPLF’s mega-corruption industries that have made the selected few filthy rich criminals.
Secondly, and more importantly, the TPLF-led tyranny should also listen to the cries of Ethiopians across the world. It should dam racism and gross human rights abuses before Abay. Most Ethiopians are wise enough to avoid the war of the two morons in Cairo and Addis. They won’t be hoodwinked.
No diversion, please! We need freedom, more than a mega dam!

Jun 18, 2013

አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?

“አዲስ አበባ የተገተሩት ህንጻዎችስ?”

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም “ዘርፈው አስቀመጡት” የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው።
የሁለት አገር ነዋሪዎችየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር 54 ተሽከርካሪዎች ተይዘውባቸዋል። ገንዘቡን ሳይጨምር 54 ተሽከርካሪዎች በስማቸው ተመዝግበው የተያዙባቸው አቶ ነጋ ፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የንግድ ሽሪክ እንደሆኑ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የማይቀሩት አቶ ነጋ በየስብሰባው ወቅት ሻይና ቡና ሲሉ ከወ/ሮ አዜብ ጋር አብረው እንደሆነ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “አትሌት ናቸው” በሚል ወደ ውጪ በጉቦ የላካቸው ሰዎች ጉዳይም ከሳቸው ጋር እንደሚያያዝ ይጠቁማሉ።  ከጨው ንግድ፣ ከካሜራ ፊልም ብቸኛ አስመጪነት ሌላ በአሁኑ ወቅት ሂልተን ጀርባ፣ አዲስ አበባ ስታዲየም ቪክ ሬስቶራንት ጎን ግዙፍ ህንጻ ያስገነቡት አቶ ነጋ ቃሊቲ ባላቸው የነዳጅ ማደያ የከፈቱት ብቸኛ የክብደት መለኪያ/የከባድ የጭነት መኪኖች የክብደት መለኪያ “የገንዘብ ማምረቻ ማሽን” አግባብነት የሌለው ቢዝነስ እንደሆነ ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየ የግል የንግድ ተቋማቸው ነው። ቀደም ሲል ከኤርትራዊያን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ነጋ ሃብታቸው በድንገት የተመነጠቀው ከ1991 ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ እንደሆነ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።
አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ከኢህአዴግ የቀድሞው የኦዲት ኮሚሽን ጸሐፊ ከነበሩት አቶ አማኑኤል አብርሃና ከቴክኒክ ክፍል ሃለፊው መቶ አለቃ ዱቤ ጁሎ ጋር በጋራ ይሰሩ እንደነበር ለጸረ ሙስና ኮሚሽን ማስረጃ እንደደረሰው የገለጸ የጎልጉል ምንጮች፣ የፌዴሬሽኑ የውጪ ምንዛሬ ሂሳብና በአትሌቶች ስም ወደ ውጪ የተላኩ በርካታ ወጣቶች ጉዳይ እንደሚመመረመር ጠቁመዋል። ኮሚሽኑ ከበቂ በላይ መረጃ ቢኖረውም ማህበራትንና የርዳታ ድርጅቶችን መመርመር የሚያስችል ህጋዊ ውክልና ስለሌለው ሙስና አለባቸው በሚባሉት ማህበራትና ርዳታ ተቋማት ላይ ምርመራ ለማድረግ አዲስ ህግ ለማውጣት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል። የኢህአዴግ የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድ ካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን አስፍሯል። በቤተሰብ ተዘረፈ የተባለው ሃብት በስም ዝርዝር ባለቤቶቹም ይፋ ሆነዋል።
በሙስና ቤተሰብ ስም የተከማቸ ሃብት ንብረቶች ታገዱ
በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ተፈፀመ በተባለው የሙስና ወንጀል በ544 ተጠርጣሪዎች ድርጅቶችና በቤተሰቦቻቸው ስም በመንግስትና በግል ባንኮች የተቀመጡ ጥሬ ገንዘብ ፣ አክሲዮኖች እንዲሁም የከበሩ ማእድናት ታገዱ።
በሌላ በኩል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች እስካሁን 92 ተሽከርካሪዎች እገዳ ተጥሎባቸዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በአቶ ገብረዋህድ ባለቤት ኮረኔል ሃይማኖት ተስፋይ ስም የተመዘገቡ ሲሆኑ ፥ 54 የሚሆኑት ደግሞ በአቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ስም የተያዙ ናቸው።
ከተሽከርካሪዎች አራቱ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የአዳማ ቅርንጫፍ ስራ አሰኪያጅ በነበሩት አቶ አሞኘ ታገለ ስም የተመዘገቡ ሲሆን ፥ ከውጭ የሚመጡ ባለሃብቶች ወደ ሃገር ቤት እቃዎቻቸውን ሳያስፈትሹ እንዲያስገቡ በማድረግ በእነርሱና በጉሙሩክ የስራ ሃላፊዎች መካከል ጉቦ በማቀባበል መንግስትን ጎድቶ ራሳቸውን ጠቅመዋል በሚል በተጠረጠሩት በአቶ ዳዊት መኮንን ስም  እንዲሁ አራት ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል።
ሌሎች ሰባት ተሽከርካሪዎች በአልቲሜት ፕላን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲመዘገቡ ፥ ስድስት የሚሆኑት ተሽከርካሪዎች ደግሞ በኢትባ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተመዝግበው ይገኛሉ።
የፌደራሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በተጠቀሱ ግለሰቦች ፣ ድርጅቶች እና ሌሎች አካላት እግድ የተጣለባቸው ተሽከርካሪዎች እንዳይሸጡ ፣ እንዳይለወጡ እና ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ አስደርጓል።
የእነ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ እና ሌሎች መዝገቦችን ሳያካትት በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ በተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች ፥ ተፈጸመ በተባለው የሙስና ወንጀል  ከቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ከተገኙ ሰነዶች ብቻ መንግስት ከ 230 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንደደረሰበት ነው የሚለው የኮሚሽኑ መረጃ የሚያመለክተው። አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)
በፌስቡክ “የኮንዶሚኒየም ዕድለኞች ስም ዝርዝር ይፋ ወጣ” እየተባለ የተዘበተባቸው የባንክ ሂሳባቸው የታገደባቸው ሙስ ስም ዝርዝር
አባቡ አለሙ ገብሩ
ምስጋናው ይስሃቅ እጅባ
በረከት ይስሃቅ እጅባ
ታደሉ አለምነው ተፈራ
ፀጋነሽ አለምነው ተፈራ
አባተ ጋሻው ቦጋለ
ጌጤ ጋሻው ቦጋለ
ዘርፌ ጋሻው ቦጋለ
ፀሐይ ጋሻው ቦጋለ
ትዕግስት ጋሻው ቦጋለ
አስፋው ጋሻው ቦጋለ
መብራት አበበ አብርሃ
ቤቴልሄም አማኑኤል ሰይፈ
እቁባይ ተከለ አርአያ
ብሌን አማኑኤል ሰይፈ
ሊዲያ አማኑኤል ሰይፈ
እየሩሳሌም ስማቸው ከበደ
መቅደላዊ ስማቸው ከበደ
ኤልሻዳይ ስማቸው ከበደ
ኢቫና ስማቸው ከበደ
አያልነሽ ይመር ጌታሁን
ሠለሞን ከበደ ካሳ
ምንትዋብ ከበደ ካሳ
ዳንኤል ደባሽ ሀገሩ
ናኑ ደባሽ ሀገሩ
ሰላማዊት ደባሽ ሀገሩ
ሣራ ደባሽ ሀገሩ
ኤፍሬም ነጋ ገ/እግዚአብሄር
ሄኖክ ነጋ ገ/እግዚአብሔር
ይትባረክ ነጋ ገ/እግዚአባሄር
ሠላም ነጋ ገ/እግዚአብሔር
ራሄል ነጋ ገ/እግዚአብሄር
ዮርዳኖስ ደሣለኝ ገ/እግዚአብሄር
ቅድስት ድጉማ ዋቅጅራ
አናኒያ ብርሃኔ እጅጉ
ተዋበች ወርቁ ወልፃዲቅ
ብሩክ ከበደ ታደሰ
ፍቅረማርያም ከበደ ታደሰ
ክብነሽ ከበደ ታደሰ
ዳኝነት ከበደ ታደሰ
ትዕግስት ከበደ ታደሰ
ሙሉነህ ከበደ ታደሰ
ትዕዛዙ ከበደ ታደሰ
ቴዎድሮስ ማዕረግ አዱኛ
አይንአዲስ በረከት ኃ/ጊዮርጊስ
ወይንሸት ወርቁ አንጋሶ
መብራቱ እጅጉ አበራ
የማነ ብርሃን እጅጉ አበራ
መሀሪ እጅጉ አበራ
ዮሐንስ እጅጉ አበራ
ለምለም እጅጉ አበራ
ሠናይት እጅጉ አበራ
ካሰች አምደመስቀል መገርሳ
ዮናታ ማርክነህ አለማየሁ
ኤልሻዳይ ማርክነህ አለማየሁ
ባልጊቴ አለማየሁ ወዳቦ
