Nov 30, 2012
Nov 29, 2012
ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት የ816 ሚሊዮን ብር የልማት ድጋፍ አገኘች
ኢሳት ዜና:-የድጋፍ ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ሱፊያን አህመድና የአውሮፓ ኅብረት የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተርና የአፍሪካ ካሪቢያን ፓስፊክ አስተባባሪ ፍራንሲስካ ሞስካ ናቸው።
ድጋፉ የወጪ ምርቶችና በተመረጡ ኢንቨስትመንት መስኮች በቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፣ ጨርቃጨርቅ ፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያና መድኃኒት ፋብሪካዎችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ፣ በልምድና ክህሎት እንዲሁም የገበያ ልማትን በማጠናከር ተወዳዳሪነታቸውን ለማጠናከር እንዲሁም በቢዝነስ ፣በሥራ አመራርና በፈጠራ ሥራ ለግሉ ዘርፍና ለመንግሥት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ-አውሮፓ የቢዝነስ ትምህርት ቤት ለመክፈት ይውላል ተብሎአል።
ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ በስልጠና ላይ አሉ በሺ የሚቆጠሩ የወጣት ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ስራ ይጀምራሉ።
በአየር መንገድ ውስጥ በጉልበት ስራ ላይ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሰራተኞች በኢህዴግ ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ሊተኩ ነው

ኢህአዴግ በወሰደው እርምጃ ያዘኑ ሰራተኞች እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም በሚል ከስራ መባረራቸው ህገመንግስቱን የሚጥስ ብቻ ሳይሆን ሳንወድ በግድ ለእንጀራ ብለን ኢህአዴግን እንድንደግፍ የሚያደርግ ነው።
ኢህአዴግ በቀጣዩ የወረዳና የከተማ ምርጫ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ያስችለው ዘንድ የወጣት ፎረም አባላትን በጊዜያዊ ስራ እየሸነገለ ነው በማለት ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ወቀሳ ያቀርባሉ።
በተያያዘ ዜናም ኢህአዴግ አንዳንድ አባላቱን ከድርጅት አባልነት ያስወጣ በማስመሰል በወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስመራጮች አድርጎ ሊያሾም መሆኑን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
በይፋ የማይታወቁ የድርጅቱ አባላት በገለልተኛ ስም በምርጫ አስፈጻሚነት ለማወዳደርና ለማሰራት መታቀዱን ነው ለማወቅ የተቻለው።
ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ የሀርቡ አካባቢ ሙስሊም ነዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የቀረበላቸውን የሰልፍ ጥሪ ባለመቀበል አንወጣም ማለታቸው ተገለጸ። ባለስልጣናቱ ተማሪዎቹን ከትምህርት ቤት በማስወጣት ሰልፍ እንዲያደርጉ ማድረጋቸውም ተዘግቧል።
በመንግስት በተጠራ ሰልፍ የሀርቡ ህዝብ ሳይገኝ ቀረ
ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ የሀርቡ አካባቢ ሙስሊም ነዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የቀረበላቸውን የሰልፍ ጥሪ ባለመቀበል አንወጣም ማለታቸው ተገለጸ።
ባለስልጣናቱ ተማሪዎቹን ከትምህርት ቤት በማስወጣት ሰልፍ እንዲያደርጉ ማድረጋቸውም ተዘግቧል።
በገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የቀረበው የሰልፍ ጥሪ ያልተገኘ ነዋሪ 50 ብር እንደሚቀጣ ቢገለጽም ህዝቡ ለማስጠንቀቂያው ቦታ ባለመስጠት በሰልፉ ሳይገኝ ቀርቷል።
ከሬዲዮ ቢላል ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው የፌደራል ፖሊሶችና ያካባቢው ባለስልጣናት በየቤቱ እየዞሩ ለሰልፍ ውጡ በማለት ሲያስገድዱ የነበረ ቢኋንም አብዛኛው ሙስሊም አሻፈረኝ ሲል እምቢ ብሎል።
የሰልፉ አላማ በግልጽ አልተገለጸም ያለው የሬዲዮ ቢላል ዘገባ ሙስሊም ያልሆኒ የአካባቢው ባለስልጣናት ከትምህርት ቤት ይዘዋቸው ለሄዱት ህጻናት ሰልፈኞች አሸባሪነትን እንቃወማለን ፣ አካባቢያችን ሀርቡ ሰላም ናት የሚል መፈክሮችን እያሰሙ እንዲቀበሏቸው ሲሞክሩ እንደነበር ገልጾል።
በቀጥታ ከትምህርት ቤት ወደ ሰልፍ እንዲወጡ የተደረጉት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት.ቤት ተማሪዎች አብዛኞቹ በገዢው ፓርቲ አባላት ሰዎች የሚነገረውን መፈክር ተቀብለው እንዳላስተጋቡም ከዘገባው መረዳት ተችሎል።
በሰልፉ ላይ የአካባቢው መኪኖች ሰልፉን እንዲያጅቡ ታዘው እንደነበር ያመለከተው ዘገባ አናደርገውም ብለው ሳይገኙ መቅረታቸውን ገልጾል።
ሞረሽ ወገኔ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት የማፍረስ እቅድ ተቃወመ
ኢሳት ዜና:-ሞረሽ ወገኔ የአማራው ድርጅት የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልትን ለማፍረስ መንግስት ማቀዱ የአማራው ታሪክን ለማጥፋት የተያያዘው እርምጃ አካል በመሆኑ እናወግዘዋለን ሲል አስታወቀ።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንን የመንግስት እቅድ በመቃወም ድምጹን እንዲያሰማ ሞረሽ ወገኔ ጥሪ አቅርቧል።
ሞረሽ ወገኔ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የአማራው ህዝብ ላይ የማጽዳት እርምጃ ሲወስድ የቆየው ገዥው ፓርቲ ታሪኩንም ሲያጠፋ ቆይቷል ካለ በኋላ የአባቷቻችን የክብር አጽም ያረፈበትን ቦታ አፈረሰ፣ የዋልድባ ገዳምን አረሰ፣ የዝቋላ አቦን አቃጠለ ሲል በአብነት ዘርዝሮል በመግለጫው።
የአማራ ህዝብና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርገው ታሪክና ቅርስ የማጥፋት እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሎል ያለው ሞረሽ ወገኔ የአማራው ድርጅት የአቡና ጴጥሮስ ሀውልት ሳይፈርስ በአንድነት ተነስቶ ቁጣውንና አሻፈረኝ ባይነቱን ሊያሳይ ይገባል በማለት በመግለጫው አሳስቧል።
ድርጊቱን ለኢትዮጵያ ታሪክና አንድነት ተጠብቆ መዝለቅ ጽኑ አላማ ያላቸው ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተው የአቡኑን ሀውልት ለማፍረስ የታቀደውን እቅድ እንዲቃወሙ ጥሪውን አስተላልፏል።
ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ በስልጠና ላይ አሉ በሺ የሚቆጠሩ የወጣት ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ስራ ይጀምራሉ።
በአየር መንገድ ውስጥ በጉልበት ስራ ላይ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሰራተኞች በኢህዴግ ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ሊተኩ ነው
ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ በስልጠና ላይ አሉ በሺ የሚቆጠሩ የወጣት ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ስራ ይጀምራሉ።
ኢህአዴግ በወሰደው እርምጃ ያዘኑ ሰራተኞች እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም በሚል ከስራ መባረራቸው ህገመንግስቱን የሚጥስ ብቻ ሳይሆን ሳንወድ በግድ ለእንጀራ ብለን ኢህአዴግን እንድንደግፍ የሚያደርግ ነው።
ኢህአዴግ በቀጣዩ የወረዳና የከተማ ምርጫ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ያስችለው ዘንድ የወጣት ፎረም አባላትን በጊዜያዊ ስራ እየሸነገለ ነው በማለት ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ወቀሳ ያቀርባሉ።
በተያያዘ ዜናም ኢህአዴግ አንዳንድ አባላቱን ከድርጅት አባልነት ያስወጣ በማስመሰል በወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስመራጮች አድርጎ ሊያሾም መሆኑን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
በይፋ የማይታወቁ የድርጅቱ አባላት በገለልተኛ ስም በምርጫ አስፈጻሚነት ለማወዳደርና ለማሰራት መታቀዱን ነው ለማወቅ የተቻለው።
ጥንቃቄ
ይህ ነው ወንድማማችነት ምንም ቢሆን ክርስትያን ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችህ ከጎናችሁ ነን ምናልባት ነገ የመጀመሪያ ተግባሮቻችን እንጀምራለን ሁላችንም ሙስልም ወንድሞቻችን እን እህቶቻችን በፀሎት እናስባቸው ለሁሉም እንደሚፀለይ ፈጣሪ በቅዱስ ቃሉ ያዛልና
ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!
አቶ ሃይለማም ሲፈሩሲተቡ ቆይተው ዛሬ የካቢኔ ሹመት ለማደረግ ፓርላማ ብቅ ብለው ነበር አሉ። ይዘዋቸው ከመጡዋቸው ካቢኔዎቻቸውመካከል ሌላ ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ይገኙበታል።
አቶ ሃይለማሪያም ሲያስቡት ሲያስቡት ለአቶ ደመቀ ብቻ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መስጠት አይችሉትም ብለው ሰጉ መሰለኝ…(መሰለኝ ነው ያልኩት) ዛሬ አቶ ሙክታር ከድር እና አቶ ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤልን ደጋፊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው አሹመዋል። በጥቅሉ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አሏተው።
እኛ ከላይ ከላይ የምናየው የመንግስታችን አድናቂዎች “እሰይ ሀገራችን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እድገት እመርታ አሳየች” ብለን ካገኘን ፅዋ ካን ደግሞ ግንባራችንን እያጋጨን ደስታችንን ገልፀናል።
የምር ግን አቶ ሃይለማሪያም ያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሰሩ የነበረ ጊዜ እንደው ሰውየው መለስ ሆነውባቸው “ተሸከሙ” ያሏቸውን ሁሉ “እሺ ጌታዬ” ይሏቸው ነበር እንጂ፤ የጫኑባቸው ሸክም በእጅጉ ከብዷቸው ነበር ማለት ነው!? አዎና ይኸው አቶ ደመቀ ሸክሙን አይችሉትም ብለው የጠረጠሯቸው ከራሳቸው ልምድ ተነስተው አይመስልዎትም!?
ሌላው ጥርጣሬ የኢህአዴግ “ፈላጭ ቆራጮች” (ይሄ “ፈላጭ ቆራጭ” የሚለው ቃል ኢህአዴግ ይፈልጣል ይቆርጣል ብሎ ለማሽሟጠጥ ታስቦ የገባ ቃል አለመሆኑን በቅንፍ አሰውቀን እንቀጥል) እና የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጮች አቶ ሃይለማሪያምን ለአንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ አምነው መተው ምቾት አልተሰማቸውም ይሆናል!
ለማንኛውም ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖምን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተሩ ከጤና ጥበቃ የተነሱት ጤና ስለነሱ ይሁን ወይስ የውጭ ጉዳዩ ስራ ህክምና ስለሚያስፈልገው አልታወቀም። ሲታወቅ እናወጋዋለን!
Nov 28, 2012
Nov 27, 2012
በራስ አሉላ አባነጋ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ዜናዊ ተቀየረ
በራስ አሉላ አባነጋ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ዜናዊ ተቀየረ
(ከእየሩሳሌም አርአያ)
በትግራይ ተምቤን - አቢይ አዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ
የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን
ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።
በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ
ሲያስተምር ከቆየ በኋላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ
መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች
ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው
ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን
ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ
ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።
ከምረቃው ጋር በተያያዘ የራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰርዞ “መለስ ዜናዊ ሁለተኛ ደረጃ
ት/ቤት” ተብሎ መሰየሙን ባለስልጣናቱ በይፋ እንደገለጹ ምንጮች አረጋግጠዋል። በት/ቤቱ
በይፋ የመለስ ስም ተፅፎ መለጠፉ ተጠቁሞዋል። በህዝብ ገንዘብ መዋጮ የተገነባን ት/ቤት
በጡንቻና በማን አለብኝነት ህዝብን በመናቅ የተፈጸመ ተግባር ነው ሲሉ የአካባቢው
ተወላጆች ማውገዛቸው ታውቁዋል።
በተለይ በአውስትራሊያ፡ ጀርመን፡ ኖርዌይ፡ አሜሪካ፡ ካናዳና… ሌሎች አገራት የሚኖሩ
የአካባቢው ተወላጆች ባካሄዱት ቴሌ ኮንፈረንስ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል። ተሳታፊዎቹ እንዳሉት « የአፄ
ምንሊክን፡ የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ለማፍረስ የተጀመረው አፍራሽ እንቅስቃሴ ወደ ራስ አሉላ ተሻግሮዋል። ይህ
የሚያመለክተው የቆየውን የኢትዮጲያን ታሪክ ለማጥፋት ቆርጠው መነሳታቸውን ነው። ይህ ትውልድ ታሪኩን አስጠብቆ የማቆየትና
የተጀመረው አደገኛ አፍራሽ እንቅስቃሴ ከማውገዝ ባለፈ ለትግል መነሳሳት አለበት።ኢትዮጲያዊያን እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፤»
ብለዋል። አክለውም « የኢትዮጲያዊነት ጉልህ መታወቂያና መገለጫ የሆኑ አኩሪ ታሪኰችንና ታሪክ ሰሪ ጀግኖችን ለማጥፋት ኤርትራዊው
ቴውድሮስ ሃጎስ፡ በረከት ስሞንና ስብሃት ነጋ የሚመሩት አካል በአገራችን ላይ የጥፋት ዘመቻ ከፍተዋል» ሲሉ አንድ ተሳታፊ ተናግረዋል።
« የዶጋሊ ዘመቻ » በሚል በየአመቱ ራስ አሉላ የሚዘከሩበት ታሪካዊ ቀን እንደነበረና ሕወሓት ወደ ስልጣን ከመጣ በሑዋላ ግን ይህ
እንዲቀር መደረጉን እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ።
በሌላም በኩል በመቀሌ ከተማ ፒያሳ አካባቢ የአፄ ዮሃንስን መታሰቢያ ሃውልት ለማቆም ተጀምሮ የነበረው እንቀስቃሴ እንዲቆም
መደረጉን የቅርብ ምንጮች አጋልጠዋል። ባለፈው አመት ከህዝብ በተዋጣ ገንዘብ ሓውልቱን ለማቆም የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ እንደነበር
ጠቁመው፤ በኋላ ግን “የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ስለተቃወሙ ሃውልቱን መስራት አይቻልም» በማለት እነ ቴውድሮስ ሃጎስ
መወሰናቸውን ምንጮቹ ገልፀው፦ “አሳፋሪና ተቀባይነት የሌለው ተራ ምክንያት» ሲሉ ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች
አጣጥለውታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአድዋ ከተማ አደባባይ ላይ ተሰቅሎ የነበረ የመለስ ፖስተር ተቀዳዶ መጣሉን ምንጮች ጠቆሙ። የክልሉ ካድሬዎች
«የመድረክ ተለጣፊ የሆነው አረና ፓርቲ ነው ይህን የፈፀመው » በማለት ያልተጨበጠ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩና እየዛቱ ነው ያሉት
ምንጮች አክለውም ድርጊቱን የፈፀመው የአካባቢው ህዝብ እንጂ የትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ አይደለም ብለዋል።
የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ እና አገራዊ ፋይዳው፤ አጭር ቁዘማ (ስደተኛው መስፍን ነጋሽ፤ ከአገረ ስዊድን) ላለፉት ሰባት ወራት በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ምህዳር (public sphere) ሳይበርዱ ከሰነበቱት ርእሰ ጉዳዮች አንዱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ እና መንግሥት ለጥያቄው የሰጠው ትርጉምና ምላሽ ይገኝበታል። ነገሩ ሰሞኑን ተካሮ ሰንብቷል። የመነጋገሪያ አጀንዳነቱም እንዲሁ በጣም ጨምሯል። በዚህ ንግግር ውስጥ በስሕተትም በእቅድም እየተምታቱ የሚቀርቡ ጉዳዮች መኖራቸውን ብዙዎች ያስተውሉታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ሆኖም ጉዳዮቹን ነቅሶ ማውጣቱ ለውይይት ብቻ ሳይሆን አቋምን ለመፈተሽም ይረዳል በሚል እምነት ነገሩን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ። ነገሩ ብዙ ጉዳዮችን የሚያሰናስል እንደመሆኑ ቁዘማዬም (reflection) ጥቂት ረዝሞ ልታገኙት ትችላላችሁ። ትእግስታችሁን እማጸናለሁ። በዚህ ጽሑፍ የኢትዮጵያውን ሙስሊሞች ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄዎች በሁለት ምክንያቶች በሌላውም ኢትዮጵያዊ መደገፍ አለባቸው እላለሁ። ሕጋዊ ጥያቄዎቹ ”ከአክራሪነት/ሽብርተኝነት” ጋራ ተደባልቀውና ተምታተው እየቀረቡ ችላ መባልም ሆነ መረገጥ አይገባቸውም ስል እከራከራለሁ። I am at Awelia because injustice is there!
