Pages

Oct 21, 2013

“ለዋልያዉ ልጫወት”…በቻምፕዮንስ ሊግ የተጫወተዉ ዋሊድ አታ የስዊድኑ ሂልስነቦርግ ተከላካይ

ይህ ከዋሊድ አታ የስዊድኑ ሂልስነቦርግ ተከላካይ ለTeam Ethiopia የfacebook pageየተላከ ደብዳቤ ነዉ፤ተጫዋቹ በዩሮፓ ሊግ እና ቻምፕዮንስ ሊግ ተጫዉትዋል፤ለዋልያዉም ለመጫወት ፍላጎቱን የገለፀዉ ከናይጄሪያ ጨዋታ በፊት ቢሆንም ከዋልያ በኩል ምንም ምላሽ አላገኘም..ከዚህ ደብዳቤ ጋር አብሮ የተጫዋቹን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ምስል አለ..እናም እናንት የዋሊድን ጥያቄና ምስሉን አይታችሁ ትፈርዱ ዘንድ እነሆ!!!
My name is Walid Atta, born in Riyadh in Saudi Arabia in August 28th 1986. My career as a professional football player started in early 2008 when I joined team AIK in Stockholm Sweden. Team AIK was founded in 1891 (122 years ago) and is measured as top club in the Swedish league for decades. During my engagement with AIK (3 years) I gained a lot of experience in all aspect of professionalism as a football player. Throughout these years a became a key player and performed very well in many games in the league also in some international games as well. These 3 successful years became my key to the Swedish national team of U21 and many offer from international clubs, like Glasgow Rangers from Scotland, Valencienne from France and Dinamo Zagreb from Croatia and a few more. After consulting family and my agent I decided to sign up for Dinamo Zagreb from Croatia. Less successful journey with injuries and unstable club economy leading to the club not been able to pay players’ salaries.  Subsequently free ticket from Dinamo Zagreb to leave the club and sin up for any other club with no obligation what so ever.

Helsingborg IF, Swedish football clublocated in a city of  Helsingborg. the club was previous year champions of Swedish league which means Europa Champions League qualifications games to be played if I signed up for the club which I did. Successful story again many international games like hanover 96, Levante and Twente , 7 goals as a center back more than any defender in the league, many offers from clubs in Europe, and voted to be player of the year.

I  have been following the Ethiopian national team in African cup and world cup qualification and I am so impressed and proud how they are progressing just getting better and better It looks good and promising for Ethiopian football in future and hopefully I can be a part of that team and contribute to an even greater success, that would be a fantastic honor.

Kind Regards
Walid Atta
http://www.youtube.com/watch?v=0xHxGnHlJ6M&feature=youtu.be

Oct 20, 2013

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት አይሏል::

 

ምንሊክ ሳልሳዊ
ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገው ሩጫ ተቃውሞ ገጥሞታል::
ከፍተኛ ጄኔራሎች ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አብዝተዋል::የምስጢራዊ ስብሰባ ቃለ ጉባዬ የምትይዝ የሆነችው የአንድ ከፍተኛ ጄነራል ጸሃፊ ትክዳ ወይም ትገደል አልታወቀም::ለሜ/ጄ ዮሃንስ ethiopian_troops_pickup-300x222ገብረመስቀል የተሰጠው የሌ/ጄ ማእረግ የታሰበው ሌ/ጄ ሳሞራን ይተካሉ ተብለው ለነበሩት ለሜ/ጄ አበባው ታደሰ የነበረ ቢሆንም በምን ምክንያት እንደተዘዋወረ አልታወቀም::
በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በከተማ እና በሌሎች የእዝ መምሪያዎችም መቀጠሉን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየኡ መሆኑ ተጠቁሟል::
ሰራዊቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሳው ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው:: በቅርቡ ከስልጣን ይነሳል የሚባለው ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የብኣዴን ታጋይ መኮንኖች የተቃወሙት ሲሆን እኛም ከማንም ያላነሰ የታገልን ስለሆነ ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው ብኣዴን እያለው ለምን እንዲህ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አንስተዋል::
ከፓርቲ አጣብቂኝ ያልተላቀቀው የመከላከያ ሰራዊቱ የበላይ አመራር ህገመንግስታዊ መዋቅር እንዲይዝ ለማድረግ ምንም አይነት ስራ አለመሰራቱ በሰራዊቱ አዳዲስ መኮንኖች ዘንድ አቤቱታ ቢያስነሳም ጄኔራሎቹ የሚያደርጉት ምስጢራዊ ስብሰባ እንዴት መፍታት ሳይሆን ማክሸፍ እንደሚቻላቸው እየመከሩ ሲሆን አዳዲስ ወታደራዊ ደህንነቶችን በየእዙ አስርጎ በማስገባት እንዲሁም የሰራዊቱን አቤቱታ ያስተባብራሉ የሚባሉትን በስራ ምክንያት በየማእዘኑ በመበተን ለመስራት የታቀደ ሲሆን የአበታተኑን ሁኔታ በማስጠናት ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በተጨማሪ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ይረዳቸው ዘንድ ኮማንዶዎችን እና ንቁ የደህንነት ጠባቂዎችን ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ለመመደብ ተነጋግረዋል::
መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ምዽር ጦር መምሪያ እንዲሁም ደብረዘይት እና አስፈላጊም ሲሆን በመኖሪአ ቤቶቻቸው የሚያደርጉትን ስብሰባ ቃለጉባዬ የምትይዘው የአንድ ጄኔራል ጸሃፊ ከድታ ይሁን ተገድላ ሳይታወቅ ካለፈው ሳምንት ጀምራ በስራ ገበታዋ ላይ ያልተገኘች እና የት እንዳለች የማይታወቅ ሲሆን ስልኳም መዘጋቱን ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ

Oct 19, 2013

ዜጎችን እያቀጨጨ የሚፈረጥም መንግስት… ብዙ አይራመድም ስንት እድሜ ይኖረዋል?

 

Image

የውጭ ንግድ ፈቅ አላለም፤ ባለበት ደንዝዞ ቆሟል - የንግድ ሚኒስቴር መረጃ።
የግል ኢንቨስትመንት ተዳክሟል፤ ድርሻው በግማሽ ቀንሷል - የIMF መረጃ።
የአገሪቱ የባንክ ብድር፣ 90% ወደ መንግስት ይሄዳል - የአለም ባንክ ሪፖርት።
“ትልልቅ ፕሮጀክቶች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተቀየዱ የሚሄዱበት እድል ሰፊ ነው” … የኤክስፖርት ገቢ መዳከሙን በመግለፅ ይህን የተናገሩት የንግድ ሚኒስቴር ሃላፊዎች ናቸው። ያሳስባል፣ እውነታቸውን ነው። ነገር ግን፣ ትልቁና አሳሳቢው ነገር፣ የመንግስት ፕሮጀክቶች መስተጓጎላቸው አይደለም። የውጭ ንግድ መዳከም፣ ጠቅላላ በአገር ኢኮኖሚና በዜጎች ኑሮ ላይ ተጨማሪ ችግር እንደተደቀነ የሚጠቁም ምልክት ነው። ደግሞስ፣ የመንግስት ገናናነት እየገዘፈ፣ የግል ኢንቨስትመንት እየቀጨጨ፣ እንዴት ጥሩ ውጤት ይገኛል ብሎ መጠበቅ ይቻላል?
አሳዛኙ ነገር፣ መንግስት ራሱን በራሱ ጠልፎ እየጣለ መሆኑን አለመገንዘቡ ነው። መንግስት “የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ” ውስጥ የዘረዘራቸውን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ለማሳካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስፈልገዋል። ግን ምን ዋጋ አለው? ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ የሆነው የግል ኢንቨስትመንት እየቀጨጨ የመጣው፣ “በእድገትና ትራንፎርሜሽን እቅድ” ሳቢያ ነው። ተግባራዊ የተደረጉ የመንግስት እቅዶች፣ የኤክስፖርት ገበያውንና የውጭ ምንዛሬ ምንጮችን እንዴት እየጎዱ እንደሆነ ለማሳየት እሞክራለሁ።
በእርግጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የሚስተጓጎል ፕሮጀክት የለም ብለዋል። የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በጭራሽ አይጓተትም ያሉት ጠ/ሚ ኃይለማሪያም፣ ሌሎቹ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ደግሞ በውጭ ብድር የሚካሄዱ በመሆናቸው የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደማያሳስብ ለመግለፅ ሞክረዋል።
እንዲያም ሆኖ፣ ከኤክስፖርት የሚገኘው ገቢ የታሰበውን ያህል እንዳልተሳካ አልካዱም። ቢሆንም፣ ይህንን ጉድለት የሚሸፍን ነገር ተገኝቷል። ከተለያዩ ምንጮች ወደ ኢትዮጵያ የተላከው የውጭ ምንዛሬ ከተጠበቀው በላይ ሆኗልና። ለነገሩ፣ በየአገሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየአመቱ የሚልኩት ገንዘብ ቀላል አይደለም። በአመት ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ እየላኩ ነው። ከኤክስፖርት ከሚገኘው ዶላር ይልቅ፣ ከዳያስፖራ የሚመጣው በልጧል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለቤተሰብና ለዘመድ የሚልኩት ገንዘብ መጨመሩ ጥሩ ነው። ነገር ግን፣ የኤክስፖርትን ጉድለት ይሸፍናል በሚል የሚያፅናና አይደለም - በእጅጉ የሚያሳስብ እንጂ።
ከሳምንት በፊት ጠ/ሚ ኃይለማሪያም፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት የመንግስት ፕሮጀክቶች እንደማይስተጓጎሉ ቢገልፁም፤ ከምር ሳያሳስባቸው የቀረ አይመስለኝም። በዚያው ሳምንት የንግድ ሚኒስቴር ሃላፊዎች ከክልል መስተዳድር ተወካዮች ጋር ተሰብስበው የተነጋገሩበት ዋና ርዕሰ ጉዳይ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ነው። ወደ ውጭ የሚላኩ የእርሻና የፋብሪካ ምርቶች፣ በጥራትና በብዛት እየቀረቡ አይደለም በማለት የተናገሩት የንግድ ሚኒስቴር ሃላፊዎች፣ “ትልልቅ ፕሮጀክቶች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተቀየዱ የሚሄዱበት እድል ሰፊ ነው” በማለት አሳሳቢነቱን ገልፀዋል።
ከአመት አመት የኤክስፖርት እድገት እየተዳከመ መምጣቱን የሚክድ ይኖራል ብዬ አልገምትም። አሁን ደግሞ፣ ከነጭራሹ ቅንጣት እድገት አልታየም። እንዲያውም የኤክስፖርት ገቢ ቀንሷል። በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ከተዘረዘሩት “ግቦች” ጋር ሲነፃፀርማ፣ በእጅጉ ወደኋላ ቀርቷል። የእቅዱ ግማሽ ያህል እንኳ አልተሳካም።
በእቅዱ የመጀመሪያ ዓመት በ2003 ዓ.ም፣ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የነበረውን የኤክስፖርት ገቢ በአንድ ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ (3 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ) ቢታሰብም፣ የእቅዱ 75 በመቶ ብቻ ነው የተሳካው። ቀላል እድገት ነው ማለቴ አይደለም። 2.75 ቢሊዮን ደርሷል። በቀጣዩ ዓመት ግን፣ እድገቱ ተዳክሟል። በ“ኦሪጅናሉ” እቅድ መሰረት፣ የኤክስፖርት ገቢ በ2004 ዓ.ም ወደ አራት ቢሊዮን ዶለር የሚጠጋ ይሆናል ተብሎ ነበር የታሰበው። በተግባር የተገኘው ገቢ ግን 3.15 ቢ. ዶላር ነው። ከመነሻው አመት ጋር ሲነፃፀር በሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ገቢ ለማግኘት ቢታቀድም፣ በተግባር የተገኘው እድገት 1.2 ዶላር ገደማ ነው። እናም እቅዱ 60 በመቶ ብቻ ነው የተሳካው ማለት ይቻላል።
አሁንም ኦሪጅናሉን እቅድ ካስታወስን፣ በ2005 ዓ.ም ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የኤክስፖርት ገቢ ለማግኘት ታስቦ እንደነበር እናያለን። በተግባር የተገኘው ውጤት ደግሞ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው። የአመት አመት እድገቱ ተዳክሞ ከመቆሙም በላይ፣ የኋሊት መንሸራተት ጀምሯል። በ2002 ዓ.ም ከነበረው መነሻ አሃዝ ጋር ስናነፃፅረው፣ በሦስት ቢሊዮን ዶላር የላቀ እንዲሆን ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ 1.1 ቢሊዮን ዶላር ያህል ብቻ ነው የተሳካው። የእቅዱ 37% ብቻ ማለት ነው። ከአመት አመት የስኬቱ መጠን እየቀነሰ መሆኑን የምታስተውሉ ይመስለኛል።
ዘንድሮም የኤክስፖርት ገቢ ከሰባት ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ይሆናል ተብሎ በእድገትና ትራንስፎርሜሽ እቅዱ ውስጥ ተጠቅሷል። ሃሙስ እለት የወጣው የአይኤምኤፍ መግለጫ እንደሚያመለክተው ግን፣ የኤክስፖርት ገቢው 3.6 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ይሆናል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
እንግዲህ አስቡት፤ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ የሰፈረው፣ በ2002 ዓ.ም ሁለት ቢሊዮን ዶላር የነበረውን የኤክስፖርት ገቢ፣ በ2006 ዓ.ም በአምስት ቢሊዮን ዶላር ይጨምራል የሚል እቅድ ነው። በእውን ይታያል ተብሎ የሚጠበቀው ጭማሪ ግን 1.5 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው። የእቅዱ 33% ብቻ መሆኑ ነው።
የእቅዱ ስኬት ከአመት አመት እየቀነሰና እየተሸረሸረ የመጣው አለምክንያት አይደለም። የእቅዱ መዘዝ ከአመት አመት እየጨመረና እየተደራረበ ስመጣ ነው። ‘መዘዝ’ ስል፣ ያልታሰበና ያልተጠበቀ መመዝ ማለቴ አይደለም። በደንብ ታስቦበታል። ከዚያም አልፎ፣ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ በይፋ ተዘርዝሯል። በአምስት አመታት ውስጥ በአገሪቱ ከሚካሄዱ የኢንቨስትመንት ስራዎች ውስጥ 67 በመቶ ያህሉ በመንግስት ፕሮጀክቶች፣ 33 በመቶ ያህሉ ደግሞ በግል ኢንቨስትመንት እንደሚሸፈን በ“እቅዱ” ውስጥ ተጠቅሷል። በሌላ አነጋገር፣ የመንግስት ፕሮጀክቶች፣ ከግል ኢንቨስትመንቶች በእጥፍ እንዲበልጡ ነው የታቀደው።
ድሮ እንደዚያ አልነበረም። ኢህአዴግ ስልጣን በያዘባቸው የመጀመሪያ አመታት፣ ከመንግስት ፕሮጀክቶች ይልቅ የግል ኢንቨስትመንት ድርሻ ይበልጥ ነበር - (የግል ኢንቨስትመንት 70 በመቶ የመንግስት ደግሞ 30 በመቶ)። መንግስት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን እገነባለሁ ቢልም፣ ቀስ በቀስ የግል ኢንቨስትመንት ድርሻ እየቀነሰ፣ በተቃራኒው የመንግስት ፕሮጀክቶች ድርሻ እየጨመረ መጥቷል። የዛሬ አስር አመት ገደማ ነው፣ የሁለቱ ድርሻ እኩል የሆነው (ሃምሳ በመቶ - ሃምሳ በመቶ)። የዚህን ጊዜም ነው፣ በመላው ዓለም ወደ ሶሻሊዝም ያዘነበሉ ናቸው ከሚባሉ አምሳ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ የተገለፀው።
የቁልቁለት ጉዞው ግን በዚሁ አላቆመም። አይኤምኤፍ ሀሙስ እለት ባሰራጨው ዘገባ እንደገለፀው፣ የግል ኢንቨስትመንት ድርሻ ወደ 25 በመቶ እንደወረደና የመንግስት ፕሮጀክቶች ድርሻ 75 በመቶ እንደደረሰ ይገልፃል። በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ከተጠቀሰውም በላይ የከፋ መሆኑን ተመልከቱ። እንዲህ አይነት የመንግስት ገናናነት፣ በብዙ አገራት ውስጥ የለም። በእጅጉ ሶሻሊስታዊ የኢኮኖሚ አካሄድን ከሚከተሉ ሶስት የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ሆናለች የተባለውም በዚህ ምክንያት ነው። ነፃ ገበያ እንዲህ ነው እንዴ?
የመንግስት ፕሮጀክቶች ድርሻ እያበጠ፣ የግል ኢንቨስትመንት ድርሻ እየተደፈጠጠና እየቀጨጨ የመጣው፣ በተለያዩ ምክንያቶች ቢሆንም፣ ትልቁና ዋናው ሰበብ ግን ከባንክ ብድር ጋር የተያያዘ ነው። የባንክ ብድሮች ከአመት አመት ከግል ኢንቨስትመንት እየራቁ ወደ መንግስት ፕሮጀክቶች እንዲጎርፉ ተደርጓል። ከ20 አመታት በፊት፣ ከግማሽ በላይ የባንክ ብድሮች ለግል ኢንቨስትመንትና ለግል ቢዝነሶች የሚውሉ ነበሩ።
ግን ብዙም ሳይቆይ የባንክ ብድር አቅጣጫው ተቀይሮ፣ ወደ መንግስት ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች መጉረፍ ጀመረ። በ2003 ዓ.ም፣ ከባንኮች አዲስ ብድር ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ ለመንግስት ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች እንደተሰጠ የሚገልፀው የአለም ባንክ ሪፖርት፣ ከዚያ ወዲህ ባሉ አመታትም የግል ድርጅቶች የሚያገኙት ብድር ይበልጥ እየቀነሰ እንደመጣ ያትታል። አሁን፣ ከባንኮች ብድር ውስጥ 90 በመቶ ያህሉን የሚወስዱት የመንግስት ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች ናቸው። State Owned Enterprises are increasingly absorbing domestic banking sector credit. In the six-month period from June 2011 to December 2011, 71 percent of new loans were directed towards public enterprises. This share increased to 89 percent during the second half of 2012. A substantial share of the available foreign exchange is similarly diverted towards public investment. (የአለም ባንክ ሪፖርት Ethiopia Economic Update II፡ Laying the Foundation for Achieving Middle Income Status፡ June 2013 … ገፅ 24)
በዚህ መልኩ፣ ለግል ኢንቨስትመንት የሚውል የባንክ ብድር እየተንጠፈጠፈ፣ የግል ኢንቨስትመንት እየቀጨጨ ሲሄድ፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እየቀነሰ መምጣቱን ምኑ ይገርማል? ከሞላ ጎደል በሸቀጦች ኤክስፖርት የሚገኘው ገቢ፣ በግል ድርጅቶችና ኢንቨስትመንቶች አማካኝነት የሚመጣ ነዋ። ታዲያ፣ መንግስት ራሱን በራሱ ጠልፎ አልጣለም ትላላችሁ? በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ የተዘረዘሩትን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ለማከናወን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስፈልገዋል። ነገር ግን፣ “እቅዱ” ልሹ፣ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ የሆኑ የግል ኢንቨስትመንቶችን የሚደፈጥጥና የሚያቀጭጭ ነው።

Oct 17, 2013

የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ?