ባፋነ አለማየሁ ወዳቦ
አየለ አለማየሁ ወዳቦ
ብርሃኑ ዓለማየሁ ወዳቦ
አበራ አለማየሁ ወዳቦ
እጀትግስት ዓለማየሁ ወዳቦ
ሚካኤል አምደመስቀል መገርሳ
ዳኛቸው አምደመስቀል መገርሳ
ተረፈ አምደመስቀል መገርሳ
ተክሉ አምደመስቀል መገርሳ
ደርባቸው አምደመስቀል መገርሳ
መቅደስ አምደመስቀል መገርሳ
ትዝታ አምደመስቀል መገርሳ
ሙሉጸጋ አምደመስቀል መገርሳ
ውቢት ኃይለገብርኤል አስፋው
ያዕቆብ ደጉ ሆቢቾ
ዮናታል ደጉ ሆቢቾ
ዳግማዊ ደጉ ሆቢቾ
ኡፋይሴ ሆቢቾ አልቤ
ዲቃም ቤቢሶ አልቤ
ካሳሁን ኃይለገብርኤል አስፋው
አምሃ ኃይለገብርኤል አስፋው
ዝናሽ ኃይለገብርኤል አስፋው
ምሳዬ ኃይለገብርኤል አስፋው
አበባ ኃይለገብርኤል አስፋው
ፍሬህይወት ጌታቸው ሀብቴ
ጌታቸው ምስጋና ተፈሪ
ዮሴፍ ጌታቸው ምስጋና
ዮናታን ጌታቸው ምስጋና
ጌታቸው ሀብቴ ተክለሃይማኖት
አብረኸት ገብረመድህን ጣሰው
አበባው ጌታቸው ሀብቴ
ገስጥ ጌታቸው ሀብቴ
ደሳለኝ ጌታቸው ሀብቴ
ቤተልሄም ጌታቸው ሃብቴ
ዜና ጌታቸው ሀብቴ
ሳህሌ ገላው ፈንቴ
ላይኩን ውብየ ተሰማ
አበባው ላይኩን ውብየ
በትረወርቅ ላይኩን ውብየ
ዳዊት ላይኩን ውብየ
አብርሃም ለይኩን ውብየ
ህሉፍ አብርሃ ሐጎስ
አስመለሻ አብርሃ ሐጎስ
ስዬ አብርሃ ሐጎስ
አሰፋ አብርሃ ሐጎስ
ወ/ስላልሴ አብርሃ ሐጎስ
ትምኒት አብርሃ ሐጎስ
ፀሐይነሽ ገ/ሚካኤል ገብሩ
ንግስቲ ሳመሶነ ብሩ
እጅግጋየሁ ሳምሶን ብሩ
ኢትዮጵያ ሳምሶን ብሩ
ያለም መብራት ሳምሶን ብሩ
ቢተወደድ ሳምሶን ብሩ
ሚዛን ሳምሶን ብሩ
በእግዚአብሔር አለበል ኃይሉ
ኤልሳ ታደለ ኃይሉ
ናአምን በእግዚአብሔር አለበል
ቅዱስ በእግዚአብሄር አለበል
በረኽት በእግዚአብሄር አለበል
አለበል ኃይሉ አዱኛ
እቴነሽ ብሩክ ደስታ
ዘላለም አለበል ኃይሉ
ነፃነት አለበል ኃይሉ
የሰውዘር አለበል ኃይሉ
በሁሉም አለበል ኃይሉ
ሰላም አለበል ኃይሉ
ዮናስ ታደለ ኃይሉ
ሚካኤል ታዳለ ኃይሉ
ዮሴፍ አዳዩ ገብሩ
ሃና በርሄ ሀጎስ
ግሎሪ ዮሴፍ አዳዩ
ሊዮ ዮሴፍ አዳዩ
አዳዩ ገብሩ ዲኒ
አብርሃ አዳዩ ገብሩ
ራህዋ አዳዩ ገብሩ
ብርክቲ አዳዩ ገብሩ
ኢንዲሪያስ አዳዩ ገብሩ
ፋና አዳዩ ገብሩ
ታበቱ አዳዩ ገብሩ
ስላስ አውዓለ ሐጎስ
ኃ/ስላሰ በርሄ ሀጎስ
ተስፋይ በርሄ ሀጎስ
ብሩር በርሄ ሀጎስ
ዘቢብ በርሄ ሀጎስ
ጌታነህ ግደይ ንርኤ
ኤደን ብርሃነ ገ/ህይወት
አበባ ግደይ ንርኤ
ዙፋን ግደይ ንርኤ
ደስታ ግደይ ንርኤ
ዮሐንስ ግደይ ንርኤ
መንግስቱ ግደይ ንርኤ
ሀብቶም ግደይ ንርኤ
ቢኒያም ብርሃነ ገ/ህይወት
ኤልሻዳይ ብርሃነ ገ/ሕይወት
ብርክታዊት ብርሃን ገ/ህይወት
ገ/መድህን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ገ/ህይወት ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ኪዳን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ሱራፌል ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ብርያ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