ከሁሉ በፊት የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2005 የአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤
ይድረስ ለእስልምናና ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች
ይሄይስ አእምሮ(yiheyisaemro@gmail.com)
ከሁሉ በፊት የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2005 የአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤
ኢሣት ኢትዮጵያ ውስጥ በመዘጋቱ ምክንያት ስንት ነገር አምልጦኛል ለካንስ እባካችሁ? ይህችነን ማስታወሻ ለመጻፍ አስቤ ብዕሬን ከወረቀት ላዋድድ ስል ከዜናና ከዜና ትንታኔው በኋላ ትቼው የተለየሁትን ይህን የኢትዮጵያ የወቅቱ ብቸኛ መተንፈሻ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተመልሼ እንድከታተል ባለቤቴ ስትጠራኝ “ተይኝ ባክሽ ሌላ ሥራ አለብኝ” ብላት ስሜቴን ስለምታውቅ “ታማኝ መጣልህ!” አለችኝና የመከታተል ወይ ያለመከታተል ምርጫውን ለኔው ትታ ወደሥራዋ ገባች፡፡ በዚህ ረገድ በደንብ ታውቀኛለችና እንድመለስ ሌላ ቃል አልጨመረችም፡፡ በዚህች አባባል ሌሎች በመንፈስ እንጂ በሥጋ እንዳትቀኑ አደራችሁን – “ወላድ በድባብ ትሂድ! የታማኝ እናት ደጋግመሽ ውለጂ! ቢስ አይይብን፡፡ የልጅ ዐዋቂ ነህና ከዐይን ይጠብቅህ፡፡” አሜን በል ወንድማለም፡፡ ከአሜን ይቀራል አሉ፡፡
ታማኝ – ወይ ጉድ ስም ይቀድሞ ለነገር አሉ – በኦነግና በግንቦት ሰባት ጥምረት በተደረገ ስብሰባ ተገኝቶ ያደረገውን ንግግርና ስብከተ ሀገር ነበር ኢሣቶች እያቀረቡ የነበረው – የቆዬ ዝግጅት ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ የምንኖር ዘጎች ከተናጋሪ እንስሳነት እምብዝም የማንለይ – ኧረ እንዲያውም እነሱ ከእኛ የሚሻሉበት ብዙ ነገር አላቸው – በመሆናችን ሁሉም የዜና ማዕከላት ተጠርቅመው የወያኔን ቅርሻት ብቻ እንድንሰማና እንድናይ ስለተፈረደብን በወቅቱ አላየሁትም፡፡ አሁን ግን ዕድሜ ለዲያስፖራው የኢትዮጵያ ሕዝብ – በኢሣት ጥረት የተደበቁ ዜናዎችንና መረጃዎችን መከታተል ጀምረናል፡፡ ይህ የዜና ተቋም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁለንተናዊ አቅም ያላችሁ ዜጎች እባካችሁን አንድነታችሁንና ኃይላችሁን አስተባብራችሁ ታገሉ፤ ሁሉም ያልፋል፡፡ የማያልፈው ግን አጥርን ዘልሎ የሚሻገር የመልካም ወይም የክፉ ሥራ ውጤት ነው፡፡ የዚህ የተገፋ ሕዝብ የየጨለመ የመኖር ተስፋ ብታለመልሙ ፈጣሪ ወሮታውን ይከፍላችኋል፡፡ የአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ጉዞ የሚጀመረው በአንድ ሜትር ነውና አንዳንድ ጨለምተኞች “ወሬ ምን ዋጋ አለው! በወሬ ሆድ አይሞላም…” ቢሉም ብዙም ጆሮ አንስጣቸው፡፡ መጽሐፉ “እስመበተስፋሁ ሀደረት ሥጋየ” ይላልና የነጻነታችን ፋናወጊ የመረጃ ምንጭ የሆነውን ኢሣትን በየአቅማችን እንርዳ – እርግጥ ነው ድረ ገፆቻችንንም ሳንዘነጋ፡፡ ምርጫም የለንም፡፡ ምርጫ ከተባለም ያለን ሌላውና ብቸኛው ምርጫ በቦሌም በባሌም ብለን ባከማቸነው ገንዘብ የተንደላቀቀ ኑሮ እየመራን እንደከብት እያመነዠክን እንደዓሣም ያገኘነውን መጠጥ እየማግን መኖር ነው፡፡ ይህ ደግሞ እንስሳነት ነው፡፡ ይህ ከጤናማ ሰውነት የወረደ ወያኔያዊ ባሕርይ ለታሪክ ፍርድ አመቻችቶ ይተወናል፤ ለኋላ ፀፀትም ይዳርገናል – ‹ኋላ› ለሚባል ነገር ለምንደርስ፡፡ አንዳንዴ ‹ፊተኛ›ን ብቻ ለሚያውቅ ግብዝ ፍጡር ‹ኋለኛ› የሚባል ነገር ስለመኖሩም አይገባውም፤ ሁለቱንም ኑባሬያት በነቢባዊና ተግባራዊ አንድምታቸው የሚያውቅ ሰው የተረጋጋና ለየትኛውም መቼት የሚያበቃ ሕይወትን መርቶ በፊተኛውም በኋለኛውም የመኖርና ያለመኖር የሕይወት ቅምብቦች ውስጥ ዘወትር እየተወደሰና በሠናይ ምግባሩ እንደ አብነት እየተወሳ ዘመድ አዝማድንና ሀገርን አኩርቶ እስመለዓለመ ዓለም ይኖራል፡፡ (ታማኝ በርቺ – ጀምረሻል – እንዳትንሸራተች የኢትዮጵያን አምላክ ጠበቅ አድርገሽ ያዢ!! በተንሸራታች ፋብሪካ ሀገር ጥንቃቄና ምርመራ ውስጠት ዘወትር ካልታከለ ችግር ማስከተሉ አይቀርምና ራስን በየወቅቱ መፈተሽ፣ ራስን ብቻ ሳይሆን ግራ ቀኝን – ባላንጣን ጭምር ማዳመጥ ይገባል፤ ትምክህትን በፈጣሪና በምስኪን ሕዝብ ያደረገ ወድቆ አይወድቅም፡፡ ብዙዎች የአሁን ኢትዮጵያውን ደግሞ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ፍጡራን መሆናችንን ለማወቅ ይህች ጦማር በአንዱ ድረገጽ እስክትለጠፍ መጠበቅ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ መንጌ ምን አለ? ‹ሀገሬን ለሰው አልሰጥም አለ› ብለህ እንዳትቀልድብኝ፤ ከርሱ ቀጥሎ ያለው ቁም ነገር አለ … ወርቅ ቢያነጥፉለት … ችግሩ እነሱ እንደሚሉን እየሆንላቸው የተግባራቸው ብቻም ሳይሆን ለትንቢቶቻቸውና ለዕብሪት ንግግሮቻቸው እውናዊነትና ተፈጻሚነት አጋር መሆናችን ነው፡፡ ለሁሉም ግን ተስፋ መቁረጥን ራሱን ተስፋ እናስቆርጠውና ለእውነት ልዕልና ቆርጠን እንነሳ … የቀረበው የነጻነት ቀን ልደት በምንም መንገድ አይጨነግፍም የሚል ጽኑ እምነት አለኝ… ግን ጽንሱ ከታሪክ ማኅጸን በቅጡ እንዲወጣ ልምድና ዕውቀት ያላቸውን አዋላጆች ከዬአህጉሩ እየፈለግን በማሰባሰብ እንደስካሁኑ መደዴና ስድ አደግ ሁሉ እጁን ሳይታጠብና በቂ ችሎታ ሳይኖረው ማዋለጃ ክፍል ውስጥ እየገባ ችግር ከመፍጠሩ በፊት እውነተኞቹ ባለሙያዎች ዕድል እንዲያገኙ እናድርግ፡፡…)
ትናንት ማታ የዶክተር ብርሃኑንና የፋሲል የኔዓለምን ውይይት ተመለከትኩ – ግሩም ነበር፡፡ ግን ፋሲል ግማሹን ቃለ መጠይቅ በአንተ፣ ቀሪውን ደግሞ በአንቱ በማካሄዱ እንደመዝናኛም ቆጥሬ ፈገግ ብያለሁ፡፡ ወጥነት እንዲኖር ለማሳሰብ ፈልጌ ነበር ግን ቀላል ጉዳይ ስለሆነ ተውኩት፡፡ ለነገሩ ቀረቤታንና አክብሮትን በአንድ መድረክ በማሳየቱ በጨዋታነት ደረጃ ደስ ይላል፡፡ ይህችን ነቁጥ ነገር ለትችትም የሚያበቃት ሰው አይጠፋ ይሆናል እኮ፡፡ አደራ እኔ ለቀልድ ነው እያነሳሁ ያለሁት!
በነገራችን ላይ የ24 ሰዓት የዜናና የሀተታ አገልግሎት ዝግጅት በጣም ከባድ ነው፤ የሰው ኃይል አለ፤ የማቴርያልና የበጀት ጉዳይ አለ፤ ብዙ ተያያዥ ተግዳሮቶች አሉ፡፡ ስለዚህ ኢሣት በቢሊዮን ዶላሮችና በሺዎች ሠራተኞች እንደሚንቀሳቀሱት የአልጀዚራና ቢቢሲ ጣቢያዎች እንዲሆን መጠበቅ አይገባንም፡፡ በአቅም ውስጥ ግን የሚቻለውን ያህል መንቀሳቀስ ይቻላል፡፡ እናም በበኩሌና በዚህ አጋጣሚ ይህ ጣቢያ ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ ሕጻናትን፣ አረጋውያንን… በጥቅሉ አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል እንዲይዝ በብልሃት ቢመራ ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ ለምሳሌ በቀደምለት ‹ፈረቃ› በሚል ርዕስ የነዶኪሌን ቀልድ ስመለከት በጣም ደስ ብሎኛል – ደስ የማይለው ደግሞ ሊኖር ይችላል፡፡ ግን ለኔ ሲል ይታገሳል ብዬ አምናለሁ፡፡ ስፖርት ለኔ ብዙም አይጥመኝም – ስሜቴ በአብዛኛው በሀገሬ ላይ ስላረፈ ከመዝናኛ ቀልዶችና ጭውውቶች ወጣ የሚሉ ሌሎች ዝግጅቶች እምብዝም አይስቡኝም፡፡ ለሌሎች ስል ግን እታገሳለሁ – እከታተላለሁም፤ የፖለቲካ ትንተና ሲጀመር ግን አፌን ከፍቼ ላነጋ እችላለሁ፡፡ በመሠረቱ ሁሉን ማስደሰት ከባድ ነው – በተለይ ሰውን፤ በተለዬ በተለይ ደግሞ የዘመኑ ኢትዮጵያውንን – እንዴ፣ ለይቶልን የጥንቶቹን ባቢሎንያውያንን ሆነናል እኮ፡፡ … ይሁንና በአስተያየት መስጫ መድረኮች የሚሰሙ ጥቆማና አስተያየቶችን በጥሞና ማዳመጥ ሲቻልም ለመቀበል መሞከር መልካም ነው፡፡ በኢንስትሩመንታል ሙዚቃ ብዙ ጊዜ ባይባክን፣ ከየብሔረሰቡ ማራኪ ዘፈኖችና ውዝዋዜዎች በፕሮግራም ማሸጋገሪያነት ቢገቡ፣ የነልመንህና አለባቸው፣ የነደረጀና ሀብቴ፣ የሌሎች ሀገሮች አርቲስቶች ቀልድና ጭውውቶችም ቢዘወተሩ… ጥሩ ነው፡፡ በተነሱበት ያልተነሱበትን መናገር በኔ አልተጀመረም፡፡
መነሻየን የሚከተል ሌላ ጉዳይ ላክልና ወደ ዋናው ጉዳይ ልንደርደር፡፡
እንደውነቱ ከሆነ ብዙ ጊዜ ልጻፍ እልና በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚው ሰው ቁጥር ተስፋ አስቆራጭ በመሆኑ ማን ያነበኛል በሚል እተወዋለሁ፡፡ የሀገራችን ወጣትና ጎልማሣ አንዳች ጠበል ካልተረጨ ወይም በወያኔ የተራገፈብን አፍዝ አደንግዝ ካልተነሳልን የሀገር ውስጡ ነገር አሳሳቢ እየሆነ ነው፡፡ አብዛኛው ዜጋ በሚያሳፍር ሁኔታ ለሆዱና በሆዱ ምክንያት ታስሮ ቢኮረኩት እንኳን ለመሳቅ ጊዜ የሌለው ሆኗል፡፡ ኢንተርኔት ካፌዎች ብትገቡ ሰው ከአፍ እስከገደፋቸው ጢም ብሎ ሞልቶ ታገኛላችሁ – በተለይ ወጣቱ፡፡ ግና የሀገራችን ወጣት ምን ነካው ብለን እስክንገረም ድረስ ከሞላ ጎደል ሁሉም የሚፎሰቡከው ፆታዊ ግንኙነትን ማዕከል ያደረገ ትርኪ ምርኪ ነገር ላይ ነው፡፡ ሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳይ ይቅርና የረባ ቁም ነገር የሚፎሰቡክ ለማየት አንገትህ እስኪቀነጠስ ዙሪያ ገባህን ብዙ ብታማትር ማግኘት ይሳንሃል፤ ተረግመናል፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ ዳሰሳ ጥናት ለማድረግ ሞክሬያለሁ – በጨረፍታና በስለላ መልክ፡፡ ይሁንና ከዘመድ አዝማድና ጓደኛ ተራ የኢሜል ግንኙነትና ከወሲባዊ የፍቅር ጨዋታ እንዲሁም ከዚሁ ያልወጡ ግትርና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ምልከታ በስተቀር በፕሮክሲዎች ገብቶ የተቃውሞ ድረገጾችን ለመፈተሽ የሚደረግ ሙከራ አልታዘብኩም፤ እርግጥ ነው ፍርሀትና የግንዛቤ ዕጥረት በመንስኤነት ሊጠቀሱ ይችሉ ይሆናል፡፡ የግብጾችንና ሌሎች የአረቡ ዓለም ወጣቶችን ስታስብ ደግሞ ተስፋህ እንደጉም ሊበንብህ ይችላል – ስለዚህ መፍትሔው እነዚያን ሀገሮች አታስብ ብዬ ነው የምመክርህ፡፡ ወያኔና ተቃዋሚዎች እግዜር ይይላቸው – በተለይ ወጣቱን ስሜትየለሽ አደረጉት፤ ግዴለሽ ዜጋ በዛ፡፡ ሆዱ ከሞላ ለሌላ የማያስብና ለሀገር ቀርቶ ለራሱም የማይጨነቅ ነሁላላ ዜጋ እየተበራከተ መጣ፡፡ በጁ ቆንጨራና ጩቤ አታይም እንጂ ሰው በተለይ የንግዱ ማኅበረሰብ ድሆች ዜጎችን በጠራራ ጠሐይ እየከተፈ ይበላው ይዟል፤ በይውና ጠጪው አሥረሽ ምቺው ላይ ነው – ‹ነገ ዓለም ታልፋለች› የተባለ ይመስል፡፡ የቢሮ ሠራተኛው ሁላ በእጅህ ካልሆነ በእግርህ ሄደህ ጉዳይህን አይፈጽምልህም፡፡ የሚኖሩት በሚሞቱት ላይ እየጨፈሩ ሲታይ ሀገርና ሕዝብ ያሉ ይመስላሉ እንጂ ሁሉ ነገር አብቅቶልናል፡፡ እንደሕዝብም እንደሀገርም ትናጋችን ተዘግቶ ኅልውናችን ቀጥ ሊል የቀሩት ሐሙሶች ከሁለትና ከሦስት የሚበልጡ አይመስልም፡፡ ‹ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል› እንዲሉ ሆኖ እንጂ በቁማችን ሞተናል ብንል አልዋሸንም፡፡ እንደዘመነ ሶዶምና ገሞራ ልንሆን ነው መሰለኝ፡፡ አንዱ አንዱን እየበላ ገንዘብ ከማካበትና ሌትና ቀን በየዝጉብኚው ዳንኪራና ጮቤ ከመርገጥ በስተቀር አቅልን ገዝቶ ስለሀገር ቆም ብሎ የሚያስብ ሰው እየጠፋ ነው – በሀገር ቤት ውስጥ በተለይ፡፡ ምሁር ተብዬውም በዬወረቀቱ ተሸጉጦ ለዕለታዊ ጉርስና ለዓመታዊ ልብስ የምትሆነውን ሶልዲ የሚያገኝበት “የጥናትና ምርምር” ሥራዎችን በከተፋ – በኮፒ ፔስት የዘመን አመጣሽ ‹ምሁራዊ› ልክፍት ተጠምዶ – ከማምረት በስተቀር ይህ ነው የሚባል የረባ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ሥራ ሲሠራ አይታይም፡፡ ሀገሪቱ በርግጥም የወላድ መካን የሆነች ትመስላለች – ዛሬ! ስለነገው በአቤቶኪቻዊ አባባል በአዲስ መስመር እንገናኝ፡፡
የነገው ግን በርግጠኝነት ሌላ ነው፤ ከአሁኑ እንቅልፍና ስንፍና ብዙ የተማረ አዲስ ትውልድ ሲፈጠር ወይም የአሁኑ ከተኛበት ሲነቃ ኢትዮጵያ ልዩ ሀገር ትሆናለች፡፡ የቀኝ ኋላው ዙር ዐዋጅ ሲታወጅ በርግጠኝነት የመከራችን ደመናና ጭጋግ ይገፈፋል፤ ወያኔ የጀመረውን ጉዞ በቅርቡ ሲያጠናቅቅ ሁላችን ከየተሸጎጥንበት የጥፋት ጭምብልና ከየመሸግንበት የፍርሀት ዋሻ ስንወጣ – ማንና የት እንደምንገኝ ስንገነዘብ – ያኔ ያለንን ሁሉ አቀናጅተን በምንፈጥራት አዲሲቷ ኢትዮጵያ አዲስና የተከበረ ስብዕና ይኖረናል፤ በወያኔው የተዋረደው አሮጌው ስብዕናችን ከነዘረኝነቱና ከነሃይማኖታዊ የቁርቋሶ ቱማታው እንክትክቱ ወጥቶ ወደመጣበት ወደ ሀገረ ሳጥናኤል ሲመለስ ያኔ ዐይናችን ይበራል፤ ድንቁርናችን በዕውቀትና በማስተዋል ይተካል፤ የግላዊ ብልጽግና የተናጠል ሩጫችን እንደአሁኑ በዘርና በጎሣ በተቀነበበ ይሉኝታቢስነት አንዲትን ሀገር የብቻ ቁጥጥርና ዐይን ያወጣ ዝርፊያ ላይ ሳይሆን የንግድም ሆነ አጠቃላዩ የኢኮኖሚ ግንኙነት ለሁሉም ምቹ ሁኔታን በሚፈጥር የተስተካከለ የውድድር ሜዳ ላይ በሚከናወን የግልና የወል ሕጋዊና ሚዛናዊ ጥረት ላይ የሚመሠረት ይሆናል፡፡ የወደፊቷ ኢትዮጵያ በእኩልነትና በነጻነት የምንኖርባት የሁላችንንም የልብ ትርታ በሚያዳምጥና አንዳችም አድልዖ በማይኖረው ሀገራዊ የጋራ ሕግ ታስተዳድረናለች፡፡
አሁን በአዲስና ተለዋጭ ርዕስ ወደተነሳሁበት ጉዳይ ከእውነት ገባሁ፡፡
የፋሲካው በግ በገናው በግ ይስቃል
ሰሞኑን በሙስሊሙ ማኅበረሰብና በመለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ በሚታዘዘው የወያኔው ሥውር(abstract) መንግሥት መካከል የጦፈ ግጭት እንዳለ ይወራል፡፡ ይህም የሚደመጠው ድረገጾቻችንን ጨምሮ ኢሣትን ከመሳሰሉ የውጭ የዜና ማዕከላት እንጂ የሀገር ቤቱ የወያኔ የውሸት ወፍጮማ ሁሉም ሰላም እንደሆነ ነው ሰርክ እየተደሰኮረ ያለው፡፡ ይህ ሃይማኖትን ተመርኩዞ የተቀሰቀሰ ግጭት ወዴት ሊያመራ እንደሚችል መጨረሻው ወደፊት የሚታይ ሆኖ በተለይ ስለእስልምናና ክርስትና ሃይማኖቶች (በኢትዮጵያ) ትንሽ ነገር መናገር እፈልጋለሁ፡፡ ግጭቱ የሃይማኖት ሳይሆን የመብት ረገጣ የወለደው የአትንኩኝ ባይነት ትግል መሆኑን አምናለሁ፡፡ ወያኔ ዜጎችንና ጦርነትን በቆረጣ መግጠሙ ዛሬ የጀመረው አይደለም፡፡ ጠላቶቹ ተቆጥረው አያልቁም፤ የሚገጥምበት ሥልት ግን በተራና በቆረጣ ነው፡፡ ይህን የተበላ ዕቁብ ሕዝበ ክርስቲያንና ሕዝበ ሙስሊም ካልነቃበት ራሱ ያልቅበታል፡፡ ወያኔ ተንኮለኛ ነው፡፡ ሃይማኖት የለውም፡፡ ሃይማኖት አለን የሚሉ ወገኖችን ግን እርስ በርስ ሊያባላቸው የአንዱ ዕንባ አባሽ መስሎ አንዱን ከሌላው ሊያጋጭ ይሞክራል፡፡ ሞኝ ካገኘ ይሳካለታል፡፡ ከተነቃበት ግን ራሱ ያልቅለታል፡፡ ይህን ነው ሁሉም ሕዝብ መረዳት ያለበት፡፡ በየተራ ማለቅ ነው የሚጠቅመው ዌንስ ተባብሮ የጋራ ጠላትን ልኩን እንዲያውቅና መብትን መርገጥን እንዲያቆም ማድረግ? ምርጫው የምዕመናን ነው፡፡