TPLF-Logo

ከነበሩስ እነማን ናቸው?
ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው።
በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሃገራችን አሁንም  እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው።
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ  ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው።
ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ 1. አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር  2. ዘርኡ ገሰሰ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ገሰሰው አየለ 5. አባይ ፀሃየ 6. ሥዩም መስፍን 7. አለምሰገድ መንገሻ 8. አስፍሃ ሃጎስ ተመርጠው ተሓህትን መርተዋል።
በዚህ ጊዜ ነበር የማገብትን ውርስ ተሓህት ተረከበው ብሎ በጊዜው የነበረ ታጋይ ደስታውን የገለጸው። ውርስ ማለት ፕሮግራሙ ነው። በጊዜው የነበረ ሁሉም ታጋይ ግን የፕሮግራሙን ይዘትና ምንነትቱን አያውቅም ነበር።  ይህ ፕሮግራም ነበር በ1968 ቀስ በቀስም ተሓህትን ለሁለት የመሰንጠቅ አደጋ የፈጠረበት።
 á‹¨á‰°áˆ“áˆ…á‰ľ-ህወሓት የመጀመሪያ መሰንጥቅ
ተሓህት ገና ከደደቢት በረሃ ሳይወጣ በፊት በሁለት ጎራ የተሰነጠቀበት ወቅት ነው። ይህን መከፋፈል የፈጠረው የፕሮግራሙ ባለቤት ነን የሚሉ አመራር በድብቅና ከታማኝ ታጋዮች ጋር በመተባበር ወስጥ ለውስጥ ፕሮግራሙ ይዘጋጅ ነበር። ይህን የማይደግፉና የሚቃወሙ አመራርም ነበሩ።
አክራሪና በአቋማቸው የጸኑ ግን ፕሮግራሙ በትክክል የተዘጋጀ ሃቀኛ የትግራይ ሕዝብ ምኞትና ፍላጎትን በጭብጥ ያስቀመጠ፤ ትግራይን እና ሕዝቧን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነፃ የሚያወጣ፣ የትጋላችን መርህ ፕሮግራም ነው አሉ። የዚህ ተሳታፊውች፤ 1. አረጋዊ በርሄ 2፣ አባይ ፀሃየ 3. ሥዩም መስፍን 4. ግደይ ዘራጽዮን 5. ስብሃት ነጋ 6. መለሾ ዜናዊ 7. አስፍሃ ሃጎስ 8. አውአሎም ወልዱ 9. ስየ አብርሃ 10. ሃይሉ መንገሻ ናቸው። እነዚህ ሁሉ አመራር የነበሩና ጥቂቶቹ ደግሞ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አመራር የመጡ ናቸው።
በሁለተኛ ደረጃ በተቃውሞ የቆሙትና ፕሮግራሙ በጣም አደገኛ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ፣ ሕዝብ በታኝ፣ ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው በማለት የተነሱት ደግሞ 1. ገሰሰው አየለ 2. አግአዚ ገሰሰ 3. አጽብሃ ዳኘው 4. ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ሲሆኑ፣ ከሻእቢያ መጥቶ ተሓህትን የተቀላቀለው መሃሪ (ሙሴ) ተክሌም 5ኛ ሆኖ ከነገሰሰው አየለ ጋር ተቀላቀለ። እነዚህ ሁሉም የተሓህት አመራር የነበሩ ናቸው።
ማህበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) ገና ሲፈጠር ጎባጣ፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ሆኖ ነው የተመሰረተው። ይህንን ውርስ ያስረከበው ለተሓህት በየካቲት ወር 1967 ነው። በደደቢት በረሃ ተጠናክሮ ፕሮግራም ሆነ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፕሮግራሙን በመቃወም የተሰለፉት ያነሱት ነጥብ፤
  1. ተሓህት በጸረ ኢትዮጵያና በሕዝቧ ተቀናጅቶ መፈጠሩ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር መበታተን አለባት የሚለው በገጽ 8 የተዘጋጀው የባእዳን ሴራና ጸረ ሃገር ነው፣
  2. አማራ የትግራይ ሕዝብ ጨቋኝና ረጋጭ፤ ለድህነት፣ ለሽርሙጥና፣ ለስደት፣ ለመከራ የዳረጋት ጠላት ነው የሚለው ትንተና ሃቅነት የሌለው የፈጠራ ወሬ ነው። የተጻፈው አማራን ሆን ብሎ ለማጥቃት ነው። ይህም ከፕሮግራሙ መወገድ አለበት፣
  3. ኤርትራ የአማራው (ኢትዮጵያ) ቅኝ ግዛት ናት የሚለው ቅንጣት ታህል ሃቅነት የሌለው እናንተ አመረር የፈጠራችሁት የተገንጣይ ዓላማ ነው፣
  4. ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት ማለት የአእምሮ ድህነትና ጠባብ ዘረኝነት ነው፣ ስለሆነም መወገዝ አለበት።
  5. ተሓህት የኢትዮጵያ ጥንታዊና ታሪካዊ ግዛትዋን እና የባሕር በሯን የሚያስነጥቅ ፕሮግራም ነው። ስለሆነም ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው። ፕሮግራሙ ይለወጥ ወዘተ. የሚሉ ሃሳቦች በማንቀሳቀስ ቀሪው ታጋይም የእነገሰሰው አየለን ሃሳብ መደገፉን በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች በትክክል ተናግረውታል።
 á‰ á‰°áŒ¨áˆ›áˆŞáˆ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጨመሩበት ነጥብ ተሓህት በትግራይ ሕዝብ ተቀባይነት ወይም የውክልና መሰረት የሌለው፣ ፕሮግራሙን በትግራይ ሕዝብ ስም መዘርጋት አግባብነት የሌለው፣ በሕዝብ ስም ማጭበርበር ነው ብለው በማመን በወቅቱ የነበሩ አነስተኛ ታጋዮች በዚህ ሃሳብ ተስማሙ። በዚህ ጊዜ 1. በስብሃት ነጋ 2. መለሾ ዜናዊ            3. አውአሎም ወልዱ 4. ስየ አብርሃ ወዘተ. ተባብረው በአቶ ገሰሰው አየለ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ። በስብሃት ነጋ እየተመሩ የገሰሰው አየለን ስምና ዝና በጥቁር ቀለም ቀቡት። ሻእቢያም ገሰሰው ከተሓህት ተቀላቅሎ መታገሉን ከመጀመሪያው ያልተቀበለው ስጋት ወስጥ ስለጣለው ነው። ሻእቢያ ለተሓህት አመራር ያስተላለፈው መልእክት፣ ገሰሰው አየለ በዚህ ከቀጠለ ተሓህትም ሆነ ሻእቢያ ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ተናግሯል። ገሰሰው አየለ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት የሚለውን የተህሓት ጥቂት አመራር ሃሳቡን ተቀበሉት።
የእነ ስብሃት ነጋ ቡድን በገሰሰው አየለ ላይ ሲያስፋፉት የነበረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ጥቂቱን እንመልከት፤
  1. ድርጅታችን ተሓህት የገሰሰው አየለ ፊውዳል ድርጅት ነው እየተባለ ነው። ይህንን ግለሰብ ከድርጅቱ ማስወገድ ስላለብን እንተባበር (መለሾ ዜናዊ)፣
  2. ገሰሰው አየለ ፊውዳል፣ ጸረ-ትግራይ ትግል በመሆኑ በተመቸው ጊዜ ጠብቆ ተሓህትን ከማጣፋት አይመለስም። የትግራይን ነፃ ሃገርነትና የትግራይን መንግሥት አይቀበልም። ጸረ-ኤርትራ ትግል ነው። የመትከል አገራችን ሻእቢያም  ተማረውበታል። (ስብሃት ነጋ)፣
  3. ኤርትራና ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት አይደሉም፣ አልነበሩም። ሁሉም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ግዛትና አካል ናቸው፣ ስለዚህ የተሓህት ፕሮግራም ውድቅ ነው እያለ እንደ ምስጥ ውስጥ ለውስጥ እየተሽሎከሎከ ከሕዝብ እየነጠለን ነው (ስብሃት ነጋ)።
በዚህ ጊዜ የነበሩ ታጋዮች እንደሚናገሩት ከሆነ በገሰሰው አየለ ላይ በስብሃት ነጋና መለሾ ዜናዊ የሚመራው ቡድን የተሰማሩበት የስም ማጥፋት ዘመቻ በየቀኑ ይደርሰው ነበር። በመጨረሻ ተማሮ በህዳር 1968 ከማ/ኮሚቴ ሃላፊነቱ ራሱን አግልሏል። ይህ በመሆኑ በሃዘን እና በቁጭት የሚናገሩ በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች ነበሩ። አክራሪውን አመራር ለመቆጣጠር አቅም ነበረን ግን ስህተት ፈጸምን ያሉም አልታጡም።
የዲማ ኮንፈረንስ
የዲማ ኮንፈረንስ የተካሄድው በመጋቢት መጀመሪያ በ1968 ነበር። በዚህ ጊዜ አቶ ገሰሰው አየለ በስብሰባው አልታየም። በወቅቱ በዚህ ጉባኤ የተሳተፉት ታጋዮች ገሰሰው/ስሁል የት ሄደ ብለው ሲጠይቁ የተሰጠው መልስ በሥራ ምክንያት ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል የሚል እንደነበር ይናገራሉ። ኮንፈረንሱ ከመድረሱ በፊት የስብሃት ነጋ ቡድን በአግአዚ ገሰሰ፣ በጥቂቱም ቢሆን በግደይ ዘርአጽዮን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። ነገር ግን ውጤት አልባ ነበር።
በዲማ ኮንፈረንስ የተመረጡት 1. አረጋዊ በርሄ፣ የተሓህት ሊቀመንበር 2. ስብሃት ነጋ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ሥዩም መስፍን 5. አግአዚ ገሰሰ 6. አባይ ፀሃየ 7. ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ ነበሩ። ምርጫው ጸረ-ዲሞክራሲ ስለነበር የነበረው አመራር ስብሃት ነጋን መርጦ መለሾ ዜንዊን ድምጽ ነሳው። በዚሁ ሁሉም ወደየሥራው ሄደ።
ቀደም ብዬ በአርእስቱ ላነሳሁት ጥያቄ መልስ ለመስጠት፣ የተሓህት – ህወሓት ጸረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማን በመቃወም ለሁለት መሰንጠቁና የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው? ለሚለው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እነሆ ፎቶግራፋቸውን ከዚህ በማያያዝ አቀርባለሁ።
   ገሰሰው አየለ       አግአዚ ገሰሰ         ሙሴ መሃሪ ተክሌ            አጽብሃ ዳኛው     ዶ/ር አታክልት ቀጸላ
አቶ ገሰሰው አየለ የበረሃ ስሙ ስሁል፣ ተወልዶ ያደገው ሽሏ አውራጃ ነው። ገና በወጣትነቱ የሽሬ አውራጃ ማዘጋጃ ቤት ዋና ሹም በመሆን አገልግሏል። በ1950 አጋማሽ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል በመሆን ሠርቷል። ለሶስት ተከታታይ ምርጫ በማሸነፍ 15 ዓመት ሙሉ የፓርላማ አባል ነበር። በኢትዮጵያ የተቀጣጠለው አብዮት እየተጠናከረ ሲመጣ በ1966 የማገብት አባል ሆነ።
አቶ ገሰሰው አየለ የማገብትን አላማ፣ ተግባርና ፕሮግራም በጸረ-ኢትዮጵያነት የተሞላ መሆኑን ትኩረት ሳይሰጥ በየካቲት 11 ቀን 1967 ለተመሰረተው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም መስራች በመሆን በአመራር ደረጃ ግንባሩን ሲመል ነበር። የተሓህትን ፕቶግራምና ዓላማ ካየ በኋላ ፍጹም ጸረ-ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብነትን የጨበጠ ፕሮግራምና በፋሽስት ጣልያን የተዘጋጀ ነው እስከማለት ደረሰ። በህዳር 1968 ከአመራሩ ወረደ።
አቶ ገሰሰው አየለ ያነሳው ተቃውሞ ብዙ ቢሆንም ከተራ ቁጥር 1-4 ያሉትን አንኳር ሃሳቦች አስነስቷል። ታጋዩም ድጋፍ ሰጠው። ከአመራሩም እንደነ አግአዚ ገሰሰ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክለት ቀጸላና መሃሪ ከጎኑ ተሰለፉ። በተሓህት ውስጥም ጭንቀትና ሽብር በአመራሩ ወስጥ ተፈጠረ። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድንም ገሰሰው አየለን በዘዴ ለማጥፋት እቅዱን ዘረጋ።
 á‹¨áŒˆáˆ°áˆ°á‹ አየለ ደብዛ መጥፋት
ከዲማ ኮንፈረንስ በኋላና ክዛም ትንሽ ቀደም ብሎ ገሰሰው አየለ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ሲሉ የት ገባ የሚሉ ታጋዮችም በዙ። በዚህ ጊዜ የተሓህት አመራር እርስ በርሱ የሚጋጭ ወሬዎች በድርጅቱ አሰራጨ።
  1. በአዲ ነብራኡድ ወስጥ በኢዲዩ ወይም ጠርናፊት ድንገተኛ ጦርነት ከፍተው ጠርናፊት ገደለችው፣
  2. እኔ ስለሸመገልኩ አልታገልም ገንዘብ ስጡኝና ሱዳን ሄጄ ልኑር በማለት ገንዘብ ከድርጅቱ ተሰጥቶት በመኪና ተሳፍሮ ሲሄድ በመኪና ውስጥ የነበሩ የኢዲዩ አባላት ገደሉት የሚል ነበር። ሁሉም ውሸት ነው።
ኢዲዩም ይህንን በተመለከተ ሰፊ መግለጫ በተነ። ገሰሰው አየለን እኛ አልገደልነውም፣ ልንገድለውም አንችልም። የወንድማቻቾች ደም በከንቱ አናፈስም የሚል ሲሆን፣ የገደለችው ተሓህት ናት አሉ።
በአዲ ነብራኡድ ተገደለ የተባለበት ምክንያት ሕዝቡ ልሹ ምስክርነቱን በሰጠበት በመጋቢት ወር ጦርነት አልነበረም። የደም መፋሰስ አልታየም አለ። የገደሉት ራሳቸው ወያኔዎች ናቸው ሲል ሕዝቡ ምስክርነቱን ሰጠ። አዲ ነብራኡድ የገሰሰው አየለ ቤት ነው። ጊዜው የአቶ ገሰሰው አየለ ስሁል አሟሟት እውነቱ ግልጽ ሆኖ የወጣበት ጊዜ ነበር። ገሰሰው በስብሃት ነጋ የሚመራው የተሓህት አመራር በማይታወቅ ቦታ ደብቀው ወይም እንደ ግዞተኛ አቆይተው በሰኔ 1968 በጥይት ደብደበው ሽላሎ ቡምበት አካባቢ ተገደለ። በግድያው የተሳተፉትም አውአሎም ወልዱና አሰፋ ማሞ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን አልታወቁም። ይህንን እውነታ ተከታትለው ሃቁን ያገኙት በተሓህት ወስጥ ለትግል የተሰለፉት የገሰሰው አየለ የቅርብ ዘመዶቹ ናቸው። በጊዜው ሃቁን አስቀምጠው አለፉ። ላደረጉት ጥረት የሚመሰገኑና ባለውለታም ናቸው። ጥቂቶቹ፣ ማለትም እንደነ አዘናው ገ/ጻዲቅ ታፍነው የት እንደገቡ የማይታወቁም አሉ።
የአቶ ገሰሰው አየለ በተሓህት ፕሮግራም ያስቀመጠው ነቀፌታና ሃሳቡን የደገፉት ግለሰቦች በከፍተኛ ዲግሪ ከቀ. ኃ. ሼ. ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ እንደነ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋህድ የመሳሰሉ ዘጠኝ ምሁራን የተሓህትን አመራር የውሸት ስም በመስጠት የሥልጣን ሱሰኞች ተብለው ሽልሎ ውስጥ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። እነዚህም በተሓህት አመራር ቅጥራኛ ባንዳዎች ተገድለዋል። ይሁን እና መልእክታቸውን አስተላልፈው ከዚች ዓለም በግፍ ተገድለው አልፈዋል። ስማቸው ግን አልጠፋም፤ ለዘላለም ይኖራል።
2.  ዘርኡ ገሰሰ
ዘርኡ ገሰሰ የበረሃ ስሙ አግአዚ ሲሆን፣ በቀ. ኃ. ሼ. ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነበር። ማገብትን ከመሰረቱት አንዱ ነው። በአመራርም እስክ እለተ ሞቱ ተሓህትን ከሚመሩት መካከል ነበር። ዘርኡ ገሰሰና አቶ ገሰሰው አየለ  በተሓህት ፕሮግራም ጠማማነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑ በሁሉም ነጥብ አይለያዩም፣ አንድ  አቋም ነበራቸው።
ዘርኡ ገሰሰ የተሓህትን ፕሮግራም አጥብቆ ያወግዘዋል፣ በታጋዩም ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ክብርም ያገኘ አመራር ነበር። ይህች ግን ለነስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን እና መለሾ ዜናዊ አትዋጥላቸውም። አደገኛ መሪ ብለው ፈርጀው የሚጠበቀው ልክ እንደ ገሰሰው አየለ በዘዴ ማጥፋት ነበር።
ዘርኡ ገሰሰ በተሓህት ፕሮግራም በገጽ 8 ላይ የሰፈረውን እና ሌላውን ፕሮግራም ሁሉ አደገኛ ስለሆነ ፈጽሞ መወገድ አለበት በማለት ከብዙ አመራሮች ጋር መነጋገሩ የቅርብ ሰዎች የሚሉት ሃቅ ነበር። ነገር ግን ሰሚ አላገኘም። እነ ስብሃት ነጋ የሚገደልበትን ዘዴ ለማመቻቸት ይሯሯጡ ነበር።
አግአዚ ገሰሰ ከግደይ ዘርአጽዮን እና ከአረጋዊ በርሄ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው የሚያውቁ ታጋዮች በዚሁ ሴል ሁለቱ ምንም ዓይነት ተሳታፊነት አልነበረባችውም የሚሉም ብዙ ናቸው። የሴራው አካላት ስብሃት ነጋ፣ መለሾ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ናቸው በማለት ያረጋግጣሉ።
ይህ በእንዲህ እያለ የተሓህት አመራር ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ሆነው ዘዴውን አቀነባብረው ከጨረሱ፣ አግአዚን ጨምሮ በአክሱም ከተማ ትልቅ ሼል እንዳለ አስመስለው ሃሳባቸውን በማቅረብ የሚፈጸመውም በአመራር ደረጃ ስለሆነ አግአዚ ተዘጋጅ ብለው በትንሽ ቀናት እንደሚገናኙ ተወሰነ። ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጠላት በብዛት የሚገኝበት ለመንቀሳቀስም ሆነ መንገዱን መጠቀም በማይቻልበት ቦታ ወቅሮ ማራይ መሆኑ በሕዝብ ግንኙነት ጥናት አግኝተዋል። ወቅሮ ማራይ በደርግ ሚሊሺያ የታጠረ ነው። ቀኑ ደረሰ፣ አግአዚ ገሰሰና ነፃነት ሰንደቅ አብረው ከነስብሃት ጋር ሰመማ በሚባል ቦታ ተገናኙ። ስብሃት ነጋ ለአግአዚ በየትኛው ቦታ ለመሄድ አስበሃል ሲለው በመደባይ ታብር በኩል ሲለው የመረጥከው መንገድ አደገኛ ነው በማለት በሕዝብ ግንኙነት አጥንተን ወቅሮ ማራይ ነፃ መሆኑን፣ ሚሊሻም ሆነ የደርግ ሰራዊት የሌለበት ነው ካሉት በኋላ በህሳቡ ተስማምተው መንገዳቸውን ቀጠሉ። ነፃነት ሰንደቅ አብሮት ስለነበረ ሁሉንም ሰምቶታል። ወቅሮ ማራይ እንደገቡ በሚሊሻ ተከበው በተተኮሰ ጥይት አግአዚ ገሰሰ ወዲያውኑ ወድቆ ሞተ። ነጻነት ግን አመለጠ። እንደምንም ብሎ ዘና ወረዳ ገባ። እዛ ላገኛቸው ታጋዮች የደረሰባቸውን ሲነግራቸው፣ ነፃና ጥሩ መንገድ ነው ብለው ስብሃትና አባይ ፀሃየ አግአዚም የተናገሩትን አምኖ በሚሊሻ ተከበን የጥይት ናዳ ወርዶብን አግአዚን ገደሉት፣ እኔ አመለጥኩ። ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ባዘጋጁት የግደያ ዘዴ የሚቃወማቸውን አግአዚ ገሰሰውን አጠፉት ብሎ የተናገረው በተሓህት ውስጥ ተሰራጨ። ስብሃትና አባይ ተከታትለው ነፃነትን ለማግኘት የተፈጠረው ነገር ለማንም እንዳይነገር አስጠነቀቁ። ሆኖም ግን ነገሩ ተሰራጭቷል። አመራሩም የአግአዚን ሁኔታ አንዲት ቀንም ሳያነሳ ቆይቶ በ1ኛው ጉበኤ በጠላት ተገደለ ብለው ተናገሩ። የስብሃት የግድያ ሴራም ሰመረለት።
3.  መሃሪ ተክለ
መሃሪ ተክለ የበረሃ ስሙ ሙሴ ነው። በቀ. ኃ. ሼ. ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ሲማር የቆየ፤ ከሻእቢያ ጋር የተሰለፈ የሻእቢያ ታጋይና አመራር የነበረ ሰው ነው። ሻእቢያና ማገብትን በማይበጠስ የብረት ሰንሰለት ያቆራኘው መሃሪ ተክሌ ነው። ማገብትን የመሰረቱት እነ አረጋዊ በርሄ በጥር 1967 ሳህል ኤርትራ በረሃ ወርደው በሻእቢያ ወታደራዊ ትምህርት ሰልጥነው ብረት ታጥቀው ደደቢት በረሃ እንዲወርዱ ትልቅ ሚና የተጫወተው መሃሪ ተክሌ ነው። መሃሪ ተክሌ በሻእቢያ ተፈቅዶለት በተሓህት ውስጥ እንዲታገል ደደቢት በረሃ ከነ አረጋዊ በርሄ ተቀላቅሎ የተሓህት ተዋጊም ሆነ።
 á‹¨áˆ™áˆ´ ያልተጠበቀ የአቋም ለውጥ
ሙሴ የሁሉንም ታጋይ ባህሪ ጥናት ለመውሰድ ጥቂት ወራቶች ቢወስድበትም የተሓህት ታጋይ ለምንም ለውጥ ዝግጁ መሆኑን አወቀ። የእነ ገሰሰው አየለ አግአዚ ወዘተ. በተሓህት ፕሮግራም ላይ ያላቸውን አመለካከት አወቀ። ከአስገደ ገ/ሥላሴም ጋር ጥሩ ግንኙነት መሰረተ። ታጋዩና ሙሴ ውህደት ፈጠሩ፣ ወደዱትም። በዲማ ኮንፈረንስ ለአመራር ብቁ ነው ብሎ ታጋዩ ወደ ተሓህት መሪነት አደረሰው። ም/ወታደራዊ አዛዥም ሆነ። ይህ በወቅቱ ለነበረው ታጋይ ታላቅ ድል ነበር።
ሙሴ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጸረ-ሻእቢያ አቋም ያዘ። ሻእቢያ ጸረ-ሕዝብ፣ በተለይ ደግሞ ጸረ-ትግራይ ሕዝብ ነው። ሻእቢያ የኔ ጠላት የትግራይ ሕዝብ ነው የሚል አክራሪ ድርጅት ነው፤ የተሓህት አመራር ደግሞ ሻእቢያን እንደፈጣሪ እየቆጠሩ ጠዋት ማታ እግሩን ይስማሉ በማለት በተጠናከረ መልኩ ጸረ-ሻእቢያ ቅስቀሳውን በማቀነባበር በስፋት ቀጠለበት፣ ታጋዩም አብሮት ቆመ።
አመራሩም ሙሴ ከመትክል የትግላችን አጋር ሻእቢያ እየለያየን ነው በማለት ሲናገሩ፣ በእንጻሩ ሙሴ ነፃ ሁኑ፣ አሽከር አትሁኑ፣ የሻእቢያ አገልጋይና ታዛዥ አትሁኑ ነው የምላችሁ ሲላቸው የተሓህት አመራር ሙሴን ማውገዙን ቢቀጥሉበተም በታጋዩ ተቀባይነት አላገኘም። ይበልጡኑ የሙሴ ተቀባይነት ከፍ አለ። በዚህ ምክንያት አመራሩ ሙሴ መሃሪ ተክሌ የሚጠፋበትን መንገድ ማጠንጠን ጀመሩ። የግድያ ሴል በስብሃት ነጋ የሚመራው የመለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየና ሥዩም መስፍን በመተባባር እቅዱን አወጡ። ተግባር ላይ የሚያውሉት ደግሞ ስየ አብርሃና ጻድቃን ገብረተንሳይ ሲሆኑ ግድያውን የሚፈጸመው በርሄ ሃጎስ ሆኖ ተመረጠ። በርሄ ሃጎስ አሁን ካናዳ፣ ኦቶዋ በመኖር ላይ ያለ ግለሰብ ነው። በላፈው ግንቦት 2005 አማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው እያለ አማራውን ኢትዮጵያዊ ሲሰድበውና ሲያንቋሽሸው የነበረ ሰው ነው። በገዘ ተጋሩ ፓል ቶክ።
ስየ አብርሃ በሚመራት ሃይል 41 አመቺ ጊዜ ሲጠብቅበት የነበረው ሙሴ ጻድቃን ገብረተንሳይ በኮሚሳርነት የሚመራት ጋንታ በርሄ ሃጎስ የነበረባት ጋንታ በመጠባበቅ ላይ የነበሩት ሁለቱ በአጋጣሚ ሓምሌ መጨረሻ 1968 ከሽራሮ ወጣ ብላ የምትገኘው ቁሽት ጫአ መስከበት ስየ አብርሃ ም/ሃይል መሪ በያዛት ሃይል በኢዲዩ ላይ ጥቃት እንደተጀመረ፣ ሙሴ ታጋዮቹን እያስተባበረ ጦርነቱን በመምራት ላይ እንዳለ በስተኋላው የነበሩት ጻድቃን ገ/ተንሳይና በርሄ ሃጎስ ውጊያው እየበረታ ሲሄድ በርሄ ሃጎስ አነጣጥሮ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌን ግራ እጁ ላይ ትከሻውን ጨምሮ ቆርጦ ጣለው። ዞር ሲል ጻድቃን ገ/ተንሳይና በርሄ ሃጎስ ከኋላ ሆነው እንደመቱት አወቀ። አይን ለአይንም ተገጣጠሙ። በርሄ ሃጎስ ሙሴን የመታበትን ደምመላሽ ጠመንጃም ለጻድቃን ሲሰጠው አየው። ክፉኛ የቆሰልውን ሙሴን በቃሬዛ ተሸክመውት ሲሄዱ የነበሩትን ታጋዮች ሁሉ የነገራቸው እኔ በኢዲዩ ጥይት አልተመታሁም፤ የመቱኝና የገደሉኝ ጻድቃን ገብረተንሳይና በርሄ ሃጎስ ናቸው እያለ ሲናገር እንደነበረና አንድ ሰዓት ተኩል ያህል ቆይቶ ከዚች ዓለም እንደተሰናበተ ይናገራሉ። አዲ ፀጸር ቀሽት ወስጥ ተቀበረ። ወዲያው በርሄ ሃጎስ ትንሽ ገንዘብ ተቀብሎ ሱዳን ገባ። ሙሴ  የተናገረውን ኑዛዜ አውአሎም ወልዱ ሰምቶታል፣ ምስክርነቱን ይስጥበት።
4.  አጽብሃ ዳኘው
አጽብሃ ዳኘው፣ የበረሃ ስሙ ሸዊት ነው። በቀ. ኃ. ሼ. ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ትምህርት የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበር። ማገብት እንደተመሰረተም ከወራት በኋላ አባል ሆነ። መጋቢት 1967 ከተሓህት ጋረ ተቀላቀለ።  ከጊዜ በኋላም በተሓህትን ፕሮግራም አደገኛነት ሂስ መሰንዘር በመጀመር ፕሮግራሙ ጸረ-ሃገር ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብና በታኝ፣ ሕዝብን እርስ በርሱ ለግጭት የሚዳርግ በመሆኑ አዲስ ፕሮግራም ማርቀቅ ይጠበቅብናል በማለት ከነ ገሰሰው አየለ – አግአዚ ገሰሰ ጋር በአቋም ተስማሙ። በሚሰነዝረው ሃሳብ በታጋዩ ተወዳጅ ሆነ፣ በድፍረቱም ምክንያት ስሙ ገነነ። በዚህ መልክ ሲቀጥል፣ ሱዳን፣ ካርቱም ለሼል ሂዶ በነበረበት ወቅት መለሾ ዜናዊና ስብሃት ነጋ በአስቸኳይ አስጠርተው ሱዳን ባለህበት ጊዜ ጾታዊ ግንኙነት ፈጽመሃል በማለት በውሸት ከሰው 06-ሃለዋ ወያነ አስገብተው አሰሩት። አረጋዊ በርሄ ይህን እንደሰማ ከነበረበት ቦታ በቶሎ ደርሶ ከእሰር አስወጥቶ ሥራውን እንዲቀጥል አደረገ። ሐምሌ 1968 አመራሩ ወደ አምስት ስለወረደ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ በተሓህት አመራር ስለተገደሉ፤ በአመራር ላይ የቀሩት አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃየ ብቻ ነበሩ። ከላይ በጠቀስኩት ወርና ዓ.ም. አምስቱ አመራር ተሰብስበው የሚከተሉት ወደ አመራሩ ገቡ። መለሾ ዜናዊ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ወደ ተሓህት አመራር ወጡ።