እግዜሄሩ ወ/ጊዮርጌስ ወ/ሚካኤል
ግደይ ተስፋ ገ/ስላሴ
ስላስ ተስፋይ ገ/ስላሴ
ለተመስቀል ተስፋይ ገ/ስላሴ
ማህተመሥላሴ ጥሩነህ በርታ
ማሞ በርታ ባቦ
ታደሰ በርታ ባቦ
ዳዊት በርታ ባቦ
ብሩክ በርታ ባቦ
አበበች በርታ ባቦ
አመለወርቅ በርታ ባቦ
እመቤት በርታ ባቦ
ፍቅርተ በርታ ባቦ
ይልማ ፈንታ ቻይ
አንጋች ፈንታ ቻይ
ሸዋዬ ፈንታ ቻይ
ፈጠነ ታገለ አወቀ
ቻለ ታገለ አወቀ
እማዋ ታገለ አወቀ
አልጋነሽ ታጋለ አወቀ
እመቤት ታጋለ አወቀ
ዳዊት አሰፋ ዘውዱ
ትዕግስት አሰፋ ዘውዱ
ጥሩወርቅ አሰፋ ዘውዱ
ተወዳጅ አሰፋ ዘውዱ
መልካም አሰፋ ዘውዱ
ማህሌት አሰፋ ዘውዱ
ዝናሽ ብርሃኑ በሻህ
ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
ፍሬህይወት ብርሃኑ በሻህ
አብዮት ብርሃኑ በሻህ
ግልነሽ ብርሃኑ በሻህ
ሰለሞን ብርሃኑ በሻህ
አዲስ ብርሃኑ በሻህ
ካህሳይ ጉላል አለመ
ዘውዲቱ ለምለም ገ/ማርያም
ብስራት ገ/መድህን ተስፋይ
ግርማይ ብስራት ገ/መድህን
ዮሀንስ ብስራት ገ/መድህን
አበባ ብስራት ገ/መድህን
ለተመስቀል ብስራት ገ/መድህን
ሚዛን ብስራት ገ/መድህን
አክበረት ብስራት ገ/መድህን
ገ/መድህን ሀጎስ ንጉሴ
ጌቱ ገ/መድህን ሀጎስ
ሳራ ገ/መድህን ሃጎስ
ፍፁም ገ/መድህን አብርሃ
ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
አለም ስንሻው አማረ
ሐጎስ ፍፁም ገ/መድህን
ኃይሌ ፍፁም ገ/መድህን
ኤርሚያስ ፍፁም ገ/መድህን
ደሊና ፍፁም ገ/መድህን
ገነት ገ/መድህን ሀጎስ
ኮነ ምህረቱ እሸቱ
መንበረ ታምራት በየነ
ፍስሐ ኮነ ምህረቱ
ፍረህይወት ኮነ ምህረቱ
መስከረም ኮነ ምህረቱ
ቅድስት ኮነ ምህረቱ
ዘይሰድ ኢሳ አወል
ተስፋዬ ወልዱ ፍስሃ
ሰብለወንጌል ዘውዴ ዋለ
ዳንኤል ዘውዴ ዋለ
ሙሉቀን ዘውዴ ዋለ
ብርሃኑ ዘውዴ ዋለ
ጌትነት ዘውዴ ዋለ
ታምራት ዘውዴ ዋለ
አምባው ሰገድ አብርሃ
ብርነሽ ሐጎስ ካህሳይ
ህሊና አምባው ሰገድ
ብሩክ አምባው ሰገድ
ሜሮን ገ/ስላሴ ገብሩ
ሳባ ኪሮስ ወ/ገብርኤል
አፀደ ገ/ስላሴ ገብሩ
አብርሃ ገ/ስላሴ ገብሩ
ያሬድ ሰገድ አብርሃ
ክብሮም ሰገድ አብርሃ
ፀዳለ ሰገድ አብርሃ
ፅጌ ሰገድ አብርሃ
ፀሐይነሽ ሰገድ አብርሃ
ተክለአብ ዘርአብሩክ ዘማርያም
ፅጌረዳ ደርበው አዳነ
ዘርአብሩክ ዘማርያም ረዳ
ሂሩት ፀጋዬ ገ/መድህን
አቤል ተክለአብ ዘርአብሩክ
ምህረትአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ሠላማዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ፀጋዘአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ሣምራዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ዳንኤል ደርበው አዳነ