እንደደራሲ ሰርቫንቴስ የምናብ ፍጡር እንደዶን ኪሾት የሚመሰለው ወያኔ ይህን የሙስሊሞችን ጥያቄ በቀላሉ ሊመልሰው ሲችል ተፈጥሮው ከሁሉም ነገሮች ጋር(ሕይወት ካለውም ከሌለውም ጋር) የመጋጨት እንጂ ሰላምን የመፍጠር ባለመሆኑ ይሄውና የራሱን መቃብር እየቆፈረ ይገኛል፡፡ ወያኔ ሰዓት ስንት እንደሆነ እንኳ ቢጠየቅ – እንደተቋም – “ሰዓት መጠየቅ እንደአካሄድ ትክክል ሞሆን አለሞሆኑ አነጋጋሪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን ማን ነው ሰዓት ጠያቂው? የግንቦት ሰባት አባል ነው ወይንስ የመድረክ? ለምን ዓላማ? ሰዓት ጠያቂው ሰዓት መጠየቅ ከሽብርተኝነት ጋር ቁርኝት ሊኖረው እንደሚችል ያልተገነዘበበት ምኽኒያቱ ምንድነው? ሰዓት የተጠየቀው ለሽብር የሚጠመድን የ‹ሠ› ሰዓት ፈንጂ ለማስተካከል አለሞሆኑ እስኪረጋገጥ ሰዓት ጠያቂውና ዘመድ ወዳጆቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ከተጣራ በኋላ ሰዓቱ ሊነገረውም ላይነገረውም ይችላል…” ሊል ይችላል፡፡ ስለዚህ ወያኔን ምንም ነገር መጠየቅ በሽብርተኝነት ሊያስጠረጥር፣ ሊያስከስስና በታዛዥ ዳኞች – በሰው መሰል የወያኔ ሮቦት ዳኞች – ዕድሜ ይፍታህ ወይም የስቅላት ሞት ሊያስበይን የሚችል አደገኛ ወንጀል ነው፤ ‹ራበኝ አጉርሱኝ፣ ጠማኝ አጠጡኝ፣ ታረዝኩ አልብሱኝ፣ መንገድ አሳዩኝ …› በወያኔ በአሸባሪነት ሊያስጠረጥሩ የሚችሉ ‹ወንጀሎች› ናቸው፤ ይህ ዓይነት ዕንቆቅልሽ ፍጡር ለግማሽ ምዕተ ዓመት በሕይወት መኖሩ በርግጥም ያስደንቃል – በድንቃድንቅ ታሪኮች መዝገብም ሊሠፍር ይገባዋል፡፡ ወያኔ እኮ በማሰብህም የሚከስህ የመጀመሪያው የዓለማችን ጉድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራቸው ደግሞ በነጻነት መናገር እንደቅንጦት የሚቆጠር ሆኖ እንዲሁ ማሰብም መብላት መጠጣትም የማይቻልባት የመጀመሪያዋ ሀገር ናት – ለኢ-ወያኔያዉያን ነው ታዲያ፡፡ ኢ-ወያኔነት ደግሞ በእውነተኛ ኢትዮጵያዊነት የሚያገኙት የሚከብድ ሸክም እንጂ በዘርና በሃይማኖት ተፈጥሯዊና የግል ጉዳዮች የሚወሰንና ለተመረጡ ብቻ የሚሰጥ ምንዳ አይደለም፡፡ ከዚህ አኳያ ሙስሊሙም፣ ክርስቲያኑም፣ አማራውም፣ ኦሮሞውም፣ አደብ ካልገዛና የወቅቱን በረከተ መርገም ከአሌታዊው(ዘረኛ) ሥርዓት ተለጥፌ ከርሴን አልሞላም ብሎ ከቆረጠ ትግሬውም ጭምር ከዚህ ወያኔያዊ የጭካኔ በትር አያመልጡም – አብዮት ልጆቿን የመብላቷ መዝሙር በደርግ ዘመን ብቻ ተዜሞ አልቀረም፡፡ ወያኔን ያልመሰለና ያልሆነ አሣር ይደርስበታል፡፡ በምንም ሁኔታ ተከፋፍሎ መገኘት ለወያኔው ዱላ ይበልጥ ምቹ መሆን ነው፡፡ አለመተባበር መሰባበርን እንደሚያስከትል ዶክተር መራራ አስቀድመው አስታውቀዋል- ለሚገባው፡፡ ግን ግን አፍዝ አንግዟን ማን ወንድ ይፍታት! ለነገሩ ከላይ የመጣው ከላይ ካሉት ፍትሃቱን ጀምሯልና ዋናው መታገስ ነው – ‹እናያለን ገና› ብሏል አቀንቃኙ፡፡ በጊዜ የተመለሰ ብቻ ይድናል፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ነው እንግዲህ ሙስሊሞች መብታችን ይከበር ሲሉ ክርስቲያኑ ፀጥ ረጭ ብሎ የሚታየው፡፡ ሁለቱም መታረዳቸው የማይቀር በጎች ናቸው – የገናና የፋሲካ በጎች፡፡ ነገር ግን የፋሲካው አንድ ሦስት ወሮች ያህል ዕድሜ ስላሉት እየታረደ ባለው የገናው በግ ይስቃል ይባላል – በምሳሌያዊ አነጋገሩ፡፡ ለነገሩ በግ ባኣኣ ይላል እንጂ አይስቅም፡፡ እኛም ክርስቲያን ነን የምንል ወገኖች እየሳቅን ሳይሆን ባኣኣ ባንልም ዕርዱ እንደማይቀርልን ተገንዝበን በማጉረምረም ላይ የምንገኝ የወያኔ ጭዳዎች ነን፡፡ ዝምታን ድጋፍን ሳይሆን በአብዛኛው ተቃውሞን እንደሚተቁም መገንዘብ ተገቢ ነውና የቁርጡ ሲመጣ ሙስሊሞች አጋዥ የለንም ብለው እንዳይሰጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ ይልቁናም ሁለቱም ሃይማኖቶች መጠንቀቅ የሚገባቸው በውስጣቸው የሚገኙ የሁለት ጫፍ አክራሪዎችን ነው – ትልቁ መጥፎ ነገር ዘመድ መስሎ የሚቀርብ ጠላት ነው፡፡ የአክራሪነት ምንጭ ደግሞ የተወሳሰበ ነው – ያንተ ‹አክራሪ›ና የኔ ‹አክራሪ› የኛ አለመሆናቸውን ምናልባትም ከጋራ ጠላታችን የተላኩና በውስጣችን የሠረጉ ምንደኞች መሆናቸውን የምናውቅበት መንገድ ለሰላምና ለብዙኃን ድምጽ አንገዛም ያሉ እንደሆነ ነው፤ ‹አጭበርባሪ አይተኛኝም› ያለችዋን የሴተኛ አዳሪዋን ምሳሌ መቀበል ከብዙ ጉዳት ይሠውራልና ጠንቀቅ እንበል ጎበዝ፡፡ አክራሪነት በየትኛውም ሁኔታ ጎጂና አፍራሽ ነው፡፡ አክራሪ ክርስቲያን ይጠንቀቅ፤ አክራሪ እስላምም ይጠንቀቅ፡፡ አለበለዚያ ያከረሩት ነገር ሲበጠስ ከነአክራሪው ነው ገደል የሚከተው፡፡ አክርሮ ዘወር የማይባልባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ ሁልጊዜ ጌትነት የለም፡፡ … ወያኔን ስለምናውቅ በሌሎች መጨፍጨፍ የምንደሰት ጤናማ ዜጎች በመካከላችን አንኖርም፡፡ ግን የወያኔ ፕሮፓጋንዳና ለዘመናት የተረጨብን ፍርሀትን የሚያነግሥ ፕሮፓጋንዳ እንዲሁም ከደርግ ጀምሮ የወረደብን የልጆቻችንን ሬሣ ሳይቀር ከመንግሥት የመግዛት አረመኔያዊ ድርጊት ሰንገው ይዘውን አንዳችን የአንዳችንን መከፋት ተከትሎ ብቻም ሳይሆን እኛ ራሳችን እየተገረፍንም ቢሆን ላለመጮህና ተቃውሞኣችንን ላለማሰማት የማልን እንመስላለን፡፡ እንጂ ይህ ወቅት ሁላችን ሃይማኖትና ብሔር ሳንል ሁላችን በህብረት ‹ሆ› ብለን በመውጣት ይህን አናቱ ተቆርጦ የተጣለ የቀትር እባብ ወያኔ ቆራርጠን የምንጥልበት ዘመን ነበር፡፡ መቆራረጥ ሲባል ሥጋዊ ትርጉም ሳይሆን መንፈሳዊ ፍቺን እንዲይዝልኝ እወዳለሁ፡፡ መቆራረጥ ክፉ ሃሳብን ነው – አካልን አይደለም፡፡ አካል ቢቆረጥ አካልን ይተካል፡፡ ክፉ አስተሳሰብ ከተቆረጠና ከተወገደ ግን የወደፊቱ ትውልድ ከመሰል ዕኩይ ፍልስፍናና ጠማማ አስተሳሰብ ይድናል፡፡ መቆራረጥ የሚለያየንንና የሚከፋፍለንን የወያኔን የዘውገኛነት ልክፍት ነው፤ መቆራረጥ ሀገርንና ሕዝብን ለከፋ ችግር የሚዳርግ የወንድሞቻችንንና የእህቶቻችንን የሆድ አምላኪነት የአስተሳሰብ ደዌ ነው፡፡
በኢትዮጵያ እስልምናና ክርስትና በሰላም ኖረዋል፡፡ የሃይማኖቶች በሰላምና በፍቅር የመኖር አርአያ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በአንዳንድ ወቅቶች በዚህ ወያ በዚያ ሃይማኖት ተከታይ ምክንያት አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርስውን ጉዳት ከታሪክ ማኅደር ማስታወስ ይቻላል ፤ ግን የግጭትን ታሪክ እያስታወሱ የሻረ ቁስልን ከማንቆርና ቂም በቀልን ከማጫር ይልቅ ያሳለፍናቸውን የፍቅርና የደስታ፣ የመተሳሰብና የመተዛዘን ገጽታዎችን እያወሱ ተንኮለኞች ከቀደዱልን የጥፋት ቦይ መውጣት ነው የሚበጀን፡፡
አንድ መታወቅ ያለበት ነገር አለ፡፡ የአንድን ሰው ወይም የአንድን ማኅበረሰብ ሃይማኖታዊና ዘውጋዊ ማንነት በተመለከተ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ንጹሕ ዘርና ንጹሕ ሃይማኖት የሚባል ነገር በጭራሽ የለም፡፡ በዘመናት የአብሮነት ሕይወት ምክንያት ሁሉም ተባዝቆ ተባዝቆ ተቀላቅሏል፤ አንዱን ከሌላው ለመለየት በሚያስቸግር ሁኔታ ተዋህዷል – የኔን ብነግራችሁ ትገረማላችሁ፡፡ አንድ ወቅት የአፋሩ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ አባት አሊሚራህ እንዲህ አደረጉ አሉ፡- ሁሉም ሰው በዬሽብራሩ ወተት እንዲያመጣ አደረጉ፡፡ ሁሉም ያመጣውን ወተት ወደ አንድ ትልቅ ማጋቢያ እንዲገለብጥ አዘዙ፡፡ በኋላም ሁሉም ሰው ከዚያ የወተት ጋን ውስጥ የራሱን ወተት እየለዬ ባመጣበት ሽብራር መልሶ እንዲወስድ አስታወቁ፡፡ ሰው ሁሉ በአግራሞት ተጨንቆ “እንዴ! እንዴት ይታወቃል? ተደበላለቆ የለም እንዴ አባታችን?” ብሎ ይጠይቃቸዋል፡፡ ያም ብልሁ የሀገር አባት “የኢትዮጵያ ሕዝብም እንደዚህ ነው! ሁላችንም ስለተዋሃድን አንዳችንን ከአንዳችን ለመነጠል አይቻልም” በማለት ሕዝባቸውን በጉልበትና በዐዋጅ ከጋጋታ ሳይሆን በጥበብ አስተማሩ፡፡ የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን አፋሮች ግመሎቻቸው እንደሚያውቋት የመሰከሩትም ያን ጊዜ ነው፡፡
ዶክተር ብርሀኑ በትናንቱ ቃለ መጠይቅ (እንዴት ያለ ግሩም ቃለ መጠይቅ ነበር!) እንዳሉት ከሞላ ጎደል በሁላችንም ቤት እስልምናና ክርስትና አሉ – እንዲያውም ከነዚህም በላይ፡፡ የሃይማኖት ውርርሱ በጋብቻ ወይም በትውልድ ሐረግ ከአባት እናት የተወረሰ ወይም በማወቅና በይሁንታ ከአንዱ ወደ ሌላኛው በመዛወር የተገኘ ሊሆን ይችላል፡፡ በየትም ይምጣ ዋናው ነገር ግን የሃይማኖት ጉዳይ የግል እንጂ የሀገር አይደለም፡፡ ሁሌ እንደሚባለው ሀገር የጋራ ናት፡፡ ሃይማኖት ግን የግል ነው፡፡ በአንድ ቤት ውስጥ አምስትም አስርም ሃይማኖት ሊኖር ይችላል፡፡ በአንድ ቤት ውስጥ ግን አምስትም አስርም ሀገር ሊኖር አይችልም፡፡ ስለዚህ የማይቀላቀልን ነገር ማቀላቀል ለብንም፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ቅድሚያውን እንስጥ፡፡
ዋናው ነገር ሃይማኖትም ሆነ የራሳችን ኅልውና ሊኖረን የሚችለው በቅድሚያ ሀገር ስትኖረን ነው፡፡ ሀገር ሊኖረን የሚችለው ደግሞ የግልና የቡድን ነጻነታችንን የሚያከብር ቢቻል በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ራሳችን የምንመርጠው ባይቻል እንኳን የልብ ትርታችንን የሚያዳምጥ ከእኛው የወጣ እኛኑ የመሰለ ሀገርና ዜጋ የማይሸጥ እንደመለስ ያለ ወፍዘራሽ የርግማን ውጤት ሳይሆን ሀገር በቀል የሆነ መሪ ሲኖረን ነው – እንደኃይለማርያምም የራሱን ማንነት ለመናኛ ጥቅም ያልለወጠ – እንደኤሳውም በምሥር ብኩርናውን ያልሸጠ፡፡ ዴሞክራሲ እዬዬም ሲዳላ ነው እንዲሉ ነው፡፡ ቀድሞ የመቀመጫዬን ብላለች ዝንጀሮ፡፡ አሁን እኮ ብዙዎቻችን ጨካኙን መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ሳይቀር እየናፈቅን ነው – አትታዘቡኝ እኔ መንግሥቱን መናፈቅ ከጀመርኩ ቢያንስ ሰባት ዓመት አልፎኛል፡፡ መንግሥቱ እኮ ሥልጣኑን አትይበት እንጂ ከመሬት ተነስቶ የ‹ዐይንህን ቀለም› እያየ ሞትና እሥራት ርሀብና ሥቃይ አያዝብህም ነበር – እንዴ፣ መንጌ እኮ በጭካኔው ካባ ሥር የነበረው የሀገር ፍቅርና የሕዝብ ወገናዊነት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አልነበረም፤ ሰውን መጥላትም ሆነ ማፍቀር በፈርጅ በፈርጁ እንጂ ሕጻኑን ከነታጠበበት ቆሻሻ ውኃ መድፋት ተገቢ አይመስለኝም(አንድ የኦሮምኛ አባባል ትዝ አለኝ፡- ‹አህያ እረዱ ቢሉን አህያ አረድን፣ አይጠቅማችሁም ቢሉን ጠራርገን ጣልን፣ እንዴ – ይጠቅማችሁ ነበር እኮ ቢሉንና ሄደን ብንፈልገው አጣነው› ይላል ይህ ቆንጆ ብሂል፡፡ አሁን መንጌን የት እናግኘው?(አቤት – ብዙ ሰው ሲንጫጫብኝ ታየኝ!)፡፡ ሰው የሚመሰገነው አንድም ሲሞት አንድም ሲለይ የሚባለው አውነት ነው፡፡ የራሳችንን ጨካኝ እንደዋዛ ሸኝተን አሁን የሰው ዘመሚትና ተምች አንበጣና የዓሣማ ግሪሣ በላያችን ላይ አነገሥን፡፡ ሰበቡ እኛ አይደለንም፤ ደግሞም እኛው ነን፡፡ የዘመን ዕንቆቅልሽ፡፡
እስላምና ክርስቲያን አንድ ነን አንድ አይደለንም ቅብጥርሶ የሚለው ክርክር ለተመቸው ነው፡፡ እኛ እሾህ ላይ ቆመን፣ የሲዖል እሳት ላይ ተቀምጠን የምንገኝ ዜጎች በመሆናችን ቢያንስ በአንድ የሥቃይ ቋት ውስጥ ገብቶ እንደሚወቀጥ የጋራ ዕጣ ተቋዳሽ ራሳችንን በመቁጠር በተናጠል ላለማለቅ በጋራ የጋራ ጠላታችን ላይ እንነሳ እላለሁ፡፡ ወያኔ የዘራብንን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ከቁብ አንጣፈው፡፡ መጀመሪያ ሀገር ትኑረን፤ ሀገር እንዲኖረን በማድረጉ ሂደት ጎን ለጎን የዴሞክራሲያዊ መንግሥት ምሥረታ በሚመለከታቸው የሀገሪቱ ልሂቃን ይሠራ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ቀጣፊና አጭበርባሪ ወደሥልጣን የማይመጣበት አስተማማኝ የሕግ መደላድል በሀገራችን እንዲፈጠር ሁሉም ወገን ከዘርና ከሃይማኖት ግላዊ ጉዳዮች ተቆጥቦ በጋራ የኅልውና ማስጠበቂያ አውታሮች ላይ ይረባረብ፡፡
ታማኝ በየነን ጆሮ እንስጠው፡፡ ዛሬ ጧት ያዳመጥኩት የዛሬ ዓመቱ ንግግሩ አንጀቴን ነው የበላው፡፡ ለመቃወም ሲባል የተፈጠረ ሰው ካልሆነ በስተቀር ያን ንግግሩን መቼም የሚቃወም ሰው የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ድል ማለት አንዱት ትቶ ሌላውን አንስቶ ነውና ግላዊ ጉዳዮችን ወደጎን እየተውን አንድ በሚያደርጉን ነገሮች ብቻ እንሰባሰብ፡፡ ያን ባናደርግ ተጎጂዎቹ እኛ ስንሆን ተጠቃሚዎቹ የጋራ ጠላቶቻችን ወያኔና መሰል የሀገር ውስጥና የሀገር ውጪ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ ጨው የሚጣፍጠው በጨውነቱ እስከቆዬ ድረስ ነው፡፡ ጨው ድንጋይ ነበር፤ ድንጋይም ጨው ነበር፡፡ ምርጫው የጨውና የድንጋይ ነው፡፡ ይህን ነባራዊ እውነት ዕንወቅ – ወቅቱን ጠብቆ ጨውም ጨው ድንጋይም ድንጋይ ይሆናሉ፡፡ የጭንቅላት ሥጋ መብሰሉ ለማይቀረው እሳት ፈጃል ይባላል፤ የኢትዮጵያ ጠላቶችም መቸ(ሸ)ነፋቸው ለማይቀረው ብዙ ‹ትግስት›ን እየጨረሱብንና ውድመትን እስያከተሉብን ተቸገርነ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ!