አጽብሃ ዳኘው ለስልጣን እና ሹመት እጁን አልሰጠም። የተሓህት ፕሮግራም ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ፣ አውዳሚና በታኝ ስለሆነ መወገድ አለበት፣ ተሓህት ጠባብና ዘረኛ ስለሆነ ትግላችን ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት። ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት፣ አማራ ጠላት ነው ማለት ሕገወጥ የፖለቲካ አቋም ነው በማለት ተከራከረ። ክርክሩን እገላ ወረዳ ስብኦ ቁሽት ሲከራከሩ ስብሃት፣ መለስና አባይ ተናደዱ። ሆያ አዲጨጓር የሚገኘው 06-ሃለዋ ወያነ ሃላፊዎች፣ ሙሉጌታ አለምሰገድና ክንፈ ገ/መድህንን አስጠርተው ዛሬውኑ አጽብሃ ዳኘውን እና ጓደኛው መኮንን በዛብህን ግደሏቸው። ስብሃት ነጋ ጸረ-ተሓህት ናቸው የሚል ወረቀት ጽፎና አዘጋጅቶ ሰጣቸው። እነአጽብሃ መኮንን የተሰጣቸውን ወረቀት ይዘው በመሄድ ሆያ ላይ ጉድጓድ ተቆፍሮ በጥይት ተደብድበው በመገደል ከዚህ ዓለም ተሰናበቱ።
አረጋዊ በርሄ የአጽብሃ ዳኘውና የመኮንን በዛብህን መታሰር ሰምቶ ከነበረበት ተምቤን አካባቢ ሌት ተቀን ተጉዞ ሕይወታቸውን ለማዳን ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። ሆያ እንደገባ እነ አጽብሃ ወደኔ አምጡልኝ፣ ተፈትተዋል፣ ጥፋት የለባቸውም ሲል ከሙሉጌታ አለምሰገድ ጋር ያገኘው መልስ፣ ስብሃትና መለሾ አባይ ሆያ እንደገቡ ሳይውሉ ሳያድሩ ይገደሉ ብለው ስላዘዙን ገደልናቸው አለው። የትእዛዝ ወረቀቱም የኸው ብሎ ሰጠው። አረጋዊ በርሄ ይህንን አሳዛኝ ግድያ ሰምቶ እነስብሃት ነጋ ወደሚገኙበት እገላ ሰብኦ፣ ቁሽት በመሄድ ተገናኛቸው። ነገር ግን ምንም አላደረገም። የተሓህት ሊቀመንበር እንደመሆኑ ለምን ይሆን በነስብሃት ነጋ፣ መለሰ ዜናዊ ወዘተ. ላይ እርምጃ ሳይወሰድ የቀረው የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር። አሁንም እየተነሳ ነው። መልስ መስጠት ያለበትም የወቅቱ የተሓህት ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ ነው።
 5.  ዶ/ር አታክልት ቀጸላ
ዶ/ር ራስወርቅ ቀፀላ የበርሃ ስሙ ዶ/ር አታክልት ቀፀላ የህክምና ባለሙያ ነው። ቀደም ሲል ከግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሓት) አባል ሆኖ በረሃ ሲንቀሳቀስ የግገሓት የትግል ስልት አደገኛ ነው በማለት በሰኔ 1967 ከተሓህት ተቀላቀለ። በተሓህትም ብዙ ስህተቶች እንደሚኖር አልተጠራጠርም ነበር። ነገር ግን ስህተቱን ለማስተካከልና ለማረም ብዙ ታጋዮች ይኖራሉ የሚለው እምነቱን እንደያዘ ቀስ በቀስ ፕሮግራሙን የማየት እድል ገጠመው። ከነገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪና አጽብሃ ዳኘው ጋር ጥሩ ግንኙነት ስለፈጠረ፣ እነዚህ ሁሉ የተሓህት ፕሮግራምን የሚቃወሙ ናቸው። አጽብሃ ዳኛው በነስብሃትና መለሾ እንደተገደለም ዶ/ር አታክለት ቀጸላ በአጽብሃ ፈንታ የተሓህት አመራሩን ጨበጠ። ግን እጁን አልሰጠም።
ዶ/ር አታክለት በፕሮግራሙ መጥፎና አደገኛ፣ ሃገርንና ሕዝብን የሚበታተን ነው ብሎ በማመን ከተለያዩ አመራር ጋር ሲነጋገርበት እንደነበር ይታወቃል። ከግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ መግባባት እንደነበረውም ልሹ የተናገረው ነው።
ከመለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና ከሌሎቹ አመራር ጋር ግን የሻከረ ግንኙነት እንደነበረው ታጋዩ ሁሉ ያውቃል። ሌላው ቀርቶ ስብሃት ነጋ በየቦታው በሄደበት “የኢትዮጵያ ባንዲራ ልሹ ላይ ጠምጥሞ ዶ/ር አታክለት ቀጸላ በድርጅታችን ተሓህት ችግር እየፈጠረብን ነው” በማለት በየቦታው መናገሩን እኔ ልሴ አስታውሳለሁ። ዶ/ር አታክልት ቀጸላ በ1ኛው ጉባኤ የተሓህት የአመራር ምርጫ በከፍተኛ የድምጽ ቁጥር ተመርጦ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ም/ወታደራዊ አዛዥ ሆነ። የነስብሃት ነጋ የስም ማጥፋት ዘመቻ አልተሳካም። በነገሩም ተደናግጠው ነበር።
ይህ በየካቲት 5 ቀን 1971 በአዲነብር ኡድ ወረዳ ማይ አባይ በተባለው ቦታ የተካሄደው 1ኛ ጉባኤ፣ የተሓህት ውርስ ስብሃት ነጋ ሊቀመንበር የሆነበት ጉባኤ ወርሱን የተረከቡት ስብሃት ነጋና ህወሓት ናቸው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቀደም ብሎ የመጣው ፋሽስት ቡድን እውቅና ያገኘበት ጊዜ ነበር።
እነስብሃት ነጋ ዶ/ር አታክልትን ለማጥፋት ብዙ ጥናት በማካሄድ የተመቸ ጊዜ አገኙ። ግንቦት 1971 የውጊያው ዓይነት ጥቃት በኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የውጊያው ቦታ ተምቤን፣ አብይ አዲ ጎንባስ ሞሞና ነበር። የህወሓት ሰራዊትም ይዘጋጅበት ነበር። ቀኑ ደርሶ ሁሉም የህወሓት ሰራዊት ወደ ውጊያው ቀጠና አመራ። ውጊያው የሚጀምርበት ጠዋት በስተምእራብ በኩል ከውጊያው ቦታ በግምት በ10 ኪ.ሜ. ርቀት ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና ሳሞራ የኑስ፣ የታጠቀው መሳሪያ ሲሞኖቭ ባለመነጽር ሆነው ዶ/ር አታክልት ቀጸላን የህወሓት ሊቀመንበር ስብሃት ነጋ ስለጦርነቱ ለመነጋገር ብሎ አስጠራው። እነሱም ለግድያው በመዘጋጀት በጠሩት መሰረት ደረሰ። ፊታቸውን ወደ ውጊያው ቀጠና ምስራቅ በማዞር ቀስ እያሉ መንገዱን ቀጠሉ። እኔና ዶ/ር አባዲ መስፍን ከነስብሃት ነጋ ፊት 500 ሜትር ያህል በሚገመት ርቀት ወደ ጦርነቱ ቀጠና እንጓዝ ነበር። ዶ/ር አታክለት ቀጸላ ስብሃት ነጋ እንዳሰናበተው በፍጥነት እየተጓዘ ሳለ ከ250-300 ሜትር ርቀት ከነሱ መካከል ሳሞራ የኑስ በያዘው ሲሞኖቭ ባለመነጽር ጠመንጃ አስተካክሎና አነጣጥሮ በመተኮስ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጀርባው አከርካሬ ላይ መታው። ‘Special Column’ ተመትቶ ሲወድቅ አዩት። አባይ ፀሃየ በፍጥነት ሩጦ ወደኛ ተጠግቶ አባዲ፣ አባዲ፣ ብሎ በመጥራት በእጅ ምልክት ኑ ሲለን ሄደን አገኘነው። ዶ/ር አታክልት ስለሞተ ቅበሩት፣ ነገር ግን ለማንም እንዳትናገሩ ብሎ ተመልሶ ከነስብሃት ነጋ ጋር ተቀላቀለ። በኋላም ሶስቱም ተያይዘው ሲሄዱ አየናቸው።
ዶ/ር አባዲ መስፍን እና እኔ ጉድጓድ ስንቆፍር እሱ እንደ ባለሙያነቱ ሬሳውን መመርመር ጀምረ። ጀርባው ላይ የመታችን ጥይት ሰውነቱን ከፍቶ አወጣት። በሲሞኖቭ ጥይት ሳሞራ የኑስ ገደለው ብሎ እምባውን መግታት አቃተው። ጥይቷን በወርቀት ጠቅልሎ ያዛት። እኔና ዶ/ር አታክልት አፈርና ድንጋይ በመጫን ቀብረን ተሰናብተን ወደ ጦርነቱ ተመለስን። ዶ/ር አታክልት ሞቶ ይቀበር እንጂ ታሪኩ ህያው ህኖ ይኖራል። እነ ስብሃት ነጋ መለሾ ዜናዊ ወዘተ. በንጹሃን ደም መታጠብ የጀመሩት ገና ከጥዋቱ ነበር። እነዚህ ጀግኖች በሞት ቢለዩንም ድምጻቸውና የተቀደሰ ተቃውማቸው፣ የህወሓት ፕሮግራም ይውደም ያሉት ድምጻቸው ግን በታጋዩ ዘንድ ተሰራጨ። በዚህም ምክንያት ብዙ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን በማንሳት የተሓህት- ህወሓት አመራርን አስጨነቁት። አመራሩ ተቃውሞውን አጠፍ በማድረግ በድርጅታችን ሕንፍሽፍሽ ተነሳ ብሎ ብዙ ታጋዮችን እና ንጹሃንን መጨፍጨፊያ ምክንያት አደረገው። የዲሞክራሲ ጥያቄው ተዋንያኖች፤ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ፣ አጽብሃ ዳኘውና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ያቀጣጠሉት ነው። የህወሓት ፋሽስትና አምባገነን መሪዎች የመጥፊያቸው ጊዜ እየቀረበ ነው፣ ተያይዘው በሕዝብ ሃይል ለፍርድ ይቀርባሉ።
 6. ግደይ ዘርአጽዮን
ግደይ ዘርአጽዮን ከአረጋዊ በርሄ ጋር በመሆን የማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡ ህወሓትን የፈጠሩት ሁለቱ ናቸው። ሌላ የለም። ግደይ የተፈጸሙ ጥፋትም ሆነ ወንጀል ካሉ ከነበሩት አመራር እኩል ተጠያቂ ነኝ በማለት በግልጽ ተናግሯል። በህወሓት አመራር አስከቆየሁበት በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ነኝ። ነጻ ነኝ ብሎ ራሱን ያላገለለ በመሆኑ ያስመሰግነዋል።
ግደይ ዘርአጽዮን የተሓህት-ሀወሓት ከፍተኛ አመራር የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር በነበረበት ጊዜ አመራሩ የሚፈጽመውን ግድያና ሽብር አውግዞ ከ1969 መጨራሻ ልሹ ነፃ በመሆን የስንት ታጋይና ሰላማዊ ዜጋ ሕይወት ያዳነ ነው። ግን ብቻውን በመሆኑ የህወሓትን አመራር ክሚፈጽሙት ወንጀል ሊያቆማቸው አልቻለም። በሰላማዊው ዜጋና በታጋዩ ግን ሰፊ የታማኝነት፣ አጋርነትና ክብር የተሰጠው ግደይ ዘርአይጽዮን ነው። ግደይ የታጋዩ ጥብቅ ጓደኛ ሆነ፣ ተወደደ። ማንኛውም ታጋይ ችግር ሲገጥመው ለግደይ ያናገራል። ግደይም ችግሩን ይፈታለታል። ግደይ ራሱም የታጋዩን እና የሕዝቡን ፍቅር ጣእሙን ስላወቀው ሁልጊዜም ደስተኛ ነበር።
መለሾ ዜናዊ የሚመራውን ማርክሲስት ሌሊኒስት ሊግ ትግራይ ለማቋቋም የሃላፊነቱ ተሰጠው። በ1ኛው ጉባኤ በኮሚሽን ደረጃ እንደተቋቋመ በአቋም ልዩነታቸው እነ መለሾ ዜናዊ፣ ግደይን እንደጠላት ማየት፣ ግደይ ዘርአጽዮንም በአቋሙ ስለጸና መፋጠጥ የጀመርንበት ጊዜ ነበር። የነበራቸው ልዩነትም የማይፈታ ሆነ። ሁለቱም በተጻራሪ መንገድ ቀጠሉበት።
በእነ መለሾ ዜናዊና አበሮቹ የሚያቀርቡት፤     
ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮት የአብዮቱ መሰረታዊ ሃይሎች ድሃ ገበሬ፤ ላብ አደሩ ሲሆኑ፣ እነዚህን ካሰባሰብን የአብዮቱ ትግል ዓላማው እና ግቡን ይመታል። ሃብታም ገበሬ ከሁለት ጥንድ በሬዎች በላይ ያሉት ሃብታም ገበሬ ስለሆነ በማርክስ ሌኒናዊ ሳይንስ ሃብታም ገበሬ የትግላችን ጠላት ነው፣ በማለት አስረግጠው ተናግረዋል። ሃብታም ገበሬ መደምሰስ መጥፋት አለበት። ለምን የማርክስ ሌኒናዊ ጠላት ሃብታም ገበሬ ነው። መለሾ ዜናዊ ይህንን በወይን መጽሔት እያተመ ታጋዩን ያስተምርበት ነበር።
ግደይ ዘርአጽዮን
ሃብታም ገበሬ የማርክሲዝም ሌኒኒዝም ጠላት አይደለም። አሁንም በህወሓት የሚመሰረተው ማርክሲስት ፓርቲ ሃብታም ገበሬ ጠላት ሳይሆን የትግል አጋራችን እና ወዳጃችን ነው ተብሎ በትግሉ እንደ ወዳጅ መታወቅ አለበት። ከሁለት ጥንድ በሬ በላይ ያለው ሃብታም ገበሬ ነው ስለሆነም ጠላት ነው እያላችሁ ምክንያት በመፍጠር ያምታጠቁት የትግራይ ሕብረተሰብ ፍጹም ጸረ-ሕዝብ ነው። ንብረቱ ሁሉ እየተወረሰ ለህወሓት ገቢ ሲደረግ ለተገደለው ሕዝብና ለፈረሰው ቤት ተጠያቂ ናቸው። ይህ የሃሳብ ልዩነት በነመለስ ዜናዊ ቡድን እና በግደይ ዘርአጽዮን መካክል ሰፍቶ በመውጣት ለዓመታት ቀጠለ።
መለስ ዜናዊ
በእኛና በግደይ ዘርአጽዮን መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። አብረን መታገልም አንችልም። ግደይ ዘርአጽዮን ሃብታም ገበሬ የማርክስ ሌኒናዊ የትግል አጋር ነው፣ ጠላት አይደለም ብሎ ያምናል። ይህ የሚያመለክተው ግደይ ዘርአጽዮን ጸረ-ማርክስ-ሌሊናዊና በራዥ ነው ሲል በያዘው አቋም የማይነቃነቀው ግደይ፣ አንተና ጓደኞችህ ናችሁ በራዥና ከላሽ ነህ ስለአለው ንትርኩ ሰማይ ወጣ። ግደይ ዘርአጽዮን አሁንም በዚህ ጉባኤ አቀርበዋለሁ። ሃብታም ገበሬ የትግላችን አጋርና ወዳጅ መሆኑ ሙሉ እምነቴ ነው። ሃብታም ገበሬ ጠላት ነው ብሎ ማስቀመጥ ጸረ-ሕዝብ ነው። እነ መለሾ ዜናዊ ሃብታም ገበሬ ጠላት ነው ማለታቸው ማንነታቸውን በትክክል ይገልጸዋል።
 2.  በማለሊት ጉባኤ አመራሩ ዳግም ለሁለት መሰንጠቅ
የማለሊት ጉባኤ በዚህና በሌላውም ጸረ-ዲሞክራሲ ሲካሄድ ሰንብቶ ሐምሌ 21 ቀን 1977 ምርጫው ደረሰ። ይህ ምርጫ ሕገወጥነትን የተከተለና ሁለት ዋና ዋና ዓላማ የያዘ ነበር።
  1. የሥልጣን ሽኩቻ ዋና ዓላማው ነበር፣
  2. በዚህ የሥልጣን ሽኩቻ ማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠው በጸረ-ዲሞክራሲና በጸረ-ሕዝብነቱ አብረው እየመሩት የመጡት አንጋፋ አመራሮች ለማባረር በድርቅ የተጠቃው መከረኛው የትግራይ ሕዝብ እያለቀ ከአፉ ነጥቀው በነስብሃት ነጋ፣ በስንት ሚሊዮን ብር የተዘጋጀው ማለሊት ስልጣናቸውን ለማደላደል ነበር።
ምርጫው
በሙሉ ድምጽ የመራጭ ብዛት 250 ነበር። ምርጫው በምስጢር ሆኖ በወረቀት የምትፈልገውን መምረጥም ነበር። ምርጫው ተካሄደ። ድምጹ ተቆጠረ። በዝርዝር ተነገረ። 1ኛ. ግደይ ዘርአጽዮን፣ ያገኘው ድምጽ 247፤ 2ኛ. አረጋዊ በርሄ፣ ያገኘ ድምጽ 245፤ 3ኛ. ሃየሎም አርአያ፣ ያገኘው ድምጽ፣ 236፤ 4ኛ. ስየ አብርሃ ወዘተ. እያለ የድምጽ ቆጠራው ቀጠለ። ወደ መጨረሻው ድምጽ ቆጠራ ደረሰ። ይህንን የሚገልጸው ህብሩ ገብረኪዳን ነበር። በጥቁር ሰሌዳ ላይ የተመረጡት ያገኙትን ድምጽ እየጻፈ ሲገልጽ የሚይዘው የሚጨብጠውን አጣ። የጉባኤው ተሳታፊ ቀጥል ብሎ አፋጠጠው። ላብ ፊቱ ላይ እየወረደ ቀጠለ። 24ኛ. መለሾ ዜናዊ፣ ያገኘው ድምጽ 130፤ 25ኛ. ስብሃት ነጋ፣ ያገኘው ድምጽ 127 በማለት የ25ቱን የማለሊት ተመራጮች የማለሊት ማ/ኮሚቴ ብሎ በጥቁር ሰሌዳው ላይ በማስቀመጥ ተመልሶ ወደ ቦታው ሄዶ ተቀመጠ። መለሾ ዜናዊ ራሱን ደፋ። ፊቱ የተጠበሰ ስጋ መሰለ። ስብሃት ነጋ ደግሞ አዳራሹን ለቆ ወጣ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የጉባኤው ሊቀመንበር የነበረው ሥዩም መስፍን ከሰዓት በኋላ በ11 ሰዓት እዚህ እንገናኝ ብሎ ጉባኤተኛውን አሰናበተ። በዚህ ዓይነት ነበር ታጋዩ እነ መለሾ ዜናዊን መሬት ውስጥ የቀበራቸው። ነገር ግን ተመልሰው ታጋዩን አጠቁት። ብዙ ነባር ታጋይ በእነ መለሾ፣ ስብሃት ወዘተ. ተገደለ፣ ከሞት የተረፈውም ሸሸ።
ልክ በ11 ሰዓት ጉባኤው ተሰየመ። በስብሃት ነጋ አመራር የተመረጡት ማ/ኮሚቴ ማለሊት አሰባስቦ ሹመትና ሥልጣን እየሰጠ እንዲተባበሩት አደረገ። ከአረጋዊ በርሄ ስልጣን አገኛለሁ ብሎ ስየ አብርሃ በከፍተኛ ድምጽ የመረጥነው በግንባር ቀደምትምነት ክህደት ከነ ስብሃት ጋር ተሰለፈ። በዚሁ ጉባኤ የመጀመሪያው ተናጋሪ መለሾ ዜናዊ፤ ቀጥሎ ስብሃት ነጋ፤ ቀጥሎ ስየ አብርሃ በመተባበር ግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ ከህወሓት ከማለሊት ተባረዋል ተባለ። ታጋዩ ተደናገጠ፣ አጉረመረመ አለቀሰ። ከአመራሩ ጻድቃን፣ ሥዩም ገብሩ፣ ወዘተ. በየተራ በሁለት አንጋፋ አመራር አሰነዋሪ የሆነ ስድብ አወረዱባቸው። የተባረሩትም ክኛ ጋር ተቀላቀሉ። እነ መለሾ ዜናዊ ተደላድለው በህወሓት-ማለሊት ኮርቻ ላይ ተቀመጡ። የህወሓት ሁለተኛ መሰንጠቅ ይህ ነው።
የስየ አብርሃ ክህደት
ስየ አብርሃ ደፋርና ጎበዝ እንደነበረ አውቃለሁ። ከሃዲነቱን ግን አላውቅም ነበር። በ1969 የሕንፍሽፍሽ ዋና ተዋናይ ነበር ተብሎ በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን እስከ 1977 ድረስ በዓይነ ቁራኛ ሲከታተሉት እንደነበር አውቃለሁ። ከህወሓት ታጋዮች ደግሞ ለሰየ አብርሃ ጥብቅና እና ድጋፍ አልተለየውም ነበር። ከዚህም የተነሳ ነው በማለሊት ጉባኤ በከፍተኛ ድምጽ የመረጥነው። ነገር ግን ከሃዲውና እምነተ ቢሱ ስየ አብርሃ የሥልጣን ጥማቱን ለማርካት የህወሓት-ማለሊት ሙሉ ወታደራዊ አዛዥ ለመሆን ግደይ ዘርአጽዮንን እና አረጋዊ በርሄን በውሸትና በስም ማጥፋት ደበደባቸው። ሲጠብቀውና ሲንከባከበው የቆየውን ታጋይ ለምን መለሾ ዜናዊን እና ስብሃት ነጋን በአነስተኛ ደምጽ መረጣችሁ ብሎ ነባሩን ታጋይ እንደ እባብ እራስ እራሱን ቀጠቀጠው። በየቦታው እየሄደ አጠፋው።seye
በህዳር 1980 የህወሓት ታጋይ ባነሳው ተቃውሞ ኤርትራም ሆነ ሌላ ቦታ ሂደን አንዋጋም። ትግራይን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነፃ አውጥተን የትግራይን መንግሥት መመስረት ነው እንጂ ከዚህ ውጭ የምናውቀው ነገር የለም። ኤርትራ ሄደው በረሃ የበላቸውና ያለቁት የትግራይ ወጣት ሴትና ወንድ እስከ አሁን 130,000 ደርሷል። የኛ ድርጅት ህወሓት ከየት ወረዳና ዞን መጡ የሚል ዝርዝር ስማቸው እንኳን አያውቀውም። እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ከብት እየታፈስን ሂደን ሞተን ቀረን። አሁንም ትግራይን ነፃ እናወጣለን እንጂ ሌላ ቦታ አንሄድም አለ። በዚህ ጊዜ እነ መለሾ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ስየ አብርሃን አነጋግረው በ36,000 ታጋይ ላይ ሞት ፈረዱበት። ይህ ሁሉ ታጋይ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። በዚህ ግድያ የተሰማሩት መለሾ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሃየሎም አርአያ፣ ሳሞራ የኑስ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተክለሃይማኖት፣ ስየ አብርሃ፣ ክንፈ ገብረመድህን፣ አርከበ እቁባይ፣ ገብሩ አስራት፣ ዓረጋሽ አዳነ፣ አውአሎም ወልዱ ወዘተ. ነበሩ።
የተግባሩ አፈጻጸም በስየ አብርሃና በክንፈ ገ/መድህን ትእዛዝና አመራር ነበር። ገዳዮቹ፣ ብስራት አማረ፣ ሃሰን ሽፋ፣ ወልደሥላሴ፣ ዘአማኑኤል ለገሰ (ወዲ ሻምበል)፣ ተስፋዬ ጡሩራ (መርሳ)፣ ተስፋዬ አፈርሰው (አጽብሃ) ወዘተ. ነበሩ። ከ200 በላይ የሃለዋ ወያነ (06) ታጋዮችን በማሰለፍ ታጋዩን ገደሉት። የሃውዜን ጥቃትም በደርግ ሚግ 21-23-27 በእጅ አዙር ያስደበድቡት እነ ስብሃት ነጋ፣ መለሾ ዜናዊ ወዘተ. ከዚህ ተነስተው ነው።
ስየ አብርሃ ይህንን ክህደትና አረመኔያዊ ተግባር ከመፈጸሙ ትንሽ ቀደም ብሎ ከነመለስ፣ ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጋር ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ተጧጡፎ ቀጠለ። ስየ አብርሃ ሁሉንም ያጣ ብቻውን ሆኖ እየተናገረ መሄድ ጀመረ። ታጋዩ ሁሉ ጠላው፣ ራቀው። የፖሊት ቢሮ አባላት በየወሩ በስብሃት ነጋ የተፈቀደውን የኪስ ገንዘብ ብር 1,000 አልቀበልም አለ። ተወልደ፣ ገብሩ አስራትም እንደዚሁ አንቀበልም ብለዋል። ስየ አብርሃ በፈጸመው ክህደት እስከ ዛሬ በህወሓት ታጋይ እየተወገዘ ነው።
3.  የህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ወቅቱ ጥቅምት 1980 ነበር። የህወሓት ማ/ኮሚቴን ጨምሮ የማለሊት ማ/ኮሚቴ በአንድነት የተጠራ ስብሰባ ነበር። በዚህ ጊዜ የተነሱት ጥያቄዎች የስልጣን ሽኩቻ ሳይሆን የህወሓት-ማለሊት ፖሊት ቢሮ ዱሮ ከነበረውና ከተፈጸሙት ስህተቶች ያልተማረ፣ ብዙ ስህተት እየፈጸመ ነው። ከዚህ ስህተቱ መማር አለበት ወዘተ. በማለት የቀረበው ጥያቄ አነታራኪ ሆኖ በመቀመጡ፣ ስብሃት ነጋ በሚመራው ስብሰባ የቀረቡትን ጥያቄዎች በሙሉ ውድቅ አደረጋቸው። መለሾ ዜናዊም የስብሃት ነጋን ሃሳብ ደገፈ። ጥያቄቆቹን ያነሱት በ1975 በ2ኛው ጉባኤ የተመረጡት የህወሓት አመራር ናቸው። እነሱም፤
  1. ክብሮም ገ/ማርያም የህወሓት ማ/ኮሚቴና የሰራዊቱ የሎጂስቲክ ዋና ሃላፊ የነበረ፣
  2. ኃ/ሥላሴ መስፍን፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴ፣ ጠቅላላ የህወሓት ክፍለ ጦሮች የኮሚሳሮች የበላይ ሃላፊና ተቆጣጣሪ የነበረ፣
  3. ሰአረ ገብረጻድቅ፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ጠቅላላ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ፖሊት ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረ፣
  4. ተክሉ ሃዋዝ፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴና የቀድሞ የድርጅቱ ዋና የደህንነት ሃላፊ የነበረ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱት አራቱ አመራር ባቀረቡት ሃሳብ አፈንጋጩ የእነ ግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ ደጋፊዎች ተብለው ተወነጀሉ። ወንጃዮቹ፣ መለሾ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ገብሩ አስራት፣ አርከበ እቁባይ ናቸው፡ እነዚህ የፖሊት ቢሮ አባላት ተሰብሰበው ተወንጃዮቹን በማስጠራት እርማት እንዲያደርጉ ወሰኑ። በቀረቡበት ጊዜም፣ ያቀረባችሁት ሃሳብ ጸረ-ህወሓት-ማለሊት በመሆኑ፤ ከአመራርና ከሃላፊነታችሁ ተወግዳችሁ በተራ ታጋይነት ቀጥሉ ተብለው በስብሃት ነጋና መለሾ ዜናዊ ተሰናበቱ። ይህ ወቅት ህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ የተሰነጠቀበት ወቅት ነበር።
5.  የህወሓት ለአራተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ይህ የህዋሓት ለአራተኛ ጊዜ መሰንጠቅ በ1993 የተፈጠረው ነው። ዋናው ዓላማ የስልጣን ሽኩቻ ነበር። ሌላው አንዱ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ሆኖ ሌላው ደግሞ ጸረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተፈጠረ መበታተን አይደለም። በእነ ስየ አብርሃ የሚመራው ቡድንም ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያን ያፈረሱ፣ የቀይ ባህር የባህር በሯን የሸጡና ያስነጠቁ፣ የዘር ማጥፋት እልቂት የፈጸሙ፣ ሕዝብን ለድህነት፣ ለችግር፣ ለበሽታና ለስደት የዳረጉ እነ መለሾ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣ ተወልደ ወ/ማርያም፣ ገብሩ አስራት ወዘተ. ተባብረው በሕዝብና በሃገር ከባድ ወንጀል የፈጸሙ ናቸው። በሁለት የተሰነጠቁበት ቀንደኛ ምክንያት ደግሞ የስልጣን ሽኩቻ ነው። ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
6.  የህወሓት ለአምስተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ህወሓት ኢትዮጵያን ወሮ በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረ በኋላ መሪው መለሾ ዜናዊና የህወሓት አመራር ሁሉም በሃገራችን ከፍተኛውን የሥልጣን ወንበር ላይ ተደላድለው በመቀመጥ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት በገዙበት ጊዜ በሕዝብና በሃገር ከፍተኛ ወንጀል በመፈጸም የኢትዮጵያን ሃብት ዘርፈዋል። ሕዝብን ያደኸየውን ስርዓት የመሰረተው መለሾ ዜናዊ ሰኔ 7 ቀን 2004 ከዚህ ዓለም በሞት ተቀጠፈ። ብስራት አብሳሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታና መመኪያ እንዲሁም ዓይን እና ጆሮ ኢሳት በጥዋቱ የመለስ ዜናዊን ሞት ነገረን። ለወዳጆቹ ሃዘን ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የእፎይታ ቀን ሆነ። አረመኔው መሪ መለሾ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተቀጥፎ መኖሪያውን ሲኦል አደረገ። በዚህም ምክያት ህወሓት ለአምስተኛ ጊዜ ተሰነጠቀ። ከላይ እስከ ታች በቅራኔና በሥልጣን ሽኩቻ እንደ ዱባ ተፍረከረከ።
    1. የተህሓት ወግ አጥባቂ
ተረካቢ (Old guard)
    2. ተንኳሽ
(Catalyst)
    3. የመለስ ዜናዊ ውርስ
(Legacy)
ስብሃት ነጋደብረጽዮን ገ/ሚካኤልአባይ ወልዱ
ብርሃነ ገ/ክርስቶስጌታቸው አሰፋሳሞራ የኑስ
አርከበ እቁባይቴዎድሮስ አድሃኖምበየነ ምክሩ
ጸጋይ በርሄአለም ገ/ዋህድቴዎድሮስ ሃጎስ
አባዲ ዘሞክንደያ ገ/ሕይወት
ብርሃነ ማረት፤
ትርፉ ኪ/ማርያም
