Pages

Apr 10, 2013

ድምጻዊ ብዙአየሁ ደምሴ በካናዳ ጥገኝነት ጠየቀ

(ዘ-ሐበሻ) ተወዳጁ ድምጻዊ ሙሉቀን መለስ ሙዚቃ በቃኝ ካለ በኋላ የርሱን ሥራዎች በመጫወት “ዳግማዊ ሙሉቀን መለሰ” የሚል ስያሜን በአድናቂዎቹ ያገኘው ድምጻዊ ብዙአየሁ ደምሴ በካናዳ ጥገኝነት መጠየቁን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገለጹ። በወቅታዊው የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ውስጥ የመንግስት በእጅ አዙር አፈና እየከፋ መምጣቱና አርቲስቶች ለሚሠሯቸው ሥራዎች በመንግስት የደህነንት ኃይሎች “ምን ለማለት ፈልገህ ነው” በሚል እየተመነዘረ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ከፍተኛ የስነልቦና ጭቆና ውስጥ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ የተገለጸ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ
ወዲህ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በውጭ ሃገር ጥገኝነት መጠየቅ
ማብዛታቸውም ከዚሁ ጋር እንደሚያያዝ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ተናግረዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንኳ በካናዳ ከ6 የማያንሱ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች
ጥገኝነት መጠየቃቸውን የሚጠቅሱት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ድምጻዊው ብዙአየሁ ደምሴም የስደቱ ሰለባ ሆኗል
ብለዋል።
በአንድ ወቅት በባህል ሙዚቃ ታዋቂነትን ያገገኘው የድምጻዊት ብርቱካን ዱባለ ልጅ አርቲስት መሰሉ ፋንታሁን፣
የማዲንጎ አፈወርቅ ወንድም፣ ኮሜዲያን እና ድምጻዊ ይርዳው ጤናው በካናዳ ጥገኝነት መጠየቃቸውን የሚገልጹት
እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አዲሱን አልበሙን እየሠራ የሚገኘው ድምጻዊ ብዙአየሁ ደምሴም በካናዳ ጥገኝነት አቅርቦ
እዛው መኖር እንደጀመረ ገልጸዋል።
ድምጻዊ ብዙአየሁ ደምሴን ጥገኝነት በመጠየቁ ዙሪያ ቃለምልልስ ለማድረግ ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው ባይሳካም፤
ድምጻዊውን እንዳገኘነው የሚለውን ለማቅረብ ዝግጁ ነን።
(የድምጻዊውን ዘፈን እንጋብዛችሁ)

No comments:

Post a Comment

Total Pageviews

Translate