አላሁዋክበር! (እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን)
ሐምሌና ነሐሴ ከባድ ዝናባማ ወራት ጠቅልለው ከሄዱ ቆይተዋል። ለወጥሮው የኢትዮጵያን ሰማይ ሸፍኖ የነበረው ከባድ ጥቁር ዳመና ከረር ከረር እያለች በመጣችው የፀሐይ ሙቀት ምክንያት እየተሸነፈ እንደ ባለሙያ ሴት የጥጥ ንድፍ እዚህም እዚያም በተን በተን ያለ እጅግ በጣም ስስ ጉም መሆን ከጀመረ ውሎ አድሯል። ሜዳ፣ ጋራና ሸንተረሩ ውሃ ጠግቦ በቃኝ ብሎ በሙሉ ደረቱ የሚያፈስባቸውና በተለምዶ የአበባ ወራት ተብለው የሚጠሩት ወራቶችም ምድሪቱን ካስወቡበት ምትሃታማ አስደማሚና ህሊናን ያዥ ህብር ቀለማቸው እየሸሹ የምድሪቱን አላባ እንካችሁ የሚሉበት ወርሃ ጥጋብ ወርሃ ምርት ጊዜ እየደረሰ ነው። ጓዳ ጎድጋዳው፣ ሸጥና ወንዙ፣ ኩሬ ሸለቆው፣ ወጣ ገባ ተራራው ባጠቃላይ ምድሪቱ በሚላስ በሚቀመስ ሲሳይ የምትጎበኝበትና የምትሞላበት መልካም የደስታና የጥጋብ ወራት፤ ወርሃ ምርት ኢትዮጵያ።
መፈረካከሱ ቀጥሏል፤ ፍርሃት፣ ጭንቀትና መደነባበሩም በወያኔ መንደር ተባብሷል

የእያንዳንዱ አርሶ አደር ጎጆ በአንጻራዊ ሲሳይና ደስታ በሚጎበኝበት በዚህ ጊዜ፤ ምድሪቱ ያላትን በረከት ያለስስት እየጋበዘች ባለችበት በዚህ ወራት፤ የምግብ እጦት ፍርሃት ለጊዜውም ቢሆን በተረሳበት፣ የርሃብና የስደት ፍርሃት ላፍታ እንኳ በማይታሰብበት የጥጋብ ወራት፣ ምርት እንዴት እንደሚሰበሰብ እንጅ የጥላቻ፣ የመራራቅና የጦርነት ስጋት እንደደራሽ እንግዳ እንኳ ቢሆን ትዝ በማይልበት በዚህ የኢትዮጵያ የደስታና የሃሴት ወራት ምነው ወያኔ ፍርሃት ፍርሃት አለውሳ። በ99.6 የኢትዮጵያ ህዝብ ተመረጥኩ እያለ ያወራበት አፉ ሳይደርቅ እንዴት ወያኔ በህዝባችን የልበ ሙሉነት ወራት ስለፍርሃት ያወራል? ምነው ወያኔዎች ተራሮችን ያንቀጠቀጡ ጀግኖች አልነበሩም እንዴ? ታዲያ ሰሞኑን ምን ተገኝቶ ነው ተንዘፈዘፉሳ።
አርበኞች ግንባር በየቀኑ ፋታ አሳጥቶ እየኮረኮመኝ ነው፤ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ደግሞ ያለ እረፍት እየቆነጠጠኝ ነው፤ ፌደራል ፖሊስም በተከታታይ የእከዳና ወደ ጠላት እየተቀላቀለ ነው፤ በጠላት ተከበናል፤ ስለ ኢትዮጵያ እንደሚያስብ ጥሩ መንግስትና ለሕዝብ እንደሚጨነቅ አመራርም ሀገራችንን ለማፍረስ ተነስተውብናል ዘምተን ልንከላከላቸው ይገባል ወዘተ ወዘተ እና ሌሎችም። የወያኔ የትንፋሽ እርግብግቢት ፍርሃቱን እያሳበቀበት ነው፤ በእርግጥም ወያኔ መፈረካከስ ጀምሯል። ሰራዊቱን ይቅርታ ፌደራል ፖሊስን ወደ ግዳጅ ለመላክ የተጠቀሙበት የማሳመኛ ዘዴ እንኳ እርስ በርሱ የሚጋጭና የራስ መተማመን የጎደለው ደካማ ነበር። እንድ ጊዜ ”ኢትዮጵያ ሀገሬ ማለትና ስለ አድዋ ማውራት ዋጋ የለውም ታሪከ ስለሆነ” ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ ”ሰራዊታችን ግዳጅን በመፈጸም ያታወቃል ጀግና ነው ለዚህም ታሪክ ምስክር ነው” ይሉናል። ባንድ ራስ ሁለት ምላስ ይላል ይህን ነው።
ያርበኞች ግንባር፣ ትህዴን እና ሌሎችም የዴሞክራሲ ሃይሎች ለሀገራችን ሉአላዊነትና ለሕዝባችን አርነት ከወያኔ ጋር ወያኔ በመረጠው ቋንቋ ግንባር ለግንባር ሲፋለሙ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም የመጨረሻቸውም አይሆንም። ወያኔ ተጨነቀም አለቀሰ፣ ፈራም ተርበደበደ፣ አቅራራም አስጠነቀቀ ሀገራችን ከወያኔ ነጻ አስክትሆንና ሕዝባችንም በነፃነት መንቀሳቀስ እስከሚችል ድረስ ከዲሞክራሲያዊ ሃያሎች የሚደርስበት ጥቃት ተጠናክሮ ይቀጥላል። ስለዚህም የነዚህ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጥቃት ላሁኑ የወያኔ ባለስልጣናት ለቅሶና ሙሾ ሰበብ ይሆን እንደሁ እንጅ እንደዋና ምክንያት ሊጠቀስ አይችልም።ስለሆነም የወያኔ ባለስልጣናት ፍርሃትና ጭንቀት ዋናው መነሻ የሰራዊቱና ፌደራል ፖሊስ በገፍ መኮብለልና ከዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር መቀለቀል ነው እንጅ ሌሎች ምክንያቶች ሁሉ አጃቢዎች ናቸው።
ወያኔ በጣም ከመረበሹና ግራ ከመጋባቱ የተነሳ ፌደራል ፖሊስን እንደ ሀገሪቱ ጦር ሰራዊት በየጦር ግንባሩ በግልጽ ወታደራዊ ትእዛዝ እያዘመተ ይገኛል። ይህም ፌደራል ፖሊስ ከተመሰረተበትና ከሰለጠነበት ዓላማ ውጭ እንዲያገለግል እየተገደደ መሆኑን ያሳያል። ይህን በማድረግም ወያኔ ከስልጠናው ዓላማ ውጭ በማንአለብኝነት ፖሊስን ወደ ግንባር በማዝመት የራሱ የወያኔ ህገመንግስት ያጸደቀውን የጋራ ስምምነት እንኳ በመጣስ አምባገነንነቱን መግልጽ አሳይቷል። በግልባጩ የወያኔ ድንጉጥ ባለስልጣናት ግን በቅድሚያ እራሳቸው የደፈጠጡትን ተራራ የሚያክል የህግ ሽረት ትተው ከድተው ከዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር ስለተቀላቀሉት ፌደራል ፖሊሶች ውል ማፍረስ እየተርበተበቱና እየተንተባተቡም ቢሆን ያለ ሃፍረት ሊገልጹ ሲሞክሩ ያታያሉ።
የወያኔ ፌደራል ፖሊስ ድረ ገጽ በግልጽ እንደሚያሳው የፌደራል ፖሊስ ራዕይ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ፤ የህዝቦችንእርካታና አመኔታ ያረጋገጠ የፖሊስ አገልግሎት ተፈጥሮ ማየት የሚል ሲሆን፡፡ ዓላማውም የሀገሪቱን ሕገ-መንግስትናሌሎች ህጐችን በማክበርና በማስከበር ሕብረተሰቡን በወንጀል መከላከልና ምርመራ በማሳተፍ የመንግስትና የሕዝብንሠላምና ደህንነት መጠበቅና ማረጋገጥ ነው ይላል፡፡ ስለሆነም ከላይ እንዳየነው ወያኔ ራሱ ካስቀመጠው ብንነሳ እንኳ ፌደራል ፖሊስ ከሕዝብ ጋር ሆኖ ሕዝብን ያገለግላል እንጅ እንዲህ ሰሞኑን እንደሰማነውና እንዳየነው የወያኔ ባለስልጣናት ወዬው እናቴ አይነት ልቅሶ እና ራስ መተማመን የጎደለው ልፍስፍስ ትእዛዝ እንደ ሀገር ጥበቃ ሰራዊት ታጥቆና ወታደራዊ ትእዛዝ እየተቀበለ ድንበር ለማስከበር እንዲዘምት የሚገደድ አልነበረም። አይደለምም።
ስለዚህ የሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሃይሎችና አባላት እንዲሁም ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ ጀምበር እየተለቀች መሆኑን ከዚህ ማሳያ በላይ ሌሎች ማረጋገጫዎች አያሹንም። ወያኔ ከመዳከምም አልፎ በያቅጣጫው እየተፈረካከሰና እየተለያዬ በራሱ ለመጥፋት ተቃርቧል። ስለሆነም ከወያኔ በሗላ ስለሚመጣው መንግስት መነጋገርና መወያየት ከማስፈለጉም በላይ ይህን ጉዳይ ለማስፈጸም እንድ ሆኖ መቆምና እየሞተ ያለውን ወያኔ ግብአተ መሬት ማፋተን ይጠበቅብናል።
“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ነውና ብሂሉ ይነስም ይብዛ የሚናቅ እገዛ የለም። ዴሞክራሲያዊ ሃይሎችን የሚያጠናክር፣ የሕዝበችንን ሞራል የሚገነባና ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያመጣ፣ ጠላት ወያኔን የሚያጋልጥ ማንኛውም አይነት መረጃ በማቅረብ፣ ተስማሚውን ወቅት፣ ሁኔታና ጊዜ በመምረጥ ወያኔን በመክዳት ከዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር በመቀላቀል ወያኔን በማደከም ትግላችንን ማስፋትና ማጠናከር ይቻላል። ለዚህ ደግሞ ቀጠሮ አያስፈልገንም ዛሬውኑ ወስነን ስራችንን እንጀምር።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 15-2005 ዓ.ም አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘራፊውና ከነፍሰ-ገዳዩ የወያኔ አምባገነናዊ ገዥ ቡድን ለማላቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ መንገድ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ማንበርከክ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሀገርንና ወገንን ለመታደግ ቆርጦ በመነሳት በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ወታደራዊ ስትራቴጅውን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ 26 የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን፣ ከሞቱት 14 የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን መካከል አበበ የሚባለው የቀራቅር ተወላጅና አለልኝ የሚባል የደባርቅ ተወላጅ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ በፈፀመው ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻና በጠላት ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ኪሳራ የተደናገጠው የወያኔ ቡድን ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው እያጓጓዘ መሆኑንም ከአካባቢው የተሰራጩ የዜና ምንጮች አጋልጠዋል።
ይሁን እንጅ በዓላማቸው ፅናትና በሐገራዊ ፍቅር የተገነባው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በጀመረው ሕዝባዊና ሐገራዊ ተልዕኮ የፈረጠመ ክንዱን በጠላት ላይ በማሳረፍ አይበገሬነቱንና ቁርጠኝነቱን ሰሞኑን በተከታታይ ባደረጋቸው ውጊያዎች አስመስክሯል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በመጨረሻም ውጊያው በተፈፀመባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ እንዲገፋበትና እኛም የተለመደውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ግንባሩን ለመቀላቀል የሚያስችል መነሳሳትን የፈጠረ አኩሪ የአርበኝነት ገድል መፈፀሙን ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በበኩሉ በስልጣን ላይ ያለው ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ኢትዮጵያ ወንጀለኛ የወያኔ ቡድን የመጨረሻ ግብዓተ-መሬቱ እስኪፈፀም ድረስ ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፆ የአገዛዙን እድሜ ለማሳጠርም የተለመደው ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለመላው ነፃነት ናፋቂና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ መልዕክቱን አስተላለፏል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 15-2005 ዓ.ም አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በጃንሱማ ጥቃት ፈጸመ። |
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 15-2005 ዓ.ም አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘራፊውና ከነፍሰ-ገዳዩ የወያኔ አምባገነናዊ ገዥ ቡድን ለማላቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ መንገድ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ማንበርከክ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሀገርንና ወገንን ለመታደግ ቆርጦ በመነሳት በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ወታደራዊ ስትራቴጅውን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ 26 የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን፣ ከሞቱት 14 የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን መካከል አበበ የሚባለው የቀራቅር ተወላጅና አለልኝ የሚባል የደባርቅ ተወላጅ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ በፈፀመው ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻና በጠላት ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ኪሳራ የተደናገጠው የወያኔ ቡድን ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው እያጓጓዘ መሆኑንም ከአካባቢው የተሰራጩ የዜና ምንጮች አጋልጠዋል።
ይሁን እንጅ በዓላማቸው ፅናትና በሐገራዊ ፍቅር የተገነባው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በጀመረው ሕዝባዊና ሐገራዊ ተልዕኮ የፈረጠመ ክንዱን በጠላት ላይ በማሳረፍ አይበገሬነቱንና ቁርጠኝነቱን ሰሞኑን በተከታታይ ባደረጋቸው ውጊያዎች አስመስክሯል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በመጨረሻም ውጊያው በተፈፀመባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ እንዲገፋበትና እኛም የተለመደውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ግንባሩን ለመቀላቀል የሚያስችል መነሳሳትን የፈጠረ አኩሪ የአርበኝነት ገድል መፈፀሙን ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በበኩሉ በስልጣን ላይ ያለው ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ኢትዮጵያ ወንጀለኛ የወያኔ ቡድን የመጨረሻ ግብዓተ-መሬቱ እስኪፈፀም ድረስ ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፆ የአገዛዙን እድሜ ለማሳጠርም የተለመደው ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለመላው ነፃነት ናፋቂና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ መልዕክቱን አስተላለፏል።
|
ብርሃንና ሰላም = ጽልመትና ሽብር
ብርሃንና ሰላም = ጽልመትና ሽብር
ከሰሎሞን ተሰማ ጂ.