እነ ስብሃት ነጋ ያላቸው ደጋፊ ጥቂት ሲሆን፤ እነ አባይ ወልዱ የህወሓት ማ/ኮሚቴውን በብዛት ይዘዋል። እነ ደብረጽዮንም ከነአባይ ወልዱ ድጋፍ አላቸው። አንድ ተረት አለ፣ ‘ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ’ እንደሚባለው ነው። የህወሓት መንጋ ከአመራሩ ጀምሮ እስከ ተራ አባላቱ በወንጀልና በሰው ልጅ ደም የታጠበ ነው። በዚህ ዓይነት በሳሞራ የኑስ የሚመራው ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ደህንነቱ፣ የፌደራሉ ሁሉ ወንጀለኞችና ጸረ-ሕዝብ ናቸው። መለሾ ዜናዊ በሕይወት በነበረበት ጊዜ በ1993 የተነሳው የስልጣን ሽኩቻ በሁለት ሲሰነጥቀው፤ አሁንም ተመሳሳይ ዓይነት እጣ የደረሰው ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ነው፤፡ ህወሓትን በሶስት የከፈለው ዋናው የሥስልጣን ሽኩቻ ብቻ ሳይሆን ኢፈርትን ማን ይምራ፣ ማንስ ይቆጣጠር የሚለው ነበር። በ’ለ’ ሾር የተዘረዘሩት የኢፈርት ዋናው የዝርፊያ መሳሪያ ስለሆነ በኛ ይመራ ባዮች ናቸው። በ’ሀ’ ምደብ ሾር ያሉት እነ ስብሃት ነጋ ከላይ እሰክ ታች ኢፈርትን መቆጣጠርና መምራት ያለብን እኛ ነን ብለው ቁመዋል። በተጨማሪም፣ ከሥልጣኑም የሚንስትርነት ቦታ ለኛም ይገባናል ባዮች ናቸው። በተለይ አዜብ መስፍን በሕገወጥ መንገድ ከስብሃት ነጋ የወሰደችው የኢፈርት መሪነት ለኛ tedrosይመለስልን ሲሉ በ’ለ’ እና በ’ሐ’ የተሰለፉት አልተቀበሉትም። አዜብ መስፍንን ከኢፈርት አስወግደን በሌላ ሰው እንተካታለን በማለት ተስማምተው ብርሃነ ኪዳነማርያምን በቦታዋ በዳይሬክተርነት አስቀመጡት። እነ ስብሃት ነጋ ግን ይህንን አልተቀበሉትም። የኢፈርት የበላይ ሃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ነው። እነ ስብሃት ነጋ በዚህ ግራ ተጋብተዋል።
በ’ለ’ ምደብ ያሉትን እነ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ትልቁ ጥረታቸው በአባይ ወልዱ የሚመራው በ’ሐ’ ምድብ ሾር ያሉት በ’ሀ’ እና በ’ሐ’ ምድብ ያሉት እንዳይስማሙና በመካከላቸው ሆነው ነገር በመተንኮስ ቅራኔ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋሉ። አዜብ መስፍንን ካነሳን ዘንድ፤ አንበሳ ባንክን ወዘተ. ተቆጣጠሩ ተብሎ ለነስብሃት ነጋ የተሰጠ ገጸ በረከት ነው። የኤርትራው ተወላጅ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ‘ኢትዮ ቴሌኮምን’ የግል ሃብቱ በማድረግ የሃገርና የሕዝብ ሃብት እየበዘበዘ ገንዘቡን በቻይና ባንክ በማስቀመጥ ኢትዮጵያን እያደማ ይገኛል። በ2007 ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ፍላጎትም አለው።
ኤርትራዊው ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የሃገር ሃብት እየዘረፈ በማሌዢያና በተለያዩ ሃገራት ባንኮች ሃብቱን እያደለበ የሚገኝ የህወሓት መሪ ነው። ኢፈርትንም መለሾ ዜናዊ ከሞተ በኋላ በሃላፊነት የተረከበ ሰው ነው። በ2007 ምርጫም በእነ ወልዱ ድጋፍ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ያገኘ ሰው ነው። እነ አባይ ወልዱ በትግራይ ውስጥ የሚገኙት የኢፈርት ፋብሪካዎች፣ እንደ አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ፣ መሶብ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ መስፍን ኢንጂነሪንግ ወዘተ. ወፍራሙን ድርሻ ያገኛሉ። በዚሁ መሰረት ኢፈርት ከተመሰረተ ከ1985 ጀምሮ ለመንግሥት ግብር አይከፍልም። ከብሄራዊ ባንክና ከንግድ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ አይመልስም፣ እንዲያስከፍለው የሚያስገድደው ሕግም የለም። የተለያዩ እቃዎች ሲያስገባና ሲያስወጣ ቀረጥ ለመንግሥት አይከፍልም። ምክንያቱም ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሾር የያዘው የህወሓት ባለሥልጣናት የግል ንብረታችው ስለሆነ በማንም ሕግ የማይገዛ ኢፈርት ነው።debretsion gebremichael
መለሾ ዜናዊ ከሞተ በኋላ በህወሓት ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሯል፣ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሃይላቸውም የተበታነ እርስ በርሳቸው አለመተማመን ነግሷል። ሁሉም የህወሓት አመራርና አባሎቹ ደጋፊዎቹ በሙስና የተጨማለቁ በዘር ማጥፋት ወንጀል በመሰማራት ከ8.9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የገደሉ ናቸው። ከ30 ሚሊዮን በላይም ኢትዮጵያዊ ከተወለደበት ከሚወዳት ሃገሩ ሠርቶ ከሚበላባት፣ ልጆቹን አስተምሮ፣ አሳድጎ ለቁም ነገር ካበቃበት መሬቱ በማፈናቀል ግማሹ ለስደት ግማሹ ለሞት፣ ግማሹ ለችግር፣ ለረሃብ፣ መኖሪያ አልባ አድርገውታል። ከዚህ በመነሳት ህወሓቶች በጽኑ አቋም የሚስማሙበት አጀንዳ አላቸው። ። ከህወሓት የተባባሩ አመራር የነበሩትም በዚህ በጸና አቋም ይስማማሉ።
  1. አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሕገመንግሥት የህወሓት ሕገመንግሥት ነው። ይህም ከ1967 እየታገልን ይዘነው የመጣን የሕይወታችን እና የንብረታችን መድን ነው። ይህ ሕገመንግሥት ከተናደ አሁን ያለነው የተባረሩት አመራርም ተለቅመን ታሰርን፣ ሃብታችን ተወረሶ እኛም እንገደላለን። ስለሆነም ያለውን ሕግመንግሥት መክላከል የግድ ይሆናል። ሁሉም በዚህ ይስማማሉ፣
  2. ኢፈርት የህወሓት ሃብት ነው። ኢፈርትም በኢትዮጵያ ያሉትን ገዢ ተቋማት በተዘዋዋሪና በቀጥታ የሚቆጣጠር ነው። ለምሳሌ፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንክ፣ መአድናት፣ ትራንስፖርት ወዘተ. የሃገሪቱ ንግድም ከትንሹ እስከ ትልቁ የሚቆጣጠር ነው። ይህ የደም ስራችን ከወደመ በሕዝብ ቁጥጥር ከዋለ ህወሓትና መሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ የህወሓት መንግሥታዊ ተቋማት ጭምር ይወድማሉ። ስለሆነም ባለን አቅማችን ኢፈርትን መከላከል በበለጠ ማሳደግ አለብን። በዚህም በማያወላውል መንገድ ይስማማሉ፣
  3. የሕዝብ የአመጽ ተቃውሞ ወይም አብዮት ከተነሳ ባለን መከላከያ ሰራዊት ደህንነት፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ልንመልሰው አንችልም። ሕዝቡ ከአሸነፈ የህወሓት አመራር አባሎችና ደጋፊዎቻችንን በእሳት እንደሚቀቅለን እናውቃለን። ለዚህ መድሃኒቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ በየጎሳ ከፋፍለን አሁን ባለው አይነት ደፍጥጠን ማጥቃት፣ ተቋዋሚ ድርጅቶችን ማዳከም፣ መግደል ማዋከብ አለብን። የአገዛዛችን መንገድ ሕዝቡን ማስጨነቅ፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ በስደት እንዲጓዙ ማድረግ እነዚህን በዋናነት እንደ መሳሪያ መጠቀም አለብን። ወጣቱን ዜጋ ደግሞ በሽርሙጥና፣ ሃሺሽ ወዘተ. በብዛት አስፋፍቶ ከጥቅም ውጭ ማድረግ። በጎሳ ከፋፍለንም ኢትዮጵያዊነት የሚል ሾር የሰደደውን እምነት ማጥፋት፣ የአማርኛ ቋንቋን ማጥፋት፣ በየትኛውም ጎሳ የሚገኘውን ሾር መሰረቱን ነቅለን እንዳልነበረ ማድረግ። በዚህም ሁሉም ይስማማሉ።
ኢትዮጵያን አሁን ማን እየመራት ነው?
መለሾ ዜናዊ ከሞተ በኋላ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር ተብሎ እንደተሰየመ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቀዋል። ነገር ግን ኃ/ማርያም የእውነት ሳይሆን የውሸት ጠ/ሚኒስቴር ነው። ኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ አሁንም መዋቅሩን የዘረጋው ህወሓት ነው። ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ኢትዮጵያን የሚመሩትና የሚያስተዳድሩት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ቴዎድሮስ አድሃኖምና ንዋይ ገብረአብ ናቸው። ስለዚህ ኢትዮጵያን ማን እየመራት ነው ለሚለው ጥያቄ በትክክል ከላይ የተጠቀሱት ሶስቱ የህወሓት አመራር ናቸው። የስርዓቱን መዋቅርም በነዚህ ግለሰቦች ይመራል። ኃ/ማርያም ደሳለኝ አድርግ ያሉትን የሚያደርግ ጉልቻና ቃል አቀባይ ነው።
በ1922 የተወለደው የ83 ዓመቱ ዘራፊና ገዳዩ ሽማግሌ ስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ለባለሥልጣናቱ እንቅፋት አይሆንባቸውም። መሪዎቹ የሚፈልጉት ዝርፊያ ብቻ ነው። እነ አባይ ወልዱ ከነ ደብረጽዮን ጋር ተስማምተው በትግራይ ሪፓብሊክ መንግሥት ውስጥ እጃችሁን አታስገቡ። ገንዘብ እንፈልጋለን፣ ከፍተኛ ባጀት መድቡልን፣ እኛም የእናንተ ደጋፊዎች ነን በማለት ተስማምተዋል።
hailemariam speakingለሚቀጥለው የ2007 ምርጫ ህወሓት በአሸናፊነት ወጥቶ ለጠ/ሚኒስቴር፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሆኑትን እጩዎቹን አዘጋጅቷል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናል ተብሎ የታጨው ቴዎድሮስ አድሃኖም ሲሆን፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊሆን የታሰበው ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ነው። “አባይ ማደርያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል” ማለት ይህ ነው። ህወሓት የተዳከመ፣ የበሰበሰ ግንድ ነው። በዚህ ደረጃ ላይ ያለ ፋሽስታዊ ድርጅት ኢትዮጵያን ረግጦ የመግዛት አቅም የለውም። በኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይል ክንድና አንድነት ይደመሰሳል። ይህንን ድክመታቸውን በመጠቀም ሃገር ቤትም በውጭ ሃገር የምንገኘውን ጨምሮ አንድነታችንን አጠናክረን በሕዝባዊ አመጽ ወያኔ ህወሓትን የመደምሰስ ጊዜው አሁን ነው።
የመለስ ዜናዊ ራእይ
በዚሁ ጥቂት ጥያቄዎችን በመለስ እደመድማለሁ። መለሾ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ማን ነው?
መለሾ ዜናዊ ለኢትዮጵያ የጠላት ጠላት ደመኛ ጠላት ነው። ከአባቱ፣ ከእናቱና ከአያቶቹ የወረሰው በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ የፈጸመው ግፍ፤ የሃገር ማፍረስ ድርጊት በታሪክ የማይረሳ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የህወሓት አመራርንም ይጨምራል። የስም ዝርዝራቸውን በተለያዩት ጽሁፎቼና ከዚህ በላይም ስላካተትኳቸው እንሱን መመልከትና ማመሳከር ይቻላል።
የመለስ ዜናዊ ራእይ በኢትዮጵያ ልማት፣ እድገት፣ ዲሞክራሲ ማለትስ ምን ማለት ነው? በእርሱ አመራር ለ21 ዓመታት ኢትዮጵያ በልማትና በዲሞክራሲ አብባለች የሚሉት የህወሓት ደጋፊዎችና አጋር ድርጅት ተብለው የሚጠሩት ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ኢትዮጵያ ስብስብ ብቻ ናቸው። ብዙ ለሆዳቸው ያደሩም አሉባቸው። ነገሩ የተጋላቢጦሽ ነው። መለሾ ዜናዊ የሚመራው ህወሓትና አመራሩ በተፈጥሮው ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ዲሞክራሲ ነው። ህወሓት አፈጣጠሩ አምባገነን እና ፋሽስት፣ እንዲሁም ጸረ-ዲሞክራሲ ሆኖ ያደገ ከመቅጽበት የልማት፣ እድገትና ዲሞክራሲ አራማጅ ሊሆን አይችልም። ጎባጣና ጠማማ ሆኖ ያደገ ባህር ዛፍ ተቃንቶ ለኤሌክትሪክ ምሰሶ ወይም ለቤት መስሪያ ማገር ልታደርገው አትችለም። በምሳር ቆራርጦ ማገዶ ከማድረግ ውጪ። ህወሓትን በዚህ አይነት ልንመለከተው ይገባል። ስለሆነም የመለስ ዜናዊ ራእይ ጸረ-ሕዝብ፣ ጸረ-ልማት፣ ጸረ-እድገት፣ ጸረ-ዲሞክራሲ ነው። መለስና ግብረአበሮቹ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማሩ፣ በሙስና የሕዝብና የሃገር ሃብት የዘረፉ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በፋሽስት መዋቅራቸው ያሰቃዩና የገደሉ ናቸው። እንደዚህ ያለ ጨቋኝና ፋሽስት መንግስት ልማታዊ ሊሆን አይችልም።
መለሾ ዜናዊና ህወሓት ለኢትዮጵያና ሕዝቧ ምን ናቸው? በመለስ ዜናዊና በስብሃት ነጋ የሚመራው ፋሽስት ፓርቲ፣ ኢትዮጵያን ከግንቦት ወር 1983 ጀምሮ ከተቆጣጠሩ ወዲህ ኢትዮጵያና ሕዝቧ በወያኔ ሀውሓት ቅኝ አገዛዝ የወደቀችበት ወቅት ሆኖ፣ እነሆ ቅኝ ገዢው ህወሓት በሃገራችን አረመኔያዊ ድርጊት እየፈጸመ ይገኛል። በመለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመን የኢትዮጵያ ሉአላዊንት ፈርሷል። ጥንታዊና ታሪካዊ የቀይ ባሕር ወደቦቿን አጥታለች። ሕዝብ በዘሩ እየታየ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል። ስለዚህ መለሾ ዜናዊና ህወሓት እንዲሁም አመራሩ የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላት ናቸው።
መለሾ ዜናዊ የወታደራዊ ሳይንስና ስትራተጂ ባለ ራእይ ይባላል። ይህ አነጋገር ደረቅ ውሸት ነው። መለሾ ዜናዊን የሚያውቁና አብረውት በትግሉ የነበሩ ታጋዮች የማይቀበሉት ጉዳይ ነው። የህወሓት መንጋ በምን ዓይነት የውሸት አዘቅት ውስጥ እንደሰመጠ በግልጽ የሚያሳይ ነው። መለሾ ዜናዊ ከትግሉ መጀመሪያ አንስቶ ለብዙ ዓመታት አብረን ተጉዘናል። በጣም የሚተማመንብን ጓደኞቹ ተክሉ ሃዋዝና እኔ ገ/መድህን አርአያ ነበርን። በሚገባ ስለምናውቀው የወታደራዊ ስታርቴጂስት አልነበረም። እውቀቱም ችሎታውም ፈጽሞ አልነበረውም። ሃቁ ይህ ነው።
“ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” እንዳለው ዓይነት ነው። መለሾ ዜናዊ ከፈሪነቱ የተነሳ በተለያዩ ጦርነቶች ፈርቶ የሸሸ፣ በህወሓት ታሪክ ውስጥ በፈሪነቱ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ግለሰብ ነው። ከሸሸባቸው ጦርነቶች ለአብነት፤
  1. በ1969 ከአድዋ ኦፐሬሽን ጦርነቱ እንደተጀመረ ፈርቶ የሸሸ፣
  2. በ1970 ከአዲ ደእሮ ፈርቶ የሸሸ፣
  3. በ1971 መጀመሪያ ላይ ከማይቅነጠል ውጊያ ፈርቶ የሸሸ፣
  4. በ1971 ህዳር ወር ከፈረስ ማይ ጦርነት ፈርቶ የሸሸ፣
  5. ሰኔ ወር 1971 ከሃገረ-ሰላም ውጊያ ታመምኩ ብሎ መሬት ላይ ሲንከባለል በበቅሎ ተጭኖ እንዲምለስ የተደረገው  ናቸው። በምስክርነት የሰራዊቱ የጦር አዛዥ አረጋዊ በርሄ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
በህወሓት ውስጥ ማንም ታጋይና አመራር የሚያውቀው ሃቅ አለ። ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ የነደፈው ጥናት እያደረገ ወታደረአዊ ስትራተጂ ወታደራዊ ታክቲክ የአሸዋ ገባታ ለረጅም አመታት ጥናት በማካሄድ የጻፈና ያዘጋጀ ብቸኛው አረጋዊ በርሄ ነው። ለሁሉም ወታደራዊ አመራር ስየ አብርሃ፣ ሃየሎም አርአያ ወዘተ. አስተምሮ ያሳደጋቸው አረጋዊ በርሄ ነው። ስየ አብርሃ ይሁን ሌላው የሚኩራሩበት ውሸት ነው። ወያኔ ህወሓት እስከ አሁን የሚጠቀሙበት ወታደራዊ ጉዞ በአረጋዊ በርሄ የተዘጋጀ እንጂ መለሾ ዜናዊ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ወታደራዊ ሳይንስ ይሁን ስትራተጂ የጤፍ ቅንጣት የምታክል እውቀት አልነበረውም። ሁሉም የሚዋሸው ለሆዱ፣ ለጥቅሙና የሙስና ዘርፊያውን በስፋት ለመቀጠል ስለሚፈልግ የሚመታው የውሸት ነጋሪት ነው።
ግደይ ዘርአጽዮን ከህወሓት ወጥቶ ወደ ስደት ሲሄድ በህቡር ገብረኪዳን መሪነት ተክለወይን አሰፋ፣ ተሻለ ደብረጽዮንን ጨምሮ ተፈትሾ የያዘውን ሰነዶች ሁሉ፣ ብጣሽ ወረቀት ሳትቀር፣ ጠራርገው በመውሰድ ባዶ እጁን ሱዳን ገባ።
አረጋዊ በርሄ፣ ህቡር ገ/ኪዳን፣ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ እቁባይ ሁነው ለብዙ ዓመታት ሲያካሂዱት የነበረውን ወታደራዊ ጥናትና ስትራተጂ የአሸዋ ገበታ፤ በትልልቅ ወረቀቶች ላይ በሰእል መልክ የተዘጋጁ ጠቅላላ ወታደራዊ መጻሕፍት ብጣሽ ወረቀት ሳትቀር በሁለት የማዳበሪያ ከረጢት ሞልተው የወረሱትን በታጋዮች አሸክመው ለመለሾ ዜናዊ አስረከቡት። ‘በሰው ደንደስ በርበሬ ተወደሰ’ እንደተባለው፣ መለሾ ዜናዊ ባልሰራውና በማያውቀው ወታደራዊ ስትራተጂ የአሸዋ ገበታ ንድፈ ሃሳብና አረጋዊ በርሄ ደክሞ ያዘጋጀው ነው። አሁን ወያኔ የሚጠቀምበት ወታደራዊ አካሄድ የአረጋዊ በርሄ ሥራና ጥናት ነው። ባልሰራኸው፣ በማታውቀው ጥበብ የራስህ አስመስለህ መጠቀም ያስንቃል፣ ያዋርዳል። ስለዚህ መለስና የህወሓት መንጋ ውሸታምና በምን ዓይነት ድቅድቅ የውሸት ጨለማ እንደተዘፈቁና ማንነታቸውን እንዲያውቁ ይህንን የጽሑፍ ሰነድ ያንብቡ።
የስብሃት ነጋ መርዶ ነጋሪ
ቀደም ብሎ በተህሓት-ህወሓት የነበረው የኢትዮጵያውያን አመራር ነበር። እነ አቶ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ በምን ምክንያት በምን ዘዴ እንደገደሏቸው በትክክል አስቀምጬዋለሁ። በየካቲት 1981 በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የነበረው ደርግ ትግራይን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ወያኔ ህወሓት ካለምንም ውጊያና ውጣ ውረድ ትግራይን ተቆጣጠረ። ሃቁ ይህ ሆኖ፣ በ1983 በለስ ቀንቷቸው አዲስ አበባ ዘው ብለው ኢትዮጵያን እነደተቆጣጠሩ፣ ነብሰ ገዳዩ ስብሃት ነጋ በመርዶ ነጋሪነት ተሰማራ። የዶ/ር አታክልት ቀጸላ ወላጅ አባት የሚኖርበት ቤት በመሄድና እራሱን በማስተዋወቅ የዶ/ር አታክልትን ሞት ነገራቸው። በአረጋዊ በርሄ እንደተገደለ ሲነግራቸው፣ አረጋዊ በርሄ የማን ልጅ ነው ብለው ሲጠይቁት፣ የቀኛዝማች በርሄ ገብረማርያም ነው ሲላቸው፣ የልጅ በዛብህ ፍላቴ ልጅ? ብለው ጠየቁት፣ አዎን አላቸው። የቅርብ ወንድሙ ለምን ገደለው? ሲሉት፣ በአረጋዊ መገደሉን እንጂ ሌላውን ሳይነግራቸው መርዶውን አሰምቶ ተሰናበተ። በጅሮንድ ቀጸላም በሚወዱት ልጃቸው መርዶ የተነሳ ታመው ከብዙ ስቃይ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ስብሃት ነጋ ይህ አልበቃውም። አድዋ አቶ ዳኘው ገ/ሥላሴ ቤት ደረስ በመሄድ የአጽብሃ ዳኘው ወላጅ እናትና ጠቅላላ ቤተሰቡ ባሉበት፣ በአክብሮት ተቀብለው ቤት ያፈራውን ከጋበዙት በኋላ፣ እናቱ ወ/ሎ ማና ተፈሪ ልጄ ‘ሞላ’ (የቤት ስሙ) እንባቸውን እያፈሰሱ፣ ልጄ ጠፋብኝ፣ የምታውቀው ነገር አለ ወይ ብለው ሲጠይቁት፣ ስብሃት፣ አጽብሃ፣ ሰዊት ተገድሎ ከሞተ ብዙ ዓመት ሆኖታል አላቸው። አባትየው ቀበል አድርገው እንዴት ሞተ ሲሉት፣ አረጋዊ በርሄ ገደለው አላቸው። አረጋዊ፣ የቀ/አ በርሄ ገ/ማርያም ልጅ? ብለው ሲጠይቁት፣ አዎን አላቸው። ያሳደገው ወንድሙ ገደለው? የአጽብሃ ዳኘው እናት በዚህ ደንግጠው ታመው በሃዘን በሽታ ተሰቃይተው ሞቱ። ሽማግሌው አቶ ዳኘው ገ/ሥላሴ አሁንም በሕይወት አሉ። የዶ/ር አታክለት ቀጸላ ወላጅ አባትም በመርዶው ምክንያት ታመው፣ ልሾ ወርቅ ልጄ እንዳሉ ሞቱ። በ1998 የሁለቱ ቤተውስቦች ስልክ በቀጥታ ወደ እኔ ደውለውልኝ ተነጋግረናል። በዚህ ሃሳብ ላይ እንዳለን፣ የዶ/ር አታክልት ቀጸላ ወላጅ አባት በጅሮንድ ቀጸላ ብሩ፣ ወላጅ እናቱና የእኔ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ገ/መድህን አርአያ ወላጅ እናቴ ወ/ሎ አጸደ ገብሩ እናት፣ የሁለቱ እናቶች ታላቅና ታናሽ የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው። በዚህ መሰረት ነው የዶ/ር አታክለት ቀጸላ ቤተሰቦች አረጋዊ በርሄ በምን ምክንያት እንደገደለው የጠየቁኝ። እኔም ስብሃት (ወ/ሥላሴ) ነጋ የነገራችሁ ውሸት ነው። ዶ/ር አታክልትን የገደለው ስብሃት ነጋ ነው፣ በማለት በጽሑፍ እንደገለጽኩት ስነግራቸው አምነውኝ ተለያያን። ያመኑኝ ምክንያት የአታክልት መገደል ለእኔም የሚሰማኝ ልክ እንደ እነሱ ስለሆን ነው። ለእኔም ለነሱም ወንድማችን ነው።
ቀጥሎ ከትንሽ ወራት በኋላ በ1998 ከአጽብሃ ዳኘው ቤተሰብ ወንድሙ ከእንግሊዝ ሃገር ደወለልኝ። በጽሑፍ እንዳስቀመጥኩት ገልጬለት አልቅሶና አጽናንቼው ተለያየን። ቀጥሎ ለሁለተኛ ጊዜ በ2000 ወንድሙ ደውሎልኝ፣ ያቀረብኩለትን ሁሉ እንዳለ አምኖ ተቀበለኝ። ሌላው ያቀረበልኝ ጥያቄ ቤተሰቦቼ በአረጋዊ በርሄ ቅሬታ አድሮባቸው ነበር፤ በምን አይነት ይቅርታ ልጠይቀው፣ እባክህ ንገርልኝ ሲለኝ፣ የለም ከሆነ ባንተ ነው መሆን ያለበት ብዬው እንደሚደውልለት ነግሮኝ ተሰነባበትን። አረጋዊ በርሄ ግምት ያልሰጠው እውነት አለ። የህወሓት ፕሮግራምን ጽፎ ለ12 ዓመት በከፍተኛ አመራር ላይ ሆኖ ያስተዳደረው ድርጅት ነው። ማንም የማያቀውን የድርጅቱን ወንጀሎች በዝርዝር ያውቃል። ህወሓት በሥልጣን ላይ ሆኖ ለፈጸመው ግፍ ተጠያቂ እንዳይሆን አረጋዊ በርሄ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወያኔን ማጋለጥ አለበት።
እነ ስብሃት ነጋ፣ መለሾ ዜናዊ ወዘተ. በትግሉ ጊዜ የተገደሉት ታጋዮች፣ ሰላማዊ ዜጎች በስንት ሺህ የሚቆጠሩ ናቸው። ከ1982 በዘመቻ መልክ ተነስተው ያስፈጁትን አረጋዊ በርሄ እንደገደላቸው አድርገው ስሙን በክፉ መልክ አጥፍተውታል፣ አሁንም እንደቀጠሉበት ነው። የህወሓት አባላትና ደጋፊዎቹ እስከ አሁን እኛን የፈጀን አረጋዊ በርሄ ነው እያሉ ይገኛሉ። እሱም ይህንን ነገር በትክክል ያውቃል። አረጋዊ የሚለውና የሚሟገተው፣ ማስረጃችሁን አቅርቡ እያለ ነው። ይህ አባብሉ ግን ትክክል አይደለም። የፖሊት ቢሮ አባልት ሁሉ በየ06 ሃለዋ ወያነ እየተበተኑ ሕዝብ የጨረሱት አመራሩ ናቸው። በ06 ሃለዋ ወያነ ሃላፊዎች የምርመራ ሪፖርት ጭፍን ፍርድ ሲሰጥ የነበረው አመራር ነው። በሰነድ ተደግፎ የሚፈጸም ግደሏቸው የሚል ትእዛዝ በተህሓት-ህወሓት አሰራር አይታወቅም።
እነ ስብሃት ነጋ በአረጋዊ በርሄ ላይ የሚያካሂዱት የስም ማጥፋት እልባት ማግኘት አለበት ከሚል ሃሳብ ተነስቼ መጋቢት 2 ቀን 2000 በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጆች ማህበር፣ በዶ/ር ግደይ አሰፋ ሊቀመንበርነት፣ በአቶ ተስፋየ አጽብሃ የሚመራው ቡድን በተጠቀሰው ቀን ተሰበሰበ። ለአረጋዊ በርሄ ያቀረብኩት ሃሳብ በእነ ስብሃት ነጋና በወያኔ ስርዓት ስምህ እየጠፋ ነው። አንተም በመጀመሪያ ማድረግ ያለብህ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀህ በህወሓት የተፈጸሙትን ወንጀሎች ለሕዝብ አቅርብ። ያን ስታደርግ የአእምሮ እረፍት ታገኛለህ። በህወሓት በርካታና ከባድ ወንጀሎች ተፈጽመዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር ባይ ነው የሚል ሃሳብ አቀረብኩለት። በወቅቱ የነበሩ አመራርና በቴሌ ኮንፈረንስ የነበሩት የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። አረጋዊ በርሄ ለምን ደፈርከኝ ብሎ ብዙ ተናገረ። ቁም ነገሩ ቴሌ ኮንፈረንስ በመሆኑ ነው እንጂ በአካል አጠገቡ ብገኝ ኖሮ ረጋግጦ ያጠፋኝ ነበር። የሁላችንም ግንኙነት ከዚህ ጊዜ በኋላ ተቋረጠ። ጥሩ ምክር በመለገሴ ጠላት አፈራሁ። የመከራና የችግር ጊዜ ወንድሙን ጠላኝ። ይባስ ብሎ የህወሓት ጠላትና ጽንፈኞች በማለት፣ አስገደ ገ/ሥላሴን እና እኔ ገ/መድህን አርአያን ፈረጀን። ይህን ለማለቱ ብዙ የሰው ምስክሮችት አሉን። የተማረ ሰው ነው። በህወሓት ውስጥ ያለፈ አመራር ሁሉ፣ ከትግሉ መጀመሪያ አንስቶ፣ ብዙ ወንጀል ፈጽሟል፣ በመፈጸም ላይም ነው። ስለዚህ ማንም አመራር እኔ ነፃ ነኝ የሚል ካለ ተሳስቷል። ልክ እንደ ግደይ ዘርአጽዮን ጥፋተኛ ነኝ ብሎ ደጋግሞ እንደሚናገረው ሌላውም ይህንን አርአያነት መከተል አለበት።
ውድ ኢትዮጵያውያን የህወሓት ታሪክና እንወቀው የሚሉት ጽሑፎቼ በዝግጅት ላይ ናቸው። በጥቂት ወራት ውስጥ ለሕዝብ ይቀርባሉ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ሶስተኛው ጽሑፌ ደግሞ “ተጠያዊዎቹ እነማን ናቸው” ይሚለውን በማዘጋጀት ላይ ነኝ። ከማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመጡ አመራር አንድ በአንድ ምን ሰሊ፣ በምንስ ይጠየቃሉ የሚለው ሰፊና ግልጽ መጽሓፍ እየተዘጋጀ ነው።
ማሳሰቢያ፡ በድህረ ገጽ የማስተላልፋቸውን ጽሁፎች ኢትዮጵያዊ ሁሉ በማተም ሰብስባችሁ “የህወሓት ገበና” በማለት በማህደር አጠራቅሙት። ጥሩ የሰነድ ማስረጃ ነው። የህወሓት አመራርና ካድሬዎቹ በሕዝብ የሚፈረዱበት ቀን ደርሷል።
ገብረመድህን አርአያ
ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይል ይደመሰሳል!!!
አውስትራሊያ
2006 ዓም የነጻነት ዓመት ናት!!!
መስከረም 6 ቀን 2006