ሠላዊት ደርበው አዳነ
ሄሳን ደርበው አዳነ
ኤደን ደርበው አዳነ
ጌታሁን ቱጂ ደበላ
ምኞት ብርሃኑ አበራ
ሮዳስ ጌታሁን ቱጂ
አዴራት ጌታሁን ቱጂ
ሲሳይ ቱጂ ደበላ
እመቤት ቱጂ ደበላ
ጋሻው ብርሃኑ አበራ
አዲሱ ብርሃኑ አበራ
ሠላም ብርሃኑ አበራ
ክብረወሰን ብርሃኑ አበራ
ዘለቀ ልየው ካሳ
ግንቻየው አድሮ ኃይሉ
ዮሐንስ ዘለቀ ልየው
ሊዲያ ዘለቀ ልየው
ጥሩአለም አድሮ ኃይሉ
ዮሴፍ አድሮ ኃይሉ
ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
ተናኜ እሸቴ አዳፍሬ
ሠላማዊት ያዴሳ ሚዴቅሳ
ገመቺሳ ያዴሳ ሚዴቅሳ
ብልሴ ያዴሳ ሚዴቅሳ
መኮንን ሚዴቅሳ ዲባባ
በጂጌ ሜዴቅሳ ዲባባ
ሽታዬ ሚዲቅሳ ዲባባ
ፅጌ ሚዴቅሳ ዲባባ
ልኪቱ ሞሲሳ ቦኮ
ከበደ ደጀኔ ገለታ
ፍስሐ ደጀኔ ገለታ
የሻነው ደጀኔ ገለታ
ዘላለም ደጀኔ ገለታ
ትዕግስት ደጀኔ ገለታ
መታሰቢያ ደጀኔ ገለታ
ሠናይት ደጀኔ ገለታ
መላኩ ግርማ ገብሬ
እህተ ቱኒ ኦርጋጋ
ብርሃኑ ግርማ ገብሬ
ጌትነት ግርማ ገብሬ
አብርሃም ግርማ ገብሬ
ዳዊት መኮንን ተመስገን
እሴታ ባረጋ ሽራጋ
አሚን ዳዊት መኮንን
ዘሪሁን ዳዊት መኮንን
ዜና መኮንን ተመስገን
ማርታ መኮንን ተመስገን
መኮንን ተመስገን የሽታ
ፍሬሕይወት ማሞ አና
መቅደስ ባረጋ ሽራጋ
ብርሃኑ ባረጋ ሽረጋ
ቅጣው ባረጋ ሽራጋ
ባረጋ ሽራጋ ሽራጋ
አስፋው ስዩም ታፈረ
ማርታ የማነህ ተስፈሚካኤል
መስፍን ስዩም ታፈረ
መንገሻ ስዩም ታፈረ
አንባቸው ስዩም ታፈረ
ሂሩት ስዩም ታፈረ
ሠላማዊት ግርማ ፈለቀ
በፀሎት አበበልኝ ተስፋዬ
ኪሮስ ገ/መድህን ገ/ተክለ
ትዕግስት ተስፋዬ ፊታሞ
ሊዲያ ተስፋዬ ፊታሞ
ሐዲያወርቅ ተስፋዬ ፊታሞ
ታሪኩ አበበ ፊታሞ
ፍስሃ አበበ ፊታሞ
ማርክስ አበበ ፊታሞ
ምንአለ አበበ ፊታሞ
ዘይነባ እሸቱ ኃይሌ
ኑርሃን ጌታቸው አሰፋ
ሐይመን ጌታቸው አሰፋ
ሰሚሩ ጌታቸው አሰፋ
ኢምራን ጌታቸው አሰፋ
የንጉስነሽ አሰፋ ሀምዛ
መንገሻ አሰፋ ሃምዛ
መሰለ አሰፋ ሃምዛ
ልዑልሰገድ አሰፋ ሀምዛ
መሐመድ አሰፋ ሀምዛ
ናስር እሸቱ ሃይሌ
ዛህር እሸቱ ሃይሌ
መሐመድ እሸቱ ሀይሌ
ራቢያ እሸቱ ሃይሌ
ምፅላል ሃይሉ አለማየሁ
ጌጤ ማቲዮስ ገ/ኪዳን
ትዕግስት በላቸው በየነ
ሱራፌል በላቸው በየነ
ሰላማዊት በላቸው በየነ
አበባየሁ ዘበነ ተኮላ
ማሚቱ በየነ ገ/ዮሐንስ
አዳነ ተሰማ በረሳ
ታሪኩ ተሰማ በረሳ
ሲሳይ ተሰማ በረሳ
ተፈሪ ተሰማ በረሳ
ዜና ተሰማ በረሳ
ሙሉጌታ ተሰማ በረሳ
እመቤት ተሰማ በረሳ
ጠጅነሽ ጎሳዬ በረሳ
አንለይ አሳምነው ተሰማ
ራሄል ገበደ ኃ/ማርያም
ናርዶስ አንለይ አሳምነው
ፍፁም አሳምነው ተሰማ
ማናዬ አሳምነው ተሰማ
ይርጋለም አሳምነው ተሰማ
ፍፁም ከበደ ኃ/ማርያም
በኃይሉ ከበደ ኃ/ማርያም
ሱራፌል ከበደ ኃ/ማርያም
ቢኒያም ከበደ ኃ/ማርያም
መስፍን ከበደ ኃ/ማርያም
እመቤት ከበደ ኃ/ማርያም