emnaworeq.blogspot.com
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊውን የፍትሕ ጋዜጣ እንዳይሰራጭ አገደ፤” (www.fetehe.com እና በአዲስጉዳይ መጽሔት፣ ሐምሌ 2004 ዓ.ም)
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንዳይታተም ከለከለ፡፡” (www.fnotenetsanet.com እና amharic.voanews.com October 02, 2012/ መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም)
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሪፖርተር ጋዜጣን ገጽ ቁጥር ገደበ፡፡” (ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም)
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በሁሉም ዜናዎች በበጎ ጎኑ አልተነሳም፡፡“እንዳይሰራጭ አገደ!” “እንዳይታተም ከለከለ!” እና “ቁጥር ገደበ!” የሚሉት ሃረጎች የማተሚያ ቤቱን ስምና ክብር የሚያጎድፉ ናቸው፡፡ ይህ ማተሚያ ተቋም፣ የዛሬዎቹ ሹመኞችና ባለሥላጣናቱ አወቁትም – አላወቁትም ትልቅ ራዕይና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ነበር፡፡ እነዚህን ተልዕኮዎቹን ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል መስዋዕት ማድረግ ግን ከተጠያቂነትና ከታሪክ-ሕሊና ተወቃሽነት አያድንም፡፡
“ብርሃንና ሰላም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት” በመስከረም 3 ቀን 1914 ዓ.ም በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ተቋቋመ፡፡ ይህ ማተሚያ ቤት በጥቃቅን ፔዳሎች ማለትም በእግር በመርገጥ በሚንቀሳቀሱ የማተሚያ መኪናዎች ሥራውን የጀመረው ስድስት ኪሎ በሚገኘው የዛሬው የቋንቋዎች አካዳሚ ሕንፃ ውስጥ ነበር፡፡ በዚያ ሁናቴ የተጀመረው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በ1958 ዓ.ም ሠላሳ ሺህ ጋዜጦችን በሰዓት ለማተም የሚችሉ ዘመናዊ የኦፍሴት ማተሚያ መኪናዎች ባለቤት ሆኗል (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ቅዳሜ ኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም፤ ገጽ 3 ይመልከቱ)፡፡
በወቅቱ፣ የማተሚያ ቤቱ የቴክኒክና ፕሮዳክሽን ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ አክሊሉ እንዳሉት፣ “ማተሚያ ቤቱ እየተሻሻለ በመሔዱ ባለፈው ዓመት እንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ መጽሐፍትን (1,500,000)፣ ከአስር ሚሊዮን በላይ ጋዜጦችን (10,000,000)፣ ሠላሳ ሚሊዮን (30,000,000) ቴምብሮችና ሃያ ሁለት ሚሊዮን (22,000,000) ሌብሎችን፣ አንድ ሚሊዮን ተኩል (1,500,000) የአውቶቡስ ካርኔና ቁጥራቸው ያልተገለጠ እጅግ ብዙ የምስጢር እትሞች እና የሎተሪ ትኬቶችንም አትሟል፡፡”
አቶ አክሊሉ ጨምረውም፣ “ማተሚያ ቤቱ ከሁለት ዓመታት በፊት ገዝቶ ያስመጣው ትልቁ ኦፍሴት፣ 32 ገጾች ያሉትን መጽሐፍ 18ሺ እትም በሰዓት፣ አጥፎና ቆርጦ ሲቆልላል፣ እንዲሁም በቀን አንድ መቶ ሺ ጋዜጦችን ለመሥራት እንደሚችል፣” አስታውቀዋል፡፡ ከሁለት ዓመት ወዲህም አድገቱ አርባ በመቶ (40%) ያህል ያደገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው እንደገለጹት ከሆነ፣ በ1958 ዓ.ም እንኳን፣ ሮላንድ የተባለው ኦፍሴት መሳሪያ በልዩ ልዩ ሕብረ ቀለም አድርጎ ከሦስት ሺ እስከ አምስት ሺ ጋዜጦችን በአንድ ሰዓት ውስጥ ለማተም የሚችል ነበር፡፡ ትልቁ ኦፍሴት ደግሞ በሦስት ቀለማት አድርጎ በሰዓት ሠላሳ ሺ ጋዜጦችን ለማተም መቻሉን ገልጸዋል፡፡
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አምስት መቶ ስድሳ ሠራተኞች የሚሠሩ ሲሆን፣ አራቱ ብቻ የውጭ አገር ሰዎች ናቸው፡፡ ከጠቅላላው ሠራተኛ ውስጥ ስድሳ በመቶዎቹ (60%) ሴቶች ናቸው፡፡ ማተሚያ ቤቱ በሥራው ጥራትና በቀጠሮ አክባሪነቱ ብዙ ደንበኞችን ለመሳብ ይችላል፤” ይላሉ አቶ አክሊሉ፡፡
ዛሬ ደግሞ አቶ አክሊሉ ስለማተሚያ ቤቱ እንዲገልጹ ቢጠየቁ፣ እነዚህን ወርቃማ ቃላትና ሐሳቦች አፋቸውን ሞልተው እንደማይደግሙት እግጥ ነው፡፡ ዛሬ፣ ብርሃንና ሰላም በቀጠሮ አክባሪነቱና ደንበኞቹን በመሳብ በኩል ብዙ ርቀት ቁልቁለቱን ይዞ ተንሸራቷል፡፡ ይህ ቁልቁለት የተጀመረው ደግሞ የአራት ኪሎው ግርማ “ሽብር ነዝቶ” የማተሚያ ቤቱን ወዝአደሮች በ1970 ከፈጀና ካስፈጃቸው በኋላ እንደነበር ይታወሳል (ነበር፣ ቅጽ 1፣ ገጽ —)፡፡
ባለፈው ሰሞን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር በፓርላማ ስለብርሃንና ሰላም ሲጠየቁ የመለሱት ነገርም በማተሚያ ቤቱ ላይ ሕዝባዊ ትኩረትን ስቧል፡፡ “የወረቀት ችግር የለብንም፡፡ … ማተሚያ ቤቱ አስተዳደራዊ ርምጃ የመውሰድ” መብት አለው፤ አይነት ነበር ንግግራቸው፡፡ ንግግራቸውን ለማመን ግን ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም፣ ማተሚያ ቤቱ ነፃና ገለልተኛ የንግድ ተቋም አለመሆኑን ስለምናውቅ ነው፡፡ ማለትም፣ በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የዕዝ ትዕዛዝ ሥር እንደሚሰራም ግልጽ ነውና፡፡ ሁለተኛውም ምክንያት፣ የውጭ ምንዛሪው እጥረት ምን ያህል መንግሥትንና ባንኮቹን እግር ተወርች አሳስሮ እንደሚኮረኩዳቸው አብጠርጥረን ስለምናውቅ ነው፡፡
* * *
በአገራችን የጽሕፈት መኪናዎች ከመምጣታቸው በፊት የነበረው ችግር ብዙ ህትመት እንዳይኖር አድርጓል፡፡ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሲቋቋም ጀምሮ ለበርካታ አመታት ያህል በቁም ጸኃፊነት የሠሩት አቶ ተክለ ጊዮርጊስ ናቄ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ሪፖርተር ጠይቋቸው ሲመልሱ እንዳሉት ከሆነ፣ “በአገራችን የቁም ጽሐፊ የሚባለው መንፈሳዊ መጽሐፍትንና ቁም ነገርነት ያላቸውን ጽሑፎች የሚጽፍ ፀሐፊ ናቸው፡፡ ክታቡን፣ አስማቱን፣ ድግምቱንና ሌላውን ተራ ነገር የሚጽፍ ቁም ጸሐፊ አይባልም፡፡ ሐዲሳትን፣ ድጓውን፣ ስንክሳሩን፣ መልኩን ለመጻፍ የሚያገለግለውን የኢትዮጵያውያን አበውን ከዚህኛው ለመለየት ጽሑፉ “ቁም ጽሕፈት” ተባለ፤” ሲሉ ስለሙያቸው ያስረዳሉ፡፡
አያይዘውም፣ “ቁም ጽሕፈትና ድርሰት በአገራችን ቀድሞ ያለ ቢሆንም፣ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በጣም ተስፋፍቶ እንደነበር ይነገራል፡፡ ከዚህም ወዲህ በጎንደር ነገሥታት ዘመነ መንግሥት በተለይም በአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት መጽሐፍትን የሚጽፉና የሚያዘጋጁት ሊቃውንት ተመድበው ይሠሩ ነበር፡፡ እንዲያውም መለክዓ ፊደሉ የተጠነቀቀው በአፄ አድያም ሰገድ እያሱ ዘመን ነበር፡፡” ሆኖም፣ የጋዜጣና የኅትመት ጉዳይ ለብዙ ዘመናት ፈቅም አለማለቱን አቶ ተክል ጊዮርጊስ ያስረዳሉ (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም፤ ገጽ–)፡፡
ይኼው፣ በኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም የወጣው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ በፊት ለፊት ገጹ ላይ ደግሞ እንዲህ የሚል ዜና አስነብቧል፡፡ “ግርማዊ ጃንሆይ 3,886,812 ብር የፈጀውን የብርሃንና ሰላም ሕንፃ መረቁ!” ከጋዜጣው ሐተታ ውስጥ የሚከተለው ዘገባ ቀልብን ይገዛል፡፡ እንዲህ ይላል ዝርዝሩ፡፡ “አዲሱ ማተሚያ ቤት ሕንፃ የፈጀው 1,385,581 ብር ከ36 ሳንቲም ሲሆን፣ ለሌሎች የሲቪል መሐንዲስ ሥራዎች 116,352 ብር ከ33 ሳንቲም ወጪ ሆኗል፡፡ እንዲሁም፣ ከፈረሳይ፣ ከእንግሊዝ፣ ከጀርመ፣ ከሲዊድንና ከጃፓን ተገዝተው የመጡት ለማተሚያ ቤቱ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ዋጋ 2,364,879 ብር ከ17 ሳንቲም ነው፡፡ በጠቅላላው ለሕንፃውና ለመሣሪያው የፈጀው 3,886,812 ብር ከ86 ሳንቲም መሆኑ ታውቋል፡፡” (በወቅቱ የነበረው የብር ምንዛሪ ከዶላር አንፃር ሲታይም አንድ ዶላር በሁለት የኢትዮጵያ ብር ነበር የሚመነዘረው፡፡ ስለዚህም፣ በወቅቱ የምንዛሬ ታሪፍ መሠረት $1,943,406.43 የአሜሪካን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል፡፡)
በዕለቱ ተመርቆ ሥራውን የጀመረው ዌቭሴት የተባለው የማተሚያ መኪና፣ ባለ16 ገጽ የሆነውን A-2 size አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በሰዓት 30,000 ኮፒ በስምንት ቀለማት አትሞና አጥፎ የሚያወጣ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አዲሱ ሕንፃ፣ 200,000 የተማሪዎች መማሪያ ደብተሮችን በ24 ሰዓት ውስጥ የሚያዘጋጅ መሣሪያ ያለው ሲሆን፤ 60,000 ኢንቨሎፖችን በአንድ ቀን አትመውና አዘጋጅተው የሚያወጡ መሳሪያዎችም አሉት፡፡ የተቀናጀው የኢንቨሎፖች መሥሪያ ክፍልም የተሟላ በመሆኑ፣ በልዩ ልዩ መጠንና ዓይነት በየቀኑ እስከ ስድሳ አምስት ሺ እንቨሎፖችን እያቀናበረ ያቀርባል፡፡ ባመት ሲታሰብም ደግሞ ከሠላሳ ሚሊዮን የማያንስ ኤንቨሎፖችን እያዘጋጀ ያትማል፤” ሲሉ ኃላፊው አቶ አክሊሉ ገልጸው ነበር፡፡ የጋዜጣው ሪፖርተር እንዳለው ከሆነ፣ “ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አሁን (በ1958 ዓ.ም) ባለው አቋሙ መሠረት መጽሐፍትንና ጋዜጦችን በብዛት በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ለማሰራጨት የሚችል ታላቅ ድርጅት ሆኗል” (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም፤ ገጽ–)፡፡
ከዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ መውጣት አንድ ቀን ቀደም ብሎ፣ በዕለተ ዓርብ ኅዳር 17 ቀን 1958 ዓ.ም የወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በበኩሉ፣ ጃንሆይ ማተሚያ ቤቱን ሲመርቁ ያደረጉትን ንግግር ሙሉ ቃል ይዞ ነበር፡፡ በዕለቱም ባደረጉት ንግግራቸው እንዳወሱት ከሆነ፣ በሁለት ቁም ነገሮች ላይ አተኩረው ነበር (በገጽ 1 እና 3 ላይ ይመልከቱ)፡፡ እንዲህ አሉ፤ “ማተሚያ ቤቱ ሥራውን የጀመረው፣ የመጀመሪያውን ማተሚያ መሣሪያ በግል ገንዘባችን ገዝተን በቤተ መንግሥታችን ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ አሁን ለዩኒቨርሲቲነት በሰጠነው የአባታችን ቦታ ላይ ነው፡፡ እንደምናስታውሰው ቁጥራቸው ከ15 በማይበልጡ ሠራተኞች ስናቋቁም በሁለት ዓይነተኛ ምክንያቶች በመመራት ነበር፡፡
“አንደኛ፣ የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፍተ ሐዲሳት ንባባቸውና ትርጓሜያቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በየስፍራው እንዲገኙና ክርስቲያን የሆነ ሁሉ እየተመለከተ እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ በእጅ ጽሑፍ ተጽፎ በየገዳማቱና በየአድባራቱ፣ እንደዚሁም በየአውራጃው ለኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ለማደል የሚቻል መሆኑን በማሰብና፤ ሁለተኛም፣ የአገራችን ሕዝብ በጽሑፎች ፍላጎት ረክቶ ርምጃው የተፋጠነ እንዲሆንና በዕለት ወሬም ያገሩንና የውጭውን ሁናቴ ማወቅ እንዲችል በመመኘት ነበር፤” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ጃንሆይ አክለውም፣ ሦስት አንኳር ጉዳዮች ላይ አጽንዖት ሰጥተው ነበር የተናገሩት፡፡ አንደኛ፣ “ማተሚያ ቤቱን በ1914 ዓ.ም ስናቋቁም በዚያን ጊዜ ከነበሩት ሰዎች መካከል አቶ ገብረ ክርስቶስ ተክለ ሃይማኖት ለስራው ሃሳባችንን ጥለንበት ስለነበር – የማቋቋም ሥራውን በእጅጉ ረድቷል፡፡ የመጀመሪያው ሥራ አስኪያጅም በመሆን ሠርቷል፡፡” ካሉ በኋላ፣ “ማተሚያ ቤቱ ሥራ እንዳይፈታም በማለት እንደብላቴን ጌታ ኅሩይ ያሉት ልዩ ልዩ ጽሑፎችን ለአገራችን በማበርከት ረገድ ረድተዋል፤” ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ሁለተኛም፣ “ይህ ማተሚያ በልዩ ልዩ አውራጃዎች (ከተሞች) ‘ከሣቴ ብርሃን የልዑል ራስ መኮንን ማተሚያ ቤት’ ተብለው ሦስት ቅርንጫፎች በሐረር፣ በአሥመራና በጎንደር እንዲኖረው ማድረጋችንንም እናስታውሳለን፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ በግፍ ወረራዋ ጅምራችንን እስከምታደናቅፈን ድረስ ብዙ ጥረናል፡፡” በመጨረሻም አሉ ግርማዊነታቸው፣ “ከዚህ ማተሚያ ቤት የሚገኘውን ገቢ ሁሉ፣ ለቤተ ሳይዳ ሆስፒታል (የዛሬው የካቲት 12 ሆስፒታል ነው፤) እንዲረዳ ስለወሰንን፣ የተወዳጁ ሕዝባችንን ጤንነት በመጠበቅ በኩል እንዲያግዝልን ሰጥተናል፡፡ የማተሚያ ቤቱ ገቢ ለአካል ጉዳተኞች መርጃ እንዲሆንም አዘናል፤” በማለት ነበር ንግግራቸውን የቋጩት፡፡
ማሳረጊያ፤
ስለብርሃንና ሰላም አንድትና ጥምረት የሚያስረዱ አንድ ሦስት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንጥቀስ፡፡ ነቢዩ ኢሳያስ በትንቢቱ እንደተናገረው፣ “ንባብዋ ውስተ ልባ” (ለኢየሩሳሌም የልቦናዋን ተናገሩዋት) ሲል ስለሕዝቡም የተናገረው ቃል ነው (ምዕራፍ 40፣2)፡፡ ነቢዩ ሲራክም በ(ምዕራፍ 30፣13) ላይ በተመሳሳይ መልኩ፣ “ናዝዛ ለልብከ” (ልብህን አጥናናው) ሲል ምክሩን የሰጣል፡፡ ለሰብዓዊ ባሕሪያት በሞላ፣ የልቦናን መናገርና ልብንም ማጽናናት አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ሰው ብርሃንን ካገኘና ዕውቀትንም ከተመገበ፣ አእምሮውም እንደምኞቱ መጠን ይጎለብታል፡፡ አእምሮው የጎለበተም ሰው፣ ልቦናውን ስለሚያስደስት እዝነ-ልቡናው ዕረፍትንና መጽናናትን ያገኛል፡፡ ያን ጊዜም አእምሮው ሰላምን አገኘ ማለት ነው፡፡
በዮሐንስ ወንጌል (ምዕራፍ 4፣5) ላይ የተጠቀሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይለ-ቃልም፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ!” ካለ በኋላ፣ ደቀመዛርቱን “እናንተም የዓለም ብርሃን ናችሁ!” ሲል ያውጃል፡፡ ይኼው የብርሃን አዋጅም ወደ ኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ይወስደናል፡፡ ያኔ፣ ፈጣሪ “ብርሃን ይሁን” (ለይኩን ብርሃን) ነበር ያለው፡፡ ከምዕራፉ እንደምንማረው ከሆነ፣ የብርሃን ጉድለት (ጽልመት) የነገሰበት ወይም የሰፈነበት ዓለም፣ እርሱ ዕውቀት አልባም ነው፡፡ ያለብርሃን የመኖርን ባዶነት የምንረዳው፣ በብርሃነ-አእምሮአችን እንጂ በጽለመታዊው እእምሮአችን አይደለም፡፡ ብርሃን ሲጠፋ፣ ያኔ አእምሮም ወደ ጽልመቱ ተመልሶ ይገባል፡፡
ብርሃን ለሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ ፀጋ ነው፡፡ “ሕፃን ልጅ ልክ እንደተወለደ ዓይኖቹን ወደ ብርሃነ ቀላይ በአራቱም ማዕዘናት እያዟዟረ ያቁለጭልጫል” ይባላል፡፡ በብርሃን ውቅያኖስ ውስጥ እንደፈለገው ለመዋኘት ያለውን ሰብዓዊ ናፍቆት በሕፃኑ ውስጥ እናያለን፡፡ ጨቅላው በብርሃኑ አማካይነት የሚያየው ነገር ውሱን ነው፡፡ ወሰኑም በአድማሳት አጥር/ኬላ መጠን የተከለለ ነው፡፡
ስለዚህ ሰው በዐይኑ ብርሃን ከሚያየው የበለጠ ረቂቅ የሆነ ብርሃን በአእምሮው ዐይኖች ያያል፡፡ ማየት የተሳነው ሰው ቢሆን እንኳን፣ በአእምሮው ብርሃንን ያያል፡፡ የአድማስ ጥጋት ከማየት አይከለክሉትም፡፡ ብርሃኑ በተለይም በትምህርትና በዕውቀት ከጎለበተማ የባሕር መቀመቅ፣ የምድርም ጥልቅ ውስጥ ዘልቆ ይገባል፡፡ ረቂቅ አቅምን የሚጋርደው ግንብም ሆነ ድንበር ስለሌለ ነው፡፡
ከዚህ የአእምሮ ብርሃንም ሰላመ ይወለዳል፡፡ ስጋት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀትና ሽብር እንዲሁም “ምን ይመጣብኝ ይሆን?” የሚል ስሜት ሁሉ በብርሃን ይወገዳል፡፡ የሽብር ምንጩ ጽልመት ነው፡፡ ምን ይመጣብኝ ይሆን ብሎ መስጋት ከጭለማ የሚወለድ ጋኔል ነው፡፡ ጽልመቱ በብርሃን ጮራዎች ከተወገደ በኋላ ግን፣ ልብ ሰላምን ያገኛል፡፡ ሰላምም፣ ሰላማዊ መንግሥት እንዲመሠረት ያደርጋል፡፡ ለሰው ልጅ ሰላምን ከመስጠት የበለጠ ምን በጎ ምግባር አለ?