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ላይ ተቃውሞ አሰማች

ጥቅምት (ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በቤተክርስቲያኑዋ ታሪክ  ተሰምቶ የማያውቅ ተቃውሞ ተከስቷል። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት እንደገለጹት በስብሰባው ላይ ”  á‹­áˆ… መንግስት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በስፋት ተነግሯል።

የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ዛሬ ሾለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ገለጻ ለመስጠት በተገኙበት ወቅት ነው ተቃውሞው የተሰማው።
እድሉን ያገኙት 6 ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም የሰሜን ወሎ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቄርሊዮስ ፣ የምእራብ ወለጋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ ሄኖክ፣ የጋሞ ጎፋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤሊያስ ፣ የወላይታ ዳውሮ ዋና ሾል አስኪያጅ፣ የምስራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ ብጹ አቡነ ማርቆስ ፣ የደቡብ ጎንደር ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድሪያስ የመንግስትን ፖሊሲ እአነሱ ትችት አሰምተዋል።
በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ፣ ግድያና ጫና መጨመሩን የተነጋሩት አባቶች ፣ ፓትሪያርኩም እውነት ነው ይህ ሁሉ ጫና አለብን በማለት በሊቀ ጳጳሳት የቀረቡውን ሀሳብ ደግፈዋል።
ከመላው አለም የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀይማኖቱ መሪዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን የሀይማኖት ታሪክ በማሳነስ ባቀረቡበት ወቅት  የሀይማኖት አባቶች ስሜት በተቃቀለበት ሁኔታ መልስ ሰጥተዋል።
የህዝቡን መሬት ነጥቃችሁ ፣ ህዝቡንም መሬቱንም የመንግስት ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ኢትዮጵያዊው ሀብትና ንብረት እንዳይኖረው አደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ከዚህ ቀደም ከነበሩት መንግስታት በባሰ ህዝቡን ያስጨነቀ ይህ መንግስት ነው በማለት አባቶቹ ተናግረዋል።
“በአጼዎችም ዘመን ቢሆን ይህችን አገር  áˆľá‰ľáˆ¨áŠ¨á‰Ą እስከ ታሪኩዋ ነው፣ ታሪኩዋን አላጠፋችሁም ወይ?” በማለት ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ሲናገሩ ከተሰብሳቢው ከፍተኛ ድጋፍ ተችሮአቸዋል።
የሀይማኖት አባቶች የቤተክስርቲያኑዋን ታሪክ አዛብታችሁዋል፣ ቤተክርስቲያኑዋንም ታሪኩዋን አጥፍታችሁዋል በማለት ወጥረው መያዛቸው ታውቋል።