መሰረት መንግስቱ በየነ
ሠላማዊት ማሩ ፍቅሩ
ፍቅርተ ማሩ ፍቅሩ
ስንታየሁ ወይም አሰለፈች ማሩ ወርዶፋ
በቀለች ማሩ ወርዶፋ
ጥሩወርቅ መንግስቴ በየነ
ገ/መድህን ገ/የሱስ ስብሃት
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የሱስ
ንብረት ገ/መድህን ገ/የሱስ
ማሞ ኪሮስ በዛብህ
ራሄል አስረስ መኮንን
አዶኒያስ ማሞ ኪሮስ
ብሩክ ማሞ ኪሮስ
ዳግም ማሞ ኪሮስ
ኢዮስያስ ማሞ ኪሮስ
ናሆም ማሞ ኪሮስ
ደሳዊ ማሞ ኪሮስ
ኪሮስ ገ/ህይወት በርሄ
አለም ኪሮስ በዛብህ
ፅጌ ኪሮስ በዛብህ
ፋና ኪሮስ በዛብህ
አፀደ ኪሮስ በዛብህ
አብይ አስረስ መኮንን
ቤተልሄም አስረስ መኮንን
ሂሩት አስረስ መኮንን
ፀደይ አስረስ መኮንን
ሸዋዬ መስፍን አበራ
ኤልዳና ስንሻው አለምነህ
አርሴማ ስንሻው አለምነህ
ምስጋና ይሳቅ ገድባ
በረከት ይሳቅ ገድባ
የመከረ መኮንን ተሰማ
ማራማዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
መቅደላዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
ቤተል ዳዊት ኢትዮጵያ
ወለላ ተስፋዬ ብሩ
ተፈሪ ኢትዮጵያ መኮንን
ፍሪው ኢትዮጵያ መኮንን
ግሩም ኢትዮጵያ መኮንን
ትዕግስት ኢትዮጵያ መኮንን
ውቢቱ ኢትዮጵያ መኮንን
ለምለም ኢትዮጵያ መኮንን
ፀሐይነሽ መንግስቱ አዳል
መቅደስ መኮንን ተሰማ
እሸቱ ግረፍ አስታክል
ብስኩት ደመቀ ታከለ
ማየት እሸቱ ግረፍ
ቤተል እሸቱ ግረፍ
ኢዮስያስ እሸቱ ግረፍ
ታደሰ ደመቀ ታከለ
በኃይሉ ደመቀ ታከለ
ብርሃኑ ደመቀ ታከለ
ልፍነሽ ገለታ ዳዲ
እቴነሽ ግረፍ አስታክል
በላይነሽ ግረፍ አስታክል
ዘውዱ ግደይ ካህሲ
በረከት ተመስገን ስዩም
ሚሚ ተመስገን ስዩም
ካህሳይ ጉልላት አለመ
ሰመረ ግደይ ካህሲ
ኢሊኑ ግደይ ካህሲ
ምህረት ገ/መድህን ገ/የስ
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የስ
ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ
ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማ
ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል
አዲስ የልብ ህክምና ክሊኒክ
ምፍአም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ነፃ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዎው ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ኤምዲ ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዲ ኤች ሲሚክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የስም ዝርዝሩን የወሰድነው ከኢሳት ነው።

Total Pageviews

Translate