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትም የያዘው ስያሜ ሞላው ዓለም የሚስማማበት ምኞት ነው፡፡ የብርሃንና የሰላም ምኞት ነው፡፡ ብርሃን ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ሰላምም ሰብዓዊ ነው፡፡ የመላው ዓለም ሕዝብ ለብርሃንና ለሰላም የጋለ መሻት፣ ጉጉትና ናፍቆት አለው፡፡ ዘላለማዊ መሻት ነው፡፡ ጊዜያዊ የፖለቲካ ሽቀላና ትርፍ አጋባሽነት ያንን ዘላለማዊ ናፍቆትና መሻት አያሰናክለውም፡፡ ከጽልመትና ከሽብር ይልቅ ብርሃንና ሰላም በመላው ዓለም እንዲነግስ፣ በተለይም በኢትዮጵያችን እንዲንሰራፋ ዘላለማዊ ጸሎታችንን እናድርስ!
መፍትሄ የናፈቃቸው የኑሮ ችግሮች የኢህአዴግና የተቃዋሚዎች 3 የምርጫ አጀንዳዎች የተመራቂዎች ሥራ አጥነት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተመራቂዎች ሥራ አጥ ሆነዋል፤ በየአመቱ ግማሽ ሚሊዮን ያህል ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ይመረቃሉ። የኑሮ ውድነት ሸክም የዋጋ ንረት በአስር አመት በአምስት እጥፍ ጨምሯል። የደሞዝተኛ ሰራተኞች የኑሮ ደረጃ ደግሞ በግማሽ አሽቆልቁሏል። የአነስተኛና ጥቃቅን ችግር በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች በገበያ እጦትና በመንግስት የተንዛዛ ቢሮክራሲ ሳቢያ ከስረዋል፤ የተበደሩትን ሳይመልሱ ጠፍተዋል በመጪው ግንቦት የሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ ምን አይነት መልክ ሊኖረው እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ይከብዳል። በዚያው ጊዜ በመላ አገሪቱ በሚከናወኑት የወረዳና የቀበሌ ምርጫዎች፤ ከሞላ ጎደል ኢህአዴግና አጋሮቹ በዘጠና ምናምን ፐርሰንት እንደሚያሸንፉ አያጠራጥርም። የአዲስ አበባውም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። ግን ላይሆንም ይችላል። የሆነ ሆኖ፤ ከምርጫው ጋር ተያይዞ፤ ለረዥም ጊዜ ጠፍቶ የነበረው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምፅ ሰሞኑን ብቅ ብቅ ማለት ጀምሯል። የገዢው ፓርቲ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውዝግብም ሞቅ ሞቅ ማለቱ አይቀርም – ፉክክር መሆኑ ነው። ግን ምን ዋጋ አለው? ፉክክራቸውና ውዝግባቸው ሁሉ ያን ያህልም ከዜጎች ተጨባጭ የኑሮ ችግር ጋር ግንኙነት የለውም። የምርጫ ንትርክና ውዝግብ ለግለሰብ ነፃነት የተሻለ ክብር እየሰጡ፣ በስልጣኔ ጎዳና ደህና የተራመዱ አገራት ውስጥ የምናየው ፉክክር ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናየው ውዝግብ በእጅጉ ይለያል። የአሜሪካና የእንግሊዝ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በምርጫ ወቅት የሚያነሷቸው አጀንዳዎች፣ ከዜጎች ኑሮ ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው። በዜጎች ኑሮና ፍላጎት ዙሪያ እየተከራከሩ፣ በዜጎች ችግርና በመፍትሄ ሃሳቦች ላይ እየተፎካከሩ የምርጫ ውድድር ያካሂዳሉ። “ያኛው የዜጎች ችግር፣ ቅድሚያ ትኩረት ያሻዋል… አይ ይሄኛው ችግር ይቀድማል” እያሉ ይከራከራሉ። “እኔ ያቀረብኩት የመፍትሄ ሃሳብ ይበልጣል … አይ፤ የኔ ሃሳብ ይሻላል” እያሉ ይፎካከራሉ። ፓርቲዎቹ በምርጫ ውድድራቸው አብዝተው የሚከራከሩትና የሚፎካከሩት፤ በዜጎች የኑሮ ችግርና በመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ነው። በአጭሩ፤ የምርጫ ውድድሩ ዋነኛ አጀንዳ፣ “የዜጎች ኑሮ” ይሆናል – በሰለጠኑት አገራት። በእርግጥ በኛ አገርም፤ ለምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎች እንደነገሩ ለወጉ ያህል አነሰም በዛም “ይከራከራሉ፤ ይፎካከራሉ” ይባል ይሆናል። ነገር ግን፣ “ክርክራቸውና ፉክክራቸው”፣ በዜጎች ኑሮና ችግር ላይ ወይም በመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ አይደለም። በራሱ በምርጫ ጉዳይ ነው የሚነታረኩትና የሚወዛገቡት። ምርጫውን ራሱ፣ ዋነኛ የምርጫ አጀንዳ ስለሚያደርጉት፤ “ክርክርና ፉክክር” ሳይሆን፤ “ንትርክና ውዝግብ” ገንኖ ይወጣል። ድሮም፣ በግለሰብ ነፃነት ላይ ያልተመሰረተ ኋላቀር ፖለቲካ፣ ከንትርክና ከውዝግብ ውጭ ሊሆን አይችልም። እንዴት አትሉም? ለግለሰብ ነፃነት ብዙም ክብር የማይሰጥ ገዢ ፓርቲ፤ ነፃ ምርጫዎችን የማካሄድ ፍላጎቱ ዝቅተኛ ነው። ምርጫዎች የስልጣን ማራዘሚያ መሳሪያ ሆኖ የሚታየው ከሆነ፤ ዜጎችን በአፈናም በጫናም ለመቆጣጠር ይጥራል። ተቃዋሚዎችን በዛቻም በወከባም መፈናፈኛ ያሳጣቸዋል። በዚያው ልክ፤ ለግለሰብ ነፃነት ብዙም ዋጋ ለማይሰጡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የምርጫ ውድድር ምን ሆኖ እንደሚታያቸው አስቡት። የምርጫ ውድድር ማለት፣ እያንዳንዱ ዜጋ በነፃነት ሃሳቡን የሚገልፅበትና ድምፁን የሚሰጥበት መድረክ ነው? ወይስ የምርጫ ውድድር በአመዛኙ የአመፅ ሰበብ ሆኖ ይታያቸዋል?sostu yenuro chigrochያው የምርጫ ውድድር በመጣ ቁጥር፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምሬታቸውን ይገልፃሉ – “የገዢው ፓርቲ አፈናና ወከባ በዛብን፤ ምርጫው ነፃ አይደለም” እያሉ። ገዢው ፓርቲም እንዲሁ ያማርራል – “ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመፅ ይሰብካሉ፤ ስርዓቱን ለማፍረስ ይፈልጋሉ” እያለ። ንትርኩና ውዝግቡ እስከ ምርጫው እለት ይቀጥላል። በእርግጥ፤ ከምርጫው ጋር የተያያዙ የአፈናና የወከባም ሆነ የአመፅ ጉዳዮች አይነሱ ማለቴ አይደለም። መነሳት አለባቸው። ነፃ ምርጫ እንዲካሄድ፤ አፈናና ጫና፣ ወከባና እስር መቆም አለበት። ሰላማዊ ምርጫ እንዲካሄድ፣ አመፅ መቅረት ይኖርበታል። ለነገሩ አሁን አሁን እንኳ ስለ አመፅ የሚናገር ይቅርና ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠራ ተቃዋሚ ፓርቲም ያለ አይመስልም። ቢሆንም ግን፤ ጨርሶ ጉዳዩ መነሳት የለበትም ብሎ መናገር ያስቸግራል። እናም ይሁን … በምርጫ ውድድር ውስጥ፤ አፈናንና ወከባን እንዲሁም አመፅን በማውገዝ ላይ ያተኮሩ፤ ከምርጫ ጋር የተያያዙ አጀንዳዎች ይኑሩ። ነገር ግን፤ ምርጫው በእነዚህ አጀንዳዎች ታጥሮ የንትርክና የውዝግብ ሰርከስ መሆን አይገባውም። ከዜጎች ህይወት ጋር በቀጥታ የተያያዙ ሌሎች አጀንዳዎችን የማንሳትና የማስተጋባት ልምድም ሊኖረን ይገባል። ለዚህም ነው፤ ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊከራከሩባቸው የሚገቡ ሦስት ዋና ዋና የኑሮ አጀንዳዎችን መርጬ የማቀርበው። መፍትሄ የናፈቃቸው የኑሮ ችግሮች ፅሁፌ ውስጥ በርከት ያሉ ቁጥሮችን ስትመለከቱ ቅር እንዳይላችሁ። ደግሞስ ቁጥርን ጠልተን የት እንደርሳለን! ኑሯችንኮ በቁጥሮች የተሳሰረ ነው። የሥራ ሰዓት በቁጥር፤ ግዢና ሽያጭ በቁጥር፤ ደሞዝና አስቤዛ በቁጥር፣ ትርፍና ኪሳራ በቁጥር፣ የዋጋ ንረትና ሥራ አጥነት በቁጥር… ቁጥር ሳንጠቀም ውለን አናድርም። ቢሆንም ግን፤ ሦስቱን አጀንዳዎች አስተሳስረን ለማገናዘብ የሚረዱ መረጃዎችን የማቀርብላችሁ፤ በተቻለ መጠን የቁጥር ጋጋታ ሳላበዛ ነው። ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ኤጀንሲ፤ “የምርት ተቋማት”ን በሚመለከት ካሰራጫቸው ሪፖርቶች ልነሳ። በነገራችን ላይ፤ በኤሌክትሪክ ወይም በነዳጅ የሚንቀሳቀስ አንዳች መሳሪያ ተጠቅሞ የሚያመርትና ለገበያ የሚያቀርብ ተቋም ሁሉ፤ የምርት ተቋም ይባላል። የሰራተኞቹ ቁጥር ከአስር በታች ከሆነ፣ አነስተኛ የምርት ተቋም ተብሎ ይጠራል – በአብዛኛው የሰራተኞቻቸው ብዛት ከሶስት አይበልጥም። መበየጃ ተጠቅሞ የብረት በርና መስኮት የሚሰራ፤ እንጀራና ዳቦ መጋገሪያ፤ ወፍጮ ቤት የመሳሰሉ ሊጠቀሱ ይችላሉ። ለምሳሌ በ94 ዓ.ም በመላ አገሪቱ ከነበሩት 32 ሺ ገደማ አነስተኛ የምርት ተቋማት መካከል 27ሺ ያህሉ ወፍጮ ቤቶች እንደነበሩ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት ያሳያል። ያኔ፣ በአነስተኛ የምርት ተቋማት ውስጥ ይሰሩ ከነበሩ መቶ ሺ ገደማ ሰራተኞች መካከል 45ሺ ያህሉ ያለ ደሞዝ የሚሰሩ ነበሩ – የቤተሰብ አባላት ናቸውና። ደሞዝ የሚከፈላቸው 55ሺ ሰራተኞች በአማካይ 120 ብር የወር ደሞዝ እንደሚያገኙ በወቅቱ የወጣው መረጃ ያመለክታል (የ1994 ዓ.ም REPORT ON SMALL SCALE MAIYUFACTURING INDUSTRIES SURVEY)። ከጠቅላላው ሰራተኛ ውስጥ በቴክኒክና ሙያ ወይም በከፍተኛ ትምህርት የተመረቁ ሰራተኞች፤ 2ሺ አይሞሉም ነበር (ገፅ 28)። እንግዲህ፤ በ1994 ዓ.ም የአነስተኛ የምርት ተቋማት ብዛት፤ የሰራተኞቻቸው ቁጥር፤ የትምህረት ብቃታቸው ደረጃ፤ የደሞዛቸው መጠን አየን። “ከስድስት አመት በኋላስ የአነስተኛ የምርት ተቋማት እድገት የት ደረሰ?” ብለን እንጠይቅ። የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት ላይ ምላሹን እናገኛለን – (የ2000 ዓ.ም REPORT ON SMALL SCALE MANUFACTURING INDUSTRIES SURVEY)። በስድስት አመታት፣ የተቋማቱ ቁጥር በአስር ሺ ስለጨመረ 43ሺ ደርሷል። የሰራተቹ ቁጥር ደግሞ 140ሺ ሆኗል። በእርግጥ ስልሳ ሺ ያህሉ ደሞዝ የማይከፈላቸው የቤተሰብ አባላት ናቸው። ሰማኒያ ሺዎቹ ደግሞ፣ ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ደሞዝተኞች ናቸው – በአማካይ በወር 240 ብር የሚከፈላቸው። በቴክኒክና ሙያ ወይም በከፍተኛ ትምህርት የተመረቁ ሰራተኞች ቁጥር ከአርባ ሺ በላይ ሆኗል። ግራ አያጋባም? በቴክኒክና ሙያ ተመርቆ በሶስት መቶ ብር በታች ደሞዝ የሚከፈለው ወጣት ይታያችሁ። በስድስት አመታት ውስጥ በቴክኒክና ሙያ ወይም በዩኒቨርስቲ የተመራቁ ሰራተኞች ቁጥር፣ ከሃያ እጥፍ በላይ ቢጨምርም፤ የሰራተኞች አማካይ የወር ደሞዝ ግን በ120 ብቻ ነው የጨመረው (ከ120 ወደ 240 ብር)። ለነገሩ ይህንን የደሞዝ ለውጥ፣ እንደ ጭማሪ ከቆጠርነው ተሳስተናል። ለምን ቢባል፣ በእነዚያ ስድስት ዓመታት ውስጥ የዋጋ ንረት በእጥፍ ጨምሯል። ስለዚህ፤ በ1994 ዓ.ም የነበረው 120 ብር የወር ደሞዝ እና በ2000 ዓ.ም የነበረው 240 ብር የወር ደሞዝ እኩል ናቸው። የሰራተኞቹ ኑሮ አልተለወጠም ማለት ነው። የተለወጠ ነገር ቢኖር፤ አብዛኞቹ ደሞዝተኛ ሰራተኞች የቴክኒክና ሙያ ወይም የዩኒቨርስቲ ምሩቃን መሆናቸው ብቻ ነው። ነገር ግን ምሩቃን በመሆናቸው ምክንያት ከቀድሞዎቹ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያና የተሻለ ኑሮ አላገኙም። ቢሆንም፤ ቢሆንም… “ደሞዝ አነስ፣ ተምረን እንዳልተማረ ሆንን” ብለው ባያማርሩ ይሻላቸዋል። የባሰምኮ አለ። ብዙ ተመራቂዎች ስራ አጥ ሆነዋላ። በዚያ ላይ በየአመቱ በቴክኒክና ሙያ የሚመረቁ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሥራ አጡን ጎራ ይቀላቀላሉ። በእርግጥ ትምህርቱና ስልጠናው አስተማማኝ ስላልሆነ፤ “መመረቅ” ማለት የሙያ ባለቤት መሆን ማለት አይደለም። ከተመረቁት መካከል ሩብ ያህሉ ናቸው የሙያ ብቃት መመዘኛ የሚያልፉት። ለማንኛውም፣ በስድስት አመት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ተመርቀዋል። ነገር ግን፤ ቢበዛ ቢበዛ አርባ ሺ ያህሉ ብቻ ናቸው በአነስተኛ የምርት ተቋማት ውስጥ ስራ ያገኙት (በአማካይ በአመት ሰባት ሺ ተመራቂዎች ብቻ ማለት ነው)። ታዲያ ሌሎቹ ተመራቂዎችስ ሌላ ምን እድል አላቸው? ምናልባት መካከለኛና ትላልቅ የምርት ተቋማት ውስጥ ሥራ ያገኙ ይሆን? የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት እንግዲህ አነስተኛ የሚባሉትን የምርት ተቋማት አይተናል – ከአስር በታች ሰራተኞችን የያዙ ናቸው። መካከለኛና ትላልቅ የምርት ተቋማት የሚባሉት ደግሞ አስር ወይም ከዚያ በላይ ሰራተኞች የያዙ ተቋማት ናቸው። እነዚህ ተቋማትስ በስድስት አመታት ውስጥ ለምን ያህል ሰራተኞች የስራ እድል ፈጠሩ? የማዕከላዊ ስታትስቲክስ የ1994 ዓ.ም ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ መካከለኛና ትላልቅ ተቋማት ውስጥ መቶ ሺ ሰራተኞች ነበሩ – በአማካይ በወር 630 ብር የሚከፈላቸው (ገፅ 24)። ከስድስት አመት በኋላ በ2000 ዓ.ም ግን የሰራተኞቹ ቁጥር በ30 ሺ ገደማ ጨምሯል – ወደ 130 ሺ። በወር የሚያገኙት አማካይ ደሞዝ 1060 ብር እንደነበረም የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን የ2000 ዓ.ም ሪፖርት ያመለክታል (ሰንጠረዥ 3.6)። ሁለት ነገሮችን አስተውሉ። አንደኛ ነገር፤ በስድስት አመታት ውስጥ የሰራተኞች አማካይ ደሞዝ የጨመረ ይመስላል እንጂ፤ በተቃራኒው የሰራተኞቹ የኑሮ ደረጃ ወደ ታች ወርዷል። ለምን ቢባል፤ በስድስቱ አመታት ውስጥ የዋጋ ንረት በእጥፍ ጨምሯል። የሰራተኞቹ አማካይ የወር ደሞዝ ግን በእጥፍ አልጨመረም። እናም ኑሯቸው በዚያው ልክ ዝቅ ብሏል ማለት ነው። ሁለተኛ ነገር፤ በስድስት አመታት ውስጥ ለ30 ሺ ተጨማሪ ሰዎች ብቻ ነው የሥራ እድል የተፈጠረው (በአመት 5ሺ ያህል ማለት ነው)። ከ2000 ዓ.ም ወዲህ ያለውን መረጃ ስንመለከትም ተመሳሳይ ውጤት ነው የምናገኘው። ነሐሴ ወር ላይ በማእከላዊ ስታትስቲክስ የተለቀቀውን የመካከለኛና የትላልቅ አምራች ተቋማት የ2003 ዓ.ም ሪፖርት ተመልከቱ። የተቋማቱ የሰራተኞች ቁጥር ወደ 170 ሺ አድጓል። አማካይ የሰራተኞች የወር ደሞዝ ደግሞ ወደ 1330 ብር ጨምሯል። የደሞዛቸው መጠን ከ1994 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር በአስር አመት ውስጥ በእጥፍ ጨምሯል ማለት ይቻላል። ነገር ግን በእነዚያ አስር አመታት ውስጥ የብር የመግዛት አቅም ክፉኛ ተሸርሽሮ የዋጋ ንረት በአራት እጥፍ ጨምሯል። ምን ማለት ነው አትሉም? ያኔ በ1994 ዓ.