Oct 16, 2013

“የሃሰት መንገድ ሁሌም መጥፊያ እንጂ መዳኛ ሆኖ አያውቅም!!” ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅ/ማርያም ቤ/ክ የተሰጠ መግለጫ

london
ባለፈው ቅዳሜና እሑድ (በ12/10/2013 እና በ13/10/2013) ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን áŠĽáŠ“ አካባቢውን ያናወጠ የአባ ግርማና ተከታዮቻቸው የሃሰትና የእብሪት ሼል ውጤት።
Read full story in PDF

Oct 14, 2013

ስንቱን አጣን! (ከፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም)

 

Pro Mesfin
እንደኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ልሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደአሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት ሰዎች በእንደዚህ ያለ ማኅበረሰባዊ ኋላቀርነት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዴት መራመድ ትችላለች? እያለ ይሰጋ ነበር።
ደብዳቤውን ላቋርጥና ስለሰውየው ትንሽ ልናገር፤ ተማሪ ሆኖ ክፍል ውስጥ ምንም ነገር የማያሳልፍ በጣም ተከራካሪ ተማሪ ስለነበረ አደንቀው ነበር፤ አንድ ጊዜ እንዲያውም የዘውድ መንግሥት ደጋፊ ነኝ አልሁና አንዴት በትከሻው ላይ ጭንቅላት ያለው ሰው ዓመቱን በሙሉ የዘውድ አገዛዝ የሚያደርስብንን በደልና ችግር ሲነግረን ቆይቶ አሁን ደግሞ ያንን ደጋፊ ነኝ ይላል ብሎ ወረፈኝ፤ ልጁን ስለማውቀው አነጋገሩ አሳቀኝ እንጂ አላስቆጣኝም፤ ጥያቄህ ይገባኛል፤ ግን እኔን ሳትወርፈኝ መጠየቅ ትችል ነበር በዬ ቢቀበለውም ባይቀበለውም ለጥያቄው መልሱን ሰጠሁት፤ በኋላም ጥሩ ጓደኛዬ ነበር።
ከአሜሪካ ትምህርቱን ጨርሶ እንደመጣ ተገናኘንና ወደቀድሞ ሥራው ወደወንጂ ተመልሶ እንደሆነ ስጠይቀው ‹‹áŠĽáŠ•á‹´á‰ľ ብዬ! ዕድሜ ልኬን የፈረንጅ አሽከር ሆኜ መኖር አልፈልግም፤ አሁን ደግሞ ያስተማረኝን ሕዝብ ላገልግል እንጂ!›› ነበር ያለኝ፤ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በወንጂ ባሉት ደመወዞች መሀከል ከፍተኛ ልዩነት ነበረ፤ ቁም-ነገረኛነቱን፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን ታማኝነት፣ የግል ጥቅሙን ቀንሶ ኢትዮጵያን ለመርዳት ባሳየው ተግባራዊ አርአያነት የማደንቀው የወታደር ልጅ ነው።
ይህ ሰው በደርግ ጊዜም አልሸሸም፤ በአንድ ኢንዱስትሪ ውስጥ በሥልጣን ቦታ ላይ ነበር፤ ወያኔ/ኢሕአዴግ ወንበሩን ሲይዝ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የማይፈለጉ መሆናቸው ሲታወቅ አገሩን ጥሎ ተሰደደ፤ በትልቅ ዓለም-አቀፍ መሥሪያ ቤት ጥሩ ሼል አግኝቶ ዕድሜው ለጡረታ እስቲደርስ ቆየ፤ ወደሚወዳት አገሩ ለመመለሾ አልቻለም፤ ከአንድ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር ግንኙነት እንዳለው አውቃለሁ፤ አንድ ቀን ስለዚሁ የጋራ ጓደኛችን ስናወራ ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ጠየቅሁ።
የዚህ ወጣት አጎት በወታደርነት ኢትዮጵያን ለረጅም ጊዜ በክብር ያገላገለ ነው፤ ይህ ሰው ወያኔና ሻቢያ በተጣሉ ጊዜ ዜግነታቸው በጉልበት እየተገፈፈ ከአገራቸው እንዲወጡ ከተደረጉት ሰዎች አንዱ ነው፤ በዚያን ጊዜ በሌላ የኤርትራ ተወላጅ ላይ የተፈጸመውን ግፍ ልሹ ሰውዬው በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ሲናገር የሰማሁት የሚከተለውን ነው፤– ‹‹áˆˆáŠ˘á‰ľá‹ŽáŒľá‹Ť በአለኝ ሁሉ አገልግያለሁ፤ ኢትዮጵያን ሳገለግል አንድ እግሬን አጥቻለሁ፤ አንድ ሰው ለአገሩ ከዚህ የበለጠ ምን ያደርጋል?›› ብሎ ሲናገር አስለቅሶኛል።
የኔ የቀድሞ ተማሪና ወዳጅም ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ሲጠየቅ ‹‹áˆˆáŒ‹áˆź (ማለት ለአጎቱ) ያልሆነች ኢትዮጵያ ለእኔ አንዴት ትሆነኛለች? በማለት በጥያቄ መለሰ አሉ፤ አባቱ ያገለገላትን፣ አጎቱ የለፋላትን፣ አያት ቅድመ-አያቶች የሞቱላትንና የደሙላትን አገር እንዲህ በቀላሉ ማጣት ነፍስን ያቆስላል፤ የነዚያን ሰዎች ሁሉ መስዋእት ያከሽፋል፤ ያረክሰዋል፤ ይህንን የተገነዘቡና ያዘኑ፣ ያለቀሱ ሰዎች ናቸው –
እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

Bomb blast in Ethiopian Addis ababa kills two

ADDIS ABABA (Reuters) – A bomb blast in the Ethiopian capital Addis Ababa killed two people on Sunday, state radio said.
There was no immediate claim of responsibility for the bombing, but Ethiopia says it has thwarted plots of attacks in the past two years and blames rebel groups based in the south and southeast, as well as Somalia’s al Shabaab insurgents.
“A bomb blast occurred at a residential house in the Bole district and killed two unidentified individuals,” a report on national radio said, quoting the National Security and Intelligence Service.
The explosion occurred in the city’s upscale Bole district, about 5 km (3 miles) from a soccer stadium where thousands of fans were queuing for tickets to a World Cup qualifier against Nigeria and gathering at squares in the capital to watch the match on giant screens.
The radio did not mention any suspected link to the match.
It quoted the security service as saying it was investigating the incident and gave no more details.
Ethiopian troops have been fighting al Qaeda-linked al Shabaab militants in Somalia since 2011, alongside African Union forces from Uganda and Burundi and Kenya.
However, the Horn of Africa nation has so far been spared the sorts of attacks the militants have carried out in nearby countries – such as the siege at the Nairobi mall last month and the attack on soccer fans in Uganda in 2010 – although it has been hit by sporadic explosions in recent years.
Thirteen people were wounded when an explosive device ripped through a bus near the border with Eritrea in 2010, while a bomb explosion near a court in the capital wounded two in 2011.
(Reporting by Aaron Maasho; Editing by Alison Williams)

የአዲስ አበባና የፌዴራሉ ህገ ወጥ መጅሊሶች የኢደል አድሃ (አረፋ) በአል ዝግጅትን ሙሉ ለሙሉ ለመንግስት አስረከቡ

ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው፦
አረፋ በዓል 1የኢድ በአል አከባበርን አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ደረጃ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተደረገው ስብሰባ መንግስት ሙሉ ሃላፊነቱን እንደተረከበ ተገለፀ ፡፡ ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ጥቅምት 5 \2006 እንደሚከበር የሚጠበቀው የኢደል አደሃ (አረፋ) በዐል ላይ የፌዴራልም ሆነ የአዲስ አበባ ህገ ወጥ መጅሊስ አመራሮች (ሸህ ኪያርንና ዶክተር አህመድን ይጨምራል) ወደ ሃጅ በመሄዳቸው የበአል አከባበሩን ሙሉ ሃላፊነት ለመንግስት እንደተሰጠ የመንግስት ሃላፊዎቹ ግልፅ አድርገዋል ፡፡
በዛሬው ስብሰባ ከአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሃላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኢንተሊጀንስ ፣ የፌዴራል ፖሊስ ሃላፊና ኢንተሊጀንስ ፣ የአዲስ አበባ መረጃና ደህንነት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በአሉ መንግስት በሚፈልገው መልኩ እንዲጠናቀቅ የተለያዩ መመሪያዎችን አውርደዋል ፡፡ ከወረዱት መመሪያዎች በዋነኝነት ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ወደ ስታዲየሙ የሚገቡበት የቴዲየም በር ቁጥር ስለሚሰጣቸው ክፍለ ከተሞቹ የየራሳቸውን የመንግስት ደጋፊ ሙስሊሞችን(አህባሾችን )ና ካድሬዎችን በመያዝ አንድ ላይ ከየአካባቢያቸው እንዲነሱና እስከ ከጠዋቱ አንድ ሰዐት ድረስ የስታዲየሙን የመጀመሪያ ሶፍ እንዲይዙ ታስቧል ፡፡
ሙስሊሙ ማህበረሰብ በእለቱ ተቃውሞ ማድረጉ እንደማይቀር መንግስት ያመነ ሲሆን ይህን ለመከላከል በየክፍለከተማው የሚገኙ አህባሾችና የመንግስት ደጋፊዎች ፣ እንዲሁም ከሁሉም አደረጃጀቶች (ከነዋሪዎች ፎረም ፣ ከሴቶች ፎረም ፣ ከወጣቶች ፎረምና መሰል አደረጃጀቶች) የተውጣጡ ካድሬዎች እስከ ጠዋቱ አንድ ሰዐት ባለው ግዜ ውስጥ ስቴዲየም ቀድመው በመግባት ተቃውሞ አድራጊዎቹ የመጀመሪያዎቹን ረድፎች እንዳይዙት መቅደም እንዳለባቸው ትእዛዝ አውርደዋል ፡፡
በእለቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ወይም ተወካያቸው ፣ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲሁ አንድ ተወካይ በመገኘት የመንግስትን አቋም የሚያንፀባርቅ ንግግር እንዲያደርጉ እቅድ የተያዘ ሲሆን ተቃዋሚዎች ይህን ንግግር እንዳያስተጓጉሉና ሚዲያውም የበአሉን አከባበር በነፃነት ማስተላለፍ እንዲችል በስታዲየም ውስጥ የተቃዋሚዎችን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሚና መቀነስ መቻል አለብን ብለዋል ፡፡
አረፋ በዓልኦረንቴሽኑን እየሰጡ ከነበሩት የመንግስት ሃላፊዎች መካከል አንዱ “ እኛ ከስታዲየሙ ውጪ ችግር የለብንም ፡፡ ውጪውን የሚጠብቅ የራሱ ባለቤት አለው ፣ መረባረብ ያለብን በስቴዲየም ውስጥ እንዳይረብሹን ነው ፡፡ ከሰላት በፊት በስታዲየሙ ውስጥ የሚደረጉ ንግግሮችና ሌሎች መሰል ፕሮግራሞች በሁከት መቆም የለባቸውም ፡፡ ከኢደል ፊጥር በአል ባገኘነው ተሞክሮ ተቃዋሚዎቹ ስታዲየም ውስጥ አይገቡም ማለት አይቻልም ፡፡ እንኳን እነሱ ይቅርና ባነራቸውንም አስገብተዋል” ያሉት የመንግስት ሃላፊው “ ቁም ነገሩ ግን አሁን የሚፈለገው ማክሰኞ ስታዲየም ውስጥ ገብተው የሚቃወሙትን ሀይሎች የኛ ካድሬዎች በማስደንገጥ ማስቆም መቻል አለባችሁ ፡፡ እነሱ መጮህ ሲጀምሩ የኛ ደጋፊዎች ደግሞ ዞር ዞር እያሉ እንዲገለምጧቸውና አጠገባቸው ያሉትም ምንድን ነው የምትጮሀው እያሉ ማስደንበር አለባቸው፡፡ ስቴዲየም ውስጥ ስለሆኑ ደንግጠው ያቆማሉ ፡፡ በዛ ላይ ለኢደል ፊጥር የደረሰባቸውን ስለሚያውቁ ይፈሯቸዋል፣ ስለዚህ ይህን መመሪያ በጥንቃቄ እንዲተገበር ወደ ታች እንድታወርዱ ” ብለዋቸዋል ፡፡
ሌላኛው የመንግስት ሃላፊ በበኩላቸው “ ከስግደት በኋላም ቢሆን ተቃዋሚዎቹ ሲረብሹ የኛ ሰዎች በመጡበት አኳኋን ወደ እስታዲየሙ በገቡበት በሮች ግር ብለው መውጣት ነው ያለባቸው ፡፡ ምክንያቱም ተቃውሞ አድራጊዎቹ ከስግደት በኋላም እንደተለመደው ረብሻቸውን ሲጀምሩ የኛ ደጋፊዎ ድንገት ግር ብለው እየደረመሷቸው ሲወጡ ብቸኝነት ተሰምቷቸው ተቃውሟቸውን ያቆማሉ ፡፡ ከወጣችሁም በኋላ የትም ቦታ አትቁሙ ፡፡ ቀጥ ብላችሁ ወደቤታችሁ ነው መሄድ ያለባችሁ ፡፡ ፖሊስም ሆነ ደህንነት የሚረዳው ወደ ኋላ የሚቀር ሁሉ ረብሻ ፈላጊ ነው ብሎ ነው ፡፡ ይህ ኮዳችን ነው ፡፡ ከሰላት በኋላ የኛ መጅሊስ ሰዎችና ካድሬዎች ምንም ሳይቆሙ ወደ ቤታቸው ነው መንገድ መጀመር ያለባቸው ፡፡ ወደ ኋላ የሚቀረው ግን ተቃዋሚዎች ናቸው ብለን ነው የምናምነው ” ብለዋል ፡፡
በዚህ መሰረት እያንዳንዱ የከፍለ ከተማ መጅሊስ ሰብሳቢዎች ከኢማሙ ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያው ሶፍ ላይ እንዲሆኑ ፣ እያንዳንዱ የክፍለ ከተማ መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢዎች በሁለተኛው ሶፍ እንዲሆኑ ፣ እያንዳንዱ የክፍለ ከተማ መጅሊስ ፀሃፊዎችና ቀሪዎቹ አራቱ አመራሮች ደግሞ ከበር እስከ መድረክ በመያዝ እንግዳ እንዲቀበሉ ፣ እንዲከታተሉና እንዲያስተናግዱ እቅድ ወጥቷል ፡፡ የአህባሽ ሱፊ ማህበር አባላት ደግሞ ከነዚህ ኋላ ያለውን ሶፍ እንዲይዙ ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡ ከነዚህ በተጨማሪም እያንዳንዱ የክፍለ ከተማ አመራሮች ፣ ከተለያዩ ዘርፎች የተዋቀሩ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ደግሞ ክፈለ ከተማቸው እንዲገቡ በተነገራቸው የስታዲየም በር ቁጥር በመጠቀም ቦታቸውን መያዝ እንዳለባቸው መመሪያ ወርዷል ፡፡
ልደታና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ለስቴዲየሙ ቅርብ እንደሆኑ ስለሚታሰብ በጠዋት ተነስተው ወደ እስታዲየም በእግራቸው እንዲሄዱ የተነገራቸው ሲሆን ሌሎቹ ግን መኪና እንደሚታዘዝላቸው ታውቋል ፡፡
ተልእኮ
1) ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ በተቃዋሚዎቹ ሲደረግ ባሉበት ቦታ ሆነው በአንድ ድምፅ “ዝም በሉ አትጩሁብን ” በማለት ለማስቆም መሞከር
2) ከተሰገደ በኋላም ሁሉም አባላት መንገዱን ቶሎ በማስከፈት ግር ብሎ በሁሉም የስቴዲየሙ በሮች በመውጣት ተቃዋሚዎቹን በማስደንገጥ መበተን ፡፡ ሙሰሊሞቹ ተቃውሞ በሚያደርጉበት ወቅት ሁሉም አባል በአንድ ላይ በሁሉም በር ግር ብሎ ሲወጣ ህዝበ ሙስሊሙን የመበተን እድል ይኖራል የሚል መላምት ቀርቧል ፡፡
ሆኖም በስብሰባው የነበሩ አመራሮች “ የኛ የመጅሊስም ሆኑ ሌሎች አባላቶች ይህን መመሪያ በተቀላጠፈ ሁኔታ ይተገብሩለናል ወይ ብዙዎቹ ይፈራሉ ወይም በሰዐቱ ላይገኙ ይችላሉ “ የሚል ቅሬታ ቢያቀርቡም ይህን ተከታትላችሁ ማስፈፀም የናንተ ግዴታ ነው የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ፡፡
በመጨረሻም የመጅሊሱ ሁሉም አመራሮች ወደ ሃጅ ስለሄዱ መድረኩ በመንግስት ሰዎች ብቻ እንዳይያዝ ከሰላት በፊት ህዝቡን ተክቢራ የሚያስብሉና መጅሊሱን ወክለው ንግግር እንዲያደርጉ ከክፍለ ከተሞች የመጅሊስ አመራሮችና ለመንግስት ቅርብ የሆኑ ኢማሞች እንዲመለምሉ ክፍለ ከተሞች ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ፡፡ የኢድ ስግደት የሚከናወነውም ከጠዋቱ 2 ሰዐት ላይ እንደሚሆን ወስነው ስብሰባቸውን አጠናቀዋል ፡፡
በነገው እለትም ለየክፍለ ከተማ ህገ ወጥ መጅሊስ ሰባት አመራሮች ኦረንቴሽን እንደሚሰጥም ታውቋል ፡፡
አላህ ከተንኮለኞች ሴራ ይጠብቀን
ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!!
አላሁ አክበር!!

ይሄ እየታየ እንዴት ያ መንገድ ይታሰባል?

ይሄ እየታየ እንዴት ያ መንገድ ይታሰባል? ለኔ የአመቱ ምርጥ እዉነተኛ አስተማሪ ፊልም ነዉ!!!! እስከመቼ ድረስ ስደት? ባገራችን መኖር ካልቻልን ለምንስ ነው የማንታገለው?  ለኔ እዚህ ፊልም ውስጥ  ያሉት በሙሉ በጣም የማከብራቹ ትልቅ ማስተማሪያ የያዛችሁ ወንድሞቼ ናችሁ!!! ***ክብር አለኝ ለእናንተ ሁሌም*** ለሞቱት ወንድሞቻችንም አምላክ ነፍሳቹውን በገነት ያኑር !!!  R , I , P,

ስብሃት ነጋን አጅበው አክቲቪስት መስፍን ላይ ድብደባ የፈጸሙት ግለሰቦች ማንነት ታወቀ

(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው ዕለት ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና ባቀረበቸው ቪድዮ ላይ አክቲቪስት መስፍንን በቡጢ የተማቱትና የቆሙ መኪናዎችን ገጭተው ያመለጡት ግለሰቦች ማንነትን ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አረአያ ማወቁን ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታወቀ፡፡
የሕወሓት መንደርን ከቃረምኩት በሚል በኢትኦጵ ጋዜጣ ላይ የሕወሓት ምስጢሮችን በሚያጋልጠው ጽሁፎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ጋዜጠኛ አረአያ ተስፋማርያም (ኢየሩሳሌም አረአያ) በትናንትናው እለት በአክቲቪስቱ ላይ ድብደባ የፈጸሙትን በሕግ የሚጠየቁት ግለሰቦች ሶስቱም የሕወሓት አባላት መሆናቸውን ጠቅሶ ማንነታቸውን ዘርዝሯል።
1ኛው. የሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ወንድም ታምራት ገ/መድህን፣
2ኛው. የወያኔ ኪነት አባልና ጊታሪስት ወዲ ሰቦቃ (በአሜሪካ ፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ)፣
ስብሃት ነጋ
ስብሃት ነጋ
3ኛው ሃይሌ በአሜሪካ – የኢትዮጲያ ኤምባሲ የብርሃነ ገ/ክርስቶስ ሹፌር የነበረና በአሁኑ ወቅት በቪዛ ክፍል የሚሰራ ናቸው።

አክቲቪስት መስፍን ለደረሰበት ድብደባ ሕክምና የተከታተለ ሲሆን ጉዳዩን በሕግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። በሌላ በኩል የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን አንድ የቨርጂኒያ ጠበቃ አነጋግሮ ባቀረበው ዘገባው ስብሃት ነጋን ጨምሮ እነዚህ ግለሰቦች ሰውን በመደብደብና የሰው መኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀሎች ከተከሰሱና ፍርድቤትም ጥፋተኛ ካላቸው በ እያንዳዱ ክስ እስከ አንድ አመት የሚያስቀጣ ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። ስብሃት ነጋም የወንጀል ተባባሪ፣ እንዲሁም የሰው መኪና ገጭቶ ባመለጠ መኪና ውስጥ በመሄዳቸውና ወንጀልን በመተባበር ክስ በአሜሪካ ህግ በወንጀል ተባባሪነት ሊከሰሱ የሚችሉበት ህግ አለ።