ም ገበያ ወጥተን በ630 ብር እንገዛቸው የነበሩ ነገሮች፤ በ2003 ዓ.ም ዋጋቸው ከ2400 ብር በላይ ሆኗል። በሌላ አነጋገር፤ የሰራተኞች ደሞዝ በእጥፍ ቢጨምርም እንኳ የዋጋ ንረት በአራት እጥፍ ስለጨመረ፤ የሰራተኞቹ የኑሮ ደረጃ በግማሽ ቀንሷል ማለት ነው። ብር ስለረከሰ የዛሬ ደሞዛቸው … ከአስር አመት በፊት ከነበረው 300 ብር ጋር እኩል ነውና። እንግዲህ የዜጎች ኑሮ፤ በተለይ ደግሞ የሙያተኞችና የከተሜዎች ኑሮ ባለፉት አስር አመታት ምን ያህል እንደተደቆሰ ለማየት፤ ከዚህ የማዕከላዊ ስታትስቲክ መረጃ የተሻለ ግልፅ ማስረጃ የሚገኝ አይመስለኝም። የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት፣ ዋነኛው የምርጫ አጀንዳ መሆን የሚገባውም በዚህ ምክንያት ነው። ገዢው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የኑሮ ውድነትን ዋነኛ አጀንዳ ካላደረጉት፤ ከዚያም ግልፅና አሳማኝ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማቅረብ ካልሞከሩ… በእርግጥም ከዜጎች ኑሮ በእጅጉ ተራርቀዋል ማለት ነው። ሁለተኛው አጀንዳ፤ ከኑሮ ችግር ጋር የተያያዘው የሥራ አጥ ተመራቂዎች ጉዳይ ነው። የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሄድም፤ ያንን የሚመጥን የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ እድገት ስላልተፈጠረ ብዙዎቹ ተመራቂዎች ሥራ አጥ እየሆኑ ነው። የመንግስት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ሰነድ እንደሚያሳየው፤ በ97 ዓ.ም መቶ ሺ ገደማ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ቁጥር፣ በ2002 ዓ.ም ወደ ሰባት መቶ ሺ ደርሷል። በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች 80ሺ ገደማ የነበረው የተማሪዎች ቁጥርም ወደ 190ሺ የሚጠጋ ሆኗል። ባለፉት ሦስት አመታትም በቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሁም በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የተማሪዎች ቁጥር ስለጨመረ፤ የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች ቁጥር በአመት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ሆኗል። የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች ቁጥርም በተመሳሳይ መንገድ በአመት ወደ መቶ ሺ እየተጠጋ መጥቷል። የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ትምህርት፤ በአብዛኛው ለምርት ተቋማት በሚያመች መንገድ (ለአነስተኛ፣ ለመካከለኛና ለትላልቅ አምራቾች የሚጠቅም መንገድ) እየተቃኘ እንደሆነ ይናገራል መንግስት። የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ገፅ 74 መመልከት ትችላላችሁ። አብዛኞቹ ተመራቂዎችም በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ለሥራ ይሰማራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ማለትም በአነስተኛ፣ በመካከለኛና በትላልቅ አምራች ተቋማት ውስጥ የስራ እድል ያገኛሉ፤ ወይም ተመራቂዎቹ ራሳቸው ተቋማቱን በመመስረት የስራ እድል ይፈጥራሉ። ታዲያ እንዲህ በእቅድ የሰፈረው ሃሳብ፤ በተጨባጭ እውን ሆነ? አልሆነም። የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አመታዊ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ በአማካይ በየአመቱ የሚፈጠረው የሥራ እድል ቢበዛ ከ20ሺ አይበልጥም። ለአብዛኛው ተመራቂ የሥራ እድል ይፈጥራሉ ተብለው የሚጠበቁት የምርት ተቋማት፤ እንዲህ 5 በመቶ ያህሉን ተመራቂ እንኳ ማስተናገድ አልቻሉም ማለት ነው። ታዲያ በየአመቱ እየተመረቀ የሚወጣው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ወጣት የት ይገባል? ከአመት አመት ሥራ አጥ ተመራቂ በተበራከተ ቁጥር፤ የዚያኑ ያህል አደጋው እያበጠ ይመጣል። አብጦ አብጦ ከመፈንዳቱ በፊት መፍትሄ ሊበጅለት ስለሚገባ፤ በመጪው ምርጫ ትልቅ የመከራከሪያና የመፎካከሪያ አጀንዳ መሆን ይገባዋል። ሦስተኛው አጀንዳ፣ የኑሮ ችግርንና ሥራ አጥነትን እንደሚያቃልሉ የሚነገርላቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ላይ ማተኮር አለበት – በከፍተኛ ችግሮች የተከበቡ ናቸውና። በእርግጥ፣ የተወሰኑ ሰዎችና ተቋማት እንደየትጋታቸው ሲሳካላቸውና ሲመነደጉ ይታያል። ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት እንዲስፋፉ፣ መንግስት በየአመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር በጀት፣ ብድር እና ድጋፍ ሲመድብ መቆየቱም አይካድም። ነገር ግን፤ የተወራላቸውን ያህል ጉልህ ለውጥ አላስገኙም። አልፎ አልፎ ከሚታየው የጥቂት ታታሪ ሰዎች ስኬት በስተቀር፤ እቅዱ እንደታሰበው አለመሳካቱንና በርካታ ገንዘብ መባከኑን መንግስት ራሱ ያምናል። መንግስት የማምረቻ መሳሪያዎች ገዝቶ ለበርካታ ወጣቶች ቢያከፋፍልም፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በየቦታው ተጥለው ባክነዋል። በአንድ ቀበሌ ብቻ፤ ብድር ወስደው ያልመለሱ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሥም ዝርዝራቸው በአደባባይ ተለጥፎ ማየት እንግዳ ነገር አይደለም። ከሳምንት በፊት በፓርላማ በተካሄደ ስብሰባ፤ ብድር ለማስመለስ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት የፓርላማ አባላት ማሳሰቢያ ሲሰጡ የተመለከትነው ለምን ሆነና! ድሮም ቢሆን መንግስት ብድርና ድጋፍ እሰጣለሁ ብሎ የቢዝነስ ስራ ውስጥ ሲገባ፤ የገንዘብ ብክነት መፈጠሩ አይቀሬ ነው። በዚያ ላይ፤ የመንግስትን ድጎማና ድጋፍ የለመደ እጅ፤ እድሜ ልክ በጥገኝነት ለመቀጠል ይመኛል እንጂ ራሱን ችሎ የመስራት ልምድ አያዳብርም። ይህም ብቻ አይደለም። የመንግስት አሰራር በተፈጥሮው በተንዛዛ ቢሮክራሲ የተተበተበ በመሆኑ፤ ወቅቱንና ጊዜውን ጠብቆ ክፍያ አይፈፅምም። የሥራ መንፈስን ይደገድላል። እናም እንደታቀደው አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ተስፋፍተው አልተጠናከሩም። ታዲያ በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ዙሪያ የሚታየውን የገንዘብ ብክነት፤ ጥገኝነትና ስራ አጥነት ማስወገድ የለብንም? ዜጎች የሥራ መንፈሳቸው ተነሳስቶ የሥራ እድል እንዲፈጥሩና በራሳቸው ጥረት ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ መንገዱን ማስተካከል አይኖርብንም? የመጪው ምርጫ ሶስተኛ አጀንዳ፤ በአነስተኛና ጥቃቅን የቢዝነስ ተቋማት ዙሪያ መሆን ያለበትም በዚህ ምክንያት ነው።
መፍትሄ የናፈቃቸው የኑሮ ችግሮች
የኢህአዴግና የተቃዋሚዎች 3 የምርጫ አጀንዳዎች
የተመራቂዎች ሥራ አጥነት
በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተመራቂዎች ሥራ አጥ ሆነዋል፤ በየአመቱ ግማሽ ሚሊዮን ያህል ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ይመረቃሉ።
የኑሮ ውድነት ሸክም የዋጋ ንረት በአስር አመት በአምስት እጥፍ ጨምሯል። የደሞዝተኛ ሰራተኞች የኑሮ ደረጃ ደግሞ በግማሽ አሽቆልቁሏል።
የአነስተኛና ጥቃቅን ችግር
በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች በገበያ እጦትና በመንግስት የተንዛዛ ቢሮክራሲ ሳቢያ ከስረዋል፤ የተበደሩትን ሳይመልሱ ጠፍተዋል በመጪው ግንቦት የሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ ምን አይነት መልክ ሊኖረው እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ይከብዳል። በዚያው ጊዜ በመላ አገሪቱ በሚከናወኑት የወረዳና የቀበሌ ምርጫዎች፤ ከሞላ ጎደል ኢህአዴግና አጋሮቹ በዘጠና ምናምን ፐርሰንት እንደሚያሸንፉ አያጠራጥርም። የአዲስ አበባውም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። ግን ላይሆንም ይችላል። የሆነ ሆኖ፤ ከምርጫው ጋር ተያይዞ፤ ለረዥም ጊዜ ጠፍቶ የነበረው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምፅ ሰሞኑን ብቅ ብቅ ማለት ጀምሯል። የገዢው ፓርቲ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውዝግብም ሞቅ ሞቅ ማለቱ አይቀርም – ፉክክር መሆኑ ነው። ግን ምን ዋጋ አለው? ፉክክራቸውና ውዝግባቸው ሁሉ ያን ያህልም ከዜጎች ተጨባጭ የኑሮ ችግር ጋር ግንኙነት የለውም።
የምርጫ ንትርክና ውዝግብ
ለግለሰብ ነፃነት የተሻለ ክብር እየሰጡ፣ በስልጣኔ ጎዳና ደህና የተራመዱ አገራት ውስጥ የምናየው ፉክክር ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናየው ውዝግብ በእጅጉ ይለያል። የአሜሪካና የእንግሊዝ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በምርጫ ወቅት የሚያነሷቸው አጀንዳዎች፣ ከዜጎች ኑሮ ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው። በዜጎች ኑሮና ፍላጎት ዙሪያ እየተከራከሩ፣ በዜጎች ችግርና በመፍትሄ ሃሳቦች ላይ እየተፎካከሩ የምርጫ ውድድር ያካሂዳሉ። “ያኛው የዜጎች ችግር፣ ቅድሚያ ትኩረት ያሻዋል… አይ ይሄኛው ችግር ይቀድማል” እያሉ ይከራከራሉ። “እኔ ያቀረብኩት የመፍትሄ ሃሳብ ይበልጣል … አይ፤ የኔ ሃሳብ ይሻላል” እያሉ ይፎካከራሉ። ፓርቲዎቹ በምርጫ ውድድራቸው አብዝተው የሚከራከሩትና የሚፎካከሩት፤ በዜጎች የኑሮ ችግርና በመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ነው። በአጭሩ፤ የምርጫ ውድድሩ ዋነኛ አጀንዳ፣ “የዜጎች ኑሮ” ይሆናል – በሰለጠኑት አገራት። በእርግጥ በኛ አገርም፤ ለምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎች እንደነገሩ ለወጉ ያህል አነሰም በዛም “ይከራከራሉ፤ ይፎካከራሉ” ይባል ይሆናል። ነገር ግን፣ “ክርክራቸውና ፉክክራቸው”፣ በዜጎች ኑሮና ችግር ላይ ወይም በመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ አይደለም። በራሱ በምርጫ ጉዳይ ነው የሚነታረኩትና የሚወዛገቡት። ምርጫውን ራሱ፣ ዋነኛ የምርጫ አጀንዳ ስለሚያደርጉት፤ “ክርክርና ፉክክር” ሳይሆን፤ “ንትርክና ውዝግብ” ገንኖ ይወጣል። ድሮም፣ በግለሰብ ነፃነት ላይ ያልተመሰረተ ኋላቀር ፖለቲካ፣ ከንትርክና ከውዝግብ ውጭ ሊሆን አይችልም። እንዴት አትሉም? ለግለሰብ ነፃነት ብዙም ክብር የማይሰጥ ገዢ ፓርቲ፤ ነፃ ምርጫዎችን የማካሄድ ፍላጎቱ ዝቅተኛ ነው። ምርጫዎች የስልጣን ማራዘሚያ መሳሪያ ሆኖ የሚታየው ከሆነ፤ ዜጎችን በአፈናም በጫናም ለመቆጣጠር ይጥራል። ተቃዋሚዎችን በዛቻም በወከባም መፈናፈኛ ያሳጣቸዋል። በዚያው ልክ፤ ለግለሰብ ነፃነት ብዙም ዋጋ ለማይሰጡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የምርጫ ውድድር ምን ሆኖ እንደሚታያቸው አስቡት። የምርጫ ውድድር ማለት፣ እያንዳንዱ ዜጋ በነፃነት ሃሳቡን የሚገልፅበትና ድምፁን የሚሰጥበት መድረክ ነው? ወይስ የምርጫ ውድድር በአመዛኙ የአመፅ ሰበብ ሆኖ ይታያቸዋል?sostu yenuro chigrochያው የምርጫ ውድድር በመጣ ቁጥር፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምሬታቸውን ይገልፃሉ – “የገዢው ፓርቲ አፈናና ወከባ በዛብን፤ ምርጫው ነፃ አይደለም” እያሉ። ገዢው ፓርቲም እንዲሁ ያማርራል – “ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመፅ ይሰብካሉ፤ ስርዓቱን ለማፍረስ ይፈልጋሉ” እያለ። ንትርኩና ውዝግቡ እስከ ምርጫው እለት ይቀጥላል። በእርግጥ፤ ከምርጫው ጋር የተያያዙ የአፈናና የወከባም ሆነ የአመፅ ጉዳዮች አይነሱ ማለቴ አይደለም። መነሳት አለባቸው። ነፃ ምርጫ እንዲካሄድ፤ አፈናና ጫና፣ ወከባና እስር መቆም አለበት። ሰላማዊ ምርጫ እንዲካሄድ፣ አመፅ መቅረት ይኖርበታል። ለነገሩ አሁን አሁን እንኳ ስለ አመፅ የሚናገር ይቅርና ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠራ ተቃዋሚ ፓርቲም ያለ አይመስልም። ቢሆንም ግን፤ ጨርሶ ጉዳዩ መነሳት የለበትም ብሎ መናገር ያስቸግራል። እናም ይሁን … በምርጫ ውድድር ውስጥ፤ አፈናንና ወከባን እንዲሁም አመፅን በማውገዝ ላይ ያተኮሩ፤ ከምርጫ ጋር የተያያዙ አጀንዳዎች ይኑሩ። ነገር ግን፤ ምርጫው በእነዚህ አጀንዳዎች ታጥሮ የንትርክና የውዝግብ ሰርከስ መሆን አይገባውም። ከዜጎች ህይወት ጋር በቀጥታ የተያያዙ ሌሎች አጀንዳዎችን የማንሳትና የማስተጋባት ልምድም ሊኖረን ይገባል። ለዚህም ነው፤ ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊከራከሩባቸው የሚገቡ ሦስት ዋና ዋና የኑሮ አጀንዳዎችን መርጬ የማቀርበው።
መፍትሄ የናፈቃቸው የኑሮ ችግሮች