Oct 13, 2013

በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ – እውነትና ከሕደት………(ከ ይድነቃቸው ከበደ)

ooohhhh
(የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
ኪነ-ጥበብ ምኞታችን፣ደስታችን፣አዘናችንን እና ክፋታችን የምናይበት እና የምናዳምጥበት የህይወታችን ነፀብራቅ ነው፡፡ ኪነ-ጥበብ ህይወትን ቀለል አድርጎ ከማዝናናት ባለፈ በገለሰብ አስተሳሰብ ላይ የራሱ የሆነ በጎ ወይም በጎ ያልወነ አስታውጾ የሚያበረከት ጥበባዊ ሃይል ነው፡፡ይህ ሃይል በመልካም አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ ወደ ህብረተሰቡ ውስጥ ሲገባ የሚኖረው አገራዊ ፋይዳ እጅግ በጣም የበዛ ነው፤፤ በመሆኑም ኪነ-ጥበብ እንዲህ አይነቱ ጠቀሜታ እንዲኖረው የሚያደርጉት በጥበብ ሙያ ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች ናቸው ፤እነኚህ ባለሙያዎች ሙያቸው ከመሬት የፈለቀ ሣይሆኖ በልምድና በት/ት የዳበረ ጥበባዊ ተስጥኦ ነው፡፡
ከኪነ-ጥበብ ዘርፎች ውስጥ ከሚመደቡት አንዱ ቴአትር ነው፤ ቴአትር በአገራችን ያለው ተቀባይነት ቀላል የሚባል አይደለም ፤ቴአትር አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ የቴአትር ባለሙያዎች የከፈሉት ዋጋ ከዕድሜቻው፣ ከገንዘባቸው እና ከዕለት ተዕለት ማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ጎምዶ ያስቀረባቸውን የሚያውቁት ዋጋውን የከፈሉት እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ ቢሆንም በቴአያትር ጥበብ የዝወትር እንቅስቃሴችን መጥፎዉንና የተሸለውን በመለየት ጥበባዊ በሆነ መንገድ እየተዝናናን እንድንማርበት ለሚያደርጉ የቴአትር ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ስንመለከትና ስናደምጥ እውነትም ለሙያው እድገት የተከፈለ ነገር እንዳለ ያስገነዝበናል፡፡
ስለሆነም ለቴአትር ባለሙያዎቻችን ከትላንት ዛሬ የምንሰጣቸው ከበሬታና አድናቆት የሚበረታታና የሚያስደነቅ ነው፤ይህ ደግሞ ለቴአትሩም እድገት የሚጠቅም ነው፡፡ይሁን እንጂ በቀርብ በብሔራዊ ቴአትር ቀደምት ባለሙያዎች ላበረከቱት አስታዋጽኦ በማስታወስ የሽልማት ፕሮግራም የተዘጋጀ ቢሆንም ዝግጅቱ እውነትና ከሕደት የተቀላቀለበት ነበር፡፡
‹‹……. ቀደምት ባለሙያዎች እንዲገናኙና ባለፈው ላደረጉትም አስታውጽኦ ሽልማት መሰጠቱ ተገቢነት ያለው ድርጊት ነው፡፡ባለሙያዎቹ ሲገናኙና በመነፋፈቅ ፈቅራዊ ሰላምታቸውን ሲለዋወጡ ስመለከት እጅጉን ደስ ብሎኝ ነበር የምከታተለው፡፡ እየቆየሁ ሲሄድ በውስጤ ቅሬታ ተሰማኝ በብሔራዊ ቴአትር በተከናወነው ስርአት ላይ በሞት የተለዩትን ተነሱ፤ በነፍስ ያሉት ግን ተገኝተው የሚመሰገነው ተመሰገነ፤ የሚሸለመው ተሸለመ እዚህ ላይ ነው ቅድም የጀመረኝ ቅርታዬ የበረታብኝ፡፡………. ››
በማለት በብሔራዊ ቴአትር ቤት የተካሄደውን ሽልማት ስነስርአት በኢቲቪ ፕሮግራሙን ሲከታተል የነበረ ሰው ትዝብቱን እና ቁጭቱን በሎሜ መፅሔት በባለፈው ሳምንት ዕትም ላይ ያስነበበን፡፡
እኔም የሰውዬውን ትዝበት እና ቁጭት አብዝቼ የምጋራው ነው፤ አርቲስት ደበበ እሸቱ በሙያው ከበሬታን ያተረፈ ለብሔራዊ ቴአትር ቤት እድገት የተቻለውን አስታውጾኦ ያበረከተ እና በህይወተ ከቀሩልን አንጋፋ አርቲስቶች መካከል አንዱ ስለመሆኑ ማንኛውም ሰው የሚሰጠው ምስክር ነው፡፡እውቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ ተዋናይ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆነ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ሾል እና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል፡፡ ቤተ መንግስት ተገኝቶ አፄ ኃይለሥላሴን ከሥልጣን ሲወርዱ ያነጋገራቸው ጋዜጠኛ ደበበ እሸቱ ነው፡፡ የተለያዩ ሃላፊነቶችን ይዞ ሠርቷል ፤ በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል እንዲሁም በአትላንታ አንድ ቀን በስሙ ተሰይሞለታል፡፡ የአርቲስት ደበበ እሸቱ የጥበብ እረዥሙ የህይወት ጉዞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኪነጥበባት ወ ቴአትር ተጀምሩ በብሔራዊ ቴአትር የቀጠለ ሲሆን በአገር ፍቅር ቴአትር ቤት ያበቃ ነው፡፡
ሾለ አርቲስቱ ካነበብኩት እና ከማቀው ይህን ብልም ከእኔ እውቀት ማነስ ያስቀረውበት መልካም የሆኑ ስራዎቹ እንደሚኖሩት ተስፋ አደርጋለው፡፡ በመሆኑም በብሔራዊ ቴአትር ቤት በተካሄደው የማስታወስ እና የሽልማት ስነስርአት ላይ አርቲስት ደበበ እሸቱን ለማስታወስም ሆነ ለመሸለም አለመቻሉ ከምን እንደመነጨ አንድ ለበዓሉ ዝግጅት ቅርብ የሆነ ለሆዱ ያደራ አርቲስት በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ በፈጀ ወጪ እውነትና ክሕደትን ዘርዝሩ የተናገረው፡፡ ይህን ሰው ሆድ አደር ያልኩበት ምክንያት የሚያውቀውን እውነት በፍራቻ ምክንያት በአደባባይ አለመግለፁ እንዲሁም የዝግጅቱ አስተባባሪ ከሆኑት ውስጥ አንዱ እንደመሆኑ መጠን የራሱን እምነት ወይም አቋም በዝግጅቱ ሂደት ላይ ምንም ሳይገልፅ ሌሎችን ለመኮነን የሄደበት መንገድ ነው፡፡
ይህ ለበዓሉ ዝግጅት ቅርብ የሆነው አርቲስት የቀረበለትን ምግብ እና መጠጥ እየጠጣ አርቲስት ደበበ እሸቱ በሙያው አንቱታን ያተረፈ ለቴአትር ሙያ እድገት አስታውጾኦ ያበረከተ መሆኑ እና በቀድሞ የሙያ አጋሮቹ ፍቅርና ከበሬታ ያለው መሆኑን ምግብና መጠጥ ለጋበዘው ሰው ገልጾአል፡፡ ንግግሩን ሲቀጥል ‹‹ ደቢሾ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ስለሆነ በፕሮግራሙ ላይ እንዲሳተፍ አልተፈለገም ፤ በሱ ጉዳይ ላይ ስንቱ አፈ ልጉም ሁሉ ልወደድ በሚል አፉን ፈታ መሰለህ፡፡ የሚገርመው ግን ደቢሾ ወደ ቴአትር ቤት አንድ ሁለት ጊዜ መጥቶ በነበረ ጊዜ ሁሉም እንዴት እየተንደረደሩና እላዩ ላይ እየተጠመጠሙ እንደሚስሙት አይ ነበር እነዚያው ሰዎች አሁንም እንዳይጠራ ብለው ሲሞግቱ በጣም ነው የተገረምኩት ፡፡ ዋናው ደግሞ ሾል አስኪያጁ እንዴት እንደተቃወመና በጭራሽ ሊጠራ አይገባም ፤ እሱ የሚጠራ ከሆነ እኔ በበዓሉ አልገኝም ስራዬንም እለቃለው አለ ! በቃ ያንን ስንሰማ ሁላችንም ፈራን……….. ስማ እንግዲህ ይህ በእኔና ባንተ የሚቀር የግል ጨዋታ ነው፤ የኔን ስም በጽሁፍም ሆነ በግልም ለደቢሾም ቢሆን እንዳታነሳ፤ አደራህን ነገ የሚሆነውን ማን ያውቃል ? ›› በማለት የነገሩን ሂደት ሰፋ አድርጎ የገለፀው፡፡
ውድ አንባቢያን 1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና 12 ድራፍት ብርጭቆ የፈጀ ወጪ በመሸፈን በብሔራዊ ቴአትር ቤት የተካሄደውን የሙያ ክሕደት እውነቱ እንዲወጣ ያደረገው አርቲስት እና ምግብና መጠጥ አሸንፎት እውነቱን የተናገረው ሌላኛው አርቲስቲ ሙሉውን ታሪክ መስከረም 18 ቀን 2006 ዓ.ም በወጣው ሎሚ መፅሔት ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
ወደ መነሻዬ ልመለስ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ እድሜ ልኩን በሙያው ያገለገለ እውቅ አርቲስት ነው ፡፡ በዚያው መጠን አሁን ባለው በገዢው ስርዓት ለታየው ብልሹ አስተዳደር ግንባር ቀደም በመሆን ሲተች እና ሲታገል ነበር በዚህም ምክንያት ለተደጋጋሚ እስር እና ለተደጋጋሚ ይቅርታ ጥያቄ ተዳርጓል፡፡ ይህ ግለሰባዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ በኪነ-ጥበብ ውስጥ ላበረከተው በጎ አስታውጾ በየትኛውም በኩል መመዘኛ ሊሆን አይገባም !!! እርግጥ ነው ገዢው መንግስታችን ለልማታዊ አርቲስቶች ያለው ድጋፍ ቀላል የሚባል አይደለም ፤ ልማታዊ አርቲስቶችም ለኢህአዴግ መንግስት ያላቸው ድጋፍ ወደር አይገኝለትም፡፡
አርቲስቶቻችን ሰው እንደመሆናቸው መጠን የራሳቸው የሆነ የሃሳብ ነፃነት ያላቸው ሲሆን በዚህ መብታቸው በመጠቀም የሚፈልጉትን የፖለቲካ አስተሳሰብ የመደገፍ ሳይመስላቸው ሲቀር የመተቸትና የመቃወም መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ተፈጥራዊ የሃሳብ ነፃነት መብት በሃይል ወይም በጥቀማጥቅም በመደለል እና በማስገደድ የአንድ የፖለቲካ ስርአት ብቻ ደጋፊና አቀንቃኝ ማድረግ የሞራል ጥያቄ ያስነሳል፡፡
በመሆኑም እንዲህ አይነቱ አካሄድ ለአርቲስቱም ሆነ ለሙያው እድገት ጉዳት እንጂ ጠቀሜታ የለውም፡፡ በአገራችን የፖለቲካው ስርአት ሲለወጥ የአገር መከላኪያ ሠራዊት ( ጦሩ) እየተለወጠ በአዲስ መልክ እየተቋቋመ ተቸግረናል ፡፡ አሁን ደግም የመከላኪያ ሠራዊት ( ጦሩ) ብቻ ሳይሆን አርቲስቶቻችንም ከፖለቲካ ስርአታችን ጋር እየተቀየሩ በአዲስ መልክ ልናያቸው ይሆን ? ፡፡ እንዲህ አይነቱ አደገኛ ከስረት ውስጥ ከመግባታችን በፊት የነገሩን አካሄድ ሊመረመር ይገባል ፡፡
በመሆኑም በአርቲስት ደበበ እሸቱ ላይ የተፈጸመው የሙያ ከሕደት እጅግ በጣም የሚያሳዝን እንዲሁም የሚያሳፍር ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ አገርን አስተዳድራለው ከሚል መንግስት እንደሰፈር ጉልበተኛ ጎረምሳ እልህ በመጋባት በአርቲስቱ ላይ የሙያ ከሕደት እንዲፈፀም ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ አስታውጾኦ በመንግስት ካድሬዎች በመፈጸሙ ሌላኛው አሳፋሪ እንዲሁም አስቂኝ ነገር ነው፡፡
ስለዚህም ለእውነት ያደሩ ሙያተኞች እንዲህ አይነቱን አሳፋሪ ተግብር ለህዝብ ከማጋለጥ ባለፍ ለሙያቸው እና ለእራሰቸው እድገት የሚበጀውን ቀና መንገድ ለማምጣት ውጫዊ እና ውስጣዊ ሙያዊ ትግል ሊያካሂዱ ይገባል፡፡ በተጨማሪ በቀብር ስነስርአት ላይ ጥቁር ለብሶ እና በእመም ጊዜ ለመታከሚያ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከመታየት በለፈ በሙያቸው እውቅ የወኑትን አርቲስቶች በህይወት እያሉ በማሰብ እና በማበረታታት ሙያዊ አጋርነታቸውን ለእውነት የቆሙ አርቲስቶች ሊያሳዩን ይገባል፡፡

እስክንድር ነጋ በአራት ጎብኚዎች ብቻ እንዲጎበኝ ተደረገ

ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡
የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን ጠያቂዎች ቁጥር በአራት መወሰኑ ታውቋል፡፡
ህገ መንግስቱ በግልጽ እስረኞች በወዳጅ ዘመዶቻቸውና ሊጠይቋቸው በሚፈልጓቸው ሰዎች መጎብኘት እንደሚገባቸው ቢደነግግም የቃሊቲው መንግስት ግን ህገ መንግስታዊውን ድንጋጌ በመጣስ በማን አለብኝነት የእስክንድር ጠያቂዎችን በዝቅተኛ ቁጥር ገድቧል፡፡
የማረሚያ ቤቱ ምንጮች እስረኞች ጥፋት ሲፈጽሙ እንዲህ አይነት ህግ ለተወሰነ ግዜ እንደሚወጣባቸው በማስታወስ በእነ እስክንድር ላይ የተላለፈው ውሳኔ ግን ‹‹áŒĽá‹á‰ľ መፈጸማቸው ሳይነገራቸው ፣ፈጸሙት ለተባለው ጥፋትም ቀርበው መከራከሪያ ሳያቀርቡ መሆኑ ውሳኔውን ፖለቲካዊ ያደርገዋል››á‰Ľáˆˆá‹‹áˆ፡፡
ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ በተመሳሳይ መልኩ ከጥቂት ሰዎች ውጪ እንደማትጎበኝ እርሷን ለመጠየቅ የሚፈቀድላቸው ሰዎችም ለአስር ደቂቃ ብቻ እንደሚያገኟት ከዚህ ቀደም መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል:: MUST READ !!!

"አገሪቱ በልማት ጎዳና ላይ እየነጎደች ...." ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በትእዛዝ የካዱት
"የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል::" ሪፖርተር ርእስ አንቀጽ 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ሪፖርተር መግለጫ ግጭት #1 ምንሊክ ሳልሳዊ

ኖሚናል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተባሉት እና በህገመንግስት የተሰጣቸውን ስልጣን በትእዛዝ ብቻ የሚሰሩበት ምንም አይነት አገራዊ ፋይዳ የማያደርጉት ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እና የሕወሓት ታማኝ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ያሰፈረው ርእስ አንቀጽ የሃገሪቷ ላይ የሰፈነው አብዮታዊ ዲሞክራሲ አምባገነንነት እያደረሰ ያለውን ችግር እና መጪውን አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገሪቱ ምንም አይነት ችግር እንዳሌለ እና ሁሉም ነገር በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዳለ በዲሞክራሲ እና በልማት እየነጎድን ህዝባዊ ድሎችን እየተጎናጸፍን ..ምናምን...የሚሉ እና ሃሰትን የተሞሉ የማደናገሪያ እና የማስፈራሪያ ቃላት ፍርሃት በሚነበብበት ፊታቸው እያስገመገሙ ደስኩረዋል:: የእርሳቸው ንግግር እንደተጠበቀ የሕወሓት ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ እንዲህ ብሎናል::የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት ፕሮፓጋንዳ እና የሚከተለውን የሪፖርተር ወቀሳ ይመዝኑት::ሪፖርተር እንደውስጥ አዋቂነቱ ያየውን እና የታዘበውን ሃይለማርያም ደሳለኝ ግን በትእዛዝ የካዱት እኛ ደሞ ያነበብነውን የተከፋፈልነው የታዘብነውን እንደራሳችን እይታ እንደሚከተው በዝርዝር ለማየት እንፈቅዳለን::

ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሌለ እና እንደሚያስፈልግ በግልጽ አስቀምቷል:: የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለዩና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሰየሙ ምንም ችግርና ብጥብጥ እንዳልነበር ይህ ማለት መሪ አልተተካም ሳይሆን ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ መንግሥትና አመራር ስላሌለ አገራችን ያያስፈልጋል እያልን ዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ እኛንም እየጐዳን ነው፡፡ ትላልቅና በርካታ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሲደረጉ በደመነፍስ ባጀት ተመድቦ ከፍተኛ ፋይናንስ ሳይኖር ወደ ላማት ይገባል ፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበረ የሃይማኖት ግጭትና ልዩነት እየታየ ነው፡፡ ችግሩ ካልተፈታ አስጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ዕድገት የማይሹና የማይመኙ ጠላቶች በእጅጉ እየተፈታተኑን ናቸው፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ጠንካራ መንግሥትና ጠንካራ አመራር የግድ ይላል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ተንካራ መንግስት እና አመራር እንደሌለ በግልጽ ሪፖርተር አስቀምጧል::

ገዥው ፓርቲ እርስ በኤርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሓዴግ አራት ድርጅቶችን አክፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከልመራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ቃላቶች ተክቶ አቅርቦታል::


የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ጋዜጣ ሪፖርተር ግጭት === #2 ምንሊክ ሳልሳዊ
 
-ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን የሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር
-ሙሰኞችን ማደን - ‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል
-የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡

ገዥው ፓርቲ እርስ በእርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሕኣዴግ አራት ድርጅቶችን አቅፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል መራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን በሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ተክቶ አቅርቦታል::

ሙስናው በስፋት ተንሰራፍቷል ያልው የሪፖርተር ጋዜጣ "አገር በሙስና እየተጨማለቀች ናት" ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተናገሩት በተቃራኒ ጎኑ መጭውን አደገኛ የሃገር ኢኮኖሚ የዳግም ስርኣተቀብር ሙስናው እያሳየን መሆኑን ጠቁሟል:: ሙስናን ለመዋጋት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የውስጥ የፖለቲካ ባላንጣዎችን ለማፈን እና ለማስወገድ የእጅ አዙር መጥረቢያነት ከማገልገል ውጭ ምንም አይነት እርምጃ በሙሰኞች ላይ ሲወሰድ አልታየም ይባስ ሙስና በሃገሪቱ እየተስፋፋ እና እያበበ ነው::‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል እንደሆነ ይጠቁማል::ሙስና ኢትዮጵያን እያጨማለቀ ሲሆን ከስርቆትና ከዝርፊያ በፊት ሙስናን የሚያስቆሙና የሚያጋልጡ አሠራሮች፣ ሕጐች፣ መዋቅሮችና የሥነ ምግባር ደንቦች እንዳይወጡ የመንግስት ባለስልጣናት እንቅፋት ሁነዋል::የመንግስት ባለስልጣናት በራሳቸው ለሙስና የሚያመች ሁኔታ እየፈጠሩ ሙስናን እንዋጋለን ማለት አያስኬድም፡፡ ከአሿሿም ጀምሮ፣ ከቁጥጥር ጀምሮ፣ ከቅጥር ጀምሮ አሠራሩ ሁሉ ሙስናን የሚያስወግድ ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝነትን የጠበቀ ነው፡፡

አገሪቷ በሙስና መጨማለቋ የመልካም አስተዳደር እጦት ፈጥሯል:: ጠቅላያችን እንዳሉን ማንጫውንም ነገር መልካም አስተዳደርን ጨምሮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸው እና በሂደት እየተሻሻሉ እንደሚሄዱ ነግረውናል ይህ ነገር ላለፉት 22 አመታት ሲነገረን የነበረ እና ምንም አይነት ለውጥ ከማየት ይልቅ በካድሬዎች ብልሹ አሰራር እና ቢሮክራሲ የመልካም አስተዳደሩ እየተበላሸ ገደል መግባቱን ብቻ ነው::የመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝቡን ተስፋ እያስቆረጠ ነው ብሎናል ለገዢው ፓርቲ ቅርብ የሆነው ሪፖርተር- አዎን ገዥው ፓርቲ መልካም አስተዳደር አለመኖሩን እያመነ ነው፡፡ ዕርምጃም እወስዳለሁ ቢባልም ለስልጣኑ ማራዘሚያ የሚጠቀምባቸው በጥቅም የተተበተቡ ካድሬዎቹ ይገለበጡብኛል በሚል ፍራቻ ምንም አይነት ርምጃ ሳይወስድ የመልካም አስተዳደር እጦቱ እንደቀጠለ ነው ፡፡

መልካም አስተዳደር ይኑር ይስፋፋም የሚሉ የመንግስት ሚዲያዎችም ይሁኑ ፕሮፓጋንዲስቶች ቃላቶችን ህዝብን ለማጭበርበር እየተጠቀሙበት ነው ፡፡ በቃላት ላይ ችግር የለም፡፡ በተግባር ግን መልካም አስተዳደር እውን ሊሆን አልቻለም፡፡ የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡ ሕገ መንግሥቱና የተለያዩ ሕጎች ተግባር ላይ የሚያውላቸው አጥተዋል፡፡ የሙስና ተጠርጣሪዎች ታሰሩ ቢባልም ፈጥረውታል የተባለው በደል ግን ሲስተካከል አይታይም፡፡ ይህ ችግር በእጅጉ አደገኛ ነው፡፡ ዜጋ አገሩን እንዲጠላና ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረገ ያለ ችግር ነው፡፡ 


#3 ምንሊክ ሳልሳዊ 
በአንድ አገር ላይ ሁለት አገር የለም ሃይለማርያም ደሳለኝ ስለ የትኛው አገር መግለጫ እንደሰጡን አሁንም አልገባንም::ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ የታዘብኩት ያየሁት የሰማሁት በሚል አበይት ብሎ ያለውን የሃገርቱን እውነታዎች በከፊት አስቀምጧል:: በርግጥ የተሸፋፈነ ቢሆንም ፍንጭ ግን አገሪቷ አደጋ ላይ እንዳለች ጋዜጣው መስክሯል:: እኛም ያየነውን የምናውቀውን ጤቅላይ ሚኒስትሩን እና ጋዜጣውን ይዘን ተንትነናል ::

የሃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ እና የሪፖርተር ጋዜጣ ግጭት
- የመንግስት የጥንቃቄ ጉድለት እና የፖለቲካ አጀንዳ ሃይማኖቶችን እየበረዘ ነው:;
- የኢኮኖምው ድቀት አገ

ሪቷን ወደማትወጣበት አደጋ ውስጥ የከተተ ሲሆን ከፍተኛ ስራ አጥነት ፈጥሯል::
- በወያኔ መንግስት የመወያየት የመነጋገር የመቀራረብ መንገዶች ስለተዘጉ ችግሮች እየበረከቱ ነው::