ፅሁፌ ውስጥ በርከት ያሉ ቁጥሮችን ስትመለከቱ ቅር እንዳይላችሁ። ደግሞስ ቁጥርን ጠልተን የት እንደርሳለን! ኑሯችንኮ በቁጥሮች የተሳሰረ ነው። የሥራ ሰዓት በቁጥር፤ ግዢና ሽያጭ በቁጥር፤ ደሞዝና አስቤዛ በቁጥር፣ ትርፍና ኪሳራ በቁጥር፣ የዋጋ ንረትና ሥራ አጥነት በቁጥር… ቁጥር ሳንጠቀም ውለን አናድርም። ቢሆንም ግን፤ ሦስቱን አጀንዳዎች አስተሳስረን ለማገናዘብ የሚረዱ መረጃዎችን የማቀርብላችሁ፤ በተቻለ መጠን የቁጥር ጋጋታ ሳላበዛ ነው። ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ኤጀንሲ፤ “የምርት ተቋማት”ን በሚመለከት ካሰራጫቸው ሪፖርቶች ልነሳ። በነገራችን ላይ፤ በኤሌክትሪክ ወይም በነዳጅ የሚንቀሳቀስ አንዳች መሳሪያ ተጠቅሞ የሚያመርትና ለገበያ የሚያቀርብ ተቋም ሁሉ፤ የምርት ተቋም ይባላል። የሰራተኞቹ ቁጥር ከአስር በታች ከሆነ፣ አነስተኛ የምርት ተቋም ተብሎ ይጠራል – በአብዛኛው የሰራተኞቻቸው ብዛት ከሶስት አይበልጥም። መበየጃ ተጠቅሞ የብረት በርና መስኮት የሚሰራ፤ እንጀራና ዳቦ መጋገሪያ፤ ወፍጮ ቤት የመሳሰሉ ሊጠቀሱ ይችላሉ። ለምሳሌ በ94 ዓ.ም በመላ አገሪቱ ከነበሩት 32 ሺ ገደማ አነስተኛ የምርት ተቋማት መካከል 27ሺ ያህሉ ወፍጮ ቤቶች እንደነበሩ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት ያሳያል። ያኔ፣ በአነስተኛ የምርት ተቋማት ውስጥ ይሰሩ ከነበሩ መቶ ሺ ገደማ ሰራተኞች መካከል 45ሺ ያህሉ ያለ ደሞዝ የሚሰሩ ነበሩ – የቤተሰብ አባላት ናቸውና። ደሞዝ የሚከፈላቸው 55ሺ ሰራተኞች በአማካይ 120 ብር የወር ደሞዝ እንደሚያገኙ በወቅቱ የወጣው መረጃ ያመለክታል (የ1994 ዓ.ም REPORT ON SMALL SCALE MAIYUFACTURING INDUSTRIES SURVEY)። ከጠቅላላው ሰራተኛ ውስጥ በቴክኒክና ሙያ ወይም በከፍተኛ ትምህርት የተመረቁ ሰራተኞች፤ 2ሺ አይሞሉም ነበር (ገፅ 28)። እንግዲህ፤ በ1994 ዓ.ም የአነስተኛ የምርት ተቋማት ብዛት፤ የሰራተኞቻቸው ቁጥር፤ የትምህረት ብቃታቸው ደረጃ፤ የደሞዛቸው መጠን አየን። “ከስድስት አመት በኋላስ የአነስተኛ የምርት ተቋማት እድገት የት ደረሰ?” ብለን እንጠይቅ። የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት ላይ ምላሹን እናገኛለን – (የ2000 ዓ.ም REPORT ON SMALL SCALE MANUFACTURING INDUSTRIES SURVEY)። በስድስት አመታት፣ የተቋማቱ ቁጥር በአስር ሺ ስለጨመረ 43ሺ ደርሷል። የሰራተቹ ቁጥር ደግሞ 140ሺ ሆኗል። በእርግጥ ስልሳ ሺ ያህሉ ደሞዝ የማይከፈላቸው የቤተሰብ አባላት ናቸው። ሰማኒያ ሺዎቹ ደግሞ፣ ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ደሞዝተኞች ናቸው – በአማካይ በወር 240 ብር የሚከፈላቸው። በቴክኒክና ሙያ ወይም በከፍተኛ ትምህርት የተመረቁ ሰራተኞች ቁጥር ከአርባ ሺ በላይ ሆኗል። ግራ አያጋባም? በቴክኒክና ሙያ ተመርቆ በሶስት መቶ ብር በታች ደሞዝ የሚከፈለው ወጣት ይታያችሁ። በስድስት አመታት ውስጥ በቴክኒክና ሙያ ወይም በዩኒቨርስቲ የተመራቁ ሰራተኞች ቁጥር፣ ከሃያ እጥፍ በላይ ቢጨምርም፤ የሰራተኞች አማካይ የወር ደሞዝ ግን በ120 ብቻ ነው የጨመረው (ከ120 ወደ 240 ብር)። ለነገሩ ይህንን የደሞዝ ለውጥ፣ እንደ ጭማሪ ከቆጠርነው ተሳስተናል። ለምን ቢባል፣ በእነዚያ ስድስት ዓመታት ውስጥ የዋጋ ንረት በእጥፍ ጨምሯል። ስለዚህ፤ በ1994 ዓ.ም የነበረው 120 ብር የወር ደሞዝ እና በ2000 ዓ.ም የነበረው 240 ብር የወር ደሞዝ እኩል ናቸው። የሰራተኞቹ ኑሮ አልተለወጠም ማለት ነው። የተለወጠ ነገር ቢኖር፤ አብዛኞቹ ደሞዝተኛ ሰራተኞች የቴክኒክና ሙያ ወይም የዩኒቨርስቲ ምሩቃን መሆናቸው ብቻ ነው። ነገር ግን ምሩቃን በመሆናቸው ምክንያት ከቀድሞዎቹ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያና የተሻለ ኑሮ አላገኙም። ቢሆንም፤ ቢሆንም… “ደሞዝ አነስ፣ ተምረን እንዳልተማረ ሆንን” ብለው ባያማርሩ ይሻላቸዋል። የባሰምኮ አለ። ብዙ ተመራቂዎች ስራ አጥ ሆነዋላ። በዚያ ላይ በየአመቱ በቴክኒክና ሙያ የሚመረቁ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሥራ አጡን ጎራ ይቀላቀላሉ። በእርግጥ ትምህርቱና ስልጠናው አስተማማኝ ስላልሆነ፤ “መመረቅ” ማለት የሙያ ባለቤት መሆን ማለት አይደለም። ከተመረቁት መካከል ሩብ ያህሉ ናቸው የሙያ ብቃት መመዘኛ የሚያልፉት። ለማንኛውም፣ በስድስት አመት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ተመርቀዋል። ነገር ግን፤ ቢበዛ ቢበዛ አርባ ሺ ያህሉ ብቻ ናቸው በአነስተኛ የምርት ተቋማት ውስጥ ስራ ያገኙት (በአማካይ በአመት ሰባት ሺ ተመራቂዎች ብቻ ማለት ነው)። ታዲያ ሌሎቹ ተመራቂዎችስ ሌላ ምን እድል አላቸው? ምናልባት መካከለኛና ትላልቅ የምርት ተቋማት ውስጥ ሥራ ያገኙ ይሆን?
የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት
እንግዲህ አነስተኛ የሚባሉትን የምርት ተቋማት አይተናል – ከአስር በታች ሰራተኞችን የያዙ ናቸው። መካከለኛና ትላልቅ የምርት ተቋማት የሚባሉት ደግሞ አስር ወይም ከዚያ በላይ ሰራተኞች የያዙ ተቋማት ናቸው። እነዚህ ተቋማትስ በስድስት አመታት ውስጥ ለምን ያህል ሰራተኞች የስራ እድል ፈጠሩ? የማዕከላዊ ስታትስቲክስ የ1994 ዓ.ም ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ መካከለኛና ትላልቅ ተቋማት ውስጥ መቶ ሺ ሰራተኞች ነበሩ – በአማካይ በወር 630 ብር የሚከፈላቸው (ገፅ 24)። ከስድስት አመት በኋላ በ2000 ዓ.ም ግን የሰራተኞቹ ቁጥር በ30 ሺ ገደማ ጨምሯል – ወደ 130 ሺ። በወር የሚያገኙት አማካይ ደሞዝ 1060 ብር እንደነበረም የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን የ2000 ዓ.ም ሪፖርት ያመለክታል (ሰንጠረዥ 3.6)። ሁለት ነገሮችን አስተውሉ። አንደኛ ነገር፤ በስድስት አመታት ውስጥ የሰራተኞች አማካይ ደሞዝ የጨመረ ይመስላል እንጂ፤ በተቃራኒው የሰራተኞቹ የኑሮ ደረጃ ወደ ታች ወርዷል። ለምን ቢባል፤ በስድስቱ አመታት ውስጥ የዋጋ ንረት በእጥፍ ጨምሯል። የሰራተኞቹ አማካይ የወር ደሞዝ ግን በእጥፍ አልጨመረም። እናም ኑሯቸው በዚያው ልክ ዝቅ ብሏል ማለት ነው። ሁለተኛ ነገር፤ በስድስት አመታት ውስጥ ለ30 ሺ ተጨማሪ ሰዎች ብቻ ነው የሥራ እድል የተፈጠረው (በአመት 5ሺ ያህል ማለት ነው)። ከ2000 ዓ.ም ወዲህ ያለውን መረጃ ስንመለከትም ተመሳሳይ ውጤት ነው የምናገኘው። ነሐሴ ወር ላይ በማእከላዊ ስታትስቲክስ የተለቀቀውን የመካከለኛና የትላልቅ አምራች ተቋማት የ2003 ዓ.ም ሪፖርት ተመልከቱ። የተቋማቱ የሰራተኞች ቁጥር ወደ 170 ሺ አድጓል። አማካይ የሰራተኞች የወር ደሞዝ ደግሞ ወደ 1330 ብር ጨምሯል። የደሞዛቸው መጠን ከ1994 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር በአስር አመት ውስጥ በእጥፍ ጨምሯል ማለት ይቻላል። ነገር ግን በእነዚያ አስር አመታት ውስጥ የብር የመግዛት አቅም ክፉኛ ተሸርሽሮ የዋጋ ንረት በአራት እጥፍ ጨምሯል። ምን ማለት ነው አትሉም? ያኔ በ1994 ዓ.ም ገበያ ወጥተን በ630 ብር እንገዛቸው የነበሩ ነገሮች፤ በ2003 ዓ.ም ዋጋቸው ከ2400 ብር በላይ ሆኗል። በሌላ አነጋገር፤ የሰራተኞች ደሞዝ በእጥፍ ቢጨምርም እንኳ የዋጋ ንረት በአራት እጥፍ ስለጨመረ፤ የሰራተኞቹ የኑሮ ደረጃ በግማሽ ቀንሷል ማለት ነው። ብር ስለረከሰ የዛሬ ደሞዛቸው … ከአስር አመት በፊት ከነበረው 300 ብር ጋር እኩል ነውና። እንግዲህ የዜጎች ኑሮ፤ በተለይ ደግሞ የሙያተኞችና የከተሜዎች ኑሮ ባለፉት አስር አመታት ምን ያህል እንደተደቆሰ ለማየት፤ ከዚህ የማዕከላዊ ስታትስቲክ መረጃ የተሻለ ግልፅ ማስረጃ የሚገኝ አይመስለኝም። የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት፣ ዋነኛው የምርጫ አጀንዳ መሆን የሚገባውም በዚህ ምክንያት ነው። ገዢው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የኑሮ ውድነትን ዋነኛ አጀንዳ ካላደረጉት፤ ከዚያም ግልፅና አሳማኝ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማቅረብ ካልሞከሩ… በእርግጥም ከዜጎች ኑሮ በእጅጉ ተራርቀዋል ማለት ነው።
ሁለተኛው አጀንዳ፤ ከኑሮ ችግር ጋር የተያያዘው የሥራ አጥ ተመራቂዎች ጉዳይ ነው። የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሄድም፤ ያንን የሚመጥን የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ እድገት ስላልተፈጠረ ብዙዎቹ ተመራቂዎች ሥራ አጥ እየሆኑ ነው። የመንግስት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ሰነድ እንደሚያሳየው፤ በ97 ዓ.ም መቶ ሺ ገደማ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ቁጥር፣ በ2002 ዓ.ም ወደ ሰባት መቶ ሺ ደርሷል። በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች 80ሺ ገደማ የነበረው የተማሪዎች ቁጥርም ወደ 190ሺ የሚጠጋ ሆኗል። ባለፉት ሦስት አመታትም በቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሁም በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የተማሪዎች ቁጥር ስለጨመረ፤ የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች ቁጥር በአመት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ሆኗል። የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች ቁጥርም በተመሳሳይ መንገድ በአመት ወደ መቶ ሺ እየተጠጋ መጥቷል። የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ትምህርት፤ በአብዛኛው ለምርት ተቋማት በሚያመች መንገድ (ለአነስተኛ፣ ለመካከለኛና ለትላልቅ አምራቾች የሚጠቅም መንገድ) እየተቃኘ እንደሆነ ይናገራል መንግስት። የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ገፅ 74 መመልከት ትችላላችሁ። አብዛኞቹ ተመራቂዎችም በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ለሥራ ይሰማራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ማለትም በአነስተኛ፣ በመካከለኛና በትላልቅ አምራች ተቋማት ውስጥ የስራ እድል ያገኛሉ፤ ወይም ተመራቂዎቹ ራሳቸው ተቋማቱን በመመስረት የስራ እድል ይፈጥራሉ። ታዲያ እንዲህ በእቅድ የሰፈረው ሃሳብ፤ በተጨባጭ እውን ሆነ? አልሆነም። የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አመታዊ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ በአማካይ በየአመቱ የሚፈጠረው የሥራ እድል ቢበዛ ከ20ሺ አይበልጥም። ለአብዛኛው ተመራቂ የሥራ እድል ይፈጥራሉ ተብለው የሚጠበቁት የምርት ተቋማት፤ እንዲህ 5 በመቶ ያህሉን ተመራቂ እንኳ ማስተናገድ አልቻሉም ማለት ነው። ታዲያ በየአመቱ እየተመረቀ የሚወጣው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ወጣት የት ይገባል? ከአመት አመት ሥራ አጥ ተመራቂ በተበራከተ ቁጥር፤ የዚያኑ ያህል አደጋው እያበጠ ይመጣል። አብጦ አብጦ ከመፈንዳቱ በፊት መፍትሄ ሊበጅለት ስለሚገባ፤ በመጪው ምርጫ ትልቅ የመከራከሪያና የመፎካከሪያ አጀንዳ መሆን ይገባዋል።
ሦስተኛው አጀንዳ፣ የኑሮ ችግርንና ሥራ አጥነትን እንደሚያቃልሉ የሚነገርላቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ላይ ማተኮር አለበት – በከፍተኛ ችግሮች የተከበቡ ናቸውና። በእርግጥ፣ የተወሰኑ ሰዎችና ተቋማት እንደየትጋታቸው ሲሳካላቸውና ሲመነደጉ ይታያል። ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት እንዲስፋፉ፣ መንግስት በየአመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር በጀት፣ ብድር እና ድጋፍ ሲመድብ መቆየቱም አይካድም። ነገር ግን፤ የተወራላቸውን ያህል ጉልህ ለውጥ አላስገኙም። አልፎ አልፎ ከሚታየው የጥቂት ታታሪ ሰዎች ስኬት በስተቀር፤ እቅዱ እንደታሰበው አለመሳካቱንና በርካታ ገንዘብ መባከኑን መንግስት ራሱ ያምናል። መንግስት የማምረቻ መሳሪያዎች ገዝቶ ለበርካታ ወጣቶች ቢያከፋፍልም፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በየቦታው ተጥለው ባክነዋል። በአንድ ቀበሌ ብቻ፤ ብድር ወስደው ያልመለሱ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሥም ዝርዝራቸው በአደባባይ ተለጥፎ ማየት እንግዳ ነገር አይደለም። ከሳምንት በፊት በፓርላማ በተካሄደ ስብሰባ፤ ብድር ለማስመለስ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት የፓርላማ አባላት ማሳሰቢያ ሲሰጡ የተመለከትነው ለምን ሆነና! ድሮም ቢሆን መንግስት ብድርና ድጋፍ እሰጣለሁ ብሎ የቢዝነስ ስራ ውስጥ ሲገባ፤ የገንዘብ ብክነት መፈጠሩ አይቀሬ ነው። በዚያ ላይ፤ የመንግስትን ድጎማና ድጋፍ የለመደ እጅ፤ እድሜ ልክ በጥገኝነት ለመቀጠል ይመኛል እንጂ ራሱን ችሎ የመስራት ልምድ አያዳብርም። ይህም ብቻ አይደለም። የመንግስት አሰራር በተፈጥሮው በተንዛዛ ቢሮክራሲ የተተበተበ በመሆኑ፤ ወቅቱንና ጊዜውን ጠብቆ ክፍያ አይፈፅምም። የሥራ መንፈስን ይደገድላል። እናም እንደታቀደው አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ተስፋፍተው አልተጠናከሩም። ታዲያ በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ዙሪያ የሚታየውን የገንዘብ ብክነት፤ ጥገኝነትና ስራ አጥነት ማስወገድ የለብንም? ዜጎች የሥራ መንፈሳቸው ተነሳስቶ የሥራ እድል እንዲፈጥሩና በራሳቸው ጥረት ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ መንገዱን ማስተካከል አይኖርብንም? የመጪው ምርጫ ሶስተኛ አጀንዳ፤ በአነስተኛና ጥቃቅን የቢዝነስ ተቋማት ዙሪያ መሆን ያለበትም በዚህ ምክንያት ነው።

Subscribe to:
Posts (Atom)