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የድርጅታቸው የበላይ አካሎች በሰጧቸው ኦረንቴሽን መሰረት አጥንተው ገብተው በሃገሪቱ የተከሰቱ የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄዎችን እና መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን በተለመደው አሸባሪ አክራሪ እና ጽንፈኛ በሚሉ ወያኔያዊ ቃላት ተጠቅመው ሲያስፈራሩ ... ይህን መሰል የመንግስት ማስፈራሪያ በህዝቦች መብት ላይ መስጠት በሃገሪቱ ያሉ ሃይማኖቶች ነጻነታቸውን መጋፋት ሲሆን ዋናው የችግሩ ፈጣሪ ወያኔ የፈጠረው የስልጣን ማስረዘሚያ የወንጀል ቃላቶች መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል :: ሃይማኖቶች በመርሃቸውም ይሁን በተግባራቸው አይጋጩም፡፡ ሁሉም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ችግሩ ያለው እምነት ላይ አይደለም፡፡ ችግሩ ያለው የዚህ ሃይማኖት ጠበቃና አለኝታ እኔ ብቻ ነኝ፣ አንተ ወይም ያኛው አይደለም በሚል ሃይማኖትን ተገን በማድረግ በሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ስለዚህ የችግሩ መንሴ የሆነው ወያኔ የሃይማኖቶ ጠበቃ በመምሰል በህገመንግስት ንግድ ውስጥ ተጀቡኖ እጁን ወደ ሃይማኖቶች በማስገባት ራሱን የሃይማኖት አለኝታ በማስመሰል ሃይማኖቶችን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋሉ የህዝብ ጥያቄዎች በአደባባይ መሰማት ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል::
የክርስትና፣ የእስልምናና የአይሁድ እምነቶች በጋራ በሚኖሩበት አገር ውስጥ፣ ጋብቻ ፈጽመውና ተፋቅረው መኖር የሚችሉ የተለያዩ የሃይማኖት እምነት ተከታዮች ያሉበት አገር አለን እያልን፣ የወያኔ መንግስት በፈጠረው የፕሮፓጋንዳ እና የከፋፍለህ ግዛ ድርጊት ተጋጨ፣ ጠንካራ የነበረን ሕዝብ ተፋጀ ወደሚል አሳፋሪ ታሪክ እየቀየርነው ነው፡፡ ወያኔ ለስልጣን ማስረዘሚያ ብሎ የተጤቀመበት ስልት ነገ ለቁጭት የሚዳርገን እና ወደማንወጣበት ውድቀት የሚከተን ሲሆን ታሪካችንን፣ ማንነታችንና ደኅንነታችንን ለአደጋ እያጋለጠ ነው::

የሃገሪቷ ኢኮኖሚ በወያኔ ባለስልታናት እና በብሄራዊ ጥቅም በታወሩ ምእራባውያን እንደሚወራል ሳዮን እጅግ በጣም እየተንኮታኮተ መሆኑ እሙን ነው::በመንግስት ካዝና ውስጥ ከባድ የሆነ የገንዘብ ችግር አለ:: የመንግስት ካዝና ባዶ ነው ቢባል የሚያስኬድበት ደረጃ ላይ ተኩኖ የሃገሪቷን በጀት ማጽደቅ እንደት እንደሚቻል ግራ እየገባን ነው:: በጀት ሲጸድቅ እንጂ ሲለቀቅ የማይታይባት ኢትዮጵያ አስደንጋጭ የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ውስጥ እየዳከረች ነው:: የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ብቻ ከጥቂት ነጋዴዎች እና ብሄርተኞች ጋር በሙስና ተጨማልቀው የሚሰሩት የአየር በአየር ንግድ የሃገሪቷ ኢኮኖሚ አይደለም የመንደር ኢኮኖሚ ሊባይ አይችልም::ክፍያ አፈጻጸም ላይ እንኳን ግለሰብ መንግሥትም እየተቸገረ ነው፡፡ የግል ባንኮች እየተዳከሙ ናቸው፡፡ የብድርና የውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት አለ፡፡ ግሽበትን ለመቆጣጠር የሚወሰደው ዕርምጃ የራሱን ችግር እየስከተለ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ፣ የውኃ መጥፋት፣ የኔትወርክ አለመኖር፣ በሁሉም ዘርፍ ችግር እያስከተለ ነው፡፡ ገንዘብ ማሸሽና መደበቅ እየታየ ነው፡፡ ሌባው ሲፈራ ባይገርምም፣ ንፁኃን ሲሸማቀቁና ብታሰርስ እያሉ በመፍራት ከቢዝነስ እንቅስቃሴ ሲቆጠቡ እየታየ ነው፡ ይህንን ወያንኤ አምኖ ሊቀበለው አይደለም ጭራሽ በጠላይ ሚኒስትር ደረጃ መካድ ተጀምሯል:: ከሕዝብ ብዛትና ከሚመረቁ ተማሪዎች አንፃር በቂ የሥራ ዕድል አልተፈጠረም፡፡ ሼል ለማግኘት ወደ ዓረብ አገሮች የሚደረገው ስደት በአስፈሪ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ ወደ ወንጀል እየተገባ ነው፡፡ ለባለ ገንዘብ ራስን ለሽያጭ ማቅረብ እየተስተዋለ ነው፡፡ ይህ ችግር ካልተፈታ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ያሰጋል፡፡ ልዩ ትኩረትና መፍትሔ ይደረግበት፡፡ የተራበ ሆድ አደገኛ ነውና፡፡

በወያኔ መንግስት የመወያየት የመነጋገር የመቀራረብ መንገዶች ስለተዘጉ ችግሮች እየበረከቱ ነው:: በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ችግሮች ኢትዮጵያዊያን ሊፈቱዋቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ በመንግሥትና በሕዝብ፣ በመንግሥትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ፣ በመንግሥትና በሲቪል ማኅበረሰቡ፣ በመንግሥትና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች መካከል መቀራረብ፣ መወያየትና መመካከር ስለሌለ በቀላሉ የሚፈቱ ችግሮች እየተባባሱ ናቸው፡፡ ችግሮችን ለመንግሥት ማቅረብ አልተቻለም፡፡ መንግሥትም የሕዝብን ችግርና ስሜት ማወቅ አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ቀላል ችግሮች እየተካበዱና ወደማያስፈልግ አቅጣጫ እየተሸጋገሩ ናቸው፡፡ መንግሥት በአስቸኳይ ቲንክ ታንክ ያቅድ፣ የጋራ መድረክ ይፍጠር፣ የሕዝብና የመንግሥት፣ የመንግሥትና የባለሙያዎችን ግንኙነት ያጠናክር፡፡ 

   ምንሊክ ሳልሳዊ

 

Oct 12, 2013

Africa vs ICC: Quotes on court before Kenya trial

By JASON STRAZIUSO and TOM ODULA
The Associated Press

FILE - In this Thursday, Jan. 3, 2008 file photo, a young girl cries as she is carried by a man and woman fleeing an area of wooden kiosks which was set on fire by supporters of Raila Odinga's party, the Orange Democratic Movement (ODM), during post-election violence in the Kibera slum area of Nairobi, Kenya. Kenya's foreign minister Amina Mohamed said at a news conference Wednesday, Oct. 9, 2013 that no sitting president in the world has had to appear before a court, a statement that comes as Kenya appears to be laying the groundwork to avoid having President Uhuru Kenyatta appear at the International Criminal Court next month. BEN CURTIS, FILE — AP Photo Read more here: http://www.adn.com/2013/10/10/3119796/africa-vs-icc-quotes-on-court.html#storylink=cpyFILE – In this Thursday, Jan. 3, 2008 file photo, a young girl cries as she is carried by a man and woman fleeing an area of wooden kiosks which was set on fire by supporters of Raila Odinga’s party, the Orange Democratic Movement (ODM), during post-election violence in the Kibera slum area of Nairobi, Kenya. Kenya’s foreign minister Amina Mohamed said at a news conference Wednesday, Oct. 9, 2013 that no sitting president in the world has had to appear before a court, a statement that comes as Kenya appears to be laying the groundwork to avoid having President Uhuru Kenyatta appear at the International Criminal Court next month.
BEN CURTIS, FILE — AP Photo
ADDIS ABABA, ETHIOPIA — Foreign ministers from around Africa on Friday meet at the African Union headquarters in Ethiopia to discuss Africa’s relationship with the International Criminal Court.
The meeting comes a month before Kenyan President Uhuru Kenyatta is scheduled to appear in The Hague, Netherlands court to answer charges of crimes against humanity for his alleged role in Kenya’s 2007-08 post-election violence that killed more than 1,000 people.
Kenya’s parliament, in a nonbinding resolution, voted last month to pull out of the treaty that created the ICC, amid indications Kenyatta may not show up in The Hague for his November court case. Kenya has petitioned the court for Kenyatta to appear by video link.
There is growing criticism inside Africa that the ICC has only prosecuted Africans. On Saturday African heads of state and government meet on the ICC issue. Below are different views on Africa’s relationship to the ICC and Kenyatta’s judicial dilemma.

— “Why should the Kenyan flag be dragged into the court? Kenyatta should not leave the country. If the president goes to the ICC it’s like the whole country is being prosecuted. … Kenyatta wants to go but his advisers are telling him not to go.” — James Gakuya, Kenyan member of parliament from Kenyatta’s political party.
— “Needless to say, the work and functioning of the ICC should not be beyond scrutiny and improvement. However, considerations of withdrawal risk grave consequences for civilians in Africa, who tend to bear the brunt of serious crimes committed in violation of international law.” — Statement by 130 African and international civil society organizations.
— “Instead of promoting justice and reconciliation and contributing to peace and stability, (the ICC) has degenerated into a political instrument targeting Africa and Africans. This is totally unacceptable and that is why Africa has been expressing its serious reservation against the ICC.” — Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, in his role as chairman of African Union, as told to the U.N. General Assembly last month.
— “He has cooperated fully with the court up until now. … Are the circumstances different? Absolutely. Totally. Completely different. Before he wasn’t the head of state of the republic. … It’s going to be the first time that a sitting head is brought before any court of any time, not just here but anywhere in the world.” — Kenyan Foreign Minister Amina Mohamed, speaking on Wednesday.
— “He won’t go.” David M. Crane, professor at Syracuse University College of Law, on whether Kenyatta will report to the ICC.
— “Whatever its merits as an institution of international law, the ICC is apparently tone deaf to growing public perception in Africa … that the tribunal has it out for Africans, given that all eight of its current investigations involve Africans. … Nevertheless, I doubt that President Kenyatta will blow off the ICC entirely; that would be overplaying his hand.” — J. Peter Pham, director of the Africa Center at the Atlantic Council.
— “This trial could well sound the death knell for the ICC. … Kenya is a fully functioning democracy, more than capable of prosecuting violators of its laws. Not only have no charges been brought against Kenyatta and Ruto in Kenya, they were recently elected in a free and fair election to run the country. That should be the only verdict that matters.” — Charles Stith, director of Boston University’s African Presidential Center, former U.S. ambassador to Tanzania.
— “Impunity for politically-motivated violence has been the norm in Kenya for far too long and, so far, the Kenyan authorities have failed to undertake any domestic accountability process to address the crimes committed during the post-election violence that rocked the country in late 2007 and early 2008.” Statement by No Peace Without Justice, a group promoting human rights and international justice.

MIGRANT BOAT SINKS 10 DEAD, EXCEPT 200IN

A ship carrying about 250 people capsized Friday off the coast of Sicily, according to the Maltese military and the Italian news agency ANSA.
The ship is believed to have been carrying migrants.
The incident occurred in international waters about 60 nautical miles south of Lampedusa, Italy, according to a posting on the Armed Forces of Malta Facebook page.
Malta's military Rescue Coordination Centre has assumed control of what it called a "major search and rescue incident," according to the Facebook posting.
According to the Maltese military, the ship was being followed by military chase planes and "appeared unstable."
"A few minutes later, the aircraft reported that the boat had capsized and that numerous persons were in the water. Initial assistance was provided by the aircraft, which dropped a life raft in close proximity of the persons in distress," according to the Facebook posting.
The fate of those aboard the capsized ship was not immediately clear.
It is the second such incident this month in the region.
Earlier this week, a boat carrying more than 500 African migrants sank off the coast of Lampedusa, killing 309 people in what Lampedusa Mayor Giusi Nicolini called "the biggest sea tragedy in the Mediterranean Sea since World War II."
That ship originated in Libya, caught fire off the Italian coast and sank.
Survivors, many of them from Eritrea, told CNN they used bodies to keep themselves afloat until they were rescued.
The incident sparked calls for efforts to reform migration policies in the region.
A week ago Friday, the United Nations' human rights office urged the European Union to work to prevent another such incident.
The agency called on authorities to work to reduce migrant trafficking and address economic and security issues that have driven thousands of African residents to make the risky voyage to Europe in search of a better life.

MIGRANT BOAT SINKS 10 DEAD, EXCEPT 200IN
In the Strait of Sicily, a boat full of migrants sank. On board were about 250 people. At least a dozen dead, as confirmation that the Navy with ships and helicopters took part in the rescue. The survivors rescued so far are 200, about 150soccorsi by Maltese vessels and about 50 from Italian means, including ten children.
The tragedy occurred in Maltese waters, on the border with Libya, 70 miles from Lampedusa, where a week ago died 339 refugees.

አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ !!!

ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።
ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በመገናኛ ብዙኋን ፊት ያየዉን አላየሁም፤ የሰማዉን አልሰማሁም፤ ያልሆነዉን ሆነ የሆነዉን ደግሞ አልሆነም እያለ ሽምጥጥ አደርጎ የካደዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ በእርግጥም ጎበዝ የመለስ ዜናዊ ተማሪ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ኃይለማሪያም ባለፈዉ ዓርብ አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ይህ ግለሰብ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር ከሚመራ ሰዉ ቀርቶ ከአንድ ተራ የቢሮ ተላላኪ እንኳን የማይጠበቅ መልስ ሲመልስ ተስተዉሏል።
ኃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት ከቀረቡለት ብዙ ዲሪቶ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ አገር ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ሠላማዊ ሰልፍ ጉዳይ ነበር። ኃይለማሪያም አገር ቤት የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች “በራሳቸው የሚደረጉ ሳይሆኑ ከኋላ ባሉ ሌሎች ኃይሎች መሪነት የሚደረጉ” ናቸው ሲል ተናግሯል። ኃይለማሪያም ጌቶቹ ፊቱን በጨርቅ አስረዉት የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር፤ መከራና ስደት አልታይ ብሎት ነዉ አንጂ ወያኔን የመሰለ ነብሰ ገዳይ ባለበት አገር ዉስጥ የህዝብን ብሶት የሚያስጋቡ ጥያቄዎች በየቀኑ ይመነጫሉ አንጂ ከዉጭ አገርማ አይመጡም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄዉ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያፈራቸዉ ዋሾ ሰዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉት ሠላማዊ እንቅስቃሴ የአሸባሪዎች እጅ ያለበትና፤አማኞቹ ሃይማኖታቸውን የወደዱ መስሏቸው ሳያውቁ የገቡበት ስለሆነ እንዲታረሙ እንመክራቸዋለንም” ብሏል። እዚህ ላይ በግልጽ እንደምናየዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እመራዋለሁ የሚለዉን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ፈጽሞ ሊረዳ አልቸለም፤ ስለዚህ ምክር የሚያስፈልገዉ መብትና ነጻነት ምን እንደሆኑ ገብቶት የሚታገለዉ የአትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ኃይለማሪያም እራሱ ነዉ።
እኛ ግንቦት ሰባቶች ወያኔን የመሰለ ጨካኝ እና ምንም አይነት አገራዊ ኃላፊነት የማይሰማውን ዘራፊና ዘረኛ ቡድን በሠላማዊ መንገድ የሚጋፈጡ ወገኖቻችንን እናደንቃለን። እነዚህ ወገኖቻችን ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንደሚለው የማንንም አጀንዳ የተሸከሙ ሳይሆኑ የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ያላቸውና ኃይለማሪያም በዉክልና ለሚያስረግጣቸዉ ወገኖቻችዉ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ጅግኖች ናቸዉ። አጀንዳቸውም የተደበቀ ወይም ከጀርባውም ሌላ ነገር ያለው አጀንዳ አይደለም።አጀንዳቸው ግልጽ እና የታወቀ የነፃነት፤ የእኩልነት፤የፍትህና የሠላም አጀንዳ ነው። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የዜጎችን ጥያቄ አድምጦ መልስ መስጠት ሲገባው እነዚህን የኢትዮጵያን ህዝብ አጀንዳ ተሸክመው የሚታገሉ ወገኖች ደካሞች አድርጎ ለመሳል የሚያደርገዉ ሙከራ አንድም በተቃዋሚዎቹ ዙሪያ የተሰባሰበውን የሰው ኃይል ካለማወቅ፤ አለዚያም ደግሞ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” እንደሚባለው ነገር ነው።
ሌላው ኃይለማሪያም የሚናገረዉ ቃል ጠፍቶት በተደጋጋሚ ሲንተባተብ የታየዉ በሽብርተኝነት አካባቢ የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመለሾ ነዉ። በእኛ እይታ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋነኛው አገር በቀል አሸባሪ ህወሃት እና ህውሃት ብቻ ነው። ህወሃት ስልጣን ላይ ያቆየኛል ብሎ ከገመተ የማይመሰርተው የክስ ዓይነት፤ የማያፈሰው የንጹህ ሰው ደም ፤የማያፈነዳው የቦንብ እና የፈንጂ ዓይነት እንደሌለ ከሃውዜን እስከ አዲስ አበባ ያሉ መንገዶች ቋሚ ምስክሮች ናቸው። ይህንን እኩይ ተግባሩን ዓለም ሁሉ እንደሚያውቀው በዊክ-ሊክ ላይ የወጣው መረጃም አሳይቷል።
የህውሃት ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሠላማዊ ትግሉን ለማፈን ከፈለገ በትግሉ ዙሪያ የተሰባሰቡትን ዜጎች ከሌላ ከማንም ጋር ማነካካት አያስፈልገውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሁሉ አንደ ኃይለማሪያም ሞቶ የተቀበረን ሰዉ ራዕይ የተሸከሙ የአመለካከት ደሃዎች ሳይሆኑ የራሳቸው አስተሳሰብና ህያዉ ራዕይ ያላቸው ዜጎች ናቸው። አነዚህን ሠላማዊ ታጋዮች ከማይገናኝ ሌላ ኃይል ጋር አቆራኝቶ ለመምታት መሞከር ለኃይለማሪያምም ሆነ ለጌቶቹ አይበጃቸዉም። ዛሬ በወያኔ ነብሰ ገዳይ ወታደሮች ተከብቦ እዩኝ እዩኝ የሚለዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝም የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ የነደደ ቀን ደብቁኝ ማለት ይመጣልና ያ ቀን ከመምጣቱ በፊት የበደለዉን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ የነጻነት ኃይሎችን እንዲቀላቀል ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳለን።
በመጨረሻም ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሾለ ግንቦት ሰባት ተጠይቆ ሲመልስ ግንቦት ሰባት “በህልም ውስጥ ያለ ድርጅት” ነው ብሏል። ታድያ ምነዉ ተኝቶ ህልም የሚያልም ድርጅት ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል? ለምንስ ይሆን ወያኔና ታማኝ ሎሌዉ ኃ/ማሪያም ያገኙትን ሁሉ ግንቦት ሰባት እያሉ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት? ያገኛችሁትን ሁሉ የግንቦት ሰባት አባል እያላችሁ ትከሳላችሁ? ለምንስ በግንቦት ሰባት ስም ታስራላችሁ? ትገርፋላችሁ? ትገድላላችሁ? ተኝቶ ለሚያንቀላፋ ድርጅት ለምን ትሸበራላችሁ፤ ለምንስ እንቅልፍ አጥታችሁ ትባዝናላችሁ? ግንቦት ሰባት እናንተ አልገባችሁም አንጂ መነሻውንና መድረሻውን አጥርቶ የሚያውቅ፤ ከደመናው ባሻገር ፍንትው ያለ የነፃነት ዉጋገን የሚታየው ባለ ታላቅ ራዕይ ድርጅት ነው። አስኪ ምናልባት ቢገባችሁ ተረት ቢጤ እንንገራችሁ፤
“አንዲት ሚዳቋ ነበርች አሉ። ሚዳቆ ከመሬት ገንዘብ ተበድራ ሲትኖር ከእለታት አንድ ቀን መሬት አፍ አውጥታ ብድሬን መልሽ አንጂ ብላ ትጠይቃታለች። ሚዳቆዋም ደንግጣ ከነበረችበት ቦታ ፈትለክ ብላ ወደ ተራራ ጫፍ ላይ ወጥታ እፎይ ያንን ድምጽ ከአሁን በኋላ አልሰማም አለች። መሬትም በይ ብሬን ክፈይኝ ስትል ዳግም ጠየቀቻት። እንዴ ይህች መሬት የሌለችበት ዬት አገር ሊሂድ ብላ ሚዳቆ ወደ ማይታወቅ ቦታ ተፈተለከች። ከዚያም እያለከለከች በቃ አሁንስ አታገኚኝም ስትል አሁንም መሬት ብቅ ብላ እየጠበኩሽ ነውኮ ብድሬን ክፈይ እንጂ ስትል ጠንከር አድርጋ ጠየቀቻት። ሚዳቆዋም መሬት የሌለችበት ልትደረስ ስትበር ስትበር ሳንባዋ ፈንድቶ ሞተች”ይባላል።
የፍትህ፤ የእኩልነት፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እንደ መሬት ናቸው። የትም ሂዱ፤ የትም ግቡ ይከተሏችኋል። መስጊድ ዉስጥ አሉ፤ ቤተክርስትያናት ውስጥ አሉ። ቤተመንግሰት ዉስጥም አሉ። የሌሉበት ቦታ የለም። መፍትሄው እንደ ሚዳቆዋ መሸሽ አይደለም። መፍትሄው ዜጎች የሚያነሷቸውን የፍትህ፤ የእኩልነ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን አድምጦ ትክክለኛ መልስ መስጠትና ከዕዳ ነጻ መሆን ብቻ ነዉ ። ከዚህ ዉጭ ጥያቄን ላለመስማት ወይም ሰምቶ ለመደፍጠጥ የሚደረገው ከንቱ ሩጫ መጨረሻው እንደ ሚዳቆዋ መፈንዳት እንጂ ህይወት አይሆንላችሁም።
እኛ ግንቦት ሰባቶች ዘረኛዉንና አሸባሪውንና የወያኔ ስርዐት ለመደምሰስና ህዝብ በነፃነት ያለፍርሃት የሚኖርበትን አገር ለመፍጠር ቆርጠን ተነስተናል። ከእንግዲህ የሚያቆመን ምንም ነገር የለም። የምንታገለዉ ለህዝብ ጥያቄያችንም ህዝባዊ ጥያቄ ነዉና እኛም አንደጥያቄዉ በየመስጊዱ፤ በየቤተክርሲቲያኑና በየሰፈሩ ዉስጥ አለን።እኛ የሌለንበት ስፍራ የለም። በዚህ አጋጣሚ የዘመናት ትግላችን ፍሬዉ የሚታይበት ቀን እጅግ በጣም ቅርብ ነዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አገር ተረካቢ የሆነዉ ወጣቱ ትዉልድ እራሱን፤ ወገኖቹንና እናት አገሩን ለማዳን የሚደረገዉን የነጻነት ትግል እየመጣ እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪያችንን አቅርበናል። ኑ እና ተቀላቀሉን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Total Pageviews

Translate